መሰረታዊ ትምህርት

"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!" (ማቴ 3: 1-2)

ተከታታይ ትምህርትና ለጥያቄዎት ምላሽ ለማግኘት ቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ

መሰረታዊ ትምህርት

ምስጢረ ሥላሴ

👉🏾👉🏾👉🏾ስለ #ሥላሴ የአንድነት አና ሦስትነት

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን በሙሉ፤ ዛሬ መጋቢት 7 ወርሃዊ የቅድስት ሥላሴን በዓል በማስመልከት በርዕሱ የተጠቀሰውን የትምህርት ክፍል ከ “ማስያስ” መጽሐፍ ወስጥ ያገኘነው ሲሆን ይህም ጠቃሚ ትምህርት ስለሆነ እንደሚከተለው ልከንላችኋልና አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።

እግዚአብሔር አንድም፤ ሦስትም ነው። አንድ ሲባል የቁጥር (የመቆጠር) አንድ ማለት አይደለም፤ የባሕርይ አንድነትን ለማመልከት ነው እንጂ። ሦስት ሲባልም ከቁጥር በላይ የሆነ ልዩ ሦስትነትን (ሥሉስ ቅዱስ መሆንን) የሚያመለክት ነው።

ይኸውም ማንም ቢሆን እግዚአብሔርን በቁጥር ሕግ (በመቁጠር) አላወቀውም፤ አያውቀውም ማለታችን ነው። የሥላሴን የባሕርይ አንድነት እና የአካል ሦስትነት ፍጡር ይረዳ ዘንድ እግዚአብሔር እንዲገልጥለት የግድ ነው። ለዚህም ነው የመገለጦች ሁሉ መገለጥ የሆነው፡ የአምላክ ሰው መሆን (ሥጋዌ)፤ የሥላሴን ምሥጢር ወደ ልቡናችን ያመጣልን። በወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስ በሥጋ መገለጥ፤ እውነተኛ ዘለዓለማዊ አባትነት እና ልጅነት ታውቋል። ክርስቶስ የእግዚአብሔር አብ ዘለዓለማዊ ልጁ እንደሆነ፥ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ ለዓለም ታወቀ። ከጥምቀቱ በኋላም ጌታችን ባስተማራቸው ትምህርቶቹ የእርሱን ልጅነት የእግዚአብሔር አብን አባትነት፤ የባሕርይ ሕይወታቸው መንፈስ ቅዱስም ከእነርሱ ጋር ያለውን መተካከል ገልጧል። በክርስቶስ ያለ ይህ ባሕርያዊ ዕውቀት አካሉ ለሆነች ለቤተ ክርስቲያን ተገልጦላት አውቃዋለች። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ስለ እግዚአብሔር አብ ነገረን። ቤተ ክርስቲያ በቅዳሴ ጸሎቷ እግዚአብሔር አብን ስታናግረው “የወለድኸው ልጀህ የአንተን ነገር ነገረን። ይህ እርሱ ከአንተ የተወለደው፡ ልጅህ ዜናህን ለእኛ ነገረን። አንተ እንደወለድኸው፤ ለዘለዓለሙ ክቡር ነው። አንተም ራስህ የእርሱን ነገር ነገርኸን፣ በእውነት ልጅህ እንደሆነ፡ አንተም በእውነት አባቱ እንደሆንህ በቃልህ ምስክሩ አንተ ነህ” ትላለች። ስለ አብ አባትነት ወልድ ነገረን፤ ሰለ ወልድም እውነተኛ ልጅነት አብ በቃሉ ምስክር ሆነ። ይኸውም በዮርዳኖስ እና በደብረ ታቦር የሆነው ነው። በዮርዳኖስ እና በደብረ ታቦር ምሥጢረ ሥሳሴ ለሰዎች ታወቀ። የሚያነጻ፣ የሚያከብር ሕይወት የሆነ መንፈስ ቅዱስም አብ እና የወልድ ሕይወታቸው ሆኖ፡ በእነርሱ ውስጥ በህልውና ተገናዝቦ የሚኖር አምላክ መሆኑን በክርስቶስ ተረዳን። በተጠመቀ ጊዜ በርግብ አምሳል ወርዶ ታይቷልና። (ማቴ 3፡17) ክርስቶስ እውነተኛ አምልኮት የሚገለጥባትን የጥምቀትን ሥርዓት ሲሠራ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንድትጠመቅ በማዘዝ የመንፈስ ቅዱስን መተካከል አስተምሮናል። (ማቴ 28፡19)

የተወደደ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን በመጀመሪያ ቃል ነበር በማለት በአካላዊ ቃል ዘለዓለማዊ ህላዌ ጀመረ። ቃል በአካላዊነቱ ብቻውን የሚኖር ሳይሆን ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንድነት፡ በሦስትነት የሚኖር መሆኑን የወንጌሉ ሁለተኛ እና አራተኛ ዐረፍ ነገሮች
ይገልጻሉ። በመጀመሪያ ቃል ነበር (ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ) የሚለው አነጋገር ግን የቃል ስሙ ቀዳማዊ ተብሎ መጠራት መሆኑን የሚያመለክት ነው። ከዚህ አንጻር የቤተ ክርስቲያን አበው ብሉይ ኪዳንን፡ በሐዲስ ኪዳን መነጽርነት ተመልክተው ተርጉመውታል። በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ የሚለው የኦሪትዘልደት አነጋገር እግዚአብሔር (አብ) በቀዳማዊ ቃሉ (ማለትም በወልድ) ሰማይና ምድርን እንደፈጠረ ተርጉመዋል። አስቀድመን እንደተናገርን ወልድ በሥጋ ሲገለጥ ስለ አባቱ ነገረን፤ ብሉይ ኪዳንንም በሐዲስ ኪዳን አስተርጓሚነት ተረዳናት። ስለሆነም የኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ
በመጀመሪያ ብላ ወልድን፤ እግዚአብሔር ብላ አብን እንዲሁም የእግዚአብሔር መንፈስ ብላ መንፈስ ቅዱስን አስታወቀችን። የዮሐንስ ወንጌል የአንድነት እና የሦስትነትን ምሥጢር በማስተማር እንደጀመረች፤ ኦሪት ዘፍጥረትም በሥላሴ ምሥጢር ነገሯን እንደጀመረች ተረዳን።

ክብር ይግባውና መድኅን ክርስቶስ ስለራሱ ማንነት ደቀ መዛሙርቱን ሲጠይቅ ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ፤ ክርስቶስ ነህ አለው። (ማቴ 16፡16) ጌታም የዚህ ምስክርነት እና ዕውቀት መነሻ የባሕርይ አባቱ አብ መሆኑን ተናገሮ፣ በፈቃዱ የመሰከረለትን ጴጥሮስን ብፁዕ ብሎ አመሰገነው። በእርሱ (በእርሱ ምስክርነት) ላይ ቤተ ክርስቲያን የምትመሠረት መሆኗን እና ክፉዎች እንደማያሸንፏት ጌታችን ተናገረ። ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ምስክርነት እንመለስ። ሐዋርያው እንዲያ ብሎ ሲመሰክር፣ ስለምን ተናገረ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ። አንተ አለው፤ ከሁለት ባሕርያት በተዋሕዶ አንድ ባሕርይ የሆነው ክርስቶስን አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ አለ። አብ እና ወልድ ሕያው የሚሆኑበት ሕይወታቸው መንፈስ ቅዱስ ነውና፤ አንተ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ሕያው የሆነ የእግዚአብሔር አብ፣ የባሕርይ ልጁ ነህ ማለቱ ነው። በዚህ ምሰክርነቱ ቅዱስ ጴጥሮስ ምሥጢረ ሥላሴን ተናገረ። በዚህም ሳያበቃ፤ ክርስቶስ ነህ ብሎ ተናገረ። በሥጋ የተገለጥኸ፣ በነቢያት ትንቢት የተጠባበቅኸ፡: አንተ እውነተኛው መሲሕ ነህ ሲል ነው። ስለሆነም ቅዱስ ጴጥሮስ በአንድ ምስክርነት፣ የሥላሴ እና የሥጋዌን ምሥጢር በአምላካዊ መገለጥ ተናገረ። እግዚአብሔር አንድነት ሦስትነቱን የገለጠው ዓለምን ሲፈጥረው እና ከጥፋት ሲያድነው ነው። እንዲህ ሰንል በቅዱሳት መጻሕፍት የተገለጠውን የፈጣሪ እና የፍጥረት ግንኙነት ሁሉ ማለታችን ነው። በብሉይ ኪዳን የተነገሩት እና የተገለጡት ሁሉ እግዚአብሔር ዓለምን የማዳኑ ሂደት መሆናቸውንም ማስተዋል ይገባል። በዘለዓለማዊው አኗኗሩ አንድም ሦስትም መሆኑን በወንጌለ ዮሐንስ መጀመሪያ አይተናል። ይህን ዓለም ሲያድንም እንዲሁ አንድም ሦስትም መሆኑ በወንጌል (በክርስቶስ ትምህርት) ተገልጧል። ከዚህም በላይ አስቀድሞ ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው የፈጠሩ ሥላሴ፤ ዓለም በበደል ምክንያት ውድቀት ቢያገኘው በአንዲት ሥልጣናቸው ዓለምን አድነዋል።

ይቆየን

ምንጭ ፦ ከ ማስያስ መጽሐፍ ገጽ 53-56
ዲያቆን ሚክያስ አስረስ

ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ

👉🏾👉🏾👉🏾ስለ #ቅድስት #ሥላሴ

“ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው” (ዘፍ11፥7)

የተከበራችሁ እና የተወደዳችሁ የዮሐንስ ንስኀ ድረገፅ መንፈሳዊ ፕሮግራም አባላት በሙሉ፥ የፍጥረታት ሁሉ ባለቤት አጋዕዝተ አለም ቅድስት ሥላሴ እንኳንስ ለጥር 7 ቀን ለሚከበረው አመታዊ የሥላሴ ክብረ በዓል አደረሳችሁ። በዚህ እለት ስለሚከበረው የቅድስት ሥላሴ አመታዊ በዓል አጭር ትምሀርት ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን፦

በመሰረቱ ስለ ቅድስት ሥላሴ መናገር ወይም ማስተማር በፍጡር አንደበት የማይደፈርና  ከአይምሮ በላይ የሆነ ምስጢር ስለሆነ እፁብ ድንቅ ብለን በአንክሮና በተዘክሮ የምናምን የምንመሰክረው ቢሆንም እንኳን እግዚአብሔር አይምሯችንን እና አይነ ህሊናችንን ከፍቶ የገለፀልንን ያህል እንመሰክራለን። በዚህ ጥር 7 ቀን የሚከበረው ስለአጋዕዝተ አለም ቅድስት ሥላሴ ከመናገራችን በፊት ማንኛውም ሃይማኖት ያለው ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ከሁሉ አስቀድሞ መመስከር ያለበት ስለ ምስጢረ ሥላሴ መሆን ስላለበት ከዚህ በፊት ሐምሌ 7 ቀን የሚከበረውን የቅድስት ሥላሴ በዓል ምክንያት በማድረግ ስለ ሥላሴ አንድነት እና ሦስትነት የሚያስተላልፈውን የምስጢረ ሥላሴ ትምህርት እያስታወስን ዛሬም ቢሆን ከምስጢረ ሥላሴ ትምህርት በላይ የምናስቀድመው እና የሚበልጥብን ምንም አይነት የሃይማኖት ምስጢር ባለመኖሩ ወደ እለቱ የበአሉ ታሪክ እና ሃተታ ከመግባታችን በፊት በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን ስለሚስጥረ ሥላሴ መፅሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚናገር እንመለከታለን።

1ኛ/ በብሉይ ከዳን ስለ ምስጢረ ሥላሴ የተነገረውን ኀይለቃል በማስመልከት፦

1. “እግዚአብሔርም  አለ፥  ሰውን  በመልካችን  እንደ  ምሳሌአችን  እንፍጠር” በማለት ‘እግዚአብሔር አለ’ የሚለው ቃል የአንድነትን ምስጢር የሚያመለክት ሲሆን  ‘ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር’ የሚለው ቃል ደግሞ ከአንድ በላይ የሚያመለክት ሲሆን የሦስትነትን ምስጢር ያስረዳል። (ኦሪ ዘፍ 1፥6)

2.  “እግዚአብሔር አምላክም አለ ፥ እነሆ አዳም መልካምንና ክፉውን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ” የሚለውን ቃል ስንመለከት ‘እግዚአብሔር አምላክ አለ’ የሚለው አንድነትን፣ ‘አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ’ የሚለው ደግሞ የ ሦስትነትን ምስጢር የሚገልፅ ሆኖ ከሦስቱ አካላት አንዱ እግዚአብሔር ወልድ ከአዳም ዘር መወለዱን እና ሥጋ መዋሃዱን የሚያመለክት ምስጢር ነው።

3.  እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም ረዳቱ የምትሆነውን ሄዋንን ለመፍጠር መለኮታዊ ፈቃዱ በሆነ ጊዜ “እግዚአብሔር አምላክ አለ፤ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረዳት  እንፍጠርለት” በሚለው ኀይለቃል የእግዚአብሔርን የአንድነት እና የሦስትነት ምስጢር መረዳት እንችላለን።

4.  በትምህርታችን መነሻ ርዐስ አድርገን የመረጥነው ኀይለቃልም “ኑ፥  እንውረድ፤  አንዱ የአንዱን  ነገር  እንዳይሰማው  ቋንቋቸውን  በዚያ  እንደባልቀው” ‘ኑ፥ እንውረድ’ የሚለው ቃል የሥላሴን ሦስትነት የሚያመለክት ቃል ነው። (ዘፍ11፥7)

5. አባታችን አብርሀም በመምሪ አድባር ዛፍ በተገለፁለት ጊዜ ፤ ሦስት በእድሜ ሽማግሌ የሆኑ የተከበሩ ሰዎችን ባገኘ ጊዜ እንግዳ በመቀበል በረከት ለማግኘት ከነበረው ጉጉት አንፃር ወደ ቤቱ ይገቡለት ዘንድ የክብር ሰላምታ ካቀረበላቸው በኋላ ጌቶች ሆይ ወደቤቴ ግቡ በማለት  ያቀረበውን የክብር መስተንግዶ ተቀብለው ከእሱ ጋር ማዕድ እንደቆረሱ ቅዱስ መፅሐፍ ይነግረናል። አባታችን አብርሐም ከመምሬ ዛፍ እግዚአብሔር እንደተገለፀለት የሚገልፅ ሲሆን በመቀበሉም እግዚአብሔር አንድም ሦስትም እንደሆነ የሥላሤን አንድነት እና ሦስትነት እንዲያውቅ ስለተፈቀደለት ሦስቱም ሥላሴ በቤቱ እንደተገኙለት ቅዱስ መፅሐፍ ያስረዳል። (ኦሪ ዘፍ 18፥1-8)

6. እንዲሁም ነብየ እግዚአብሔር ኢሳያስ ሦስትነትን ሲገልፅ “አንዱም ለአንዱ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ ፥ቅዱስ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮህ ነበረ” የሚለው ኀይለቃል የሚያመለክተው የስላሴን አንድነት እና ሦስትነት ነው። (ኢሳ 6፥3)

2ኛ/ በአዲስ ኪዳን የሥላሴ ሦስትነት በብዙ ቦታ ተገልፆ እንመለከታለን

1. “ሂዱና አህዛብን ሁሉ በአብ በወለድ እና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ያዘዝኳችሁን ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” የሚለው ቃል አንድነትን ሦስትነትን የሚገልፅ ኀይለ ቃል ነው። (ማቴ 28፥19)

2 “እኔ እና አብ አንድ ነን እኔን ያየ አብን አይቷል፥ እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን” ‘እኔ በአብ እንዳለሁ’ የሚለው ቃል የአብን የወልድን የመንፈስ ቅዱስን ሦስትነት እና አንድነት የሚያመለክት ነው። (ዮሐ14፥9:10)

በአጠቃላይ በብሉይና በአዲስ ኪዳን ስለሚስጥረ ሥላሴ በብዙ ሁኔታ ተገልፆ የምናገኘው ኀይለቃል እጅግ ረቂቅ እና ጥልቅ ከመሆኑ የተነሳ ለብዙዎች የማይረዳ ምስጢር ቢሆንም እንኳን እውነተኛ ለሆኑ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በልዩ መለኮታዊ ጥበብ በተሰጠን የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ የምንረዳው ነው። ጠቅለል ባለ አገላለፅ የሥላሴ ሦስትነታቸው በምን እና በምን ተብሎ ቢጠየቅ፦ ሦስትነታቸው በስም፣ በግብር፣ በአካል ሲሆን አንድነታቸው ደግሞ በባህሪይ፣ በህልውና፣ በመለኮት፣ በስልጣን፣ በፈቃድ፣ ይህንን አለምና የማይታየውን አለም በመፍጠር እና በማሳለፍ ነው፦

የሥላሴን  የአንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን የማያምን ክርስቲያን  የኀጢአት ስርየትን እና ተስፋ መንግስተ ሰማያን ፈፅሞ ሊያገኝ አይችልም። ሥላሴ የሚታየውን እና የማይታየውን ሁሉ ፍጥረት ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው የፈጠሩ ህማም ድካም የማይሰማቸው፣ በሞት የማይለወጡ፣ ዘለዐለማዊ ሀልዎት ያላቸው፣ ገዢ ፈጣሪ ናቸው። ሥላሴ አለም ሳይፈጠር አስቀድሞ ባህሪያቸው ባህሪያቸውን ሲያመሰግን የነበረ፣ ያለ፣ የሚኖር ሲሆን ሆኖም  ክብራቸው በባህሪያቸው እንዳይቀር አውቀው ሰውና መላዕክትን ስማቸውን ለመወደስ ክብራቸውን ለመውረስ እንደፈጠሩ በቅዱሳን መፃህፍት ያስረዳናል። ሌላውን ስነፍጥረት ግን ለአንክሮ፣ ለተዘክሮ፣ ለምግበ ስጋ ፣ለምግበ ነፍስ ፣እንዲደፈጠሩ እንረዳለን። የሰውን ልጅ በምድር ላይ ለተፈጠሩ ፍጥረታት ሁሉ በኩርና ገዢ አድርገው ሹመውታል። (መዝ8፥6)

የመጀመሪያው ሰው አዳም እና ሄዋን በገነት 7 አመት ከ 1 ወር ከ17 ቀን ኑረው እፀበለስን ቀጥፈው በመብላታቸው ምክንያት ከርስታቸው ከገነት ተባረው በምድረ ኤልዳ ተቀምጠዋል። (ኩፋ5፥6)

በዚያም በስደት ባረፉበት ቦታ በዝተው ወልደው ተዋልደው ምድርን እንዲሞሏት በሥላሴ ዘንድም ተፈቅዶላቸዋል።

የአዳም 10ኛ ትውልድ የሆነው ፃድቁ አባታችን ኖህ በዘመኑ የሰው ልጆች ምድርን በኀጢአት ስላረከሷት አጋዕዝተ ሥላሴ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ እና ንጉስ ሥላሴ፥ ኖህን እና ቤተሰቦቹን ከጥፋት ውሀ አስቀርተው ሌላው የሰው ልጅ እና ፍጥረታት ሁሉ በንፍር ውሀ ጠፍተዋል። (ዘፍ8፥15)

(ይቀጥላል)👇👇👇

ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ

👉🏾👉🏾👉🏾ስለ #ሥላሴ #አንድነት እና #ሦስትነት የሚገልጹ ትምህርቶች በብሉይ ኪዳን እና በአዲስ ኪዳን

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገፅ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምትከታተሉ አባላቶቻችን ሁሉ፤ ዛሬ መጋቢት 7 ቀን የሚከበረውን የቅድስት ሥላሴ ወርሃዊ በአል በማስመልከት ስለ ምስጢረ ሥላሴ የሚከተለውን መሰረታዊ ትምህርት ልከንላችኋልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።

ሦላሴ የሚለው ቃል “ሠለሰ” ሦስት አደረገ ከሚለው የግእዝ ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሦስት መሆን ሦስትነት ማለት ሁኖ በምስጢራዊ አገላለጹም አንድም ሶስትም (አንድነት ከሶስትነት) ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

የሦላሴ አንድነታቸው ፦ በባሕርይ፣ በህልውና፣ በመለኮት፣ በስልጣን፣ በአገዛዝ፣ በፈቃድ፣ ሁሉንም ስነፍጥረት በየወገኑ በመፍጠር ነው።

የሦላሴ ሶስትነታቸው፦ በስም፣ በግብር፣ በአካል ነው።

የስም ሶስትነት ማለት፡- አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ማቴ 28:19

የአካል ሶስትነት ማለት፡- ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ፤ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ፤ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ አላቸው (ጥቅስ መዝ 33:14፣ 118:73፣ ኢሳ66:1 ፣ ዘፍ18:1-4 ማቴ 3:16)

የግብር ሦስትነት፦ አብ ወላዲ አስራጺ ነው። ወልድ ተወላዲ ነው፤ መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ ነው፤

አብን ወላዲ፣ ወልድን ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስን ሠራጺ ስንል ስለግብር ሶስትነታቸው ነው እንጂ እነሱማ አንዱ ከአንዱ የማይበልጥ፣ አንዱ ከአንዱ የማያንስ ዕለ እሩያን ናቸው።(ዩሓ 10:30) ቅድስት ስላሴ ስንል ቅድስት የሚለው ቅጽል ለሴት የሚሰጥ ቅጽል ቢሆንም ስላሴ በባሕርያቸው እንደ እናት ባሕርይ ስለሚመስሉ ነው። ልጅ ከእናቱ ባሕርይ እንደሚገኝ ይህ ዓለም ከስላሴ ባሕርይ ተገኝቷልና ነው። እናት ለልጇ የሚያስፈልገውን አስባ ተጨንቃ እንደምታቀርብለት ሁሉ፤ ስላሴም ለፈጠሩት ፍጥረት ሁሉ ከወዳድ እናት በላይ ስለሚያስቡ የሚያስፈልገውን ሁሉ አስቀድመው አዘጋጅተዋል (ማቴ 6:14)

በ40 በ80 ቀኑ የስላሴን ልጅነት አግኝቶ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሁሉ አስቀድሞ የስላሴን አንድነት ሦስትነት ወይም ስለምስጢረ ስላሴ መማርና ማወቅ መንፈሳዊ ግዴታው ነው። ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ማን ፈጠረህ ተብሎ ቢጠየቅ መልስ እንዳያጣና መናፍቃንና ኢአማንያን በዘረጉት የክህደት ጉድጓድ ውስጥ እንዳይወድቅ ሊጠነቀቅ ይገባዋል።

የእግዚአብሔር ባሕርይ ረቂቅ ፥ አኗኗሩም ምጡቅ በመሆኑ እንደ ሌላው ትምህርት በቀላሉ ሊያውቀው የሚችለውንና የሚገባውን ያህል እግዚአብሔር ለአባቶቻችን በቃልም በራእይም በመገለጥም በልዩ ልዩ መንገድ አንድነቱንና ሦስትነቱን አሳውቋቸዋል አስተምሯቸዋልም። ይህም በቅዱሳት መጻሕፍት ተጽፎ ስላለ እና የታወቀውን ምሥጢርና የተገኘውን ትምህርት አክብረን በእምነት መቀበል እንጂ በምርምርና ፍልስፍና የሚረዱት ትምህርት አይደለም። በመለኮታዊ መገለጥ የተገኘውን በእምነት ከመቀበል አልፈን ተርፈን በአእምሮ ችሎታችንና በምርምር ሃይላችን በልቡና መስፈርት ሰፍረንና በኅሊና ሚዛን መዝነን ምሥጢረ ሥላሴን እናውቃለን ማለት ዘበት ነው። ይህን ማድረግ የውቅያኖስን ውሀ በጭልፋ ቀድተን እንጨርሳለን እንደ ማለት ይሆናል።

ስለ ሥላሴ አንድነት እና ሦስትነት

1ኛ/ በብሉይ ከዳን ስለ ምስጢረ ሥላሴ የተነገረውን ኀይለቃል በማስመልከት፦

1. “እግዚአብሔርም  አለ፥  ሰውን  በመልካችን  እንደ  ምሳሌአችን  እንፍጠር” በማለት ‘እግዚአብሔር አለ’ የሚለው ቃል የአንድነትን ምስጢር የሚያመለክት ሲሆን  ‘ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር’ የሚለው ቃል ደግሞ ከአንድ በላይ የሚያመለክት ሲሆን የሦስትነትን ምስጢር ያስረዳል። (ኦሪ ዘፍ 1፥6)

2.  “እግዚአብሔር አምላክም አለ ፥ እነሆ አዳም መልካምንና ክፉውን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ” የሚለውን ቃል ስንመለከት ‘እግዚአብሔር አምላክ አለ’ የሚለው አንድነትን፣ ‘አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ’ የሚለው ደግሞ የ ሦስትነትን ምስጢር የሚገልፅ ሆኖ ከሦስቱ አካላት አንዱ እግዚአብሔር ወልድ ከአዳም ዘር መወለዱን እና ሥጋ መዋሃዱን የሚያመለክት ምስጢር ነው።

3.  እግዚአብሔር አምላክ ለአዳም ረዳቱ የምትሆነውን ሄዋንን ለመፍጠር መለኮታዊ ፈቃዱ በሆነ ጊዜ “እግዚአብሔር አምላክ አለ፤ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም የሚመቸውን ረዳት  እንፍጠርለት” በሚለው ኀይለቃል የእግዚአብሔርን የአንድነት እና የሦስትነት ምስጢር መረዳት እንችላለን።

4.  እግዚአብሔር አለ “ኑ፥  እንውረድ፤  አንዱ የአንዱን  ነገር  እንዳይሰማው  ቋንቋቸውን  በዚያ  እንደባልቀው” ‘ኑ፥ እንውረድ’ የሚለው ቃል የሥላሴን ሦስትነት የሚያመለክት ቃል ነው። (ዘፍ11፥7)

5. አባታችን አብርሀም በመምሪ አድባር ዛፍ በተገለፁለት ጊዜ ፤ ሦስት በእድሜ ሽማግሌ የሆኑ የተከበሩ ሰዎችን ባገኘ ጊዜ እንግዳ በመቀበል በረከት ለማግኘት ከነበረው ጉጉት አንፃር ወደ ቤቱ ይገቡለት ዘንድ የክብር ሰላምታ ካቀረበላቸው በኋላ ጌቶች ሆይ ወደቤቴ ግቡ በማለት  ያቀረበውን የክብር መስተንግዶ ተቀብለው ከእሱ ጋር ማዕድ እንደቆረሱ ቅዱስ መፅሐፍ ይነግረናል። አባታችን አብርሐም ከመምሬ ዛፍ እግዚአብሔር እንደተገለፀለት የሚገልፅ ሲሆን በመቀበሉም እግዚአብሔር አንድም ሦስትም እንደሆነ የሥላሤን አንድነት እና ሦስትነት እንዲያውቅ ስለተፈቀደለት ሦስቱም ሥላሴ በቤቱ እንደተገኙለት ቅዱስ መፅሐፍ ያስረዳል። (ኦሪ ዘፍ 18፥1-8)

6. ነብየ እግዚአብሔር ኢሳያስ ሦስትነትን ሲገልፅ “አንዱም ለአንዱ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ ፥ቅዱስ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮህ ነበረ” የሚለው ኀይለቃል የሚያመለክተው የስላሴን አንድነት እና ሦስትነት ነው። (ኢሳ 6፥3)

(ይቀጥላል) 👇

ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ

ነገረ ስጋዌ

👉ጥያቄ፡- እንዴት ናችሁ ቤተሰቦቼ? ጥያቄ ነበረኝ አባታችን፣ እሱም እኛ ኦርቶዶክሳውያን ሥጋና መለኮትን ስናምን ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕሪ አንድ ባሕሪ ብለን ነው? ወይስ ሁለት አካል አንድ ባሕሪ ብለን ነው?

👉🏾 ስለ ነገረ #ስጋዌ

✍መልስ፡- ሐሳቡ ጥሩ ነው፣ መልካም ጥያቄ ነው መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ነው፣ ያልተረዳ ሰው መጠየቅ አለበት ማለት ነው፣ የእኛ የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ተዋሕዶ ስንል ምን ማለታችን ነው? የሚለውን ለማየት ጥያቄው ላይ እንደተባለው ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕሪ አንድ ባሕሪ ብለን ነው እንደ ኢትዮጶያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምናስተምረው፣ የምናምነው፣ ሁለት አካል ማለት መለኮትና ሥጋ፣ መለኮት ማለት ወልድ ነው፣ ወይም ቃል እንለዋለን፣ መለኮት አንድ አካል ነው፣ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ እርሱ ፍፁም መልክ፣ ፍፁም ገፅ፣ ፍፁም አካል ያለው፣ ረቂቅ ያለው አካል ያለው ስለሆነ አንድ አካል ይባላል፣ ሌላኛው አካል ደግሞ የሥጋ አካል ነው፣ ስለዚህ አሁን ተዋሕዶ ስንል፣ ከሁለት አካል አንድ አካል የሚለውን እንዳንዘነጋ ያስፈልጋል፡፡

አንድ አካል የምንለው አካላዊ ቃል ወይም እግዚአብሔ ወልድ ነው፣ እሱ አካሉ ረቂቅ የሆነ አካል አለው፣ ለአብ ፍፁም አካል፣ ፍፁም መልክ አለው፣ ለወልድም እንደዚሁ፣ ለመንፈስ ቅዱስም እንዲሁ ብለን በሚስጥረ ሥላሴ እንደምንማረው አካል የምንለው እሱን ነው፣ የእግዚአብሔር ወልድ አካል ነው፣ ባሕሪው ደግሞ እግዚአብሔር ከሁለት አካል አንድ ብሕሪ፣ ከአንድ ባሕሪ ሁለት አካል ማለት የእግዚአብሔር ባሕሪው የማራብ፣ የማይጠማ፣የማይደክም፣ የማያንቀላፋ ይሄ አንድ ባሕሪ ነው፣ ወደ ሥጋ ስንመጣ ደግሞ የሥጋ አካሉ ግዙፍ ነው፣ የሚታይ የሚጨበጥ፣ የሚዳሰስ ነው፡፡

ሥጋ ደግሞ በባሕሪው የሚራብ፣ የሚጠማ፣ የሚደክም ነው፣ ስለዚህ ተዋሕዶ ስንል ከሁለት አካል አንድ አካል ማለት ቅዱስ ቄርሎስ የቃል ገንዘብ ለሥጋ፣ የሥጋ ገንዘብ ለቃል ሆነ እንዳልነው፣ ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕሪ አንድ ባሕሪ ማለት ይሔ ነው፣ በተዋሕዶ ጊዜ የማይለወጠው አምላክ የሚለወጥ ሥጋ የነበረን የማይለወጥ አምላክ አደረገው፣ ረቂቅ የነበረው አምላክ ግዙፍ ሥጋን ገንዘብ አደረገ፡፡

ስለዚህ ምሉዑ ተወሰነ ውስሉ ሞላ፣ ምሉዕ እግዚአብሔር ወልድ ነው፣ አካሉ ምሉዕ ነው፣ ያ ምሉዕ አካል ውስን በሆነው በሥጋ ተወሰነ፣ ውስኑ ሥጋ ደግሞ በምሉዕ መለኮት ምሉዕ ሆነ፣ ግዙፉ ረቀቀ፣ ረቂቁ ገዘፈ፣ ምሉዑ ተወሰነ፣ ውስኑ መላ፣ አምላክ ሰው ሆነ፣ ሰው አምላክ ሰው ሆነ ብለን እናምናለን፣ ስለዚህ ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕሪ አንድ ባሕሪ ማለት ይሄ ነው፡፡

ከዚህ በኋላ ፍፁም መለያየት የለም፣ በዚህ መካከል አምላክና ሰው፣ ወይም መለኮትና ሥጋ ከተዋሐደ በኋላ ይሄ የዚህን ስራ ይሠራል፣ ይሔ የዚህን ሥራ ይሠራል አይባልም፣ ከዚያም በኋለ የወጣለት ስም ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አማኑኤል የሚለው ነው፣ ይህ ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕሪ አንድ ባሕሪ ቢሆን የወጣለት ስም ነው ይላል መጽሐፍ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ይሔ ነው ብለን ነው የምናምነው፣ ከተዋሕዶ በኋላ ለቅፅበት የሚያክል እንኳን መለያየት የለም፣ ሰው እንደመሆኑ ተራበ እንለዋለን፣ አምላክ እንደመሆኑ ደግሞ የተራቡትን አጠገበ፣ በአምስት እንጀራ፣ በሁለት አሣ አበርክቶ አምስት ሺህ ሰዎችን አጥግቦ አሥር ሁለት ቅርጫት ተርፎ ተነሣ፣

ሰው እንደመሆኑ በቃና ዘገሊላ ሠርግ ቤት ተጠርቶ ሄደ፣ አምላክ እንደመሆኑ ውኃውን ሙሉ ብሎ ወደ ወይን ለወጠው፣ ሰው እንደመሆኑ በመቃብር ተቀበረ፣ አምላክ እንደመሆኑ መቃብር ክፈቱልኝ፣ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ከሞት ተነሣ፣ እንዲህ ብላ ነው ቤተክርስቲያን የምታምነው፣ ሰው እንደመሆኑ በመርከቡ መካከል ተኛ፣ አንኮራፋ፣ እንቅልፍ ያዘው፣ አምላክ እንደመሆኑ ተነስቶ መርከቡን ሊጥል ሲያናውጥ የነበረውን ማዕበል ፀጥ አደረገው፣ ስለዚህ ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕሪ አንድ ባሕሪ ብለን ነው እኛ የምናምነው፣ “ሁለት አካል አንድ ባሕሪ” ብለው የሚያምኑ የካቶሊክ እምነት ነው፣ ሥጋና መለኮት እንደተዋሐደ ያምናሉ፣ ተዋሕዶን ያምናሉ ግን ባሕሪውን ግን ይለያሉ፣ መለኮት የራሱን ሥራ ይሠራል፣ ሥጋም የራሱን ሥራ ይሠራል ብለው ያምናሉ፡፡

ለምሳሌ በእነሱ ወይም በካቶሊክ አስተምህሮ ቃል የራሱን ሥራ ይሠራል፣ ሥጋ የራሱን ሥራ ይሠራል ብለው ከተዋህዶ በኋላ ለያያተው ነው የሚናገሩት፣ እንዲህ ዓይነት አስተምህሮ በቤተክርስቲያን በፍፁም የለም፣ ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕሪ አንድ ባሕሪ ብለን፣ ከተዋሕዶ በኋላ ለቅፅበት እንኳን መለያየት የለም፣ ስለዚህ ጠያቂያችን የተነሳው ሐሳብና ጥያቄው በጣም ሰፊ ስለሆነ፣ የበለጠ ግልፅ ካለሆነልዎት፣ ግልፅ እንዲሆን መልሰው መጠየቅ ይችላሉ።

በጥቅሉ ግን ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕሪ አንድ ባሕሪ ብለን ነው እኛ የምናምነው፣ ሁለት አካል አንድ ባሕሪ የሚሉት የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ናቸው፣ እግዚአብሔር አምላካችን ኃይማኖታችንን እንድናውቅ ረድቶን፣ በኃይማኖታችን እስከ መጨረሻው ፀንተን የማታልፈውን መንግሥተ ሰማያት እንድንወርስ ቸሩ መድኃኔዓለም ይርዳን፡፡

ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር አድርጉ፡- https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q

👉ጥያቄ፦ በገዳመ ቆሮንቶስ ስለፆመ ለመለኮት ፍቅር እንሰግዳለን፣ በገዳመ ቆሮንቶስ ለተራበ ለተጠማ በክርስቶስ ፍቅር እንሰግዳለን የሚለው ላይ ምልክት የመራብና የመጠማት ባሕሪ አለበት፣ መለኮት ማለት ነው፤ ክርስቶስ ኢየሱስ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይጋባውና የተራበው፣ የተጠማው፣ በለበሰው ደካማ ሥጋ መሆኑን ኦርቶዶክስ ታምናለች ታስተምራለች፣ ታዲያ ከላይ በምስጋና መልክ የቀረበው ምን ማለት ነው?

