ስለ ትዳር የጥያቄና መልስ

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!" (ማቴ 3: 1-2)

ተከታታይ ትምህርትና ለጥያቄዎት ምላሽ ለማግኘት ቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

ስለ ትዳር  

ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች​

በማንኛውም ግዜ የፆም የፀሎት ሱባኤ በራሳችንም ይሁን በአባቶቻችን ቀኖና ተሰጥቶን የፆምና የፀሎት ሱባኤ በያዝን ግዜ፣ በእለተ ሰንበት እና በታወቁ በአላት ቀን ፈፅሞ ሚስትም ከባልዋ ተለይታ ወንድም ከሚስቱ ተለይቶ መኝታቸውንም የተለየ አድርገው የሚበላውንም የሚጠጣውንም ከተለመደው የአመጋገባቸው ስርአት ቀንሰው አጠቃላይ ፈቃደስጋቸውን ተቆጣጥረው ነው መፆም የሚገባቸው። ፆም ራሱን የቻለ ከእግዚአብዜር ጋር የምንገናኝበት የፅድቅ መንገድ ስለሆነ በዚህን ግዜ ማንኛውም ክርስቲያን የስጋ ፈቃዱን መቆጣጠር እንዳለበት የቤተክርስቲያን ቀኖና ይደነግጋል። ይህን ስንል በቀኖና የተደነገጉ 7ቱ አፅዋማትና እንደገናም በአባቶቻችን ሱባኤ ተሰጥቶን የምንፆምባቸው አፅዋማትን ይመለከታል። ይሁን እንጂ ከአቅም በላይ በሆነ ፈተና ፈቃደስጋችን አሸንፎን በዚህ ምኞት ከወደቅን ላጠፋነው ጥፋት የህሊና ፀፀት ተፀፅተን ለንስሐ አባታችን ወደፊት የምንነግረው ሁኖ ፆምና ፀሎትን ሳናቋርጥ እስከመጨረሻው ልንፈፅም ይገባናል በማለት ለጠያቂያችን ይሄ ምክር እንዲደርስዎ አድርገናል።

በመሰረቱ ራሳችን የፈፀምነውና የበደልነው ከቅዱስ ቁርባን ሊለየን የሚችል ኅጥያት ከሌለብን በስተቀር ከቅዱስ ቁርባን መለየት እንደሌለብን ቅዱሳት መጽሐፍት ያስተምራሉ። በዚህ መሠረት ምናልባት ከባለቤትዎ ጋር የተለያዩበት ምክንያት ለመለያየት የሚያበቃ ከባድ ጉዳይ መሆኑን ባናውቅም ነገር ግን በአባቶች አስመክረው በሽማግሌዎች መክረው ለመመለስ ፈቃደኛ ካልሆኑ ከንስሐ አባትዎ ጋር በየግዜው እየተነጋገሩ ቅዱስ ቁርባን የመቀበል ስርአቱን መቀጠል አለብዎት። ከቅዱስ ቁርባን የሚከለክልዎ አንዳችም ነገር የለም። ወደፊት ባለቤትዎ በእግዜአብሔር ፈቃድ ተመልሰው አብረው ለመኖር ፈቃደኛ ከሆኑ ራሳቸውን በንስሓ አባታችሁ በማስመርመር አብሮ መኖር ይቻላል። በውስጣችሁ ያለውን ችግር ግን ለመፍታት እኛም እንድንረዳዎት በውስጥ መስመር ሊያገኙን ይችላሉ።

በስርዓተ ቁርባን ተወስነው የሚኖሩ ባል እና ሚስት እግዚአብሔር ሳይፈቅድላቸው በሞት ወይም ደግሞ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ቢለያዩ፤ ቢቻል የመጀመርያው አማራጭ፦ ስጋቸውን ከኀጥያት ወይም ከዝሙት ጠንቅ የሚያሸንፉ ከሆነ በመጀመርያው አላማቸው ጸንተው ለመቀጠል እንደሚችሉ የቤተክርስቲያን ቀኖና ያዛል። የውስጥ ኑሯቸውን ግን በሞግዚት ወይም ሰራተኛ በመቅጠር ሊሸፈን ይችላል። ሁለተኛው አማራጭ፦ ስጋውን መግዛትና ማሸነፍ የማይችል ሰው በዝሙት ጠንቅ ተፈትኖ ከፈጣሪው ጋር ከሚጣላ በሃይማኖትና በስነ ምግባር የምትመስለውን/የሚመስላትን በነበረበት/በነበረችበት አላማ ማለትም በቅዱስ ቁርባን ተወስኖ/ተወስና አግብቶ/አግብታ መኖር ይችላል/ትችላለች። ማስረጃ፦ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ አገር ለሚኖሩ ክርስቲያኖች “ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ፦ እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው። ነገር ግን፤ በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና፥ ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ” (1ኛ ቆሮ 7፥8-9) በማለት በዝሙት መንፈስ እየተቃጠሉ ነፍሳቸውን ከሚወጉና ከፈጣሪያቸው ጋር የሚያጣላቸውን ስራ ከሚሰሩ ስርዓተ ቤተክርስቲያንን በጠበቀ መልኩ በኑሮ ወይም ደግሞ በአላማ የምትመስለውን/የሚመስላትን አግብቶ/አግብታ እንዲኖሩ እንደመከራቸው እንመለከታለን።

በዚሁ መሠረት ጠያቂያችን ቤተሰብ ሊኖሮት ቢችልም ባይችልም፣ በእድሜ ደረጃ ወጣትና መካከለኛ እድሜ ቢሆኑም ባይሆኑም ከፈጣሪ ቀጥሎ እራሶትን ያውቃሉና በክርስቲያናዊ ስነምግባር ለመኖር ለመረዳት መጠየቅዎ እጅግ የሚያስደንቅዎ እና የሚያስመሰግንዎ ስለሆነ ወደፊትም እግዚአብሔር ከፈተና እንዲጠብቅዎ መልካም ምኞታችንን እየገለጽን በመረጡት ክርስቲያናዊ ህይወት አብራዎት የምትቀጥለውን መርጠው በማግባት በቅዱስ ቁርባን ተወስነው መኖር ይችላሉ።

በራሳቸው የዝሙት ሃሳብ የፈፀሙ በሌላ በኩል አካላዊ ድንግልናቸውን ያላጡ ወይም የግብረስጋ ስጋ ግንኙነት ያላደረጉ ተክሊል ይገባቸዋል ወይ ተብሎ ስለተጠየቀ በሚመለከት የተሰጠ ምላሽ።

ከሁሉ በፊት መታወቅ ያለበት ከራሳቸው ጋር የዝሙት ሃሳብ ለመፈፀም ተነሳስተው በሃሳብና በምኞት ራሳቸውን በሰይጣናዊ ስራ ተገዚነት የሚያደርጉ ሰወች አካላዊ የዝሙት ግብረ ስጋ ከሚፈፅሙት ሰወች የበለጠ ሃጥያት ነው። እንዲያውም ከሰዶማዊነት መንፈስ ጋር ይያያዛል። ይህ ማለት 21ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ሰይጣን በግልፅ የሰለጠነበት የመጨረሻው ዘመን ስለሆነ ከትንሽ እስከ ትልቅ፣ አዋቂነን እሚሉ ሳይቀሩ አብዛኛው ሰው ለማለት ይቻላል በዚህ ኀጥያት እየወደቁ መሆኑን ብዙ የመረጃ ምንጮች ያመለክታሉ። ይሁን እንጂ እንደ ቅዱስ መጽሐፍት አስተምሮ ከስነ-ተፈጥሮ ሕግ ውጪ የሆነ ድርጊት ስለሆነ በዚህ ክፉ ተግባር እያወቁ የወደቁ ሰወች ቢኖሩ ንስሃ ገብተው መንግስተ ሰማይ መውረስ ይችላሉ እንጂ በስርአተ ተክሊል ጋብቻ መፈፀም ግን አይችሉም። 

ነገር ግን በልጅነት እድሜ ሳያውቁ እና ምንም አይነት ሃይማኖታዊ ግንዛቤ ወይም መንፈሳዊ እውቀት ሳይኖራቸውና ተፈጥሮአዊ ነውር መሆኑንም ሳይገነዘቡ የፈፀሙት ከሆነ የቅርብ የነፍስ ሀኪማቸው በሆነ የነፍስ አባታቸው የቀኖና ንስሐ ተሰጥቷቸው ንስሃቸውን ሲጨርሱ በስርአተ ተክሊል ጋብቻ መፈፀም ይችላሉ። በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት የጥፋተኛው ሰው የግንዛቤ ደረጃ እና የጥፋቱ መጠን ነው።

ውድ የዮሐንስ ንስኀ ድረገፅ መንፈሳዊ ፕሮግራም አባላቶቻችን፤ ስለ ዝሙት ንስኅ መግባት አስፈላጊ መሆኑን አንድ አባላችን ከዚህ በታች ባቀረቡልን ጥያቄ መነሻነት የቀረበ አጭር ትምህርት ስለሆነ ሁላችሁም እንድትከታተሉት በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን።

ጥያቄው፦ (1) ንሰሐ ሰንገባ ማለትም የሰራነውን ስራ ለካህኑ ስንናዘዝ፤ አሁን ለምሳሌ ከብዙ ስዉ ዝሙት ከፈጸምን ከብዙ ስዉ ከሰረቅን ምን ብለንነው የምንናዘዘው? ዝሙት ፈፀሜያለሁ፡አመንዝሬአለው፡ብለን ነው? ወይስ? ቢብራራልኝ።

(2) ንስኀ አባት አለኝ ግን ንስኀ ለመግባት በጣም እፈራለው የንስሓ አባቴን መንገድ ላይ ሳያቸው በጣም እፈራለው ፤ምንላድረግ? ደግምም፡ንስኀ መግባት እፈልጋለው።

መልስ ፦

ንስሓ አባት የነፍስ ሃኪም ነው፥ ስለሆነም አንድ ምእመን ድካመ ስጋ ቢያገኘው የሰራውን ኀጢአት በጥቅሉ ሳይሆን በዝርዝር ማስረዳት አለበት። በቀላሉ ዝሙት ሰርቻለው ብሎ የሚተወው አይደለም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያለውን በዝርዝር ማስረዳት አለበት፤ ካህኑም ወይም የንስሓ አባቱም በዝርዝር መጠየቅ አለበት። ምክንያቱም በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ለእያንዳንዱ ጥፋታችንና በደላችን ወደ መምሕረ ንስኀችን ቀርበን ኀጥያታችንን ስንናዘዝ ባጠፋነው ደረጃ ንስኀ መቀበል እንዳለብን በቀኖና ቤተክርስቲያን ተደንግጓልና።
ንስኀ የማንኛውንም ምእመን ቁስለ ነፍስ የሚፈውስ መንፈሳዊ መድኃኒት ነው። ካህንም ረቂቋን ነፍስ የሚያድን ሃኪም ነው። አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ያለ ንስሐ አባት አንድ ቀንም መኖር የለበትም።
ንስኀን ስናስብ ሁል ጊዜ ኀጢአታችንን ማሰባችን አይቀርም ። ምክንያቱም አንድ ሰው የሰራው ኀጢአት በእግዚአብሔር፣ በሌሎች ሰዎች፣ በራሱ ወይም በቤተክርስቲያን ላይ የተፈፀመ ጥፋት ነውና። ኀጢአት ባይኖር ንስሃ ባላስፈለገ ነበር ኀጢአቱንም በምንናስብበት ጊዜ ደግም ምንጩን፣ መነሻውንና የሚያባብሱትን ነገሮች መመርመራችን የግድ ነው፤ ይህም መንፈሳዊ ህይወታችንን በመፈተሽ እንድናሳድግ ይረዳናል። ወደፊትም ቀድመን ለመጠንቀቅ ማለትም አርቆ ለማጠር ይጠቅመናልና ለመናዘዝ ወደንስኀ አባታችን ስንቀርብ የሰራነውን ኀጢአት ወይም በህሊናችን ያለውን ጥፋት በዝርዝር ማስረዳት አለብን ማለት ነው። ከዚህ በተጨማሪም ወደዚህ ኀጢአት እንዳንመለስ የንስሓ አባታችን ትኩረት ሰጥቶ ሊያስተምረን ይገባል። እኛም በምክረ ካህን ዘመናችንን ሁሉ መኖር አለብን። “የካህኑን ምክሩንና ተግሳፁን አንሰቀቅ፤ ነፍስን የሚያድን ባለመድኃኒት ነውና” (ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ)
ስለዚህ ጠያቂያችን ማንኛውም ክርሰቲያን የፈፀመውን በደል ከእግዚአብሔር ቀጥሎ በሚስጥር ለንስሐ አባቱ መናገር አለበት፤ የሚሰጠውም ንሰሐ በጥፋቱ መጠን የሚቀበለው መሆን ይገባዋል። ለንሰሐ አባቶቻችን የምንደብቀው ወይም የምናስቀረው የኀጢአት ሚስጥርም የለንም። እንደምሳሌ ወደ ሀኪም ቤት የሚሄድ ታማሚ ወይም ታካሚ የህመሙ አይነትና መጠን ተለይቶ በሀኪም ዘንድ ሳይረጋገጥ መድሀኒት አይታዘዝለትምና።
 
ዝሙት ምንድነው?
 

በመፅሐፍ ቅዱስ አስተምሮ ዝሙት ብዙ የኅጢአት አይነቶችን ያካትታል።

1/ ዝሙት ማለት ከህጋዊ ጋብቻ ውጭ የሚደረግ ማንኛውም አይነት የሥጋ ግንኙነት እና ሴሰኝነት ወይም አመንዝራነት ዝሙት ይባላል።

2/ ከእግዚአብሔር ያልተሰጠ እና ያልተፈቀደ ስልጣንን ወይም ሹመትን ሥጋዊ ክብርን አብዝቶ መፈለግና መመኘትም ዝሙት ይባላል።

3/ የወንድሙን ሀብት ወይም የሌላውን ሰው ማንኛውም ነገር አጥብቆ መፈለግም ዝሙት ይባላል።

4/ በአምልኮ ባእድ ወይም በአምልኮ ጣኦት ማመን ዝሙት ይባላል።

5/ ከአንዱ ወደ አንዱ ሃይማኖት እያሉ ሃይማኖት መቀያየርም ዝሙት ነው።

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የዚህ መንፈሳዊ ፖሮግራም ተከታታዮቻችን አሁን በዚህኛው ትምህርታችን የምናስረዳችሁ ስለ ግብረስጋ ዝሙት በተመለከተ ይሆናል።

በ1ኛ ተራ ቁጥር እንደገለፅነው አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ወይም አንዲት ሴት ከሌላ ሰው ባል ጋር ወይም በህጋዊ ጋብቻ ጓደኛው ወይም ጓደኛዋ ካልሆነ ወንድ እና ካልሆነች ሴት ጋር የግብረ ስጋ ተራክቦ በማድረግም ሆነ በዝሙት ሃሳብ እየተቃጠሉ መኖር ዝሙተኝነትና አመንዝራነት ይባላል። ይህንን የዝሙት ስራ የሚሰሩ ሰዎች በስጋቸው ላይ የነገሰውን የዝሙት መንፈስ ያመጣባቸው ወይም ለዝሙቱ ሃሳብ መነሻ የሆናቸው ለሰው ልጅ ውድቀት ዘወትር በጥፋት መንገድ የቆመው ሰይጣን የሚያመጣው ጠንቅና መዘዝ ነው። የዝሙት ስራ በዚህ ደካማ ስጋችን የነገሰ ቢሆንም እንኳን ለነፍስ ብቻ ሳይሆን ለሥጋ ጤንነትም እንደማይጠቅም በዘመኑ በአለም አቀፍ ከዝሙት ጋር ተያይዞ የሚመጣ ደዌም ወይም ወረርሽኝ በሰው ልጅን ሁሉ በጅምላ ሲገልና ሲጨፈጭፍ ተመልክተናል። ስለዚህ ዝሙት ነፍስንም ስጋንም የሚገል መሆኑን ከኛ በላይ ሌላ ማስረጃ አያስፈልገንም። እንግዲህ ዝሙት ወይም አመንዝራነት በቃላት ስንገልፀው የሚያሳፍር በተግባር ግን ሁሉ ሰው የሚፈልገውና በተግባር የሚያውለው የሁሉ ሰው ፈተና ነው። ይህ ሲባል አንዳችን ፃድቅ ወይም ከደሙ ንፁህ ሆነን ሌላው ደግሞ በዝሙት ኅጢአት ተጠያቂ በማድረግ  ሌሎቹን በመተቸት እጃችንን የምንቀስርበት መንገድ አይደለም። የዝሙት ስራ በሰው ስነልቦና ውስጥ የሚያደርሰው ፈተና እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ በሥጋ ያቃታቸው እንኳን በልባቸው ይመኙታል ባፋቸው ያወሩታል። ስለዚህ የዝሙት የመነሻው ምንጩ ሃሳብ ነው። ከሃሰብ ሲወጣ በአንደበት ይነገራል፣ ከአንደበት የተነገረው ደግሞ ጊዜ ሲገጥም በተግባር ይውላል። ስለዚህ የመጀመሪያው የዝሙት ድርጊት ፅንሱ ማሰብ ነው። ብዙዎቻችን በሃሳብና በአፍ በዝሙት ጉዳይ ላይ አብዝቶ የማይነጋገርና በሃሳቡ የማይቃጠል የለም ማለት ይቻላል። 

እንግዲህ እንደ ቅዱስ መፅሐፍ የዝሙትን ዓይነት መመልከት ስለሚያስፈልግና ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል “በዚህም በዘማዊና በኅጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላዕክት ጋር በመጣ ጊዜ በርሱ ያፍርበታል” (ማር 8፥37) በማለት የዝሙትን የኅጢአት ምክንያት ከአምልኮ ባዕድ ጋር በማያያዝ ተናግሮናል።

እንዲሁም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ  “ወይስ አመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግስት እንዳይወርሱ አታውቁምን፥ አትሳቱ ሴሰኛዎች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝራዎች ወይም ቀራጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሰሩ ወይም ሌባዎች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርሱም። ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደዚህ ነበራችሁ ነገር ግን በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፤ ታድሳችኋል ፀድቃችኋል” በማለት የዝሙትን አይነት እና ዝሙት ከፍተኛ ኅጢአት መሆኑን ከዘረዘረ በኋላ እግዚአብሔርን በመፍራት ወደ ንስኅ ስንመለስ እንዴት ከኅጢአታችን እድፍ እንደምንታጠብና እንደምንቀደስ እንደምንፀድቅም አስተምሮናል። (ቀኛ ቆረ 6፥9፤10)

እንግዲህ ጠያቂችን ወዳቀረቡልን ጥያቄ ስንመለስ ዝሙት በስሙ ዝሙት ቢባልም በስራው ወይም በኅጢአት ሲገለፅ እጅግ ከፍተኛ የኅጢአት አይነት ከመሆኑም ሌላ የኅጢአቱም ብዛትና ደረጃም ይለያያል ምክንያቱም ከአንድ ሰው ጋር መዘሞትና ከብዙ ሰው ጋር መዘሞት ኅጢአትነቱ ልዩነት አለው። ስለዚህ ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርነው ኅጢአቱን ለማድረግ ካላፈርነው ከብዙ ሰዎች ጋር የዝሙት ኅጢአት ፈፅሜያለሁ ብለን ለካህኑ ለመናገር የሚያሳፍረን ነገር የለም።  ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ለምናምነው ለንስኀ አባታችን የሰራነውን የዝሙት አይነት ዘርዝረን መናገር አስፈላጊ ነው፤ ይህም ለሰራነው ለእያንዳንዳንዱ የዝሙት ኅጢአት መጠን በአንቀፀ ንስኅ የሚሰጠን ቀኖና ስላለ ነው።

ስለዚህ አንዳንዶቻችን ለራሳችን ደህንነትም ሆነ ለማህበራዊ ግንኙነታችን ችግር የሚያመጣብን ቢሆን እንኳን እጅግ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድና አስፈላጊም ከሆነ ወደሌላ ቅዱስ ቦታ ራቅ ብለን በመሄድ ለቤተክርስቲያን አባቶች መናዘዝና ንስኅችንን ማከናወን ይገባናል። እኛም በዚህ ፕሮግራም ሰዎች ይድኑ ዘንድ በተቻለን መጠን ስለናንተ የምናደርገው ጥረትና የምንሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት ከዚህ የተነሳ ስለሆነ የእያንዳንዳንዳችሁንም የውስጥ ችግር በሃሳብም ቢሆን ስለምንረዳችሁ ምናልባት ለንስኅ አባት ለመንገር የሚያስፈራችሁና የሚያሰጋችሁ ነገር ካለ እኛንም በውስጥ መስመር አግኝታችሁ ብታሳውቁን መፍትሄ እንሰጣችኋለን። 

አሁንም ጥያቄ ያቀረቡልን አባላችንና ለሁሉም ጠቃሚ ምክር እንድንሰጥበት የመነሻ ምክንያት ለመሆንና ትክክለኛም የንስኅ ህይወትን ከመፈለግ አንጻርም ስለሆነ ጠያቂያችንን እያደነቅን ወደፊትም በንስኅ ህይወት እንዲበረቱ ምክራችንን እየለገስን ሁላችሁም ኦርቶዶክሳዊያን የእግዚአብሔር ልጆች እንደ ሃይማኖት ወይም እንደ ክርስትና ስንኖር ዘወትር የማንረሳውና ቋሚ ተግባር የምናደርገው የንስኅ ህይወት እንደሆነ ታውቁ ዘንድ ይህንን አጭር የንስኅ መልዕክት እንዲደርሳችሁ አድርገናል።

ስለ ድንግልና እና በተክሊል ስለመጋባት የጠየቁን አባላችን በትክክል የድንግልና ክብራችሁን ጠብቃችሁ መቆየታችሁን በእግዚአብሔር እና በካህኑ ፊት ሳትዋሹ የምታረጋግጡ  ከሆነ በሌላው የመቀራረብ ምክንያት ከስርዓተ ተክሊል ጋብቻ ስለማይከለክላችሁ አደረግን የምትሉትን ነገር ለንስሓ አባታችሁ በግልጽ ከተናገራችሁ በኋላ በስርዓተ ተክሊል ልትፈጽሙ ትችላላችሁ።

