ስለ ቅዱስ ቁርባን ጥያቄና መልስ

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!" (ማቴ 3: 1-2)

ተከታታይ ትምህርትና ለጥያቄዎት ምላሽ ለማግኘት ቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

ቅዱስ ቁርባን ጥያቄና መልስ

ሰሞኑን በቴሌግራም ግሩፓችን የተነሱ ጥያቄዎች

ስጋ ደሙን ከመቀበል በፊት አንድ ክርስቲያን ማሟላት ወይም ማድረግ ያለበት ነገር፦

1/   የንሰሓ አባትቱን በማነጋገር ኀጢአት ካለ ንስሓ መግባት፣

2/  በስጋ ደሙ ከተወሰኑ በኋላ ወደ ኋላ መመለስ አይቻልምና ከቤተሰብዎም ይሁን ከማህበራዊ ኑሮ የሚያገናኙና የሚያጨቃጭቁ ቂም በቀል የሚያመጡ ሃሳቦች እንዳይኖሩ በተቻለ መጠን ሁሉንም ነገር ከመቁረብ በፊት ማስተካከል፣

3/   የተቀየምነው የተቀየመን፣ ያስቀየምነው  ያስቀየመን፣ የተጣላነው የተጣላን ማንኛውም ሰው ካለ በንስሓ አባት ወይም በሽማግሌ አማካኝነት ይቅርታ ጠይቆ ቂም በቀልን መተዉ፣ 

4/   በግል ህይወታችን ሁል ግዜ በቋሚነት የምንጸልየው የጸሎት ፕሮግራም ለኖረን ያሰፈልጋል። ሰይጣን እንዳይዋጋንና በቅዱስ ቁርባን ያገኘነውን በረከት እንዳያሳጣን የምንቋቋምበት መንፈሳዊ ተጋድሎ  በጸሎት ስለሆነ ነው፣

5/   ለመቁረብ ሁሉን ነገር አሳክተን ከወሰንን በኋላ ከምንቆርብ 3 ቀን በፊት ወንድ ይሁን ሴት ቤተሰብ ካለ  ከግንኙነት (ፆታዊ ግንኙነት) መቆጠብ ያስፈልጋል። 

6/   በሰጋ ወደሙ አንድ ሰው ተወሰነ ማለት እንደ ቤተክርስቲያን ስርአት ፈጽሞ ከአለማዊ ጠባይ ወጣ ማለት ስለሆነ በተቻለ መጠን አቀሙ የሚችለውን የበጎ ስራና የርህራሄ ስራ መስራት፣ ቅዱስ ቁርባን በበጎ ስራ መገለጽ ስላለበት ለድኆች ርህራሄ ማድረግ፣ ጠቃሚ የሆኑ መንፈሳዊ ስራ ላይ መሳተፍ፣ 

እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ሁሉ ለቅዱስ ቁርባን የምንበቃባቸው ከአንድ ክርስቲያን የሚጠበቁ መልካም እሴቶች ናቸዉ።

በተጨማሪም ለቅዱስ ቁርባን በምንቀርብበት ግዜ የምንለብሰው ልብሳችን  ለዚህ ብቻ ተብሎ የተዘጋጀ መንፈሳዊነትን ሊገልጽ የሚችል ራሱን የቻለ ልብስ ሊኖረን ይገባል። ንጹሕ ባሕርይ እግዚአብሔር ንጹሕ ነገርን ይወዳልና። በአለም ላይ ስንኖር በአለም ራሳችንን ለመግለጥ ልዩና ውድ ልብስ የምንገዛ ከሆነ ከዚህ በላይ በከበረው በእግዚአብሔር ጉባኤ ራሱን የቻለ ልብስ ቢኖረን፤ ባይኖረን እንኳ ያንኑ ልብሳችንን በጽዳት ልንይዘው ይገባል። አንፃራዊ ትርጓሜው በልብሱ አንፃር ውስጣችንንም ንጹሕ አድርገን ቀርበናል አንተም ንጹሕ ባሕርይ አምላክ ነህ ለማለት ነው።

ሴትም ሆነ ወንድ በሱባኤ እያለ እንዲህ አይነት ፈተና ቢገጥመው ፈተናው ባጋጠመው እለት የሱባኤውን ጋብ ፈጥሮ ሱባኤውን እንደገና በሚቀጥለው እለት መፈጸም ይችላል።  ኢሄ ካጋጠመው ከ 3 ቀን በኋላ ቁርባንም መቁረብ ይችላል። ነገር ግን ይህ የሚሆነው በህልም እርኩስ መንፈስ ለፈተነው እንጂ ራሱ አስቦት የፈጸመው ዝሙት ካለ ግን እንደገና ለንስሓ አባቱ ተናዞ ባለፈዉ ከተሰጠው ንስሓ በላይ በእጥፍ ቀኖና መቀበል እንዳለበት የቤተክርስቲያን ስርዓት ያዛል።

ጠያቂያችን እንዳሉት ሲቆርቡ ኑረው በመካከል ወደ ቅዱስ ቁርባን የማያቀርብ ነውር ካጋጠማቸው ወይም ደግሞ በኀጢአት ከተሰናከሉ ለጊዜው መቁረባቸውን አቁመው ወደ ንስሓ አባታቸው ቀርበው የፈጸሙትን በደል ከተናዘዙ እና ንስሓቸውን ከጨረሱ በኋላ መቁረባቸውን መቀጠል ይችላሉ። ነገር ገን ጥፋቱን በመደጋገም ሁል ጊዜ በንስሓ እመለሳለሁ በሚል መንፈስ መሄድ እንደሌለባቸው የቤተክርስቲያን ቀኖና ይደነግጋል። ዋናው ቁም ነገር ማንኛውም ክርስቲያን በምንም ይሁን በምን ከቅዱስ ቁርባን ላለመለየት በየጊዜው መንፈሳዊ አላማውን በማጽናት መታገል እንዳለበት እንመክራለን።

ቅዱስ ቁርባን የሚቀበል ማንኛውም ሰው ለንስሐ አባቱ መናገር ያለበት ራሱ የሚያውቀው ጥፋት ከሌለበት በስተቀር ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል በተዘጋጀ ቁጥር መናገር አይጠበቅበትምና ይህንን የጠየቁን አባላችን በዚህ ጉዳይ ላይ የሚያሳስብዎት ነገር የለም።

መልስ፦ ስርአተ ተክሊል አስባችሁ በመካከል ላይ ራሳችሁን ለመግዛት ሳትችሉ በመቅረታችሁ በመካከል ባደረጋችሁት የስጋ ድካም ከስርአተ ተክሊል በፊት የድንግልናችሁን ክብር ስላጣችሁት የፈፀማችሁትን ጥፋት ለንስሓ አባት በመናገር ቀኖና ከተቀበላችሁ በኋላ በስጋው ደሙ መጋባት ትችላላችሁ። ስርአተ ተክሊል ግን መፈፀም አይቻልም። ዋናው ነገር ለስጋዊ ስም እና ዝና ተብሎ እግዚአብሔርን በሚያሳዝን ሁኔታ የማይገባንን ስርአተ ተክሊል ከመፈፀም ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ እውነቱን አረጋግጠን የምናገኘው ክብር በስርአተ ተክሊል ከምናገኘው ክብር እኩል ስለሆነ የሚያሳስበን እና የሚያስጨንቀን ነገር አይኖርም።

መልስ. ፦ ጠያቂያችን ወደ ቤተክርስቲያን ለመግባት ከሚያስከለክሉ ነገሮች አንዱ በሕጋዊ የጋብቻ ስነስርዓት የተጋቡ ባል እና ሚስትም ቢሆኑ ፈቃደ ስጋቸውን በፈፀሙበት ቀን ወደ ቤተክርስቲያን ቅፅር ገብተው በጉባኤ መቀመጥ፣ ወይም ስጋ ደ
ሙን መቀበል፣ ፀበል መረጨት፣ መስቀል መሳለም፣ እምነት መቀባት አይችሉም። ምክንያቱም ምንም እንኳን ስርዓተ ቤተክርስቲያን ጠብቀው በአላትን አክብረው የፈፀሙት ፈቃደ ስጋ ስለሆነ ኀጢአት ባይሆንም እንኳን ሚስት ከባልዋ ጋር ወይም ባል ከሚስቱ ጋር ባደሩ በዚያኑ እለት ከቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ውጭ ሆነው መንፈሳዊ አገልግሎትን መከታተል እንጂ መግባት ክልክል ነው። ሁላችሁም የፕሮግራሙ ተከታታዮች እነዚህን የሚመሳስሉ ጥያቄዎችን የምንመልስላችሁ በልብ ወለድ ወይም ከፈጠራ ሳይሆን የቤተክርስቲያን ስርዓት እና ቀኖና ከሚያስተምሩ በቀኖና ስርዓት የተደነገገውን መሰረት በማድረግ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። እነዚህ መፅሐፍቶችም ፍትሐ ነገስት፣ የሐዋርያት ሲኖዶስ መፅሐፍ፣ የሃይማኖተ አበው እና ሌሎች የስርዓት መፅሐፍት እንደሆኑ ማስገንዘብ እንፈልጋለን።
መልስ ፦ አንድ ቆራቢ ክርስቲያን የክርስቶስን ቅዱስ ስጋ እና ክቡር ደም ከተቀበለ በኋላ ማድረግ ስለሚገባው ጥንቃቄ በሚመለከት የጠየቁን ጠያቂያችን ፤ ከዚህ በፊት  ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል በፊትና በኋላ አንድ ክርሰቲያን ማድረግ ያለበትን ጥንቃቄ በሚመለከት ከሞላ ጎደል ትምህርት የሰጠንበት ቢሆንም ከዚህ በፊት ደጋግመን መልእክት እንዳስተላለፍነው አቅማችን በፈቀደ መጠን እግዚአብሔር ከረዳን በእኛ መንፈሳዊ መልእክት ሰዎች ሁሉ በነፍስ የሚድኑ ሆነው ከተገኘ ለማገልገልና ለመታዘዝ ፈቃደኞች ስለሆንን  ለዚህ ጥያቄ ከተጨማሪ ማብራሪያ ጋር መልስ ለመስጠት ችለናል። አንድ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን በተቀበለበት እለት ገላውን በውሀ መታጠብ የለበትም ፣ ልብሱን አውልቆ እርቃኑን መሆን የለበትም፣ ከሰውነቱ ደም ማውጣት የለበትም ከሕግ ጋብቻ ጋር ቢሆንም የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ የለበትም ፣ በሰውነታችን ላይ ፈሳሽ ሊያስከትል የሚችል ከባድ ስራ መስራት የለበትም፣ እሩቅ መንገድ መሄድ የለበትም (እንደ ስራ ስለሚቆጠር) ፣ የሚያሰክር እና የበላነውን የጠጣነውን የሚያውክ መጠጥ መጠጣት የለበትም ፣ ጭቅጭቅ ያለበት አደባባይ ወይም የህዝብ ቦታ መሄድ የለበትም፣ ከሰው ጋር መጨቃጨቅ ሃይለ ቃል መነጋገር በአጠቃለይ ለፀብ የሚጋርድ ስራ ሁሉ ማድረግ የለበትም። 
እነዚህን የመሳሰሉ ሌሎችንም ከቁርባን በኋላ ማድረግ እንደሌለብን በቀኖና ቤተክርስቲያን ተደንግጎ ይገኛል። ዋናው ምክንያት የእግዚአብሔርን ቅድስና ወይም ቅዱስ ቁርባን ለማርከስ የሚችል ሌላ ነገር ኖሮ ሳይሆን፤ እኛ ግን ከክርስቶስ ስጋና ደም ጋር ስለተዋሀድን በኛ አላማ በቅናት ያበደው ሰይጣን ሊፈትነንና በሚያጠምደው መሰናክል ሊጥለን ስለሚችል ከሁሉ ነገር ተቆጥበንና ተሰብስበን ለዘላለማዊ ድህነት የወሰድነውን የክርስቶስን ቅዱስ ስጋና ክቡር ደም በልዩ ስርአት አክብረን የተወሰነውን ጊዜ ማሳለፍ ስላለብን ነው ። ሰይጣን ብዙ ጊዜ እኛን የሚጥልበት መሰናክል ረቂቅ ስለሆነ ክርስቲያናዊ ንቃት ኑሮን መጠንቀቅ ስለሚያስፈልግ ነው።
ስለኪዳን የተጠየቀውን በሚለከት በስርአተ ቤተክርስቲያን እንኳንስ ቆራቢ ቀርቶ ቅዳሴ የሚያስቀድስ ክርስቲያን ሙሉ ቅዳሴ አስቀድሻለው ማለት የሚችለው ከኪዳን ፀሎት ጀምሮ በመገኘት ነው። ካህኑም ኪዳን ሳያደርስ መቅደስ እንደማይችል ማንኛውም ክርስቲያን ከኪዳን ፀሎት ጀምሮ ሳይገኝ መቁረብ እንደሌለበት የቤተክርስቲያን ስርአት ያዛል። ከምንም በላይ ግን ቅድሚያ ሰጥተን ማድረግ ያለብን ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል የጊዜ ቀጠሮ አለመስጠትና በጥቃቅን ምክንያት ባለብን የውስጥ ፍርሀት ከቅዱስ ቁርባን መለየት እንደሌለብን በዚህ አጋጣሚ የአደራ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