👉🏾 ስለ #ነገረ #ስጋዌ፣ #ነገረ #ተዋህዶ

✍መልስ፦ መጻሕፍት ብዙ ያመሰጠሩት ነገር፣ ብዙ የተራቀቁበት ነገር፣ ብዙ የፈለጉትና የደረሱበት ነገር፣ አለና አንዳንድ ጊዜ በገፀ ንባባ ብቻ እኛ እንዳንሰናከል፣ ሳይገባን እንዳይቀር መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡

“ንባብ ይቀትል ወትርጓሜ ያኽዩ” ገጸ ንባበ አንዳንድ ጊዜ አለመግባት ይሆናል፣ አለመረዳትን ያመጣል፣ ማለትም በገጸ ንባብ ከሔድን፣ የሥጋን ባሕሪንና የመለኮትን ባሕሪ፣ የሥጋን አካልና የመለኮትን አካል ለይቶ ያለማወቅ፣ ያለመረዳት ክርስቶስ በሥጋ ማርያም በተገለጠ ጊዜ ማለታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ፣ ሥጋዋን ተዋሕዶ በአጭር ቁመት፣ በጠባብ ደረት በዚህ ምድር ላይ በተገለጠ ጊዜ በዓይናችን የምናየው አካለ ሥጋ ነው፡፡

ዓይተን የምናረጋግጠው በእኛ ዘንድ ባለን ውሱን እውቀትና መረዳት፣ ባሕርየ ሥጋና አካለ ሥጋን ነው፤ ግን በኃይኖማት ደግሞ በመመራመር፣ ደግሞ በመማር በማወቅ መንፈሳዊ በመሆን ደግሞ በተሰጠን ጸጋ የምናውቀው ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከዚያ ከምናየው አካል የሚታየው አካል የማይታየውን የመለኮትን አካል ነው፡፡ ይህ ምን ማለት ነው? የሚታየው የሥጋ አካል የማይታየውን የመለኮትን አካል ተዋሕዷል፣ የሚታየው የሥጋ ባሕሪ የማይታየውን የመለኮትን ባሕሪ ተዋሕዷል፣ ስለዚህ ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕሪ አንድ ባሕሪ ሆኖ፤ ብቻ የመለኮት ብቻ የሥጋ ያልሆነ፤ ከሁለት ባሕሪ አንድ ባሕሪ፣ ከሁለት አካል አንድ አካል ሆኖ የተጠራበት ስሙ ነው ይላል ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው፡፡

ስለዚህ ሁልጊዜ በነገረ ሥጋዊ መለኮትን አንስተን ለብቻ ለመለኮት የሰጠነው ነገር የሚመስለን ለማን ማለት ነው? በአንፃረ መለኮት የተዋሐደውን ሥጋ መለየት የሚባል ነገር አይታሰብም የሚሆንም ነገር ስላልሆነ ፡፡

የእሱ ነገረ ተዋሕዶ ሚስጥር ከሌላው መዋሐድ፣ ከሌላው አንድ መሆን የተለየ የሚሆነው ለዚህ ነው፣ ተፈልጦ የሌለበት እያልን የምንናገረው ለዚህ ነው ስለዚህ እንዳሉት ለመለኮት ፍቅር ስንል መለኮትን ለተዋሐደው ሥጋ፣ አምላክ ለሆነው ሥጋና፣ ሥጋን ለተዋሐደው መለኮት እንዲህ ማለት ነው አገላለፁ፡፡

በነገር ተዋሕዶ ውስጥ አሁን ጠያቂያችን እንዳሉት ቆሮንቶስ ከተነሳ፣ ነገረ ሥጋዊ ከተነሳ፣ ሥጋን ብቻ ነጥሎ ያየ የሚመስለን ገጸ ንባብ በሥጋ አንፃር ያኔ ልናጎላው የፈለግነው፣ ልናስተምረው የፈለግነው፣ እሱ የተዋሐደው ሥጋ አምላክ ሆኗል፡፡

ሥጋ ላይ ያነፃፀረ ይመስለናል እንጂ በሥጋ አጠራር ሥጋን ያማከለ በነገረ መለኮት ንግግራችን ስለ መለኮትም እየተናገርን ነው ማለት ነው፤ ከዚህ አንፃር ነው ስለ ለመለኮት ፍቅር ስንል፤ መለኮትን ለተዋሐደው ሥጋ ወይም ሥጋን ለተዋሐደው መለኮት ማለት ነው፡፡

ያ ከሆነማ እንደ ጸጋ ኃይማኖት፣ እንደ ቅባት ኃይማኖት፣ ካቶሊክ ኃይማኖት፣ ሥጋንም መለኮትን እየለያየን በልደትም ጊዜ፣ በጥምቀትም ጊዜ፣ ሕማማትን በመቀበል ጊዜ፣ በተሰቀለም ጊዜ፣ በሞተም ጊዜ አንዱን አንዱ ቆሞ የሚያየው ነገር አድርገን ወይም ደግሞ በዚያ በመከራ ጊዜ መለኮት ተለይቶ ሥጋ ብቻውን መከራን ሲቀበል መለኮት ቆሞ ያይ ነበር ብሎ እንደ ማመን ነው፡፡

ሁሉንም ነገር መሞትንም፣ መከራ መቀበልንም፣ መራብን መጠማትን ለምን ለሥጋ ብቻ ሰጥቶ፣ ተዋሕዶ የሚለውን ነገር አስቀርተን መለኮት ብቻውን ያለ አድርገን እናያለን፡፡

ተዋሕዶ የምንለው እኛ በለበሰው ሥጋ፣ እንደ ሥጋ ባሕሪ፣ እንደ ሥጋ የሚሠራው ሥራ ሲሰራ ሁሉ መለኮት ከእሱ ጋር አለ፣በሞተ ጊዜ፣ ከሞተም በኋላ በአካለ ሥጋ መቃብር ሲወርድ መለኮት አልተለየም፡፡

በአካለ ነፍስ ወደ ሲዖል ሲወርድም መለኮት አልተለየም ማንም አስነሺ፣ ረዳት ሳይኖር ከመቃብር መነሳት እኮ የመለኮት ስልጣን ነው፣ አምላክ ስለሆነ ነው ያንን ሁሉ ማድረግ የቻለው እንጂ፤ በመደመኛ ተፈጥሮማ ሥጋ እኮ አስነሺ ያስፈልገዋል፣ እንደ አልአዛር እንደ ሌሎቹ ሙታኖች ማለት ነው፡፡ለዚህ ነው ይሔንን ሁሉ ለነገሩ ግልፀኝነት ይረዳል ብለን ስላሰብን ነው ይሔንን ምሳሌ ያደረግነው፣ ለተራበ ለተጠማ ለክርስቶስ ፍቅር እንሰግዳለን ሲል ደግሞ፤ የላይኛው ለመለኮት ፍቅር ስንል መነሻ አድርጎ ነው የተናገረው፡፡

ይኼኛው ደግሞ ክርስቶስ ስንል ሁል ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አማኑኤል ስንል ትዝ የሚለን ሁልጊዜ የተዋሐደው ሥጋ ነው፣ ይሔኛው ታዲያ በገዳመ ቆሮንቶስ ለተራበ፣ ለተጠማ ክርስቶስ፣ የተራበው የተጠማው ወይም ተራበ ተጠማ ብሎ መናገር የተሻለው ለመራብ ለመጠማት የሚስማማ ሥጋን ስለተዋሐደ ነው፣ መለኮት ስለማይራብ ስለማይጠማ ይሔ ቃል ትርጓሜ ያጣል፡፡
ያኛው ፍቅር የሚለው ነገር ፍቅር ደግሞ የእግዚአብሔርነት ወይም ደግሞ የመለኮት ገንዘቡ ነው፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር ነው ስለተባለ አንድ ልጁን ስለወደደ አንድ ልጁን አሳልፎ ለሞት የሰጠበት ምክንያትም ሰውን ዝም ብሎ ስለወደደ ነው ይለናል፡፡

በሌላ መልኩ “ፍቅር ሳቡለወልድ ኃያል መንበሩ ወአብፅዖ እስከለሞት እስከለሞት”፡ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ኃያል የሆነው አምላክ እግዚአብሔር ከመንበረ ፀባዖት ወደ እዚህ ምድር ላይ ያመጣው፣ ሥጋን መዋሐድ ያስፈለገው፣ በሥጋ ማርያም መገለጥ ያስፈለገው፣ መከራን መቀበል ያስፈልገው መፀነሰን መወለድን መጠመቅን ዞሮ ማስተማርን፣ ተአምራት መሥራትን፣ በመጨረሻ በመስቀል ላይ መሰቀልን፣ ወደ መቃብር መውረድን ይሔን ሁሉ ያስፈለገው የሰው ልጅ ፍቅር ስላስገደደው ነው፡፡

ስለዚህ ፍቅር የማን ገንዘብ ነው? የእግዚአብሔርን ወደ እዚህ ዓለም መምጣት የሚለውን፣ መጥቶ መገለፅ፣ ሥጋን መዋሐድ የሚለውን ነገር ሁሉ በትክክለኛ አነጋገር መግለፅ የሚቻለው በፍቅር ምክንያት ስላደረገው፣ ፍቅር የመለኮት ሐብት፣ ገንዘብ የባህሪ ስልጣኑ ስለሆነ ነው፡፡

ከዚህ አንፃር እንረዳ፣ እርስዎም የተጠማው፣ የተራበው፣ በሥጋ የደከመው በለበሰው ደካማ ሥጋ መሆኑን ኦርቶዶክስ ታምናለች፣ ታስተምራለች ታዲያ ከላይ በምስጋና መልክ የቀረበው ምን ለማለት ነው? ብለዋል፡፡ ዋና ፍሬ ሐሳቡ ይሔን ይመስላል ከዚህ የሚሰፋውን እንደ ትምሕርት አድርገን ወደፊት መነጋገር እንችላለን፡፡ እርስዎም ደግሞ በእርስዎ ውስጥ ከሚታሰበውና፣ ከሚወጣው፣ ከሚወርደው ሐሳብዎ የተነሳ አሁንም መረዳት አለብኝ፣ መነጋገር አለብን የሚሉት ነገር ካለ ባለን አድራሻ ሐሳብ ቢያቀርቡ መመካከርና መነጋገር ይቻላል፡፡
በአጠቃላይ ያቀረቡት ጥያቄዎ በሰል ያለ የቤተክርስቲያን እውቀት ያለው ሰው የሚናገረው ሐሳበ ስለሆነ፣ ለሁሉም አስተማሪ ስለሆነ ነው፡፡

የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን

ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q

ነገረ ማርያም

👉🏾👉🏾👉🏾 ስለ #አመቤታችን #ቅድስት #ድንግል #ማርያም ቅድስና

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገፅ  የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምትከታተሉ አባላቶቻችን ሁሉ፤ ከላይ በርዕሱ በተጠቀሰው መነሻነት “ከእውነተኛው ክርስትና”‘ መጽሐፍ ላይ ያለውን ጠቃሚ ትምህርታዊ መልእክት እንደሚከተለው ልከንላችኋልና ሁላችሁም አንብባችሁ በመረዳት ዛሬ ሐምሌ 21 ቀን የምናከብረውን ወርሃዊ በዓልን በማሰብ በቃል ኪዳኗ በአማላጅነቷ ተማጽናችሁ ከበረከቷ ትሳተፉ ዘንድ አደራ እንላለን።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከአዳም ዘር የተገኘች፤ አንደሌሎች ሰዎች ሁሉ ነፍስና ሥጋ ያላት ስው መሆኗን እናምናለን፡፡ በቅድስናና ክብር ግን ከሰው ልጆች ብቻም ሳይሆን ከቅዱሳን መላእክትም ትበልጣለች፡፡ ቅዱሳን መላእክት ምንም እንኳን ኃጢአትንም ሆነ ጽድቅ የመሥራት ነጻ ፈቃድ የተሰጣቸው ቢሆኑም እንደ ሰው ሥጋ የለበሱ አይደሉምና በሥጋ መጎምዠት የሚሠራ ኃጢአት አያስቸግሣራቸውም፡፡ በዕለተ እሑድ ተፈጥረው ማን ፈጠረን ብለው አርስ በርሳቸው ሲጠያየቁ አንድም ራሳችውን ሲጠይቁ “አኔ ፈጠርኳችሁ” ብሎ የተነሣውን ሳጥናኤልን አንተ አልፈጠርክንም የፈጠረን ራሱን ይገልጥልናል ብለው በሃይማኖታቸው በመጽናታቸው አግዚአብሔር ራሱን ከገለጠላቸው ጊዜ አንስተው “ቅዱሰ ቅዱስ ቅዱስ” አያሉ በማመስገን ጸንተው አስከ ዛሬ ድረስ አሉ፤ ወደ ፊትም በዚሁ አገልግሎታቸው ጸንተው እንደምኖሩ አናምናለን፡፡ ገሚሶቹ ዙፋኑን ተሸክመው፣ ሌሎች ደግሞ በመንበሩ ፊት ተነጥፈው ሲያመሰግኑ በሁለት ክንፋቸው ፊታቸውን፤ በሁለት ክንፋቸው አግራቸውን ጋርደው በሁለት ክንፋቸው ከአድማስ እስከ አድማስ እያበረሩ ያመሰግናሉ አንጂ ፊቱን አይተው አካሉን ዳስሰው አያውቁም፡፡ (አኢሳ.6፥፦+1-3) አመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ መላአክት በመፍራትና በመንቀጥቀት፣ ፊታቸውን ሸፍነው በዙፋኑ ፊት የሚቆሙለትን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ ተሸከመችው፣ በክንዶችዋ ታቀፈችው፤ በጀርበዋ አዘለችው፣ የጡቶችዋን ወተት መገበችው፡፡

ለመገኘቱ ጥንት ለዘመኑ ፍጻሜ የሌለው ጌታ ሰው ሆኖ ሰውን ለማዳን በተገሰጠ ጊዜ ከፍጥረታት ሁሉ ለይቶ አርሷን መረጠ፤ በማኅፀኗ ሊያድር የጡቶችዋን ወተት ሊመገብ ወደደ፣ የፈጠራትን አመቤተቻን ቅድስት ድንግል ማርያምን እናቴ አያለ ጠራት፣ አሷም ለልጅዋ የምትችለውን ሁሉ የምታደርግ ፍጹም እናት ሆነችለት። መውለጃ ቦታ አጥታ በቤተልሔም ዋሻ ወለደችው፤ ይሁን እንጂ በቤተ መንግሥት ለሚወለዱ ለነገሥታት ልጆች ተደርጎላቸው የማያውቀውን፤ የመላአክትን ዝማሬ ሰማች፤ የአረኞች ደስታ አየች፡፡ አህያና ላም አስትንፋሳቸውን ሲገብሩ፤ ነገሥታት ደግሞ ወርቅ፣፤ አጣንና ከርቤ ስያበረክቱ አይታ ለዚህ ጌታ እናት በመሆኗ አልተመጻደቀችም፤ ይልቅ ሔሮ’ድስ አዳይገድልባት ልጂን አዝላ ወደ ግብፅ ተሰደደች፤ ስለ አርሱ ሐሩርና ቁሩን፤ ረሀቡና ጥሙን፣፤ ስድብና ዘለፋን ሁሉን ታገሠች፤ የመላእክትን ዝማሬ በሰማችበት በቤተ ልሔም ብቻ ሳይሆን የአይሁድን ግፍ የልጂን መከራ ለማያት በቀራንዮም ነበረች፤ ልጂም በክብር እንግድነት በዶኪማስ ቤት ሲጋበዝ ይዟት አንደሔደ ሁሉ በመክራው ቀንም የሚወደውን ደቀ መዝሙሩን እናቴን ጥራልኝ፤ ብሎ አስጠራት፡፡ የፈጣሪ እናት ለመሆን ከመመረጥ በለይ ምን ክብር፤ ምንስ ቅድስና አለ? አርሷ ግን በዚህ ሁሉ አልታበየችም፤ መልአኩ ተልኮ የሰማይና የምድር ፈጣሪን ትወልጃለሽ ሲላት’ “የባሪያውን ትሕትና ተመለከተ” አለች እንጂ ይገባኛል አላለችም፡፡ ታዲያ ይህችን ቅድስት እናት ከፍጥረታት መካከል ማን ይመስላታል፣ ከዚህ በላይ መመረጥ፤ ከዚህ በላይ ለእግዚአብሔር መለየት፣ ከየት ይገኛል? ለዚህም ነው አባቶቻችን ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ ነች የሚሏት፤ ቅድስተ ቅዱሳንም ይሏታል። በርግጥ የሰው ቋንቋ የመግለፅ አቅሙ ውስን ስለሆነ እንጂ ከዚህም በላይ ይገባታል፡፡

ምንጭ፦ ‘እውነተኛው ክርስትና” ክፍል ሁለት
ተስፉዬ ምትኩ 2013

ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q

👉🏾👉🏾👉🏾ስለ #ቅድስት #ድንግል #ማርያም

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገፅ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምትከታተሉ አባላቶቻችን ሁላችሁንም ዛሬ የካቲት 21 ቀን ለሚከበረውን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወርሀዊ በአል እንኳን አደረሳችሁ እያልን፤ እለቱን በማስመልከት ስለ እመቤታችን ማለትም ፦ የአምላክ እናት ሰለመባልዋ፣ ስለ ዘለአለማዊ ድንግልናዋ፣ ስለ አማላጅነትዋ እና ስለ ሌሎችም ተያያዥ ትምህርቶች በሚመለከውት መሰረታዊ እውቀት አታገኙኝም ዘንድ ከትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ህይወት መጽሐፍ ላይ ያለውን እንደሚከተለው በተከታታይ ክፍል እንዲደርሳችሁ አድርገናልና አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።

ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ

“ሥጋን… አዘጋጀህልኝ” (ዕብ 10፥5)

ከላይ እንደተመለከትነው እግዚአብሔር ሰውን ለማዳን ሰው ለመሆን ስላሰበ በሥጋም በነፍስም ኃጢአት የሌለበትን ንጹሕ ሰውነት ይፈልጋል። ኃጢአተኛ ሰው ለኃጢአተኞች መድኅን ሊሆን አይችልም፤ በራሱ ኃጢአት ይሞታል እንጅ፤ ለኃጢአተኞች ተላልፎ ሊሰጥ የሚችል በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት ንፅሕት ቅዱስ መሆን አለበት። የኦሪት መሥዋዕትም የእንስሳት መሥዋዕት ስለሆነ የሰውን ልጅ ከኃጢአትና ከሞት ሊያድነው አልቻለም። ስለዚህም የኦሪትን “መሥዋዕትንና መብዐን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ” ተብሎ እንደተጻፈው አካላዊ ቃል ወልድ የሚዋሐደውን ንጹሕ ሥጋ ከየትና እንዴት እንደመያገኝ እርሱ ባወቀ ሥጋን አዘጋጅቷል (ዕብ 10፥5-7) ይችውም ከጥንት ጀምሮ በልበ አምላክ የታሰበች አዲሲቱ ሔዋን ቅድስት ድንግል ማርያም ነበረች። የመጀመሪያይቱ ሔዋን በኃጢአቷ ወድቃ ተረግማ እንዳትቀር ያሳታትን ጠላቷን የሰይጣንን ራስ የሚቀጠቅጥላት እርሷንም የሚያድናት ከዘርዋ እንደሚመጣ እግዚአብሔር ተስፋ ሰጥቷት ነበር (ዘፍ 3፥15)። ተስፋውም ከእመቤታችን የሚገኝ ሆኗል። የሴቲቱ ዘር የተባለው ንጹሕ ዘር የተገኘው ከእመቤታችን ሥጋና ነፍስ ነው። እመቤታችን ከጥንት ተፈጥራለች፤ ያንንም ንጹሕ ፍሬ መድኃኒታችንን አስገኝታለች። አካላዊም ቃል ወልድ ከእርሷ የነሣውን ማለት የወሰደን ሥጋንና ነፍስን ተዋሕዷልና።

እንግዲህ አዲሲቱ ሔዋን ከአዳም ኃጢአት ማለት ከጥንተ አብሶና ከሌላውም የኃጢአት ዓይነት ሁሉ የነጻችና የተቀደሰች ነች። ለሚሥጢረ ሥጋዌ በቅድሚያ የተዘጋጀች፣ ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ተጠብቃ በእግዚአብሔር ጥበብ የተፈጠረች እርሷ ብቻ ነበረች። ይኸማ ባይሆን ኖሮ መለኮት እንዲዋሐደው የሚገባ ንጹሕ ሥጋ ከየት ይገኝ ነበር። ከንጹሕ ምንጭ ንጹሕ ውኃ ይቀዳል። በቆሻሻ ከተበከለ ምንጭ ንጹሕ ውሐ ማግኘት አይቻልም። ስለዚህ በአዳም ኃጢአት ከረከሰው ምንጭ ንጹሕ ዘር ማግኘት ስለማይቻል እግዚአብሔር በጥበቡና በችሎታው አዲሲቱን ሔዋንርጎ ፈጥሯታል። “ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ” ማለት ከፈጠራት ጀምሮ በምንም በምን (ከድንግልናዋ አልተለወጠችም አላደፈችም) በማለት ቅዱስ ቴዎዶጦስ መስክሯል (ሃይማኖተ አበው ገጽ 174)። የአምላክ እናት ድንግል ማርያም በእውነት ያለ አዳም ኃጢአት እንደ ተወለደች እናምናለን።

መለኮታዊ ቃል ከንጽሕት ድንግል ማህፀን አደረ፤ ለራሱ የሚሆነውን ሥጋን አዘጋጀ (ዕብ10፥5) ይህችንም ንጽሕት ሥጋ የሥራው ሁሉ መጀመሪያ አድርጎ ፈጠራት (ምሳ 8፥22 ግዕዙን ተመልከት)። ከንጽሕት ድንግል የነሣውንም ማለት የወሰደውን ሥጋና ነፍስ በመዋሐድ በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና ተወልዷል። “እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” ተብሎ ነቢዩ ኢሳያስ እንደተነበየው ተፈጸመ (ኢሳ 7፥14)። ይህው ነቢይ አሁንም እንዲህ ጽፏል፦ “ሕፃን ተወልዷልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል” (ኢሳ 9፥6)። እንግዲህ ከድንግል ማርያም የተወለደው ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ ብዙ ነው፣ ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ ይባላል፤ እርሷም እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ ተብላ ትጠራለች። በእውነትም ድንቅ መካር ለሆነው ለኃያል አምላክ እናት ሆናዋለችና።
እመቤታችን የክርስቶስ እናት እንደ መሆኗ መጠን ለእርሱ የሚነገረው የማዕረግ ስም ለእርሷም ለእናትነቷ ይሰጣል።

ልጅዋ ብርሃን ሲባል እናቱ እመ ብርሀን (የብርሃን እናት)፣ ልጅዋ አምላክ ሲባል እናቱ እመ አምላክ (የአምላክ እናት) መባል ይገባታል በማለት የእስክንድርያና የመንበረ ማርቆስ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ ሲኖዳ ሣልሣዊ በእንግሊዝኛ በተተረጎመው መጽሐፋቸው ገልጸዋል።
በኤፌሶንም በ431 ዓም በተደረገው የሦስተኛው የቤተክርስቲያን ጉባኤ የተሰበሰቡት 200 አበው ሊቃውንት እመቤታችን ሰው ለሆነው አምላክ እናት ነች እንጂ መለኮትነት ለሌለው ሰው ብቻ እናት ነች ማለት ስህተት መሆኑን በመግለፅ ይህን ኑፋቄ የሚያስተምሩትን ንስጥሮስንና ተከታየቹን አውግዘው እመቤታችን ሰው ለሆነው አምላክ እናት መሆኗን መስክረዋል። ስለዚህም ወላዲተ አምላክ እመብርሃን በማለት በዚሁ ጉባኤ በተወሰነው የሃይማኖት ቀኖና መቅድም ላይ ገልጸዋል።

ስለ ወላዲተ አምላክ ዘላለማዊ ድንግልና

(ይቀጥላል)👇

👉🏾👉🏾👉🏾 የምስጢረ #ቁርባን መገኛ እመቤታችን #ድንግል #ማርያም ናት

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን፤ በርዕሱ የተጠቀሰውን የትምህርት ክፍል ከ ” ለቅዱስ ቁርባን እንድበቃ ምን ላድርግ?” ከሚለው መጽሐፍ ወስጥ ያገኘነው ጠቃሚ ትምህርትና ስለሆነ አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።

«ከሰማይ የወረደ ሕያው አንጀራ /ሕብስት/ እኔ ነኝ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው::»> /ዮሐ. 6-5]/

ይህንን ቃል መርምራችሁት ታውቃላችሁ? የሚያስተላልፈውስ ምሥጢራዊ መልዕክት ምን እንደሆነ አስተውላችኋል? እውነት እላችኋለሁ የዘላለም ሕይወት ስለሚገኝበት ስለ ክርስቶስ ሥጋ ይናገራል፡፡ ይህ ሥጋ ደግሞ የተገኘው ከድንግል ማርያም ነው::

ከሰማይ የወረደ ሥጋ ሳይሆን ቃል /ወልድ/ ስለ መሆኑ እንደማትጠራጠሩ እርግጠኛ ነኝ፡፡: የዮሐንስ ወንጌል መጀመሪያ እንዲህ ይጀምራል «በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ… ቃልም ሥጋ ሆነ» /ዮሐ. 1+1ና14/

«ቃልም ሥጋ ሆነ» ሲል በትክክል የእግዚአብሔር ልጅ /ወልደ እግዚአብሔር/ ከሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኖ መገለጡን ማረጋገጡ ነው::

መልአኩ ገብርኤል ለድንግል ማርያም ባበሠራት ጊዜ እንዲህ አላት «እነሆም ትፀንዛለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ፣፤ እርሱ ታላቅ ነው:: የልዑል ልጅም ይባላል» /ሉቃ. 1፥31/

ይህን የመልአኩን ቃል ከመሠረቱ ለመረዳት የብሉያትን ታሪክ የነቢያትን ትንቢት እንድንመለከት እንገደዳለን: ነቢዩ (አሞጽ ልጅ ኢሳይያስ በትንቢቱ ስለ እርሷ እንዲህ አለ “… ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፡፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠ ራዋለች፡» /ኢሳ. 7፥14/

ይህን የነቢዩን ቃል ልብ በሉት! ለዚህ ነው እኛ ስለ ድንግል ማርያም ባለን አስተምህሮት የመዳን ምክንያት /የመዳን ምልክት/ የምንላት ነቢዩ ጌታ አምላክ ምልክት ይሰጣችኋል ብሉ «እነሆ» የሚለውን አያያዥ ቃል በመጠቀም ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች በማለት እግዚአብሔር ለዳዊት ቤት ለመሚው መገለጥና ለሰው ልጆች መዳን ምልክቲቱ ድንግል መሆኗን በድንግልና መጽነሷ መሆኑን ገልጧል፡፡

በኋላም ጊዜው ሲደርስ ትንቢቱ ሲፈጽም መልአኩ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከው «ወደ አንዲት ድንግል» እንደሆነ ወንጌላዊው ሉቃስ ከነቢዩ ከኢሳይያስ ቃል አገናኝቶ ሲጽፍ «የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበር» /ሉቃስ 1፥27/ በማለት ገልጧታል፡፡:

ይህ መልኦክ በፊቷ ያቀረበውን ሰላምታ ታስተውሉታላችሁ? «ደስ ይበልሽ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ጌታ ካንቺ ጋር ነው» /ሉቃ. 1ሩ28/ አላት እንጂ «ጸጋ የምትምይ» ብሎ ገና ስለሚሰጥ የወደፊት ስጦታ አልነገራትም ሰውና እግዚአብሔር በተለያዩበትና እርቅ ባልተፈጸመበት ጊዜ እርሷ ግን ጸጋን ተሞልታ ከእግዚአብሔር ተመርጣ ለተነገረሳት ትንቢት ፍጻሜ «ያመነችና ብፅዕት ነበረች» ዘመዷ ኤልሳቤጥ ወደርሷ በመጣች ጊዜ እንደሰው ሰውኛው አባባል ባልቴቷ ሴት ማለት የነበረባት ልጄ ሆይ እንዴት ወደኔ መጣሽ? ነበር እርሷ ግን «የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?» /ሉቃ. 1፥43/ አለቻት እንጂ ስለ ድንግልም ስትመሰክርና ስታመሰግናት «ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት፡> /ሉቃ. 1፥35/ ብላለች፡፡

መድኃኒተዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ስለነሳው ስለ ተዋሃደው ለዓለም መዳን ስለሚሰጠው ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ ሲያስተምር «… እውነት እውነት እላችኋለሁ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም:፡:» ዮሐ. 6፥+53/ ብሏል፡፡

ለዚህ ነው ድንግል ማርያም የምሥጢረ ቁርባን መገኛ፣ መገለጫ ናት የምንለው እርሷን ሳይዙ በወላዲተ አምላክነቷ፣ በንጽሕናዋ በድንግልናዋ፣ በክብሯ፣ ባማላጅነቷ ሳያምኑ ማቁረብም መቁረብም አይገኝም፡ አማናዊውን መሥዋዕት ማግኘት አይቻልም፡። ባለቤቱም ክርስቶስ «የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ» በማለት የተናገረው ቃል የሥጋ መገኛ፣ ፍጹም ሰው ሆኖ መገለጡ መሆኑን ያረጋግጥልናል፡፥፡ ይህም የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ የተሰኘ /የሆነ/ ከሰው ወገን ከሆነች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ከጸናች ከድንግል ማርያም በመወለዱ መሆኑን ጭምር የሚገልጽ ቃል ነው:

በዚህ ምክንያት እመቤታችን የምሥጢረ ቁርባን መገኛ እየተባለች በአበው ተመሰገነች ከአበው ወገን /አባ ሕርያቀስ/ በቅዳሴው እንዲህ አመሰገናት «ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን ከፍ ከፍም እናደርግሻለን እውነተኛ የጽድቅ መብልንና እውነተኛ የሕይወት መጠጥን ወልደሽልናልና» /ቅዳሴ ማርያም ቁ. 9/

ምስጋናውንም በመቀጠል ከላይ ዮሐንስ 6፥53 ጠቅሼ ማብራሪያ የሰጠሁበትን ነጥብ በምታገኙበት መልኩ ሊቁ አባታችን እንዲህ ይላል ድንግል ሆይ የሚበላውን ያፈራሽልን የሚጠጣውን ያስገኘሽሽልን ወዮ ካንቺ የተገኘ ኅብስት በማመን ከርሱ ለሚቀበሉ ሕይወትንና ደኅንነትን የሚሰጥ ነው: ወዮ ከአንቺ የተገኘ ኅብስት በማመን ከርሱ ለማይቀበሉ ሰዎች የማይላመጥ ጽኑ ነው:: ይኸውም ኃያል የሚሆን የአድማስ ደንጊያ ነው፣ ወዮ ከአንቺ የተገኘ ጽዋ በማመን ከእርሱ ለሚጠጡ ሰዎች ጥበብን የሚገልጽ ሕይወትንም የሚሰጥ ነው፤ ወዮ ከአንቺ የተገኘ ጽዋ በማመን ከእርሱ ለማይጠጡ ሰዎች የሚያሰክርና የሚያፍገመግም የሚጥልና ኃጢአትን ስለማስተሠርይ ፋንታ ኃጢአትን የሚጨምር ነው:>

ልጇ ክርስቶስም ከእርሷ ስለነሳው አምነው ለሚቀበሉት ሕይወት ስለሚሰጠው ለዓለም ድህነት ስለሚቆርሰው ክብር ሥጋውና ቅዱስ ደም «ይህ ሰው ሥጋውን ልንበላ ይሰጠን ዘንድ እንዴት ይችላል?» ብለው እርስ በርሳቸው ለተከራከሩ አይሁድ /ዮሐ. 6ሩ52/ መልስ ሲሰጥ እንዲህ አላቸው «ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ መና በልተው እንደሞቱ አይደለም ይህን እንጀራ የሚበላ ለዘላለም ይኖራል» /ዮሐ. 6፥58/

እንዲሁ ደግሞ በቅዳሴ ካህኑ በመባረክ ሰዓት እንዲህ ይሳል «አምናለሁ አምናለሁ እስከ መጨረሻይቱም እስትንፋስ እታመናለሁ በሁለት ወገን ድንግል ከምትሆን ከሁላችን እመቤት ከቅድስት ማርያም የነሣው የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችንም የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋው ደሙ ይህ እማሬ እንደሆነ ያለመቀላቀልና ያለትድምርት ያለመለወጥና ያለመለየት ከመለኮቱ ጋር አንድ ያደረገው የጰንጤናዊ ጺላጦስም ዘመን ባማረ ምስክርነት ምስክር የሆነ ስለ እኛና ስለ ሁላችንም ሕይወት አሳልፎ የሰጠው» ሕዝብም ሁሉ «አሜን» በማለት በዚህ ቃል መታመናችውን ይመሰክራሉ፡፡

ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች እንዲህ እናምናለን እንዲህም እንታመናለን የበጉን መገኛ የድኅነታችንን ምክንያት በክብሯ ሁሉ እናከብራታለን ያዳኛችንን እናት ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ ስንላት አንኖራለን «ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል» /ሉቃ. 1፥48/ እንዳለች በአንድ መልአክ ገብርአል በአንዲት ባልቴት ኤልሳቤጥ ብቻ ተመስግና አትቀርም. የልጅ ልጆቻችን ሁሉ ያመሳግኗታል፡:

ምንጭ “ለቅዱስ ቁርባን እንድበቃ ምን ላድርግ?”
ከ መ/ም የሺጥላ ሞገስ- 2014

ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q

👉ጥያቄ፦ ቤተ ክርስቲያናችን ስለ #እመቤታችን #ቅድስት #ድንግል #ማርያም የምታስተምራቸው ታሪኮች ለምን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተካተቱም? ሳይካተቱስ እንዴት እውነት ነው ብለን ልንቀበል እንችላለን?

መልስ ፦ቤተክርስቲያን ስለ እመቤታችን የምታስተምራቸው ታሪኮች ለምን በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተካተቱም? በምን ማስረጃ እውነት ነው ብለን እንቀበል? ብለው የጠየቁትን በሚመለከት ፦ ፍፁም እምነት ላለው ክርስቲያን በእምነት በሚገለፅ ክርስቲያናዊ ፅናት እውነቱን ለመረዳት ከእምነት የሚበልጥ ሌላ ማስረጃ አያስፈልገውም። በመሰረቱ ማንኛውም ሰው ማመን ያለበት እውነተኛ በሆነው ክርስቲያናዊ አላማ ውስጥ ለሚኖር አማኝ እግዚአብሔር አምላክ በሚሰጠው እጅግ አስደናቂና ከአይምሮ በላይ የሆነውን ድንቅ ስራ በማየት ብቻ ከሚያምን በስተቀር በተፃፈ እና በሚነበብ ቃል አምናለው ማለት በእምነት የሚገለፅ አይሆንም። ለሁሉም ነገር ሃይማኖትን መሠረት ካላደረግን በስተቀር መፅሐፍ ቅዱስም ቢሆን የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ በእምነት ካልተቀበልነው በስተቀር መፅሐፍ ቅዱስ መቼ እንደተፃፈ ማነሰ እንደጻፈው እና መለኮታዊ የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ በጊዜውና በቦታው ተገኝተን የአይን ምስክሮች አይደለንም። እግዚአብሔር አምላክ ያከበራቸውና የመረጣቸው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የእግዚአብሔርን ቃል ፅፈው መፅሐፍ ቅዱስ ተብሎ ስለተጠራ እና አለም አቀፍ እውቅናም ስላገኘ ፤ ስለመፅሐፍ ቅዱስ በቂ እውቀት የሌለው ሰው ሁሉ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተፅፎ ያልተገኘውን ማንኛውንም ታሪክ እና የቅዱሳን ህይወት አንቀበልም ሲባል መስማት የተለመደ ነገር ነው። ይህ ደግሞ ትልቅ የሃይማኖት ህፀፅ እንደሆነ ልናውቅ ይገባል።

በመሰረቱ አይምሮ ላለው ሰው እና መፅሐፍ ቅዱስን በንባብ ሳይሆን በእግዚአብሔር መንፈስ ተመርቶ ለተረዳው ሰው ስለ እመቤታችን ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ስለመሆንዋ እንዲሁም ስለ ድንግልናዋ እና ስለ እናትነትዋ በእርስዋ ላይ ስለተገለፀው የእግዚአብሔር ክብር ሁሉ መፅሐፍ ቅዱስ በስፋት ያስረዳናል። ከዚህ በፊትም ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (ነገረ ማርያም) መፅሐፍ ቅዱስን መሰረት በማድረግ በስፋት መልዕክት እንዳስተላለፍን እናስታውሳለን። አሁንም ስለ እመቤታችን ስለ ድንግል ማርያም ክብርና ቅድስና ጠያቂያችን እንዲረዱት በአጭሩ ከብሉይ ኪዳን ስለ እመቤታችን የተፃፉት በሚመለከት ፦

1ኛ “በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ።” በአንተና በሴትዋ ማለቱ ሴት ተብላ የተገለፀው ስለ ድንግል ማርያም ነ(ኦሪ ዘፀ 3፥15)

2ኛ  እንዲሁም ነብዩ ኢሳያስ  “እግዚአብሔር  አምላክ ከሰው መካከል  ዘርን  ባያስቀርልን  ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም ሆነበቀረን ነበር ተብሎ የተፃፈውን ስንመለከት ከሰው መካከል ለድህነት ምክንያት ሆና የተገኘችው ድንግል ማርያም መሆንወን እንመለከታለን”(ኢሳ 1፤9)

3ኛ) “እንዲሁም ነብዩ ኢሳያስ አሁንም  “የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። በማለት የተነገረው የትንቢት ቃል ስንመለከት ስለ ድንግል ማርያም እንደሆነ መረዳት ይገባናል። ምክንያቱም ይህን ቃል ሊተካ የሚችል እንዲህ አይነት ክብር የተሰጠውና በሰማይም በምድርም አሻሚ የሚሆን ምክንያት አናገኝምና ነው።  (ኢሳ 60፤14)

4ኛ) እንዲሁም ነብዩ እስቅኤል ወደ  ምሥራቅም  ወደ ሚመለከተው  በስተ  ውጭ  ወዳለው  ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ፤ ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም፤ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል  ተዘግቶ ይኖራል በማለት የምስራቅ የቤተመቅደስ በር የተባለችው እመቤታችን ድንግል ማርያም ስትሆን እግዘኢአብሔር የገባበት በር ማህተመ ድንግልናዋ እሱ በራሱ ፈቃድና መለኮታዊ ጥበብ በማህፀንዋ አድሮ መወለዱን የሚያመለክት ሲሆን ማህተመ ድንግልናዋ ለዘለዓለም ፀንቶ የሚኖር መሆኑን ያመለክታል። ምክንያቱም ለዘለዓለም እስከ ፍፃሜ በእስራኤልም ቢሆን ተዘግቶ የሚኖር ቤተመቅደስ የለምና ይህ ቃል የተነገረው ስለ እመቤታችን መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። (ህዝ 44፤1 5)  

5ኛ ነብዩ ኢሳያስ “እነሆ፥  ድንግል  ትፀንሳለች፥  ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” በማለት ድንግል የተባለላት እመቤታችን ድንግል ማርያም ስትሆን እስዋ ፀንሳ የወለደችው ወንድ ልጇም አማኑኤል የተባለው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመሆኑ ቃሉ ይመሰክራል።

6ኛ ነብዩ ዳዊትም እግዚአብሔር  ጽዮንን  መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ።ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።(መዝ 131፥13 14) በዚህ ኃይለቃል የተጠቀሰችው አምላክ ማደርያው ያደረጋት ድንግል ማርያም መሆንዋን እንረዳለን።

በብሉይ ኪዳን እነዚህን የሚሚመስሉ ስለ ትንቢት የተነገሩ የትንቢት ምስጢራት በጣም ብዙ ናቸው። በአዲስ ኪዳን ስለ እመቤታችን የተነገረውን በሚመለከት

1ኛ መልዐኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ናዝሬት ከተማ ሄዳ ለድንግል ማርያም በድንግለነ ፀንሳ በድንግልና እንደምትወልድ ያበሰራት መሆኑን ቅዱስ ሉቃስ ፅፎልናል (ሉቃ 1፥26 ጀምሮ)

2ኛ ) አሁንም ቅዱስ ሉቃስ እንደፃፈው “ድንግል ማርያም በእድሜ እናትዋ ወደሆነችው ወደ ቅድስት ኤልሳቤጥ ለሰላምታ በሄደች ጊዜ ስለ ድንግል ማርያምም የአምላክ እናት መሆንዋንና ዘለዓለማዊ ክብሯን በኤልሳቤጥ ማህፀን ያለው ፅንስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ መስክሮለታል። ይሄንን ድንቅ ስራ የተመለከተችው ቅድስት ኤልሰቤጥም በአይሁድ ስርዓት ባልተለመደ አነጋገር የጌታ እናት ወደ  እኔ ትመጪ ዘንድ አይገባኝም ጽንሱ የሰላምታሽን ድምፅ በሰማ ጊዜ በማህፀኔ ውስጥ ዘለለ” ካለች በኋላ ድንግል ማርያምም ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተባረለች እንደሆነች የማህፀንዋ   ፍሬ የተባረከ  መሆኑን መስክራለች። (ሉቃ 1፥39 45)

3ኛ ) እንዲሁም በዚሁ ምዕራፍ ውስጥ እራስዋ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከልጇ የተሰጣትን የእናትነት እና የአማላጅነት ክብር አረጋግጣልናለች።  “እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤ ብርቱ የሆነ እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው። ” (ሉቃ 1፤48) በማለት ፍጥረታት  ሁሉ ድንግል ማርያምን ቅድስት ነሽ ፣ንፅሂት ነሽ፣ ድንግል ነሽ፣ ልእልተ ክብርት ነሽ፣ ወላዲተ አምላክ ነሽ፣ ማህደረ መለኮት ነሽ፣ እመ ብዙሃን ነሽ፣ ሰዓሊተ ምህረት ነሽ፣ እያሉ ሊያመሰግኗት እንደሚችሉ ራስዋ መስክራለች። (ሉቃ 1፥48)

4ኛ) እንዲሁም ድንግል ማርያም ፈጣሪና አምላክዋ የሆነው ቀዳማዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድን በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ፀንሳ እንደምትወልድና እርሱም ከኀጢአታቸው ሁሉ እንደሚያድናቸው ስሙም ኢየሱስ እንደምትለው ወንጌላዊ ማቲዎስ በወንጌሉ  መስክሯል (ማቴ1፥20 23)

(ይቀጥላል)👇

ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ

👉🏾👉🏾👉🏾ስለ #እመቤታችን #ቅድስት #ድንግል #ማርያም

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገፅ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ የምክር አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን፤ ከዚህ ቀጥለን በርዕሱ የተጠቀሰውን ከመጽሐፈ አሚን ወስርዓት መጽሐፍ ላይ ያለውን ትምህርት እንደሚከተለው ልከንላችኋልና ጠቃሚ ስለሆነ ሁላችሁም አንብባችሁ በተግባር ትጠቀሙበት ዘንድ እንመክራለን።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ማርያም ተብለው የተጠሩ ብዙዎች ሲኖሩ እመቤታችን ድንግል ማርያምን ግን የአምላክ እናት ስለሆነች ከሰው ወገን ሁሉ ልዩ ነች።

“የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበር” ሉቃ 1፤27

“ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ” ሉቃ 1፥28

ማርያም ማለት ፀጋ ወሃብት፣ ፍፅምት፣ ልዕልት፣ ተከአኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ፣ መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት ማለት ነው።

አባቷ ቅዱስ ኢያቄም ይባላል እናቷ ቅድስት ሐና ትባላለች፤ መካን ሆነው ሲኖሩ እግዚአብሔር አምላክ በመጨረሻ ለራሱ እናት እንድትሆነው ከአባቶች ወገብ ጀምሮ ያዘጋጃትን ሴት ልጅ ወለዱ ስሟንም ማርያም ብለው ጠሯት። ወንድምም እህትም የላትም ለወላጆቿ ብቸኛ ናት።

“ርግቤ መደምደሚያዬም አንዲት ናት ለእናቷም አንዲት ናት፤ ለወለደቻትም የተመረጠች ናት” መሓ 6፥9

ኢያቄምና ሐና የወለዷት በስለት ነበር። ስለታቸውም የሚወልዱትን ልጅ በቤተመቅደስ እንዲኖር ለእግዚአብሔር መስጠት ነበር። በዚህም መሠረት ድንግል እመቤታችን የ3 ዓመት ሕፃን እንደሆነች ወደ ቤተመቅደስ አስገቧት።

“ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን የአባትሽንም ቤት እርሺ ንጉሥ ውበትሽን ወድዷልና እርሱ ጌታሽ ነውና” መዝ 44፥10

እመቤታችን በቤተመቅደስ 12 ዓመት ኖረች ከዚያም ሰይጣን በአይሁድ አድሮ ከቤተመቅደስ እንድትወጣ አደረጉ ምክንያታቸውም ድንግል ማርያም እንደ ሌላ ሴት መስላቸው ነበር። እርሷ ግን ከሴቶች ሁሉ ንጽሕት ናት። ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ ወደ እርሷ ሲመጣ ያላት እንዲህ ነበር።

“ደስ ይበልሽ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት” ሉቃ 1፥28

ከቤተመቅደስም በወጣች ጊዜ ከእግዚአብሔር የተሰጠች ናትና ከሽማግሌዎች ለአንዱ በአደራ እንድትሰጥ ሆኖ ዮሴፍ የተባለ ቅዱስ ሰው ይጠብቃት ዘንድ ተሰጠች።

በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ የአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ በወጣች ጊዜ ዮሴፍ እመቤታችንን ይዞ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ ሄደ በዚያም እመቤታችን የዓለምን መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስን ወለደች። ሉቃ 2፥1-7

ወላዲተ አምላክ መሆኗ

ድንግል ማርያም እመቤታችን የወለደችው ኢየሱስ እርሱ አምላክ ነው። ቀድሞ በነቢዩ በኢሳይያስ ትንቢት ነበር።

“ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል” ኢሳ 9፥6

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከሰማይ ወርዶ ከድንግል የተወለደው የሁላችን ቤዛ ኢየሱስ እኛን ለማዳን ሰው ይሁን እንጂ እርሱ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው እንዲል ሮሜ 9፥6

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ቃል መጀመሪያ ነበር ያ ቃል እግዚአብሔር ነበረ ያም ቃል የተባለ ሥጋ ሆነ ብሎ ከድንግል ማርያም የተወለደው አምላከ እግዚአብሔር እንደሆነ ተናገረ። ዮሐ 1፥1-14

ስለዚህ እመቤታችን ወላዲተ አምላክ (አምላክን የወለደች) ተብላ ትጠራለች። ይህ ሲባል ለማንም አይቀጸልም። ድንግል ማርያም ብቻ እግዚአብሔርን ልጄ ትለዋለች። እግዚአብሔርም ድንግል ማርያምን ብቻ እናቴ ይላታል።

“እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና ማደርያው ትሆን ዘንድ ወዷታልና እንዲህ ብሎ ይህች ለዘላለም ማረፊያዬ ናት” መዝ 131፥13

መረጣት ማደሪያውም ሆነች ጸነሰችው በዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ሲሞላ ወለደችው አቀፈችው አጠባችው ኢየሱስ አለችው አሳደገችው። እናቴ እያለ ይታዘዛት ነበር።

ይቀጥላል

ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ

👉🏾 #ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን እየመረመሩ ካሉ ውድ አባላችን የመጣ ጥያቄ

<<< እሺ ጥያቄዎቹ እነዚህ ናቸው፣
1/ የ #ማርያም አማላጅነት ለምን ያስፈልጋል አባታችን እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ፣
2/ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን #ሴት ልጅ በምን ዙሪያ ነው ማገልገል የሚችሉት?
3/ የብሉይ ኪዳን እና የሐዲስ ኪዳን ትምህርት እንዴት ታስረዳዋለህ?
4/ በሐዲስ ኪዳን የተሰጠን ስጦታዎችን በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንዴት ነው የምንጠቀመው?
5/ #ነፍስ #መንፈስ እና #ሥጋ ስለሚባሉት ነገሮች ትምህርት እና ልዩነት? >>>

✍መልስ፦ ለአንደኛውና፣ ለሁለተኛ ጥያቄ ቀደም ሲል መልስ ሰጥተንበታል፣ በዚሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ ላይ ያገኙታል፣ ከ3 እስከ 5 ያሉትን ጥያቄዎች እንመልሳለን።

👆መልስ፦ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን ለሚለው፣ ብሉይ ኪዳን ማለት ሕገ ኦሪት ነው፣ ሕገ ኦሪት ማለት በሙሴ አማካኝነት መጻሕፍት የተጻፉበት ዘመን ነው፣ ያን ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያልተወለደበት ዘመን ነው ማለት ነው።

ስለዚህ በዚህ ዘመን የሰው ልጅ አታድርግ የተባለውን አድርጎ እግዚአብሔርን ያህል ጌታ፣ ገነትን ያህል ቦታ አጥቶ ወደ ሲዖል የወረደበት ዘመን ነው፣ ሕጉ ሥርዓቱ የተመሠረተው በሙሴ ዘመን ነው ማለት ነው፣ ሙሴ አርባ መአልት ፣ አርባ ለሊት ጾሞ እግዚአብሔር በሙሴ አድሮ ሕገ ኦሪትን ሠርቷል፣ ሕገ ኦሪትን ስናይ ጊዜያዊ ነው፣ ምድራዊ ነው፣ የሆነ ኃጢአት እንኳን ቢሠሩ በሕገ ኦሪት የሚፈረድባቸው እለቱን ነው።

ወደ ሐዲስ ኪዳን ስንመጣ ሕጉን የመሠረተው፣ ሕገ ወንጌልን የመሠረተው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ ባለቤቱ ነው፣ እሱ ራሱ ሰው ሆኖ ተወልዶ ነው፣ ጾሞ ነው ጹሙ ያለን፣ አርባ ለሊት፣ አርባ መአልት፣ አርባ መአልት በገዳመ ቆሮንቶስ ጾሞ ነው የሠራት የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 4 ላይ እናገኘዋለን።

በዘዳግም ምዕራፍ 9 ቁጥር 9 ላይ እንደምናገኘው ሙሴ አርባ ለሊት፣ አርባ መአልት ጾሞ ነው አሥርቱ ትዕዛዛትን የተቀበለው፣ በሙሴ አማካኝነት በረድኤት ነው እግዚአብሔር ኦሪትን የሠራው፣ ሕገ ወንጌልን በኩነት ራሱ ሰው ሆኖ ያስተማረው ትምህርት ነው፣ የኦሪቱ ሕግ ጊዜያዊ ነው፣ ምድራዊ ነው፣ የሐዲስ ኪዳን ሕግ ግን ሰማያዊ፣ ዘለዓለማዊ ነው፣ ያኛው አፋዊ ነው፣ ይኼኛው ውሳጣዊ ነው፣ ያ ጊዜያዊ ነው፣ይኼኛው ዘለዓለማዊ ነው።

በሕገ ኦሪት ወይም በብሉይ ኪዳን የነበረው መስዋእቱ የላም፣ የበግ፣ የፍየል ነበር፣ የሐዲስ ኪዳን መስዋዕት ግን ራሱ ባለቤቱ ነው፣ መስዋእቱን የሚቀበለው እሱ ነው፣ መስዋእቱም እሱ ነው፣ መስዋእቱንም የሚሰዋው እርሱ ራሱ ሊቀ ካሕናት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ማለት ነው፣ ልዩነቱ ይሔ ነው።

በኦሪቱ የላም፣ የበግ መስዋዕት ነው፣ በሐዲሱ ግን ሥጋዬን የበላ፣ ደሜን የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው ብሎ ሥጋውን፣ ደሙን ነው የሰጠን እሱ ራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ በኦሪቱ ሊቀ ካሕናቱ በየዓመቱ መስዋዕት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደስ ይሄድ ነበረ፣ በሐዲሱ ግን ሊቀ ካሕናቱ ራሱ ነው፣ እሱ ራሱ መስዋእቱ አንድ ጊዜ ተሰውቷል፣ ከዚያ በኋላ የተሰዋውን ካሕናት በየዓመቱ ያቀርባሉ፣ በኦሪቱ ሊቀ ካሕናት ሲሞት በሌላ ይተካል።

በሐዲስ ኪዳን ግን የካሕናት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ አንዳንድ ሰዎች የካሕናት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሆነ ካሕናት አያስፈልገንም የሚል ጥያቄ ይጠይቃሉ፣ ካሕናት ከሌሉ እኮ በማን ላይ ሊቅ ይባላል? ሊቅ ማለት አለቃ ነው የሁሉ በላይ ነው ስለዚህ ካሕናት ከሌሉ፣ ሐዋርያት ከሌሉ፣ የሐዋርያት አለቃ ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ሊቀ ሐዋርያት ይባላል?

ስለዚህ ሊቀ ሐዋርያት፣ የሐዋርያት ሊቅ፣ ሊቀ ካሕናት የካሕናት አለቃ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ በእርሱ አለቃነት፣ በእርሱ መምህርነት፣ በእርሱ አባትነት ሌሎቹ ከስር ያሉ መምህራን ተተክተዋል ማለት ነው በብሉይ በጊዜው የነበረው ሊቀ ካሕናቱ ሲሞት ሊቀ ካሕናት ይተካል፣ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሊቀ ካሕናቱ አንድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው አሁን ደግሞ ሊቀ ካሕናት እየተሾሙ በሐዋርያት እየተተኩ ባገኙት ሥልጣን ሊቀ ካሕናት ይሾማሉ።

ሊቀ ካሕናት ያሉትን ሊቀ ካሕናት ትላላችሁ? ሊቀ ካሕናት ኢየሱስ ክርስቶስ ሆኖ እያለ ለምን ሊቀ ካሕናት ይባላል፣ ሊቀ ኅሩያን ለምን ይባላል የሚል አባባል ካለ እነኚህን በጸጋ፣ በስጦታ ነው የምንላቸው፣ የካሕናት ምንጭ፣ የክሕነት ምንጭ፣ የክሕነት አባት ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፣ ስለዚህ የብሉይና የሐዲስ ልዩነቱ እጅግ ብዙ ነው፣ ሰፊ ነው።

ለምሳሌ በብሉይ ሚስት ከባሏ ተደብቃ ምንም ብታደርግ በድንጋይ ተወግራ፣ በእሳት ተቃጥላ እንድትሞት ይደረጋል፣ ወደ ሐዲስ ኪዳን ስንመጣ ግን በንስሐ ነው፣ ኃጢአት የሠራ፣ የበደለ ሰው ካለ በጊዜው ንስሐ ይግባ ካልገባ ግን በዕለተ ምፅዓት ነው የሚፈረድበት ማለት ነው፣ በኦሪት የነበሩትን ሕግ ስናየው አትግደል፣ አታመንዝር፣ አትስረቅ፣ በሐሰት አትመስክር፣ የሚል ነው የነበረው።

ወደ ሐዲስ ኪዳን ስንመጣ ግን ከላይ የጠቀስናቸውን ሕግጋት የምናገኛቸው በዘፀአት 20 ነው፣ ማቴዎስ 5 ላይ ብንመለከት ደግሞ በብሉይ አትግደል ብሎ የነበረውን፣ በሐዲሱ ደግሞ በወንድሙ ላይ የተቆጣ ይፈረድበታል ይላል ሕግጋቱ ፍፁም ነው ያደረጋቸው፣ በብሉይ አትግደል ስለተባለ የገደለ ነበር የሚፈረድበት፣ በሐዲስ ኪዳን ስንመጣ ግን በወንድሙ ላይ የተቆጣ ይፈረድበታል ነው ያለው፣ በብሉይ ዘመን ያመነዘረ ይፈረድበታል ነበር ያለው፣ በሐዲስ ኪዳን ግን በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 5 ስንመጣ ደግሞ ወደ ሴት አይቶ የተመኘ በልቡ አመነዘረ ይላል።

በብሉይ ስንመለከት ሚስቱን የፍቺውን ምክንያት ካገኘባት ይፍታት ይላል፣ በሐዲስ ኪዳን ግን ሚስቱን ያለ ምንም ምክንያት የፈታ፣ የተፈታችውንም ያገባ አመነዘረ ነው የሚለው፣ በብሉይ እውነቱን እውነት፣ ሐሰቱን ሐሰት በሉ ተብሏል፣ በሐዲስ ኪዳን ፈፅማችሁ አትማሉ ይላል፣ አሁን ሕጉ ፍፁም ነው፣ በብሉይ ባልንጀራህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ ይላል ፣ ወደ ሐዲስ ኪዳን ስንመጣ ጠላታችሁን ውደዱ፣ ሲል እናያለን ስለዚህ ሕግጋትን ፍፁም እያደረጋቸው ነው የመጣው ማለት ነው፣ ፈፅሟቸዋል ማለት ነው።
የኦሪቱ ተሽሯል የሚሉ ሰዎችአሉ፣ ግን የኦሪቱ ሙሉ በሙሉ ተሽሯል ማለት አይቻልም የማያስፈልገው አልፏል፣ ያሉትን ግን ፍፁም ነው ያደረጋቸው፣ ያኔ መስዋእቱ የላም፣ የበግ ነበር አሁን ግን በእሱ መስዋዕትነት ፍፁም አደረገው፣ ያኔ የኦሪቱ ሊቀ ካሕን አሮን ነበረ፣ አሮን ሲሞት የአሮን ልጅ እያለ የሚተካ ነበረ፣ አሁን በሐዲሱ እሱ ፍፁም አድርጎ ሊቀ ካሕናቱ እሱ ሆኖ እናገኘዋለን ያኔ የነበረው ታቦት፣ ጽላት እሱም ምንድን ነው ካልን የከበረ እንቁ፣ እምነበረድ ነበረ፣ ከዚያ ላይ የተጻፈው አሥርቱ ቃላት፣ አሥርቱ ትዕዛዘ ወንጌል ነበሩ፣ በሐዲሱ ኪዳን ግን የእሱ ስም ተጻፈበት።

መጀመሪያ የነበርኩት እኔ ነኝ፣ አሁንም ያለሁት፣ ወደ ፊትም የምኖር እኔ ነኝ ብሎ ለስሙ እንድንሰግድ፣ ስንሰግድ ለእግዚአብሔር ስም እንድንሰግድ በፊልጵስዩስ መልእክቱ ምዕራፍ 2 ቁጥር 10 ላይ ” ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሰማይም በምድርም ያለ ሁሉ ይንበርከክ፣ ይስገድ” ተብሎ እንደተነገረ አሁን እኛ ለታቦቱ፣ ለጽላቱ ስንሰግድ ለእግዚአብሔር ስም ነው የምንሰግደው ማለት ነው ቅዱስ ጳውሎስ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሁሉም ይስገድ፣ ይንበርከክ ብሎ ነግሮናል ማለት ነው።

👇(ይቀጥላል )👇

👉🏾👉🏾👉🏾ጥር 21- #እረፍታ ለእግዚእትነ #ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ

#ዕረፍተ_ድንግል

የተከበራችሁ እና የተወደዳችሁ የዮሐንስ ንስኀ ድረገጽ ተከታታይ  ወገኖቻችን፤ ዛሬ ጥር 21 ቀን  የምናከብረውን  የእመቤታችን  የቅድስት  ድንግል  ማርያም   በዓለ  ዕረፍት  መታሰቢያ በሚመለከት ከመጽሐፈ ተአምሯ ላይ ያለውን ታሪክ  ከዚህ እንዲደርሳችሁ  ስላደረግን ትምህርቱን  በማስተዋል  አንብባችሁ ከበአሉ በረከት  ታገኙበት  ዘንድ  አደራችንን  አናስቀድማለን። 

ከመጽሐፈ ተአምሯ ፦ እመቤታችን  ከዚህ  ዓለም  ታልፍ  ዘንድ  የጸለየችው  ጸሎት  ይህ  ነው፡- ‹‹አቤቱ  ቸር  ጌታዬ  ሆይ!  ከዚህ  ሑከትና  ኀዘን  ከመላበት  ዓለም  ደገኛውን  መልአክህን  ልከህ  ወደኝ›  ስትል  በጸለየች  ጊዜ  መልአኩ  ቅዱስ  ገብርኤል  ተገለጸላት፡፡  እንዲህም  እያለች  ስትጸልይ  ሰማይ  ተከፈተ፡ ፡ ቅዱስ  ገብርኤልም  ወደ  እመቤታችን  ወርዶ  ‹ጸጋን  የተመላሽ  ሆይ!  ደስ  ይበልሽ›  በማለት  የደስታ  መልእክት  ነገራት፡፡  ዳግመኛም  ‹‹እነሆ  ጸሎትሽ  ከአንቺ  ከተወለደው  ከእግዚአብሔር  ዘንድ  ደረሰ፡፡  እንደፈቃድሽ  ከዚህ  በኃላፊው  ዓለም  ወደ  ዘላለም  ሕይወት  ትሄጂ  ዘንድ  ልመናሽ  ተሰምቶልሻል››  አላት፡፡ 

እመቤታችንም  ይህንን  ነገር  ከመልአኩ  በሰማች  ጊዜ  ወደ  በዓቷ  ተመለሰችና  ከዚያ  የሚያገለግሏትን  ደናግል  ሰብስባ  ‹አይሁድ  ሁልጊዜ  የልጄን  መቃብር  ይጠብቃሉና  ስለዚህ  የእኔን  ከዚያ  መገኘት  አንድ  ቀን  ይገለጽላቸውና  ከዚያ  መግባት  ይከለክሉኛል  ብዬ  ፈራሁ፡ ፡ ስለዚህ  ከዛሬ  ጀምሮ  ራሳችሁን  ችላላችሁ  በሰላም  ትኖራላችሁ  እኔ  ወደ  ቤተልሔም  እሄዳለሁና›  አለቻቸው፡፡  በዚህም  ጊዜ  ሁሉም  በአንድነት  ቃላቸውን  አስተባብረው  ‹ከአንቺ  ጋር  እንሄዳለን፡፡  ስለ  አንቺ  እናት  አባታችንን፣  እኅት  ወንድሞቻችንን  ያለንን  ሁሉ  ትተን  ተከትለንሻልና  እነሆ  አሁንም  አንቺ  ከሄድሽበት  እኛም  አብረንሽ  እንሄዳለን፣  ባለ  ዘመናችን  ሁሉ  ከአንቺ  አንለይም›  አሏት፡፡ እመቤታችንም  በዚያን  ጊዜ  ይዛቸው  ወደ  ቤተልሔም  ሄደች፣  በዚያም  ተቀመጠች፡፡ እንዲህም  ያለቻቸው  ስለ  አይሁድ  ፍራቻ  ሳይሆን  ከዚህ  ከኃላፊው  ዓለም  በሞት  የመለየቷ  ጊዜ  ስለመድረሱ  ነበር፡፡ እናንት  የፍቅሯን  ፈለግ  የተከተላችሁና  በፍቅሯ  ቀምበር  የተጠመዳችሁ  የወንጌል  ልጆች  ሆይ  እንግዲህ  እመቤታችን  በቤተልሔም  ተቀምጣ  ሳለች  መልአኩ  ቅዱስ  ገብርኤል  ከዚህ  ዓለም  በሞት  የምትለይበትን  ጊዜ  በክብር  እንደነገራት  አስተውሉ፡፡ ልመናዋ  ክብሯ  ለዘለዓለሙ  በዕውነት  ይደርብን፡፡     
 
እረፍታ  ለእግዚእትነ  ማርያም  ድንግል  ወላዲተ  አምላክ፡-  በ50 ዓ.ም  ገደማ  በዕለተ  እሑድ  ጌታችንም   እልፍ  አእላፍ  መላእክቱን  አስከትሎ  መጥቶ  ‹‹እናቴ  ሆይ!  ከዚህ  ዓለም  ድካም  ላሳርፍሽ  መጣሁ››  አላት፡ ፡  እመቤታችንም  ‹‹ልጄ  ሰማይና  ምድር  የማይወስኑህን  ዘጠኝ  ወር  ከአምስት  ቀን  በማኅፀኔ  ተሸክሜ፣  በድንግልና  ወልጄህ  እሞታለሁን?››  አለችው፡፡  ጌታችንም  በሲኦል  የሚሠቃዩ  ነፍሳትን  አሳያትና  ‹‹እናቴ  ሆይ!  ሞትሽ  ለእኒህ  ቤዛ  ይሆናቸዋል››  አላት፡፡  ለፍጥረታት  ሁሉ እጅግ  የምትራራ  እመቤታችንም  ‹‹እነዚህን  ከማርክልኝስ  ይሁን  ልሙት››  አለችው፡፡ ከዚህም  በኋላ  ጌታችን  ቅድስት  ነፍስዋን  ከክብርት  ሥጋዋ  ለይቶ  በዝማሬ  መላእክት  አሳረጋት፡ ፡ ደቀመዛሙርቱንም  ከያሉበት  በደመና  ጠቅሶ  ካለችበት  አድርሶ  ‹‹እመቤታችሁን  ቅበሩ››  አላቸው፡፡ እነርሱም  ይዘዋት  ወደ ጌታ  ሰማኔ  ወሰዷት፡፡ 

አበው  ‹‹እመቤታችን  ሆይ!  ሞትሽ  ሠርግን  ይመስላል››  እንዳሉት  የእመቤታችን  እረፍት  እንባ  መራጨት፣  ጠጉር  መንጨት፣  ደረት  መድቃት እንዳለበት የሰው ሞት አልነበረም፡፡ ይልቁንም  አንደ  ሠርግ  ቤት  ቅዱሳን  መላእክት  በውዳሴ፤  በማህሌት፣  በዝማሬ፣  በምስጋና  ወደ  ሰማይ  ሸኟት  እንጂ፡፡ ቅዱስ  ያሬድም  ‹‹እመቤታችን  ድንግል  ማርያም  ከምድር  ወደ  ሰማይ  ከፍ  ከፍ  አለች፤  በዚያም  ከልጇ  ጋር  በአብና  በመንፈስ  ቅዱስ  ቀኝ  ተቀመጠች››  በማለት  ዘምሯል፡፡ የእመቤታችን  ሥጋዋ  ከጌቴሴማኔ  ወደ  ገነት  መፍለሱን  አስቀድሞ  አባቷ  ቅዱስ  ዳዊት  በትንቢት  ሲናገር  ‹‹አቤቱ  ወደ  እረፍትህ  ተነሥ  አንተና  የመቅደስህ  ታቦት››  በማለት  ተንብዮዋል፡፡  መዝ 131፡8፡፡ ይህም  ‹‹ፈጣሪዬ  ሆይ  ምእመናንን  ወደምታሳርፍበት  ወደ  መንግሥተ  ሰማያት  የመቅደስህን  ታቦት  ድንግል  ማርያምን  ይዘህ  ተነሥ››  ሲል  ነው፡፡ ይህም  እመቤታችን  ቅድስት  ድንግል  ማርያም  64  ዓመት  በዚህ  ዓለም  ከኖረች  በኋላ  ነብሷ  ከሥጋዋ  ተለይቶ  እንደ  ልጅዋ  ትንሣኤ  መነሣቷን  የሚያመለክት  ነው፡፡ ‹‹ታቦት››  ያላትም  ማደሪያው  ስለሆነች  ነው።

ጠቢቡ  ሰሎሞን  በምሳሌ  ሲናገር  «ወደጄ  ሆይ  ተነሺ፣  ውበቴ  ሆይ  ነይ፡፡ እነሆ  ክረምት  አለፈ፣  ዝናቡም  አልፎ  ሄደ፣  አበቦች  በምድር  ላይ  ተገለጡ፣  የዜማም  ጊዜ  ደረሰ፣  የቁርዬውም  ቃል  በምድራችን  ተሰማ፡፡  በለሱ  ጎመራ  ወይኖችም  አበቡ  መዐዛቸውንም  ሰጡ  ወዳጄ  ሆይ  ተነሺ፤  ውበቴ  ሆይ  ነይ»  አለ፡፡  መኃ 2፡10-14፡፡ ይህ  ኃይለ  ቃል  ሲተረጎም  በውስጡ  ብዙ  ምሥጢራዊ  ነገሮችን  ያያዘ ነው፡፡  «በክረምትና  በዝናብ»  የተመሰሉ  የእመቤታችን  መከራዎች  ናቸው፡፡ የመከራሽ  ጊዜ  አልፏል  ሲላት  «አበቦች  በምድር  ላይ  ተገለጡ»  ማለቱ  ከልጅሽ  እግር  ሥር  ቁጭ  ብለው  ተምረው  ወንጌልን  የተቀበሉ  ሐዋርያት  አንቺን  በእናትነት  የተረከቡ የ ሐዋርያት  ድምፅ  ወይም  ስብከት  በምድር  ሁሉ  መሰማቱን  ያጠይቃል፡፡

ጠቢቡ ሰሎሞን  «የዜማ  ጊዜ  ደረሰ»  ያለው  የመከሩን  ወቅት  ነው፡፡ መከር  የፍሬ  ጊዜ  እንደመኖኑ  ሐዋርያት  የዘሩት  ዘር  ማለትም  ስብከታቸው  ፍሬ  አፈራና  ክርስቲያኖች  በዙ፤  «በለሱ  ጎመራ»  በጎ  ምግባር  የሌላቸው  ሰዎች  በሐዋርያት  ስብከት  ተምረው  ምግባር  መሥራት  ጀመሩ፤  «ወይኖች  አብበዋል  መዐዛቸውንም  ሰጥተዋል»  በመላው  ዓለም  ያሉ  ምዕመናን  በሃይማኖት  ማበብ፣  መዐዛ  ምግባራቸውን  ማቅረብ  መስጠት  ጀመሩ  በማለት  ሊቃውንት  አባቶች  ምሥጢሩን  ያብራሩታል፡ ፡ በዚህ  ትርጓሜ  ‹‹ወደጄ  ሆይ!  ተነሽ››  እያለ  የሚናገረው  ተወዳጁ  ልጇ  ጌታችን  መድኃኒታችን  ኢየሱስ  ክርስቶስ  እናቱ  ድንግል  ማርያምን  በመለኮታዊ  ስልጣኑ  ከሙታን  ለይቶ  ማስነሣቱን  ሲያስረዳን  ነው።

(ይቀጥላል)👇

ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q 

ስለ እመቤታችን #ድንግል #ማርያም የጽንሰቷ ነገር

እመቤታችን ድንግል ማርያም የተፀነሰችበት ነሐሴ 7 ቀን ከክርስቶስ ልደት በፊት 16 ዓመት ያህል ቀድማ የብሉይ ኪዳን ዘመን መጨረሻ ላይ ሲሆን ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከጾመ ፍልሰታ ሱባኤ ጋር ይህን በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ስነሥርዓት ታከብራለች። መጽሐፍ ቅዱስ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዘር ኀረግ ከዳዊት ወገን ከመሆኑ በስተቀር የወላጆቿንና ከጽንሰቷ ጀምሮ ያለውን የእሷን የሕይወት ታሪክ በምሣሌና በምስጢራዊ አገላለጽ ካልሆነ አስፍቶና አብራርቶ አይናገርም።

ይሁን እንጂ በነገረ ማርያም እና በቤተክርስቲያን ታሪክ እንደተጻፈ በአባቷ በኩል ከነገደ ይሁዳ የምትወለድ ሲሆን በእናቷ በኩል ደግሞ ከነገደ ሌዊ ትወለዳለች። እመቤታችን ድንግል ማርያም ከመጸነሷና ከመወለዷ በፊት የአምላክ እናት እንድትሆን ከሰው ዘር በአምላክ ሕሊና የተመረጠች መሆኑን በብሉይ ኪዳን ዘመን ታላላቅ ነቢያት ትንቢት ተናግረውላታል።

አባታችን አዳምና እናታችን ሄዋን በምክረ ሰይጣን ተታለው በኀጢአት በወደቁ ጊዜ በነፍስም በስጋም መርገመ ነፍስና መርገመ ሥጋ ተፈርዶባቸው በመንጸፈ ደይን በወደቁ ጊዜ በፍጥረቱ የማይጨክን መሐሪና ቸር የሆነው አምላክ ከልጅ ልጃቸው ተወልዶ እንዴት እንደሚያድናቸው ቃል ሲገባላቸው “በአንተና በሴቲቱ መካከል በዘርህና በዘርዋ መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፣ እሱ ራስህን ይቀጠቅጣል አንተም ሰኮናውን ትቀጠቅጣለህ” ዘፍ 3፥15 ላይ የተናገረው ቃልኪዳን የተፈጸመው በድንግል ማርያም እና ከእርሷ በተወለደው መድኅኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው (ገላ፥4)

ነቢዩ ኢሳያስም ስለ ዘር ኅረጓና ስለ ድንግልናዋ (ቅድስናዋ) በሚመለከት የትንቢት መልእክት ተናግሯል፦ 

“የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደሰዶም በሆን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር” ብሏል። ኢሳ 1፥9

“ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል ከሥሯም ቁጥቋጦ ያፈራል” ኢሳ 11፥1

“እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” አምላክን በድንግልና እንደምትወልድ ትንቢት ተነግሯል ኢሳ7፥14

የድንግል ማርያምን የጽንሰቷን ነገር እንደሚከተለው እንመለከታለን

ቅድመ አያቶቿ ቴክታና በጥሪቃ ይባላሉ። ከሃብታቸው ብዛት የተነሳ ይህ ቀረሽ የማይባሉ ባለጸጎች ነበሩ። የወንድና የሴት አገልጋይ፣ የቀንድና የጋማ ከብቶቹ፣ ወርቅና ብሩ ብዛት ስፍር ቁጥር እንደሌለው በቤተክርስቲያን ታሪክ ተመዝግቧል። ነገር ግን በዚሁ የሥጋ ሃብት ከብረውና ዝነኛ ሆነው የሚኖሩት ቢሆንም፤ ስም የሚያስጠራ ሃብቱንና ንብረቱን የሚወርስ በእግራቸው የሚተካ ልጅ አልወለዱምና አብዝተው ያዝኑና ወደ ፈጣሪ ይጮሁ ነበር። በሁሉ ነገር በበረከት አትረፍርፎና ምድራዊ ሃብቱን አብዝቶ የተሰጣቸው ፈጣሪ ልጅ የነሣቸው ለምን እንሆነ ሁል ጊዜ በፈጣሪያቸው ፊት እያለቀሱ ሕገ ጋብቻቸውን ጠብቀው ሲኖሩ አንድ ቀን በሌሊት በጥሪቃ በሕልሟ ድንቅ ነገር አየች። የሕልሟ ምስጢርም ነጭ እንቦሣ ከበረታቸው ስትወጣ እንቦሳይቱ እንቦሣ እየወለደች እስከ 6 ጊዜ ከደረሰች በኋላ ስድስተኛዋ ጨረቃ ወለደች ጨረቃም ፀሐይን ስትወልድ አየች። የሕልሟን ምስጢር ለመረዳት በዘመናቸው ወዳለው ሕልም ወደሚተረጉም ሰው ሲጠይቁ ሕልም ተርጓሚውም ደግ ልጅ እንደሚወልዱ የጨረቃው ነገር ከፍጡራን በላይ የከበረች ልጅ እንደሚወልዱ እሷም ድንግል ማርያም እንደሆነች ከተነገራቸው በኋላ የፀሐይ ትርጓሜ ግን አልተገለጸልኝም ብቻ ከሁሉ በላይ የከበረ ትውልድ እንደሚሆን ነገራቸው።

በዚህ መሠረት የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ስለነበረ ሄኤማን የተባለች ልጅ ወለዱ፣ ሄኤማን ዴርዴን ፣ ዴርዴን ቶናን ፣ ቶና ሲካርን ወለዱ ፣ ሲካር ሄርሜላን ፤ ሄርሜላ የድንግል ማርያም እናት ሀናን ወለደች። እናታችን ቅድስት ሀናም መካንነቱ በዘር መጥቶባት ልጅ ባለመውለዷ በእጅጉ ታዝንና ታለቅስ ነበር። በብሉይ ኪዳን ዘመን በእስራኤል ማህበር ዘንድ ያልወለደ ሰው በእግዚአብሔር የተጠላና የተረገመ እንደሆነ ይታመን ነበር። ወደ ቤተ እግዚአብሔር በሄደች ጊዜ ከማህበሩ ተለይታ ትገለል ነበር። ኢያቄምና ሃና ምድራዊ ሃብትና ንብረት አጣን ብለው ሣይጨነቁ እንኳንስ በአርአያውና በምሣሌው ለፈጠረው ለሰው ልጅ ቀርቶ ለአራዊትና ለእንስሣት ለሁሉም ፍጥረታት ዘር ሣይከለክላቸው አምላክ እኛን ለምን ትውልድ እንድንተካ አልፈቀደልንም በማለት ሃዘናቸውና ለቅሷቸው እጥፍ ድርብ ሆኖ በየጊዜው በእግዚአብሔር ፊት እየቆሙ በልጅ እስኪጎበኛቸው በጾምና በጸሎት ይጠይቁት ነበር።

ከዕለታት አንድ ቀን ኢያቄምና ሃና በየራሳቸው ሕልምን አዩ። የኢያቄም መቋሚያ አፍርታ ፍጥረት ሁሉ ፍሬዋን ሲመገባት፣ ሃና ደግሞ ነጭ ርግብ ሰባቱን ሰማያት ሰንጥቃ በማህሐኗ ስታድር ተመለከተች። ሁለቱም ያዩትን ሕልም ሕልምን ለመተርጎም የእግዚአብሔር ፀጋ ያለበት ተርጓሚ ከእነሱ ዘንድ እጅግ የተከበረች ልጅ እንደምትወለድ ነገራችው።

በዚህ መሠረት ኢያቄምና ቅድስት ሀና ልጅ እንደሚወልዱ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ተረድተው ወደቤታቸው ደስ እያላቸው ከተመለሱ በኋላ በዚያው ሌሊት ነሐሴ 7 ቀን ድንግል ማርያም ተጸንሣለች። ቅድስት ሀና ገና ጽንሱ በማህፀኗ እያለ በእርጅና ዘመኗ በመጸነሷ የተደነቁ ዘመዶችና ወዳጆቿ ሁሉ ወደ እሷ እየመጡ እንኳንስ እግዚአብሔር በልጅ ጎበኘሽ እያሉ የፈጣሪን ሥራ እያደነቁ በሆዷ ያለውን ጽንሱን ሲነኩ ዓይን አብርቷል፣ የሞተ ዘመዷን እያለቀሰች በሆዷ ስትነካው እንደተነሣ፣ እና ሌሎች ብዙ ተአምራት እንደተደረጉ በነገረ ማርያም መጽሐፍ እና ስለ እመቤታችን በሚነገር ታሪክ ውስጥ ተጽፎ ይገኛል።

የድንግል ማርያም መጸነስ ከእግዚአብሔር ፈቃድ የተነሣ እንጂ በባልና ሚስት ልማድ ፈቃደ ሥጋቸው አነሣሥቷቸው የተፈጸመ ምስጢር አይደለም።

ለዚህም ነው ታላቁ የብህንሣ ኤጲስ ቆጶስ አባ ሕርያቆስ “ድንግል ሆይ በሥጋዊ ሀሣብ የተጸነሽ አይደለሽም ከእግዚአብሔር በሆነ የሕግ እሩካቤ እንጂ” በማለት በቅዳሴ ማርያም መስክሯል።

የድንግል ማርያም አማላጅነት ከሁላችንም ጋር ይሁን

ነገረ መስቀል

👉🏾👉🏾👉🏾 የመስቀሉ ነገር (#መስቀል)

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገፅ  የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምትከታተሉ አባላቶቻችን ሁሉ፤ ከላይ በርዕሱ በተጠቀሰው ትምህርት መነሻነት ‘በሞት የተገለጸ ፍቅር”‘ መጽሐፍ ውስጥ ያለውን ጠቃሚ ትምህርት ልከንላችኋልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትረዱት ዘንድ አደራ እንላለን።

የመስቀሉን ነገር ስንናገር በአንድ ወቅት የአግዚአብሔር መልአክ የተናገረውን ማስቀደም ተገቢ ነው። በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ የነበረች አንዲት እሌኒ የተባለች ክርስቲያናዊት ሴት የመስቀሉ ነገር እጅግ አስጨነቃትና ሱባዔ ስትገባ የተገለፀላትን የአግዚአብሔር መልአክ አንድ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡ የመስቀሉን ነገር። መልአኩ ግን የመለሰውን መልስ ኢትዮጵያዊው ደራሲ ቅዱስ ያሬድ ሲገልጸው ‹‹ወይቤላ መልአከ ዕፁብ ነገሩ በዕንተ መስቀሉ – መልአኩም መልሶ የመስቀሉ ነገር ድንቅ ነው›› አላት ብሎ ነበር የገለጸው። ረቂቃኑ ጠላቶቻችን አጋንንት ድል የተነሡበት ብቸኛ መሣሪያ ሲሆን እንደምን አይደንቅ? የዓለም ሰላም የታወጀበት የእግዚአብሔር ሰገነት መስቀል አይደንቅ ማን ይድነቅ! የሁላችን መራርነት የጣፈጠበት፤ ሞት ራስ አራሱን ተቀጥቅጦ የተገደለበት አይደል። ለምን አይገርም! የመስቀሉ ነገር ከዓለመ መላእክት ይጀምራል። ሰው ከመፈጠሩ በፊት የመስቀሉ ነገር በሰማይ ተሰብኮ ነበር። በሰማይ የተደረገው ያ የመጀመሪው ሰልፍ በድል የተጠናቀቀው በመስቀል መሣሪያነት ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የመላእክቱ የዘንጋቸው ጫፍ የመስቀል አምሳል ያለበት ሆነ፤ ለምስጋና በሚቆሙበት በጽርሐ አርያምም በመስቀል አምሳል ክንፎቻቸውን ዘርግተው በመቆም ማገልገል የተለመደ እየሆነ ሔደ። ይህን አቋቋማቸውን ሲገልጽ ቅዱስ ኤፍሬም ‹እስመ ለዘውስተ ሕፅንኪ ይሴብህዎሥ መላእክት …ይሰፍሁ ክነፊሆሙ -መላእክት ክንፎቻቸውን እየዘረጉ በመሐል እጅሽ የያዝሽውን በክንድሽ የታቀፍሽውን ያመሰግኑታል ብሎ ነበር፡፡››

በመስቀሉ የእኛን ያክል ድኅነት ባያገኙበትም ጠላት ሰይጣንን ድል ያደረጉበት ስለሆነ ዛሬም ለዘዓለምም በመስቀል አምሳል ደምቀው ይታያሉ፡፡ የሰው ልጅም ገና ሲፈጠር ጀምሮ ነገረ መስቀሉን ሊያዘክር በሚችል ሁኔታ ነው የተፈጠረው።፡ ሰማያውያን ከሆኑት ከመሳእክት፤ ኢነባብያን ከሆኑት ከእንሰሳት፤ ግኡዛን ከሆኑ ብዙ ፍጥረታት ለይቶ ለሰው ብቻ የመስቀል ቅርፅ ሰጥቶ መሥራቱ ሕይወቱ በመስቀል የተመሠረተ መሆኑን ያጠይቃል፡። ከተፈጥሮው ጀምሮ ነበር መስቀሉን ማጥናት የጀመረው፡፡ የሰው ልጅ፤ ከገነት በወጣበት በዚያችኛዋ ዐርብ በትክሻው መስቀሉን ተሸክሞ ነው፤ ወደዚህ ዓለም የመጣ፡፡ ይህ ዓለም ያለመስቀል ጥንትም ይሁን ዛሬ የሚመች አኗኗር የለውም።

የመጀመሪያው ሰው ከትክሻው አውርዶ መስቀሉን የሚሸከም ልጅ እስኪያገኝ ድረስ መክራ መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ዓለም መጣ ይህ ዓለም ለመስቀል ጥንትም ቢሆን ዘንድሮ የሚመች አኗኗር የለውም፡። የመጀመሪያው ሰው ከትከሻው አውርዶ መስቀሉን የሚሸከም ልክ እስኪያገኝ ድረስ መከራ መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ዓለም መጣ፡። ብዙ ልጆችን ለብዙ ሺህ ዘመናት የወለደ ቢሆንም አንድም እንኳን የእርሱን ሸክም ሊያስወግድለት የተቻለው አልነበረም። ሁሉም እያንዳንዱ የራሱን ሸክም ተሸክሞ ይንገዳግድ ነበር እንጂ ‹አናንት ሸክማችሁ የከበዳችሁ ወደኔ ኑ እኔ አሳርፋችሁ አለሁ›› ብሎ የሚጣራው የአዳም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ አስኪመጣ ድረስ በዕዳ ያልተያዘ አልነበረምና።

