ስለ እኛ ጥያቄና መልስ

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!" (ማቴ 3: 1-2)

ተከታታይ ትምህርትና ለጥያቄዎት ምላሽ ለማግኘት ቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

ስለ እኛ

ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች​

መልስ ፦  ጠያቂያችን ያቀረቡልን ጥያቄ ብዙም ግልፅ ባይሆንም የዮሐንስ ንስሓ የሚለው አገላለፅዎ እንዲስተካከል ሆኖ ነገር ግን የዚህ ድረገፃችን ዮሐንስ ንስሓ በሚል ስያሜ መጠራቱን በሚመለከት ከሆነ፤ እንደሚታወቀው መጥምቁ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የጌታን መገለጥ እና የመጨረሻውን የሰው ልጅ ድህነት ሊያረጋግጥ መምጣቱን ለመናገር ከሱ መገለጥ አስቀድሞ መንግስተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ በማለት የአዲስ ኪዳን የንስሓ ህይወት ሰባኪ እና ሐዋርያ ሆኖ በግልፅ ስለመሰከረ ይሄንን የቅዱስ ዮሐንስን ስብከት መሰረት በማድረግ የተሰጠ ስያሜ ስለሆነ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመቅረብ ሰወችን ሁሉ ለማበረታታት እና ከተኙበት የኀጢአት እንቅልፍ ለማንቃት የንስሓ ደውልና ጥሪ እንዲሆናቸው የተጠቀምንበት መንገድ መሆኑን እንዲያውቁት። ስለዚህ መዳን በዮሐንስ ንስሓ ብቻ  የሚለውን አነጋገር ትተው ማንኛውም ሰው እውነተኛ ክርስቲያናዊ ህይወት ለማግኘት ተፀፅቶ ንስሓ ከገባ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ እንደነገረን የእግዚአብሔር መንግስትን መውረስ ይቻላል። የእግዚአብሔር መንግስት ደግሞ በብዙ ውጣ ውረድ በብዙ ድካምና ጥረት በብዙ ሃይማኖታዊ ተጋድሎና መንፈሳዊ ህይወት የምትወረስ ስለሆነ እንደ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ለንስሓ የሚያበቃ እውነተኛውን የኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ስብከት የሚነግረን ሁሉ ለመንግስተ ሰማይ ስለሚያበቃን ሃሳቡን በዚህ መንገድ ይረዱት ዘንድ ይህን መልእክት እንዲደርስዎ አድርገናል።

