ስለ ፀበል እና ጥምቀት

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!" (ማቴ 3: 1-2)

ተከታታይ ትምህርትና ለጥያቄዎት ምላሽ ለማግኘት ቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

ስለ ፀበል እና ጥምቀት

ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች​

ከዚህ በፊት ለተመሳሳይ ጥያቄ የተሰጠ ምላሽ፦
 
መልስ፦ 40 እና 80 ቀን ላልሞላቸው ህፃናት ጠያቂያችን እንዳሉት ለሞት የሚያበቃ ህማም ቢያጋጥማቸው ለቤተክርስቲያን አባቶች ተነግሮ እንዲጠመቁ የቤተክርስቲያን ቀኖና ያዛል። ስለዚህ እንደተባለው እግዚአብሔር ክፉ ነገርን ያርቅልን እንጂ ምንም እንኳን ህፃናቱ ስጋዊ ኀጢአት ያልሰሩ ቢሆንም ክርስትናው ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመግባት አርማ ወይም ልዩ ምልክት ስለሆነ ጥምቀት ማግኘት እንዳለባቸው እናታችን ቅድስት ተዋህዶ ቤተከርስቲያናችን የቀኖና ስርዓት አስቀምጣለች።    
ምናልባት የቤተክርስቲያን መምህራን እና አባቶች በአካባቢያችን ሳይኖሩ ሳያስረዱ ወይም ወላጆችም የዚህን አይነት የጥምቀት ስርአት ሳያውቁ ቀርተው እንደዚህ አይነት ፈተና ቢያጋጥም የተወለዱት ህፃናት የክርስቲያን ልጆች ከሆኑ የወላጆቻቸው ሃይማኖት መለያቸው ስለሆነ ፤ ማለትም የፍየል ልጅ ፍየል የበግ ልጅ በግ እንደማለት ነውና እግዚአብሔርም ከሁሉም በላይ አዋቂና ቸር ይቅር ባይ አምላክ ስለሆነ እንደኀጢአተኞች አይቆጠሩም ማለት ነው።
መልሱ ፦  ስለ ቅዳሴ ፀበል ለጠየቁን አባላችን የተሰጠ ምላሽ፦ ፀበል በ2 ከፍለን ልናየው እንችላለን 1ኛው በቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ወይም ከቤተክርስቲያኑ ርቆ ባለ በፈቃደ እግዚአብሔር የበቁ መንፈሳዊ አባቶች በሰጡት አቅጣጫ የሚፈልቅ ፀበል አለ። 2ኛው ጠያቂያችን እንዳሉት በቅዳሴ ግዜ ከቅዱስ ስጋውና ከክቡር ደሙ ጋር አብሮ የሚሰጥ የቅዳሴ ፀበል አለ። የመጀመሪያው በቅጽር ቤተክርስቲያን ወይም ከቅጽረ ቤተክርስቲያን ውጭ ሁኖ በፈጣሪ ስም እና በቅዱሳን ስም የፈለቀው ፀበል የተለያየ ደዌ እና መናፍስት ያለባቸው እንዲም ደግሞ ጤነኛ ሰወች ለበረከት የሚጠመቁበትና የሚጠጡት እንዲሁም ቤታቸውን ንብረታቸውን ሀብታቸውን ከአጋንንት መንፈስ ለመጠበቅ የሚረጩበት ፀበል በእግዚአብሔር ቃል የተቀደሰ እና ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ፀጋ ያደረባቸው አባቶች በፀሎታቸው እና በቡራኬያቸው ያከበሩት ፀበል ስለሆነ ወደ ቤተክርስቲያን መቅረብ የቻለ ፀበሉን ከቤተክርስቲያን አገልጋዮች እጅ ተቀብሎ ይሄዳል፤ በተለያየ ምክንያት ወደቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ መቅረብ ያልቻሉ ግን በመልእክተኛ ወይም በሞግዚት ፀበሉ ተወስዶላቸው ፈውስ ያገኙበታል ማለት ነው። የዚህ አይነት ፀበል በዚህ አይነት አገልግሎት የሚፈፀም ነው። የዚህ በረከት መነሻ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በራሱ ፈቃድ ከ 38 አመት ጀምሮ በፅኑ ደዌ ታሞ የነበረውን መፃጉን በፈወሰው ግዜ መዳን ትወዳለህን ብሎ ሲጠይቀው ለመዳን ይችል ዘንድ ወደ ፀበሉ የሚያደርሰው የቅርብ ረዳት እንደሌለው እና ከሱ ቀድሞ ወደ መጠመቂያው ፀበል የገቡ እንደሚድኑ ምስክርነቱን የሰጠበት የቅዱስ ወንጌል ቃል የሚያስረዳ ነው። (ዮሐ 5፥1-15) 
2ኛውየቅዳሴ ፀበል ስለተባለው እንኳንስ ሰማያዊና ዘለአለማዊ ህይወት የሚያሰጠውን ፀበል ቀርቶ በዚህ በምንኖርበት ምድራዊ ስርዓት እንኳን ከመጀመሪያው ጀምሮ በፕሮግራማችን ላይ የተገኘ ሰው ቅድሚያ ተሰጥቶት በአክብሮት ለዚያ ፕሮግራም የተዘጋጀውን የክብር መስተንግዶ እንደሚያገኝ በሁላችንም ዘንድ የተለመደ ስርዓት ነው። ከዚህ በላይ እጅግ የሚከብረውን እና ዘላለማዊ ህይወት የሚያሰጠውን የቅዳሴ ፀበል በእለተ አርብ ጌታ በመስቀል ላይ ስለኛ በከፈለው ዋጋ ከቀኝ ጎኑ ማየ ህይወት (የህይወት ውሀ) የተገኘ ስለሆነ ቢያንስ እንኳን የበለጠ በረከትና ህይወት እንድናገኝበት ቁመን ካስቀድሰን በኋላ ቅዱስ ቁርባን ባንቀበል እንኳን ፀበሉን በበረከት መጠጣት እንደሚገባን ስርዓተ ቤተክርስቲያን ይፈቅዳል። ከዚህ ውጭ ግን በፈለግነው ሰአት እና ጊዜ መጥተን ቅዳሴውን ቁመን ሳናስቀድስ እና የቅዳሴውን ስርአት ሳንከታተል ፀበሉን ብንጠጣ ወደ ቤታችንም ብንወስደው እንደ ኀጢአተኛ ባያስቆጥርም እንኳን ከሰነፎች እንደ አንዱ ሊያስቆጥረን ይችላል። ምክንያቱም ጌታ በወንጌል እንደተናገረው አብዝቶ የሚወደውን ብዙ ኀጢአቱን ይቅር እንደሚል ወይም ብዙ በረከቱን እንደሚያድል፤ በጥቂቱ የሚወደውን ደግሞ ጥቂት ኀጢአቱን ይቅር እንደሚልና ጥቂት በረከት እንደሚሰጥ የተናገረው ለኛ መንፈሳዊ ህይወት እጅግ አስተማሪ ስለሆነ ጠያቂያችን በዚሁ መሰረት እንዲረዱት መልዕክታችንን አስተላልፈናል።
መልስ፦  ስለቄደር አጠቃቀም
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሓ ድረገፅ የሚተላለፈውን ኦርቶዶክሳዊ ፕሮግራም የምትከታተሉ ወገኖቻችን በሙሉ፦ የቄደር ጥምቀት ለምን ያስፈልጋል? ጥፋቱ ቢደገምስ ዳግም ለመጠመቅ ይቻላል ወይ? በሚል ጠያቂያችን ስላቀረቡት ጥያቄ በሚመለከት ከዚህ ቀደም በተወሰነ ደረጃ መልስ የሰጠንበት ቢሆንም ለማወቅ እና በትምህርቱ ለመጠቀም ጠያቂዎች እስከጠየቁን ድረስ በኛም በኩል እንደ እግዚአብሔር መልካም ፈቃድ መልሱን ለመስጠት ዝግጁ ነን። በዚሁ መሰረት የቄደር ጥምቀት የሚያስፈልግባቸው የሃይማኖት እና የስነ-ምግባር ሕጸጾች የሚከተሉት ናቸው። 
ሃይማኖትን በሚመለከት፦ 
 –  ጨርሶ ለይቶለት እና ሃይማኖቱን ክዶ ወደ ልዩ ልዩ ሃይሞኖት ከሄደ በኋላ በንስሐ ለመመለስ ቢፈልግ፣
–  በቤተክርስትያን ውስጥ እያለም ቢሆን በክህደትና በኑፋቄ የኖረና ከሃይማኖቱ ሕጸጽ ተመክሮና ንስሐ ተሰጥቶት የተመለሰ፣
–   ጋኔን የሚስብና የሚያስብ፣
–   በዛር መንፈስ የሚጠነቁልና የሚያስጠነቁል በዚህም ሰውን ሁሉ የሚያሰግድ እና የሚያስገብር፣
–    በልዩ ልዩ የአምልኮ ባእድ ቦታ አምኖ በተለያየ ቦ
ክርስቲያናዊ ስነምግባርን በሚመለከት፦
–   እስላም ያገባ/ች፣ ካቶሊክ ያገባ/ች፣ ፕሮቴስታንት ያገባ/ች፣ (በእምነት የማትመስለውን ወይም የማይመስላትን የገባ/ያገባች)
–  በአምልኮ ባዕድ ለጣኦት የታረደውን የበላ፣ በሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ታርዶ የተዘጋጀውን ምግብ የበላ፣
–  በቅዱስ መጽሐፍ ለምግብነት ያልተፈቀዱ እንስሳትም ሆነ የዱር አራዊት የበላ
 
እነዚህ ከዚህ በላይ የተገለፁት በሃይማኖትና በስነምግባር ሕጸጽ ናቸው ተብሎ የሚታመኑ ስለሆነ የቄደር ጥምቀትም እንደሚያስፈልጋቸው በቤተ ክርስቲያን የቀኖና መጽሐፍት የተደነገጉ ናቸው። ሆኖም አንድ ክርስቲያን እነዚህን የመሰሉ የጥፋት ስራ ሳያውቅ ከሰራ ጥምቀቱን ተጠምቆ ወደፊት ይህንን የሚመስል ጥፋት እንዳያጠፋ ትምህርት እና ተግሳፅ ይሰጠዋል። እያወቀ ያጠፋ ከሆነ ግን ከቄደር ጥምቀት በኋላም የፆም፣ የስግደት እና የፀሎት ቀኖና ሊሰጠው ይችላል። ሁለተኛም እንዳይበድል ልዩ ከባድ ማስጠንቀቂያ በምክር እና በተግሳፅ ይሰጠዋል። 
 
በመሰረቱ ጠያቂያችን እንዲረዱት የምንፈልገው የቄደር ስርዓት የንስሓ አካል ነው። ንስሓ ደግሞ ኀጢአተኞች እስካሉ ድረስ የማይቋረጥ በደለኞችን ከኀጢአት ለማንፃት ተደጋግሞ የሚሰጥ የቀኖና ስርአት ነው። በሽታ ካለ ወይም ደዌ ካለ ህመምተኞች አሉ፤ ህመምተኞች ካሉ ደሞ ሀኪም አለ፤ ሀኪም ካለ ደሞ ፈውስ አለ። በዚህ መሰረት ኀጢአተኞች ካሉ የንስሓ ህይወት አለ፤ የንስሓ ህይወት ካለ ደግሞ ንስሓ አባቶች አሉ። ንስሓ እና የንስሓ አባቶች ካሉ ደግሞ ኀጢአትን ይቅር የሚል ፈጣሪ አለ። ስለዚህ ኀጢአት እስከተሰራ ድረስ የቄደር ጥምቀት የመኖሩ ሁኔታ የግድ ነው። በእርግጥ ማንኛውም ክርስቲያን ኀጢአት ለመስራት ውስጡን አሳምኖ ኀጢአትን አቅዶ መያዝ ፍፁም አይኖርበትም፤ ክርስቲያናዊ ፀባይም አይደለም። ረቂቅ የሆነው ጠላታችን ዲያብሎስ በስውር የሚዋጋን ስለሆነ እኛም ክርስቲያኖች ጠላታችን ዲያብሎስ እንዳያሸንፈን እግዚአብሔርን ጋሻና መከታ አድርገን በእናቱ ድንግል ማርያም እና በቅዱሳን አማላጅነት እና አስታራቂነት እየተረዳን እና እየታገዝን የክፉ ሃሳብ ሁሉ ምንጭ የሆነው ሠይጣንን ለማሸነፍ ሁል ግዜ መትጋት ይገባናል። ከእኛ አቅም በላይ የሆነ ከባድ ፈተና ቢያጋጥመን ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ይቀላል። ለቄደር ጥምቀት የሚያበቃ ኀጢአት ለሰሩ ሁሉ የቄደር ጥምቀት ያስፈልጋቸዋል። ስለሆነም ይሄንን የኀጢአት ጥፋት ደግሞ እስካላቆምን ድረስ ቄደር እንደሚቀጥል ሁላችሁም ልትገነዘቡት ያስፈልጋል። ሌሎችንም የንስሓ ስርአቶች በዚህ አይነት መመልከት ያስፈልጋል። በመሰረቱ 5500 ዘመን የነበረው የኀጢአት በደላችን ካሳ ከፍሎ በሞቱ ፍፁም ፍቅሩን ያሳየን የእየሱስ ክርስቶስ ካሁን በኋላ ኀጢአት የሚሰሩ ይቅር አይባሉም ብሎ በጭካኔ አልፈረደብንም። ለአምላካችን መድኀኒአለም ክብር ይግባውና ስፍር ቁጥር የሌለውን ይቅርታ እና ቸርነቱን እንዴት እንዳበዛልን ወንጌላዊ ቅዱስ ማቴዎስ እንደነገረን “በዚያን ግዜ ጴጥሮስ ጌታ ሆይ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ግዜ ልተውለት? እስከ 7 ጊዜን? አለው። እየሱስም እንዲህ አለው እስከ 70 ጊዜ 7 እንጂ እስከ 7 ጊዜ አልልህም…እልፍ መክሊት እዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደእሱ አመጡ የሚከፍለው ቢያጣ እርሱ እና ሚስቱ ልጆቹንም ያለውንም ሁሉ እንዲሸጥ እና እዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ። ስለዚህ ባርያው ወድቆ ሰገደለትና ጌታ ሆይ ታገሰኝ ሁሉንም እከፍልሃለው አለው። የዛም ባርያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው እዳውንም ተወለት” በዚህም መለኮታዊ ቃል መሰረት አምላካችን እግዚአብሔር የኛን ኅጢአት ይቅር የሚልበት የጊዜ ገደብ እና ቁጥር የሌለው መሆኑን ቸርነቱና ምህረቱ ስለኛ የበዛ መሆኑን ይህ የወንጌል ቃል ያስረዳናል። (ማቴ 18፥21-27)
መልስ፦ በሃይማኖት የማትመስለውን ያገባ ወይም ያገባች ሴት ምን አይነት ጥምቀት እንደሚያስፈልግ ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥያቄ ተጠይቆ የላክነው ምላሽ ስላለ እሱን እንዲመለከቱት ከዚህ ጋር እየላክንልዎት፤ ነገር ግን ባጭሩ ለማስረዳት በሃይማኖት የማይመስለውን ያገባ ወይም ያገባች ክርስቲያን የሚጠመቁት ጥምቀት የልጅነት ጥምቀት ሳይሆን የቄደር ጥምቀት ነው። የቄደር ጥምቀት ምን አይነት እንደሆነ በመፅሐፈ ቄደር ላይ ተቀምጧል። በሃይማኖት የማትመስለው ወይም የማይመስላት አምነው ወደ ክርስትና ህይወት ለመምጣት ፈቃደኛ ከሆኑ የሚጠመቁት ጥምቀት የክርስትና ጥምቀት ነው ወይም ክርስትና ይነሳሉ ማለት ነው። ቄደር የተጠመቀው ሰው የንስሓ ቀኖናውን ከጨረሰ በኋላ፣ አዲስ ያመነውም ክርስትና ከተነሳ በኋላ አብረው ስጋ ደሙን እንዲቀበሉ ይደረጋል። ጠያቂያችን በዚህ አይነት የሚፈፀም መሆኑን እንዲረዱት ይህን አጭር መልዕክት ልከንልዎታል።
መልስ ፦  በአዲስ ኪዳን ጥምቀት አንድ ብቻ ነው፤ እሱም የልጅነት ጥምቀት ነው። በእርግጥም በሚስጥረ ጥምቀት ትምህርታችን እንደተገለፀው አማናዊ ጥምቀቶች 1ኛ/ የወልደ እግዚአብሔር የክርስቶስ የልጅነት ጥምቀት 2ኛ/ በንስሓ ህይወት የሰው ልጅ የሚያፈሰው የለቅሶ እንባ በ3ኛ/  ደረጃ ደግሞ በሰማዕትነት ደማቸውን የሚያፈሱ ሰማእታት ደም እንደ ጥምቀት የሚቆጠሩ ናቸው። ያ ማለት አምኖ ሳይጠመቅ ለሚሞት ሰው ከልቡ ተፀፅቶ ቢያለቅስ እንባውን ቢያፈስ እንደ ጥምቀት እንደሚቆጠርለትና፣ በፍፁም እምነት ሆኖ ስለ ሃይማኖቱ ደሙን ያፈሰሰው ደሙ እንደ ጥምቀት እንደሚቆጠርለት ለመግለፅ የተነገረ ሃይመኖታዊ ምስጢር ነው።
በአዲስ ኪዳን ክርስቲያናዊ ህይወት ግን ሁሉም ሰው በ40 እና በ80 ቀን የእግዚአብሔርን ልጅነት በስርአተ ጥምቀት ስለሚያገኝ ለሌሎቹ እንደ ንስሓ የሚያስቆጥሩ ምክንያቶች አያስፈልጉትም። ከአረማዊነት እና ከአሕዛባዊ ህይወት ተመልሶ ያመነ አዋቂ ሰው ቢሆንም በዚያኑ እድሜ መጠኑ በጥምቀት የእግዚአብሔርን ልጅነት እዲያገኝ ይደረጋል እና አሁን የሰማዕትነት ደም የተባለው እግዚአብሔር ክፉውን ያርቅልን እንጂ በሃይማኖታችን በሰላምና በነፃነት እንዳንኖር ለሰማዕትነት የሚያበቃ ጠላት ሰይጣን ካስነሳብን በስጋዊ ህይወታችን ላይ በሚመጣ መከራ ሃይማኖታችንን መካድ ስለማንችል ሰማዕትነት እንድንቀበል የሚያደርገን እና በሰማእትነት ደማችንም የሚሰጠን የሃይማኖት ተጋድሎ ይህ እንደሆነ ጠያቂያችን እንዲረዱ ያስፈልጋል።
መልስ፦ ለፀሎት የምንገለገልባቸውን መፅሐፍት እና ሌሎችን የመንፈሳዊ አገልግሎት የምንሰጥባቸውን ማንኛውንም ነገር የተለየ ቦታ ተዘጋጅቶላቸው መቀመጥ አለባቸው። እኛም ለመፀለይ ስንፈልግ ካደርንበት መኝታችን ተነስተን የአድህኖ እና የምንፀልይበት ቦታ ላይ ሄደን የተለመደውን የእለት ፀሎታችንን ማድረስ፤ ቦታ ባይኖረንም እንኳን ከተኛንበት ቦታ ላይ ርቀን በውጭም ሆነ በሳሎን ውስጥ ሆነን መፀለይ፤ በተለይ ባል እና ሚስት የግብረስጋ ግንኙነት አድርገው በአደሩበት ቀን ወይም እዛ ቦታ ላይ ቅዱሳት ስዕላት ማስቀመጥ ስርዓተ ቤተክርስቲያን የተከለከለ ነው። በተጨማሪ በዚህ ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ ጥያቄ ተጠይቆ የተሰጠውን ምላሽ ከዚህ በታች ይመልከቱ።
 