የማንን ዕዳ ማን ይከፍላል፡፡ የዕዳ መክፈያው መስቀል ነበርና አማናዊው መስቀል አስኪተከል ድረስ የሰው ልጆች ነገረ መስቀሉን በተለያየ ኅብረ አምሳልና ኅብረ ትንቢት ሲያስተጋቡት ለ5,500 ዘመናት ይኖሩ ነበር፡ በተለያዩ ዘመናት የተነሥ አበው ነገረ መስቀሉን አመስጥረው የተናገሩት ሲሆን ለመረዳት እንዲያመቸን በዘመን ከፋፍለን በጥቂቱ እንመልክት፡፡

1ኛ: ከአዳም እስከ ሙሴ፣

ከሙሴ-ልደተ ክርስቶስ፤ ከገነት እስከ ግብጽ ፤ ከግብጽ አስከ ቤተ ልሔም ይህ ዘመን በዕድሜ ሲሰላ ወደ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዓመት ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል፡፡ በዚህ ዘመን ነገረ መስቀሉ ከተነገረባቸው ነገሮች መካከል ፦

1. ዕፀ ሕይወት

ዕፀ ሕይወት አሰቀድሞ በገነት የተተከለ አዳም ብላም አትብላም ያልተባለው ዕፅ ነው፡፡ አባታችን አዳም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ቢጠብቅ ኑሮ ሺህ ዓመት ከኖረ በኋላ ዕፀ ሕይወትን ተመግቦ እየታደሰ ሊኖር ነበር፡፡ስለዚህ ሞትም ሕይወትም በመብል ምክንያት የተሰጠ እንደሆነ እንመለከታለን፡፡ አዳም አትብላ የተባለውን ዕፅ በለስ ከበላ በኋላ እጁን ወደ ዕፀ ሕይወት እንዳይመልስ ለዘላለሙም ሞት እንዳይገዛው እግዚአብሔርን ገነትን በኪሩቤልና በምትገለባበጥ ሠይፍ አስጠበቀ፡፡

በአዲስ ኪዳን ዕፀ ሕይወት ሆኖ የተሠጠን በቅዱስ መስቀሉ ላይ የተቆረሰው ቅዱስ ሥጋና የፈሰሰው ክቡር ደም ነው። ይህንን ሁኔታ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ‹‹ዳግመ ከፈለነ ንብላዕ እም ዕፀ ሕይወት ዘውእቱ ሥጋሁ ለክርስቶስ፤ ከዕፀ ሕይወት አንበሳ ዘንድ አደለን፤ እርሱም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው›› በማለት የተናገረው ነው።፡፡

በመስቀሉ የተገለጠ በዚህ ጽሑፍ ቆጥረን ዘርዝረን ልንገልጠው የማይቻል ብዙ ምሥጢር አለ፡፡ እነ ለንጊኖስ የባሕርይ አምላክነቱን የተረዱት በመጽሐፍ ስሙ ያልተጠቀሰው የመቶ ዐለቃ የእግዚአብሔር ልጅነቱን የመሰከረለት፡፡ (ማቴ. 27፥54) እነ ጴላጦስ ጻድቅ ባሕርዩውን አውቀው ያሳውቁለት በዚሁ በመስቀል ተግባሩ ነበር፡፡በሰላሳ ሦስት ዓመት የምድር ላይ ቆይታው ያልገለጠውን የማንነቱን ምሥጢር የገለጠው በዕለተ ዐርብ በመስቀል ዙፋኑ ላይ በነበረ ጊዜ ነው።፡ መጋረጃው ተነሥቶ ነበርና ማየት የሚችሉ አጥርተው ያዩበት ቀን ነው፡፡ ያኔ በመስቀል በተገለጠበት ሁኔታ ደግሞ ላይገለጥ አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ ተገለጠ፡፡

ይህን የክብር መገለጫ ዙፋን ጊዜው እስኪደርስ ድረስ በኪሩቤል እንዲጠበቅ አደረገው፡፡ ፅፀሕይወትም መባሉ ፍሬ ሕይወት የሚባል ክርስቶስን ይዞ የተገኘ የሕይወት ዛፍ በመሆኑ ነው። ይህንን መነሻ በማድረግ ነው፡ ሊቃውንቱ ‹‹ዝንቱ መስቀል ቤዛነ መድኃኒትነ -ይህ መስቀል መድኃኒታችን ነው›› በማለት ያመሰገኑት ሌላውም ደራሲ ‹ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል – በቀራንዮ መድኃኒት መስቀል ተተከለ›› ብሎ ነበር፡፡ በየጊዜው የተነሡ ሊቃውንት ሁሉ መስቀልን በዚህ ሁኔታ መድኃኒትነቱን ይገልጡለት ነበር፡፡ ለሁሉም ግን መነሻው ‹የሕይወት ዛፍን ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የእሳት ሰይፍን በኤድን ገነት በሥተምስራቅ አስቀመጠ›› (ዘፍ. 3፥24) የሚለው ቃል ነው፡፡

2. የያዕቆብ መሰላል

ከላይ እንደተመለከትነው አግዚአብሔር በጥበቡ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ ማስጠበቁ ለአባታችን አዳም ተስፋ መስቀልን ሲያበሥረው መሆኑን ሊቃውንት ይስማማሉ፡፡ ጨርሶ ማጥፋት እየቻለ አላጠፋውም፤ እንዳልነበረ ማድረግ እየቻለ አላደረገውም፤ ይልቁንም ለሰው ልጆች ተስፋ ይሆን ዘንድ በመላእክት አስጠበቀው እንጂ።፡ ይሄን ተስፋመስቀል በልቡናው ትከሻ ላይ የተሸከመው ሰው ይኖር የነበረውም በመስቀል እንደ ነበር ታላቁ መጽሐፍ ምስክር ነው።

ዓለማችን ሕልውናዋ ከተረጋገጠ ከሦስት ሺህ ዓመት በኋላ አንድ ሰው በእናትና በአባቱ ፈቃድ ከትውልድ መንደሩ ከቤርሳቤህ ወጥቶ ወደ ካራን ይሔድ ነበር።

የመሔዱ ጉዳይ የአባቱን ፈቃድ ለመፈጸም በአርሱም ምክንያት ያልተባረከው የላባ ቤት እንዲባረክ ሲሆን ከበስተጀርባው ግን የጠላት ሤራ አለበት፤ የወንድሙ የኤሳው። በአርሱ ምክንያት በመሰደዱ ለስደቱ እንዳንድ ምክንያት ይጠቀሣል፡፡ እርሱ ግን ጠላቱን በትዕግሥት ድል ለመንሣት እሺ ብሎ በጠላት ዔራ የተሰደደ ሰው ነው፡፡ እግዚአብሔርም በመንገዱ ሁሉ ይመራው ነበር።፡ በአባቱ ፈቃድና ቡራኬ በጠላቱም ክፉ ምክር ፀሓይ እስክትጠልቅ ድረስ በመክራና በለቅሶ የተጓዘባት ከእናቱና ከአባቱ የተለየባት ያች ቀን ዐርብ ነበረች፡፡ በፀሐይም መጥለቅ ውስጥ ቅዳሜ ማታ የመስቀል አምሳል በሆነው በመሰላል ላይ ሆኖ እግዚአብሔር ተገለጸለት፡፡

ያች ሌሊት ለያዕቆብ ልዩ ሌሊት ነበረች፡። በጨለማ እንጂ በብርሃን አልተገለጠለትም፡፡ አማናዊው የሰው ልጆች ብርሃን ወደ ዓለም ገና አልመጣም ነበርና።፡ ያለፈችው ፀሓይ ስትጠልቅ፤ የምትመጣዋ ቀን ፀሓይ ሳትወጣ በመካከል ላይ መገለጡ ሰው በተፈጥሮው ከእግዚአብሔር ከአፉ እስትንፋስ ተከፍላ የተሰጠችው ሕይወቱ በሞት የጠለቀችበት፤ በሐዲስ ተፈጥሮ በአምላክ ሰው መሆን የምትሰጠው አዲስ ሕይወትም ሳትወጣ የነበረችበት ዘመን መሆኑን ያመለክታል ፡፡

ኢትዩጵዮዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በሥርዐተ ማኅሌቱ የቅዳሜ ዜማዎቹ ላይ በአብዛኛው በመስቀሉ ምሥጢር የተሞሉ እንዲሆኑ ማድረጉ ለያዕቆብ በተስፋ የተገለጠው መስቀል መሆኑን ለመግለጽ ነው። (ቅዳሜ ቅዳሜ ቅንዋት ስለሚበዛ ነው) መሰላሉ ከተንተራሠውድንጋይ ላይ ተተክሏል፤ ከላይ ንጉሥ ተቀምጦበታል፣ የሰማይ መላእክትም በላዩ ላይ ይወጡበታል ይወርዱበታል። ያዕቆብ ግን አሁንም በከባድ ጨለማ ውስጥ እንደተኛ ነው፡፡ ምንም መሰሳሉ ከምድር እስከ ሰማይ ደርሶ ቢተከልም፤ እግዚአብሔርም ቢገለጥለት ጊዜው ደርሶ ፀሓይ በጊዜዋ እንደጠለቀች በጊዜዋ እስክትወጣ ብርሃን ለማየት አልታደለም ነበር ጊዜው ገና ነበርና።

ከምድር ጀምሮ ሰማይን ተጠግቶ የቆመው ያ መሰላል በቅዱስ መስቀል ይመሰላል፡፡ ከምድር እስከሰማይ ደርሶ መታየቱ በደመ መለኮት የከበረ ልዕናውን ያመለክታል፡፡ በላዩ ላይ ከተቀመጠው ንጉሥ ክብር የተነሣ የሰማይ መላእክት ሁሉ ያለማቋረጥ በመሰላሉ መመላለሳቸው ንጉሣችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ባደረገው ውሎ ሰውና መላእክት እርቅ መፈጸማቸውን መናገር ነው፡፡ እርሱ ሰላማችን ነውና በመስቀሉ በሰውና በመላእክት መካከል ፍቅር አንድነትን አደረገ=

በጨለማ ውስጥ የነበረው ሰው ያዕቆብ በኃጢአት ምክንያት የጨለመች ሕይወትና የጨለማ ቦታ ሲዖል የነበረችው የሁላችን አባት አዳምን ይመስላል። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር በጨለማ ውስጥ ቢሆንም እንኳን ሰውን ይረሳው ዘንድ አልፈለገም። ወደፊት ሊያደርጋት ያሰበለት የማዳኑን አሳብ ገለጸለት እንጂ: በመሰላል የተመሠለው መስቀል ያዕቁብ የተንተራሰው ድንጋይ ላይ መተከሉ የጌታ መስቀልም የአዳም የራሱ ቅል የተቀበረበት ቦታ ላይ የሚተከል መሆኑን አመላካች ምስጢር ነበር፡። በመስቀሉ ላይ የተቀመጠው ንጉሥ ያዕቆብን ዝም አላለውም፤ ለቀጣይ ሕይወቱ ጉልበት የሚሆን ቃል ኪዳን የገባለት በዚሁ ቦታ ነበር እንጂ: (ዘፍ. 28፥13-15) አማናዊው መሰላላችን ቅዱስ መስቀልም ለዘላዓለም ጸንቶ የሚኖር, ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ለሕዝቡ የገባበት ነው።፡ (ማቴ. 26+28) አዲሱ ኪዳን የተመሠረተው በራሱ በቅዱስ መስቀል ላይ ስለሰው በፈሰሰው ደም ነው፡።

ያዕቆብ የሰማዩን ምሥጢር በመሰላሉ አማካኝነት ከተመለከተ በኋላ በእንቅልፍ ውስጥ አለመቆየቱና አፈፍ ብሎ ፈጥኖ መነሣቱ ደግሞ ሌላው አስደናቂ የመስቀሉ ነገር ነው፡ በአማናዊው መስቀል ላይ ሆኖ ጌታ ደሙን ባፈሰሰ ጊዜ ከመስቀሉ ሥር የነበሩ ሙታን የመብረቅ ብለጭልጭታ ከሚፈጥነው በላይ ፈጥነው መነሣታቸውን የሚያመለክት አሳብን የያዘ ነው። ያዕቆብ ከተነሣ በኋላም ‹‹ይህ የሰማይ ደጅ ነው ከዚህ ላይ የአግዚአብሔር ደጅ ይሠራል›› ብሎ ነበር፡ በዚህም የእግዚአብሔር ቤት የሰማይ ደጅ ተብላ የምትጠራው ቤተክርስቲያን በመስቀል ላይ በፈሰሰው ንጹሕ ደም የምትመሠረት መሆኗን አና ከመሥራቾቿም መካከል ከእግረ መስቀሉሥር አፈፍ ብለው እንደያዕቀብ የተነሱ ቅዱሳን መሆናቸውን ለመግለጽ ነው።፡ አባታችን ያዕቆብ እንደመሰከረው አካባቢው የሚያስፈራ ግርማ ሞገስን የተጎናጸፈ ነበር ‹‹ይህ ቦታ አንዴት ያስፈራ›› የጠላትን ሽንፈትም በእውነት እግዚአብሔር ለባለሟሉ ያዕቆብ አስቀድሞ ከገለጠለት ምሥጢራት መካከል ይገኝበታል። ይህንን የያዕቆብን አሳብ ለመተርጎም በመጽሐፈ ኪዳን እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል ‹‹ፈርሃ ወደንገፀ ዲያብሎስ፤ ዲያብሎስ ፈራ ደነገጠ›› በመስቀሉ ዙሪያ ለአጋንንት የፍርሃት ድንኳን ተዘርግቶ ነበርና ያንን ለመግለፅ ነው ያዕቆብም ‹‹ይህ ቦታ እንዴት ያስፈራ›› ብሎ የተናገረው፡፡ በጠላት ምክር ያዕቆብ በአናትና በአባቱ ፈቃድ ከቤርሳቤህ ወደ ካራን ለመሄድ ተገደደ።

ጌታም በባሕርይ አባቱ ፈቃድ ወደዚህ ዓለም በፈቃዱ መጥቶ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ተወለደ፡፡ ያዕቆብ በመንገዱ የተሳለው ሥዕለት ደግሞ ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ልዩ የምሥጢር ሙዳይ ያደርገዋል: ‹‹አግዚአብሔር ከአኔ ጋር ቢሆን በምሔድበትም በዚህች መንገደ ቢጠብቀኝ የምበላውን እንጀራ፤ የምለብሰውን ልብስ ቢሰጠኝ ወደ አባቴ ቤትም በደህና ቢመልሰኝ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል› (ዘፍ. 28፥+
20-21) ብሎ ነበር የተሳለው። እግዚአብሔር ሰው የመሆኑ ምሥጢር ከሩቅ እየታየው ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ፤ ባሕርያችንን ባሕርይ አድርጎ የመገለጡ ነገር እየተገለጠለት ‹‹አግዚአብሔር ከኔ ጋር ቢሆን›› ብሎ ተናገረ ይህ ምኞቱ ሲፈጸም አግዚአብሔር ከያዕቆብ ቤት ተወለደ፤ አማኑኤልም ተብሎ ተጠራ። ይህንም ቢተረጐሙት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። (ማቴ. 1፥23) እንዲህ ዐይነት ምሥጢር ያለው ባይሆንማ ኑሮ ከላይ ቁጥር 15 ላይ ‹‹እኔ ካንተ ጋር ነኝ››። አያለው አግዚአብሔር ከአኔ ጋር ቢሆን ባላለም ነበር፤ ከኔ ጋር ሆነ ይል ነበር እንጂ፡። በጣም የሚደንቀው ግን የምበላውን ምግብ፣ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ ማለቱ ነው፡፡ ምግብ ያለው ሥጋውን ደሙን ሲሆን ልብስ የሚለው ደግሞ ልጅነትን ነው፡። ሁሉም መሰላሉ በራእይ ከተገለጠለት በኋላ መነገራቸው ሥጋውና ደሙ፤ ልጅነት ከመስቀል በኋላ የተሰጡ የፍቅር ስጦታዎች መሆናቸውን ለመናገር ነው፡፡

ወደ አባቴ ቤት በጤና ብትመልሰኝ ማለቱም ከመስቀል በኋላ ሰው ወደ አባቱ ወደ አዳም የቀደመ ቤት ገነት መንግሥተ ሰማያት መመለሱን ለማጠየቅ ነው።፡ (ሉቃ. 23፥43) ‹‹አግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል” ማለቱ ደግሞ ጌታ ከተሰቀለ በኋላ በተመሠረተችው ቤተክርስቲያን አምልኮተ አግዚአብሔር ጸንቶ መኖሩን ለመናገር ነው:፡፡ እግዚአብሔር በአንድነቱ በሦስትነቱ የተመለከው በሰማያውያንና በምድራውያን ድምፅ በአንድነት የተቀደሰው ጥል በጌታ መስቀል ከተገደለ በኋላ ነው፡፡ (ኤፌ. 2፥14) በዚህም ምክንያት ለዘለዓለም የያዕቆብ አምላክ እየተባለ ሲጠራ ይኖራል። የተሳለው ስለት እንደተፈጸመ ለማሳየት ጌታችን በዚህ ምድር በነበረ ጊዜ ‹‹የአብርሃም ፤ የይስሐቅ፤ የያዕቆብ አምላክ እኔ ነኝ›› ብሎ ነበር።፡ (ሉቃ. 22፥31) ስንዘምርም እንዲህ ማለትን እናዘወትራለን ‹‹በረዳን በእግዚአብሔር ደስ ይበለን ለያዕቆብ አምላክም እልል በሉ›› (መዝ80፥1)

የመስቀሉ ነገር

(ክፍል 3)👆👇

3. የእግዚአብሔር በትር

እስራኤል በአርባ ዓመት ውስጥ ካደረጋቸው ወደ አርባ ሁለት የሚጠጉ ጉዞዎች መካከል አንዱ በረፊደም የተደረገው ጉዞ ነው፡። በዚህ የአስራኤል ጉዞ ወቅት የተከሰተ አንድ ቸግር ነበር እርሱም የአማሌቅ በጠላትነት መነሣት ነው፡የተጀመረው የከነዓን ጉዞ አይደል! ያለ ጠላት ተቃውሞ አልጋ ባልጋ ይዘለቃል ተብሎ አይታሰብም። በጎ መንገድ ነውና፡፡ ሁልጊዜ አግዚአብሔር ባዘዘን መንገድ በምንጓዝበት ጊዜ ሁሉ ሊቋቋመን ባይችልም ለጉዞው አለመሳካት ግን ጠላት የተቻለውንሁሉ እንደሚያደርግ እሙን ነው፡፡

ያ ጉዞ ምንም እንኳን እግዚአብሔር መና እያወረደ፤ በሰባት ደመና እየጋረደ፤ ከዓለትና ጭንጫ ላይ ውኃ እያፈለቀ የሚመራው ጉዞ ቢሆንም ከጠላት እይታ ግን መሰወር አልቻለም፡፡ለሌሊቱ የብርሃን ምሰሶ በመካከላቸው የተከለ፤ ቀን በጉዞአቸው የደመና ድንኳን የዘረጋ፣ በደመና አቁማዳ ቋጥሮ፣ በነፋሳት ክንፍ ጭኖ ይመግባቸው የነበረ እግዚአብሔር እነርሱን ከጠላት እይታ እንዲሰወሩ ማድረግ የሚሳነው ሆኖ አይደለም። ኤልያስን ከኤልዛቤል፤ ኤልሳዕን ከሶርያውያን ሰዎች ሰውሮ ሲያድን አይተነዋልና።

ይልቁንም የሚወርሱት አገር ዛሬ እኛ ለምንወርሳት መንግሥተ ሰማያት አምሳል መርገፍ ነውና በመከራ ባልተፈተነ እምነት ልትወረስ አንደማትችል የሚያመለክት ነው። ‹‹በብዙ ድካምና መከራ ወደ አግዚአብሔር መንግሥት እንገባ ዘንድ አለን›› እንዲል (የሐዋ.ሥራ. 14፥22)። በጉዞው ሁሉ ከባድ የሚመስሉ ፈተናዎች የገጠሙት ቢሆንም አስራኤልን የሚመራው እግዚአብሔር ደግሞ ከጦርነቱ የማምለጫውን መንገድ ሳይጠቁማቸው አላለፈም፡፡

ሙሴ በዋናነት ለሚደርስበት ችግር ሁሉ መፍትሔ ያመጣለት ዘንድ በጉዞው ሁሉ ከእጁ እንዳይለየው የታዘዘው አንድ ቅዱስ ዕቃ ነበር።፡ እርሱም ሙሴ መጀመሪያ እንደ እቃ እንኳን ይቁጥራት ዘንድ ያልፈለጋት የናቃት የእረኝነት በትሩ ናት።፡ በዚህች በትር ሙሴ ከአስራኤል በፊት በጎቹን በምድረ በዳ የሚጠብቃቸው የነበረው በዚያች በትር ዙሪያ ነበር። ከለመለመ መስክ ሲደርስ ከመካከላቸው በትሩን ተክሎላቸው እልፍ ብሎ ሥራውን ይሠራ ነበር፡፡ በጎቹም ከበትሩ ፈቀቅ ሳይሉ የሙሴን ከነርሱ ጋር መኖር በበትሩ አያረጋገጡ በበትሩ ዙሪያ ሠፍረው እስከማታ ይውሉ እንደነበር ታሪክ ምስክር ነው፡ በዚህች በትሩ ሁለቱን ጠንቋዮች ኢያኔስንና ኢያንበሬስን ድል አድርጎባታል፡ ከዓለት ላይ ውኃን አፍልቆባታል፤ የቀይ ባሕርን ከፍሉባታል፣ መጀመሪያ በጎችን በኋላም ሕዝቡን በደኅንነት መርቶባታል። በኋላም ነቢዩ ሙሴ ለዚች በትር ስም ሲያወጣላት የእግዚአብሔር በትር ብሎ ሰይሟታል፡፡ (ዘፀ. 17፥9) አሷን ምክንያት አድርጎ እግዚአብሔር ታላላቅ ተአምራትን አድርጎለታልና፡፡

የአግዚአብሔር በትር ተብላ የተጠራችው የሙሴ በትር በቅዱስ መስቀል ትመሰላለች፡፡ ሙሴ መንጋዎቹን እንዳሠማራባት ክርስቶስም ምአመናንን ወደ መሠማሪያቸው መንግሥተ ሰማት ያሠማራቸው በቅዱስ መስቀል መሆኑትን ያሳያል፡፡ የሙሴን ከእነርሱ ጋር መኖር በበትሩ አረጋግጠው ከበትሩ ሳይለዩ በበትሩ ዙሪያ ተሰብስበው ሳይንቀሳቀሱ መዋላቸው ምንኛ ድንቅ ነው፡፡ ምእመናንም በዚህ ዓለም መሰቀሉን ዐላማ፤ ወንጌሉን መሰማሪያ ከተማ አድርገው፤ የእግዚአብሔርን ከነርሱ ጋር መኖር በመስቀሉ አረጋግጠው ፀሓይ ሕይወታቸወ እስክትጠልቅ ድረስ በተስፋ መኖራቸውን አስቀድሞ ያበሥራቸዋል፡፡

ከዓለት ላይ ውኃ የተገኘውም በዚህች በትር በኩል ነበር፡። ይህም ከአማናዊውና ከመንፈሳዊው ዐለት ከኢየሱስ ክርስቶስ የዘለዓለም ሕይወት ውኃ የፈለቀው በመስቀሉ በኩል ስለሆነ ነው፡፡ መጀመሪያ በእጁ ባለችው በትር ድል መንሳትን ያስተማረው ባለቤቱ እግዚአብሔር ቢሆንም አሁን ግን ሙሴ ያለዚህች በትር ማሸነፍ እንደማይችል ተረድቷል። የአግዚአብሔርን በትር ከእጁ እንደማይለይ ለደቀ መዝሙሩ ለኢያሱ ቃል ገብቶለት ነበር። (ዘፀ. 17+9) ያለዚያማ ኃያሉ ያማሌቅ ጦር እንዴት ድል ሊነሣ ይችላል? ይህ ጦርነት ሰው በማንኛውም የሰልፍ ሜዳ ላይ ያለ እግዚአብሔር እርዳታ ማሸነፍ የማይችል ፍጡር መሆኑ የተረጋገጠበት መስክ ነው ።

ሲነጋ ለጦርነት የተከተተው የእስራኤል ጦር ምንም እንኳን በአሱ የጦር መሪነት አቅም ያላቸው ጎልማሶች የተካተቱበት የጦር ሜዳ ቢሆንም ማሸነፍ የሚችሉት ግን ሙሴ እጁን ከዘረጋላቸው ብቻ ነበር፡፡ ከተራራው ጫፍ ላይ ከፍ ብሎ የቆመው ሙሴ እጁን ሲዘረጋ የእስራኤል ጎልማሶች ያሸንፋሉ፡፡ እጁን ካጠፈው ግን እስራኤል ወደ ኋላው ይሸሽ ነበር። በዚህም ሙሴ ዓለም ከጠላቶቿ ከአጋንንት ውጊያ የምትድነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ እጁን ሲዘረጋ ብቻ መሆኑን አስቀድሞ ተስፋ መስቀሉን በመስበክ እስራኤልን አስተማራቸው፡፡ ሙሴ እጁን ሲዘረጋ አሮንና ሖር በቀኝና በግራው ይታዩ ነበር፡፡

በቀኝና በግራ ሆነው አሮንና ሖር መታየታቸው በቀኝና በግራው ሁለት ወንበዴዎች ሆነውለት እንጂ ጌታ ብቻውን የማይሰቀል መሆኑን ሲገልጥለት ነው፡፡ በሙሴ እጅ መዘርጋት አማሌቅ ድል አንደተነሣ ሁሉ ጌታችንም በመስቀል ላይ እጁን በዘረጋበት በዕለተ ዐርብ ሰልፈኞቻችን አጋንንት ድል ተነሥተውልናል፡፡ አለቃቸው ሳጥናኤል በመጽሐፈ ኪዳን ላይ መሸነፉን እንዲህ ሲል ነበር ያረጋገጠው፦ ‹‹መኑ ዝንቱ ሥጋ ለቢሶ ዘሞዐኒ፤ የሰውን ባሕርይ ተዋሕዶ ድል የነሣኝ ማነው?›› አማናዊ የጌታ መስቀል በቀራንዮ ተተክሎ ከመታየቱ በፊት በየጊዜው ለተነሡ ሰዎች በምሥጢር የተገለጠ እንጂ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አልነበረም፡፡

የመጀመሪያው የነሙሴ ጉዞ የተመራው የመስቀል አምሳል በነበረው የእግዚአብሔር በትር ነው፡፡ ሁለተኛውና በአማናዊው ሙሴ የሚመራው የመንግሥተ ሰማያት ጉዞም የሚመራው በመስቀሉ ነው ያለዚያች በትር የማይታሰብ እንደነበር ሁሉ ያሁኑ ጉዞም ያለመስቀሉ የሚታሰብ አይደለም፡፡ ለዚህ አይደል ታላቁ የቤተክርስቲያን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ስለመስቀል ሲዘምር እንዲህ ያለው፡ ‹‹መስቀል መልዕልተ ኩሉ ነገር፤ መስቀል ከሁሉም ነገር በላይ ነው፡፦› ከላይ እንደተመለከትነው በኦሪቱ ውስጥ ዜና መስቀሉ በሰፊው የተቀመጠ ቢሆንም እንደ ደመና ከከበቡን ብዙ ምስክሮቻችን መካከል ነገር ሁሉ በሁለትና በሦስት ምስክር ይጸናልና ይህን በዚህ ዘግተን ወደ አማናዊው ዜና መስቀል እንምጣ👇፡፡

ዜና መስቀል በቤተክርስቲያን

(ክፍል 4 ይቀጥላል)

ምንጭ፦ ‘በሞት የተገለጸ ፍቅር’ ገጽ 98-108
አዘጋጅ – ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ

ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንም ሼር ያድርጉ፡- https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q

👉🏾👉🏾👉🏾 የመስቀሉ ነገር (#መስቀል)

ዜና መስቀል በቤተክርስቲያን

(ክፍል 4)

ቤተክርስቲያን ከጉልላት እስከ መሠረቷ፤ ከቤተ መቅደስ እሰክ ዐውደ ምሕረቷ ከምትሰብካቸው ስብከቶች ዋናው ዜና መስቀሉ ነው= ማንኛውም የቤተክርስቲያን አገልግሎት በመስቀል ይጀምራል፡፡

ነነረ መስቀሱ በሐዲስ ኪዳን

ሐዲስ ኪዳን በተመሠረተባት በዚያች ሌሊት ሕጉ ይጸና ዘንድ የፈሰሰው እንደ ጥንቱ ሕግ እንደ ኦሪት የበግ ደም አይደለም፡። ስለ ብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የእግዚአብሔር በግ የክርስቶስ ደም በቀራንዮ ፈሰሰ እንጂ።፤ መሥዋዕት ሆኖ ከሚቀርብበት ከጥቂት ሰዓታት በፊት ሳይፈስ እንደፈሰሰ ሳይሠዋ እንደተሠዋ አድርጎ ነግህ በመልዕልተ መስቀል የሚሠዋው መሥዋዕት ይህ ነው ብሎ ሕጉን በሕግ ተካው፡፡ መሥዋዕቱ የሐዲስ ኪዳን እንጂ የብሉይ ኪዳን አልነበረም።፡ ክህነቱም የነ አሮን ዐይነት ሳይሆን ከዚያ ልዩ ነበር። ሐዲሱን መሥዋዕት በአሮጌው ድንኳን ማቅረብን አልወደደም።፡ አስቀድሞ በእጅ ያልተሠራችውን የሐዲስ ኪዳን ቤተ መቅደስ መሠረተ።፡ ቤተ መቅደሱንና መሥዋዕቱን ለሱ ሲያዘጋጅ መሠዊያውን ደግሞ አይሁድ አዘጋጁ:፡፡ እርሱም መሠዊያ የተባለው ቅዱስ መስቀል ነው።

ይህ መስቀል ሰባት ክንድ ከስንዝር እንደነበር ይነገርለታል፡፡ ሁለቱ ክንድ ወደ መሬት የገባ፤ አንዱ ክንድ ከእግሩ በታች ከመሬት በላደ የነበረ፤ አንዱ ክንድ ከራስጌው ላይ የነበረው ሲሆን ጺላጦስ አዴራ በሚባለው ቀኖት ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ የሚለውን ደብዳቤ ጽፎ የለጠፈበት ነው።፡ ሦስት ክንድ ከስንዝር የጌታ አካሉ ያረፈበት ነው፡፡ ይህን ሲደምሩት ሰባት ክንድ ከስንዝር ይሆናል፡፡ ሰባት ዓመት ከ47 ቀን አብሮን የነበረው ክብራችንን፣ ልጅነታችንን በማጣታችን ምክንያት የመጣብንን መከራ እንዳራቀልን እና የሰባት ዓመት ጸጋ ክብራችንን እንደመለሰልን ለማጠየቅ በሰባት ክንድ ከስንዝር መስቀል ተሰቀለ፡፡

ቤተ ክርስቲያኒቱ የተገኘችው ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ በተደረገው ፍኖተ መስቀል ነው።፡ በዚህ ጎዳና ላይ መስቀሉን ተሸክሞ ይሔድ በነበረ ጊዜ መኖሪያውን ጫካ ያደረገ የእነ እስክንድሮስና የሩፊኖስ አባት ስምዖን ቀሬናዊ ከጌታ ተቀብሎ መስቀሉን እንዲሸከምና ወደ ቀራንዮ እንዲሔድ አንዳስገደዱት መጽሐፍ ይነግረናል (ማር. 15+21) ለጌታ አዝነው አጋዥ ፈልገውለት አይደለም፡ መስቀሉን ከክርስቶስ ተቀብላ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለዘለዓለም ተሸክማው የምትኖር መሆኗን ለማሳየት ነው አንጂ። መስቀሉን የተሸከምነው እኛ ተገደን ነው እርሱ ግን በፈቃዱ ነው፤ አኛ ብንሸከምም እንኳን በገዛ ዕዳችን ሲሆን እርሱ ግን በምን አዳው!!

ልንወርሳት የምንሽታት የእግዚአብሔር መንግሥት ያለመከራ የምትወረስ ሆና ቢሆን ኖሮ ከአኛ አንዱም ስንኳ መከራ መቀበልን ባልመረጠ ነበር። አርሱ ግን መንግሥቱ በዚህ ዓለም ያልሆነች የዘለዓለም ንጉሥ ነው፡፡ መስቀሉን ተሸክመው እንደነገሡት እንደ ሐዋርያት ሳይሆን እርሱ ሲወለድም ንጉሥ ነበር (ማቴ. 2፥5)፡፡ የሁለቱ ልጆች አባት የሆነው አፍሪካዊው ሰው ስምዖን ተሸክሞት የነበረውን መስቀል የሁለት ልጆች (የአሕዛብና የቤተ እስራኤል) አባት ለነበረው ለአዳም ከመቃብሩ ላይ ወስደው አሸከሙት፡፡ መስቀሱ ስለሕያዋንና ስለሙታንም የተተከለ ነውና ቢሞትም መስቀሉን ከመሸከም ያገደው አንዳች የለም። ቤተ ክርስቲያንም ስንል የሙታንና የሕያዋን ሕብረት ማለታችን ነው። በአጸደ ሥጋና በአጸደ ነፍስ ላሉት ሁሉ አገልግሎት የምትሰጥ መንፈሳዊት ተቋም ነች። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለዘለዓለም ነገረ መስቀሉን ስትሰብክ ትኖራለች።፡ በጉዞዋ ሁሉ በተገኘው አጋጣሚ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት ትናገራለች፡፡ (ሉቃ. 24፥18) እርሱ እንደተናገረ (ሉቃ. 22፥20) ይህን ለመታሰቢያዬ ታደርጋላችሁ ብሎ፡፡

ለዚህ አምላካዊ ቃል የምትገዛው ቤተ ክርስቲያናችን ያለመስቀሉ ሕይወት የለም ብላ ታምናለች። ለፍጥረት ሁሉ ይሆን ዘንድ ሕይወት የመነጨው ከመስቀሉ ሥር ነውና፡፡ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ መንፈስ ቅዱስ በተዋሐደው አንደበቱ አንደ መሰከረው ሁል ጊዜም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ‹‹በመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ› ተብሎ ይዘምራል። በዐውደ ምሕረቷም ከጌታዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምህርት ከኔ ይራቅ ተብሉ ይሰበካል፡፡ በአጠቃላይ ቤተክርስቲያን ነገረ መስቀሉን በልዩ ልዩ መንገድ ትሰብከዋለች።

በሕንፃዋ ፡

ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የተለየ ሕንፃ ሁሉ ባንድ ነገር ልዩ ነው፤ በቅዱስ መስቀል። ሕንፃውን በመስቀል ምልክት በመሥራት ወይም በማንኛውም ዐይነት ቅርፅና መጠን ቢሠራም ከጉልላቱ ላይ የመስቀል ምልክት ማድረግ የተለመደ ነው፡። ይህም የሚደረገው ለሕንፃው ጌጥ እንዲሆን ተብሎ ሳይሆን ምእመናን ሁልጌዜ ሦስት ነገሮችን በሕይወታቸው መርሳት ስለሌለባቸው ያን ለማሳሰብ ነው፡

1. ዘወትር ምእመናን በሕይወታቸው ነገረ መስቀሉን እንዲሸከሙ

ሰውና እግዚአብሔር የሚገናኙበት መሥዋዕተ እግዚአብሔር የሚቀርብበት ቤተ መቅደሱ ዘወትር መስቀሉን ተሸክሞ መታየቱ የጌታ ቤተ መቅደስ ለመሆን የተሠራው የምእመናን ሰውነትም ዘወትር መስቀሉን ሳይሸከም መኖር የማይገባው መሆኑን የማያሳስብ ሕያው መምህር ነው:: ሕንፃው ያለመስቀሉ ምልክት ትርጉም እንደሌለው ሁሉ የምእመናን ልቡናም ያለጌታችን መስቀል ትምክህትና ኩራት የላቸውም [ገላ. 6፥14፤1ኛ ቆሮ. 3፥16)፡ ስለዚህም ሲበሉና ሲጠጡ፤ ሲወጡና ሲገቡ የመስቀሉን ምልክት ያሳያሉ፡፡ የመገልገያ ቁሶችን ሳይቀር ከመስቀል ጋር ያመሳስላሉ፡፡ የሚለብሱት ልብሳቸውን በመስቀል አምሳል ይጎናጸፋሉ። በዚህም በሥጋቸው ለሞትም ይሁን ለሌላ መከራ ከርሱ ጋር ለመሔደ መወሰናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

ከፍቅራቸው ጽናት የተነሣ ሰውነታቸውን በጥተው በእሾህ በመርፌ ወግተው የመስቀል ምልክት ይሠራሉ፡፡ መመኪያቸውም እንደመሆኑ መጠን አስደንጋጭ ነገር ሲገጥማቸው የማንንም ስም ከመጥራት በፊት የፈጣሪያቸውን ስም በማንሳት በእጆቻቸው የመስቀል ምልክት ይሠራሉ ምእመናን ሁሉ የተገኙት ከመስቀሉ ሥር ነውና ያለመስቀሉ የሚያከናውኑት አንዳችም ነገር የላቸውም በጸሎታቸውም ጌዜ ‹‹መስቀል ኃይልነ››፤ ‹‹መስቀል ፅንጽነ››፤ ‹‹መስቀል ቤዛነ›፤ “መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ›› ብለው ያመሰግናሉ:

“ኀይልነ›› ማለታቸው እርሱ የእግዚአብሔር ጎይል ስለሆነ ነው። (1ቆሮ. 1+18) ‹‹ፅንዕነም›› ማለታቸው ሰማዕታትን ለደም፤ ፃድቃንን ለገዳም፣ ሐዋርያትን ለስብከት፣ ሊቃውንትን ለድርሰት እንዲተጉ፤ ራሳቸውን እንዲለዩ ያደረጋቸውና ያበረታቸው ዛሬም ላሉ ምእመናን ብርታታቸው እርሱ ነውና መስቀሉ ብርታታችን ነው ሲሉ ይኖራሉ።፡ “ቤዛነ›› ማለት፡ዲያብሎስ የሞተበት፣ ሰው ሕያው ፍጥረት የሆነበት፤ መላእክት ከሰው ልጆች ጋር የእርቅ ኑሮ የጀመሩበት ስለሆነ ነው። (ኤፌ. 2,16)

(ክፍል 5 ይቀጥላል)👇

👉🏾👉🏾 የመስቀሉ ነገር (#መስቀል)

ዜና መስቀል በቤተክርስቲያን

(ክፍል 5)

መከራው ፈውሳችን፣ ቁስሉ መድኃኒታችን ነው። (ኢሳ. 53፥5) ታዲያ ለዚህ ነው መስቀል ቤዛነ ብለን የምንናገረው እንዲያውም አባቶቻችን (በዕብ. 2፥7) ያለውን ‹‹የክብርና የምስጋናን ዘውድ ጫንህለት›› የሚለውን ሲተረጉሙ የክብርና የምስጋና ዘውድ የተባለው መከራው ነው ብለውናል፡፡ እኛን ያከበረ ነውና የክብር ዘውድ ተባለ አዎ! መስቀሉ ክብራችን ነው: ‹‹መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ›› የሥጋችን የነፍሳችንም መድኃኒት የጌታችን መከራ መሆኑን ለማስረዳት ይደጋግመዋል።

በሥጋችን ሙስና መቃብር፣ በነፍሳችን ርደተ ገሃነም የቀረልን ከመስቀሉ የተነሣ ነውና፡፡ አንዳንዶቹ ሳይገባቸው ይህ ጸሎት ትክክል እንዳልሆነ ይናገራሉ፡፡ ግን እኮ የሚያደርጉትን አያውቁም እንጂ ‹በአርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን›› ብለው መዘመራቸው አልቀረም፡፡ በአርሱ ቁስል ማለት በመከራው ማለት አይደል? በእርሱ መከራ ማለት ደግሞ በመስቀሉ ማለት ነው፡ ስለዚህ ‹‹መስቀል ኀይልነ ብሎ መጸለይ አስፈላጊ አንደሆነ ማሳየት እፈልጋለሁ፡፡ ‹”በመስቀሉ ቤዘ ወነ አሞት ባልሀነ፡በመስቀሉ አዳነን ከሞትም እጅ አስጣለን።”