መልስ፦  ማንኛውም ክርስቲያን በ40 ቀን በ80 ቀን በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጅነት ከተቀበሉ ጀምሮ ከቅዱስ ቁርባን እንዲለዩ አይፈቀድላቸውም። ቅዱስ ቁርባን ለነፍሳችን ዘለአለማዊ ህይወት በስጋዊ ህይወታችን ደግሞ በበረከት እና በእግዚአብሔር አጋዥነት እንድንኖር ስለሚረዳን በእግዚአብሔር ፈቃድ በሞት እስከምንጠራበት ዘመን ድረስ ቅዱስ ቁርባን መቀበል ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው። በመንፈሳዊ ህይወታችን ውስጥ በሃይማኖትም በምግባርም ያበረከትናቸው የትሩፋት ስራዎች ሁሉ ማሳረጊያውና መደምደምያው ቅዱስ ቁርባን ነው። ስለዚህ ጠያቂያችን ምናልባት በስራ ብዛት የማንበብ እድል ካልገጠመዎ በስተቀር ስለቅዱስ ቁርባን እጅግ ሰፊ ትምህርት ማስተላለፋችንን እናስታውሳለንና እሱንም መልሰው መላልሰው ቢመለከቱት ለጥያቄዎ ይበልጥ መልስ ያገኛሉ። በዋናነት አሁንም መረዳት ያለብዎት የሰው ልጅ በራሱ ድካም የኀጢአት ሸክም ሲበዛበት ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ ድፍረት እና ብቃት ስለሚያጣ ማንም ሳያርቀው ራሱን ከቅዱስ ቁርባን እያራቀ ስለሚሄድ የነፍስ ረሃብና መታረዝን ያስከትላል እንጂ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ማንኛውም ክርስቲያን ከህፃንነቱ ጀምሮ እስከ መጨረሻ የእድሜ ዘመኑ ከቅዱስ ስጋውና ከክቡር ደሙ እንዳይለይ ዘወትር ታስተምራለች ትመክራለች። እኛን ዘወትር ኀጢአት የሚያሰራን ጠላታችን ዲያብሎስ ስለሆነ የዘላለም ህይወት እንዳናገኝ ራሳችንን በኀጢአት ወጥመድ እየጠለፈ ወደ ዘለአለማዊ ሞት እንድንወድቅ ያስገድደናል ማለት ነው። ስለዚህ ጠያቂያችን ቅዱስ ቁርባንን መቀበል የማይቋረጥ ቀጣይነት ያለው መንፈሳዊ ስርአት እንደሆነ እንዲረዱት ይህን መልዕክት እንዲደርስዎ አድርገናል።

ስለ ቅዱስ ቁርባን ድረገጻችን ላይ ያንብቡ፦ https://yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን/

መልስ፦ መንፈስ የያዛቸው ሰዎች ሁሉ ጠያቂያችን እንዳሉት ከቅዱስ ቁርባን ሊከለከሉ አይችሉም። የአጋንንት መንፈስ በተለያየ ረቂቅ ምስጢር ሊያድር ይችላል። በፍጹም መንፈሳዊነትም የሚኖሩ ክርስቲያኖችን ሳይቀር መንፈስ በተለያየ መንገድ ሊዋጋቸው ይችላል። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ከቅዱስ ቁርባን ሊከለከሉ አይችሉም። ሆኖም ጨርሶ የለየላቸው ወደ እብደት ደረጃ ያደረሳቸው አይምሯቸውን አስቶ ልብሳቸውን አስወልቆ በሰው ዘንድ ነውር የሆነውን እያሰራና እያናገረ ሰይጣን የማረካቸውን ሰዎች በተለየ የፀሎት ስርዓት እና የጥምቀት ስርዓት ወደ አእምሮዋቸው እስከሚመለሱ ከቅዱስ ቁርባን እንዲከለከሉ ይደረጋል። ስለዚህ አይነት ስርዓት ፍትሐ ነገስት በሚበለው የቤተክርስቲን ቀኖና ስለህሙማን በሚናገረው አንቀፅ በተደነገገው ስርዓት እንዲሁም ስለ ቅዱስ ቁርባን መቀበል ስለሚገባቸው እና ስለማይገባቸው ሰዎችም የተደነገገውን የቤተክርስቲያን ስርዓት መመልከት ይቻላል።

መልስ፦ ለመቁረብ ያሰበው ሰው ለቄደር ጥምቀት የሚያበቃ ኀጢአት ካለበት አስቀድሞ ለንስሓ አባቱ ተናዞ ንስሓውን ጨርሶ ቄደር ተጠምቆ ሊቆርብ ይችላል። ነገር ግን ማንኛውም ክርስቲያን መቁረብ ስላለበት ብቻ ቄደር እንዲጠመቅ አይገደድም። የቄደር ጥምቀት የሚያስፈልግባቸው የሀይማኖት እና የስነምግባር ህጸጾችን ከዚህ በፊት የላክን ቢሆንም ምናልባት ጠያቂያችን አላዩት ወይም አላነበቡት ከሆነ በድጋሚ ከዚህ በታች ለግንዛቤ እንዲረዳዎት ልከንልዎታል።   
 
ሃይማኖትን በሚመለከት፦ 
 
 –  ጨርሶ ለይቶለት እና ሃይማኖቱን ክዶ ወደ ልዩ ልዩ ሃይሞኖት ከሄደ በኋላ በንስሐ ለመመለስ ቢፈልግ፣
 
–  በቤተክርስትያን ውስጥ እያለም ቢሆን በክህደትና በኑፋቄ የኖረና ከሃይማኖቱ ሕጸጽ ተመክሮና ንስሐ ተሰጥቶት የተመለሰ፣
 
–   ጋኔን የሚስብና የሚያስብ፣
 
–   በዛር መንፈስ የሚጠነቁልና የሚያስጠነቁል በዚህም ሰውን ሁሉ የሚያሰግድ እና የሚያስገብር፣
 
–    በልዩ ልዩ የአምልኮ ባእድ ቦታ አምኖ በተለያየ ቦታ ሄዶ
 
ክርስቲያናዊ ስነምግባርን በሚመለከት፦
 
–   እስላም ያገባ/ች፣ ካቶሊክ ያገባ/ች፣ ፕሮቴስታንት ያገባ/ች፣ (በእምነት የማትመስለውን ወይም የማይመስላትን የገባ/ያገባች)
 
–  በአምልኮ ባዕድ ለጣኦት የታረደውን የበላ፣ በሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ታርዶ የተዘጋጀውን ምግብ የበላ፣
 
–  በቅዱስ መጽሐፍ ለምግብነት ያልተፈቀዱ እንስሳትም ሆነ የዱር አራዊት የበላ
 
እነዚህ ከዚህ በላይ የተገለፁት በሃይማኖትና በስነምግባር ሕጸጽ ናቸው ተብሎ የሚታመኑ ስለሆነ የቄደር ጥምቀትም እንደሚያስፈልጋቸው በቤተ ክርስቲያን የቀኖና መጽሐፍት የተደነገጉ ስለሆነ ጠያቂያችን አንብበው ይረዱት።
መልስ፦ የተወደዱ የእግዚአብሔር ልጅ ጠያቂያችን ”ከሁለቱ አንዱ የቀደመውን ሐጢያት ቢደግም ከሁለት አንዱ ድጋሚ ንስሐ ገብቶ ለሚስጥር መቅረብ አይችልም?” ብለው ለላኩልን ጥያቄዎት መልስ ልንሰጥዎ ስለሆነ ሃሳብዎ ግልፅ እንዲሆንልን ትንሽ ማብራሪያ ሰጥተው በአስቸኳይ ቢልኩልን ምላሹን ወድያው እናደርሳለን።
መልስ፦ ጠያቂያችን ሃሳብ እና ዝሙት የሚለው ቃል በቤተክርስቲያን አተረጉጐም ብዙ ትርጉም አለው ። ይህ ማለት አንድ ክርስቲያን የዝሙት ስራ ሊሰራ ፣ሰው ሊገድል ፣ ገንዘብ ሊሰርቅ፣ አምልኮ ባዕድ ሊፈፀም ወይም ለጣኦት ሊያመልክ ፣ ሊያስጠነቁል፣ ሊጠነቁል ፣ሊያሟርት የቀን ቀጠሮ ይዞ እግዚአብሔርን ለማታለልና ለመደለል ወይም እግዚአብሔርን እንደ አላዋቂ ለመቁጠርና ለመፈታተን ወደ ቅዱስ ቁርባን መቅረብ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ፣ ማስቀደስ፣ መጸለይ ከንቱ ነው ማለት ነው። ሃሳብ ማለት ፍጹም መላ ሕይወታችንን ለኀጢአት ተገዢ ለማድረግ መወሰን ማለት ነው :: ነገር ግን አንዳንድ ግዜ በሃሳብ እየተዋጋን ታግለን እያሸነፍነው በአላማችን የምንኖራቸውን እንደማይመለከት መገንዘብ ያስፈልጋል። ምክንያቱም የሰው ልጅ የሚያስተውል እና ሁሉን ለይቶ የማወቅ ጥበብ የተሰጠው የሚያስብ ስለሆነ በአይናችን ያየነው ነገር ወዲያውኑ በሃሳብ ሊፈትነን ይችላል ፤ነገር ግን ከዋናው አላማችን እስካልወጣን ድረስ ውስጣችንም ስለሚፀፀትበት እና የህሊና ንስኀም ስለምንገባበት ኀጢአተኞች ሊያስብለን እንደማይችል መረዳት ያስፈልጋል፡፡
ከቅዱስ ቁርባን በፊት የሚያስፈልግ ዝግጅት እና ከቆረብን በኋላ ምን ምን ማድረግ እንዳለብን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ትምህርት እንዳስተላላፍን እናስታውሳለን። የሆነ ሆኖ ምናልባት ጠያቂያችን ያንን አልተከታተሉ ከሆነ አሁንም በተጠየቅነው መሰረት የምናስተላልፈው መልዕክት ፦ 
 
1ኛ/ ቅዱስ ቁርባን ከመቀበላችን በፊትከማንኛውም የስጋ ኀጢአት መራቅ ፤ ማለትም ከዝሙት ድርጊት፣ ከነፍስ ገዳይነት፣ ከስርቆት፣ ከሀሜት፣ ከሱሰኝነት፣ ከአጭበርባሪነት፣ ከሀሰተኛነት፣ እና ከመሳሰሉት የሥጋ ስራዎች መራቅ :: 
 
2ኛ/   ቅዱስ ቁርባንን በድፍረት ተቀብለን እዳ እንዳይሆንብን ከመቀበላችን በፊት ወደ ንስኀ አባታችን ቀርበን እራሳችንን ማስመርመርና ተግሳፅ ተቀብለን የንስኀ ቀኖና መውስድ:: 
 
3ኛ/ ቅዱስ ቁርባን ከመቀበላችን በፊት በተከታታይ የሚስጢረ ቁርባን ትምህርትን መማር ፤በአጠቃላይ የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ፣ወደ ቤተክርስቲያን መሄድን ማዘውተር፣ መፀለይ፣ መፆም፣ መስገድ ።
 