ስለ ፀሎት ቦታ፣ እና ቅዱሳን ስእሎችን ቅባ ቅዱስ መቀባት ይቻላልን፣ እና የፀሎት ውሀ ምንድነው ብለው ለጠየቁን አባላችን የተሰጠ ምላሽ ፦ የቦታ ችግር ከሌለብን ራሱን የቻለ ቦታ ጠዋትም ማታም ራሳችንን ለይተን የዘወትር ፀሎታችንን የምናደርስበት የተለየ ቦታ ቢኖረን መልካም ነው። ከሌለን ደግሞ የኛን ችግር ከኛ በላይ እግዚአብሔር ያውቀዋልና በዛችው በምንኖርባት ጎጇችን ውስጥ ጠዋት ከመኝታችን ተነስተን ተጣጥበን ሳሎን ላይም ቢሆን ቁመን መፀለይ ይቻላል።
 
ቅዱሳን ስእሎችን በምንበላበት፣ በምንጠጣበት፣ በምንተኛበት ቤት ውስጥ ግድግዳ ላይ እንደ ጌጥ ማንጠልጠል በልማድ የመጣ እንጂ ትክክለኛ ክርስቲያናዊ ስርአት አይደለም። መክንያቱም ስእላቶቹ በቤተመቅደስ ውስጥ ከታቦታቱ ጋር አክብረን ስርአተ አምልኮት የምንፈፅምባቸው ስለሆኑ የተለየ ቦታ አዘጋጅተን በቤታችን አካባቢ የተለየ ቦታ ከምንተኛበትና ምግብ ከምንበላበት ውጪ የተለየ ቦታ አዘጋጅተንላቸው ስልጣነ ክህነት ያላቸውን አባት አስባርከን በንፅህና ሆነን እንድንፀልይባቸው ይፈቀዳል። ቅዱሳት ስእል ግን ቅባ ቅዱስ አይቀባም። 
 
‘የፀሎት ውሀ’ ያሉት አነጋገሩ የቤተክርስቲያን ቋንቋ ባይሆንም ጠያቂያችን ግን ይረዱት ዘንድ ቤታችን ውስጥም ዘወትር ስንፀልይ ከቤተክርስቲያን በእቃ ያመጣነውን ፀበል ወይም ደግሞ የቤተክርስቲያን አባት ፀሎት አድርሰውበት በእቃ ያስቀመጥነውን ፀበል ልዩ ቦታ ላይ አስቀምጠን ግቢያችንን ልንረጨው እኛም ልንጠመቅበት ብንችል የእግዚአብሔር በረከት እና ቸርነት ወደ እኛ ይቀርባል። ዘወትር የሚቃወመን የሰይጣን መንፈስ ደግሞ ከእኛ እንዲርቅ ይሆናል በዚሁ መሰረት ፀበል ማለት በቤታችን ውስጥ ዘወትር የሚኖር መዝገበ ፀሎት ወይም ከቤተክርስቲያን የምናመጣው ፀበል በመባል ይታወቃል።
መልስ፦  በቤታችን ውስጥ ፀበል መጠመቅ ቢያስፈልገን ሀብተ ክህነት ወይም ክህነት የሌለው ሰው ማጥመቅ አይችልም። ነገር ግን በአካባቢያችን ካህን የማይገኝ ቢሆን ካህኑ በውሀው ላይ ፀሎት  ፀልየውበት በመስቀልም ባርከውት አንተው በላይህ ላይ ፀበሉን እያፈሰስክ ተጠመቅ ብለው ከሰጡን መረጨትም ሆነ በራሳችን ላይ ማፍሰስ እንችላለን። ይህ ግን ማጥመቅን የሚተካ ስርዓት አይደለም። ወደ ገዳም ሄደን የምናመጣው ፀበል ከአባቶች ተፈቅዶ በእቃ የምናውለው ፀበል እኛም ራሳችን መረጨትም እንችላለን ቤተሰቦቻችንም ፀበሉን እንዲጠጡትም ሆነ ሰውነታቸውን እንዲቀቡት ማድረግ ይቻላል፤ ካህንን ተክቶ ግን አንዱ አንዱን ማጥመቅ አይችልም።
መልሰ፦   ከማያውቁት ወንድ ጋር በህልመ ለሊት ግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ የሰው ልጅ በራሱ ስጋዊ ስሜት አስቦበትና ፈለጎት ያደረገው ኅጢአት ስላልሆነ መደበኛ የንስሓ ቀኖና አያስፈልገውም። ነገር ግን በህልመ ሌሊት እየመጣ ለወንዱ ሴት መስሎ፣ ለሴትዋ ደግሞ ወንድ መስሎ የሚገናኝ ስጋ የለበሰ እርኩስ መንፈስ ስለሆነ ስጋዊ ህይወታችንንም ሆነ መንፈሳዊ ህይወታችንን ስለሚያበላሸው ከኛም ተለይቶ መወገድ ስላለበት ለአባቶች ቀርቦ በመናዘዝ ልዩ ፀሎት፣ ስግደት፣ እና ጥምቀት ማደረግ ያስፈልጋል። ሁሌ የሚፈታተነን ክፉ መንፈስ ከኛ ተለይቶ እስከሚጠፋልን ድረስ የተለያየ ልዩ ፀጋ ያላቸው አባቶች በፀሎት እንዲያስቡን በማድረግ እኛም በግላችን በምንችለው አቅማችን ዘወትር መፀለይ ያስፈልገናል። እንዲህ በሆነ ግዜ እርኩስ መንፈሱን የእግዚአብሔር ቃል ስለሚያቃጥለውና እኛ ጋር ያለው መንፈሳዊ ህይወትም ስለሚዋጋው ፈፅሞ ይጠፋል ፤ ስለዚህ ጠያቂያችን ይህንን ጉዳይ ንስሓ እንሚያስፈልገው አድርገው ማሰብ የለብዎትም። ስለዚህ ይህ ሲሆን ስንት ቀን ነው ጸበል ከመጠመቅ እና ሌሎች መንፈሳዊ ተግባራት የምከለከለው ላሉት፤ አንኳንስ ለመቆየት እንዲያውም ወድያውኑ ሰይጣን ሊፈትነኝ መጣ ብለን በዛኑ ቀን ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ ፀበል መጠመቅና በመስቀል መዳስ እንችላለን
መልስ፦ ሁሌ ንስሓ መግባት እየሞከሩ ግን የሚረሱት ነገር እንደሚኖር ጠቅሰው ያቀረቡትን ጥያቄ በሚመለከት፤ በተቻለን መጠን የምናስታውሰውንና ያልረሳነውን ማለትም ጠዋት ማታ ውስጣችንን እረፍት የነሳንን በደላችንን እና ኅጢአታችንን መናዘዝ ከቻልን ከዚህ በላይ እግዚአብሔርን የሚያስደስተው ነገር የለም። በክርስቲያናዊ ህይወት ስንኖር ሁል ግዜ ማሰብ ያለብን ስለሰራነው ኅጢአት ንስሓ በገባን ግዜ ኅጢአታችን የሚሰረይልን ከእኛ ፅድቅ የተነሳ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ቸርነትና ምህረት የተነሳ ስለሆነ ከእኛ የሚጠበቀው አስቀድመን እንደተናገርነው የሰራነውን ኅጢአት መናዘዝና እግዚአብሔር ደግሞ ኅጢአታችንን ሁሉ ይቅር እንደሚል እርግጠኛ በመሆን ማመን ነው። በተቻለ መጠን ሰው የሰራውን ክፉ ስራም ሆነ በጎ ስራ ባይዘነጋ መልካም ነው። ምክንያቱም ሁሉም የህይወታችን ታሪክ ስለሆነ ሃብታችንን፣ ንብረታችንን እድሜያችንን፣ ገንዘባችንን ወዘተ የመሳሰለውን ቆጥረን እንደምናውቅ ሁሉ እና እንደማንረሳ ሁሉ ስለ ኅጢአታችንም ባንዘነጋ መልካም ነው። መክንያቱም የሚያዘናጋንና በደላችንን ችላ እንድንል የሚያደርገን በንስሓ ህይወት እንዳንመላለስ የሚያሳንፈን ጠላታችን ዲያብሎስ ስለሆነ ክርስቲያን ደግሞ ሁልግዜ የማያንቀላፋ ትጉህ እና ንቁ ሊሆን ይገባል። ለንስሓ የሚያበቁ የኅጢአት አይነቶችን ዝርዝር በሚመለከት አትስሩ የሚበል ነገር ከሰራን፣ አታድርጉ የሚባል ነገርን ካደረግን፣ እንደ ኅጢአታችን ከባድነትና ቀላልነት የሚሰጠን የንስሓ አይነት ይለያያል እንጂ የማንናዘዘው ኅጢአት አይኖርም። ምክንያቱም ጌታችን መድኅኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በወንጌል “ለቀደሙት አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል። እኔ ግን እላችኋለሁ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል። እንግዲህ መባሕህ በመሰዊያው ላይ ብታቀርብ በዚያም ወንድምህን አንዳች ባንተ ላይ ቂም እንዳለው ብታስብ በዚያ በመሰዊያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ፤ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ።” በማለት ወንድምን የሚቆጣ ፣ ጨርቃም ብሎ የሚሳደብ፣ ደንቆሮ የሚል፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድ እንዳለበትና መባውም ፀሎቱም ፆሙም ሌላውም መንፈሳዊ አገልግሎቱ ተቀባይነት ስለሌለው እነዚህን ዘወትር እንደ ተራ ነገር የምንጠቀምባቸው የስድብ ቃሎች ሳይቀር ንስሓ እንድንገባባቸው በቃሉ አስተምሮናል። (ማቴ 5፥21-24)
 
ጠያቂያቸን ከዚህ ጥያቄ ጋር አያይዘውም ጸበል ከመጠመቅ የሚያስከለክሉ በደሎች ምን ሞን ናቸው? ብለው ለጠየቁን ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦልን የላክነውን ምላሽ  ከዚህ በታች ልከንልዎታልና አንብበው ይረዱት።
 
ጥያቄው፦ ንስሀ ገብተን ቀኖና ተሰቶን፣ እሱን እየፈጸምን በመሀል ጸበል መጠመቅ መጠጣት እንችላለን ወይስ ቀኖናችን አልቆ እግዚአብሔር ይፍታ እስክንባል መጠበቅ አለብን?
 
