ስለ ንስሐ
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!" (ማቴ 3: 1-2)
ተከታታይ ትምህርትና ለጥያቄዎት ምላሽ ለማግኘት ቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ
ስለ ንስሐ አገልግሎት መሰረታዊ ትምህርት
ስለ አበነፍስ (ስለ ንስሐ አባት) አገልግሎት በሚመለከት
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ መርጦ የመንጋው እረኞች እንዲሆኑ ለሾማቸው ቅዱሳን ሐዋርያት በአንብሮተ እድ የሰጣቸው ስልጣነ ክህነት ከኃጢአት ማሰሪያ የሚፈታ፣ አመፀኞችን የሚያሥሩበት፤ ቦታ እና ጊዜ የማይወስነው ረቂቅ ስልጣን ነው። ስልጣኑን የሰጣቸውም ራሱ ባለቤቱ “የመንግስተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለው በምድር የምታሥረው ሁሉ በሰማያት የታሠረ ይሆናል በምድር የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል” ማቴ 16:19 “እውነት እላችኋለው በምድር የምታሥሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈቱት በሰማይ የተፈታ ይሆናል” በማለት ለቅዱስ ጴጥሮስ እና ለሁሉም ሐዋርያት አስተምሯቸዋል። የክህነቱ ስልጣን ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ነው፤ ከምድራዊ ስልጣን ጋር የማይነፃፀርና ከፈጣሪ በስተቀር ማንም የማይሽረው መሆኑን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት ገልጾላቸዋል።
ስለክህነት በብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ኪዳን ያለውን አመጣጥና አገልግሎት ወደፊት በስፋት የምንገልጸው ሆኖ፤ አሁን ግን በአጭሩ በንስሐ አባት አያያዝ ዙሪያ ጥያቄ ላላችሁ የምናስተላልፈው መልእክት፤ ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ክህነት የእግዚአብሔር ስጦታ ከሆነና የስልጣኑ አገልግሎትም ቦታ እና ጊዜ የማይወስነው ከሆነ፤ በየትኛውም ክፍለ ዓለም የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ሁሉ በሚኖሩበት ከተማ /አካባቢ/ ቤተክርስትያንና አባቶች ካህናት በቅርብ ከሌሉ፤ በዕውቀታቸውና በሕይወታቸው አስተምረውና መክረው ወደ ንስሐ ሕይወት በማቅረብ በክርስቲያናዊ ስነምግባር እና በሃይማኖታችሁ ጸንታችሁ እንድትኖሩ የሚጠብቋችሁን አባቶች ከየትኛውም ክፍለ ዓለም መርጦ መያዝ ይቻላል። ምክንያቱም በአካባቢያችን በጠዋትና በማታ በቅርበት የንስሐ አባት የሚሆንዎ ካህን ከሌለ ዓለጠባቂና ዓለአስተማሪ አንድም ቀን መኖር ስለማይገባን በቅርብ ከእኛ ጋር በአካለ ስጋ ሆኖ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጠን አባት ከሌለ፤ ያለብንን የውስጥ ችግር ከምንም በላይ እሱ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላካችን ስለሚያውቀው በሃይማኖታቸውና በስነምግባራቸው የተመሰከረላቸውን አባቶች በማነጋገር የንስሐ አባት ማድረግ ይገባናል።
የአንድ እውነተኛ የንስሐ አባት ለንስሐ ልጆቹ ማስተማር የሚገባው እንዲጾሙ፣ እንዲፀልዩ፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲማሩ፣ እንዲያስቀድሱ፣ ንስሐ እንዲገቡ፣ የክስቶስን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንዲቀበሉ (እንዲቆርቡ) አሥራት በኩራት እንዲከፍሉ፣ ለተቸገሩ ወገኖች የርሕራሄ ሥራ እንዲያደርጉ በአጠቃላይ በተዋሕዶ ሃይማኖታቸውና በክርስትያናዊ ሕይወታቸው ጸንትው እንዲኖሩ ስለሆነ፤ ይህ ደግሞ ከየትም ቦታ ሆኖ ዘመኑ በአስገኘው ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ ከንስሐ አባቱ ጋር በየቀኑ መገናኘት ስለሚቻል የተፈለገውን መንፈሳዊ አገልግሎት ለማግኘት እንችላለን ማለት ነው። ከባዱ ፈተና ግን በአንዳንድ አጉል አማካሪ ግራ ተጋብተን የነፍሳችን እረኛና ጠባቂ ከሆኑት አባቶች ተለይተን መኖር ግን በዱርና በሜዳ ያለእረኛ እንደተሰማራ መንጋ እንሆናለን። እንደሚታወቀው እረኛ የሌለው መንጋ በተኩላና በአውሬ ይበላል። ማንኛውም ስጋዊ ሀብታችን ጠባቂና ተቆጣጣሪ ከሌለው በነጣቂዎችና በወንበዴዎች እንደሚዘረፍ ሁሉ በጧት በማታ በአባትነት የሚጠብቁን አበነፍስ (ንስሐ አባት) ከሌለን ከምንም በላይ ክፉና ጨካኝ የሆነው ዲያብሎስ ነፍሣችንን የማይገባትን የክፋትና የአመጽ ሥራ ስለሚያሠራት ያለጠባቂና ያለመካሪ አባት አንድ ቀን መኖር የለብንም።
“ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም” (ሉቃ 5፡32)
ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች
ጌታችን በወንጌሉ ካህናትን “እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ” ማቴ 5 -14 ይላቸዋልና ከርኩሰት አረንቁዋ ከጨለማውና ከኀጢአት ሥራ ሁሌ በንስሐ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚመሩንና ኀጢአትን ጠልተን በበጎ ምግባር እንድንኖር መንገዱን የሚመሩን ናቸው፡፡