4ኛ / ቅዱስ ቁርባን ከመቀበላችን በፊት በትዳት ብንኖር እንኳን ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ከ3 ቀን በፊት መቆጠብ ከ18 ሰአት በላይ መፆም፣ የሚያሰክሩ እና አይምሮ የሚያደንዙ መጠጦችን አለመጠጣት እነዚህን የሚመስሉ ተዛማጅ ድርጊቶችን አለመሰራት። 
 
5ኛ/ ቅዱስ ቁርባን ከተቀበልን በኋላ (ከቆረብን በኋላ)  በተቀበልንበት እለት ገላችንን በውሀ መታጠብ የለብንም ፣ ልብስን አውልቆ እርቃን መሆን የለብንም፣ከሰውነታችን ፈሳሽ ነገርና ደም፣  ማውጣት የለብንም፣ ማስታወክ የለብንም፣ እንዲሁም ከሕግ ጋብቻ ጋር ቢሆንም እንኳን እስከ 2 ቀን የግብረ ሥጋ ግንኙነት አለማድረግ ፣ በሰውነታችን ላይ ፈሳሽ ሊያስከትል የሚችል ከባድ ስራ መስራት የለብንም፣ እሩቅ መንገድ መሄድ የለብንም (እንደ ስራ ስለሚቆጠር) ፣ የሚያሰክር እና የበላነውን የጠጣነውን የሚያውክ መጠጥ መጠጣት የለብንም ፣ ጭቅጭቅ ያለበት አደባባይ ወይም የህዝብ ቦታ መሄድ የለብንም፣ ከሰው ጋር መጨቃጨቅ ሃይለ ቃል መነጋገር በአጠቃለይ ለፀብ የሚጋርድ ስራ ሁሉ እና እነዚህን የመሳሰሉ ሌሎችንም ከቁርባን በኋላ ማድረግ የለብንም። 
 
 በተጨማሪ ከዚህ በፊት በዚህ ጉዳይ ያስተላለፍናቸውን መልዕክቶች ከላይ አንድ አባላችን ሼር ስላደረገልዎት አንብባው እንዲረዱ በአፅንዎት እንመክራለን :: ከዚህ ሌላ ያልተረዱት ጉዳይ ካለ በውስጥ መስመር ሊያገኙን ይችላሉ።
 
ስለ ቅዱስ ቁርባን ያስተላለፍነውን ተከታታይ ትምህርት ድረገጻችን ላይ ያንብቡ፦  Yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን

የተከበሩ ጠያቂያችን ወንድ ልጅ ሆነ ሴት ልጅ በ 40ና በ80 ቀን ክርስትና ተነስተው ቅዱስ ቁርባንመቀበል ከጀመሩበት እለት ጀምሮ እስከ  መጨረሻው ድረስ ከቅዱስ ቁርባን መለየት የለባቸውም። ሴት ልጅ ብትሆንም የወር አበባ ማየት ከጀመረች ከፈሳሹ ንፁህ የምትሆንበትን ጊዜ ትጠብቃለች እንጂ የወር አበባ በማየትዋ ብቻ ከቅዱስ ቁርባን እንድትርቅ የሚያደርጋት ምክንያት የለም። ሴትም ሆነ ወንድ ቅዱስ ቁርባን እንዳይቀበሉ የሚያደርጋቸው ምክንያት ለአካለ መጠን መድረሳቸው ብቻ ሳይሆን ለአካለ መጠን ደርሰውም ድንግልናቸውን ጠብቀው በስርዓት የሚኖሩ ከሆነ መቁረብ ይችላሉ። ነገር ግን በዝሙት እና በልዩ ልዩ ኢክርስቲያናዊ ምግባር ከወደቁ ግን በአባቶች ተመክረውና ተገስፀው ንስኅ እንዲገቡ ተደርጎ ሁለተኛ ወደ ጥፋት እንዳይገቡ ንስኅ ተቀብለው እንዲመለሱ ከተደረገ በኅላ ብቻ እንዲቆርቡ ይደረጋል ማለት ነው።

ጠያቂያችን፤ 
1ኛ/ ከቁርባን በፊት መደረግ የሚገባው ጥንቃቄ ጡት የሚጠባ ህፃን ከሆነ ወይም አራስ ህፃን ከሆነ ቅዳሴ ከተገባ ጊዜ ጀምሮ ወይም ወንጌል ከተነበበት ጀምሮ ጡት እንዳይጠባ ማድረግ ነው። 
 
2ኛ/ ተጨማሪ ምግብ ለመብላት የደረሰ ህፃን ከሆነ በጠዋት ቅዳሴ ምግብ እንዳይበሉ ተከልክሎ  እንዲቆርቡ ይደረጋል። ህጻናት የሚቆርቡት የጠዋት ቅዳሴ ሲሆን መሆን አለበት ምክንያቱም ጾመው መዋል አይችሉምና።
 
3ኛ/ ከቆረቡ በኋላ ከዚህ ቀደም ስለ ቅዱስ ቁርባን በተገለፀው መሰረት፦ በቆረቡበት እለት በልዩ ጥበቃ ማለትም እማይሆን ነገር እንዳይበሉና እንዳይጠጡ፣ እራቁታቸውን እንዳይሆኑ፣ በቁርባንጊዜ የለበሱትን ልብሳቸውን እንዳያወልቁ፣ ከሰውነታቸው ደም እንዳይወጣ፣ በውሀ እንዳይታጠቡ፣ ሜዳ ላይ ወጥተው እንዳይጫወቱ፣ ብቻቸውን እሩቅ ቦታ እንዳይሄዱ እነዚህን የሚመሳስሉ ጥንቃቄዎች ሊደረግላቸው ይገባል።
 
4ኛ/ ቅዱስ ቁርባን ከተቀበሉ በኅላ የቅዳሴው ስርአት ተፈፅሞ ‘በሰላም ወደ የቤታችሁ ግቡ’ ተብሎ ስንብት ከተደረገ በኋላ ወድያውኑ ወደሌላ እንቅስቃሴ  ከመገባቱ በፊት የተዘጋጀ ምግብ ማቁረር (መቅመስ) ይገባል። ፀበል መጠጣት ግን ከቅዱስ ስጋውና ከክቡር ደሙ ቀጥሎ የምንቀበለው ስለሆነ የቁርባኑ አካል ነው እንጂ እንደ ምግብ የሚቆጠር እንዳልሆነ መረዳት አለብን።
 
5ኛ/ ተገቢው ጥንቃቄ ከተደረገ በተከታታይ ቀን መቁረብ ይቻላል የሚከለክል ህግም የለም። ዋናው ነገር ቅዱስ ቁርባን በድፍረት የማንቀበለው ስለሆነ ህፃናትም ቢሆኑ እነሱ ሳይሆኑ እኛ ወላጆቻቸው እና ካህናት  ስለነሱ የሚያስጠይቅ ሃላፊነት ስላለባቸው ለቁርባኑ የሚያበቃ ጥንቃቄ ማድረግ ከቻልን በተከታታይ ከማቁረብ የሚከለከል ህግ የለም።  
ህጻናትን በተከታታይ ለማቁረብ ስለሚደረግ ጉዳይ ከመቁረባቸው በፊት ፅዳታቸውን ጠብቀን በተከታታይ እንዲቆርቡ በምናደርግበት ጊዜ እለት እለት ሳይታጠቡ ቢቆርቡ እንደመንፈሳዊ ወይም ሃይማኖታዊ ስርዓት ነውር ሆኖ የሚቆጠር አይደለም። ምናልባት እኛ በራሳችን የህፃናቱን ፅዳት ወይም ንፅህና ለመጠበቅ የምናደርገው እለታዊ ነገር ካለም የግድ መጨናነቅ ሳይኖርብን አራርቀን ማቁረብ እንችላለን። በገዳም ያሉ መናኞች እኮ አንዱ ተጋድሏቸው ለስጋዊ የሚያስፈልግ ፅዳት ላይ አንዳችም ሳይጨነቁ ነፍሳቸው ለምትቀደስበትና ለምትነፃበት ህይወት ነው የሚጋደሉት። ስለዚህ በልብሳችን እና በአካላችን በምናደርገው ጥንቃቄ መልካም ነገር ቢሆንም ይህ ብቻ ግን ፅድቅ ሊሆን አይችልምና ጠያቂያችን እንዲህ አይነት ጥቃቅን ነገር ብዙም ሳያሳስብዎት በዋናነት በውስጣችን ያለው ፍጹም እምነት ብቻ ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበን መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። ለምሳሌ አንድ ሰው ልጁን አቁርቦ ውሃ ቢያስነካ ወይም ራሱ ውሃ ቢነካ ፈፅሞ ኅጢአት ይሆንበታል ወይም የእግዚአብሔርን ክብር ያሳጣል ማለት ሳይሆን የውስጣችንን ቅድስናና ንፅህና ለማጠየቅ ሲሆን በአካለ ሥጋችን የምናደርገው ፅዳትም ለእግዚአብሔር መታዘዝን ለማመልከት ነው። ስለዚህ ጠያቂያችን የዚህን ጥያቄ ሃሳብ ከሃይማኖታዊ ወይም መንፈሳዊ ጉዳይ ጋር ሳያያይዙት፤ ከዚህ በፊት ህፃናትን ሲቆርቡ ከቅዱስ ቁርባን በፊትና በኋላ መደረግ ስላለባቸው ተግባሮች የላክንልዎትን መንፈሳዊ መመሪያ በመከተል እና ይህን ማብራረያ በመረዳት በአግባቡ መፈፀም ይችሉ ዘንድ ይህን መልዕክት ልከንልዎታል። በተጨማሪም ከዚህ በፊት ስለ ቅዱስ ቁርባን ያስተላለፍነውን መሰረታዊ ትምህርት እንዲመለከቱት እንመክራለን።
 
 
ጃንደረባ ማለት በሌላ የአገላለፁ ትርጉም ድንግል ማለት ነው።ይህ ማለት ህገ ጋብቻን ንቀው ወይም ትተው ብቻቸውን በድንግልና ህይወት ለመኖር የወሰኑ የእግዚአብሔር ሰዎች ናቸው። ጃንደረባነት በ3 አይነት መንገድ ሊገለፁ ይችላል።1ኛ/ ከእናታቸው መሀፀን ጀምሮ አካላዊ የስሜት ምልክት ሳይኖራቸው ጀንደረባ ሆነው የተወለዱ አሉ።2ኛ ደግሞ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ወይም በሌላ ምክንያት በሰው አካላቸው ተሰልቦ ጃንደረባ የሆኑ አሉ። 3 ኛ/ ስለ መንፈሳዊ የእግዚአብሔር መንግስት ብለው (ስለ መንግስተ ሰማያት ብለው) ራሳቸውን ጀንደረባ ያደረጉ  አሉ። ስለዚህ ጉዳይ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በፈሪሳዊያን ዘንድ ስለ ጋብቻ በቀረበለት ጥያቄ መነሻነት ማግባትም ሆነ አለማግባት ወይም ጃንደረባ ሆኖ መኖር ከእግዚአብሔር ዘንድ ለተሰጣቸው መሆኑን በሰጣቸው መልስ የጃንደረባን ምስጢር ነግሮናል።(ማቴ 19፥10-11) ስለዚህ ጠያቂያችን ማንኛውም ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ሀብት ፀጋ ምን እንደሆነ ለይቶ በማወቅና በመረዳት በፀጋው መኖር አለበት። በጋብቻ ተመስርቶ ትውልድ ማትረፍም ከእግዚአብሔር ፍቃድ የተነሳ እንጂ ሰው በራሱ አቅም ወይም ችሎታ ያመጣው ህልውና አይደለም።በሌላም በኩል አለምን ንቀው ሁሉን ትተው በዱር በገዳም እንደሚኖሩ ባህታውያን ወይም መናንያን ሳያገቡና ዘር ሳይተኩ በጃንደረባነት የሚኖሩ ፍጹማን የእግዚአብሔር ሰዎች ደግሞ የተሰጣቸው ፀጋ ዘመናቸውን ሁሉ እግዚአብሔርን ማገልገልን በነፍስም በሥጋም ለእግዚአብሔር በመገዛት ለማገልገል ከልጅና ከትዳር የበለጠ ስም ወይም ክብር ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኛሉ።ነብየ እግዚአብሔር ኢሳያስ ጃንደረባን “እነሆ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ አይበል፤ እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያስኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረባዎች እንዲህ ይላልና ፤ በቤቴ በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ የማይጠፋም የዘላለም ስም ሰጥቻቸዋለሁ” በማለት ለጀንዳረባዎች በጋብቻና በትዳር ከሚገኘው ትውልድ በላይ በእግዚአብሔር ዘንድ ለዘላለም የማይጠፋ ስም እንደሚሰጣቸው ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል (ኢሳ 56፥3-5) ስለዚህ ጠያቂዎችንም ሆኑ የዚህ የዮሐንስ  ንስኀ ድረ ገፅ መንፈሳዊ ፕሮግራም አባሎቻችን ስለ ጃንደረባ በዚህ ትረዱት ዘንድ ይህን አጭር ማብራሪያ ልከንላችኋል።
 