መልስ፦ ክርስትናን በአለማ በመግለፅ እስከመጨረሻው ያለውን መንፈሳዊ ግዜያችንን ለማጠናቀቅ እንዳንችል ሰይጣን በብዙ መንገድ የፈተና መሰናክል የማከናወኑ ነገር የተለመደ የህይወት ፈተና ነው። ስለዚህ ራሳችንን ከኅጢአት አግልለን እውነተኛ ክርስቲያን ለመሆን ራሳችንን መካድ ያስፈልጋል፤ ማለትም ክርስቲያን ለመሆን የክርስቲያንን ስራ መስራት ያስፈልጋል። ክርስቲያን ደግሞ በስጋ ምኞት ተፈትኖ የወደቀበት ኀጢአት ቢኖር እንኳን ለሰራው ኅጢአት ጊዜ ሳይሰጥ ወድያውኑ በንስሓ ህይወት ከወደቀበት ይነሳል። 
ጠያቂያችንም ሰወች ሁሉ ከሚፈተኑበት ኅጢአት እርስዎም በዚህ ፈተና ውስጥ መውደቅዎ እንደ መንፈሳዊነት የሚያሳዝን ነገር ቢሆንም በንስሓ ህይወት ተመልሰው ከወደቁበት የኅጢአት ጉድጓድ ለመነሳት ፈቃደኛ መሆኖም እጅግ የሚያስደስት በመሆኑ እርስዎ እየተፈተኑበት ያለውን የስጋ ፈቃድ እኛ ከምንሰጥዎ መንፈሳዊ አባት ጋር በመመካከር እና ትምህርት በመውሰድ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ ለዘመናት የሚፈታተንዎትን የሰይጣን ፈተና ተላቀው እንዲወጡ ነፃ እንዲሆኑ ያደርጉዎታል። በተለያያ መንገድ የሚፈታተነንን የሰይጣን ሃሳብ በመንፈሳዊ ቁርጠኝነት አላማችንን አፅንተን በእውነተኛ ሃይማኖትና ምግባር መጋደል ከቻልን እንኳንስ ይሄንን ትንሹን የኀጢአት ጥፋት ቀርቶ ሌላውን አስጋራሚ የፅድቅ ስራ ሁሉ ለማከናወን እንድንችል አምላከ ቅዱስ እግዚአብሔር ኃይሉን እና ጥበቡን ያቀዳጀናል። ስለዚህ ከዚህ ከማይጠቅም የዝሙት እና በተፈጥሮ እንኳን ካልተፈቀደው ሰይጣናዊ ዝሙታዊ ስራ ፈጥነው ይወጡ ዘንድ በአስቸኳይ መንፈሳዊ ምክር እንድንሰጥዎ በውስጥ መስመር ያነጋግሩን በማለት ይህን ጠይቅልኝ ብለው ለጠየቁዎትና እርስዎም እኛን ለጠየቁን አባላችን መልእክቱን ያድርሱላቸው እንላለን።
መልስ፦ ስርአተ ተክሊል አስባችሁ በመካከል ላይ ራሳችሁን ለመግዛት ሳትችሉ በመቅረታችሁ በመካከል ባደረጋችሁት የስጋ ድካም ከስርአተ ተክሊል በፊት የድንግልናችሁን ክብር ስላጣችሁት የፈፀማችሁትን ጥፋት ለንስሓ አባት በመናገር ቀኖና ከተቀበላችሁ በኋላ በስጋው ደሙ መጋባት ትችላላችሁ። ስርአተ ተክሊል ግን መፈፀም አይቻልም። ዋናው ነገር ለስጋዊ ስም እና ዝና ተብሎ እግዚአብሔርን በሚያሳዝን ሁኔታ የማይገባንን ስርአተ ተክሊል ከመፈፀም ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ እውነቱን አረጋግጠን የምናገኘው ክብር በስርአተ ተክሊል ከምናገኘው ክብር እኩል ስለሆነ የሚያሳስበን እና የሚያስጨንቀን ነገር አይኖርም።
መልስ ፦ ጠየቂያችን እንዳቀረቡት ወንድም ሆነ ሴት ለአካለ መጠን ደርሷል ወይም ለህግ ጋብቻ ደርሷል የምንለው ወንድ ቢያንስ ከ 20 አመት በላይ ሲሆን፣ ሴትም ቢያንስ 15 አመት እድሜና በላይ ስትሆን ነው። በእርግጥም የመጀመሪያዎቹ የሰው ዘር መገኛ የሆኑት አዳም እና ሄዋን ሲፈጠሩ ለአካለ መጠን የደረሱ ሆነው እንደሆነ የስነ-ፍጥረት መፅሐፍ ይነግረናል። ይህ ማለት አዳም አባታችን የ 30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ እንደተፈጠረ እናታችን ሄዋን የ 15 አመት ሴት ሁና እንደተፈጠረች ከዚያም ከተፈጠሩባት ደብር ቅዱስ እግዚአብሔር ወደ አዘጋጀላቸው ወደ ምድረ ገነት እንደገቡ የስነ-ፍጥረት መፅሃፍ ያስረዳናል። ይሁን እንጂ ዘመን የራሱን ታሪክ ይዞ የሚጓዝ ስለሆነና የሰዎችን የመኖር ታሪክ እንደየዘመኑ ገፀባህሪ ወይም ስልጣኔ እና እድገት የሚለካ ስለሆነ የወንድ እና የሴት የአካለ መጠን መድረስ እና በጋብቻ መወሰን በቤተክርስቲያን የቀኖና ስርአት ከላይ በተገለፀው መሰረት ተወስኗል። በሌላ መልኩ አንድ ሰው በትክክለኛ አነጋገር ለአካለ መጠን ደርሷል የምንለው የተፈጥሮ ባህሪ አስገድዶት በዝሙት ሃሳብ እንዳይወድቅ ወይም በራሱ ፍላጎት እና አካላዊ ብቃት ለአካለ መጠን ደርሻለው ማግባት አስፈልጎኛል ካለ በዝሙት ጠንቅ እንዳይወድቅ ወይም እንዳትወድቅ መጋባት ይኖርባቸዋል። በእርግጥ በድንግልና ህይወት መኖርም ሆነ በቅዱስ ጋብቻ መወሰን ውሳኔው ከእግዚአብሔር ስለሆነ፥ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለግሪክ ክርስቲያኖች በፃፈው ክታቡ “ሁሉም እንደ እኔ በድንግልና ቢኖር መልካም ነው፤ ነገር ግን በዝሙት ሃሳብ እና ፍትወት ከመቃጠል ማግባት ይሻላል” ብሏልና የጋብቻ ጉዳይ የግለሰቡ የተፈጥሮ ሁኔታ ይወስነዋል። 
 
ጣራ አለው ወይ ለሚለው ከዝሙት እና ከሴሰኝነት ሃሳብ ነፃ ሆኖ ቅድስናውን ጠብቆ ለሚኖር ሰው እስከ 40ም 50ም ከዛም በላይ አመት መኖር ይችላልና የግድ ካላገባህ ተብሎ የሚገደድበት ሁኔታ አይኖርም፤ ማግባት በሚፈልግበትም ግዜ ማግባት ይችላል።
መልስ፦ ጠያቂያችን የቤተክርስቲያንን ቀኖና እና ስርዓት ለማክበር ብለው ለመረዳት መጠየቅዎ አግባብ ነው። ምክንያቱም “የእግዚአብሔርን ቃል አባትህን ጠይቀው እውነቱንም ይነግርሃል” ይላልና። በመሰረቱ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ወደ ቤተመቅደስ ተጠግተን ለማስቀደስ 3 ቀን ከስጋ ስርዓት እንድንርቅ የሚደረግበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስለኛ በተቀበለው መከራ በእለተ አርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ስጋው ለይቶ 3 መአልትና 3 ለሊት በከርሰ መቃብር ውስጥ ቆይቷል። በዚህም ምክንያት ቅዱሳን ሐዋሪያት እና ከሱ ጋር ይከተሉት የነበሩት ደቀመዛሙርት የጌታን ትንሳኤ ሳናይ የሚበላ አንበላም የሚጠጣም አንጠጣም ብለው በፆም ተወስነው ስለቆዩ ነው። ስለዚህ ዛሬም የምንቀበለው ቅዱስ ቁርባን የክርስቶስን አማናዊ ስጋና አማናዊ ደም ስለሆነ ያንን መነሻ አብነት አድርገን ለ 3 ቀናት ንፅህናችንን እና ቅድስናችንን ጠብቀን የምንቆየው ነው።
 
በመሆኑም ህግ እና ቀኖና የሆነውን ነገር በህግነትና በቀኖናነቱ የተወሰነውን እውነቱን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ በደካማ ስጋችን ተፈትነንና ስጋዊ ምኞት አሸንፎን ቀኖናን የሚሽር ስህተት ፈፅመን ብንገኝ ወይም ደግሞ ከ 3 ቀን ባነሰ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ጠያቂያችን ያነሱትን ስህተት ፈፅሞ ቢገባ ያ ክርስቲያን ፈፅሞ የተወገዘ የተረገመ ነው ማለት አይደለም። የቤተክርስቲያን ስርዓት እና ቀኖና በመሻሩ ተግሳፅና ምክር ሊሰጠው ይችላል። ወደፊት እያወቀ እንዲህ አይነት ጥፋት እንዳትፈፅም ተብሎ ምክር ይሰጠዋል። ይሄ የሚሆነው በህጋዊ ጋብቻ ተወስነው ለሚኖሩ ነው። ከዚህ ውጭ ለሚሆነው ግን እንኳን ቤተክርስቲያን በድፍረት ለገባንበት ይቅርና ከሕግ ውጭ ላደረግነው ግንኙነትም ከባድ የቀኖና ቅጣት ይጠብቀዋል። በዚሁ መሰረት ጠያቂያችን ቀኖና ባለመሻር እና ከእግዚአብሔር በረከት ለማግኘት በምናደርገው መንፈሳዊ አገልግሎት በነፍስ የምንጎዳበት እርግማን እንዳያመጣብን ከወዲሁ ክርስቲያናዊ ስነምግባር እና ጥንቃቄ ሊኖረን ይገባል በማለት መልዕክታችን እንዲደርስዎት አድርገናል።
መልስ፦ ጠያቂያችን የቤተክርስቲያንን ቀኖና እና ስርዓት ለማክበር ብለው ለመረዳት መጠየቅዎ አግባብ ነው። ምክንያቱም “የእግዚአብሔርን ቃል አባትህን ጠይቀው እውነቱንም ይነግርሃል” ይላልና። በመሰረቱ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ወደ ቤተመቅደስ ተጠግተን ለማስቀደስ 3 ቀን ከስጋ ስርዓት እንድንርቅ የሚደረግበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስለኛ በተቀበለው መከራ በእለተ አርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ስጋው ለይቶ 3 መአልትና 3 ለሊት በከርሰ መቃብር ውስጥ ቆይቷል። በዚህም ምክንያት ቅዱሳን ሐዋሪያት እና ከሱ ጋር ይከተሉት የነበሩት ደቀመዛሙርት የጌታን ትንሳኤ ሳናይ የሚበላ አንበላም የሚጠጣም አንጠጣም ብለው በፆም ተወስነው ስለቆዩ ነው። ስለዚህ ዛሬም የምንቀበለው ቅዱስ ቁርባን የክርስቶስን አማናዊ ስጋና አማናዊ ደም ስለሆነ ያንን መነሻ አብነት አድርገን ለ 3 ቀናት ንፅህናችንን እና ቅድስናችንን ጠብቀን የምንቆየው ነው።
 
በመሆኑም ህግ እና ቀኖና የሆነውን ነገር በህግነትና በቀኖናነቱ የተወሰነውን እውነቱን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ በደካማ ስጋችን ተፈትነንና ስጋዊ ምኞት አሸንፎን ቀኖናን የሚሽር ስህተት ፈፅመን ብንገኝ ወይም ደግሞ ከ 3 ቀን ባነሰ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ጠያቂያችን ያነሱትን ስህተት ፈፅሞ ቢገባ ያ ክርስቲያን ፈፅሞ የተወገዘ የተረገመ ነው ማለት አይደለም። የቤተክርስቲያን ስርዓት እና ቀኖና በመሻሩ ተግሳፅና ምክር ሊሰጠው ይችላል። ወደፊት እያወቀ እንዲህ አይነት ጥፋት እንዳትፈፅም ተብሎ ምክር ይሰጠዋል። ይሄ የሚሆነው በህጋዊ ጋብቻ ተወስነው ለሚኖሩ ነው። ከዚህ ውጭ ለሚሆነው ግን እንኳን ቤተክርስቲያን በድፍረት ለገባንበት ይቅርና ከሕግ ውጭ ላደረግነው ግንኙነትም ከባድ የቀኖና ቅጣት ይጠብቀዋል። በዚሁ መሰረት ጠያቂያችን ቀኖና ባለመሻር እና ከእግዚአብሔር በረከት ለማግኘት በምናደርገው መንፈሳዊ አገልግሎት በነፍስ የምንጎዳበት እርግማን እንዳያመጣብን ከወዲሁ ክርስቲያናዊ ስነምግባር እና ጥንቃቄ ሊኖረን ይገባል በማለት መልዕክታችን እንዲደርስዎት አድርገናል።
መልስ ፦ ጥያቄው መቅረቡን በአክብሮት ብንቀበለውም ነገር ግን ከጋብቻ ጋር በተያያዘ ቅድመ ጋብቻም ይሁን ድህረ ጋብቻ ስላሉት ስለሚፈቀዱና ስለማይፈቀዱ ሁኔታወችም በስፋት መልእክት ማስተላለፋችን ይታወሳል። ይሁን እንጂ ጠያቂያችን ከዚህ በፊትም ያስተላለፍናቸውን መልዕክቶች ማየት ካልቻሉ አሁን ለጠየቁን ጥያቄ መረዳት ያለብዎ ማንኛውም ሃይማኖት ያለው ክርስቲያን ለአካለ መጠን ወይም ለአካለ ጋብቻ ደርሶ እና በሃይማኖት ስርዓትና በባህላዊ ትውውቅና በስርዓተ በጋብቻ ከመፈፀማቸው በፊት ማንኛውንም የአካለ ስጋ ሩካቤ ማድረግ ፈፅሞ ክልክል ነው። ለዚህም ነው በቅዱስ ጳውሎስ ስጋችሁን ለመግዛት ፍላጎታችሁን ለማሸነፍ ካልቻላችሁ በምኞት ከመቃጠል ማግባት ይሻላል ያለው። በዚህ መሰረት ማንኛውም ወንድም ሆነ ሴት ክርስቲያን የስጋውን ፍላጎት መግዛትና መቆጣጠር በማይችልበት የእድሜ ደረጃ ሲደርስ በሃይማኖት ስርዓትና በአገራዊ ባህል የፈለጋትን ወይም የፈለገችውን ተስማምተው ማግባት እንደሚችል ተፈጥሮዋዊ ማንነት ከእግዚአብሔር ተሰጥቷል። ከዚህ የተነሰ የተሰጠንን የነፃነት ፀጋ መጠቀም መቻል እንጂ ከጋብቻ በፊት የድብብቆሽ ስራወች መፈፀም እኛንም በነፍስ ይጎዳናል ከፈጣሪ ጋርም ያጣላናል በሰው ዘንድም መሀበራዊ ማንነታችንን ያዛባል። እና ጠያቂያችን በዚህ መልክ ስራ ላይ ብናውለው በእግዚአብሔር ዘንድም በረከትና መንፈሳዊ እድገት ያሰጣል በማለት እንመክራለን።
መልስ፦  ጠያቂያችን በመንፈሳዊ ትምህርት እየተማሩ መኖርና እንዲሁም ደግሞ አስረ ክህነት ሳይኖረው መፅሐፍትን እየተረጎሙና እያስተማሩ መኖር የትኛው ይሻላል ለሚለው ፤ ሁሉም ነገር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚፈፀም ቢሆንም ሁለቱም ትልቅ መንፈሳዊ በረከት የሚያሰጡ ስለሆነ  ፤በመጀመሪያ ሰው የእውቀት መሰረት በሆኑ በአብነት መምህራን እና በመንፈሳዊ ትምህርት ቤት ዋጋ ከፍሎ እውቀትን በእግዚአብሔር ስም የእለት ጉርሱን እያገኘ ገንዘብ የማይገዛውን እውቀት መሸመት ትልቅ መንፈሳዊ ተጋድሎና ከሁሉ የሚጠቅም ተግባር ነው ። በመቀጠልም የተማሩት ጥልቅ መንፈሳዊ እውነት በመዝራት ሌሎችን ወገኖችን በማስተማር ከሰማያዊ ሞት እና ከጨለማ ህይወት ማዳን ሌላው ከበረከት የሚያሰገኝ ተጋድሎ ነው። ስለዚህ በመጀመሪያ  ሰው ራሱን ለመካድም ሆነ ወደዚህ አላማ ለመግባት በስጋዊ ስሜትና ፍላጎት ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጠየቅና በአላማው ያለፉ አባቶችን ማማከር ያስፈልጋል። ስለጉዳዩም በግል ከፈጣሪ ጋር በፀሎት ወይም በልዩ ሱባዔ ማነጋገር ያስፈልጋል እንዲህ ከሆነ እግዚአብሔር የሚጠቅመንን እና የሚጎዳንን ነገር  አሱ ስለሚያውቅ ሁሉ ነገር  በሱ ፈቃድ ይወሰናል ማለት ነው። ከዚህ ውጭ የሚያማክሩን ሃሳብ ካለ በውስጥ መስመር ሊያናገኙን ይችላሉ።
መልስ ፦በቤተክርስቲያን ስርዓትም ሆነ በአገራችን ባህል የቅዱስ ጋብቻ አፈፃፀም የተለያየ ገፅታ አለው። ጠያቂያችን እንዳሉት አንዳንድ የአገራችን አካባቢ በባህላዊ አሰራር ተጋቢወቹ ሳይፈላለጉና ሳይተጫጩ ቤተሰቦቻቸው በሚያደርጉት መቀራረብ ብቻ ጥቅምና ጉዳቱን ሳያመዛዝኑ በቤተሰብ ግፊት የሚጋቡ አሉ። እንደተባለው የእርስዎም ጥያቄ ጥፋትና ልማቱን በሃይማኖት ስርዓትም እንደ ኀጢአት እንደሚቆጠር የተረዱት ነገር ሳይኖራቸው ህግ ሰርተው አብረው የሚኖሩ አሉ። በአጠቃላይ በእንዲህ አይነት ጋብቻ የቆዩ ሰወች ወደፊት አብረው ጋብቻቸውን አፅንተው ከኖሩ እንደ ጥፋተኛ አያስቆጥራቸውም፣ እንደ ዝሙተኛም አይቆጠሩም። ምክንያቱም በቤተሰቦቻቸውም ሆነ በቤተክርስቲያን አባቶች ስለተፈፀመው የጋብቻ ሁኔታ የተሰጣቸው ምክርና ተግሳፅ ባለመኖሩ ባለማወቅ የተደረገ ስለሆነ የነሱ ጥፋት እዚህ ውስጥ የለም ማለት ነው። ነገር ግን በጋብቻቸው ፀንተው ወደፊት በዱስ ቁርባን ለመወሰን እንዲበቁ የንስሓ አባት መንፈሳዊ ምክርና የሃይማኖት ትምህርት ያስፈልጋቸዋል። እንደ ጥፋት የሚያስ ቆጥርባቸው የፈለጉትን ግዜ ያህል ሳያውቁም ቢሆን እንደፈለጋቸው ሲሆኑ ኖረው ከጊዜ በኋላ የነበራቸውን ግንኙነት አፍርሰው ወደ ሌላ ፍላጎት ከገቡ በመንፈሳዊ ህይወታቸው እንደ ኀጢአተኛ ሊያስቆጥራቸው ይችላል ማለት ነው።
መልስ፦ በሃይማኖት አንድ ያልሆነውን ወንድ ወይም ሴት በጋብቻም ሆነ በልዩ መንፈሳዊ ዝምድና መቀራረብ በሃይማኖታችን ስርአት ፈፅሞ አይፈቀድም። በእርግጥ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ቢቻልስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ ብሎ እንደመከረን የግል ሃይማኖታችንን እና መንፈሳዊ ህይወታችንን በማይነካና እኛን ኀጢአተኛ በማያደርግ መኃበራዊ ጉዳይ አብሮና ተባብሮ እንደ ጎረቤትም ሆነ እንደ ስራ አጋር መኖር ይቻላል። ይሁን እንጂ በሌላ ለሚስትነትም ሆነ ላልተፈቀደ ፍቅረኝነት ፈቃደ ስጋችን አሸንፎን በሃሳብም ሆነ በተግባር የወደቅንበት ጉዳይ ካለ ይህንኑ ጥፋታችንን ለንስሓ አባታችን ተናዘን ለጥፋታችን ቀኖና መውሰድ አለብን። ጠያቂያችን አሁን እንዳሉት ከሆነ በተግባር የተፈፀመ ነገር ባለመኖሩ በትክክለኛ ለመቀራረብ ከፈለጋችሁ ወደፊት በረጅም ግዜ ቢሆንም ትምህርትና ምክር በመስጠት በማሳመን በሃይማኖትም ለመተባበር ፈቃደኛ ሆና ከተገኘች አብሮ ለመኖር ብትወስኑ በእግዚአብሔር ዘንድ ያላችሁ ክብራችሁ እጥፍ ድርብ ይሆናል። ከዚህ ውጭ ከሆነ ግን ‘መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና’ እንዲሉ ሊቃውንት ከወዲሁ ሰብሰብ ብሎ እራስን መቆጠብ እጅግ ያስፈልጋል በማለት ጠያቂያችን ይህን ምክር ልከንልዎታል።
 
መልስ፦ ጠያቂያችን ሚዜ ከሆነለት ሰው እህቱን ሊያገባ ይችላል ብለው የጠየቁን ነገር በልማድ እንደምናየው እንኳንስ የሚዜን እህት ማግባት ቀርቶ ከዚህም ባለፈ ብዙ የማይገቡ ነውሮች ሲፈፀሙ ዘወትር በአይናችን የምናየው ነው። እውነተኛውና ትክክለኛው ስርዓት ግን ቅድስት ቤተክርስቲያንም ያስተማረችን ስጋዊና መንፈሳዊ ዝምድና ያስተሳሰራቸው ሰወች ጋብቻ በተወሰነ ገደብ ይከለከላሉ። መንፈሳዊ ዝምድና ማለት ክርስትና አባት ወይም እናት መሆን፣ የንስሓ አባትና የንስሓ ልጅ መሆን፣ በቃል ኪዳን ሚዜ መሆን፣ እነዚህን የመሳሰሉ ይገኙበታል። በስጋ ተዋልደው ደግሞ የሰው ዝምድናው ቁጥር እስከ 7ኛ ትውልድ እስከሚደርስ ጊዜ ድረስ እንደሚከለከል በፍትሓ ነገስትም ተደንግጓል። ስለዚህ ጠያቂያችን የዘመኑን አያድርገውና እንደዚህ ሁሉም ሰው በጥፋት መንገድ ሜዳ ሳይገባ የቤተክርስቲያን ቀኖና እንዲሁም የአባቶቻችን ትምህርት እና ተግሳፅ በሚከበርበት የቀደሙ የአባቶቻችን ዘመን እንዲህ አይነት ተግባር እንዳይፈፀም ይከለክል እንደነበረ እንዲረዱት ይህን መልዕክት ልከንልዎታል።
 
