ስለ ንስሐ
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!" (ማቴ 3: 1-2)
ተከታታይ ትምህርትና ለጥያቄዎት ምላሽ ለማግኘት ቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ
ስለ ንስሐ አገልግሎት መሰረታዊ ትምህርት
ስለ አበነፍስ (ስለ ንስሐ አባት) አገልግሎት በሚመለከት
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ መርጦ የመንጋው እረኞች እንዲሆኑ ለሾማቸው ቅዱሳን ሐዋርያት በአንብሮተ እድ የሰጣቸው ስልጣነ ክህነት ከኃጢአት ማሰሪያ የሚፈታ፣ አመፀኞችን የሚያሥር፣ ቦታና ጊዜ የማይወስነው ረቂቅ ስልጣን ነው። ስልጣኑን የሰጣቸውም ራሱ ባለቤቱ “የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለው በምድር የምታሥረው ሁሉ በሰማያት የታሠረ ይሆናል በምድር የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል” ማቴ 16:19 “እውነት እላችኋለው በምድር የምታሥሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈቱት በሰማይ የተፈታ ይሆናል” በማለት ለቅዱስ ጴጥሮስ እና ለሁሉም ሐዋርያት አስተምሯቸዋል። የክህነቱ ስልጣን ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ነው፤ ከምድራዊ ስልጣን ጋር የማይነፃፀርና ከፈጣሪ በስተቀር ማንም የማይሽረው መሆኑን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት ገልጾላቸዋል።
ስለክህነት በብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ኪዳን ያለውን አመጣጥና አገልግሎት ወደፊት በስፋት የምንገልጸው ሆኖ፤ አሁን ግን በአጭሩ በንስሐ አባት አያያዝ ዙሪያ ጥያቄ ላላችሁ የምናስተላልፈው መልእክት፤ ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ክህነት የእግዚአብሔር ስጦታ ከሆነና የስልጣኑ አገልግሎትም ቦታ እና ጊዜ የማይወስነው ከሆነ፤ በየትኛውም ክፍለ ዓለም የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ሁሉ በሚኖሩበት ከተማ /አካባቢ/ ቤተክርስትያንና አባቶች ካህናት በቅርብ ከሌሉ፤ በዕውቀታቸውና በሕይወታቸው አስተምረውና መክረው ወደ ንስሐ ሕይወት በማቅረብ በክርስቲያናዊ ስነምግባር እና በሃይማኖታችሁ ጸንታችሁ እንድትኖሩ የሚጠብቋችሁን አባቶች ከየትኛውም ክፍለ ዓለም መርጦ መያዝ ይቻላል። ምክንያቱም በአካባቢያችን በጠዋትና በማታ በቅርበት የንስሐ አባት የሚሆንዎ ካህን ከሌለ ዓለጠባቂና ዓለአስተማሪ አንድም ቀን መኖር ስለማይገባን በቅርብ ከእኛ ጋር በአካለ ስጋ ሆኖ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጠን አባት ከሌለ፤ ያለብንን የውስጥ ችግር ከምንም በላይ እሱ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላካችን ስለሚያውቀው በሃይማኖታቸውና በስነምግባራቸው የተመሰከረላቸውን አባቶች በማነጋገር የንስሐ አባት ማድረግ ይገባናል።
የአንድ እውነተኛ የንስሐ አባት ለንስሐ ልጆቹ ማስተማር የሚገባው እንዲጾሙ፣ እንዲፀልዩ፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲማሩ፣ እንዲያስቀድሱ፣ ንስሐ እንዲገቡ፣ የክስቶስን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንዲቀበሉ (እንዲቆርቡ) አሥራት በኩራት እንዲከፍሉ፣ ለተቸገሩ ወገኖች የርሕራሄ ሥራ እንዲያደርጉ በአጠቃላይ በተዋሕዶ ሃይማኖታቸውና በክርስትያናዊ ሕይወታቸው ጸንትው እንዲኖሩ ስለሆነ፤ ይህ ደግሞ ከየትም ቦታ ሆኖ ዘመኑ በአስገኘው ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ ከንስሐ አባቱ ጋር በየቀኑ መገናኘት ስለሚቻል የተፈለገውን መንፈሳዊ አገልግሎት ለማግኘት እንችላለን ማለት ነው። ከባዱ ፈተና ግን በአንዳንድ አጉል አማካሪ ግራ ተጋብተን የነፍሳችን እረኛና ጠባቂ ከሆኑት አባቶች ተለይተን መኖር ግን በዱርና በሜዳ ያለእረኛ እንደተሰማራ መንጋ እንሆናለን። እንደሚታወቀው እረኛ የሌለው መንጋ በተኩላና በአውሬ ይበላል። ማንኛውም ስጋዊ ሀብታችን ጠባቂና ተቆጣጣሪ ከሌለው በነጣቂዎችና በወንበዴዎች እንደሚዘረፍ ሁሉ በጧት በማታ በአባትነት የሚጠብቁን አበነፍስ (ንስሐ አባት) ከሌለን ከምንም በላይ ክፉና ጨካኝ የሆነው ዲያብሎስ ነፍሣችንን የማይገባትን የክፋትና የአመጽ ሥራ ስለሚያሠራት ያለጠባቂና ያለመካሪ አባት አንድ ቀን መኖር የለብንም።
“ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም” (ሉቃ 5፡32)
ስለ ንስሐ ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች
ጌታችን በወንጌሉ ካህናትን “እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ” ማቴ 5 -14 ይላቸዋልና ከርኩሰት አረንቁዋ ከጨለማውና ከኀጢአት ሥራ ሁሌ በንስሐ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚመሩንና ኀጢአትን ጠልተን በበጎ ምግባር እንድንኖር መንገዱን የሚመሩን ናቸው፡፡
የንስሐ አባት ማለት ምስጢረኛችን በመንፈሳዊም በሥጋዊም ህይወታችን የቅርብ አማካሪዎቻያችን ማለት ነው፡፡ ጠቢቡ ሲራክ “ብዙ ሰዎች ወዳጆች ይሁኑህ ከብዙዎች አንዱ ምክርህን የምትነግረው ከልቡናህ ጋር አንድ ይሁን፡፡” ሲራክ 6-6 በማለት ይናገራል፡፡ ይህ ማለት ምእመናን ስለ ሃይማኖትና በጎ ምግባር የሚያስተምሩዋቸው ብዙ ካህናት ሊኖሩዋቸው ቢችሉም ከብዙዎች አንዱ ግን ንስሃቸውን የሚናዘዙለት መምህረ ንስሃ ሊሆናቸው እንደሚገባ ያስረዳልና መምህረ ንስሕ ማለት ምስጢረኛና አማካሪ ማለት ነው ፡፡
አበ ነፍስ ማለት ኃጢአታችንን የምንናዘዝለት ማለት ነው፡፡ ኀጢታችንን ለካህን ስንናዘዝ ለእግዚአብሄር መናዘዝና ክብር መስጠት ነው፡፡ ኢያሱ እንዳለ “ልጄ ሆይ ለአምላክ ከብርን ስጥ፡ ለእርሱም ተናዘዝ፡ ያደረግከውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ” ኢያሱ 7-19፡፡ ኀጢአትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር ክብር መስጠት እንደሆነ ያሳየናል፡፡ አበዉ ካሀናትም ኑዛዜን ከተቀበሉ በኋላ “እግዚአብሔር ይፍታህ” እንጂ ”ፈትቼሃለሁ ” አይሉም፡፡ ኀጢአተዘችንን በነሱ ፊት ብንናገርም ሰሚዉም ሆነ በእነርሱ እጅ ስርየተ ኀጪአት የሚሰጠዉ እርሱ ባለቤቱ ስለሆነ ነው፡፡ በመሆኑም አበ ነፍስ ማለት ኀጢአታችንን በዝርዝር ምንም የሚያስፈራ ኀጢአት ቢኖረንም እያሰታወስን አንዳች ሳናስቀርና ሳንጠራጠር በዝርዝር የምንነግረው የእግዚአብሔር አይን ነው ማለት ነው፡፡
የንስሐ አባት/አበ ነፍስ ወይም መምህረ ንስሐ ማለት የንስሐ ልጆቹ ትክክለኛውን ዓላማ ይዘው የንስሐ ሕይወት እንዲጀምሩ የሚያደርግ በጎ መሪ ማለት ነው፡፡
መምህረ ንስሐ ማለት ልጆቹን መሠረታዊ ትምህርተ ሃይማኖት የሚያስተምርና የልጁቹን ሁለንተናዊ ለውጥ የሚከታተልና ስለ በጎቹ የሚጨነቅ እረኛ ማለት ነው፡፡
የንስሐ አባት ማለት ምእመናን ሃይማኖታቸውን እንዳይለውጡ፣ ምግባራቸውን እንደይስቱ በርካቶችም ለጠንቋዮችና ለአሳቾች ሰለባ እንዳይሆኑ የጠራውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ከምንጩ ማስጎንጨት የሚችልና እሄንንም የማድረግ ግዴታ ያለበት ባላደራ ማለት ነው፡፡
የንስሐ አባት ማለት ልጆቹ ለሥጋ ወደሙ እንዲበቁ ያለመታከት የሚተጋ ማለት ነው፡፡ የንስሐ አባት ልጆቹ ለሥጋ ወደሙ እንዲበቁ ሁሌም መጐትጐትና መቀስቀስ አለበት፡፡ ይህም የሚሆነው በኃይል፣ በማጣደፍ ወይም በማስፈራት አይደለም፡፡ ካህኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወኪል፣ የእግዚአብሔር አደረኛ ስለኾነ ሁሌም ማትጋት፣ መጐትጐት፣ መቀስቀስ ይጠበቅበታል፡፡
የንስሐ አባት ለእያንዳንዱ ልጆቹ እንደየ አቅማቸውና እንደየሃይማኖት እውቀት መጠናቸውና እንደየ መንፈሳዊ እውቀታቸው አቻ እስከሚሆኑለት ለያይቶ በማስተማር ማብቃት አለበት፡፡
የንስሐ አባት ማለት በንስሐ ልጆቹ መካከል ፍጹም መቀራረብ እንዲኖር የሚያደርገ ነው፡፡ የንስሐ ልጆች ለብዙ ችግሮች የመፍትሔ አካል ኾነው እንዲያገለግሉ ዕድል ይሰጣልና፡፡ የተቸገሩትን ከመርዳት ዠምሮ አንዱ ለሌላው አርአያ ኾኖ በተግባር እስከማስተማር ድረስ ማድረግም የንስሐ አባት ድርሻ ነው፡፡ ይህ ማለት የአንድ ካህን ንስሐ ልጆች ከአንድ የሥጋ አባትና እናት የተወለዱ እህትማመቾች እና ወንድማማቾች ያህል ከዚያም በበለጠ ሁኔታ መቀራረብ አለባቸው ማለት ነው፡፡የንስሀ አባት ማለት ይህን የሚተገብር ማለት ነው፡፡
ከቊርባን በፊት ንስሐ ይቀድማልና፡፡ ሰው ከኃጢአት ንጹሕ ሆኖ የሚገኝበት ጊዜ ስለሌለ ጧት የሠራውን ለማታ፤ ማታ የሠራውን ለጧት ለመምህረ ንስሐው ነግሮ መምህረ ንስሐው ያዘዘውን ሠርቶ ሊቀበል ይገባዋልና ይህ ታላቅ ሀላፊነት የተጣለው ደግሞ በመምህረ ንስሀው ላይ ነው፡፡
የንስሐ አባት ማለት ባለአደራ ማለት ነው፡፡ ጌታችን በወንጌል “መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በበረኻ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ማን ነው?” ሉቃ.15 -5 ያለው፡፡ ካህናት ከእግዚአብሔር በአደራ እንዲጠብቁ የተሰጣቸውን ኹሉንም ሳይዘነጉ እያንዳንዱን በነፍስ ወከፍ ሊጠብቁና ሊያገለግሉ የሚገባቸው ናቸው፡፡
የንስሐ አባት ከንስሐ ልጆቹ ጋር የሚፈጥረው ግላዊ ግንኙነት ከቤተሰባዊነት ያልተሻገረ ኾኖ ሲቀነጭርና እጅጉን ያነሰ ሲሆን ነው፡፡ ብዙ ካህናት ወደ ምእመናን ቤት መጥተው ሲያበቁ መስቀል ከማሳለምና ጠበል ከመርጨት ያለፈ አገልግሎት አይሰጡም፡፡ ካህናት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዳስቀመጠላቸው ከሥራቸው ኹሉ ቅድሚያውን ሰጥተው ማስተማር፣ መምከር፣ ኑዛዜን መቀበል፣ ማጽናናትና መገሰጽ ይገባቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የንስሐ ልጃቻቸውን በጥንቃቄ ይዘው ለሥጋ ወደሙ ማብቃት ግባቸው ስለኾነ ትኩረታቸው ኹሉ ወደዚኽ ዋነኛ የክህነት ዓላማቸው መሆን አለበት ፡፡ ይህም የካህኑ ትልቁ ሀላፊነት ነው፡፡