2. ውለታውን

ክርስቲያን የሚሞተው ጌታ የዋለለትን ውለታ የረሳ እንደሆነ ነው፡፡ ክርስትና የከበዳቸውን ሰዎች ያየን እንደሆነ የዕለተ ዐርብን የጌታ ሥራ ከጭንቅላታቸው አውጥተው የጣሉ ናቸው።፡ ርቀው ለተመለከቱት መስቀሉ ከባድ ነው፡፡ ቀርበው ከተመለከቱት ግን ከዓለም ሸክም ይልቅ ቀላል ነው፡፡እርሱ አንደተናገረ ‹‹ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀላል ነው፡፡›› (ማቴ. 11፥30) ብሎናልና፡፡ ርቀው ለሚመለከቱት ግን ከባድ ከመሆኑም በላይ መስቀሉን ሳይሸከሙ፤ የቀራንዮን ዳገት ለመውጣት የማይቻል በመሆኑ ከክርስቶስ ፍቅር ለመለየት ሰይጣን ከባድ ፈተና በነሱ ላይ ማምጣት አይጠበቅበትም፡፡ እንደቀድሞው ነገሥታቱን አስቆጥቶ፣ መናፍቃትን አነሣሥቶ በእነርሱ ላይ መከራ ማጽናት አይጠበቅበትም፡፡ በተናቀችው የገረዲቱ ቁጣ ጌታን አላውቀውም እንዲሉ ማድረግ ይችላል፡፡ (ሉቃ. 22፥57) አያችሁት መስቀሉን ሳይሸከሙ ጌታን መከተልና ወደ ቀራንዮ መውጣት አደጋ አለው፤ ያለመስቀል ምንም አይነት ጉዞ ማድረግ በቀላሉ በሰይጣን እጅ ለመውደቅ ይዳርጋልና፡፡

የዚህ ዓለም ገረዶች የተባሉት ገንዘብን መውደድ፣ ሥልጣን፤ ክብርና ዝና፤ ሆዳምነት ወዘተ. የታወቁ ብዙ ገረዶች አሉ። መስቀሉን ባልተሸከመ ክንድ ሊሸነፉ የሚችሉ ግን አይደሉም፡፡ ከእንደዚህ ዐይነት ሸንፈት ለመታደግ ቤተክርስቲያን ዘወትር ምአመናን ውለታውን እንዳይረሱ ለማድረግ በመስቀሉ አጊጣ ትታያለች፡፡ ስለዚህም ክርስቶስ ዘወትር በፊታቸው እንደተሰቀለ ሆኖ ተስሎ ይታያል። (ገላ. 3፥1) የክርስትና ራአይ ሁልጊዜ መስቀሉን መሸከም፤ ግቡም መንግሥተ ሰማያት በመሆኑ ምእመናን በሕይወታቸው አንድም ጊዜ መስቀሉን ከዐይነ ህሊናቸው አይነጥሉትም፡። በቀራንዮ የጌታ መስቀል ከመተከሉ በፊት የነበሩ ሰዎች እንኳን በተስፋና በአምነት የመስቀሉን ነገር ትኩር ብለው እየተመለከቱ ራሳቸውን ለመከራ ያዘጋጁ ነበር።፡ (ዕብ 11፥23) የዛሬዎቹ መምህራንና ምእመናንም ስለ መስቀሉ ዕለት ዕለት እንደሚታረዱ በጎች ሆነዋል።፡ (ሮሜ. 8፥35) ለውለታው የሚከፍሉት ነገር ባይኖራቸውም ‹‹ስላንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን ዕለት ዕለት እንደሚታረዱ በጎች ሆነናል›› ብለው ይዘምራሉ፡፡

ከዕለታት ባንድ ቀን አባ ጳኩሚስ ሲሰግዱ በዐታቸውን ከግንባራቸው በሚፈሰው ወዝ አጨቀዩት።፡ መንፈቀ ሌሊት ላይ ጌታ ተገልጦ ወዳጂ ጳኩሚስ ሆይ ስለምን ትደክማለህ ብሎ ጠየቃቸው፡። እርሳቸውም ሲመልሱ ስላንተ ውለታ ነው አንጅ አሉት። ጌታም መልሶ እኔም እንጂ ስላንተ መከራ ተቀብያሁ ብሎ የተወጋ ጎኑን የተቸነከረ እጁን እግሩን አሳይቶአቸዋል። አንዳንዶቹ የታረዱት፤ አንዳንዶቹም ወደ ዕቶን እሳት የተማገዱት፤ አንዳንዶቹም ወህኒ የወረዱት ስለውለታው ነው፡፡ውለታውን ማሰብ የዘወትር ሥራቸው እየሆኑ ከመጡ ሰዎች ስለያዙት ነገር ከመጨነቅ ይልቅ ‹‹ስላደረገልኝ ሁሉ ለእግዚአብሔር ምን እመልሳለሁ›› ብለው ያስባሉ የሚከፍሉትን ፍለጋ እንደነ አብርፃም መርዓዊ ያሉት ጫጉላቸውን፤ እንደነ ዐፄ ካሌብ ያሉት ቤተ መንግሥታቸውን፣ እንደነ የዋህ ጳውሊ ያሉት ትዳራቸውን እየተው መከራ ወደ በዛበት የገዳም ኑሮ ገብተዋል። ጤናማ ሆኖ ላስተዋለው የክርስቶስ ውለታ ራሳችንን እንኳ እስከመስጠት ደርሰን ብናገለግለው ዋጋ ሊሆነው አይችልም፡፡

3. በዋጋ የተገዙ መሆናቸውን

በዋጋ ተገዝታችኋል እንጂ የራሳችሁ አይደላችሁም ተብሎ እንደተጻፈው ሁሉ ክርስቲያን የራሴ ነኝ ብሎ የሚናገርበት አንደበት ሊኖረው አይችልም፤ በክበረ ዋጋ ተገዝቷልና፡፡ ከአቤል ጆምሮ በምድር ላይ የፈሰስው የጻድቃን ደም ሰውን መግዛት አልቻለም ነበር፡፡ የባርነቱ ዘመን ሲያበቃ በዕለተ ዐርብ ከጌታ በፈሰሰው ደም የሰው ልጆች ተገዙ ይህም ሰው በወርቅና በብር የማይተመን በዕሩቅ ብዕሲ ደም የማይገዛ ባለውድ ዋጋ የአግዚአብሔር ምርጥ ዕቃ መሆኑን ለማሳየት መለኮት በተዋሐደው ንጹሕ ደም ሰውን ተቤዠው፡፡:

ስው ክቡር ፍጡር አንደመሆኑ መጠን ለክብሩ የሚመጥን ሌላ ዋጋ ባለመገኘቱ ሰውን በደሙ ገዝቶታል፡፡ ዋጋው የተከፈለው የተከፈለለትን ሰው ባሪያ ስለማድረግ ግን አልነበረም፡፡ ባል ሰሚወዳት ሚስቱ የሚወዶውን ውድ ስጦታ ሰጥቶ የግሉ አንደሚያደርጋት ዐይነት ጌታችንም የግሉ ሊያደርገን የከፈለልን የማጫ ዋጋ ነበር አንጂ፡:፡ ለዚህ አይደል ሐዋርያውስ ባል ለሚስቱ ራስ አንደሆነ ክርስቶስም የቤተክርስቲያን ራስ ነው ብሎ የመሰክረለት:፡ (ኤፌ. 5፥24) ሌላውም ሊቅ ስለ ክርስቶስና ቤተክርስቲያን ሲናገር ‹‹መርዓዊሃ ለቤተክርስቲያን፤ የቤተ ክርስቲያን ሙሽራዋ›› ሲል የቅዱስ ጳውሎስን ቃል ይተረጉመዋል፡: ከፍቅሩ ጽናት የተነሣ የደም ማጫ የከፈለ አውነተኛ የቤተክርስቲያን ሙሸራ ክርስቶስ ብቻ ነው:፡፡ ቤተክርስቲያኒቱም ለፍቅሩ መገለጫ ይሆን ዘንድ መስቀሉን ዘወትር ተሸክማ ትታያለች፡፥ ሚስት ለባሏ መታመኑዋን በቀለበት አንደምትገልጸው ሁሉ ቤተክርስቲያንም ታማኝ አካሉ መሆኙኑዋን በመስቀል ከመግለጿም በተጨማሪ ‹‹ከፍቅሩ ጽናት የተነሣ ታምሜ አለሁ›› (መጎኀ. 5፥8) በማለት ያለማቋረጥ ትናገራለች: የውስጥ ምስጢራቸውን አንዲገልጽ ምአመናን ልብሳቸውን ሳይቀር በመስቀል ምልክት ያሠራሉ። በቤቶቻቸው ላይ የመስቀል ምልክት ይሠራሉ፤ ይህ የውስጥ ስሜታቸው ነፀብራቅ እንጂ ውጫዊ ስሜት አይደለም፡፡ ቀለበት ያጠለቀችን ሴት ማንም ቢሆን ቀና ብሎ ሊዳፈራት እንዳይቻለው የተፈጥሮ ሕጋችን ያስተምረናል።፡ ምክንያቱም እርሏ የሌላ ሰው ሚስት ናትና፡፡ ቤተክርስቲያንም መስቀሉን ገንዘብ አድርጋ የምትኖረው ከሙሽራዋ የተቀበለችው ቀለበቷ ነው፡። የደም ማጫ የተከፈለባት የክርስቶስ ሙሽራ መሆኗን በዚህ ስለሚያውቅ ሰይጣን አንገቱን ደፍቶ ይኖራል እንጂ ሊዳፈራት አይቻለውም፡፡

እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ሲያጫት ከነድህነቷ ባዶነቷን እያወዉቀ አካሉ እንድትሆን አጫት፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ክርስቶስን የተቀበለችው ከነመስቀሉ ነው፡፡ ይኹን ፍቅር ተመልከቱ! አርሱ ቢፈልግ ኖሮ በእውነት በሰማይ ያለችውን ማኅበር ባልተዋሐደም ነበር፡። ቤተ ክርስቲያንንስ በሰማይ ባልመሠረታትም ነበር፡፡

(ክፍል 6 ይቀጥላል)👇

👉🏾👉🏾 የመስቀሉ ነገር (#መስቀል)

ዜና መስቀል በቤተክርስቲያን

(ክፍል 6)

እስኪ ተመልከቱት! ክርስቶስ እኛን ያገኘን በገነት ሳለን፣ ሁሉ የእኛ በነበረ ጊዜ እንኳን አይደለም። ወደዚህ ምድር ተጥለን ከሁሉም ነገር ባዶ በሆንበት ሰዓት አግኝቶናል እንጂ፡። ቤተ ክርስቲያንን የወደደበት መውደድ ሁልጊዜ ሲደነቅ የሚኖረውም ለዚህ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያንም ክርስቶስን የወደደችው በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ደግሶ ሲያበላ፣ በቃና ዘገሊላ ድንቅ ወይን ሲያጠጣ፤ በቤተልሔም ዋሻ የምድር ነገሥታት ስለ ክብሩ ወድቀው እጅ ሲነሡ አይደለም በቀራንዮ ራቁቱን በመስቀል ላይ ስታየው ወደደቸው እንጂ፡፡

እኛ ወደዚህ ምድር ስንጣል ራቁታችንን እንደመጣን አባታችን አዳም ቋሚ ምስክር ነው።፡ (ዘፍ. 8፥10) እግዚአብሔር የሚወድ ልብሳችንን ሳይሆን ሰውነታችንን በመሆኑ አኛን ፈልጎ ሲመጣ ራቁታችንን አገኘን፤ እኛም እርሱን ፍለጋ ወደ ቀራንዮ ብንወጣ በገነት ተራራ ላይ እኛን ያራቆተ ሰይጣን እርሱንም በቀራንዮ ተራራ ላይ በአይሁድ ልቡና አድሮ ልብሱን ገፎት አገኘነው፡፡ ራቁቱን ሳለ ወደድነው ከፍቅር የተነሣ ምእመናን የክርስቶስ፤ ክርስቶስም የምእመናን ልብስ ሆነ (ገላ 3፥27)፡ በፍቅር ስጥ ራትነት የለም።

4. ነገረ ምጽአቱን ለማስታወስ

አምላካችን ከኛ በነሣው ሥጋ ከዚህ ዓለም ዐረገ በተባለበት ቀን ቅዱሳን መላእክት ለአባቶቻችን ሐዋርያት ያስተላለፏት መልእክት ‹‹ይህ ከናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንደተመለከታችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል፡›› (የሐዋ. ሥራ. 1-11) የሚል ነው፡፡ ለቤተክርስቲያን፡ጌታ ተናግሮት ከሄደው ሁለት ተስፋዎች መካከል ያልተፈጸመልንና ወደፊትገና የምንጠብቀው ትልቁ ተስፋችን የጌታ ዳግም ምጽአት ነው።፡ የቀጠሮአቸው ቀን ደርሶ በመቃብር ውስጥ ተጠልለው እንዲቆዩ ከተወሰነባቸው ቀደምት ወገኖቻችን ጀምሮ በሕይወት እስከተወሰነልን ዘመን እንድንቆይ ዕድል የገጠመን ሁላችን ይህን ተስፋ እንቀበላለን። በመቃብር ያሉት ራሳቸውን ወደ ምዕራብ እግራቸውን ወደ ምሥራቅ ዐይኖቻቸውን ወደ ብሩህ ሰማይ አድርገው በጀርባቸው መተኛታቸው የሚመጣውን ሕይወት ተስፋ እናደርጋለን ማለታቸው ነው።፡

እንዲያውም የጥንት ሰዎች መቃብራቸውን በልዩ ጥበብ ባለ ድርብ ክፍል አድርገው በመሥራት በታችኛው ክፍል ሰው እየቀበሩ በላይኛው ክፍል የስንዴ ዘር የሚዘሩበት እርሻ ነበራቸው። (ዘፍ. 23፥17) በእኛም አገር በመቃብራቸው ላይ የተለያዩ ተክሎች የሚተክሉ አንዳንድ ምእመናን አይታጡም፡፡ መቃብር ለጊዜው በሐሳር ተዘርተን በክብር የምንበቅልበት ሥፍራ እንጂ የዘለዓለም መኖሪያችን እንዳልሆነ ለማሣየት ነው፡። በጭቃ ተዘርተን ከጭቃ ወጥተን በክብር አፍርተን መታየታችን አይቀርምና፡፡

በሕይወት ያሉ ምእመናን ነገረ ምጽዓቱን እንዳይረሱ ከሚደረጉባቸው መንገዶች አንዱ በቤተክርስቲያኒቱ ጉልላት ላይ የሚሰቀለው የጌታ መስቀል ነው። ጉልላቱ ጌታ በመጨረሻው ቀን የሚገለጥበትን ደብረ ጽዮን የተሰኘውን ታላቅ ተራራ ያሣያል። (ራእ. 14፥1) በጉልላቱ ላይ ጸንቶ የሚታየው ክቡር መስቀል በደብረ ጽዮን የሚቆመውን ጌታ የሚወክል ሲሆን በመስቀሉ ላይ ያሉት ሰባቱ የሰጎን እንቁላሎች የሚመጣው ለወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ሰባቱን ከዋክብት በእጁ ይዞ የተገለጠለት ጌታ መሆኑን የሚገልጽ ናቸው። (ራእ. 1፥16) ፍጹም ፍዳ ለኃጥአን፤ ፍጹም ጸጋ ለጻድቃን የሚሰጥበት ቀን ነውና፡፡ ከቤተክርስቲያኒቱ ጉልላት ላይ ሁልጊዜም ሰባት የሰጎን እንቁላልን የተሸከመ መስቀል አይታጣም፡፡

ከዚያም ባሻገር ሲመጣ ለሰው ሁሉ የሚገለጠው ዐይን ሁሉ አየተመለከተችው ለወጉት ሰዎች የተወጋ ጎኑን፣ የተቸነከረ እጁን እያሳየ ከፊት ከፊት መስቀሉን የተሸከሙ ቅዱሳኑን አስቀድሞ የሚመጣ መሆኑንም ምእመናን በልባቸው ሰሌዳ እንዲሳልባቸው ታደርጋለች፡፡ (ራእ. 1፥7) ከዚህም የተነሣ በምእመናኑ ልቡና የምጽዓአቱ ነገር ከትናንት እስከ ዛሬ ሲታወስ ይኖራል፡፡ ቀና ብለው ጉልላቱን ያዩ ሁሉ የመጨረሻውን የፍርድ ቀን ሲያስታውሱ ይኖራሉ።

ምንጭ፦ ‘በሞት የተገለጸ ፍቅር’ ገጽ 109-118
አዘጋጅ – ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ

ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንም ሼር ያድርጉ፡- https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q

👉ጥያቄ፦ #አምስቱ #ቅንዋተ_መስቀል ከምን ከምኑ ላይ ነው የተመቱት ? ብዙ ሊቃውንት የተለያየ ትምህርት ስለሚያስተምሩ ነው።

መልስ፦ ጠያቂያችን፤ ከዚህ በፊት የደረሰንን ተመሳሳይ ጥያቄ መሰረት አድርገን የ 5ቱ ቅንዋተ መስቀል ምስጢራዊ ትርጓሜ እና አገልግሎት በሚመለከት ያስተላለፍነው ትምህርታዊ ማብራሪያ ስላለ አሁን እርስዎ ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ እና ተጨማሪ ማብራሪያ ስለሚያገኙበት ይህንኑ እንደሚከተለው በድጋሚ ልከንልዎታልና አንብበው ይረዱት።

👉የጥያቄው ሃሳብ ፦ ስለ አምስቱ ችንካሮች (በተለይ አዴራ ና ሮዳስ) መዝገበ ጸሎትን ጨምሮ የተለያዩ ጽሁፎች ላይ የተለያየ መረጃ ሆነብኝና ልጠይቃችሁ ወደድሁ፡፡ የሚያውቁ ሰዎችም እንዲሁ የተለያየ መልስ ሰጠውኛል፡፡…. ሁለቱ ችንካሮች ከጌታችን አካል ውጭ ነውና ያረፉት እንዴት እንደ ህማማት እንቆጥራቸዋለን?

መልስ፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቸነከረባቸው 5ቱ ቅንዋት (ችንካሮች) ምስጢራዊ ትርጓሚያቸው ምን እንደሆነ፣  እንዴት እንደተዘጋጁ፣ እና ሥራ ላይ እንዴት እንደዋሉም የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በአስተማሩን እና ቅዱሳት መፃሕፍት በነገሩን  መሠረት እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

ቀኖት (ችንካር) ፦ ተቀነወ ከሚለው የግዕዝ ቋንቋ የተገኘ ሲሆን የአማርኛ ትርጎሜውም፣ ተቸነከረ፣ ተበሣ ተነደለ ወዘተ የመሳሰለውን ፍቺ ይዞ እናገኘዋለን።

ቀኖተ ማለትም ችንካር፣ ምስማር፣እሻህ ፣ጋሬጣ ማለት ሲሆን ከብረትና ከእንጨት የሚሰራ ነው።

ማስረጃ፦

– ነቢዩ ኤርምያስ ስለ አሕዛብ ጣዖታት አዘገጃጀት ከንቱነት በተናገረበት ትንቢቱ ላይ “በብርና በወርቅ ያሰጌጡታል እንዳይናወጥም በችንካርና በመዶሻ ይቸነክሩታል” ብሏል(ኤር 10፥4)

– ነብዩ ዳዊትም በራሱ የሚደርስ መከራ በሚመስል አገላለፅ ስለ ክርስቶስ በቅንዋት መቸንከር በዓይነ መንፈስ ተመልክቶ ትንቢት ሲናገር “እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ” ብሏል (መዝ 21፥16)  

– ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተነሣ በኋላ ደቀመዛሙርቱ በዝግ ቤት እያሉ በመካከላቸው ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” ሲላቸው መንፈስ ያዩ መስሏቸው በደነገጡና በፈሩ ጊዜ እሱም “ስለምን ትደነግጣላችሁ? ስለምንስ አሳብ በልባችሁ ይነሣል? እኔ ራሴ እንደሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ … ይህንንም ብሎ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው” (ሉቃ 24፥38-40)

ከዚህ የወንጌሉ ቃል የምንረዳው ከደቀመዛሙርቱ በተዘጋው ቤት በመካከላቸው ቁሞ ሰላም ለእናንተ ይሁን ያላቸው መንፈስ እንዳልሆነና ራሱ ጌታችን እንደሆነ ያምኑ ዘንድ በቅንዋት (በችንካር) የተቸነከሩ እጆቹንና እግሮቹን አይተው እንዲያምኑ በተግባር ያሳያቸው መሆኑን ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀኖት (በችንካር) እግሮቹንና እጆቹን እንደተቸነከረ ከሚነግረን በስተቀር ስለችንካሮቹ ስምና ቁጥር ስለ ስያሜያቸውም ሆነ ከእግሮቹና ከእጆቹ ውጪ ምን ምን አካሉ ላይ እንደተቸነከሩ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ አይሰጥም። ይሁን እንጂ በሌሎቹ አዋልድ መጽሐፍትና በታወቁ ሊቃውንት በተዘጋጀ መፅሐፍት 5ቱ ቅንዋት ስማቸውና አገልግሎታቸው በግልጽ ተቀምጧል።

5ቱ ቅንዋት ስያሜ በሚመለከት፦

1ኛ/ 1. ሳዶር 2. አላዶር 3. ዳናት 4. አዴራ 5. ሮዳስ ይባላሉ።

2ኛ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አይሁድ በቀራንዮ አደባባይ በመስቀል ላይ በሰቀሉት ጊዜ ምን ምኑ ላይ ቸነከሩት ለሚለው ጥያቄ የቤተክርስቲያችን ሊቃውንት ከአንድ በላይ የሆነ አተረጓጎምና አገላለፅ ቢኖራቸውም እንኳ የችንካሮቹን አቀማመጥ በሚመለከት እንጂ ቁጥራቸው 5 መሆናቸውንና በስያሜያቸው ላይ ምንም ዓይነት ልዩነት የለም።

5ቱ ቅንዋት የተቸነከሩበት የጌታ አካሉ ምን ላይ እንደሆነና  በመስቀሉም ላይ ምን ቦታ ላይ እንዳረፉ  በሚከተለው አይነት አጭር ማብራሪያ ተገልፇል፦

–  “ሳዶር” ፦ የሚባለው ችንካር አይሁድ ጌታን ለመስቀል የሚያዘጋጁትን መስቀል በመስቀል ቅርጽ አመሳቅለው የተቸነከረበት ነው።
–  “አላዶር” ፦ የተባለው ችንካር ቀኝ እጁ የተቸነከረበት ነው።
–  “ዳናት”፦ የተባለው ችንካር ግራ እጁ የተቸነከረበት ነው።
– “አዴራ”፦ የተባለው ችንካር ሁለቱም እግሮቹ ተጣምረው የተቸነከረበት ነው።
–  “ሮዳስ” ፦ የሚበለው ችንካር የአይሁድ ንጉሥ የሆነው መስፍን ጲላጦስ “ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ” የሚለው ቃል በሮማይስጥ ቋንቋ ፅፎ ያዘጋጀውን ሰሌዳ (ደብዳቤ) በመስቀሉ ራስ ላይ የተቸነከረበት ቀኖት ነው።

በዚህ አገላለፅ መሠረት 5 ችንካሮች ከጌታ አካል ላይ በቀጥታ ባይቸነከሩም ሁሉም ግን በመስቀሉ ላይ ተሣትፎ ስላላቸው በ5 ቀኖዋት ተቸነከረ የሚለውን ምስጢር አያፋልሰውም።

ለ አንድም ስለ አምስቱ ቅንዋት አገልግሎት ሌላው አገላለፅ የሚከተለው ነው።

 የችንካሮቹ (የቅንዋቱ) አሠራራቸውን በሚመለከት ራሳቸው እንደ መሮ እራስ ሲሆን  ፣ ወርዳቸው እንደሞረድ አራት ማዕዘን ያለው፣ ቁመታቸውም እንድ ክንድ ከስንዝር የሆነ፣ ስለታቸው እንደ ወስፌ የሆኑ 5ት ቅንዋትን አይሁድ አዘጋጅተዋል።

ሳዶር በሚለው ችንካር ቀኝ እጁን፣ አላዶር በሚባለው ችንካር ግራ እጁን፣ አዴራ በሚባለው ችንካር መሐል ልቡን፣ ዳናት በሚባለው ችንካር እግሩን፣ ሮዳስ በሚባለው ችንካር ደረቱን እንደቸነከሩት ሌላው የቤተክርስቲያናችን ታሪክ ያትታል።

ዋቢ ማስረጃ መጽሐፍት የማቴዎስ ወንጌል ትርጓሜው ምዕ 26፥26 13ቱ ሕማማተ መስቀል በሚል ርዕስ በ60ዎቹ አካባቢ በተስፋ ገብረ ስላሴ ማተሚያ ቤት የታተመው መፅሐፍ ‘በሞት የተገለጠ ፍቅር’ የሚለው የሊቀሊቃውንት ስሞኮነ መፅሐፍ እና ሌሎቹም ይገኙበታል።

በአጠቃላይ ያም ሆነ ይህ ጠያቂችንም ሆኑ የፕሮግራማችን ተከታታዮች ዋናው ዓላማችን ሊሆን የሚገባው በመለኮቱ ወልደ እግዚአብሔር በትስብእቱ ወልደ ማርያም ተብሎ ስጋን ተዋህዶ በምድር ላይ የተገለፀው ቀዳማዊ ቃል እየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል ለአምላክነቱ ያማይስማማውን ህማማተ መስቀል በለበሰው ስጋ ተቀብሎ ለሰው ልጅ ካለው ፍቅር የተነሳ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በ5 ችንካር ቀንዋት ተቸንክሮ የሾክ አክሊልም ደፍቶ ጎኑን በጦር ተወግቶ መራራ ሃሞትን ተጎንጭቶ ሞታችንን በሞቱ አጥፍቶ ደምስሶ የእሱን ህይወት ለእኛ ሰጥቶ እኛን ለማዳን የፈፀመው ምስጢራዊ ጥበቡን ብቻ ማሰብ እውነተኛ ሃይማኖት ነው። ስለ ቅንዋቱ የስራ ድርሻ ምንም ሆነ ምን እሱ መከራ የተቀበለባቸው እንደሆነ ስለምናምን ችንካሮቹ ስለዋሉበት ቦታ ሰውን ሊያጠራጥርም ሆነ የአይምሮ ጥያቄ ሊሆን የሚችል አንገብጋቢ ጉዳይ ስላልሆነ ለግንዛቤ ያህል ይህን ማስረጃ መሰረት አድርጋችሁ ለማንኛውም ጠያቂ ምላሽ ትሰጡ ዘንድ ዘወትር የተዘጋጃችሁ እንድትሆኑ በእግዚአብሔር ስም አደራ  እንላለን።

ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ

ነገረ መስቀል

👉🏾👉🏾👉🏾 #ቤተክርስቲያን

ቤተ ክርስቲያንን የመሠረተ ክርስቶስ ነው

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን፤ በርዕሱ መነሻነት የተዘጋጀውን ይህ ትምህርት ከ ‘ኀብረ ሥርዐት ዘቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክስ’ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ፥ ይህን ጠቃሚ ትምህርት የዛሬውን እለት መሰረት አድርገን ለእናንተ እንዲደርሳችሁ አድርገናልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትጠቀሙበት ዘንድ አደራ እንላለን።

1.ቤተ ክርስቲያንን የመሠረተ ክርስቶስ ነው

ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን የመሠረታት በጴጥሮስ ሃይማኖት ላይ ነው፡፡የጴጥሮስም ሃይማኖት ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ፣አልፋ ዖሜጋ፤ ቀዳማዊ ወደኃራዊ፣ በነቢያት አድሮ ትንቢት ያናገረ ያናገረውንም ትንቢት አምላክ ወሰብኦ ሁኖ በገቢር የፈጸመ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የሆነ አምላክ መሆኑን ማመን ነው፡፡ ይህም ሃይማኖት የጴጥሮስ መሆኑን ለመረዳት ጌታ በቂሳርያ ጉባኤ ‹‹የሰውን ልጅ ሰዎች ማን ይሉታል?›› ብሎ በጠየቀ ጊዜ ሌሎች ደቀ መዛሙርት ከሰዎች የሰሙትን ኤልያስ፣ ዮሐንስ መጥምቅ፣ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል አያሉ ከተናገሩ በኋላ ጥያቄው ግን በዚህ አላበቃምና ጌታ መልሶ ‹አንትሙሰኬ መነ – ትብሉኒ – ከዊነ፦እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?›› ሲላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ መልሶ ‹‹አንተ ውእቱ ክርስቶስ ወልደ አግዚአብሔር ሕያው፦ አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ›› ብሎ የሃሃይማኖት መሠረት የሚሆንበትን ነገር ተናግሯል፡፡ ማቴ 16፥16 ዮሐ 1፥41

እንዲሁም ሌላ ጊዜ ደግሞ ጌታ ስለ ምስጢረ ቁርባን በሚያስተምርበት ጊዜ ከሕዝቡ ብዙዎቹ ትምህርቱ ስለ ከበዳቸው ‹‹ዕፁብ ዝንቱ ነገር ወመኑ ይክል ሰሚዖቶ፥ይህ ነገር የሚያስጨንቅ ነው ማንስ ሲሰማው ይችላል?›› እያሉ ወደ ኋላ ሲመለሱ ጌታ ሐዋርያትን ‹‹አንትሙኒ ትፈቅዱኑ ትሑሩኑ፦ እናንተ ደግሞ ልትሄዱ ትሻላችሁን?›› ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ መልሶ ‹‹አቤቱ የዘለዓለም የሕይወት ቃል እያለህ ወደ ማን እንሄዳለን? እኛስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ አንተ እንደሆንህ አምነናል አውቀናልም›› ብሎ የራሱንና የባልንጀሮቹን ሃይማኖት መስክሯል፡፡ ዮሐ 6፥80-89

በመልእክቱም ራሱ ቅዱስ ጴጥሮስ ስለ ክርስቶስ ሞት ሲናገር ‹‹ሞተ በሥጋ ወሐይወ በመንፈስ፦፥በሥጋ ሞተ በመንፈስ(በመለኮት) ግን ሕያው ነው፡› ብሏል። 1ኛ ጴጥ 3፥19 የጴጥሮስ ሃይማኖት ማለትም ይህ ነው፡፡በዚህች ሃይማኖት የማያምንም የክርስቶስ አካል ብልት፤ማኅበር ቤተሰብ ከሆነችው ከቤተ ክርስቲያን አንድነት የተለየ ነው፡፥ የጴጥሮስ ተከታይ ደቀ መዝሙርም አይባልም።፡ስለዚህም ርትዕት የሆነችው ኦርቶ ዶክሳዊት ቤት ክርስቲያን የተመሠረተችው ጸንታ የቆመችው ወደ ፊትም የምትቀጥለው ይህን የሊቀ ሐዋርያቱ የቅዱስ ጴጥሮስን ቃለ ሃይማኖት መሠረት አድርጋ ይዛ ነው፡፡ ርቱ ሃይ ገጽ 34

ይህንንም ዮሐንስ ወንጌላዊ በመልእክቱ ‹‹ወመኑ ሐሳዊ ዘእንበለ ዘይክድ ወይብል አስመ ኢየሱስ ኢኮነ መሲሐ፦ኢየሱስ መሲሕ አይደለም ብሎ ከሚክድ በቀር ሐሰተኛ ማነውን?›› 1ኛ ዮሐ 2፥22 ‹‹ኢየሱስ መሲሕ አንደሆነ የሚያምን ሰው ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል ወላጁንም የሚወድ ሁሱ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወድዳል፡፡» ብሏል፡፡ 1ኛ ዮሐ 5፥1 ስለዚህ ማንም ሰው ክርስቲያን የሚባለው ይኽን የሐዋርያትን ትምህርት አውቆ ሃይማኖታቸውን ጠንቅቆ ተረድቶ ተቀብሎ አሠራቸውን ሲከተል ነው አንጅ በዘፈቀደ፣ በይሆናል፣በማን አለብኝነት ፣ በራስ ፍልስፍናና ተመርቶ የሚያምኑት ሃይማኖት ከፍርድ አያድንም፡፡

የጴጥሮስም ሃይማኖቱ ትክክል አንደሆነ የሚያስረዳው ጌታ የጴጥሮስን ቃል ሰምቶ ዝም አላለውም፡፡፡‹‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ አንተ ብፁዕ ነህ በሰማይ ያለው አባቴ ነው እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና እኔም አልሃለሁ አንተ ዐለት ነህ በዚያች ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን አሠራታለሁ የሲኦል በሮችም አይበረታቱባትም›› ማቴ 16፥17 ብሎ ‹‹ብፅዓን›› ሰጥቶ አመስግኖታል፡፡ ስለሆነም የጴጥሮስ መሠረትነት የሃይማኖት ነው፡፡ ሃይማኖቱም ወልድ ዋሕድ ብሎ ማመን ነው፡፡ በዚህ ሃይማኖት የፀና በጴጥሮስ ዐለትነት ላይ የቆመና የሚያድግ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አንዱ አካል ነው፡፡ የጴጥሮስ መሠረትነት ማመን ሲሆን የክርስቶስ መሠረትነት ደግሞ መታመን ነው :፡‹‹ነገር ግን ከተመሠረተው በቀር ሌላ መሠረት ሊመሠርት የሚችል የለም መሠረቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ሃው›› 1ኛ ቆሮ 1፥11

ቤተ ክርስቲያንም የሚባለው በነቢያት ትንቢት፣በሐዋርያት ስብከት፣በሊቃውንት ትምህርት፣ በሰማዕታት ጥብዓት፣ በቅዱሳን ጻድቃን ጸሎት፣በባህታውያን ትግሃታተ መዓልት ወሌሊት የተመሠረተና የፀና ሲሆን ነው:: ‹‹በነቢያትና በሐዋርት መሠርት ላይ ታንጻችኋልና የሕንጻው የማዕዘን ራስ ድንጋይም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው›› ኤፌ 2፥19-20 ክርስቶስም ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ ስንል በጦር ተወግቶ ከቀኝ ጎኑ ባፈሰሰው ማየ ገቦ ወልዶ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በቆረሰው ሥጋ ባፈሰሰው ደም ያሳደጋት መነሻዋም መድረሻዋም እረሰሱ ነው ማለታችን ነው::

ይህም ማለት ቀዳማይ አዳም ከጎኑ ሞትን የምታመጣ ሄዋንን አንዳስገኘ ዳግማይ አዳም ክርስቶስም ሕይወትን የምትሰጥ ቤተ ክርስቲያን የምትመሠረትበትን ማየ ገቦን ከጎኑ አፍልቋልና፡፡ ራስ ከአካል ሁሉ በላይ ሁኖ የአካላት ሁሉ መሰብሰቢያ አንደሆነ ክርስቶስም የቤተ ክርስቲያን ራስ ሆኖ የምዕመናን ሁሉ መገኛ ነውና:፡፡ ‹‹አኛ የአካሉ ሕዋሳት ነንና» ኤፌ 5፥30 -‹‹አርሱ ከሁሉ አስቀድሞ ነበረ ሁሉም በአርሱ ጸና እርሱ የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው በኩር አርሱ ለሁሉ ራስ ይሆን ዘንድ ከሙታን ሁሉ አስቀድሞ ተነሥቶአልና›› ቆላ 1፥17 ኤፌ 1፥21፣ ኤፌ 5፥23

2. በዚህ መሠረት ላይ የሚያንጽ ይጠንቀቅ

(ይቀጥላል)👇

👉🏾👉🏾👉🏾 #ቤተክርስቲያን

(ክፍል ሁለት)

2. በዚህ መሠረት ላይ የሚያንጽ ይጠንቀቅ

ክርስቶስም ቤተ ክርስቲያንን መሥርቶ እንዲሁ አልተዋትም፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የሚመሩና የሚያስተዳድሩ ስለርሱ አያስተማሩ ወዶርሱ የሚያደርሱ ሐዋርያትን ሰብዓ አርድእትን መርጦ ሹሟል እንጂ፡፡ ‹‹አርሱም ጸጋን ሰጠ ከቤተ ሰቦችም ሐዋርያትን ከእነርሱም ነቢያትንና የወንጌል ሰባኪዎችን ጠባቂዎችንና መምህራንን ሾመ ቅዱሳን ለአገልግሎቱ ሥራና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ እንዲጸኑ›› ኤፌ 4፥11 1ኛቆሮ 12፥27

ስለዚህም እነዚህ ስዩማን ከሕዝቡ ከአህዛቡ እያስተማሩ እያሳመኑ እያጠመቁ እያቆረቡ ወደ አግዚአብሔር ያቀርባሉ:: ከዚያም በተሰጣቸው ሥልጣን እየናዘዙ ሥርየተ ኃጢአትን ያሰጣሉ፡፡ከእግዚአብሔርም ምሕረትን ይቅርታን ይለምናሉ፡፡: ‹ኃጢአታቸውን ይቅር ብሎ በደላቸውንም ሳያስብ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለሙን ከራሱ ጋር አስታርቆአልና የዕርቅ ቃሉንም በእኛ ላይ አደረገ የይቅርታውንም መልእክት ሰጠን እኛስ በክርስቶስ አምሳል እንለምናለን እግዚአብሔርም በአኛ መጽናናትን ይሰጣችኋል ከእግዚአብሔርም ጋር ትታረቁ ዘንድ ታረቁ ብለን በክርስቶስ አንለምናለን›› 2ኛ ቆሮ 5፥19

ይህም አዲስ መሠረት ይመሠርታሉ ማለት ሳይሆን በተመሠረተው ላይ ያሳድጋሉ እንዳይናድ በትምህርት ይጠብቃሉ፡፡ ወደ አግዚአብሔር የሚወስደውን መንገድ ያዘጋጃሉ፡፡ ሰውን ለእግዚአብሔር መንግሥት ያበቁት ዘንድ ይተጋሉ ማለት ነው።::‹‹እግዚአብሔር እንደ ሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልህ የጠራቢዎች አለቃ ሆኜ አኔ መሠረት ጣልሁ ሌላውም በአርሱ ላይ ያንጻል አያንዳንዱ ግን በአርሱ ላይ እንዴት እንደሚያንጽ ይጠንቀቅ›› 1ኛ ቆሮ 3፥10

እናም ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን ያከበራትን ከዓለም በግብርም በክብርም በአነዋወርም የለያትን ከፍ ከፍ ያደረጋትን ቤተ ክርስቲያን የመጠበቅ ኃላፊነት ያለው እንዲጠብቁና እንዲያስተዳድሩ በሾማቸው ላይ ነው፡፡‹አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ›› ሐዋ 20፥28 እነርሱም በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በመንፈሳዊ የእግዚአብሔር ሕግና ትእዛዝ ተመሥርተው ለሚያዝዙት ትእዛዝ የማይገዛ ቢኖር እንደ አረማዊ እንደ መጸብሐዊ መሆኑ ነው፡:‹‹ቤተ ክርስቲያንንም ባይሰማት እንደ አረማዊና አንደ ቀራጭ ይሁንልህ››ተብሎአልና፡፡ ማቴ 18፥17 ስለዚህም ምአመን ቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ የተወለደች በሐዋርያት ሞግዚትነት ያደገች፤ በሊቃውንት ትምህርት በስማዕታት ጥብዓት የጸናች በመሆኗ መነሻዋ ክርስቶስ እንደሆነ መድረሻዋም ክርስቶስ ነው::

ይቆየን

ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q

👉ጥያቄ፦ የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #ቤተክርስቲያን ከሌሎች የእምነት ተቋማት ጋር ያላት ልዩነት ምንድነው? በጥምቀት፤ በቁርባን፤ በመልካም ምግባርእና መንፈሳዊ ተጋድሎ ለምሳሌ ከካቶሊክ ፤ከእስልምና እና ከመናፍቃን?