 
መልስ፦ ጠያቂያችን በሃይማኖት አንድ ሳትሆኑ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ የሆነውን የትዳር ጓደኛ በማድረግ ልጆች ወልዳችሁ ሰላማዊ የሆነ የትዳር ህይወት ቢኖራችሁም በሃይማኖት በኩል ያለው ልዩነት ከእግዚአብሔር መንግስት እንዳይለይዎ ምን ማድረግ እንደሚገባዎ መፍትሄና መንፈሳዊ መክር እንድንሰጥዎ ለጠየቁን የተሰጠ ምላሽ።
 
በቅድሚያ ስለሃይማኖትዎ እና ስለመንፈሳዊ ህይወትዎ (ስለነፍስ ጉዳይ) ቅድሚያ ሰጥተው ከቤተክርስቲያን አባቶች መፍትሄ ለማግኘት መጠየቅዎ እጅግ የሚያስደስት ስለሆነ በዚህ መንፈሳዊ ትጋትና ጥንካሬ እንዲቀጥሉ እግዚአብሔር ይርዳዎት። ይሁን እንጂ ብዙ ሰዎች የእርስዎን ሕይወት በሚመስል አኳኀን ሃይማኖታቸውን እየተፈታተናቸው ያለ ብዙ የህይወት ገጠመኝ አለ። አንዳንዶቹ ክርስቲያኖች ሆን ብለው እያወቁ ሃይማኖታቸው የማይፈቅደውን ነገር የሚያደርጉ አሉ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ክርስቲያን ከመሆን ያለፈ ምንም እውቀትና ሃይማኖታዊ ግንዛቤ ስለሌላቸው ጥፋትና ጉዳት ያለው ሳይመስላቸው ሃይማኖታቸው እና ክርስትናቸው የማይፈቅደውን የሚያደርጉ አሉ። ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተጠያቂዎች እኛው የቤተክርስቲያን አባቶችና መምህራን ነን። ምክንያቱም በ40 እና በ80 ቀን ከ እግዚአብሔር ቤት በጥምቀት የተቀበልናቸውን በሃላፊነት ልናስተምርና ልንጠብቅ የተረከብናቸውን የመንፈስ ልጆቻችንን የሃይማኖትና የምግባር ትምህርት እያስተማርን በምድራዊ ህይወታቸው በሚኖሩበት ጊዜ ለሚያጋጥማቸው የፈተና ህይወት እንዴት መወጣት እንዳለባቸውና ወደ ፈተና ህይወት እንዳይገቡ እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና አስተምሮ መሠረት ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች ሁሉ ክርስትናቸው የማይፈቅደውን እንዳያደርጉ ገና ከህፃንነት ህይወት ጀምሮ ኮትኩተን እና ተከታትለን፣ ተቆጣጥረን እና ተንከባክበን ብናሳድጋቸው ኑሮ ከሞት ይልቅ ሕይወትን፣ ከስጋዊነት ይልቅ መንፈሳዊነትን፣ ከምድራዊነት ይልቅ ሰማያዊነትን፣ ከሚያልፈው ይልቅ ዘለአለማዊውን፣ ከጨለማ የልቅ ብርሃንን፣ ከጠላታችን ዲያብሎስ ይልቅ የፈጠረንን አምላክ፣ ከጣኦት የልቅ የእግዚአብሔር ማደርያ የሆነውን ታቦትን፣ ከሚያልፈው ምድራዊ ሃብትና ንብረት  ይልቅ የማያልፈውን የእግዚአብሔርን መንግስት ለመምረጥ እንዲወስኑ ያስችላቸው ነበር።  
 
ስለዚህ ጠያቂያችን ለጊዜው አንድ ግዜ የገቡበት አላማ በመሆኑ በትዳር ህይወታችሁም ብዙ ረጅም ጎዞ የሄዳችሁ ስለሆነ ከምንም በላይ ደግሞ ልጆች የእግዚአብሔር ፀጋና ስጦታዎች ስለሆኑ እናንተም ባልና ሚስትም ይሄን ያህል ግዜ ተጣምራችሁ ተመካክሮ እና ተረዳድቶ መኖር እየቻላችሁ ሃይማኖት ስለማይፈቅድ ብቻ እንድትፋቱ ወይም እንድትለያዩ መወሰን እጅግ ከባድ ነው። ምክንያቱም የምትመሩትን ሕይወትና የሃይማኖቱን ጉዳይ አነፃፅረን እና አገናዝበን የምናይበት አቅጣጫ እጅግ ከባድ ስለሆነ። ስለዚህ አሁን እርስዎ እንደነገሩን ጥሩ ትዳር ስለሆነ ያላችሁ በመካከላችሁ ሌላ ቅሬታ ሳይገባም እንዲህ አይነት ሃይማኖት አጀንዳም አንስታችሁ ልዩነት ሳይፈጠርባችሁ ኑሯችሁን ቀጥሉ። 
 
ነገር ግን ይህን ስንል በሃይማኖት በኩል የምናጣውን የእግዚአብሔር ክብር እንዳጡ ይቀጥሉ ማለት ስላልሆነ ከእናንተም ሆነ ከኛም በላይ የእናንተን የውስጥ ሃይማኖታዊ ችግር የፍጥረታት ሁሉ ባለቤት የሆነው አልፋና ኦሜጋ (ሁሉን ቻይ) አምላክ ስለሚያውቀው እሱ አግዞን ፀጋውን እና ጥበቡን አድሎን በቀጣይነት በምክርና በትምህርት ልናመጣው የምንችል መፍትሄ ስለሚኖር ችላ ሳይሉና ሳይዘናጉ በውስጥ መስመር በላክንልዎ ስልክ ቁጥር ደውለው ያግኙንና ስለቀጣይ ህይወታችሁ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንመካከራለን እንወያያለን በማለት ይህን አጭር መንፈሳዊ ትምህርታዊ መልዕክት ለእርስዎና እርስዎን ለሚመስሉ ልከናል። መልእክቱን አንብባችሁ ትረዱ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን።
ስለቅዱስ ጋብቻ ያለወትን የቃልኪዳን አክብሮትና ስለመንፈሳዊ ፅናትዎ እጅግ አድርገን እናደንቃለን። ስለ አንዳንድ ካህናት ስናነሳ የእርስዎን የንስሓ አባት የእውቀት ችሎታ እና የምግባር ጉዳይ ባናውቅም አንዳንድ ካህናት ግን ከሃይማኖታዊ እውቀት እጥረትና ከግዴለሽነት ወይም ከምንደኝነት የተነሳ በነፍስ ስለሚጠፉት የመንፈስ ልጆቻቸው (ስለመንጋው ጥበቃ) የማይገዳቸው ሁሉም ካህን አይደሉም ግን እንደተባለው ሁሉም ካህናት በአገልግሎት ያላቸው መታመን እና ብቃት እኩል አይደለም። እንደማንኛውም ስጋ እንደለበሰ ሰው ታማኝነታቸውን አጉድለው በሚያልፈው ስጋዊና ምድራዊ ሃሳብ የሚወድቁ ብዙወች እንደሆኑ መረዳት አለብዎት። እኛ ከፈጣሪ ዘንድ ለራሳችን ነፍስ ብቻ ሳይሆን በሃላፊነት በምንጠብቃቸው በመንፈሳዊ ልጆቻችን ህይወትም እንጠየቃለን፤ እግዚአብሔር አምላክ በነብዩ በእስቅኤል ላይ አድሮ እንደተናገረው “የበጎቼን ደም ከእጃችሁ እፈልጋለው ይላል”።  
ስለዚህ ጠያቂያችን በንስሓ አባትዎ በኩል የጠበቁትን አባታዊ አቋም ማጣትዎ ቢያሳዝኖም በዚህ አይነት ክርስቲያናዊ ህይወት በመፅናትዎ ቸሩ መድኅኒአለም ከእናቱ ጋር ችግሩን ስለሚፈታ ከዚህ ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለብዎ በተላከልዎ የውስጥ መስመር ያግኙንና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የመፍትሔ ሃሳብ እንሰጦታለን። በዋናነት ግን ስጋዊ የትዳር ጉዳይ እጅግ አስፈላጊ እና የምድራዊ ህይወት መሠረት ቢሆንም ከነፍሳችን እና ከዘላለማዊ ህይወታችን የሚበልጥ ግን ስላልሆነ የምድሩን ነገርም ቢሆን እሱ ስለ እኛ ያስባልና ለሁሉም ችግራችን እግዚአብሔር ቁልፍ መፍትሄ አለውና ዛሬ ላይ የተጨናነቁበት ጊዜያዊ ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ በእግዚአብሔር ፈቃድ በእናቱ አማላጅነት በቅዱሳኑ ተራዳይነት እንደሚፈታ አምነው በአላማዎ በትእግስት ፀንተው እንዲጠብቁ ምክራችንን እንለግሳለን። 
የእግዚአብሔር ፀጋ አይለይዎት።
መልስ፦ ሁለት በእጮኝነት ያሉ ወንድና ሴት ንፅህናቸውን ጠብቀው በድንግልና ህይወት ካሉ ጠያቂያችን እንዳሉት ጋብቻቸውን እስከሚፈፅሙ ድረስ ለየብቻቸው መቁረብ ይችላሉ። ነገር ግን ቀደም ሲል የፈፀሙት ኀጢአት ኑሮ ንስሓ ካልገቡበትና አሁንም በእጮኝነት ከጋብቻቸው በፊት የሚያደርጉት ነገር ካለ ግን መቁረብ አይችሉም ።
መልስ፦ ጠያቂያችን የቀረቡት ሃሳብ ባል እና ሚስት ከተፋቱ በኋላ ከሌላ የትዳር አጋር ጋር ጋብቻ እስከሚፈፅሙ እየቆረቡ መቆየት ይችላሉ ወይ? የሚለውን ጥያቄ በሚመለከት፦ በመሰረቱ ከዚህ በፊትም እንደመከርነው ባል እና ሚስት የስጋ አስተሳሰብ በሆነ ፈተና ለሚያጋጥማቸው ችግሮች እንዲፋቱ አይፈቀድላቸውም። ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከተፋቱ እንኳን፦
 
1. በየግላቸው ስጋው ደሙን ለመቀበል የሚችሉት በቀጣይ ህይወታቸው ሴቷም እንደስዋ በቁርባን ተወስኖ የሚኖረውን ለማግባት፣ ወንዱም እንደሱ በቁርባን ተወስና የምትኖረውን ለማግባት ከሆነ እየቆረቡ ለመኖር ይችላሉ።
 
2. ወንዱም ሆነ ሴቷ አብረው የነበሩበት የጋብቻ ቆይታቸውንና የተፋቱበትን ዋና ምክንያት ተናዘው እንደነሱ በሃይማኖትና በምግባር የሚወሰነውን ባል ወይም ሚስት በማግባት እየቆረቡ መንፈሳዊ ህይወታቸውን ማስቀጠል።  
 
3. ሁለተኛ ላለማግባት የወሰኑ ከሆነ ንፅህናቸውን እና ቅድስናቸውን ጠብቀው በየግዜው የነፍስ አባታቸውን እያማከሩ በስርዓተ ቁርባን ህይወታቸውን ማስቀጠል ይችላሉ። 
 
4. ሌላው ቀጣይ ህይወታቸውን ስርዓተ ምንኩስና በመወሰን መንፈሳዊ ልባዊ ውሳኔ ካላቸውም በስርዓተ ቁርባኑ ተወስነው ከቆዩ በኋላ በቤተክርስቲያን ቀኖና መሰረት የንስሓ አባታቸውን አማክረው ለምንኩስና የሚያበቃቸውን መስፈርት ሲያሟሉ እንዲመነኩሱ ይደረጋል ማለት ነው።
 
5. ዲያቆን ወይም ቄስ ሚስቱ ብትሞትበት ወይም ከሱ አቅም በላይ በሆነ ፈተና ቢፋታ፤ ያለ ሚስት የሚቀድሰውም ሆነ አባት የሚሆነው እስከ 6 ወር እንደሆነ በፍትሐ ነገስት ተወስኗል። ከዚያ በኋላ ግን ወይ መንኩሶ በክህነቱ ይቀጥላል፤ ወይም ፈተናውን የማይችለው ከሆነ ለቤተክርስቲያን አባቶች በግልፅ ተናግሮ በቅዱስ ቁርባን ተወስና የምትኖረውን ያገባል። ከዚህ በኋላ ግን መቀደስም ሆነ አባት መሆን አይችልም። የውጭ አገልግሎቱን እያከናወነ እየፀለየ ለመንግስተ ሰማያት የሚያበቃውን የቱሩፋት ስራ እነሰራ መኖር ይችላል።
 
ስለዚህ ጠያቂያችን በአጭሩም ቢሆን ይህንን ማብራሪያ እንዲደርስዎ ስላደረግን አንብበው እንዲረዱት በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን።

መልስ፦ጠያቂያችን አንድ ክርስቲያን በእስልምና ወይም በሌላ ሃይማኖት ያለዉን ወይም ያለችውን ለማግባት ቢፈልግ ወይም ብትፈልግ እና ቢስማሙ በሁለቱ መካከል በእምነት ለመመሳሰል ከወሰኑ በኋላ የቤተክርስቲያናችንን ዶግማ እና ቀኖና ጠንቅቀው ለሚያውቁ የቤተክርስቲያን መምህር ሃሳቡን በማስረዳት ወደ ክርስትና የመጣውን ወይም የምትመጣውን ከሁሉ በፊት ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ዝርዝር መረጃ በመስጠት ከተማረ ወይም ከተማረች በኋላ ፤ እምነቱን ለጋብቻ ተብሎ ሳይሆን በትክክል ገብቶኛል አምኛለሁ ክርስቲያን ለመሆንም ወስኛለው በሚል ቃል ኪዳን እንዲገባ ወይም እንድትገባ ከሆነ በኋላ የክርስትና ጥምቀት እንዲጠመቁ በማድረግ መጋባት ወይም ጋብቻ መፈፀም ይቻላል ::

ሁለቱም ቀደም ሲል ሌላ ጋብቻ የፈፀሙ ከሆነ በስጋና ደሙ ጋብቻ መፈፀም ይችላሉ። በድንግልና የቆዩም ከሆነ ደግሞ በስርዓተ ተክሊል ሊጋቡ ይችላሉ ::በዚህ አይነት ሙስሊምን ወይም የሌላ ሃይማኖት ተከታይን ክርስቲያን አድርጐ ያገባ ሰው እንዲያውም ሌላ ነፍስ ለማዳን በመቻሉ ዋጋው እጥፍ ድርብ ይሆናል።ከእስልምና ሃይማኖት ወደ ክርስትና ሃይማኖት ለመጣውም ሰው  ቅዱስ ጳውሎስ እንደነገረን ያላመነ ባል ባመነች ሚስቱ የተቀደሰ እንደሚሆን ፣ ያላመነች ሴትም በእምነት በሚኖረው ባልዋ የተቀደሰች እንደምትሆን ባስተማረን መሰረት ከማንኛውም አይነት ሃይማኖት ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት በመመለስ ማግባት ስለሚቻል ጥያቄ ያቀረቡት አባልም ሆኑ ሌሎቹም የዚህ መንፈሳዊ ድረገጽ ተከታታዮች ይህን እና በተመሳሳይ ጥያቄ ላይ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ ከዚህ በፊት በሌላ ጥያቄ ምላሽ የሰጠንበትን ልብንላችኋልና አንብባችሁ ሃሳቡን ትረዱት ዘንድ እንመክራለን፦

 ……………

ከዚህ በፊት የተጠየቀ ጥያቄ:—እኔ እንደ ብዙሀኑ ምኞቴም ህልሜም ንሰሀ መግባት ነው ። ባለትዳርና የሁለት ለጆች እናት ነኝ። ባለቤቴ ግን እምነቱ ሌላ ነው የልጆቻችንም እንደ እምነቴ እየኖሩ ነው ምንም ጫና አያፈሳድርብኝም እንደውም ያግዘኛል ። እኔን መስሎ ነው የሚኖረው ያው መምሰል መሆን አይደለም ….. ። ግን ንሰሀ ለመግባት አባቶችን ጠይቄ ነበር ። ወይ አንድ መሆን ወይ መለያየት አለባቹ አሉኝ ። ይህ የእኔ ብቻ ችግር አይደለም በዚህ ውጥረት ውስጥ ሌሎች የማወቃቸውም አሉና መፍተሄ ካለው እባካቹ እርዱን።

መልስ፦ ጠያቂያችን በሃይማኖት አንድ ሳትሆኑ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ የሆነውን የትዳር ጓደኛ በማድረግ ልጆች ወልዳችሁ ሰላማዊ የሆነ የትዳር ህይወት ቢኖራችሁም በሃይማኖት በኩል ያለው ልዩነት ከእግዚአብሔር መንግስት እንዳይለይዎ ምን ማድረግ እንደሚገባዎ መፍትሄና መንፈሳዊ መክር እንድንሰጥዎ ለጠየቁን የተሰጠ ምላሽ።

በቅድሚያ ስለሃይማኖትዎ እና ስለመንፈሳዊ ህይወትዎ (ስለነፍስ ጉዳይ) ቅድሚያ ሰጥተው ከቤተክርስቲያን አባቶች መፍትሄ ለማግኘት መጠየቅዎ እጅግ የሚያስደስት ስለሆነ በዚህ መንፈሳዊ ትጋትና ጥንካሬ እንዲቀጥሉ እግዚአብሔር ይርዳዎት። አንዳንዶቹ ክርስቲያኖች ሆን ብለው እያወቁ ሃይማኖታቸው የማይፈቅደውን ነገር የሚያደርጉ አሉ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ክርስቲያን ከመሆን ያለፈ ምንም እውቀትና ሃይማኖታዊ ግንዛቤ ስለሌላቸው ጥፋትና ጉዳት ያለው ሳይመስላቸው ሃይማኖታቸው እና ክርስትናቸው የማይፈቅደውን የሚያደርጉ አሉ። ለዚህ ሁሉ ጥፋት ተጠያቂዎች እኛው የቤተክርስቲያን አባቶችና መምህራን ነን። ምክንያቱም በ40 እና በ80 ቀን ከ እግዚአብሔር ቤት በጥምቀት የተቀበልናቸውን በሃላፊነት ልናስተምርና ልንጠብቅ የተረከብናቸውን የመንፈስ ልጆቻችንን የሃይማኖትና የምግባር ትምህርት እያስተማርን በምድራዊ ህይወታቸው በሚኖሩበት ጊዜ ለሚያጋጥማቸው የፈተና ህይወት እንዴት መወጣት እንዳለባቸውና ወደ ፈተና ህይወት እንዳይገቡ እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና አስተምሮ መሠረት ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች ሁሉ ክርስትናቸው የማይፈቅደውን እንዳያደርጉ ገና ከህፃንነት ህይወት ጀምሮ ኮትኩተን እና ተከታትለን፣ ተቆጣጥረን እና ተንከባክበን ብናሳድጋቸው ኑሮ ከሞት ይልቅ ሕይወትን፣ ከስጋዊነት ይልቅ መንፈሳዊነትን፣ ከምድራዊነት ይልቅ ሰማያዊነትን፣ ከሚያልፈው ይልቅ ዘለአለማዊውን፣ ከጨለማ የልቅ ብርሃንን፣ ከጠላታችን ዲያብሎስ ይልቅ የፈጠረንን አምላክ፣ ከጣኦት የልቅ የእግዚአብሔር ማደርያ የሆነውን ታቦትን፣ ከሚያልፈው ምድራዊ ሃብትና ንብረት  ይልቅ የማያልፈውን የእግዚአብሔርን መንግስት ለመምረጥ እንዲወስኑ ያስችላቸው ነበር።  

ስለዚህ ጠያቂያችን ለጊዜው አንድ ግዜ የገቡበት አላማ በመሆኑ በትዳር ህይወታችሁም ብዙ ረጅም ጎዞ የሄዳችሁ ስለሆነ ከምንም በላይ ደግሞ ልጆች የእግዚአብሔር ፀጋና ስጦታዎች ስለሆኑ እናንተም ባልና ሚስትም ይሄን ያህል ግዜ ተጣምራችሁ ተመካክሮ እና ተረዳድቶ መኖር እየቻላችሁ ሃይማኖት ስለማይፈቅድ ብቻ እንድትፋቱ ወይም እንድትለያዩ መወሰን እጅግ ከባድ ነው። ምክንያቱም የምትመሩትን ሕይወትና የሃይማኖቱን ጉዳይ አነፃፅረን እና አገናዝበን የምናይበት አቅጣጫ እጅግ ከባድ ስለሆነ። ስለዚህ አሁን እርስዎ እንደነገሩን ጥሩ ትዳር ስለሆነ ያላችሁ በመካከላችሁ ሌላ ቅሬታ ሳይገባም እንዲህ አይነት ሃይማኖት አጀንዳም አንስታችሁ ልዩነት ሳይፈጠርባችሁ ኑሯችሁን ቀጥሉ። 

ነገር ግን ይህን ስንል በሃይማኖት በኩል የምናጣውን የእግዚአብሔር ክብር እንዳጡ ይቀጥሉ ማለት ስላልሆነ ከእናንተም ሆነ ከኛም በላይ የእናንተን የውስጥ ሃይማኖታዊ ችግር የፍጥረታት ሁሉ ባለቤት የሆነው አልፋና ኦሜጋ (ሁሉን ቻይ) አምላክ ስለሚያውቀው እሱ አግዞን ፀጋውን እና ጥበቡን አድሎን በቀጣይነት በምክርና በትምህርት ልናመጣው የምንችል መፍትሄ ስለሚኖር ችላ ሳይሉና ሳይዘናጉ በውስጥ መስመር በላክንልዎ ስልክ ቁጥር ደውለው ያግኙንና ስለቀጣይ ህይወታችሁ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንመካከራለን እንወያያለን በማለት ይህን አጭር መንፈሳዊ ትምህርታዊ መልዕክት ለእርስዎና እርስዎን ለሚመስሉ ልከናል። መልእክቱን አንብባችሁ ትረዱ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን።

መልስ፦ በጋብቻ ለነበረ ወይ በነበረች ማንኛውም ክርስቲያን በመጀመርያ ጋብቻን ለማፍረስ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥም እና በቂ  ምክንያት ሲኖር በቤተክርስቲያን ተረጋግጦ የተፈጸመ ፍቺ ከሆነ ሌላ ለማግባት ሲፈልጉ ንስኀ ተቀብለው በስጋው ደሙ መጋባት ይችላሉ እንጂ በስርዓተ ተክሊል ግን መፈጸም አይችሉም ::ምክንያቱም ከዚህ በፊት ስለ ጋብቻ ባስተላለፍነው ትምህርት ስርዓተ ተክሊል የሚፈፀምላቸው ተጋቢዎች ሁለቱም በድንግልና ህይወት ፀንተው ከቆዩ በኋላ ነው፡፡ ለተጨማሪ ማስረጃ ከዚህ በፊት የስርዓተ ጋብቻ ዙሪያ የፃፍነውን ትምህርት ከዚህ በታች መመልከት ይቻላል ::