የንስሐ አባት የንስሐ ልጀቹን የቤተ ሰብ አባላት ቁትርና እያንዳንዱን በሚገባ ማወቅ አለበት፡፡
አንድ የንስሐ አባት ልጆቹንና አጠቃላይ ቤተሰቡን እያሰታወሰ አዘውትሮ ስለ ሁለንተናቸው መጠየቅ አለበት፡፡
የንስሐ አባት ከልጆቹ ጋር አብሮ በመጸለይ ጸሎትን ማለማመድ፤ ሆኖ በማሳየት እውነተኛ የአባትና የልጅ ፍቅርን ማሳየት፤ በመንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን በሥጋዊም ሕየዋታቸው መጨነቅ፤ ስራቸው እንዲባረክ አዘውትሮ፤መጸለይ በአጠቃላይ ልጆቹን በቅርበት መከታተል፤ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ተግባሩ እሄ ነው፡፡
“እውነት ነው በዚህ አምናለሁ ዋናው ነገር የሰራሁትን ኅጢአት በማወቅም ሆነ ባለማወቅም ለበደልኩት ላጠፋሁት ጥፋት ኅጢአቴን መናዘዝ እፈልጋለሁ ከእኔ የሚጠበቀው መስፈርትስ ምንድን ነው?” ብለው ለጠየቁ አባላችን የምንሰጣቸው ምላሽና የምክር አገልግሎት እንደሚከተለው ነው።
በቅድሚያ በድያለሁ ጥፋት ሰርቻለሁ ኅጢአት ፈጽሜያለሁ ብሎ ኅጢአትን ለመናዘዝ ፈቃደኛ መሆንና የኅጢአት ሥርየት ለማግኘት መፈለግ የእውነተኛ ክርስቲያን መገለጫ ነው። በመሠረቱ በአዳማዊ ተፈጥሮ ሰው ሁኖ የተፈጠረ የሰው ልጅ ሁሉ ወዶ ጽድቅ መሥራትም ሆነ ወዶ ኅጢአት ለመሥራት የሚችልበት የተፈጥሮ ነፃነት ያለው ፍጡር ስለሆነ በለበሰው ደካማ ሥጋው ተሸንፎ ኅጢአት እንደሚሠራ ይታወቃል። ሰው ሁኖ ተፈጥሮ በሰውነቱ ፈፅሞ ኅጢአት አልሠራም ብሎ ማሰብም ሆነ መናገር እራስን ከማታለል አልፎ ስለሁላችንም መዳን በመስቀል ላይ የሞተልንን የኢየሱስ ክርስቶስ አባታዊ ፍቅሩንና ውለታውን እንደመካድ ይቆጠራል። ሁላችንም የሰው ልጆች እንደምንሞት ብናምንም እንኳ፤ ነገር ግን መቼ በሞት እንደምንጠራ ቀንና ሰዓቱን (ዘመንና ጊዜውን) ለይቶ ማወቅ ከእሱ ከባለቤቱ በስተቀር ፈጽሞ የሚያውቅ የለምና ኅጢአትን ለመናዘዝ ቅድሚያ መስጠትና በንስሐ ሕይወት ራስን አዘጋጅቶ መጠበቅና ንስሐ ለመግባት መዘጋጀት ከእውነተኛ ክርስቲያን የሚጠበቅ ታማኝነት ነው።
ኅጢአት ማለት የብዙ ጥፋቶች ወይም ስሕተቶች መጠሪያ ስም ነው ኅጢአት የሥጋ ሥራ ሁኖ ነፍስን ከፈጣሪ ጋር አጣልቶ ዘለዓለማዊና ሰማያዊ ሞትን የሚያስከትል ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም የኅጢአት ውጤት ሞት እንደሆነ ሲናገር “ኅጢአት ስታድግ ሞትን ትወልዳለች” (ያዕ1፥15) ካለ በኋላ “የኅጢአት ደመወዝ ሞት ነው” (ሮሜ 6፥23) በማለት ኅጢአት የሕሊናና የመንፈስ ሞት መሆኑን አረጋግጧል።
የሥጋና የመንፈስ (የነፍስ) ሥራዎች አብዛኛዎቹን ቅዱስ ጳውሎስ ወደገላትያ ሰዎች በላከው መልእክቱ በምዕ 5፥19-22 ላይ የሥጋ ሥራ እና የመንፈስ ፍሬዎች በማለት ዘርዝሯቸዋል።
የሰው ልጅ ኅጢአት ሰርቻለሁ እግዚአብሔርን በድያለሁ፣ ሰውንም አሳዝኛለሁ ብሎ ራሱን ካሳመነ በነፍሱ የኅጢአት ደዌ አድሮበታልና ንስሐ የመግባት ሕክምና ያስፈልገዋል ማለት ነው። “እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ “(ማቴ3፥8) ኅጢአት ሠርቶ የንስሐ ሕክምና ያላገኘ ሰው በነፍሱ ምውት ነው። ሉቃ 15፥24
ከዚህ የተነሣ ኅጢአት ለመናዘዝና ንስሐ ለመግባት ከሚፈልግ አንድ ክርስቲያን የሚጠበቀው ፡-
በቅድሚያ ኅጢአት መሥራቱን አምኖ ለራሱ ሕሊና መናዘዝ (መፀፀት)።
ስለሠራው ኅጢአት ወይም በደል እየተጸጸተ ጧት ማታ በደሉን በፀሎትና በልመና ለፈጣሪው መናዘዝና ኅጢአትን በእግዚአብሔር ፊት ማመን (መዝ50 ፣ ዳን9፥5፣ ነህ1፥6-7)
ኅጢአትን (በደልን) ለካህን መናዘዝና ንስሐ መግባት። ካህኑ የእግዚአብሔር አገልጋይና እንደራሴ ስለሆነ የሠራነውን ኅጢአት ለካህኑ በመናዘዝ ንስሐ መግባት፤ ኅጢአታችን እንዲሠረይልን በእግዚአብሔር ፊት ንስሐ መግባትና መናዘዝ ማለት ነው። (ኢያሱ7፥19 ማቴ3፥6 ዘሌ5፥5-6 የሐዋ19፥18)
የበደልናቸውንና የበደሉንን ሁሉ ይቅር በማለት የጥል ግድግዳ አፍርሰን በፍቅር አሸንፈን ስለዘለዓለማዊ ሕይወት ብለን በፍጹም ሕሊና በሰላም መኖር ነው።
ተመልሶ በኅጢአት ላለመውደቅ አዘውትሮ የንስሐ አባትን ወይም የሚቀርቡትን የሃይማኖት መምህር ማማከር፣ ምክር ማግኘት በታቻለ መጠን መጸለይ፣ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድና ቃለ እግዚአብሔር መስማት፣ በቤትም ውስጥ ቢሆን መንፈሳዊ መዝሙርና ትምሕርት ማዳመጥ አስፈላጊ እንደሆነ የምናስገነዝበው ለጠየቁን ምዕመን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ክርስቲያን እንዲጠቅም ነው።
የእግዚአብሔር ሰላም በያላችሁበት ከእናንተጋር ይሁን።
ጠያቂያችን ምንም እንኳን በክፉ ሃሳብ መውደቅዎን አምነው በመናገርዎ እና መፍትሄ በመፈለግዎ ካንድ ለንስሃ ከተዘጋጀ ክርስቲያን የሚጠበቅ ጥሩ ሃሳብ መሆኑን እየገለፅን ነገር ግን የምንወድቅበትን የኀጥያት ጉድጓድ ሰይጣን በየጊዜው ስለሚቆፍር እና ወደ እግዚአብሔር እንዳንመለስ የጽድቅ መንገዳችንን ሁሉ ስለሚዘጋብን የተስፋ መቁረጥ ስሜት ሊሰማን ይችላል። ማንም ሰው በራሱ የሰራው ከባድ ኀጥያትም ቢሆን ራሱን ብቻ ሳይሆን ሌላውንም ወገን አብሮ ሊፈትን ስለሚችል ጥፋታችንን እጥፍ ድርብ ሊያደርገው ይችላል። ለምሳሌ ጫት የሚቅም ሰው፣ ወይም መጠጥ የሚጠጣ ሰው፣ ወይም የመሳሰሉተን ጥፋቶች የሚፈፅም ሰው ስራውን ብቻውን ስለማያደርገው በሱ ጥፋት ብዙ ሰዎችም ይወድቁበታል።ስለዚህ በበደል ላይ በደል በክፋት ላይ ክፋት እየተጨመረ በሄደ ቁጥር ሸክማችን እየከበደ እና ለመክፈል የምንችልበት አቅማችን ሳይደክም ወደ ንስሐ ህይወት ለመመለስ ማሰብዎ ታላቅነት ስለሆነ ለእርስዎ የምንመክርዎት አሁኑኑ ወስነው በሚኖሩበት በአያት ጣፎ አካባቢ የሚገኙ እርስዎን መክረው በንስሐ ህይወት ወደ እግዚአብሔር ቤት ሊያቀርብዎ የሚችሉ መምህር በአካባቢዎ ወደመረጥንልዎ መጋቢ ሀዲስ ላእከማርያም የተባሉ መምህር በቅ/ስ አማኑኤል ቤ/ክ ስለሚገኙ ከንስሐ አባት ድረገፃችን ላይ: yohannesneseha.org/የንስሐ-አባት-ገጽ ይህን አካባቢ እና ስም ተከትለው በስማቸው የሚያገኙትን ፎርም ሞልተው ሲጨርሱ በሚደርስዎ ስልክ ቁጥራቸው ደውለው እንዲያገኙዋቸውና ለችግርዎ መፍትሔ እንዲያገኙ እንመክርዎታለን።
ምክራችንን ተቀብለው ስራ ላይ ከአዋሉት መንፈሳዊ ህይወትዎ እንደሚስተካከል እናምናለን። የደረሱበትን በየጊዜው ሊያሳውቁን እና በውስጥ መስመር ሊያነጋግሩን ይችላሉ።
መልስ፦ያለ ንስሓ አባት ንስሓ መግባት አልችልም ወይ ብለው የጠየቁን አባላችን ምናልባት ስለ ንስሓ አባት እና ስለ ንስሓ ልጅ ብዙ ግንዛቤ ላይኖርዎት ይችላል። ነገር ግን ያለንስሓ አባት ወይም ያለ መምረ ንስሓ መኖር ያለ ባል ልጅ መውለድ ነው ወይም ከባል በፊት ልጅ ይስጥሽ ማለት ነው። ምክንያቱም በእግዚአብሔር ፊተ ለምንሰራው መንፈሳዊ ስራ ሁሉ ምስክር ሆኖ ሊቆምልን የሚችል ካህን ያስፈልገናል። በረቂቅ እና በሚስጢር አሠራር ቅዱሳን መላዕክት የኛ ጠባቂ ሆነው ይቆማሉ። በዚህ በገሃዱ አለም ደግሞ እንደ አንድ ክርስቲያንበምንኖርበት ህይወት ውስጥ ካህናት አባቶቻችን ለእኛ የነፍስ እረኞች ሆነው በእግዚአብሔር ዘንድ ተሹመዋል።
ስለዚህ ንስሓ አባት መያዝ የሰው ትዕዛዝ ሳይሆን የፈጣሪ መመሪያ ነው። ስለንስሓ አባት አያያዝና የንስሓ ልጅ ስለመሆን እንዴት እንደሚገባን ከዚህ በፊት ደጋግመን መልዕክት ማስተላለፋችን እያስታወስን። ጠያቂያችን ያልተረዱት ነገር ካለ በውስጥ መስመር አግኝተው ሊያናግሩን እንደሚችሉ እየገለፅን፤ በይበልጥም ስለንስሓ በድረገፃችን ላይ የተላለፉና እየተላለፉ ያሉትን ተከታታይ ትምህርቶች እንዲያነቡ እንመክራለን።
ትምህርት ስለ ንስሓ – ይህን ሊንክ ይጫኑ፦https://yohannesneseha.org/ስለ-እኛ/
ካህናት እግዚአብሔር ይፍታህ ብለውን መስቀል ሲያሳልሙን የሚሰረይልን ኀጥያት (የሃልዮ/የነቢብ/የገቢር) የቱ ነው? ብለው ለጠየቁን አባል የሚከተለውን መልስ ጽፈንልዎታል።
ሰው በውስጣዊ ህሊናው አውጥቶና አውርዶ ገና በስራ ላይ ያልዋለው በሃሳቡ ብቻ ያቀደው የክፋት ምኞት ሁሉ ያሃልዮ (የሃሳብ) ኀጥያት ይባላል። በልቡ የታሰበው ኀጥያት በአፍ ሲነገር የነቢብ (የመናገር) ኀጥያት ይባላል። በአፍ የተነገረው ኀጥያት በስራ ላይ ከዋለ የገቢር (የተግባር) ኀጥያት ይባላል።
ስለሆነም በልብ ታስቦ ሳይናገርና ስራ ላይ ሳይውል ከቀረ የታሰበውን ኀጥያት የሚያውቀው ልብና ኩላሊትን የሚመረምር እግዚአብሔር በመሆኑ በልብ ታስቦ ስራ ላይ ስላልዋለው ኀጥያት እና አንዳንዴም ጥፋት ሳይመስለን ባለማወቅ የምንፈፅማቸው ጥቃቅን ጥፋቶች በየጊዜው ወደ ካህኑ ቀርበን እና ከልባችን አምነን መስቀሉን ተሳልመን ካህኑ እግዚአብሔር ይፍታህ ቢሉን በውስጣችን የሚዋጋን ክፉ መንፈስ እንደ አሮጌ ልብስ ተገፎ እንዲወልቅ በካህኑ ላይ ያደረው ሃብተ ክህነት ያደርግልናል። ሆኖም በመናገርም ሆነ በመስራት የፈፀምነውን ከባድ በደል ግን እንደማያስፍቅልን መረዳት ያስፈልጋል።
ንሰሐ የገባ ሰው ንሰሐውን እንደጨረሰ የግድ መቁረብ አለበት? ወይሰ በንስሐ አባቱ ከንስሐው ጋር ከታዘዘለት ነው የሚቆርበው? ብለው ለጠየቁ አባል የተሰጠ ምላሽ።
መልስ፦ በመሠረቱ ንሰሐ ማለት በለበስነው ደካማ ስጋችን አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ያልተፈቀደውን ሕግ ተላልፈን ስለፈፀምነው ኀጥያታችን ከልብ ተፀፅተን ንሰሐ ለመግባት ወደ ቤተክርስቲያን ካህን (ንሰሐ አባት) ቀርበን የሰራነውን ጥፋት በተናዘዝን ግዜ ካህኑ የሚሰጠን ንሰሐ በፆም ወይም በስግደት ወይም በፀሎት ወይም በምፅዋት የቀኖና ሱባዔ ሲሰጠን በቤታችን ሆነን ወይም ወደ ገዳም ሄደን የተሰጠውን ንሰሐ ልንፈጽም እንችላለን። ሱባዔውን (ንስሐችንን) ከጨረስን በኋላ ደግሞ ያንን ኅጥያት እንዳንሰራ መጠንቀቅ እና ከአባቶች ምክር እንዲሁም ከቤተክርስቲያን እና ከበጎ ስራ መራቅ የለብንም።
ነገር ግን ማንኛውም ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባንን የመቀበል መንፈሳዊ ግዴታ ቢኖረውም፤ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ራሱን የቻለ ዝግጅት ከሌለ ንስሐ ስለገባን ብቻ የክርስቶስን ቅዱስ ስጋውን እና ክቡር ደሙን ለመቀበል አንገደድም። ምክንያቱም ትዳር ያለው ከኑሮ አጋሩ ጋር ተስማምቶ መዘጋጀት ስላለበት፤ ያላገባ ክርስቲያንም ከራሱ እና ከመንፈሳዊ አባቱ ተማክሮ ራሱን የቻለ ፕሮግራም ማድረግ ስላለበት ነዉ።