መልስ፦ አሁንም ለአባላቶቻችን  አጥብቀን የምንነግራችሁ ከሁሉ በፊት መታዘዝን ማስቀደም ያስፈልጋል እንደመንፈሳዊነት ስንኖርም ሁሉን ነገር ለበጎ ነው ብለን በእግዚአብሔር አሰራር ወይም በመንፈሳዊ ህይወት ውስጥ ጊዜያዊ እና ወቅታዊ የሚባል ነገር ትርጉም አልባ ነው። ስለዚህ አባቶቻችን እኛን ለመጠበቅ ወይም እኛን ለመምከር እና እኛን ወደ መንፈሳዊ ህይወት ለመመለስ ሁል ግዜ እንደወታደር በተጠንቀቅ ቆመው ሊያገለግሉ የተዘጋጁ ናቸው። እኛ በአለም ስንኖር ስፍር ቁጥር የሌለው ጣጣ ስላለን ካንዱ አገር ወደ አንዱ አገር፣ ካንዱ ሃሳብ ወደ ሌላው ሃሳብ እየተንከራተትን ስለምንባዝን በያለንበትና በየደረስንበት ሁሉ ያለጠባቂ አንድ ቀንም እንዳናድር ባላችሁበት ቦተ ሁናችሁ በቅርብ ቦታ አባት ብታጡ እንኳን በርቀት ያሉትን አባት የመንፈስ ግንኙነትን የቦታ እርቀት ስለማይከለክለው በርቀት ንስሓ አባት እንድትይዙ ሁኔታዎችን ያመቻቸንላችሁ ለእናንተው በመጨነቅና በማሰብ ነው።
ስለዚህ ይሄን ጥርጣሬ እና ስጋትዎን አርቀው የመዳን ቀን አሁን ነውና አሁኑኑ ፈጥነው የተመደበልዎትን አባት ያናግሩ። ያገጠምዎት ችግር ካለ በውስጥ መስመር ያነጋግሩን። መዳን የጋራ ስለሆነ አገልግሎቱን የግዴታ ማድረግ አያስፈልግም።
መልስ፦ በድረገፃችን ላይ የሰጠናችሁ የንስሓ አባቶች እንዲካተቱ ያደረግነው በግልፅ አላማው ተነግሯቸው በመሆኑ ለማገልገል ፈቃደኛ ናቸው። በዚህ ጉዳይ  የተቸገሩበት ነገር ካለ እንድንረዳዎት በውስጥ መስመር ያሳውቁን።  
አገልግሎቱ ምን ያህል እውነት ነው? ብለው ለጠየቁን፦ በዮሐንስ ድረገፅ እና ቴሌግራም ቻናል ውስጥ በተከታታይ ወደ እናንተ የምናደርሳቸው የሃይማኖት ትምህርቶች እንዲሁም ከአባላቱ የቀረቡትን ጥያቄ መነሻ በማድረግ በየቀኑ የምንሰጣቸው ምላሾች ወደእናንተ ደርሰው እንደምትመለከቷቸው እና ጠቃሚ የሆነ የሃይማኖት ትምህርት እንደምታገኙባቸው እናምናለን። በመሰረቱ በእግዚአብሔር መንገድ የመጣ ሰው የእግዚአብሔርን ስራ ይሰራል፥ በወንጌል እንደተፃፈው ከመልካም ዛፍ የሚለቀም ጣፋጭ ፍሬ ነው፥ ከክፉ ዛፍ ደሞ የሚለቀም መራራ ፍሬ ነው። ከዚህ የተነሳ ጣፋጩን እና መራራውን ፍሬ መለየት የሚቻለው እግዚአብሔር በሰጠን የተፈጥሮ ስሜት በማጣጣም ነው። ስለዚህ ጠያቂያችን ምናልባት ምን እንዳሳሰብዎት ግልፅ ባይሆንም እስካሁን ድረስም በዚህ ፕሮግራም ያስተላለፍናቸው መልዕክቶች የሰውን ልጅ ከነፍስ ሞት ለመታደግ አስበን እና ምርኮ ለማትረፍ እግዚአብሔር በሰጠን ትንሽ የእውቀት ፀጋ ከእናንተ ጋር በዚህ እግዚአብሔር በሚወደው መልካም ፕሮግራም ወስነን የገባንበት የውዴታ መንፈሳዊ ግዴታ ስለሆነ እንጂ በሌላ በምንም አይነት የስጋዊ ጥቅም የሚለካ አንዳች ነገር የለም። 
የክርስቲያን ወገኖቻችን አስረግጠን እውነቱን የምንነግራችሁ በዚህ አላማችን ውስጥ የመናፍቅነት፣ የክህደት፣ የስነምግባር ችግሮች ቦታ እንዳይኖራቸው ሰይጣንን ከብዙ ህይወት ውስጥ ሳይወድ በግድ ታግለን በእግዚአብሔር ሃይል እና ጥበብ ለመለየት በዘመኑ የሰለጠነውን የኀጢአት እና የክፋት መንገድ አስቀርተን ሁላችሁም የዘላለም ህይወት እንድታገኙ እስካሁንም ብዙ ተጉዘናል ወደፊትም እግዚአብሔር ከኛ ጋር እስከሆነ ድረስ የሚያቆመን ነገር የለም።
በመሆኑም ማንኛውም ክርስቲያን ጭንቀትን አስወግዶ በፕሮግራማችን በእግዚአብሔር ቸርነት እየታገዘ እንዲቀጥል እናቱ ወላዲት አምላክ እና ቅዱሳን በፀሎታቸውና በምልጃቸው እንዲያግዙን ከዚህ በላይ መንፈሳዊ ትርፍ እንድናገኝበት እንዲሁም የአውሬው መንፈስ ከሰለጠነበት ከዚህ ዘመን አሰቃቂ ፈተና እና መከራ ለመውጣት እንድንችል የእናንተ ድርሻ መሆን ያለበት በሃሳብ፣ በፀሎት በሌላም አስፈላጊ በሆነው ምክረ ሃሳብ እየተረዳዱ፥ አንዱ አንዱን እያበረታው፣ አንዱ አንዱን እያገዘው መቀጠል የምንችልበትን ሃሳብ እያሳደጉ መምጣት እንጂ ስለነገው እግዚአብሔር ያስባልና ምን የፈጠር ይሆን? ምን ይመጣ ይሆን? ምን ያጋጥማችሁ ይሆን? ማለት የኛ ድርሻ አይደለም። ስለዚህ በምንሰጠው አገልግሎት ደስ እያላችሁ እየተከታተላችሁ በነፍሳችሁም እረፍት ታገኙ ዘንድ ይህን መልዕክት አስተላልፈናል።
መልስ፦ በዚህ ፕሮግራማችን ላይ የሃይማኖት ትምህርት የሚያቀርቡና ለጥያቄዎቻችን መልስ የሚሰጡልን አባቶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና ጠንቅቀው የሚያውቁ የጉባኤ መምህራን ከመሆናቸውም በላይ አሁንም በቤተክርስቲያንዋ የአገልግሎት ዘርፍ በሃላፊነት ደረጃ ላይ ይገኛሉ ፤ አባላችን እንደጠቀሱት ከትልቅ አክብሮት ጋር ስማቸው ማነው ብለው መልካምና የፍቅር አጠያየቅ ስለሆነ ያቀረቡት በመጀመርያ ሀሳብዎን  ለመረዳት እንድንችል በውስጥ መስመር በላክንልዎ ስልክ ቁጥር ደውለው ቢገልፁልን ለጥያቄዎ መልስ ያገኛሉ።
“የዘለዓለም ሕይወትን አገኝ ዘንድ ምን መልካም ነገር ላድርግ?” (ማቴ 19፥16)
 
በዚህ መለኮታዊ ኃይለቃል መነሻነት ጠያቂያችን ላቀረቡልን የመልካም ስራ ጥያቄ እንደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን መፅሐፍ ቅዱሳዊ አስተምሮ መሰረት የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተናል። 
 
መልስ፦ ጠያቂያችን ከሁሉም በላይ በየግዜው በዮሐንስ ንስሓ ድረገፅ የምናስተላልፈውን የሃይማኖትና ክርስቲያናዊ የስነምግባር ትምህርት እያነበቡና እየተረዱ እንደሆነ ካቀረቡልን ጥያቄ ተገንዝበናል። በዚህ መንፈሳዊ ትምህርት ያገኙትን መንፈሳዊ እርካተ በመግለፅ ከእርስዎ የሚጠበቀውን መንፈሳዊ ድርሻዎን ለመወጣት እና ከአንድ እውነተኛ ክርስቲያን የሚጠበቀውን የምግባር ወይም የቱሩፋት ስራ ለመስራት በማሰብ “ምን ልደግፍ?” በማለት ያቀረቡትን ጥያቄ ስንመለከት በእኛም በኩል እግዚአብሔር በፈቀደልን መጠን የዘራነውን የእግዚአብሔር ቃል ፍሬ እንዳፈራ ስላስተዋልን በእጅጉ እንዲህ አይነት የእምነትና የምግባር ሰዎችን እግዚአብሔር እንዲያበዛ ከወዲሁ ያለንን ልባዊ ምኞት እንገልፃለን። ከምንም በላይ ትምህርቱ ከፈጣሪዎ እና ከቅድስት ቤተክርስቲያን ጋር ለማገናኘት እንዲችሉ እና በግል ህይወትዎም ለንስሓ ህይወት የበቁበት እድል እንደሆነ ካቀረቡልን ጥያቄ ለመረዳት ችለናል ። በመሰረቱ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንደምንማረው ገበሬው ንፁህ ዘር የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል ንጹህ መሬት በሆነው በክርስቲያኖች ልቦና ላይ የሚዘራው ዘር በቅሎና አብቦ መልካም ፍሬ አፍርቶ ገበሬው ተገቢውን ምርት አፍሶ ወደ ጎተራው ለማስገባት እንደሚችል ያስተምረናል። ጤናማ እና ታታሪ ገበሬ የእርሻው መሬት ዘር ቆርጥም ሆኖ እንዳይቀርበት አስቀድሞ ወቅቱን ጠብቆ የእርሻውን መሬት አለስልሶ እና ዘር አዘጋጅቶ ስለሚያስቀምጠው የተፈለገውን ምርት በመስጠት ለገበሬው የድካም ዋጋውን ይከፍለዋል።
 