የተሰጠው ምላሽ፦  ጠያቂያችን ንስሓ ገብቶ በቀኖና ላይ ያለ ክርስቲያን ፈፅሞ ሃይማኖትን የካደ ካልሆነ ቆሞ ማስቀደስ፣ ፀበል መጠመቅ፣ ፀበል መጠጣት፣ መስቀል መባረክ፣ በክርስቲያኖች ማህበር ጉባዔ መካከል ተገኝቶ የእግዚአብሔርን ቃል መማር፣ በቅፅረ ቤተክርስቲያን ቆሞ መፀለይ ይችላል። ከእንዲህ አይነት ስርአት የሚከለከሉ ጨርሶ ሃይማኖታቸውን ክደው የነበሩ ወይንም ደግሞ ከባድ የተባለ የመጨረሻ ኅጢአት የሰራ ሰው ከሆነ ያ ሱባኤ የሚገባበት ቦታ ሰው የማይደርስበትና ከሰው የማይገናኝበት ልዩ ቦታ ስለሚሆን ያንን ንስሓውን ጨርሶ ከፈጣሪው ዘንድ የይቅርታ ምላሽ እስከሚያገኝ የተለመደውን የቤተክርስቲያን አገልግሎት ማግኘት አይችልም።
 
ስለዚህ ጠያቂያችንም ሆነ ሌሎቹ የድረገፁ አባላቶቻችን ይህን ለመሳሰሉ ጥያቄዎች መጠነኛ ግንዛቤ እንዲሆናችሁ ይህን መልእክት ወደእናንተ ስላደረስንላችሁ በመረዳት እንድትማሩበት አደራ እንላለን።
መልስ፦ ጠያቂያችን ፀበል ከጠጣን በኋላ መቆየት ያለብን የግዜ ገደብን በሚመለከት ልክ እንደ ማስቀደስ እና ቅዱስ ቁርባንን እንደመቀበል ሁሉ ለነፍሳችን ምግብ የሆነውን ፀበል ፤ በስጋችን ያደረውን ደዌ ለመፈፈወስ የተጠቀምነው ፀበል የራሱን የሃይል ስራ እስከሚሰራ ድረስ ለተወሰነ ግዜ ከምግብ ተቆጥበን መቆየታችን ጥቅሙ ለኛ ለራሳችን ነው። ነገር ግን ጠያቂያችን እንዳሉት ይህን ያህል ሰአት ቆዩ ተብለን የምንገደድበት ግዜ አይኖርም። ስለዚህ የጠጣነው ፀበል ከውስጣችን ያለውን ነገር በእግዚአብሔር ቃል እና በአባቶች ፀሎት ከተፈጥሮ ውሃ ተለይቶ ልዩ ሃይል ስላደረበት ለስጋ ምግብ ሳንቸኩል ከፀበሉ የምናገኘውን ፈውስ ምላሽ እስከምናገኝ ብንታገስ የሚመረጥ መሆኑን እንመክራለን።
 
ወደቤታችን በእቃ የወሰድነውን ፀበል በሚመለከት፤ ልክ ለፀሎት የተለየ ቦታ እንዳለን ሁሉ፤ በአባባል እንደምንሰማው፦ የስጋ ተግባር ከሚፈፀምበት ቦታ አርቀን እራሱን የቻለ ቦታ ላይ ማስቀመጥ ነው። በእግዚአብሔር ስም የተቀደሰው ፀበልም ሆነ ሌላ ነገር ሁሉ እኛ በሰው ሰውኛ በምንፈፅመው ጥፋት አይረክስም። ምክንያቱም የሰው ጥፋት የእግዚአብሔርን ቅድስና አያረክሰውም።  ነገር ግን ኀጢአታችንንም ሆነ የፈፀምነውን ጥፋትና በደል እያወቅን እግዚአብሔርን ሳንፈራ በድፍረት ብናደርገው ግን የፈለግነውን ጥቅምና ድኅነት አናገኘውም። እንድያውም ለፈተና ሊሆንብን ይችላል። ከዚህ የተነሳ ነው ሁል ግዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኘነውን ነገር በንፅህና እና በቅድስና ሆነን እግዚአብሔርን በመፍራትና ራሳችንን በትህትና  ዝቅ አድርገን እንድንገለገልበት የሚያስፈልገን። ስለዚህ ጠያቂያችን ያቀረቡትን ጥያቄ በዚህ በሰጠነዎት የማብራሪያ ሃሳብ እንዲረዱት ይህ መልዕክት እንዲደርስዎ አድርገናል።
መለስ፦ ጠያቂያችን ፀበል ስንጠመቅ በሚመለከት ላቀረቡልን ጥያቄ፦ ፀበል መጠመቅ ከቤተክርስቲያናችን አንዱ መንፈሳዊ አገልግሎት ነው። ፀበልን በ 2 አይነት መንገድ ልንጠቀመው እንችላለን። 1ኛው ማንኛውም ክርስቲያን  በእግዚአብሔር ቃል የተባረከውንና የተቀደሰውን ፀበሉን በረከት ለማግኘት እንጠቀምበታለን፣ እንጠጣለን። 2ኛው በተለያየ ደዌ የሚሰቃዩ ህሙማን ድህነት ላማግኘት ይጠመቃሉ። እነዚህ ህሙማን በተጠመቁ አንዳንዶቹ በፀበሉ ሲጠመቁ በውስጣቸው በረቂቅ ተሰውሮ የሚያሰቃያቸው መንፈስ በፀበሉ ላይ ያለው የእግዚአብሔር ቃል እና ቅዱስ መስቀሉ ሲያቃጥለው ይለፈልፋል። 
ይህ ማለት እርኩስ መንፈስ በተለያየ መንገድና ታማሚው ሰው እንዴት እንደተቆራቸው ሳያውቅ በሰው ላይ ስለሚያድር የሰውን ልጅ  እንደ መኖሪያቤት በመቁጠር ለረጅም ግዜ ተቆራኝቶ በተለያየ መንገድ ሲያሰቃየው ከእግዚአብሔር የሚያጣላውን ስራ ሲያሰራው ከኖረ በኋለ ለአንድ ቀን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ወደ ፀበል ቦታ ሄዶ ሲጠመቅ በመንፈሱ ገበና ተጋልጦ ይወጣል ማለት ነው። አንዳንዱ መንፈስ ደግሞ ከስጋችን ጋር ተቆራኝቶ በምንጠመቅ ግዜ ምልክት ላያሳይ ይችላል። ስለዚህ እንደተባለው አንድ በሽተኛ ባለመጮሁ መንፈስ የለበትም ማለት አንችልም። ማረጋገጫው የሰውየው ውስጣዊ እና ውጫዊ ጤንነቱ ከእርኩስ መንፈስ የራቀ ለመሆኑ የቤተክርስቲያን አባቶች በፀሎት እና በቅዱስ መስቀሉ ባርከውና አክብረው ሲያጠምቁት ምንም አይነት ምልክት ካልታየበት ያ ሰው ጤነኛ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል። ስለዚህ ማንኛውም ክርስቲያን ማወቅና መረዳት ያለበት የእርኩስ መንፈስ ውግያ በረቂቅ እና በስውር ስለሆነ ጤነኛ መስሎ በስጋው ላይ የህመም ምልክት ያማይታይበት ሁሉ እርኩስ መንፈስ አይዋጋውም ወይም የለበትም ብሎ ማሰብ በጣም ስህተት ነው። ራስንም ማታለል ይሆናል። ምክንያቱም ሁሉም ሰው በተለመደ አመለካከት አንድ ሰው ልብሱን ጥሎ ሲያብድ ወይም ደግሞ በሰው ዘንድ የሚያሳፍር ነገር ሲያደርግ ለይቶለት ሲለፈልፍና ሲጮህ ብቻ እርኩስ መንፈስ እንዳደረበት እናምነን። ይሁን እንጂ ይሄን የመሰለ ምልክት ያልታየባቸው ሰወች ጥፋታቸው በየግዜው የሰይጣንን ውግያ ተከታትለው ስለማይገነዘቡ በማንኛውም እለታዊ ኑሮ ውስጥ ብዙ ፈተናዎችን የሚየደርስባቸው እርኩስ መንፈስ እንደሆነ መታወቅ ይገባዋል። የሰው ልጅ አታድርግ የተባለውን ካደረገ አትፈፅም የተባለውን ከፈፀመ በፈጣሪ ዘንድ ያለውን ሰማያዊ ክብር የሚያሳጣውን ክፉ ስራ ከሰራ እነሆ አሁንም ረቂቅ የሆነ የሰይጣን ፈተና እንዳለበት ማወቅ ይገባል።  
እንግዲ ጠያቂያችን ስለዚህ ስላቀረቡት ጥየቄ ባጭሩ የተሰጠውን መልስ ተመልክተው ግንዛቤ ያገኙ ዘንድ ይህን መልዕክት ልከንልዎታል።
 
ጠያቂያችን የጥያቄ አገላለፅዎን የበለጠ እንድንረዳው ማብራሪያ ቢያስፈልገውም፤ ነገር ግን እንደ ስርዓተ ቤተክርስቲያን አፈፃፀም ከሆነ ለቄደር የሚያበቃ ኀጢአት የሰራ ክርስቲያን ከቄደሩ በፊት መጀመርያ ንስኀ መግባት ያስፈልገዋል። ንስኀውን ከጨረስ በኋላም ቄደር ሊጠመቅ ያስፈልገዋል። ወደ ገዳም ሄዶ በጋራ ቄደር መጠመቅ እንዴት እንደሆነ ግልፅ ባይሆንልንም ከቄደሩም በኋላ ቢሆን የሁሉም ሰው ጥፋትና የቄደር ጥምቀት ያስፈለጋቸው ምክንያት አንድ አይነት ስለማይሆን በየግላቸው ከቄደር ጥምቀት በኋላም ቢሆን ንስኀ መግባት መንፈሳዊ ፀጋንና ክብርን ያበዛል እንጂ የሚያገጎለው ነገር ባለመኖሩ እንዳሉትም የቤተክርስቲያን አባቶችን በማናገር ንስኀ መግባት ይችላሉ።

መልስ፦በክርስቶስ የሚኖሩ የእግዚአብሔር ልጆች የመጀመሪያ የልጅነት ጥምቀት ያገኙት ከሐዋሪያት ዘመን ጀምሮ ነው። ምክንያቱም ቅዱሳን ሐዋሪያትና እናቱ ድንግል ማሪያም እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ልጅ ለማዳን በፍጹም ፍቅሩ በፈፀመው የመስቀል አገልግሎት እና በቆረሰው ሥጋውና ባፈሰሰው ደሙ ከአዳም ጀምሮ ያሉ በአፀደ ነፍስም በአፀደ ሥጋም በራሱ መለኮታዊ ጥበብ በሱ ደም ተዋጅተው እንደ ጥምቀት የተቆጠረላቸው የእግዚአብሔር ልጆች የሆኑ የሚጠሩበትን ሰማያዊ መንግስትን ወርሰዋል። ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታ በተነሳ በ50ኛው ቀን የወረደው አፅናኙ መንፈስ በነሱ ላይ በእሳት አምሳል በወረደላቸው ጊዜ እንደ ጥምቀት ሆኗቸዋል። ያ እለት የቤተከርስቲያንም የልደት ቀን ነው ተብሎ ይታመናል። በመሰረቱ ለሁላችንም ደግሞ ከውሃና ከመንፈስ እንድንወለድ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በራሱ መለኮታዊ ቃል ከውሃና ከመንፈስ ያልተወለደ የእግዚአብሔርን መንግስት አያይም ከማለቱም በተጨማሪ ያመነ የተጠመቀ ይድናል ያላመነ ያልተጠመቀ ደግሞ አይድንም ብሎ እራሱ የልጅነት ጥምቀት እንድንጠመቅ ከነገረን ጊዜ ጀምሮ ስርዓተ ጥምቀት በክርስቲያኖች ዘንድ ህግ ሆኖ ተሰርቷል። ከዚያ በፊት ግን እሱ የተጠመቀው ጥምቀትና በመስቀል ያፈሰሰው ደሙ ለኛ እንደ ጥምቀትም ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመግባት እንደ አርማ ሆኖ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ አብቅቶናልና ፤ ጠያቂያችን ለግዜው ሃሳቡን በዚህ ተረድተውት ወደፊት በብሉይ ኪዳን እና አማናዊ የልጅነት ጥምቀት በአዲስ ኪዳን ምን እንደሚመስል የምናብራራው ስለሚሆን በትዕግስት ሆነው በመስመር እንዲጠብቁን እንጠይቃለን።

መልስ፦ ጠያቂያችን፤ ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦልን ያስተላለፍነው ምላሽ ውስጥ እርስዎ አሁን ካቀረቡት ጥያቄ ጋር ስለሚመሳሰል  አንብበው ሃሳቡን እንዲረዱት ልከንልዎታል። ምናልባት በዚህ ምላሽ ውስጥ ግልጽ ያልሆነልዎት ወይም ያልተመለሰልዎት ጉዳይ ካለ ደግመው ቢያሳውቁን ተጨማሪ ማብራሪያ እንሰጥዎታለንና በመስመር ላይ ሆነው ይጠባበቁን ዘንድ እንጠይቃለን። 

ተጠይቆባቸው የነበረው ጥያቄ  1 ፦ሁለት በእጮኝነት ላይ ያሉ ጥንዶች ቢኖሩ ለየብቻ መቁረብ ይችላሉ?

መልስ፦ ሁለት በእጮኝነት ያሉ ወንድና ሴት ንፅህናቸውን ጠብቀው በድንግልና ህይወት ካሉ ጠያቂያችን እንዳሉት ጋብቻቸውን እስከሚፈፅሙ ድረስ ለየብቻቸው መቁረብ ይችላሉ። ነገር ግን ቀደም ሲል የፈፀሙት ኀጢአት ኑሮ ንስሓ ካልገቡበትና አሁንም በእጮኝነት ከጋብቻቸው በፊት የሚያደርጉት ነገር ካለ ግን መቁረብ አይችሉም ።

ተጠይቆ የነበረው ጥያቄ 2፦  ሁለት በጓደኝነት ላይ ያሉ ወንድና ሴት ከ ትዳር በፊት ሩካቤ ሲጋ ማድረግ የለባቸውም ግን የበለጠ ማወቅ ያስችለኝ ዘንድ መፅሐፍ ጥቅስ ብትነግሩኝ?

መልስ ፦ ጥያቄው መቅረቡን በአክብሮት ብንቀበለውም ነገር ግን ከጋብቻ ጋር በተያያዘ ቅድመ ጋብቻም ይሁን ድህረ ጋብቻ ስላሉት ስለሚፈቀዱና ስለማይፈቀዱ ሁኔታወችም በስፋት መልእክት ማስተላለፋችን ይታወሳል። ጠያቂያችን መረዳት ያለብዎ ማንኛውም ሃይማኖት ያለው ክርስቲያን ለአካለ መጠን ወይም ለአካለ ጋብቻ ደርሶ እና በሃይማኖት ስርዓትና በባህላዊ ትውውቅና በስርዓተ በጋብቻ ከመፈፀማቸው በፊት ማንኛውንም የአካለ ስጋ ሩካቤ ማድረግ ፈፅሞ ክልክል ነው። ለዚህም ነው በቅዱስ ጳውሎስ ስጋችሁን ለመግዛት ፍላጎታችሁን ለማሸነፍ ካልቻላችሁ በምኞት ከመቃጠል ማግባት ይሻላል ያለው። በዚህ መሰረት ማንኛውም ወንድም ሆነ ሴት ክርስቲያን የስጋውን ፍላጎት መግዛትና መቆጣጠር በማይችልበት የእድሜ ደረጃ ሲደርስ በሃይማኖት ስርዓትና በአገራዊ ባህል የፈለጋትን ወይም የፈለገችውን ተስማምተው ማግባት እንደሚችል ተፈጥሮዋዊ ማንነት ከእግዚአብሔር ተሰጥቷል። ከዚህ የተነሳ የተሰጠንን የነፃነት ፀጋ መጠቀም መቻል እንጂ ከጋብቻ በፊት የድብብቆሽ ስራወች መፈፀም እኛንም በነፍስ ይጎዳናል ከፈጣሪ ጋርም ያጣላናል በሰው ዘንድም መሀበራዊ ማንነታችንን ያዛባል። እና ጠያቂያችን በዚህ መልክ ስራ ላይ ብናውለው በእግዚአብሔር ዘንድም በረከትና መንፈሳዊ እድገት ያሰጣል በማለት እንመክራለን።

ተጠይቆ የነበረው ጥያቄ  3 ፦ ሁለቱ ተጋቢዎች በተክሊል/በቁርባን ሊጋቡ አስበው ግን ከጋብቻ በፊት ብዙ ጊዜ አብረው በፍቅር ከመቆየታቸው አንፃር ስህተት ቢሰሩ(ግንኙነት ቢያደርጉ) በኋላ(በጋብቻ ጊዜ) ጋብቻቸውን በቁርባን ማድረግ ይችላሉ?