ጠያቂያችንም ሆኑ የዚህ የዮሐንስ ንስኀ ድረገፅ መንፈሳዊ ፕሮግራም ተከታታዮች ሁላችሁም መረዳት ያለብን በልማድ የምናደርገውን ነገር የሃይማኖታችን ህግ ከሚለን ስርዓት ለይተን ማየት አለብን። ምክንያቱም ብዙ ጥፋቶቻችን ፦1ኛ/ በቂ የሃይማኖት ትምህርት ካለማግኘት የተነሳ ፣ 2ኛ ደረጃ የሃይማኖታችን ስርአት እንደሚከለክለን እውቀቱም እያለን ያዋቂ አጥፊ በመሆን ብዙ ጥፋቶችን በድፍረት ስንፈፀም መታየት የተለመደ ነው። ኀጢአትን ደጋግመው ከሰሩት እንደ ፅድቅ እንቆጥረዋለን ማለት ነው።ይህንን ቅድመ ሁኔታ ልንገልፅበት የቻልነው ዋናው ምክንያት በስርዓተ እርግዝና ጊዜ ማንኛውም ሰው ራሱን መግዛት ስለሚያቅተው ጥፋት እንደሚፈፅም የሚታወቅ ቢሆንም እንደ ሃይማኖታችን ቀኖና ግን ራስን መግዛትና ሥጋዊ ስሜትን በመቆጣጠር በእርግዝና ወቅት የወንድ እና የሴት ተራክቦ የተከለከለ ነው።ይህ ሲባል የሰው ልጅ ለኀጢአት የሚሰማማ ደካማ ሥጋን ለብሶ የተፈጠረ ስለሆነ የዚህ አይነቱ ስህተት በሁሉም ዘንድ እንደሚያጋጥም በመንፈሳዊ አይናችን መገመት እንደምንችል ይታወቃል :: ነገር ግን ብዙ ሰዎች ስለተባበሩበት ኀጢአት ፅድቅ ሊሆን ስለማይችል እውነተኛውና ትክክለኛው ነገር ከላይ የተገለፀው መሆኑን ትረዱ ዘንድ ይህን አጭር መልዕክት ልከንላችኋል።

ጠያቂያችን በጋብቻ ተወስነው ኑሯቸውን ሲኖሩ ከቆዩ በኋላ በሆነ አጋጣሚ የጋብቻ ቃል ኪዳናቸውን ቢያፈርሱና (ቢፋቱና) ሌላ የጋብቻ ቃል ኪዳን ለመፈጸም ቢፈልጉ ቀደም ሲል ያሳለፉትን የጋብቻም ሆነ የግል ህይወታቸውን ለንስኀ አባታቸው በመናዘዝ አባታዊ እና መንፈሳዊ ምክር ተቀብለው ንስኀ የሚያስፈልጋቸው ከሆነም የንስኀቸውን ቀኖና ተቀብለው ከፈፀሙ በኋላ ፤ ሌላ 2ኛ ጋብቻ ለመፈጸም በፈልጉ ከንስኀ አባታቸው ወይም ደግሞ ስለ ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖት እውቀት ያላቸውን መምህር በማነጋገር ለ2ኛ ጊዜ የሥርዓተ ጋብቻ ቃል ኪዳናቸውን ለመፈጸም ንስኀ ገብተው በቅዱስ ቁርባን ተወስነው መፈጸም ይችላሉ። ስለዚህ በስርዓተ ተክሊል የሚፈፀምና በንስኀ የሚፈጸም ስርአት ጋብቻ ልዩነቱ ከዚህ አንፃር እንደሆነ ጠያቂያችን እንዲገነዘቡት በማለት ከዚህ በፊት ከላክንልዎ ምላሽ በተጨማሪ ላቀረቡት ጥያቄ ይህን ማብራሪያ ልከንልዎታል።

ጠያቂያችን ፤ ቅዱስ ቁርባን ሲቀበሉ የለበሱትን ነጠላ ወይም ልብስ በሌላ ጊዜ ቅዱስ ቁርባን ሲቀበሉ መልበስ እችላለሁ ወይ? በማለት በእኛ በኩል ምክር እንድንሰጥዎ ያቀረቡትን ጥያቄ ይመለከታል።

ወደ ቅዱስ ቁርባን እና ወደ እግዚአብሔር ቤት ስንቀርብ ራሱን የቻለ ለዚህ አገልግሎት ብቻ የሚውል ሙሉ ልብስ ቢኖረን ይመረጣል። ምክንያቱም ይህን በማድረጋችን በውስጣችን ፍጹም የሆነ ልባዊ ሃይማኖትና ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዳለ ያመለክታልና። ስለዚህ ጠያቂያችን ያንን በቁርባን ጊዜ የለበሱትን ነጠላ ሌላ ጊዜም እያጠቡ እርሶ እንዳሉት መገልገል ይችላሉ።

በሌላም በኩል የተለየ ልብስ ወይም ትርፍ ልብስ የሌላቸው በድህነት ያሉ ክርስቲያኖች ያንን ያላቸውን የድህነት ልብሳቸውን ባላቸው አቅም በንፁህ አጥበው መቁረብ እንዳለባቸው ደግሞ መዘንጋት የለበትም። ምክንያቱም ገና ሀብታሞች እንደሚለብሱት የተለየ ልብስ የለንም በሚል ምክንያት ከቅዱስ ቁርባን እርቀው መኖር ስለማይገባቸው ነው።

ስለዚህ ጠያቂያችን ሀሳቡን በዚህ እንዲረዱት ይህን አጭር መልዕክት ልከንልዎታል።

መልስ፦ ጠያቂያችን አንድ ኦርቶዶክስ ክርስቲየን ቅዱስ ቁርባን ከተቀበለ በኋላ 1ኛ/ የማቁረሪያ ምግብ እስከሚቀምስ ድረስ ከሰው ጋር መነጋገር የማይችልበት ምክንያት መለኮታዊ እሳት የተዋሀደውን ቅዱስ ሥጋና ክብር ደሙን በተቀበለ ጊዜ ለነፍስ መድኅኒት ለስጋም በረከትን የሚያመጣውን የከርስቶስን ስጋውንና ደሙን ተቀብሎ ሌላ የሰውኛ ንግግርን መነጋገር ሃሳብን ማውጣትና ማውረድ ፈፅሞ ስለማይፈቀድ ነው። ከቅዱስ ቁርባን በላይ የሚከብር ነገር ባለመኖሩ በብዙ ፈተና የረከሰውን ህይወታችንን የቀደሰውንና የተዋረደውን ማንነታችንን ያከበረውን ቅዱስ ቁርባን ማቃለል ለኛም ከቅዱስ ስጋውና ከክቡር ደሙ ያገኘነውን ክብር ስለሚያሳንስብን ባጠቃላይ አፋችንን የመሸፈናችን ነገር ክፉ ከመናገር፣ ክፉ ከማሰብ፣ ክፉውን ድርጊት ከመፈፀም የራቅን ለመሆናችን የሚያመለክት ስርዓት ነው። ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ እህል ውሀ ቀምሰንም ቢሆን ከአንደበታችን የሚወጣው ነገር የተቀደሰና በጎ ነገር ሊሆን ይገባዋል ወይም ክፉ ሃሳብና ክፉ ድርጊት ከኛ እንዳይወጣ ያስፈልጋል ለማለት ነው። በዋናነት እንደማስረጃ የምናደርገው ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ቤዛ ለመሆን በመስቀል ላይ ቅዱስ ስጋውን ቆርሶ ክቡር ደሙን አፍስሶ ለኛ ያለውን ፍቅር በመስቀል ካረጋገጠ በኋላ 3 መአልትና 3 ሌሊት በከርሰ መቃብር በቆየ ጊዜ ቅዱሳን ሐዋሪያትና ሌሎችም ተከታዮቹ በሀዘንና በለቅሶ የላመ የጣመ እህል ውሀ ሳይቀምሱ መቆየታቸውን የሚያመላክት ነው። ስለዚህ ዛሬ ለኛ ህይወት መድሃኒታችን የሚሆነው የሚሰጠን የተገኘው መራራ በሆነ የመስቀል መከራ ስለሆነ እኛም ዛሬ ከሚበላ ከሚጠጣ፣ ከነገር እና ከክፉ ድርጊት ራሳችንን ቆጥበን መቀበል እንደሚገባን የሚያመለክት ነው። 

በ 2ኛ/ ደረጃ የተቀደሰ ሰላምታ አስፈላጊ በሆኑ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በአካልም ሆነ በስልክ እኛንም ሆነ ቁርባኑን አያረክሰውም፤ ብቻ በህሊናችን ራሳችንን ለእግዚአብሔር ማስገዛት ያስፈልጋል ለማለት ነው።

3ኛ/ ቅዱስ ቁርባን የተቀበለ ሰው ከቁርባን በኋላ ብቻውን አይሄድም የሚባለው የቆረበ ሰው ከምንም በላይ ህይወቱ የከበረና መንፈሳዊ ሙሽራ ስለሆነ የተለየ ክብርም ስለሚያስፈልገው ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን አማናዊ ክብር ለማመልከት ነው። በሌላ በኩል በዚህ ህይወትና መድኅኒት በሆነው በቅዱስ ቁርባን የከበረውን ሰው ሰይጣን በክፉ መንፈስ በጠላትነት ስለሚቃወመው አንደ አንዳንድ ባለስልጣናት ወይም በሙሽርነት የከበረ ሰው ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ እንደሚያስፈልጉት ሁሉ ከዚህም በላይ የሰው ልጅ ፍጹም ሰማያዊ ክብር የሚያገኝበትን ቅዱስ ቁርባን በተቀበለ ጊዜ ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ ስለሚያስፈልገው ብቻ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሌሎችም ብዙ አይነት ምሳሌና ሃሳብ  ማቅረብ ቢቻልም ለጊዜው ግን ጠያቂያችን ሃሳቡን በዚህ እንዲረዱትና ለተጨማሪ መረጃ በቀኖና ቤተክርስተያንም ዝርዝር ሁኔታውን መመልከት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን። 

ይሁን እንጂ መረዳት ያለብን ከላይ የገለፅናቸው ምክንያቶች ለስጋ ደሙ ክብር ከመስጠት የተነሳ እንጂ ስጋ ደሙን የተቀበለ ሰው ለሌላ አደጋ የተጋለጠ ይሆናል ብሎ ማሰብ የተሳሳተ ነው። እንዲያውም ከምንም በላይ ስጋውን ደሙን የተቀበለን ሰው የአጋንንት መንፈስም ሆኑ ሌላ ሃይል እንዳይቃወመው ታላቅ ግርማ ሞገስና ሃይልና ጉልበት ስለሚሆነው ብቻውን ስለሄደ ችግር ያጋጥመዋል ብሎ ማመን የተሳሳተ ሃሳብ ነው። በየገዳማትም ሆነ በየአብያተክርስቲያናት ቅዳሴ አስቀድሰው ቅዱስ ቁርባን የሚቀበሉና የሚያቀብሉ ብቻቸውን አገር አቋርጠው ሲሄዱ እነሱ ለሌላው ክብርና ሞገስ ይሆናሉ እንጂ በነሱ ላይ የሚደርስባቸው አንዳችም ክፉ ነገር የለም።

https://yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን/

ስለ ቅዱስ ቁርባን የጠየቁን አባላችን ሆይ፤ በመጀመሪያ ከዚህ ቀደምም ደጋግመን እንደገለፅነው ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በ40 ቀን እና በ80 ቀን የእግዚአብሔርን ልጅነት በጥምቀተ ክርስትና አግኝቶ በቅዱስ ቁርባን ከታተመበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መጨረሻ የዘመኑ ፍፃሜው ድረስ ከቅዱስ ሥጋውና ከክቡር ደሙ መለየት እንደሌለበት ክርስቲያናዊ ግዴታውም እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። ይህም በቅዱስ መፅሐፍ በግልፅ ታዟል። ምክንያቱም የጌታን ቅዱስ ሥጋ ካልበላን ክቡር ደሙን ካልጠጣን የዘለዓለም ህይወት የለንም።  ሰው በሥጋው በህይወት ለመኖር ዘወትር ለስጋው ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ በነፍሱም የዘላለም ህይወት ለመውረስ የነፍሳችን ምግብ ቅዱስ ቁርባን ስለሆነ ነፍሳችን ደግሞ ቅዱስ ቁርበንን ካጣች እንደሞተች ወይም ህይወት እንደሌላት ማመን ያስፈልጋል።