ኅጥያቶን በመናዘዝ ከልብ ተጸጽተው ወይም ተመልሰው፤ ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት በማገልገል ላይ ለሚገኘው የንስሐ አባትዎ (ካህን) ራስዎን በማስመርመርና ከፈጸሙት በደል የሚነፁበትን ንስሐ ተቀብለው ከሄዱና ከዳግም ጥፋትም እርቀው በካህኑ የተሰጠዎትን ንስሐ በትክክል ከፈጸሙ፤ ከተያዙበት የኅጥያት ማሰሪያ ስለተፈቱ ንስሐም ገብተው ስለተናዘዙበት እንደገና ይፍቱኝ ለማለት ወደ ካህኑ የሚያስኬድ ጉዳይ አይኖርብዎትም።
ምክንያቱም በኅጥያት እድፍ የቆሸሸውን ህይወትዎን ከካህኑ በተቀበሉት የንስሐ ውሃ ታጥበው ከኅጥያት እድፍ ፀድተዋልና። ዳግም እንዳይበድሉ፣ ኅጥያት ሰርተውም የቅድስና ሕይወትዎን እንዳያቆሽሸው፣ በየጊዜው ከቤተ ክርስቲያን መምህራንና የንስሐ አባቶች ትምህርትና ተግሳጽ እያገኙ ምንም እንኳን የኑሮ ፈተና ቢበዛብዎ ከእናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ሳይርቁ እየፆሙና እየፀለዩ ከገንዘብዎ፣ ከእውቀትዎ እና ከጉልበትዎም አስራት በኩራት እያወጡ በጎ ስራ በመስራት ከሰይጣን ወጥመድ ለማምለጥ የሚችሉበትን መንፈሳዊ ፀጋዎትን በተቻለ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ ማሳደግ እንዳለብዎ እመክራለው። ለዚህም ዋናውና መታወቅ ያለበት ነገር ማንም ክርስቲያን ያለጠባቂና ያለመካሪ ንስሐ አባት አንድ ቀንም መኖር ስለሌበት ወደ ንስሐ አባትዎ (ካህን) መሄድ ያለብዎ በየጊዜው የእለት እለት ህይወትዎን በካህኑ ምክር እንዲመራ ለማድረግ ነው።
በመሆኑም፤ ወደንስሃ አባትዎ ወይም ንስሐ ወደተቀበሉበት ካህን መሄድ የሚኖርብዎ ካህናት አባቶች የነፍሳችን እረኛ ሆነው በነፍስ ጉዳይ ላይ በሃላፊነት እግዚአብሔር ስለሾማቸው ሁልግዜም ቢሆን ከአባቶች ምክርና ተግሳጽ ላለመራቅ ነው እንጂ ቀደም ሲል ንስሐ ስለገቡበት ኅጥያት ይፍቱኝ ለማለት አለመሄድዎን እንደጥፋት ቆጥረው እንደገና ንስሐ እንዲገቡበት አያስፈልግዎትም በማለት መንፈሳዊ ምክሬን እለግሳለው። (ማቴ18፤18) ዩሐ(20፤21-23) ዩሐ (21፤15-18)
ከዚህ በላይ ስላቀረቡት ጥያቄ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ከፈለጉና ያልተመለሰልዎት ጥያቄ ካለም በውስጥ መስመር ሊያነጋግሩን ይችላሉ። ለሁሉም ነገር የእግዚአብሔር አጋዥነት ከእርስዎ ጋር ይሁን።
መልሱ አይቻልም ነው ። ምክንያቱም በቀኖና ቤተ ክርስቲያን በእያንዳንዱ ጥፋታችንና በደላችን ወደ መምሕረ ንስሐችን ቀርበን ኀጥያታችንን ስንናዘዝ ባጠፋነው ደረጃ ንስሐ መቀበል እንዳለብን በቀኖና ቤተክርስቲያን ተደንግጓል። ስለዚህ ማንኛውም ክርሰቲያን የፈፀመውን በደል ከእግዚአብሔር ቀጥሎ በሚስጥር ለንስሐ አባቱ መናገር አለበት፤ የሚሰጠውም ንሰሐ በጥፋቱ መጠን የሚቀበለው መሆን ይገባዋል። ስለዚህ ለንሰሐ አባቶቻችን የምንደብቀው የኀጢአት ሚስጥር የለንም። እንደምሳሌ ወደ ሀኪም ቤት የሚሄድ ታማሚ ወይም ታካሚ የህመሙ አይነትና መጠን ተለይቶ በሀኪም ዘንድ ሳይረጋገጥ መድሀኒት አይታዘዝለትምና። በቀጣይነት በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የምንሰጥበት መሆኑን እየገለፅን ለግዜው ለጥያቄው ምላሽ እንዲሆናቸው ይሄን ምክረ ሀሳብ ሰጥተናቸዋል።
አንድ ሰው ንስሀ ሳይገባ ጸበል መጠመቅ ይችላል? ወይንም ንስሀ ገብቶ ግን አንድ የረሳው ነገር ቢኖር ያልተናገረው፣ መጠመቅ እና ፀበል መጠጣት ይችላል? በማለት ለጠየቁን አባል ስለጸበል አጠቃቀምና አገልግሎት የተሰጠ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሽና ማብራሪያ ነው።
በቅድሚያ ፀበል ምንድነው? ለሚለው ካህኑ ውሃውን በእግዚአብሔር ቃል እና በቅዱስ መስቀሉ ሲባርከውና ሲቀድሰው ተራ የነበረው ውሃ በጥምቀት የእግዚአብዜር ልጅነት ይገኝበታል።
“ሰው ከውኅና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም” (ዩሐ 3፤5) በማለት የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ዳግም ለመወለድና ሰማያዊ መንግሥቱን ለመውረስ የእግዚአብሔር መንፈስ ባደረበት በውሃው (በጸበሉ) መጠመቅ እንዳለብን ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሌሊት ወደ እሱ ለመጣው ለወዳጁ ለኒቆዲሞስ በስፋት እንዳስተማረው ወንጌላዊው ቅዱስ ዩሐንስ ጽፎታል።
ለጥምቀት የተዘጋጀው ውሃ (ፀበል) የቤተክርስቲያን አባቶች ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀውን ጸሎት ከጸለዩበት እና በመስቀል ከባረኩት በኋላ ልዩ ልዩ ደዌ (በሽታ) ያለባቸው ሰዎች ይፈወሱበታል፣ ርኩሳን መናፍስት (አጋንንት) ያደሩበት ሰውም ሲጠመቅበት በፀበሉና በመስቀሉ ኃይል አጋንንቱ ከታመመው ሰው ዳግም ወደሰውየው እንዳይመለሱ በእግዚአብሔር ቃል ታሥረውና ተወግዘው ይለያሉ።
በጸበሉ ፈዋሽነት የሚያምን ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊም ሆነ ሌላው ወገን ሳያውቅም ሆነ እያወቀው የድግምት፣ የመተት፣ የሟርት መንፈስ ቢኖርበት በጸበሉ ከተጠመቀና ቤቱም ንብረቱ ጸበል ከተረጨበት ፈጽሞ ይድናል። ክፉ መንፈስም በእርሱ ላይም ሆነ በሃብቱና በቤቱ ላይ ጥፋት ለማድረስ ስልጣን የለውም።
አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በተለያየ ምክንያት ክርስቲያናዊ ሕይወቱን የሚያጎድፍና በእምነቱ ያልተፈቀደለትን ፈጽሞ ቢገኝ ደግሞ ወደ ካህናት (ወደ ንስሐ አባቱ) ቀርቦ ጥፋቱን መናዘዝ ወይም ንስሐ በመግባት በሥርዓተ ቄዶር እንዲጠመቅ ይደረጋል። ለምሳሌ ሃይማኖቱን ቀይሮ ቢገኝ፣ በሃይማኖት የማይመስለውን ቢያገባ (በዝሙት ቢወድቅ)፣ ለክርስቲያን ያልተፈቀደውን ምግብ ቢበላ ወዘተ የመሳሰለውን ኢክርስቲያናዊ ግብር ፈጽሞ ቢገኝ የቀድር ጥምቀት ያስፈልገዋል ማለት ነው።
በርዕሱ ወደተገለጸው ጥያቄ ስንመለስ ፀበል አንዱ የንስሐ መንገድ ስለሆነ ለንስሐ ከሚያበቃን የኅጢአት ሥራችን ለመመለስ በቁርጠኝነት ከወሰንን ጠያቂው እንዳሉት ፀበል ለመጠመቅም ሆነ ለመጠጣት እንችላለን። ይህን ስንል ግን የሠራነው ኅጢአት ተለይቶ መታወቅ አለበት። ምክንያቱም ለምሣሌ የወለደች ሴት፣ የሴቶች ልማድ የምታይ ሴት እስከሚነፁ መጠበቅ አለባቸው። ከዚህም በላይ ፀበሉን ብንጠጣውም ሆነ ብንጠመቅበት ከልብ በሆነ እውነተኛ መጸጸት ወደ ንስሐ ሕይወት ተመልሰን ከበደላችን ነፃ ካልሆን ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝራዎች፣ ሟርተኞች ፣ መተተኞች፣ አስማተኞች፣ ቀማኞች፣ ወንበዴዎች፣ ትዕቢተኞች፣ ፍርድ አጉዳዮች፣ ከሃዲዎች ወዘተ ሁነን በአጠቃላይ ከአንድ ክርስቲያን የማይጠበቅ ክፉ ሥራ እንደፈጸምን እያወቅንና በንስሐ ሣንታጠብ እግዚአብሔርንና ራሣችንን በመደለል በአስመሣይነት ፀበሉን ብንጠመቅበትም ሆነ ብንረጭ ጥቅም አይሰጥም። እንዲያውም ከበረከት ይልቅ መርገምን ያመጣብናል። በመሆኑም ኅጢአተኛ ሰው ስለበደሉ የጊዜ ቀጠሮ ሣይሰጥ የመዳን ቀን ዛሬ ስለሆነ ባለበት ቦታ ሁኖ ያለምንም ድካምና ውጣ ውረድ ከልብ ለሚያምነውና ለነፍሱ እረኛ አባት አድርጎ ለተቀበለው አባቱ ኅጢቱን መናዘዝ አለበት። በእርግጥ የእኛ ኅጢአት የእግዚአብሔርን ቅድስና አያረክስም። እኛ ግን ንስሐ ሳንገባ በድፍረት የምናደርገው ሁሉ ተጨማሪ ኅጢአት ስለሚሆንብን፤ ወደ ቤተክርስቲያን ለመግባትና ፀበል ለመረጨትም ሆነ ለመጠጣት የሚያስከለክለውን በደላችንን ለይቶ ለማወቅ ሁልጊዜም ቢሆን መምህራንን ወይም የቤተክርስቲያን አባቶችን እንድታማክሩ በእግዚአብሔር ስም አደራ እላችኋለሁ።
የመድኅኔዓለም ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን
ካህኑ ስለ አንድ ሰዉ ወይም ሰለ ብዙ ሰዎች በሚጸልይበት ጊዜ የክርስትና ስማቸዉን በመጥራት ወይም ዝም ብሎ ሊጸልይ ይችላል ምከንያቱም ካህኑ ጸሎቱን ከመጀመሩ በፊት ሁሉን ቻይ የሆነ አምላክ ስለማን እንደ ሚጸለይ ያውቀዋል አባቶች ካህናት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የክርስትና ስም መጥራት ሳያስፈልጋቸው ዘወትር ስለ ሁላችንም ይፀልያሉ እግዚአብሔርም ጸሎታቸውን ተቀብሎ ጥያቄያቸውን እንደሚፈፅምላቸው በቃሉ አረጋግጧል (ማቴ,16÷19) (ማር,1÷44) ዋናው ምስጢር ግን የሚጸለይለት ሰው በካህኑ ጸሎት ሐጢአቱ እንደሚሠረይለት ማመን ነው። ስለሆነም ካህኑ ንስሀ ስምዎን ቢሳሳቱም ድጋሚ ንሰሃ መግባት አየስፈልጎትም።
ጥያቄ 1 ፦ የንሰሀ አባት ነበረኝ ግን መተው አይጠይቁንም ትምህርትም አያስተምሩንም በታቸው እርቋል ምንድነው ማድረግ ያለብኝ ሌላ ለመያዝ እሳቸውን ማማከር አለብኝ ወይስ መቀየር ነው ያለብኝ ይሄንን ንገሩኝ ጥያቄ 2 ፦ንስሀ አባት እያለን ለሌላ ቄስ ብንናዘዝ ለዚህ መልሰን ንሰሀ መግባት አለብን ?
መልስ (ለጥያቄ #1) ፦ ንስሓ አባት እያለን ሳንሰናበት ወይም እስካሁንም የነበሩንን የንስሓ አባት ምንም አይነት ምክንያት ሳናገኝባቸው በራሳችን ምክንያት ብቻ ተነሳስተን ወደ ሌላ ንስሓ አባት ብንሄድ ስርአተ ቤተክርስቲያን አይፈቅድም። ምክንያቱም ጉዳዩ የነፍስ አባት እስከሆነ ደረስ የነፍስ አባት የመያዛችን ስርአትም አሰራሩ መንፈሳዊ ምሥጢር ስለሆነ የነበሩንን የንስሓ አባት ተሰናብተን ወደ ሌላው ለመሄድ በቂ ምክንያት ሊኖረንና፤ ሌላ አባት የፈለግንበትንም ምክንያት ያለምንም ማፈር ነግረናቸው ተሰናብተን መሄድ መብታችን ነው። ካህኑም በስርአት ካልጠበቁን ለምን ማለት አይችሉም። (ለጥያቄ #2) ዝም ብሎ ተነስቶ ሳይሰናበት የሄደ ግን እንደ ስርአተ ቤተክርስቲያን ትክክል ባይሆንም ነገር ግን የሄደውም ወደ ካህን ስለሆነ ይህ ንስሓ የሚያስገባ ጉዳይ አይደለም።
ጥያቄ 3. ፦ የንስሐ አባቶች ለንስሀ ልጆቻቸው ለምን በደንብ አያስተምሩም ለምንስ አይጠይቁም እኛ ስንጠፋ አይፈልጉም አሁን ለምሳሌ የኛ አሉ እኔ ደውዬ ካልጠየኩኝ አይጠይቁንም እና ለምን እንደዚህ ይሆናል?