በአንፃሩ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል “እነሆ ዘሪ ሊዘራ ወጣ እርሱም ሲዘራ አንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ ወፎችም መጥተው በሉት፣ ሌላው ብዙ መሬት በሌለበት በጭንጫ ወደቀ ጥልቅ መሬት ስላልነበረበት ወድያውኑ በቀለ ፀሀይ በመጣ ጊዜ ግን ጠወለገ ስርም ስላልነበረው ደረቀ፣ ሌላው በእሾህ መካከል በቀለ እሾህም ወጣና አነቀው፣ ሌላው በመልካም መሬት ላይ ወደቀ አንዱ መቶ፥ አንዱም ስልሳ፥ አንዱም ሠላሳ ፍሬ ሰጠ፤ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።” በማለት ንፁህ ዘር የተባለው የእግዚአብሔር ቃል ሲሆን፣ በገበሬ የተመሰለው የእግዚአብሔርን ቃል የሚያስተምረው የቤተክርስቲያን ወይም የወንጌል መምህር በየጊዜው በምእመናን ልቦና ላይ የሚዘራው የወንጌልን ቃል አምነው ልባቸው በተነካ ጊዜ በጎ ምግባር ለመስራት የተነሳሱ የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በገንዘባቸው፣ በጉልበታቸው፣ በእውቀታቸውና በጊዜያቸው ሁሉ በጎውን እና የቀናውን ምግባረ ሰናይ ለመስራት በወሰኑ ግዜ ወደ አስተማሪዎቻቸው ወይም ወደ ሃይማኖት አባቶቻቸው ቀርበው ምን እናድርግ? ምንስ እንታዘዝ በማለት ፈቃደኝነታቸውን በእግዚአብሔር ፊት እንደሚገልፁ በምሳሌ ገልፆ አስተምሮናል። ጠያቂያችንም ሆኑ ሁላችሁም የዚህ መንፈሳዊ ድረገፅ አባላት በዚህ ጥያቄ መነሻነት የምናስተላልፈው መንፈሳዊ የምክር አገልግሎት ለጠያቂ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖች አርአያ እና ሞዴል የሚሆን ትምህርት ስለሆነ ከላይ በመግቢያችን እንደተጠቀሰው እግዚአብሔር አምላካችን አለም ሳይፈጠር አስቀድሞ ለወዳቾቹ ያዘጋጃትን ሰማያዊመንግስቱን ለመውረስ የሚያስችለን የምግባርና የትሩፋት ስራ ለመስራት ምን እናድርግ ከእኛ የሚጠበቅ ምንድነው በየትኛው አገልግሎትስ እንሳተፍ በማለት ፀሀይ እድሜያችን ሳይጠልቅ የመስራት አቅማችን ሳይደክም የፅድቅ ስራ የምናውለው ሃብታችን እና ጉልበታችን ሳይደቅ በክብራችን እና በሞገሳችን ገና ሳለን መታዘዝ እና እግዚአብሔር የሚወደውን ነገር ለማድረግ መትጋትና በፅድቅ ስራ መጋደል አለብን።
 
አሁንም በድጋሚ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ “የዘለአለም ህይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ?” (ማር10፥17) “የዘላዓለም ህይወት እንድወርስ ምን ላድርግ?” ሉቃ 18፥18 በማለት በመነሻችን ከጠቀስነው ሃይለቃል ጋር የሚተባበሩ የወንጌል ቃል ናቸው። ሁሉንም አውቄያለው ሁሉንም አድርጌያለው ብሎ ከስራው የሚመፃደቅና ራሱን ከፍ ከፍ ያደርግ የነበረ ከአይሁድ ወገን የነበረ አንድ ሰው ነበር።  ጌታችን መድኅኒታችን እየሱስ ክርስቶስ መምህር ሆይ አንተ ደግ እና እውነተኛ መምህር እንደሆንክ አውቃለውና ስለዚህ ሰማያዊ መንግስትን ለመውረስ የሚያበቃኝን ምን ላድርግ ወይም የትኛውን በጎ ምግባር ልስራ የሚል ጥያቄ እንደቀረበለት ቃሉ ያስረዳናል። እውነተኛ መምህርና ጠባቂ እረኛ የሆነው አምላካችን መድኅኒታችን እየሱስ ክርስቶስም ቀጥሎ ያለውን ሲያስረዳው ያባለፀጋ ወይም ፈሪሳዊ ሃብታም አድርግ ስለተባለው የምግባር ስራ ለመታመን ቢፈተንም እንኳን ለእኛና ለተከታዮቹ እና እስከ አለም ፍፃሜ ላለነው ለሁላችንም ለምግባር ስራ መሰረት የሆነ ትምህርት አስተላልፎልናል። አንዳንድ ግዜ ሃብታቸውን ወይም ገንዘባቸውን የደምስር አድርገው የሚቆጥሩ ባለፀጋዎች (ብዑላን) ከፈጣሪያቸው ወይም ከነፍሳቸው ጉዳይ ይልቅ ሃብታቸውን የሚያመልኩ ይበዛሉ የዚህ አለም ሰዎች እግዚአብሔር በሰጣቸው ሃብታቸውና ሙሉ ጤንነታቸው በጎ ስራ ሰርተው ለነፍሳቸው የሚሆን የፅድቅ ስራ ሳይሰሩበት እንዲሁ በከንቱነት ሀብታቸው እና እድሜያቸውም አልቆ ሁሉም ነገር ታሪክ ሆኖ በኪሳራ የሚያልፉ ብዙዎች ናቸው። 
 
ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ከፍጥረታት ሁሉ እኛን በልዩነት በአርአያውና በምሳሌው እንዴት እንደፈጠረን ስናስብ እያንዳንዱ ከተሰጠን የተፈጥሮ አካል ጀምሮ ምንም ዋጋ ሳንከፍልበት ከፈጣሪ በነፃ ወይም በልግስና ያለ ዋጋ ያገኘነውን ነገር ሁሉ ስናስብ ለእግዚአብሔር እሱ ከሰጠን ነገር በልጅነት መንፈስ ሆነን ትንሽን ነገር ብንታዘዘው ምን ሊጎናን ይችላል? ነብየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊትም “ስላደረገልኝ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምን እከፍለዋለው?” በማለት እግዚአብሔር ስላደረገልን ነገር ሁሉ ዋጋ ለመክፈል ብናስብም እንኳን ተመጣጣኝ ክፍያ ለሱ ለማቅረብ ስለማንችል እንደው ዝም ብለን በልጅነት መንፈስ ዘወትር ጠባቂያችን እና መጋቢያችን ለሆነው አምላክ ትንሽ ነገር የልጅነት ስጦታ (አመሃ እና መባ) ልናቀርብ ይገባናል። 
 
በመሰረቱ የዮሐንስ ድረገፅ አገልግሎት የነፃ ትምህርትና የምክር አገልግሎት የሚሰጥበት ድረገፅ እንደሆነ ሳንዘነጋ ነገር ግን በእናንተ ከሚቀርቡ ጥያቄዎችና በትምህርቱ ውስጥ ባለውም በእግዚአብሔር ቃል ትምህርት በሚተላለፈው መልዕክት ውስጥ ስለቱሩፋት ስራዎች አስመልክቶ የሚተላለፍ መልዕክት እንደሆነ ሁላችንም መረዳት ያስፈልገናል። ስለዚህ ጠያቂያችንም ሆኑ ሌሎቹ የመንፈሳዊ ፕሮግራማችን አባላት ደካማ በሆነው አቅማችን ወደ እናንተ የምናስተላልፈው የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ህይወት ውስጥ በጥቂቱም ቢሆን ምክር እና ተግሳፅ ሁኖዋችሁ ከሆነ (ትምህርት ያገኛችሁበት ከሆነ) በዚህ በፈተናው ዘመን ለቤተክርስቲያን ለጎደለው ነገር እና ድጋፍና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖቻችን መልካም ስራ በማድረግ ብትሳተፉ እግዚአብሔር በእድሜ ላይ እድሜ በጤና ላይ ጤና በሃብት ላይ ሃብት ሊለግሰን እንደሚችል ሳንጠራጠር በፍፁም እምነት ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን በአጠቃላይ ጠያቂያችን ምን ላድርግ ብለው ባቀረቡልን የምግባር ጥያቄ ይህን መልዕክት ለሁላችሁም ኦርቶዶክሳዊያን ትምህርቱን አንብባችሁ በመረዳት ምን ያህል እንደተጠቀማችሁ ለመገንዘብ የሚያስችል በጎ ምላሻችሁን እንጠብቃለን።
 
እግዚአብሔር አምላክ የማያልፈውን በጎ ስራ ሰርተን ሰማያዊ መንግስቱን ለመውረስ ያብቃን
መልስ፦   ጠያቂያችን እንዲሁም ሌሎች የዮሐንስ ንስሓ ድረገፅ አባላት፤ በልዩ ምክንያት ወይም ለተጨማሪ ምክርና ማብራሪያ ደውለው ሊያገኙን እንደሚችሉ ገልፀን ስልክ ቁጥር በውስጥ መስመር አንዲደርሳችሁ ካደረግን በማንኛውም ጊዜ ማለትም ከሰኞ እስከ እሁድ ባሉት ቀናት  ከጠዋቱ 3 ሰአት እስከ ምሽቱ 3 ሰአት ባለው ጊዜ ውስጥ ደውለው ሊያናግሩን እንደሚችሉ እንገልፃለን።

መልስ፦ ጠያቂያችን በንስኀ አባቶች ዙርያ የሰጡት የጥርጣሬ ሃሳብ ከትክክለኛ አማኝ ወይም ክርስቲያን ዘንድ የሚጠበቅ አባባል አይደለም። የስልጠና ክህነት ፀጋ በምድራዊ የሹመት ደረጃ የሚታይ ስላልሆነ ፤ ፀጋው የክህነት ባለቤት ከሆነው ከእግዚአብሔር የተሰጠ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በመሆኑ የሚጨበጥ ወይም በአይን የሚታይና በስጋዊ ጥበብ ሊመረመር የሚችል አይደለም :: በተጨማሪም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት እንዲያሥሩና እንዲፈቱ የሰጣቸው ስልጣነ ክህነት የጊዜና የቦታ ርቀት የማይወስነው ስለሆነ ፤ በአካባቢው አባት የሚሆን ካህን ከጠፋ ያለጠባቂ ብንኖር ጠላታችን ዲያብሎስ ነፍሳችንን እንዳይነጥቃት የንስሐ አባት በርቀትም መያዝ እንችላለን። ስለዚህ ጠያቂያችን ማወቅ ያለብዎት ንስኀ በአካልም ይሁን በርቀት-በመገናኛ መንገድ ፤ ዋነኛው አላማው የሰራነውን በደላችንን እና ኀጢአታችንን በንስሓ ማጥፋት ነው። የካህኑ ክህነት የሚመዘነው በሃይማኖቱ እና በምግባሩ ብቻ ነው። ከእግዚአብሔር በተሰጠው አደራ መሰረት መንጋውን በስርዓት የሚያሰማራ የእግዚአብሔርን ቃል የሚፈፁም ፣ ስጋ ደሙን ተቀበሉ የሚል ፣ ኀጢአት አትስሩ የሚል፣ በምግባር በሃይማኖት ፀንታችሁ ኑሩ የሚል ፣ በነገሮች ሁሉ ከሰዎች ጋር በሰላምና በፍቅር አንድንኖር የሚመክር፣ የቱሩፉት ስራ አብዝተን እንድንሰራ የፅድቅን አቅጣጫ ወይም የጽድቅን በር የሚያሳይ አባት ከሆነ ትክክለኛ ካህን መሆኑን የምናረጋግጥበት ምስጢር ይህ ነው :: ከዚህ ውጭ በአንዳንድ ሰዎች ህሊና የሃይማኖት ህፀፅ የኑፋቄ እና የክህደት ትምህርት ሲያድርባቸዉ እንዲህ አይነት የነቀፉ ጥያቄ ሲቀርቡ የመሰማታችን ጉዳይ የተለመደ ስለሆነ ነገር ግን በዚህ ፕሮግራም ይህን ጥያቄ ያቀረቡ አባል ከምን አኳያ እንደሆነ ብዙ ግልፅ አይደለም :: ምክንያቱም ካህናትን ለመንቀፍ ታስቦ ይሁን ወይም እኛ ያልተረዳነው ችግር አጋጥሞዎት ይሁን ለመረዳት የሚያዳግት ሃሳብ ስለሆነ አመለካከትዎን ቢያስተካክሉት ከሁሉ የተሻለ መሆኑን እንመክራለን :: ለቅዱሳን የመማፀኑ እና የአማላጅነት ጥያቄ ማቅረቡ እኛንም የሚያስደስተን ዋና አላማችን ቢሆንም ነገር ግን ዛሬ ላይ በመከራም በደስታም በመካከላችን የሚያገለግሉንን ካህናትን ለመንቀፍ የተጠቀሙበት ሃይለ ቃል ከሆነ ግን እንዲያስተካክሉ ምክራችንን በታላቅ አክብሮት እና ትህትና እንለግሳለን። በተጨማሪም ስለ ስልጣነ ክህነት ከመፅሐፍ ቅዱስ ቃል ማስረጃ ለጠየቁት ከዚህ በፊት ያስተላለፍነውን ትምህርት እንደሚከተለው ልከንልዎታልና አንብበው እንዲረዱ እመክራለን።

“የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።” (ማቴ ፲፮᎓፲፱) ይህ ማለት ምን ማለት ነው?

ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርሰቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሰጣቸው የክህነት ስልጣን ማሰር እና መፍታት የሚችሉበት ረቂቅ እና ሰማያዊ ስልጣንን ነው። ወደ መንግስተ ሰማያት ለመግባትም ሆነ ከመንግስተ ሰማያት ለመከልከል የሚያስችል ከመንፈስ ቅዱስ የተሰጣቸው ስልጣንም ነው። ይህ ማለት ስልጣን ሁሉ የራሱ ገንዘብ የሆነው የባህርይ አምላክ እየሱስ ክርስቶስ 12ቱን ሐዋርያት እና 72ቱን አርድእት ከዓለም መካከል መርጦ በሾማቸው ግዜ ኀጥያት ሰርተው በደል ፈጽመው ወደ ሐዋርያት ቀርበው በኀጢአታቸው ተጸጽተው የተናዘዙትን ኀጥያታቸውን የማስተሰረይ ስልጣን ስለተሰጣቸው ኀጥያታችሁ ይቅርላችሁ ያሏቸው ሁሉ የተሰጣቸው ረቂቅ ስልጣን ኅጥያታቸው ሁሉ እንዲደመሰስ ያደርጋል።

በሰሩት ጥፋት ሳይጸጸቱ እና ከበደላቸው የማይመለሱትን ደግሞ በተሰጣቸው ረቂቅ ስልጣን ሲፈርዱባቸው በስጋቸው ሞትና ልዩ ልዩ መቅሰፍት ይቀጣሉ ማለት ነው። 

ለዚህ ማስረጃ የሚሆነን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ፦

–  ግያዝ የተባለው የነብዩ ኤልሳዕ ደቀመዝሙር ከመምህሩ ተሰውሮ ከለምጽ በሽታ ካዳነው ሶርያው ንጉስ ከንዕማን ላይ የማይገባውን ጥቅም በመውሰዱ ምክንያት ነብዩ ኤልሳዕ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ፀጋ ግያዝን በለምጽ ደዌ አንደቀጣው እንመለከታለን። 2ኛ ነገስት 5፥20-27

–  ሐናንያ እና ሰጲራ የተባሉ ባልና ሚስቶች በሐዋርያት ፊት ያላቸውን የሀብታቸውን እኩሌታ ለእግዚአብሔር ሊሰጡ ቃል ከገቡ በኋላ ሳይፈጽሙ በመቅረታቸው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስን አታላችኋል ብሎ በተሰጠው የክህነት ስልጣኑ የሞት ቅጣት እንዲደርስባቸው አድርጓል። የሐዋ 5፥1-10

–  በጥንቆላ መንፈስ የሚኖር ሲሞን መሠሪ የተባለው ሰው ሐዋርያት እጅ በመጫን  የመንፈስ ቅዱስ ኅይል የሚሰሩትን አስደናቂ ሚስጥር ባየ ግዜ እንደእናንተ ይሄንን ታላቅ አስደናቂ ስራ ለመስራት እንድችል ከመንፈስ ቅዱስ ያገኙትን ስልጣን በገንዘብ ሽጡልኝ ባላቸው ግዜ እድል ፋንታውን ከክፉዎች ጋር እንዲሆን እና የጥፋት ሰው አንደሆነ ረግመውታል። ዩሐ 8፥18-24

ከዚህ በላይ በጠቀስናቸው ማስረጃዎች የመንግሰተ ሰማያት መክፈቻ ለሐዋርያት ተሰጠ ሲባል በተሰጣቸው ስልጣነ ክህነት መንግስተ ሰማያት ማስገባት እንደሚችሉ እና የማይገባቸውን መከልከል የሚችሉ መሆናቸውን ለመግለጽ እንጂ የቤት ወይም የበር ቁልፍ መክፈቻና መዝጊያ ቁሳዊ ነገር አለመሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። ማሰር መፍታት የሚለውም በዚህ አለም ላይ ሰው በፈጸመው ወንጀል የሚታሰርበት እግር ብረት ወይም ገመድ ወይም ሌላ ነገር ሳይሆን ከላይ እንደገለጽነው በተሰጣቸው ረቂቅ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ስልጣን ኅጥያትን የማስተሰረይ፣ የኀጥያተኞችን ኅጥያት የመያዝ ፀጋ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል።

ጠያቂያችን እንዲሁም ሌሎች የዮሐንስ ንስሓ ድረገፅ አባላት፤ በልዩ ምክንያት ወይም ለተጨማሪ ምክርና ማብራሪያ ደውለው ሊያገኙን እንደሚችሉ ገልፀን ስልክ ቁጥር በውስጥ መስመር አንዲደርሳችሁ ካደረግን በማንኛውም ጊዜ ማለትም ከሰኞ እስከ እሁድ ባሉት ቀናት  ከጠዋቱ 3 ሰአት እስከ ምሽቱ 3 ሰአት ባለው ጊዜ ውስጥ ደውለው ሊያናግሩን እንደሚችሉ እንገልፃለን።