ይሁን እንጂ ቅዱስ ቁርባን በሰው ህይወት ሲገለፅ በህፃንነት እድሜ ደረጃ ያሉ ክርስቲያኖች ሲቆርቡ ቆይተው አካለ መጠናቸው ወደ አዋቂነት ሲደርስ ይበልጥ ስለሚስጥረ ቁርባን ተምረውና አውቀው መቀጠል ሲገባቸው፤ ይባስ ብለው ቅዱስ ቁርባን እንደማይጠቅም በማሰብ ይሁን ባለማወቅ ባይገባንም ከቅዱስ ቁርባን የሚርቁ ብዙዎች ናቸው። ይሄም ነገር የቤተክርስቲያን አባቶች በእግዚአብሔር ቤት ዘንድ የሚያስጠይቃቸው የክህነት ሃላፊነት ነው። ምእመናንም ቢሆኑ የቅዱስ ቁርባንን ዘለዓለማዊ ህይወትነቱ እየተነገራቸው እያወቁና እየተረዱ ከቅዱስ ቁርባን የሚርቁ ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድ ይጠብቃቸዋል።

ስለዚህ ጠያቂያችን ምንም እንኳን የሰው ልጅ በልዩ ልዩ ኅጢአት የመወደቁ ሁኔታ የደካማ ሥጋ ባህሪ ቢሆንም በሰራነው ኅጢአት ተፀፅተን ወደ ንስኅ ህይወት ተመልሰን ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል የሚለክለን ህግ ግን የለም። ጠያቂያችን እንዳሉት ቅዱስ ቁርባን ሲቀበሉ ቆይተው በመሃከሉ በዝሙት ተሰናክለው ከቅዱስ ቁርባን ከራቁ ወይም ርቀው ከቆዩም አሁን ማድረግ ያለብዎት ፦

1ኛ የክርስቶስ ሥጋና ደሙ ከኅጢአት የሚያፀዳና የሚቀድሰንና የሚያነፃን እንጂ የሚያርቅ ስላልሆነ በኅጢአት መውደቆትን ቢያምኑም በንስኅ ተመልሰው ሥጋ ደሙን የመቀበሉን ስርዓት እንደገና መቀጠል አለብዎት።

በ2ኛ ደረጃ ሚስት ለማገባት እቅድ ካለዎት በሥጋ ህይወት ውስጥ ባይገደዱበትም እንደ መንፈሳዊነት ግን ወደ ትዳር ህይወት ሲገቡ በቅዱስ ቁርባን ቢሆን በሥጋም ሆነ በነፍስ በረከትንና ክብሮትን ያበዛዋል።

በ3ኛ ደረጃ ማግባት ካልፈለጉም ስለሰሩት ኅጢአት በንስኅ የኅጢአት ስርየት በማግኘት ብቻዎትን በቁርባን ተወስነው መኖር ይችላሉ።

ለሁሉም ነገር ግን ስለ አንቀፀ ንስኅ  ጠንቅቀው የሚያውቁ  የቤተክርስቲያን አባቶች (ሊቃውንት) ሁልጊዜ በማነጋገርና በማማከር ትምህርት እያገኙ ማንኛውንም ነገር እንደ ስርዓቱና እንደ ህጉ ማስቀጠል የሚችሉበትን ፕሮግራም እንዲያደርጉ ይህን አጭር መልእክት ለእርስዎ እና ለዮሐንስ ንስኅ ድረገፅ መንፈሳዊ ፕሮግራም ተከታታይ አባሎቻችን ሁላችሁም አንብባችሁ ትረዱት ዘንድ መልዕክቱ እንዲደርሳችሁ አድርገናል።

 

https://yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን/

ጠያቂያችን እንዳሉት ንስኀ ገብተው ለቅዱስ ቁርባን ከበቁ በኋላ ተመልሰው በኀጢአት ከተሰናከሉ ወይም ሲቆርቡ ኑረው በመካከል ወደ ቅዱስ ቁርባን የማያቀርብ ነውር ካጋጠመዎት ለጊዜው መቁረብዎን አቁመው ወደ ንስኀ አባትዎ ቀርበው የፈጸሙትን በደል ከተናዘዙ እና ንስኀዎትን ከጨረሱ በኋላ ለመቁረብ መቀጠል ይችላሉ። ምክንያቱም አንድ ሰው ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ እዳ በደል እንዳይሆንበት አስቀድሞ ከኀጢአት እና ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ ከሚከለከልባቸው ጥፋቶች  መራቅ አለበት። ምክንያቱም ቅዱስ ቁርባን ከተቀበለ በክርስቲያናዊ ህይወት ውስጥ የመጨረሻው ክብር ላይ የደረሰ ሰው ነውና፤ ይሄንን ታላቅ ክብር በማቃለል ተመልሶ የማይገባውን ነውር መፈፀም ማለት ግን ታጥቦ ጭቃ እንደማለት ይቆጠራልና ተመልሰን ንስኀ መግባት ብቻ ሳይሆን የንስኀውም ደረጃ እጥፍ ድርብ ሊሆን እንደሚችል ተገንዝበን ራሳችንን በመግዛት በምግባርና በሃይማኖት ጸንተን ለመኖር መታገል አለብን፤ በኀጢአት ከወደቅንም ቶሎ በንስኀ ልንነሳ ያስፈልጋል። ሆኖም ጥፋቱን በመደጋገም ሁል ጊዜ በንስኀ እመለሳለሁ በሚል መንፈስ መሄድ እንደሌለብን የቤተክርስቲያን ቀኖና ይደነግጋል። ዋናው ቁም ነገር ግን ማንኛውም ክርስቲያን በምንም ይሁን በምን ከቅዱስ ቁርባን ላለመለየት በየጊዜው መንፈሳዊ አላማውን በማጽናት መታገል እንዳለበት እንመክራለን።

https://yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን/

ይህንን ጥያቄ ያቀረቡ አባላችን ጥያቄው ተገቢ ቢሆንም እንኳን ማንኛውም ክርስቲያን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደሙን ተቀብሎ በቆረበበት እለት ማንኛውም የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ ስለማይፈቀድለት ለስጋችን የምንፈልገውን ማንኛውንም የእርድ ስርአት ማከናወን አይፈቀድለትም፤ ከሁሉ ነገር ራሱን መቆጠብ ስላለበት። ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደሙን ባልተቀበለበት ቀን ግን ማንኛውም የእርድ ስጋ ምግብ ይሆን ዘንድ ማረድ ማለት ወጥ ሰርቶ እንጀራ ጋግሮ ምግብ እንደማዘጋጀት ነውና ይቻላል።

ጠያቂያችን ስለ አጿማት ያለው የቤተክርስቲያን ስርዓት ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ከ7 አመት ጀመሮ የፆም ስርዓት እንዲለማመዱ ያዛል። ከእርስዎ እንደተረዳነው 10 አመት የሆነው ወይም የሆናት በጤና ምክንያት አይፆምም ወይም አትፆምም እንደተባለው ያጋጠመውን የጤና ችግር በእኛ በኩል የተወቀ ነገር ባይኖርም ፤ ነገር ግን ማድረግ ያለብዎት የቁርባን ስረዓት በጠዋት ቅዳሴ እንዲሆን ማድረግ የአማራጭ መንገድ ነው። በ2ኛም ደረጃ ምናልባት የህመሙን አይነት ብናውቀው መፆም ወይም አለመፆም ስለመቻሉ ጉዳይ መልሱን ከተጨማሪ ምክረ ሃሳብ ጋር ልናሳውቅዎት እንችላለን። ስለዚህ ጠያቂያችን ለሁሉም ነገር በውስጥ መስመር በላክንልዎ ቁጥር ደውለው ቢያገኙን መልካም ነው።

ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ

ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የንስኀ አባትዎን አነጋግረው የንስኀ ቀኖና ተቀብለው በትክክል ከፈፀሙ በኋላ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ይችላሉ። ነገር ግን ሳንረዳውና ሳይዘረዝሩት የቀረ ሃሳብ ካለ እርስዎም  እኛም ህሊናችን ነፃ ይሆን ዘንድ ደውለው ቢያገኙን መልካም ሲሆን ያም ሆነ ይህ ግን የምንችለውን ያህል ንስኀ ከገባንና በውስጣችን ፈሪሀ እግዚአብሔር ካለ ከቅዱስ ቁርባን እንድንርቅ የሚከለክለን ህግ ስለሌለ፥ እኛንም የሚያስደስተን ነገር የምዕመናን ለዚህ መብቃት ነውና ጠያቂያችን ሃሳቡን በዚህ ተረድተው እንዲፈፅሙ እንመክራለን።   

ስለ ጋብቻ ቁርባን የጠየቁን ጠያቂያችን ከሁሉ በፊት በቅዱስ ጋብቻ መወሰንና ልጅ ወልዶ መተካት የእግዚአብሔር በረከትና ስጦታ ስለሆነ ከምንም በላይ የሚያስደስት እና የሚያኮራ ህይወት ነው። ይሁን እንጂ ለቅዱስ ቁርባን ቅድሚያ ሰጥቶ ዋጋ ያማይከፈልበትን፣ ከኀጢአት በስተቀር ክልከላ የሌለበትን የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም መቀበል የሃይማኖታችን እና የምግባራችን ሁሉ መደምደሚያ ነው። ምክንያቱም ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል ሥጋዬን ካልበላችሁ ደሜን ካልጠጣችሁ የዘላለም ህይወት የላችሁም በማለት ነግሮናል። ይህም የክርስቶስ ሥጋና ደም ከኀጢአት ስለሚያነፃ ህይወትን ሁሉ የሚሰጥ ምድራዊ ኑሯችንን ሁሉ የሚያስባርክና ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር በኩል እንዲመራ ከክርስቶስ ጋር አንድ የሚያደርገን ለኋለኛው አለምም እግዚአብሔር አምላክ ለወዳጆቹ ያዘጋጃትን ሰማያዊ መንግስት እንድንወርስ የሚያበቃ በክርስትና ጉዞ ውስጥ የመጨረሻው የቅድስና ህይወት ስለሆነ በስጋ ስንኖር የሚያጋጥሙን ልዩ ልዩ ምክንያቶች ሽፋን እና ሰበብ አድርገን ለቅዱስ ቁርባን አልተዘጋጀውም ማለት ክርስቲያናዊ ጠባይ አይደለም። በእርግጥ ቅዱስ ጳውሎስ እንደነገረን የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን እንድንቀበል ካስተማረን በኋላ በድፍረት ከነኀጢአታችን ብንቀበል እዳ ፍዳ እንደሚሆንብን ነግሮናል። ይህ ማለት የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም እንደ ተራ ነገር እንዳንቆጥረው እና ከለየለት የኀጢአት ህይወት ውስጥ እያለን በትዕቢት እና በድፍረት እንዳንቀበል የሚገስፅጽና የሚያስጠነቅቅ ኃይለቃል እንጂ ከቅዱስ ቁርባን እንድንርቅ የሚያደርግ አይደለም። ሁሌም ማሰብ ያለብን ወደ ቅዱስ ቁርባን ስንቀርብ እኛን የሚዋጋን ኀጢአትም ሆነ በኀጢአት እንድንወድቅ የሚያደርገን ጠላታችን ዲያብሎስ ፈፅሞ ከኛ እንዲርቅ የሚያደርግልን ሃይላችን ነው። 
 
