ጥያቄና መልስ
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!" (ማቴ 3: 1-2)
ጥያቄና መልስ
ስለ ንስሐ የሰጡት ትምህርቶች
👉ጥያቄ፦ ላጠፋነው ጥፋት እግዚአብሔርን በቀጥታ ይቅር በለን ማለት አንችልም ወይ ለአባቶች ከመናዘዝ ይልቅ ማለቴ ነው።
መልስ፦ ይሄ አነጋገር በአብዛኛው ከእውነተኛዋ ሃይማኖት ወይም ከቀጥተኛ መንገድ የወጡ ሰዎች የሚያቀርቡት ሃሳብ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው። ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ችግር የሚፈጠረው የእግዚአብሔርን ቃል እያጣመሙ ከዋናው መንገድ ሊያወጡን ቀጥተኛውን ነገር የሚያጣምሙ ሰዎች የሚያቀርቡት ሃሳብ እኛን ሊያሰናክለን ወይም ደግሞ መናፍቃን በሚያቀርቡልን የክህደት ትምህርት ህሊናችን ሲሰናከልብን የሚቀርብ ጥያቄ ይመስላል።
መታወቅ ያለብት በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ይቅር ባይና ኃጢአትን የሚያስተሰረይ እግዚአብሔር እንደሆነ ነው። ይህን ከዚህ በፊትም ሰፋ አድርገን ማስተላለፋችንን እናስታውሳለን፤ ምናልባት ጠያቂያችን ካልተመለከቱት እንዲደርስዎ ስለምናደርግ በመስመር ሆነው እንዲከታተሉ አደራ እያልን አሁን ላቀረቡልን ጥያቄ ግን የሚከተለውን አጭር ማብራሪያ ሰጥተንበታል።
ሐዋሪያው እንዳለው በአይንህ የምታየውን በተፈጥሮ አንተን የሚመስልህን እለት እለት በማህበራዊ ኑሮና በማንኛውም ኑሮ አብሮህ ያለውን ወንድምህን የማትወድ ከሆንክ ታዲያ አንድ ቀን አይተሀው የማታውቀውን ፈጣሪን እንዴት ልትወደው ትችላለህን ይላል። ስለዚህ እኛ እዚህ እግዚአብሔር እራሱ ሾሜያቸዋለሁ ኀጢአትን እንዲናዝዙ ንስሐ እንዲሰጡ በመንጋው ላይ በህዝቡ ላይ ሾሜያችኋለሁ ኃጢአቱን የያዛችሁበት የተያዘ ይሆናል፤ ኃጢአቱን ይቅር ያላችሁለት ደግሞ ኃጢአቱ ይቅር ይባልላቸዋል። ብሎ የሾማቸው ሰዎች በአይናችን የምናያቸውን ሰዎች አምነን በእነሱ አማካኝነት እግዚአብሔር ይቅር እንደሚለን እንደሚማለደን ማመን ያቃተን ሰዎች ታዲያ ይሄን ያህል ለካህን ቀርቦ ኃጢአትን መናገር ለክብራችን እንደማይመጥነንና እንደሚያንስብን በመቁጠር እራሳችንን ከፈጣሪ ጋር አስተካክለን ወይም ከካህናት በላይ ብቃት እንዳለን በማሰብ ይሄን ያህል መጨናነቅና መፈላሰፍ የለብንም። መቼም የመጨረሻው መደምደምያና ሁላችንንም ሊያስማማን የሚችል የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ስለዚህ ጠያቂያችን ወደ መልሱ የምንሄድበት መንገድ፦ ሂድና እራስክን ለካህን አሳይ፤ ሂድና የነፍስህን በሽታ ወረርሽኝ በካህን መንፈሳዊ ሀኪም በሆነው በካህኑ አስመርምር ብሎ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀጥታ ማዳን ስልጣኑ ሆኖ እያለ ማዳን እንደሚችል ሁሉ ብዙ አስገራሚ ተአምራቱን ያየንበት አምላክ ግን ያንን በማቴዎስ 8 የተጻፈውን ቃል ሂድና ራስህን አስመርምር ስላለን እኛም እንደ ሕጉ እንደ ቃሉ እንፈፅማለን ማለት ነው። በነሱ ስለሚማለድና፥ እንደሚማለድም ስለነገረን ነው። በአካለ ስጋ ያሉ አባቶቻችን ካህናትም እነሱ እንኳን ሰው እንደመሆናቸው መጠን በስጋ ቢደክሙና አንዳንድ ጥፋት አጥፍተው ብናይ በነሱ ላይ ያደረው ስልጣነ ክህነት እኛም በፍፁም እምነት ስለሆነ የምንቀርበው እኛ ኃጢአት በመናዘዝ እነሱ በሚሰጡን የኃጢአት ስርየት አምነን ወደ እነሱ እስከቀረብን ድረስ በዚህ ላይ ስልጣን ያለውና ሁሉን ነገር በረቂቅ ጥበቡ የሚፈጽመው አምላክ ነው።
ስለዚህ ጥቃቅን ነገር እየመዘዝን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ጠላት ዲያብሎስ ልባችንን እያስታበየ እንዴት ለካህን ቀርቤ እናገራለሁ ደሞ እሱስ ካህኑ ከእኛ የተሻለ ህይወት ምን አለው እያልን እያብጠለጠልን በየሜዳው አፋቸውን ሲከፍቱ የሚውሉ መናፍቃን የካህንን ክብር ሲያጎድፉ እየሰማን አንዳንዱም ደግሞ እምነት እና ሃላፊነት የጎደላቸው ፤ ካህን ሳይሆኑ መነኩሴ ሳይሆኑ ካህን ነን እያሉ የሚያጭበረብሩ ለግል ጥቅማቸው የተሰለፉ የሚያደርጉት አስመሳዮችንም እያየንም የካህን ክብር በዚህ አይነት ማየት እና ማቃለል እኛን ወደበለጠ ጥፋት እና ወደ በለጠ ክህደት ያደርሰናልና በህይወታችን ስለማያንጸን መጠንቀቅ እንዳለብን እንመክራለን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
እግዚአብሕር ማስተዋሉን እና ጥበቡን ለሁላችንም ይስጠን
👉ጥያቄ፦በ #ንስሐ የማይሰረይ #ኀጢአት አለን? ወይስ የለም?
መልስ፦ ጠያቂያችን፦ ፈፅሞ በንስሐ የማይሰይ ኀጢአት የለም። ምናልባት የመጨረሻ ከባድ ኀጢአት የሰራን ኀጢአተኞች ብንኖር፤ እንደ ኀጢአቱ ክብደት እኛም በሚያልፈው በሚሞተው በሚበሰብሰው ደካማ ስጋችን የማያልፍና የማይሞት ለዘለአለም በነፍስ የሚያስጠይቀን ኀጢአት ለመስራታችን ሰው ደግሞ በሰማይ ካለው ዘለዓለማዊ ሞት ተጥሎ እንዳይቀር ከወዲሁ በዚሁ ደካማ ባህሪይ በለበስነው ስጋችን የሰራነውን ኀጢአታችንን ይሄንኑ ደካማ ስጋችንን በንስሐ ህይወት ለነፍስ ስራ በማስገዛት እግዚአብሔር በሾማቸውና እኛንም ቢሆን ከኀጢአታችን ለመናዘዝ የኀጢአት ስርየት ወደሚያስገኙልን ወደ አባቶቻችን ቀርበን ከልብ በሆነ መፀፀት አንዳችም ነገር በሰው ሰውኛ አፍረን ተሳቀን የምንደብቀው ኀጢአት ሳይኖር ከተናዘዝን እና በሰራነው የኀጢአት መጠን ቀኖናችንን ተቀብለን በስርዓት ከልብ በተሰበረ ህሊና በፍፁም መንፈሳዊ ስርዓት ሆነን ከፈፀምነው ፈፅሞ የማይሰረይ ኀጢአት የለም። እግዚአብሔር አምላካችን ሰው የሆነበት ዋናው ምስጢሩ የማይሰረይና ከእኛ የማይለይ የሚመስል በምድር ላይ ይህ ቀረሽ የማይባል የኀጢአት አይነት እንድንሰራ በሰይጣን ባርነት ውስጥ ወድቀን ሰይጣን በረቂቅ መንፈሱ ያዘዘንን ሁሉ እንድንፈፅም፤ ሁላችንም ባንሰራውም በአዳማዊ የተፈጥሮ ባህሪያችን ኀጢአት በውርስ ለሁላችንም እየደረሰ 5ሺ500 ዘመን የሰይጣን ባሪያዎች ሆነን በኀጢአት ቀንበር ተይዘን ኖረን እግዚአብሔር አምላክ በራሱ መለኮታዊ ጥበብ እና እኛን ከመውደዱ የተነሳ አለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ሰው ሆኖ ስጋን ተዋህዶ አለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣልና ይህ ቀረሽ የማይባል የአባትነት የአምላክነት ስ ሰርቶ ከዚያ ከከባዱ ኀጢአታችን ነፃ አውጥቶናል። ዛሬም ቢሆን ጠፍተን እንዳንቀር ዳግም በየጊዜው የሚደርስብንን የኀጢአት ውድቀት በንስኀ እንድንነሳ ንስሐ የሚሰጡንን ከታሰርንበት የኀጢአት ማሰሪያ የሚፈቱንን አባቶች ስላስቀመጠ በፍጹም ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በንስሐ የማይሰረይ ኀጢአት አለ ብሎ ማመን እንደውም እንደ ሃይማኖት ክህደትም ይቆጠራል።
አባቶች ካህናት የጢአታችንን ክብደት የኀጢአታችንን አይነ ት ተመልክተው በቤተክርስቲያናችን ቀኖና መሰረት የታዘዘውን ለኀጢአታችን ስርየት ይሆን ዘንድ የሚሰጡንን ቀኖና ከፈፀምን እንዲሁም ወደ ንስሐ ህይወት ስንቀርብ ስጋዊ እና በሰው ዘንድ ለመታየት ሳይሆን ከልብ በመፀፀት ውስጣዊ ህሊናችንን መመርመር የእራሱ ባህሪይ የሆነው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከውስጥ መፀፀታችንን ከሁሉ ቀድሞ ስለሚያውቅ ልቦታችንን በፍፁም በመመለስ ለእግዚአብሔር አስገዝተን ንስሐ ከገባን የማይሰረይ ኀጢአት የለም። እነንተ የፈታችሁት የተፈታ ይሆናል እናንተ ኀጢአታቸውን የያዛችሁባቸው ደግሞ የተያዘ ይሆናል የሚል ቃል ተፅፏልና፤ ይሄን ጥያቄ ያቀረቡልን አባላችን እና ይሄን መልእክት የምትከታተሉ ኦርቶዶክሳዊ ወገኖቻችን ፥በዋናነት አስቀድመን የምንመክረው ኀጢአትን ላለመስራት ፣ በኀጢአትም ተመልሰን ላለመውደቅ፣ ራሳችንን ከኀጢአት ለመለየት የምንችለውን ጥረት ሁሉ ማድረግ አለብን። ከአቅማችን ባላይ በሆነ ምክንያት ካልወደቅን በስተቀር አስበንበት እቅድ ይዘን የምንሰራው ኀጢአት ግን መኖር የለበትም። ሁላችንም ሰይጣን በስንፍና እንድንኖር እንዳንፀፀት፣ ንስሐ እንዳንገባ ቀጠሮዋችንን እያራዘመ ወደ ንስሐ የምንቀርብበትን ቀን በብዙ ፈተናና መሰናክል እያደናቀፈ በኀጢአት ላይ ኀጢአት እየጨመረብን እንድንቀጥል የሚያደርገን እሱ ጠላታችን ዲያብሎስ ስለሆነ የዲያብሎስን ሽንገላ እና የዲያብሎስን ፈተና ፈፅሞ ልንቃወመውና ድል ልንነሳው ይገባል።
ስለዚህ ጠያቂያችን ከላይ ያብራራነውን መሰረታዊ የንስሐ ትምህርት በዋናነት እንዲረዱት እየመከርን ምናልባት አሁን እርስዎ “ይቅር ስለማይባል ኃጥያት ብታብራሩ?” በማለት ያቀረቡት የጥያቄ መነሻ ሃሳብ ፥ በመጽሐፍ ‘መንፈስ ቅዱስን የተሳደበ ኀጢአቱ አይሰረይለትም’ ከሚለው ቃል ተነስተው ከሆነ ይህም ለምን እና ከምን አንጻር እንደሆነ ገልጸን ያስተላለፍነውን ማብራሪያ እንደሚከተለው ልከንልዎታልና ይህን አንብበው ይረዱት።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋለ ስጋዌው ህሙማነ ስጋን በተአምራቱ ህሙማነ ነፍስን በትምህርቱ እየፈወሰና በቃሉ እያጸና ማንም ሊሰራው የማይችለውን ድንቅ ስራ እየሰራ በሚመላለስበት ጊዜ ፈሪሳውያን እና የአይሁድ ወገኖች የሚያደርገውን ተአምራቱን በእሱ መለኮታዊ ኃይል የተሰራ መሆኑን አምነው ላለመቀበል ሲሉ ሌላ ኃይል ወይም በእርኩስ መንፈስ ኃይል እንደሚሰራ በድፍረት ይናገሩ ስለነበረ ይህ ክህደታቸው ደግሞ የባህሪይ አምላክ መሆኑን ወይም እግዚአብሔርነቱን የካዱ ስለሆነ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ የሆነውን አምላክ ጋኔን ወይም እርኩስ መንፈስ አድሮበታል ብሎ ከመሳደብ የበለጠ ሌላ ምንም ክህደት ስለሌለ በዚህ ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱ 1ኛ/ “ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገርግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም። በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።” በማለት የተናገረው ከዚህ አንፃር ነው። (ማቴ 12፥31፡32)
እንዲሁም 2ኛ/ “እውነት እላችኋለሁ፥ ለሰው ልጆች ኃጢአት ሁሉ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ኃጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም። ርኵስ መንፈስ አለበት ይሉ ነበርና።” በማለት አይሁድ ፥ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እንደሆነ፣ የባህሪይ አባቱ እግዚአብሔር የምወደው ልጄ ይህ ነው ብሎ የመሰከረለትን፣ እንዲሁም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያለመለየት አንድ መሆኑን በእርግብ አምሳል በራሱ ላይ መገለፁን አምነው ሳይቀበሉ ጋኔል ወይም እርኩስ መንፈስ አድሮበታል በማለት መናገራቸው መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ወይም መካድ ስለሆነ፤ የሰው ልጅ ደግሞ ከኀጢአት ሁሉ የመጨረሻ ኀጢአት እና በንስኀም የማይታጠብ ትልቁ በደል ኀጢአትን ይቅር የሚል ፈጣሪን መሳደብ ስለሆነ ፈጣሪውን የተሳደበ ከሆነ ደግሞ በማንም ሊቀር ስለማይችል መንፈስ ቅዱስን የተሳደበ ንስኀ የለውም የሚባለው ለዚህ ነው። (ማር 3፥28፡29)
3ኛ/ ካህኑ ኤሉ በእድሜ በሸመገለ ጊዜ እሱን ተክተው የእግዚአብሔርን ቤት ያገለግሉ የነበሩ ሁለቱ ልጆቹ በእግዚአብሔር ፊት አስጠያፊ የሆነ ኀጢአት በመፈፀማቸው ምክንያት አባታቸው ከእግዚአብሔር ጋር እንደተጣሉ ሲነግራቸው “ሰውስ ሰውን ቢበድል እግዚአብሔር ይፈርድበታል፤ ሰው ግን እግዚአብሔርን ቢበድል ስለ እርሱ የሚለምን ማን ነው?” (1ኛ ሳሙ 2፤25) በማለት ሰው ከሰው ጋር ቢጣላ ወይም ሰውን ቢሳደቡት በእግዚአብሔር ስም በመማፀን ሊታረቅ ይችላል በደሉም ይቅር ይባልለታል ፤ ከፈጣሪ ጋር ከተጣላን አስታራቂ ሽማግሌ ሊኖር ስለማይችል ለዚህ ነው በማቴዎስ ወንጌል መንፈስ ቅዱስን የተሳደበ ኀጢአቱ አይሰረይለትም የተባለው።
ለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ባርያዎቹን አገልጋዮቹን ልጆቹን የማይዘነጋ ቸል የማይልየማይል አምላክ ስለሆነ እሱ ሃይሉን እና ጥበቡን እሱ ያድለን።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
ስለ ንስሐ (ጥያቄና መልስ)
👉ጥያቄ#1 ፦ #ንስሐ ማለት ምን ማለት ነው?
መልስ፦ ንስሓ የሚለው ቃል ከግዕዝ ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን በአማርኛ ትርጓሜው ወይም የቃሉ ፍች እና ማብራሪያ፦ ማዘን፣ መፀፀት፣ መቆጨት፣ መቀጣት፣ ቀኖና መቀበል፣ ስለተሰራው ኀጢአት ካሳ መክፈል።፣ የሰሩትን በደል እና ጥፋት ማመን፣ አና በአጠቃላይ ማንኛውም ክርስቲያን ስለሰራው ኀጢአት ተፀፅቶ ወደ ፈጣሪው ሲመለስ የሚቀበለውን የቀኖና ንስሐ ያመለክታል።
አንድ ክርስቲያን ንስሓ ለመግባት ተዘጋጀ ወይም ንስሓ ገባ ሲባል ማመኑን፣ መፀፀቱን፣ ወደ እግዚአብሔር መመለሱን፣ ክፉ ፀባዩን መተዉን፣ ከጥፋት ስራ መቆጠቡን እና መታረሙን የምናውቅበት መንገድ ነው። በተጨማሪም ንስሓ ማለት አንድ ክርስቲያን በሰራው ጥፋት በፈፀመው ኅጢያት እና ባደረገው ስህተት ሰለተፀፀተ እና ስለተቆረቆረ ሌላ ጊዜ ከፈጣሪ ጋር የሚያጣላውን እና ሰማያዊ የዘላለም ህይወት ሊያሳጣው የሚችል ኀጢያትን ላለመፈፀም የመጨረሻ ውሳኔ የሚደርስበት የመደምደሚያ ሃሳብ ነው።
👉🏾👉🏾👉🏾የንስሐ መሰናክሎች (እንቅፋቶች)
👉ጥያቄ፦ ህይወቴ በሀጥያት ቆሽሾ ቆይቷል ንሰሀ መግባት ፈልጌ ነበር፤ ነገር ግን መልሼ በዛው ሀጥያት እንዳልወድቅ በጣም ፈራሁና እስኪ መጀመሪያ ንሰሀ ከመግባቴ በፊት የሚፈታተነኝን ሀጥያት ለማሸነፍ ልሞክር አሸንፌ ከዚያ ከቆየሁ የባለፈውንም ንሰሀ በመግባት እራሴን ማፅዳት አለብኝ ብየ አሰብኩ በዚህ ላይ ምን ይመክሩኛል?
መልስ፦ ሰይጣን ከሚዋጋቸው የድኅነት መንገዶች ውስጥ ንስሓን የሚያክል የለም ምክንያቱም ንስሐ ጠላት ዲያብሎስ የክርስቲያኖችን ሕይወት ለማጥፋት የገነባውን የኃጢአት ሕንፃ ሁሉ በእግዚአብሔር ቸርነት እንዳልነበረ በማድረግ ስለሚያፈርስበት ነው። ከዚህ የተነሳ የሰው ልጅ ንስሐ እንዳይገባ ቢገባም ቶሎ እንዳይሆን የተቻለውን ከማድረግ ፈፅሞ አያርፍም። ጠላት ዲያብሎስ ሰዎችን በኃጢአት ለማቆየት ወይም ንስሐ የሚበቡበትን ጊዜ ለማራዘም ከሚጠቀምባቸው የንስሐ መሰናክሎች መካከል ፦
1/ እንቅፋት መፍጠር፦ ድንገተኛ ፈተናዎች ወይም አጋጣሚዎች ሊሆኑ ይችላሉ ብቻ እንቅፋት በመፍጠር ያሰናክላቸዋል።
2 / ኃጢአተኛው ራሱን ከእርሱ የበለጠ ኃጢአት ሠሩ ከሚላቸው ጋር በማነፃፀር የተሻለ እንደሆነ እንዲገምትና ንስሓም እንደማያስፈልገው ራሱን ማሳመን፥ ቅድስና ግን ከኃጢአተኛ ሕይወት ጋር ሊነጻጸር አይገባም ።
3/ ከሥጋ ድካም የተነሣ በአካባቢ ተጽእኖ መመራት። ቅዱስ ጳውሎስ “ይህን ዓለም አትምሰሉ” በሏል ሮሜ 12፥2 ዓሳ ትንሽ ሲሆን ማዕበል በሚያናውጠው ባሕር ውስጥ ይዋኛል ክርስቲያንም እንዲህ ፈተናን ተቋቁሞ ለንስሓ መብቃትና መንፈሳዊ ህይወት መኖር ይገባዋል።
4 መዘግየት ፦ ዲያብሎስ ንስሓ እንዳንገባ የሚዋጋን በቀጥታ አይደለም ነገር ግን የተለያዩ ስውር ፈተናዎችንና ምክንያቶች እየደቀነ ንስሐ እንዳንገባ ያዘገየናል። መዘግየት ከሚያስከትለው አደጋ መካከል አንዱ ለንስሐ የተዘጋጀውን ልቡና መለወጥና ለንስሓ ያለውን ዕድል ማጥፋት ነው። ኃጢአት ወዲያው ካልተቀጨና ከቀጠለ ሥር ይሰዳል ሱስ ሆኖ ይዋሀደንና ከዚያም ለንስሓ የተዘጋጀውን ጸጸትና ፍላጎት ሊያጠፋው ይችላል።
5 ተስፋ መቁረጥ ። ሰይጣን በኃጢአት ከመውደቃችን በፊት የእግዚአብሔርን ቸርነትና ይቅርታ በማሰብ ኃጢአት እንድንሠራ ያደርገናል ከሠራነው በኋላ ደግሞ የእግዚአብሔርን ፍርድና ጨካኝ እንደሆነ ያሳስበናል ንስሐ እንዳንገባም ተስፋ ያስቆርጠናል።
6 ተነሳሒው ራሱን በማድነቅ በመመጻደቅ ኃጢአተኛ እንዳልሆነ እንዲያስብ በማድረግ። ሰው መልካም ነው ብሎ የሚገምተው የራሱ ሕይወት በኃጢአት የተዳደፈ መሆኑን ካላመነ በቀር ሊለወጥ አይችልም። በሕይወቱ ውስጥ መንፈሳዊ ለውጥ ከሌለ ደግሞ ስለ ንስሐ አያስብም፤ ንስሐም አይገባም ስለዚህ ራሱን አይመረምርም ።
7 በልቡና ውስጥ ፈሪሃ እግዚአብሔር አለመኖሩ፦ ቅዱስ ይስሐቅ እንዳለው ፈሪሃ እግዚአብሔር ከሌለ ንስሐ መግባት የለም ብሏል አንዳንድ ሰዎች በፍቅር ሰበብ ፈሪሃ እግዚአብሐርን ከልቡናቸው ፈጽመው ያስወግዳሉ። በዚህ ጊዜም ስለ ንስሐ ህይወታቸው ግድ የለሽ ይሆናሉ በኃጢአት ይወድቃሉ። ከኃጢአት የተነሳም ፍርሃትን አውጥቶ በመጣል ወደ ንስሓ የሚያቀርበውን የእግዚአብሔርን ፍቅር ያጣሉ።
በአጠቃላይ ጠያቂያችን በዚህ ሁሉ ከዲያብሎስ ጋር ታግሎ በማሸነፍ በንስሐ እየወደቁም እየተነሱ መጋደል ነው እንጂ የኃጢአት ባርያ ሆኖ መኖር ወይም ንስሐ ሳይገቡ መጋደል ተገቢ አይደለም ። ኢያሱ ወልደ ሲራክ ለልጁ የነገረው እግዚአብሕርን ለማገልገል ከተነሣ ለሚገጥሙት ፈተናዎች ራሱን ማዘጋጀት እንዳለበት ነው። ሰይጣን መጾማችንንና ንስሓ መግባታችንን በተመለከተ ጊዜ በመንፈሳዊ ሥራችን ይቀናል። ድካማችንን ዋጋ እንዳንቀበልም ከመንገድ ሊያስቀረን ይዋጋናል። የምንወድቅበትንም ወጥመድ ሁሉ ዘጋጃል። እጅ እስክንሰጥ አልተዋችሁም ይለናል። ነገር ግን ቅዱስ ጴጥሮስ እንደነገረን “ባለጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራል በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንደተቀበሉት እየወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት (1 ጴጥ 5፥89) ሲል የመከረውን አስታውሶ መጋደል ያስፈልጋል እንጂ ተስፋ መቁረጥ ወይም ፈርቶ መሸሽ አይገባም።
ሰው በሚሠራው ሥራ ሰውነቱን እየተቆጣጠረ መልካሙን በትሕትና እያበረከተ ክፉውን ሥራ የጧቱን ለማታ የማታውን ለጧት እያወጣ የሚጥልበት ሕዋስ ንስሓ ተሰጥቶታል ። “ኃጢአትን እንደ ውኃ የሚጠጣት ሰው ይቅርና ሰማይ ስንኳ በእግዚአብሔር ፊት ንጹሕ አይደለም” ኢዮ 15፥15 ። ሰው ከኃጢአት ንጹሕ ሆኖ ለመገኘት የማይቻለው ስለሆነ ንስሐ በጧት በማታ የሚፈጽም እንጂ እስከዚህ ቀን ወይም ዘመን ተብሎ አይወሰንም ወይም ቀጠሮ በማራዘም ኀጢአትን በመከመር አይከረምም። ሰው ዕለት ዕለት የሚሠራውን ጽድቅ ወይም ኃጢአት በእግዚአብሔር መዝገብ ይጻፋል። በሠራነው ኃጢአት ተጸጽተን ለመምህረ ንስሓ ነግረን በንስሓ ዕንባ ብናጥበው ግን ይደመሰሳል። ዛሬ ለካህኑ መንገር አሳፍሮን ወይም እንዳሉትም እንደገንዘብ አጠራቅመን እንናገር ብለን ብንተወው ግን እድሜያችንን በኪሳችን ቆጥረን አልያዝንምና በቁርጥ ፍርድ ቀን ከእኔ ሒዱ ያሰኘናል፤ ምክንያቱም በኃጢአት ሳለን ንስሓ ሳንገባ ሞት ቢያገኘን ሥቃየ ገሃነም ያገኘናል። በመሆኑም ለኃጢአት ተገዢ ሆኖ በኃጢአት ለመኖር ማሰብ ኃፍረተ ነፍስ ኀሣረ ነፍስ መሆኑን መገንዘብ አለብን።
ከዚህም በተጨማሪ ንስሐ ባለመግባታችን የምናጣው የነፍስ ሞት ብቻ ሳይሆን በምድር ስንኖርም ጾማችን ጸሎታችን ያለ ንስሓ ተሰሚነት የለውም፣ በጾም ጸሎትና በንስሓ እናገኘው የነበረ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በረከትም ከኛ ይርቃል። ጾም ወይም ማንኛውም መንፈሳዊ አገልግሎት ወደ እግዚአብሕር ለመቅረብ ጥረት የምናደርግበት የልምምድ ወቅት መሆኑ ኃጢአት ከዚህ ሕይወት ሊያስወጣን ይገፋናል። ስለዚህ ወደ እግዘአብሔር ለመቅረብ ኃጢአትን ቶሎ በንስሐ ማስወገድ ይገባል። በጾም ጊዜ ሰውነት ከምግብ እንደሚከለከል ነፍስም ከምድራዊና ዓለማዊ ፍትወት ሁሉ ትከለከላለች፤ ለዚህም በንስሐ አማካኝነት ወደ እግዚአብሔር እንመለሳለን ፤ እግዚአብሔርም ወደ እኛ ይመለሳል። “እነሆ የእግዚአብሔር እጅ ከማዳን አላጠረችም ጆሮውም ከመስማት አልደነቆረችም ፤ ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።” ይላል (ኢሳ 59፥1 ፣2 ስለዚህ በአማረና በተወለወለ ጠረጴዛ የቀረበ ምግብ ደስ እነደሚያሰኝ ሁሉ በንስሓና በንጽሕና በተወለወለ ሰውነት የሚደረግ ጾምና ጸሎትም ዋጋን ያስገኛል። “ወደ እኔ ተመለሰ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ” (ሚል 3 ፥ 7 ) በማለት እግዚአብሔር በነቢያቱ እያደረ ሕዝቡን ወደ ንስሓ ጠርቷል።
👉🏾👉🏾👉🏾የ #ንስሐ #መሰናክሎች (እንቅፋቶች)
(ቀጣይ ክፍል👆)
ስናጠቃልለው፦ በኃጢአት መኖር ሞት እና ባርነት ነው። ኃጢአት ሰላምን ዕረፍትን መረጋጋትን ማስተዋልን ይነሳል። ለጭንቀትም ያጋልጣል። ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ፍሬም ያርቃል። ለሥጋ ምኞት አሳብና ተግባርም አሳልፎ ይሰጣል። ከእግዚአብሔር ልጅነት ከሥላሴ ጥበቃ ከሕይወት ከፍቅር ከእግዚአብሔር ቸርነት ያርቃል ። ለዘለዓለም ሞትም አሳልፎ ይሰጣል። በሕይወት ጉዞ ውስጥ መውደቅና መነሣት አለ። መነሻው ምርኩዛችን ደግሞ ንስሓ ነው። ንስሐ ሁለተኛ እንደመወለድ ወይም በየጊዜው እንደመታደስ ነው ማለት ማንም ሰው በየጊዜው ኀጢአት የሚሠራ በእርጅና ላይ እርጅና በበሽታ ላይ በሽታ ይጨምራል ንስሐ የማይገባ ሰው ክርስትናው ከንቱ ነው እንዲሁ በደሉ የበዛ ይሆናል። ንስሐ የሚገባ ራሱንም ለአበ ነፍሱ የሚያስመረምር ሰው ግን ሁል ጊዜ ሐኪምን ርዳታ ከመጠየቁ የተነሳ በጤና በሰላም የሚኖር ሰውን ይመስላል።
ስለዚህ ጠያቂያችን ፤ ከንስሐ ሸሽቶ ኃጢአትን ለመዋጋት ማሰብ በኃጢአት ላይ ኃጢአት ለመደረብ በሩን ሰፋ እንደማድረግ እቅድ መያዝ ወይም ለንስሓ የቀን ቀጠሮ ማርዘም ስለሆነ ይህ እንደማይገባ እንመክራለን። ይልቁንስ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደነገረን ሸክማችሁ የከበደ ወደ እኔ ኑ ብሎናልና የጠራን ከሸክማችን ሊገላግለን ሊረዳን ነውና ንስሐ ገብቶ አሁንም አሁንም ሸክማችንን በማውረድ ከኀጢአት ለመላቀቅ መታገል ነው ያለብን። እግዚአብሔር አንችለውም ላልነው ነገር መቻልን የሚያድል ኃይላችን ነው። ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል (ያዕ 4፥8) ተብሏልና ስለዚህ ጠያቂያችን አስችለን ብሎ የንስሐ ጥሪውን ሰምቶ በንስሐ ወደ እርሱ መቅረብ ይገባል። በዚህ ጊዜ የኃይሉን ጸጋ ያድላል። “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” (ያዕ4፥6) ያለው ቃሉ አይታበልምና በየጊዜው ከሚሠራው ከባድ ኀጢአት ሰው ሁሉ እንዳይወድቅና ከእግዚአብሔር ልጅነት እንዳይለይ በየጊዜውም የሚሰጠው ጸጋ እንዳይጓደልበት ከልብ መመለስ መጸጸት ንስሐ መግባት ለክርስተያን ሁሉ ዋና ተግባሩ ነውና ይህን ትምህርት ተከታትለው ምክርችንን ተግባራዊ እንዲያደርጉ የደረሱበትንም እንዲያሳውቁን አደራ እንላለን።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ#2 ፦.የንስሐ ጠቀሜታ ምንድነው?