መልስ፦ ስርአተ ተክሊል አስባችሁ በመካከል ላይ ራሳችሁን ለመግዛት ሳትችሉ በመቅረታችሁ በመካከል ባደረጋችሁት የስጋ ድካም ከስርአተ ተክሊል በፊት የድንግልናችሁን ክብር ስላጣችሁት የፈፀማችሁትን ጥፋት ለንስሓ አባት በመናገር ቀኖና ከተቀበላችሁ በኋላ በስጋው ደሙ መጋባት ትችላላችሁ። ስርአተ ተክሊል ግን መፈፀም አይቻልም። ዋናው ነገር ለስጋዊ ስም እና ዝና ተብሎ እግዚአብሔርን በሚያሳዝን ሁኔታ የማይገባንን ስርአተ ተክሊል ከመፈፀም ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ እውነቱን አረጋግጠን የምናገኘው ክብር በስርአተ ተክሊል ከምናገኘው ክብር እኩል ስለሆነ የሚያሳስበን እና የሚያስጨንቀን ነገር አይኖርም።

መልስ፦አዎ ከቅዳሴ በኋላ ማንኛውም ያስቀደሰ ሰው የቅዳሴ ፀበል መጠጣት፣ መጠመቅ መረጨትም ሆነ የቀደሱትን ካህን ቤትን ጸበል ማስረጨት ይችላል።  የቀደሱት ካህናት እና የቆረቡት ምእመናን ግን ከቅዳሴ በኋላ ፀበል መጠጣት እንጂ መጠመቅ አይችሉም። ስለዚህ ጠያቂያችን ስርዓቱን በዚህ ይረዱት ዘንድ ለጥያቄዎ ይህን አጭር ምላሽ ልከንልዋታል። 

በተጨማሪም ከዚህ በፊት ስለ ፀበል ያስተላለፍነውን ማብራሪያ አንብበው ይረዱ ዘንድ ከዚህ በትች ልከንልዎታል።

ፀበል በ2 ከፍለን ልናየው እንችላለን 1ኛው በቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ወይም ከቤተክርስቲያኑ ርቆ ባለ በፈቃደ እግዚአብሔር የበቁ መንፈሳዊ አባቶች በሰጡት አቅጣጫ የሚፈልቅ ፀበል አለ። 2ኛው ጠያቂያችን እንዳሉት በቅዳሴ ግዜ ከቅዱስ ስጋውና ከክቡር ደሙ ጋር አብሮ የሚሰጥ የቅዳሴ ፀበል አለ። የመጀመሪያው በቅጽር ቤተክርስቲያን ወይም ከቅጽረ ቤተክርስቲያን ውጭ ሁኖ በፈጣሪ ስም እና በቅዱሳን ስም የፈለቀው ፀበል የተለያየ ደዌ እና መናፍስት ያለባቸው እንዲም ደግሞ ጤነኛ ሰወች ለበረከት የሚጠመቁበትና የሚጠጡት እንዲሁም ቤታቸውን ንብረታቸውን ሀብታቸውን ከአጋንንት መንፈስ ለመጠበቅ የሚረጩበት ፀበል በእግዚአብሔር ቃል የተቀደሰ እና ልዩ ልዩ የእግዚአብሔር ፀጋ ያደረባቸው አባቶች በፀሎታቸው እና በቡራኬያቸው ያከበሩት ፀበል ስለሆነ ወደ ቤተክርስቲያን መቅረብ የቻለ ፀበሉን ከቤተክርስቲያን አገልጋዮች እጅ ተቀብሎ ይሄዳል፤ በተለያየ ምክንያት ወደቤተክርስቲያን ቅጽር ግቢ መቅረብ ያልቻሉ ግን በመልእክተኛ ወይም በሞግዚት ፀበሉ ተወስዶላቸው ፈውስ ያገኙበታል ማለት ነው። የዚህ አይነት ፀበል በዚህ አይነት አገልግሎት የሚፈፀም ነው። የዚህ በረከት መነሻ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በራሱ ፈቃድ ከ 38 አመት ጀምሮ በፅኑ ደዌ ታሞ የነበረውን መፃጉን በፈወሰው ግዜ መዳን ትወዳለህን ብሎ ሲጠይቀው ለመዳን ይችል ዘንድ ወደ ፀበሉ የሚያደርሰው የቅርብ ረዳት እንደሌለው እና ከሱ ቀድሞ ወደ መጠመቂያው ፀበል የገቡ እንደሚድኑ ምስክርነቱን የሰጠበት የቅዱስ ወንጌል ቃል የሚያስረዳ ነው። (ዮሐ 5፥1-15) 

2ኛውየቅዳሴ ፀበል ስለተባለው እንኳንስ ሰማያዊና ዘለአለማዊ ህይወት የሚያሰጠውን ፀበል ቀርቶ በዚህ በምንኖርበት ምድራዊ ስርዓት እንኳን ከመጀመሪያው ጀምሮ በፕሮግራማችን ላይ የተገኘ ሰው ቅድሚያ ተሰጥቶት በአክብሮት ለዚያ ፕሮግራም የተዘጋጀውን የክብር መስተንግዶ እንደሚያገኝ በሁላችንም ዘንድ የተለመደ ስርዓት ነው። ከዚህ በላይ እጅግ የሚከብረውን እና ዘላለማዊ ህይወት የሚያሰጠውን የቅዳሴ ፀበል በእለተ አርብ ጌታ በመስቀል ላይ ስለኛ በከፈለው ዋጋ ከቀኝ ጎኑ ማየ ህይወት (የህይወት ውሀ) የተገኘ ስለሆነ ቢያንስ እንኳን የበለጠ በረከትና ህይወት እንድናገኝበት ቁመን ካስቀድሰን በኋላ ቅዱስ ቁርባን ባንቀበል እንኳን ፀበሉን በበረከት መጠጣት እንደሚገባን ስርዓተ ቤተክርስቲያን ይፈቅዳል። ከዚህ ውጭ ግን በፈለግነው ሰአት እና ጊዜ መጥተን ቅዳሴውን ቁመን ሳናስቀድስ እና የቅዳሴውን ስርአት ሳንከታተል ፀበሉን ብንጠጣ ወደ ቤታችንም ብንወስደው እንደ ኀጢአተኛ ባያስቆጥርም እንኳን ከሰነፎች እንደ አንዱ ሊያስቆጥረን ይችላል። ምክንያቱም ጌታ በወንጌል እንደተናገረው አብዝቶ የሚወደውን ብዙ ኀጢአቱን ይቅር እንደሚል ወይም ብዙ በረከቱን እንደሚያድል፤ በጥቂቱ የሚወደውን ደግሞ ጥቂት ኀጢአቱን ይቅር እንደሚልና ጥቂት በረከት እንደሚሰጥ የተናገረው ለኛ መንፈሳዊ ህይወት እጅግ አስተማሪ ስለሆነ  በዚሁ መሰረት እንድትረዱት መልዕክታችንን አናስተላልፋለን።

https://yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ/

ጠያቂያችን ስለ ንስኀ ቀኖናም ሆነ ስለ ቄደሩ እና ስለሌላውም ወደ ንስኀ አባትዎ ቀርበው በንስኀ አባትዎ በተሰጠዎት የንስኀ ቀኖና የፈፀሙ ከሆነ ስለዚህ ጉዳይ እርስዎን የሚያሳስብዎት አይደለም።  ከሌላ አባትም ጋር በዚህ መመካከርም ሆነ ግራ መጋባት የለብዎትም። ምናልባት የቀኖና ቤተክርስቲያን እና በአንቀፀ ንስኀ ካለው ስርዓት አኳያ ተጨማሪ ትምህርት እና ምክር ለማግኘት ካስፈለገዎ ግን በውስጥ መስመር ቢያገኙን ልንገልፅልዎት እንችላለን።

 የቄደር ጥምቀት በንስኀ ቀኖና ውስጥ የሚካተት ስርዓት ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው የቄደር ጥምቀት የሚታዘዝለት ሃይማኖቱ ወይም ኦርቶዶክሳዊ የክርስትና ስርዓት የማይፈቅድለትን የተከለከለውንና ነውር የሆነውን ተግባር የፈፀመ ክርስቲያን የሚፈፅመው የንስሀ ቀኖና እንደሆነ ማወቅ ይገባል። የቄደር ጥምቀት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች የምግባር ችግር ያለባቸው እንደሆኑ ከዚህ በፊት ቄደር ለመጠመቅ የሚያስፈልገንን ዋና ምክንያታዊ ነገር በፈፀምነው የኀጢአት ጥፋት ነው። ከዚህ በፊትም ለቄደር ጥምቀት የሚያበቁ የጥፋት ወይም የኀጢአት አይነቶችን በዝርዝር እና በስፋት ገልፀናቸዋል።  ስለዚህ ማንኛውም ኦርቶደክሳዊ ክርስቲያን የፈፀመውን ኢክርስቲያናዊ ተግባር ወይም ኀጢአት በራሱ አምኖ እና ተፀፅቶ ለመንፈሳዊ አባቱ  ሲናዘዝ እንደ ቤተክርስቲያናችን ቀኖና የቄደር ጥምቀት የሚያስፈልገው ጥፋት ሆኖ ከተገኘ የቄደር ጥምቀት እንዲደረግ ይደረጋል። በአንፃሩ የቄደር ጥምቀት የሚያስፈልገው አይነት ከሆነ ደግሞ አንቀፀ ንስኀው የቤተክርስቲያን ቀኖና በሚያዘው ሌላ የንስኀ ቀኖና ይሰጣል ማለት ነው። ስለዚህ ጠያቂያችን የቄደር ጥምቀት አንዱ የንስኀ ክፍል መሆኑን እንዲረዱት ይህን አጭር መልዕክት ልከንልዎታል።

ጠያቂያችን ስለ ንስኀ ቀኖናም ሆነ ስለ ቄደሩ እና ስለሌላውም ወደ ንስኀ አባትዎ ቀርበው በንስኀ አባትዎ በተሰጠዎት የንስኀ ቀኖና የፈፀሙ ከሆነ ስለዚህ ጉዳይ እርስዎን የሚያሳስብዎት አይደለም።  ከሌላ አባትም ጋር በዚህ መመካከርም ሆነ ግራ መጋባት የለብዎትም። ምናልባት የቀኖና ቤተክርስቲያን እና በአንቀፀ ንስኀ ካለው ስርዓት አኳያ ተጨማሪ ትምህርት እና ምክር ለማግኘት ካስፈለገዎ ግን በውስጥ መስመር ቢያገኙን ልንገልፅልዎት እንችላለን።
 
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ
 ጠያቂያችን ፀበል ለመጠመቅ፣ ወይም   ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል፣ ወይም ወደ ቤተመቅደስ ተጠግተን ለማስቀደስ ለ 3 ቀን ከስጋ ስርዓት እንድንርቅ ያስፈልጋል። ይህ የሚደረግበት ምክንያትም ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስለኛ በተቀበለው መከራ በእለተ አርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ስጋው ለይቶ 3 መአልትና 3 ለሊት በከርሰ መቃብር ውስጥ ቆይቷል። በዚህም ምክንያት ቅዱሳን ሐዋሪያት እና ከሱ ጋር ይከተሉት የነበሩት ደቀመዛሙርት የጌታን ትንሳኤ ሳናይ የሚበላ አንበላም የሚጠጣም አንጠጣም ብለው በፆም ተወስነው ስለቆዩ ነው። ስለዚህ ዛሬም የምንቀበለው ቅዱስ ቁርባን የክርስቶስን አማናዊ ስጋና አማናዊ ደም ስለሆነ ያንን መነሻ አብነት አድርገን ለ 3 ቀናት ንፅህናችንን እና ቅድስናችንን ጠብቀን የምንቆየው ነው።
 
በመሆኑም ህግ እና ቀኖና የሆነውን ነገር በህግነትና በቀኖናነቱ የተወሰነውን እውነቱን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ በደካማ ስጋችን ተፈትነንና ስጋዊ ምኞት አሸንፎን ቀኖናን የሚሽር ስህተት ፈፅመን ብንገኝ ወይም ደግሞ ከ 3 ቀን ባነሰ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ጠያቂያችን ያነሱትን ስህተት ፈፅሞ ቢገባ ያ ክርስቲያን ፈፅሞ የተወገዘ የተረገመ ነው ማለት አይደለም። የቤተክርስቲያን ስርዓት እና ቀኖና በመሻሩ ተግሳፅና ምክር ሊሰጠው ይችላል። ወደፊት እያወቀ እንዲህ አይነት ጥፋት እንዳትፈፅም ተብሎ ምክር ይሰጠዋል። ይሄ የሚሆነው በህጋዊ ጋብቻ ተወስነው ለሚኖሩ ነው። ከዚህ ውጭ ለሚሆነው ግን እንኳን ቤተክርስቲያን በድፍረት ለገባንበት ይቅርና ከሕግ ውጭ ላደረግነው ግንኙነትም ከባድ የቀኖና ቅጣት ይጠብቀዋል። በዚሁ መሰረት ጠያቂያችን ቀኖና ባለመሻር እና ከእግዚአብሔር በረከት ለማግኘት በምናደርገው መንፈሳዊ አገልግሎት በነፍስ የምንጎዳበት እርግማን እንዳያመጣብን ከወዲሁ ክርስቲያናዊ ስነምግባር እና ጥንቃቄ ሊኖረን ይገባል በማለት መልዕክታችን እናስተላልፋለን።
 
በመጨረሻም ፤ ወደ ቅዱስ ቁርባን ወይም ወደ ቤተክርስቲያን ከስንት ቀን ጀምሮ ንፅህናችንን መጠበቅ እንዳለብን እንደዚሁ ከዚህ በፊት ያስተላለፍነውን ሰፊ መልዕክት እንዲመለከቱትና ተጨማሪ ግንዛቤ እንዲኖርዎት እንደሚከተለው አያይዘን ልከንልዎታልና አንብበው ሃሳቡን ይረዱ።
 
በትዳር ላይ ላሉ ባልና ሚስት   ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ከተራክቦ ወይም ከግንኙነት ለ 3 ቀን  መራቅ እንዳለባቸው እና ከቀረቡም በጓላ ለስንት ሰዓታት መታገስ እንዳለባቸው ከዚህ በፊት መልዕክት ማስተላለፋችንን እናስታውሳለን።  ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ከሐሙስ በኋላ ያሉትን ቀናት ማክበር አለብን። ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ብቻ ሳይሆን ፀበል ለመጠመቅ፣  ወደ ቤተከርስቲያን ገብቶ ለመፀለይና ለመሳለምም ሩካቤ ስጋ አድርጎ መሄድ አይፈቀድም። ምናልባት እንደተባለው የተለመደ የዘወትር ፀሎታችንን በቤታችን አካለ ስጋችንን ታጥበን በፀሎት ቤታችን ቆመን ማድረስ እንችላለን ወይም ወደ ቤተክርስቲያን ሄደን ከመግቢው ቅጽር ሆነን መፀለይ እንችላለን።  
 
ስለመንፈሳዊ ወይም ስለ ክርስቲያናዊ ህይወት ከባልና ሚስት አንዱ ጥንካሬ ካለው ማሸነፍ ያለበትና ተቀባይነት ያለው የሃይማኖቱና የነፍሱን ጉዳይ ተቀዳሚ እና ተፈፃሚ መሆን ያለበት መሆን አለበትና ጠያቂያችን ሃሳቡን በዚህ እንዲረዱት እንመክራለን።
 
በማንኛውም ግዜ የፆም የፀሎት ሱባኤ በራሳችንም ይሁን በአባቶቻችን ቀኖና ተሰጥቶን የፆምና የፀሎት ሱባኤ በያዝን ግዜ፣ በእለተ ሰንበት እና በታወቁ በአላት ቀን ፈፅሞ ሚስትም ከባልዋ ተለይታ ወንድም ከሚስቱ ተለይቶ መኝታቸውንም የተለየ አድርገው የሚበላውንም የሚጠጣውንም ከተለመደው የአመጋገባቸው ስርአት ቀንሰው አጠቃላይ ፈቃደስጋቸውን ተቆጣጥረው ነው መፆም የሚገባቸው። ፆም ራሱን የቻለ ከእግዚአብዜር ጋር የምንገናኝበት የፅድቅ መንገድ ስለሆነ በዚህን ግዜ ማንኛውም ክርስቲያን የስጋ ፈቃዱን መቆጣጠር እንዳለበት የቤተክርስቲያን ቀኖና ይደነግጋል። ይህን ስንል በቀኖና የተደነገጉ 7ቱ አፅዋማትና እንደገናም በአባቶቻችን ሱባኤ ተሰጥቶን የምንፆምባቸው አፅዋማትን ይመለከታል። ይሁን እንጂ ከአቅም በላይ በሆነ ፈተና ፈቃደስጋችን አሸንፎን በዚህ ምኞት ከወደቅን ላጠፋነው ጥፋት የህሊና ፀፀት ተፀፅተን ለንስሐ አባታችን ወደፊት የምንነግረው ሁኖ ፆምና ፀሎትን ሳናቋርጥ እስከመጨረሻው ልንፈፅም ይገባናል።
 