ጠያቂያችን ፤ በዚህ ደረገጽ ላይ የሃይማኖት ትምህርት የሚያቀርቡና ለጥያቄዎቻችን መልስ የሚሰጡልን አባቶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና ጠንቅቀው የሚያውቁ የጉባኤ መምህራን ከመሆናቸውም በላይ አሁንም በቤተክርስቲያንዋ የአገልግሎት ዘርፍ በሃላፊነት ደረጃ ላይ ይገኛሉ ፤ ስለዚህ አባላችን እንደጠቀሱት  ለማንኛውም መንፈሳዊ ጥያቄ ከላይ በገለጽነው መሰረት ከአባቶች መልስ ያገኛሉና ይጠይቁ።
 
ጠያቂያችን በዮሐንስ ንስኀ መንፈሳዊ ፕሮግራም ድረገጽ የሚተላለፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና የጥያቄና መልስ በቴሌግራም ገጻችን በመከታተል ያገኙትን ጠቃሚ ትምህርት ታሳቢ በማድረግ በግል መንፈሳዊ ህይወትዎ ምን ያህል ተጠቃሚ እንደሆኑ በመግለፅ እንዲሁም  በዚህ ፕሮግራም ያዩትን የሌሎቹን መንፈሳውያን ክርስቲያኖች ተሳትፎ ግምት ውስጥ በማስገባት ሁሉም አባላት በያሉበት አካባቢ ወደ ንስኀ አባቶቻቸው ቀርበው ንስኀ ለመግባት እንዲችሉና ጥያቄዎችንም ወደ ንስኀ አባታቸው የመውሰድ ልምድ እንዲኖር ፤   እርስዎ የነበረቦትን ሥጋዊ ደካማነት መሰረት በማድረግ በአንጻሩ ድግሞ በዚህ መንፈሳዊ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆኖትን ከአድናቆት ጋር ስለ ገለጹልን በእኛም በኩል ይህን ያህል ፕሮግራማችንን በትኩረት ተሳትፈው ስለተከታተሉ እናመሰግናለን። ወደፊት መንፈሳዊ ህይወትዎን፣ ፀጋዎን፣ እንዲያሳድጉ ከምንም በላይ እግዚአብሔር እንዲረዳዎት እንጸልያለን። 
 
ነገር ግን እርስዎ ስላነሱት ዋና ጥያቄ ስንመለስ ፤ መታወቅ ያለበት የዚህ ድረ ገጽ ዋና አላማ (ታርጌት) በ40ና በ80 ቀን የእግዚአብሔርን ልጅነት አግኝተው በስመ ክርስቲያን እየተጠሩ ከቤተክርስቲያንና ከመንፈሳውያን አባቶቻቸው እርቀው የሚኖሩትን ወገኖቻችንን በነፍስም በስጋም ከሚያጠፋቸው ጥንተ ጠላታችን ከዲያብሎስ እጅ ነፃ ለማውጣት ይቻል ዘንድ የምናደርገው ሐዋርያዊ ተልዕኮ ስለሆነ በዚህ ፕሮግራም የተሰጠውን ትምህርት የሚከታተሉ ወገኖቻችን ሁሉ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንዲቀርቡ፣ የንስኀ አባት እንዲይዙ፣ ስለሚሰሩት ኀጢአትም ንስኀ እንዲገቡ ለማስቻል የሚደረግ መንፈሳዊ ጉዞ እንደሆነ ጠያቂያችንም ሆኑ አባላቶቻችን እንዲረዱት ያስፈልጋል።
 
ከምንም በላይ የዮሐንስ ንስኀ ድረ ገፅ ዋና አላማው በተለያየ ዓለማዊ እና ሥጋዊው ተግዳሮት ከመንፈሳዊ አላማ እርቀው የሚኖሩትንም ወገኖቻችን ሁሉ ወደ አባታቸውና ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር እና ወደ እናታቸው ወደ ቤተክርስቲያን እንዲቀርቡና ዘወትር እንዲያገለግሏቸው እንደ አባት እንዲሆኗቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ከተሰጧቸው ከመንፈሳዊ አባቶቻቸው ጋር ለማገናኘት እንደሆነ ሁላችሁም በአትኩሮት ልትረዱ ይገባችኋል ::
 
በሁሉም ነገር ተሳትፎዋችሁን እናደንቃለን።
 
ከዚህ በፊት ለተጠየቁ ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾችን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፦ https://yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ​
 
ንስሐ አባት ለመያዝ እዚህ ይጫኑ፦ https://yohannesneseha.org/የንስሐ-አባት-ገጽ/

መልስ፦ጠያቂያችን የንስኅ አባት በመያዝ በደወሉ ጊዜ በመጀመርያ መግባባት እንዳልቻሉና ሆኖም የደወሉላቸው አባት ለበጎ ነገር እንደሆነ በመገንዘብ ተቀብለው እባት እንደሆኑዎት የገለፁልንን አስተያየት ተመልክተነዋል። በእርግጥ በኛ በኩል በሁሉም ቦታ ከአዲስ አበባ ጀምሮ በየክልሉና በየአካባቢው የሚገኙ አባቶችን አመቺ በሆነ ሁኔታ በወቅቱ የንስኅ አባት እንዲሆኑ በማዘጋጀት አላማውንም በማስረዳት የሚደውሉላቸውን የመንፈሳዊ ልጆች ተቀብለው የንስኅ አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ስራ መስራታችን እውነት ነው። በዚህም አንዳንድ አባቶች እንደተደወለላቸውና አገልግሎቱንም እየሰጡ እንደሆነ እናውቃለን፤ ከአባላቶቻችን በየጊዜው ከሚደርሱን መልዕክትና አስተያየትም በዚሁ ድረገፅ አማካኝነት የንስኅ አባት አግኝተው በአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሆኑ መስክረዋል። ነገር ግን አንዳንድ አባቶች ጋር በወቅቱ አባት ፈልጎ የደወለላቸው ሰው ባለመኖሩ ከብዙ ጊዜ ቆይታ በኋላ ሲደወልላቸው ሊዘነጉ እንደቻሉ ከአባላት ከደረሰን አስተያየት ተነስተን ለማጣራት ባደረግነው ጥረት ካናገርናቸው አባቶች ተገንዝበናል። የሆነ ሆኖ የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጪው እንዲሉ ዋናው ነገር እንዲህ አይነት ጥቃቅን ችግር በሚገጥም ጊዜ መበርገግ እንደሌለባችሁ እየመከርን፤ ምንም አይነት የተቸገራችሁበት ነገር ካለ በቀላሉ እዛው ድረገፁ ላይ ባስቀመጥነው ስልክ ቢደውሉ በኛ ዘንድ አስፈላጊውን አገልግሎት ያገኛሉ። እናንተ የሚያስተምር እና የሚመክር አባት ለማግኘት ለንስኅ ህይወት አላማ ፀንታችሁ ከተጋችሁ እኛም ለእናንተ ምቹ ሁኔታዎችን ለማዘጋጀት የሚከብድ አይደለምና አባት የሚሆናችሁን በአድራሻችሁ የምንሰጣችሁ መሆኑን ተገንዝባችሁ በዚህ ሁኔታ አንዳችም ነገር የሚያስጨንቃችሁ አጋጣሚ እንደማይኖር ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።  