መልስ፦ መንፈሳዊ እና ክርስቲያናዊ ህይወታችንን በአባትነት እንዲጠብቁን የያዝናቸው የንስሓ አባት ያደረግናቸው ካህን በራሳቸው ምክንያት እና ስንፍና ምንደኛ ቢሆኑ ማለትም ጠዋት ማታ እየገሰጹ እየመከሩ የማይጠብቁን አና ይበልጥ ወደ መንፈሳዊ አገልገሎት የማያተጉን ከሆነ ለአውሬ ወይም ደግሞ ለነጣቂ ለዲያብሎስ የሚያሰጥ ሰነፍ እረኛ ስለማያስፈልገን ያለምንም ቅድመ ሀኔታ ትጉህ እና ቅን የሆነ ለንስሓ ልጆቹ አገልግሎት ቅድሚያ ሁኔታ የሚሰጥ አባት መያዝ አለብን። በዚህ ጉዳይ ድረድርም ሆነ ማመንታት አያስፈልግም።
መልስ ፦ አባት ያደረግናቸው የንስሓ አባት ኃላፊነታቸውን ካልተወጡ ወደ ሌላ አባት ስንሄድ በስርአተ ቤተክርስቲያን ካህኑ በስርአት አሰናብተውን እንዲያሸጋግሩን የኃላፊነት ድርሻ አለባቸው። ያንን የማያደርጉ ከሆነ ግን ከምእመን ይልቅ ካህኑ ስለሆነ ትልቅ ኃላፊነት ያለው፣ በኛ ጉዳይም በቅድሚያ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚጠየቀው ካህኑ ስለሆነ የሱን ድርሻ ባለመወጣቱ በተሻለ መንፈሳዊ ጥበቃ ሊመራን እና ሊያስተምረን ወደሚችል ካህን ከመሄድ የሚያግደን ስርአት የለም። ስለዚህ ጠያቂያችን አሁን ከጠየቁት እና ከሚያሳስብዎት ጉዳይ ነፃ ስለሆኑ ሌላ አባት ይዘው ከመኖር የሚያግድዎት ሕግ ወይም ስርአት የለም።
መልስ ፦ ማንም ክርስቲያን ባለበት ደብር ወይም አካባቢ ንስሓ አባት እያለው፤ ለሌላ መንፈሳዊ አገልግሎት ወይም ደግሞ ወደ ገዳማት እና ቅዱሳት መካናት ወይም ቦታዎች ሄዶ በዛ ቦታ ላገኛቸው አባት፥ አለኝ የሚለውን አነጋግሮ ወይም ኅጢአቱን ተናዞ አስፈላጊውን የንስሓ ህይወት መቀበል ይችላል። የአባቶቻችን ፀጋ የአንዱ ፀጋ ከሌላው ፀጋ ይለያልና ሁሉም አባቶች ባላቸው ፀጋ በረከት ቢያድሉን ፀጋችንን ያበዛዋል እንጂ ነውር አይደለም።
ጥያቄ 6 ፦ ሰላም ፤ የሆነ ግዜ ንስሐ ገብቼ ነበር። በጣም ቆይቷል። እና ንስሐ የሰጡኝ አባት ንስሐዬን ከተቀበሉና ማድረግ ያለብኝን ነገር ከነገሩኝ በኋላ ተመልሰሽ ነይ አላሉኝም ነበር፤ ማለት ይፍቱኝ አልተባልኩም። እንደዛ መሆኑንም አሁን ቅርብ ጊዜ ነው ያወቅኩት። እና ድጋሚ ንስሐ መግባት አለብኝ?
ጥያቄ 7 ፦ ሰላም ለእርስዎ ይሁን መምህር ከንስሀ አባቴ ንስሓ ከተቀበልኩ ና ቀኖናየን ከጨረስኩ በሗላ ስትጨርስ እንገናኝ ብለውኝ ነበር ነገር ግን ሳልገናኛቸው ሌላ ቦታ ሄድኩ ምን ባደርግ ይሻለኛል ?? ።።
መልስ ፦ ማንም ክርስቲያን ባለበት ደብር ወይም አካባቢ ንስሓ አባት እያለው፤ ለሌላ መንፈሳዊ አገልግሎት ወይም ደግሞ ወደ ገዳማት እና ቅዱሳት መካናት ወይም ቦታዎች ሄዶ በዛ ቦታ ላገኛቸው አባት፥ አለኝ የሚለውን አነጋግሮ ወይም ኅጢአቱን ተናዞ አስፈላጊውን የንስሓ ህይወት መቀበል ይችላል። የአባቶቻችን ፀጋ የአንዱ ፀጋ ከሌላው ፀጋ ይለያልና ሁሉም አባቶች ባላቸው ፀጋ በረከት ቢያድሉን ፀጋችንን ያበዛዋል እንጂ ነውር አይደለም።
መልስ ፦ አንድ ከርስቲያን ንስሓ ገብቶ የተሰጠውን ቀኖና ከጨረሰ በኋላ፤ ጊዜ ካለው በአካል፣ ጊዜ ከሌለው ደግሞ በስልክ ወይም በሌላ መገናኛ መንገድ የተሰጠኝን ትእዛዝ ፈጽሜያለሁ ብሎ ሊነግራቸው ይችላል። ይህን ለማድረግ ከአቅሙ በላይ የሆነ ችግርቢያጋጥመው ግን ፤ ለሰራው ኀጢአት ካሳ ስለከፈለ፣ ከታሰረበትም የኅጢአት ማሰሪያ ስለተፈታ ለፈጣሪው በምስጢር ነግሮ ከዛ በኋላ ከመንፈሳዊ ነገር ላለመራቅ መትጋት አንጂ ወደ አባቴ ተመልሼ ይፍቱኝ ብዬ ስላልተናገርኩኝ ወይም እግዚአብሔር ይፍታህ ሰላላሉኝ ጥፋት ሊሆንብኝ ይችል ይሆን በማለት ሊያሳስብዎት አይገባም።
መልስ፦ ጠያቂያችን እንዲረዱት የምንፈልገው አንድ ንስሓ የሚገባ ክርስቲያን ከልቡ ተፀፅቶ እና አምኖ የሰራውን ጥፋቱን ለንስሓ አባቱ ከተናገረ በኃላ ንስሓ አባቱ ባመኑበት ነገር እንደ ቤተክርስቲያን ቀኖና ንስሓ ይሰጥዎታል። የሚሰጠውም ንስሓ ለሰራው ኀጢአት የተመጣጠነ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ኀላፊነት መውሰድ ያለባቸው የንስሓ አባቱ ናቸው። በእያንዳንዱ የንስሓ አይነት ምን አይነት ቀኖና መስጠት እንዳለባቸው አንቀፀ ንስሓ ያዛል። ስለዚህ በዚህ ነገር ንስሓ የሚቀበለውን ሰው ሊያሳስበው የሚገባ ነገር የለም። ነገር ግን መጠንቀቅ ያለንብን አስቀድመን በእውቀት እና በሃይማኖት የበሰሉ አባቶችን ከመያዙ ላይ ነው።
መልስ፦ ኅጢአት እየፈፀሙ መሆኑን ገልፀው ከዚህ ክፉ ሃሳብ የሚወጠበትን መንገድ እንድናሳይዎት ለጠየቁን አባላችን የተሰጠ ምላሽ፦
በመጀመሪያ ኅጢአት የሚስማማው ሰው ሆነን በመፈጠራችን ብቻ ጠላታችን ዲያበሎስ ይህንን እንደ ትልቅ ድክመት ቆጥሮብን ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር የምንታገለውን የፅድቅ ስራ እያስጣለ እሱ ወደሚፈልገው የኅጢአት መንገድ በጎተተን ቁጥር እንደ ደካማ ጎናችን ለያንዳንዳችን የምንወድቅበትን ኅጢአት ያሰራናል። የሰው ልጅ መላ ዘመኑን ለፅድቅ ስራ ከሚያሳልፈው ግዜ ይልቅ ለኅጢአት የሚያውለው ግዜ ብዙ ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር በኅጢአት ጠፍተን እንዳንቀር ተመልሰን ንስሓ እንድንገባ የሚፈቅድ አምላክ ስለሆነ ለዘመናት ከሰራነው ኅጢአት ይልቅ በተወሰነ የቀኖና ግዜ የሰራነው ፅድቅ ያንን ሁሉ ስፍር ቁጥር የሌለውን ጥፋት ፍቆ ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባት እንድንበቃ ታደርጋለች።
ስለዚህ ጠያቂያችን በኅጢአት መውደቅ የተለመደ የሰው የስጋ ባህሪ መሆኑን፥ በፅድቅ ወይም በንስሓ መነሳት ግን የክርስቲያን መንፈሳዊ ተጋድሎ ስለሆነ እስካሁን ድረስ ያሳለፉት የኅጢአትና የነውር ዘመን ምንም እንኳን ሰይጣን ቢፈታተንዎትም፤ እግዚአብሔር ከእርስዎ ህይወት ጨርሶ ስላልራቀ በውስጥዎት ፀፀት እና ወደ እግዚአብሔር መመለስን እያንፀባረቁ በመሆኑ ፈፅሞ ከጠሉት ህይወት ውስጥ እንደሚወጡና እግዚአብሔርም እንደሚረዳዎት እናምናለን። ከዚህ የጠለቀ የኅጢአት ጉድጓድ ውስጥ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመውጣት እንዲችሉ በግልዎት ሊያደርጉ የሚገባዎትን ምክር እና ትምህርት እንድንሰጥዎ ደግሞም በአባቶች በኩል እርስዎን ለማዳን መደረግ የሚገባውን መንፈሳዊ አገልግሎት ለማከናወን ይቻል ዘንድ አሁንም በውስጥ መስመራችን ደውለው ቢያገኙን መመካከር እንችላለን በማለት በድጋሚ ለማስታወስ እንወዳለን። ።
መጀመሪያ ንስሐ አባት ለመቀየር ያሰቡበት መንገድ መታወቅ አለበት ወይም ደግሞ ግልፅ መሆን አለበት። ምክንያቱ የቦታ ርቀት ከሆነ፣ ወይም ግዜ ሰጥተው የማያስተምሩ፣ የማይመክሩ ከሆነ፣ ዘወትር ክትትል እያደረጉ የማይጠብቅዎ ከሆነና ይሄን በመሰለ በቂ ምክንያት መቀየር ይችላሉ። ከዚህ ውጭ ግን ስላልፈለግኩኝ በሚል ሰበብ እንደ ምድራዊ ፍላጎት መንፈሳዊ አባትን ብዙም መቀያየሩ አስፈላጊ እንዳልሆነ እንመክርዎታለን። በበቂ ምከንያት አባት ተሰናብቶ ሌላ ይመክሩኛል፣ ያስተምሩኛል፣ በሃይማኖት እና በስነምግባር ያበረቱኛል ብለው ያሰቡትን አባት በማነጋገር በቤተክርስቲያን ስርአት መሠረት አባት ማድረግ ይችላሉ። ከንስሐ አባትዎ እንዴት እነደሚሰናበቱና እንዴት ሌላ ንስሐ አባት እንደሚይዙ የንስሐ አባቶችን እንጂ እርስዎን ስለማይመለከትዎ አያሳስብዎትም።
በመሰረቱ ቀኖና ወይም ንስሐ የሚሰጠን በፈጸምነው ኅጥያት መጠን ተለክቶ ስለሆነ እያንዳንዱ ያጠፋነውን ጥፋት ከባድም ቢሆን ሳንፈራ፤ ቀላልም ቢሆን ሳንንቅ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ለነፍሳችን እረኛ ላደረግነው ካህን መናገር እንዳለብን የቤተክርስቲያን ቀኖና ያዛል። የኅጥያት ደረጃችን ተለይቶ ሲታወቅ ንስሐ የሚሰጡን አባቶችም በጥፋታችን መጠን ስለሆነ ንስሓ ላልገቡበት ኅጥያት እንደገና መናገርና ቀኖና መቀበል ያስፈልጎታል።
በቅድሚያ ስለኀጢአታችን ስናስብ ትክክለኛ ሃሳብ የሚሆነው ኀጢአትን ማፈር ያለብን ስንሰራው እንጂ ስንናገረው መሆን የለበትም። እሱማ እንደ እውነቱ ካሰብነው ከኀጢአት የበለጠ ምንስ የሚያሳፍር ነገር አለ። ምክንያቱም እግዚአብሔር አሳምሮ አክብሮ ቀድሶ የፈጠረውን አካላችን በቅድስና እንዲኖር ተፈጥሮ ሳለ እራሳችንን መግዛት አቅቶን ብናደርገው ምንም ላይጠቅመን፣ ባናደርገውም የሚቀርብን ነገር ላይኖር ያው ጠላታችን ዲያብሎስ በመራን የጥፋት መንገድ ሄደን ኀጢአት ስንሰራ ለጊዜው የጠቀመን ወይም የተደሰትንበት ቢመስልም ነገር ግን ንፁህ የሆነው የቅድስና ልብሳችንን በኀጢአት እድፍ ቆሽሾ ስናየው እኛንም አንገት የሚያስደፋ በእግዚአብሔር ፊትም የሚያሳፍር ነውር ነው። ይሁን እንጂ ኀጢአት ባንሰራው መልካም ሆኖ ሳለ ከሰራነው ግን የመጨረሻ አማራጫችንና ከእግዚአብሔር ጋር የምንታረቅበት መንገድ ንስሓ ነውና የነፍስ እረኛ እንዲሆኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የክህነት ስልጣን የተሰጣቸው አባቶች ካህናት ስለሆኑ ጠያቂያችን ለንስሓ አባቶ ኀጢአቶን ተናዘው ቀኖናዎትን መውሰድ አለቦት። ያን ግዜ በግል ኑሮዎትም በማህበራዊ ህይወቶትም ያለው ግንኙነት ሰላም ይሆንልዎታል፤ የተረጋጋ መንፈስም ይኖርዎታል። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ፀጋና ሰላም ከእርስዎ ጋር ስለሚሆን። የንስሓ አባቴን ቀርቤ ለማማከር አፈርኩ ላሉት፥ እንደ ቤተክርስትያናችን ስርዓት ከሆነ በእርስዎ እና በንስሓ አባትዎ መካከል ለመናገር እሚያሳፍርም ሆነ የማይነገር ምስጢር መኖር የለበትም። እማትታየውን ረቂቋን ነፍስ በኃላፊነት የተሰጠው ካህን ስለሆነ ለመናገር መድፈር አለብዎት እንላለን። ከዚህ ሌላ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ወይም እኛ ያልተረዳንዎት ጉዳይ ካለ መፍትሄ እንድንሰጥዎት በውስጥ መስመር የግኙን።
ጠያቂያችን በመጀመሪያ ንሰሐ መግባት ወይም ኀጥያታችንን መናዘዝ ማለት ምን ማለት እንደሆነ መንፈሳዊ ትርጉሙን እና ሚስጥሩን በማስተዋል እና በትእግስት ሆነው መረዳት ያሰፈልጋል። እስካሁን ስለ ንሰሐ በ ዩሐንስ ንስሐ ድረ ገፃችን ላይ ባሰፈርናቸው ፅሁፎች በቂ የግንዛቤ መልእክት እንዳስተላለፍን ተስፋ እናደርጋለን። የእርሶም ጥያቄ እስካሁን ከፃፍናቸው መልእክቶች ጋር አብሮ የሚያያዝ ቢሆንም፤ ነገር ግን ለመረዳት መጠየቅ ከምንም በላይ የሚበረታታ በመሆኑ ለእውነተኛ ንስሐ ህሊናዎትን በማሳመን ተፀፅቻለው፣ ንሰሐ ገብቻለሁ፣ ኅጥያቴን ተናዝዣለሁ ብሎ ማመን የሚቻለው ለንስሐ የሚያበቁ መስፈርቶች እና ቅደም ተከተሎች ተጠብቀው ማለትም ፦
1/ የተሰራውን ኅጥያት ጥፋት መሆኑን ማመን ፣
2/ ስለተሰራው ጥፋት ከልብ ተፀፅቶ ንሰሐ ለመግባት መዘጋጀት፣