ተጨማሪ ማብራሪያ ፦
1ኛ/ በመሰረቱ የአንድ ቀን ቁጥር የሚጀምረው ከዋዜማው ወይም ከማታው 12 ሰአት ጀምሮ እስከ የቀኑ 12 ሰዓት በድምሩ 24 ሰዓት 1 ቀን ይባላል። ይሄም ማለት ለምሳሌ  የቅዳሜን 24 ሰአት የምንጀምረው ከአርብ የቀኑ 12 ሰአት በኋላ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ የቀኑ 12 ሰአት ድረስ  ነው። ይሄ 1 ቀን ይባላል። ስለዚህ ለምሳሌ የእሁድን በዓል ማክበር የምንጀምረው ከቅዳሜ 12 ሰዓት ጀምሮ ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ የአንድን ቀን  አቆጣጠር ሂደት በዚህ ይረዱት።
 
2ኛ/   አንድ ሰው እሁድ ቤተክርስቲያን ለመግባት ቢያንስ ከአርብ ማታ ጀምሮ ከስጋ ሩካቤ መቆጠብ አለበት ማለት ነው።  
 
– እሁድ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ከሐሙስ በኋላ ያሉትን ቀናት ማክበር አለብን። ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ብቻ ሳይሆን ወደ ቤተከርስቲያን ገብቶ ለመፀለይና ለመሳለምም ሩካቤ ስጋ አድርጎ መሄድ አይፈቀድም። ምናልባት እንደተባለው የተለመደ የዘወትር ፀሎታችንን በቤታችን አካለ ስጋችንን ታጥበን በፀሎት ቤታችን ቆመን ማድረስ እንችላለን ወይም ወደ ቤተክርስቲያን ሄደን ከመግቢው ቅጽር ሆነን መፀለይ እንችላለን።  
 
በአጠቃላይ ስለመንፈሳዊ ወይም ስለ ክርስቲያናዊ ህይወት ከባልና ሚስት አንዱ ጥንካሬ ካለው ማሸነፍ ያለበትና ተቀባይነት ያለው የሃይማኖቱና የነፍሱን ጉዳይ ተቀዳሚ እና ተፈፃሚ መሆን ያለበት መሆኑን እንዲረዱት እንመክራለን።

 በሰው ልጅ ዘንድ የሞት አደጋን የሚያስከትሉ ከፍተኛ ደዌ በተከሰተ ጊዜ፥ ለምሳሌ እንደ ኤች አይ ቪ እና እንደ ኮሮና እና ሌሎችም ገዳይ የሚባሉ በሽታዎች በሁሉም እርዳታ መከላከልና መዳን እንዲቻል ቢሆንና፤ ደግሞ መድኀኒቱን በማቋረጥ የሚያስከትለው አደጋ እስከ ሞት የሚያደርስ ስለሆነ በቤተክርስቲያን እነዚህን ታማሚወች መድኀኒቱን ፀበል እየጠጡም ሆነ እየተጠመቁ ማቋረጥ እንደሌለባቸው  ከዚህ በፊት ከ ኤች አይ ቪ ጋር በተያያዘ በራስዋ ውሳኔ ፈቅዳለች። ስለዚህ የሀኪሞችም ህክምናም ሆነ መድሃኒት ከእግዚአብሔር ጥበብ የተከገኘ ስለሆነ ፀበሉም በእግዚአብሔር ቃል ተባርኮና ተቀድሶ የሚሰጥ ስለሆነ ሁለቱንም በፍፁም እምነት ለመድኀኒትነት የምንወስደው ስለሆነ ኀጢአት የመያስገባን ወይም ኀጢአተኞች የሚያሰኘን አለመሆኑን መረዳት ያስፈልገጋል።

ጠያቂያችን ፤ ‘ሰው ከመጠመቁ በፊት እምነቱ ምንድን ነው?’ ብለው ለጠየቁን የሚከተለውን መልስ ልከንልዎታል። 
ማንኛውም ሰው ከመጠመቁ በፊት ስላለው እድል በ2 መንገድ ልናየው እንችላለን፦፦
 
1ኛ/ የክርስቲያን ልጆች ሆነው 40 እና 80 ቀን ሞልቷቸው እስከሚጠመቁ ድረስ በእነሱ በስጋ የወለዷቸውና ንስኀ አባታቸውም ስለሆኑ ሃይማኖታቸው ምንድነው ለሚለው ‘የእንክርዳድ ዘር እንክርዳድ ነው የሚያበቅለው የስንዴ ዘር ደግሞ ስንዴ ነው የሚያበቅለው’ እንደሚባለው፤ እነሱ ክርስቲያኖች ናቸውና ሌላ ህይወት እንዳላቸው መታሰብ የለበትም። ምክንያቱም ገና በእናት መሀፀን ፅንስ ሲዘራ ጀምሮ ክርስቲያን የሆነው እናትም ሆነች አባት በሃይማኖት እና በምግባር ፀንተው ቅዱስ ቁርባን እየተቀበሉ፣ በመስቀል እየተባረኩ፣ እየተጠመቁ ፣ እየፀለዩ ቤተክርስቲያን እየተሳለሙ፣ ቃለ እግዚአብሔር እየሰሙ ስለሚኖሩ ከነዚህ ህይወት የተቀዳው አካል ክርስቲን ነው እንጂ ሌላ አካል ነው ተብሎ ሊታመን ስለማያስፈልግ ነው።
 
2ኛ/ በሌላ ሃይማኖት ኖሮ ሃይማኖት የለሽ ሆኖ ከቆየ በኋላ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት እና  የኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያናዊ ምግባርን ተቀብሎ ለመጠመቅ ቢፈልግ ከመጠመቁ በፊት ሃይማኖቱ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን እንደማይባል መታወቅ አለበት። በምክረ ካህን ተመክሮና ተሰብኮ ፣ቀኖና ተሰጥቶት፣ በፍጹም  እምነት ውስጥ መጥቶ ከተጠመቀ በኋላ ግን ስመ ክርስትና ተሰይሞለት ፥ ክርስትናው በኦርቶዶክሳዊያን በቤተክርስቲያን ፊት በአማኞች ፊት ተረጋግጦለታልና ከዚህ በኋላ ክርስቲያን ይባላል።
 
በቤተክርስያን ቀኖና አንድ  የተወለደ ህፃን ለሞት የሚያደርስ ደዌ ቢያሰጋው እንዲጠመቅ ይፈቀዳል። ይህም ሳይሆን ቀርቶ በእግዚአብሔር ቢጠራ ከላይ በ1ኛ ተ.ቁ. ላይ እንደገለፅነው የክርስቲያን ልጅ ክርስቲያን ነው እንዳልነው ሁሉ በዚያ የእድሜ ደረጃም ህፃናት እግዚአብሔርን  የሚያሳዝን፣ ሰውን የሚያስቀይም እዳ በደል የሚሆን ኀጢአት ያልፈፀሙ ስለሆኑ እነሱ የመንግስተ ሰማይ ልጆች ናቸው። ሄሮድስ በግፍ ያስገደላቸው እልፍ የቤተልሔም ሕፃናት ከመላእክት ማህበር እንደተቆሩ ሁሉ የእነዚህም ህፃናት እድል ፋንታ እንደዚህ ይሆናል። በመሰረቱ  ስንት ኀጢአተኛ በበዛበት ዘመን እነዚህ ህፃናት ይኮነናሉ ወይ? ብሎ ማሰብ በራሱ የአይምሮን ደህንነት ጥያቄ ያስገባል። ማንኛውም ክርስቲያን እንድንጠመቅ አምላካዊ ትዕዛዝ ቢሆንም ተጠምቀን የእግዚአብሔር ልጅ መሆናችንንና ፍፁም ክርስቲያን መሆናችን በእርሱ የረቀቀ ጥበቡ ከሰው ስንወለድ እንደሚገለፀው አካላዊ እይታ አይነት ከመንፈስ ቅዱስ ስንወለድ በአይናችን የምናየው በእጃችን የምንዳስሰው አይደለምና፤ ስለዚህ እነዚህ ህፃናት ደግሞ ከመላእክት ማህበር እንደሚደመሩ በረቀቀ ጥበቡ ስለሚፈፅመው እኛ የራሳችንን ስራ መስራት የሚገባንን ትተን በእግዚአብሔር ስራ ውስጥ ገብተን ሊያስጨንቀን የሚገባ አይደለም።

ጠያቂያችን፥ ‘በ40 እና በ80 ቀን ካልተጠመቀ ሙስሊም ነው ይሉኛል’ ብለው ላሉት ፥ በመሰረቱ እነሱ የሚሉት ነገር ሁሉ የእኛ ባህሪና የእኛ መገለጫ አይደለም። ሁልጊዜ ክፉ መንፈስ ያለባቸው በሃይማኖት የእግዚአብሔርን ስራ መፈታተን እና ማጣጣል ልማዳቸው ስለሆነ ፥ እርስዎ መልሱን ከላይ በቁጥር 1 እና 2 በመመልከት የትኛው እስላም እንደሚባል በዚህ አንብበው እንዲረዱት እየጋበዝን ለበለጠ መረዳት አስፈላጊ ከሆነም ወደፊት ስለ ጥምቀትና  ስለ እግዚአብሔር ልጅነት ትምህርት የምንሰጥበት ይሆናል።
 
መልስ# 4፦ ያልተጠመቁ ህፃናት ሲኦል ከገቡ የእግዚአብሔር ቸርነት የት አለ? ከላይ እንደገለፅነው የክርስቲያን ልጅ ክርስቲያን ነው ብለናል። በሌላም መልኩ መልካም ዛፍ መልካም ፍሬ እንደሚያፈራ፤ ክፉ ዛፍ ደግሞ መራራ ፍሬ እንደሚያፈራ ይታወቃል። ፈፅሞ ሰይጣን የማረከው ካልሆነ በስተቀር የክርስቲያን ልጅ ክርስቲያን ፣ የመናፍቅ ልጅ መናፍቅ፣ ከየሃዲ ልጅ ከሃዲ ነው። ጌታችን ኢየሱስም መልካም ዛፍ በፍሬው ይታወቃል ክፉ ሰዎችንም በፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን በማለት በነገረን መሰረት የክርስቲያን ልጆች ክርስቲያን እንደሚሆኑ እግዚአብሔርም ቤተክርስቲያንም ስለምታውቅ እነሱ ለጥምቀት ባይደርሱ የእግዚአብሔርን ሰማያዊ መንግስት እንደሚወርሱ ቤተክርስቲያን የምታስተምረው ነው። ከዚህ ውጪ ነገሮችን ሁሉ አጣመን ከመመልከት ይልቅ ቀና በሆነ መንገድ ካየነው ሃሳቡን በግልፅ ልንረዳው እንችላለን። ዋናው ነገር እግዚአብሔር ምን ብንሆን እንደሚያፀድቀን ምን ብንሆን ደግሞ እንደሚኮንነን አስቀድሞ ስላስቀመጠልን በዚህ ተረድገተን ብንተጋ መልካም ነው፤ ከዚህ ውጪ እርሱ ረቂቅ በሆነ ጥበቡ የሚፈፅመው ነው እንጂ እኛ በምናስበው መንገድ እየተረጎምን በመመልከት ‘የእግዚአብሔር ቸርነት የት አለ?’ በማለት የእርሱን ስራ መዳኘት ግን አግባብ አይደለም።
 
‘ሰው ከመጠመቁ በፊት ከርስቲያን ከሆነ ለምን እንጠመቃለን?’ ብለው ለጠየቁን ፤ በመሰረቱ ሰው ከመጠመቁ በፊት ክርስቲያን ነው የሚል አስተምሮ የለንም። ይህን በዝርዝር ለመረዳት ከፈለጉ ከዚህ በላይ የሰጠናቸውን መልሶች በማስተዋል እንዲያነቡ እንመክራለን።

ጠያቂያችን፤  ከዚህ በፊት ቄደር ጥምቀት የሚያስፈልገው ምን አይነት ህጸጽ ሲኖረው እንደሆነና እንዴት እና በማን መጠመቅ እንደለበት በሰፊው መልዕክት ማስተላለፋችንን እናስታውሳለን። እርስዎም እንዳነበቡት ቢገልጹልንም፥ የጠየቁት ጥያቄ ግን ባስተላለፍነው መልዕክት የተብራራ ስለሆነ በድጋሚ እንዲያነቡትና ምናልባት አሁንም ግልፅ ያልሆነልዎት ነገር ካለ፤ ወይም እኛ የጥያቄዎን ሃሳብ በትክክል አልተረዳነው ከሆነ በውስጥ መስመር ቢያገኙን ልናብራራልዎት እንችላለን።
 
የቄደር ጥምቀት በንስኀ ቀኖና ውስጥ የሚካተት ስርዓት ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው የቄደር ጥምቀት የሚታዘዝለት ሃይማኖቱ ወይም ኦርቶዶክሳዊ የክርስትና ስርዓት የማይፈቅድለትን የተከለከለውንና ነውር የሆነውን ተግባር የፈፀመ ክርስቲያን የሚፈፅመው የንስሀ ቀኖና እንደሆነ ማወቅ ይገባል። የቄደር ጥምቀት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች የምግባር ችግር ያለባቸው እንደሆኑ ከዚህ በፊት ቄደር ለመጠመቅ የሚያስፈልገንን ዋና ምክንያታዊ ነገር በፈፀምነው የኀጢአት ጥፋት ነው።   ስለዚህ ማንኛውም ኦርቶደክሳዊ ክርስቲያን የፈፀመውን ኢክርስቲያናዊ ተግባር ወይም ኀጢአት በራሱ አምኖ እና ተፀፅቶ ለመንፈሳዊ አባቱ  ሲናዘዝ እንደ ቤተክርስቲያናችን ቀኖና የቄደር ጥምቀት የሚያስፈልገው ጥፋት ሆኖ ከተገኘ የቄደር ጥምቀት እንዲደረግ ይደረጋል። በአንፃሩ የቄደር ጥምቀት የማያስፈልገው አይነት ከሆነ ደግሞ አንቀፀ ንስኀው የቤተክርስቲያን ቀኖና በሚያዘው ሌላ የንስኀ ቀኖና ይሰጣል ማለት ነው። 
 
 የቄደር ጥምቀት የሚያስፈልግባቸው የሃይማኖት እና የስነ-ምግባር ሕጸጾች የሚከተሉት ናቸው። 
ሃይማኖትን በሚመለከት፦ 
– ጨርሶ ለይቶለት እና ሃይማኖቱን ክዶ ወደ ልዩ ልዩ ሃይሞኖት ከሄደ በኋላ በንስሐ ለመመለስ ቢፈልግ፣
– በቤተክርስትያን ውስጥ እያለም ቢሆን በክህደትና በኑፋቄ የኖረና ከሃይማኖቱ ሕጸጽ ተመክሮና ንስሐ ተሰጥቶት የተመለሰ፣
– ጋኔን የሚስብና የሚያስብ፣
– በዛር መንፈስ የሚጠነቁልና የሚያስጠነቁል በዚህም ሰውን ሁሉ የሚያሰግድ እና የሚያስገብር፣
– በልዩ ልዩ የአምልኮ ባእድ ቦታ አምኖ በተለያየ ቦ
ክርስቲያናዊ ስነምግባርን በሚመለከት፦
– እስላም ያገባ/ች፣ ካቶሊክ ያገባ/ች፣ ፕሮቴስታንት ያገባ/ች፣ (በእምነት የማትመስለውን ወይም የማይመስላትን የገባ/ያገባች)
– በአምልኮ ባዕድ ለጣኦት የታረደውን የበላ፣ በሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ታርዶ የተዘጋጀውን ምግብ የበላ፣
– በቅዱስ መጽሐፍ ለምግብነት ያልተፈቀዱ እንስሳትም ሆነ የዱር አራዊት የበላ
 