 ጠያቂያችን በዮሐንስ ንስኀ ድረገፅ መንፈሳዊ ፖሮግራም ተደራሽ የምናደርገውን ተከታታይ ትምህርትና እና ጥያቄና መልሶችን በማንበብዎና በመከታተልዎ እኛም እጅግ አድርገን እናመሰግናለን። በእንዲህ አይነት መንፈሳዊ አገልግሎት ፀንተን እንድንኖር እግዚአብሔር ለሁላችንም የፅድቅ መንገድ ያመቻቸልን ስለሆነ ከጠፋንበትም ተመልሰን በእግዚአብሔር እቅፍ ስር እንድንሆን አስተማሪዎችን መካሪዎችን ያላሳጣን ስለሆነ ሁላችንም ተያይዘን የእግዚአብሔርን መንግስት የምንወርስበትን በጎ ስራ ሁሉ ማስቀደም ስላለብን፤ እርስዎም የእግዚአብሔርን ቃል ለመመከር ቅድሚያ መስጠትን ወደፊትም ቸል እንዳይሉ አደራ በማለት ለጠየቁን ጥያቄም በውስጥ መስመር በሰጠነው አድራሻ ያገኙን ዘንድ የኛም ፈቃድ ነው።

ጠያቂያችን፦ እንደሚታወቀው የዚህ መንፈሳዊ ፕሮግራማችን ዋና አላማ በአንድም በሌላም መንገድ በልዩ ልዩ ምክንያት የእግዚአብሔርን ቃል በቅርብ ለመከታተል የማይችሉ፣ በፈተና ውስጥ ያሉ ወገኖችን ትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ የስነምግባር ትምህርት በቀላሉ እንዲያገኙ በማድረግ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ማቅረብ ነው። በመሆኑም በዚህ ድረገፅ የቴሌግራም ግሩፕ በመቀላቀል አባል የሆናችሁ ወገኖቻችን ሁላችሁም በድረገፁ ላይ የምንልካቸውን ተከታታይ ትምህርቶችን እና እናንተ ለምታቀርቧቸው ጥያቄዎች የሚሰጡ መልሶች ሁሉ እናንተን ያስታምራል፣ ይመክራል፣ ንስሓ እንድትገቡ ያደርጋል በአጠቃላይ በሃይማኖታችሁና በምግባራችሁ ታንጻችሁ የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ ያበቃል ብለን በማሰብ ያለንን መንፈሳዊ ሃላፊነት ለመወጣት ነው። በመሆኑም በዚህ ፕሮግራማችን ላይ የሃይማኖት ትምህርት የሚያቀርቡና ለጥያቄዎቻችን መልስ የሚሰጡልን አባቶችና መምህራን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና ጠንቅቀው የሚያውቁ የጉባኤ መምህራን ከመሆናቸውም በላይ አሁንም በቤተክርስቲያንዋ የአገልግሎት ዘርፍ በሃላፊነት ደረጃ ያሉ መሆናቸውን እንድትረዱት ያስፈልጋል። ስለሆነም ሁላችሁም አባላት የምታቀርቡት ሃሳብና ተሳትፎ ለእነሱ እንደሚቀርብ ተረድታችሁ ከአለማዊ አነጋገር ወጣ ብላችሁ ለአባቶቻችን የሚገባውን መንፈሳዊ አክብሮት በመስጠት መንፈሳዊ ስነምግባርን በተላበሰ አነጋገር እንድትሳተፉ አደራ እንላለን።
 
በተጨማሪም በሚሰጠው ትምህርትና ባጠቃላይ በድረገጹ ለይ ያላችሁን የግል አስተያየት በመስጠት አገልገሎቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንዲሄድ የበኩላችሁን ድጋፍና ተሳትፎ ማድረግ፣ እንዲሁም ከዚህ በታች ያሉትን ሊንኮች በቀላሉ ሼር በማድረግ  ሌሎች ወገኖችንም የዚህ ቴሌግራም አባል በመሆን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትጋብዟቸው ዘንድ በአጽንዎት እንመክራለን ።
 
የዮሐንስ ንስኀ ድረገጸ መንፈሳዊ ትምህርት አና ምክር እንዲሁም ለጥያቄዎ መልስ ለማግኘት :-
 
የቴሌትግራም ገፅችን፦https://t.me/joinchat/GA5ccrpz33ESz04q
 
የፌስቡክ ገፅችን፦ https://www.facebook.com/YohannesNeseha/
 
የኢሜል አድራሻችን፦ yohannes.neseha@gmail.com

የተወደዳችሁ የዮሐንስ ንስሐ ድረ-ገጽ አባላት፤ እንደሚታወቀው ያለ መቋረጥ ዘወትር ጠዋት እና ማታ በቀን ሁለት ጊዜ ትምሕርተ ሃይማኖት እና ከአባላት የሚቀርቡልንን ልዩ ልዩ ጥያቄዎች መሰረት በማድረግ በቴሌግራም አና በፌስቡክ ቻናላችን እያስተላለፍን እንገኛለን እናንተም በትምህርቱ ተጠቃሚ እንደሆናችሁ ከምትልኩልን መልእክቶች ተገንዝበናል።  አሁንም የእናንተን ጥያቄና አስተያየት ተቀብለን በቴሌግራም አና በፌስቡክ ከምናስተላልፈፈው በተጨማሪ የዩቱብ ቻናል  የድምፅ ስርጭት  ከፍተን አገልግሎት መጀመራችንን በደስታ እንገልፃለን!