….
ከዚህ በፊት የተጠየቀ ጥያቄ:—

ስለ ጋብቻ ለጠየቁ አባላችን የተሰጠ አጭር ምላሽ፦

ሚስጥረ ተክሊል የሚፈጸምላቸው ተጋቢዎች በሃይማኖትና በምግባር ጸንተው በድንግልና ሕይወት ለተገኙ ሙሽራውና ሙሽራይቱ ብቻ ነው። ሚስጥረ ተክሊልም ለአንድ ሰው አንድ ጊዜ ብቻ የሚፈፀም ስርአት እንጂ አይደጋገምም። ሚስጥር የተባለበት ምክንያቱም ባልና ሚስት አንድ የሆኑበት ስርዓት ስለሆነ ነው። በጥንተ ተፈጥሮ ሴት የተገኘችው ከወንድ በመሆኑ “ይቺ አጥንት ከአጥንቴ ስጋዋም ከስጋዬ ናት” ተብሎ ሄዋን ከአዳም እንደተገኘችና አንድዋ ሄዋን ለአንድ አዳም እንደተፈጠረች ቅዱስ መፅሐፍ ያስረዳል። ዘፍ 2፤24

በስርአተ ተክሊል ጋብቻቸውን የሚፈፅሙ ጥንዶች ሁለቱም በድንግልና ጸንተው የኖሩ ለመሆናቸው በእግዚአብሔር ፊት ቀርበው ለንስሐ አባታቸው እራሳቸውን ሲያስመረምሩ ብቻ ነው። ከሁለት አንዳቸው ከስርዓተ ተክሊል በፊት ድንግልናቸውን ሊያሳጣ የሚችል ጥቃት ከፈፀሙ በቅዱስ ቁርባን አንድ ሊሆኑ ይችላሉ እንጂ የክብር አክሊል መቀዳጀት የሚችለው በድንግልና ሕይወቱ ጸንቶ የተገኘ ብቻ ነው። ምክንያቱም ስርአተ ተክሊል ማለት በቤተክርስቲያን ውስጥ በካህናት አባቶቻችን የተለየ የክብር ልብስ ሲለብሱ፣ በራሳቸው ላይ የክብር አክሊል ሲቀዳጁ፣ የሚፈፀምላቸው ስርአተ ፀሎት፣ በካህኑ የሚቀቡት የተቀደሰ ቅባት፣ የቃልኪዳኑ ምልክት የሆነው ቀለበት፣ በመጨረሻም ሁለቱም አንድ የሚሆኑበትና የአንድነታቸው ማሰርያ የሆነውን ቅዱስ ቁርባን ሲቀበሉ ነው። ይህ ደግሞ ታላቅ ሚስጥር ስለሆነ እግዚአብሔር ላደለው ሰው በፍፁም መንፈሳዊ ሕይወት ፈሪሃ እግዚአብሔር ኖሮን በምክረ ካህን ንስሐ ተቀብለን ከሰራነው ነውራችን አንዱንም ነገር ሳንፈራና ሳንደብቅ ግልፅ ሁነን የምንፈፅመው ስርዓት ከሆነ ኑሯችን፣ ትውልዳችን፣ ስራችን፣ ጤናችን፣ ሁሉ የተቀደሰና የተባረከ ይሆናል። ጋብቻ ቅዱስ ነው የተባለውም በዚህ ነው። ቅዱስ ጋብቻን የባረከው እግዚአብሔር አምላካችን ነው። ምክንያቱም አዳምና ሄዋንን ሲፈጥር አንድ ወንድን ለአንዲት ሴት ፈጥሮ ያጣመረ እሱ ነውና። በጣና ዘገሊላ በተደረገው የሰርግ ቤት ተገኝቶ ጋብቻን እንደባረከ ወንጌላዊ ዩሐንስ ነግሮናል። (ዩሐ 2፤1-11 እብ13፤4 ኤፌ 5፤31 እና 32)

ለጋብቻ የሚደረገው ጥንቃቄ የአንድ ትውልድ፣ ያንድ ታሪክ፣ ያንድ መንደር፣ ያንድ ሃገር የመነሻ መሠረት ስለሆነ ነው። ስለዚህ ጋብቻ በቅዱስ መፅሓፍ ሰፋ ያለ ታሪክ ያለው ቢሆንም ለጠየቁን አባላችን በመጨረሻ እንዲገነዘቡ የምንፈልገው የስርአተ ተክሊሉ አፈፃፀም ከ ሁለት አንዳቸው ከጋብቻ በፊት በተለየ ስህተት ፈተና ላይ የወደቁ ከሆነ በድንግልና ፀንቶ የቆየው የክብር አክሊል ሲደረግለት ሌላው ግን ንስሐውን በቀኖና ከፈፀመ በኋላ አብረው ስጋውና ደሙን በተቀበሉ ጊዜ አንድ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። በዚህ አይነት ስርዓት ጸንተው እንዲኖሩም ቤተክርስቲያን በፍቅርና በአንድነት ቃል ታገባባቸዋለች። ከዚህ በላይ መረዳት የሚፈልጉት ነገር ካለ በውስጥ መስመር ሊያገኙን ይችላሉ።

 ጠያቂያችን ክርስቲያን መሆን በራሱ በጥንቃቄና በማስተዋል የሚጓዙት ስለሆነ በተቻለ መጠን ለቅዱስ ቁርባን እራሷን የዘጋጆች እንዲት ክርስቲያን በየወሩ ከሚመጣው የሴቶች ልማድ ነፃ የምትሆንበትን ጊዜ አስባ መሆን አለበት። ይሄንንም ጥንቃቄ አድርጋ ባልተጠበቀና ባልተለመደ ሰዓት ይህ ፈተና ቢከስት የፕሮግራሙ ስርዓተ ተክሊልም ይሁን ያለ ተክሊል የሚፈፀም ቁርባንም ቢሆን ከቤተክርስቲያን አባቶች ጋር በመመካከርና ለችግሩ ሲባል ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ መያዝ እና በሌላ ቀን ስርዓተ ቁርባንን መፈጸም ይገባል እንጂ አንድ ግዜ የተያዘ ቀጠሮ ነው በሚል ቅዱስ ቁርባንን በመድፈር የሚፈፀም ስርዓት እንዳልሆነ ማስተዋል ያስፈልጋል። በክርስቲያኖች የህይወት ጉዞ ውስጥ የፈተና መስናክልን የሚያመጣ አሰናካይ የሆነው ጠላታችን ዲያብሎስ ከሱ ወጥመድ አምልጠን ወደ እግዚአብሔር ህብረት ውስጥ እንዳንገባበት እና በናፍሳችንም የዘለአለም ህይወት እንዳንወርስበት ቀናተኛና ምቀኛ ጠላት ስለሆነ በጊዜውም ያለጊዜውም በሚያመጣብን ጥቃቅንና ከባድ ፈተና ተሸንፈን ሳንወድቅ በክርስቲያናዊ ስነምግባር ፀንተን በአላማችን ፀንተን ቆመን ልናሸንፈውና ድል  ልንነሳው ይገባናልና ጠያቂያችንም እርስዎ የጠየቁትን የሚመስል ፈተና ቢያጋጥምዎ ከላይ በሰጠነዎት ምክር መሰረት ፈተናውን ማለፍ እንደሚችሉ ምክራችንን እንለግሳለን።

 በቅዱስ ጋብቻ የተጋቡ ባልና ሚስት አንድ አካል ስለሆኑ፤ በነፍሳቸው ስለሆነ ጉዳይና ጥያቄ የሚያደርጉትን በጎ ነገር ሁሉ በሃሳብ ሳይለያዩ ቢፈጽሙት ከምንም በላይ የተቀደሰ ተግባር ነው። እንኳንስ ለመንግስተ ሰማያት የሚያበቃቸውን ንስኀ በመቀበል ይቅርና በሥጋዊ ኑሯቸውም ባል  ለሚስቱ ሚስትም ለባልዋ የሚያቀርቡት ሂሳብ የኑሯቸውን መሰረት የሚያፀናው ከሆነ እየተናበቡና እየተማከሩ መቀጠላቸው አስፈላጊ ነው። የንስኀ አባት የተባሉት ካህንም እንደኛው ንስኀ ልግባ ሲል ሌላው ደግሞ ፈቃደኛ የማይሆንበት ምክንያት ካለ ወደ ህይወታቸው ጠልቀው በመግት አባታዊ ምክር እና ተግሳፅ በመስጠት ወደ አንድ መንገድ ሊያመጧቸውና ሊያስማሟቸው እንዲችሉ የማድረግ መንፈሳዊ ግዴታ አለባቸው :: እንኳንስ ሚስት ንስኀ እንግባ  በማለት ጠይቃ ይቅርና፤ ራሱ ካህኑ የነፍስ አባት የተባለበት ዋናው ምስጢር ጠዋት ማታ በናፍሳቸው ጉዳይ ላይ ክትትል በማድረግ በመካከላቸው ለሚያጋጥመው ፈተና በትምህርትና በምክር እያስተካከሉ ለንስኀ ሕይወትና ለቅዱስ ቁርባን ያበቋቸው ዘንድ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው። 
 
በዚሁ መሰረት ጠያቂዎችን የኑሮ አጋርዎ የሆኑት ባለቤትዎ ንስኀ  አልገባም ካሉ  ካህኑም ንስኀ  ግቡ ብሎ ከመምከር ይልቅ ባልሽ ካልመጣ ንስኀ አልሰጥም ካሉ፤ እርስዎ የሚጠበቅቦትን ስላደረጉ በግልዎ ንስኀ መግባት ይችላሉ። የንስኀ አባትም ቢሆን ቀይረው መያዝ አለብዎት። በእርግጥ ከቤተሰብ ጋር ያለዎች የኑሮ መሰረት በዚህ ምክንያት እንዳይፈተንና ሰይጣንም መንገድ እንዳያገኝ ተጨማሪ ምክር እንድንሰጥዎ በውስጥ መስመር በላክንልዎ ቁጥር ደውለው ሊያማክሩን ይችላሉ። 
ለሁሉም ነገር የእግዚአብሔር አጋዥነት ከእርሱዎ ጋር ይሁን።

መልስ፦ጠያቂያችን እንዳሉት ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ከተራክቦ ወይም ከግንኙነት ለስንት ሰአታት መራቅ እንዳለባቸው እና ከቀረቡም በጓላ ለስንት ሰዓታት መታገስ እንዳለባቸው ከዚህ በፊት መልዕክት ማስተላለፋችንን እናስታውሳለን። ይሁን እንጂ አላማችን ለእናንተ የሚያስፈልገውን ትምህርት በየጊዜው ተደራሽ እንዲሆን ስለሆነ አሁንም ቢሆን እርስዎ እንደገለፁት እሁድ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ከሐሙስ በኋላ ያሉትን ቀናት ማክበር አለብን። ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ብቻ ሳይሆን ወደ ቤተከርስቲያን ገብቶ ለመፀለይና ለመሳለምም ሩካቤ ስጋ አድርጎ መሄድ አይፈቀድም። ምናልባት እንደተባለው የተለመደ የዘወትር ፀሎታችንን በቤታችን አካለ ስጋችንን ታጥበን በፀሎት ቤታችን ቆመን ማድረስ እንችላለን ወይም ወደ ቤተክርስቲያን ሄደን ከመግቢው ቅጽር ሆነን መፀለይ እንችላለን።  

ስለመንፈሳዊ ወይም ስለ ክርስቲያናዊ ህይወት ከባልና ሚስት አንዱ ጥንካሬ ካለው ማሸነፍ ያለበትና ተቀባይነት ያለው የሃይማኖቱና የነፍሱን ጉዳይ ተቀዳሚ እና ተፈፃሚ መሆን ያለበት መሆን አለበትና ጠያቂያችን ሃሳቡን በዚህ እንዲረዱት እንመክራለን።

በመጨረሻም ከዚህ በፊት ከደረሱን ተመሳሳይ ጥያቄዎች ተነስተን ያስተላለፍናቸውን መልዕክቶች እንዲመለከቱ ከዚህ በታች ልከንልዎታል።

  በማንኛውም ግዜ የፆም የፀሎት ሱባኤ በራሳችንም ይሁን በአባቶቻችን ቀኖና ተሰጥቶን የፆምና የፀሎት ሱባኤ በያዝን ግዜ፣ በእለተ ሰንበት እና በታወቁ በአላት ቀን ፈፅሞ ሚስትም ከባልዋ ተለይታ ወንድም ከሚስቱ ተለይቶ መኝታቸውንም የተለየ አድርገው የሚበላውንም የሚጠጣውንም ከተለመደው የአመጋገባቸው ስርአት ቀንሰው አጠቃላይ ፈቃደስጋቸውን ተቆጣጥረው ነው መፆም የሚገባቸው። ፆም ራሱን የቻለ ከእግዚአብዜር ጋር የምንገናኝበት የፅድቅ መንገድ ስለሆነ በዚህን ግዜ ማንኛውም ክርስቲያን የስጋ ፈቃዱን መቆጣጠር እንዳለበት የቤተክርስቲያን ቀኖና ይደነግጋል። ይህን ስንል በቀኖና የተደነገጉ 7ቱ አፅዋማትና እንደገናም በአባቶቻችን ሱባኤ ተሰጥቶን የምንፆምባቸው አፅዋማትን ይመለከታል። ይሁን እንጂ ከአቅም በላይ በሆነ ፈተና ፈቃደስጋችን አሸንፎን በዚህ ምኞት ከወደቅን ላጠፋነው ጥፋት የህሊና ፀፀት ተፀፅተን ለንስሐ አባታችን ወደፊት የምንነግረው ሁኖ ፆምና ፀሎትን ሳናቋርጥ እስከመጨረሻው ልንፈፅም ይገባናል።

ጠያቂያችን የቤተክርስቲያንን ቀኖና እና ስርዓት ለማክበር ብለው ለመረዳት መጠየቅዎ አግባብ ነው። ምክንያቱም “የእግዚአብሔርን ቃል አባትህን ጠይቀው እውነቱንም ይነግርሃል” ይላልና። በመሰረቱ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ወደ ቤተመቅደስ ተጠግተን ለማስቀደስ 3 ቀን ከስጋ ስርዓት እንድንርቅ የሚደረግበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስለኛ በተቀበለው መከራ በእለተ አርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ስጋው ለይቶ 3 መአልትና 3 ለሊት በከርሰ መቃብር ውስጥ ቆይቷል። በዚህም ምክንያት ቅዱሳን ሐዋሪያት እና ከሱ ጋር ይከተሉት የነበሩት ደቀመዛሙርት የጌታን ትንሳኤ ሳናይ የሚበላ አንበላም የሚጠጣም አንጠጣም ብለው በፆም ተወስነው ስለቆዩ ነው። ስለዚህ ዛሬም የምንቀበለው ቅዱስ ቁርባን የክርስቶስን አማናዊ ስጋና አማናዊ ደም ስለሆነ ያንን መነሻ አብነት አድርገን ለ 3 ቀናት ንፅህናችንን እና ቅድስናችንን ጠብቀን የምንቆየው ነው።

 

 

በመሆኑም ህግ እና ቀኖና የሆነውን ነገር በህግነትና በቀኖናነቱ የተወሰነውን እውነቱን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ በደካማ ስጋችን ተፈትነንና ስጋዊ ምኞት አሸንፎን ቀኖናን የሚሽር ስህተት ፈፅመን ብንገኝ ወይም ደግሞ ከ 3 ቀን ባነሰ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ጠያቂያችን ያነሱትን ስህተት ፈፅሞ ቢገባ ያ ክርስቲያን ፈፅሞ የተወገዘ የተረገመ ነው ማለት አይደለም። የቤተክርስቲያን ስርዓት እና ቀኖና በመሻሩ ተግሳፅና ምክር ሊሰጠው ይችላል። ወደፊት እያወቀ እንዲህ አይነት ጥፋት እንዳትፈፅም ተብሎ ምክር ይሰጠዋል። ይሄ የሚሆነው በህጋዊ ጋብቻ ተወስነው ለሚኖሩ ነው። ከዚህ ውጭ ለሚሆነው ግን እንኳን ቤተክርስቲያን በድፍረት ለገባንበት ይቅርና ከሕግ ውጭ ላደረግነው ግንኙነትም ከባድ የቀኖና ቅጣት ይጠብቀዋል። በዚሁ መሰረት ጠያቂያችን ቀኖና ባለመሻር እና ከእግዚአብሔር በረከት ለማግኘት በምናደርገው መንፈሳዊ አገልግሎት በነፍስ የምንጎዳበት እርግማን እንዳያመጣብን ከወዲሁ ክርስቲያናዊ ስነምግባር እና ጥንቃቄ ሊኖረን ይገባል በማለት መልዕክታችን እንዲደርስዎት አድርገናል።

ጠያቂያችን በመጀመሪያ ከዚህ በፊት ከደረሱን ተመሳሳይ ጥያቄዎች ተነስተን ያስተላለፍናቸውን መልዕክቶች እንዲመለከቱ የላክንልዎትን ሃሳቡን እንደመነሻነት አንብበው እንደተረዱት እናምናለን። አሁንም ወደ እርስዎ ጥያቄ ስንመጣ በዋነኝነት መረዳት ያለብን፤ ማንኛውም ወንድም ሆነ ሴት ክርስቲያን  ከጋብቻ በፊት ቃልኪዳን  ገብተው እያሉ ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድላቸውም። ምክንያቱም ከጋብቻ በፊት የሚደረገው የግብረስጋ ሩካቤ እንደ ቤተክርስቲያን ቀኖና ስንመለከተው በዝሙት መንፈስ የተፈፀመ ግንኙነት እንጂ በስርአተ ቤተክርስቲያን የተፈቀደ አይደለም። ስለዚህ ከጋብቻቸው በፊት ገና በቃል ኪዳን በመተሳሰብ እያሉ የስጋ ሩካቤ ካደረጉ በየግላቸው መቁረብም መቀበልም የለባቸውም። ስለፈፀሙት ስህተት በአንቀፀ ንስኅ መሰረት ንስኅ ገብተው ከግብረ ስጋ ግንኙነት እርቀው የጋብቻቸው እለት ቅዱስ ቁርባን መቀበል ይችላሉ። ስለዚህ ጠያቂያችንም ከጋብቻ በፊት እንዲህ አይነት ስህተት ፈፅመው ከሆነ ወደ ንስኅ አባትዎ ቀርበው በመመካከር ተገቢውን ቀኖና መቀበል አለብዎት በማለት ይህን አጭር መልዕክት ልከንልዎታል።

ጠያቂያችን ምናልባት የእርስዎ ችግር ከመንፈሳዊ አንፃር ስንመለከተው ጥንተ ጠላታችን ዲያቢሎስ የመልካም ነገር ሁሉ ጠላት ስለሆነ ወደ ወደ አሰቡት የትዳር ህይወት እንዳይገቡ የሚያደርግ መሰናክል እያስቀመጠ የእርስዎን ልቦና እንዳይረጋጋና ውሳኔ ላይ እንዳይደርሱ የሚያደርግ ሃይል ስላለው በኛ በኩል እንደመፍትሄ ሃሳብ አድርገን የምንመክርዎት በቤተክርስቲያናችን አስተምሮ መሠረት ቢችሉ በተረጋጋ መንፈስ ሆነው ከእግዚአብሔር ጋር እንዲነጋገሩ ወደ ገዳም በመሄድ ያለብዎትን ችግር ለአባቶች ግልፅ በማድረግ ቢያንስ የ አንድ ሱባኤ ጊዜ ይዘው ፀበል እየተጠመቁ፣ እየፆሙ፣ እየሰገዱ፣ በአባቶች እጅ መስቀል እየተዳበሱ፣ ቅባ ቅዱስም እየተቀቡ ሱባኤውን ቆይተው ቢመለሱ ይሄ እርኩስ መንፈስ ከእርስዎ ተለይቶ ሊጠፋ ይችላል።  ይህን ማድረግ ካልቻሉ ደሞ እኛን በውስጥ መስመር ያነጋግሩንና በምንሰጥዎት ምክርና ትምህርት ከዚህ ፈተና የሚወጡበትን መንገድ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ልናሳይዎት እንችላለን። በአብዛኛው እንዲህ አይነት ችግሮች ከሰይጣን ውግያ የተነሳ ብቻ ሳይሆን እኛም ራሳችን በራሳችን ምክንያቶች የምንሆንበት መንገድ ብዙ ስለሆነ በራሳችን ቆራጥ ህሊና ወስነን በሃይማኖታችን እና በስነምግባራችን ፀንተን ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ሃይል እንደምናሸንፍ እርግጠኞች ስንሆን እንደ ድንጋይ የከበደውና አዚም የሆነብን ሁሉ ከኛ ፈፅሞ ስለሚርቅ ይህን የሰጠነዎትን መክረ ሃሳብ እንዲጠቀሙበት አደራ እንላለን።

መልስ፦ጠያቂያችን እንዳሉትም በአፇማት እና  የበዓል ቀናት ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ከሩካቤ ስጋ መጠበቅ እንዳለብን የቤተክርቲያን ቀኖና ይደነግጋል። እንዴት ማክበር እንዳለብን በሚመለከት፦

1ኛ/ ስለአፇማት፦ ለምሳሌ ሮብ ለመፆም ማክሰኞ ለሮብ፣ ሐሙስ ለአርብ መታቀብ አለብን ማለት ነው።

2ኛ/  ሌሎችን የአዋጅ ፆም በሚመለከት ፦ ወንዱ ከሴቷ፣ ሴቷም ከወንዱ እርቃ በሱባኤ ተለይቶ ማሳለፍ እንዳለብን የቤተክርስቲያናችን ቀኖና ያዛል። ይሁን እንጂ ከአቅም በላይ በሆነ ፈተና ፈቃደስጋችን አሸንፎን በዚህ ምኞት ከወደቅን ላጠፋነው ጥፋት የህሊና ፀፀት ተፀፅተን ለንስሐ አባታችን ወደፊት የምንነግረው ሁኖ ፆምና ፀሎትን ሳናቋርጥ እስከመጨረሻው ልንፈፅም ይገባናል።

3ኛ/ በአላትን በሚመለከት እለተ ሰንበት፣ የእመቤታችን በዓል፣ የባለቤቱ የጌታችን የመድኅኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በአላት ፣ እና ሌሎችም ታላላቅ የታወቁ በዓላት ከዋዜማቸው ጀምሮ ከሩካቤ እርቀን ማክበር አለብን።