ስለዚህ በጠያቂያችን ብቻ ሳይሆን በጋብቻ ውስጥ ብዙ ባልና ሚስቶች አንደኛው ቅዱስ ቁርባን እንቀበል ሲል ሌላው ደግሞ በቂ ያልሆነና አሳማኝ ያልሆነ ምክንያት በመደርደር የቀጠሮ ቀን የሚያራዝሙ ከዚህም አልፈው እንቢ የሚሉ እስከ ትዳር መፍረስ ጠብ የሚያደርሱ ብዙዎች ናቸው። ይህ ደግሞ እንዴት እንደሚፈጠር በእውነተኛ ሆነን ስናስብ አንዱና ዋናው የእኛ የካህናት ድክመት ነው። ምክንያቱም ሊቀካህናት ክርስቶስ የበጎቹ እረኛ አድርጎ ሲሾመን ከህፃንነት እድሜ ጀምሮ በቃለ እግዚአብሔር እና በቅዱስ ቁርባን ኮትኩተን እና ተንከባክበን እንድናሳድጋቸው ኃላፊነት ስለሰጠን ነው። እንዲያውም ምዕመኑ ልቁረብ ብሎ ጥያቄ ከማቅረቡ በፊት የንስኀ አባትየው ወደ ንስኀ ህይወት እንዲመጡና ቅዱስ ቁርባን እንዲቀበሉ ያለምንም መሰልቸትና ያለመታከት ጠዋት ማታ ሊመክራቸውና ሊገስፃቸው ይገባል። የንስኀ አባት የተባሉት ካህንም አንደኛው ቅዱስ ቁርባን ልቀበል ሲል ሌላው ደግሞ ፈቃደኛ የማይሆንበት ምክንያት ካለ ወደ ህይወታቸው ጠልቆ በመግባት እስከመጨረሻ ድረስ አባታዊ ምክር እና ተግሳፅ በመስጠት ወደ አንድ መንገድ ሊመጧቸውና ሊያስማሟቸው እንዲችሉ መንፈሳዊ ግዴታ አለባቸው። 
 
ስለዚህ አሁን ጠያቂያችን ባል ለምን አልቆርብም እንዳሉ የሰጡት ምክንያት በቂ ባይሆንም ከዚህ ሌላ ያላሳወቁት ወይም ሊያሳውቁት ያልፈቀዱት አሳማኝ ምክንያት ካለ እሱንም ቢሆን በትምህርት እና በምክር ለማስተካከል ስለሚቻል ትዳራቸው ወደ ጠብ አምርቶ ከመበተኑ በፊት፥ በእኛ በኩል መጀመሪያ ለመቁረብ ፈቃደኛ የሆኑትን አካል አግኝተን ጉዳዩን በዝርዝር ከተነጋገርን በኋላ በቀጣይነት ምን ማድረግ እንዳለባቸው የመፍትሄ አቅጣጫ እንሰጣቸዋለን።
 
በተጨማሪም በጥያቄው እንደተላለፈው፥ እንደ ቀኖና ስርዓት በቂ የሆነ ምክንያት ከሌለ በስተቀር ባል እና ሚስት ተለያይተው መቁረብን ይከለክላል። ይሄንን ስንል ግን አንዱ አካል ጽድቅን ፈልጋለው ሲል አንደኛው ደግሞ በኀጢአት እቀጥላለው ሲል ለሰይጣን እና ለኀጢአት ጊዜ ተሰጥቶ የቀጠሮ ቀን እንዲራዘም የእኛ የቤተክርስቲያን ቀኖና ስለማይፈቅድ ለመቁረብ የተቸገሩበትን ምክንያት በበቂ ምክንያት ከተረዳነው በኋላ ለመቁረብ የተዘጋጁትን ወገን አንድ መፍሄ የሚደርሱበትን አቅጣጫ ስለምንሰጥ እስከዚያው ይሄን መልዕክት አንብበው ይረዱት ዘንድ እግዘኢአብሔር የእውነት አምላክ ስለሆነ ለሱ ክብር ለመብቃት ያለዎትን መልካም ምኞት ለፍቃፃሜ ያብቃዎ በማለት አስፈላጊ ከሆነ በውስጥ መስመር በላክንልዎ አድራሻ አግኝተው ሊያናግሩን እንደሚችሉ እንገልፃለን።
አንድ ሰው ቆርቦ ውሃ ቢነካ ፈፅሞ ኅጢአት ይሆንበታል ወይም የእግዚአብሔርን ክብር ያሳጣል ማለት ሳይሆን የውስጣችንን ቅድስናና ንፅህና ለማጠየቅ ሲሆን በአካለ ሥጋችን የምናደርገው ፅዳትም ለእግዚአብሔር መታዘዝን ለማመልከት ነው። ስለዚህ ጠያቂያችን የዚህን ጥያቄ ሃሳብ ከሃይማኖታዊ ወይም መንፈሳዊ ጉዳይ ጋር ሳያያይዙት፤ ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጥያቄ የሰጠነውን ማብራረያ በማንበብ አጠቃላይ ምክንያቱን በይበልጥ ለመረዳት  ይችሉ ዘንድ እንደሚከተለው በድጋሚ ልከንልዎታል። በተጨማሪም ከዚህ በፊት ስለ ቅዱስ ቁርባን ያስተላለፍነውን መሰረታዊ ትምህርት ከድረገጻችን ላይ እንዲመለከቱት እንመክራለን።
 
ተጠይቆ የነበረው ጥያቄ ፦አንድ ሰው ሥወደሙን ከተቀበለ በኋላ ምግብ እስከሚቀምስ ድረስ ቃላት አውጥቶ መናገር አይችልም፤ ለዚህም ነው ሰዎች ልክ እንደቆረቡ አፋቸውን በነጠላቸው የሚሰፍኑት” ይባላል። ይህ ነገር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ይዘት አለው ወይንስ እንደት ነው? መጽሐፍ ቅዱሳዊ ከሆነስ ባልና ሚስት ቆርበው ሲወጡ በቤተክርስቲያን ግቢ ያለው ሰው በጣም ቢበዛ (በተለይ በንግስ በዓላት) እና ወደቤታቸው ሲሄዱ ለመገናኘት በስልክ መነጋገር ካልቻሉ እንዴት መገናኘት ይችላሉ? ጥያቄ 1 ሌላው ደግሞ የቆረበ (ሥጋ ወደሙን የተቀበለ) ሰው ብቻውን አይሆንም፣ የተወሰነ ርቀትም ቢሆን ብቻውን አይሄድም ይባላል። ይህስ እስከመቼ ነው የቆረበ ሰው ብቻውን መሆን የማይችለው? ለምሳሌ ከቤተክርስቲያን እስከ ቤቱ ድረስ አብሮት የሚሄድ ሰው ባይኖር ምን ማድረግ ይቻላል? ይቅርታ በዘልማድ ይሁን ቀኖና ለማወቅ ስላልቻልኩ ነው። ምክንያቱም በገጠሩ አካባቢ ያሉ እናቶች እና አባቶች ወይም ሌሎች ቤተሰቦች ልጆችን ሲመክሩ (ሲያስተምሩ) አንድን ነገር ይደረጋል ወይም አይደረግም ብለው ነው እንጂ ምክንያቱን የማስረዳት ነገር አልተለመደም። ስለዚህ በአባቶች ቢብራራልኝ በዬ ነው። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
 
መልስ፦ ጠያቂያችን አንድ ኦርቶዶክስ ክርስቲየን ቅዱስ ቁርባን ከተቀበለ በኋላ 1ኛ/ የማቁረሪያ ምግብ እስከሚቀምስ ድረስ ከሰው ጋር መነጋገር የማይችልበት ምክንያት መለኮታዊ እሳት የተዋሀደውን ቅዱስ ሥጋና ክብር ደሙን በተቀበለ ጊዜ ለነፍስ መድኅኒት ለስጋም በረከትን የሚያመጣውን የከርስቶስን ስጋውንና ደሙን ተቀብሎ ሌላ የሰውኛ ንግግርን መነጋገር ሃሳብን ማውጣትና ማውረድ ፈፅሞ ስለማይፈቀድ ነው። ከቅዱስ ቁርባን በላይ የሚከብር ነገር ባለመኖሩ በብዙ ፈተና የረከሰውን ህይወታችንን የቀደሰውንና የተዋረደውን ማንነታችንን ያከበረውን ቅዱስ ቁርባን ማቃለል ለኛም ከቅዱስ ስጋውና ከክቡር ደሙ ያገኘነውን ክብር ስለሚያሳንስብን ባጠቃላይ አፋችንን የመሸፈናችን ነገር ክፉ ከመናገር፣ ክፉ ከማሰብ፣ ክፉውን ድርጊት ከመፈፀም የራቅን ለመሆናችን የሚያመለክት ስርዓት ነው። ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ እህል ውሀ ቀምሰንም ቢሆን ከአንደበታችን የሚወጣው ነገር የተቀደሰና በጎ ነገር ሊሆን ይገባዋል ወይም ክፉ ሃሳብና ክፉ ድርጊት ከኛ እንዳይወጣ ያስፈልጋል ለማለት ነው። በዋናነት እንደማስረጃ የምናደርገው ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ቤዛ ለመሆን በመስቀል ላይ ቅዱስ ስጋውን ቆርሶ ክቡር ደሙን አፍስሶ ለኛ ያለውን ፍቅር በመስቀል ካረጋገጠ በኋላ 3 መአልትና 3 ሌሊት በከርሰ መቃብር በቆየ ጊዜ ቅዱሳን ሐዋሪያትና ሌሎችም ተከታዮቹ በሀዘንና በለቅሶ የላመ የጣመ እህል ውሀ ሳይቀምሱ መቆየታቸውን የሚያመላክት ነው። ስለዚህ ዛሬ ለኛ ህይወት መድሃኒታችን የሚሆነው የሚሰጠን የተገኘው መራራ በሆነ የመስቀል መከራ ስለሆነ እኛም ዛሬ ከሚበላ ከሚጠጣ፣ ከነገር እና ከክፉ ድርጊት ራሳችንን ቆጥበን መቀበል እንደሚገባን የሚያመለክት ነው። 
 
በ 2ኛ/ ደረጃ የተቀደሰ ሰላምታ አስፈላጊ በሆኑ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በአካልም ሆነ በስልክ እኛንም ሆነ ቁርባኑን አያረክሰውም፤ ብቻ በህሊናችን ራሳችንን ለእግዚአብሔር ማስገዛት ያስፈልጋል ለማለት ነው።
 
3ኛ/ ቅዱስ ቁርባን የተቀበለ ሰው ከቁርባን በኋላ ብቻውን አይሄድም የሚባለው የቆረበ ሰው ከምንም በላይ ህይወቱ የከበረና መንፈሳዊ ሙሽራ ስለሆነ የተለየ ክብርም ስለሚያስፈልገው ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን አማናዊ ክብር ለማመልከት ነው። በሌላ በኩል በዚህ ህይወትና መድኅኒት በሆነው በቅዱስ ቁርባን የከበረውን ሰው ሰይጣን በክፉ መንፈስ በጠላትነት ስለሚቃወመው አንደ አንዳንድ ባለስልጣናት ወይም በሙሽርነት የከበረ ሰው ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ እንደሚያስፈልጉት ሁሉ ከዚህም በላይ የሰው ልጅ ፍጹም ሰማያዊ ክብር የሚያገኝበትን ቅዱስ ቁርባን በተቀበለ ጊዜ ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ ስለሚያስፈልገው ብቻ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ ሌሎችም ብዙ አይነት ምሳሌና ሃሳብ  ማቅረብ ቢቻልም ለጊዜው ግን ጠያቂያችን ሃሳቡን በዚህ እንዲረዱትና ለተጨማሪ መረጃ በቀኖና ቤተክርስተያንም ዝርዝር ሁኔታውን መመልከት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን። 
 