የንስሐ አባት ማለት ምስጢረኛችን በመንፈሳዊም በሥጋዊም ህይወታችን የቅርብ አማካሪዎቻያችን ማለት ነው፡፡ ጠቢቡ ሲራክ “ብዙ ሰዎች ወዳጆች ይሁኑህ ከብዙዎች አንዱ ምክርህን የምትነግረው ከልቡናህ ጋር አንድ ይሁን፡፡” ሲራክ 6-6 በማለት ይናገራል፡፡ ይህ ማለት ምእመናን ስለ ሃይማኖትና በጎ ምግባር የሚያስተምሩዋቸው ብዙ ካህናት ሊኖሩዋቸው ቢችሉም ከብዙዎች አንዱ ግን ንስሃቸውን የሚናዘዙለት መምህረ ንስሃ ሊሆናቸው እንደሚገባ ያስረዳልና መምህረ ንስሕ ማለት ምስጢረኛና አማካሪ ማለት ነው ፡፡
አበ ነፍስ ማለት ኃጢአታችንን የምንናዘዝለት ማለት ነው፡፡ ኀጢታችንን ለካህን ስንናዘዝ ለእግዚአብሄር መናዘዝና ክብር መስጠት ነው፡፡ ኢያሱ እንዳለ “ልጄ ሆይ ለአምላክ ከብርን ስጥ፡ ለእርሱም ተናዘዝ፡ ያደረግከውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ” ኢያሱ 7-19፡፡ ኀጢአትን ለካህን መናዘዝ ለእግዚአብሄር ክብር መስጠት እንደሆነ ያሳየናል፡፡ አበዉ ካሀናትም ኑዛዜን ከተቀበሉ በኋላ “እግዚአብሔር ይፍታህ” እንጂ ”ፈትቼሃለሁ ” አይሉም፡፡ ኀጢአተዘችንን በነሱ ፊት ብንናገርም ሰሚዉም ሆነ በእነርሱ እጅ ስርየተ ኀጪአት የሚሰጠዉ እርሱ ባለቤቱ ስለሆነ ነው፡፡ በመሆኑም አበ ነፍስ ማለት ኀጢአታችንን በዝርዝር ምንም የሚያስፈራ ኀጢአት ቢኖረንም እያሰታወስን አንዳች ሳናስቀርና ሳንጠራጠር በዝርዝር የምንነግረው የእግዚአብሔር አይን ነው ማለት ነው፡፡
የንስሐ አባት/አበ ነፍስ ወይም መምህረ ንስሐ ማለት የንስሐ ልጆቹ ትክክለኛውን ዓላማ ይዘው የንስሐ ሕይወት እንዲጀምሩ የሚያደርግ በጎ መሪ ማለት ነው፡፡
መምህረ ንስሐ ማለት ልጆቹን መሠረታዊ ትምህርተ ሃይማኖት የሚያስተምርና የልጁቹን ሁለንተናዊ ለውጥ የሚከታተልና ስለ በጎቹ የሚጨነቅ እረኛ ማለት ነው፡፡
የንስሐ አባት ማለት ምእመናን ሃይማኖታቸውን እንዳይለውጡ፣ ምግባራቸውን እንደይስቱ በርካቶችም ለጠንቋዮችና ለአሳቾች ሰለባ እንዳይሆኑ የጠራውን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ከምንጩ ማስጎንጨት የሚችልና እሄንንም የማድረግ ግዴታ ያለበት ባላደራ ማለት ነው፡፡
የንስሐ አባት ማለት ልጆቹ ለሥጋ ወደሙ እንዲበቁ ያለመታከት የሚተጋ ማለት ነው፡፡ የንስሐ አባት ልጆቹ ለሥጋ ወደሙ እንዲበቁ ሁሌም መጐትጐትና መቀስቀስ አለበት፡፡ ይህም የሚሆነው በኃይል፣ በማጣደፍ ወይም በማስፈራት አይደለም፡፡ ካህኑ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወኪል፣ የእግዚአብሔር አደረኛ ስለኾነ ሁሌም ማትጋት፣ መጐትጐት፣ መቀስቀስ ይጠበቅበታል፡፡
የንስሐ አባት ለእያንዳንዱ ልጆቹ እንደየ አቅማቸውና እንደየሃይማኖት እውቀት መጠናቸውና እንደየ መንፈሳዊ እውቀታቸው አቻ እስከሚሆኑለት ለያይቶ በማስተማር ማብቃት አለበት፡፡
የንስሐ አባት ማለት በንስሐ ልጆቹ መካከል ፍጹም መቀራረብ እንዲኖር የሚያደርገ ነው፡፡ የንስሐ ልጆች ለብዙ ችግሮች የመፍትሔ አካል ኾነው እንዲያገለግሉ ዕድል ይሰጣልና፡፡ የተቸገሩትን ከመርዳት ዠምሮ አንዱ ለሌላው አርአያ ኾኖ በተግባር እስከማስተማር ድረስ ማድረግም የንስሐ አባት ድርሻ ነው፡፡ ይህ ማለት የአንድ ካህን ንስሐ ልጆች ከአንድ የሥጋ አባትና እናት የተወለዱ እህትማመቾች እና ወንድማማቾች ያህል ከዚያም በበለጠ ሁኔታ መቀራረብ አለባቸው ማለት ነው፡፡የንስሀ አባት ማለት ይህን የሚተገብር ማለት ነው፡፡
ከቊርባን በፊት ንስሐ ይቀድማልና፡፡ ሰው ከኃጢአት ንጹሕ ሆኖ የሚገኝበት ጊዜ ስለሌለ ጧት የሠራውን ለማታ፤ ማታ የሠራውን ለጧት ለመምህረ ንስሐው ነግሮ መምህረ ንስሐው ያዘዘውን ሠርቶ ሊቀበል ይገባዋልና ይህ ታላቅ ሀላፊነት የተጣለው ደግሞ በመምህረ ንስሀው ላይ ነው፡፡
የንስሐ አባት ማለት ባለአደራ ማለት ነው፡፡ ጌታችን በወንጌል “መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በበረኻ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ማን ነው?” ሉቃ.15 -5 ያለው፡፡ ካህናት ከእግዚአብሔር በአደራ እንዲጠብቁ የተሰጣቸውን ኹሉንም ሳይዘነጉ እያንዳንዱን በነፍስ ወከፍ ሊጠብቁና ሊያገለግሉ የሚገባቸው ናቸው፡፡
የንስሐ አባት ከንስሐ ልጆቹ ጋር የሚፈጥረው ግላዊ ግንኙነት ከቤተሰባዊነት ያልተሻገረ ኾኖ ሲቀነጭርና እጅጉን ያነሰ ሲሆን ነው፡፡ ብዙ ካህናት ወደ ምእመናን ቤት መጥተው ሲያበቁ መስቀል ከማሳለምና ጠበል ከመርጨት ያለፈ አገልግሎት አይሰጡም፡፡ ካህናት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እንዳስቀመጠላቸው ከሥራቸው ኹሉ ቅድሚያውን ሰጥተው ማስተማር፣ መምከር፣ ኑዛዜን መቀበል፣ ማጽናናትና መገሰጽ ይገባቸዋል፡፡ እያንዳንዱን የንስሐ ልጃቻቸውን በጥንቃቄ ይዘው ለሥጋ ወደሙ ማብቃት ግባቸው ስለኾነ ትኩረታቸው ኹሉ ወደዚኽ ዋነኛ የክህነት ዓላማቸው መሆን አለበት ፡፡ ይህም የካህኑ ትልቁ ሀላፊነት ነው፡፡
የንስሐ አባት የንስሐ ልጀቹን የቤተ ሰብ አባላት ቁትርና እያንዳንዱን በሚገባ ማወቅ አለበት፡፡
አንድ የንስሐ አባት ልጆቹንና አጠቃላይ ቤተሰቡን እያሰታወሰ አዘውትሮ ስለ ሁለንተናቸው መጠየቅ አለበት፡፡