3/ ወደ ንስሐ አባታችን በማምራት ኅጥያታችንን በመናዘዝ ንስሐ መቀበል፣
4/ የተሰጠንን ንስሐ በአግባቡ መፈጸም፣
5/ ዳግመኛ ኅጥያት ላለመስራት በአባቶች ትምህርትና በመንፈሳዊ አገልግሎት መፅናት፣
6/ በፆም፣ በፀሎት፣ በስግደት ዘወትር በመትጋት መንፈሳዊ ህይወትን ከጊዜ ወደ ጊዜ ማጠናከር ያስፈልጋል።
በዚህ ክርስቲያናዊ ስነምግባር ስንበረታ ከግዜ ወደ ግዜ መንፈሳዊ ፀጋችን እያደገ የእግዚአብሔር መንፈስ ከእኛ ጋር ሲሆን፤ ለንስሐ እንዳንዘጋጅና ከልባችን እንዳንፀፀት ዘወትር የሚቃወመንን እና ሠይጣናዊ አዚም የሚጥልብን ክፉ መንፈስ ከዛ ርቆ ለመሄድ ይገደዳል። በአጠቃላይ መንፈሳዊ ፀጋ በሂደት እና በመንፈሳዊ ተጋድሎ የሚመጣ እንጂ በአንድ ግዜ የማይሆን ስለሆነ አባቶቻችንን በማማከር መንፈሳዊ ጉዞዎን በትእግስት እንዲቀጥሉ እንመክራለን። ንስሐ ስለገቡበት ኅጥያትም ለሁለተኛ ጊዜ ደግመው መናዘዝ አያስፈልግዎትም።
የንስሐ አባት ይዘው እንደማያውቁና ንሰሐ ለመግባት ፍላጎት እያለዎት ወደ እግዚአብሔርም ለመመለስ እያሰቡ በማያዉቁት ምክንያት የፈለጉትንና የተመኙትን የንስሐ ህይወት ለመፈፀም እንዳልቻሉ በመግለፅ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ለጠየቁን አባላችን የሚከተለውን የምክር አገልግሎት እንዲደርስዎት አድርገናል።
እንደ ቅዱስ መፅሐፍ አስተምሮ ማንኛውም ክርስቲያን በ 40 እና በ80 ቀን የእግዚአብሔር ልጅ ከሆኑበት ቀን ጀምሮ ከእግዚአብሔር ቤት እና ከምክረ ካህን መለየት እንደሌለባቸው ይደነግጋል። በመፅሐፍ ቅዱስም ሆነ በሌሎች የሃይማኖታችን መፃህፍት እንደምንረዳው የሰው ልጅ ለመኖር ለስጋው ምግብ ፣ ልብስ ፣ መጠለያ ወዘተ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለነፍሱም መንፈሳዊ ምግብ ያስፈልጉታል። የነፍስ ምግብ ማለት በተዋህዶ ሃይማኖት ፀንቶ መኖር፣ ንሰሐ መግባት፣ መፆም፣ መፀለይ፣ መስገድ፣ ቃለ እግዚአብሔር መስማት፣ ወደ ቤተክርስቲያን ሄዶ መሳለም፣ አስራት በኩራት ማውጣት፣ ለነዳያን ምፅዋት (ቸርነት) ማድረግ፣ በህመምና በእስር ቤት ያሉትን መጎብኘት፣ የእለት ማስቀደሻ ላጡ አብያተ ክርስቲያናት ንዋየ ቅዱሳት ማሟላት፣ የጌታን ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን መቀበል ባጠቃላይ በክርስቲያናዊ ስነምግባር ተወስኖ መኖር የማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ተቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል። ይሁን እንጂ ጠያቂያችን መንፈሳዊ ሆኖ መቀጠልን እየወደዱ ወደ አስቡት በጎ ምኞት እንዳይገቡ የሚያከላክልዎት የበጎ ነገር ጠላት የሆነው ክፉ መንፈስ እየተቃወምዎት በመሆኑ መሠረታዊ የአባቶች ምክር እና በፀሎት የሚሆን የንስሐ ጥሪ ያስፈልግዎታል። በፅሁፍ በሚደርስ መልእክት ብቻ ከገቡበት ፈተና መውጣት ስለማይችሉ ስለእርስዎ በአባቶች በኩል ፀሎት ያስፈልግዎታል። እራስዎም የሚፀልዩበት የግል እና የስግደት ፆም ወዘተ ያስፈልግዎታል። ከፈተና ሊወጡ እንዲችሉ የሚያበቃዎትን የእግዚአብሔርን ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‘ነገር ግን ወደ ንሰሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወድዶ ስለእናንተ ይታገሳል። በማለት እግዚአብሔር የእኛን ወደ ንስሐ መመለስ በትእግስት እንደሚጠብቀን አረጋግጧል። (ጴጥ 3፥9)
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በአቴንስ ከተማ ለሚኖሩ የግሪክ ሰዎች ።”እንግዲህ እግዚአብሔር የቀድሞውንስ ያለማወቅ ዘመን አሳልፎታል (በኀጥያት የመኖር ዘመንን) ፤ ዛሬ ግን በመላው አለም ንስሐ እንዲገቡ ሰውን ሁሉ አዟል። (የሐዋ 17፥30)
ነብዩ ሕዝቅኤል እግዚአብሔር የሰውን ሞት የማይወድ እና ሰው ወደ ንስሐ መመለሱን የሚወድ መሆኑን ሲናገር ”ንሰሐ ግቡ፤ ኀጥያትም እንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኀጥያታችሁ ሁሉ ተመለሱ። የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ። አዲስ ልብ እና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ፤ ..ስለምን ትሞታላችሁ የሟችን ሞት አልፈቅድምና ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ስለዚህ ተመለሱ እና በህይወት ኑሩ። (ሕዝ 18፥30-32)
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በበዓለ ሃምሰ መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ሰወች ሁሉ ዘለአለማዊ ህይወት እንዲቀርቡ የንስሐ ጥሪ ሲያቀብላቸዉ ”እንግዲህ ከጌታ ፊት የመፅናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ …ኀጥያታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንሰሐ ግቡ ተመለሱም” በማለት አስተምሯል። (የሐዋ 3፥19-20)
ነብዩ ሚልክያስም “ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር” በማለት ሰው በንሰሐ ሲመለሰ እግዚአብሔርም ይቅር እንደሚል ተናግሯል። (ሚል 3፥7)
ነብዩ እዩኤልም ” አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍፁም ልባችሁ በፆም በለቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ ልባችሁን እንጂ ልብሳችኹን አትቅደዱ መሓሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔር ፤ ቁጣው የዘገየ ምህረቱም የበዛ ለክፋትም የተፀፀተ ነዉና ወደ እርሱ ተመለሱ” በማለት የእግዚአብሔርን መሓሪነት እና ቸርነት ይቅር ባይነትንም አስተምሯል።
ብርሃናተ አለም ቅዱስ ጳውሎስም የሰው ልጅ ከጥፋቱ ተፀፅቶ ወደ ንሰሐ ህይወት እንዳይመለስና ለማድረግ የፈለገዉን በጎ ስራ እንዳይፈፅም ርኩስ መንፈስ እንዴት እንደሚቃወመው ሲናገር “እኔ ግን የኃጢያት በታች ልሆን ተሽጫለሁ…የማደርገውን አላዉቅምና፤ ያንኑ የምጠላውን ብቻ አደርጋለሁና፤ ዳሩ ግን የምወደውን እሱን አላደርገውም፤ የማልወደውን ግን የማደርግ ከሆንሁ…ያን የማደርገው አሁን እኔ አይደለሁም በእኔ የሚያድረው ኀጥያት ነዉ እንጂ” በማለት በአገልግሎት የደረሰበትን የመንፈስ ዉግያ ምሳሌ በማድረግ መክሮናል። ( ሮሜ 7፥14-47)
በመጨረሻም የንስሐ ህይወት ለአንድ ክርስቲያን ቋሚና አስፈላጊ ተግባር ስለሆነ ከልብ በሆነ መንፈሳዊ ፍላጎት ይኸን አጭር መልእክት ደጋግማችሁ እንድታነቡና በተጨማሪ መረጃ ስትፈልጉም በዉስጥ መስመር ማግኘት የምትችሉ መሆኑን አበክሬ እመክራለሁ።
ከሁሉ አስቀድሞ እንዲረዱት የሚያስፈልገው ማንኛውም ሰው ኀጥያት ሰርቶ ንስሐ ከገባ በኋላ ተመልሶ በኀጥያት መሰናከል የተለመደ ስጋዊ ተፈጥሮ ነው። ምንም እንኳን የኛ አምላክ መድኃንያለም ስለኛ ኀጥያት በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ለአንዴና ለመጨረሻ ሞትና መቃብርን ሽሮ ነፃ ቢያወጣንም፤ ሰው ግን ከጠላቱ ከዲያብሎስ በየጊዜው በሚጠመድበት የኀጥያት ወጥመድ እየተያዘ፣ እግዚአብሔር ስለኛ ያደረገውን ውለታም በመዘንጋት በደል ቢፈጽምም እንኳን ቸርና መሃሪ የሆነ አምላካችን ግን አሁንም በንስሐ ወደ እሱ እንድንመለስ መንገድ ሰጥቶናል።
በዚሁ መሰረት ከሰይጣን ጋር ያለን ውግያ የማይቋረጥ ስለሆነ አንድ ግዜ ስንወድቅ፣ አንድ ግዜ ስንነሳ የምንቀጥልበት አለም የፈተና ጊዜ ስለሆነ በእርስዎ ብቻ የደረሰ አድርገው ተስፋ መቁረጥ የለቦትም። ኀጥያት ለሰው ልጅ ሞትን የሚያስከትል ክፉ ደዌ ቢሆንም ንስሐ ደግሞ የሚፈውስ መድሀኒት ነው። ስለሆነም አብዝቶ መፀለይ፣ መፆም፣ ንስሐ መግባት፣ በአጠቃላይ ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔርን ቸርነትና ምህረት መጠየቅ ክርስቲያናዊ ፀባይ መሆን አለበት።
ከዚህ በላይ የተቸገሩበት ነገር ካለ በውስጥ መስመር ስልክ እንዲደርስዎ አድርገናልና ደውለው ቢያሳውቁን ምክራችንን እና ከፈተና የሚወጡበትን መንገድ እናሳይዎታለን፣ በአባቶች ዘንድም በፀሎት እንዲታሰቡ ይደረጋል።
መጀመሪያ ንስሐ አባት ለመቀየር ያሰቡበት መንገድ መታወቅ አለበት ወይም ደግሞ ግልፅ መሆን አለበት። ምክንያቱ የቦታ ርቀት ከሆነ፣ ወይም ግዜ ሰጥተው የማያስተምሩ፣ የማይመክሩ ከሆነ፣ ዘወትር ክትትል እያደረጉ የማይጠብቅዎ ከሆነና ይሄን በመሰለ በቂ ምክንያት መቀየር ይችላሉ። ከዚህ ውጭ ግን ስላልፈለግኩኝ በሚል ሰበብ እንደ ምድራዊ ፍላጎት መንፈሳዊ አባትን ብዙም መቀያየሩ አስፈላጊ እንዳልሆነ እንመክርዎታለን። በበቂ ምከንያት አባት ተሰናብቶ ሌላ ይመክሩኛል፣ ያስተምሩኛል፣ በሃይማኖት እና በስነምግባር ያበረቱኛል ብለው ያሰቡትን አባት በማነጋገር በቤተክርስቲያን ስርአት መሠረት አባት ማድረግ ይችላሉ። ከንስሐ አባትዎ እንዴት እነደሚሰናበቱና እንዴት ሌላ ንስሐ አባት እንደሚይዙ የንስሐ አባቶችን እንጂ እርስዎን ስለማይመለከትዎ አያሳስብዎትም።
ስለሰራነው ጥፋት የንስሓ ካሳ ልንከፍል ወይም ደሞ የፈፀምነውን በደል ሊየስፍቅልን የሚችለው ንስሓ ብቻ ስለሆነ ለካህን በመናገር ንስሓ መግባት ያስፈልግዎታል። የቃል ኪዳን ቦታ ያሉት ለቅዱሳን የተሰጣቸው ፀጋ ልዩ ልዩ ስለሆነ በቃልኪዳን ቦታ ስንሄድ እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት የምናገኘውን በረከት እሱ ብቻ ነው የሚያውቅ እንጂ በግላችን በሰራነው ኀጢአት የቃልኪዳን ቦታ ሄደናልና ኀጢአታችን ሊፋቅልን ይችላል ማለት አንችልም።
እርሰዎ የሚያውቁት እና ከልብ ያልፋቁት ኀጢአት ካለ ወይም ለንሰሓ ያልበቁበት ኀጢአት ካለ ለንሰሓ አባትዎ ተናግረው ቀኖና መቀበል ያስፈልጋል ። ከዚህም በላይ ክርስቲያን ኀጢአቱን አምኖ ለንስሐ አባቱ መንገር ማለት ከልብ ተጸጽቶ ኀጥአትን ተጸይፎ እጁን ለፈጣሪው መስጠቱን የሚገልጽበት መንፈሳዊ መንገድ ነው። ከምንም በላይ ውስጣችን ከሚዋጋን ኀጢአት ነጻ ይሆን ዘንድ ዘወትር ትግላችን ከረቂቅ መናፍስት ጋር ነው። ስለዚህ በዚህ አይነት መንፈሳዊ ስርአት ኀጢአት ከተናዘዝን በኋላ በእግዚአብሔርም ቤት አየተመላለስን ከምህረት አደባባዩ እንዳልተለየን እያወቅን ሰይጣን ከፉ መንፈስ ባደረባቸው ሰዎች ላይ በሚለፈልፈው እና በሚያቃዠው ቀዠት ኀጢአታችን አልተፋቀልንም ማለት አንችልም። የብዙ ሰዎች ችግራችን ምልክት ፈላጊዎች ነን። በሌላም መልኩ ሲጀመር ሰይጣን የሀሰት አባት ስለሆነ ከሰይጣን ምን አይነት እውነት ይጠበቃል? እሱ በተናገረው የሀሰት ቃል ካመንን የእግዚአብሔርንስ እንዴት እንሆናለን? ስለዚህ ይሄ እንዳያሳስብዎት አይምሮዎትን ነፃ ያድርጉ። ይልቁን ከሚያጨናንቅዎት መንፈስ ወጥተው ቸርነትና ምህረቱ ብዙ የሆነ አምላክ ስለ እኛ ያለው ፍቅርም ወሰንና ገደብ የለውምና እንደኛ ኀጢአትና በደል ሳይሆን እንዳንተ ምህረት እና ቸርነት አስበኝ እያሉ በዘወትር ጸሎት ይጠይቁት።