ይሁን እንጂ መረዳት ያለብን ከላይ የገለፅናቸው ምክንያቶች ለስጋ ደሙ ክብር ከመስጠት የተነሳ እንጂ ስጋ ደሙን የተቀበለ ሰው ለሌላ አደጋ የተጋለጠ ይሆናል ብሎ ማሰብ የተሳሳተ ነው። እንዲያውም ከምንም በላይ ስጋውን ደሙን የተቀበለን ሰው የአጋንንት መንፈስም ሆኑ ሌላ ሃይል እንዳይቃወመው ታላቅ ግርማ ሞገስና ሃይልና ጉልበት ስለሚሆነው ብቻውን ስለሄደ ችግር ያጋጥመዋል ብሎ ማመን የተሳሳተ ሃሳብ ነው። በየገዳማትም ሆነ በየአብያተክርስቲያናት ቅዳሴ አስቀድሰው ቅዱስ ቁርባን የሚቀበሉና የሚያቀብሉ ብቻቸውን አገር አቋርጠው ሲሄዱ እነሱ ለሌላው ክብርና ሞገስ ይሆናሉ እንጂ በነሱ ላይ የሚደርስባቸው አንዳችም ክፉ ነገር የለም።

ጠያቂያችን በእርስዎ በኩል ያቀረቡልን ጥያቄ ተገቢ ስለሆነ የመፍትሄ ሃሳብ ለማግኘት እስከሆነ ድረስ እጅግ እናበረታታለን። ምክንያቱም የሰው ልጅ በህይወት በሚያጋጥመው መንፈሳዊም ሆነ ስጋዊ ፈተና መፍትሄ የሚሆን ምክር ከመንፈሳዊ አባቶችም ሆነ ከሌላ ባለሞያዎች ማማከር እጅግ ብልህነት ነው። ይሁንና በጤና ባለሞያዎች መድሃኒት ህክምና ላይ ያለውን ሰው እንደገና በመንፈሳዊ ስርዓት እውነተኛ  መድኃኒት የሆነውንና ዘለዓለማዊ ህይወት የሚያሰጠውን ቅዱስ ቁርባን እንደ 2ኛ አማራጭ በማሰብ ሃኪም ባዘዘው መድኀኒት ላይ ደርቦ በአንድ ጊዜ ለመውሰድ በቤተክርስቲያን ቀኖና መሰረት አግባብነት አይኖረውም። እንዳሉትም በፍፁም እምነት ላለ አንድ ክርስቲያን ከቅዱስ ቁርባን በላይ እውነተኛ መድኀኒት የለምና የህክምና ክትትሉንና መድኀኒቱንም አቋርጥ ብንለው ታማሚውን አደጋ ላይ እንዳንጥለው የጤና ባለሞያዎችም ወይም ሀኪሞችም በተሰጣቸው ዕውቀት የሰውን ልጅ አክመው እንዲያድኑ የሚያደርጉት ጥበብ የእግዚአብሔር ፀጋም ስለሆነ፥ በተወሰነ ጊዜ መድኀኒቱን የሚጨርስበት ወይም ለተወሰኑ ቀናት የሚያቆምበትን ሁኔታ ካለ ሀኪሙን በማማከር በዚያ ባለው የጊዜ ክፍተት ውስጥ ቅዱስ ቁርባን እንዲወስድ ማድረግ ይቻላል። እስከዚያው ድረስ ግን ፀሎተ ቀንዲል የሚባለው ፀሎት ደርሶለት፣ ቅባቅዱስ እየተቀባ፣ የሚችል ከሆነም ፀበል እየተጠመቀ ካልቻለም እየጠጣ፣ በራሱ እምነቱን እየተቀባ የእግዚአብሔርን ቸርነት እና ምህረት መለመን ይችላል። ስለዚህ ጠያቂያችን በዚህ ይረዱት ዘንድ ይህን አጭር ማብራሪያ ልከንልዎታል።

እርግዝና እራሱን የቻለ ልዩ እንክብካቤ እና ክብር የሚያስፈልገው የህይወት መሰረት ነው። ያረገዘች ሴት በተፈጥሮ ፀጋ ያገኘችው የእግዚአብሔር ስጦታ ቢሆንም እግዚአብሔር በአርአያውና በምሳሌው የፈጠረውን ስነፍጥረት በመሀፀንዋ 9 ወር ከ 5 ቀን ሃላፊነት ወስዳ መሀፀንዋን እንደ አለም አድርጋ በእግዚአብሔር ልዩ ጥበብ ፅንሱ ከእርሰዋ የህይወት እስትንፋስ እያገኘ የመቆየቱ ሂደት ከንስሓ ህይወት የበለጠ ፈጣሪዋን እንድታውቅ የሚያደርጋት ህይወት ስለሆነ ጠያቂያችን እንዳሉት ያረገዘች ሴት ንስሓ በመግባት መስገድም ሆነ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል አትችልም። በፆም ያረገዘች ሴት በቤተክርስቲያን ለፀሎት፣ ለማስቀደስ እና ቃለ እግዚአብሔርን ለመስማት ብዙ እንድትቆምም አትገደድም። ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጉባኤ እና ከእግዚአብሔር ጸጋ እንዳትለይ ብቻ ድካመ ስጋ እስከሚሰማት ድረስ ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ መስቀል መሳለም፣ ፀበል መጠጣት እምነት መቀባት ትችላለች። ጤነኛው ሰው በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ቁሞ መስማት ሲገደድ እስዋ ግን ልክ እንደታመመ ሰው ቁጭ ብላ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት የእርግዝና ቆይታዋን ታሳልፋለች። ያረገዘች ሴት በእርግዝና ግዜ ንስሓ መውሰድ የማትችልበት ምክንያት መስገድን፣ ለረጅም ሰዓት መፆምን፣ ቁሞ መፀለይን የሚጠይቅ መንፈሳዊ አላማ ስለሆነ እነዚህን አይነት ንስሓ እንዲቀበሉ አይደረግም። የታመሙ ሰወችም እንዲሁ። ስለዚህ ጠያቂያችን በዚህ አግባብ እንዲረዱት ይህን መልእክት ልከንልዎታል።

ጠያቂያችን  ከዚህ በፊት በዚህ ጉዳይ ተመሳሳይ ጥያቄ ተጠይቆ ያስተላለፍነውን ይህን አጭር ምላሽ እንደ አጠቃላይ ሃሳብ ይረዱትና፤ የእርስዎ ጥያቄ በዚህ ምላሽ ካልተመለሰልዎ ተጨማሪ ማብራሪያ ልንሰጥዎት ስለምንችል በድጋሚ በውስጥ መሰመር ያሳውቁንና መልሱን ይጠባበቁ ዘንድ እናሳውቃለን ። 
 
ጠያቂያችን እንዳሉት ንስኀ ገብተው ለቅዱስ ቁርባን ከበቁ በኋላ ተመልሰው በኀጢአት ከተሰናከሉ ወይም ሲቆርቡ ኑረው በመካከል ወደ ቅዱስ ቁርባን የማያቀርብ ነውር ካጋጠመዎት ለጊዜው መቁረብዎን አቁመው ወደ ንስኀ አባትዎ ቀርበው የፈጸሙትን በደል ከተናዘዙ እና ንስኀዎትን ከጨረሱ በኋላ ለመቁረብ መቀጠል ይችላሉ። ምክንያቱም አንድ ሰው ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ እዳ በደል እንዳይሆንበት አስቀድሞ ከኀጢአት እና ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ ከሚከለከልባቸው ጥፋቶች  መራቅ አለበት። ምክንያቱም ቅዱስ ቁርባን ከተቀበለ በክርስቲያናዊ ህይወት ውስጥ የመጨረሻው ክብር ላይ የደረሰ ሰው ነውና፤ ይሄንን ታላቅ ክብር በማቃለል ተመልሶ የማይገባውን ነውር መፈፀም ማለት ግን ታጥቦ ጭቃ እንደማለት ይቆጠራልና ተመልሰን ንስኀ መግባት ብቻ ሳይሆን የንስኀውም ደረጃ እጥፍ ድርብ ሊሆን እንደሚችል ተገንዝበን ራሳችንን በመግዛት በምግባርና በሃይማኖት ጸንተን ለመኖር መታገል አለብን፤ በኀጢአት ከወደቅንም ቶሎ በንስኀ ልንነሳ ያስፈልጋል። ሆኖም ጥፋቱን በመደጋገም ሁል ጊዜ በንስኀ እመለሳለሁ በሚል መንፈስ መሄድ እንደሌለብን የቤተክርስቲያን ቀኖና ይደነግጋል። ዋናው ቁም ነገር ግን ማንኛውም ክርስቲያን በምንም ይሁን በምን ከቅዱስ ቁርባን ላለመለየት በየጊዜው መንፈሳዊ አላማውን በማጽናት መታገል እንዳለበት እንመክራለን።
 
በተጨማሪም እርኩስ ፊልምን በማየት ወደ መጥፎ አቅጣጫ የሚያስኬድ እና መንፈሳዊ ህይወትን ሊዋጋ የሚችል ነገር ሁሉ ከአንድ በክርስቲያናዊ ህይወት ከሚኖሩ ምእመናን የማይጠበቅ ስለሆነ ይሄንን ክፉ ልማድ ለመተው ሁል ጊዜ መጸለይና የተለያዩ የቤተክርስቲያን መጻሕፍትን በማንበብ እንዲሁም በዚህ ምትክ የተባለውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በድምፅ አና በምስል የተዘጋጁ ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ መልእክት የሚያስተላልፉ ትምህርቶች፣ መዝሙሮች እና ድራማዎችን መከታተል ማዘውተር። ግን ያም ሆነ ይህ እርሶ እና ፈጣሪ በሚያውቀው ከፊልሙ ጋር ተያይዞ ከባድ የሆነ ጥፋት ካለብዎ ለንስሓ አባትዎ በመናገር ንስሓ መቀበል። ከቅዱስ ቁርባን ግን ፈጽሞ መራቅ የለብዎትም። ይህን ሁሉ ፈተና የሚያርቅልዎ እና በኀጢአት የረከሰውን ህይወታችንን የሚቀድሰው ቅዱስ ቁርባን ስለሆነ ሁል ጊዜ ፣ከቁርባን መራቅ የለብንም።
 