የንስሐ አባት ከልጆቹ ጋር አብሮ በመጸለይ ጸሎትን ማለማመድ፤ ሆኖ በማሳየት እውነተኛ የአባትና የልጅ ፍቅርን ማሳየት፤ በመንፈሳዊ ብቻ ሳይሆን በሥጋዊም ሕየዋታቸው መጨነቅ፤ ስራቸው እንዲባረክ አዘውትሮ፤መጸለይ በአጠቃላይ ልጆቹን በቅርበት መከታተል፤ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ተግባሩ እሄ ነው፡፡
የንስሐ አባት ይህን የድረ ገጻችንን አድራሻ በመጫን ይያዙ: https://yohannesneseha.org/የንስሐ-አባት-ገጽ/
ለዚህ ጥያቄ መልሱ ንስሀ መግባት ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ ነጭ ልብስ ገዝተን የተወሰኑ ቀናት ከለበስን ቦሃላ ማደፉ ወይም መቆሸሹ አይቀርም ነገር ግን ስለቆሸሸ አንጥለውም ስናጥበው የቀደመ ጽእዳዌውን ያገኛል አሁንም ይቆሽሸብናል ብለን ሳንለብሰው አንቀርም ሊቆሽሽ ይችላል ከኛ የሚጠበቀው እንደገና አጥቦ መልበስ ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን እንዳይቆሽሽ የምንችለውን ጥንቃቄ ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ የሰውም ሰውነት እንዲሁ ነው በሀጢአት ስናዳድፍ በንስሀ ቶሎ መጣጠብ ተገቢ ነው፡፡ነገር ግን ንስሀ መግባት ስናስብ እግዚአብሔር ይቅር የለኝ ይሆን? በደሌን ይደመስስልኝ ይሆን? እኔንማ ምረኝም ወዘተ ማለት ትልቅ ኃጠእት ከመሆኑም ባሻገር የእግዚአብሔርንም ምህረትና ይቅር ባይነት መጠራር ነው፡፡ ቲቶ 3-5 እንደ ምህረቱ መጠን ለአዲስ ልደት አዳነን፡፡1ኛ ጴጥ1 3-5፡፡
ሐጢአት በሦስት መንገድ ይሰራል፡፡ ይኸውም ሀ. በሀልየ (በሀሳብ) ለ. በነቢብ (በመናገር) ሐ. በገቢር (በተገባር) ነው፡፡ ከዚህ አንጻር አሥሩን ትእዛዛት በትክክል ያከበረ ሰው በሦስቱም መንገድ የተዘረዘሩ ሀጢአቶችን ማለትም ሀ. በሀልየ (በሀሳብ) ለ. በነቢብ (በመናገር) ሐ. በገቢር ማ(በተገባር) አልሰራም ማለት ነው፡፡አስሩን ትእዛዛት ማክበር ያልቻለ ሰው ግን ሀ. በሀልየ (በሀሳብ) ለ. በነቢብ (በመናገር) ሐ. በገቢር (በተግባር) በሦስቱም መንገድ ሐጢአት ሠራ ማለት ነው፡፡ ጥያቄው ግን አስሩን ትእዛዛት በትክክል ሁላችንም አክብረናል ወይ? ነው፡፡ ከፍጡራን ወገን በሀሳብም በመናገርም በተገባርም ከእመቤታችን በቅረ ሐጢአት ያልሰራ የለም፡፡ በተግባራ ባንሰራ በመናገር ሰርተናል በመናገር ባንሰራ በሐሳብ ሰርተናልና ነው፡
1.ከኔ በቀር ሌሎችን አማልክት አታምልክ፡፡ በተግባር
2.የእግዚአብሔር አምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ፡፡ በመናገር
3.የሰንበትን ቀን አክብር፡፡ በተግባር
4.አባትና እናትህን አክብር፡፡ በተግባር
5.አትግደል፡፡ በተግባር
6.አታመንዝር፡፡ በተግባር
7.አትስረቅ፡፡ በተግባር
8.በሐሰት አትመስክር፡፡ በመናገር
9.የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፡፡ በሐሳብ
10.ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ የሚሉት ናቸው፡፡ በተግባረ
በተለያዩ ቦታዎች ሰዎች ሀጢያታቸዉን ይናዘዙ እንደነበር በመፅሀፍ ቅዱስ ተገልÚል፡፡ ሐዋ 19-18 ፡ማቴ3 5-6 ፡ዘሌ 5-16፡ ኢያ 2- 19፡፡ ነገር ግን አባት የግድ ሊኖረን የሚፈለግበት ምክንያት 4ኛ ጥያቄ ላይ በዝርዝር የተቀመጡትን ስንመለከት መለሱን እናገኛለን፡፡ ንስሀ አባቶች ከመንፈሳዊ ህያወታችን ባሻገር በስጋዊ ህይወታችንም በደስታችንንም በሀዘናችንም ሁሌም ከእኛ ጋር ሆንው የሚጋሩንና ሁሌም በቅርበት የምናገኛቸው የየራሳችን ኣባቶች ሊኖሩን የግድ ነው፡፡በምክረ ካህን በ ፈቃደ ካህን የሚኖር ሰው ነፍሱ ከሃጢአት እንደ ምትጠበቅ ይታወቃል፡፡ ካህናትን ደግሞ “እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ” ማቴ 5-14 ነው ያላቸው፡፡ በመሆኑም በሀጢአት የጨለመ ህይወታችንን በንስሀ ብርሃን ያበሩልናል፡፡በሲራክ 6-6 ላይ “ብዙ ሰዎች ወዳጆች ይሁኑህ ከብዙዎች አንዱ ምክርህን የምትነግረው ከልቡናህ ጋር አንድ ይሁን፡፡” ይህ ማለት የየራሳችን ኣባቶች ሊኖሩን እንደሚገባ የሚያስረዳን ነው፡፡
ሀጢያትን በካህን ፊት መናዘዛች የሚከተሉት ጠቀሜታዎች አሉት፡-
- ሀጢያትን በዝርዝር በካህን ፊት መናዘዝ ዳግመኛ በዚያ ሀጢያት ላለመያዝ ሀይልን ይሰጣል፡፡ዮሃንስ አፈወርቅ “በበደሉ ላይ ድፍረትና ሽንገላን የሚጨምር (ሀጢያት ሰርቶ እንዳልሰራ ዝም የሚል) ከዚያች ሀጢያት መጠበቅ ይችልም፡፡ እርስዋን በምትመስል ሀጢያት ከመዉደቅም አይድንም” እንዳለ፡፡
- ሀጢያታችንን በካሀኑ ፊት ስንዘረዝርም ያለፈዉን ሀጢያታችንን ሽረን በሚመጣዉም ህይወት ያንን ሀጢያት ላለመድገም እየወሰንን ነው፡፡
- ኑዛዜ ያሳቅቃል፡፡ መሳቀቁ ደግሞ ለሰራነዉ ሀጢያት ዋጋ ነዉ፡፡ በፍርድ ቀን ጌታ በሰማይ መላእክት ፊት ሀጢያታችንን ገልጦ ከሚያሰቅቀን ይልቅ እኛዉ እራሳችን እዚሁ እንደኛዉ ደካማ ሰዉ በሆነው በካህኑ ፊት በመናዘዝ ለሰራነው ሃጢያት የምንቀበለው ኢምንት ቅጣት ነው፡፡