ወንድ የወለደች አንድ ሱባዔ (7ቀን) ፤ ሴት የወለደች (14 ቀን) ፀበል እስከምትረጭ ማንም ሰው ወደ እርሷ አይገባም እንጂ ከንስሓ መግባት ጋር ወይም ደግሞ የወለደችጋ በመግባታችን ወይም በመጠየቃችን ንስሓ የሚያስገባ ኀጢአት መሆኑ አይደለም። አራሷም ብትሆን በወለደች ጊዜ ክርስትናዋን አጥታለች ማለት አይደለም። እሰከ 7 ወይም እሰከ 14 ቀን ድረስ የተፈጥሮ ልማድ ለሰውነቷ እርኩሰት ስላመጣባት ማንም ሰው በዛን ሰአት ወደሷ መቅረብ እንደሌለበት ነብዩ ሙሴ በኦሪት ዘሌላዉያን ላይ ስለደነገገው ከዚያው ጋር ተያይዞ የመጣ ስርአት ነው። (ዘሌ 12፥1-8)
መልስ፦ ከንስሓ በኋላ ምን ላድርግ ብለው ለጠየቁን አባላችን፦ አንድ ክርስቲያን በኅጢአት የጎደፈውን ሰውነቱን ከታጠበ በኋላ መላ ህይወቱ ንፁህ ስለሆነ ለማንኛውም መንፈሳዊ አገልግሎት መንገዱ ሁሉ ቀና ስለሆነ ማድረግ ያለበት ምን እንደሆነ ከዚህ በፊት በተጠየቅነው ሃሳብ ተነስተን ምላሽ የሰጠንበት ቢሆንም አላማችን ምእመናንን ማገልገል እስከሆነ ድረስ አሁንም ጠያቂያችን ከንስሓ በኋላ ምን መሆን እንዳለብዎት የምናስረዳዎት፦
1ኛ/ ከምንም በላይ ዳግም ወደ ኀጢአት ተመልሰው የተቀደሰውን ህይወትዎትን እንዳያረክሱት መጠንቀቅ፣
2ኛ/ እግዚአብሔር ቢፈቅድልዎት በቅዱስ ቁርባን መወሰን፣ አቅምዎት በሚፈቅደው መጠን ሳያቋርጡ እና ሳይሰለቹ መፆም፣ መፀለይ፣ እና መስገድ፣
3ኛ/ በአቅምዎት ከሚያገኙት ነገር ለድሆችና ለእግዚአብሔር የሚገባውን አስራተ በኩራት ማዋጣት፣
4ኛ/ ዘወትር ከአባቶች ምክር እና መታዘዝ አለመራቅ፣ በፕሮግራም ወደ ቤተክርስቲያን እየቀረቡ ቃለ እግዚአብሔር መማር፣
5ኛ ሁሌ እንደቅርብ አስተማሪና መካሪ ሁነው የሚያገለግሎትን መንፈሳዊያን መፃህፍትን ማንበብ፣ ከዚህም በላይ በኑሮዎት ውስጥ፣ በስራ ቦታ፣ በማህበራዊ ጉዳይ ከሰው ልጅ ሁሉ ጋር በሰላም እና በፍቅር በትዕግስት እና በጥበብ ለመኖር ድርሻዎትን መወጣት።
እነዚህን ሁሉ እና ሌሎችንም መንፈሳዊ ነገሮችን አጠቃሎ ለመስራት የሚቻለው ሰው ህይወቱ በንስሓ ሲታደስ ስለሆነ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የእርስዎን ህይወት በንፅህና በቅድስና እንደሚጠብቃት በማመን ከዚህ በላይ የተሰጠዎትን መንፈሳዊ ምክር በስራ ላይ ለማዋል እንዲችሉ እግዚአብሔር ይርዳዎት።
የንስሐ ሱባኤ ከተሰጣቸው በኋላ ንስሐቸውን ሳይጨርሱ የወር አበባ ቢመጣባቸው፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚፈፀም ንስሐ ከሆነ ወይም ደግሞ ወደ ገዳም ሄደው የሚፈፀም ከሆነ በዚህ ወቅት መቅረብ ስለማይቻል ባሉበት ቦታ ሆነው መፆምና መስገድ ይችላሉ። በቀኖና ቤተክርስቲያን እንደተወሰነው በተወሰነ ርቀት ላይ ቆመው መንፈሳዊ ስርአቱን መከታተል የችላሉ።
የንስሐ ሱባኤ ከተሰጣቸው በኋላ ንስሐቸውን ሳይጨርሱ የወር አበባ ቢመጣባቸው፤ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚፈፀም ንስሐ ከሆነ ወይም ደግሞ ወደ ገዳም ሄደው የሚፈፀም ከሆነ በዚህ ወቅት መቅረብ ስለማይቻል ባሉበት ቦታ ሆነው መፆምና መስገድ ይችላሉ። በቀኖና ቤተክርስቲያን እንደተወሰነው በተወሰነ ርቀት ላይ ቆመው መንፈሳዊ ስርአቱን መከታተል የችላሉ።
መልስ፦ ንስሓ በስልክ ይቻላል ወይ ብለው ለጠየቁን ከዚህ በፊት ይህንን በሚመለከት ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦልን ስለነበር ተገቢውን መልስ ሰጥተንበታል። ጠያቂያችን ማወቅ ያለብዎት በስልክም ይሁን በአካልም ይሁን በሌላም መገናኛ መንገድ ይሁን ዋነኛው አላማው የሰራነውን በደላችንን እና ኀጢአታችንን በንስሓ ማጥፋት ነው። ስለዚህ በአካባቢዎ ካህን ማግኘት የማይችሉ ከሆነ በራስዎትም ሆነ በሚያምኑት ሰው በኩል ያገኙዋቸውን እውነተኛ ካህን፤ ወይም በድረገፃችን ላይ ካሉ አባቶች ንስሓ አባት በማድረግ ባሉበት ቦታ ሁነው በስልክም ይሁን በሌላ መገናኛ መንገድ ንስሓ መግባትና ተግሳፅና ምክርንም ማግኘት ይችላሉ። በይበልጥም እንዲረዱት ከዚህ በፊት በዚህ ጉዳይ ላይ የተሰጠውን ምላሽ እንደሚከተለው በድጋሚ ልከንልዎታል።
“ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ (አማኝ) የሆነ ክርስቲያን ለአካለ መጠን ከደረሰበት ግዜ ጀምሮ የንስሐ አባት መያዝ ክርስትያናዊ ግዴታው እንደሆነ በቤተክርስቲያን የቀኖና መጽሐፍ ተደንግጓል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመናን ኑሮዋቸውን ለማሸነፍና የተሻለ ኑሮ ለመፈለግ ሲሉ ቤተክርስቲያንና ካህናት አባቶች ወደማይገኙበት ክፍለ ዓለም በልዩ ልዩ ምክንያት ተበትነው እንደሚኖሩ ይታወቃል። ሌላው ቀርቶ በኢትዮጵያ አገራችን ሳይቀር በረሃማና ጠረፋማ በሆነ አካባቢ እንዲሁም አህዛብ በሚበዛበት ቦታ የሚኖሩ ክርስቲያኖች በመከራና በፈተና ግዜ የሚያጽናናቸውና የሚመክራቸው አባት ሊያገኙ አይችሉም። የሚጸልዩበት እና ፈጣሪያቸውን የሚማፀኑበት ቤተክርስትያንም አያገኙም።
ስለዚህ በቅዱስ መጽሐፍ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነግረን ሰውን በነፍስ የማዳን ሥራ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው። ቤተክርስቲያንና አባቶች ካህናት በቅርብ የማይገኙበት ክፍለ ዓለም (አካበቢ) የሚኖሩ ማለትም በአውሮፓ፣ በአሜሪካ፣ በአፍሪካ፣ በአረብ አገሮች እና በሌላውም ክፍለ አለም ሁሉ እየኖሩ የንስሐ አባት ለመያዝ ቢፈልጉ ከምንም በላይ እግዚአብሔር የኛን የውስጥ ችግር ያውቀዋልና አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ያለ ንስሐ አባት አንድ ቀንም መኖር ስለሌለበት የንስሐ አባት እንዲኖረው በሃይማኖቱና በመንፈሳዊ ህይወቱ የመረጠውን ካህን እርቀት ሳይገድበው መያዝ ይችላል። ካለው ችግር አንፃርም በስልክ እና በሌላ መልእክት በመገናኘት መንፈሳዊ ትምህርት እና ከንስሐ አባት የሚሰጠውን የንስሃ ቀኖና መቀበል ይችላል። ማንኛውንም በጎ ስራ ሁሉ አባቱ የሚመክሩትን እና የሚያዙትን ሁሉ በመፈፀም የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ ስለሚችል የግድ በአካል ካላገኘኋቸው አብሬ በአንድ አጥቢያ ካልኖርኩኝ የንስሐ አባት መያዝ አልችልም በሚል ምክንያት ያለጠባቂ መኖር የለበትም።
ይህን በሚመለከትም ከዚህ በፊት ስለ ንስሐ አባት አያያዝ ጥያቄ ቀርቦ በአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት እና በቤተክርስትያን መምህራን ንስሐ አባት በርቀት መያዝ እንደሚቻል በተደጋጋሚ ምላሽ የተሰጠበት ሃሳብ ስለሆነ፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት እንዲያሥሩና እንዲፈቱ የሰጣቸው ስልጣነ ክህነት ጊዜና የቦታ ርቀት የማይወስነው ስለሆነ በአካባቢው አባት የሚሆን ካህን ከጠፋ ያለጠባቂ ብንኖር ጠላታችን ዲያብሎስ ነፍሳችንን እንዳይነጥቃት የንስሐ አባት በርቀት መያዝ ይችላሉ። በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ላይ ምእመናን መጨናነቅ እንደማያስፈልጋቸው መንፈሳዊ ምክራችንን እንለግሳለን።”
በተጨማሪም፤ ስለንስሓ ትምህርት በድረገፃችን ላይ የተላለፉና እየተላለፉ ያሉትን ተከታታይ ትምህርቶች ይህን ሊንክ በመጫን ያንብቡ።
ትምህርት ስለ ንስሓ – https://yohannesneseha.org/
የንስሓ አባት ገጽ – https://yohannesneseha.org/
መልስ፦ ስለ ንስሓ ህይወት የጠየቁን አባላችን ንስሓ ማለት ማንኛውም በእግዚአብሔር ሀልዎት የሚያምን እና በክርስቲያናዊ ስነምግባር የሚኖር በየጊዜው በስጋ ምኞት በሚመጣበት ፈተና ከትንሽ እስከ ትልቅ ወይም ቀላልም ይሁን ከባድ ኀጢአት እንደሰራ የሰው ምስክር ሳያስፈልግ ራሱ በህሊናው ተጸጽቶ የፈፀመውን ኀጢአት ካመነ ወደ ንስሓ አባቱ ቀርቦ የሰራውን ጥፋት በመናዘዝ እንደ ኀጢአቱ ክብደት ንስሓ ይሰጠዋል። አስቀድመን በተደጋጋሚ እንደተናገርነው ከልብ መፀፀትና ንስሓ ለመግባት የቀጠሮ ጊዜ ሳናራዝም ወይም ባለብን የዘወትር ስጋዊ ፈተና ሳንፈራና ነገሮችን ሳናከብድ በአስቸኳይ የነፍሳችን ሃኪም ወደሆኑት የንስሓ አባት በመሄድ በፅኑ ከተያዝነው የኀጢአት ደዌ በንስሃ ህክምና የነፍስ ድህነት ማግኘት አለብን። በዚህ ንስሓ በሚቀበለው ክርስቲያን እና ንስሓ በሚሰጠው አባት መካከል የሚፈፀመው አገልግሎት የሚታይ መንፈሳዊ ስርአት ሲሆን በዚህ መታዘዝ ውስጥ እግዚአብሔር በረቂቅ መለኮታዊ ጥበቡ በካሕኑ ላይ አድሮ በፍጹም እምነት ኀጢአቴ ይፋቅልኛል ብሎ ከልብ በመታዘዝ ለንስሓ ህይወት የቀረበውም ምእመን ያለምንም ጥርጣሬ ኀጢአቱ ይቅር ይባላል ማለት ነው። ስለዚ በመፅሐፍ ቅዱስ እና በሌሎቹ ቅዱሳን መፃሕፍት በብዙ ቦታ ላይ እንደተገለፀው እግዚአብሔር ኀጢአት ይቅር እንደሚል እኛም ከኀጢአታችን እና ከበደላችን ተፀፅተን ወደ ፈጣሪ እንድንመለስና የእግዚአብሔር እንደራሴ ለሆኑ የሃይማኖት አባቶቻችን እንድንናዘዝ ታዘናል። ስለዚህ ጠያቂያችን በእርስዎ በኩል እኛ ያላወቅነውና ያልተረዳነው ውስጣዊ ችግር ቢኖር እንኳን ሁሉም ነገር በፈጣሪ ዘንድ ኢምንት ስለሆነ ከባድ ያሉትን ጭንቀት እና ሃሳቦትን በእግዚአብሔር ላይ በመጣል ሳይጠራጠሩና ሳያመነቱ ከተያዙበት የኀጢአት ደዌ በፍጥነት ለመውጣት ጊዜ ሳይሰጡ ወደ ቤተክርስቲያን እና ወደ አባቶች ይቅረቡ። ታሰር ተፈለጥ በሚል ስጋዊ ዳኝነት የሚጠየቁበት ጉዳይ ስለሌለ ምህረቱና ቸርነቱ ፍቅሩና ትእግስቱ ወደ በዛው ወደ እውነተኛው አምላክ ስለሆነ የሚቀርቡት፤ የንስሓ ህይወትም ለክርስቲያኖች እድል የሚመች አላማ ስለሆነ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሲኦል ወደ መንግስተ ሰማያት፣ ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ፅድቅ፣ ከሞት ወደ ህይወት የሚያመጣ ቀና መንገድ ስለሆነ የጊዜ ቀጠሮ ሳይሰጡ ወደ ቤተክርስቲያን አባቶች ቀርበው ችግሮትን በማስረዳት መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ለማግኘት ህሊናዎትን ያዘጋጁ። የንስሓ ግዜን በሚመለከት እንደተፈፀመው የኀጢአት ክብደትና ቅለት ከሰአታት ጀምሮ እስከ ቀናትና ሳምንታት የሚወሰን ይሆናል። ስለዚህ የኀጢአት አይነት ሲታወቅ በቤተክርስትያን ቀኖና በተደነገገው መሰረት ንስኃ ሚሰጡን አባቶች የንስኀውን ግዜ ይወስኑታል እና በዚህ አይነት ከባድ እንደሆነ ግን ማሰብ የለቦትም ። ባጠፋነው መንገድ እንድንቀጥል ሰይጣን ነገሮችን ሁሉ ስለሚያከብድ እና ስለሚያጨልም ብቻ ካለንበት የኀጢአት ጉድጓድ ውስጥ እንዳንወጣ ስለሚያደርግ ነው። ከዚህ በላይ እኛ ያልተረዳንዎት ከእርስዎም አቅም በላይ የሆነ ችግር ካለ መንፈሳዊ ትምህርት እንድንሰጥዎት በውስጥ መስመር ያነጋግሩን።