1/ ንስሓ ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው። ማስረጃ፦
– የእግዚአብሔር ሰው ነቢዩ ሚልክያስ እንደተናገረው “ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሥርአቴ ፈቀቅ ብላችኋል። ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሣለሁ” በማለት ከእግዚአብሔር ሕግ በመተላለፍና ትእዛዙን በማፍረስ ለበደሉት ሰወች የንስሓ ጥሪ እንዳቀረበላቸው እንመለከታለን።(ሚል 3፥7)
– ጠቢቡ ሰለሞን “ኀጢአቱን የሚሰውር አይለማም፣ የሚናዘዝባት እና የሚተዋት ግን ምህረትን ያገኛል” በማለት ስለ ኀጢአት ግልፀኝነትና ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለሚሆንልን ምህረት ተናግሯል። (ምሳሌ 28፥13)
– ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ ሲናገር በኀጢአት ወድቆ በንስሓ ስለተመለሰው የሰው ልጅ ኅጥያቱን ተመራምሮ እና በልቡ ተጸጽቶ ወደ ሰማያዊ አምላክ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ ውሳኔ ላይ ቢደርስ የምህረት እና የቸርነት አባት እግዚአብሔርም በደስታ እና በፍቅር እንዴት እንደሚቀበለው ተመዝግቦ እናገኛለን (ሉቃ 15፥1824)
2/ ንስሓ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅን ያመለክታል፦
ሐዋርያው ቅዱስ ጰውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በፃፈላቸው መልእክቱ ስለዚህ ሲናገር “እንግዲህ እግዚአብሔር ለእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልዕክተኞች ነን ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን እንለምናችኋለን” ሲል ተናግሯል። (2ቆሮ5፥20) በመሠረቱ ንስሓ መግባት ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር በሰዎች ልቦና እንደሚያድር የምናውቅበት መንገድ ነው። የሰው ልጅ ኀጢአትና በደሉን ትቶ በንስሓ እንደገና ተቀድሶ ከህይወቱ ካላስወገደ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ እና የመንግስቱ ወራሽ ሊሆን ስለማይችል ከሰማያዊ አባቱ ከእግዚአብሔር ጋር በመታረቅ የመንፈስ ቅዱስ ማደርያ ለመሆን መላ ህይወቱን ማዘጋጀት አለበት። ( 2ኛ ቆሮ 5፥19)
3/ ንስሓ ክርስቲያን ከኀጢአት እንቅልፉ የሚነቃበት ደወል ነው፦
በትምህርቱ የአለም ብርሃን የተባለ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በሮሜ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች በፃፈላቸው መልእክቱ ላይ “ከእንቅልፍ የምትነሱበት ሰዓት አሁን እንደደረሰ ዘመኑን እወቁ” በማለት ከኀጢአት እንቅልፍ ነቅተው ንስሓ እንዲገቡ አስረግጦ መክሯቸዋል (ሮሜ 13፥11)። የሰው ልጅ በኀጢአት አንቀላፍቶ የተኛበት ዘመን ይበቃኛል ብሎ በንስሓ ህይወት ወደ ቀደመው ማንነቱ ለመመለስ የሚችልበት የጽድቅ መንገዱ ሰፊ እና ቀና ጉዞ ስለሆነ በቤተክርስቲያን አባቶች ምክር እና ተግሳጽ ወደ ቀደመው ክብሩ መመለስ ይገባዋል (ሉቃ 15፥7)
4/ ንስሓ በኀጢአት ምክንያት ወድቆ የነበረ ክርስቲያን ወደ መንፈሣዊ ህይወቱ መመለሱን ያመለክታል፦
የኀጢአት ደዌ ያደረበት ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በንስሓ ህክምና ፈውስ ካላገኘ በመጨረሻ የሚገጥመው እድል የነፍስ ሞት ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር “አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሳ ክርስቶስም ያበራልሃልና ሲል ተናግሯል (ኤፌ 5፤14)። ወንጌላዊ ቅዱስ ዩሃንስም “እኛ ……ከሞት ወደ ህይወት እንደተሻገርን እናውቃለን። በማለት ስለ ህይወት መንገድ መስክሯል።
ሐዋርያው ቅዱስ ያእቆብ በመልእክቱ ላይ “ኅጢአተኛን ከተሳሳተበት መንገድ የሚመልሰው ነፍሱን ከሞት እንዲያድን የኀጢአትንም ብዛት እንዲሸፍን ይወቅ” ሲል ኀጢአተኛ መሆን በነፍስ መሞት እንደሆነ በንስሓ መመለስ ደግሞ በህይወት መኖር እንደሆነ መስክሯል። (ያዕ 5፤20)
ስለሆነም ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ከርስቲያን ከሁሉ አስቀድሞ ማወቅ እና መረዳት ያለበት በንስሓ ህይወት ወደ እግዚአብሔር መመለስ የህይወት ትንሳኤ ማግኘት ሲሆን ፀፀት በሌለው ኀጢአት ፀንቶ መኖር ደግሞ በመንፈሣዊ ህይወት የነፍስ ሞት መሆኑን ነው።
5/ ንስሓ ከሃጢያታችን እድፍ የምንታጠብበት ንጹህ ውሃ መሆኑን እና ጽድቅ እና ኩነኔን ለይተን የምናውቅበት አዲስ ልብ ነው።
ጽድቅ እና ኩነኔን፣ ህይወት እና ሞትን፣ ብርሃን እና ጨለማን፣ ገነት እና ሲኦልን፣ ታቦት እና ጣኦትን፣ መንግስተ ሰማያትን እና ገሃነመ እሳትን፣ እግዚአብሔርን እና ሰይጣንን (ቤልሆር) ለይተን ለማወቅ እና ለማስተዋል የምንችልበትን ንጹህ የሆነ የንስሓ ልቦና እግዚአብሔር እንዲሰጠን መለመን ያስፈልጋል። (2ኛ ቆሮ 6፥14-16
የእግዚአብሔር ሰው ነብዩ ሕዝቅኤልም ስለዚህ ሲናገር “ጥሩ ውሃንም ረጭባችኋለው እናንተም ትጠራላችሁ፣ ከርክሠታችሁ ሁሉ ከጣኦቶቻችሁ ሁሉ አጠራችኋለው አዲስ ልብ ሰጣችኋለሁ አዲስ መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ የድንጋዩንም ልብ ከስጋችሁ አወጣለሁ የስጋንም ልብ እሰጣችኋለው መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትዕዛዜም አስኬዳችኋለው ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ” በማለት አስተምሯል። (ሕዝ 36፥25-27
6/ ንስሓ የዲያቢሎስን ስራ በመቃወም ከኀጢአት ባርነት ነፃ የሚወጣበት መንገድ ነው።
ዲያብሎስ ያደረበት ሰው ሁል ጊዜም የኀጢአት ባርያ ነው።
መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል “እውነት እውነት እላችኋለሁ ኀጢአትን የሚያደርግ ሁሉ የኀጢአት ባርያ ነው፣ባሪያም ለዘላለም በቤት አይኖርም…. እንግዲህ ልጅ አርነት ቢያወጣችሁ በእውነት አርነት ትወጣላችሁ። በማለት ከዚህ አለም የኀጢአት ባርነት ነፃ መውጣት የሚቻልበት ዋናው መንገድ ለንስሓ የተዘጋጀ እና የወሰነ ንፁህ ልቦና መሆኑን አስተምሯል። ከምንም በላይ ንስሓ ለመግባት የተዘጋጀ እና በቁርጠኝነት ወስኖ ኀጢአትን የተወ ሰው ለእውነትም ከኀጢአት ባርነት ነፃ እንደወጣ የእግዚአብሔር ቃል ይነግረናል። ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ “እናንተ በቃሌ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛምርቴ ናችሁ እውነትንም ታቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል” በማለት አስተምሯል።(ዩሐ 8፥32)። “እንግዲህ የዲያብሎስን ስራ በመቃወም ለእግዚአብሔር መታዘዝ እና መገዛት ያስፈልጋል” (ያዕ 4፥7)
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ የንስሐ አባት ማለት ምን ማለት ነው?
መልስ ፦ ጌታችን በወንጌሉ ካህናትን “እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ” ማቴ 5 -14 ይላቸዋልና ከርኩሰት አረንቁዋ ከጨለማውና ከኀጢአት ሥራ ሁሌ በንስሐ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚመሩንና ኀጢአትን ጠልተን በበጎ ምግባር እንድንኖር መንገዱን የሚመሩን ናቸው፡፡
የንስሐ አባት ማለት ምስጢረኛችን በመንፈሳዊም በሥጋዊም ህይወታችን የቅርብ አማካሪዎቻያችን ማለት ነው፡፡ ጠቢቡ ሲራክ “ብዙ ሰዎች ወዳጆች ይሁኑህ ከብዙዎች አንዱ ምክርህን የምትነግረው ከልቡናህ ጋር አንድ ይሁን፡፡” ሲራክ 6-6 በማለት ይናገራል፡፡ ይህ ማለት ምእመናን ስለ ሃይማኖትና በጎ ምግባር የሚያስተምሩዋቸው ብዙ ካህናት ሊኖሩዋቸው ቢችሉም ከብዙዎች አንዱ ግን ንስሃቸውን የሚናዘዙለት መምህረ ንስሃ ሊሆናቸው እንደሚገባ ያስረዳልና መምህረ ንስሕ ማለት ምስጢረኛና አማካሪ ማለት ነው ፡፡
አበ ነፍስ ማለት ኃጢአታችንን የምንናዘዝለት ማለት ነው፡፡ ኀጢታችንን ለካህን ስንናዘዝ ለእግዚአብሄር መናዘዝና ክብር መስጠት ነው፡፡ ኢያሱ እንዳለ “ልጄ ሆይ ለአምላክ ከብርን ስጥ፡ ለእርሱም ተናዘዝ፡ ያደረግከውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ” ኢያሱ 7-19፡፡ ኀጢአትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር ክብር መስጠት እንደሆነ ያሳየናል፡፡ አበዉ ካሀናትም ኑዛዜን ከተቀበሉ በኋላ “እግዚአብሔር ይፍታህ” እንጂ ”ፈትቼሃለሁ ” አይሉም፡፡ ኀጢአተዘችንን በነሱ ፊት ብንናገርም ሰሚዉም ሆነ በእነርሱ እጅ ስርየተ ኀጪአት የሚሰጠዉ እርሱ ባለቤቱ ስለሆነ ነው፡፡ በመሆኑም አበ ነፍስ ማለት ኀጢአታችንን በዝርዝር ምንም የሚያስፈራ ኀጢአት ቢኖረንም እያሰታወስን አንዳች ሳናስቀርና ሳንጠራጠር በዝርዝር የምንነግረው የእግዚአብሔር አይን ነው ማለት ነው፡፡
የንስሐ አባት/አበ ነፍስ ወይም መምህረ ንስሐ ማለት የንስሐ ልጆቹ ትክክለኛውን ዓላማ ይዘው የንስሐ ሕይወት እንዲጀምሩ የሚያደርግ በጎ መሪ ማለት ነው፡፡
መምህረ ንስሐ ማለት ልጆቹን መሠረታዊ ትምህርተ ሃይማኖት የሚያስተምርና የልጁቹን ሁለንተናዊ ለውጥ የሚከታተልና ስለ በጎቹ የሚጨነቅ እረኛ ማለት ነው፡፡
የንስሐ አባት ማለት ምእመናን ሃይማኖታቸውን እንዳይለውጡ፣ ምግባራቸውን እንደይስቱ በርካቶችም ለጠንቋዮችና ለአሳቾች ሰለባ እንዳይሆኑ የጠራውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ከምንጩ ማስጎንጨት የሚችልና እሄንንም የማድረግ ግዴታ ያለበት ባላደራ ማለት ነው፡፡
የንስሐ አባት ማለት ልጆቹ ለሥጋ ወደሙ እንዲበቁ ያለመታከት የሚተጋ ማለት ነው፡፡ የንስሐ አባት ልጆቹ ለሥጋ ወደሙ እንዲበቁ ሁሌም መጐትጐትና መቀስቀስ አለበት፡፡ ይህም የሚሆነው በኃይል፣ በማጣደፍ ወይም በማስፈራት አይደለም፡፡ ካህኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወኪል፣ የእግዚአብሔር አደረኛ ስለኾነ ሁሌም ማትጋት፣ መጐትጐት፣ መቀስቀስ ይጠበቅበታል፡፡
የንስሐ አባት ለእያንዳንዱ ልጆቹ እንደየ አቅማቸውና እንደየሃይማኖት እውቀት መጠናቸውና እንደየ መንፈሳዊ እውቀታቸው አቻ እስከሚሆኑለት ለያይቶ በማስተማር ማብቃት አለበት፡፡
የንስሐ አባት ማለት በንስሐ ልጆቹ መካከል ፍጹም መቀራረብ እንዲኖር የሚያደርገ ነው፡፡ የንስሐ ልጆች ለብዙ ችግሮች የመፍትሔ አካል ኾነው እንዲያገለግሉ ዕድል ይሰጣልና፡፡ የተቸገሩትን ከመርዳት ዠምሮ አንዱ ለሌላው አርአያ ኾኖ በተግባር እስከማስተማር ድረስ ማድረግም የንስሐ አባት ድርሻ ነው፡፡ ይህ ማለት የአንድ ካህን ንስሐ ልጆች ከአንድ የሥጋ አባትና እናት የተወለዱ እህትማመቾች እና ወንድማማቾች ያህል ከዚያም በበለጠ ሁኔታ መቀራረብ አለባቸው ማለት ነው፡፡የንስሀ አባት ማለት ይህን የሚተገብር ማለት ነው፡፡
ከቊርባን በፊት ንስሐ ይቀድማልና፡፡ ሰው ከኃጢአት ንጹሕ ሆኖ የሚገኝበት ጊዜ ስለሌለ ጧት የሠራውን ለማታ፤ ማታ የሠራውን ለጧት ለመምህረ ንስሐው ነግሮ መምህረ ንስሐው ያዘዘውን ሠርቶ ሊቀበል ይገባዋልና ይህ ታላቅ ሀላፊነት የተጣለው ደግሞ በመምህረ ንስሀው ላይ ነው፡፡
የንስሐ አባት ማለት ባለአደራ ማለት ነው፡፡ ጌታችን በወንጌል “መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በበረኻ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ማን ነው?” ሉቃ.15 -5 ያለው፡፡ ካህናት ከእግዚአብሔር በአደራ እንዲጠብቁ የተሰጣቸውን ኹሉንም ሳይዘነጉ እያንዳንዱን በነፍስ ወከፍ ሊጠብቁና ሊያገለግሉ የሚገባቸው ናቸው፡፡
የንስሐ አባት ከንስሐ ልጆቹ ጋር የሚፈጥረው ግላዊ ግንኙነት ከቤተሰባዊነት ያልተሻገረ ኾኖ ሲቀነጭርና እጅጉን ያነሰ ሲሆን ነው፡፡ ብዙ ካህናት ወደ ምእመናን ቤት መጥተው ሲያበቁ መስቀል ከማሳለምና ጠበል ከመርጨት ያለፈ አገልግሎት አይሰጡም፡፡ ካህናት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዳስቀመጠላቸው ከሥራቸው ኹሉ ቅድሚያውን ሰጥተው ማስተማር፣ መምከር፣ ኑዛዜን መቀበል፣ ማጽናናትና መገሰጽ ይገባቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የንስሐ ልጃቻቸውን በጥንቃቄ ይዘው ለሥጋ ወደሙ ማብቃት ግባቸው ስለኾነ ትኩረታቸው ኹሉ ወደዚኽ ዋነኛ የክህነት ዓላማቸው መሆን አለበት ፡፡ ይህም የካህኑ ትልቁ ሀላፊነት ነው፡፡
የንስሐ አባት የንስሐ ልጀቹን የቤተ ሰብ አባላት ቁጥርና እያንዳንዱን በሚገባ ማወቅ አለበት፡፡
አንድ የንስሐ አባት ልጆቹንና አጠቃላይ ቤተሰቡን እያሰታወሰ አዘውትሮ ስለ ሁለንተናቸው መጠየቅ አለበት፡፡
የንስሐ አባት ከልጆቹ ጋር አብሮ በመጸለይ ጸሎትን ማለማመድ፤ ሆኖ በማሳየት እውነተኛ የአባትና የልጅ ፍቅርን ማሳየት፤ በመንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን በሥጋዊም ሕየዋታቸው መጨነቅ፤ ስራቸው እንዲባረክ አዘውትሮ፤መጸለይ በአጠቃላይ ልጆቹን በቅርበት መከታተል፤ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ተግባሩ እሄ ነው፡፡
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን ላይ ያገኛሉ
👉👉👉ጥያቄ# 4 “የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።” (ማቴ ፲፮᎓፲፱) ይህ ማለት ምን ማለት ነው?
መልስ፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሰጣቸው የክህነት ስልጣን ማሰር እና መፍታት የሚችሉበት ረቂቅ እና ሰማያዊ ስልጣንን ነው። ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባትም ሆነ ከመንግስተ ሰማያት ለመከልከል የሚያስችል ከመንፈስ ቅዱስ የተሰጣቸው ስልጣንም ነው። ይህ ማለት ስልጣን ሁሉ የራሱ ገንዘብ የሆነው የባህርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ 12ቱን ሐዋርያት እና 72ቱን አርድእት ከዓለም መካከል መርጦ በሾማቸው ግዜ ኀጥያት ሰርተው በደል ፈጽመው ወደ ሐዋርያት ቀርበው በኀጢአታቸው ተጸጽተው የተናዘዙትን ኀጥያታቸውን የማስተሰረይ ስልጣን ስለተሰጣቸው ኀጥያታችሁ ይቅርላችሁ ያሏቸው ሁሉ የተሰጣቸው ረቂቅ ስልጣን ኅጥያታቸው ሁሉ እንዲደመሰስ ያደርጋል።
በሰሩት ጥፋት ሳይጸጸቱ እና ከበደላቸው የማይመለሱትን ደግሞ በተሰጣቸው ረቂቅ ስልጣን ሲፈርዱባቸው በስጋቸው ሞትና ልዩ ልዩ መቅሰፍት ይቀጣሉ ማለት ነው።
ለዚህ ማስረጃ ፦2ኛ ነገስት 5፥20-27፣ የሐዋ 5፥1-10፣ ዩሐ 8፥18-24
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን ላይ ያገኛሉ
መልስ፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሰጣቸው የክህነት ስልጣን ማሰር እና መፍታት የሚችሉበት ረቂቅ እና ሰማያዊ ስልጣንን ነው። ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባትም ሆነ ከመንግስተ ሰማያት ለመከልከል የሚያስችል ከመንፈስ ቅዱስ የተሰጣቸው ስልጣንም ነው። ይህ ማለት ስልጣን ሁሉ የራሱ ገንዘብ የሆነው የባህርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ 12ቱን ሐዋርያት እና 72ቱን አርድእት ከዓለም መካከል መርጦ በሾማቸው ግዜ ኀጥያት ሰርተው በደል ፈጽመው ወደ ሐዋርያት ቀርበው በኀጢአታቸው ተጸጽተው የተናዘዙትን ኀጥያታቸውን የማስተሰረይ ስልጣን ስለተሰጣቸው ኀጥያታችሁ ይቅርላችሁ ያሏቸው ሁሉ የተሰጣቸው ረቂቅ ስልጣን ኅጥያታቸው ሁሉ እንዲደመሰስ ያደርጋል።
በሰሩት ጥፋት ሳይጸጸቱ እና ከበደላቸው የማይመለሱትን ደግሞ በተሰጣቸው ረቂቅ ስልጣን ሲፈርዱባቸው በስጋቸው ሞትና ልዩ ልዩ መቅሰፍት ይቀጣሉ ማለት ነው።
ለዚህ ማስረጃ ፦2ኛ ነገስት 5፥20-27፣ የሐዋ 5፥1-10፣ ዩሐ 8፥18-24
ከዚህ በላይ በጠቀስናቸው ማስረጃዎች የመንግሰተ ሰማያት መክፈቻ ለሐዋርያት ተሰጠ ሲባል በተሰጣቸው ስልጣነ ክህነት መንግስተ ሰማያት ማስገባት እንደሚችሉ እና የማይገባቸውን መከልከል የሚችሉ መሆናቸውን ለመግለጽ እንጂ የቤት ወይም የበር ቁልፍ መክፈቻና መዝጊያ ቁሳዊ ነገር አለመሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። ማሰር መፍታት የሚለውም በዚህ አለም ላይ ሰው በፈጸመው ወንጀል የሚታሰርበት አግር ብረት ወይም ገመድ ወይም ሌላ ነገር ሳይሆን ከላይ እንደገለጽነው በተሰጣቸው ረቂቅ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ስልጣን ኅጥያትን የማስተሰረይ፣ የኀጥያተኞችን ኅጥያት የመያዝ ፀጋ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ. ንስሐ አባት በርቀት መያዝ ይቻላል ወይ? ንስሐስ በስልክ ይሆናል ወይ?
መልስ፦ ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ (አማኝ) የሆነ ክርስቲያን ለአካለ መጠን ከደረሰበት ግዜ ጀምሮ የንስሐ አባት መያዝ ክርስትያናዊ ግዴታው እንደሆነ በቤተክርስቲያን የቀኖና መጽሐፍ ተደንግጓል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያውያን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመናን ኑሮዋቸውን ለማሸነፍና የተሻለ ኑሮ ለመፈለግ ሲሉ ቤተክርስቲያንና ካህናት አባቶች ወደማይገኙበት ክፍለ ዓለም በልዩ ልዩ ምክንያት ተበትነው እንደሚኖሩ ይታወቃል። ሌላው ቀርቶ በኢትዮጵያ አገራችን ሳይቀር በረሃማና ጠረፋማ በሆነ አካባቢ እንዲሁም አህዛብ በሚበዛበት ቦታ የሚኖሩ ክርስቲያኖች በመከራና በፈተና ግዜ የሚያጽናናቸውና የሚመክራቸው አባት ሊያገኙ አይችሉም። የሚጸልዩበት እና ፈጣሪያቸውን የሚማፀኑበት ቤተክርስትያንም አያገኙም።
ስለዚህ በቅዱስ መጽሐፍ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚነግረን ሰውን በነፍስ የማዳን ሥራ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው። ቤተክርስቲያንና አባቶች ካህናት በቅርብ የማይገኙበት ክፍለ ዓለም (አካበቢ) የሚኖሩ ማለትም በአውሮፓ፣ በአሜሪካ፣ በአፍሪካ፣ በአረብ አገሮች እና በሌላውም ክፍለ አለም ሁሉ እየኖሩ የንስሐ አባት ለመያዝ ቢፈልጉ ከምንም በላይ እግዚአብሔር የኛን የውስጥ ችግር ያውቀዋልና አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ያለ ንስሐ አባት አንድ ቀንም መኖር ስለሌለበት የንስሐ አባት እንዲኖረው በሃይማኖቱና በመንፈሳዊ ህይወቱ የመረጠውን ካህን እርቀት ሳይገድበው መያዝ ይችላል። ካለው ችግር አንፃርም በስልክ እና በሌላ መልእክት በመገናኘት መንፈሳዊ ትምህርት እና ከንስሐ አባት የሚሰጠውን የንስሃ ቀኖና መቀበል ይችላል። ማንኛውንም በጎ ስራ ሁሉ አባቱ የሚመክሩትን እና የሚያዙትን ሁሉ በመፈፀም የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ ስለሚችል የግድ በአካል ካላገኘኋቸው አብሬ በአንድ አጥቢያ ካልኖርኩኝ የንስሐ አባት መያዝ አልችልም በሚል ምክንያት ያለጠባቂ መኖር የለበትም ።
ይህን በሚመለከትም ከዚህ በፊት ስለ ንስሐ አባት አያያዝ ጥያቄ ቀርቦ በአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት እና በቤተክርስትያን መምህራን ንስሐ አባት በርቀት መያዝ እንደሚቻል በተደጋጋሚ ምላሽ የተሰጠበት ሃሳብ ስለሆነ ፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት እንዲያሥሩና እንዲፈቱ የሰጣቸው ስልጣነ ክህነት ጊዜና የቦታ ርቀት የማይወስነው ስለሆነ ፤ በአካባቢው አባት የሚሆን ካህን ከጠፋ ያለጠባቂ ብንኖር ጠላታችን ዲያብሎስ ነፍሳችንን እንዳይነጥቃት የንስሐ አባት በርቀት መያዝ ይችላሉ። በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ላይ ምእመናን መጨናነቅ እንደማያስፈልጋችሁ መንፈሳዊ ምክራችንን እንለግሳለን።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ፦ ንስሐ ለመግባት ፈራሁ ፍርሐቴን ላለመፍራት ምን ላድርግ?
መልስ፦ከእውነተኛ ሃይማኖትና ምግባር ስንርቅ የንስሐ ህይወታችን ጨርሶ ይቀጭጫል። ያኔ ደግሞ በሰራነው ኀጥያት (ጥፋት) ነፍሳችን ፈፅሞ ትቃተታለች ትጨነቃለችም። ስጋችን ምድራዊ የሆነውን የስጋ ስራ ለመስራት ነፍሳችን ደግሞ ሰማያዊ የሆነውን የፅድቅ ስራ ለመስራት ለኛ ግልፅ ሆኖ በማይታወቅና በማንረዳው ሁኔታ ሁለቱም ህይወታችንን የጦር አውድማ ሲያደርጓት በኛ ላይ የፍርሃት መንፈስ ይነግስብናል። ከጥፋታችን ተመልሰን ንስሐ እንዳንገባ ደግሞ የበጎ ነገር ሁሉ ጠላት የሆነው እና የእኛን ፅናት የማይፈልገው ሰይጣንም ግራ እንዲገባን እና የፍርሃቶቻችን ምክንያቶች እንዲበዙ ያባብስብናል። ስለዚህ፤ ጠያቂያችን ለዚህ ችግርዎ የምንመክርዎት የሰይጣን ውግያ ስለሆነ እግዚአብሔር ደግሞ የፍርሃት አምላክ ሳይሆን የፍቅርና የሰላም አምላክ በሃጥያት የወደቀውን አይዞህ ልጄ ብሎ የሚያነሳ እና ከጠፋንበት ፈልጎ የሚያገኝ አምላክ ስለሆነ የሚቃወምዎትን ክፉ መንፈስ እንደምንም ታገሉት። የመዳን ቀን አሁን ስለሆነ የቀጠሮ ቀን እና ሰዓት ሳያራዝሙ በአካባቢዎ ወደሚገኙ አባቶች ካህናት ቀርበው በማማከር የፈለገውን ያህል ከባድ ኀጥያት ሰራው ብለው ቢያምኑም እንኳ በእግዚያብሔር ዘንድ የማይፋቅ በደል የለምና ፍርሃቶትን አርቀው ወደ ይቅር ባይ አምላክ ይቅረቡ በማለት ምክራችንን እንለግሳለን። የበለጠ መንፈሳዊ ምክርና አገልግሎት ከፈለጉ በውስጥ መስመር ያነጋግሩን።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ፦ ኀጢአቴን መናዘዝ እፈልጋለሁ ከእኔ የሚጠበቀው መስፈርትስ ምንድን ነው?