እነዚህ ከዚህ በላይ የተገለፁት በሃይማኖትና በስነምግባር ሕጸጽ ናቸው ተብሎ የሚታመኑ ስለሆነ የቄደር ጥምቀትም እንደሚያስፈልጋቸው በቤተ ክርስቲያን የቀኖና መጽሐፍት የተደነገጉ ናቸው። ሆኖም አንድ ክርስቲያን እነዚህን የመሰሉ የጥፋት ስራ ሳያውቅ ከሰራ ጥምቀቱን ተጠምቆ ወደፊት ይህንን የሚመስል ጥፋት እንዳያጠፋ ትምህርት እና ተግሳፅ ይሰጠዋል። እያወቀ ያጠፋ ከሆነ ግን ከቄደር ጥምቀት በኋላም የፆም፣ የስግደት እና የፀሎት ቀኖና ሊሰጠው ይችላል። ሁለተኛም እንዳይበድል ልዩ ከባድ ማስጠንቀቂያ በምክር እና በተግሳፅ ይሰጠዋል። 
 
ከላይ እንደገለጽነው የቄደር ስርዓት የንስሓ አካል ነው። ንስሓ ደግሞ ኀጢአተኞች እስካሉ ድረስ የማይቋረጥ በደለኞችን ከኀጢአት ለማንፃት ተደጋግሞ የሚሰጥ የቀኖና ስርአት ነው። በሽታ ካለ ወይም ደዌ ካለ ህመምተኞች አሉ፤ ህመምተኞች ካሉ ደሞ ሀኪም አለ፤ ሀኪም ካለ ደሞ ፈውስ አለ። በዚህ መሰረት ኀጢአተኞች ካሉ የንስሓ ህይወት አለ፤ የንስሓ ህይወት ካለ ደግሞ ንስሓ አባቶች አሉ። ንስሓ እና የንስሓ አባቶች ካሉ ደግሞ ኀጢአትን ይቅር የሚል ፈጣሪ አለ። ስለዚህ ኀጢአት እስከተሰራ ድረስ የቄደር ጥምቀት የመኖሩ ሁኔታ የግድ ነው። በእርግጥ ማንኛውም ክርስቲያን ኀጢአት ለመስራት ውስጡን አሳምኖ ኀጢአትን አቅዶ መያዝ ፍፁም አይኖርበትም፤ ክርስቲያናዊ ፀባይም አይደለም። ረቂቅ የሆነው ጠላታችን ዲያብሎስ በስውር የሚዋጋን ስለሆነ እኛም ክርስቲያኖች ጠላታችን ዲያብሎስ እንዳያሸንፈን እግዚአብሔርን ጋሻና መከታ አድርገን በእናቱ ድንግል ማርያም እና በቅዱሳን አማላጅነት እና አስታራቂነት እየተረዳን እና እየታገዝን የክፉ ሃሳብ ሁሉ ምንጭ የሆነው ሠይጣንን ለማሸነፍ ሁል ግዜ መትጋት ይገባናል። ከእኛ አቅም በላይ የሆነ ከባድ ፈተና ቢያጋጥመን ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ይቀላል። ለቄደር ጥምቀት የሚያበቃ ኀጢአት ለሰሩ ሁሉ የቄደር ጥምቀት ያስፈልጋቸዋል። ስለሆነም ይሄንን የኀጢአት ጥፋት ደግሞ እስካላቆምን ድረስ ቄደር እንደሚቀጥል ሁላችሁም ልትገነዘቡት ያስፈልጋል። ሌሎችንም የንስሓ ስርአቶች በዚህ አይነት መመልከት ያስፈልጋል። በመሰረቱ 5500 ዘመን የነበረው የኀጢአት በደላችን ካሳ ከፍሎ በሞቱ ፍፁም ፍቅሩን ያሳየን የእየሱስ ክርስቶስ ካሁን በኋላ ኀጢአት የሚሰሩ ይቅር አይባሉም ብሎ በጭካኔ አልፈረደብንም። ለአምላካችን መድኀኒአለም ክብር ይግባውና ስፍር ቁጥር የሌለውን ይቅርታ እና ቸርነቱን እንዴት እንዳበዛልን ወንጌላዊ ቅዱስ ማቴዎስ እንደነገረን “በዚያን ግዜ ጴጥሮስ ጌታ ሆይ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ግዜ ልተውለት? እስከ 7 ጊዜን? አለው። እየሱስም እንዲህ አለው እስከ 70 ጊዜ 7 እንጂ እስከ 7 ጊዜ አልልህም…እልፍ መክሊት እዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደእሱ አመጡ የሚከፍለው ቢያጣ እርሱ እና ሚስቱ ልጆቹንም ያለውንም ሁሉ እንዲሸጥ እና እዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ። ስለዚህ ባርያው ወድቆ ሰገደለትና ጌታ ሆይ ታገሰኝ ሁሉንም እከፍልሃለው አለው። የዛም ባርያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው እዳውንም ተወለት” በዚህም መለኮታዊ ቃል መሰረት አምላካችን እግዚአብሔር የኛን ኅጢአት ይቅር የሚልበት የጊዜ ገደብ እና ቁጥር የሌለው መሆኑን ቸርነቱና ምህረቱ ስለኛ የበዛ መሆኑን ይህ የወንጌል ቃል ያስረዳናል። (ማቴ 18፥21-27)
ስለዚህ ጠያቂያችን ባጭሩ ይህንን ማብራሪያ ልከንልዎታልና አንብበው ይረዱት።
ጠያቂያችን ፀበል ለመጠመቅ፣ ወይም   ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል፣ ወይም ወደ ቤተመቅደስ ተጠግተን ለማስቀደስ ለ 3 ቀን ከስጋ ስርዓት እንድንርቅ ያስፈልጋል። ይህ የሚደረግበት ምክንያትም ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስለኛ በተቀበለው መከራ በእለተ አርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ስጋው ለይቶ 3 መአልትና 3 ለሊት በከርሰ መቃብር ውስጥ ቆይቷል። በዚህም ምክንያት ቅዱሳን ሐዋሪያት እና ከሱ ጋር ይከተሉት የነበሩት ደቀመዛሙርት የጌታን ትንሳኤ ሳናይ የሚበላ አንበላም የሚጠጣም አንጠጣም ብለው በፆም ተወስነው ስለቆዩ ነው። ስለዚህ ዛሬም የምንቀበለው ቅዱስ ቁርባን የክርስቶስን አማናዊ ስጋና አማናዊ ደም ስለሆነ ያንን መነሻ አብነት አድርገን ለ 3 ቀናት ንፅህናችንን እና ቅድስናችንን ጠብቀን የምንቆየው ነው።
 
በመሆኑም ህግ እና ቀኖና የሆነውን ነገር በህግነትና በቀኖናነቱ የተወሰነውን እውነቱን ማወቅ አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ በደካማ ስጋችን ተፈትነንና ስጋዊ ምኞት አሸንፎን ቀኖናን የሚሽር ስህተት ፈፅመን ብንገኝ ወይም ደግሞ ከ 3 ቀን ባነሰ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ጠያቂያችን ያነሱትን ስህተት ፈፅሞ ቢገባ ያ ክርስቲያን ፈፅሞ የተወገዘ የተረገመ ነው ማለት አይደለም። የቤተክርስቲያን ስርዓት እና ቀኖና በመሻሩ ተግሳፅና ምክር ሊሰጠው ይችላል። ወደፊት እያወቀ እንዲህ አይነት ጥፋት እንዳትፈፅም ተብሎ ምክር ይሰጠዋል። ይሄ የሚሆነው በህጋዊ ጋብቻ ተወስነው ለሚኖሩ ነው። ከዚህ ውጭ ለሚሆነው ግን እንኳን ቤተክርስቲያን በድፍረት ለገባንበት ይቅርና ከሕግ ውጭ ላደረግነው ግንኙነትም ከባድ የቀኖና ቅጣት ይጠብቀዋል። በዚሁ መሰረት ጠያቂያችን ቀኖና ባለመሻር እና ከእግዚአብሔር በረከት ለማግኘት በምናደርገው መንፈሳዊ አገልግሎት በነፍስ የምንጎዳበት እርግማን እንዳያመጣብን ከወዲሁ ክርስቲያናዊ ስነምግባር እና ጥንቃቄ ሊኖረን ይገባል በማለት መልዕክታችን እናስተላልፋለን።
 
በመጨረሻም ፤ ወደ ቅዱስ ቁርባን ወይም ወደ ቤተክርስቲያን ከስንት ቀን ጀምሮ ንፅህናችንን መጠበቅ እንዳለብን እንደዚሁ ከዚህ በፊት ያስተላለፍነውን ሰፊ መልዕክት እንዲመለከቱትና ተጨማሪ ግንዛቤ እንዲኖርዎት እንደሚከተለው አያይዘን ልከንልዎታልና አንብበው ሃሳቡን ይረዱ።
 
በትዳር ላይ ላሉ ባልና ሚስት   ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ከተራክቦ ወይም ከግንኙነት ለ 3 ቀን  መራቅ እንዳለባቸው እና ከቀረቡም በጓላ ለስንት ሰዓታት መታገስ እንዳለባቸው ከዚህ በፊት መልዕክት ማስተላለፋችንን እናስታውሳለን።  ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ከሐሙስ በኋላ ያሉትን ቀናት ማክበር አለብን። ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ብቻ ሳይሆን ፀበል ለመጠመቅ፣  ወደ ቤተከርስቲያን ገብቶ ለመፀለይና ለመሳለምም ሩካቤ ስጋ አድርጎ መሄድ አይፈቀድም። ምናልባት እንደተባለው የተለመደ የዘወትር ፀሎታችንን በቤታችን አካለ ስጋችንን ታጥበን በፀሎት ቤታችን ቆመን ማድረስ እንችላለን ወይም ወደ ቤተክርስቲያን ሄደን ከመግቢው ቅጽር ሆነን መፀለይ እንችላለን።  
 
ስለመንፈሳዊ ወይም ስለ ክርስቲያናዊ ህይወት ከባልና ሚስት አንዱ ጥንካሬ ካለው ማሸነፍ ያለበትና ተቀባይነት ያለው የሃይማኖቱና የነፍሱን ጉዳይ ተቀዳሚ እና ተፈፃሚ መሆን ያለበት መሆን አለበትና ጠያቂያችን ሃሳቡን በዚህ እንዲረዱት እንመክራለን።
 
በማንኛውም ግዜ የፆም የፀሎት ሱባኤ በራሳችንም ይሁን በአባቶቻችን ቀኖና ተሰጥቶን የፆምና የፀሎት ሱባኤ በያዝን ግዜ፣ በእለተ ሰንበት እና በታወቁ በአላት ቀን ፈፅሞ ሚስትም ከባልዋ ተለይታ ወንድም ከሚስቱ ተለይቶ መኝታቸውንም የተለየ አድርገው የሚበላውንም የሚጠጣውንም ከተለመደው የአመጋገባቸው ስርአት ቀንሰው አጠቃላይ ፈቃደስጋቸውን ተቆጣጥረው ነው መፆም የሚገባቸው። ፆም ራሱን የቻለ ከእግዚአብዜር ጋር የምንገናኝበት የፅድቅ መንገድ ስለሆነ በዚህን ግዜ ማንኛውም ክርስቲያን የስጋ ፈቃዱን መቆጣጠር እንዳለበት የቤተክርስቲያን ቀኖና ይደነግጋል። ይህን ስንል በቀኖና የተደነገጉ 7ቱ አፅዋማትና እንደገናም በአባቶቻችን ሱባኤ ተሰጥቶን የምንፆምባቸው አፅዋማትን ይመለከታል። ይሁን እንጂ ከአቅም በላይ በሆነ ፈተና ፈቃደስጋችን አሸንፎን በዚህ ምኞት ከወደቅን ላጠፋነው ጥፋት የህሊና ፀፀት ተፀፅተን ለንስሐ አባታችን ወደፊት የምንነግረው ሁኖ ፆምና ፀሎትን ሳናቋርጥ እስከመጨረሻው ልንፈፅም ይገባናል።
 
ተጨማሪ ማብራሪያ ፦
1ኛ/ በመሰረቱ የአንድ ቀን ቁጥር የሚጀምረው ከዋዜማው ወይም ከማታው 12 ሰአት ጀምሮ እስከ የቀኑ 12 ሰዓት በድምሩ 24 ሰዓት 1 ቀን ይባላል። ይሄም ማለት ለምሳሌ  የቅዳሜን 24 ሰአት የምንጀምረው ከአርብ የቀኑ 12 ሰአት በኋላ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ የቀኑ 12 ሰአት ድረስ  ነው። ይሄ 1 ቀን ይባላል። ስለዚህ ለምሳሌ የእሁድን በዓል ማክበር የምንጀምረው ከቅዳሜ 12 ሰዓት ጀምሮ ይሆናል ማለት ነው። ስለዚህ የአንድን ቀን  አቆጣጠር ሂደት በዚህ ይረዱት።
 
2ኛ/   አንድ ሰው እሁድ ቤተክርስቲያን ለመግባት ቢያንስ ከአርብ ማታ ጀምሮ ከስጋ ሩካቤ መቆጠብ አለበት ማለት ነው።  
 
– እሁድ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ከሐሙስ በኋላ ያሉትን ቀናት ማክበር አለብን። ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ብቻ ሳይሆን ወደ ቤተከርስቲያን ገብቶ ለመፀለይና ለመሳለምም ሩካቤ ስጋ አድርጎ መሄድ አይፈቀድም። ምናልባት እንደተባለው የተለመደ የዘወትር ፀሎታችንን በቤታችን አካለ ስጋችንን ታጥበን በፀሎት ቤታችን ቆመን ማድረስ እንችላለን ወይም ወደ ቤተክርስቲያን ሄደን ከመግቢው ቅጽር ሆነን መፀለይ እንችላለን።  
 
በአጠቃላይ ስለመንፈሳዊ ወይም ስለ ክርስቲያናዊ ህይወት ከባልና ሚስት አንዱ ጥንካሬ ካለው ማሸነፍ ያለበትና ተቀባይነት ያለው የሃይማኖቱና የነፍሱን ጉዳይ ተቀዳሚ እና ተፈፃሚ መሆን ያለበት መሆኑን እንዲረዱት እንመክራለን።
 
መልስ፦ በሰው ልጅ ዘንድ የሞት አደጋን የሚያስከትሉ ከፍተኛ ደዌ በተከሰተ ጊዜ፥ ለምሳሌ እንደ ኤች አይ ቪ እና እንደ ኮሮና እና ሌሎችም ገዳይ የሚባሉ በሽታዎች በሁሉም እርዳታ መከላከልና መዳን እንዲቻል ቢሆንና፤ ደግሞ መድኀኒቱን በማቋረጥ የሚያስከትለው አደጋ እስከ ሞት የሚያደርስ ስለሆነ በቤተክርስቲያን እነዚህን ታማሚወች መድኀኒቱን ፀበል እየጠጡም ሆነ እየተጠመቁ ማቋረጥ እንደሌለባቸው  ከዚህ በፊት ከ ኤች አይ ቪ ጋር በተያያዘ በራስዋ ውሳኔ ፈቅዳለች። ስለዚህ የሀኪሞችም ህክምናም ሆነ መድሃኒት ከእግዚአብሔር ጥበብ የተከገኘ ስለሆነ ፀበሉም በእግዚአብሔር ቃል ተባርኮና ተቀድሶ የሚሰጥ ስለሆነ ሁለቱንም በፍፁም እምነት ለመድኀኒትነት የምንወስደው ስለሆነ ኀጢአት የመያስገባን ወይም ኀጢአተኞች የሚያሰኘን አለመሆኑን መረዳት ያስፈልገጋል።
 