መልስ፦ ከዚህ በፊት “ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት” ከሚለው ቃል ትርጉም በመነሳት ተከታታይ ትምህርት በድረገፃችን ማስተላለፉችን ይታወሳል፡፡ ንጽሂትና ቅድስት የሆነችውን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ፥ከሌሎቹ የስም ሃይማኖቶች ፥ከቃል ትርጉም ጀምሮ የምትለይበት ቀኖናዊ ይዘት ምን እንደሚመስል ፥በቀላሉ መረዳት ይቻል ዘንድ በቤተክርስቲያን የአስተምሮ ዘይቤ አዘጋጅተን ያቀረብነው ስለሆነ ፥ በቅድሚያ ይህን አንብበው ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት መሰረታዊ የሆነ እውቀት እንዲያገኙና ተጨማሪ ትምህርትና ምክር እስከምንልክልዎት እርስዎም ልዩነቱን በማስተዋል እንዲያገናዝቡ በማሰብ እንደሚከተለው ልከንልዎታል። በተጨማሪም የተለያዩ ጥያቄዎችን መሰረት አድርገን በድምጽ ካስተላለፍነው ትምህርት ውስጥ ሁለቱን ከዚህ ጋር አያይዘን ልከናልና ይህንንም አዳምጠው ይረዱት ዘንድ እና ቀሪዎቹን ደግሞ ከድረገፃችን ላይ እየተመለከቱ እንዲማሩበት ከወዲሁ እንመክራለን ። ምናልባት በዚህ ያልተረዱት ካለ የጥያቄዎን ሃሳብ ጠቅለል አድርገው ለማወቅ የፈለጉትን ለይተው ቢገልጹልን ያንን መሰረት አድርገን ተገቢውን ምላሽ ልንሰጥዎት እንችላለን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ማን ናት? በሰው ልጅ የማዳን ሥራ ያላት ድርሻ ምንድን ነው?

በቅድሚያ ‘ኦርቶ’ – ‘ዶክስ’ – ‘ተዋሕዶ‘ ‘ሃይማኖት‘ የሚለውን ቃል፥ በምስጢራዊ አተረጋጎሙ እና በነገረ መለኮት አስተምሮ የአገላለጽ ዘይቤና ስልት መሰረት በአጭሩ መረዳት ያስፈልጋል።

“ኦርቶ ዶክስ” ፡- ማለት፤ ቃሉ የግሪክ ሲሆን፤ “ቀጥተኛ መንገድ (እውነተኛ ሃይማኖት)” ማለት ነው።

በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማለትም በ325 ዓ.ም. 318 ሊቃውንት (የቤተክርስቲያን አባቶች) በኒቅያ ከተማ  የሃይማኖት ጉባኤ (የሲኖዶስ ጉባኤ) በማድረግ፤ በወቅቱ አርዮስ የተባለው የክሕደት ሰው “ፈጣሪን፤ ፍጡር ነው”፤ በሚል የክሕደት ትምሕርት ብዙዎች እንዲክዱ አድርጓል። በመሆኑም ፤ የቤተክርስቲያናችን ታሪክ እንደሚመሰክረው፤  በዚህ ጉባኤ ሊቃውንትም፥ እውነተኛዋን ፣ ቀጥተኛዋን የተዋሕዶ ሃይማኖት ከ አርዮስ  የክሕደት ሃይማኖትና፣ የክህደት ትምህርት ለመለየት  “ኦርቶ ዶክስ (ቀጥተኛ መንገድ) ሃይማኖት” በማለት ሰይመውታል።  

ነብዩ ኤርምያስም ስለ እውነተኛዋና ቀጥተኛዋ መንገድ (ሃይማኖት) ሲናገር “የቀደመችውን ቀጥተኛዋን መንገድ ጠይቁ በእርሷም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁ እረፍት ታገኛላችሁ” ብሏል (ኤር 6፤16)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም “እኔ መንገድ እውነት ሕይወት ነኝ” ብሏል (ዩሐ 14፤6)

ሐዋርያው ቅ/ጰውሎስም ለእብራውያን ወገኖቹ (ተከታዮቹ) በጻፈው መልእክቱ፦ “የመጀመሪያ እምነታችንን፥ እስከ መጨረሻው አጽንተን እንጠብቅ”፤ በማለት ስለቀደምት፣ እና ስለመጀመሪያዋ ቀጥተኛ ሃይማኖት አስተምሯል (ዕብ 3፤14)

2.“ተዋሕዶ” ማለት ቃሉ የግእዝ ቃል ነው። በ 431 ዓ.ም. 200 ሊቃነ ጰጰሳት (የቤተክርስቲያን አባቶች) በኤፌሶን ከተማ በሲኖዶሳዊ ጉባኤ ተሰብስበው ነበር። የመለኮት እና የስጋን መዋሐድ :- እግዚአብሔር ወልድ፥ በድንግል ማርያም ማሐፀን አድሮ፤ ከሥጋዋ ፥ ሥጋ ፤ ከነፍሷ ፥ ነፍስ፤ ነሥቶ ፤ በ ተወለደ ጊዜ ፤ “ቃልና ሥጋ፥ በተዋሕዶ ከበረ”። ንስጥሮስ የተባለው የክሕደት ሰው ግን ይህንን እውነተኛ እና ቀጥተኛ አስተምሮ በመቃወም፤ ስለ ‘የመለኮትና የሥጋን ተዋሕዶ’ እያፋለሰ ያስተምርም ነበር። ስለሆነም ፥ ‘ኦርቶዶክስ’ በሚለው ቃል ላይ፤ ‘ተዋሕዶ’ የሚለውን ቃል ፥በመጨመር ፤ “ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት” ፥ ተብሎ እንዲጠራ ፥ሊቃነጳጳሳቱ ፥በዚህ ጉባኤ ፥ወስነዋል። በትምሕርትና በተግሣጽ ከክሕደቱ አልመለስም አሻፈረኝ በማለት የክሕደት አመጹን የቀጠለበትን ንስጥሮስንም ፤ አውግዘው ከቤተክርስትያን ለይተውታል።

3.“ሃይማኖት” ማለት ምንድን ነው? ብለው ጥይቄ ለሚያቀርቡ ወገኖች ሁሉ ፥ሊያውቁት የሚገባቸው ዋና ቁም ነገር ፥ ፈጣሪና ፍጡር፣ ጽድቅና ኩነኔ፣ ብርሃንና ጨለማ፣ ሕይወትና ሞት፣ ገነትና ሲኦል፥ ተለይተው የሚታወቁበት ፥የሁላችንም የሕሊና መነፅር በ ፥ ‘ሃይማኖት’ ነው። የሰው ልጅ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ፤ በአይን የማይታየውን፣ በእጅ የማይዳሰሰውን፣ ረቂቁን አምላክ (ፈጣሪ)፣ ለማወቅ እና ለመድረስ የሚችልበት እውነተኛ መንገድ ሃይማኖት ነው።

ሃይማኖት ማለት እግዚአብሔርን የምናምንበትና የምናውቅበት ረቂቅ መንገድ ነው፤ ሲባል፦ በዓይነ ሥጋ ተመልክተን፣ በዕዝነ ሥጋ ሰምተን ፣ በልብ አስበን እና፣ በስሜት ሕዋሳታችን አድምጠን ፣ ልንመረምረውና ልንደርስበት የማይቻለን እና፤ ከእኛ ሥጋ ደካማነትና ከፀጋ ብቃታችን ማነሥ የተነሣ ነው። ስለዚህ ሩቅ እና ረቂቅ የሆነብንን መለኮታዊ ጥበብ፤ ይሆናል፥ እና ይደረጋል ብለን፤ በእምነት ለመቀበል ፥ የምንችልበት ምስጢር ስለሆነ ነው።

ሐዋርያው ቅ/ጰውሎስ ለእብራውያን ተከታዮቹ ስለ እምነት በተናገረበት መልእክቱ ላይ “እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፤ የማናየውን ነገር የሚያስረዳ ነው” ፤ ሲል፤ ሃይማኖት፤ በዓይነ ሥጋ የማናየውን እግዚአብሔርና ረቂቅ ሥራውን የምናይበት፤ ልዩ ፀጋ መሆኑን ተናግሯል (ዕብ 11፤1)

በመሠረቱ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ስንል የእግዚአብሔርን አንድነት እና ሦስትነት፥ እና በስጋዊ አይናችን የማናየውን፣ በእጃችን የማንዳስሰዉን፣ እሮጠን የማንቀድመውን፣ ተመራምረን የማንደርስበት፥ አምላክ (ፈጣሪ ) አለ ብሎ ማመን ነው። በስነ ተፈጥሮ ህግ በኩልም ፥ሰማይ እና ምድርን፣ ጨለማን እና ብርሃንን፣ ቀኑንና ሌሊቱን ፣ሰውን እና መላእክትን፣ የዱር አራዊትን እና እንሰሳትን፣ አዝርእትን እና አትክልትን፣ በየብስ እና በባህር ውስጥ የሚሽከረከሩ፣ በደረታቸው የሚሳቡ፣ በክንፉቸው የሚበሩ ልዩ ልዩ ፍጥረታትን ፥ በአጠቃላይም 22 ስነፍጥረታትን ፥ ፈጥሮ ፥  ስነፍጥረታትን ሁሉ የሚመግብ እና፣ የሚመራ ፈጣሪ መሆኑን አምነን የተቀበልንበት ቀጥተኛ መንገድ ‘ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት’ ነው። ከሌሎቹ የእምነት አይነቶች የተለየ የሚያደርገውም ዋናው ሚስጢር ይህ ነዉ። ምክንያቱም እምነት ሁሉ ሃይማኖት አይደለም፤ ለምሳሌ ፦ በሠይጣን የሚያምኑ፣ በአምልኮ ጣኦት የሚያምኑ፣ በዛር መንፈስ የሚያምኑ፣ በእሳት፣ በወንዝ፣ በዛፍ፣ በድንጋይ፣ በልዩ ልዩ መንፈስ፣ የሚያመልኩ ሰዎች የሚያምኑትን እምነት ሁሉ ሃይማኖት አንለውም። እውነተኛውና ቀጥተኛው ሃይማኖት እግዚአብሔርን ብቻ   አምላክ ፈጣሪ፣  መጋቢ ፥ብለን ፥ ለማመን ፥ የተሰጠን የመንፈስ ቅዱስ ሀብት ነው።ታላቁ የሃይማኖት አባት ቅዱስ- ዩሐንስ አፈወርቅ፤ “ሃይማኖት የሁሉ ነገር መሠረት ናት፤ ሌሎቹ ግን ህንፃ እና ግንብ ወይም ደግሞ ጣራ አና ግድግዳ ናቸው” በማለት እንደ ህንፃ እና እንደ ግንብ ከሚቆጠሩት የምግባር እና የትሩፋት ስራዎች ሁሉ በፊት ሃይማኖት ተቀዳሚ እና መሠረት መሆንዋን አረጋግጦልናል።

(ይቀጥላል)👇👇👇

የአንድ ቤት መሠረት ህንፃውን ሁሉ አንደሚሸከም፤ እምነት ፣ ምግባር፣  አና ልዩ ልዩ በጎ ስራዎችን ሁሉ ሃይማኖት ትሸከማለች።ህንፃ ያለ መሠረት እንደማይቆም ምግባርም ያለ ሃይማኖት አይኖርም፤ ወይም ትርጉም የለውም።  ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ “ስራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው”  በማለት ሃይማኖት እና ምግባር ፤ ተለያይተው የማይነገሩ እንደ አንድ ሳንቲም ገፅታመሆናቸውን በዚህ ተናግሯል።

በአጠቃላይ ጠያቂያችን ከዚህ በፊት ስለ ሃይማኖት ያስተላለፍናቸው ብዙ ትምህርቶች ከድረገፃችን ላይ ስለሚገኝ ከዚያ ተመልክተው እንዲማሩበትም እንመክራለን።

በመጨረሻም ፤ ” ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት እና ካቶሊክ ሃይማኖት ልዩነታቸው ምንድነው?” ብለው ላቀረቡት ጥያቄ የድምጽ ማብራርያ የሰጠንበት ስለሆነ ይህንኑ ትምህርት አዳምጠው እንዲረዱት ከዚህ በታች ልከንልዎታል።

👉ጥያቄ፦ #ቤተክርስቲያን ለምን #አማናዊት እንደ ተባለች ማብራርያ ብሰጡን?

መልስ፦ ቤተክርስቲያን ለምን አማናዊ ተባለች ብለው ለጠየቁን አባላችን የተሰጠ ምላሽ፦ በብሉይ ኪዳን ህግ በተለይ በኦሪቱ ሀግ የተፃፉት ብዙዎቹ ለአዲስ ኪዳን ምሳሌና ጥላ ወይም ንባብ ናቸው። አዲስ ኪዳን ደግሞ የብሉይ ኪዳኑ ትርጓሜና አማናዊ ነው። ስለዚህ አማናዊት ማለት አስቀድሞ በምሳሌ የተነገረውና ወደፊት ይሆናል የተባለው በሙሉ ፍፃሜ ሲያገኝ እውነተኛነቱ ሲረጋገጥ አማናዊ ወይም የኦሪት ምሳሌ ሳይሆን የምሳሌውን እውነተን ማረጋገጫ ነው። ለምሳሌ፦ 

 – በብሉይ ኪዳን የነበረው የአዲስ ኪዳን ምሳሌ ነበር። ክርስቶስ ስለእኛ ብሎ በመስቀል ላይ የቆረሰው ቅዱስ ስጋውን እና ያፈሰሰውን ክቡር ደሙ አማናዊ ቅዱስ ቁርባን በመባል ይጠራል። ምክንያቱም የዘለዓለም ህይወት የማይሻር፣ የማይለወጥና የማይሻሻል ፍፁም ስለሆነ  አማናዊ ይባላል።

– ድንግል ማርያምም ከሷ ቀዳማዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ሰው እንደሚሆን በትንቢትና በምሳሌ ሲነገር ቆይቶ እንደተባለውም ስትወልድ በአይናችን አይተን በእጃችን ዳሰን ስላረጋገጥን አማናዊ እናታችን ወላዲተ አምላክ ትባላለች።

– እንዲሁም በብሉይ ኪዳን የነበረው ቤተመቅደስ ስርዓተ ኦሪቱ ሲፈፀምበትና ሲከናወንበት የነበረ ሲሆን ለአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ያንኛው ምሳሌ ነበር ምክንያቱም የሚያልፈው ያ በጊደር በጥጃ በበግ በፍየል  በአጠቃላይ በእንስሳ ደም ይሰዋበት የነበረው የሚያልፈውና የሚሻረው መስዋዕት ነበርና በአዲስ ኪዳን ግን አማናዊ የሆነው ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ የሚፈተትበት አማናዊት ቤተክርስቲያን ስለሆነች በዚህ ምክንንያት አማናዊት እንላታለን። የሰማያዊት እየሩሳሌምና የሰማያዊው ቤተመቅደስ መገለጨማም ስለሆነች አማናዊት እንላታለን። 

ስለዚህ አማናዊ በሚል የሚጠሩ የአዲስ ኪዳን በቋሚነት የእግዚአብሔር ምስጢራት የሚገለፁባቸው ናቸው።

ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ

👉🏾👉🏾👉🏾 የ #ትንሰኤ የመጀመሪያው ዓርብ

የፋሲካ ሥድስተኛዋ ቀን ዓርብ #ቤተክርስቲያን ትባላለች፡፡

(ክፍል አምስት)

ቅድስት  ቤተ  ክርስቲያን   በክርስቶስ  ደም ተዋጅታ  የተመሠረተች ደመ መለኮት የነጠበባት ናትና ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር የሚፈተትባት በመሆኑዋ  ይቺን እለት ሊቃውንት አባቶቻችን ቤተ  ክርስቲያን   ብለዋታል ፡፡

ቤተክርስቲያን የተመሰረተችው በክርስቶስ ደም በመሆኑ ይህች ዕለት ለቤተ ክርስቲያን ታላቅ  መታሰቢያ ሆና ተሰጥታለች፡፡ የቤተ ክርሰቲያን ሊቃውንት መምህራን እንደሚያስተምሩት ዛሬ ቤተክርስቲያን የምትታነጸው እርሱ እግዚአብሔር በሚያውቀው ድንቅ ጥበቡ በእለተ ዓርብ ቅዱሳን መላእክት ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብለው ነበርና ዓለምን ዙረው የክርስቶስን ደም ረጭተዋልና ዛሬ ቤተ ክርሰቲያን የምትታነጸው ደሙ ባረፈበት ወይም በነጠበበት እንደሆነ የነገራል፡፡ከዚህ አንጻር የዛሬዋ እለት ቤተ ክርስቲያን ትባላለች፡፡

በሌላ መልኩ የዛሬዋ ዓርብ ፀአተ ሲኦልም ትባላለች፡- ነፍሳት ከ5500 ዘመናት በሁዋላ ከሲዖል የወጡባት ጌታችን በዕለተ ዓርብ በመልዕልተ መስቀል ቅዱስ ሥጋውን ቆርሶ ክቡር ደሙን አፍስሶ በአካለ ነፍስ ወደ ሲዖል ወርዶ በሲዖል ያላችሁ ውጡ በጨለማ ያላችሁ ተገለጡ ብሎ ግእዛነ ነፍስን የነፍስን ይኸውም የነፍሳትን ነፃነት ሰበከላቸው ሰይጣንን አሰረው ሲዖልንም መዘበረው ነፍሳትን ነፃ አወጣቸው ልምላሜ ገነትን አወረሳቸው ይህ ዕለት ጌታችን በተነሳ በስድስተኛው ቀን  ዓርብ እንዲታሰብ  ፀአተ ሲኦልም የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ 

ንስሐ ገብተን ሥጋውን በልተን ደሙን ጠጥተን የመንግሥቱ ዋራሾች እንሆን ዘንድ አምለከ ቅዱሳን በቸርነቱ ያድለን፡፡

6. የፋሲካ 7ኛዋ ቀን ቅዳሜ

የፋሲካ 7ኛዋ ቀን ቅዳሜ አንሰት ወይም ቅዱሳት አንስት በመባል ትታወቃለች፡፡

ለምን የፋሲካ 7ኛ ቀን ቅዳሜ አንሰት ወይም ቅዱሳት አንስት ተባለች?

(ይቀጥላል)

ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q

መሰረታዊ ትምህርት

(አመታዊ የስላሴ ክብረ በዓልን በማስመልከት የተጻፈ)

“ገሀሡ አጋዕዝትየ ቤተ ገብርክሙ አብርሃም”

“ጌቶቼ ወደ ቤት ገብታችሁ እረፉ” ዘፍ 18:3

ሐምሌ 7 ቀን የአጋዕዝተ ዓለም ቅድስ ስላሴ በዓል በየአመቱ የምናከብርበት ዋና ምስጢራዊ ምክንያቱን በአጭሩ እንደሚከተለው እናቀርባለን።

በቅድሚያ ስለ ስላሴ ሦስትነትና አንድነት በአጭሩ ግንዛቤ ማስጨበጥ ስለሚያስፈልግ፤ ስላሴ የሚለው ቃል “ሠለሰ” ሦስት አደረገ ከሚለው የግእዝ ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሦስት መሆን ሦስትነት ማለት ሁኖ በምስጢራዊ አገላለጹም አንድም ሶስትም (አንድነት ከሶስትነት) ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። የስላሴ ሶስትነታቸው በስም፣ በግብር፣ በአካል ነው። አንድነታቸው ግን በባሕርይ፣ በህልውና፣ በመለኮት፣ በስልጣን፣ በአገዛዝ፣ በፈቃድ፣ ሁሉንም ስነፍጥረት በየወገኑ በመፍጠር ነው።

የስላሴ ሶስትነት ፡ –

  1. የስም ሶስትነት ማለት፡- አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ማቴ 28:19
  2. የአካል ሶስትነት ማለት፡- ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ፤ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ፤ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ አላቸው (ጥቅስ መዝ 33:14፣ 118:73፣ ኢሳ66:1 ፣ ዘፍ18:1-4 ማቴ 3:16)
  3. የግብር ሶስትነት ማለት፡- የአብ ግብሩ መውለድ ማሥረጽ፤ የወልድ ግብሩ መወለድ፤ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረጽ

አብን ወላዲ፣ ወልድን ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስን ሠራጺ ስንል ስለግብር ሶስትነታቸው ነው እንጂ እነሱማ አንዱ ከአንዱ የማይበልጥ፣ አንዱ ከአንዱ የማያንስ ዕለ እሩያን ናቸው።(ዩሓ 10:30) ቅድስት ስላሴ ስንል ቅድስት የሚለው ቅጽል ለሴት የሚሰጥ ቅጽል ቢሆንም ስላሴ በባሕርያቸው እንደ እናት ባሕርይ ስለሚመስሉ ነው። ልጅ ከእናቱ ባሕርይ እንደሚገኝ ይህ ዓለም ከስላሴ ባሕርይ ተገኝቷልና ነው። እናት ለልጇ የሚያስፈልገውን አስባ ተጨንቃ እንደምታቀርብለት ሁሉ፤ ስላሴም ለፈጠሩት ፍጥረት ሁሉ ከወዳድ እናት በላይ ስለሚያስቡ የሚያስፈልገውን ሁሉ አስቀድመው አዘጋጅተዋል (ማቴ 6:14)

በ40 በ80 ቀኑ የስላሴን ልጅነት አግኝቶ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሁሉ አስቀድሞ የስላሴን አንድነት ሦስትነት ወይም ስለምስጢረ ስላሴ መማርና ማወቅ መንፈሳዊ ግዴታው ነው። ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ማን ፈጠረህ ተብሎ ቢጠየቅ መልስ እንንዳያጣና መናፍቃንና ኢአማንያን በዘረጉት የክህደት ጉድጓድ ውስጥ እንዳይወድቅ ሊጠነቀቅ ይገባዋል።

ሐምሌ 7 ቀን ወደሚከበረው በዓል ስንመጣ የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ዘመን ጀምሮ አባታችን አዳምና እናታችን ሄዋን በምክረ ሰይጣን ተጠልፈው  ከወደቁ በኋላ የሰው ልጅ የሆነው ሁሉ በዲያብሎስ ቅኝ ግዛት (በሞት ጥላ ሥር) የወደቀ ቢሆንም እንኳ ከአዳም ልጅ ከአቤል ጀምሮ አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረጉ ብዙ ቀደምት አበው እንደነበሩ መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል።

ከቀደሙት አበው መካከልም አባታችን አብርሃም ይገኝበታል። አባታችን አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅና ታማኝ ሰው እንደነበረ በቅዱስ መፅሐፍ ውስጥ በብዙ ቦታ ተጠቅሶ ይገኛል።አብርሃም በዘመኑ ከነበሩ ጣዖት አምላኪዎች ራሱን በመለየት እውነተኛውን አምላክ ፈልጎ ለማግኘት በፍጹም እምነት በስነፍጥረታት ተመራምሮ የፈጣሪን ሥራ እያደነቀ በነበረበት ጊዜ እግዚአብሔር ለሚፈልጉትና ለሚጠሩት ሁሉ አቤት የሚል የቅርብ አምላክ ነውና በከራን ምድር ለወዳጁ ለአብርሃም ተገልጾ “ከሃገርህ ከአባትህ ቤትና ከዘመዶችህ ተለይተህ እኔ ወደማሣይህ ምድር ውጣ” ታላቅ ህዝብም አደርግሃለሁ…የሚባርኩህን እባርካለሁ የሚረግሙህንም እረግማለሁ የምድር ነገዶች ሁሉ በአንተ ይባረካሉ” ዘፍ12:1 በማለት የጥሪ ድምጹን በሰማው ጊዜ አብርሃም ለፈጣሪው ታማኝ ሰው በመሆኑ ሳይጠራጠርና ሣያመነታ ከሀገሩና ከቤተሰቡ (ከዘመዶቹ) ይልቅ የጠራውን አምላክ አምኖ በመቀበል እግዚአብሔር ወደመረጠለትና ወደ አዘጋጀለት ምድር (ወደ ምድረ ከነአን) ሊሄድ ችሏል።

አባታችን አብርሃም የእግዚአብሔርን ጥሪ ተቀብሎ ወደተዘጋጀለት ምድር ካቀና በኋላ እምነቱ ፍጹም ስለነበረ መላ ሕይወቱ የሚመራው በእግዚአብሔር ቸርነት ነበረ። በቅዱሳት መጽሐፍት ታሪክ ውስጥ አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ ተባለ። ዘርህን እነደ ሰማይ ከዋክብት እነደ ምድር አሸዋ አበዛለው ተብሎ እነደ አብርሃም የተባረከ ከቶ ማንም አልነበረም። ከዚህ የተነሳ አባታችን አብርሃም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር በማድረግ ቋሚ ሃብትና ንብረት ከማካበት ይልቅ በተመሣቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ተክሎ ዕለት ዕለት የወጣ የወረደውን ያለፈ ያገደመውን እንግድነት እየተቀበለ የሚኖር ሆነ። በዚህ የተቀደሰው ሥራው አብርሃም በፈጣሪው ዘንድ ትልቅ ሞገስና ክብርን አገኘና ፀጋው እየበዛ እንደሆነ ያወቀው ጥንተ ጠላት ሰይጣን በምቀኝነት ተነሣስቶ በምትሃት ራሱን በድንጋይ ገምሶ ደሙን በማፍሰስ አጥንቱ ተከስክሶ የተጎዳ ሰው በማስመሰል በትልቅ ጎዳና ላይ ተጠምጦ ወደ አብርሃም ቤት የሚመጡትን እንግዶች ወዴት ትሄዳላችሁ በሚላቸው ጊዜ ርቦን ሊያበላን ጠምቶን ሊያጠጣን ከአብርሃም ዘንድ እንሄዳለን ሲሉት የወትሮው አብርሃም መሰላችሁ እንዴ እኔም እንደናንተ ያበላኝ ያጠጣኛል ብዬ ብሄድበት ራሴን ገምሶ አጥንቴን ከስክሶ ሰደደኝ ሲላቸው እነሱም እያዘኑ የሚመለሱ ሁነዋል። አብርሃምም ወደ ቤቱ የሚመጣ እንግዳ በመጥፋቱ ያለ አንዳች እንግዳ ምግብ የማይቆርስ መፍቀሬ እንግዳ ስለነበረ በፍጹም ልቡ እያዘነ እስከ 3 ቀን ያለ እንግዳ ግብር አላገባም (ምግብ አልበላም) ብሎ ሣይመገብ ቆይቷል።

በ3ኛው ቀን ግን ቀትር ላይ ከድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሣለ ስላሴ በታላላቅ ሽማግሌዎች ምሳሌ ሆነው በመምሬ አድባር ዛፍ ሥር ተቀምጠው ታዩት። አብርሃምም እነዚህን አረጋውያን ሽማግሌዎች የሚመስሉ እንግዶች በማየቱ ደስ ብሎት ወደ እነሱ ገስግሶ በመሄድ “ጌቶቼ ወደ ቤቴ ገብታችሁ እረፉ አላቸው” በጣም የደከማቸው መንገደኞች ይመስሉ ስለነበር ደክሞናል ሲሉት አንዱን አዝሎ ወደ ቤቱ ሲገባ ሁለቱ በግብር  አምላካዊ ቀድመው በቤቱ ውስጥ ተገኝተዋል። አብርሃምና ሣራም ለተከበረ እንግዳ መቅረብ የሚገባው የመስተንግዶ ዝግጅት በማድረግ የፍጥረት ሁሉ ባለቤት ስላሴን በቤታቸው አስተናግደዋል። ወደ ወዳጃቸው ወደ አብርሃም ቤት በዕንግድነት የገቡት ሰለስቱ ስላሴም የእጃቸው ፍጥረት ከሆነው ከአብርሃም እና ከሣራ እጅ የቀረበላቸውን መስተንግዶ (ምግበ ሥጋ) እንደበሉ እንደጠጡ ሁነው ለአብርሃም ያላቸውን ፍቅር ገልጸዋል።

ስላሴ ምግብ በሉ ማለት እሳት ቅቤን በላ እነደማለት ስለሚቆጠር የአብርሃምን በጎ ስራ በስላሴ ዘንድ የተወደደ መሆኑን ለማጠየቅ ነው። አብርሃም ፈጣሪውን በእንግድነት የተቀበለ ብቸኛ ሰው ነው። ለመስተንግዶ የታረደው ወይፈንም ተነሥቶ ለአብ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና እንደሚገባ መስክሯል። በቤቱ የተገኙት ሦስቱ ስላሴም ለአብርሃም የአንድነትን ነገር ሲገልጹለት “የዛሬ ዓመት እነደዛሬው ወደ አንተ በእውነት እመለሣለሁ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች አለ” (ዘፍ 18:10) የሚለው አገላለጽ የአንድነትን ሚስጥር ያመለክታል። በዚህ መሠረት አብርሃም የስላሴን አንድነትና ሦስትነት (ምስጢረ ስላሴን) የማወቅ ምስጢር ተገልጾለታል። ልጅ በማጣት አዝነው የነበሩትን በእርጅና ዘመናቸው በልጅ ተባርከዋል። ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለመኖሩንም አረጋግጠዋል። የወደፊት ተስፋቸውን ከነገራቸው በኋላ በሰዶምና በጎመራ ስለሚሆነው የእግዚአብሔር ቁጣ እና የሰዎች ጥፋት እግዚአብሔር አምላክ ለወዳጁ ለአብርሃም ሣይደብቅ በግልጽ ተናግሮታል። አባታችን አብርሃም የአማላጅነት ጥያቄ አቅርቦ እግዚአብሔር አምላክም ስለወዳጁ አብርሃም ጥቂት ደጋግ ሰዎች እንኳ ቢኖሩ እንደሚምርለት ቃል እንደገባለት እንመለከታለን። (ኦሪት ዘፍ18) ባጠቃላይ ሐምሌ ስላሴ የምናከብረው በዓል ከላይ የገለጽነውንና ሌሎችን የእግዚአብሔር ሥራዎች የምንዘክርበት ታላቅ በዓል ነው።

የቅድስት ሥላሴ ቸርነት እና ምህረት በሁላችን ላይ ይደርብን።

ነገረ ተዋህዶ (ነገረ ክርስቶስ)
 
እየሱስ ክርስቶስ በእውነት የባሕሪይ አምላክ ነው

የተከበራችሁ እና የተወደዳችሁ የዚህ የዮሐንስ ንስሐ መንፈሳዊ ድረ ገጽ ተከታታይ አባላቶቻችን ሁላችሁም፦

ከጥንት ዘመን ጀምሮ፥ ሰይጣን በራሱ አላማ ያሰለፋቸው የክህደት እና የምንፍቅና ሰዎች፥ በፈጠጠው አይናቸው ያዩትን፣ በጆሮዋቸው የሰሙትን፣ በእጃቸው የዳሰሱትን፥ እውነተኛውንና የተረጋገጠውን ትምህርተ መለኮት ፥ ማወቅ እና መረዳት ሲገባቸዉ፤ ነገር ግን፥ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ዓለማዊ እውቀት እና የልብ ወለድ ትምህርት በመቁጠር፥ እንደራሳቸው ሃሳብ እና በራሳቸው አገላለፅ የእግዚአብሔርን ቃል እየመነዘሩ ትርጉሙን እያጣመሙ ሰዉንም እያሳቱ የመታየታቸው ነገር እጅግ ያሳዝናል። ከዚህም በላይ ፥ የባሕሪይ አምላክ የሆነውን ክርስቶስን እንደ ፍጡር በመቁጠር፥ ወይም እንደ አማላጅነት በማድረግ፤ እንዲሁም፥ እግዚአብሔር ያከበራቸውን፦ እናቱን ወላዲት አምላክን እና ቅዱሳንን፥ አያማልዱም በማለት፥ በድፍረት ቃል የሚናገሩ፥ ብዙዎች አሉ። ስለሆነም መናፍቃን በሚዘሩት እንክርዳድ ትምህርታቸው ሳትሰናከሉና ሳትወናበዱ፣ የመንፈስ ብዥታም ሳይፈጥርባችሁ፥ በሃይማኖትና በምግባራችሁ ጸንታችሁ ትቆሙ ዘንድ እንመክራለን። ለዚህም ፥ እናታችን ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምስጢር ባለቤት፣ ትርጓሜ ባለቤት፣ የብዙ ሊቃውንት ባለቤት ስለሆነች፤ በሃይማኖት እንዳትበደሉ ወይም በክህደት ትምህርት እንዳትወሰዱ ይህን መሰረታዊ ትምህርት አዘጋጅተንላችኋል። ይህንን የክርስቶስ የባሕሪይ አምላክነት ትምህርት በአጭሩም ቢሆን ለብዙዎቻችሁ አንድትጠቀሙበት ቀለል ባለ አቀራረብ ዛሬ መጋቢት 27 ቀን የምናከብረውን አመታዊ በአል በማስመልከት በስድስት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ተመርኩዘን እንደሚከተለው በድጋሚ ያዘጋጀንላችሁ ስለሆነ ሳትሰለቹ ጥቅሶችንና ማብራሪያዎችን በደንብ አንብባችሁ ትረዱ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላችኋለን።  

1ኛኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት የባሕርይ አምላክ ነው

2ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነው

3/ ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት የሰው ልጅ ነው 

4/ ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት እርሱ ክርስቶስነው

5/ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በእውነት እውነተኛ አምላክ ነው

6ኛ/  ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት የጌቶች ሁሉ ጌታ ነው 

መግቢያ 

ቀዳማዊ ቃል፥ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ከድንግል ማርያም ተወልዶ፣ ሥጋን ተዋህዶ ሰው በሆነ ጊዜ፤ ከተጠራባቸው የ ተዋህዶ ስሞቹ አንዱ፥ ‘ኢየሱስ’፥ የሚለው ሲሆን፥ ምስጢራዊ ትርጓሜው ‘መድኃኒት’ ማለት ነው።

ቅዱስ ሉቃስም በፃፈው ቅዱስ የወንጌል ቃል ላይ፤ “መድኃኒት፣ እርሱም ክርስቶስ፣ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፤” በማለት መድኃኒት የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ መወለዱን ባበሰረበት የወንጌል ቃል ይገልፃል።(ሉቃ 2፥11)

ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስም እንደፃፈው፦ ሳምራዊቷ ሴት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባነጋገራት ጊዜ፥ የአምላክነቱ ምስጢር ተገልፆላት ነበርና ፥ ስለ መሰከረችው ቃል ከዚያች ከተማ የሰማርያ ሰዎች ብዙ አመኑበት። የሰማርያ ሰዎችም የጌታ ቃል ከሰሙ በኋላ “አሁን የምናምን ስለ ቃልሽ አይደለም፤ እኛ ራሳችን ሰምተነዋልና፤ እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን ይሉአት ነበር።”  (ዮሐ 4፥42)

ኢየሱስ ክርስቶስ ማለት፥ የመለኮታዊ ቃል የትስብዕት ስም ብቻ ያልሆነ፣ ከሁለት ባህሪይ- አንድ ባሕሪይ፣ ከ ሁለት (አካል)፦ አንድ አካል ሆኖ፥ ‘አምላክ ወሰብእ’ ተብሎ የተጠራበት፥ የሥጋዌ ስሙ ነው። ሌሎቹም ስሞቹ፥ ለምሳሌ፦ ክርስቶስ፣ አማኑኤል፣ መድኃኒዓለም ወዘተ የተባሉት ስሞቹ፥ አካላዊ ቃል ሥጋን በተዋሀደ ጊዜ የተጠራባቸው ሲሆኑ፥ ትርጓሜውም በዚሁ ዓለም ሳለ በአምላክነቱ እና እንደ ሰውነቱ የፈፀማቸውን ልዩ ልዩ ተአምራትና የቃሉ ትርጉም ያመላክታል።

የእሱ ስሞች ባሕሪይውን እና ስራውን የገለፀባቸው ናቸው። እኛ ሰብአዊ ፍጡርን እንደምንጠራው አይነት (ክፉውን ሰው በመልካም ሰው ስም እንደምንጠራው ፣ ወይም ደጉን ሰው በክፉ ሰው ስም እንደሚጠራው) አይደለም፤ የእሱን ስሞች በመንፈሳዊ ጥበብ ካልሆነ በስተቀር፥ በሥጋዊ እውቀት ለመመርመር አይቻልም።  ኢየሱስ ክርስቶስ ‘የባህሪይ አምላክ’ ነው፥ ሲባል የማይጨበጠውን እና የማይዳሰሰውን የእግዚአብሔርነት ባሕሪይ ማለታችን ነው። ሁሉም ፍጥረት የራሱ የሆነ ደካማ፥ ወይም ጠንካራ ባሕሪይ አለው፤ የእግዚአብሔር ባሕሪይ ግን፥ ሥጋን እንደለበሰ፥ እንደማንኛውም የሰው ልጅ ባህሪይ፥ (ሰብዓዊ ባህሪይ) አይደለም። እንዲህ፥ ሲባል ግን፥ ለልባሞች ካልሆነ በስተቀር፥ ለሰነፎች ፈፅሞ ሊረዱትም ሆነ፣ ሊገባቸው አይችልም። ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ ካልገለፀለት በስተቀር፣ የእግዚአብሔርን ባሕሪይ የፍጡር ሰብአዊ እውቀት ሊመረምረው ስለማይችል፥ በሃይማኖት እና በምግባር ልባሞች ያልሆኑ ሰነፍ ሰዎች፥ በስጋ ጥበብ ባሕሪየ ክርስቶስን ይመረምሩ ዘንድ ፈጽሞ አይቻላቸውም። (1ኛ ቆሮ 2፥ 7 -16)

በ325 ዓ.ም. አርዮስና ተከታዮቹ፥ በምሳሌ 8፥22 እንዳለው ቃል ፥ ባልተረዱት እና ባላወቁት ምስጢር- የክርስቶስን ባሕሪይ በስጋ ጥበብ ሊመረምሩ በመሞከራቸው፥ ኢየሱስ ክርስቶስን- ያህል አምላክ፣ እና መንግስተ ሰማያትን – ያህል ርስት (ስፍራ) አጥተዋል። ዛሬም በዘመናችን ለብዙዎቹ ያልተረዳቸው ይኸው ‘ክርስቶስ፥ የባሕሪይ አምላክ ነው’፥ የሚለው ምስጢር ነው። ይህን ጥበብ ከማየት የተከለከሉ እጅግ ብዙዎችም ናቸው። “የእግዚአብሔር ኀይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የኾነው ክርስቶስ ነው።” (በ1ኛ ቆሮ 1፥24) 

ጥበብ በክርስቶስ ተጠቅሷል። “የተሰወረ የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ በእርሱ ነውና።” (ቆላ 2፥3) 

ክርስቶስ ወልድ፥ ‘አባቴ ወለደኝ ፣ከአብ ወጥቼ ወደ አለም መጣሁ፤’ አለ እንጂ፥ በአንድም ቦታ፥ ‘ፈጠረኝ’ ብሎ አላለም። (የሐ16፥ 28 ፣ መዝ 110፥3)

መውለድ እና መፍጠር፥ የሰማይ እና የምድር ያህል ሁለት የተለያዩ  እና የተራራቁ ነገሮች ናቸው። ማንም፥ የሚወልደውን- አይፈጥረውም፥ የሚፈጥረውንም -አይወልደውም።

++++++++

የአብ የመዉለድ፣ የወልድ መወለድ፥ በሥጋ ለባሽ ስርዓት ወይም ድርጊት ሕግ የሚተረጐም አይደለም። ሰዉ ህልውናውን የሚጀምረው በዘመን ነው፤ ለእሱ ግን፥ ዘመን አይቆጠርለትም። በአንድ ወቅት ልጅ ይባል የነበረው፥ በሌላ ጊዜ ፥ አባት ይባላል፤ ልጅ ያለ አባት አይኖርም። በአብ እና በወልድ ግን፥ እንደዚህ አይነት የለም። የስም ለውጥም ሆነ የአካል ለውጥ የለም። አብም፥ አባት ሲባል ይኖራል፥ ወልድም፥ ሁልግዜ ፥ ፍጻሜ የማይኖረው፥ ወልድ ሲባል ይኖራል።

ወደ መጀመሪያ ርዕሰ ስንመለስ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም የባሕሪይ አምላክ ነው እንጂ መናፍቃን እንደሚሉት በአብ የተዘጋጀ ትንሽ አምላክ አይደለም።  ከአንድ አምላክ ውጪ፥ ሌላ ትንሽ አምላክ እንዳለ፥ የሚመሰክር ፥ መጽሐፍም ሆነ እውነተኛ አማኝ፥ እስካሁን አልተገኘም።

1ኛኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ነው

ቅዱሳት መጻሕፍትም፥ የክርስቶስን፥ የባሕሪይ አምላክነት፥ ወይም እግዚአብሔርነት በእርግጠኝነት ይመሰክራሉ።

ማስረጃ: –

  1. ህፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነት በጫንቃው ላይ ነው፤ ስሙም፦ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ፥ ተብሎ ይጠራል።” (ኢሳ 96)
  2. አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ ከአንቺ ግን አወጣጡ፦ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ፤ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል” (ሚክ 53)
  3. ከዚችም ዓለም ገዥዎች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውትስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር” (1ቆሮ 28)
  4. በእርሱ፥ የመለኮት ሙላት ሁሉ፥ በሰውነት ተገልፆ ይኖራልና። ለአለቅነት እና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል።” (ቆላ29:10)
  5. ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው” (ሮሜ95)
  6. አምላካችንና አባታችን ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ” (1 ተሰ 3 11) 
  7. የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር፥ መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በፅድቅ፣ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንኑር” .( ቲቶ2 13:14)
  8. እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።” (1 የዮሐ መልዕክት 520)
  9. በክርስቶስ ትምህርት ለማይኖር ሰው፥ አምላክ የለውም። ክርስቶስ ትምህርት ለሚኖር አብና ወልድ አሉ ት። ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ፥ ይህንም ትምህርት ባያመጣ፥ በቤታችሁ አትቀበሉት፣ ሰላምም አትበሉት፤ ሰላም የሚለው ሰው በክፉ ሥራው ይካፈላልና.” (2 ዮሐ 19-11)
  10. ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፣ በክብሩም ፊት፥ በደስታ፥ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ፥ ለሚችለው፥ ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን፤ ከዘመን ሁሉ በፊት፣ አሁንም፣ እስከ ዘላለምም ድረስ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፥ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።” (ይሁዳ 24 25) 10. “ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፣ በክብሩም ፊት፥ በደስታ፥ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ፥ ለሚችለው፥ ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን፤ ከዘመን ሁሉ በፊት፣ አሁንም፣ እስከ ዘላለምም ድረስ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፥ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።” (ይሁዳ 24 25)
  11. ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።” (ዮሐ219)
  12. ነፍሴን በፈቃዴ አሳልፌ እሰጥ ዘንድ ስልጣን አለኝ፤ አስነሳትም ዘንድ ስልጣን አለኝ” (ዮሐ1018)
  13. ድሆችስ፥ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር፥ ይኖራሉና፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም አለ። (ዮሐ128)
  14. ሰንበትን የፈጠረ እግዚአብሔር ሲሆን ፈሪሳውያን ስለ ሰንበት መሻር ሲጠይቁት፥ እሱ የሰንበት ጌታ መሆኑን ገለፀላቸው (ማቴ12 8)
  15.  “ቶማስም ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት፤ ኢየሱስም፥ ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው አለው” (ዮሐ 202829)   

በዚህ ኃይለቃል እንደምንመለከተው፥ ቶማስጌታዬ አምላኬባለው ጊዜ፥ ኢየሱስ ቶማስንአምላክ አትበለኝአላለውም፥ስለ አየኸኝ አምነሃልብሎ አለው እንጂ። 

  1. እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።“( ዮሐራዕ 22 12)

በተጫሪም፤ በሥጋ የተገለጠው ክርስቶስ፥ ዋጋ ከፋይ እንደሆነ እና ፊተኛውና መጨረሻው እሱ እንደሆነ፥ እንደተናገራቸው በብሉይም (ኢሳ 414 446 4812 እንዲሁም ዮሐራዕ (22 12) (18 እና 11) በተደጋጋሚ ተፅፏል።

  1. አባቴ ሁል ጊዜ ይሰራል፤ እኔም ፥ደግሞ፥ እሰራለሁ።” (ዮሐ 517)
  2. ተግሣጹን ተቀበሉ፥ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፤ ቍጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።” (መዝ212)
  3. ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውሀን በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ፥ ስሙ ማን የልጁስ ስም ማን ነው?” (ምሳሌ304)
  4. እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።” (መክ1214)
  5.  “ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።” (ማቴ1127)
  6. በነቢዩ በኢሳይያስ፥ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ የተባለለት ይህ ነውና።”(ማቴ33)
  7. አምላክ ሆይ፦ ዙፋንህ እስከ ዘለዓለም ድረስ ይሰራል፤ የመንግስትህም በትር የቅንነት በትር ነው”(ዕብ 168)

2ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነው

ቅዱሳት መጻሕፍትም፥ ኢየሱስ ክርስቶስ፥ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን በእርግጠኝነት ይመሰክራሉ።

ማስረጃ: –

  1. “እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።” (ማቴ 3፥1)
  2. በታንኳይቱም የነበሩት። በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብለው ሰገዱለት።” (ማቴ 1433)
  3. ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፤ አንተ ክርስቶስ፥ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።” (ማቴ 1616)
  4.  “ደመናም መጥቶ ጋረዳቸው፥ ከደመናውም፥ የምወደው ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።” (ማር 97)
  5. የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።” (ማር11)
  6. በዚያም በአንጻሩ የቆመ የመቶ አለቃ፥ እንደዚህ ጮኾ ነፍሱን እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ፦ይህ ሰው በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረአለ።” (ማር 1539)
  7.  “እንግዲያስ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህን? አሉት። እርሱም፥ እኔ እንደ ሆንሁ እናንተ ትላላችሁ አላቸው።” (ማር 1539)
  8. ማርታም፥ አዎን ጌታ ሆይ፥ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ አለችው። ” (ዮሐ 1127)
  9. ወዲያውም፥ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ፦ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ፥ በምኵራቦቹ ሰበከ።” (የሐዋ 920)
  10. ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።” (ገላትያ 2 20)
  11. በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ፣ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ፤ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ፥ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ።” (ኤፌ 212)
  12. ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ምንም ብታውቁ በእናንተም ዘንድ ባለ እውነት ምንም ብትጸኑ፥ ስለ እነዚህ ዘወትር እንዳሳስባችሁ ቸል አልልም።” (2 ጴጥ 1 12 )
  13.  (ዕብ 11-15)

3/ ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት የሰው ልጅ ነው 

ማስረጃ: –

  1. “ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” (ኢሳ 7 ፥ 14)
  2. “ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።” (ኢሳ 9፥6)
  3. “እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ፥ አሥራ አራት ትውልድ ነው።” (ማቴ 1፥117)
  4. “ኢየሱስም፤ ለቀበሮዎች ጉድጓድ፣ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፤ ለሰው ልጅ ግን ፥ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም፥ አለው። ” (ማቴ 8፥20 )
  5. “ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱን፥ ‘ሰዎች የሰውን ልጅ፥ ማን እንደ ሆነ ይሉታል?’ ፥ብሎ ጠየቀ።” (ማቴ 16፥13) 
  6. የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል፥ ከሽማግሌዎችም ከካህናት አለቆችም ከጻፎችም ሊጣል፥ ሊገደልም ከሦስት ቀንም በኋላ ሊነሣ እንዲገባው ያስተምራቸው ጀመር፤ ቃሉንም ገልጦ ይናገር ነበር። ” (ማር 8 31)
  7. በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በብዙ ኃይልና ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።” (ማር 13 26)
  8. በዚያም በአንጻሩ የቆመ የመቶ አለቃ እንደዚህ ጮኾ ነፍሱን እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ። ይህ ሰው በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ አለ። ” (ማር 15 39 )
  9. ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር ” (ሉቃ 3 23)
  10. እላችሁማለሁ፥ በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል፤ ” (ሉቃ 12 8)
  11. የሰው ልጅም ስለ ሆነ ይፈርድ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው። ” (ዮሐ 5 27)
  12. ነገር ግን አሁን ከእግዚእብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ፥ አብርሃም እንዲህ አላደረገም። ” (ዮሐ 8 40)
  13. ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፤ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን።” (ሮሜ 95)
  14. እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” (1 ጢሞ 2 5)
  15. እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።” (1 ወደ ጢሞ 3 16)
  16. የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ ታውቃላችሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደ መጣ የሚታመን መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፥” (1 ዮሐ 4 2)

4/ ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት እርሱ ክርስቶስነው

ማስረጃ: –

  1.  “የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።” (ማቴ 11)
  2. እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።” (ማቴ 161 8)
  3. የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው፤ እነርሱም፥ . . .  ‘አንቺ  ቤተልሔም የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን፥ ከአንቺ ይወጣልና፤ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና፦ በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት።” (ማቴ 24-6 )
  4. ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ። አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ፥ . . .  ያን ጊዜም እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለማንም እንዳይነግሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው። . . . ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ፥ አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ። እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን። ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።” (ማቴ 16162022)
  5. የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ፣ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥ (ማቴ 13.41)
  6. እንግዲህ እነርሱ ተሰብስበው ሳሉ ጲላጦስ፥በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ማንኛውን ልፈታላችሁ ትወዳላችሁአላቸው። . . .  ጲላጦስ፥ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን እንግዲህ ምን ላድርገውአላቸው። ሁሉም፥ ይሰቀል አሉ።” (ማቴ 271722)
  7. የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፤ . . .  በልዩ ልዩ ደዌም የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፥ ብዙዎችንም አጋንንት አወጣ፤ አጋንንትም ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ነበርና፤ ሊናገሩ አልፈቀደላቸውም።” (ማር 1 134)
  8. ስለ እርሱም ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።” (ማር 8 30)
  9. የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ፥ በስሜ ጽዋ ውሀ የሚያጠጣችሁ ሁሉ፦ ዋጋው እንዳይጠፋበት፥ እውነት እላችኋለሁ።” (ማር 9 41)
  10. ኢየሱስም፥ እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ።” (ማር14 62)
  11. ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ፥ ተወልዶላችኋልና።” (ሉቃ 211 )
  12. አጋንንትም ደግሞ፥ አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፥ እያሉ እየጮኹም ከብዙዎች ይወጡ ነበር፤ ” (ሉቃ 441 )
  13. ክርስቶስ አንተ ነህን? ንገረን አሉት፤ እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ ብነግራችሁ አታምኑም፤” (ሉቃ 2267)
  14. ይህ ሕዝባችንን ሲያጣምም ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል ደግሞም፥ እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ ሲል አገኘነው ብለው ይከሱት ጀመር። ” (ሉቃ 232)
  15. ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው። ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም። ” (ሉቃ 245)
  16. ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ። ” (ዮሐ 1 1720 )
  17. ሳምራዊቲቱ፥ ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንዲመጣ አውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉን ይነግረናል አለችው።” (ዮሐ 4 25 )
  18. ስምዖን ጴጥሮስ፡ ጌታ ሆይ፥ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ” (ዮሐ 6 68 )
  19. እንግዲህ ከኢየሩሳሌም ሰዎች አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ። ሊገድሉት የሚፈልጉት ይህ አይደለምን? ” (ዮሐ 7 25)

5/ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በእውነት እውነተኛ አምላክ ነው

ማስረጃ: –

  1. መጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ” (ዮሐ 1 1 )
  2. እኔና አብ አንድ ነን። አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ። ኢየሱስ ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ ማናቸው ሥራ ትወግሩኛላችሁ? ብሎ መለሰላቸው። አይሁድም፦ ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት። ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦እኔ አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን? መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፥ ትሳደባለህ ትሉታላችሁን? እኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ፤ ባደርገው ግን፥ እኔን ስንኳ ባታምኑ አብ በእኔ እንደ ሆነ እኔም በአብ እንደ ሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ። እንግዲህ ደግመው ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም ወጣ።” (ዮሐ 10 30-39)
  3. ቶማስም፥ ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።” (ዮሐ 20 28 )
  4. በገዛ ደሙ የዋጃትን፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ፥ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት፥ ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ፥ ተጠንቀቁ።” (የሐዋ 20 28 )
  5. አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው፤ አሜን። ” ( ሮሜ 9 5 )
  6. እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ፥ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥” (ፊልጵ 2 6)
  7. ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤” (ቲቶ 2 13)
  8. ስለ ልጁ ግን፥ አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።” (ዕብ 1 8)
  9. የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው። ” (1 ዮሐ 5 20)
  10. ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፤ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።” (ዮሐ 3 13)

6ኛ/  ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት የጌቶች ሁሉ ጌታ ነው 

ማስረጃ: –

  1. ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፤ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።” (ዮሐ 3 13)
  2. ፈሪሳውያንም ተሰብስበው ሳሉ፥ ኢየሱስ። ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው? ብሎ ጠየቃቸው። የዳዊት ልጅ ነው አሉት። እርሱም። እንኪያስ ዳዊት። ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል? ዳዊትስ ጌታ ብሎ ከጠራው፥ እንዴት ልጁ ይሆናል? አላቸው” (ማቴ 2242-45)
  3. እነሆም፥ ሁለት ዕውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው፥ ኢየሱስ እንዲያልፍ በሰሙ ጊዜ። ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረን ብለው ጮኹ።ሕዝቡም ዝም እንዲሉ ገሠጹአቸው፤ እነርሱ ግን። ጌታ ሆይ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረን እያሉ አብዝተው ጮኹ። ኢየሱስም ቆሞ ጠራቸውና። ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ? አለ። ጌታ ሆይ፥ ዓይኖቻችን ይከፈቱ ዘንድ አሉት” (ማቴ 2030-33)
  4. ማንምስለ ምን እንዲህ ታደርጋላችሁቢላችሁ፤ ለጌታ ያስፈልገዋል በሉት፥ ወዲያውም ደግሞ ወደዚህ ይሰደዋል አላቸው።” (ማር 11 3)
  5. ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ። እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።” (ማር 16 19-20)
  6. ዛሬ በዳዊት ከተማ፥ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ፥ ተወልዶላችኋልና። (ሉቃ 211 )
  7. ሐዋርያትም ጌታን፥ እምነት ጨምርልን አሉት። ” (ሉቃ 175)
  8. አባቴ እኔን እንደ ሾመኝ እኔ ደግሞ በመንግሥቴ ከማዕዴ ትበሉና ትጠጡ ዘንድ፥ በአሥራ ሁለቱ በእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በዙፋኖች ትቀመጡ ዘንድ ለመንግሥት እሾማችኋለሁ።” (ሉቃ 2230)
  9. እንግዲህ ደቀ መዛሙርቱ፥ ጌታ ሆይ፥ ተኝቶስ እንደ ሆነ ይድናል አሉት። . . . እርስዋም። አዎን ጌታ ሆይ፤ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆንህ እኔ አምናለሁ አለችው። ” (ዮሐ 11 1227)
  10. ወደ ስምዖን ጴጥሮስም መጣ፤ እርሱምጌታ ሆይ፥ አንተ የእኔን እግር ታጥባለህን‘  አለው።እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ፤ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ።” (ዮሐ 13 613 )
  11. ዳዊት ወደ ሰማያት አልወጣምና፥ ነገር ግን እርሱ ጌታ ጌታዬን፦ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው አለ። እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።” (የሐዋ 234-36 )
  12. ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤” (ሮሜ 10 9 )
  13. ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር፥ ኢየሱስ የተረገመ ነው የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር፥ ኢየሱስ ጌታ ነው ሊል አንድ እንኳ እንዳይችል አስታውቃችኋለሁ። ” (1 ቆሮ12 3 )
  14. ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ፥ ራሳችንን አንሰብክምና፤ ስለ ኢየሱስም ራሳችንን ለእናንተ ባሪያዎች እናደርጋለን።” (2 ቆሮ4 5 )

ስለዚህ ተከበራችሁ እና የተወደዳችሁ የዚህ የዮሐንስ ንስሐ መንፈሳዊ ድረ ገጽ ተከታታይ አባላቶቻችን ሁላችሁም፤ ይህንን የክርስቶስ የባሕሪይ አምላክነት ትምህርት ደጋግማችሁ አንብባችሁ ትረዱ ዘንድ በድጋሚ በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላችኋለን።

እግዚአብሔር ምስጢርና ጥበቡን ይግለጽልን።

ሥርዓተ ጸሎት
 
ጸሎት በሃይማኖት (በተአምኖ) የሚኖር ክርስቲያን ከፈጣሪው ጋር የሚነጋገርበት ምስጢራዊ ቋንቋ ነው። ማንኛውም ክርስቲያንም ሆነ ምእመን በየዕለቱና በየሰዓቱ መጸለይ ክርስቲያናዊ ግዴታው ነው። የሰው ልጅ በሥጋዊ ባሕርይው ሣይበላ እና ሳይጠጣ መኖር እንደማይችል ሁሉ በየሰዓቱና በየጊዜያቱ ካልፀለየ ነፍስ ትራባለች፣ ትጠማለች መላ ሕይወቱም ከእግዚአብሔር በረከት ይርቃል። ስለዚህ ጸሎት በክርስትና ሕይወት ውስጥ እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚ ነው።
ከዚህ በመቀጠል በምን ጊዜ እና በምን ሰዓትና እንዴት መፀለይ እንዳለብን እንመለከታለን። 
7ቱ የጸሎት ጊዜያት (በ 24 ሰአት ውስጥ) ፦
1ኛ/  ጸሎተ ነግህ (የነግህ ጸሎት)
በዚህ ሰዓት መጸለይ የሚገባን የሌሊቱን እና የጨለማውን ግዜ አሳልፈን የቀኑን የብርሃኑን ጊዜ ስለአመጣልን በሰላምና በሙሉ ጤንነት ከመኝታችን ስለአስነሣን ሁሉ፣ በማታ የበላነው የጠጣነው ተስማምቶን ስላደረ፣ በጨለማው ከሚንቀሳቀሱ ሥጋውያንና ረቂቃን ጠላቶች ጠብቆ ስላሣደረን ለፈጣሪያችን የምስጋና ጸሎት እናቀርባለን። ነብዩ ቅዱስ ዳዊት “አምላኬ አምላኬ በማለዳ ወደ አንተ እገሰግሣለሁ” በማለት ከመኝታችን ተነሥተን በነግህ መጸለይ ስለሚገባን ይህን የጸሎት ጊዜ አስተምሮናል። (መዝ 62፥11)
 
የመጀመርያው ሰው አባታችን አዳም የተፈጠረበት ሰዓት በዕለተ ዓርብ በነግህ ስለሆነ ሁላችን የአዳም ልጆች በመሆናችን በአርአያውና በምሣሌው የፈጠረንን አምላክ በዚያው ሰዓት ማመስገን ይገባናል፤
 
የሰው ልጅ በሌሊቱና በመዓልቱ ክፍለ ጊዜ የሚጠብቁት መላእክት ስለሚታዘዙለት በሌሊቱ የሚጠብቀው መልአክ ሲሄድ የቀኑ መልአክ ሊጠብቀው የሚተካበትና የሚገናኙበት ጊዜ በመሆኑ እግዚአብሔር አምላክ በመላእክቱ ስለአደረገለት ጥበቃ መጸለይ ስለሚገባ ነው፤
 
ሌላውና ዋና ምክንያት ጌታችን መድኅኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስለአዳምና ስለልጆቹ ኅጢአት ዋጋ (የዕዳ ካሣ) ለመክፈል ሲል ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ ሲነጋ (በነግህ) አይሁድ በንጉሡ በጲላጦስ አደባባይ እንደ ወንጀለኛ ይዘው ያቀረቡበት ሰዓት ስለሆነ ይህንን በማሰብ እንፀልያለን። (ማቴ 27፥)
 
2ኛ/  በ3 ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት (ጸሎተ ሰለስቱ ሰዓት)
ከጠዋቱ 3 ሰዓት የምንጸልየው የጸሎት ሥርዓት የሶስት ሰዓት የጸሎት ክፍለ ጊዜ ይባላል። 
 
ይህ ሰዓት የሰው ልጅ ሁሉ የመጀመሪያ እናት የሆነችው ሄዋን የተፈጠረችበት ሰዓት ስለሆነ በዚህ ሰዓት እንፀልያለን፤
 
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ጌታን እንደምትወልደው ብስራቱን የነገረበት ሰዓት ስለሆነ እንጸልያለን፤
 
ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጅ በደል ሲል በአደባባይ የተገረፈበት ሰዓት ስለሆነ ይህንን እያሰብን እንጸልያለን፤
 
ነብዩ ዳንኤል በባቢሎን ሀገር በስደት (በምርኮ) በነበረበት ሰዓት ቅድስት ሃገር እየሩሳሌምን እያሰበ ፊቱን ወደ እየሩሳሌም አቅጣጫ አዙሮ የቤቱን መስኮት ከፍቶ የጸለየበት ሰዓት ስለሆነ ነው፣
 
ለቅዱሳን ሐዋርያትም በበዓለ ሃምሣ መንፈስ ቅዱስ የወረደላቸው በ 3 ሰዓት ስለነበረ እግዚአብሔር ለሁላችንም የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ እንዲበዛልን እንፀልያለን።
 
3ኛ/  በ6 ሰዓት የሚጸለይ ጸሎት (ጸሎተ 6ቱ ሰዓት)
ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ እንድንጸልይ በሕገ ቤተክርስቲያን ታዟል። ይህ ጊዜ ሰይጣን፤ አባታችን አዳምን እና እናታችን ሄዋንን ያሳተበት ሰዓት ስለሆነ፣
 
በዕፀበለስ መብላት 5500 ዘመን የተፈረደባቸው አዳምና ልጆቹን ለማዳን ሲል ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ከቀኑ 6 ሰዓት ሲሆን በጠራራ ፀሐይ በአይሁድ እጅ በቀራንዮ አዳባባይ የተሰቀለበት ሰዓት ስለሆነ የእሱን መከራ መስቀል እያሰብን ከጸብአ አጋንንት እንዲጠብቀን መፀለይ አለብን። (ዮሐ 19፥14)
 
ነብዩ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በቀትር ወደፈጣሪው ይጮህና ይጸልይ እንደነበረ በቀረበ የመዝሙር ምስጋና ሲናገር “እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር ጮህሁ እርስም ሰማኝ በማታና በጧትም በቀትርም እናገራለሁ እጮህማለሁ ቃሌንም ይሰማል”ብሏል (መዝ 54፥17)
 
4ኛ/   በ 9 ሰዓት የሚጸለይ (ጸሎተ ተስዓቱ ሰዓት)
ከቀኑ 9 ሰዓት ሲሆን አራተኛው የጸሎት ሥርዓት እናደርሳለን። በዚህ ሰዓት የምንጸልይበት ዋናው መሰረታዊ ምስጢር ፦
 
ጌታችን መድኅኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለአዳም እና ለሰው ልጅ ሁሉ ቤዛ ለመሆንና ከዲያብሎስ የባርነት አገዛዝ ነፃ ለማውጣት በገባው ቃል መሠረት በዕለተ አርብ ሁሉንም ህማማተ መስቀሉን ከተቀበለ በኋላ “ሁሉ ተፈፀመ” ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በራሱ ስልጣን የለየበት ሰዓት ስለሆነ እና በመስቀል ላይ ሆኖ ሰባቱን አፅረሐ መስቀል የተናገረበት ሰዓት ስለሆነ የእኛን ሞት ለእሱ ወስዶ የእሱን ሕይወት ለእኛ ስለሰጠን ይህንን እያሰብን ልንፀልይ ይገባል። (ማር 15፥34፣ ማቴ27፥45-50)
 
ቅዱሳን መላእክት የሰው ልጅ ለፈጣሪው የሚያቀርበውን ምስጋናና መሥዋዕት (ጸሎትና ቅዳሴ) የሚያደርሱበት የሰዎችን በጎ ስነምግባር እና ክፉ ሥራቸውን ቅድመ እግዚአብሔር የሚያደርሱበት ሰዓት ነው።
 
ከጌታ 12 ደቀመዛሙርት መካከል ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስ በዘጠኝ ሰዓት ወደ ቤተመቅደስ ወጥተው ጸሎት ያደርሱ እንደነበረ በሐዋርያት ስራ ላይ ተመዝግቦ እናገኛለን። (የሐ 3፥1)
 
ቆርኖሌዎስ የተባለው የመቶ አለቃ ወደ ፈጣሪው ያቀርበው የነበረው ጸሎት ቅድመ እግዚአብሔር የደረሰለት በ 9 ሰዓት ነው። (የሐዋ10፥9) እኛም የቆርነሌዎስን ጸሎት የሰማ አምላክ የእኛንም ጸሎት እንዲሰማ በማሰብ በዚህ ሰዓት መጸለይ ይገናባል።
 
5ኛ/  የሠርክ ጸሎት (በ11 ሰዓት የሚጸለይ)
ለአምስተኛ ጊዜ በ 11 ሰዓት የሚጸለየው ጸሎት የሠርክ ጸሎት ይባላል።በዚህ ሰዓት በዘመነ ኦሪት መስዋዕት የሚቀርብበት ጊዜ እንደነበር በቅዱስ መጽሐፍት እንዲህ ሲል ተመዝግቦ እናገኘዋለን።
 
“አንዱን ጠቦት በማለዳ ቁርባን አድርገህ ታቀርበዋለህ፣ ሁለተኛውን ጠቦት በማታ ቁርባን አድርገህ ታቀርበዋለህ…” (ዘጸ 29፥39-42) ቅዱስ ዳዊትም “ፀሎቴን በፊትህ እንደ እጣን ተቀበልልኝ ፤ እጅ መንሣቴንም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ትርጋ” በማለት ስለ ሠርክ ጸሎት ወደ ቅድመ እግዚአብሔር ማረግ ራሱ ባቀረበው ጸሎት አስተምሮናል (መዝ 140፥2)
 
በዚህ ሰዓት ዓለምን ለማዳን ሕማማተ መስቀሉን ከተቀበለ በኋላ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ስጋው ለይቶ ወደ መቃብር ወርዷል።እኛ ሁላችን የእግዚአብሔር ልጆች የሆንን ሁሉ ለሰው ልጅ ሁሉ ትንሣኤ እና መድኅኒት ይሆን ዘንድ በመቃብር ውስጥ ፈርሶና በስብሶ መቅረትን ያስወግድልን ዘንድ ስለ እኛ ወደመቃብር መውረዱን እያሰብን መጸለይ ይገባናል። (ማቴ 27፥59-61)
 
6ኛ/   በመኝታ ጊዜ የሚጸለይ ጸሎት (ጸሎተ ንዋም)
ይህ ሰዓት ያሣለፍነው የቀኑ ጊዜ ባርኮና ቀድሶ ሥራችንን ሁሉ እንድናከናውን ስለረዳንና ቀኑንም ለእኛ የሰላም ጊዜ አድርጎ ስለአዋለን እና ሌሊቱም የሰላም ሌሊት አድርጎ እንዲያሳልፍልን በጤና እንዲያሣድረን ለፈጣሪያችን ጸሎትና ምስጋና ማቅረብ አለብን።
 
ነብዩ ቅዱስ ዳዊት “ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፤ ሞገሱ ግን ለህይወት ዘመን ልቅሶ ማታ ይመጣል፤ ጧት ግን ደስታ ይሆናል” በማለት በማታ ከመተኛታችን በፊት ውስጣዊ ልቦናችን በሃዘን እና በለቅሶ ተሞልቶ ወደ ፈጣሪያችን ፀሎት ባቀረብን ግዜ ማታ በሀዘን እና በፀሎት የዘራነውን ጠዋት በፍጹም ደስታ እንደምናጭድ አስተምሮናል። (መዝ 29፥5) በዚህ ሰአት ጌታችን መድኅንያለም እየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያትም ስርዓተ ፀሎትን ያሳየበትና አይሁድም ሌባና ወንበዴ እንደሚይዝ፣ ጭፍራ አስተባብረው ሰይፍና ገመድም ይዘው ጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ተረባርበው የያዙበት ሰአት በመሆኑ ወደፈተና እንዳትገቡ እንዲህ ብላችሁ ፀልዩ በማለት ይህን በሚመስል ለኛ ከመከራ እና ፈተና ለመዳን ተግተን እንድንፀልይ አርአያ ይሆን ዘንድ በጌተ ሰማኔ የአትክልት ቦታ ተንበርክኮ የጸለየበት ሰአት ስለሆነ ይህንን እያሰብን ከመኝታ በፊት መፀለይ ይገባናል። (ማቴ 26፥38-43)
 
7ኛ/   በመንፈቀ ለሊት የሚፀለይ ጸሎት
ከሌሊቱ በ 6 ሰአት ላይ ማንኛውም ክርስቲያን እንዲፀልይ ስርዓተ ቤተክርስቲያን ያዛል። 
 
ቅዱስ ዳዊት በመንፈቀ ለሊት መፀለይ እንዳለብን “በእኩለ ለሊት አመሰግንህ ዘንድ እነሳለሁ” በማለት ለፀሎት ከመኝታችን ተነስተን መትጋት እንዳለብን ስላደረገልን ነገር ሁሉ ፈጣሪን ማመስገን እንዳለብን በመዝሙሩ እንዳስተማረን እንመለከታለን። (መዝ 118፥62) 
 
ነብዩ ኢሳያስም “ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሀለች፤ መንፈሴም በውስጤ ወደአንተ ትገሠግሣለች” በማለት በሌሊት ክርስቲያን በፀሎት ከፈጣሪ ጋር መገናኘት እንዳለበት ተናግሯል።በዚህ ሰአት ጌታችን መድኅኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ለ5500 ዘመን በአዳምና በልጆቹ ላይ ተፈርዶባቸው የነበረውን የእዳ ደብዳቤ ቀዶ ሞትን በሞቱ ሽሮ በአካለ ስጋ ሙትና መቃብርን አጥፍቶ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ነፃ አውጥቶ በታላቅ ሃይል እና ሥልጣን መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል የተነሳበት ሰአት ነው። (ማቴ 28፥ ቁ.1 ጀምሮ) ስለዚህ እኛ በክርስቶስ ክርስቲያን በወልድ ውሉደ እግዚአብሔር ተብለን ስመ ክርስትና ያለን የእግዚአብሔር ልጆች በመንፈቀ ለሊት ተነስተን ፈጣሪያችን ያደረገልንን ሁሉ ታላቅ ውለታውን እና ስለኛ የገለፀውን ፍፁም ፍቅሩን እኛም ወደፊት በትንሳኤ ዘጉባኤ እንደምንነሳ እሱ የትንሳኤያችን በኩር የሆነውን የእሱን መነሳት እያሰብን ልንፀልይ ይገባናል። (1ኛ ቆሮ 15፥20)
 
የቤተክርስቲያን አባቶች በገዳማት ስርዓት ተወስነው የሚኖሩ በከተማ እና በገጠር ባለችው ቅድስት ቤተክርስቲያን በመንፈሳዊ አገልግሎት ተወስነው የሚኖሩ መነኮሳት ቀሳውስት መምህራን ዲያቆናት እንዲሁም ምእመናንና ምእመናት ሁሉ በ 24 ሰአት ውስጥ 7 ጊዜ ፀሎት እንዲፀልዩ በስርዓተ ቤተክርስቲያን አባቶቻችን የፀሎትን ጥቅም በአይነ መንፈስ ተመልክተው ስርዓት ሰርተውልናል። ማንኛውም ክርስቲያን በተለየ ምክንያት ከአቅሙ በላይ የሆነ ችግር ካላጋጠመው በስተቀር በዚህ ሰአት ቢያንስ አጭር ፀሎት ለፈጣሪ ማቅረብ ይገባዋል። ምክንያቱም በሰላም አውሎ ስላሳደረን፣ የእጃችንን ስራ ስለባረከልን፣ ኑሮዋችንን እና ቤተሰባችንን በሰላም ስለጠበቀልን፣ ያጋጠመንን የጤና ችግር እና ልዩ ልዩ ፈተና ከእኛ ስላስወገደልን፣ እነዚህን የመሳሰሉትን ሁሉ ገንዘብ ሳንከፍል ደጅ ሳንጠና ማመልከቻ ሳናቀርብ ያለአንዳች ውጣ ውረድ ብዙ ነገር ላደረገልን ፈጣሪ በአጭር ፀሎት ማመስገን ለኛ የማይበዛብን አገልግሎት ስለሆነ የፀሎትን ጥቅምና ታላቅነት እያሰብን ልንጸልይ ይገባናል።
 
ምን መፀለይ እንዳለብን እና እንዴት መፀለይ እንዳለብን በሚቀጥለው የትምህርት ክፍል እንዲደርሳችሁ እናደርጋለን፤ ለጊዜው እዚህ ላይ ይቆየን።
 
እግዚአብሔር አምላክ ዘመነ ማቴዎስን (2013)  ለአገራችን ለህዝባችን የሰላምና የፍቅር ያድርግልን
ስለ ፀሎት ትምህርት ክፍል ሁለት
 
እንዴት መፀለይ እና በምን አይነት መንገድ መፀለይ እንደሚገባን
 
ባለፈው በክፍል አንድ የፀሎት ትምህርት ውስጥ ጸሎት ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት ምስጢር እንደሆነና እኛም ከስጋና ከነፍስ ፈተና የምንድንበት ትልቁ መሳሪያችን እና ሃይላችን ፀሎት መሆኑን ለመግለፅ ሞክረናል። ዛሬም በክፍል ሁለት የጸሎት ትምህርት ውስጥ ለዮሐንስ ንስሓ መንፈሳዊ ድረገፅ ተከታታዮችና ሌሎችም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖች በምናስተላልፈው መልዕክት፦
 
1ኛ/ በምን አይነት መንገድ መፀለይ እንዳለብን፣
 
2ኛ/ ምን መፀለይ እንዳለብን፣ 
 
3ኛ/ እንዴት መፀለይ እንዳለብን አጭር መልእክት እናስተላልፋለን። 
 
1ኛ/ በምን አይነት መንገድ መፀለይ እንደሚገባን
 
1.1 ፀሎት ስንጀምር መላ ሰውነታችንን በትምእርተ መስቀል ማማተብ ይገባናል። ምክንያቱም በትምእርተ መስቀል ፊታችንን እና መላ ሰውነታችንን ፀሎት ከመጀመራችን በፊት የምናማትበው በሃሳብ የሚቃወመንን እና ከፈጣሪያችን ጋር በፀሎት እንዳንገናኝ የሚፈታተነንን እርኩስ መንፈስ በመስቀሉ ሃይል ቀጥቅጠን ከእግራችን ስር ለመጣል ወይም ፈፅሞ ከእኛ እንዲርቅ ለማድረግ ነው። የጨለማ ሃሳብ ተገፎ ከእኛ እንዲርቅ እና በብርሃን ለመመላለስ እንድንችል መላ ሰውነታችንን እና ፊታችንን ስናማትብ ከላይ ወደታች ከግራ ወደቀኝ ማማተብ ይገባል። ስልጣነ ክህነት ያላቸው አባቶች በያዙት መስቀል ሲያማትቡ ምእመናን ደግሞ ከአውራ ጣት ቀጥሎ ያሉትን የጣቶች ክፍል በመስቀል ቅርፅ በማመሳቀል ማማተብ ይገባናል። የዚህ ምሳሌና መንፈሳዊ ምስጢርም ከላይ ወደታች ስናማትብ ቀዳማዊ ቃል አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሰው ይሆን ዘንድ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ለማመልከት ነው። ከቀኝ ወደ ግራ የምናማትብበት ምክንያት ደግሞ የሰውን ልጅ ለማዳን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ ስጋን በመዋሃድ ሰው የሆነው አምላክ ስለኛ ኀጢአት ህማማተ መስቀሉን ተቀብሎ በምልዕተ መስቀል ተሰቅሎ ሞቶ እኛን ከሞት ወደ ህይወት ከአሳር ወደ ክብር ከሲኦል ወደ ገነት አሸጋግሮ ወደ ቀደመ ክብራችን የመለሰበትን ምስጢር ምሳሌ ለመግለፅ ነው። በቀኝ ገነት ትመሰላለች ፤ ግራ ደግሞ የሲኦል ምሳሌ ነው። (ፍትሓ ነገስት አንቀፅ 14) 
 
በትምእርተ መስቀል የምናማትብባቸው ግዜያትም፦ 
– ፀሎት ለመጸለይ ስንፈልግ፣ 
– በምንፀልየው የጸሎት ቃል ውስጥ ስለመስቀል የሚያወሳ ቃል ላይ ስንደርስ፣ 
– በምንበላው እና በምንጠጣው ምግቦች ላይ፣ 
– በምንለብሰው ልብሳችን ላይ፣ 
– ስንተኛ እና ከመኝታ ስንነሳ፣ 
– ማንኛውንም መንፈሳዊ እና ስጋዊ ስራችንን ከመጀመራችን በፊት በትምእርተ መስቀል ማማተብ የገባናል። 
 
1.2 ስንፀልይ በፍፁም እምነት ሁነን መፀለይ ይገባናል። የምናቀርበው ፀሎት ቅድመ እግዚአብሔር እንዲደርስ እና እኛም የምንፈልገውን በጎ ምላሽ በፈጣሪ ዘነድ ለማግኘት እንድንችል በፍጹም ልብ እና በፍፁም እምነት ውስጥ ሆነን ልንፀልይ ይገባናል።  
 
ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ “አምናችሁ በፀሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ” (ማቴ 22፥21) 
 
አሁንም ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ፤ ሳይታክቱ ዘወትር ሊፀልዩ እንደሚገባቸው ይህንን ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው “ አንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውን የማያፍር አንድ ዳኛ እንደነበረ በመግለፅ ወደዚህ ዳኛም እየቀረበች እለት እለት ዳኝነት የምትጠይቅ አቤት የምትል መበለት እንደነበረችና ያቺ መበለት ወይም ደሃ ሴት ሳትሰለችና ሳትታከት ዘወትር ዳኛውን ፍረድልኝ እያለች ስለጨቀጨቀችው ጥያቄዋን ተቀብሎ ፍርድ እንደሰጣት በሉቃስ ወንጌል ተመዝግቧል። (ሉቃ18፥1-6) 
 
1.3 በንፁህ ልቦና እንዲሁም በቅን መንፈስ ሆኖ መፀለይ በእኛ እና በእግዚአብሔር መካከል እንደ ግርዶሽ የሆነውን ክፉ ስራችንን ገርስሶት እግዚአብሔርን ለማየት ስለሚያስችለን ልቦናችንን ንፁህ ማድረግ አለብን። ስለዚህም “የቂመኛ ሰው ጸሎት በእሾህ መካከል እንደወደቀ ዘር ነው” ተብሎ በመፅሐፈ መነኮሳትና በሌሎችም መፅሐፍት ተመዝግ ይገኛል። 
 
1.4 ሃሳብን ሰብስቦ በአንድ ልብ ተወስኖ መፀለይ ይገባል። ቅዱሳን ሐዋርያት እና የመጀመሪያዎቹ የጌታ ተከታዮች (120 ቤተሰቦች) ከጌታ ትንሳኤና እርገት በኋላ በክርስትና አላማቸው ፀንተው በአንድ ቦታ ሆነው ሲፀልዩ ባሉበት ግዜ፤ ከሞቱ በፊት ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ የሚያጽናናቸውን መንፈስ ቅዱስን እንደሚልክላቸው በገለፀላቸው መለኮታዊ ቃል መሰረት በፀሎት እየተጉ እያሉ መንፈስ ቅዱስን እንደተቀበሉ ቅዱስ መፅሐፍ ይነግረናል። (የሐዋ 2፥1-4)  
 
1.5 በፈሪሃ እግዚአብሔር ሁነን እግዚአብሔርን በመፍራት ህይወታችንን በንስሓ አድሰን መፀለይ ይገባናል። ምክንያቱም ሰው የእምነቱ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ማስቀደም አለበት፤ ቀጥሎም በፀሎት እግዚአብሔርን ለማመስገን ወይም ደግሞ የፈለገውን ለመጠየቅ ሰውነቱን እና መላ ህይወቱን በንስሓ ህይወት መቀደስ አለበት። በዚህ አይነት የምንፀልየው ጸሎት እድሜያችንን ያረዝማል ብዙ በረከትም ያሰጣል። 
 
ንጉሱ ሕዝቂያስ በፈጣሪ በእግዚአብሔር ዘንድ ስለሰራው ኀጢአቱ ከልቡ ተፀፅቶ እያዘነና እያለቀሰ በመፀለዩ በእድሜው ላይ 15 አመት ተጨምሮለታል። (ሁለተኛ ነገስት 20፥1-8)  
 