መልስ፦ “እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ “(ማቴ3፥8) ኅጢአት ሠርቶ የንስሐ ሕክምና ያላገኘ ሰው በነፍሱ ምውት ነው። ሉቃ 15፥24
ከዚህ የተነሣ ኅጢአት ለመናዘዝና ንስሐ ለመግባት ከሚፈልግ አንድ ክርስቲያን የሚጠበቀው ፡-
1 በቅድሚያ ኅጢአት መሥራቱን አምኖ ለራሱ ሕሊና መናዘዝ (መፀፀት)።
ስለሠራው ኅጢአት ወይም በደል እየተጸጸተ ጧት ማታ በደሉን በፀሎትና በልመና ለፈጣሪው መናዘዝና ኅጢአትን በእግዚአብሔር ፊት ማመን (መዝ50 ፣ ዳን9፥5፣ ነህ1፥6-7)
– ስለሠራው ኅጢአት ወይም በደል እየተጸጸተ ጧት ማታ በደሉን በፀሎትና በልመና ለፈጣሪው መናዘዝና ኅጢአትን በእግዚአብሔር ፊት ማመን (መዝ50 ፣ ዳን9፥5፣ ነህ1፥6-7)
– ኅጢአትን (በደልን) ለካህን መናዘዝና ንስሐ መግባት። ካህኑ የእግዚአብሔር አገልጋይና እንደራሴ ስለሆነ የሠራነውን ኅጢአት ለካህኑ በመናዘዝ ንስሐ መግባት፤ ኅጢአታችን እንዲሠረይልን በእግዚአብሔር ፊት ንስሐ መግባትና መናዘዝ ማለት ነው። (ኢያሱ7፥19 ማቴ3፥6 ዘሌ5፥5-6 የሐዋ19፥18) የተሰጠንን የንስሐ ቀኖና በአግባቡ መፈፀም።
– የበደልናቸውንና የበደሉንን ሁሉ ይቅር በማለት የጥል ግድግዳ አፍርሰን በፍቅር አሸንፈን ስለዘለዓለማዊ ሕይወት ብለን በፍጹም ሕሊና በሰላም መኖርና ተመልሶ በኅጢአት ላለመውደቅ አዘውትሮ የንስሐ አባትን ወይም የሚቀርቡትን የሃይማኖት መምህር ማማከር፣ ምክር ማግኘት በታቻለ መጠን መጸለይ፣ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድና ቃለ እግዚአብሔር መስማት፣ በቤትም ውስጥ ቢሆን መንፈሳዊ መዝሙርና ትምሕርት ማዳመጥ አስፈላጊ እንደሆነ የምናስገነዝበው ለጠየቁን ምዕመን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ክርስቲያን እንዲጠቅም ነው።
የንስሓ አባትን በሚመለከት ፦ ይመክረኛል ያስተምረኛል ያሉትን የንስሓ አባት የሚሆን ካህን በአካባቢዎ ካሉ ይያዙ፤ በአከባቢዎ ማግኘት የማይችሉ ከሆነ በራስዎትም ሆነ በሚያምኑት ሰው በኩል ያገኙዋቸውን እውነተኛ ካህን በርቀትም ቢሆን ይያዙ፤ ወይም ደግሞ እኛ በህይወታቸው ምሳሌ ይሆናሉ ብለን የመረጥናቸው አባቶች አድራሻ በድረገፃችን ላይ ስለሚገኝ ደውለው በማናገር ንስሓ አባት በማድረግ መያዝ ይችላሉ።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ:ንሰሐ ስንገባ የሰራነውን ኀጥያት አጠቃለን መናገር እንችላለን? ዋሽተን ከሆነ ዋሽቻለው፣ ሰርቀን ከሆነ ሰርቄያለው ብለን ሌሎችንም ኀጢያቶች እንደዚህ መናገር ይቻላል?
መልስ፦ መልሱ አይቻልም ነው ። ምክንያቱም በቀኖና ቤተ ክርስቲያን በእያንዳንዱ ጥፋታችንና በደላችን ወደ መምሕረ ንስሐችን ቀርበን ኀጥያታችንን ስንናዘዝ ባጠፋነው ደረጃ ንስሐ መቀበል እንዳለብን በቀኖና ቤተክርስቲያን ተደንግጓል። ቀኖና ወይም ንስሐ የሚሰጠን በፈጸምነው ኅጥያት መጠን ተለክቶ ስለሆነ እያንዳንዱ ያጠፋነውን ጥፋት ከባድም ቢሆን ሳንፈራ፤ ቀላልም ቢሆን ሳንንቅ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ለነፍሳችን እረኛ ላደረግነው ካህን መናገር አለብን ። የሚሰጠውም ንሰሐ በጥፋቱ ደረጃ ፣ አይነት እና መጠን የሚቀበለው መሆን ይገባዋል። ንስሓ ላልገቡበት ኅጥያት ካለም እንደገና መናገርና ቀኖና መቀበል ያስፈልጎታል። ስለዚህ ለንሰሐ አባቶቻችን የምንደብቀው የኀጢአት ሚስጥር የለንም። እንደምሳሌ ወደ ሀኪም ቤት የሚሄድ ታማሚ ወይም ታካሚ የህመሙ አይነትና መጠን ተለይቶ በሀኪም ዘንድ ሳይረጋገጥ መድሀኒት አይታዘዝለትምና።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ# 10 ፦ አንድ ሰው ንስሀ ሳይገባ ጸበል መጠመቅ ይችላል? ወይንም ንስሀ ገብቶ ግን አንድ የረሳው ነገር ቢኖር ያልተናገረው፣ መጠመቅ እና ፀበል መጠጣት ይችላል?
መልስ፦ ፀበል አንዱ የንስሐ መንገድ ስለሆነ ለንስሐ ከሚያበቃን የኅጢአት ሥራችን ለመመለስ በቁርጠኝነት ከወሰንን ጠያቂው እንዳሉት ፀበል ለመጠመቅም ሆነ ለመጠጣት እንችላለን። ይህን ስንል ግን የሠራነው ኅጢአት ተለይቶ መታወቅ አለበት። ሌላው፥ የወለደች ሴት፣ የሴቶች ልማድ የምታይ ሴት እስከሚነፁ መጠበቅ አለባቸው። ከዚህም በላይ ፀበሉን ብንጠጣውም ሆነ ብንጠመቅበት ከልብ በሆነ እውነተኛ መጸጸት ወደ ንስሐ ሕይወት ተመልሰን ከበደላችን ነፃ ካልሆን ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝራዎች፣ ሟርተኞች ፣ መተተኞች፣ አስማተኞች፣ ቀማኞች፣ ወንበዴዎች፣ ትዕቢተኞች፣ ፍርድ አጉዳዮች፣ ከሃዲዎች ወዘተ ሁነን በአጠቃላይ ከአንድ ክርስቲያን የማይጠበቅ ክፉ ሥራ እንደፈጸምን እያወቅንና በንስሐ ሣንታጠብ እግዚአብሔርንና ራሣችንን በመደለል በአስመሣይነት ፀበሉን ብንጠመቅበትም ሆነ ብንረጭ ጥቅም አይሰጥም። እንዲያውም ከበረከት ይልቅ መርገምን ያመጣብናል። በመሆኑም ኅጢአተኛ ሰው ስለበደሉ የጊዜ ቀጠሮ ሣይሰጥ የመዳን ቀን ዛሬ ስለሆነ ባለበት ቦታ ሁኖ ያለምንም ድካምና ውጣ ውረድ ከልብ ለሚያምነውና ለነፍሱ እረኛ አባት አድርጎ ለተቀበለው አባቱ ኅጢቱን መናዘዝ አለበት። በእርግጥ የእኛ ኅጢአት የእግዚአብሔርን ቅድስና አያረክስም። እኛ ግን ንስሐ ሳንገባ በድፍረት የምናደርገው ሁሉ ተጨማሪ ኅጢአት ስለሚሆንብን፤ ወደ ቤተክርስቲያን ለመግባትና ፀበል ለመረጨትም ሆነ ለመጠጣት የሚያስከለክለውን በደላችንን ለይቶ ለማወቅ ሁልጊዜም ቢሆን መምህራንን ወይም የቤተክርስቲያን አባቶችን እንድታማክሩ በእግዚአብሔር ስም አደራ እላችኋለሁ።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ፡- የንስሐ መገለጫ ምንድን ነው?
#ንስሐ
✍መልስ፡- ንስሐ የሚለው ቃል ትርጓሜው ምን እንደሆነ፣ ምንን እንደሚያመለክት፣ አስፈላጊነቱ፣ ጥቅሙ ምን እንደሚመስል ከዚህ በፊት ስፍር ቁጥር የሌለው ውይይት አድርገናል፡፡
ሁሉም ሰው በአንድም በሌላም መንገድ የመነሻውም፣ የመዳረሻውም፣ ሐሳቡ ንስሐ በሚመለከት በመሆኑ በእሱ ዙሪያ ላይ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ብዙ ሥራ ሰርተናል ብለን እናምናለን፡፡
ንስሐ የሚለው ቃል የግዕዝ ቋንቋ እንደሆነ፣ ትርጓሜውና ፍቺው መመለስን፣ መፀፀትን፣ የሚያመለክት ሌሎቹም እነዚህን የመሰሉ ወርቃማ ንድፍ ሐሳቦች የያዘ እንደሆነ ተነጋግረናል፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ንስሐ ትልቁና ዋናው ዓላማ ነው፣ ቤተክርስቲያናችን ብዙ ልጆቿን ከማጣት የምትድንበት መልሳ ወደ እቅፏ የምትይዝበት፣ ከገቡበት፣ ከወደቁበት፣ ከጠፉበት ሁሉ ፈልጋ የምታገኝበት፣ ለመንግሥተ እግዚአብሔር የምታበቃበት ለእውነተኛ ኃይማኖት፤ ለእውነተኛ ምግባር የምታበቃበት ትልቁ መገለጫዋ ንስሐ ነው፡፡
አንድ ክርስቲያን ማንም የማያውቅበትን፣ ማንም ያልደረሰበትን ምንም ዓይነት መረጃና ማስረጃ የሌለበት፣ በመቼም ጊዜ እሱ ስለሠራው፣ ስለፈጸመው ድርጊት ከቶም የሚያሰጋው ነገር፣ና የሚጠየቅበት መንገድ እንደሌለ እያወቀ በራሱ ልባዊ ወይም ፍፁም በሆነ እምነት ያንን የፈጸመውን ስህተት በማሰብ ተፀፅቶ፣ አዝኖ፣ ከዚህ በደሌ፣ ከዚህ ኃጥያቴ፣ ከዚህ ጥፋቴ እንዴት መውጣት እንዳለብኝ፣ ስለፈጸምኩት ኃጢያት በደልስ ተጠያቂ እንዳልሆን ምን ማድረግ አለብኝ? ይላል፡፡
እንደዚሁም ደግሞ ከልብ ተፀፅቶ፣ ለዚህም ፈተና ቁልፍ የሆነው መፍትሔ በፍፁም እምነት ወደ “አበነፍስ ወይም ወደ ንስሐ አባት” በመሔድ መናዘዝና ከልብ በሆነ ፀፀት መመለሱንና ስለ ሰራው በደል ኃጢያት የሚሰጠውን ቀኖና ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁ መሆኑን ለመግለፅ “አበስኩ ገበርኩ” በማለት ለንስሐ አባት የሚደረገው ኑዛዜና፣ የሚሰጠው የንስሐ ቀኖና የንስሐ መገለጫ ነው፡፡
በአጠቃይ ተነሳሒ ወይም ደግሞ ንስሐ ለመግባት የመጣው አማኝ፣ ምእመን፣ ለመንፈስ ቅዱስ ልጃቸው በሠራው በደል፣ ኃጥያት፣ጥፋት ሁሉ ተገቢውን ንስሐ የሚሰጡ አባት፣ የሚሰጠው የንስሐ ቀኖና “የንስሐ መገለጫ” ይባላል፡፡
በዚህ የኃይማኖት ስርዓት የሚከናወነው ነገር ሁሉም ነገር ከልብ በሆነ እምነት ስለሆነ የሚፈጸመው በቁሳዊ ነገር፣ በሥጋዊ ዳኝነት፣ በሚጨበጥ፣ በሚዳሰስ እና ከሥጋዊ ዳኝነት ወይም ማስረጃ ጋር፣ መረጃ ጋር የሚያያዝ ሆኖ የሚታይ አይደለም፡፡
ሁሉም ነገር መንፈሳዊ ነው፣ ሁሉም ነገር እንደ መንፈሳዊነቱ ለብዙዎቹ የማይገባ፣ ለብዙዎቹ የማይገለጥ፣ የማይረዳ ረቂቅ ሚስጥር ያለበት ነው ስለዚህ ነው በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ በንስሐ ቀኖና የምናልፍበት መንፈሳዊ ጉዟችን የንስሐ መገለጫ ነው፡፡
ጠያቂያችን የንስሐ መገለጫ ምንድን ነው? ያሉት ምናልባት የራሳቸው የታሰባቸውና፣ የሐሳባቸው መነሻ ያደረጉት እግዚአብሔርና እሳቸው የሚያውት ነገር ሊኖር ይችላል፤ እንደ እውነተኛው አስተምሕሯችንና፣ ሁላችንም ልንጋራ የምንችለው ሐሳብ ግን አሁን የተገለፀውና ከዚህም የሚሰፋው ከዚህ ጋር የሚያያዘው ሐሳብ ነው ማለት ነው፡፡
ስለ ንስሐ ሕይወት ብዙ ነገር በቅዱስ መጻሕፍት፣ በሌሎቹም ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ንስሐ የተፃፈውን ነገር እያነሳን ስላወራን ማለት ነው፤ በዋናነት ከላይ በመግቢያችን ላይ እንዳልነው አንድ ተነሳሒ ማንም ሳያስገድደው ዝሙት ኃጢያት ነው፣ ሐሜት ኃጢያት ነው፣ አመንዝራነት ኃጢያት ነው፣ ሴሰኝነት ኃጢያት ነው፣ ስርቆት፣ አምልኮ ባእድ፣ ጥንቆላ እነዚህን የሚመስሉ ሁሉ ኃጢያቶች ናቸው፡፡
በዚህ ሁሉ በአንዱም በሌላውም በድያለሁ፣ አጥፍቻለሁ ብሎ ራሱን ማሳመንና፤ መንፈሳዊ ነገር ሁሉ በማንም የማይመረመር የማይገለጥ፣ በምድራዊ ዳኛ ዳኝነት የማይሰጥበት፣ ፍትሕ የማያገኝ ሁሉም ነገር ረቂቅና ሁሉም ነገር ድንቅ፣ ሁሉም ነገር መንፈሳዊ የሆነ ነው፣ እንዲህ ብሎ በማመን ለዚህም ችግሬ ደግሞ መፍትሔው ይሔ ነው ብሎ ወደ ንስሐ አባት መሔድ፡፡
የንስሐ አባቱ በሚቻለውና በሚሆነው ነገር ጹም፣ ጸልይ፣ ስገድ፣ መፅውት ብለው በሚሰጡት ቀኖና የኃጢያት ስርየት አገኛለሁ ብሎ፣ የኃጥያት ስርየት እንዳገኘም ደግሞ በዓይኑ ሳያየው፣ በእጁ ሳይጨብጠው፣ሳይዳስሰው፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚከናወነውን ነገር ይሆናል ብሎ ማመን ይሔ ሁሉ የንስሐ መገለጫ ነው፡፡
ከዚህ የሚሰፋ፣ ከዚህ የሚረቅ፣ ከዚህ የሚጠልቅ ወርቃማ ሐሳብ የያዘ ነው የንስሐ መገለጫ ብለናል፤ በጥቂቱ ይሔንን ሐሳባችንን ካጋራናችሁ ከዚህ በፊት እግዚአብሔር በፈቀደ ብዙ ተወያያተንበታል፣ እሱንም በማከል ስለ ንስሐ በቂ ግንዛቤ ይኖራችኋል ብለን እናምናለን፡፡
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፡- 1ኛ የሰው ልጅ ከስንት ዓመቱ በኋላ ነው ለሠራው ኃጢያት #ንስሐ መግባት የሚጀምረው? ወይስ ከስንት ዓመቱ ጀምሮ ነው ንስሐ መግባት ያለበት?
#የንስሐ #አባት እና #ዕድሜ
👉ጥያቄ፡- 2ኛ የንስሐ አባት መያዝ ያለበት ከስንት ዓመት በኋላ ነው? አንዳንዶቹ ስጠይቃቸው ከአሥራ አምስት ዓመት በኋላ ነው ይላሉ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ከሰባት ዓመት ጀምሮ ነው ይላሉ የቱ ነው ትክክለኛው?
✍መልስ፡- በእግዚአብሔር ፈቃድበአርባና በሠማኒያ ቀን ሁላችንም የእግዚአብሔር ልጀች እንድንሆን በእግዚአብሔር ጉባኤ ከተቀላቀልንበት ከቆጠርንበት ጊዜ ጀምሮ የአባቶች ጥበቃ፣ እንክብካቤ፣ አመራር፣ ትምሕርት፣ ተግሣፅ ከእኛ አይለይም፡፡
ሁልጊዜ በአይምሯችን ላይ የነገሠብን ዘወትር የማንለይበት የኃጢያት ጉዳይ ስለሆነ እንቅልፍ የሚነሳንም፣ እረፍት የሚያሳጣንም. የሚያስጨንቀንም ጉዳይ እሱ ስለሆነ ለይቶልን ኃጢያት የሠራንበት ጊዜና ዘመን እግዚአብሔር ለረዳቸው ደግሞ ኃጢያታቸውን በንስሐ ሕይወት ለመታጠብ ወደ ንስሐ አባት መቅረብ ወይም የንስሐ አባት እንዲኖራቸው የማስፈለጉን ሁኔታ ብቻ ስለምናስብ ነው፡፡
ሕፃናት በዚያው እድሜያቸው እንደ ጡጦ እንደ ወተት ጠብተው የሚያድጉት ትምሕርት አለ መንፈሳዊ ትምሕርት ማለት ነው ልክ እንደ እሳትና ውኃ በባሕሪያቸው ተለይተው እንዲያውቋቸው ማለትም ይሔ የሚያቃጥል ነው፣ ይሔ ደግሞ ውኃ ነው፣ ስለዚህ ወደ ውኃው እጅህን ብትልክ አትጎዳም፣ ወደ እሳቱ ብትልክ የሚያቃጥል ነው ብለው ወላጆች ለልጆቻቸው እከሰከሚያስተምሯቸው ሁሉ በቤተክርስቲያንም ይሔ ኃጢያት ነው፣ ኃጢያት የሚሆነውም በዚህ በዚህ ምክንያት ነው የምንላቸው፡፡
የሚበላ ምግብን የሚመር፣ የሚጣፍጥ፣ ብለን እንደምናውቀው፣ የሚገድል፣ ሕይወት የሚሰጥ ብለን እንደምናሳውቃቸው እንደዚሁ በእድሜ መጠናቸው አብረው ተዋሕዷቸው እንዲያድግ ነው ቤተክርስቲያንና የቤተክርስቲያን አባቶች ማስተማር ያለባቸው፡፡
የንስሐ አባትነት ማለት ሕፃናትንም የንስሐ አባት ሆነው መሳደግ ማለት ነው ከዚህ በላይ ልንለውም አንችልም ሕፃናት ወደ እኔ ይምጡ ማለት እኮ መርሑ ይሔ ነው፣ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ይመጡ ዘንድ ማለትም ይሔው ነው፡፡
ብዙ ጊዜ አባቶችም፣ አስተማሪዎችም፣ በየመድረኩ ወንጌል የሚሰብኩም ሕፃናት አይምሮ ጠባያቸው በኃጢያት ስላላደፈ፣ ሌላውን ነገር ለይተው ስለማያውቁ ብዙ ጊዜ ጉባኤ የረበሹ ይመስለናል፡፡
እንደዚያ የማድረጋቸው ነገር ሁሉ እንኳን ለእኛ ይመስለናል ለእግዚአብሔር የሚያስደስተው ነገር ስለሆነ ሕፃናትን በአፀደ ቤተክርስቲያን ቦታ ሰጥተን ማሳደግ ነገ ከኃጢያት ለመለየታቸው፣ ኃጢያትን ከፅድቅ ለይተው ለማወቃቸው መሠረት ነው፡፡
አንድ ሰው አካለ መጠን ደርሶ ከእናት አባቱ ጀርባ ወርዶ ራሱን የቻለ ሕይወት፣ ኑሮ፣ ትዳር፣ ሌላ ነገር የሚመራበት ያን ጊዜ የራሱ አባት ኖረውት፣ እንደ አዋቂ ምእመን ሆኖ፣ ታዞ ተቀጥቶ፣ ተሠርቶ የሚኖርበት ያ የታወቀ ነው፡፡
እኛም አባቶችን ሳንጠይቅ በባሕላችንም እናውቀዋለን፣ የዓለሙ ጠባይም ነግሮናል ትምሕርት የሚማሩ ልጆች መቼ እንደሚጨርሱ፣ ወደ ኮሌጅ ገብተው ስንት ዓመት እንደሚቆዩ፣ ከዚያ በኋላ ከቤተሰብ ጫንቃ እንደሚወርዱ፣ በገጠርም ያሉ ልጆች ሚስት አጋብተናቸው የራሳቸው እርሻ ኖሯቸው፣ ጎጆ ኖሯቸው እንዴት እንደሚኖሩ እናውቃለን፣ ከዚያ ጀምሮ ራሱን የቻለ አባወራ ሆኗል፣ ስራ የሚሠራ የቤተሰብ ኃላፊ ነው ማለት ነው፡፡
ጠቦቶቼን ጠብቁ፣ በጎቼን ጠብቁ፣ ሕፃናቱን ጠብቁ፣ ወጣቱን ጠብቁ፣ ሽማግሌዎችን ጠብቁ ነው የተባለው በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 21 ቁጥር 15 ቅዱስ ጴጥሮስ ወይም ሐዋርያት የተሰጣቸው መጀመሪያው ስርዓት ይሔ የጥበቃ ስራ ነው፡፡
በጎቹን በየስማቸው፣ በየቁጥራቸው አውቃለሁ ነው ያለው ጌታ አንዱም እነዳይጎድል፣ ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ነገር ድካም ሲበዛብን እንዲህ ዓይነት ጥያቄ በካሕናትም ይሁን በምእመናን ይነሳል፡፡
አንድ ሰው ንስሐ መግባት ያለበት እንደ ኃጢያት የሚቆጠርበት ከስንት እድሜ ጀምሮ ነው? የንስሐ አባት በቋሚነት የሚይዘው በስንት ዓመቱ ነው? ይሔ የድካም ነገር ነው፣ በቤተሰብ የንስሐ አባት ካለ፣ ጠንካራ ከሆነ እሱ ራሱ ያ የቤተሰቡ ንስሐ አባት አባት ሊሆን ይችላል፡፡
እኒህ ንስሐ አባትም ጌታ እንዳለን ሁሉ ሕፃናቱንም ወደ ቅዱስ ቁርባን አምጡ፣ ቤተክርስቲያን አምጥታችሁ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲሰሙ ታደርጋላችሁ? እንዴት ለብሰው፣ በአፀደ ቤተክርስቲያን በምን ቦታ እንደሚቆሙ፣ እንዴት እንደሚለብሱ ያያሉ፣እንዴት እንደሚጸለይ ያያሉ፣ ስርዓቱን እያዩ ይከተሉዋችኋል፡፡
እንደዚሁም ደግሞ ለወጣቶቹስ እናንተስ የወጣትነት እድሜ እንዳያጠፋችሁ ይሔ የእሳት ዘመን ነው ዘመናችሁና ይሔ የወጣትነት ባሕሪ የእሳትነት ባሕሪ ነው፣ እሳት ደግሞ ሁሉንም የሚበላ ነው፣ ስለዚህ እነዚህ ወጣቶችስ ወደ ቤተእግዚአብሔር እየመጡ ነው? እየቆረቡ ነው? ምን እያሉ ነው? እንዲህ ብሎ ከጠበቀ ምንም አይደርስባቸውም፡፡
በሰንበት ትምሕርት ቤት ከታቀፉ፣ የተለየ ምክር ያገኙ ሰዎች ቶሎ ብለው የራሳቸውን አባት ቢይዙ የእናት አባቶቻቸውን ፈቃድ እንደሻሩ፣ ቀኖና ቤተክርስቲያን እንደሻሩ የሚያስቆጥር አይደለም፣ እንደ ጥበቃው ዓይነት ነው፣ በዚህ ላይ ምንም የተሰራ ድንበር የለም፣ ልጆች ለምን ሌላ አባት ኖራቸው፣ አስተማራቸው የሚባል አይደለም ፡፡
አባላቶቻችን በየደብራችሁ፣ በየአካባቢያችሁ የንስሐ አባቶቻችሁ አሉ አይደለም? የንስሐ አባት ሊሰራው የሚችለውን ሥራ እኛ ተጨማሪ አቅም ፈጠርን እንጂ ሌላ የተፈጠረም አዲስ ነገር የለም፡፡
የበለጠ ብዙ ችግሮቻችሁ በልማድ በመጣ ነገር ዛሬ የንስሐ አባትና የንስሐ ልጅ በየቀኑ፣ በየጊዜው ተገናኝተው፣ ተመካክረው አያውቁም ለዚህም ነው ዛሬ ኃጢያት በእኛ ሕይወት ላይ እየነገሠ ያለው፡፡
ግልፀኝነት ሁሉ ቀርቷል፣ መተፋፈር አለ፣ መፍራት አለ፣ አባቴ ዛሬ እንዲህ ሆኛለሁ፣ ሴቷም ወንዱም አይሉም ልነግራቸው ነበር ፈራሁ እየተባለ ስንት ነገር እየተደበቀ ነው ያለው፣ ብዙ የደበቅነው ነገር አለ ስንት ችግር አለ፡፡
ብንቀራረብ ግን ለአባት ምንም እንደማይደበቅ፣ አባትም ደግሞ የልጆቻቸው ሚስጥር እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው ይሔ ልምድ፣ ይሔ ባሕል ቢኖር ስነ ስርዓት በሕይወታችን ያነግስ ነበር፡፡
ዛሬ ግን አንዳንድ ጊዜ እኛም እንዳለመታደል ሆኖ እስከ አለታመን ድረስ ሚስጥሬን ያወጡብኛል እየተባልን እስከ መጠርጠር መድረስ ይሔ ለእኛ ለአባቶች ውርደት ነው እንጂ ክብር አይደለም፡፡
በንስሐ አባትና በንስሐ ልጅ መካከል መራራቅ፣ ልጆች እንዴት ተብሎ በንስሐ አባት እንደሚኖሩ እንኳን ይሔንን ሁሉ ማወቅ ይሔ በአባቶችና በልጆቻቸው መካከል ያለው ክፍተት ነው መራራቅ ያመጣው ጣጣ ነው፡፡
ጠያቂያችን ለተጨማሪ ምክር ካስፈለግዎት በውስጥ መስመራችን ይደውሉና ያነጋግሩን ፡፡
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
ከንስሐ በፊት (ጥያቄና መልስ)
👉ጥያቄ፦ #ንስሐ ከመግባታችን በፊት ምን ማድረግ አለብን?