ስለዚህ ጠቂያችን በእኛ በኩል የምንመክርዎት የመዳን ቀን አሁን ስለሆነ የቀጠሮ ቀን እና ሰዓት ሳያራዝሙ አሁኑኑ ወስነው የንስኀ አባትዎን ማግኘት የማይችሉ ከሆነ በራስዎትም ሆነ በሚያምኑት ሰው በኩል ያገኙዋቸውን እውነተኛ ካህን በማነጋገር ንስኀ መግባት እንዳለብዎ እንመክራለን። ይህንንም ማድረግ ካልቻሉ ደግሞ በእኛ በኩል በውስጥ መስመር በላክንልዎ አድራሻ የሚያገኟቸውን አባት በማነጋገር ባሉበት ቦታ ሁነው በስልክም ይሁን በሌላ መገናኛ መንገድ ንስሓ መግባትና ተግሳፅና ምክርንም ማግኘት ይችላሉ። 
 ጠያቂያችን፤ የጠየቁት ጥያቄ ጥሩ ጥያቄና ማንም ሰው ሊያውቀው የሚገባ  ነው። በቤተክርስቲያናችን አስተምሮ አንፃር በቁርባን መጋባት እና ከተጋቡ በኋላ አብሮ መቁረብ ፍጹም የተለያየ ነው። በመሰረቱ ማንኛውም ክርስቲያን በ 40 ቀን  እና በ80 ቀን የእግዚአብሔር ልጅነት በጥምቀተ ክርስትና አግኝቶ በቅዱስ ቁርባን ከታተሙበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መጨረሻ የህይወት ፍፃሜ ድረስ ከቅዱስ ስጋውና ከክቡር ደሙ መለየት እንደሌለበት ክርስቲያናዊ ግዴታ እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። በዚህ ማህተምነትም በመስቀል ምልክት ታትምና ይሄን ዘግቻለሁ አትሜያለሁ ብላ ቤተክርስቲያን ራሳቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ ሴትም ወንዱም ስርዓት ሰርታ ቃለ እግዚአብሔር እየተማሩ ለአቅመ አዳም ለአቅመ ሄዋን እስኪደርሱ ድረስ ተጠብቀው እንዲቆዩ ታደርጋለች። በኋላ ለአቅመ አዳም ለአቅመ ሄዋን ሲደርሱ ቤተክርስቲያን የአክሊል ሽልማት ታደርጋለች ። ይህ የአክሊል ሽልማት የሰማይ አክሊል ምሳሌ ነው ። ስለዚህ እህቶች ወንድሞች ድንግልናቸውን ቢያጡ በሰማይ ቅጣት አለ በምድር ደግሞ የሚያገኙትን ክብር ይነፈጋሉ፥ አክሊላቸውን ያጣሉ፣ አክሊል ሽልማት ነው። 
አሁን አሁን ግን ቅዱስ ቁርባን በሰው ህይወት ሲገለፅ በህፃንነት እድሜ ደረጃ ያሉ ክርስቲያኖች ሲቆርቡ ቆይተው አካለ መጠናቸው ወደ አዋቂነት ሲደርስ ይበልጥ ስለሚስጥረ ቁርባን ተምረውና አውቀው መቀጠል ሲገባቸው፥ ይባስ ብለው ቅዱስ ቁርባን የሚርቁ ፥ ይህም አልበቃ ብሏቸው ጋብቻቸውን ከቤተክርስቲያን ስርዓት ውጪ በሆነ አለማዊ ጋብቻ የሚፈፅሙ ብዙዎች ናቸው። ይሄም ነገር የቤተክርስቲያን አባቶችን በእግዚአብሔር ቤት ዘንድ የሚያስጠይቃቸው የክህነት ሃላፊነት ነው። ምእመናንም ቢሆኑ የቅዱስ ቁርባንን ዘለዓለማዊ ህይወትነቱን እያወቁና እየተረዱ ከቅዱስ ቁርባን የሚርቁ ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድ ይጠብቃቸዋል። ምክንያቱም ለትዳር የተጫጩ ወንድና ሴት ጋብቻቸውን ከመፈፀማቸው በፊት የሚያደርጉት የግብረስጋ ሩካቤ እንደ ቤተክርስቲያን ቀኖና ስንመለከተው በዝሙት መንፈስ የተፈፀመ ግንኙነት እንጂ በስርአተ ቤተክርስቲያን የተፈቀደ አይደለምና እንደ ዝሙት ይቆጠራል። ነገር ግን የጥፋቱ መጠን ታይቶ በንስኀ አባታቸው የንስኀ ቀኖና እና ቀጣይ ምክር እና ትምህርት የሚሰጣቸውና ንስኀ ገብተው ቀኖና ጨርሶው ስጋ ደሙን በመቀበል ጋብቻ መፈፀም ይችላል። ተክሊል ግን አይፈጸምላቸውም።
 
ስለዚህ ጠያቂያችን ወደጠየቁን የጥያቄ ሃሳብ ስንመጣ ፥ በቁርባን መጋባት ማለት አንደኛው እንደተባለው ተክሊል የሚፈፀመው ሁለቱ ማለትም ሴት እና ወንዱ ድንግልናቸውን ጠብቀው ከቆዩ በኋላ በስርዓተ ተክሊል በቤተክርስቲያን ስርዓት ቤተክርስቲያን አዋጅ ብላ ልጆቿን ለክብር ለመዓረግ የምታበቃበት ነው። ስለ ድንግልናቸው ክብር ምድራዊ የምናየው ዋጋ ሁሉ ሰማያዊ ዋጋ በኋላ ያሰጣልና። ይህ የአክሊል ሽልማት የሰማይ አክሊል ምሳሌ ነው።  ሌላው ድንግልናቸውን ያጡ ከሆነ ከላይ እንደተገለፀው ንስኀ ገብተው የሚፈፀም ፀሎት አለ ፀልየው በቅዱስ ቁርባን ይጋባሉ ማለት ነው። አክሊል ግን አይደረግላቸውም። እና እህቶች ወንድሞች ድንግልናቸውን ቢያጡ በሰማይ ቅጣት አለ በምድር ደግሞ የሚያገኙትን ክብር ይነፈጋሉ፣ አክሊላቸውን ያጣሉ፣ አክሊል ሽልማት ነው። ከአንዱ ክብር ሌላው ክብር ሊበልጥ ቢችልም፥ ነገር ግን እነዚህም ንስኀ ገብተው ቀኖናቸውን ፈፅመው በቅዱስ ቁርባን በቤተክርስቲያን ስርዓት ሊጋቡ ይችላሉ።  
 
ከተጋቡ በኋላ አብሮ መቁረብ ላሉት ግን ፤ በመሰረቱ  በአለማዊ ጋብቻ መጋባት ቤተክርስቲያን ስርዓት አይደለም ። በዓለማዊ ጋብቻ መጋባት የአሕዛብ እንጂ የክርስቲያን ጋብቻ አይደለም። ፀጋ መንፈስ ቅዱስን ያርቃል። ስለዚህ በኋላ ቆርባለሁ አሁን ልጋባ ማለት የክርስቲያን ስነምግባር ውጪ የሆነ እና የዝሙት ሃሳብ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ሳያውቁ ቀርተው ወይም ይህ ሳይሆን ቀርቶ ወደ ጋብቻ ከገቡ ግን  የሰው ልጅ በልዩ ልዩ ኀጢአት የመውደቁ ሁኔታ የደካማ ስጋ ባህሪ ቢሆንም በሰራነው ኀጢአት ተጸጽተን ወደ ንስኀ ህይወት ተመልሰን ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል የሚከለክለን ህግ ግን የለም። ሆኖም፦ እኛ የማናውቀው በመዘግየታችን የምናጣው ፀጋ አለ ። ያን ፀጋ ላናገኘው እንችላለን። ልናቆየው የማንችለው እግዚአብሔር ሊሰጠን የሚችለው ጸጋ። ስለዚህ ራሳችንን በንፅህና በቅድስና ስንጠብቅና በቤተክርስቲያን ስርዓት ጸንተን በቅዱስ ቁርባን በመኖር ስንተጋ እኛ የማናውቀው እግዚአብሕር የሚያውቀውን ፀጋ በጊዜው እንጎናፀፋለን፣ ትዳራችንም ከጅምሩ ይባረካል ። በመሆኑም ሲጋቡ መቁረብ እና ከተጋቡ በኋላ መቁረብ አንድ አይደለም።

 ጠያቂያችን፤ በመጀመሪያ በተቻለ መጠን ይህ እንዳይሆን በመንፈሳዊ ስርዓት ሆነን ህሊናችንን ሰብስበን ለስጋዊ አስተሳብ ቦታ ሳንሰጥ፥ በፀሎት በመትጋት ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ ተዘጋጅቶ መጠበቅ ያስፈልጋል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ወይም ደግሞ እርስዎ እንዳሉት ከእኛ አቅም በላይ በሆነ ፈተናው ገፍቶ ቢያጋጥም ግን ገና ለገና ቤተሰብም ሆነ ሙሽሮቹ ተዘጋጅተዋል በሚል ምክንያት የእግዚአብሔርን ህግ መጣስ ስለማይቻል ቅዱስ ቁርባን የመቀበሉን ስርዓት ለሌላ ጊዜ እንዲዛወር ይደረጋል እንጂ ሰውን ላለማሳዘን ተብሎ የእግዚአብሔርን ህግ መተላለፍ እንደማይገባ ማወቅ አለብን። ስለዚህ ጠያቂያችን ሃሳቡን በዚህ እንዲረዱት ይህን አጭር መልዕክት ልከንልዎታል።

ጠያቂያችን ከቅዱስ ቁርባን በኋላ ሥጋ ነክ ወይም የፍስክ ምግብ የማይበሉ ሰዎች አሉ፥ በማለት ላቀረቡት ጥያቄ የሚከተለው መልስ እንዲደርስዎ አድርገናል።
 
ሥጋ ነክ እና የፍስክ ምግቦች የሚበሉበት እና የማይበሉበት ጊዜ በቤተክርስቲያን ቀኖና የተደነገገ ሲሆን በአማኞችም ዘንድ በግልጽ የታወቀ ነው። በፆም ጊዜ እንደሚታወቀው ከቅዳሴ በኋላ የጾም ምግብ እንድንበላ የተፈቀደ ሲሆን በፍስክ ጊዜ ደግሞ ከቅዳሴ ወይም ከቅዱስ ቁርባን በኋላ የፍስክም ምግብ እንድንበላ ይፈቀድልናል። ዋናው መታወቅ ያለበት ምስጢር ግን ሰው በራሱ ፈቃድ ለቅዱስ ቁርባን ካለው አክብሮት የተነሳና ለፈቃደ ነፍሱ ቅድሚያ ከመስጠትም በራሱ ልዩ ፍቃድና ውሳኔ ቅዱስ ቁርባን በተቀበለበት እለት የፍስክ ምግብ አለመመገቡ በህግ ባይገደድም በግሉ ግን በረከትን  ያገኝበታል። ምክንያቱም ከአዋጅ ፆም ውጪ በራሳችን ፆምን ስንፆም የእግዚአብሔርን ፀጋ ያበዛልናል እንጂ አያስነቅፈንም።
 
በዋነኝነት ግን መታሰብ ያለበት ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ካህንም ሆነ ምእመን ከቅዱስ ቁርባን በኋላ የሚያስጨንቅ እና ሰውነትን የሚያውክ ምግብም ሆነ መጠጥ አብዝቶ መውሰድ ተገቢ አይደለም። ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን በተቀበልንበት ወቅት ከክርስቶስ ቅዱስ ሰጋ እና ክቡር ደም ሌላ ለስጋችን ድሎት የሚሆን እና ስጋዊ ሃሳባችንን ሊፈትን የሚችል ማንኛውም የሚበላ እና የሚጠጣ ቀርቶ ተገቢ የማይሆን ሃሳብ ውስጥ መግባት እንኳን ሳይቀር እንደሌለብን መገንዘብ ያስፈልጋል።
 
ስለዚህ ፤ ጠያቂያችን ለጥያቄዎ ግልፅ እንዲሆንልዎት እስካሁን ቤተክርስቲያን እያስተማረች የመጣችበትን እና ሁልጊዜ ቀድሰው የሚያቆርቡን አባቶች የሚበሉትን እና የሚጠጡትን በማየት፣ የሚያደርጉትንም በማየት እርስዎም ይህን ነባራዊ የሆነ መንፈሳዊ ትውፊት በመገንዘብ ለጥያቄዎ ምላሽ እንዲሆንዎት አሳቡን በዚህ ይረዱት። ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በውስጥ መስመር ሊያገኙን ይችላሉ።
ጠያቂያችን ፤ 18 ሰዓት አፋችን ምሬት እስኪሰማው ለማለት ነው፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ 3 ሰዓት በአይሁድ ተያዘ፥ እስከ 9 ሰዓት ነፍሱ ከስጋው እስክትለይ ድረስ 18 ሰዓት ይሞላል እና ያን በማሰብ አፋችን ምሬት እስኪሰማው ድረስ ብላ ቤተክርስቲያናችን ታስተምረናለችና ነው። ውሀ የሚለው ለምሳሌ ነገ ቅዳሜ ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን የምንቀበል ከሆነ አርብ ማታ ላይ በጊዜ ገላን መታጠብ ያስፈልጋል፥ ነገር ግን ጠዋት ልንሄድ ስንል አፍ መጉመጥመጥ አይቻልም፥ በአይናችን ውሃ እንዳይገባ ፊትንም መታጠብ አይገባም። ትንሽ ነካ ነካ አድርጎ አድርገን ከላይ ከላይ ብንታጠብ ግን ችግር የለም። አባቶች ሲያስተምሩን ሰውነታችን ክፍት ስለሆነ ውሃ በአይን ይገባል ይላሉ፦ ስለዚህ ጠዋት ላይ ፥አፋችነን ባንጉመጠሞጥ ፥ይምረረን ግዴለም ፥ ምሬቱ መከራውን እንድናስብ ሀሞቱን እንድናስብ ለ 18 ሰዓት መጾም ለማለት እንጂ፥ እንደነገን የምንቆርብ ከሆነ ዛሬ ማታ መታጠብን አይከለክልም፥ መመገብ ወይም ውሃ መጠጣት ግን አይቻልም።