የንስሐ አባት ይህን የድረ ገጻችንን አድራሻ በመጫን ይያዙ: https://yohannesneseha.org/
ከዚህ በፊት በዚህ ጉዳይ ላይ የተሰጠውን ምላሽ እንደሚከተለው በድጋሚ ልከንልዎታልና ይመልከቱት ፦
በቅድሚያ በድያለሁ ጥፋት ሰርቻለሁ ኅጢአት ፈጽሜያለሁ ብሎ ኅጢአትን ለመናዘዝ ፈቃደኛ መሆንና የኅጢአት ሥርየት ለማግኘት መፈለግ የእውነተኛ ክርስቲያን መገለጫ ነው። በመሠረቱ በአዳማዊ ተፈጥሮ ሰው ሁኖ የተፈጠረ የሰው ልጅ ሁሉ ወዶ ጽድቅ መሥራትም ሆነ ወዶ ኅጢአት ለመሥራት የሚችልበት የተፈጥሮ ነፃነት ያለው ፍጡር ስለሆነ በለበሰው ደካማ ሥጋው ተሸንፎ ኅጢአት እንደሚሠራ ይታወቃል። ሰው ሁኖ ተፈጥሮ በሰውነቱ ፈፅሞ ኅጢአት አልሠራም ብሎ ማሰብም ሆነ መናገር እራስን ከማታለል አልፎ ስለሁላችንም መዳን በመስቀል ላይ የሞተልንን የኢየሱስ ክርስቶስ አባታዊ ፍቅሩንና ውለታውን እንደመካድ ይቆጠራል። ሁላችንም የሰው ልጆች እንደምንሞት ብናምንም እንኳ፤ ነገር ግን መቼ በሞት እንደምንጠራ ቀንና ሰዓቱን (ዘመንና ጊዜውን) ለይቶ ማወቅ ከእሱ ከባለቤቱ በስተቀር ፈጽሞ የሚያውቅ የለምና ኅጢአትን ለመናዘዝ ቅድሚያ መስጠትና በንስሐ ሕይወት ራስን አዘጋጅቶ መጠበቅና ንስሐ ለመግባት መዘጋጀት ከእውነተኛ ክርስቲያን የሚጠበቅ ታማኝነት ነው።
ኅጢአት ማለት የብዙ ጥፋቶች ወይም ስሕተቶች መጠሪያ ስም ነው ኅጢአት የሥጋ ሥራ ሁኖ ነፍስን ከፈጣሪ ጋር አጣልቶ ዘለዓለማዊና ሰማያዊ ሞትን የሚያስከትል ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም የኅጢአት ውጤት ሞት እንደሆነ ሲናገር “ኅጢአት ስታድግ ሞትን ትወልዳለች” (ያዕ1፥15) ካለ በኋላ “የኅጢአት ደመወዝ ሞት ነው” (ሮሜ 6፥23) በማለት ኅጢአት የሕሊናና የመንፈስ ሞት መሆኑን አረጋግጧል።
የሥጋና የመንፈስ (የነፍስ) ሥራዎች አብዛኛዎቹን ቅዱስ ጳውሎስ ወደገላትያ ሰዎች በላከው መልእክቱ በምዕ 5፥19-22 ላይ የሥጋ ሥራ እና የመንፈስ ፍሬዎች በማለት ዘርዝሯቸዋል።
የሰው ልጅ ኅጢአት ሰርቻለሁ እግዚአብሔርን በድያለሁ፣ ሰውንም አሳዝኛለሁ ብሎ ራሱን ካሳመነ በነፍሱ የኅጢአት ደዌ አድሮበታልና ንስሐ የመግባት ሕክምና ያስፈልገዋል ማለት ነው። “እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ “(ማቴ3፥8) ኅጢአት ሠርቶ የንስሐ ሕክምና ያላገኘ ሰው በነፍሱ ምውት ነው። ሉቃ 15፥24
ከዚህ የተነሣ ኅጢአት ለመናዘዝና ንስሐ ለመግባት ከሚፈልግ አንድ ክርስቲያን የሚጠበቀው ፡-
– በቅድሚያ ኅጢአት መሥራቱን አምኖ ለራሱ ሕሊና መናዘዝ (መፀፀት)።
– ስለሠራው ኅጢአት ወይም በደል እየተጸጸተ ጧት ማታ በደሉን በፀሎትና በልመና ለፈጣሪው መናዘዝና ኅጢአትን በእግዚአብሔር ፊት ማመን (መዝ50 ፣ ዳን9፥5፣ ነህ1፥6-7)
– ኅጢአትን (በደልን) ለካህን መናዘዝና ንስሐ መግባት። ካህኑ የእግዚአብሔር አገልጋይና እንደራሴ ስለሆነ የሠራነውን ኅጢአት ለካህኑ በመናዘዝ ንስሐ መግባት፤ ኅጢአታችን እንዲሠረይልን በእግዚአብሔር ፊት ንስሐ መግባትና መናዘዝ ማለት ነው። (ኢያሱ7፥19 ማቴ3፥6 ዘሌ5፥5-6 የሐዋ19፥18)
– የበደልናቸውንና የበደሉንን ሁሉ ይቅር በማለት የጥል ግድግዳ አፍርሰን በፍቅር አሸንፈን ስለዘለዓለማዊ ሕይወት ብለን በፍጹም ሕሊና በሰላም መኖር ነው።
– ተመልሶ በኅጢአት ላለመውደቅ አዘውትሮ የንስሐ አባትን ወይም የሚቀርቡትን የሃይማኖት መምህር ማማከር፣ ምክር ማግኘት በታቻለ መጠን መጸለይ፣ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድና ቃለ እግዚአብሔር መስማት፣ በቤትም ውስጥ ቢሆን መንፈሳዊ መዝሙርና ትምሕርት ማዳመጥ አስፈላጊ እንደሆነ የምናስገነዝበው ለጠየቁን ምዕመን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ክርስቲያን እንዲጠቅም ነው።
የንስሓ አባትን በሚመለከት ፦
ይመክረኛል ያስተምረኛል ያሉትን የንስሓ አባት የሚሆን ካህን በአካባቢዎ ካሉ ይያዙ፤ በአከባቢዎ ማግኘት የማይችሉ ከሆነ በራስዎትም ሆነ በሚያምኑት ሰው በኩል ያገኙዋቸውን እውነተኛ ካህን በርቀትም ቢሆን ይያዙ፤ ወይም ደግሞ እኛ በህይወታቸው ምሳሌ ይሆናሉ ብለን ከመረጥንልዎ በድረገፃችን ላይ ካሉ አባቶች ንስሓ አባት በማድረግ መያዝ ይችላሉ።
በተጨማሪም፤ ስለንስሓ ትምህርት በድረገፃችን ላይ የተላለፉና እየተላለፉ ያሉትን ተከታታይ ትምህርቶች ይህን ሊንክ በመጫን ያንብቡ።
ትምህርት ስለ ንስሓ – https://yohannesneseha.org/
የንስሓ አባት ገጽ – https://yohannesneseha.org/
መልስ፦ ንስሓ መቀበል ያለብን ስጋ ደሙን ስንቀበል ብቻ አይደለም። ስጋው ደሙ ለክርስቲያን ቋሚ የነፍስ ምግብ ስለሆነ ምግብ ደግሞ በየግዜው የሚያስፈልግና ከተቋረጠም በህይወታችን ሞትን የሚያመጣ ስለሆነ ማንም ክርስቲያን ከክርስቶስ ስጋና ደም እንዳይለይ በራሱ በባለቤቱ መለኮታዊ ቃል ሁላችን ታዘናል። ስለዚህ ክርስቲን ኀጢአትን እንደ ቋሚ ተግባር አስቦ በእቅድ የሚይዘው ፕሮግራም አይደለም። ሁሌ ክርስቲያን ከክፉ ነገርና ከኀጢአት ውረኝ ብሎ ነው መፀለይ ያለበት። በአጋጣሚ ግን በዚህ በለበስነው ደካማ ስጋችን የፈፀምነው በደል ካለ ቅዱስ ቁርባን ብንቀበልም ባንቀበልም ጀምበር ሳትጠልቅ እኛም የበደሉንን ይቅር ብለን የኛም ኀጢአት በእግዚአብሔር ዘንድ ይቅር እንዲባልልን በካህኑ አማካኝነት ንስሓ እንቀበላለን እንጂ ቅዱስ ቁርባን ካልተቀበልን የፈለግነውን በደልና ኀጢአት እየፈፀምን በደለኛና ኀጢአተኛ ሆነን በውንብድና እንድንኖር የእግዚአብሔር የአምላካችን ፈቃድ አይደለም። ስለዚህ ቅዱስ ቁርባን እና የንስሓ ህይወት ለህይወታችን ያስፈልጉናል ማለት ነው። ለሁሉም ነገር ከዚህ ቀደም ስለንስሓ ሰፊ ትምህርት እና ለጥያቄዎች መልስ ገለፃ ስለተሰጠበት እሱን ከድረገፃችን ላይ መልሰው እንዲመለከቱትና እንዲረዱት እንመክራለን።
ስለ ንስሐ እዚህ ያንብቡ: https://yohannesneseha.org/ስለ-
በሴቶች ልማድ ወይም የወር አበባ ለሴቶች የተፈጥሮ ፀጋ እንደሆነ እና የሰው ዘርን ለመተካትም ተፈጥሮአዊ ምክንያት ነው። በዘመነ ኦሪት በእናታችን ሄዋን በመጣብን እርግማን ምክንያት የመርገም ደም ተብሎ ስለሚታመን ሴቶች ሁሉ ሲነቀፉበት የነበረ የነውር ምልክት ነበር። በመጀመርያዋ ሄዋን የመጣው መርገም በዳግማዊት ሄዋን ቅድስት ድንግል ማርያም ስለጠፋልን ሴቶች ዛሬ የወር አበባ ወይም የሴቶች ልማድ በመጣባቸው ግዜ እንደ እርኩስ አይቆጠርባቸውም፤ ሆኖም ፈሳሹ እስከሚቆም ወይም ከደም እስከሚነጹ ድረስ ቢያንስ ለ 1 ሱባኤ እስከ 7 ቀን ድረስ ከመቁረብ፣ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከማስቀደስ፣ ፀበል ከመጠጣትም ሆነ ከመጠመቅ ይቆጠባሉ። ጠያቂያችን እንዳሉት ንስሓም አንዱ መንፈሳዊ የአገልግሎት ቀኖና ስለሆነ በዚህን ሰአት የተሰጣቸውን የንስሓ ቀኖና እንዲፈፅሙ አይደረግም። በአጋጣሚ ግን የንስሓ ቀኖና ከተሰጣቸው በኋላ ንስሓቸውን ሳይጨርሱ በሰይጣን ፈተና ባልተጠበቀ ቀን የሴቶች ልማድ ቢያጋጥማቸው፤ በዚህ ወቅት መቅረብ ስለማይቻል በቤት ውስጥ የሚፈፀም ንስሓ ከሆነ ካህኑን በማማከር ሰውነታችንን በመታጠብና ንፁህ ልብስ በመልበስ ሳናቋርጥ መቀጠል እንችላለን። በቤተክርስተያን ውስጥ ወይም ደግሞ ወደ ገዳም ሄደው የሚፈፀም ከሆነ በማስተዋልና በመንፈሳዊ ፅናት ሆነው ከደረሱበት አቋርጠውት ባሉበት ቦታ ሆነው መፆምና መስገድ ይችላሉ፤ በቀኖና ቤተክርስቲያን እንደተወሰነው በተወሰነ ርቀት ላይ ቆመው መንፈሳዊ ስርአቱን መከታተል ይችላሉ። ያጋጠማቸው የሴቶች ግዳጅ የተለመደው የጊዜ ገደብ ሲያልቅም ንስሓቸውን መቀጠል ይችላሉ። ስለሆነም ጠያቂያችን ሃሳቡን በዚህ እንዲረዱትና በተጨማሪም ከዚህ በፊት በተማሳሳይ ጥያቄ ላይ የላክነውን ምላሽ እንዲያነቡት ከዚህ በታች አያይዘን ልከንልዎታል።
መልስ፦ በአዲስ ኪዳን የሴቶች የወርሃዊ ግዳጅ ሲመጣ ወደ ቤተክርስቲያን ለመግባት ለራስዋም ሆነ ለተመልካች መሰናክል እንዳይሆን በሌላ መልኩ መስቀሉንም ሆነ ፀበሉን ለመጠቀም በረከት ለምናገኝበት ንዋየ ቅዱሳን ክብር ስለምንሰጥ እንጂ እንደ ኦሪቱ ስርዓቱ የወር ግዳጅ የመጣባት የተረገመች ነው ማለት እንዳልሆነ መረዳት ያስፈልጋል። ለምሳሌ የማይገባ ልብስ ለብሰን በሰው ፊት ለመቅረብ፣ ወይም በአካላችን የሚታይ ነውር ይዘን በሰው ፊት ለመቅረብ እንደምንሳቀቅ ሁሉ ከዚህም በላይ ንጽሐ ባሕሪይ ዘላለማዊ አምላክ በሆነው አምላክ ፊት ስንቀርብ ታላቅ አክብሮትና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያስፈልገናል። የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ተብሎ ተፅፏልና።
ስለዚህ ጠያቂያችን፤ የሴት ልማድ የመጣባት ሴት ከማንኛውም መንፈሳዊ አገልገሎት ግዳጅዋን እስትጨርስ መራቅ አለባት። ማለትም ሌላ አደጋ ወይም ችግር ካላጋጠማት በስተቀር የተለመደው የጊዜ ገደብ እስከሚያልቅ ድረስ ፀበል ከመጠጣትም ሆነ ከመጠመቅም ወይም መስቀል ከመባረክ ትቆጠባለች። ነገር ግን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ተለይቶ ለማያውቅ ሰው አንድ ቀንም ቢሆን የሰይጣን ውግያ እንዳይኖርበት ከቤተክርስቲያን ቅፅር ራቅ ብሎ መንፈሳዊ አገልግሎቱን ካህናት አባቶች ህዝቡን ሲባርኩና እግዚአብሔር ይፍታ ሲሉ ባሉበት ሁነው ይሁንልኝ ይደረግልኝ በማለት በረከቱን ማግኘት ይቻላል።
መልስ፦ ንስሓ ለመግባት የማንኛውም ክርስቲያን መንፈሳዊ ግዴታው ነው። በሰራነው ኀጢአት የሚሰጠንን ንስሓ በሌላ ነገር ለማተካካት አንችልም። እንደ ኀጢአታችን መጠን አባቶቻችን የንስሓ ሱባኤ ሲሰጡን ማድረግ ያለብንን ነገር በቀኖና ቤተክርስቲያን በተወሰነው መሰረት ስግደት መስገድ ካለብን እንሰግዳለን፣ መፆም ካለብን እንፆማለን፣ መጸለይ ካለብን እንጸልያለን፣ ሌላም ለንስሓ ቀኖና ከተሰጠን የተባልነውን እንፈፅማለን ማለት ነው። በእርግጥ በህመም ያሉ በእርጅና ያሉ በእርግዝና ወይም በወሊድ ያሉ በጦር ሜዳ ያሉ ንስሓውን ለመፈፀም በማያመች አስቸጋሪ ቦታ ያሉ ከሆነ ችግራቸውን ለንስሓ አባታቸው በግልፅ በማስረዳት ከችግራቸው አንፃር እየታየ እንደሁኔታው ለንስሓ ቀኖና እንዲሰጣቸው ይደረጋል። ጠያቂያችን የንስሓ አፈፃፀምን በዚህ አኳያ እንዲያዩት ያስፈልጋል በማለት ይህን አጭር መልዕክት ልከንልዎታል። ከዚህ ቀደምም ስለ ንስሓ የሰጠናቸውን ሰፊ ትምህርትና መልዕክቶች እንዲያነቡት በማለት እንመክራለን።