መልስ፦
ንስሐ ለመግባት ከሚፈልግ አንድ ክርስቲያን በመጀመሪያ የሚጠበቀው ፡-
1. በቅድሚያ ኅጢአት መሥራቱን አምኖ ለራሱ ሕሊና መናዘዝ (ከልብ መፀፀት)።
2. ስለሠራው ኅጢአት ወይም በደል እየተፀፀተ ጧት ማታ በደሉን በፀሎትና በልመና ለፈጣሪው መናዘዝና ኅጢአትን በእግዚአብሔር ፊት ማመን (መዝ50 ፣ ዳን9፥5፣ ነህ1፥6-7)
3. ኅጢአትን (በደልን) ለካህን መናዘዝና ንስሐ መግባት። ካህኑ የእግዚአብሔር አገልጋይና እንደራሴ ስለሆነ የሠራነውን ኅጢአት ለካህኑ በመናዘዝ ንስሐ መግባት፤ ኅጢአታችን እንዲሠረይልን በእግዚአብሔር ፊት ንስሐ መግባትና መናዘዝ ማለት ነው። (ኢያሱ7፥19 ማቴ3፥6 ዘሌ5፥5-6 የሐዋ19፥18)
4. የበደልናቸውንና የበደሉንን ሁሉ ይቅር በማለት የጥል ግድግዳ አፍርሰን በፍቅር አሸንፈን ስለዘለዓለማዊ ሕይወት ብለን በፍጹም ሕሊና በሰላም መኖር ነው።
4. ተመልሶ በኅጢአት ላለመውደቅ አዘውትሮ የንስሐ አባትን ወይም የሚቀርቡትን የሃይማኖት መምህር ማማከር፣ ምክር ማግኘት በታቻለ መጠን መጸለይ፣ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድና ቃለ እግዚአብሔር መስማት፣ በቤትም ውስጥ ቢሆን መንፈሳዊ መዝሙርና ትምሕርት ማዳመጥ አስፈላጊ እንደሆነ የምናስገነዝበው ለጠየቁን ምዕመን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ክርስቲያን እንዲጠቅም ነው።
የንስሓ አባትን በሚመለከት ፦
ለመንፈሳዊ ልጆቹ (ለመንጋው ጥበቃ) የማያንቀላፋና ዘወትር ቁጥጥር እና ክትትል የሚያደርግ አባት መያዝ እንደሚገባ እንመክራለን። ስለዚህ ይመክረኛል ያስተምረኛል ያሉትን የንስሓ አባት የሚሆን ካህን በአካባቢዎ ካሉ ይያዙ፤ በአከባቢዎ ማግኘት የማይችሉ ከሆነ በራስዎትም ሆነ በሚያምኑት ሰው በኩል ያገኙዋቸውን እውነተኛ ካህን በርቀትም ቢሆን ይያዙ፤ ወይም ደግሞ እኛ በህይወታቸው ምሳሌ ይሆናሉ ብለን ከመረጥንልዎ በድረገፃችን በሚያገኙት ስልክ ቁጥር ደውለው ንስሓ አባት በማድረግ መያዝ ይችላሉ።
በተጨማሪም ለጠያቂያችንም ሆነ ለሌላው ሁሉ ምክር የምንሰጠው ምናልባት የሰራነውን ኀጢአት ሁሉ ለመደበኛ የንስሓ አባታችን ለመናዘዝ የምናፍርበት ወይም በካህኑ ላይ እምነት ቢያጣ ወይም ምስጢር ይባክንብኛል ብሎ ከተጠራጠረ፤ ያ ነገር ደግሞ በህይወቱ ጉዳት ያደርስብኛል ብሎ ካሰበ ከተቻለ አባቱን በደንብ አነጋግሮ መተማመን ላይ ቢደርስ፤ ይህን ማድረግ ካልቻለ ደግሞ ስርአታዊ መንገድ ተጠቅመን በመንፈሳዊ ጥበብና በትህትና ሁነን ተሰናብተን ፤ ሳንጠራጠር ከልብ የምናምናቸውን ሌላ አባት መርጠን መያዝ ይገባናል። ይህን የምንልበት ምክንያት ብዙዎቹ ምእመናን ለንስሓ አባቶቻቸው ግልፅ ሆነው የሰሩትን በደል ለመንገር የማይችሉበት ዋናው ምክንያት ምስጢር ይባክንብናል ብለው ከነኀጢአታቸው የሚኖሩ አሉና ነው፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ለአባቶቻቸው ግልፅ ለመሆን በአካባቢያቸው በማህበራዊ ህይወት ከመንፈሳዊ አባቶቻቸው ጋር አብረው ስለሚኖሩ የመተፋፈርም ነገር ስለሚያጋጥማቸው በዚህም ምክንያት የሚሳቀቁ ምእመናን እንዳሉ መረጃው ስላለን፤ ከዚህ ሁሉ ስጋት ነፃ ለመሆን የሚያምኑበትን እና የማይጠራጠሩበትን አባት መያዝ እንደሚገባቸው በአፅንዎት እንመክራለን። ለዘላለማዊ የነፍስ ድህነት ጉዳይ የምንሰራውና የምናደርገው ተጋድሎ በስጋዊ አመለካከት ወይም ምድራዊ በሆነ አሰራር የምንኖረው ሂደት ስላልሆነ ልዩ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።
2. ንስሓ ከገቡ በኋላ ማድረግ ያለብዎት፦
አንድ ክርስቲያን በኅጢአት የጎደፈውን ሰውነቱን ከታጠበ በኋላ መላ ህይወቱ ንፁህ ስለሆነ ለማንኛውም መንፈሳዊ አገልግሎት መንገዱ ሁሉ ቀና ስለሆነ ማድረግ ያለበት ምን እንደሆነ የምናስረዳዎት፦
1ኛ/ ከምንም በላይ ዳግም ወደ ኀጢአት ተመልሰው የተቀደሰውን ህይወትዎትን እንዳያረክሱት መጠንቀቅ፣
2ኛ/ እግዚአብሔር ቢፈቅድልዎት በቅዱስ ቁርባን መወሰን፣ አቅምዎት በሚፈቅደው መጠን ሳያቋርጡ እና ሳይሰለቹ መፆም፣ መፀለይ፣ እና መስገድ፣
3ኛ/ በአቅምዎት ከሚያገኙት ነገር ለድሆችና ለእግዚአብሔር የሚገባውን አስራተ በኩራት ማዋጣት፣
4ኛ/ ዘወትር ከአባቶች ምክር እና መታዘዝ አለመራቅ፣ በፕሮግራም ወደ ቤተክርስቲያን እየቀረቡ ቃለ እግዚአብሔር መማር፣
5ኛ ሁሌ እንደቅርብ አስተማሪና መካሪ ሁነው የሚያገለግሎትን መንፈሳዊያን መፃህፍትን ማንበብ፣ ከዚህም በላይ በኑሮዎት ውስጥ፣ በስራ ቦታ፣ በማህበራዊ ጉዳይ ከሰው ልጅ ሁሉ ጋር በሰላም እና በፍቅር በትዕግስት እና በጥበብ ለመኖር ድርሻዎትን መወጣት።
እነዚህን ሁሉ እና ሌሎችንም መንፈሳዊ ነገሮችን አጠቃሎ ለመስራት የሚቻለው ሰው ህይወቱ በንስሓ ሲታደስ ስለሆነ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር የእርስዎን ህይወት በንፅህና በቅድስና እንደሚጠብቃት በማመን ከዚህ በላይ የተሰጠዎትን መንፈሳዊ ምክር በስራ ላይ ለማዋል እንዲችሉ እግዚአብሔር ይርዳዎት።
በተጨማሪም፤ ስለንስሓ ትምህርት በድረገፃችን ላይ የተላለፉና እየተላለፉ ያሉትን ተከታታይ ትምህርቶች ይህን ሊንክ በመጫን ያንብቡ።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ፦ #ንስሐ ሳይገባ #ሱባዔ መግባት ይቻላል ውይ?
መልስ፦ ጠያቂያችን፤ ሱባኤ ለመግባት ከሁሉ በፊት ስለ ስባኤ ምስጢራዊ ትርጒም እና በሱባኤ ስለሚገኝበት መንፈሳዊ ጥቅም መረዳት አለብን። ሱባኤ ማለት በግዕዝ ቋንቋ 7 ቁጥርን የሚያመለክት ሲሆን ይህ 7 ቁጥር ደግሞ የአንድ ሱባኤ ጊዜ ማለት ነው። 7 ቁጥር በዕብራዊያን ዘንድ ፍጹም ቁጥር ነው። የቃሉ ምስጢራዊ ትንታኔ ይህ ከሆነ፤ ሱባኤ የተጀመረው በአባታችን በአዳም ነው። አባታችን አዳም 7 አመት ከ1ወር ከ 17 ቀን በገነት ውስጥ በደስታ ከኖረ በኋላ አታድርግ የተባለውን ትዕዛዝ በማድረጉና አትብላ የተባለውን ዕፀበለስ በመብላቱ ከገነት ርስቱ መባረሩ ምክንያት ስለ ስራው በደል ተፀፅቶ ወደ ፈጣሪው በማልቀሱና በመጮሁ ምክንያት ከፈጣሪው ዘንድ ይቅርታን ያገኝ ዘንድ 5 ሱባኤ ማለትም 35 ቀናትን በሱባኤ ተወስኖ ወደፈጣሪው ያቀረበው ልመና ተቀባይነት አግኝቶ ከፈጣሪው ዘንድ ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ቃል ኪዳን ተገብቶለታል። ስለዚህ ከአባታችን ከአዳም ጀምሮ በኀጢዓትና በልዩ ልዩ ምክንያት የሱባኤ ጊዜ እየወሰኑ ከፈጣሪያቸው ዘንድ ምህረትን እና ይቅርታን አግኝተውበታል።
ሱባኤ የሚገባው በ2 ምክንያት ነው:- 1ኛው ማንኛውም ክርስቲያን የኀጢአት ፈተና ደርሶበት የበደለውን በደል አስቦ በመፀፀት ከሰውና ከማህበራዊ ኑሮ ራሱን ደብቆና ሰውሮ በለቅሶ በፀሎት ፈጣሪውን ይቅርታ የሚጠይቅበት ሂደት ነው። 2ኛው ደግሞ ማንኛውም ክርስቲያን ፀጋውን ለማሳደግና ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርበው ልዩ ልመና ሲኖረው ጊዜ ወስኖ ቦታ ለይቶ ሱባኤ ይገባል ማለት ነው። በፆም በፀሎት ተወስኖም ከፈጣሪው ጋር ይነጋገራል። በጠየቀውና በለመነው ፍፁም ክርስቲያናዊ ሕይወት አንፃር ከእግዚአብሔር ዘንድ ለግል ህይወቱና ለቤተሰቡ፣ ለወገንና ለሀገርም የሚጠቅም በጐ ምላሽ ሊያገኝ ይችላል።
ሌላው የሱባኤ አስፈላጊነት ፤ እግዚአብሔር አምላክ ስላደረገልን ነገር ሁሉ እና ስለቸርነቱ ብዛት ምስጋና ለማቅረብ፣ ወደፊትም ጠብቆቱና መግቦቱ እንዳይለየን ለመማፀን ፣ ከእናታችን ከድንግል ማርያምና ከቅዱሳን ሁሉ በረከት ለማግኘት፣ በግል ህይወትም ሆነ በሀገር ላይ ከተቃጣው መቅሰፍት ለመዳን፣ በሃይማኖትና በሥነምግባር ፀንተን በፆም በፀሎት እንድንተጋ የሚዋጋንን ጥንተ ጠላታችንን ዲያብሎስን ድል ለመንሳት፣ የተሰወረና የረቀቀ ምስጢር እንዲገለጽልን በመሳሰሉት መንፈሳዊ ጉዳዮች ሰባኤ መግባት የምንችል መሆኑን በቀኖና ቤተክርስቲያን ታዟል።
ሱባኤ ለመግባት የሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ፤ በግላችን በሰራነው በደልም ሆነ ስለሀገርና ስለወገን ከእግዚአብሔር ዘንድ ምህረት ለመጠየቅ ሱባኤ ለመግባት ባሰብን ጊዜ፦
1/ ህሊናዊና አካላዊ ቁርጠኝነትና ስነልቦናዊ ውሳኔን ይጠይቃል።
2/ ሱባኤ የምንገባበት ምክንያት እንዴትና ለምን እንደሆነ ከቤተክርስቲያን አባቶች ጋር መነጋገርና ምክር መቀበል፣ ንስኀ ያልገባበት ጥፋት ካለም ተናዞ ቀኖና መቀበል ያስፈልጋል።
3/ በሱባኤ የምንቆይበት ጊዜ ምን ያህል ሰባኤ እንደሆነ፣ ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ፣ እና የሱባኤውን ቦታ (በአትን) መወስን ያስፈልጋል።
4/ በሱባኤ ጊዜ የምናደርጋቸውን መንፈሳዊ ስርዓት ማለትም እንዴት እንደምንፆም ፣ እንዴት እንደምንፀልይ፣ እንዴት እንደምንሰግድና በመሳሰሉት በስርዓተ ቀኖና መሰረት መንፈሳዊ ግንዛቤ እንዲኖረን ያስፈልጋል።
5/ ሱባኤ በገባን ጊዜ በግል ህይወትና በቤተሰብ ጉዳይ ወይም በማህበራዊ ጉዳይ የሚያሰናክል ፈተና እንዳይመጣብን አስቀድመን ሁኔታዎችን ማስተካከል ያስፈልጋል።
6/ ሱባኤ በገባን ጊዜም እንዴት መተኛት እንዳለብን ምን መልበስ እንዳለብን ባጠቃላይ በሱባኤ የምናሳልፍበት ጊዜያችን የሚያስፈልገንን እና የማያስፈልገንን ነገር ለይተን ለማወቅ ከቤተክርስቲያን አባቶች መመሪያ መቀበል አለብን።
ይህን ሁሉና የመሳሰሉትን ሱባኤ ከመግባ በፊት ልናሰባቸውና በሱባኤ ወቅት ልናደርጋቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች ናቸው።
ሱባኤ ከጨረስን በኋላ ልናደርጋቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች ደግሞ፦
1/ ሱባኤ የገባንበት ምክንያት ኀጢአት ከሆነ ደግመን ላለማድረግ በተቻለ መጠን በመንፈሳዊ ተጋድሎ ራሳችንን ለበለጠ የሃይማኖት ፅናት ማትጋት ነው።
2/ ሱባኤ በገባንበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ያገኘነው በጎ ምላሽ ካለም የበለጠ የእግዚአብሔር ፀጋ እንዲበዛልን ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት አጠናክረን መቀጠል ነው።
3/ ማንኛውም ክርስቲያን ቦታና ጊዜ ላይቶ በሱባኤ ፈጣሪውን የሚለምን ከሆነ በፀጋ እያደገ ከመጣ ብዙ ጊዜ ለውድቀት ከሚያበቁት የኀጢአት ምክንያቶች መራቅ።
4/ በፆም በፀሎት በቅዱስ ቁርባን በአጠቃላይ በክርስቲያናዊ ስነምግባር መንፈሳዊ ጉዞን መቀጠል።
5/ ሥጋዊ ፍላጎትን እና ምኞትን ገዝቶ ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ አስገዝቶ የትሩፋት ሥራ መስራት።
6/ በአጠቃላይ አለማዊ ሰዎች ከሚሰሯቸው ስራዎች ሁሉ እርቆ በመንፈሳዊ አላማ ፀንቶ መኖርን ይጠይቃል።
እነዚህ ከላይ የዘረዘርናቸው ምክር የሚሰጠው በአለም እየኖሩ በሱባኤ እግዚአብሔርን ለሚለምኑ እውነተኛ ክርስቲያኖች እንጂ ለገዳማውያን ወይም በምናኔ ለሚኖሩ መነኮሳት አይደለም፤ የነሱ ደግሞ ከዚህ ለየት ያለ ቀኖናዊ ስርዓት ስላላቸው ነው።
ስለዚህ ጠያቂያችን ሃሳቡን በዚህ ተረድተው ፤ ለሱባኤ ወደ ገዳም ለመሄድ ያሰቡትን መንፈሳዊ አላማ በሰላም ፈፀመው የእግዚአብሔርንም በረከት እና መልስ አግኝተው እንዲመለሱ እየተመኘን፤ በገዳም በፍጹም እምነት ሆነው እንዲጸልዩና ለረዥም ጊዜ በቦታው የቆዩ የእግዚአብሔር ፀጋ አብዝቶ ያደረባቸው አባቶች ስለሚኖሩ ወደነርሱ ቀርበው ትምህርትና ምክር ማግኘት እንዳለብዎምእንመክራለን።
በአጠቃላይ ጠያቂያችንም ሆኑ የዚህ የዮሐንስ ንስኀ ድረገፅ መንፈሳዊ ፕሮግራም ተከታታይ አባሎቻችን ሁላችሁም፤ ስለ ሱባኤ መጠነኛ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ በዚህች አጭር ፅሁፍ መልዕክት የላክንላችሁ ሲሆን፤ አስፈላጊ ሆኖ ስናገኘው ወደፊት ስለ ሱባኤ አስፈላጊነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሮ ትምህርት በስፋት እንዲደርሳችሁ ልናደርግ እንችላለን።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ
👉🏾ስለ #ቅዱስ #ቁርባን፣ የ #ንስሐ ህይወትና ስለ #ዝሙት #ፈተና
👉ጥያቄ፡- ንስሐ ገብቼ መልሼ እሳሳታለሁ፡፡ የዝሙት መንፈስ በጣም ይፈታተነኛል፡፡ እኔ ግን ንስሐ ገብቼ፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል እፈልጋለሁ፡፡ ልብስም ገዝቼ ይኼው መቼ ይሆን ከአንተ ቤት የምኖረው እያልኩ እሳላለሁ፡፡ ንስሐ ገብቼ ብቆርብስ ? የድፍረት ኃጢያት ይሆናል ወይ? አንድ አባት ቢያንስ 30 ዓመት ይሙላሽ አሉኝ፡፡ እኔ ግን ከእግዚአብሔር መራቅ አልፈልግም፡፡ ግን መኖር እፈልጋለሁ እስኪ አስረዱኝ በማርያም?
መልስ፡- የጠየቁን ስለ ንስሐ ሕይወት ነው፡፡ በመቀጠልም በንስሐ ሕይወት ስለሚፈፀም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ በሚመለከት ነው፡፡ ጠያቂያችን ከንስሐ የተሸለ ምን የሚያስፈልግ ነገር አለ? ሁልጊዜም ደጋግመን እንደምንለው ኃጢያት ላለመሥራት መጋደሉ፣ መታገሉ መቸስ የማይገኝ ዕድል ነው፡፡ ለሁላችን የማይቻል ነገር ስለሆነ፤ ሁላችንም ፈተና የበዛብን ተክል ስለሆንን፣ የፈለገንን ያህል ብንምል፣ ብንገዘት፣ አጥብቀን ብንጠላው ብንታገለው ሁላችንም ተሰናክለን የምንወድቅበት የጋራ የሆነ ኃጢያት ስላለ በዚያ ተጠልፎ መውደቁ የማይቀር ነገርና መጥፎ ዕድል ሆኖብን እንጂ፤ በዋናነት ከኃጢያት ርቆ መኖር ቁጥር 1 የምንመርጠው የተቀደሰ ተግባር ነው፡፡ ይኼ ሳይቻል ቀርቶ ደግሞ በአንድም፣ በሌላ መንገድም ወይም ከባድ በሆነ ወይም ቀላል በሆነ ኃጢያት በወደቅን ጊዜ፤ ዓይነተኛው መፍትሔ ወደ ንስሐ መምጣት ነው፡፡
በቅዱሳት መጻህፍትም የንስሐ ትርጉም ወይም የንስሐ ታላቅነት ተነግሮናል፡ ንስሐ ማለት ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው፡፡ በሙሉ ልብ በፍፁም እምነት ሆነን ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው.፣ መጸጸት፣ የንስሐ ሕይወት የሚባለው ነገር ይኼ ነው፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ ጥርጊያውን አቅኑ›› እያለ በመጣ ጊዜ የአዋጁ አብሣሪ ሆኖ ሲመጣ ፤ የመጀመሪያው የስብከቱ አዋጅ ንስሐ ግቡ የማቴዎስ ወንጌል ቁጥር 1 እና 2 ላይ ንስሐ ግቡ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና፡፡ ሐዋርያትም ጌታ በተነሣ በ 50 ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸው 72 ቋንቋም ተገልጦላቸው፣ ገና በጠዋቱ በአይሁድ ዘንድ ቆመው እጅግ የብዙዎቹ ልቡና የተመሰጠበትን ትምሕርት ባስተማሩ ጊዜ ብዙዎቹ አምነው ወዲያውኑ፤ ምን እናደርግ ሲሏቸው? ንስሐ ግቡ፣ እና አምናችሁ ከመጣችሁ ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን ተጠመቁ፡፡ ይኼን ነው እንግዲህ ያስተማረ ማለት ነው፡፡
ስለዚህ የዮሐንስ ትምሕርት የመጀመሪያው ነገር የበር መክፈቻው ቁልፍ ንስሐ ግቡ ነው፡፡ ሁላችንም ከነኃጢያታችን እንዲሁ ተሸፋፍነን እንድንኖር እግዚአብሔር አይፈቅድም፡፡ እና ለንስሐ የእድሜ ገደብ የለውም፡፡ ቅዱስ ቁርባን የእድሜ ገደብ የለውም፡፡ ይኼን በሚመለከት በጣም ብዙ ጊዜ ተነጋግረናል፡፡ መቸስ በእያንዳንዱ ትምሕርት ሳንዘነጋ የምናስታውሰው ነገር ስለ ምስጢረ ቁርባን ነው፡፡ ማንኛውም አማኝ፣ ማንኛውም ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን መቀበል እንዳለበት፡፡ ደጋግመን እንደተነጋገርነው፤ ወንድ ልጅ በ40 ቀኑ፣ ሴት ልጅ በ 80 ቀኗ የእግዚአብሔር ልጅ ሆነው በስመ ክርስትና፣ በቅዱስ ቁርባን ታትመው ልጅነታቸውን ካረጋገጡ በኋላ ከቅዱስ ቁርባን አንድ ቀንም ቢሆን መለየት የለባቸውም ብለናል፡፡
ስለዚህ ጠያቂያችን፤ በተለያየ የሥጋ ድካም፣ በተለያየ የኃጢያት ምክንያት ከሥጋወደሙ መሸሽ ወይም ማቋረጥ አያስፈልግም፡፡ ከእነጭራሹ ደግሞ የምንሰማው ጉድ 30 ዓመት ይሙላችሁ፤ 40 ዓመት ይሙላችሁ፣ 25 ዓመት ይሙላችሁ አይባልም እኮ፡፡ ከምን ጋር በማያያዝ ነው የእድሜ ጣሪያ የምናስቀምጠው? ለደቂቃም፣ ለሴኪንድም ከእግዚአብሔርጋር መለየት የለበትም የሰው ልጅ እያልን ፣ ሁሉም መላ ሕይወታችን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ነው፡፡ ምናልባት ከእግዚአብሔር ክልል ውጪ፣ እርሱ ከሚገዛው፣ ከሚያስተዳድረው፣ ከፈጠረው ዓለም ውጪ ሆነ ሌላ ዓለም ኖሮ፣ ሌላ አስተዳዳሪ፣ ሌላ ገዢ ኖሮ ከእሱ ተለያይተን ከፈለግን ደግሞ ሌላ አብረን ለመኖር ውል የምንመሠርትበት ኑሮ አይደለም እኮ ይኼ፡፡ በየትኛውም ሰዓት ውስጥ፣ በኃጢያት ውስጥም እያለንም የእግዚአብሔርን ስም እንጠራለን፡፡ ከዚያ ከወደቅንበት የኃጢያት ጉድጓድ፣ የኃጢያት ማጥ ውስጥ ሊያወጣን የሚችለው፤ መፍትሔ እንዲሰጠን እግዚአብሔር ቁልፍ የሆነውም የችግራችን መፍትሔም ያለው ከእግዚአብሔር እጅ ነው፡፡ ስለዚህ ፈፅሞ እንዲህ ዓይነት ትምሕርት ልንሰማም አይገባንም፡፡ ቆይ ልጅ ናችሁ፣ እንዲህ፣ እንዲህ እያሉ የሚሉ ትምሕርት ያነሰው ሰው፣ ወይ ደግሞ ፈጽሞ መንፈሳዊ ምክርና ትምሕርት ተፈልጎ የታጣበት ሰው የሚናገረው የሚያስረዳው የሌለው መጽሐፍትን ጠቅሶ የማያስተምር፣ እንዲህ ዓይነት ካሕን በልብ ወለድ ስለሚናገር ምንቸገረው? እንዳንመነኩስም ገና ነሽ፣ እንዳንቆርብም ገና ነሽ፣ ባይሆን ካሕን ማስተማር ያለበት ሁል ጊዜ ለምዕመናን እግዚአብሔር ቢረዳቸው ከኃጢያት እንዲለዩ ብቻ ነው፡፡ ጊዜ ሳንሰጥ መናገር ያለብን ቅዱስ ቁርባን እንዲቀበሉ፣ እንደዚህ አድርጉ ኃጢያት ላይ ወድቄያለሁ አባቴ ብንባል፤ በል ቶሎ ንስሐ ግባና ወደ እግዚአብሔር ተመለስ፣ ቶሎ ቁረብ ነው ማለት ያለብን፡፡ ሁሌ የምናገረው ቋንቋ ይኼ ነው፡፡የእግዚአብሔር ቅድስና የእኛን የረከሰውን ሕይወት ከኃጢያት ያነፃል፤ የእኛ ኃጢያት ግን የእግዚአብሔርን ቅድስና አያረክስም፡፡
ስለዚህ ጠያቂያችን፤ ቅዱስ ቁርባኑም፣ ፀበሉም፣ መስቀሉም ፣ ቃለእግዚአብሔሩም፣ ቅዳሴውም ይኼ ሁሉ እኛን ከኃጢያት የሚያነፃ ነው እንጂ ጨርሶ የሚያረክስን ኃጢያታችንን የሚያባብስብን ነገር አይደለም ይኼ፡ አሁንም ጠያቂያችን እንዲህ ዓይነት ፍላጎት፣ ምኞት እያለዎት ገና ነዎት፣ የወጣትነት ዕድሜ ነው፣ ብዙ ነገር አካብደን ፣ ተስፋ ቆርጠን የምንርቅበት የሕይወት ደረጃ አይደለም ያለነው፡፡ እርስዎ ያሉት እንግዲህ 30 ዓመት ይሙላሽ የሚለው ገና የእዚህ ዕድሜ ባለቤት እንኳን እንዳልሆኑ ፣ የልጅነት የወጣትነት ዕድሜ ላይ የተፈተኑበት ነገር ምን እንደሆነ፣ በግል ሕይወትዎ ምክርም መክረን፣ እንደ ቤተክርስቲያን መምህር፤ እንደ ቤተክርስቲያን አባት የሚስተካከለው ነገር እንዲስተካክል ይደረጋል፡፡ እግዚአብሔርም ያግዘናል፣ ቸርነቱ ፣ ምሕረቱ ብዙ ስለሆነ፣ በተለመደው የውስጥ አድራሻችን ደውለው ያግኙንና ተጨማሪ ምክር እንሰጥዎታለን፡፡ በነገሩ ሁሉ የሚመክረን እግዚአብሔር የተመሰገነ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ቤት የሚለየን የሚያርቀን፡ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ምንድን ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፣ ለሮሜ ክርስቲያኖች በፃፈው መልእክቱ በሮሜ መልእክት ምዕራፍ 8 ያለው ማለት ነው፡፡ ከቁጥር 35 ጀምረን ስናነብ የምናገኘው ማለት ነው፡፡ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ ማነው? በጣም ከባድ የተባሉ ብዙ ጦርነት ነው? ረሐብ ነው? ሠይፍ ነው? ደዌ ነው? ምንድን ነው? ብሎ ዘርዝሯቸዋል፣ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ የለም ፡፡ ስለዚህ ብዙ የሥጋ ምክንያቶችን እየደረደርን ከቅዱስ ቁርባን ፍቅር የሚለየን ነገር አንዳችም የለም፡፡ይኼንን ነው ማየት ያለብን።
በአጠቃላይ ከእግዚአብሔር ቤት ልንርቅ አይገባንም፡፡ ልበ አምላክ ዳዊት ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ በጣም ደስ አለኝ ነው ያለው፡፡ ይኼ የእስራኤል ገዢ ታዋቂው፣ ዝነኛው ንጉሥ ዳዊት፤ እንደ ሥጋዊ ሐሳብ ከሆነ በታላቁ ቤተ መንግሥት ነገሦ የሚኖረው ዳዊት፣ በሥጋው ብዙ የሚያስደስቱ ነገሮች እፁብ፣ ድንቅ የሚባሉ ነገሮች እንዳሉ የሚታወቅ ነው፡፡ ነገር ግን ዳዊት ምንድን ነው ያለው? ከምንም በላይ ሰው ሁሉ በሕይወቱ ደስ ከሚሰኝበት፣ ከሚደሰትበት ነገር፤ ወደ እግዚአብሔር ቤት መሄድ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ቤት አለመራቅ፣ አለመለየት፡፤ ይኸው ነው ሌላ ፀጋ የለም፡፡ እዚያ ቅዱስ መስቀል አለ፣ እዚያ ቅዱስ ጸበል አለ፣ እዚያ ቅዱስ ቁርባን አለ፣ እዚያ የእግዚአብሔር ቃል አለ፣እዚያ ቅዳሴ አለ፣ እዚያ ዝማሬ አለ፣ እዚያ በመንፈስ የመረጋጋት፣ የመጽናናት፣ ፍቅር አለ፣ ሠላም አለ ፣ትዕግሥት አለ ከእግዚአብሔር ቤት ሊለየን የሚችል አንዳችም ነገር የለ፡፡
ስለዚህ እንዳሉትም ለቅዱስ ቁርባን የሚሆንዎት ዝግጅት አድርገው፣ ልብሱ ሳይቀር፣ ተዘጋጅቶ ብለዋል፣ ይኼንን ምኞትዎትን፣ የልብዎትን ሐሳብ እግዚአብሐየር ይሞላዋል በእርግጠኝነት እኛ ደግሞ ሳይውሉ፣ ሳይድሩ፣ ቀጠሮ ሳይበዛ፣ ቶሎ ወደዚያ እንዲቀርቡ ተጨማሪ ምክር ስለምንሰጥዎት ቅድም እንዳልኩት በውስጥ መስመራችን ያግኙን፡፡
የመከረን፣ የገሰፀን የሠራዊት አምላክ ሥሙ ይመስገን፣ ፀጋ በረከቱን በሁላችን ላይ ያሳድርብን፡፡ ወስብሓት ለእግዚአብሔር አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፦ ኀጢአት የሰራ ሰው ድንገት #ንስሐ ሳይገባ ቢሞት #ገነት ሊገባ ይችላል ወይስ አይችልም?
መልስ፦ አባላት ሁላችሁም በዚህ ጥያቄ ላይ የራሳችሁን ተሳትፎ እንድታደርጉ እድሉ ቢገጥማችሁ ምን ማለት እንደምትችሉ መገመት አያቅታችሁም። መቼም፤ የኀአተኛን ሞት አልወድም ይላል እግዚአብሔር በንስሐ ተመልሶ ዘለአለማዊ ህይወት ያገኝ ዘንድ እንጂ። ጠያቂያችን እርስዎም ቢሆን በአካል አግኝተነዎት መወያየት ብንችል ኖሮ መቼም ቅዱሳት መፃህፍት እንዳስተማሩን አባቶቻችን እንደነገሩን ከሆነ የሚኮነነው ኀጢአተኛው ሰው እንጂ ፃድቅ አይደለም። ይሄ ሁሉ በዚህ በስጋዊ አለም ውስጥ የአለሙ ነገር እያባዘናቸው ፈቃደ ስጋቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው እንዲያስገዙ ይሄንኑ ጎዶሎው የማይሞላው አለም ሲቃትቱና መከራ ስቃያቸውን ሲበሉ አንድ ቀንም እግዚአብሔር አብዝቶ ከሰጣቸው ጊዜ እና ኑሮ ለንስሐ እራሳቸውን ሳያዘጋጁ ከነኀጢአታቸው ተጠቅልለው ወደ ሰማያዊ የነፍስ ሞት የሚሄዱ በጣም ብዙዎች ናቸው ። እንግዲህ ሰው ኀጢአት የሚገለፅበት ብዙ የጥፋት መንገድ አለና፤ እየተነገረው! እየተማረ! እየተመከረ! እየተገሰፀ! እውነቱን እንዲያውቅ እየተደረገ! ወደ ንስሐ ህይወትም እንዲመለስ ቤተክርስቲያን እጅዋን ዘርግታ እየለመነችው! ኀጢአት ይሻለኛል ይሄ የጥፋቱ አለም ይሻለኛል ብሎ የእኔ ህይወቴ ይህ ነው፤ በዚህ በምድር ላይ ያልቃል ብሎ የወሰነው የልተኮነነ ሰው ማን ይኮነናል?