በተጨማሪም ወደ ቤተክርስቲያን ሄዶ ለመቁረብ ወይም ለማስቀደስ ከዚህ በፊ ስለ ቅዱስ ቁርባን መደረግ ስለሚገባው ጥንቃቄ ባስተላለፍነው ትምህርት ለ 3 ቀናት ንፅህናችንን እና ቅድስናችንን ጠብቀን መቆየት እንዳለብን ማብራራታችንን እናስታውሳለን። ስለዚህ በዚህና በሌሎች ጥያቄዎች  ዙርያ ያስተላለፍናቸውን መልእክቶች ከድረገጻችን በመመልከት ተጨማሪ ትምህርት  እንዲያገኙበት ከዚህ በታች ሊንክ ልከንልዎታል።

https://yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ/

መልስ # 1፦  ስለጋብቻ የጠየቁት አባላችን በቅዱስ ቁርባን የተመሰረተ ጋብቻ በሥጋዊ ጉዳዮችም ሆነ በመንፈሳዊ ህይወታችን ከፍተኛ ጥቅምና በረከት ስለሚያሰጠን ሁሉም ሰው ጋብቻውን በቅዱስ ቁርባን ቢፈፅም መልካም እንደሆነ ቤተክርስቲያናችን እና የቤተክርስቲያን ሊቃውንት ያለማቋረጥ ያስተምራሉ ነገር ግን ብዙ ሰዎች እንዳንዶቹ ሳይገባቸው አንዳንዶቹም እያወቁ መንፈሳዊ ጋብቻን ችላ ብለው ወይም ክብር የሚቀንስባቸው ስለሚመስላቸው በስጋዊ ስርዓት ጋብቻቸውን ይፈፅማሉ። ሆኖም ግን እነዚህም ቢሆኑ እንደ እርኩስ ነገር ሳይቆጠርባቸው ወደፊት በንስኀ አባትና በቤተክርስቲያን ሊቃውንት ተመክረው አላማው ገብቷቸው የትዳር ህይወታቸውን በቅዱስ ቁርባን ማተም ይችላሉ እንጂ ያለቅዱስ ቁርባን የተፈፀመ እንደትዳር አለመቁጠርን ወይም በግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ አድርጎ በማሰብ እያጥላላን ይባስ ብሎ ከእግዚአብሔር የሚርቁበት ምክንያት መሆን ግን አይገባምና በዚህ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

መልስ # 2፦ ለትዳር የተጫጩ ወንድና ሴት ጋብቻቸውን ከመፈፀማቸው በፊት የሚያደርጉት ግንኙነት እንደቤተክርስቲያን አስተምሮ የዝሙት ሃሳብ ነው። ምክንያቱም አንድ ሆነው ማንኛውንም የጋራ ህይወታቸውን ለመቀጠል ጋብቻቸውንም በአዋጅ በአደባባይ ለማስታወቅ በመንገድ ወይም  በቀጠሮ ላይ እያሉ ያንን ቀጠሮ ማክበር አቅቷቸው ፍትወተ ስጋቸው አሸንፏቸው የሩካቤ ስጋ ቢፈፅሙ ግን እንደ ዝሙት ይቆጠራል።   ስለዚህ የጥፋቱ መጠን ታይቶ በንስኀ አባታቸው የንስኀ ቀኖና እና ቀጣይ ምክርና ትምህርት የሚሰጣቸው ይሆናል ማለት ነው።

መልስ # 3፦  በእጮኝነት ያሉ ሁለት እጮኞች አንዳቸው በቅዱስ ቁርባን እንጋባ ሲሉ ሌላው ደግሞ አይሆንም ካለ የመጀመሪያው አማራጭ በቤተክርስቲያን አባቶች ትምህርት  እና ምክር ማግኘት ነው። ትምህርት ተሰጥቶ የቅዱስ ቁርባንን ጥቅምና የዘለዓለማዊ ህይወት ሰጭነትን በደንብ እንዲያውቅ ተደርጎ የህንንም ሁሉ እየወቀ ቅዱስ ቁርባኑን በማቃለል አልፈልግም ካለ እንደ ክህደት ወይም እንደ ኑፋቄ ስለሚቆጠር ከእንዲህ አይነቱ ወንድ ወይም ሴት ጋር ብዙ ሃላፊነት ወደሚፈልገው የትዳር  ህይወት መግባት እንደእውነቱ ከሆነ አስፈላጊ አይደለም። ምክንያቱም አንደኛው ጻድቅ አንደኛው ኀጢዕ፣ አንደኛው መንፈሳዊ አንደኛው  ሥጋዊ፣ አንደኛው ፍየል ሌላው ደግሞ በግ፣ አንደኛው ጨለማ አንደኛው ብርሃን ሆኖ መኖር እንኳን ለሰማያዊ ህይወት ቀርቶ ለምድራዊ ህይወት ፈተና ስለሚሆን ብዙ ትዕግስት እና ጊዜ በመውሰድ የሚሰጠውን ትምህርትና ምክር በአባቶች በኩል እስከ መጨረሻው በማጠናከር ተሞክሮም በቅዱስ ቁርባን ለመጋባት ፈቃደኛ ካልሆኑልን ግን ጨርሶ በአላማው መስማማት እንደሌለብን ምክር እንሰጣለን።

ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ

ጠያቂያችን፤ የጥያቄዎ ሃሳብ በደንብ ግልፅ ባይሆንም እንኳን ከጋብቻ በፊት በእጮኝነት ወይም በቃል ኪዳን የሚኖሩ ክርስቲያኖች የስጋ ሩካቤ እንዲፈፅሙ አይፈቀድላቸውም። ይህን ድርጊት ከፈፀሙ ግን ቃል ኪዳናቸው በአለማዊ ፀባይ የተፈፀመ እንጂ በመንፈሳዊ ስነምግባር የሚታይ አይሆንም። ስለዚህ ተጫጭተው እያሉ ስርዓተ ጋብቻ ሳይፈፅሙ የስጋ ግንኙነት ወይም የስጋ ሩካቤ ካደረጉ በቀጥታ ወደ ንስኅ አባታቸው ሄደው በመናዘዝ በአንቀፀ ንስኅ በታዘዘው መሰረት የቀኖና ቅጣት ተቀብለው ተገቢውን ስርዓት መፈፀም ይገባቸዋል። ማንም ሰው ስለሰራው ኅጢአት ከልቡ ተፀፅቶ ንስኅ የገባ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የኅጢአትን ስርየት እንደሚየገኝ ማመን አለበት። ሁሌም የክርስቲያናዊ ፀባይ መሆን ያለበት የመጀመሪያውና ዋናው ኅጢአት ላለመስራት መቆጠብ ነው፤ ኅጢአቱን እስካደረግነው ደግሞ ግን በንስኅ ህይወት ኅጢአትን ማስፋቅ አስፈላጊ ነው። በዚህ አላማ ደግሞ የእኛን ኅጢአት ለመፋቅና ይቅር ለማለት እግዚአብሔር የታመነ አምላክ ነው። ስለዚህ ጠያቂያችን ማድረግ ያለብዎትን በዚህ እንዲረዱት ይህን አጭር መልዕክት ልከንልዎታል። 

ከትዳር አጋርዎ ጋር በተከሰተው አለመግባባት ምክር እንድንሰጥዎ የጠየቁን አባላችን፤ በሰው ልጅ የህይወት ጉዞ ውስጥ የማያጋጥም ፈተናና ችግር የለም። በእርግጥ በመካከላችሁ ያጋጠማችሁን ፈተና ስንሰማ በእኛም በኩል እንደመንፈሳዊነት ስናየው አሳዛኝ ገጠመኝ ነው። ነገር ግን ጠያቂያችን ጉዳዩን በትዕግስትና በአፅንዎት መመልከት ያለብዎት የከፉ ነገር ሁሉ መነሻና መድረሻ የሆነው እርኩስ መንፈስ በየጊዜው በሰው ልጅ ላይ የማያመጣው ፈተና የለምና በእናንተም ላይ የተከሰተው ፈተና አሳዛኝና አስደንጋጭ አድርገን ብናየውም ነገር ግን በሰው ላይ ያልደረሰ አዲስ ክስተት እንዳልሆነ መገንዘብ አለባችሁ። በመካከላችሁ የተፈጠረውን ፈታኝ ክስተት ብቻ በመመልከት ለ10 ዓመታተ ያህል የደከማችሁበት የትዳር ጉዞ ውስጥ የገነባችሁትን ህይወት ባልተጠበቀ ገጠመኝ የተከሰተውን ነገር በማሰብ አፈራርሶ እንዳልነበረ ማድረግ ጉዳቱ በምድራዊ ኑሯችሁ ብቻ ሳይሆን በሰማያዊ ህይወትም ከእግዚአበሔር የሚለይ ፈተና ነው።

ስለዚህ በግላችንም ሆነ እንደ ሀገራዊ ባህላችንና የማህበረሰቡ አመለካከተ ተፅኖ አንፃር በመካከላችሁ የተከሰተውን ችግር ለመሸከም እጅግ ከባድ ቢሆንም እንደ መንፈሳዊ ህይወት በትዕግስት ሁነን ስናስበው ግን ማንኛውም በደልና ጥፋት በትምህርት በተግሳፅ በንስኀ ህይወት አስተካክሎ ለመመለስ እንደሚቻል በማመን ሁለቱም ወገን ሰከን ብለው እስከመጨረሻው ድረስ ሁሉን ነገር ለእግዚአብሔር በመስጠት በይቅርታና በምህረት ማለፍ ይገባናል። እኛ ኀጢአተኞች ስንሆን በእኛም ላይ የደረሰብንን ችግር እንደ ትልቅ ጥቃትና ውርደት ቆጥረን ኑሯችንን ፣የግል ህይወታችንን ፣ የቤተሰብ ህይወታችንን የሚጎዳ ነገር እንዳንፈፅም ምክራችንን እንለግሳለን።

ከሁሉም በላይ የእኛን ህይወት ማንነት የተደበቀውንም ሆነ የተገለጠውን ድክመታችንን የሚያየው አምላካችን ምን ያህል እንደታገሰን ስንመለከት ሁሉን ነገር በትዕግስት እንድንመለከት ያደርገናልና ጠያቂያችን ማድረግ ያለብዎት፦

1ኛ እስካሁን ያሳለፋችሁትን የትዳር ህይወት በማሰብ፣ ደግሞም በእግዚአብሔር ቸርነት ያፈራችኋቸውን ሁለት ህፃናት በማሰብ፣

2ኛ ሰው ሆኖ የተፈጠረ ሁሉ በስህተትና በፈተና የመውደቅ አጋጣሚው ያለና የነበረ ስለሆነ፣

3ኛ እውነተኛ ክርስቲያን በፈጠጠ አይኑ ያየውንና በጆሮው የሰማውን ክፉ ነገር ሁሉ በትዕግስትና በፍቅር የሚያሸንፍ መሆን ስላለበት፣ በተቻለ መጠን እስከመጨረሻው ፀጥታ ድረስ ወደ ቀደመው ህይወታችሁ ለመመለስ በራስዎ በኩል ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አለብዎት። የተከሰተውን ጥፋትም በቤተክርስቲያን አባቶች ትምህርት እና ምክር ተግሳፅና የንስኀ ህይወት በማሰጠት ማስተካከል ይቻላል። የበለጠ ምክር እና ትምሀርት ካስፈለገ በውስጥ መስመር ሊያገኙን ይችላሉ።

ለሁሉም ነገር የእግዚአብሔር አጋዥነት አይለይዎት

ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ

ጠያቂያችን ከትዳር ጓደኛዎ ጋር የደረሰብዎትን ፈተና በሚመለከት ተጨማሪ ማብራሪያና ጥያቄ የላኩልን አባላችን ከሁሉ በማስቀደም እርስዎ እንዲረዱት የሚያስፈልገው በሰው ልጅ የህይወት ጉዞ ውስጥ የማያጋጥም ፈተና እንደሌለ ነው። ብዙ ጊዜ ሰው በዚህ በፈተናው አለም ውስጥ ያጋጠመውን ጊዜያዊና ስጋዊ ፈተና  አስቦ መሸከም ሲያቅተው ከፈጣሪው ጋር እስከመጣላት የሚደርስ ውድቀት ያጋጥመዋል። ይሁን እንጂ እንደ እውነቱ ከሆነ በእርጋታና በክርስቲያናዊ አመለካከት ስናስበው፤ እርኩስ ረቂቅና ስውር የሆነው ጠላታችን ዲያብሎስ ቀርቶ በአይነ ስጋ የሚኖሩ በቅርብ በማህበረሰቡ መሃል በቅርብ አብረውን የሚኖሩ ሰዎች የሚያደርሱብንን ጥፋት ስናስበው ከባድና አሳዛኝ ነው።

ስለዚህ ጠያቂያችን በእርስዎና በቤተሰብዎ የደረሰውም እጅግ አሳዛኝና ፈታኝ ቢሆንም እንኳን ከደረሰብዎ ፈተና የሚወጡበትን የመፍትሄ ሃሳብ በእግዚአብሔር ቸርነትና አጋዝነት አሸንፈውት ወደቀደመው የተረጋጋ ኑሮዎት እንዲመለሱ ማድረግ ይቻል ዘንድ፦

1ኛ በውስጥ መስመር በላክንልዎ ቁጥር ደውለው አግኝተው ቢያናግሩንና ተገቢውን ምክር እንድንሰጥዎ ቢያደርጉ፣

2ኛ በእንዲህ አይነት አሳዛኝ ህይወት ውስጥ የወደቁት ባለቤትዎ በንስኀ አባትም ሆነ በሌላ ሽማግሌ አማካኝነት እኛን ሊያገኙ የሚችሉበትን መንገድ ቢያመቻቹ እግዚአብሔር ቢያግዘን ችግሩ ሊስተካከል ይችላል፣

3ኛ በአስማትም ሆነ በሟርት ተደረገብኝ የሚሉትን ፈተና ለማስወገድ ወደ ቤተክርስቲያን አባቶች ቀርበው ችግርዎን በመናገር ቢያንስ ለአንድ ሱባኤም ቢሆን ፀበል በመጠመቅ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ በማድረግ ከችግሩ ለመውጣት ይችላሉ።

4ኛ ሁልገዜ ሃይላችን እና መፅናኛችን የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ ተከታታይ ትምህርት እና ምክር የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣

5ኛ በግልዎ ዘወትር በቋሚነት የሚፀልዩትን ፀሎት ለይተው ሳያቋርጡ መፀለይ፤

እነዚህን እና የመሳሰሉትን የቤተክርስቲያን አገልግሎት በማግኘት ከችግሩ ፈፅሞ መውጣት ስለሚችሉ ተስፋ ሳይቆርጡ በእምነት ከዚህ በላይ የሰጠንዎትን ስራ ላይ እንዲያውሉ እንመክራለን።

ጠያቂያችን ስርዓተ ተክሊሉ የሚፈፀምበት እለት የሰርግ በዓል ከመከበሩ በፊት ቀድሞ የሰርግ በዓሉ ራሱን የቻለ ቀን ተቀጥሮለት የሚፈፀም እንጂ የተክሊል ስርዓት በተከበረበትና ቅዱስ ቁርባን በተቀበሉበት ቀን መሆን የለበትም። ምክንያቱም በቤተክርስቲያን የሚፈፀመው የስርዓተ ተክሊሉ እና የቅዱስ ቁርባኑ ስርዓት የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ በዓል ስለሆነ ንፅህና ቅድስናን የሚጠይቅና ስጋዊ አሰራር ጋር የማይገናኝ ስርዓት ነው። የሰርግ በዓል የሚከበርበት ስርዓት ደግሞ በባህላዊ ስርዓት ዘመድ አዝማድ የሚጋበዝበት ለዝምድናና ለሥጋ ክብር መገለጫ የሚዘጋጅ ስለሆነ ከመንፈሳዊ ህይወት ጋር የማይጣጣሙ ብዙ ልማዳዊ አሰራሮች ስላሉ እራሱን የቻለ የሰርግ ጊዜ ቀጠሮ የሚቀጠርበት ስርዓት ነው።
 
ይሁን እንጂ ጠያቂያችን ባቀረቡልን ጥያቄ ሃሳብ ቢሆንም እንኳን ለምሳሌ እሁድ እለት የሰርግ በአል ቢፈፅሙ ሮብ 3ኛ ቀናቸው ስለሆነ የግድ የግብረሥጋ ተራክቦ ለመፈፀም የሚያስገድዳቸው ነገር የለም። እንደ ቤተክርስቲያን ስርዓት በአላትም ሆኑ አፇማትም የሚከበሩበት እለት ከሆነ በክርስቲያናዊ ስነምግባር ፀንቶ የሚኖር አማኝ በነዚያን ቀኖች ራሱን ከማንኛውም የሥጋ ውድቀት መጠበቅ ይገባዋል። 
 
ስለዚህ ራሳችንን ከሥጋዊ ግንኙነት የምንጠብቅባቸው በአላትና የአፇማትን ለይተን ካወቅን በዚሁ አሰራር መሰረት መመራት አለብን እንጂ ጥቃቅን ምክንያቶችን እንደ ከባድ ነገር በመቁጠር እና ጥያቄ እያነሳን እራሳችንን ወደማይሆን አቅጣጫ እና ዕርቀት መምራት እንደሌለብን እንመክራለን።

 ጠያቂያችን ባለቤትዎ በንስኀ ህይወት እራሳቸውን በማዛጋጀት ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ፈቃደኛ መሆናቸውና እርስዎንም ወደ ንስኀ ህይወት እንቅረብ  በማለት ምክር ማቅረባቸው እጅግ የሚያስደስትና ከአንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን የሚጠበቅነው። ይሁን እንጂ በእርስዎ በኩል ወደ ንስኀ እና ወደ ቅዱስ ቁርባን ህይወት መብቃት ፈልገው ለመቅረብ ያልቻሉበት ምክንያት ከላይ እንደገለፁት ጥቃቅን ምክንያቶችን እያሰቡ በመፍራትዎ እንደሆነ ስለሚያሳይ ስጋዊ የሆነው አስተሳሰባችን የነፍስ ጉዳይን ፈፅሞ የሚጎዳ ስለሆነ ሁሉን ነገር እርግፍ አርገው በመተውና ሥጋዊ ፍርሃቶትንም በማስወገድ ለመንፈሳዊ አባትዎ ወይም ደግሞ ለዚሁ ጉዳይ አምንባቸዋለው የሚሏቸውን የቤተክርስቲያን አባት በማማከር ለአንዴ እና ለመጨረሻ አለኝ የሚሉትን ንስኀዎትን በዝርዝር በመናዘዝ ምክርና ትምህርት የሚያስፈልገውም ሆነ የንስኀ ቀኖና የሚያስፈልገውን ከንስኀ አባት መቀበል አለቦት። ስለዚህ በእግዚአብሔር ፈቃድ ከእኛ ጋር ለመገናኘት ስለበቁ ይህንን ለመናገር የተሳቀቁበትን ምስጢሮትን በውስጥ መስመር በሚላክልዎት አድራሻ ደውለው እኛ ጋር ተነጋግረው አስፈላጊውን ትምህርት እና የምክር አገልግሎት ልንሰጥዎ እንደምንችል እንገልፃለን።

 ጠያቂያችን ወደ ሴቶች በቀረቡ ጊዜ ቀድሞ የዘር መፍሰስ ልምድ ያጋጥመኛል ያሉት ጥያቄ ሃሳቡን ለቤተክርስቲያን መምህራን ወይም ለመንፈሳዊ አባቶች ለማማከር መምረጥዎ እጅግ የሚያስደንቅዎ ቢሆንም ፤ ወደ ዋና ሃሳብዎ ስንገባ ግን በመጀመሪያ ወደ ሴት ስቀርብ ያሉት አገላለፅ ከህጋዊ የትዳር ጓደኛ ጋር ከሆነ ብቻ ነው በእኛ በኩል እንደትክክለኛ ጥያቄ የምንቆጥረው። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ከዝሙት ሃሳብ ከብዙ ሰዎች ጋር መሄዱ እንዲህ አይነት ሁኔታ ማጋጠሙ ስጋዊ ጠባይ ቢሆንም እንደ መንፈሳዊ ግን እጅግ የተከለከለ ነው። ስለዚህ እርስዎ ከህጋዊ ጋብቻ ጋር ይህ ችግር እንዳጋጠመዎት በማመን ብቻ የመንሰጥዎ ምላሽ ይሆናል ማለት ነው።
 
እርኩሳን መናፍስት ከሰው በከፋ ሁኔታ ቀናተኛ እና ምቀኛ በመሆናቸው የሰውን ልጅ በተለያየ ጠባይ ይቆራኙታል። ከሰዎች ጋር መቆራኘታቸውንም እራሱ ባለቤቱ ያማያውቀው ነገር ግን በህይወቱ የሚያስተውለው ችግሩ ጎልቶና ተደጋግሞ ሲደርስበት ብቻ ነው። ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የሰው ውጊያው ከስጋዊያን እና ከደማዊያን ጋር ሳይሆን ከረቂቃን መናፍስት ጋር እንደሆነ በመልዕክቱ የገለፀልን።
 
በቅዱስ ወንጌል እንደተፃፈ ማርያም መግደላዊት በተባለችው ሴት ላይ 7 አጋንንት ሲያድሩባት  ሰባቱም የተለያየ የ 7 ኀጢአት ያሰሯት እንደነበረ ቅዱስ ወንጌል ይነግረናል። ስለዚህ አጋንንት ከቁጥራቸው የክፋት ስራቸው በእኛ ህይወት ላይ ሲሰለጥኑ የተለያየ የክፋት ስራቸውን ያሰራሉ። በሴት የሚመሰሉ አጋንንት የሴት ስራ ያሰራሉ፣ በወንድ የሚመሰሉ አጋንንት የወንድ ስራ ያሰራሉ። ብቻ በምርምርና ቁጭ ብሎ እንደ ሂሳብ በስሌት የማይደረስበት ስፍር ቁጥር የሌለው የክፋት ስራ አላቸውና እርስዎ ከዚህ ክፉ መንፈስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይድኑ ዘንድ ጉዳዩን በዝርዝር ከተረዳን በኋላ የመፍትሄ ሃሳብ የሚሆን ምክር እንድንሰጥዎ በውስጥ መስመር በሚላክልዎት አድራሻ እንዲያገኙን ሆኖ ፤ እስከዚያው ድረስ ግን በሚችሉት አቅም ፀሎት መፀለይ አለብዎት፤ ቢችሉ ድርሳነ ሚካኤልን፣ ወንጌለ ዮሐንስን፣ ውዳሴ ማርያምን፣ ዳዊትን ቢፀልዩ ፣ እንዲሁም ለተወሰነ ለአንድ ሱባኤም ቢሆን ይህንኑ ችግርዎትን ለካህን ነግረው ቢጠመቁና ሁሌም ከእርስዎ የማይለዩ ፀሎት መፃህፍትን እና መስቀልን መያዝ ቢያዘወትሩ በዚህ ሁሉ ያለውን ለውጥ በገሀድም ቢሆን ወይም በራእይ መልክ ምልክት ሊያዩበት ይችላሉ። በዋነኝት ግን እኛን ማግኘት ቸላ እንዳይሉ እንመክራለን።
ጠያቂያችን ለቋሚ ህይወት እና ለዘላቂ ፍቅር ማሰቡ መልካም ስለሆነ ከወዲሁ ማስተዋሉ አስፈላጊ ስለሆነ ጥያቄዎ ተገቢ ነው። ይሁን እንጂ እኛ በትምህርት እና በምክር አይነት ጥያቄዎን በደፈናው ከመመለሳችን በፊት እርስዎ በውስጥ መስመር አግኝተውን በእኛም በኩል የእግዚአብሔር ፈቃድ እስከሚሆን ድረስ ፤ በሰው ልጅ መካከል የሚፈጠሩት ችግሮች ምን አይነት መልክ እና ቅርፅ እንዳላቸው ከልምድ ተሞክሯችን የተገነዘብነውን ያህል በማመዛዘን፤ በእናንተም መካከል ስለተፈጠረው ችግር ከሚሰጡን ምላሽ ተነስተን የመጨረሻ መፍትሄ ለመስጠት በእኛም በኩል የምናቀርብልዎት ጥያቄዎች ስለሚኖሩ እና ከእርስዎ መረዳት ያለብን ተጨማሪ ሃሳብ ስለሚኖር፤ ይሄንን መልዕክታችንን ተቀብለው ሳይጨናነቁና ተስፋ ሳይቆርጡ ያነጋግሩን በማለት ይህን አጭር ምላሽ ልከንልዎታል። 
 
መልስ፦ ጠያቂችን   ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦልን የሰጠነውን ምላሽ ልከንሎታልና ይህን አንብበው ሃሳቡን ይረዱት። 
 
1. ተጠይቆ የነበረው ጥያቄ ፦ ለትዳር የተሳሰቡ እና ተወስነው የሚኖሩ ጥንዶች ከመጋባታቸው በፊት ግንኙነት ቢጀምሩ እንደ ዝሙት ይቆጠራል ወይ?
 