ትምህርት ስለ ንስሐ፦ https://yohannesneseha.org/ስለ-
መልስ፦ ጠያቂያችን ያቀረቡልን ጥያቄ በንስሓ ሱባኤ ላይ እያሉ ያጋጠመዎትን ፈተና ወይም መሰናክል በእርስዎ ታስቦ የተደረገ ካለመሆኑም በላይ ስላጋጠመዎት መሰናክልም በቅዠት መልክ አካል ያለው ሰው መሰል እርኩስ መንፈስ ጾታዊ ግንኙነት እንዳደረጉ በማስመሰል የጀመሩትን መንፈሳዊ አላማ ለማሰናከል ያደረገው እኩይ ተግባር በመሆኑ የጀመሩትን የንስሓ ሱባኤ እንዲያቋርጡ የሚያደርግ ጥፋት አይደለም። ይልቁንም ከተቀበሉት የንስሓ ቀኖና ፍጹም የሆነ የነፍስ ድህነት እንዳገኙና ከሰይጣን ወጥመድ እንዳመለጡ ያረጋገጠው የሰው ልጅ ሁሉ ጥንተ ጠላት የሆነው ዲያብሎስ የዘወትር ቋሚ ተግባሩ በሰው ልጅ መንፈሳዊ ጉዞ የመሰናክል ወይም የፈተና ድንጋይን ማስቀመጥ ስለሆነ በዚህ ረቂቅ የጥፋት ስራው የያዙትን የተቀደሰ አላማ ያሰናከለ ቢመስለውም በያዙት የንስሓ ጉዞ ያሸነፉት ስለሆነ በህልም ያዩት የሰይጣን መንፈስ ስለሆነ የጀመሩትን አላማ ማቋረጥ የለብዎትም። ስላዩትም የህልመ ለሊት ፈተና መፀለይና ለመምህረ ንስሓዎ ያጋጠመዎትን እንቅፋት በማስረዳት በፀሎት እንዲያስቦት ማድረግ እንጂ ከዚህ ያለፈ ሌላ የእርስዎን የተቀደሰ ተግባር የሚያሰናክል አንዳችም ነገር እንደሌለ ህሊናዎትን ንፁህ ያደርጉ ዘንድ ይህን አጭር መልዕክት ልከንልዎታል።
መልስ፦ ጠያቂያችን ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በሃይማኖቱ እና በምግባሩ ፅንቶ በትክክለኛው ክርስቲያናዊ ስነምግባር ተወስኖ የሚኖር ከሆነ እንደተባለውም በደረሰበት ስፍራ ሁሉ እውነተኛ የቤተክርስቲያን አባቶችን አነጋግሮ የፈፀመውን ኀጢአት ሳይሰውር በመናዘዝ ንስሓ መግባት ይችላል። ምክንያቱም፤ የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጪው እንዲሉ ዋናው አላማ የተፈፀመውን በደልና ኀጢአት በንስሓ ለማስፋቅ በፍጹም ልባዊ እምነት በካህኑ አማካኝነት የተቀበልነውን የንስሃ ህይወት የኀጢያት ስርየት እንደሚያስገኝልን ማመን ብቻ ስለሆነ ነው። በእርግጥም በሰራነው ኀጢአት አፍረን እና ተሸማቀን ክብራችን እንዳይነካ ለመሰወር እና ጥፋታችንን ለመደበቅ የምናደርገው ስጋዊ አስተሳሰብ ካለ ሰውን ብናሞኝ እግዚአብሔርን ማታለል ስለማንችል የዚህ አይነት አካሄድ ከእውነተኛ ክርስቲያን የማይጠበቅ ተግባር ነው። በደረስንበት መንፈሳዊ ቦታ ሁሉ እውነተኛ የቤተክርስቲያን አባቶችን በማነጋገር የዋለው ኀጢአታችን እንዳያድርብን ያደረውም እንዳይውልብን በጊዜውም ያለጊዜውም በአባቶች ጥበቃ የንስሓ ህይወት መኖር ከሁሉም ክርስቲያን ይጠበቃል። ለጠያቂያችንም ሆነ ለሌላው ሁሉ ምክር የምንሰጠው ምናልባት የሰራነውን ኀጢአት ሁሉ ለመደበኛ የንስሓ አባታችን ለመናዘዝ የምናፍርበት ወይም ካህኑንም የምንጠራጠራቸው ነገር ካለ ስርአታዊ መንገድ ተጠቅመን በመንፈሳዊ ጥበብና በትህትና ሁነን ተሰናብተን ፤ ሳንጠራጠር ከልብ የምናምናቸውን ሌላ አባት መርጠን መያዝ ይገባናል። ይህን የምንልበት ምክንያት ብዙዎቹ ምእመናን ለንስሓ አባቶቻቸው ግልፅ ሆነው የሰሩትን በደል ለመንገር የማይችሉበት ዋናው ምክንያት ምስጢር ይባክንብናል ብለው ከነኀጢአታቸው የሚኖሩ አሉና፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ለአባቶቻቸው ግልፅ ለመሆን በአካባቢያቸው በማህበራዊ ህይወት ከመንፈሳዊ አባቶቻቸው ጋር አብረው ስለሚኖሩ የመተፋፈርም ነገር ስለሚያጋጥማቸው በዚህም ምክንያት የሚሳቀቁ ምእመናን እንዳሉ መረጃው ስላለን፤ ከዚህ ሁሉ ስጋት ነፃ ለመሆን የሚያምኑበትን እና የማይጠራጠሩበትን አባት መያዝ እንደሚገባቸው በአፅንዎት እንመክራለን። ለዘላለማዊ የነፍስ ድህነት ጉዳይ የምንሰራውና የምናደርገው ተጋድሎ በስጋዊ አመለካከት ወይም ምድራዊ በሆነ አሰራር የምንኖረው ሂደት ስላልሆነ ልዩ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። በመጨረሻም ጠያቂያችን በተመሳሳይ ጥያቄ ከዚህ በፊት የላክነውን አጭር ምላሽ እና ስለንስሃ አስመልክቶ የፃፍናቸውን መልዕክቶች ተመልሰው እንዲያነቧቸው ከዚህ በታች ሊንኩን ልከንልዎታል።
ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ተጠይቆ የነበረው ጥያቄ፦ ንስሐ አባት እያለን ሌላ ቤተክርስትያን ብንሄድ በድንገት የምናስታውሰው ሀጥያት ቢኖር እዛው ላገኘናቸው አባት ሐጥያታችንን ብንናዘዝ ችግር ይኖረዋል???
የተላከው መልስ ፦ ማንም ክርስቲያን ባለበት ደብር ወይም አካባቢ ንስሓ አባት እያለው፤ ለሌላ መንፈሳዊ አገልግሎት ወይም ደግሞ ወደ ገዳማት እና ቅዱሳት መካናት ወይም ቦታዎች ሄዶ በዛ ቦታ ላገኛቸው አባት፥ አለኝ የሚለውን አነጋግሮ ወይም ኅጢአቱን ተናዞ አስፈላጊውን የንስሓ ህይወት መቀበል ይችላል። የአባቶቻችን ፀጋ የአንዱ ፀጋ ከሌላው ፀጋ ይለያልና ሁሉም አባቶች ባላቸው ፀጋ በረከት ቢያድሉን ፀጋችንን ያበዛዋል እንጂ ነውር አይደለም።
መልስ፦ጠያቂያችን ለመግለጽ የፈለጉትን ነገር በግልፅ ተረድተነው ከሆነ ንስሓ የጊዜ ገደብ አለው ወይ፤ ወይም ለተመሳሳይ ኀጢአት ድጋሚ ንስሓ መግባት ይቻላል ወይ ከሆነበተመሳሳይ ጥያቄ ከዚህ በፊት የላክነውን 2 አጫጭር ምላሾች እና ስለንስሃ አስመልክቶ የፃፍናቸውን ሌሐሎች መልዕክቶች ተመልሰው እንዲያነቧቸው ከዚህ በታች ልከንልዎታልና አንብበው ይረዱት።
ጥያቄ፦ንስሓ በገባሁበት ጊዜ ያልተናገርኩት ኀጢአት አለ፤ ይህን ኀጢአት መናገር የለብኝም ወይ? ላሉን ጠያቂያችን የተሰጠ ምላሽ፡
መልስ፦በመሰረቱ ቀኖና ወይም ንስሐ የሚሰጠን በፈጸምነው ኅጥያት መጠን ተለክቶ ስለሆነ እያንዳንዱ ያጠፋነውን ጥፋት ከባድም ቢሆን ሳንፈራ፤ ቀላልም ቢሆን ሳንንቅ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ለነፍሳችን እረኛ ላደረግነው ካህን መናገር እንዳለብን የቤተክርስቲያን ቀኖና ያዛል። የኅጥያት ደረጃችን ተለይቶ ሲታወቅ ንስሐ የሚሰጡን አባቶችም በጥፋታችን መጠን ስለሆነ ንስሓ ላልገቡበት ኅጥያት እንደገና መናገርና ቀኖና መቀበል ያስፈልጎታል።
ጥያቄ፦አንድ ሰው ንስሓ ገብቶ ቀኖና ተሰጥቶት እያለ በዚህ መሀል ግን በደል ስራ፤ በዚህ ሰአት ይህ ሰው ምን ቢያደርግ ይሻላል?
መልስ፦ አንድ ክርስቲያን የተፈፀመውን በደል በራሱ ግዜ አምኖ ተፀፅቶ ንስሓ ገብቶ በቀኖና ላይ እያለ ይባስ ብሎ የተሰጠውንም ቀኖና ሳይፈፅም ወደፊት ኅጢአት ላለመስራት በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን ከገባ በኋላ ሌላ በደል ከፈፀመ ሰውነቱን የተቆራኘው የኀጢአት ደዌ ብሶበታል ማለት ነው። እጅግ ህይወቱ አሳዛኝ ቢሆንም ስለአድን ሰው መጥፋት ቤተክርስቲያን ዝም ስለማትል ተስፋ ሳይቆረጥ ይሄን ሰው በተለያየ መንገድ የንስሓ አባቱ ወይም ሌላም አባት በቅርብ ውስጣዊ ችግሩን ተረድተው እና መርምረው አሁንም ወደ ንስሓ ህይወት እንዲቀርብ እና በተደጋጋሚ ከተፈተነበት የኀጢአት መዘዝ ውስጥ እንዲወጣ ማድረግ የግድ አስፈላጊ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል እንደተናገረን ሐዋሪያው ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን አቤቱ ወንድሜ ምን ያህል ቢበድለኝ ምን ያህል ይቅር ልበለው እስከ 7 ጊዜ ነውን ብሎ በጠየቀው ጊዜ እስከ 7 አልልህም 7ቱን አንድ እያልክ እስከ 70 ነው እንጂ” በማለት ለኅጢአት ይቅርታ የጊዜ እና የቁጥር ገደብ እንደሌለው አረጋግጦልናል። (ማቴ 18፥21-22)
ስለዚህ በዚህ መሠረት ከኅጢያት ደዌ እስካልተፈወሱ ድረስ የንስሓ ህይወት አይቋረጥም ይቀጥላል እንጂ።
ስለ ንስሓ ጥያቄና መልስ፦https://yohannesneseha.
መልስ፦ በጠያቂዎችን ለቀረበው ጥያቄ የምንሰጠው መልስ ለሁሉም አባላቶቻችን መሰረታዊ ግንዛቤ ማስያዝን በማሰብ ስለሆነ ሁላችሁም ትረዱት ዘንድ አደራ እያልን ከዚህ በፊትም ስለ ስግደት መልስ የሰጠን መሆኑን ብናስታውስም አሁንም ጠያቂያችን ያቀረቡት ለበጐ ስለሆነ ወይም የማያውቁትን ለመረዳት ነውና የንስኀ ስግደትም ሆነ ማንኛውም የስግደት አይነት ስንሰግድ በመንፈሳዊ ህይወታችን ዋጋ ከምናገኝበት እና አጋንንትን ከምንቃወምበት አንዱ ትልቁ ሃይላችን ከስግደት በፊት ፊታችንን በትምዕርት መስቀል በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በማማተብ የዘወትር ፀሎት ከሚለው ጀምረን ከፀለይን በኋላ በአቡነ ዘበሰማያት አሳርገን ስግደቱን እንጀምራለን፤ ስንጨርስም በአቡነ ዘበሰማያት ከደመደምን በኋላ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ ፣በእንተ አግዚትነ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ 12 ጊዜ እንፀልያለን:: በየጊዜው በምንሰግድበት ጊዜ ከቤተክርስቲያን ውጭ ከሆነ የምንሰግደው ስንሰግድ በፊታችን የጌታና የቅዱሳን ስእል ወይም መስቀል ወይም ቅዱስ ወንጌል ሊኖር ይገባል። በዋናነት ግን የቀኖና ንስኀ የምንቀበለው ከአባቶች ስለሆነ በአንቀፀ ንስኀ በተደነገገው መሰረት ስንሰግድ ምን ማለት እንዳለብን፣ እንዴት መፀለይ እንዳለብን እና ምን መፀለይ እንዳለብን፣ ምክር እና መመርያ ስለሚሰጡን ብዙ የሚያስጨንቅ አይደለም :: የበደልነውን ኀጥያት በልባችን እያሰብን እና እየተፀፀትን ልንሰግድም እንችለን። ለምሳሌ ስለ ፀሎት እውቀት የሌለው ሰው በፍፁም ሃይማኖት እና በቅን ልቦና ሆኖ ቢሰግድ ለማን እንደሚሰግድ ከምንም በላይ እግዚአብሔር የውስጣችንን ስለሚያውቀው ስግደቱ ተቀባይነት እንዳለው ማመን አለብን። አንዳንድ አባላቶቻችን ከቤተክርስቲያን ወይም ከአንዳንድ አባቶች ያገኙትን መንፈሳዊ እውቀት ማካፈል ተገቢ ቢሆንም መሰረታዊ እውቀት የሌላቸው አንዳንድ አስተማሪ ነን የሚሉ ሰዎች በልብ ወለድ እና በፈጠራ የፃፉትን እንደ ቤተክርስቲያን እውቀት አድርጐ ማስተላለፍ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን ሁላችሁም የዚህ ድረ ገፅ ተከታታዮች ከወዲሁ በማስተዋልና በጥንቃቄ እንድትማማሩ አደራ እንላለን።
መልስ፦ https://yohannesneseha.