በእርግጥ ጥፋተኞችን በ 2 መንገድ ልንከፍላቸው እንችላለን። አንዳንዶቹ ጨርሰው የድንቁርና ጨለማ ውስጥ ገብተው ማንም ሳያስተምራቸው ሳይገስፃቸው ባላዋቂነት እንዲሁ እንደተጠቀለሉ ይመጡና እውነትና ሀሰትን፣ ጽድቅንና ኩነኔን፣ ጨለማና ብርሃንን፣ ህይወትና ሞትን ለይተው ሳይነገራቸው ሳያውቁት የሚኖሩ አሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ አጣጥመው ሁሉን ነገር አውቀው ተረድተው የምድሩ ነገር ይሻለናል ብለው የምድሩን ነገር ይዘው ሃይማኖታቸውን ምግባራቸውን አቃለው አርክሰው በኀጢአት ህይወት ውስጥ እድሜ ዘመናቸውን የሚኖሩ አሉ። ከነዛኞቹ ጥፋት የነዚህኞቹ እጥፍ ድርብ ነው።
እግዚአብሔር መቼስ እውነተኛ ከፋይ ፍርድ የማያዳላ ለእያንዳንዱ እንደየስራው ወጋውን የሚሰጥ እውነተኛ ዳኛ ስለሆነ በሰራነው ኀጢአት መጠን በሰራነውም ፅድቅ መጠን ተመጣጣኝ ዋጋ ይከፍላል። ኀጢአተኞችም የሚፈረድባቸው በሰሩት መጠን ነው። እነሱ ባልሰሩት በሌላው ኀጢአት አይፈረድባቸውም። ሰው ነው በፍርደ ገምድልነት የወደደውን ኀጢአተኛም ቢሆን ያፀድቃል፣ የጠላውን ደግሞ ፃድቅ ቢሆንም ይኮንናል ፍርዱም እጥፍ ድርብ አድርጎ የሚፈርድባቸው አለ የሚያቀልላቸውም አለ። እግዚአብሔር ግን አይሳሳትም። የሰው ፊትም አይቶ አያዳላም። አንተ ትቀርበኛለህ፥አንተ ትርቀኛለህ ፣ አንተ ዘመዴ ነህ ፥ አንተ ባእዴ ነህ ፣ አንተ ባለውለታዬ ነህ አንተ ውለታ አልከፈልክም አይልም። እሱ በሰጠን እኛ በምንጸድቅበት እኛ በምንድንበት በዚህ በእውነተኛ ሃይማኖታችን ምግባራችን ፀንተን እንድንኖር ነው። እሱን መውደዳችን እሱጋር መሆናችን ለእሱ ማድረጋችን እሚገለፅበት ከዚሁ እኛው እርስ በእርሳችን በመልካም ነገር አንዱን አንዱ እያከበረው እየወደደው እየተፈቃቀርን የምንሄድበት ጉዞ ሁሉ እኛው እራሳችን የዘራነውን ስለምናጭድ መልካም ብንዘራ መልካም የስንዴ ፍሬ ያለበትን እንሰበስባለን እናጭዳለን፤ ኀጢአት ብንሰራ ደግሞ ኀጢአት እናጭዳለን መለት ነው። ጽድቅም ብንሰራ ጽድቅን ነው ኩነኔም ብንሰራ ኩነኔን እናጭዳለን ማለት ነው።
ስለዚህ እየተነገረው፣ እየሰማ፣ እውነትና ሀሰቱን ጽድቅና ኩነኔ በረሃንና ጨለማው ለይቶ የኀጢአት መጨረሻውና ፍፃሜው ሞት እንደሆነ እያወቀ ከዚህኛው አለም የተለየ አለም እንዳለ እየተነገረው፤ ከዚህኛው ህይወት የተሻለ የሚበልጥ ዘለዓለማዊ ህይወት እንዳለ እይተነገረው፤ ከዚህኛው ከስጋዊ ኩነኔ ይልቅ በነፍስ ያለው ኩነኔ እጅግ የፀና መሆኑ እየተነገረው ይሄን ሁሉ ሳይሰማ ሳይለማ የያዝኩት ይሻለኛል ብሎ አሻፈረኝ ብሎ ክብረ ቤተከርስቲያንን ንቆ ደፍሮ የኖረ ሰው ያልተኮነነ ማን ሊኮነን ይችላል?! ሁላችንም ግን ስለ ወንድሞቻችን ስለ ወገኖቻችን መፀለይ ያለብን ማንም ሰው በነፍስ እንዳይጠፋ መፀለይ ነው። በአንዳችንም ላይ ለመፍረድ አቅሙ የለንም፤ ሁላችንም ኀጢአተኞች ነን። ምንስ ጽድቅና ኀጢአትን፣ እውነትና ሀሰትን ፣ ብርሃንና ጨለማን እንደው ከትምህርትም በፊት እኮ አዋቂ ፍጥረት አድርጎ ስለፈጠረን ብቻ በተሰጠን የተፈጥሮ ፀጋችን ማወቅ እንችላለን። ይሄን ሁሉ እንዲያውም በእኛ ላይ አሳድሮብን፣ ቀርፆብን ፣የሚረዳን አይምሮ ኖሮን ወደን ፈቅደን ለመኮነን ተስማምተን በግብረ ሰይጣን ትላንትና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጌታችን ድል ነስቶ ከእኛ የለየውን ሰይጣንን ዘመድ አድርገን አሁን እሱጋር መቀጠል ከፈለግን ኀጢአተኛ ሰው እንደሚፈረድበት ቅዱሳን መፅሐፍትም አስተምረውናል። በእርግጥ እኛ በእግዚአብሔር የጽድቅ ወንበር ላይ ተቀምጠን በፍርድ አደባባይ ተሰይመን አንዳችን በአንዱ ላይ የምንፈርድበት ምንም አይነት ሁኔታ የለም። እግዚአብሔር ያከበራቸው የመረጣቸው ቅዱሳኑ በዚህ በፍርድ አደባባይ በእያንዳንዱ ላይ ሊመሰክሩበት በእርግጥ ቅዱሳን ሐዋሪያት እናንተስ በኋለኛው ዘመን በፍርድ አዳባባይ ስመጣ በ12 ወንበር ላይ ትሰየማላችሁ ብሏቸዋል። እነዚህ የተለየ ክብር ያለቸው የተለየ ረቂቁንና የተሰወረውን ነገር አጥርተው ለማየት እግዚአብሔር ፀጋወን ያሳደረባቸው ቅዱሳን ናቸውና፤ ስለዚህ ወገኖች መቼ እንደምንጠራ አናውቅምና ከወዲሁ ሳይመሽብን ሳይረፍድብን ከጠፋንበት የጨለማ ጉዞ ውስጥ ወጥተን እጅግ እግዚአብሔርን ልናይ ወደሚያስችለን ብርሀን መጥተን በእውነተኛ መንገድ ተጉዘን ወደ ንስሐ ህይወት ተመልሰን የቤተክርስቲያንን ድምፅ ሰምተን ከኀጢአት ማሰሪያ ተፈተን እውነተኛውን መንግስት ለመውረስ እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳን።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ፡- አባ እንዴት ነዎት? በመጀመሪያ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይሉ ምእመናን ለሚጠይቁት ጥያቄ በቂና ወደ ንስሐ የሚመልስ፣ ልባችን ተሰብሮ ወደ ንስሐ እንድንመለስ ስለረዱን እግዚአብሔር አምላክ ረጅም እድሜ ይስጥዎት እኔ ደካማ ኃጢአተኛ ስሆን፣ ኃጢአቴም ሁሌ እያነዘዘኝ እያቆሰለኝ መፈጠሬን ሁሉ አስጠልቶኝ ተስፋ የቆረጥኩ ሰው ነኝ፣ ግን አጋጣሚ ድረ-ገጻችሁን አግኝቼ ኃጢአቴን ሳስበው የምትሰጡትን ትምሕርት እንኳን መከታተል አልቻልኩም፣ ልፈነዳ ነው የምደርሰው ፈጣሪን እንዴት አድርጌ ብለምነው ነው ይቅር የሚለኝ? እኔ በጣም ከባድ ነው ብዘርዝረው አያልቅም፣ አባ ፈቃደኛ ከሆኑ እርስዎን በአካል ነው ማግኘት ነው የምፈልገው፡-
✍መልስ፡- ጠያቂያችን እግዚአብሔር ወዶና ፈቅዶ እንኳንስ ወደዚህ መንፈሳዊ ፕሮግራማችን በሰላም መጡ ነው የምንለው፣ ወደ እዚህ የመምጣትዎ ነገር ወደ እግዚአብሔር የመቅረብዎት አጋጣሚ ነው ሁላችንም ያየነው፣ እግዚአብሔር ደግሞ ወደ እሱ የመጣውን ሰው ዝም አይለውም፡፡
በዚህ ጭንቀት ውስጥ፣ በዚህ ኃጢአት ውስጥ፣ በዚህ ፈተና ውስጥ፣ በዚህ መከራ ውስጥ እንደወደቀ አይተውም፣ ቸርና መሐሪ አምላክ ነው፣ ሁሌም ከአንደበታችን መለየት የሌለበት ኃይለ ቃል “ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምህረት የተነሣ ነው” ቤተክርስቲያናችን የንሰሐ ግምጃ ቤት ናት፣ ንስሐ ለሚገቡ የኃጢአት ስርየት ለማግኘት የተዘጋጀ ማንም የማይከለክለው፣ ማንም የማይወስድብን በጎ እድል አለን፡፡
በንስሐ ሕይወት ወደ እግዚአብሔር እንመለስ ዘንድ የእግዚአብሔር የምሕረት እጆቹ፣ የይቅርታ እጆቹ የተዘረጉ ናቸው ይቅር ይለን ዘንድ አኛም የመማፀኛችን ከተማ አድርጎ በዚህ ዓለም ላይ ስለ እኛ የተከላትና፣ ስለእኛ በደሙ የዋጃት ቅድስት ቤተክርስቲያንም በሮቿ የተከፈቱ ናቸው፣ የተዘጉ በሮች የሏትም ፡፡
እግዚአብሔር የተዘጋ በር የለውም ሁላችንም እስከ ጢያታችን፣ እስከበደላችን፣ እስከጉዳችን፣ እስከኮተታችን ፣ እስከሰቀቀናችን፣ እስከ ኃፍረታችን ምሕረትና ቸርነት ወደሚያበዛልን አምላካችን ቤት እንመጣ ዘንድ የእግዚአብሔር በር ክፍት ነው፣ የእግዚአብሔር የምሕረት እጅ፣ የይቅርታ እጅ የተዘረጉ ናቸው፡፡
ከዚህ አንፃር ነው አኛም ብንሆን እስከነ ኃጢያታችን፣ እስከነ በደላችን በፍፁም ልጅነት፣ በፍፁም እምነት፣ በድፍረት ግድላችሁም ኑ ተያይዘን ከምንጠፋ፣ ተያይዘን እንልማ፣ ተያይዘን ኃጢያተኛ ከምንሆን ይልቅ ተያይዘን ፃድቅ እንሁን፣ እንፅደቅ እያልን ጥሪ የምናደርገው ከሌላው የተሻለ ሕይወት ያለን፣ እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ መሆኑን ቀምሰን አጣጥመን ስለምናውቅ ብቻ ነው፡፡
እግዚአብሔር ልጁ በጠፋበት በአንድ ሐብታም ራሱን መስሎ የጠፋውን ልጄን አግኝቼዋለሁ ደስ ይበላችሁ፣ ደስ ብሎኛል ነው ያለው፣ የልጁን መገኘት ለደስታው ወደር አጠቶለት የተለየ ዝግጅት አድርጎ ከዚህ የሚበልጥ ሌላ የደስታ ጊዜ የለኝም የሚያስደስተኝም አንዳች ነገር የለም፣በልጄ መገኘት ደስታዬ ወደር የሌለው ስለሆነ ለዚህ ደስታዬ ይሆን ዘንድ እነሆ ወደ ግብዣዬ እንድትመጡ ነው ያለው፡፡
ፍሪዳው ታርዷል፣ ተወራርዷል፣ ጠጁ ተጥሏል፣ ዳሱም ተሠርቷል፣ ሁሉ ነገር በተገቢው መንገድ ፧ተዘጋጅቷል፣ ተሟልቷል ኑ ከእኔ ጋር ተደሰቱ ከእኔ ጋር ደስ ብሎኛል ነው ያለው፣ በንስሐ ተፈልጎ የተገኘ ሰው በእኛና በራሱ በባለቤቱ ዘንድ ብቻ ሳይሆን ደስታው በሰማይ መላእክትና በእግዚአብሔር ዘንድም ደስታ ይደረገናል ይለናል መጽሐፉ፡፡
ከዚህ የተነሳ ጠያቂያችን በእርግጥም ነው ኃጢያት ያላሳፈረው፣ ኃጢያት ያላስለቀሰው፣ ኃጢያት ያላሳዘነው ሰው ሌላ በምን ሊያዝን ይችላል? እውነትም እንዳሉት ነው እግዚአብሔር ቀድሶ በፈጠራት ምድር እንዲህ በረከሰ ሕይወት ስንኖር እስከነ ጉዳችን ወደን ፈቅደን የገባንበትን ኃጢያታችንን ተሸክመን እስከ መቼ ድረስ ነው እንዲህ ብለን ደንዝዘንስ የምንቀጥለው? እውነትም ነው ያጨናንቃል፣ ግን ከአሁን በኋላ በእርስዎ ሕይወት ላይ ጭንቀት አይሠራም፣ ሐፍረት አይሠራም፡፡
ጠያቂያችን እስካሁን የመጡበት የኃጢያት ጉዞ፣ የፈተና ጉዞም ሊቀጥሉ አያስፈልግም ወደ ንስሐ ሕይወት ይምጡና ትክክለኛውን መንገድ እግዚአብሔር ወደ እውነተኛዋ፣ ለልጆቹ ያወርሳት ዘንድ ወደ አዘጋጃት መንግሥቱ ሁላችንም እንዲያሰባስበን አሁኑኑ ፈጥኖ ወደ ንስሐ ሕይወት መምጣት ያስፈልጋል ” የመዳን ቀን ዛሬ ነው፣ ያውም አሁን ነው” ተብለናል የኃጢያት ቀጠሮ አያስፈልግም፡፡
ስለዚህ እርስዎም በትክክለኛ የእኛን ድረ-ገጽ አግኝተው፣ በእሱ ደግሞ ከእርስዎ ጉዳይ ጋር፣ ከእርስዎ ሐሳብ ጋር፣ ከእርስዎ ጭንቀት ጋር አብሮ ሊሔድ፣ ሊመክር፣ ሊገስፅ፣ ሊያስተምር የሚችል መልእክታችንን አግኝተው፣ ከልብ ተመልሰው ከሆነ ሌላ ተጨማሪ ጊዜ ሳያጠፉ በቶሎ ያግኙን፡፡
እንዳሉትም በአካል አግኝተውን፣ እኛም እግዚአብሔር በእውነትም የዘራነውን ለፍሬ አብቅቶታል፣ በእኛ በደካሞቹ ጥረትና ትጋት የተዘራው ዘራችን ሠለሳ፣ ስልሳ፣ መቶ አፍርቷል የምንለው በእንዲህ ዓይነት ሕይወት ውስጥ ያሉትን ሰዎች ለንስሐ ሕይወት አብቅተን ማየት፣ ለቅዱስ ቁርባን አብቅተን ማየት፣ ወደ መንፈሳዊ ሕይወታቸው፣ ወደ ቀደመ ክብራቸው ተመልሰው ማየት ከዚህ በላይ እኛንም እግዚአብሔርንም የሚያስደስት ነገር የለም፡፡
እግዚአብሔር ይመስገን ደግሞም እግዚአብሔር ያደርገዋል በዚችው ከሁሉ ባነሰቸው አገልግሎታችን እና ይህንን አገልግሎት ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ ወገኖቻችን ከገቢረ ኃጢያት፣ ወደ ገቢረ ፅድቅ፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከጨለማ ወደ ብርሐን፣ ካለማመን ወደ ማመን በጣም ብዙ መጥተዋል እግዚአብሔር ይመስገን፣
ከዚህ የተነሣ በአካልም ተገናኝተን እንዳሉትም ጊዜም አጥፍተን፣ ደክመንም ቢሆን እርስዎን ማትረፍ እንደምንችል እናምናለን፣ ባለን አድራሻ ደውለው ያግኙን፡፡
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፡- ሰላም አባታችን እንዴት ነዎት? የእርስዎን ግሩፕ በቅርቡ ነው የተቀላቀልኩት የምትሰጡት ትምህርት በጣም ደስ ይላል፣ አባታችን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን፣ አይምሮዬን ሰላም የሚያሳጣኝ ችግር አለብኝ፣ ምን እንደማደርግ አላውቅም፣ የዲያቢሎስ መጫወቻ እንዳልሆን እፈራለሁ፣ ንስሐ መግባት ፈልጌ ነበር፡-
👉🏾 ስለ #ፍርሃት መንፈስ እና #ንስሐ
✍️መልስ፡- ጠያቂያችን ግልጽ ያላደረጉት ነገር እንዳለ ይታያል፣ ከአእምሮዎት ጋር ያለ ችግር ምንድን ነው? የሚለውን ግልፅ ቢያደርጉት እዚህ ግሩፕ፣ በቅርብ እንደተቀላቀሉ ነው የነገሩን፣ ይበርቱ አይዞዎት፣ ተስፋ መቁረጥ የለብዎትም፣ እኛ ሁላችንም የምንችለውን ሁሉ ለማገዝ ከጎንዎት ነን፡፡
ሰላም የሚያሳጣ ችግር ምንድን ነው? የሚለውን ግልፅ ቢሆን ጥሩ ነው፣ ይሔ ችግር ያሉትን ነገር በውስጥ መስመር ያግኙንና ብንነጋገር ጥሩ ነው፣ አይምሮ ማጣት የሚለው ለምሳሌ የእንቅልፍ ማጣት፣ ራስ ጋር መጣላት ዓይነት ሌሎች ሰዎች ጋር መጨቃጨቅ፣ መረበሽ ሁሌ በሄዱበትም በሚመጡበትም ሰላምን ማጣት እንዲህ ዓይነት ብዙዎች ኃጢአተኛ ከሆነ ሰው ይገለጣሉ፣ ይከሰታሉ፡፡
ዲያቢሎስ እኛን የሚጫወትብን የእኛ ትንሽ ነፃ ፈቃድ ስላለችን ነው፣ የመዳንም ያለመዳንም፣ እሺ ማለትም፣ እምቢ የማለትም፣ የእኛን ፈቃድ ተጠቅሞ ነው፣ እኛ ኃጢአትን እምቢ ማለት ነው ያለብን፣ ዲያቢሎስ ሰውን አስገድዶ መጥፎ ደርጊት የሚያሠራ፣ ቢሆን ኖሮ ጻድቅ ደግ አባት የምንለው ሰው አይገኝም ነበር፡፡
እኛ ደካሞች ሆነን ነው፣ ለዲያቢሎስ መጫወቻ የሚያደርገን ክፉ ሥራ መሥራታችን፣ ኃጢአት፣ መሥራታችን፣ መዋሸታችን፣ መዘሞት፣ በአፅዋማት መብላት፣ በጠቅላላው ትእዛዘ እግዚአብሔርን አናደርግም ስንል ያ ትእዛዘ እግዚአብሔር ለእኛ ጠቃሚ ስለነበር ላንታዘዝ ስንል የዲያቢሎስ መጫወቻ እንሆናለን ማለት ነው፡፡
ትእዛዘ አግዚአብሔርን የምንፈፅም ከሆነ፣ ለእግዚአብሔር የምናታዘዝ፣ እሺ የምንል ከሆነ፣ እርኩስ መንፈስ እኛ ጋ ቦታ አይኖረውም፣ ሐዋርያው ያዕቆብ በመልእክቱ ምዕራፍ 4 ቁጥር 7 ላይ “እግዚአብሔርን እሺ በሉት ሰይጣንን ግን እምቢ በሉት፣ ከእናንተም ይርቃል፣ እግዚአብሔርን ቅረቡት እርሱም ይቀርባችኋል” ብሎ ተናግሯል፡፡
ስለዚህ እምቢ ማለት ይቻላል፣ ሰይጣንን እምቢ ያሉ በርካታዎች ስለሆኑ፣ እርስዎም ያንን ኃጢአትን ጠልተው ሰላም የሚያሳጣ መሆኑን አውቀው፣ ከእግዚአብሔር የሚለይ ረድኤት የሚያሳጣ፣ መሆኑን አውቀው፣ የኃጢአትን ችግር ተረድተው፣ ከዚያም የበለጠ ወደ ሲዖል እንደሚያስገባ አውቀው ተረድተው ንስሐ መግባት ነው፡፡
መፍራት ያለብን ክፉ ሥራ ስንሠራ ነው፣ መፍራት ያለብን ኃጢአትን ስንሠራ ነው እንጂ ለመዳን፣ ንስሐ ለመግባት ግን መፍራት የለብንም፣ ስለ ንስሐ በአጭሩ ለማስቀመጥ ያህል፤ ንስሐ ማለት ከእግዚአብሔር ጋር እንደገና መኖር ነው፣ ኃጢአት የሚባለው ከእግዚአብሔር ለይቶን ነበር፣ እግዚአብሔርን አሳጥቶን ነበር፣ ንስሐ ስንገባ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ልንኖር ነው ማለት ነው፡፡
“ንስሐ ዘማን እንደ ድንግል፣ ኃጠአተኛውንም እንደ ፃድቅ ታደርገዋለች” ተብሎ ተጽፏል፣ ዘማውን እንደ ድንግል ስንል የሥጋ ድንግልና ይገኛል ማለት አይደለም፣ በነፍስ ድንግል ይሆንልናል ማለት ነው፣ የበደልነው በደል አይቆጠርብንም ይቅር ይልልናል፣ አይያዝብንም ለማለት ነው፡፡
ስለዚህ ንስሐ ማለት መጥፎ ድርጊትን መተው ነው፣ ከመጥፎ ድርጊት ለመውጣት ደግሞ ከራስ ጋር ተመካክሮ፣ ያንን መጥፎ ድርጊት ጠልቶ፣ ትቶ ያ መጥፎ ድርጊት በኃጢአት ሲያኖረን የነበረው ከዲያቢሎስ ጋር ስለነበረ ዲያቢሎስን እምቢ ብሎ ወደ እግዚአብሔር መምጣት፣ ለእግዚአብሔር እሺ ማለት ነው፣ ከእንግዲህ በኋላ ተሳስቻለሁ የማይገባ ሥራ አድርጌያለሁ፣ ከእንግዲህ በኋላ ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር ፈቃደኛ ነኝ ብሎ ከእግዚአብሔር ጋር መኖር ነው ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ጠያቂያችን እንደጠየቁትም ንስሐ መግባት ይችላሉ፣ ቅዱስ ጳውሎስ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ቁጥር 37 ላይ በሚያስተምርበት ጊዜ ጌታችን መድኃታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት ከሙታን ተለይቶ እንደተነሣ፣ ሐብተ መንፈስ ቅዱስ እንዴት እንደላከላቸው ሲያስተምራቸው፣ ሲነግራቸው ልባቸው ተነካ፣ ምን እናድርግ አሉት ንስሐ ግቡና ሐብተ መንፈስ ቅዱስን ታገኛላችሁ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምናችሁ ተጠመቁ፣ ንስሐ ግቡ፣ ሐብተ መንፈስ ቅዱስን ታገኛላችሁ አላቸው ይላል፡፡
ስለዚህ እርስዎ ያጡትን ለማግኘት ንስሐ መግባት ነው፣ ምንም አማራጭ የለውም በኃጢአት የወደቀ ሰው የሚነሳው በንስሐ ምርኩዝ ነው፡፡ ስለዚህ በኃጢአት የወደቅን በንስሐ ተነስተን፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለን የማታልፈውን ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ ቸሩ መድኃኔዓለም ይርዳን አሜን ፡፡
የመከረን የገሰፀን የአባቶቻችን አምላክ ልዑለ ባሕርይ እግዚአብሔር ዛሬም ዘወትርም ስሙ የተመሰገነ ይሁን፣ አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡- https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፡- ሰላም አባቴ #ንስሐ መግባት በጣም እፈልጋለሁ፣ አሁን ደግሞ መግባት አይቻልም ተባለ፣ በቆየሁ ቁጥር ደግሞ #ኃጢአት እየበዛ ነው፣ ንስሐ እገባለሁ እያልኩ 3 ዓመት ሞላኝ አባ ጋ ስደርስ #ፍርሃት ይይዘኝና እመለሳለሁ፣ ምን ላድርግ አባቴ ጨነቀን እኮ?
✍መልስ፡- የእግዚአብሔር ወዳጆች እስኪ እናስተውል የሚጨንቀን ንስሐ ባይኖር ነበር፣ የሚጨቀን ንስሐ ገብቶ ባይዳን ነበር፣ ንስሐ ግቡና ተመለሱ እኔ ይቅር እላችኋለሁ እየተባልን ጨነቀን ማለትስ እንዴት ነው?