- በሽታውን የደበቀ መድሃኒት የለውም እንደሚባለው የነፍሱን ደዌ ሀጢያቱን የሚደብቅም እንዲሁ መፍትሄ አያገኝም፡፡ የካህኑን ፀሎትና ምክርም ያጣል፡፡ “ሀጢያቱን የሚደብቅ /የሚሰውር አይለማም፡ የሚናዘዛትና የሚተዋት ግን ምህረትን ያገኛል” እንደተባለ ፡፡ምሳ8-13
- ሀጢያትን ለካህን መንገር ለእግዚአብሄር መናዘዝና ክብር መስጠት ነው፡፡ እያሱ እንዳለ “ልጄ ሆይ ለአምላክ ከብርን ስጥ፡ ለእርሱም ተናዘዝ፡ ያደረግከውንም ንገረኝ አትሸሽገኝ” ኢያሱ 7-19፡፡ ኢያሱ “ክብርን ስጥ” ያለው ለእግዚአብሄር: “ተናገር” ያለው ግን ለእርስ ለኢያሱ ለራሱ ነው፡፡ አበዉ ካሀናትም ኑዛዜን ከተቀበሉ በ`ላ “እግዚአብሔር ይፍታህ” እንጂ ”ፈትቼሃለሁ ” አይሉም፡፡
- ካህናት የነፍስ ሀኪሞች ናቸውና እያንዳንዱን የነፍስ በሽታ (ሀጢያት) በዝርዝር በእነርሱ ፊት ልንናዘዝ ይገባል፡፡ በሀኪሙ ፊት ምንናዘዘው የእግዚአብሔርን ፈዋሽነት ክደን እንዳልሆነ ሁሉ በካህናት ፊት የምንናዘዘውም የእግዚአብሔርን ሰሚነት ክደን አይደለም፡፡
- ለምን በቀጥታ ለእግዚአብሔር አልናዘዝም? ማለት በራሱ ትዕቢት ነው፡፡ ንስሃ የሚገባ ሰው ሊል የሚገባው ”ከበደሌ ብዛት የተነሳ ቀና ብዬ የሰማይን ርዝመት አይ ዘንድ እንኩዋ አገባቤ አይደለም” ነው፡፡ በወንጌል ”እርስ በርሳችሁ ሀጢያታችሁን ተናዝዙ” ያለው ሰው ከፈጣሪ ይልቅ ሰውን ስለሚፈራና ስለሚያፍር በሃጢያቱ እንዲሳቀቅ ደግሞም እንዳይሰራት ስለፈለገ ነው፡፡
ወስብሀት ለእግዚአብሔር
በእርገጥ አሁን ከቤት መውጣት አስቸጋሪ ነው እግዚአብሔርም የምህረት እጁን ልኮልን ይህ ጊዜ እንደሚያልፍ እናምናለን፡፡ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን አልተዘጋችም ስብሀተ እግዚአብሔርም እየተደረሰ ነው ቅዳሴም አልታጎለም ማህሌቱም አልቀረም ይህ ሁሉ የቀረ እንደሆነ ተዘጋች ልንል እንችላለን፡፡ በእርገጥ ለምእመናን ክፍት አይደለም ለምእመናን ዝግ ናት በሚለው ቢታረም የተሸለ ነው፡፡ ወደጥያቄው እንግባና ንስሀ መግባት እፈልጋለሁ ለሚለው ጥያቄ ንስሀ አባት ለሌላችሁ የተዋህዶ ልጆች ለእናንተ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ በህይወታቸው ምሳሌ የሚሆኑአችሁ በጸሎታቸውም ሊያግዙአችሁ የሚችሉ ስለናንተ የሚያገባቸውንና የሚጨነቁላችሁን አባቶችን በአዲስ አበባም ሆነ በክልል ለምትኖሩ ኦርቶዶክሳውያን አባቶች የሚያገለግሉበትን መደበኛ ቦታ (ደብር) ስማቸውን ስልካቸውን በዚህ ሳምንት መጨረሻ በዚሁ ፔጅ እንለቅላችሁአለን እንደሚቀርባችሁ ቦታ እየደወላትሁ ከእነርሱ ጋር መነጋገር ትችላላችሁ፡፡ እንደተባለውም በበአለ 50 በእርግጥ ንስሐ አይሰጥም ነገር ግን አባቶቻችሁን ካገኛችሁ በሁዋላ የነፍሳችሁ ሀኪሞች እነርሱ ናቸውና ከእነርሱ ጋር መነጋገር ትችላላችሁ፡፡ እዚህ ጋር ሊታወስ የሚገባው አንድ ነገር ምንም አይነት ክፍያ እንደሌለው መገንዘብ ነው፡፡ምክንያቱ ደግሞ የነፍስ ሥራ ስለሆነ ነው፡፡
በእርግጥ በዚህ አስጨናቂ ወቅት ንሰሀ ገብትን እግዚአብሔርን ከመጠባበቅ ውጪ ምንም አማራጭ የለንም፡፡ ይሁንና ከላይ እንደጠቀስነው በጸሎታቸውም ሊያግዙአትሁ የሚችሉ አባቶችን በአዲስ አበባም ሆነ በክልል ለምትኖሩ ኦርቶዶክሳውያን አባቶቻችሁ በዚህ ፔጅ ከንስሐ አባት ገጽ ስር ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዚህ መልስ ከእረሳቸው ጋር በመነጋገር እርስዎ ሁሌም ሊያገኙአቸው የሚችሉአቸውንና እርሰዎን አሰተምረው ለንስሀ የሚያበቁ አባት መያዝ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡ ምክንያቱም የንስሀ አባትና ልጅ ተራርቀው መኖር በፍጹም የማይቻል በመሆኑ ነው፡፡
ለዚህ ጥያቄ መልስ ከመስጠታችን በፊት ንስሐ ማለት ምን ማለት ነው? የሚለውን መሰረታዊ ቁምነገር መመልከቱ እጅጉን ጠቃሚ ነው፡፡
ንስሐ ማለት፦ ሐዘን፣ፀፀት፣ቁጭት፣ምላሽ፣፣ቅጣት ፣ቀኖና፣የኃጢአት ካሣ ፤ሰው በሠራው ጥፋት፣ባደረገው ስህተት፣በፈጸመው ኃጢአት ማዘኑና መቆርቆሩን፣መፀፀቱን የሚያሳይ ፤ወደ እግዚአብሔር መመለስ ፤ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ ፤ከኃጢአት እንቅልፍ መንቃት፤ወደ መንፈሳዊ ሕይወት መመለስ ፤ከእግዚአብሔር የሚሰጥ እግዚአብሔርን የሚያስወድድ ከንጹሕ ልብ የሚመነጭ ጸጋ ፤ ከኃጢአትና ከዲያብሎስ ባርነት ነፃ መውጣት ፤ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር የሚያስገባ ቁልፍና የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ በር ማለት ነው፡፡
የንስሐ ቅድመ ዝግጅቶች፡-አበ ነፍስ(የንስሐ አባት) መያዝ፤የሰራነውን ኃጢአት ማመን፤በሰራነው ኃጢአት ከልብ ማዘንና ማልቀስ፤እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን በፍጹም ትህትና ራስን በማዋረድ መጠየቅ፤ ከእኛ ኃጢአት ይልቅ የእግዚአብሔር ቸርነት እንደሚበልጥ ማመን፤እና ወዘተርፈ ናቸው፡፡
ንስሐ ማለትና ቅድመ ዝግጅቶቹ ከላይ በተገለጠው መልኩ ከሆነ አንድ ሰው ስለሠራው ኃጢአት ሳይጸጸት ፤ሳይቆጭ እግዚአብሔርን ማሳዘኑን ሳይረዳ ለይሰሙላ ንስሐ ላይ ነኝ ቢል ንስሐው እውነተኛ ንስሐ አይሆንለትም፡፡ ይህንንም ለመረዳት ንስሐ ማለት ምን ማት ነው የሚለውን ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡
ነገር ግን ተነሳሒው ወይም ንስሐ የገባው ሰው ንስሐውን ተቀብሎ መጸጸት አለመጸጸቱን እኛ ማወቅ አንችልም፡፡ ይህን ማወቅ የሚችሉት እርሱና እግዚአብሔር ብቻ ናቸው፡፡ ንስሐ ማለት ግን ከላይ እንዳየንው ከእውነት በእውነት መጸጸት ማለት ነው፡፡
ሌላው በሰው ተገፋፍቶ ኀጢአት ከመስራት በሰው ተገፋፍቶ ንስሐ መግባት እጀግ ተወዳጅ ነው፡፡ መጥፎ ጉዋደኛ መልካሙን አመል እንደሚያጠፋው ሁሉ መለካም ጉዋደኛም በመልካምነጣችን እንድንቀጥል ያግዘናል፡፡ እንደተባለው ጉዋደኛችን ወደ ንስሐ የሚገፋፋን ከሆነ ከልብ እስከምንጸጸት አይተወንምና ለሁላችንም ወደንስሐ የሚገፋፋንን ሰው ይዘዝልን፡፡
የመጨረሻው ነጥብ አንድ ሰው ንስሐ ገባ ማለት ዳግም ኀጢአት አይሠራም ማለት አይደለም፡፡ ሰው ያደፈ ልብሱን እንደሚያጥብ በኀጢአት የጎሰቆለ ማናነታችንን በንስሐ መታጠብ ማለት ነው እንጂ፡፡የታጠበ ልብስ ሲቆሽሽ እንደሚታጠብ ሁሉ ሁሌም ሰውነታችን በኀጢአት ሲቆሽሽ በንስሐ ይታጠባል ማለት ነው እንጂ ንስሐ የገባ ሰው ኀጢአት አይሠራም ማለት አንችልም፡፡ አደራ አደራ ይህን ስንልም ኀጢአት ይሥራ እያልን አለመሆኑን ተረዱን ፡፡እንደሰውነቱ ግን በኀቲአት ሊወድቅ ይችላል እያልን ነው፡፡ ነገር ግን መድኃኒቱ አሁንም አሁንም በንስሐ መታጠብ ብቻ ነው፡፡
መልስ፦ ሴትም ይሁን ወንድ ልጅ ለአካለ መጠን ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ እያወቁ በፈጸሙት የኀጢአት በደል በነፍስ ስለሚጠየቁ ንስሓ መግባት እንዳለባቸው የቤተክርስቲያን ቀኖና ይደነግጋል።
ነሰሐ እግዚአብሔር ጠፍተን እንዳንቀር ወሰን በሌለው ፍቅሩ እኛን ወደእርሱ የሚጠራበት የፍቅር ጥሪ ነው። ሐጢአት ግን ከእርሱ የሚለየን የእርሱ ማደሪያዎች ከምንሆን ይልቅ የሰይጣን ማደሪያዎች እንድንሆን ያደርገናል። ደግሞም እርሱ ሐጢአትን እንጂ ሐጢአተኛውን አይንቀውም የምንጠየቀውም ለምን ሐጢአት ሠራህ/ሽ ሳይሆን ለምን ንስሐ አልገባህም/ሽም በሚል ነውና ንስሐ ሐጢአትን አያበረታታም።ንስሐ ሐጢአትን ያበረታታል ካልንማ ከፍጡራን መሐል ከእመቤታችን በቀር ሐጢአትን ያልሠራ ማን ይኖርና። በመሖኑም ንስሐን አርሱ ባያዘጋጅልን ሁላችንም ጠፍተን ነበርና በዚህም ገደብ የሌለው ምህረቱንና ቸርነቱን ማየት ችለናል።ደግሞ እርሱም ሰው ሆኖ በምድር ሲመላለስ የትምሕርቱ መጀመሪያ ንስሐ ግቡ የሚል ነው እንጂ ሐጢአትን ለምን ሠራችሁ የሚል አይደለም በመሆኑም ንስሐ ፈጽሞ ሐጢአትን አያበረታታም።ንስሐ ማለትኮ አንድ ታማሚ ታሞ ሕክምና ሲሄድ የሚሰጠው መድሐኒት እንደማለት ነው። ንስሐ ሐጢአትን ያበረታታል ካልን ለታማሚው መድሐኒት መስጠት ታማሚዎች ቁጥራቸው እንዲጨምር ማበረታታት ማለት ነውና ንስሀ ሐጢአትን አያበረታታም።በአጭሩ ንስሐ ማለት ለታመመ ሰው መድሐኒት መስጠት ማለት ነው። ንስሐማ በይኖር ሑላችንም ሐጢአተኞች ነንና በጠፋን ነበር እርሱ ግን ዛሬም እድሜን ለንስሐ ሰጥቶናልና እናመሰግነዋለን።
አዎ በደንብ ይሰረይለታል ክፋቱ ንስሐ አለመግባት ብቻ ነው።በንሰሐ ሐጢአት በደንብ ይሰረያል።ሲጀመር ስጋ ወደሙ ያልተቀበለ አርቶዶክሳዊ የታለና ስጋወደሙ መቀበል የጀመርነው ገና በእናቶቻችን ጀርባ ሳለን በ40ና በ80 ቀናችን ነውና። መቼም ያ በሕጻንነታችን የተቀበልነው ነው እሱ አይቆጠርም የሚል ማንም አይኖርም። ይህ እንደውም ክርስቶስን ማሳነስ ነውና ሐጢአቱ ይህ ነው።ሁላችንም ስጋወደሙ ተቀብለናል ደግሞም ሁላችንም ሐጢአትን ሠርተናል እርሱ ግን ዛሬም በፍቅር አጠራሩ ወደእርሱ በንስሐ እየጠራን ይገኛል።እውነት ነው ስጋወደሙ የተቀበለ ሰው ሐጢአት ሊሠራ ይችላል ነገር ግን ራሱን ለንስሐ ካዘጋጀ በንስሐ ይሰረይለታል። አደራ አንድ ሰው ንስሐ ገባ ማለት በቃ የመጨረሻ አይበድልም ቢበድልም ንስሐ የለውም የሚል ሐሣብ እንዳይኖርዎ ይበደላል ደግሞ በነስሐ ሲታጠብ ንጹህ ይሆናል ማለት ነውእንጂ። አንድ ምሳሌ አዲስ ልብስ ገዝተን ይቆሽሽብናል በማለት ሳንለብሰው አንቀርም በእርግጥ እንለብሰዋለን ደግሞ ይቆሽሻል ስለቆሸሸ አንጥለውም አጥበን እንለብሠዋለን። በመሆኑም ንስሐ ስንል ልክ ከላይ እንዳየነው ምሴሌ ነፍሳችንና ሰውነታችን በሐጢአት ሲቆሽሽ በቃ ሐጢአቴ አይሸረይለኝም በማለት ተስፋ መቁረጥ ሳይሖን ምንም በደለኛ ብሆን ንስሐ ብገባ ይቅር ይለኛል ንስሐም የተዘጋጀው ለኔ ለሐጢአተኛው ነው ብሎ በማመን ወደንስሐ መመለስ አስተዋይነት ነው።ነገር ግን እሄንን ሐጢአቴን ይቅር አይለኝም ማለትና ነስሐ በገባንበት ሐጢአት መጸጸት ትልቅ ሐጢአት ነው እግዚአብሔርንም ጨካኝ ማድርግ ነውና ንስሐ ስንገባ ይቅርታውን እንዳገኘን ማመንና ንስሐ የገባንበት ሐጢአቶ እንደጠፋና እንደተሠረዘልን እነደተረሳልን በእርሱ ዳግም ማንም እንደማይወቅሰን እርግጠኞች መሆን አለብን።
ባልና ሚስት በእግዚያብሄር ዘንድ አንድ አካል ናቸዉና ንስሐ ሲገቡ ሆነ ሲቆርቡ አንድ ላይ ነዉ ማድረግ ያለባቸዉ።