የተሰጠው ምላሽ፦  ፦ ለትዳር የተጫጩ ወንድና ሴት ጋብቻቸውን ከመፈፀማቸው በፊት የሚያደርጉት ግንኙነት እንደቤተክርስቲያን አስተምሮ የዝሙት ሃሳብ ነው። ምክንያቱም አንድ ሆነው ማንኛውንም የጋራ ህይወታቸውን ለመቀጠል ጋብቻቸውንም በአዋጅ በአደባባይ ለማስታወቅ በመንገድ ወይም  በቀጠሮ ላይ እያሉ ያንን ቀጠሮ ማክበር አቅቷቸው ፍትወተ ስጋቸው አሸንፏቸው የሩካቤ ስጋ ቢፈፅሙ ግን እንደ ዝሙት ይቆጠራል።   ስለዚህ የጥፋቱ መጠን ታይቶ በንስኀ አባታቸው የንስኀ ቀኖና እና ቀጣይ ምክርና ትምህርት የሚሰጣቸው ይሆናል ማለት ነው።
 
2. ተጠይቆ የነበረው ጥያቄ ፦የወሊድ መቆጣጠሪያ መጠቀም የቤተክርስቲያናችን አስተምሮ ምን ይላል?
 
የተሰጠው ምላሽ፦   ጠያቂያችን እንዳሉት የወሊድ መቆጣጠሪያ መጠቀም በቤተክርስቲያናችን ቀኖና ፈፅሞ ክልክል ነው። ባለፈው ፅንስ ማስወረድን ከባድ ኀጢአት እንደሆነ እንደተናገርነው ሁሉ መውለድ ያልፈለገ ሰው እራሱን ለመግዛት ላለመውለድ መቆጣጠር ያለበት ወንድም ሆነ ሴት ፈቃደ ስጋን በማሸነፍ ነው እንጂ የራሱን የስጋ ፈቃድ ፈፅሞ በህገ ተፈጥሮ ከፈጣሪ ዘንድ የተሰጠንን ፀጋ በሰው ሰራሽ መድሀኒት መከላከል ግን የእግዚአብሔርን ስራ እንደመቃወም ስለሚቆጠር ክልክል መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።
 
ጠያቂያችን ጋብቻ ቅዱስ ነው መኝታውም ንፁህ ነው ተብሎ ተፅፏልና ትክክለኛ በሆነ ክርስቲያናዊ ስነምግባር በቃል ኪዳን የፀኑ እጮኞች ጋብቻቸውን በቤተክርስቲያን ማድረጋቸው ከክብር በላይ ክብር ነው የሚያሰጠው። በቤተክርስቲያን የሚያደርጉት የጋብቻ እለትም የቤተክርስቲያንም በአል ነው ማለት ይቻላል፤ የእግዚአብሔርንም ፀጋ ያበዛል። 
 
ስለዚህ ወደ ጥያቄዎ ስንመጣ ፤ ወደ ገዳም ሄዶ በፀሎት የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጠየቅ የተቀደሰ ሃሳብ ቢሆንም እንኳን ነገር ግን በመጨናነቅ እና የተመቻቸ ጊዜ ሳይኖር በማይሆን ምኞት ውስጥ መጠመዱ ሌላ ፈተናም ሊያመጣ ስለሚችል ጠያቂያችን እንዳሉት እንደገና ተመካክራችሁ እዛው ያላችሁበት ደብር የስራ ጊዜን በማይሻማ መልኩ ለአንድ ሱባኤም ይሁን ለ3 ወይም ለ5 ቀን በአቅራቢያችሁ ባለው ቤተክርስቲያን እየሄዳችሁ ጠዋት ጠዋት ሁለታችሁም በአንድ ስፍራ ቆማችሁ በፀሎት እግዚአብሔርን ብትለምኑት ገዳም ሄዳችሁ ሱባኤ በመግባት የምታገኙትን የእግዚአብሔር በረከት እዚሁ ማግኘት እንደምትችሉ ማመን አለባችሁ። እግዚአብሔር ሁል ጊዜ በሰዎች ጭንቀት ውስጥ ቀድሞ የሚገኝ እና ማንኛውም ክርስቲያን ወደ እግዚአብሔር ደጅ በቀረበ ቁጥር ወይም ህገ እግዚአብሔር በፈፀመ ቁጥር ደስ ብሎት እና ችግሩ ሁሉ ተፈቶለት እንዲሄድ የሚፈቅድ አምላክ ነው እንጂ በጭንቀት ላይ ጭንቀት፣ በሃሳብ ላይ ሃሳብ እንዲበዛብን የሚፈቅድ አምላክ አይደለምና አሁንም በጋራ ተመካክራችሁ ፍፁም በሆነ ስምምነት ወደ አንድ ሃሳብ በመምጣት በአንድ ልብና በተሰበሰበ መንፈሰ መፈጸም ትችሉ ዘንድ ምክራችን እንዲደርስዎት አድርገናል።
ጠያቂያችን ከዚህ ቀደም ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ከርስቲያን የስነ ምግባር ጉዞ እና መንፈሳዊ ህይወቱ ምን መምሰል እንደለበት መልዕክተ ማስተላለፋችንን እናስታውሳለን። በመሰረቱ በ40 እና በ80 በጥምቀት ክርስትና የእግዚአብሔር ልጅ ሆነን በመንፈስ የተወለድንባትን ክርስትናችንን በቅዱስ ቁርባን ታትመን የእግዚአብሔር ከሆንበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ድረስ ማንኛውም ክርስቲያን ከስጋ እና ደሙ እንዳይለይ የቤተከርስቲያን ቀኖና ያዛል። በዚህ መሰረት ስጋ እና ደሙን እየተቀበለ ከቆየ በኋላ በጋብቻ ጊዜ ወይም ትዳር ሲመሰርት የነበረውን መንፈሳዊ ጉዞ በማቋረጥ ቅዱስ ቁርባንን እንደማይጠቅም በመቁጠር ሌላ ዓለም ውስጥ መግባት እጅግ የሚያሳዝን ነው። ታጥቦ ወደ ጭቃ ውስጥ እንደመግባት ወይም ከብርሃን ይልቅ ጨለማን፣ ከፅድቅ ይልቅ ኀጢአትን እንደመምረጥ ይቆጠራል። ባይሆን እንኳን፥ ወደ ትዳር ሲመጣ ወንዱ ወይም ሴቷ ለትዳር የመረጡት አጋራቸው ወደ እነሱ የክርስትና አላማ ውስጥ ለመጓዝ የሚያስቸግር ከሆነ ዝግ ብሎና አስተውሎ ከቤተከርስቲያን ሊቃውንት ወይም አባቶች ጋር በመነጋገር ያንን ሰው በምክር እና በትምህርት ማሳመንና ወደጋራ አላማ መምጣት እንጂ፤ የሚያልፈውን እና የዓለሙን የሥጋ ጥቅም መርጦ የእግዚአብሔርን ፀጋ እንደቀላል ነገር ቆጥሮ ወደኋላ በመተው ቅልጥ ወዳለው ዓለም ውስጥ መግባት ግን ጨርሶ መጥፋት ስለሆነ እንዲህ አይነት ነገር ፈፅሞ መሆን እንደሌለበት እንመክራለን።
 
በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ጥያቄ “በቅዱስ ቁርባን ለመጋባት የ አንድ ወገን ፍቃደኝነት ባይኖር የግንኙነቱ መጨረሻ ምን መሆን አለበት?” ብለው ለጠየቁን አባላችን ያስተላለፍነውን መልዕክት ለተጨማሪ ግንዛቤ እንዲረዳዎት እንደሚከተለው ልከንልዎታል።
…..
በእጮኝነት ያሉ ሁለት እጮኞች አንዳቸው በቅዱስ ቁርባን እንጋባ ሲሉ ሌላው ደግሞ አይሆንም ካለ የመጀመሪያው አማራጭ በቤተክርስቲያን አባቶች ትምህርት  እና ምክር ማግኘት ነው። ትምህርት ተሰጥቶ የቅዱስ ቁርባንን ጥቅምና የዘለዓለማዊ ህይወት ሰጭነትን በደንብ እንዲያውቅ ተደርጎ የህንንም ሁሉ እያወቀ ቅዱስ ቁርባኑን በማቃለል አልፈልግም ካለ እንደ ክህደት ወይም እንደ ኑፋቄ ስለሚቆጠር ከእንዲህ አይነቱ ወንድ ወይም ሴት ጋር ብዙ ሃላፊነት ወደሚፈልገው የትዳር  ህይወት መግባት እንደ እውነቱ ከሆነ አስፈላጊ አይደለም። ምክንያቱም አንደኛው ጻድቅ አንደኛው ኀጢዕ፣ አንደኛው መንፈሳዊ አንደኛው  ሥጋዊ፣ አንደኛው ፍየል ሌላው ደግሞ በግ፣ አንደኛው ጨለማ አንደኛው ብርሃን ሆኖ መኖር እንኳን ለሰማያዊ ህይወት ቀርቶ ለምድራዊ ህይወትም ፈተና ስለሚሆን ብዙ ትዕግስት እና ጊዜ በመውሰድ የሚሰጠውን ትምህርትና ምክር በአባቶች በኩል እስከ መጨረሻው በማጠናከር ተሞክሮም በቅዱስ ቁርባን ለመጋባት ፈቃደኛ ካልሆኑልን ግን ጨርሶ በአላማው መስማማት እንደሌለብን ምክር እንሰጣለን።
 
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
 
👉ጥያቄ፦ ሙሉ በሙሉ ንስሀውን ሳይጨርስ ከትዳር አጋሩ ጋር #ቅዱስ #ቁርባን ቢቀበል ይችላል? #ንስሀ ያልጨረሰበት ምክንያት ትዳሩን አደጋ ላይ ይጥልብኛል ብሎ ቢያስብ እና ወደፊት ራቅ ወዳለ ቦታ ኤዶ ለመናዝ።
 
መልስ፦ጠያቂያችን በዚህ በዮሐንስ ንስዓ ድረገፅ ፕሮግራም ወደእናንተ የምናደርሳቸው ትምህርት እና መክር ወደ ንስኀ ህይወት እንድትመለሱና በሃይማኖት እና በምግባራችሁም ፀንታችሁ እንድትኖሩ ቤተክርስቲያናችሁን እና ሃይማኖታችሁንም በስሜት እና በዘልማ ሳይሆን እውቀት ላይ በተመሰረተ ግንዛቤ በደንብ እንድታውቋት ለማድረግ ስለሆነ አሁን እርስዎ የጠየቁን ጥያቄ መንም እንኳን የእርስዎ ችግር የኛ ችግር ቢሆንም የተቀበሉትን የንስኀ ሳይጨርሱ ስጋዊውን ነገር በማስቀደም እና መንፈሳዊውን ነገር ግን ወደ ኋላ በማስቀረት በእንዲህ አይነት የስህተት መንገድ መጓዝ እንደሌለብዎት እንመክራለን።
 
ነገር ግን በትዳርዎ ዙሪያ ያለው ችግር እኛንም ስለሚያሳስበን ይሄን ትምህርትም የምናቀርበው አገልጋዮች በአባትነት ደረጃም ስለ ንስኀ ሀይወት ስለምንረዳ፥ በውስጥ መስመር አግኝተው ቢያነጋግሩን የመፍትሄ አቅጣጫ ልንሰጥዎት እንችላለን እንጂ በድፍኑ የእርስዎ ችግር ብቻ ተመልክተን የእግዚአብሔርን ስራ የሚቃወም ሃሳብ ማስተላለፍ የለብንምና በዚህ በሰጠንዎት ምክር ይጠቀሙ፤  ለተጨማሪ ምክርና ትምህርት በውስጥ መስመር ሊያገኙን ይችላሉ። ለሁሉም ነገር ያሰቡት ነገር በጎ ስለሆነ እግዚአብሔር ይርዳዎት።
ጠያቂያችን ፤ ከእርስዎ ጥያቄ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ጥያቄዎች ዙሪያ ከዚህ በፊት ያስተላለፍነውን መልዕክቶችን በተጨማሪ አንብበው ሃሳቡን ይረዱ ዘንድ አደራ እያልን  ከዚያ በፊት ግን  ለግንዛቤ ይረዳዎት ዘንድ ፦
 
1ኛ/ በመሰረቱ የአንድ ቀን ቁጥር የሚጀምረው ከዋዜማው ወይም ከማታው 12 ሰአት ጀምሮ እስከ የቀኑ 12 ሰዓት በድምሩ 24 ሰዓት 1 ቀን ይባላል። ይሄም ማለት ለምሳሌ  የቅዳሜን 24 ሰአት የምንጀምረው ከአርብ የቀኑ 12 ሰአት በኋላ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ የቀኑ 12 ሰአት ድረስ  ነው። ይሄ 1 ቀን ይባላል። ስለዚህ ለምሳሌ የእሁድን በዓል ማክበር የምንጀምረው ከቅዳሜ 12 ሰዓት ጀምሮ ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ የአንድን ቀን  አቆጣጠር ሂደት በዚህ ይረዱት።
 
2ኛ/  እርስዎ ወደጠየቁን ወደ ሩካቤ ሥጋ ስንመጣ ደግሞ ፥ አንድ ሰው እሁድ ቤተክርስቲያን ለመግባት ቢያንስ ከአርብ ማታ ጀምሮ ከስጋ ሩካቤ መቆጠብ አለበት ማለት ነው።  በተጨማሪ ወደ ቅዱስ ቁርባን ወይም ወደ ቤተክርስቲያን ከስንት ቀን ጀምሮ ንፅህናችንን መጠበቅ እንዳለብን እንደዚሁ ከዚህ በፊት ያስተላለፍነውን መልዕክት እንዲመለከቱት አያይዘን እንደሚከተለው ልከንልዎታልና አንብበው ሃሳቡን ይረዱ።
 
– እሁድ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ከሐሙስ በኋላ ያሉትን ቀናት ማክበር አለብን። ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ብቻ ሳይሆን ወደ ቤተከርስቲያን ገብቶ ለመፀለይና ለመሳለምም ሩካቤ ስጋ አድርጎ መሄድ አይፈቀድም። ምናልባት እንደተባለው የተለመደ የዘወትር ፀሎታችንን በቤታችን አካለ ስጋችንን ታጥበን በፀሎት ቤታችን ቆመን ማድረስ እንችላለን ወይም ወደ ቤተክርስቲያን ሄደን ከመግቢው ቅጽር ሆነን መፀለይ እንችላለን።  
 
ስለመንፈሳዊ ወይም ስለ ክርስቲያናዊ ህይወት ከባልና ሚስት አንዱ ጥንካሬ ካለው ማሸነፍ ያለበትና ተቀባይነት ያለው የሃይማኖቱና የነፍሱን ጉዳይ ተቀዳሚ እና ተፈፃሚ መሆን ያለበት መሆኑን እንዲረዱት እንመክራለን።
 
–  በማንኛውም ግዜ የፆም የፀሎት ሱባኤ በራሳችንም ይሁን በአባቶቻችን ቀኖና ተሰጥቶን የፆምና የፀሎት ሱባኤ በያዝን ግዜ፣ በእለተ ሰንበት እና በታወቁ በአላት ቀን ፈፅሞ ሚስትም ከባልዋ ተለይታ ወንድም ከሚስቱ ተለይቶ መኝታቸውንም የተለየ አድርገው የሚበላውንም የሚጠጣውንም ከተለመደው የአመጋገባቸው ስርአት ቀንሰው አጠቃላይ ፈቃደስጋቸውን ተቆጣጥረው ነው መፆም የሚገባቸው። ፆም ራሱን የቻለ ከእግዚአብዜር ጋር የምንገናኝበት የፅድቅ መንገድ ስለሆነ በዚህን ግዜ ማንኛውም ክርስቲያን የስጋ ፈቃዱን መቆጣጠር እንዳለበት የቤተክርስቲያን ቀኖና ይደነግጋል። ይህን ስንል በቀኖና የተደነገጉ 7ቱ አፅዋማትና እንደገናም በአባቶቻችን ሱባኤ ተሰጥቶን የምንፆምባቸው አፅዋማትን ይመለከታል። ይሁን እንጂ ከአቅም በላይ በሆነ ፈተና ፈቃደስጋችን አሸንፎን በዚህ ምኞት ከወደቅን ላጠፋነው ጥፋት የህሊና ፀፀት ተፀፅተን ለንስሐ አባታችን ወደፊት የምንነግረው ሁኖ ፆምና ፀሎትን ሳናቋርጥ እስከመጨረሻው ልንፈፅም ይገባናል።
 
– ቀርቦልን የነበረ ጥያቄ ፦  ሰላም ጥያቄ ነበረኝ ባልና ሚስት ሆነው ግንኙነት ከፈፀሙ ሦስት ቀን ሳይሞላ ቤተመቅደስ መግባት አይችሉም ሲባል በሰአት ቢቀመጥ ለምሳሌ አርብ ቢፈፀም እሁድ ልጅ ለማቁረብ መቅደስ መግባትም ሆነ ፀበል መጠመቅ ይቻላል?
 
ያስተላለፍነው ምላሽ፦ ጠያቂያችን የቤተክርስቲያንን ቀኖና እና ስርዓት ለማክበር ብለው ለመረዳት መጠየቅዎ አግባብ ነው። ምክንያቱም “የእግዚአብሔርን ቃል አባትህን ጠይቀው እውነቱንም ይነግርሃል” ይላልና። በመሰረቱ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ወደ ቤተመቅደስ ተጠግተን ለማስቀደስ 3 ቀን ከስጋ ስርዓት እንድንርቅ የሚደረግበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስለኛ በተቀበለው መከራ በእለተ አርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ስጋው ለይቶ 3 መአልትና 3 ለሊት በከርሰ መቃብር ውስጥ ቆይቷል። በዚህም ምክንያት ቅዱሳን ሐዋሪያት እና ከሱ ጋር ይከተሉት የነበሩት ደቀመዛሙርት የጌታን ትንሳኤ ሳናይ የሚበላ አንበላም የሚጠጣም አንጠጣም ብለው በፆም ተወስነው ስለቆዩ ነው። ስለዚህ ዛሬም የምንቀበለው ቅዱስ ቁርባን የክርስቶስን አማናዊ ስጋና አማናዊ ደም ስለሆነ ያንን መነሻ አብነት አድርገን ለ 3 ቀናት ንፅህናችንን እና ቅድስናችንን ጠብቀን የምንቆየው ነው።
 
በመሆኑም ህግ እና ቀኖና የሆነውን ነገር በህግነትና በቀኖናነቱ የተወሰነውን እውነቱን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ በደካማ ስጋችን ተፈትነንና ስጋዊ ምኞት አሸንፎን ቀኖናን የሚሽር ስህተት ፈፅመን ብንገኝ ወይም ደግሞ ከ 3 ቀን ባነሰ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ጠያቂያችን ያነሱትን ስህተት ፈፅሞ ቢገባ ያ ክርስቲያን ፈፅሞ የተወገዘ የተረገመ ነው ማለት አይደለም። የቤተክርስቲያን ስርዓት እና ቀኖና በመሻሩ ተግሳፅና ምክር ሊሰጠው ይችላል። ወደፊት እያወቀ እንዲህ አይነት ጥፋት እንዳትፈፅም ተብሎ ምክር ይሰጠዋል። ይሄ የሚሆነው በህጋዊ ጋብቻ ተወስነው ለሚኖሩ ነው። ከዚህ ውጭ ለሚሆነው ግን እንኳን ቤተክርስቲያን በድፍረት ለገባንበት ይቅርና ከሕግ ውጭ ላደረግነው ግንኙነትም ከባድ የቀኖና ቅጣት ይጠብቀዋል። በዚሁ መሰረት ጠያቂያችን ቀኖና ባለመሻር እና ከእግዚአብሔር በረከት ለማግኘት በምናደርገው መንፈሳዊ አገልግሎት በነፍስ የምንጎዳበት እርግማን እንዳያመጣብን ከወዲሁ ክርስቲያናዊ ስነምግባር እና ጥንቃቄ ሊኖረን ይገባል በማለት መልዕክታችን እንዲደርስዎት አድርገናል።
ጠያቂያችን ያቀረቡት ጥያቄ ተገቢና መንፈሳዊ ሃላፊነት ከሚሰማው ክርስቲያን የሚቀርብ በመሆኑና ፈሪሀ እግዚአብሔርም በውስጥዎ እንዳለ የሚያሳውቅ ስለሆነ በቅድምያ ልናመሰግንዎ እንወዳለን። ወደ ጥያቄዎ ስንመለስ እንዲህ አይነት በግል ህይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ በአብዛኛው በአካል ወደ ንስኀ አባት ቀርበው ምክር እና ትምህርት መቀበል የሚያስፈልግባቸው ናቸው። በውስጡ ሊጎዳም ሊጠቅምም የሚችል ብዙ ዝርዝር ሃሳብ የሚኖርበት ጉዳይ በተለይ በጋብቻ ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች ከባለጉዳዮቹ በላይ ኃላፊነት ወስዶ ችግሩን ሊፈታ የሚችለው ካህን በሰው ዘንድ የሚያስወቅስ በእግዚአብሔር ዘንድም ሊያስጠይቀው የሚችል ስለሆነ እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምሮ ጉዳዩን በእግዚአብሔር ቃል አስረጂነት መሰረት በማድረግ ውሳኔ መስጠት ስለሚገባው ንስኀ የሚያስገባ ጉዳይ ከሆነም ፣እንዲሁም ችግሩን በመመካከርና ትምህርት በማግኘት የሚፈታ ቢሆንም ወይም በህይወታቸው ጎጂ ጉዳይ ከሆነም መለያየት እንዳለባቸው ለመወሰንም ይቻል ዘንድ በቤተክርስቲያን አባቶች ምክርና ተግሳፅ ፈልጎ ጥያቄ ያቀረበውን አካል ቢያንስ በስልክም ይሁን በአካል ማነጋገር እና ለችግሩ በእኛ በኩል መፍትሄ መስጠት ስላለብን አሁንም ጠያቂያችን የጊዜ ቀጠሮ ሳያስረዝሙ በውስጥ መስመር በላክንልዎት ቁጥር ደውለው እንዲያገኙን ይህን አጭር መልዕክት ልከንልዎታል።    
 