ንስሐ የሌለው ሰይጣን ይጭነቀው መመለስ የማይችለው ሰይጣን ይጭነቀው፣ እኛ እግዚአብሔር ተመለሱ እኔም እመለሳለሁ ነው ያለን፣ ይሔን ያህል ማለትም ሦስት ዓመት ሙሉ ንስሐ እገባለሁ እያሉ መኖርም ትክክል አይደለም፣ ሲጀመርም ንስሐ ለነገ አይባልም፡፡
ንስሐ ቀጠሮ አያስፈልገውም ክርስቲያኖች እባካችሁ ሕሊናችሁን ክፍት አድርጉ፣ የእግዚአብሔር ቃል በሕሊናችሁ ይፃፍና፣ አላስፈላጊው ክፉ ነገር ጠፍቶ መልካም ነገር በሕሊናችሁ ተፅፎ ሥራ እንድትሠሩ ፈቃደኖች ሁኑ፣ እግዚአብሔር በራዕይ ዮሐንስ እንዲህ ይላል “እያንዳንዱን አንኳኳለሁ፣ በየበሩ አንኳኳለሁ የሚከፍትልኝ ካገኘሁ ከእሱ ጋር እራት እበላለሁ “ይላል፡፡
እግዚብሔር በእኛ ልቦና እንዲያድር ፈቃደኞች እንሁን፣ ጠያቂዎች ብቻ መሆን የለብንም፣ ለመዳን ፈቃደኖች እንሁን፣ ንስሐ ቀጠሮ አይሰጠውም፣ እግዚአብሔር ቸር ነው ሰው የሚሞተው አንዲት ደቂቃ ባልሞላበት ውስጥ ነው፣ ኃጢያትን ተሸክሞ ሁል ጊዜ መኖር እጅግ ከባድ ነው፡፡
እስከዚህ ሰዓት ያደረሰን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን እና ንስሐ ቀጠሮ የለውም፣ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ቁጥር 33 ላይ ኃጢአታችሁን ለነገ እንናዘዛለን አትበሉ፣ አታውሉ አታሳድሩ የእለቱን ተናዘዙ፣ የነገውን ደግሞ ነገ ንስሐ ትገባላችሁ ተብሎ የተፃፈው፣ ምክንያቱም ነገ የእኛ አይደለም፣ ነገ ምን እንደሚሆን አናውቅም፣ ከዚህ አንፃር ንስሐ ቀጠሮ የለውም ኃጢአታችንን ተናዘዝን ወዲያው ንስሐ መግባት ነው ያለብን፡፡
በዚህ በበዓለ ሃምሳ ንስሐ የለውም ለተባለው፣ የንስሐው ዓይነት ይለያያል፣ ሃምሳ ቀን ሙሉ ሰው ንስሐ ሳይገባ ቀረ ማለት ምን ማለት ነው? ለምሳሌ በዚህ ሰዓት ጾም የለም፣ ስግደት የለም፣ ይሔ ዓይነት ቀኖና አይሰጥም እንጂ፤ መስዋእት፣ ጸሎት መስጠት ተገቢ ነው፣ እንጂ ይሔን ያህል ቀን ሃምሳ ቀን ሙሉ በኃጢአት ውስጥ ኃጢአትን ተሸክመን ኖርን ማለት ዛሬን ብንሞትስ? ኃጢያት ታስሮ ወደ ሲዖል መጣል ነው እድላችን ማለት ነው፡፡
የንስሐው ዓይነት ቀኖናው አሰጣጡ ይለያያል፣ ልክ እንደሌላው ቀን ስግደት፣ ጾም ላይኖር ይችላል፣ ነገር ግን በጸሎትና በምፅዋት አማካኝነት ንስሐው እንዲከናወን ይደረጋል፡፡
ጠያቂያችንም ንስሐ መግባት በጣም እፈልጋለሁ ነው የሚሉት፣ ነገ ዛሬ አንበል፣ በእርግጥም እየዋልን ባደርን ቁጥር፣ በቆየን ቁጥር፣ በኃጢአት ላይ ኃጢአት እየጨመርን ነው የምንሔደውና ያን ሁሉ ሳንናገረው፣ ሳንናዘዘው ታስረን፣ ተተብትበን እንዳንሔድ ኃጢአታችንን ማዋል ማሳደር የለብንም፣ ምክንያት መፍጠር የለብንም፣ ራሳችን በኃጢአት የወደቅን ሰዎች ራሳችንን በንስሐ አንፅተን ሥጋወ ደሙን ተቀብለን እንድንኖር ቸሩ መድኃኒዓለም ይርዳን፡፡
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፡- ንስሐ መግባት እፈልጋለሁ፤ ኃጥያቴ እጅጉን በዛ፣ ንስሐ ለመግባት ምን ማድረግ ነው ያለብኝ? ሁሉን ትቼ ወደ ፈጣሪዬ መመለስ እፈልጋለሁ፣ እባክዎትን አባቴ መላውን ንገሩኝ፡-
✍ መልስ፦ በጣም መልካም ነገር ነው፤ ዛሬውኑ በተለያየ ጥያቄ ላይ ተመስርተን የሰጠነው የጥያቄ መልስ፣ ምክር፣ ትምሕርት አብዛኛው ማለት ነው ንስሐ ከመግባት ጋር የተያያዘ ነው፡፡
ንስሐ መግባት ለእኛ አስፈላጊ እንደሆነ፣ ወደ ንስሐ እንድንቀርብ ምክንያት የሚሆኑን አባት፣ መካሪ የሚሆኑን አባቶች የሚያስፈልጉን መሆኑን ነው እየተነጋገርን ያለነው፡፡
ጠያቂያችን ኃጢያት ሰልችቶኛል፣ ኃጢያት ዘግንኖኛል፣ ኃጢያት ስልችት ብሎኛል፣ ስለዚህ ወደ በጎ ነገር ልመለስ የኃጢያት ስርየት ላገኝ እንደሚገባኝ ሁሉ ወስኛለሁ ብሎ በራሱ መጠየቁ እጅግ የሚደነቅ ሰው መሆኑን ይነግረናል፡፡
“ፃድቅ ሰባት ጊዜ ቢወድቅም ሰባት ጊዜ ይነሳል” ተብሎ ተጽፏል፣ በኃጢያት መሰናል፣ አደናቅፎን መውደቅ የግድ ከሆነ እግዚአብሔር ደግሞ ተስፋ ቆርጠን፣ ወድቀን፣ ተሰብረን፣ ተዘርረን፣ እንዳንቀር ደግሞ ትነሳላቸሁ ብሎናል፡፡
ሊያስነሳን፣ ሊያግዘን፣ ሊረዳን፣ ሊደግፈን፣ አፅንቶ፣ አበርትቶ ሊያቆመን የወደደና ያታመነ አምላክ አለን፣ ክብርና ምስጋና ለእሱ ይሁን፤ ሰው ሁሉ ሰው ሆኖ የማይበድል፣ እንጨት ሆኖ የማይጨስ የለምና፡፡ሐዋርያው ዮሐንስም በመልአክቱ በአንደኛ ዮሐንስ ምዕራፍ 1 ቁጥር 8 ላይ ኃጢያት የለብንም ብንል፤ እራሳችንን እናስታለን፣ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም ይላል፡፡
እንዲህ ብሎ መናገር ነው ሁል ጊዜም የምንላችሁ፣ እንዳውም እኛ ምንም አንሳሳትመም፣ ኃጢያት አንሰራም፤ በደል አንሰራም፣ ክፋት አንሰራም፣ በደል አንሰራም ብንል በፍፁም ስሕተት ነበር የሚሆነው፡፡
ከዚህ ሁሉ የተጠበቁ፣ ከዚህ ሁሉ የራቁ፣ የተጠበቁ ልዩ ጸጋ ያላቸው፣ ልዩ ፅናትና ብርታት ያላቸው አባቶቻችን ካልሆኑ በስተቀር ሁላችንም በየቦታችን ስለምናውቀው፣ በየቤታችን፣ በምናውቃችው ሰዎች ሁሉ ኃጢያትን ስለምናውቀው፤ እኛም ደግሞ በተወሰነ ደረጃ እንደየጥፋት መንገዳችን ኃጢያትን ስለምናውቀው እንዴት ብለን ነው ኃጢያት የለብንም የምንለው፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ ኃጢያት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን ነው ያለው፤ እውነትም በእኛ ውስጥ ዓለም የለም ማለት ነው፤ ከዚህ በላይ ምን አለ? የእግዚአብሔር ቃል ነው ይሔ፤ ስለዚህ ክርስቲያን ፈርዶብን በኃጢያት ብንወድቅም እግዚአብሔር ይመስገን፣ ፈጥነን በንስሐ እንነሳለን፡፡
አንድ ጊዜ ወድቄያለሁ ብሎ በኃጢያት ላይ ኃጢያት፣ በበደል ላይ በደል እየጨመሩ በዚያው እስከ በደላችን እንዲሁ እድል ፈንታችን ሞት ሆኖ፣ ጥፋት ሆኖ፣ ኩነኔ ሆኖ፣ ጨለማ ሆኖ መኖር የለም፣ በቀቢፀ ተስፋ እንዳንኖር የሁሉ ነገር ምሳሌና መሪ የሆነን እግዚአብሔር ነው፡፡
በትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 18 ቁጥር 21-23 የተጻፈውን ስናይ ኃጢያተኛውም ካደረገው ኃጢያት ሁሉ ቢመለስ፣ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቅ፣ ፍርድና ቅን ነገርን ቢያደርግ ፈፅሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም ይላል፡፡
ስለዚህ ጠያቂያችን በጣም መልካም ነገር አስበዋል፣ እግዚአብሔር ይመስገን፣ ለዚህ አገልግሎት ዘወትር የሚተጉ አባቶች አሉ፣ የንስሐ ሕይወትን በየደረጃው፣ የእኔ ንስሐ፣ የእኔ ኃጢያት፣ የእኔ በደል ይህ ነው ብለው ለመናገር አስቀድመው የሕሊና ዝግጅትና፣ ከልብ መፀፀት የሐጥያት ስርየት እንደሚያገኙ ማመን ነው፡፡
በእኛ ላይ ተራራ የሚያክለውን የእዳ በደላችን ሁሉ ጠራርጎ፣ ደምስሶ፣ ከሕይወታችን አጥቦ የሚያጠፋልን የሁሉ ነገር የባሕርይ ሥልጣን ያለው እግዚአብሔር ነው፡፡
ለመዳን፣ ለመናዘዝ ምክንያት አድርጎ ያስቀመጣቸው፣ የሾማቸው መልእክተኞቹ፣ አገልጋዮቹ አድርጎ ያቆማቸው፣ የላካቸው አባቶች አሉን፣ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡
ሐሰተኞች ሺህ ነገር ቢያወሩ አንስማ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ብንጠቅስ፣ ብንጠቅስ፣ ሐሰተኞች የሐሰት ነገር አያጡም፣ የሚያወሩት ወሬ አያጡም፣ ሰውን ለማሳት ሰይጣን ነው በቅርቡ በአንደበታቸው ላይ የሚያቀብላቸው፡፡
እንዲህ ዓይነት ሕይወት እንዲኖረን ያገዘን እግዚአብሔር፤ እኔስ ኃጥያቴ፣ በደሌ በጣም ብዙ ነው ብሎ ማለት፣ አይደለም ለኋለኛው ዓለም፣ ለዘላዓለማዊው ዓለም፣ ለሠማያዊው ዓለም ይቅርና፤ በዚህ ምድር ላይ እረፍት ነስቶን የሚኖር በጣም ብዙ ጉድ ያለብን ነው፡፡ ላልጠቀመን፣ ውጤታማ ላልሆንንበት ነገር ስንስገበገብ የገባንበት ነገር መውጫ አቅቶን፣ በጣም ብዙ ጉድ ተሸክመን ነው ያለነው እግዚአብሐር በቸርነቱ እንጂ፣ አንድ ቀን የእዳ ደብዳቤያችንን ቢገልጠው እኮ ለመስማትም ለማንበብም የሚሰለች ጉድ ያለብን ሰዎች ነን፡፡
የአግዚአብሔር ቸርነቱና ምሕረቱ ግን በዝቶልን፣ የእኛ ኃጢያትና በደል፣ የኃጢያት ክምራችን ሁሉ በእሱ ቸርነትና ምሕረት ተከድኖልን፣ የንስሐ ሕይወታችንም ከኃጢታችን በላይ ዋጋ ኖሮት ይሔን ሁሉ በደልና ኃጢያት እግዚአብሔር ይቅር ይለናል፡፡
ከዚህ የተነሳ ወደ ፈጣሪ መመለስ እፈልጋለሁ፣ ንስሐ ለመግባት ምን ማድረግ አለብኝ? ብለዋል፣ ምናልባት ከእርስዎ የሆነ ነገር ለመረዳት የመጨረሻ ደረጃ እንዲያደርጉ ለመምከር ባለን የስልክ አድራሻ አናግሩን፡፡
ስርዓቱማ የታወቀ ነው፣ የንስሐ አባት አለዎት ማለት ነው፣ የእኛ የንስሐ አባቶቻችን ወይም፣ የነፍስ አባቶቻችን ከእግዚአብሔር ቀጥሎ የምናምናቸው ሴትም ለባሏ ፣ወንድም ለሚስቱ የማይነገረውን፣ ለእናትም፣ ለአባትም የማይነገረውን፣ ለምንወደው ሚስጥረኛ ጓደኛ የማንነግረውን፣ ከምንም በላይ ሊቀርቡን ልጆቻችን፣ እህቶቻችን የማንናገረውን ከእነሱ የተደበቀውን፣ የተሰወረውን በዚህ ምድር ላይ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ የምንነግረው ለካሕን ብቻ ነው፡፡
እኛን በዚህ ምድር ላይ እንደ ተራራ ያክል አጉብጦ የከበደንን የኃጢያት ሸክም አውረደን እናሳርፈዋለን፣ ካሕኑ ደግሞ ስለ እኛ ይታመናል፣ በተሰጠው አደራ መሠረት ደግሞ የኃጢያት ስርየት የምናገኝበትን ቀኖና ይሰጠናል፡፡
የሚሰጠን ቀኖና መጾም ይሁን፣ መጸለይ ይሁን፣ መስገድ ይሁን፣ ምፅዋት ማድረግ ይሁን፣ በዚህ መሠረት የንስሐ አባት የሌለው ሰው እንዴት መያዝ እንዳለበት እንነግራለን፣ የንስሓ አባት ከተያዘ ደግሞ ከልብ ተፀፅቶ፣ ወደ ንስሐ አባት ቀርቦ የተሰጠንን ቀኖና በስርዓት ማከናወን አለበት፡፡
አባቶችም በስርዓቱ ዋጋ እንድናገኝበት፣ የኃጢያት ስርየት እንድናገኝበት የሚያስችለውን ቀኖና እንዲሰጡን ያስፈልጋል፤ በእውነተኛ እምነት ማለት ነው፣ ከዚህ አንፃር ነው እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ አምላክ ስለሆነ ሁሉን እያደረገልን ነው፡፡
በዚህ ጾም ጊዜ ብዙዎች ወደ ንስሐ ሕይወት እንደቀረቡ፣ ከምንም በላይ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር እንዳስረከቡ፣ ኃጢያታቸውን እንዳስመረመሩ ሁሉ ተስፋ ያደረግንበት ነገር ብዙ ነው፡፡
ከዚህ ቀደምም ስለ ንስሐ ሕይወት የሰጠነው ምክርና ትምሐርት በድረ ገጻችን ገብተው እንዲከታተሉ በአከብሮት እንነግራለን፡፡👇
https://t.me/c/1172495782/34692
https://t.me/c/1172495782/22081
https://t.me/c/1172495782/37500
https://t.me/c/1172495782/30259
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፦ ንስሐ መግባት ሁል ጊዜ እመኛለሁ ግን ሳስብ የሆነ መሰናክል አያጣኝም ምን ላድርርግ ግራ ገባኝ?
መልስ፦ እንግዲህ ጥያቄው እንደተመለከታችሁት ንስሐ መግባት ፈልጌ ለንስሐ ህይወት እዘጋጃለሁ፤ የንስሐ ቀኖና ተቀብዬ እንዳልፈፅም ግን ምክንያቶችና መሰናክል ይበዙብኛል ነው የሚለው ። መቼስ የመዳን ቀን አሁን ነው የሚለውና ጠያቂያችን በመሰረቱ ለንስሐ ቀጠሮ አይሰጥም፤ ስለዚህ የመጀመሪያ ነገር መታወቅ ያለበት ይሄ ነው። የመዳን ቀን አሁን ነው ማለት ፥ በየጊዜው ያደረው እንዳይውልብን የዋለው እንዳያድርብን ነውና ለንስሐ ቀጠሮ መስጠት የለብንም። ሰው ዛሬ አጣዳፊ ድንገተኛ በሽታ ይዞት ለሞት የሚያበቃ ነገር ይዞት ፤ መሰናክል በዝቶብኛል ብሎ ወይም አሁን ጊዜ የለኝምና ልዋልና ልደር ነገ ከነገወዲያ ሀኪም ጋር ሄዳለው አይባልም እኮ፤ እንደዚሁ ሁሉ የንስሐ ህይወት የነፍስ ጉዳይ ስለሆነ ከዚህ ባለፈ ነው መታየት ያለበት። ያኛው የስጋ ደዌ ነው ወደ ድንገተኛ ክፍል ቶሎ አስቸኩለን እንድናስገባው የሚያስገድደን፤ ይሄ ደግሞ የነፍስ ደዌ ነውና በአስቸኳይ ወደ ንስሐ አባት መሄድ ይገባናል።
ለረጅም ጊዜ ቀኖና የሚያስፈልገውን በየደረጃው አባቶች ናቸው ቀኖናውን በመስጠት የህክምና መሳሪያቸው በእጃቸው ስለሆነ፤ ቀላሉን ደግሞ ቶሎ ብለው ለማውረድ ብለው ብዙ ሸክም የበዛበትን ሰውም በአንድ ጊዜ አካብደውበት በሸክም ላይ ሸክም አያሸክሙትም። ቀለል ባለ ሁኔታ ምክር ትምህርት ተግሳፅ እየሰጡት ወደ እግዚአብሔር አቅርበውት ከሰይጣን እጅ አውጥተውት እያስታመሙት ያስተምሩታል። መድሃኒትም እኮ ቢሆን በአንድ ጊዜ አይሰጥም ለምሳሌ መጀመሪያ ግሉኮስ ውሰድና አቅም ስትገዛና ስታገግም ይሄኛውን ትቀጥላለህ ነው የሚሉት እንጂ በሽታው በገባው ሰው የማይችለውን መድሃኒት ሰጥተው ለሞት አደጋ አያጋልጡትም ሃኪሞቹ፤ መንፈሳዊ እርዳታም እንደዚሁ ነው። ይሄንን ኀጢአትና የመሰናክል ፈተና የበዛበትን ሰው ፍፁም ወደሆነ የንስሐ ቀኖና ለማድረስ ተከታታይ ምክር ትምህርት ሰጥተው ለንስሐ ያበቁታል ማለት ነው።
ስለዚህ መሰናክል የበዛብዎት አባላችን በዚህ አይነት እንዲመለከቱት እባክዎን። መሰናክል ይመጣ ዘንድ የግድ ነውና ደግሞ ለሚያሰናክል ለዚያ ለእየእለት አሰናካያችን በፍጹም ለሁላችንም የጋራ የህይወት ችግራችን ሰይጣን ነው። ጥቃቅኑንም ከራሳችን ከግል ስራ ጀምሮ ከቤተሰብ አስተዳደር ጀምሮ የማህበራዊ ጉዳዮችንም ጀምሮ የውስጥም ሆነ የውጭ መሰናክሎች ልክ እንደ ንስሐ መግባት ቀጠሯችን እንዲረዝም ይሄን ሁሉ ፈተና የሚያመጣብን ከላይ እንደጠቀስነው ለሁሉ ነገር አሰናካይ ሰይጣን ነው። ስለዚህ እርስዎ ይሄን ተረድተው በቆራጥነት ወስነው ንስሐ መግባት እንዳለብዎት፤ አኛንም በውስጥ መስመር አግኝተውን ወደኋላ ያስቀረዎትን ጉዳይ በግልጽ ሲነግሩን ለዚያ የሚሆነውን ተገቢ ምክርና መፍትሄ ምን ማድረግ እንዳለብዎት መንገዱን እንመክርዎታለን አቅጣጫውን እናሳይዎታለን።
ስለዚህ ጠያቂያችን መንፈሳዊ ስራ ልስንሰራ ስንል መሰናክል አለ፤ በረቂቅ ገመድ ከኋላ ሆኖ ወደ ፊት እንሂድ ስንል ወደኋላ የሚጎትተን መንፈስ አለ ። በእርግጠኝነት እርስዎ እንዳሉት ለእርስዎ መሰናክል ነው፤ ግን ቁጭ ብለን ብናወራበትና ችግሩን ከመንፈሳዊ አንፃር ብናየው መሰናክል አይሆንም፤ ስለዚህ አንድ ሰው ይሄንን መሰናክል የመሰለውን ይሄ እሩቅ መንገድ የመሰለውን ፈተና በቁርጠኝነት ወስነው ያለምንም ፍርሃት እንዲሄዱበት የሚያስችል አንድ የእግዚአብሔር ፀጋ ያደረበት አንድ አባት መካሪና አስተማሪ መያዝ ያስፈልጋል። ዋናው ነገር ደግሞ ደጋግመው ይጸልዩ ይህ ፈተና ይህ መከራ ካለ ጸሎትና ጾም ካለስግደት ወደ እግዚአብሔር እርስዎን ካለመቅረብ ቅዳሴውን ቃሉን ካለመስማት ሌላ አዋጪ መፍትሄ የለም። ይህ የስጋ ዘመድ ዲያብሎስ ያለጸጾምና ያለጸሎት ከቶ አይወጣም ብለዋልና ስለዚህ ጸሎት ትልቁ ሃይላችን ነው። ጸሎት ደግሞ ከምን እንደሚጀምር ከዚህ በፊትም ተነጋግረናል፤ እንዲያው አጭሯ ጸሎት አባታችን ሆይ የሚለው አቅሟና የምትሰራው ሃይል ከባድ ነው ብለናልና ጠያቂያችን በዚህ ተረድተው ይህን ፈተና እንዲያልፉት እንመክራለን።
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፦ ሰላም 🙏እኔ ያለሁት ሰበታ የሚባል አካባቢ ነው፤ እና በእናንተ በኩል ንስሐ አባት እንዴት ማግኘት እችላለሁ በጣም ለበዙ ጊዜ አምላኬን አሳዝኜዋለሁ አሁን ግን የእናንተ አባል ከሆንኩ በኋላ ብዙ ትምህርት እና የፈጣሪ ፍቅር ገብቶኛል፤ ስለዚህ ንስሐ መግባት እፈልጋለሁ፤ እባካችሁ አባቶቼ እርዱኝ🙏🙏🙏😢😢
መልስ፦ ጠያቂያችን፤ ከምንም በላይ በዚህ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ትምህርት ተከታትለው በግል ህይወትዎ ለንስሓ ህይወት የበቁበት እድል እንደሆነ ከላኩልን መእክት ስንመለከት በእኛም በኩል እግዚአብሔር በፈቀደልን መጠን የዘራነውን የእግዚአብሔር ቃል ፍሬ እንዳፈራ ስላስተዋልን በእጅጉ እንዲህ አይነት የእምነትና የምግባር ሰዎችን እግዚአብሔር እንዲያበዛ ከወዲሁ ያለንን ልባዊ ምኞት እንገልፃለን። ሌሎች አባላትም እንደዚሁ የደረሳችሁበትን በሂደት የማሳወቅ ልምደሰ ቢኖር እኛም የአገልግሎታችንን ተደራሽነትና ውጤታማነት የምንለካበት አንዱ መንገድ ከመሆኑም በላይ በአባላት መካከልም የህይወት ተሞክሮን ማካፈል አንዱ መማማርያና መመካከርያ መንገድ ይሆናል ብለን እናምናለን።
ጠያቂያችን፤ ወደ ጠየቁን ዋና ጉዳይ ስንመጣ፤ ንስሐ ለመግባት ወይም ወደ ንስሐ ህይወት ለመምጣትና ኅጢአትን ለመናዘዝ ቅድሚያ ሰጥተው ለንስኀ መዘጋጀትዎ ከእውነተኛ ክርስቲያን የሚጠበቅ ታማኝነትና ከምንም በላይ የተቀደሰ ተግባር ነው ። እንዳሉትም እግዚአብሔር የፍቅር አምላክ ነውና ሁሌ እጆቺን ዘርግት ኑ ልጆቼ በማለት በንስሐ እንድንመለስ ይጠብቀናል።
ነብዩ ሕዝቅኤል እግዚአብሔር የሰውን ሞት የማይወድ እና ሰው ወደ ንስሐ መመለሱን የሚወድ መሆኑን ሲናገር ”ንሰሐ ግቡ፤ ኀጥያትም እንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኀጥያታችሁ ሁሉ ተመለሱ። የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ። አዲስ ልብ እና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ፤ ..ስለምን ትሞታላችሁ የሟችን ሞት አልፈቅድምና ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ስለዚህ ተመለሱ እና በህይወት ኑሩ። (ሕዝ 18፥30-32)
ስለዚህ በእኛ በኩል፥ በህይወታቸው ምሳሌ ይሆናሉ ብለን ለአባትነት የመረጥናቸው የቤተክርስቲያን አባቶች በሃይማኖታቸውና በእውቀታቸው የታመነባቸው አባቶች ስላሉ የመዳን ቀን አሁን ስለሆነ የቀጠሮ ቀን እና ሰዓት ሳያራዝሙ በድረገፃችን ላይ ባለው ቁጥር ወይም ደግሞ በውስጥ መስመር በላክንልዎ ቁጥር ደውለው የሚያገኟቸውን አባት ያማክሯቸውና በአካባቢዎ ካሉ ካህናት ጋር ሊያገናኞት ይችላሉ።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ፦ አዲሱን አመት በ#ንስሐ መቀበል እፈልጋለው፤ #ንስሐ_አባት ግን የለኝም…ምን ትመክሩኛላቹ አባቶቼ?
መልስ፦ ጠያቂያችን፤ ማንም ክርስቲያን አለ ንስሐ አባት አንድ ቀንም መኖር የለበትም፤ አሁንም እርስዎ አዲሱን አመት በንስሐ መቀበል መፈለጎትን እያደነቅን፤ አበአሰቡት አላማ ጸንተው እንዲፈጽሙም አደራ እንላለን። የተነሱበትን የዘመን መለወጫ ፥ አዎ እንዳሉትም አሮጌውን አመት አሳልፈን አዲሱን አመት የምንቀበልበትን መስከረም 1 ቀን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ርዕሰ ዐውደ አመት ፣ ቅዱስ ዮሐንስ፣ አዲስ ዘመን መለወጫ ተብሎ ይጠራል። ሃይማኖታዊ መሰረቱን በሚመለከት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ “እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ” ተብሎ በነቢዩ ኢሳይያስ በተነገረለት የትንቢት ቃል መሰረት የካህኑ የዘካርያስ እና የቅድስት ኤልሳቤጥ ልጅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አመተ ኩነኔ፣ አመተ ፍዳ፣ አመተ አለም ተብሎ የሚጠራው 5500 ዘመን መደምደሚያ እና የአዲስ ኪዳን ዋዜማ ላይ ሆኖ “መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ እያለ ስለመሲህ ክርስቶስ መምጣት እና ስለአዳኝነቱ ስለባሕሪይ አምላክነቱ በምድረ በዳ እየመሰከረ የንስሓ ጥምቀትን በማጥመቅ ለኃጢአተኞች ሁሉ የኀጢአት ስርየትን እየሰበከላቸው የብሉይ ኪዳን የመጨረሻ ነብይ እና የአዲስ ኪዳን የመጀመሪያ ሐዋርያ ምስጢር መሆኑን እንረዳለን። መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ለአዲስ ኪዳን ዘመን የመሸጋገርያ ድልድይ ሆኖ መገለጡን በመረዳት የቤተክርስቲያን አባቶች የዘመን መለወጫ በአልን ሲደነግጉ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ መታሰብያ በአል በየአመቱ መስከረም 1 ቀን እንዲከበር የዘመኑ መጀመሪያ በሱ ስም እንዲጠራ ወስነዋል። ማስረጃ (የቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ ድርሳን ገፅ 1/3)
የሰው ልጅ እግዚአብሔር በረዳው እና እሱም ቀና ሲሆን ዘመናትን እየዋጀ እግዚአብሔር ያለዋጋ በልግስና የሰጠንን ገንዘብ የማይገዛውን ጊዜ ፥ ለማይጠቅመን፣ ለውጥ ለማያመጣልን፣ ለክፉ ስራ ወይም ደግሞ በነፍሳችን ለምንጎዳበት የኀጢአት ስራ ከምናውለው ይልቅ እኛ በነፍስ እና በስጋ ለሚጠቅመን በሃይማኖት እና በምግባር ለሚያፀናን፣ ከሰው ልጆች ሁሉ ጋር በሰላም እና በፍቅር ለመኖር ለሚያስችል ጠቃሚ አላማ ላይ ብናውለው ያኔ ትርፋማ ያደርገናል። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ዘመኑን ዋጁ” (ኤፌ5፥15) በማለት እያንዳንዱን ዘመን በመመርመርና በጥንቃቄ መመልከት እንደሚያስፈልገን ተናግሯል።
ስለዚህ ጠያቂያችን፤ ወደ ጥያቄዎ ስንመጣ ከላይ እንደገለጽነው ንስሐ አባት መያዝ መንፈሳዊ ግዴታው ነው። በረቂቅ እና በሚስጢር አሠራር ቅዱሳን መላዕክት የኛ ጠባቂ ሆነው ይቆማሉ። በዚህ በገሃዱ አለም ደግሞ እንደ አንድ ክርስቲያን በምንኖርበት ህይወት ውስጥ ካህናት አባቶቻችን ለእኛ የነፍስ እረኞች ሆነው በእግዚአብሔር ዘንድ ተሹመዋል። ስለዚህ ንስሓ አባት መያዝ የሰው ትዕዛዝ ሳይሆን የፈጣሪ መመሪያ ነው።
ስለሆነም ጠያቂያችን፤ የምንመክርዎት መልካምን ነገር ወስነዋልና አሁንም በአሰቡት አላማ ጸንተው የቀጠሮ ቀን እና ሰዓት ሳያራዝሙ ይመክረኛል ያስተምረኛል ያሉትን የንስሓ አባት የሚሆን ካህን በአካባቢዎ ካሉ ይያዙ፤ በአከባቢዎ ማግኘት የማይችሉ ከሆነ በራስዎትም ሆነ በሚያምኑት ሰው በኩል አጠያይቀው ያገኙዋቸውን እውነተኛ ካህን በርቀትም ቢሆን ይያዙ፤ ወይም ደግሞ በእኛ በኩል በህይወታቸው ምሳሌ ይሆናሉ ብለን ለአባትነት የመረጥናቸው የቤተክርስቲያን አባቶች በሃይማኖታቸውና በእውቀታቸው የታመነባቸው አባቶች ስላሉ በድረገፃችን ላይ ባለው ቁጥር ወይም ደግሞ በውስጥ መስመር በሚላክልዎ ቁጥር ደውለው የሚያገኟቸውን አባት አነጋግረው ንስኀዎን መፈጸምም እንዲሁም ንስሐ አባት በማድረግ መያዝ እንዳሉትም በየጊዜው በጸሎት እንዲያስቡዎት መጠየቅ እንዲሁም ማንኛውንም መንፈሳዊ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
በተጨማሪም፤ ስለ ንስሐ ፣ ስለ ንስሐ አባት እና ሌሎችም መንፈሳዊ ትምህርቶች በድረገጻችን ላይ መጽሐፉ ቅዱስን መሰረት አድርገን ሰፊ ትምህርት የሰጠንበት ስለሆነ በዚያም እየተከታተሉ የበለጠ ግንዛቤ ቢያገኙ መልካም ነው።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ፦ #ንስሐ ከስንት አመት ጀምሮ ነው መግባት የሚቻለው??
መልስ፦ጠያቂያችን ከዚህ በፊት “ከስንት አመት ጀምሮ ስለሰራነው ኀጢአት ነው ንስሓ የምንገባው?” የሚል ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦልን የሰጠነውን ምላሽ አንብበው ሃሳቡን ይረዱት ዘንድ እንደሚከተለው ልከንልዎታል፦
ሴትም ይሁን ወንድ ልጅ ለአካለ መጠን ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ እያወቁ በፈጸሙት የኀጢአት በደል በነፍስ ስለሚጠየቁ ንስሓ መግባት እንዳለባቸው የቤተክርስቲያን ቀኖና ይደነግጋል።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
ንስሐ // የፍርሃት ስሜት
👉ጥያቄ፦ #ንስሐ ለመግባት እፈልጋለሁ ግን #እፈራሁ ፍርሐቴን ላለመፍራት ምን ላድርግ?