የንስሐ አባትዎ እርስዎን በስጋዊም ሆነ በመንፈሳዊ ህይወቶ መክረው ገስጸው ማብቃት ካልቻሉና ለእርስዎ በጎ ምሳሌ መሆንም ካልቻሉ ይህንንም እርስዎ ከተረዱ እውነት ነው በትክክለ መቀየር ይችላል።ነገር ግን ሌላ አባት መቀየር ሲያስቡ በራስዎ ጊዜ ዝም ብለው ጥለው መሔድ ግን አይቻልም። ከእርሳቸው መሰናበት ቸገቢ ነው።እርሳቸውም የእርስዎን ጥያቄ ተቀብለው ፍትሀት ዘወልድ የሚባል ጸሎት አለ ያንን ደግመው እርሰሸዎን ማሰናበት አለባቸው። ነገር ግን እርሳቸው ይህንን ለማድረግ ፈቃደኛ ባይሆኑ እርስዎ ወደመረጡት አባት መሄድ ይችላሉ።ከዚህ ጋር መታሰብ ያለበት ስለሚይዟቸው አባት ማንነት እና መንፈሳዊ ህይወት ማወቅ ተገቢ ነውና እዚህ ላይ በትኩረት መመልከት እንዳለብዎ መዘንጋት የለቦትም።
በቅድሚያ በድያለሁ ጥፋት ሰርቻለሁ ኅጢአት ፈጽሜያለሁ ብሎ ኅጢአትን ለመናዘዝ ፈቃደኛ መሆንና የኅጢአት ሥርየት ለማግኘት መፈለግ የእውነተኛ ክርስቲያን መገለጫ ነው። በመሠረቱ በአዳማዊ ተፈጥሮ ሰው ሁኖ የተፈጠረ የሰው ልጅ ሁሉ ወዶ ጽድቅ መሥራትም ሆነ ወዶ ኅጢአት ለመሥራት የሚችልበት የተፈጥሮ ነፃነት ያለው ፍጡር ስለሆነ በለበሰው ደካማ ሥጋው ተሸንፎ ኅጢአት እንደሚሠራ ይታወቃል። ሰው ሁኖ ተፈጥሮ በሰውነቱ ፈፅሞ ኅጢአት አልሠራም ብሎ ማሰብም ሆነ መናገር እራስን ከማታለል አልፎ ስለሁላችንም መዳን በመስቀል ላይ የሞተልንን የኢየሱስ ክርስቶስ አባታዊ ፍቅሩንና ውለታውን እንደመካድ ይቆጠራል። ሁላችንም የሰው ልጆች እንደምንሞት ብናምንም እንኳ፤ ነገር ግን መቼ በሞት እንደምንጠራ ቀንና ሰዓቱን (ዘመንና ጊዜውን) ለይቶ ማወቅ ከእሱ ከባለቤቱ በስተቀር ፈጽሞ የሚያውቅ የለምና ኅጢአትን ለመናዘዝ ቅድሚያ መስጠትና በንስሐ ሕይወት ራስን አዘጋጅቶ መጠበቅና ንስሐ ለመግባት መዘጋጀት ከእውነተኛ ክርስቲያን የሚጠበቅ ታማኝነት ነው።
ኅጢአት ማለት የብዙ ጥፋቶች ወይም ስሕተቶች መጠሪያ ስም ነው ኅጢአት የሥጋ ሥራ ሁኖ ነፍስን ከፈጣሪ ጋር አጣልቶ ዘለዓለማዊና ሰማያዊ ሞትን የሚያስከትል ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም የኅጢአት ውጤት ሞት እንደሆነ ሲናገር “ኅጢአት ስታድግ ሞትን ትወልዳለች” (ያዕ1$15) ካለ በኋላ “የኅጢአት ደመወዝ ሞት ነው” (ሮሜ 6$23) በማለት ኅጢአት የሕሊናና የመንፈስ ሞት መሆኑን አረጋግጧል።
የሥጋና የመንፈስ (የነፍስ) ሥራዎች አብዛኛዎቹን ቅዱስ ጳውሎስ ወደገላትያ ሰዎች በላከው መልእክቱ በምዕ 5$19-22 ላይ የሥጋ ሥራ እና የመንፈስ ፍሬዎች በማለት ዘርዝሯቸዋል።
የሰው ልጅ ኅጢአት ሰርቻለሁ እግዚአብሔርን በድያለሁ፣ ሰውንም አሳዝኛለሁ ብሎ ራሱን ካሳመነ በነፍሱ የኅጢአት ደዌ አድሮበታልና ንስሐ የመግባት ሕክምና ያስፈልገዋል ማለት ነው። “እንግዲህ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አድርጉ “(ማቴ3$8) ኅጢአት ሠርቶ የንስሐ ሕክምና ያላገኘ ሰው በነፍሱ ምውት ነው። ሉቃ 15$24
ከዚህ የተነሣ ኅጢአት ለመናዘዝና ንስሐ ለመግባት ከሚፈልግ አንድ ክርስቲያን የሚጠበቀው ፡-
- በቅድሚያ ኅጢአት መሥራቱን አምኖ ለራሱ ሕሊና መናዘዝ (መፀፀት)።
- ስለሠራው ኅጢአት ወይም በደል እየተጸጸተ ጧት ማታ በደሉን በፀሎትና በልመና ለፈጣሪው መናዘዝና ኅጢአትን በእግዚአብሔር ፊት ማመን (መዝ50 ፣ ዳን9$5፣ ነህ1$6-7)
- ኅጢአትን (በደልን) ለካህን መናዘዝና ንስሐ መግባት። ካህኑ የእግዚአብሔር አገልጋይና እንደራሴ ስለሆነ የሠራነውን ኅጢአት ለካህኑ በመናዘዝ ንስሐ መግባት፤ ኅጢአታችን እንዲሠረይልን በእግዚአብሔር ፊት ንስሐ መግባትና መናዘዝ ማለት ነው። (ኢያሱ7$19 ማቴ3$6 ዘሌ5$5-6 የሐዋ19$18)
- የበደልናቸውንና የበደሉንን ሁሉ ይቅር በማለት የጥል ግድግዳ አፍርሰን በፍቅር አሸንፈን ስለዘለዓለማዊ ሕይወት ብለን በፍጹም ሕሊና በሰላም መኖር ነው።
- ተመልሶ በኅጢአት ላለመውደቅ አዘውትሮ የንስሐ አባትን ወይም የሚቀርቡትን የሃይማኖት መምህር ማማከር፣ ምክር ማግኘት በታቻለ መጠን መጸለይ፣ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድና ቃለ እግዚአብሔር መስማት፣ በቤትም ውስጥ ቢሆን መንፈሳዊ መዝሙርና ትምሕርት ማዳመጥ አስፈላጊ እንደሆነ የምናስገነዝበው ለጠየቁን ምዕመን ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ክርስቲያን እንዲጠቅም ነው።
የእግዚአብሔር ሰላም በያላችሁበት ከእናንተጋር ይሁን።
በቅድሚያ ፀበል ምንድነው? ለሚለው ካህኑ ውሃውን በእግዚአብሔር ቃል እና በቅዱስ መስቀሉ ሲባርከውና ሲቀድሰው ተራ የነበረው ውሃ በጥምቀት የእግዚአብዜር ልጅነት ይገኝበታል።
“ሰው ከውኅና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም” (ዩሐ 3፤5) በማለት የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ዳግም ለመወለድና ሰማያዊ መንግሥቱን ለመውረስ የእግዚአብሔር መንፈስ ባደረበት በውሃው (በጸበሉ) መጠመቅ እንዳለብን ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሌሊት ወደ እሱ ለመጣው ለወዳጁ ለኒቆዲሞስ በስፋት እንዳስተማረው ወንጌላዊው ቅዱስ ዩሐንስ ጽፎታል።
ለጥምቀት የተዘጋጀው ውሃ (ፀበል) የቤተክርስቲያን አባቶች ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀውን ጸሎት ከጸለዩበት እና በመስቀል ከባረኩት በኋላ ልዩ ልዩ ደዌ (በሽታ) ያለባቸው ሰዎች ይፈወሱበታል፣ ርኩሳን መናፍስት (አጋንንት) ያደሩበት ሰውም ሲጠመቅበት በፀበሉና በመስቀሉ ኃይል አጋንንቱ ከታመመው ሰው ዳግም ወደሰውየው እንዳይመለሱ በእግዚአብሔር ቃል ታሥረውና ተወግዘው ይለያሉ።