ጠያቂያችን የተቸገሩበት ጉዳይ በእርግጥ የብዙዎች ችግር ስለሆነ ጥሩ ጥያቄ ነው። የእግዚአብሔር ልጆች እንዲህ ኀጢአት ሰራን በማለት እንቅልፍ አጥተው ሲጨነቁ ደስ ይላልና።   አባቶችም መገኘታቸው ለዚህ መፍትሄ ለመስጠት ነውና፥ እንግዲህ ከስርዓተ ቤተክርስቲን አንፃር አባቶችም እንዳስተማሩን ህልመ ሌሊት በማንኛውም ሰው ይከሰታል። አጋንንት ሰውን ተስፋ የሚያስቆርጡትም በዚህ ነውና በጽናት ሆነን ይህን ፈተና መዋጋት የእንደሚገባን አባቶች ይመክሩናል። በተለይ ሰይጣን ቤተክርስቲያን እንዳንገባ በጣም ተፅዕኖ ያደርግብናል። አባቶችንም ሳይቀር ይፈታተናቸዋል። ህልመ ሌሊትን ለማራቅ አብዝቶ መፀለይ መስገድ ያስፈልጋል፣ ስሜትን የሚያነሳሱ ነገሮችን መመልከት፣ ስለዚህ ጉዳይ አብዝቶ ማውራት፣ ህሊናን ለዚህ ቦታ መስጠት የመሳሰሉትን ስናደርግ አንዳንዴ ተሸናፊዎች እንሆናለን ፣ ፍትወታት ይሰለጥኑብንና የምናስበው ይሄን ብቻ ይሆናል ። በማታ በህልመ ሊሊት የምናየው ነገር በእኛ በራሳችን ስጋዊ ምኞት የሚገለፅ ስለሆነ አንዳንዱ በገሀዱ ያሰበውን በህልም የሚፈፅም፣ አንዳንዱ ደግሞ ምንም አይነት ሃሳብና ምኞት ሳይኖረው እርኩስ መንፈስ በህልም መጥቶ የሚፈትነው አጋጣሚ አለ። 
 
ስለዚህ በተቻለን መጠን እንደዚህ አይነት ሃሳብ በልባችን ሲመጣ በማስተዋል ሆነን ስሜታችንን መዝጋት መቻል አለብን። ለምሳሌ ስለ ዝሙት ፊልም የምናየው ካለ፣ ከተቃራኒ ጾታ በተደጋጋሚ በዚህ ጉዳይ የምናወራው ካለ፣ ከዚህ ጋር ምክንያት ሆኖ ማታ ላይ በህልም ይመጣብናል፤ ተኝተንም ብቻ ሳይሆን ተቀምጠንም እንዲህ አይነት ፈሳሽ ሊፈስ ይችላል፥ ያጋጥማልና። ለእንደዚህ አይነት መፍትሄው መስገድ ያስፈልጋል፣ መጾም ያስፈልጋል እንደዛም ሆኖ ግን ገፍቶ ያጋጥማል። ጠያቂያችን እንዳሉት ጓደኛዎ ጋር ስለሚያወሩት ይሄን ስለሚያስቡት ነው ከእሷ ጋር ተለያዩ መልኩ አዳንዴ ስሜት የሚቀሰቅሱ ነገሮችን መነጋገር አያስፈልግም ፣ ከአካሉም ጋር ከሚስቱም ጋር የሚነጋገሩበት ጊዜና ሰዓት አለው። መተሻሸትም አያስፈልግም፤ ወጣቱን እያስቸገረው ያለው ይሄ ነው፤ ከጋብቻ በፊት መተሻሸት ፣ መነካካት ይሄ በጣም ከባድ ነው ይፈታተናል። ምክንያቱም ህልመ ሌሊት የሚያያዘው ከማይዳሰሰው እና ከማይታየው ውስጣዊ የአስተሳሰብ ምኞት እና በሌላም በኩል በረቂቅ ከሚዋጋን እርኩስ መንፈስ ጋር የተያያዘ ውጊያ ስለሆነ ነው። እርስዎም እንዳሉት ክፉ መንፈስ ዋና መነሻው የኛን ደካማ ሃሳባችንን ፣ የአመለካከት ዝንባሌያችንን ወይም ምኞታችንን ምክንያት በማድረግ ነው። እንደተረዳነዎትም ህልመ ሌሊት የዝሙት ሃሳብ ይዞ እርስዎን የሚፈትንዎ ከጓደኛዎ ጋር በስልክ ወይም በሌላ አብዝተው የሚያወሩትንና ለእርስዎ የህሊና ዳኛ ሆነው በማስተዋል ይመርምሩ። ክርስቲያኖች ከጋብቻ በፊት ጥንቃቄ አድርገን ብንቆይ መልካም ነው። ሰይጣን በተለያየ መንገድ የሰውን ልጅ ከክብሩና ከፀጋው እያሳነሰው ነው። በማየትም በመስማትም በመናገርም የዝሙት ፈተናዎች ይመጣሉ የፈፀማሉም። የከርስቲያን እይታ ሰላምታ የተለየ መሆን አለበት፤ ስናይ ስንናገር ክርስቲያን መንፈሳዊ ሥርዓት የተሞላበት መሆን አለበት፤ ከዚህ ወጪ እየሆንን ከመጣን ግን ፀጋ እግዚአብሔርን ያርቃል፣ መንፈስ ቅዱስን ያርቃል፣ የአጋንንት መናኀርያና መጫወቻ መሆን የለብንምና ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።
 
ለወደፊት ጋብቻ መፈፀም እንዳሰቡም ነግረውናል ስለዚህ የገጠመዎት ችግር ውጊያ ነው ፥ እና መዋጋት ነው የለብዎት ፥ ሰይጣን እረፍት የለውም ክርስቲያኖች ላይ ተስፋ ለማስቆረጥ በተለያየ መልክ ስለሚመጣ እጅ መስጠት አይገባም፥ ስለዚህ 
 
ወደካህን እየቀረቡ መንገዱን አሳዩኝ እያሉ ቀኖና መቀበል መንገዱን አሳዩኝ ብሎ ምክርና ትምህርት መቀበል ያስፈልጋል እንጂ ተስፋ መቁረጥ አያስፈልግም። እኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ነን አጋንንት በተለያየ መልኩ ጦሩን ቢወረውር ተስፋ አንቆርጥም ፤ ሰይጣን እኛን ተስፋ አስቆርጦ ኀጢአተኛ ነኝ ወደ ቤተክርስቲያን እንዴት እሄዳለሁኝ፣ እንዴት በቤተክርስቲያን መኖር እችላለሁኝ እንድንልና እርስዎም ያነሷቸውን በማሳሰብ ተስፋ ሊያስቆርጠን ነውና ማስተዋል አለብን። ሰው ደግሞ ተፈተነና አለፈ የሚባለው ፍትወት እንዲህ ሰልጥኖበት ያን ተጋድሎ አሸንፎ ሲያልፍ ነው መንፈሳዊ የሚባለው።
 
በአጠቃላይ ጠያቂያችን አሁንም ይህ ችግር እየተደጋገመ በመፈታተን ከአላማዎትና ከእቅድዎት እንዳያስወጣዎት በማስተዋልና ተስፋ ባለመቁረጥ ፥ ደግሞም ከሰይጣን ሃይል ይልቅ  የእኛ ፀጋና ሃይል ስለሚበልጥ ጊዜና ቦታ ሳንሰጥ ዘወትር በፀሎትና በልዩ ልዩ መንፈሳዊ አገልግሎት ከነሱ ጋር አብዝተን በተጋደልን መጠን ይህ የሰይጣን መንፈስ በእግዚአብሔር ቃል እየተቃጠሉ ከእኛ እንዲርቁ ማድረግ ይቻላል። ስለዚህ፦
 
1ኛ /በህልመ ሌሊት የሚመጣው የሰይጣን ውጊያ በእርስዎ ህይወት በምን ምክንያት እንደሚዋጋዎ በተከታታይ ከሚያጋጥምዎ ፈተና አንፃር መንስኤውን ለይተው ይወቁ። የህሊና ዳኝነት ካደረጉ በኋላ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ግልፅ እየሆነልዎት ይሄዳልና። 
 
2ኛ / በሁለተኛ ደረጃ ይሄንኑ ያጋጠመዎትን ችግር ለመንፈሳዊ አባትዎ በግልፅ በማስረዳት አስፈላጊውን ምክርና መንፈሳዊ አገልግሎት ያግኙ፤  
 
3ኛ / በእርስዎም በኩል የማይቋረጥ ቋሚ የፀሎት ፕሮግራም በማድረግ አብዝቶ መፀለይ ፣ መፆም፣ መስገድ ያዘውትሩ፣ 
 
4ኛ / በፀበሉ በቅዱስ መስቀሉና በእምነቱ ከአጋንንት  በውጊያ ለመዳን እንደሚችሉ በማመን አስፈላጊውን አገልግሎት ማግኘትና በቤተከርስቲያን አባቶችም በፀሎት መረዳት አለብዎት፣
 
ስለዚህ ጠያቂያችን እነዚህን ከላይ የዘረዘርናቸውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ እየመከርን ለተጨማሪ ምክር እና ማብራሪያ ካስፈለገዎት በውስጥ መስመር በላክንልዎት አድራሻ ሊያገኙን እንደሚችሉ እንገልፃለን።

 ጠያቂያችን በቅድሚያ ስለ ምሥጢረ ተክሊል ይህን አጭር ትምህርትታዊ  ማብራሪያ ለሰከንልዎታልና አንብበው በመረዳት ለጥያቄዎ ምላሽ በዚህ  ውስጥ ያገኛሉ።

ምሥጢረ ተክሊል ከ7ቱ የቤተክርስቲያን ምሥጢራት አንዱ ሲሆን ይህም ከማይደገሙት ሚስጥራት ይመደባል። ምክንያቲም በድንግልና ህይወት ጸንተው የኖሩ ወይም ድንግልናቸውን አክብረው የኖሩ ሰወች በቤተክርስቲያን የሚያደርጉት የክብር አገልግሎት ስለሆነ አንድ ጊዜ ስርዓተ ተክሊል ከተፈጸመ በኋላ ሁለተኛ ደግሞ ያስፈልጋል በሚል አይደገምምና።

ሚስጥረ ተክሊል የሚፈጸምላቸው ተጋቢዎች በሃይማኖትና በምግባር ጸንተው በድንግልና ሕይወት ለተገኙ ሙሽራውና ሙሽራይቱ ብቻ ነው። ሚስጥረ ተክሊልም ለአንድ ሰው አንድ ጊዜ ብቻ የሚፈፀም ስርአት እንጂ አይደጋገምም። ሚስጥር የተባለበት ምክንያቱም ባልና ሚስት አንድ የሆኑበት ስርዓት ስለሆነ ነው። በጥንተ ተፈጥሮ ሴት የተገኘችው ከወንድ በመሆኑ “ይቺ አጥንት ከአጥንቴ ስጋዋም ከስጋዬ ናት” ተብሎ ሄዋን ከአዳም እንደተገኘችና አንድዋ ሄዋን ለአንድ አዳም እንደተፈጠረች ቅዱስ መፅሐፍ ያስረዳል። (ዘፍ 2፤24 ) በመሆኑም ቤተክርስቲያን አዋጅ ብላ ልጆቿን ለክብር ለመዓረግ የምታበቃበት ስርዓተ ምስጢረ ተክሊል ይባላል። ስለ ድንግልናቸው ክብር ምድራዊ የምናየው ዋጋ ሁሉ ሰማያዊ ዋጋ በኋላ ያሰጣልና። ይህ የአክሊል ሽልማት የሰማይ አክሊል ምሳሌ ነው። 

በስርአተ ተክሊል ጋብቻቸውን የሚፈፅሙ ጥንዶች ሁለቱም በድንግልና ጸንተው የኖሩ ለመሆናቸው በእግዚአብሔር ፊት ቀርበው ለንስሐ አባታቸው እራሳቸውን ሲያስመረምሩ ብቻ ነው። ከሁለት አንዳቸው ከስርዓተ ተክሊል በፊት ድንግልናቸውን ሊያሳጣ የሚችል ጥቃት ከፈፀሙ በቅዱስ ቁርባን አንድ ሊሆኑ ይችላሉ እንጂ የክብር አክሊል መቀዳጀት የሚችለው በድንግልና ሕይወቱ ጸንቶ የተገኘ ብቻ ነው። ምክንያቱም ስርአተ ተክሊል ማለት በቤተክርስቲያን ውስጥ በካህናት አባቶቻችን የተለየ የክብር ልብስ ሲለብሱ፣ በራሳቸው ላይ የክብር አክሊል ሲቀዳጁ፣ የሚፈፀምላቸው ስርአተ ፀሎት፣ በካህኑ የሚቀቡት የተቀደሰ ቅባት፣ የቃልኪዳኑ ምልክት የሆነው ቀለበት፣ በመጨረሻም ሁለቱም አንድ የሚሆኑበትና የአንድነታቸው ማሰርያ የሆነውን ቅዱስ ቁርባን ሲቀበሉ ነው። ይህ ደግሞ ታላቅ ሚስጥር ስለሆነ እግዚአብሔር ላደለው ሰው በፍፁም መንፈሳዊ ሕይወት ፈሪሃ እግዚአብሔር ኖሮን በምክረ ካህን ንስሐ ተቀብለን ከሰራነው ነውራችን አንዱንም ነገር ሳንፈራና ሳንደብቅ ግልፅ ሁነን የምንፈፅመው ስርዓት ከሆነ ኑሯችን፣ ትውልዳችን፣ ስራችን፣ ጤናችን፣ ሁሉ የተቀደሰና የተባረከ ይሆናል። ጋብቻ ቅዱስ ነው የተባለውም በዚህ ነው። ቅዱስ ጋብቻን የባረከው እግዚአብሔር አምላካችን ነው። ምክንያቱም አዳምና ሄዋንን ሲፈጥር አንድ ወንድን ለአንዲት ሴት ፈጥሮ ያጣመረ እሱ ነውና። በጣና ዘገሊላ በተደረገው የሰርግ ቤት ተገኝቶ ጋብቻን እንደባረከ ወንጌላዊ ዩሐንስ ነግሮናል። (ዩሐ 2፤1-11 እብ13፤4 ኤፌ 5፤31 እና 32)

ለጋብቻ የሚደረገው ጥንቃቄ የአንድ ትውልድ፣ ያንድ ታሪክ፣ ያንድ መንደር፣ ያንድ ሃገር የመነሻ መሠረት ስለሆነ ነው። ስለዚህ ጋብቻ በቅዱስ መፅሓፍ ሰፋ ያለ ታሪክ ያለው ቢሆንም ለጠየቁን አባላችን በመጨረሻ እንዲገነዘቡ የምንፈልገው የስርአተ ተክሊሉ አፈፃፀም ከ ሁለት አንዳቸው ከጋብቻ በፊት በተለየ ስህተት ፈተና ላይ የወደቁ ከሆነ በድንግልና ፀንቶ የቆየው የክብር አክሊል ሲደረግለት ሌላው ግን ንስሐውን በቀኖና ከፈፀመ በኋላ አብረው ስጋውና ደሙን በተቀበሉ ጊዜ አንድ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። በዚህ አይነት ስርዓት ጸንተው እንዲኖሩም ቤተክርስቲያን በፍቅርና በአንድነት ቃል ታገባባቸዋለች።

ጠያቂያችን እንዲረዱትና እንዲያውቁት የሚያስፈልገው ነገር በስርዓተ ተክሊል መጋባት ያለባቸው ጥንዶች ወይም ወንድና ሴት ክርስቲያኖች በቤተክርስቲያን ስርዓት ተክሊል ከመፈፀማቸው በፊት ስለወደፊት የጋብቻ ፕሮግራማቸውና ሰለሚቀጥለው የትዳር ኑሯቸው ተነጋግረው ቃል ኪዳን ከፈፀሙ በኋላ መንፈሳዊ ሰላምታ እየተለዋወጡ ለቀጣይ ህይወታቸውም የሚጠቅማቸውን ነገር ለመስራት በሃሳብና በተግባር እየተረዳዱ ስለመንፈሳዊ ህይወታቸውም እንዴት መፀለይና መበርታት እንዳለባቸው እየተመካከሩ፣ ወደ ቤተክርስቲያንም ዘወትር እየቀረቡ ቅዱስ ቁርባን በየግላቸው እየተቀበሉ እስከ ጋብቻቸው ድረስ መቀጠል እና ይሄንን የመሳሰለውን ቅድመ ሁኔታ መመካከር እንጂ ፤ ከዚህ ያለፈ በስጋዊ ፍትወት እየተቃጠሉ መዳራት እና የስሜት ፆራቸውን ከግብረ ስጋ ግንኙነት ባልተናነሰ እየፈፀሙ የቆዩ ከሆነ ስርዓተ ተክሊል አይፈፀምላቸውም።

ይልቁንም ስላደረጉት ሰህተት ለንስኀ አባታቸው በግልጽ በመናዘዝና ጥፋታቸውን በማመን በፈፀሙት ጥፋት መጠን እንደ ቤተክርስቲያን ቀኖና ንስኀ ተቀብለው ንስኀቸውን ከጨረሱ በኋላ በቅዱስ ቁርባን ሊጋቡ ይችላሉ እንጂ በበረከት ፈንታ መርገም ሊያመጣባቸው የሚችለውን ሰህተት ወይም ድፍረት መፈፀም የለባቸውም። እግዚአብሔር ላስቻለውና ከዝሙት ጠንቅ ጠብቆት በመንፈሳዊ ጽናት ለቆየ የክርስቲያን የድንግልና ዋጋ ወይም የክብር መገለጫ የሆነውን ስርዓተ ተክሊል በመፈጸም ጋብቻቸውን በስጋወ ደሙ ማረጋገጥ ከሁሉ የሚበልጥ የተቀደሰ አላማ ነው። በአንዳንድ ፈተና በኀጢአት ሰህተት ከወደቅን ግን ለስጋዊ ክብራችን ተጨንቀን ወደ ሁለተኛ ጥፋት የሚያገባንን በድፍረት ስርዓተ ተክሊል መፈፀም ግን እጅግ ነውር ስለሆነ ሁላችሁም ይሄንን መልዕክት በአጽንዖት እንድትረዱት አደራ እንላለን።

ከዚህ በተጨማሪ፤  አንድ ክርስቲያን የሆነ ወንድ ልጅ ወይም ሴት ልጅ በቤተ ክርስቲያን ቀኖና ድንግልናቸውን ጠብቀዋል  ሲባል : –

#1- ከጋብቻ በፊት የግብረ ሥጋ ግንኙነት አለማድረጋቸው በራሳቸው ቃለ መሓላ÷ በንስሐ አባትና በቤተሰበ ሲረጋገጥ

#2- በሃይማኖታቸውና በክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ጸንተው ከእግዚአብሔር ቤት ሣይለዩ ቅዱስ ቁርባን እየተቀበሉ  ስለመ ኖራቸው ቤተክርስቲያን ስትመሰክርላቸው

#3- ከጋብቻ በፊት  የድንግልና ክብራቸውን  ሊያሳጣ የሚችል ሐጢአት ያልሰሩ ለምሣሌ ÷ የሰው ሕይወት ማጥፋት፣ ጣዖት ማምለክ፣ ማስጠንቆል መሥረቅ  የመሣሰሉትን ጥፉቶቸ መፈጸም  ናቸው ።

#4- የወንድ ልጅ ድንግልና  ማረጋገጫ በ ራሱ ህሊና አምኖ ለነፍስ አባቱ ከሚገባው ቃል ኪዳን ዉጪ ሌላ አካላዊ ማረጋገጫ  አይኖርም   በእርግጥ ከምንም በላይ  ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ  ከሰው የሰወርነውን በደላችንን ሁሉ ሰለ  ሚያውቀው ለህሊናችንና ለሃማኖታችን ስንል እውነቱን እዉነት ሃሰቱን ሃሰት ልንል ይገባል         

#5- የሴት ልጅ ድንግልና ራሷ ፍጹም ታማኝ  እና ቅድስናዋን የጠበቀች ሁና እያለ :-  በተፈጥሮ ፣ በሕመም ምክንያት ፣ በአስገድዶ መደፈር ፣ በከፍተኛ የሥራ እንቅስቃሴ (ክብደት) – በሕክምና እና በመሳሰለው ሁሉ አካላዊ የድንግልና ምልክቷ ባይገኝባት እንደ ቤተክርስቲያ አስተምሮ ሌላ ነውር እሰከአልሠራች ድረስ የድንግ ክብሯን አያሳጣትም።   

 

ስለዚህ ስለድንግልና ማንነት ማወቅ የምንችለው በተፈጥሯዊ ዕውቀትና በሳይንሳዊ ምርምር ወይም በሰውኛ ዕውቀት ሳይሆን ብቸኛ ዐዋቂው የራሳችን ውሳጣዊ ኅሊናና  የሁሉ ባለቤት ፈጣሪ ብቻ በመሆኑ መሠረታዊ የሆነውን ትምሕርተ ሃይማኖት ከማወቅ አልፎ ያለውን ድርሻ ለእግዚአብሔር ብቻ መስጠት አለብን ጠያቂያችን እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ሁሉ ለሚስጥረ ተክሊል ስርዓት የምንበቃባቸው ሲሆኑ፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ግን በቅድሚያ ከአንድ ክርስቲያን ንስኀ ከመግባቱ በፊት እና በኋላ ምን ማድረግ እንዳለበት እንዲሁም ወደ ቅዱስ ቁርባን ከመቅረብ በፊት ልናደርጋቸው ስለሚገቡ ቅድመ ዝግጅትም መገንዘብ ስለሚያሰሰፈልግ፤ በዚህ ርዕስ ዙርያ ከዚህ በመቀጠል የምንልክልዎትን አጠቃላይ የሆነ መልዕክት አንብበው እርስዎ ለጠየቁት ጥያቄ ምላሽ እንደሚያገኙ እንገልፃለን። ከዚህ ተጨማሪ መረዳት የሚፈልጉት ነገር ካለ ሃሳብዎን ገልጸው  በድጋሚ ቢያሳውቁን ወይም በውስጥ መስመር ቢያገኙን ተጨማሪ ማብራሪያ ልንሰጥዎ እንችላለን። 