✍መልስ፦ ጠያቂያችን መፍራት ያለብን ገሃነም ሊያስገባን የሚችለውን ኅጢአት ነው እንጂ በሚደርስብን ሰው ሰውኛ ተጽእኖና ሥጋዊ አመለካከት ከእግዚአብሔር ሊያርቀን አይገባም። እግዚአብሔር የፍቅርና የሰላም ፣ የቸርነትና የምህረት እንጂ የፍርኅት አምላክ አይደለም። አዳም የተሰጠውን ሕግ ተላልፎ ደግሞም ርቃኑን መሆኑን ተመልክቶ በእግዚአብሔር ፊት መቆምን ፈርቶ በገነት ዛፎች መካከል በተደበቀ ጊዜም “አዳም ሆይ ወዴት ነህ” እያለ ፈልጓል። (ዘፍ 3፥) በእውነቱ አዳም ያለበት ቦታ ከእርሱ ተሰውሮት አይደለም። ያለበትን ቦታና ሁኔታ ማወቅና መናገር የአዳም ድርሻ ሆኑን ለማስታወቅ ነው እንጂ። በአንጻሩም እኛ ቃጢአት በሰራን ጊዜ ጥፋታችንን አምነንና ተጸጽተን ወደ ካህናት ቀርበን መናዘዝና የሚሰጠንን ቀኖና ተቀብለን መፈጸም እንደሚገናን ለማስተማር ጭምር ነው። ስለዚህ ምስጢረ ንስሓ እግዚአብሔር ራሱ የሰራልን ስርዓት ሲሆን ንስሐ አባትም በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል ሆነው እንዲያስታርቁ እግዚአብሔር ራሱ የሾማቸው ሽማግሌዎች ናቸውና ሳንፈራ በግልፅ የሠራነውን ኅጢአት ለካሕናት መናገር ከፈራንም ጸሎት አድርገን ፍርሃታችንን ከልብ አውጥተን ወዲያ ጥለን በተሰራልንን የንስሓ ስርዓት መሰረት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይገባናል። የንስሐ አባትም የንስሐ ልጁን የኅጢአት ኑዛዜ ተቀብሎ የሚያስፈልገውን ነገር ለመጠበቅና ለመምከር እና ለመምራት ኅላፊነቱን አለበት።
ስለዚህ ጠያቂያችን፥ በእርግጥ ከመነሻው ኀጢአትን ባንሰራው መልካም ሆኖ ሳለ ከሰራነው ግን የመጨረሻ አማራጫችንና ከእግዚአብሔር ጋር የምንታረቅበት መንገድ ንስሓ ነው። ይህ ደግሞ የሚፈጸመው የነፍስ እረኛ እንዲሆኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የክህነት ስልጣን በተሰጣቸው አባቶች ካህናት አማካኝነት ስለሆነ ጠያቂያችን ለንስሓ አባቶ ኀጢአቶን ተናዘው ቀኖናዎትን መውሰድ አለቦት። እግዚአብሔር ደግሞ የፍርሃት አምላክ ሳይሆን የፍቅርና የሰላም አምላክ በሃጥያት የወደቀውን አይዞህ ልጄ ብሎ የሚያነሳ እና ከጠፋንበት ፈልጎ የሚያገኝ አምላክ ስለሆነ የሚቃወምዎትን ክፉ መንፈስ እንደምንም ታግለው በማስወገድ ወደ ንስሐ ይቅረቡ። ንስሓ በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍሥን የሚያሰጥ ትልቅ ምስጢር ነውና ያን ግዜ የእግዚአብሔር ፀጋና ሰላም ከእርስዎ ጋር ስለሚሆን በግል ኑሮዎትም በማህበራዊ ህይወቶትም ያለው ግንኙነት ሰላም ይሆንልዎታል፤ የተረጋጋ መንፈስም ይኖርዎታል።
ከጥፋታችን ተመልሰን ንስሐ እንዳንገባ ደግሞ የበጎ ነገር ሁሉ ጠላት የሆነው እና የእኛን ፅናት የማይፈልገው ሰይጣንም ግራ እንዲገባን እና የፍርሃቶቻችን ምክንያቶች እንዲበዙ ያባብስብናል። ንስሐ ግን ጠላት ዲያብሎስ የክርስቲያኖችን ሕይወት ለማጥፋት የገነባውን የኅጢአት ሕንጻ ሁሉ በእግዚአብሔር ቸርነት እንዳልነበረ የሚያፈርሰው ዋናው መንገድ በመሆኑ ሰይጣን ከሚዋጋቸው የድኅነት መንገዶች ውስጥ ንስሐን የሚያክል የለም። ንስሐ እንዳንገባ የሚዋጋንም በቀጥታ ሳይሆን የተለያዩ ስውር ምክንያቶችን እየደቀነ ንስሓ እንዳንገባ ያዘገየናል። የሚዘገይ ሰው ደግሞ እንደ ቃየን ተቅበዝባዥና ብቸኛ ይሆንና ማንም ሳያሳድደው ኅጢአቱን ተሸክሞ በእግዚአብሔር ቤት ለመቆየት ስለሚከብደው ለመሸሽ ይገደዳል። ከእውነተኛ ሃይማኖትና ምግባር ስንርቅ ደግሞ የንስሐ ህይወታችን ጨርሶ ይቀጭጫል። ያኔ በሰራነው ኀጥያት (ጥፋት) ነፍሳችን ፈፅሞ ትቃተታለች ትጨነቃለችም። ስጋችን ምድራዊ የሆነውን የስጋ ስራ ለመስራት ነፍሳችን ደግሞ ሰማያዊ የሆነውን የፅድቅ ስራ ለመስራት ለኛ ግልፅ ሆኖ በማይታወቅና በማንረዳው ሁኔታ ሁለቱም ህይወታችንን የጦር አውድማ ሲያደርጓት በኛ ላይ የፍርሃት መንፈስ ይነግስብናል።
ስለዚህ ጠያቂያችን ጊዜ ሳያራዝሙ ንስሐ መግባት በቤቱ ለመጽናት አስፈላጊ ነው ማለት ነው። ምናልባት በአንዳንድ አጉል አማካሪ ግራ ተጋብተን የነፍሳችን እረኛና ጠባቂ ከሆኑት አባቶችን ፈርተን ተለይተን ወይም ያለ ነፍስ አባት ስንኖር በዱርና በሜዳ ያለ እረኛ እንደተሰማራ መንጋ እንሆናለን። እንደሚታወቀው እረኛ የሌለው መንጋ በተኩላና በአውሬ ይበላል። ማንኛውም ስጋዊ ሀብታችን ጠባቂና ተቆጣጣሪ ከሌለው በነጣቂዎችና በወንበዴዎች እንደሚዘረፍ ሁሉ በጧት በማታ በአባትነት የሚጠብቁን አበነፍስ (ንስሐ አባት) ከሌለን ከምንም በላይ ክፉና ጨካኝ የሆነው ዲያብሎስ ነፍሣችንን የማይገባትን የክፋትና የአመጽ ሥራ ስለሚያሠራት ያለጠባቂና ያለመካሪ አባት አንድ ቀን መኖር የለብንም። ንስሐ አባት ማለት ምስጢረኛችን በመንፈሳዊም በሥጋዊም ህይወታችን የቅርብ አማካሪዎቻችን ማለት ነው። ጠቢቡ ሲራክ “ብዙ ሰዎች ወዳጆች ይኑሩህ ከብዙዎች አንዱ ምክርህን የምትነግረው ከልቡናህ ጋር አንድ ይሁን።” (ሲራክ 6፥6) ስለዚህ ጠያቂያችን በሃይማኖታቸውና በስነምግባራቸው የተመሰከረላቸውን አባቶች በማነጋገር የንስሐ አባት ማድረግ እንደሚገባዎት እንመክራለን።
ለሁሉም ነገር ወላዲት አምላክ ድንግል ማርያም በአማላጅነትዋ ታግዝዎ።
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፦ ሁል ጊዜ #ንስሐ መግባት እየፈለኩ ግን ፈርቼ እተወዋለሁ ምን ላድርግ?
መልስ፦ ጠያቂያችን ይሄ መጥፎ ነገር ነው። የሚያስፈራው ከነኅጢአት መኖር ነው እንጂ ወደ ንስሐ መምጣት አያስፈራም። ለዚህም ቤተክርስቲያን ስርዓት ሰርታለች፤ በሚስጥር ሆኖ ወደ ቤተክርስቲያን ወይም ወደ ገዳም በሚስጥር ቦታ ሆኖ አባቴ ብሎ፤ እንደው የንስሐ ህይወት ልምድ የለንም እንጂ የሚያስፈራውስ ነገ የማንኖርበት ዘመን እንደሚመጣ እያወቅን እንዲሁ በቀለኞችና በደለኞች ሆነን እስከኅጢአታችን መኖር ለዘለዓለም የሞት የሞት ፍርድ የሚያመጣብን እንደሆነ እያወቅን ለዚያውም ላይ ሰላም እንዳይኖረን ለህሊናችን እረፍት እንዳይኖረን ከነኅጢአታችን ውስጣችን እየተሰቃየ የመንፈስ እረፍት እያጣን ከመኖር የበለጠ መከራ የለም። ስለዚህ ወደ ንስሐ ህይወት መቅረብ ንስሐን መናዘዝ ከባድ ነገር አይደለም። ለዚህ መታደል አለብን።
ለሁሉም ነገር እንግዲህ ጠያቂያችን እርስዎን የከበደብዎትንና የተዘጋጋውን በር ለመከፋፈት ነገሮችን ሁሉ ቀለል አድርገው አይተዋቸው እንግዲህ ወደ ንስሐ የመቅረብ ልምድ ለሌለው ሰውኮ ቀላል አይደለም። ዝም ብለንኮ ነገሮችን እያቀለልን ወይም እያከበድን አይደለም፤ እንደ ትክክለኛ ክርስትና ስንመለከተው እንግዲህ የጽድቅን መንገድ መከተል ከሁሉ የተሻለ የሚያስደስት ነገር ስለሆነ የትምህርት ማነስ፣ የአባቶች ምክር አለማግኘት ካልሆነ በስተቀር መንፈሳዊ ልምድ አለመኖር የብዙ ሰው ችግር ይሄ ነው፤ የቤተክርስቲያን አባቶችም በትጋት ሆነው ልጆቻቸውን ተከታትለው ዘወትር ባለመምከራቸውና ባለማስተካከላቸው ኅጢአት ላይ ሲወድቁ መውጫው በሩ ይጠፋባቸዋል። ከዚያ ኋላ ቀርበው ንስሐ ከመናዘዝ ይልቅ እንዲሁ ሸሽተውና እርቀው ተሰውረው ተደብቀው እስከነ ኅጢአታቸው እስከነበደላቸው መቀጠልን ይመርጣሉ። እንደ እውነተኛ አስተሳሰብ ወይም እንደመንፈሳዊና እንደክርስቲያን ስናስበው ግን ከነኅጢአት መኖር ነው የሚያሳፍረው።
እንዲያው እኛ የኅጢአት ሰዎች ሆነን መኖራችን ብቻ ሳይሆን ለስጋዊ ህይወታችን ሁሉ የማይመች ብዙ እድሎቻችንን የሚያሰናክልብን የሚያደናቅፈብን ከነበደላችን ከነኅጢአታችን መኖር ነው። ይሄ በምድር ላይ ብዙ እድል የሚያበላሽ ነው፤ ኅጢአተኛ ሆኖ መኖር፣ በደለኛ ሆኖ መኖር፤ መቼስ እግዚአብሔርን መዋሸት እግዚአብሔርን መሸንገል አይቻልምና፤ እግዚአብሔር የሚያውቅብን እሱ ተቀይሞን ሁሉ ፤ በግል ህይወታችንም በማህበራዊ ህይወታችንም ሁሉ እንዲያውም ፈተና እና መሰናክል የሚሆንብን ከነኅጢአት መኖር ነው እንጂ ወደ ንስሐ መምጣት መንገዱ በጣም መንገዱ ሰፊ ነው፣ የብርሀን መንገድ ነው የደስታ የሰላምና የፍቅር መንገድ ነውና ወደ ንስሐ እንዲመጡ እንመክራለን የእኛም ቋሚ አገልግሎታችን በዚህ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ እንዳልነውም በውስጥ መስመር ያግኙንና ተጨማሪ ምክር ሰጥተንዎት ያለምንም ፍርሃት ወደ ንስሐ የሚያመሩ ይሆናሉ እግዚአብሔርም ያግዘናል፤ እግዚአብሕር የኅይል የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም። ዲያብሎስ ግን ከዚህ ከፍርሀት መንፈስ ተጠቃሚ ስለሚሆን ምንግዜም ወደ ሽንላ ወደ ጥርጥርና መስሎ ወደ መታየት ያስገባናል። እግዚአብሔር ግን የሰውን ሞት የማይወድ በንስሐ ወደ ሕይወት መመለሱን ግን የሚያስደስተው መሆኑን በመፅሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ነግሮናል፤ ከነዚህም የተወሰኑትን ለመመልከት የሚከተለውን ሊንክ ተጭነው የሚያገኙትን መልእክት አንብበው እንዲረዱት እንመክራለን።👇👇👇
https://t.me/c/1172495782/31617
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፦ #ንስሐ ከገባሁ ረጅም ጊዜዬ ነው በዚኽም ሁሌ ይጨንቀኛል፤ በህይወቴ ዙርያ ነገሮች ተወሳሰቡብኝ ፤ ንስሐ ለመግባት ደግሞ ፍላጎቱ እንጂ ውሳኔው የለኝም ፈራለሁም ደሞሞ እንቅፋቱ ይበዛብኛል ። ምከሩ?
መልስ፦ ጠያቂያችን ከምንም በላይ መገንዘብ ያለብዎት ኀጢአት ባንሰራው መልካም ሆኖ ሳለ ከሰራነው ግን የመጨረሻ አማራጫችንና ከእግዚአብሔር ጋር የምንታረቅበት መንገድ ንስሐ ነውና፤ የነፍስ እረኛ እንዲሆኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የክህነት ስልጣን የተሰጣቸው አባቶች ካህናት ስለሆኑ ጠያቂያችን ለንስሓ አባትዎ ኀጢአቶን ተናዘው ቀኖናዎትን መውሰድ አለቦት። ያን ግዜ በግል ኑሮዎትም በማህበራዊ ህይወቶትም ያለው ግንኙነት ሰላም ይሆንልዎታል፤ የተረጋጋ መንፈስም ይኖርዎታል። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ፀጋና ሰላም ከእርስዎ ጋር ስለሚሆን። ከእውነተኛ ሃይማኖትና ምግባር ስንርቅ ግን የንስሐ ህይወታችን ጨርሶ ይቀጭጫል። ያኔ ደግሞ በሰራነው ኀጥያት (ጥፋት) ነፍሳችን ፈፅሞ ትቃተታለች ትጨነቃለችም። ስጋችን ምድራዊ የሆነውን የስጋ ስራ ለመስራት ነፍሳችን ደግሞ ሰማያዊ የሆነውን የፅድቅ ስራ ለመስራት ለኛ ግልፅ ሆኖ በማይታወቅና በማንረዳው ሁኔታ ሁለቱም ህይወታችንን የጦር አውድማ ሲያደርጓት የፍርሃት መንፈስ በኛ ላይ ይነግስብናል። ከጥፋታችን ተመልሰን ንስሐ እንዳንገባ ደግሞ የበጎ ነገር ሁሉ ጠላት የሆነው እና የእኛን ፅናት የማይፈልገው ሰይጣንም ግራ እንዲገባንና ከንስሐ የሚያዘገዩ ምክንያቶች እንዲበዙ ያባብስብናል። ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲሰያን ሁል ጊዜ ሊዘነጋው የማይገባው የሰይጣን ቋሚ ተግባር እኛን ለመፈተን እና ከመንፈሳዊ ህይወት ለማፈናቀል ዘወትር እንቅልፍ ስሌለው በእያንዳንዳችን ላይ እንደየደካማ ጎናችን ፈተናችንን እንደሚያበዛው እና ለውድቀት የምንበቃበትን ጉድጓድ ዘወትር እንደሚቆፍርልን መዘንጋት የለብንም። የሰው ልጅ መላ ዘመኑን ለፅድቅ ስራ ከሚያሳልፈው ግዜ ይልቅ ለኅጢአት የሚያውለው ግዜ ብዙ ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር በኅጢአት ጠፍተን እንዳንቀር ተመልሰን ንስሓ እንድንገባ የሚፈቅድ አምላክ ስለሆነ ለዘመናት ከሰራነው ኅጢአት ይልቅ በተወሰነ የቀኖና ግዜ የሰራነው ፅድቅ ያንን ሁሉ ስፍር ቁጥር የሌለውን ጥፋት ፍቆ ንስሐ ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባት እንድንበቃ ታደርጋለች።
ስለዚህ፤ ጠያቂያችን ለዚህ ችግርዎ የምንመክርዎት በምክንያት ማዘግየትና ፍርሃትን ማባባስ አንዱ የሰይጣን ውግያ ስለሆነ እግዚአብሔር ደግሞ የፍርሃት አምላክ ሳይሆን የፍቅርና የሰላም አምላክ በሃጥያት የወደቀውን አይዞህ ልጄ ብሎ የሚያነሳ እና ከጠፋንበት ፈልጎ የሚያገኝ አምላክ ስለሆነ እኛም ከነፍሳችን በፊት ቅድሚያ የምንሰጠው ሌላ ጉዳይ ሊኖር ስለማይገባ የሚቃወምዎትን መንፈስ እንደምንም ታግለው ያሸንፉት። በመሰረቱ በሰው ዘንድ አዲስ የሆነ ተሰርቶ የማያውቅ ኀጢአት ከቶ አይኖርምና፥ በእርስዎም ላይ የደረሰቦትም፥ ሰው ፈፅሞት በንስኀ ህይወት ያለፈበት የኀጢአት አይነት እንደሆነ ተረድተው፤ የመዳን ቀን አሁን ስለሆነ የቀጠሮ ቀን እና ሰዓት ሳያራዝሙ ወደ ንስሐ አባት ቀርበው ፤ ንስሐአባት ከሌለዎትም በእኛ በኩል ያሉትን አባቶችን በውስጥ መስመር በማማከር የፈለገውን ያህል ከባድ ኀጥያት ሰራው ብለው ቢያምኑም እንኳ በእግዚያብሔር ዘንድ የማይፋቅ በደል የለምና አሁንም ምክንያትና ፍርሃቶትን አርቀው ወደ ይቅር ባይ አምላክ ይቅረቡ በማለት ምክራችንን እንለግሳለን።
ሌላው፥ጠያቂያችን እንዳሉት በህይወቴ ዙሪያ ሁሉ የማደርገውም ነገር ውጤታማ አይደለም ተወሳሰበብኝ ስለዚህ እግዚአብሔር ያዘነበት ወይም የተቆጣኝ ነገር አለ የሚል ሃሳብ ያለበት ጥያቄ ነው፤ በእርግጥም አንድ ክርስቲያን ማሰብ ያለበት ነገር ነው።
ሐዋሪያት እርኩስ መንፈስ ያደረበትን ሰው ባዩ ጊዜ ያንን መንፈስ ከዚያ ሰው ለማውጣት ወይም ለመለየት ባለመቻላቸው ለምንድነው እንደዚህ ያላደረግነው አሉ። ጌታም ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው ነው ያላቸው። የሰው ልጅ ትልቅ ተራራ እምነት ሳይሆን የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል እምነት ነው የተጠየቀው፤ በአይን ለማየት እንኳን በጣም የረቀቀችውና ያነሰችውን የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል እምነት ቢኖራችሁ አጋንንትን ማውጣት ትችላላችሁ ብሏል።
ስለዚህ የሰው ልጅ እየደከመ እየወጣ እየወረደ የማይሳካለት ነገር ካለ ምንድነው ይሄን ለማድረግ ያልቻልኩት ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። የዘለዓለም ህይወት እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ ያለው ያ ወጣቱ ፈሪሳዊ ባለሀብት ታሪክ ምንድነው? “እነሆም፥ አንድ ሰው ቀርቦ። መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ? አለው። እርሱም። ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው። እርሱም። የትኞችን? አለው። ኢየሱስም። አትግደል፥ አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።” (ማቴ 19፥16-19) ይሄ ማለት በኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ 20 ከቁጥር 1 ጀምሮ የተፃፈውን አስርቱ ትእዛዛት ነግሮት ይሄ መሰረት ነው አለው። ጌታም ሰው ሆኖ ሲገለጽ ያንን ሊሽር አይደለም የመጣው ሊያጸናው ነው። በደንብ ሊገልጸው ሊያብራራውና ስራ ላይ ሊያውለው ነው የመጣው። ይሄ ጎበዝ ደግሞ ፈሪሳዊ ነው፤ እብራዊ ነው፤ አይሁዳዊ ነው እነሱ ህጉን ያውቃሉ፥ በስራ ባያውሉትም በልማድ ያውቁታል፤ ጎበዙም ይሄንንማ ሁሉንም ከህጻንነቴ ጀምሬ ጠብቄዋለሁ ደግሞስ የሚጎድለኝ ምንድነው አለው። ኢየሱስም ፍፁም ልትሆን ብትወድ ሂድና ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለደሆች ስጥ ብሎ መልካም ስራ እንዲሰራ ነገረው። ስለዚህ እኛ ደክመን ጥረን ተመኝተን አስበን ያልተሳካልን ነገር ካለ ምን ስለሆን ነው? ምን ስለጎደለን ነው? ብሎ ማሰብ የእውነተኛ ክርስቲያን ጸባይ መሆን አለበት።
ስለዚህ ጠያቂያችን ክርስቲያን ሁል ጊዜ በእያንዳንዱ የስጋ ፈተና ተፈትኖ ተስፋ መቁረጥ የለበትም። እንግዲህ የሚዋጋንን ረቂቅ መንፈስ ሁሉ እኛም በረቀቀ መንፈሳዊ ጥበብ መዋጋት ነው ያለብን። ያጣነው በረከት ምንድነው? የእለት እንጀራ ነው? የአመት ልብስ ነው?፣ የእለት ጉርስ ነው? ጤና ነው? ትዳር ነው? ስልጣን ነው? እውቀት ነው? ሰላም ነው ፍቅር ነው? ብቻ ያጣነውን ነገር አለ። ያን ነገር ደግሞ ለማግኘት የሚያስችል መንፈሳዊ አቅምና ብቃት የለንም ማለት ነው? ስለዚህ ይሄን መንፈሳዊ ህይወቴን በምን ላይ ላጠንክረው በምን ላይ ላሳድገውና ይሄንን በረከት ይሄንን ጸጋዬን እንዳላገኝ የሚታገለኝን ጠላቴን እርኩስ መንፈስን ታግዬው አሸንፈዋለሁ። በዚህ አለምም ላይ እኮ ጠላትነትን ለመታገል የተሻለ ዝግጅትና አቅም ወይም ጉልበትና ትጥቅ ሊኖረን ይገባል። ስለዚህ የእኛ ዝግጅት ከጠላት ዝግጅት/አቅም በላይ ከሆነ ነው እንግዲህ ታግለን እንደምናሸንፍ እርግጠኛ የምንሆነው። መንፈሳዊ አቅማችን ከዚያ የደከመና የቀጨጨ ከሆነ ግን ለውጥ አይመጣም።
ስለዚህ ጠያቂያችን እርስዎን ሰላም ካጡበት መንፈስ ይወጡ ዘንድ ምናልባት በአደባባይ የማይናገሩት ፈተና ካለ እኛን በውስጥ መስመር ሲያገኙን ከሚነግሩን ሃሳብ ተነስተን ምን ማድረግ እንዳለብዎት ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክር እንሰጥዎታለን ፤ ዋናው ነገር አብዝተን ስንጸልይ፣ ስንፆም፣ ስንሰግድ፣ በቃሉ ስንፀና፣ መንፈሳዊ አገልግሎት ስናደርግ እግዚአብሔርም አብዝቶ ይባርከናል፥ ይጠብቀናል።
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንም ሼር ያድርጉ፡- https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፡- በ In box ወይም በውስጥ መስመር ያወራሁዎት ፈርቼ ነው፣ እና በጣም ኃጢአተኛ ነኝ፣ እናም ንስሐ ልገባ ብየ ኃጢአቴን ሳስበው ለንስሐ እንኳን ምን ብዬ እናገራለሁ? ብየ በጣም አፍራለሁ፣ ከዛሬ 4 ዓመት በፊት ምንም ባለማወቅ እና በስሜት በመገፋፋት ከወንድ ጋር የማይሆን ነገር አድርጌያለሁ፣ ግን ልጅ ነበርኩ ድንገት ነው የሆነው ልክ አንደ ጨዋታ፣ እና አሁን ግን ጓደኛ አለኝ፣ ማለትም ፍቅረኛ ግን ያ ነገር ከአይምሮዬ ሊጠፋ አልቻለም ጭንቀት ውስጥ ነኝ፣ ንስሐ ልገባ አስብና እሱን ሳስበው በጣም አፍራለሁ፡-
👉🏾 ስለ #ንስሐ እና #ኑዛዜ መፍራት
✍መልስ፡- ጠያቂችን ንስሐ መግባት ማለት ምን ማለት ነው? የመጀመሪያ ትልቁ መሠረት ኃጢአትን ማመን ነው፣ ኃጢአተኛ ነኝ ብሎ ማመን ነው፣ ፈርቻለሁ ይባላል እንዴ? ሰው ኃጢአት ሲሠራ ሳይፈራ፣ ንስሐ ገብቶ ለመዳን እንዴት ፈርቻለሁ ይባላል? በሐዋርያት ሥራ ምእራፍ 5 ቁጥር 1 ጀምሮ ተመልከቱ፣ ሐናንያ እስከ ባለቤቱ ድረስ በቅዱስ ጴጥሮስ ፊት የማይገባ ገነር አድርገው፣ የማይገባ ወሬ አውርተው ተቀስፈው ሞተዋል፡፡
ግማሹን ኃጢአት ሸሽጎ፣ ግማሹን ኃጢአት ተናገረው፤ ይሔ ኃጢአታቸው የነበረው መሬታቸውን ሸጠው የተወሰነ ገንዘብ አስቀመጡና ግማሹን ይዘው ወደ ሐዋርያት ማኅበር ለመቀላቀል መጡ፣ በዚያን ሰዓት ይሔ ማኅበር ሊፈርስ ስለሚችል አይታወቅም ነገ ቢፈርስ አሉና ግማሹን አስቀመጡ፣ ግማሹን ይዘው መጡ፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ ይሔ ብቻ ነው ወይ? ብሎ ቢጠይቃቸው አዎ የለንም ነው ያሉት፣ ግን እኮ አለ፣ እኔን አይደለም ያታለላችሁት፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ነው፣ ይፍረድባችሁ አላቸው ወዲውኑ በየተራ ባልና ሚስቱ እንደሞቱ እናያለን፡፡
ስለዚህ ካሕንን ሸሽጎ፣ መምሕርን ሸሽጎ፣ የላይ የላይ ብቻ፣ ማውራት ለመዳን ያልፈለገ አካል ነው ማለት ነው፣ ራሱ አቆራርጦ ማስቀረት ኃጢአት ነው ተገቢ አይደለም፣ በካሕኑ አድሮ የሚኖረው እግዚአብሔር ነው፣ እግዚአብሔር ደግሞ ሁሉን የሚያውቅ ነው፣ ሁሉን የሚያውቀውን ደግሞ አናታልለውም፡፡
ካልተናገርን አንድንም ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 8 ቁጥር 4 ላይ ሂድ ራስህን ለካሕን አስመርምር ተብሎ ተጽፏል፣ የእግዚአብሔር ቃል ነው፣ የማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 28 ቁጥር 20 ላይ እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ከእናንተ ጋ እኖራለሁ ብሏል እግዚአብሔር ለካሕኑ ኃጢአታችን ስንናገር ለእግዚአብሔር ነው የምንናገረው ስለዚህ ይሔንን ማመን አለብን፡፡
ኃጢአት አይደበቅም፣ አይቀነስም ከሥሩ፣ ከእውነት ነው የሚነገረው፣ ከበደኝ፣ ፈራሁ አይባልም ኃጢአት ስንሰራ ሳንፈራ በመናዘዛችን፣ ንስሐ በመግባታችን መዳን ነው ያለው፣ ሰው በኃጢአት ሲሞት ደስ እያለው፤ በንስሐ ሲድን ለምንድን ነው የሚፈራው፣ ሰይጣን ወይም በአካላችን ውስጥ ያደረ እርኩስ መንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር እንዳንገናኝ ነው እንጂ፣ ኃጢአት ስንሠራ ነው መፍራት፣ ማፈር ያለብን፣ ንስሐ ስንገባ እየዳንን ነው፡፡
ስለዚህ ከ አራት አምስት ኣመት በፊት ኃጢአትን ተሸክሞ መኖር ራሱ ኃጢአት ነው፣ የማይገባን በማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 6 ቁጥር 34 ላይ “ለነገ አትበሉ”፣ ይሔ ማለት በሰማያዊ አነጋገር ነገ ምን እበላለሁ፣ እጠጣለሁ ብላችሁ አትጨነቁ ነው የእለቱን ተመገቡ፣ ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ይመግባችኋል ማለት ነው፡፡