በጸበሉ ፈዋሽነት የሚያምን ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊም ሆነ ሌላው ወገን ሳያውቅም ሆነ እያወቀው የድግምት፣ የመተት፣ የሟርት መንፈስ ቢኖርበት በጸበሉ ከተጠመቀና ቤቱም ንብረቱ ጸበል ከተረጨበት ፈጽሞ ይድናል። ክፉ መንፈስም በእርሱ ላይም ሆነ በሃብቱና በቤቱ ላይ ጥፋት ለማድረስ ስልጣን የለውም።
አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በተለያየ ምክንያት ክርስቲያናዊ ሕይወቱን የሚያጎድፍና በእምነቱ ያልተፈቀደለትን ፈጽሞ ቢገኝ ደግሞ ወደ ካህናት (ወደ ንስሐ አባቱ) ቀርቦ ጥፋቱን መናዘዝ ወይም ንስሐ በመግባት በሥርዓተ ቄዶር እንዲጠመቅ ይደረጋል። ለምሳሌ ሃይማኖቱን ቀይሮ ቢገኝ፣ በሃይማኖት የማይመስለውን ቢያገባ (በዝሙት ቢወድቅ)፣ ለክርስቲያን ያልተፈቀደውን ምግብ ቢበላ ወዘተ የመሳሰለውን ኢክርስቲያናዊ ግብር ፈጽሞ ቢገኝ የቀድር ጥምቀት ያስፈልገዋል ማለት ነው።
በርዕሱ ወደተገለጸው ጥያቄ ስንመለስ ፀበል አንዱ የንስሐ መንገድ ስለሆነ ለንስሐ ከሚያበቃን የኅጢአት ሥራችን ለመመለስ በቁርጠኝነት ከወሰንን ጠያቂው እንዳሉት ፀበል ለመጠመቅም ሆነ ለመጠጣት እንችላለን። ይህን ስንል ግን የሠራነው ኅጢአት ተለይቶ መታወቅ አለበት። ምክንያቱም ለምሣሌ የወለደች ሴት፣ የሴቶች ልማድ የምታይ ሴት እስከሚነፁ መጠበቅ አለባቸው። ከዚህም በላይ ፀበሉን ብንጠጣውም ሆነ ብንጠመቅበት ከልብ በሆነ እውነተኛ መጸጸት ወደ ንስሐ ሕይወት ተመልሰን ከበደላችን ነፃ ካልሆን ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝራዎች፣ ሟርተኞች ፣ መተተኞች፣ አስማተኞች፣ ቀማኞች፣ ወንበዴዎች፣ ትዕቢተኞች፣ ፍርድ አጉዳዮች፣ ከሃዲዎች ወዘተ ሁነን በአጠቃላይ ከአንድ ክርስቲያን የማይጠበቅ ክፉ ሥራ እንደፈጸምን እያወቅንና በንስሐ ሣንታጠብ እግዚአብሔርንና ራሣችንን በመደለል በአስመሣይነት ፀበሉን ብንጠመቅበትም ሆነ ብንረጭ ጥቅም አይሰጥም። እንዲያውም ከበረከት ይልቅ መርገምን ያመጣብናል። በመሆኑም ኅጢአተኛ ሰው ስለበደሉ የጊዜ ቀጠሮ ሣይሰጥ የመዳን ቀን ዛሬ ስለሆነ ባለበት ቦታ ሁኖ ያለምንም ድካምና ውጣ ውረድ ከልብ ለሚያምነውና ለነፍሱ እረኛ አባት አድርጎ ለተቀበለው አባቱ ኅጢቱን መናዘዝ አለበት። በእርግጥ የእኛ ኅጢአት የእግዚአብሔርን ቅድስና አያረክስም። እኛ ግን ንስሐ ሳንገባ በድፍረት የምናደርገው ሁሉ ተጨማሪ ኅጢአት ስለሚሆንብን፤ ወደ ቤተክርስቲያን ለመግባትና ፀበል ለመረጨትም ሆነ ለመጠጣት የሚያስከለክለውን በደላችንን ለይቶ ለማወቅ ሁልጊዜም ቢሆን መምህራንን ወይም የቤተክርስቲያን አባቶችን እንድታማክሩ በእግዚአብሔር ስም አደራ እላችኋለሁ።
የመድኅኔዓለም ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን
ምላሹም – ኅጥያቶን በመናዘዝ ከልብ ተጸጽተው ወይም ተመልሰው፤ ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት በማገልገል ላይ ለሚገኘው የንስሐ አባትዎ (ካህን) ራስዎን በማስመርመርና ከፈጸሙት በደል የሚነፁበትን ንስሐ ተቀብለው ከሄዱና ከዳግም ጥፋትም እርቀው በካህኑ የተሰጠዎትን ንስሐ በትክክል ከፈጸሙ፤ ከተያዙበት የኅጥያት ማሰሪያ ስለተፈቱ ንስሐም ገብተው ስለተናዘዙበት እንደገና ይፍቱኝ ለማለት ወደ ካህኑ የሚያስኬድ ጉዳይ አይኖርብዎትም።
ምክንያቱም በኅጥያት እድፍ የቆሸሸውን ህይወትዎን ከካህኑ በተቀበሉት የንስሐ ውሃ ታጥበው ከኅጥያት እድፍ ፀድተዋልና። ዳግም እንዳይበድሉ፣ ኅጥያት ሰርተውም የቅድስና ሕይወትዎን እንዳያቆሽሸው፣ በየጊዜው ከቤተ ክርስቲያን መምህራንና የንስሐ አባቶች ትምህርትና ተግሳጽ እያገኙ ምንም እንኳን የኑሮ ፈተና ቢበዛብዎ ከእናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ሳይርቁ እየፆሙና እየፀለዩ ከገንዘብዎ፣ ከእውቀትዎ እና ከጉልበትዎም አስራት በኩራት እያወጡ በጎ ስራ በመስራት ከሰይጣን ወጥመድ ለማምለጥ የሚችሉበትን መንፈሳዊ ፀጋዎትን በተቻለ መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ ማሳደግ እንዳለብዎ እመክራለው። ለዚህም ዋናውና መታወቅ ያለበት ነገር ማንም ክርስቲያን ያለጠባቂና ያለመካሪ ንስሐ አባት አንድ ቀንም መኖር ስለሌበት ወደ ንስሐ አባትዎ (ካህን) መሄድ ያለብዎ በየጊዜው የእለት እለት ህይወትዎን በካህኑ ምክር እንዲመራ ለማድረግ ነው።
በመሆኑም፤ ወደንስሃ አባትዎ ወይም ንስሐ ወደተቀበሉበት ካህን መሄድ የሚኖርብዎ ካህናት አባቶች የነፍሳችን እረኛ ሆነው በነፍስ ጉዳይ ላይ በሃላፊነት እግዚአብሔር ስለሾማቸው ሁልግዜም ቢሆን ከአባቶች ምክርና ተግሳጽ ላለመራቅ ነው እንጂ ቀደም ሲል ንስሐ ስለገቡበት ኅጥያት ይፍቱኝ ለማለት አለመሄድዎን እንደጥፋት ቆጥረው እንደገና ንስሐ እንዲገቡበት አያስፈልግዎትም በማለት መንፈሳዊ ምክሬን እለግሳለው። (ማቴ18፤18) ዩሐ(20፤21-23) ዩሐ (21፤15-18)