መልስ #1 ፦  ጠያቂያችን ፤ ‘ሰው ከመጠመቁ በፊት እምነቱ ምንድን ነው?’ ብለው ለጠየቁን የሚከተለውን መልስ ልከንልዎታል። 
ማንኛውም ሰው ከመጠመቁ በፊት ስላለው እድል በ2 መንገድ ልናየው እንችላለን፦፦
 
1ኛ/ የክርስቲያን ልጆች ሆነው 40 እና 80 ቀን ሞልቷቸው እስከሚጠመቁ ድረስ በእነሱ በስጋ የወለዷቸውና ንስኀ አባታቸውም ስለሆኑ ሃይማኖታቸው ምንድነው ለሚለው ‘የእንክርዳድ ዘር እንክርዳድ ነው የሚያበቅለው የስንዴ ዘር ደግሞ ስንዴ ነው የሚያበቅለው’ እንደሚባለው፤ እነሱ ክርስቲያኖች ናቸውና ሌላ ህይወት እንዳላቸው መታሰብ የለበትም። ምክንያቱም ገና በእናት መሀፀን ፅንስ ሲዘራ ጀምሮ ክርስቲያን የሆነው እናትም ሆነች አባት በሃይማኖት እና በምግባር ፀንተው ቅዱስ ቁርባን እየተቀበሉ፣ በመስቀል እየተባረኩ፣ እየተጠመቁ ፣ እየፀለዩ ቤተክርስቲያን እየተሳለሙ፣ ቃለ እግዚአብሔር እየሰሙ ስለሚኖሩ ከነዚህ ህይወት የተቀዳው አካል ክርስቲን ነው እንጂ ሌላ አካል ነው ተብሎ ሊታመን ስለማያስፈልግ ነው።
 
2ኛ/ በሌላ ሃይማኖት ኖሮ ሃይማኖት የለሽ ሆኖ ከቆየ በኋላ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት እና  የኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያናዊ ምግባርን ተቀብሎ ለመጠመቅ ቢፈልግ ከመጠመቁ በፊት ሃይማኖቱ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን እንደማይባል መታወቅ አለበት። በምክረ ካህን ተመክሮና ተሰብኮ ፣ቀኖና ተሰጥቶት፣ በፍጹም  እምነት ውስጥ መጥቶ ከተጠመቀ በኋላ ግን ስመ ክርስትና ተሰይሞለት ፥ ክርስትናው በኦርቶዶክሳዊያን በቤተክርስቲያን ፊት በአማኞች ፊት ተረጋግጦለታልና ከዚህ በኋላ ክርስቲያን ይባላል።
 
መልስ # 2 ፦ በቤተክርስያን ቀኖና አንድ  የተወለደ ህፃን ለሞት የሚያደርስ ደዌ ቢያሰጋው እንዲጠመቅ ይፈቀዳል። ይህም ሳይሆን ቀርቶ በእግዚአብሔር ቢጠራ ከላይ በ1ኛ ተ.ቁ. ላይ እንደገለፅነው የክርስቲያን ልጅ ክርስቲያን ነው እንዳልነው ሁሉ በዚያ የእድሜ ደረጃም ህፃናት እግዚአብሔርን  የሚያሳዝን፣ ሰውን የሚያስቀይም እዳ በደል የሚሆን ኀጢአት ያልፈፀሙ ስለሆኑ እነሱ የመንግስተ ሰማይ ልጆች ናቸው። ሄሮድስ በግፍ ያስገደላቸው እልፍ የቤተልሔም ሕፃናት ከመላእክት ማህበር እንደተቆሩ ሁሉ የእነዚህም ህፃናት እድል ፋንታ እንደዚህ ይሆናል። በመሰረቱ  ስንት ኀጢአተኛ በበዛበት ዘመን እነዚህ ህፃናት ይኮነናሉ ወይ? ብሎ ማሰብ በራሱ የአይምሮን ደህንነት ጥያቄ ያስገባል። ማንኛውም ክርስቲያን እንድንጠመቅ አምላካዊ ትዕዛዝ ቢሆንም ተጠምቀን የእግዚአብሔር ልጅ መሆናችንንና ፍፁም ክርስቲያን መሆናችን በእርሱ የረቀቀ ጥበቡ ከሰው ስንወለድ እንደሚገለፀው አካላዊ እይታ አይነት ከመንፈስ ቅዱስ ስንወለድ በአይናችን የምናየው በእጃችን የምንዳስሰው አይደለምና፤ ስለዚህ እነዚህ ህፃናት ደግሞ ከመላእክት ማህበር እንደሚደመሩ በረቀቀ ጥበቡ ስለሚፈፅመው እኛ የራሳችንን ስራ መስራት የሚገባንን ትተን በእግዚአብሔር ስራ ውስጥ ገብተን ሊያስጨንቀን የሚገባ አይደለም።
 
መልስ #3 ፦ ጠያቂያችን፥ ‘በ40 እና በ80 ቀን ካልተጠመቀ ሙስሊም ነው ይሉኛል’ ብለው ላሉት ፥ በመሰረቱ እነሱ የሚሉት ነገር ሁሉ የእኛ ባህሪና የእኛ መገለጫ አይደለም። ሁልጊዜ ክፉ መንፈስ ያለባቸው በሃይማኖት የእግዚአብሔርን ስራ መፈታተን እና ማጣጣል ልማዳቸው ስለሆነ ፥ እርስዎ መልሱን ከላይ በቁጥር 1 እና 2 በመመልከት የትኛው እስላም እንደሚባል በዚህ አንብበው እንዲረዱት እየጋበዝን ለበለጠ መረዳት አስፈላጊ ከሆነም ወደፊት ስለ ጥምቀትና  ስለ እግዚአብሔር ልጅነት ትምህርት የምንሰጥበት ይሆናል።
 
መልስ# 4፦ ያልተጠመቁ ህፃናት ሲኦል ከገቡ የእግዚአብሔር ቸርነት የት አለ? ከላይ እንደገለፅነው የክርስቲያን ልጅ ክርስቲያን ነው ብለናል። በሌላም መልኩ መልካም ዛፍ መልካም ፍሬ እንደሚያፈራ፤ ክፉ ዛፍ ደግሞ መራራ ፍሬ እንደሚያፈራ ይታወቃል። ፈፅሞ ሰይጣን የማረከው ካልሆነ በስተቀር የክርስቲያን ልጅ ክርስቲያን ፣ የመናፍቅ ልጅ መናፍቅ፣ ከየሃዲ ልጅ ከሃዲ ነው። ጌታችን ኢየሱስም መልካም ዛፍ በፍሬው ይታወቃል ክፉ ሰዎችንም በፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን በማለት በነገረን መሰረት የክርስቲያን ልጆች ክርስቲያን እንደሚሆኑ እግዚአብሔርም ቤተክርስቲያንም ስለምታውቅ እነሱ ለጥምቀት ባይደርሱ የእግዚአብሔርን ሰማያዊ መንግስት እንደሚወርሱ ቤተክርስቲያን የምታስተምረው ነው። ከዚህ ውጪ ነገሮችን ሁሉ አጣመን ከመመልከት ይልቅ ቀና በሆነ መንገድ ካየነው ሃሳቡን በግልፅ ልንረዳው እንችላለን። ዋናው ነገር እግዚአብሔር ምን ብንሆን እንደሚያፀድቀን ምን ብንሆን ደግሞ እንደሚኮንነን አስቀድሞ ስላስቀመጠልን በዚህ ተረድገተን ብንተጋ መልካም ነው፤ ከዚህ ውጪ እርሱ ረቂቅ በሆነ ጥበቡ የሚፈፅመው ነው እንጂ እኛ በምናስበው መንገድ እየተረጎምን በመመልከት ‘የእግዚአብሔር ቸርነት የት አለ?’ በማለት የእርሱን ስራ መዳኘት ግን አግባብ አይደለም።
 
መልስ #5 ፦  ‘ሰው ከመጠመቁ በፊት ከርስቲያን ከሆነ ለምን እንጠመቃለን?’ ብለው ለጠየቁን ፤ በመሰረቱ ሰው ከመጠመቁ በፊት ክርስቲያን ነው የሚል አስተምሮ የለንም። ይህን በዝርዝር ለመረዳት ከፈለጉ ከዚህ በላይ የሰጠናቸውን መልሶች በማስተዋል እንዲያነቡ እንመክራለን።
ጠያቂያችን፤  ከዚህ በፊት ቄደር ጥምቀት የሚያስፈልገው ምን አይነት ህጸጽ ሲኖረው እንደሆነና እንዴት እና በማን መጠመቅ እንደለበት በሰፊው መልዕክት ማስተላለፋችንን እናስታውሳለን። እርስዎም እንዳነበቡት ቢገልጹልንም፥ የጠየቁት ጥያቄ ግን ባስተላለፍነው መልዕክት የተብራራ ስለሆነ በድጋሚ እንዲያነቡትና ምናልባት አሁንም ግልፅ ያልሆነልዎት ነገር ካለ፤ ወይም እኛ የጥያቄዎን ሃሳብ በትክክል አልተረዳነው ከሆነ በውስጥ መስመር ቢያገኙን ልናብራራልዎት እንችላለን።
 
የቄደር ጥምቀት በንስኀ ቀኖና ውስጥ የሚካተት ስርዓት ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው የቄደር ጥምቀት የሚታዘዝለት ሃይማኖቱ ወይም ኦርቶዶክሳዊ የክርስትና ስርዓት የማይፈቅድለትን የተከለከለውንና ነውር የሆነውን ተግባር የፈፀመ ክርስቲያን የሚፈፅመው የንስሀ ቀኖና እንደሆነ ማወቅ ይገባል። የቄደር ጥምቀት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች የምግባር ችግር ያለባቸው እንደሆኑ ከዚህ በፊት ቄደር ለመጠመቅ የሚያስፈልገንን ዋና ምክንያታዊ ነገር በፈፀምነው የኀጢአት ጥፋት ነው።   ስለዚህ ማንኛውም ኦርቶደክሳዊ ክርስቲያን የፈፀመውን ኢክርስቲያናዊ ተግባር ወይም ኀጢአት በራሱ አምኖ እና ተፀፅቶ ለመንፈሳዊ አባቱ  ሲናዘዝ እንደ ቤተክርስቲያናችን ቀኖና የቄደር ጥምቀት የሚያስፈልገው ጥፋት ሆኖ ከተገኘ የቄደር ጥምቀት እንዲደረግ ይደረጋል። በአንፃሩ የቄደር ጥምቀት የማያስፈልገው አይነት ከሆነ ደግሞ አንቀፀ ንስኀው የቤተክርስቲያን ቀኖና በሚያዘው ሌላ የንስኀ ቀኖና ይሰጣል ማለት ነው። 
 
 የቄደር ጥምቀት የሚያስፈልግባቸው የሃይማኖት እና የስነ-ምግባር ሕጸጾች የሚከተሉት ናቸው። 
ሃይማኖትን በሚመለከት፦ 
– ጨርሶ ለይቶለት እና ሃይማኖቱን ክዶ ወደ ልዩ ልዩ ሃይሞኖት ከሄደ በኋላ በንስሐ ለመመለስ ቢፈልግ፣
– በቤተክርስትያን ውስጥ እያለም ቢሆን በክህደትና በኑፋቄ የኖረና ከሃይማኖቱ ሕጸጽ ተመክሮና ንስሐ ተሰጥቶት የተመለሰ፣
– ጋኔን የሚስብና የሚያስብ፣
– በዛር መንፈስ የሚጠነቁልና የሚያስጠነቁል በዚህም ሰውን ሁሉ የሚያሰግድ እና የሚያስገብር፣
– በልዩ ልዩ የአምልኮ ባእድ ቦታ አምኖ በተለያየ ቦ
ክርስቲያናዊ ስነምግባርን በሚመለከት፦
– እስላም ያገባ/ች፣ ካቶሊክ ያገባ/ች፣ ፕሮቴስታንት ያገባ/ች፣ (በእምነት የማትመስለውን ወይም የማይመስላትን የገባ/ያገባች)
– በአምልኮ ባዕድ ለጣኦት የታረደውን የበላ፣ በሌላ ሃይማኖት ተከታዮች ታርዶ የተዘጋጀውን ምግብ የበላ፣
– በቅዱስ መጽሐፍ ለምግብነት ያልተፈቀዱ እንስሳትም ሆነ የዱር አራዊት የበላ
 
እነዚህ ከዚህ በላይ የተገለፁት በሃይማኖትና በስነምግባር ሕጸጽ ናቸው ተብሎ የሚታመኑ ስለሆነ የቄደር ጥምቀትም እንደሚያስፈልጋቸው በቤተ ክርስቲያን የቀኖና መጽሐፍት የተደነገጉ ናቸው። ሆኖም አንድ ክርስቲያን እነዚህን የመሰሉ የጥፋት ስራ ሳያውቅ ከሰራ ጥምቀቱን ተጠምቆ ወደፊት ይህንን የሚመስል ጥፋት እንዳያጠፋ ትምህርት እና ተግሳፅ ይሰጠዋል። እያወቀ ያጠፋ ከሆነ ግን ከቄደር ጥምቀት በኋላም የፆም፣ የስግደት እና የፀሎት ቀኖና ሊሰጠው ይችላል። ሁለተኛም እንዳይበድል ልዩ ከባድ ማስጠንቀቂያ በምክር እና በተግሳፅ ይሰጠዋል። 
 