ሚስጥሩ ምን ማለት ነው ኃጢአታችሁን ለነገ እንናዘዛለን፣ ነገ ንስሐ እንገባለን እያላችሁ አታውሉ፣ አታሳድሩ፣ ነገ ምን እንደሚሆን አታውቁም ማለት ነው፣ ስለዚህ አራት፣ አምስት ኣመት በኃጢአት ታስሮ መኖር በጣም እጅግ ከባድ ነው፣ አሁንም ቢሆን እግዚአብሔር ወዳጆች፣ በእውነት እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተም እግዚአብሔርን የምትወዱት ኃጢአተኛ በመሆን እግዚአብሔር ይጠላኛል ብላችሁ አታስቡ፣ ኃጢአታችሁን ለነገ እያላችሁ አታውሉ፣ አታሳድሩ ከሞት በኋላ፣ ነፍስና ሥጋ ከተለያዩ በኋላ ንስሐ ገብቼ ልዳን የሚባል ነገር የለም፤ ይሔንን እድል አሁን ነው መጠቀም ያለባችሁ፡፡
ፍቅረኛ አለኝ ብለዋል፣ ይሔ እንደ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምሕሮ ትክክል አይደለም ስህተት ነው፣ ከጋብቻ በፊት ወንድም ሴትም መገናኘት የለባቸውም፣ ይሔን ጓደኛ ያሉት ነገር በፍቃደ እግዚአብሔር ሳይሆን፣ ቤተሰብ ሳይፈቅድ ጓደኝነት ትጀምሩና ያን ፍቅር ያልቅና ነገ ሌላ ነገር ይከሰታል፡፡
ስለዚህ ጓደኛ አለኝ፣ ፍቅረኛ አለኝ ማለት በራሱ ይሔ ሁሉ ንስሐ ያስፈልገዋል፣ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ሳይሆን፣ ከእናት ከአባት ፍቃድ ሳይሆን ይደረግና፣ ጓደኝነት ትጀምሩና ያ ፍቅር ያልቅና ነገ ሌላ ችግር ፈተና ነው የሚያመጣው፣ ትክክል አይደለም፤ ኃጢአቴ በዝቶብኝ ነው፣ ኃጢአተኛ ሆኜ ነው ብለው ደግሞ ኃጢአት ስለበዛ ስንቱ ኃጢአቴ ተዘርዝሮ ያልቃል እያሉ የሚጨነቁ ሰዎች አሉ፡፡
እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ብሎ ተናግሯል የማቴዎስ ወንጌል ምዕረፍ 11 ቁጥር 28 ላይ እናንተ ሸከምችሁ የከበደባችሁ ኑ ወደ እኔ በኃጢአት የታሠራችሁ፣ የኃጢአት ሸክም ተሸከማችሁ፣ እናንተ ኑ ወደ እኔ ለነፍሳችሁ እረፍትን አደርግላችኋለሁ ይላል፣ በእውነት በኃጢአት ማሰሪያ የታሠሩትን እግዚአብሔር አምላክ ይድረስላቸው፣ በንስሐ ከታሰሩበት እንዲፈቱ አግዚአብሔር አምላክ ልቦናቸውን ያብራላቸው፡፡
እናንተ የኃጢአት ሸክም የከበደባችሁ ኑ ወደ እኔ አሳርፋችኋለሁ፣ እኔ ትሁት ነኝ ከእኔም ተማሩ፣ ልቤም ቅን ነው ይላል፣ ስለዚህ እግዚአብሔር መሐሪ ነው፣ እግዚአብሔር ይቅር ባይ ነው፣ ኃጢአት ስለበዛ እግዚአብሔር የማያድነን አይምሰለን ፣ ሰይጣን ንስሐ መግባትና በንስሐ አይመለስም አንጂ እሱንም ቢሆን እኮ ይምራል፡፡
ስለ ክርስቶስ ሠምራ ታስታውሳላችሁ እግዚአብሔርን አንድ ጥያቄ ጠየቀቸው እግዚአብሔር እባክህ ሰይጣንን ማርልኝ? አለችው ሰይጣን ሰውን ሁሉ እያሳሳተ ከእግዚአብሔር እየለየ ስለሆነ እባክህ የአዳም ልጅ ሆነ፣ ሁሉ እንዳይሳሳት እባክህ ሰይጣንን ማርልኝ አለችው፣ እግዚአብሔርም የሚማር ከሆነ ንስሐ የሚገባ ከሆነ እሺ ነው ያለው ሰይጣን ግን ንስሐ መግባት አይፈልግም፡፡
አሁን ንስሐ የማይገባ ሰው እንደ ሰይጣን ነው ማለት ነው፣ ሥጋ የለበሰ ሰይጣን እየሆነ ነው ማለት ነው፣ መጥፎ ሥራ ብዙ የተለያየ ኃጢአት እንኳን ቢሰራ ንስሐ የሚገባ ሰው እንደ አዳም ይመስላል፣ ስለዚህ የእግዚአብሔር ወዳጆች ኃጢአታችን ስለበዛ የሚጥለን አይመስለንም፡፡
ንስሐ መግባት የሚያስፈልገው ለኃጢአተኛ ነው፣ የማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ 9 ቁጥር 13 ላይ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጥአን ጋር እየተመገበ በነበረ ሰዓት ሌሎች ፈሪሳውያን መጡና ደቀ መዝሙራቸውን ይበላል፣ ይጠጣል ብለው ኃጢአተኞች እነሱ ስለሚፀየፉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለው ግን፣ በሽተኞች ባለ መድኃኒቱን ይፈልጉታል፣ ጤነኞች ግን አይፈልጉትም፣ እናንተ ጤነኛ ነኝ የምትሉ፣ ኃጢአት የለብንም ለምትሉ ለእናንተ እኔ አላስፈልጋችሁም፣ ኃጢአተኞች ለሆኑ ለእነሱ ግን እኔ አስፈልጋቸዋለሁ ነው ያለው፡፡
እኔ ወደ እዚህ ዓለም የመጣሁት ኃጥአንን ወደ ንስሐ ልጠራ ነው እንጂ፣ ፃድቃንን አደደለም ብሏል፣ ክርስቶስም ሰው የሆነው በዓለም ላይ ኃጢአት ስለበዛ ነው፣ እንጂ ኃጢአቴ በዝቶብኝ፣ ስንቱን አውርቼው አንበል፣ እግዚአብሔር መሐሪ ነው የእኛ ድርሻ፣ የሚጠበቅብን አምነን መናዘዝ ነው፡፡
(ቀጣይ ክፍል) 👆👇
ስለዚህ የእግዚአብሔር ወዳጆች በያላችሁበት እንዳንዳችን ከኃጢአት ማሠሪያ ማዳን ይጠበቅብናል፣ ንስሐ መግባት ይጠበቅብናል፣ ከሞት በኋላ፤ ነፍስና ሥጋ ከተለያዩ በኋላ ንስሐ ገብቶ መዳን የለም፣ መዋል ማደር የለብንም፣ ነገ የሚሆነውን እኛ ስለማናውቅ፣ ለነገ አትበሉ ተብሎ ነው የተጻፈው እንጂ እያመካኘኝ እንዳንጎዳ ሁላችሁም የዚህ ግሩፕ አባሎችና የእግዚአብሔር ወዳጆች በኃጢአት የወደቅን ሰዎች ራሳችንን በንስሐ አንፅተን ሥጋወ ደሙን ተቀብለን መንግሥተ ሰማያት እንድንወርስ እግዚአብሔር ይርዳን ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉 ጥያቄ ፦ ኀጢአቴን ሳስበው በጣም #እፈራለሁ #አለቅሳለሁ ግን ደግሞ ወደ አባቶች ቀርቤ #ንስሐ ለመቀበል አልቻልኩም እግሬን የሚይዘኝ ነገር አለ። ከወሰንኩ በኋላ እቀራለሁ ። እባካችሁ ምን ላድርግ? ጨንቆኛል
መልስ፦ሰው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው። ግን ሰው የእግዚአብሔር ማደርያ የሚሆነው ከበደል ከኀጢአት ነፃ ሲሆን ነው በበደል በኀጢአት ከወደቀ የዲያብሎስ ማደርያ ነው የሚሆነው። የዲያብሎስ ማደርያ ከሆነ ደግሞ መልካም ነገርን አያስብም። ሰው ግን እንደምንም ብሎ ከካህን ለመድረስ ፣ ከካህን ደርሶ ንስሐ ለመቀበል መዘጋጀት አለበት። ለካህን የተሰጠው ስልጣን አለ። በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል ይላልና። ምክንያቱም ካህን የእግዚአብሔርና የሰው ሽማግሌ ነው፤ በመካከል ተገኝቶ ለንስሐ ልጆቹ ንስሐ ሰጥቶ ቀኖና አድርጎ እግዚአብሔርን ይቅርታ ጠይቆ አስካለ ማርያምን፣ ገብረ ማርያምን ማርልኝ ብሎ ከእግዚአብሔር ጋር በተሰጠው ስልጣን ቀኖናቸውን ሲጨርሱ እግዚአብሔር ይፍታህ ይላቸዋል ያኔ በ40 ቀን በ80 ቀን ተሰጥቷቸው የነበረ ልጅነት በኀጢአት ተወስዶባቸው የነበገረው ልጅነት ይመለስላቸዋል ማለት ነው። ይሄን እንዳያደርጉ ደግሞ ዲያብሎስ የእሱ ማደርያ ሆነው እንዲቆዩ ስለሚፈልግ በመንገዳችን እንቅፋት እያስቀመጠ የቻለውን ይጥራል። ሰው ግን እንደምንም ብሎ ከካህን መድረስ አለበት፣ ካህን ማግኘት አለበት፣ በንስሐ ሳሙና መታጠብ አለበት ማለት ነው።
ስለዚህ ጠያቂያችን፤ አሁንም የምንመክርዎት የቀጠሮ ቀን እና ሰዓት ሳያራዝሙ ይመክረኛል ያስተምረኛል ያሉትን የንስሓ አባት የሚሆን ካህን በአካባቢዎ ካሉ ይያዙ፤ በአከባቢዎ ማግኘት የማይችሉ ከሆነ በራስዎትም ሆነ በሚያምኑት ሰው በኩል ያገኙዋቸውን እውነተኛ ካህን በርቀትም ቢሆን ይያዙ፤ ወይም ደግሞ በእኛ በኩል በህይወታቸው ምሳሌ ይሆናሉ ብለን ለአባትነት የመረጥናቸው የቤተክርስቲያን አባቶች በሃይማኖታቸውና በእውቀታቸው የታመነባቸው አባቶች ስላሉ በድረገፃችን ላይ ባለው ቁጥር ወይም ደግሞ በውስጥ መስመር በሚላክልዎ ቁጥር ደውለው የሚያገኟቸውን አባት አነጋግረው ንስኀዎን መፈጸም እንዲሁም ንስሐ አባት በማድረግ መያዝ ወይም ማንኛውንም መንፈሳዊ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፡- ሰላም አባታችን እኔ የ 19 ኣመት ወጣት ነኝ፣ በዓለማዊ ሕይወቴ ተማሪ ነኝ፣ በመንፈሳዊ ሕይወቴ ደግሞ የዲቁና ተማሪ ነኝ፣ አሁን በቅርቡ ስልጣነ ክሕነት እንደሚሰጠኝ መምሕሬ ነግረውኝ ነበረ፣ ግን በጣም በድያለሁ፣ ብዙ ኃጢያት ሠርቻለሁ ንስሐ ከዚህ በፊት ገብቼ ነበር፣ ግን ሕሊናዬን በጣም ስለሚያስጨንቀኝ ኃጢአት እንዳላስረዳቸውም ንስሐ የሰጡኝ አባት ዘመን አመጣሽ ኃጢአቶችን አያውቁም በዚያ ላይ ደግሞ በጣም ፈራሁ፣ አፈርኩ ከእንስሳትም ያነስኩ ሰው ስለሆንኩ፣ ቆሻሻ መሆኔን ሰዎች ሲያውቁኝ ይፀየፉኛል ብዬ ፈራሁ፣ ኃጢአቴ እጅግ ከባድ ነው፣ ሰምተው ያውቁ እንደሆን ሆኜ ፈራሁ ምን ላድርግ? ግን ንስሐ መግባት እፈልጋለሁ፣ ንስሐ መግባት አለብኝ፣ ምክንያቱም ሥልጣነ ክሕነት ያለ ንስሐ ከዚያ ሥጋ ወደሙ አይገባኝም እባክዎትን ምን ላድርግ ተቸገርኩኝ?
👉🏾ስለ #ንስሐ #ህይወት
✍መልስ፡- ጠያቂያችን ስለ ንስሐ ሕይወት ምክር እንድንሰጣቸው ነው የጠየቁን ወደ ንስሐ ሕይወት መቅረብ እንዳለብዎት አብዝተን በጣም እንመክርዎታለን፣ አሁን ይሔ ነው ብሎ እርስዎን የሚያርቅ ነገር ወይም የሚያቀርብ ነገር ወስኖ መናገር አይቻልም፣ የዲቁና ትምሕርት መማርዎት ጥሩ ነው፣ ለመቀበልም መዘጋጀትዎት መልካም ነው፡፡
ደግሞ ለበረከትና ለመንፈሳዊ አገልግሎት፣ ለመንፈሳዊ ክብር የፈለግነው ዲቁና ደግሞ ለኃጢአትና ለመርገም እንዳይሆንብን እንደሉትም ኃጢአተኛ ሆነን በድፍረት መወሰድ የለበትም፡፡ ስለዚሀ የእርስዎ ነገርም ከቤተክርስቲያን ቀኖና አንፃርም የሚገባውን ልንነግርዎት የምንችለው ሲያገኙንና በዝርዝር ሁኔታውን ሲያማክሩን ነው፡፡
ልንገናኝ የምንችልበትን ነገር ራስዎት ያመቻቹ ማለት ነው፣ ለሁሉም በምንሰጠው አድራሻችን አለ በእሱ ያግኙን፣ እንዳሉትም እግዚአብሔር ከፈተና የሚጠብቅ አምላክ ስለሆነ ወደ በለጠ ፈተናና ስህተት ከመግባታችን በፊት ከተኛኝበት፣ ካንቀላፋንበት ወይም ከደነዘዝንበት ወይም ልባችን ከደነደነበት ሕይወት ውስጥ አንቅቶ የንስሐ ጥሪ ሲደርሰን አሁን ደግሞ ሌላ ስህተት ላለመፈጸም የሚገባንን ሁሉ ማድረግ ይገልባል፡፡
ስለዚሀ እርስዎም እግዚአብሔር ከፈቀደ እኛንም ማግኘትዎ ካልቀረ የምንረዳዎት 19 ዓመቴ ነው ብለዋል፣ እስከዚህ ድረስ በኃጢያት ቆይቻለሁ የሚሉት የንስሐ ሕይወት ምን እንደሚመስል፣ ወደ ፈተና እንዳይገቡ፣ እንዳሉትም ደግሞ አንደኛ ፣ሚስጥሩን የማይችሉ ሰዎች፣ ሁለተኛ ደግሞ ዘመን አመጣሹ ኃጢአት፣ ስሙን እና ትርጉሙን ሁሉ አባቶች ለማወቅ እንደሚቸገሩበት እርስዎም አምነዋል፣ እውነትም ነው፡፡
አንዳንዴ ይሔ እኛ ዛሬ የምንጋራው የኃጢአት ዓይነት በስሙም አስፀያፊ ስለሆነ አባቶችም ይከብዳቸዋል፣ ግን መቸም ሰው እስከሠራው ድረስ ደግሞ በመፀየፍ ብቻ ሰውን ፃድቅ አናደርግም፣ በመቀየም፣ በማኩረፍ፣ አትንግረኝ በማለት፣ አትቅረበኝ በማለት አትናዘዝ በማለት፣ ሰውን ፃዲቅ ልናደርገው አንችልም፡፡
እንዲህ ዓይነት ፈተና ወደ ሰው እንዳይመጣ አጥብቀን መጸለይ አጥብቀን ማስተማር ነው፣ መምከር ነው፣ ከመጣ በኋላ ደግሞ የግድ አበድንበትም፣ ሠከርንበትም የግድ ለንስሐ ሕይወት እንዲቀርብ ነው ያለብን ኃላፊነት፡፡ እኛንም የቤተክርስቲያን አባቶችም ከኃጢአት ተጠያቂ ስለሚያደርገን፣ለምን ዝም አላችሁ? ለምን መንጋውን ወደ ኃጢአት ሲሔድ አልሰበሰባችሁም አልጠበቃችሁም? የሚል ጥያቄ አለ፡፡
ምእመናንም በእረኞቹ ወይም ደግሞ በአባቶቻቸው ምክርና ተግሣፅ ለመኖር፣ ከእነሱ ጥበቃ ላለመውጣት ደግሞ በእነሱ በኩል የሚጠበቀውን ነገር ሁሉ ማድረግ አለባቸው፣ ስለዚህ ጠያቂያችን ዝም ብለው በመፍራት፣ በመስጋት፣ በመራቅ እንዲህ እያሉ ደግሞ አሁንም ከሚያውቁት በላይ ሌላ ኃጢአት መጥቶ፣ ሌላ ፈተና መጥቶ ከእግዚአብሔር ጋር እንዳይጣሉ አስቀድመን እንዳልነው እኛን በአድራሻችን ያግኙን ያን ጊዜ ትንሽ ዘርዘር ያለ ነገር እንነጋገራለን፡፡
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፦ ንስሐ መግባት ፈልጌ አባቴን ፈራኋቸው። ሌላ ቄስ ጋር ብገባ አይፈቀድም ወይ?
መልስ፤ ጠያቂያችን፤ በመሰረቱ በሰው ዘንድ አዲስ የሆነ ተሰርቶ የማያውቅ ኀጢአት ከቶ አይኖርምና፥ እርስዎም ተፈተንኩበት ያሉት ከባድ ጥፋት ፥ ሰው ፈፅሞት በንስኀ ህይወት ያለፈበት የኀጢአት አይነት እንደሆነ መገንዘብ አለቦት።
ንስሐ አባትን በሚመለከት ለገለጹት፥ በሰራነው ኀጢአት አፍረን እና ተሸማቀን ክብራችን እንዳይነካ ለመሰወር እና ጥፋታችንን ለመደበቅ የምናደርገው ስጋዊ አስተሳሰብ ካለ ሰውን ብናሞኝ እግዚአብሔርን ማታለል ስለማንችል የዚህ አይነት አካሄድ ከእውነተኛ ክርስቲያን የማይጠበቅ ተግባር ነው። ከዚህ ውጭ በሆነ በቀና መንፈስ ከሆነ ግን በደረስንበት መንፈሳዊ ቦታ ሁሉ እውነተኛ የቤተክርስቲያን አባቶችን በማነጋገር የዋለው ኀጢአታችን እንዳያድርብን ያደረውም እንዳይውልብን በጊዜውም ያለጊዜውም በአባቶች ጥበቃ የንስሓ ህይወት መኖር ከሁሉም ክርስቲያን ይጠበቃል። ለጠያቂያችንም ሆነ ለሌላው ሁሉ ምክር የምንሰጠው ምናልባት የሰራነውን ኀጢአት ሁሉ ለመደበኛ የንስሓ አባታችን ለመናዘዝ የምናፍርበት ወይም ካህኑንም የምንጠራጠራቸው ነገር ካለ ስርአታዊ መንገድ ተጠቅመን በመንፈሳዊ ጥበብና በትህትና ሁነን ተሰናብተን ፤ ሳንጠራጠር ከልብ የምናምናቸውን ሌላ አባት መርጠን መያዝ ይገባናል። አንዳንዶቻችን ለራሳችን ደህንነትም ሆነ ለማህበራዊ ግንኙነታችን ችግር የሚያመጣብን ቢሆን እንኳን እጅግ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድና አስፈላጊም ከሆነ ወደሌላ ቅዱስ ቦታ ራቅ ብለን በመሄድ ለቤተክርስቲያን አባቶች መናዘዝና ንስኅችንን ማከናወን ይገባናል። እኛም በዚህ ፕሮግራም ሰዎች ይድኑ ዘንድ በተቻለን መጠን ስለናንተ የምናደርገው ጥረትና የምንሰጠው መንፈሳዊ አገልግሎት ከዚህ የተነሳ ስለሆነ የእያንዳንዳንዳችሁንም የውስጥ ችግር በሃሳብም ቢሆን ስለምንረዳችሁ ምናልባት ለንስኅ አባት ለመንገር የሚያስፈራችሁና የሚያሰጋችሁ በቂ ምክንያት ካለ እኛንም በውስጥ መስመር አግኝታችሁ ብታሳውቁን መፍትሄ እንሰጣችኋለን። ይህን የምንልበት ምክንያት ብዙዎቹ ምእመናን ለንስሓ አባቶቻቸው ግልፅ ሆነው የሰሩትን በደል ለመንገር የማይችሉበት ዋናው ምክንያት ምስጢር ይባክንብናል ብለው ከነኀጢአታቸው የሚኖሩ አሉና፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ለአባቶቻቸው ግልፅ ለመሆን በአካባቢያቸው በማህበራዊ ህይወት ከመንፈሳዊ አባቶቻቸው ጋር አብረው ስለሚኖሩ የመተፋፈርም ነገር ስለሚያጋጥማቸው በዚህም ምክንያት የሚሳቀቁ ምእመናን እንዳሉ መረጃው ስላለን፤ ከዚህ ሁሉ ስጋት ነፃ ለመሆን የሚያምኑበትን እና የማይጠራጠሩበትን አባት መያዝ እንደሚገባቸው በአፅንዎት እንመክራለን። ለዘላለማዊ የነፍስ ድህነት ጉዳይ የምንሰራውና የምናደርገው ተጋድሎ በስጋዊ አመለካከት ወይም ምድራዊ በሆነ አሰራር የምንኖረው ሂደት ስላልሆነ ልዩ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።
👉ጥያቄ፡- ንስሐ ለመግባት እፈልጋለሁ፣ እመኛለሁ ግን አልቻልኩም፣ አንድ ቀን ደፍሬ ወደ ንስሐ ሕይወት እንድቀርብ ምን ማድረግ አለብኝ? እንዴትስ ትመክሩኛላችሁ?
መልስ፡- ጠያቂያችን እንዳሉት በእውነትም ምክር ሚያስፈልገው ነገር ነው፣ የሁሉም ሰው ችግር ይሔው ነው፡፡ በእያንዳንዷ ጥፋታችን በእኛ አይምሮ ላይ የሚደውል፣ የሚያቃጭል፣ አትሥራው፣ አታድርገው፣ የሚለንና ያንን ጥፋት ከፈፀምነው በኋላ ደግሞ ዛሬ ስህተት ሠርተሃል፣ኃጢያት ሠርተሃል፣ በደል ፈፅመሃል፣ የሚለን በውስጣችን የእግዚአብሔር መንፈስ አለ፡፡ እውነቱን የሚመሰክርብን ማለት ነው፣ ያኔ በእኛ አይምሮ ውስጥ ደግሞ እኔ በድየለሁ፣ አጥፍቻለሁ፣ ፈጣሪዬን ኣሳዝኛለሁ፣ አስቀይሜያለሁ፣ ራሴንም ደግሞ በኃጢያት አርክሼዋሁ፣ ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ፣ ወደ ንስሐ ለመቅረብ ብዙ የተዘጉ በሮች አሉ፡፡
አቅጣጫው መንገዱ በየት እንደሆነ ሁሉ የሚጠፋብን አለ፣ ለንስሐ ሕይወት አርባ ክንድ፣ የራቅን ሰዎች ሁሉ አለን፤ እርግጥ የንስሐ አባት ይኖረናል፣ ለስሙ ክርስትና ይኖረናል፣ ግን በዓላማው በሕይወቱ ውስጥ አንድም ቀን ተጉዘንበት፣ አልፈንበት ስለማናውቅ፤ እጅግ በጣም ሩቅ ነን፡፡
የንስሐ ሕይወት የሚባለው ነገር በጣም ጨልሞ የሚታየን፣ ርቆ የሚታየን፣ ከብዶ የሚታየን ፣ አባቶቻችንን ቀረብ ብሎ ያለንን ችግር ከወለዱን ወላጆቻችን፣ ቤተሰቦቻችን በጣም ይቀርቡናል ከምላቸው፣ ችግራችንን ይረዱናል ከምንላቸው ቤተሰቦቻችን፣ ወዳጆቻችን በላይ ለእኛ ቅርብ የሚሆኑ፣ የሚያዝኑ፣ የሚያፈቅሩን፣ ሚስጥራችንን የሚሸከሙ፣ የንስሐ አባት የምንላቸው ወይም ደግሞ የንስሐ አባትም ሳይሆኑ የቤተ ክርስቲያን አስተማሪዎች መካሪዎች፣ አባቶች እንደሆኑ የማንረዳ ብዙ ሰዎች አለን፡፡
ወደ ካሕን ሄዶ በምክረ ካሕን፣ በተግሣፀ ካሕን ሕይወታችንን ማተካከል ነገሩ ሁሉ ያከብድብናል፡፡ ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ፣ ፍርድ ቤት ሄዶ እንደመቆም የምንቆጥር ሰዎች አለን፡፡ የገባቸው ክርስቲያኖቸ ደግሞ ምድርን የሞላ ኃጢያት ያለው ሰው የበዛባት ምድር ላይ ፤ አንዳንዶቹ መንገድ ላይ የገጠማቸውን መሰናክል እንኳን ለአባቶቻቸው ይናገራሉ፡፡ በዚህ በእኛ ፕሮግራም እንኳን በጣም ጥቃቅንናኛ ቀላል የሆኑ ነገሮችን፣ አጥፍቼ ይሆን፣ በድዬ ይሆን ብለው ሁሉ እኛን ያማክሩናል፣ ለንስሐ ሕይወት ቅርብ የሆኑ ሰዎች፣ ይሔን ያህል ቀላል ነው፣ እንዲያውም ለእነሱ የሚከብዳቸው ወደ ንስሐ ሕይወት የማይቀርቡበት፣ አባት አግኝተው፣ ምክር የማይቀበሉበት፣ ተግሣፅ ምክር ወደ ንስሐ ሕይወት ቀርቦ፣ ለአባት ተናዝዞ፣ እረፍትን ማግኘት ነው፡፡
በቀኖና መኖር ማለት እኮ፤ መቶ ኪሎ ጤፍ ተሸክሞ፣ ወገቡ ጎብጦ የነበረ ሰው ያንን ሸክሙን ከላዩ ላይ አውርዶ የመጣል ያህል ነው፡፡ ያን አውርዶ በጣለ ጊዜ የሚሰማው እፎይታ ያን ያህል ነው፣ ያ ማለት ነው የንስሐ ሕይወት፤ እኛ ራሳችን አጣጥመነው የሠራነውን ኃጢያት ያለምንም ከልካይ ፣ ያለምንም ገደብ፣ እንደፈለግነው የሠራነውን ኃጢያት፣ ከእኛ የሚጠበቀው በፍፁም ልቦና ተፀፅተን መመለስ ብቻ ነው፡፡
ስለሠራነው፣ ስለምናውቀው በደላችን፣ ኃጥያታችን፣ ይቅርና ባልሠራነው፣ ባልፈፀምነው፣ ባላየነው፣ ባልሰማነው ነገር ዓለም ይወነጅለን የለም እንዴ? በሐሰት ምስክር ተመስክሮብን ያለ ኃጢያታችን ወደእስር ቤት እንገባ የለም እንዴ? እግዚአብሔር ግን እንዲህ ዓይነት የተሳሳተ ዳኝነት አይሰጥም፡፡
ዘማዊ ከሆንክ ዘማዊነትህን፣ አንድ ጊዜ መዘሞት፣ ሁለት ጊዜ መዘሞት፣ ይሔን ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ስህተት ሆኖ እግዚአብሔር አንድም ቀን፤ አንዳንዶቻችን አዳልቶ፣ ጠልቶን አይፈርድብንም፡፡ በዝሙት ኃጢያት የወደቁትን ሰዎች አንድ ጊዜ ዘሙተሃል፣ ሁለት ጊዜ ዘሙተሃል፣ ይሄ ኃጢያትህ ቀላል ነው፣ ይሄ ከባድ ነው፤ አይለንም፤ በእሱ ዘንድ ምስክር አያስፈልግም፣ ማስረጃ አያስፈልግም፣ መረጃ አያስፈልግም ሁሉን አጥርቶ የሚፈርድ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡
ሌሎቹ የኃጢያቶች ዓይነት ብንሠራ፣ ብዙ ያልታመንንበት፣ እግዚአብሔርን ያሳዘንንበት ኃጢያታችን፣ በእውነተኛ ፣ በፍትሐዊነት ዳኝነት የሚሰጥ አምላክ ስለሆነ፤ እሱም ደግሞ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያለ እውነተኛ ዳኝነት የምናገኘው እንዳልነውም ወደ ንስሐ አባት ቀርቦ መሸፋፈን፣ መተፋፈር፣ መሸማቀቅ ሳይሆን ግልፅ አድርጎ ሸክማችንን ማውረድ ያስፈልጋል፡፡
ስለዚህ እርስዎ ጥሩ ምኞት አድሮቦታል፤ ጥሩ ፍላጎት አለዎት፣ ግን ደግሞ የሚያዘገይዎት መንፈስ አለ፣ አሁን እርስዎ ለጊዜው እያፈሩ፣እየፈሩ፣ እየተሳቀቁ፣ ጊዜ እያጡ፣ ልማድ ስለሌለዎት ይመስልዎታል፣ ነገር ግን “አጅሬው ነው” በዓላማ የያዝዎት፤ ሁል ጊዜ ከኃጢያታችን ጋር እንድንኖር የሚያራዝም፣ ከዚህ በላይ ደግሞ ልቦናችንን እያደነደነ፣ ከነአካቴው ቢቀርስ ብለን እንድንተውለት የሚያዘገየን ነገሮችን የሚያረሳሳን እሱ ነው፡፡
ጠያቂያችን እኛን ከፈለጉንም በውስጥ አድራሻችን ደውለው ጊዜ ሳይሰጡት፣ የዋለው ሳያድር፣ ያደረው ሳይውል፣ ንስሐ ለመግባት የተዘጋጀ ሕይወት ነገ እንዲኖርዎት፣ ሌሎቹ በጣም ጥንቁቅና፣ ብልህ የሆኑ ክርስቲያኖች የሚያደርጉት አለ፤ እንደ መጽሐፉ እንደ ሕጉ ትዕዛዝ ማለት ነው ፡፡ከማንኛውም ጋር ጠብ ክርክር ቢኖርብን፣ በግላችን የሠራነው ኃጢያት ቢኖር ነው፣ ፀሐይ ሳይገባባችሁ ኃጢያታችሁን፣ በደላችሁን አስወግዱ ነው የተባልነው፡፡ ስለዚህ ቶሎ መቅረብ ስለሚገባዎት፣ የተቸገሩበት ዋና እንቅፋት ምን እንደሆነ ሁሉ ተጨማሪ ምክር እንሰጥዎታለን፡፡ ይሄ ጾም የንስሐ ጊዜ ስለሆነ ይሔንን ሐሳብ፣ ይሔንን ምክር ለሌሎች ሁሉ እንዲጠቅማቸው አድርሷቸው፣ በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን፡፡
ለተጨማሪ ግንዛቤ ከዚህ በፊት ያስተላለፈውን ትምህርት እንደሚከተለው ልከናልና ሊንኮቹን ተጭነው ይመልከቱ።👇👇👇
https://t.me/c/1172495782/34692
https://t.me/c/1172495782/31899
https://t.me/c/1172495782/30262
በዚህ ጥያቄ ምክንያት የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q