አስረግጠን እውነቱን የምንነግራችሁ በዚህ አላማችን ውስጥ ከእውነተኛ ኦርቶዶክስ አስተምሮ አንፃር አባቶች የሚያስተላልፉልን ትምህርት እና ምክር የመናፍቅነት፣ የክህደት፣ የስነምግባር ችግሮች ቦታ እንዳይኖራቸው ሰይጣንን ከብዙ ህይወት ውስጥ ሳይወድ በግድ ታግለን በእግዚአብሔር ሃይል እና ጥበብ ለመለየት በዘመኑ የሰለጠነውን የኀጢአት እና የክፋት መንገድ አስቀርተን ፣ እንዲሁም ትክክለኛ ትምህርት ካለማግኘት በጥርጥር ፈተና ላይ የወደቁትን ወገኖች እያስተማርንና እየመከርን ሁላችሁም የዘላለም ህይወት እንድታገኙ እስካሁንም ብዙ ተጉዘናል ወደፊትም እግዚአብሔር ከኛ ጋር እስከሆነ ድረስ የሚያቆመን የለም።

በመሆኑም በሚሰጠው ትምህርትና ባጠቃላይ በድረገጹ ለይ ያላችሁን የግል አስተያየት በመስጠት አገልገሎቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እና እየተስፋፋ እንዲሄድ የበኩላችሁን ድጋፍና ተሳትፎ  በቴሌግራም ፣ በፌስቡክ፣ በዩቱብ ቻናላችን እንድታደርጉ ፣ በየቀኑ የምናስተላልፈውንም መንፈሳዊ ትምህርት እየተከታተላችሁ አንዱ አንዱን እያበረታው እና እያገዘው የምንሄድበትን አጭር መልዕክት በመለዋወጥ እንዲሁም ከዚህ በታች ያሉትን ሊንኮች በቀላሉ ለሌሎች ወገኖች ሼር በማድረግ ሁሉም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትጋብዟቸው ዘንድ በአጽንዎት እንጠይቃለን።
በአጠቃላይ ይህ ተወዳጅ የሆነውና ታላቅ መንፈሳዊ አላማ የያዘው ቻናላችን በእግዚአብሔር ቸርነት እየታገዘ እና እየተስፋፋ እንዲቀጥል የእናንተ የአባላት ዋና ድርሻ የሚሆነው እና በእግዚአብሔር ስም አደራ የምንላችሁ ይህን የቴሌግራም ግሩፕና የዩቱብ ቻናላችንን ለሌሎች ወገኖች ሼር በማድረግ እንድታስፋፉት ነው !!!

የ #ዩቱብ_ቻናላችን አድራሻ፦https://www.youtube.com/channel/UCBC-SV6VPcLppIZB7EC9JEg

የ #ድረገፃችን አድራሻ:- yohannesneseha.org

የ #ቴሌግራም ግሩፓችን አድራሻ:- https://t.me/joinchat/R55ClhgOXHIoRHg​…

የ #ፌስቡክ ገፅችን አድራሻ:- https://www.facebook.com/YohannesNeseha

የ #ኢሜል አድራሻችን:- yohannes.neseha@gmail.com

በውስጥ መስመር ወይም በግል ልታገኙን የፈለጋችሁ አባላቶቻችን በቴሌግራም፣ በፌስቡክ ወይም በኢሜል የግል መልእክት ልትልኩልን ትችላላችሁ።

በቴሌግራም የግል መልእክት ለመላክ “ዮን” የሚለውን የአካውንታችንን መለያን በመጫን ወይም የአባሎችን ዝርዝር ተጭነው <<ዮሐንስ ንስሐ >> “owner” የሚለውን በመጫን ሊፅፉልን ይችላሉ።

የዮሐንስ ንስኀ ድረገጽ መንፈሳዊ ትምህርት አና ምክር እንዲሁም ለጥያቄዎ መልስ ለማግኘት፣

ድረገፃችንን:- yohannesneseha.org

ወይም ቴሌግራም ግሩፓችንን:- https://t.me/joinchat/R55ClhgOXHIoRHg

ወይም የፌስቡክ ገፅችንን:- https://www.facebook.com/YohannesNeseha

የዩቱብ_ቻናላችን አድራሻ፦https://www.youtube.com/channel/UCBC-SV6VPcLppIZB7EC9JEg

ወይም ኢሜል አድራሻችንን:- yohannes.neseha@gmail.com

በመጠቀም ሊያገኙን እንደሚችሉ እንገልፃለን።

ጠያቂያችን፤ ተጨማሪ አድራሻ በውስጥ መስመር ለእርስዎ የላክንልዎ ስለሆነ በዚያም ሊያገኙን ይችላሉ።

ጠያቂያችን ለሰጡን ገንቢ ሃሳብ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን፤ በእኛም በኩል ትምህርቱን በተለያዩ ቋንቋዎች ለማዳረስ እቅዳችን ነው። ይህን ሙሉ ለሙሉ ማሳካት እስከምንችል ግን ለጊዜው አሁን እርስዎ በጠየቁን መሰረት መደበኛ ተከታታይ ትምህርቶችን እና የብዙ ሰው ጥያቄ ሊሆኑ ይችላሉ ብለን ያሰብናቸውን ጠቃሚ መልሶችና ምክር መርጠን በአንድ ላይ አድርገን ወደ ኦሮምኛ በማስተርጎም  በድረገጻችን ላይ ስለምናስቀምጥ በትእግስት ሆነው ይጠባበቁን። በሂደትም ይህን መንፈሳዊ አገልግሎት በአገር ውስጥ እና በአለም ዙሪያ በተለያዩ ቋንቋዎች ለማዳረስ አንዱ እቅዳችን መሆኑን ለአባላት ሁሉ በዚህ አጋጣሚ ለማስታወቅ እንወዳለን።

ለሁሉም እግዚአብሔር ይርዳን።