ከላይ እንደገለጽነው የቄደር ስርዓት የንስሓ አካል ነው። ንስሓ ደግሞ ኀጢአተኞች እስካሉ ድረስ የማይቋረጥ በደለኞችን ከኀጢአት ለማንፃት ተደጋግሞ የሚሰጥ የቀኖና ስርአት ነው። በሽታ ካለ ወይም ደዌ ካለ ህመምተኞች አሉ፤ ህመምተኞች ካሉ ደሞ ሀኪም አለ፤ ሀኪም ካለ ደሞ ፈውስ አለ። በዚህ መሰረት ኀጢአተኞች ካሉ የንስሓ ህይወት አለ፤ የንስሓ ህይወት ካለ ደግሞ ንስሓ አባቶች አሉ። ንስሓ እና የንስሓ አባቶች ካሉ ደግሞ ኀጢአትን ይቅር የሚል ፈጣሪ አለ። ስለዚህ ኀጢአት እስከተሰራ ድረስ የቄደር ጥምቀት የመኖሩ ሁኔታ የግድ ነው። በእርግጥ ማንኛውም ክርስቲያን ኀጢአት ለመስራት ውስጡን አሳምኖ ኀጢአትን አቅዶ መያዝ ፍፁም አይኖርበትም፤ ክርስቲያናዊ ፀባይም አይደለም። ረቂቅ የሆነው ጠላታችን ዲያብሎስ በስውር የሚዋጋን ስለሆነ እኛም ክርስቲያኖች ጠላታችን ዲያብሎስ እንዳያሸንፈን እግዚአብሔርን ጋሻና መከታ አድርገን በእናቱ ድንግል ማርያም እና በቅዱሳን አማላጅነት እና አስታራቂነት እየተረዳን እና እየታገዝን የክፉ ሃሳብ ሁሉ ምንጭ የሆነው ሠይጣንን ለማሸነፍ ሁል ግዜ መትጋት ይገባናል። ከእኛ አቅም በላይ የሆነ ከባድ ፈተና ቢያጋጥመን ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ይቀላል። ለቄደር ጥምቀት የሚያበቃ ኀጢአት ለሰሩ ሁሉ የቄደር ጥምቀት ያስፈልጋቸዋል። ስለሆነም ይሄንን የኀጢአት ጥፋት ደግሞ እስካላቆምን ድረስ ቄደር እንደሚቀጥል ሁላችሁም ልትገነዘቡት ያስፈልጋል። ሌሎችንም የንስሓ ስርአቶች በዚህ አይነት መመልከት ያስፈልጋል። በመሰረቱ 5500 ዘመን የነበረው የኀጢአት በደላችን ካሳ ከፍሎ በሞቱ ፍፁም ፍቅሩን ያሳየን የእየሱስ ክርስቶስ ካሁን በኋላ ኀጢአት የሚሰሩ ይቅር አይባሉም ብሎ በጭካኔ አልፈረደብንም። ለአምላካችን መድኀኒአለም ክብር ይግባውና ስፍር ቁጥር የሌለውን ይቅርታ እና ቸርነቱን እንዴት እንዳበዛልን ወንጌላዊ ቅዱስ ማቴዎስ እንደነገረን “በዚያን ግዜ ጴጥሮስ ጌታ ሆይ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ግዜ ልተውለት? እስከ 7 ጊዜን? አለው። እየሱስም እንዲህ አለው እስከ 70 ጊዜ 7 እንጂ እስከ 7 ጊዜ አልልህም…እልፍ መክሊት እዳ ያለበትን አንድ ሰው ወደእሱ አመጡ የሚከፍለው ቢያጣ እርሱ እና ሚስቱ ልጆቹንም ያለውንም ሁሉ እንዲሸጥ እና እዳው እንዲከፈል ጌታው አዘዘ። ስለዚህ ባርያው ወድቆ ሰገደለትና ጌታ ሆይ ታገሰኝ ሁሉንም እከፍልሃለው አለው። የዛም ባርያ ጌታ አዘነለትና ለቀቀው እዳውንም ተወለት” በዚህም መለኮታዊ ቃል መሰረት አምላካችን እግዚአብሔር የኛን ኅጢአት ይቅር የሚልበት የጊዜ ገደብ እና ቁጥር የሌለው መሆኑን ቸርነቱና ምህረቱ ስለኛ የበዛ መሆኑን ይህ የወንጌል ቃል ያስረዳናል። (ማቴ 18፥21-27)
ስለዚህ ጠያቂያችን ባጭሩ ይህንን ማብራሪያ ልከንልዎታልና አንብበው ይረዱት።

ጠያቂያችን በጾም ጊዜ መጠመቅ ይቻላል ወይ ብለው ለጠየቁን መልሱ አዎ በደንብ አድርጎ ይቻላል ነው። ምክንያቱም የሰው ልጅ በፆም እና በፀሎት በተወሰነ ጊዜ ከስጋ ፈተና ሁሉ እርቆ እግዚአብሔርን መስሎ የሚኖርበት ህይወት ስለሆነ ያኔ መጠመቅም፣ ቅዱስ ቁርባን መቀበልም፣ ሌሎችንም መንፈሳዊ አገልግሎቶች መቀበል እንደውም ከሌላው ጊዜ የበለጠ እና የመረጠ ጊዜ ያደርገዋል። ስለዚህ ጠያቂያችን በፆም ጊዜ መጠመቅ አይከለከልም በማለት ይህን አጭር መልእክት ልከንልዎታል።

 እጣን በብዙ መንገድ ምስጢራዊ አገልግሎት አለው። እጣንም እንደ ሃይማኖታችን ስርዓት ከተመለከትነው በዚህ ምድር ላይ በሃይማኖት እና በምግባር ስንኖር ለእግዚአብሔር ተገዚነታችንን በመግለፅ ለእውነተኛ ንጹሐ ባህሪይ የሁላችንም ፈጣሪና አምላክ ለሆነ ለልዑለ ባህሪይ ለእግዚአብሔር በአምልኮቱ ቀንተን ስንገዛለት የምናቀርበውን ምስጋና፣ ፀሎት ፣ መስዋዕት፣ መባ፣ በአጠቃላይ ለእግዚአብሔር ክብር ይገባል ብለን ባለን የልጅነት መንፈስ በእሱ ፊት የምናቀርበውን ሁሉ እግዚአብሔር ወዶ እንደተቀበለልን የምናረጋገጥ የሁሉ ነገር ማሳረጊያና ማጠቃለያ ከሆነው የቤተክርስቲያን ምስጢር አንዱ ፀሎተ እጣን ወይም ደግሞ በእጣን የምናሳርግበት ስርዓት ነው። እግዚአብሔር ያቀረብንለትን አገልግሎት ወይም መስዋዕት ወይም መታዘዝ ወይም መባ ሁሉ ወዶ ተቀብሎታል የምንለው በእጣኑ አማካኝነት የምንፈፅመው ስርዓተ አምልኮት ነው። ቅዱስ መፅሐፍ እንደሚነግረን የፀሎታችንን እና የመስዋዕታችንን አቅርቦት ወደ እግዚአብሔር በእጣኑ አማካኝነት ስናሳርገው እንደተቀበለው ያረጋግጥልናል።

ስለዚህ ጠያቂያችን ከጥያቄዎ ሃሳብ እንደተረዳነው በቤታችን ውስጥ ወይም ደግሞ በግቢያችን አካባቢ እውነተኛ በሆነ የሃይማኖት ስርዓት ከሁሉ ፈተና ለመዳን ከፈለግን እኛ ከገበያ በገንዘብ ገዝተን ያመጣነውን ዕጣን በራንሳችን ስልጣን እና ዝግጅት ማጠን ሳይሆን፥ የቤተክርስቲያን አባቶችን ወይም ስልጣነ ክህነት ያላቸውን አገልጋዮች ጠርተን እነሱ እጣኑን የሚያከብሩበትን ስርዓተ ጸሎት አድርሰው እንደ ቤተክርስቲያኑ ስርዓት በቤታችን ግቢ ያለውን ማንኛውንም ፈተና ሁሉ ለማራቅ በሚያስችል መንገድ እነሱ ፀሎተ እጣኑን ያሳርጋሉ ወይም ያጥናሉ እንጂ እኛ ራሳችን ገዝተን እንደ አምልኮ ባእድ  በገል የምናጨሰው እጣን ከስርዓተ አምልኮታችን ጋር የሚሄድ ስርዓት ስላልሆነ፤ እስካሁን ድረስ እንደበጎ ነገር በማሰብ የተደረገውን ጥፋት ሳይታወቅ እና ከአባቶቻችን ሳንረዳ ያደረግነው ስለሚሆን ብዙም የሚያጨናንቅ ጥፋት አይደለም። ከዚህ ጥያቄ መልስ በኋላ ግን እኛ በማናውቀው ልዩ ልዩ ምክንያት የሚመጣውን ፈተና ለማራቅ ግቢያችንን እና ወጥተን ወርደን በድካማችን ያፈራነውን ሃብታችንን ህይወታችንን ለማስባረክ ከፈለግን ሁላችንም የሚገባንን ጥንቃቄ አድርገን በአባቶቻችን ፈቃድ ፕሮግራም አድርገን እነሱ ከእጣን ጋር የሚያሳርጉትን ጸሎት ሁሉ በመፀለይ እጣኑን ባርከውና ቀድሰው በእጣኑ ላይም ሊፀለይ የሚገባውን ፀሎተ እጣን አድርሰው እነሱ ስርዓተ ማዕጠንቱን ሊያደርሱ ይገባቸዋል እንጂ እኛ በራሳችን ልናደርገው በቤተክርስቲያናችን ቀኖና አልተፈቀደልንም። እጣኑ በቤተክርስቲያን ስርዓት በካህናት አማካኝነት ሲታጠን የሚታጠነው እጣን ጭሱ መድሃኒተ ስጋ ነፍስ ነው፣ ደዌያችንን ያርቃል፣ እርኩስ መንፈስን ያባርራል፣ መአዛው መንፈስ ቅዱስን የበለጠ እንዲያድር ያደርጋልና በዚህ ስርዓት መፈፀም እንጂ የድርሻንን አለማወቅ በድፍረት ከአባቶች የክህነት ድርሻ ጋር መጋፋት አይገባም።

ስለዚህ ጠያቂያችን እስካሁን ባለማወቅ ባደረጉት ነገር እራስዎትን ማስጨነቅ አይኖርቦትም ነገር ግን ወደፊት በዚህ ምክር አገልግሎት እነዲፈፅሙ ይህን መልዕክት ለእርስዎ እና በአጠቃላይ ለአባላቶቻችን እንዲሁም ይህን መልዕክት የተመለከታችሁ ሁሉ እንዲህ አይነት ገጠመኝ ሲሆን በዚሁ ማብራሪያ እንድትፈፅሙ አደራ እንላለን።

ለሁሉም ነገር እግዚአብሔር በቸርነቱ አይለየን

ጠያቂያችን በመጀመሪያ በሰው ዘንድ ባልተረጋገጠ እና እውነት ባልሆነ አሉባልታ የሰውን የግል ህይወት የሚያጥላሉ እና ሰውን ኀጢአተኛ በሚያደርጉ ሰወች ዘንድ በሚነገርና በሚወራው ሃሳብ ላይ በመነሳት ባልተረጋገጠ ሁኔታ የመጨረሻ ውሳኔና ድምዳሜ ላይ መድረስ አያስፈልግም። እኚህ አባት በትክክለኛ የሚያገለግሉበትን ወይም ደግሞ አባት ሆነው የሚኖሩበት ቤተክርስቲያን የት እንደሆነ ስናውቅ፣ በግል ህይወታቸውም ከስማቸው ጀምሮ ምን እንደሚመስል ምን እንደሚሰሩ የስራ ድርሻቸው ምን እንደሆነ ማወቅ ስንችል በትክክለኛ እኚህ አባት የቅባት ሃይማኖት ተከታይ ናቸው ወይስ የእውነተኛ ቤተክርስቲያን አባት ናቸው የሚለውን ነገር መለየት እንችላለን፤ እንጂ መጀመሪያ ባልተረጋገጠ ምክንያት ሽብር ውስጥ መግባት አያስፈልግም።

እኚህን አባት ሰዎች በሚያሙት ነገር የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አገልጋይ ሆነው ሰዎች እንዲህ ነው ብለው የሚያሙት ነገር ከሆነ የፈለገ እሳቸው ራሳቸውን ደብቀው እውነተኛ አባት በመምሰል የሚሰጡት አገልግሎት የሚሰጡት የንስኀ ህይወት ከሆነ ምንም እንኳን ስልጣነ ክህንት ያላቸው አባቶቻችን የክርስቶስ እንደራሴዎች እና መልዕክተኞች ሆነው የንስኀ ህይወትን ቢሰጡንም ንስኀን ይቅር የሚል ኀጢአትን የሚያስተሰርይልን ግን እውነተኛው አምላክ እሱ የሁላችንም ፈጣሪ እግዚአብሔር ስለሆነ ነው። እንዲህ አይነቶቹ አስመሳዮች አባቶች በህይወቱ ውስጥ ሳይኖሩ እውነተኛ አባት ነን ቢሉ በኀጢአት የሚጠየቁት እራሳቸው እንጂ በየዋህነት እውነተኛ አባቶች ናቸው ብሎ የንስኀ ህይወትን ለመቀበል የሄደ ምዕመን በኀጢአት ስለማይጠየቅ በዚህ መጨናነቅ ፈፅሞ አያስፈልግም።

ነገር ግን እያወቅን እየተነገረን እየተረዳን፣ በግልፅ የሚታይ የሚዳሰስ የሚጨበጥ ማስረጃ እያለን፣ እራሳችን በሃይማኖት ለማይመስሉን አባት ወይም ከእውነተኛይቱ ሃይማኖት ያልሆኑት ሰው ጋር በመሄድ ንስኀ ብንቀበል የራሳችን ጥፋት ስለሆነ እንደገና ዳግም ሌላ አባት ጋር ሄደን የመጀመሪያ ስህተታችንን ነግረን ንስኀ የሚያስገባንንም ኀጢአታችንን ተናዘን ንስኀ መግባት አለብን እንጂ በመጠራጠር ገና ሰዎች በሚያሙት ነገር ግን መጨነቅ የሚያስፈልገን እና እኛን የሚያስጠይቀን አይደለም። ማሰብም የለብን፤ ተገቢም ፈፅሞ አይደለም። ሁሌ ጥሩነትና ገርነት የዋህነት በበዛበት ህይወት ውስጥ የምንኖር ክርስቲያኖች ከምንም በላይ እግዚአብሔር ይህን ጥሩነታችንን ገርነታችንን የዋህነታችንን ተመልክቶ ለማንም አሳልፎ የማይሰጠን አምላክ ስለሆነ በዚህ እኛ በማናውቀው የረቀቀ የስህተት መንፈስ የሚሄዱ ሰዎች ያስጠይቃቸዋል በዚህ በደል ወይም በዚህ የስህተት ወጥመድ እነሱ ራሳቸው ይያዛሉ እንጂ በቅንነት እና በየዋህነት ኀጢአታቸውን ለመናዘዝ የቀረቡትን የእግዚአብሔር ሰዎችን የሚያስወቅስና እንደኀጢአተኛ የሚያስጠይቃቸው ስላልሆነ ጠያቂያችን ከእንዲህ አይነት ሃሳብ እራስዎትን ነፃ እንዲያደርጉ ይህንን መልዕክት አስተላልፈናል። ሌሎች አባላቶቻችንም ይህን የሚመስል ፈተና ያጋጠማችሁ እና ወደፊትም የሚገጥማችሁ ካላችሁ በዚሁ ተረዱልን።

ለሁሉም ነገር ቸሩ አምላካችን ልዑለ እግዚአብሔር በየጊዜው ከሚገጥመን ፈተና እና መከራ ሁሉ ይሰውረን፥ ይጠብቀን ፆሙን በሰላም ያስፈፅመን !

 ጠያቂያችን ፤ በቤታችን ውስጥ ፀበል መጠመቅ ቢያስፈልገን ሀብተ ክህነት ወይም ክህነት የሌለው ሰው ማጥመቅ አይችልም። ነገር ግን በአካባቢያችን ካህን የማይገኝ ቢሆን ካህኑ በውሀው ላይ ፀሎት  ፀልየውበት በመስቀልም ባርከውት አንተው በላይህ ላይ ፀበሉን እያፈሰስክ ተጠመቅ ብለው ከሰጡን መረጨትም ሆነ በራሳችን ላይ ማፍሰስ እንችላለን። ይህ ግን ማጥመቅን የሚተካ ስርዓት አይደለም። ወደ ገዳም ሄደን የምናመጣው ፀበል ከአባቶች ተፈቅዶ በእቃ የምናውለው ፀበል እኛም ራሳችን መረጨትም እንችላለን ቤተሰቦቻችንም ፀበሉን እንዲጠጡትም ሆነ ሰውነታቸውን እንዲቀቡት ማድረግ ይቻላል፤ ካህንን ተክቶ ግን አንዱ አንዱን ማጥመቅ አይችልም።

ለተጨማሪ ግንዛቤ  ከዚህ በፊት ስለ ጸበል አጠቃቀምና ወደ ቤት የመውሰድ ስርዓት እንዴት እንደሆነ ጥያቄ ቀርቦልን ያሰተላለፍነውን ትምህርታዊ ማብራሪያ ከዚህ በታች ልከንልዎታልና አንብበው ይረዱት፦

ከቅዳሴ በኋላ ማንኛውም ያስቀደሰ ሰው የቅዳሴ ፀበል መጠጣት፣ መጠመቅ መረጨትም ሆነ የቀደሱትን ካህን ቤትን ጸበል ማስረጨት ይችላል።  የቀደሱት ካህናት እና የቆረቡት ምእመናን ግን ከቅዳሴ በኋላ ፀበል መጠጣት እንጂ መጠመቅ አይችሉም።