ንስሐ አባት በርቀት መያዝ ይቻላል ወይ? ንስሐስ በስልክ ይሆናል ወይ?
ይህን በሚመለከትም ከዚህ በፊት ስለ ንስሐ አባት አያያዝ ጥያቄ ቀርቦ በአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት እና በቤተክርስትያን መምህራን ንስሐ አባት በርቀት መያዝ እንደሚቻል በተደጋጋሚ ምላሽ የተሰጠበት ሃሳብ ስለሆነ ፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት እንዲያሥሩና እንዲፈቱ የሰጣቸው ስልጣነ ክህነት ጊዜና የቦታ ርቀት የማይወስነው ስለሆነ ፤ በአካባቢው አባት የሚሆን ካህን ከጠፋ ያለጠባቂ ብንኖር ጠላታችን ዲያብሎስ ነፍሳችንን እንዳይነጥቃት የንስሐ አባት በርቀት መያዝ ይችላሉ። በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ላይ ምእመናን መጨናነቅ እንደማያስፈልጋችሁ መንፈሳዊ ምክራችንን እየለገስን ከላይ በተጠቀሰው ስልክ ቁጥር ደውለዉ የንስሐ አባትን አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።