ከዚህ በላይ ስላቀረቡት ጥያቄ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ከፈለጉና ያልተመለሰልዎት ጥያቄ ካለም በውስጥ መስመር ሊያነጋግሩን ይችላሉ። ለሁሉም ነገር የእግዚአብሔር አጋዥነት ከእርስዎ ጋር ይሁን።
ሚስጥረ ተክሊል የሚፈጸምላቸው ተጋቢዎች በሃይማኖትና በምግባር ጸንተው በድንግልና ሕይወት ለተገኙ ሙሽራውና ሙሽራይቱ ብቻ ነው። ሚስጥረ ተክሊልም ለአንድ ሰው አንድ ጊዜ ብቻ የሚፈፀም ስርአት እንጂ አይደጋገምም። ሚስጥር የተባለበት ምክንያቱም ባልና ሚስት አንድ የሆኑበት ስርዓት ስለሆነ ነው። በጥንተ ተፈጥሮ ሴት የተገኘችው ከወንድ በመሆኑ “ይቺ አጥንት ከአጥንቴ ስጋዋም ከስጋዬ ናት” ተብሎ ሄዋን ከአዳም እንደተገኘችና አንድዋ ሄዋን ለአንድ አዳም እንደተፈጠረች ቅዱስ መፅሐፍ ያስረዳል። ዘፍ 2፤24
በስርአተ ተክሊል ጋብቻቸውን የሚፈፅሙ ጥንዶች ሁለቱም በድንግልና ጸንተው የኖሩ ለመሆናቸው በእግዚአብሔር ፊት ቀርበው ለንስሐ አባታቸው እራሳቸውን ሲያስመረምሩ ብቻ ነው። ከሁለት አንዳቸው ከስርዓተ ተክሊል በፊት ድንግልናቸውን ሊያሳጣ የሚችል ጥቃት ከፈፀሙ በቅዱስ ቁርባን አንድ ሊሆኑ ይችላሉ እንጂ የክብር አክሊል መቀዳጀት የሚችለው በድንግልና ሕይወቱ ጸንቶ የተገኘ ብቻ ነው። ምክንያቱም ስርአተ ተክሊል ማለት በቤተክርስቲያን ውስጥ በካህናት አባቶቻችን የተለየ የክብር ልብስ ሲለብሱ፣ በራሳቸው ላይ የክብር አክሊል ሲቀዳጁ፣ የሚፈፀምላቸው ስርአተ ፀሎት፣ በካህኑ የሚቀቡት የተቀደሰ ቅባት፣ የቃልኪዳኑ ምልክት የሆነው ቀለበት፣ በመጨረሻም ሁለቱም አንድ የሚሆኑበትና የአንድነታቸው ማሰርያ የሆነውን ቅዱስ ቁርባን ሲቀበሉ ነው። ይህ ደግሞ ታላቅ ሚስጥር ስለሆነ እግዚአብሔር ላደለው ሰው በፍፁም መንፈሳዊ ሕይወት ፈሪሃ እግዚአብሔር ኖሮን በምክረ ካህን ንስሐ ተቀብለን ከሰራነው ነውራችን አንዱንም ነገር ሳንፈራና ሳንደብቅ ግልፅ ሁነን የምንፈፅመው ስርዓት ከሆነ ኑሯችን፣ ትውልዳችን፣ ስራችን፣ ጤናችን፣ ሁሉ የተቀደሰና የተባረከ ይሆናል። ጋብቻ ቅዱስ ነው የተባለውም በዚህ ነው። ቅዱስ ጋብቻን የባረከው እግዚአብሔር አምላካችን ነው። ምክንያቱም አዳምና ሄዋንን ሲፈጥር አንድ ወንድን ለአንዲት ሴት ፈጥሮ ያጣመረ እሱ ነውና። በጣና ዘገሊላ በተደረገው የሰርግ ቤት ተገኝቶ ጋብቻን እንደባረከ ወንጌላዊ ዩሐንስ ነግሮናል። (ዩሐ 2፤1-11 እብ13፤4 ኤፌ 5፤31 እና 32)
ለጋብቻ የሚደረገው ጥንቃቄ የአንድ ትውልድ፣ ያንድ ታሪክ፣ ያንድ መንደር፣ ያንድ ሃገር የመነሻ መሠረት ስለሆነ ነው። ስለዚህ ጋብቻ በቅዱስ መፅሓፍ ሰፋ ያለ ታሪክ ያለው ቢሆንም ለጠየቁን አባላችን በመጨረሻ እንዲገነዘቡ የምንፈልገው የስርአተ ተክሊሉ አፈፃፀም ከ ሁለት አንዳቸው ከጋብቻ በፊት በተለየ ስህተት ፈተና ላይ የወደቁ ከሆነ በድንግልና ፀንቶ የቆየው የክብር አክሊል ሲደረግለት ሌላው ግን ንስሐውን በቀኖና ከፈፀመ በኋላ አብረው ስጋውና ደሙን በተቀበሉ ጊዜ አንድ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። በዚህ አይነት ስርዓት ጸንተው እንዲኖሩም ቤተክርስቲያን በፍቅርና በአንድነት ቃል ታገባባቸዋለች። ከዚህ በላይ መረዳት የሚፈልጉት ነገር ካለ በውስጥ መስመር ሊያገኙን ይችላሉ።
የአብርሃምና የሳራን ጋብቻ የባረከ አምላክ በስርዓተ ጋብቻ አንድ የሆኑትን ሁሉ ኑሯቸውን ይባርክ ዘንድ እንመኛለን።
አንድ ክርስቲያን የሆነ ወንድ ልጅ ወይም ሴት ልጅ በቤተ ክርስቲያን ቀኖና ድንግልናቸውን ጠብቀዋል ሲባል : –
1- ከጋብቻ በፊት የግብረ ሥጋ ግንኙነት አለማድረጋቸው በራሳቸው ቃለ መሓላ÷ በንስሐ አባትና በቤተሰበ ሲረጋገጥ
2- በሃይማኖታቸውና በክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ጸንተው ከእግዚአብሔር ቤት ሣይለዩ ቅዱስ ቁርባን እየተቀበሉ ስለመ ኖራቸው ቤተክርስቲያን ስትመሰክርላቸው
– ከጋብቻ በፊት የድንግልና ክብራቸው ን ሊያሳጣ የሚችል ሐጢአት ያልሰሩ ለምሣሌ ÷ የሰው ሕይወት ማጥፋት ጣዖት ማምለክ ማስጠንቆል መሥረቅ የ መሣሰሉትን ጥፉቶቸ መፈጸም ናቸው
የወንድ ልጅ ድንግልና ማረጋገጫ በ ራሱ ህሊና አምኖ ለነፍስ አባቱ ከሚገባው ቃል ኪዳን ዉጪ ሌላ አካላዊ ማረጋገጫ አይኖርም በእርግጥ ከምንም በላይ ልብንና ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ከሰው የሰወርነውን በደላችንን ሁሉ ሰለ ሚያውቀው ለህሊናችንና ለሃማኖታችን ስንል እውነቱን እዉነት ሃሰቱን ሃሰት ልንል ይገባል – የሴት ልጅ ድንግልና ራሷ ፍጹም ታማኝ እና ቅድስናዋን የጠበቀች ሁና እያለ :-
በተፈጥሮ -በሕመም ምክንያት – በአስገድዶ መደፈር – በከፍተኛ የሥራ እንቅስቃሴ (ክብደት) – በሕክምና እና በመሳሰለው ሁሉ አካላዊ የድንግልና ም ልክቷ ባይገኝባት እንደ ቤተክርስቲያ አስ ተምሮ ሌላ ነውር እሰከአልሠራች ድረስ የድንግ ክብሯን አያሳጣትም ስለዚህ
ስለድንግልና ማንነት ማወቅ የምንችለው በተፈጥሯዊ ዕውቀትና በሳይንሳዊ ምርምር ወይም በሰውኛ ዕውቀት ሳይሆን ብቸኛ ዐዋቂው የራሳችን ውሳጣዊ ኅሊናና የሁሉ ባለቤት ፈጣሪ ብቻ በመሆኑ መሠረታዊ የሆነውን ትምሕርተ ሃይማኖት ከማወቅ አልፎ ያለውን ድርሻ ለእግዚአብሔር ብቻ መ ስጠት አለብን ለሁሉም ነገር አምላካችን