የአብርሃምና የሳራን ጋብቻ የባረከ አምላክ በስርዓተ ጋብቻ አንድ የሆኑትን ሁሉ ኑሯቸውን ይባርክ ዘንድ እንመኛለን።

ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን ላይ ያገኛሉ

 ጠያቂያችን፤ ጥያቄዎ  ትንሽ ግልፅ ባይሆንልንም እኛ በተረዳነው መልኩ ጥያቄዎን ከላይ እንደተመለከተው በአጭሩ አስቀምጠን ይህን ምላሽ ሰጥተንበታል። ከፍቅረኛ ወይም ወደፊት የትዳር አጋርዎ እንዲሆን ካሰቡት ሰው ጋር ለሚሆነው የህይወ ጉዞ ከወዲሁ ለጋብቻ ቃል ኪዳን በማድረግ መኖራችሁ መልካም ሆኖ ሳለ፤ ነገር ግን ከመንፈሳዊነትም ሆነ ከጥሩ ስነምግባር ውጪ በሆነ የቃል አነጋገርም ሆነ የተግባር ስራ ከጋብቻ በፊት መፈፀም ክርስቲያናዊ ምግባር አይደለም። እርስዎ እንዳሉት ያልሆነ ነገርም  መነጋገርም ሆነ መስራት ያለንን መንፈሳዊ አቋም ሁሉ ያወርደዋልና ከአላማችንም ያስወጣናልና መንፈሳዊ ህይወታችንንም ሊያስመዝነው ይችላልና ሁሉም ነገር በቁም ነገር እንዲዘልቅ ማድረግ ለቀጣይ ህይወት እጅግ ጠቃሚ ከመሆኑም በላይ በመንፈሳዊም ሆነ በስጋዊ ህይወታችን ያስከብረናል። አንዳንድ ጊዜ እንደመብት በመቁጠር ሚስቴ ነች ፣ ባሌ ነው በማለት በዘመኑ አገላለፅ የፉገራ አይነት ነገር  በሚደረገው መቀላለድ ወይም ዋዛ ፈዛዛ እንደልብ ማውራት እየተለመደ ሲሄድ ወደ መደበኛና ቋሚ ንግግር ሊቀየር ስለሚችል  የማይገቡ ቃልም በአፋችን ማስለመድ ሰወችንም እኛንም ሊያሳዝን ስለሚችል መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

ስለዚህ ጠያቂያችን በቃል ኪዳን ያደረጋችሁት መተሳሰር ቢኖርም እንኳን የበለጠ እግዚአብሔርን ጋብቻችሁን እና የወደፊት ህይወታችሁን እንዲባርክላችሁ ሰው አላየንም አልሰማንም በማለት የሚያሸማቅቅ እና የሚያሳፍር ንግግር እና ድርጊት እንዳታደርጉ በአጽንዎት ምክራችንን እንለግሳለን።   እንዲሁም እርስዎ እንዳሉት ከእሱ የተሻለ ሃይማኖታዊ እና መንፈሳዊ ግንዛቤ እንዳለዎት በገለፁልን መሰረት እርስዎ ቀስ በቀስ ሊመክሯቸውና የመንፈሳዊነት ስነምግባር ሊያሳውቋቸው ይገባል። በክርስቲያናዊ ህይወታችን ውስጥ ነውር እና ኀጢአት የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ሊያሳውቋቸው ይገባዎታል። በተጨማሪም ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ ወይም ወደ ሃይማኖት አባቶች በመቅረብ ክርስቲያናዊ ምግባርን መማር ያስፈልጋል። ምናልባት ሁለታችሁም በባእድ አገር የምትኖሩ ከሆነና ሃይማኖታዊ ትምህርት እና ክርስቲያናዊ ስነምግባርን ለመማር ዘወትር ወደቤተክርስቲያን መሄድ የማትችሉ ከሆነ፤ በዚህ በዮሐንስ ንስኀ ድረገጽ በየጊዜው የሚላለፉትን ትምህርቶች እና ከአባላት በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ የምናስተላልፈውን ተመሳሳይ ጥያቄዎች የማግኘት እድል ስላገኛችሁ እለት እለት የምናስተላልፈውን ትምህርት እና ምክር አንብባችሁ በመረዳት እንዲሁም በውስጥ መስመርም አግኝተው ቢያናግሩን እግዚአብሔር አምላክ ምድራዊ ህይወታችሁን እንዲባርክላችሁ ላሰባችሁት የትዳር ህይወት እንዲያጸናችሁ እንዳሉትም በጸሎት እናስብዎታለን ተጨማሪ ትምህርት እና  ምክራችንም እንዲደርስዎ እናደርጋለን፥ በእናንተም በኩል ማድረግ ስላሚገባችሁ ክርስቲያናዊ ስነምግባርና መንፈሳዊ ሥርዓት በጣይ እንመክርዎታለን።

በተጨማሪም ከዚህ በፊት እንደገለጽነው ጥንዶች   ስለወደፊት የጋብቻ ፕሮግራማቸውና ሰለሚቀጥለው የትዳር ኑሯቸው ተነጋግረው ቃል ኪዳን ከፈፀሙ በኋላ መንፈሳዊ ሰላምታ እየተለዋወጡ ለቀጣይ ህይወታቸውም የሚጠቅማቸውን ነገር ለመስራት በሃሳብና በተግባር እየተረዳዱ ስለመንፈሳዊ ህይወታቸውም እንዴት መፀለይና መበርታት እንዳለባቸው እየተመካከሩ፣ ወደ ቤተክርስቲያንም ዘወትር እየቀረቡ ቅዱስ ቁርባን በየግላቸው እየተቀበሉ እስከ ጋብቻቸው ድረስ መቀጠል እና ይሄንን የመሳሰለውን ቅድመ ሁኔታ መመካከር እንጂ ፤ ከዚህ ያለፈ በስጋዊ ፍትወት እየተቃጠሉ መዳራት እና የስሜት ፆራቸውን ከግብረ ስጋ ግንኙነት ባልተናነሰ እየፈፀሙ የቆዩ ከሆነ ስርዓተ ተክሊል አይፈፀምላቸውም።  

ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ

ከትዳር በፊት ስለ መሳሳም እና አብሮ ስለማደር ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም የሚል ሃሳብ ላለው ጥያቄ የተሰጠ ምላሽ ነው፦

በመሰረቱ ከትዳር በፊትም ሆነ በትዳር ጊዜ መሳሳም የሚለው ሃሳብ ከሰው መልካም ስነ ምግባር ጋር የማይሄድ ተግባር ነው። የሰው ልጅ ፈቃደ ሥጋው ወደ ዝሙት ሃሳብ ሲሄድበት የሴሰኝነት መንፈስ ሲያይልበት የዝሙት ስራ መጀመሪያ በመሳሳም እንደሚገለፅ እነሆ በአለማችን የምናየው ትርኢት ነው። በእኛ በቤተክርስቲያን አስተምሮ በበጎ ፈቃድ የምንለዋወጠው ሰላምታ መሳሳምን የሚተካው ይህ የክርስቲያናዊ የሰላምታ አይነት ነው። ምክንያቱም ራሱን የገዛ እና ከህሊናው ጋር የሚኖር ማንኛውም ክርስቲያን ከትዳር ጓደኛውም ጋር ቢሆን ከሌላው ሰው ጋርም ቢሆን እውነተኛ ፍቅርን እና ናፍቆትን የሚገልፅበት መሳሳም በሰው ፊትም ይሁን በእግዚአብሔር ፊትም በጉባኤ ፊትም ቢሆን የማያሳፍር የማያሳቅቅ ትክክለኛ እና እውነተኛ ሰላምታ የሚገለፅበት የሰላምታ አሰጣጥ ስርአት ነው።

ከትዳር በፊት አብሮ ማደር የሚለውም አባባል ሲጀመር እንደ እግዚአብሔር ህግ ከሆነ ወንድ እና ሴት ከጋብቻ በፊት በቃልኪዳን ተሳስረው ምንም አይነት ሩካቤ ሳያደርጉ የጋብቻቸውን ቀን በማክበር ከቆዩ በኋላ ጋብቻቸው ሲፈፀም በእግዚአብሔር የተቀደሰ በማህበረሰቡም ዘንድ ስለታወቀላቸው የሚያደርጉት የተራክቦ ስጋ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተፈቀደ ህግን ፈፀሙ እንጂ የዝሙት ስራን ስላልፈፀሙ ኑሯቸው ሁሉ ህጋዊ እንደሆነ ይታመናል።

ከጋብቻ ውጭ የሆነ ማንኛውም ተራክቦ ወይም ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈፀም ግን ከዝሙት ኀጢአት የሚቆጠር ነው። ፈቃደ ስጋቸውን መግዛት ያቃታቸው በቃልኪዳን በእጮኝነት ያሉ ወንድ እና ሴት ከጋብቻ በፊት ማንኛውንም ግንኙነት ለማድረግ ቤተክርስቲያን አትፈቅድም። እነሱ በራሳቸው ፈቃድ ቢፈፅሙት እንኳን ንስኀ የሚያስገባ ኀጢአት ነው።

ስለዚህ ጠያቂያችንም ሆኑ የዮሐንስ ንስኀ ድረገፅ አባላቶቻችን ሁላችሁም በጥብቅ መገንዘብ ያለባችሁ ከዚህ በፊትም በተለያየ ጊዜ ስለዚህ ጉዳይ በሰፊው ገለፃ ማድረጋችንን እያስታወስን አሁንም ህጋዊ ከሆነ ጋብቻ ውጪ ያሉ የሴት እና የወንድ መሳሳምም ይሁን፣ ሩቤ ስጋ መፈፀምም ይሁን፣ በስሜት እየተቃጠሉ መተሻሸትም ይሁን የዝሙት መንስኤዎች እና የዝሙት ዋዜማዎች ናቸው። ስለዚህ እራሳችንን መቆጣጠር አቅቶን እነዚህን ድርጊቶች እየጨመርንበት ስንሄድ ዋናውን የዝሙት ኀጢአት ስለሚመጣ በእግዚአብሔር ዘንድ ያስጠይቀናል ማለት ነው።

ስለዚህ ጠያቂያችን ሃሳቡን በዚህ ይረዱትና ስለ ዝሙት መንፈስ ተጨማሪ ትምህርት በቅርብ ቀን ስለምንሰጥበት በዚያን ጊዜ የበለጠውን አውቀው እንዲረዱ ከወዲሁ በመስመር ላይ ይጠባበቁን ዘንድ ልናስገነዝብ እንወዳለን።

ለሁሉም ነገር የእግዚአብሔር ጠብቆቱ ከሁላችን ጋር ይሁን

ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ

ጠያቂያችን በቃልኪዳን ስትኖሩ ሁለታችሁም የየራሳችሁ ንስኀ አባት እንዳላችሁ ወደፊት ደግሞ በህጋዊ ጋብቻ ስትኖሩ አንድ አባት ሊኖራችሁ እንደሚገባ ተረድተው በእኛ በኩል መንፈሳዊ ምክር እንድንለግሰዎ የጠየቁንን ይመለከታል።

በመሰረቱ በየግላችን ሳለን የንስኀ አባት ሊኖረን እንደሚገባ በቀኖና ቤተክርስቲያን የተደነገገ ስለሆነ እስካሁን ያደረጋችሁት አካሄድ መልካም ነው። ወደፊት በጋራ ኑሮ ስትመሰርቱ እንደተባለውም ሁለቱም አባቶች በአንድ ቤት ውስጥ እረኛ ሊሆኑ ወይም አስተማሪ ሊሆኑ የማይችሉበት ምክንያት ባይኖርም እንኳን ነገር ግን ለአባቶቻችሁ ቃል ለመታዘዝ እና ለአፈፃፀም አመችነት ስለማይኖረው እንደተባለው ከሁለቱ መካከል በብዙ አማራጭ የተሻሉ አባት ናቸው የምትሏቸውን በመምረጥ በቀጣይነት አንድ ንስኀ አባት ማድረግ ትችላላችሁ።

ምክንያቱም ዘወተር ሳይሰለቹና ሳይሰንፉ በትጋት የሚከታተሉዋችሁን እና ሊቆጣጠሯችሁ የሚችሉትን ወደ እግዚአብሔር እንድትቀርቡ የሚያተጓችሁን አባት አስተማሪ መካሪ አድርጋችሁ በእናንተ ህይወት ላይ እንድትሾሟቸው ትልቁ ድርሻ የእናንተ ስለሆነ ምንም አይነት ይሉኝታ ሳይሰማችሁ የእናንተ አባት መሆን የሚገባቸውን በራሳችሁ ነፃ ፈቃድ መርጣችሁ መያዝ አለባችሁ።

በተጨማሪም በየጊዜው በአካልም ልታገኟቸው የምትችሉበት ሁኔተም አንዱ የመምረጫ ምክንያት ሲሆን ሌላው ደግሞ በሃይማኖት እና በምግባር ለእናንተ አርአያ መሆን መቻላቸው ይህም መመዘኛ ነውና ይህንኑ ምክንያት ተከትላችሁ አንድ አባት እንዲኗሯችሁ እንመክራለን።

ከዚህ ውጪ ያለውን ሃሳባችሁን ወይም ችግር ብላችሁ ያሰባችሁት ካለ በውስጥ መስመር ሊያገኙን ስለሚችሉ በእኛም በኩል መፍትሄ እና ተጨማሪ ምክር ልንሰጣችሁ እንችላለን።

ለሁሉም ነገር የእግዚአብሔር ጠብቆቱ ከናንተ ጋር ይሁን 

ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ

ጠያቂያችን፤ በሞት ምክንያት እና በዝሙት ምክንያት በሚያጋጥም የትዳር መፍረስ በኋላ ስለሚኖረው ቀጣይ ህይወት ለጠየቁን የተሰጠ መልስ።
1ኛ ባል እና ሚስት በሞት ምክንያት ከተለዩ በህይወት ያለው ወንድ ወይም ሴት ቀደም ሲል የነበረው የትዳር ህይወታቸው በስርዓተ ቤተክርስቲያን የተፈፀመ እና በቁርባን ተወስነው የሚኖሩ ከሆነ፦ ስጋዊ ፍላጎትን ለመቆጣጠር የሚችሉ ከሆኑ ከማንኛውም የዝሙት ሃሳብ እርቀው በስርዓተ ቁርባን ተወስነው ያለጋብቻ ይቀጥላሉ። የእድሜ ደረጃቸው ከፍ ሲል ወይም ደግሞ ራሳቸውንም ያዘጋጁ ከሆነ ወደ ስርዓተ ምንኩስና መግባት ይችላሉ። ነገር ግን ያለጋብቻ ብቻቸውን ለመኖር ስጋዊ ፍላጎታቸው አይሎባቸው በዝሙት ሃሳብ የሚፈተኑ ከሆነ በሃይማኖት እና በምግባር የምትመስለውን ወይም የሚመስላትን መርጠው ለንስኀ አባትዎ ነገሩን በማማከር በስርዓተ ቁርባን ህይወታቸውን ለማስቀጠል ተጋብተው መኖር ይችላሉ።
በ2ኛ ደረጃ በዝሙት ምክንያት በተፋቱ ባል እና ሚስት፦ በአላማው ወይም በአላማዋ ልትፀና ወይም ሊፀና የሚችለውን በሃይማኖት እና በምግባር የመትመስለውን ወይም የሚመስላትን መርጠው በማግባት በስርዓተ ቤተክርስቲያንና በምክረ ካህን ህይወታቸውን በጋብቻ ማስቀጠል ይችላሉ። ነገር ግን የፈቃደ ስጋውን ለመቆጣጠር የሚያስችለው ወይም የሚያስችላት ከሆነ ብቻቸውን በስርዓተ ቁርባን ተወስነው ከኀጢአት በስተቀር በተፈቀደው ማንኛውም የኑሮ ሂደት ህይወታቸውን ማስቀጠል ይችላሉ። በተጨማረም ከዚህ በፊትም ይህንኑ በሚመለከት ጥያቄ ቀርቦልን የሰጠነውን ሁለት የፅሁፍ ማብራሪያ ይመለከቱ ዘንድ ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል።

….
መልስ1 ፦
ጠያቂያችን የቀረቡት ሃሳብ ባል እና ሚስት ከተፋቱ በኋላ ከሌላ የትዳር አጋር ጋር ጋብቻ እስከሚፈፅሙ እየቆረቡ መቆየት ይችላሉ ወይ? የሚለውን ጥያቄ በሚመለከት፦ በመሰረቱ ከዚህ በፊትም እንደመከርነው ባል እና ሚስት የስጋ አስተሳሰብ በሆነ ፈተና ለሚያጋጥማቸው ችግሮች እንዲፋቱ አይፈቀድላቸውም። ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከተፋቱ እንኳን፦

1. በየግላቸው ስጋው ደሙን ለመቀበል የሚችሉት በቀጣይ ህይወታቸው ሴቷም እንደስዋ በቁርባን ተወስኖ የሚኖረውን ለማግባት፣ ወንዱም እንደሱ በቁርባን ተወስና የምትኖረውን ለማግባት ከሆነ እየቆረቡ ለመኖር ይችላሉ።

2. ወንዱም ሆነ ሴቷ አብረው የነበሩበት የጋብቻ ቆይታቸውንና የተፋቱበትን ዋና ምክንያት ተናዘው እንደነሱ በሃይማኖትና በምግባር የሚወሰነውን ባል ወይም ሚስት በማግባት እየቆረቡ መንፈሳዊ ህይወታቸውን ማስቀጠል።  

3. ሁለተኛ ላለማግባት የወሰኑ ከሆነ ንፅህናቸውን እና ቅድስናቸውን ጠብቀው በየግዜው የነፍስ አባታቸውን እያማከሩ በስርዓተ ቁርባን ህይወታቸውን ማስቀጠል ይችላሉ። 

4. ሌላው ቀጣይ ህይወታቸውን ስርዓተ ምንኩስና በመወሰን መንፈሳዊ ልባዊ ውሳኔ ካላቸውም በስርዓተ ቁርባኑ ተወስነው ከቆዩ በኋላ በቤተክርስቲያን ቀኖና መሰረት የንስሓ አባታቸውን አማክረው ለምንኩስና የሚያበቃቸውን መስፈርት ሲያሟሉ እንዲመነኩሱ ይደረጋል ማለት ነው።

5. ዲያቆን ወይም ቄስ ሚስቱ ብትሞትበት ወይም ከሱ አቅም በላይ በሆነ ፈተና ቢፋታ፤ ያለ ሚስት የሚቀድሰውም ሆነ አባት የሚሆነው እስከ 6 ወር እንደሆነ በፍትሐ ነገስት ተወስኗል። ከዚያ በኋላ ግን ወይ መንኩሶ በክህነቱ ይቀጥላል፤ ወይም ፈተናውን የማይችለው ከሆነ ለቤተክርስቲያን አባቶች በግልፅ ተናግሮ በቅዱስ ቁርባን ተወስና የምትኖረውን ያገባል። ከዚህ በኋላ ግን መቀደስም ሆነ አባት መሆን አይችልም። የውጭ አገልግሎቱን እያከናወነ እየፀለየ ለመንግስተ ሰማያት የሚያበቃውን የቱሩፋት ስራ እነሰራ መኖር ይችላል።

ስለዚህ ጠያቂያችን በአጭሩም ቢሆን ይህንን ማብራሪያ እንዲደርስዎ ስላደረግን አንብበው እንዲረዱት በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን።

መልስ #2፦
በስርዓተ ቁርባን ተወስነው የሚኖሩ ባል እና ሚስት እግዚአብሔር ሳይፈቅድላቸው በሞት ወይም ደግሞ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ቢለያዩ፤ ቢቻል የመጀመርያው አማራጭ፦ ስጋቸውን ከኀጥያት ወይም ከዝሙት ጠንቅ የሚያሸንፉ ከሆነ በመጀመርያው አላማቸው ጸንተው ለመቀጠል እንደሚችሉ የቤተክርስቲያን ቀኖና ያዛል። የውስጥ ኑሯቸውን ግን በሞግዚት ወይም ሰራተኛ በመቅጠር ሊሸፈን ይችላል። ሁለተኛው አማራጭ፦ ስጋውን መግዛትና ማሸነፍ የማይችል ሰው በዝሙት ጠንቅ ተፈትኖ ከፈጣሪው ጋር ከሚጣላ በሃይማኖትና በስነ ምግባር የምትመስለውን/የሚመስላትን በነበረበት/በነበረችበት አላማ ማለትም በቅዱስ ቁርባን ተወስኖ/ተወስና አግብቶ/አግብታ መኖር ይችላል/ትችላለች። ማስረጃ፦ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ አገር ለሚኖሩ ክርስቲያኖች “ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ፦ እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው። ነገር ግን፤ በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና፥ ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ” (1ኛ ቆሮ 7፥8-9) በማለት በዝሙት መንፈስ እየተቃጠሉ ነፍሳቸውን ከሚወጉና ከፈጣሪያቸው ጋር የሚያጣላቸውን ስራ ከሚሰሩ ስርዓተ ቤተክርስቲያንን በጠበቀ መልኩ በኑሮ ወይም ደግሞ በአላማ የምትመስለውን/የሚመስላትን አግብቶ/አግብታ እንዲኖሩ እንደመከራቸው እንመለከታለን።

በዚሁ መሠረት ጠያቂያችን ቤተሰብ ሊኖሮት ቢችልም ባይችልም፣ በእድሜ ደረጃ ወጣትና መካከለኛ እድሜ ቢሆኑም ባይሆኑም ከፈጣሪ ቀጥሎ እራሶትን ያውቃሉና በክርስቲያናዊ ስነምግባር ለመኖር ለመረዳት መጠየቅዎ እጅግ የሚያስደንቅዎ እና የሚያስመሰግንዎ ስለሆነ ወደፊትም እግዚአብሔር ከፈተና እንዲጠብቅዎ መልካም ምኞታችንን እየገለጽን በመረጡት ክርስቲያናዊ ህይወት አብራዎት የምትቀጥለውን መርጠው በማግባት በቅዱስ ቁርባን ተወስነው መኖር ይችላሉ።