1.6 ስንፀልይ ቀጥ ብለን በመቆም መፀለይ ይገባናል። በጸሎት ግዜ ሰማይ እና ምድርን የፈጠረ አምላክ ፍጥረታትን ሁሉ ፈጥሮ የሚገዛ አምላክ ዘላለማዊ ንጉስ የሆነውን የእግዚአብሔርን ስም ስንጠራ ከምንም በላይ በሰውነታችን ልንገዛለት ስለሚያስፈልግ እና በንጉሱ ፊትም ስንቆም ክብር ይገባዋልና ቁመን መፀለይ አለብን። ነብዩ የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት በማለዳ “አቤቱ ወዳንተ ፀልያለሁና በማለዳ ድምፄን ትሰማለህ፤ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ እጠብቃለሁም” በማለት በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ በማለዳ በፀሎት ፈጣሪውን እንዳመሰገነ እና የእግዚአብሔርን ቸርነት እንደጠየቀ ይናገራል። (መዝ 5፥3) 
 
1.7 ፊታችንን ወደ ምስራቅ አዙረን መፀለይ ይገባናል። ሁልግዜም ምስራቅ የጌታ መገለጫ ስለሆነች መልካም ነገሮች ሁሉ እንደ ፀሃይ ጮራ ከምስራቅ ስለሚወጡ ወይም ስለሚገለፁ ማንኛውም ካህንም ሆነ ምእመን ሲፀልይ ወደ ምስራቅ ቆሞ መሆን ይገባዋል። ምስራቅ የጌታ ምሳሌ ፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ምልክት ነው። ወደ ምስራቅ ተመልከቱ ተብሎ ተጽፏልና። 
 
በዚህም ፊታችንን ወደ ምስራቅ ማድረግ እንደሚገባን በፍትህ መንፈሳዊ ወስነዋል። 
እግዚአብሔር በመጨረሻው ዘመንም ይሄንን አለም ሊሰበስብ እኛንም በዳግም ትንሳኤ ሊጠራን ከምስራቅ እንደሚመጣ ቅዱስ መፅሐፍ ስለሚነግረን ወደ ምስራቅ ዞረን መፀለይ የሚገባን ከዚህ የተነሳ ነው። 
 
1.8 በፀሎት ግዜ መስገድ ይገባል። ፀሎት ስንጀምርና ስንጨርስም በምንፀልየው የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ስለስግደት ከሚናገርበት ቦታ ወይም አንቀፅ ላይ ስንደርስ መስገድ ይገባናል (ፍትሓነገስት አንቀጽ 14) 
 
እንኳንስ ሰማያዊ ንጉስ ለሆነው ለፈጣሪያችን ይቅርና በዚህ ምድር ላይ ላሉ ባለስልጣናትና ታላላቅ ሰዎች እንሰግዳለን። በዚህ በህሊና ከፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት መስመር ፀሎት ስለሆነ በአንተ ፊት የማቀርበውን ፀሎቴን ከኔ ደካማ ባህሪ እና ከማደርገው ኅጢአት የተነሰ የማቀርበውን ጸሎቴን አትናቅብኝ (ቸል አትበልብኝ) በማለት እየወደቅን እየተነሳን ልንፀልይ ስለሚገባን ነው።
 
አይናችንን ወደ ሰማይ በማቅናት መፀለይ ይገባናል። ምክንያቱም እኛ እንደ አህዛብ ወይም እንደ መናፍቃን በቀጲፀ ተስፋ (ተስፋ በመቁረጥ) የምንኖር ሳይሆን በዳግም ትንሳኤ ቀና ብለን ከመቃብር በላይ ተነስተን ለኛ የተዘጋቸውን ሰማያዊ ርስት እንደምንወርስ ተስፋ ያለን ስለሆነና በፈጣሪ ዘንድ ቀና ብለን ለመሄድ የሚያስችለን ሃይማኖትና ምግባር መሆኑን ለማረጋገጥ አይኖቻችን በትሁት ሰብና በአንቃእዳዎ ልቦና ሆነን አይናችንን አስፍተን መፀለይ ይገባናል። ለዚህም ዋና ማስረጃችን ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ አይኖቹን ወደ ሰማይ በማቅናት እንደፀለየ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ይነግረናል። (ዮሐ11፥4)  
 
1.9 ስለራሳችን እና ስለሌሎችም ወገኖች መፀለይ ይገባናል። እኛ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያኖች መፀለይ ያለብን ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ስለሌሎቹ ወገኖቻችን፦ 
 
– በተለያየ ፈተና ላሉ  
– በአልጋ ቁራኛ ለሚገኙ 
– በእስር ቤት ለሚኖሩ 
– በዳር ድንበር የአገርን ሰላም ለማስከበር በውትድርና ለሚኖሩ  
– በባእድ አገር ለሚኖሩ 
 
በአጠቃላይ በተለያየ ፈተና ውስጥ ለሚኖሩ ወገኖቻችን እና ለአገርም ጭምር መፀለይ ይገባናል። ነብዩ ኤርምያስ ስለአገር መፀለይ እንደሚገባ ሲናገር “በእርሷ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርሷ ላስማረክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ ስለ እርሷም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ። (ት.ኤር 29፥7)
 
ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብም ስለሌሎች መፀለይ እንደሚገባን “ትድኑ ዘንድ እያንዳንዳችሁ ለሌሎቻችሁ ፀልዩ” በማለት መክሮ አስተምሯልና። (ያዕ 5፥16) ምክንያቱም አንዱ ስለሌላው የሚፀልየው ፀሎት ታላቅ ሃይል ያደርል። ይሄ ይቅርና የሰው ልጅ ስለ አራዊቱ ስለ እንስሳቱ ስለ አዝሪቱ ስለ አትክልቱ ስለ ፈሳሹ ወንዝ ስለ ዝናባቱ ስለ መሳሰሉት ብዙሃንን እና ጥቃቅንን ፍጥረት ሁሉ እንድንፀልይ የእግዚአብሔር ቃል ያዘናል። 
 
2ኛ/ ምን እያልን እንፀልይ
 
ወደ ፈጣሪ የምናቀርባቸው ፀሎቶች በ2 ከፍለን እንመለከታቸዋለን፦
 
1. የረቀቀውን የሃይማኖት ሚስጢር የሚያውቁ እና ጥልቅ የሆነ የሃይማኖት እውቀት ያላቸው የቤተክርስቲያን አባቶችና ሊቃውንት የሚፀልዩት ፀሎት ንባቡና ትርጉሙ የረቀቀና የጠለቀ ስለሆነ እነሱ ብቻ የሚፀልዩት ፀሎት ነው።
 
2. ምእመናን ሁሉ የሚፀልዩት ፀሎት በየደረጃቸው ቢፀልዩት የማይከብድ እና በቀላሉ ሊረዱት የሚችሉት የጸሎት አይነት ነው። ካህናትም ሆኑ ምእመናን የሚፀልዯቸው የፀሎት መፃህፍትም፦
 
– የ150 መዝሙረ ዳዊት እና 15 ነብያት እና መሃልየ ሰለሞን እነዚህ ከሰኞ እስከ እሁድ የሚፀለዩ የፀሎት ክፍል ናቸው 
– የ7 ቀን ውዳሴ ማርያምና አንቀፀብርሃን እንዲሁም መልክአ ማርያምና መልክአ እየሱስ 
– ውዳሴ አምላክና ሰኔ ሎለጎታ 
– ሰይፈ ሥላሴና ሰይፈ መለኮት  
– የፃድቃንና የሰማእታት መልካቸውና ገድላቸው  
– የቅዱሳን መላእክት መልካቸውና ድርሳናቸው 
– ወንጌለ ዮሐንስ 
ሌሎችም ብዙ የፀሎት አይነት አሉ። በገዳማት ውስጥ የሚኖሩ መናኞች እና አንዳንድም እግዚአብሔር ፀጋውን ያበዛላቸው በከተማም ሆነ በተለያየ ቦታ እየኖሩ አብዝተው የሚፀልዩ የእግዚአብሔር ሰዎች አሉ።  
 
ፀሎት ለማድረግ ወይም ለመፀለይ ፈፅሞ ማመን እና ህሊናን ንፁህ ማድረግ እንጂ የእውቀት ብዛት እና የፀሎት ብዛት ለፀሎቱ ተቀባይነት ወይም ቅቡል መሆን ዋናው ምክንያት ላይሆን ይችላል። በሃይማኖት ውስጥ ያሉትን የፀሎት መፅሐፍት በቀላሉ ለመረዳትና በቂ እውቀት የሌላቸው ምእመናን ከሆኑ ቢያንስ የክርስቲያን አጭር ፀሎት አቡነ ዘበሰማያት፣ ፀሎተ ሃይማኖት፣ ፀሎተ እግዚተነ ማርያምን አጥንተውም ቢሆን ከንስሓ አባት ወይም በቅርብ ከሚያገኟቸው የቤተክርስቲያን አባቶች በመጠየቅ አጥንቶ መፀለይ ያስፈልጋል። 
 
ሲጀመር አንድ ክርስቲያን ለስጋው ምግብ ልብስ እንዲሁም መጠለያ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለነፍስም ከሚያስፈልጓት የነፍስ ተግባራት አንዱ እና ዋናኛው ፀሎት ስለሆነ ለሁሉም ጉዟችን በር ከፋችና በጎውንና ክፉውን ነገር ለማየትም የምንችልበት ብርሃን ስለሆነ ፀሎት በክርስቲያናዊ ህይወት ላይ እጅግ አስፈላጊ ነው። የግዜ እጥረት ያለባቸው ሰዎች እንደ ስጋዊ ምክንያት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚያውቀው ከአቅም በላይ የሆነ ፈተና ሲያጋጥመን ከዚህ በላይ የተገለፁትን አጫጭር ፀሎቶች ፀልየን ፈጣሪያችንን በወጣንበት በገባንበት ተከተለን ብለን ከእሱጋ ያለንን ግንኙነት አጠንክረን ወደ ስራችን ብንገባ ሁሉም ነገር ይሳካልናል ማለት ነው። 
 
3ኛ/ እንዴት ብለን መፀለይ ይገባናል
 
ፀሎት የሚቀርብበት የራሱ ስርዓት እና ቀኖናዊ ትውፊት አለው። መፀለይ ስላሰብን ብቻ ቦታና ግዜን ሳንወስን እኛም ራሳችን ሰባዊ አካላችን ሳንሰበስብና ለፀሎት ሳናዘጋጅ ከሜዳ ተነስተን ብናነበንብ ፀሎታችን የአህዛብ ፀሎት ነው የሚሆነው። ስለዚህ ፀሎት፦
 
– በቅጥረ ቤተክርስቲያን ሆነን መፀለይ ይገባናል 
– በምንኖርበት ቤት ውስጥም ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ የፀሎት ቦታ ላይ ሆነን መፀለይ አለብን 
– በግል ሆነን እና በማህበር ሆነን ስንፀልይ በቀስታ ወይም በለሆሳ (በምላስ) የሚፀለይ ፀሎት ልንፀልይ እንችላለን። የቤተክርስቲያን አባቶችና ሊቃውንት በንባብ እና በዜማ ሊፀልዩ ይችላሉ። 
-እግዚአብሔር አምላክ የእለት እለት የግል ህይወታችንን እና የማህበር ስራችንን ከመጀመራችን በፊት የእግዚአብሔርን ፈቃድ መጠየቅ ይኖርብናል 
– ለመንፈሳዊ አገልግሎት የታነፀ ቤተክርስቲያን አለ፣ ሌሎችም ለመንፈሳዊ ተግባር የሚውሉ የተገነቡ የልማት ስራዎች ካሉ በአባቶቻችን በፀሎት ተባርከው አገልግሎት እንዲውሉ ማድረግ ያስፈልጋል። ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በግል ወጥቶና ወርዶ ያተረፈውን የእጁን ስራ እግዚአብሔር እንዲባርክለት የሚሰራበትን የመኖርያ ቤትም ቢሆን የንግድ ቤትም ቢሆን መኪናም ቢሆን ፋብሪካም ቢሆን ኢንዱስትሪም ቢሆን በመሬት ላይ የምናለማውን ማንኛውም ተግባር ይሁን በፀሎት ልናስባርክና ልንገለገልበት ይገባል (2ኛ ዜና 7፥15)
 
-ጠዋት በነግህ ወይም በጠዋት የምንፀልየው ፀሎት ምግብ ሳንበላ እና ሰውነታችንን ከገቢረ ኅጢአት ጠብቀን ሊሆን ይገባል፣
 
-ከ9 ሰአት በኋላ የምናቀርበው የሰርክ ጸሎት ከሌላ የኀጢአት ስራ ተጠብቀን ፀሎት ልንፀልይ እንችላለን።
 
-ተበልቶ የማይፀለየው፦ የቅዳሴ ፀሎት እና አባቶች በሚስጢረ ቤተክርስቲያን ቤተ መቅደስ የሚያከናውኑት የፀሎት ስርዓት ምግብ ሳይበላ የሚጸለይ የፀሎት ክፍል ነው
 
በአጠቃላይ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የዮሐንስ ንስሓ ድረገፅ ፕሮግራም ተከታታዮች ወገኖቻችን፤ ፀሎት የአጋንንትን ወጥመድ የሚሰባብር፣ ሃይላቸውን የሚያዳክም ከኛ ህይወት ተለይተው እንዲጠፋ የሚያደርግ እንደ ሰይፍ የሚቆራርጣቸው እንደ እሳት የሚያቃጥላቸው ስለሆነ ለእኛ ትልቁ ሃይላችን እና ጉልበታችን ረቂቅ መሳሪያችን ስለሆነ ማንኛውም ክርስቲያን የጀመረው ጉዞ የተቃና እንዲሆንና ዘወትር ከሚያጋጥመው ፈተና ለመውጣት እንዲችል ፀሎትን ማዘውተር ስላለበት ሁላችሁም በተቻለ አቅም ከፀሎት እንዳትለዩ ባለን የአገልጋይነት ሃላፊነታችን አደራ እንላችኋለን።
 
ጌታችን መድኅኒታችን እየሱስ ክርስቶስም ለቅዱሳን ሐዋርያት በማስመሰል እና ከአፋዊ (ግብዝነት) የጸሎት ስርዓት እርቀው እውነተኛ ፀሎት የሚፀልዩ ሰወች ስለሚያገኙት መንፈሳዊ ድል ለቅዱሳን ሐዋሪያት አስተምሯቸዋል። የፀሎትንም አይነት ከዚሁ ጋር አያይዞ ነግሯቸዋል። (ማቴ 6፥5-13)
 
እንዲሁም በምሴቴ ሐሙስ (በሐሙስ ማምሻ) ለአርብ አጥቢያ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በአይሁድ እጅ ተላልፎ በሚሰጥበት ሌሊት ንዲት ሰአት ልትተጉ አልቻላችሁምን? ወደፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ” በማለት ፀሎት ከከባድ ፈተና እና ከአሰቃቂ መከራ የሚያድን መሆኑን አስተምሯቸዋል (ማቴ 26፥41)
 
ስለዚህ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በነገር ሁሉ በፀሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ አቅርቡ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ አይምሮን ሁሉ የሚያውቅ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁን አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።” (ፊልጵስዩስ 4፡6)
 
ከዚህ በላይ በክፍል ሁለት ስለ ፀሎት የቀረበውን አጭር ትምህርት ለፀሎት ያላችሁን ፍቅር እንድታሳድጉና ሁሌም ለፀሎት እንድትተጉ የሚያደርጋችሁ አቅጣጫቶች ወይም ደግሞ የፀሎትን መንገድ የሚያሳይ ትምህርት መሆኑን ተረድታችሁ የስጋንም ሆነ የነፍስን ተግባር ለማከናወን ሁሌ ከፀሎት እንዳትለዩ ይህን ምክራችንን በመስጠት ለግዜው ስለፀሎት ያለንን መልእክት በዚሁ እናጠናቅቃለን።
 
ስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክብር 
 
ይቆየን

ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷልና (1ቆሮ 57)

በዮሐንስ ንስኅ ድረገፅ መንፈሳዊ ፕሮግራም የሚተላለፈውን ኦርቶዶክሳዊ ተከታታይ የሃይማኖትና ክርስቲያናዊ የስነ ምግባር ትምህርት የምትከታተሉ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሁላችሁም፤ ከሁሉ በፊት ለቅዱስ ቃሉ እንድንተጋና ለንስኅ እንድንዘጋጅ በነገር ሁሉ የረዳንንና በአላማው ያፀናን የአባቶቻችን አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለም ይክበር ይመስገን።

ከላይ ለርዕሳችን መነሻ ባደረግነው ሃይለቃል ተመስርተን ስለ ብሉይ ኪዳን እና ሀዲስ ኪዳን የፋሲካው በግ ምስጢራዊ ትርጉም እንማማራለን። በዚህም ትምህርታችን ምክንያት የሆነን አንድ አባላችን ከዚህ በታች ያቀረቡትን ጥያቄ መነሻ በማድረግ ነው።

 ጥያቄው፦ የፋስካው በግ ወይንም የግብጻዊያ ሞተ በኩር ጋር አያይዘው ከምስጢረ ቁርባን ጋር ያለው ምሳሌነትና አንድምታውን ከስርዓተ ቁርባን ጋር ቢያብራሩልን?

መልስ፦ በኦሪቱ ስርዓት የፋሲካን በዓል ማክበር በእስራኤላውያን ዘንድ እጅግ የታወቀና ሃይማኖታዊና ብሔራዊ ግዴታም ነበር። የአባታችን የያእቆብ ልጆች አስራ ሁለት ነገደ እስራኤል ለ430 ዘመን ያህል በግብፅ ሀገር በብዙ ስቃይና ጭቆና ከቆዩ በኅላ ከግብፅ ባርነት ነፃ የወጠትና ከስደት ተመልሰው ወደ ቅድስት ሀገራቸው ምድረ ከነዓን የገቡት የፋሲካው በግ ከታረደ በኅላ ነው። 

የፋሲካው በግ የምንለውን ሁለቱን ቃላት ሃይማኖታዊ ትርጓሜውንና ምስጢሩን ለይቶ መረዳት ያስፈልጋል።

1 ፋሲካ በእብራይስጥ ‘ፐሳህ’ ማለት ትርጉሙም አለፈ ተሻገረና ነፃ አወጣ ማለት ነው።

2 የበጉ ትርጓሜም በኦሪቱ ስርዓት የእስራኤል ልጆች መሰረታዊ ህልውናቸው የተመሰረተበት ሲሆን ማለትም በግ የማርባትና ከበጎች በሚገው ጥቅም ኑሯቸውን የማስተዳደር ልምድ እንደነበራቸው በቅዱስ መፅሐፍ በስፋት የተገለፀ ሲሆን በተለይ ከእንስሳት ሁሉ በግን ለመስዋእትነት መርጠው ለእግዚአብሔር አምላካቸው አቅርበው መስዋዕት ከብዙ የእግዚአብሔር ቁጣና መቅሰፍት እንደሚድኑና ከፈጣሪያቸው ጋር እንደሚታረቁ የተለመደ ስርዓት ነበር።  በግ ስጋው ለመስዋዕትና ለምግበ ስጋ ፣ ፀጉሩና ቆዳው ለልብስና ለገቢ ምንጭ የሚሆን፣ ከቤት እንስሳት ሁሉ የዋህ የሆነና መከራን የመታገስ ችሎታ ያለው እንስሳ ነው። ለብዙ መልካም ነገርም በምሳሌነት ይጠቀሳል በዚሁ መሰረት የፋሲካ በግ የተባለበትም ምክንያት ከዚህ ቀጥለን እንመለከታለን፦ 

የእስራኤል ልጆች በግብፃዊያን ላይ የተላከው የበኩር ልጆችን የሚገለው መላከ-ሞት እንዳይገላቸው  (እንዲያልፋቸው) በነብዩ ሙሴ አማካኝነት የደረሳቸውን ትዕዛዛት አክብረው ነውር የሌለበት ማለትም ቀንዱ ያልከረከረ፣ ፀጉሩ ያላረረውንና ጥፍሩ ያልዘረዘረውን የአንድ አመት ተባይት የበግ ጠቦት መርጠው በአቢብ ወር (ሚያዚያ) (ኒሰን) በተባለው በ14ኛው ቀን ሲመሽ

አርደው የቤታቸውን መቃኑንና ጉበሩን የበጉን ደም ረጩት። የበጉን ስጋም እንደታዘዙት በእሳት ጠብሰው ከመራራ ቅጠል ጋር በሉት። ያልቦካውን ቂጣ አብረው በልተዋል። ከእግዚአብሔር የተላከው መልአከ-ሞትም በእስራኤላውያን ቤት ላይ  የተረጨውን የበጉን ደም ባዩት ጊዜ የእስራኤላውያንን ሰፈር አያለፋ የግብፃውያንን የበኩር ልጆች እየለየ በመቅሰፍት መታቸው። ንጉሱ ፈርኦንም በህዝቡ ላይና በእንስሳቱ ላይ የደረሰውን የሞት መቅሰፍት በተመለከተ ጊዜ ሙሴንና አሮንን ጠርቶ ህዝቡን ይዘው በአስቸኳይ ከሀገሩ እንዲወጡለት ትዕዛዝ በመስጠቱ፤ ያቦኩትን ሊጥ እንኳን ሳይጋግሩት ከነዕቃው (ማቡኪያው) ተሸክመው ከግብፃውያን ዘንድ የተሰጣቸውን የብር፣ የወርቅ፣ እና የልብስ ስጦታ (ገፀበረከት) ይዘው ከግብፅ ምድር ወጥተው ወደ ምድረ በዳ ጉዟቸውን ጀምረዋል። (ዘይ 12፥29-36)

እግዚአብሔር አምላክ ለነብዩ ሙሴና ለካህኑ አሮን ስለፋሲካው በግ አመራረጥና የአቀራረብ ስርዓት እንዲሁም ወደፊት የፋሲካውን በዓል እንዴት ማክበር እንደሚገባቸው እንዲህ በማለት አዘዛቸው፦

1/ እስራኤል ከግብፅ የወጡበት ወርሐኒሰን (ወርሐ ሚያዚያ/አቢብ) ስለነበረ ይህ ወር በየአመቱ የመጀመሪያ (የአዲስ አመት መጀመሪያ) እንዲሆናቸው፣

2/ እያንዳንዱ የእስራኤላውያን ቤት (የየአባወራ ቤተሰብ) ሁሉ፤ ቀንዱ ያልከረረ፣ ፀጉሩ ያላረረ፣ ጥፍሩ ያልዘረዘረ በዚያው ወር በ10ኛው ቀን የአንድ ዓመት ጠቦት መርጠው እንዲያዘጋጁ፣

3/ በዚያው ወር በ14ተኛው ቀን ሲመሽ የተዘጋጀውን ፋሲካውን በግ እንዲያርዱት፣

4/ የእስራኤል ማህበር በሚኖሩበት ቤት ሁሉ የቤቱ መቃሩንና ጉበሩን በበጉ ደም እንዲቀቡት፣

5/ የበጉን ሥጋ በእሳት ጠብሰው ያልቦካውን ቂጣ (እንጀራ) በዚያው ሌሊት ከመራራ ቅጠል ጋር እንዲበሉት፣

6/  ጥሬ ሥጋውን (ብርገዶውን) እና በውሃ የበሰለውን (ቅቅሉን) (ዝግሩን) ፈፅሞ እንዳይበሉ፣

7/  የታረደው የፋሲካው በግ ሥጋው በዚያው ሌሊት እስከጠዋት ድረስ ተበልቶ ማለቅ እንዳለበት፣

8/  እስከ ጠዋት ድረስ ተበልቶ የተረፈው ሥጋ በእሳት መቃጠል እንዳለበት፣

9/  እስራኤላውያን ሁሉ የበጉን ሥጋ ሲበሉ ወገባቸውን ታጥቀው  ጫማቸውን ተጫምተው በትራቸውን በእጃቸው ይዘው በችኮላ መሆን እንደሚገባቸው፣

10/ በዚያችው ሌሊት የግብፃዊያንን የሰውና የእንስሳት በኩር ሁሉ እንዲቀጽፍ ( እንዲመታና እንዲገል) የተዘዘው መልአከ-ሞት በእስራኤላውያን ቤት የተቀባውን (የተረጨውን) የደሙን ምልክት ባየ ጊዜ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያደርስባቸው እያለፈ እንደሚሄድ፣

11/ ለ7 ቀናትም እርሾ የሌለበት ያልቦካ ቂጣ (እንጀራ) እንዲበሉ፣

12/ እስራኤላውያን ከግብፅ የወጡበት የፋሲካው በዓል ለእግዚአብሔር የተቀደሰ በዓል ስለሆነ ከግብጽ ባርነት ለወጡበት መታሰቢያ ነውና በልጅ ልጆቻቸው ዘንድ ሥርዓት ሆኖ ሳይቋረጥ እንዲከበር፣

13/ የፋሲካው በዓል የሚከበረው ለ7 ቀናት እንዲሆንና የመጀመሪያውና የመጨረሻው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ እንዲሆንላቸው፣

14/ በዓሉ በሚከበርበት ቀናት ውስጥ ማንኛውንም ሥራ እንዳይሰሩና ለበዓሉ ተብሎ የተዘጋጀው የፋሲካውን ምግብ ብቻ እንዲበሉ፣

15/ እስራኤላውያን ልጆች ሁሉ የፋሲካውን በዓል በየአመቱ መታሰቢያ አድርገው ሲያከብሩ ከግብፅ በወጡበት በመጀመሪያው ወር ከ4ኛው ቀን እስከ 21ኛው ቀን ድረስ ለ7 ቀናት እርሾ የሌለው ቂጣ ብቻ እንዲበሉና በቤታቸው ውስጥም ምንም ዓይነት እርሾ እንዳይገኝባቸው እንዲጠነቀቁና ለዘለዓለም ለልጅ ልጆቻቸው ሥርዓት አድርገው እንዲጠብቁት እንደታዘዙ ቅዱስ መፅሐፍ ያስረዳናል። (ዘፀ 12፥1፣20)

የፋሲካው በዓል አቀራረብና የፋሲካው በግ አቀራረብ ሥርዓት እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት ከወጡበት ወር ጀምሮ የሐዲስ ኪዳን ፋሲካን የመሠረተውና የዓለሙን ኅጢአት ሊያስወግድ አማናዊ በግ ሆኖ የተገለጠው እየሱስ ክርስቶስ የሐዲስ ኪዳኑ ፋሲካ እስተተከበረበት ድረስ የበጉ ፋሲካ እንደ ኦሪቱ ሥርዓት በእስራኤላውያን ማህበር ዘንድ ሲከበር ኑሯል።

በኦሪቱ ሥርዓት የነበረው የፋሲካው በግ አማናዊ ለሆነው የሐዲስ ኪዳኑ የፋሲካው በግ ለእየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ስለነበረ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በእለተ ሐሙስ (በምሴተ ሐሙስ) በወዳጁ በስምኦን ቤት የመጨረሻውን የአይሁድ የፋሲካ በዓል እያከበረ በነበረበት ሰዓት ያኛው ሥርዓት ለሚመጣው ሐዲሱ ፋሲካ ጥላና ምሣሌ ሆኖ ማለፉንና በሐዲስ ኪዳኑ ፋሲከ መተካቱን በተግባር ሥርዓቱን አሳይቷቸዋል። (ማቴ 26፥26፣29)

የኦሪቱ ፋሲካ እና የፋሲካው በግ አማናዊ ለሆነው የሐዲስ ኪዳን ፋሲካና በፋሲካው በግ ምሣሌነቱና አንድምታውን እና ከስርዓተ ቁርባን ጋር ያለው ግንኙነት ምንድነው? 

ለዚህ ምላሽ የሚሆነውን በክፍል ሁለት ላይ በነገው እለት እንዲደርሳችሁ እናደርጋለን፤  ትምህርቱ መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርት ስለሆነ በመስመር ሆናችሁ በመጠባበቅ አስከመጨረሻው አንብባችሁ ትረዱት ዘንድ በአጽንዎት አደራ እንላለን።

ይቆየን

ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷልና (1ቆሮ 57)

የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስኅ ድረገፅ መንፈሳዊ ፕሮግራም ተከታታይ አባሎቻችን፤ በ ክፍል አንድ ላይ እግዚአብሔር አምላክ ለነብዩ ሙሴና ለካህኑ አሮን ስለፋሲካው በግ አመራረጥና የአቀራረብ ስርዓት እንዲሁም ወደፊት የፋሲካውን በዓል እንዴት ማክበር እንደሚገባቸው የሰጣቸውን ትእዛዛት፤ እንዲሁም በኦሪቱ ሥርዓት የነበረው የፋሲካው በግ አማናዊ ለሆነው የሐዲስ ኪዳኑ የፋሲካው በግ ለእየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ መሆኑን ማለትም የአይሁድ የፋሲካ በአል ስርዓት ለሚመጣው ሐዲሱ ፋሲካ ጥላና ምሣሌ ሆኖ ማለፉንና በሐዲስ ኪዳኑ ፋሲከ መተካቱን  “ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷልና” (1ቆሮ 5፥7) በሚለው  ኃይለ ቃል ተነስተን መሠረቱንና ትርጓሜውን ለማስረዳት አጠር ያለ ትምህርታዊ ትንታኔ  እንዲደርሳችሁ አድርገናል። 

ዛሬም ወደ ክፍል ሁለት የኦሪቱ ፋሲካ እና የፋሲካው በግ አማናዊ ለሆነው የሐዲስ ኪዳን ፋሲካና በፋሲካው በግ ምሣሌነቱና አንድምታውን እና ከስርዓተ ቁርባን ጋር ያለውን ግንኙነት በሚመለከት ካለፈው የቀጠለ ትምህርት  እንደሚከተለው አቅረበንላችኋልና አንብባችሁ ተማሩበት ዘንድ በአጽንዎት አደራ እንላለን። 

እስራኤል ከግብፅ ሲወጡ ያረዱት በጉ የጌታ ምሣሌ ነው። ምክንያቱም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የንስሐ ጥምቀት በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ በማጥመቅ ላይ እንዳለ ጌታን ባየው ጊዜ ወደሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ “እነሆ የዓለሙን ኅጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” በማለት የሐዲስ ኪዳን አማናዊ የፋሲካው በግ እሱ መሆኑን አረጋግጦ መስክሯል። (ዮሐ1 ፥19)

እስራኤል ዘሥጋ ከግብፅ ባርነት ለመውጣትና በግብፃውያን ዘንድ የታዘዘውን የሞት መቅሰፍት ለመዳን የፋሲካው በግ እና የደሙ ምልክት ቤዛ እንደሆናቸው ሁሉ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም “ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷልና” እንዳለ ሁሉ የሐዲስ ኪዳን የፋሲካው አማናዊ በግ እየሱስ ክርስቶስም በቀራንዮ አደባባይ በመስቀል ላይ በራሱ ፈቃድ መሥዋዕት ሆኖ አለምን ያዳነበት መለኮታዊ ጥበብ ሲሆን በየጊዜውና በየእለቱ በቤተክርስቲያን የሚሰዋው የክርስቶስ ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ ካህናቱ በቤተመቅደስ ሲያቀርቡት ይገኛሉ። እስራኤል የፋሲካውን በግ አርደው ከግብፅ የባርነት ቀንበር የመውጣታቸው ምንክያት አድርገው የነፃነት በአላቸውን ያከብሩ ዘንድ በልጅ ልጆቻቸው ስርዓት ሆኖ የዘመን መለወጫ እንዲያደርጉት ሁሉ ጌታችን መድኅኒታችን እየሱስ ክርስቶስም ስለ ሰው ልጅ በመስቀል ላይ የሞት ዋጋ ከፍሎ ለዘለዓለማዊ ህይወት ካዳነን በኋላ የአምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን አመተ ፍዳ ፣አመተ ደይን ፣ አመተ ኩነኔ ተብሎ ይጠራ የነበረውን የኅጢአት ዘመን አሳልፎ አመተ ምህረት ተብሎ እንዲጠራ አድጎታል።

የኦሪቱ ፋሲካ እና የፋሲካው በግ አማናዊ ለሆነው የሐዲስ ኪዳን ፋሲካና በፋሲካው በግ ምሣሌነቱ፦

1/  የአንድ አመት ጠቦት ወርድ እንጂ ቁመት እንደማይጨምር ሁሉ ጌታም የተሰቀለው ፍጹም የ30 አመት ጎለማሳ መሆኑን ያመለክታል።

2/  የአንድ አመት የሆነው ጠቦት ቀንዱ ያልከረከረ፣ ላቱ ወይም ፀጉሩ ያላረረ፣ ጥፍሩ ያልዘረዘረ እንደሆነ ሁሉ ጌታም በሰውነቱም ሆነ በአንደበቱ ለኅጢአት ምክንያት ያልተገኘበት ንፁኀ ባህሪ ፃድቅና እውነተኛ የፍቅር አምላክ መሆኑን ለመግለፅ ነው።

3/  በሚያዚያ ጨረቃ ስርቅ በታየችበት በ10ኛው ቀን በጉን ይዛችሁ በ14ኛው ቀን ሰዉት ተብለው እስራኤል እንደታዙበት ሁሉ አይሁድ የጌታን ምክረ ሞቱን በየወሩ 10ኛ ቀን ጀምረው በ14ኛ ቀን ፈፅመውታል፣

4/ በሁለት እጅ ብርሃን በአንድ እጅ ጨለማ በሆነበት የማታው ምሽት ክፍለ ጊዜ እስራኤል የፋሲካውን በግ እንደሰዉት ሁሉ ጌታም በምሴተ ሀሙስ ለአርብ አጥበያ በአይሁድ እጅ ተይዞ ሰቅለው ይገሉት ዘንድ አይሁድ ለፍርድ ባቀረቡት ጊዜ ከ ተነግህ እስከ ቀትር ብርሃን መሆኑን፣ ከቀትር እስከ 9 ሰዓት ጨለማ መሆኑን በማመልከት ነው።

5/  እስራኤል የፋሲካውን በግ ሲሰዉ 7 ወይም 10 ወይም 12 ሆናችሁ ሰዉት እንደተባለው ሁሉ፤

7 ቁጥር በእብራዊያን አቆጣጠር ፍፁም ቁጥር እንደሆነ ሁሉ 10 ቁጥር ደግሞ በኢትዮጲያውያን ዘንድ ፍጹም ቁጥር ነውና እኛም እስራኤል ዘነፍስ የምንባለው ፍጹማን ሆናችሁ የክርስቶስን ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን መቀበላችንን ለማጠየቅ ነው። 

6/  12 ሆናችሁ ማለቱም የክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መስዋእት ለግዜው የተቀበሉት 12ቱ ሐዋርያት መሆኑን ለማመልከት ነው።

7/  የቤቱን መቃኑንና ጉበሩን የበጉን ደም እርጩት እንደተባለ ሁሉ ለጊዜው የደሙ ምልክት እስራኤላዊያን ለግብጽ ህዝብ ከተላከባቸው የሞት መቅሰፍት እንዲድኑ ምክንያት የሆናቸው ሲሆን ፍፃሜው ግን፤ ጥላና ምሳሌ የሆነው የበጉ ደም ይህንን ያህል የሰራ፥ አማናዊ ደም የሆነው የክርስቶስ ደምማ ምን ያህል ያስፈራ? እያሉ አጋንንት ወደ ምእመን ዘንድ እንዳይቀርቡና በኅጢአት የሚኖሩ ሰዎችም ንስኅ ሳይገቡ ወደ ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ እንዳይቀርቡ ለማመልከት ነው።

8/  የፋሲካውን በግ ዝልዝሉንና ቅቅሉን አትብሉ ተብሎ የተፃፈው የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ስጋው ሙስና መቃብር አገኘው አትበሉ ማለት ነወ። ወይም ደግሞ በመቃብር ሞቶና በስብሶ ይቀራል አትበሉ ለማለት ነው።

9/  የፋሲካው በግ የስጋውን ብርንዶ አትብሉ ማለቱም ትኩስ ስጋ ከሆነ ከብርንዶው ደም አይታጣም ነፍሱም ደግሞ ከደም አትለይምና ስለዚህ ነፍስ የተለየውን የክርስቶስን ስጋ መለኮት የተዋሀደውን የክርስቶስን ስጋ እንደምንቀበል ለማጠየቅ ነው።

10/ የብርንዶ ስጋ አትብሉ ማለትም ምሳሌነቱም የክርስቶስን ቅዱስ ስጋውን እንደ ሩቅ ብእሲ ወይም እንደ ፍጡር ስጋ እንዳትቆጥሩት ማለቱ ነው። ምክንያቱም የሩቅ ብዕሲ ወይም የፍጡር ሰው ስጋ ቢበሉት ይመራል፣ ያተኩሳል ፣ ፍዳ ይሆናል፣ እርም ይሆናል፣ ባጠቃላይ ጤና ይነሳል እንጂ ከኅጢአት አያነፃም ከሞት አያድንምና የጌታ ቅዱስ  ስጋው ግን ከኅጢአት ከፍዳ የሚያድን ከዘለዓለማዊ ሞት የሚያድን መለኮት የተዋሀደው ነፍስ የተለየችው አማናዊ ቅዱስ ስጋና አማናዊ ክቡር ደም ተቀበሉ በማለት ነው።

11/ የፋሲካውን የበጉን ስጋ አታሳድሩት እንደተባለው ሁሉ የክርስቶስ ስጋ አለማደሩን ያመለክታል።

12/ የበጉን ስጋ ከአንዱ ወደ አንዱ አትውሰዱት ተብሎ እንደታዘዘው ዛሬ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ ካህናት የሚሰዉት የክርስቶስ ቅዱስ ሰጋና ክቡር ደም ካንዱ ቦታ ወደሌላ ቦታ ወስዶ መሰዋት አይቻልም ማለት ነው።

13/ የፋሲካው የበጉ ስጋ እስራኤላውያን የበሉትን በልተው የተረፋቸውን በእሳት እንዲያቃጥሉት እንደታዘዘው ሁሉ ዛሬም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀውን መስዋዕት በንፅህናና በቅድስና ከተቀበላችሁ በኋላ ሌላውን ሳትጠራጠሩና ሳትመራመሩ ስለቀረውስ ምስጢር መንፈስ ቅዱስ ያውቃል ብላችሁ በእምነት ተቀበሉ ለማለት ነው።

14/ የፋሲካውን በግ እስራኤላውያን ካረዱ በኋላ ስጋውን በእሳት ጠብሳችሁ ብሉ እንደተባለው ሁሉ እሳቱ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ስለሆነ የክርስቶስ ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙን ለተቀበሉት ሁሉ መንፈስ ቅዱስ እንደማይለያቸው ለማጠየቅ ነው።

15/ የፋሲካውን በግ ነውር የሌለበት ቀንዱ ያልከረረ ጸጉሩ ያላረረ ጥፍሩ ያልዘረረ እንከን የሌለበት የአንድ አመት ንጹህ በግ እንደሆነ ሁሉ ጌታችን መድኅኒታችን እየሱስ ክረስቶስም የአዳም ኅጢአት ዘር ያላለፈበት ንጹሀ ባህሪ አምላክ መሆኑን ያመለክታል። በፋሲካ ሳምንት እስራኤላውያን የሚበሉት ከመራራ ቅጠል ጋር ሲሆን ይህምበሆዳቸው ውስጥ ያለውን ምግብ እንዲበትንላቸው ነው፤ ምሳሌው ግን የክርስቶስ ስጋና ደሙን መቀበል እየሚገባችሁ የበላችሁትና የጠጣችሁት ምግበ ስጋ ከሆዳችሁ ጠፍቶ ለአፋችሁ መራራ ሲሰማችሁ ነው ለማለት ነው።

16/  እስራኤላውያን የተዘጋጀውን የፋሲካውን በግ ስትበሉ ጫማችሁን ተጫምታችሁ ነው የተባሉበት ምሳሌነቱ እስራኤል ዘነፍስ የተባሉ ክርስቲያኖች የወንጌል ምግባርንና ትሩፋትን ሰርታችሁ ኑሩ ለማለት ነው።

17/  ወገባችሁን ታጥቃችሁ ብሉት የተባለበት ምሳሌነቱ ንጽህናንና ቅድስናን ይዛችሁ ኮፌታችሁን ለብሳችሁ ማለቱም አክሊለ እሶክ ወይም ህማማተ መስቀሉን እያሰባችሁ ተቀበሉት ማለቱ ነው።

18/ የበጉን አጥንቱን አትስበሩ መባሉ ለግዜው በፋሲካው በአል አጥንት እንዳይሰብሩ የኦሪት ህግ የሚከለክላቸው ሲሆን ምሳሌው ግን በእለተ አርብ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ አይሁድ የሁለት ወንበዴዎችን ጭን ጭናቸውን ሲሰብሩ ጌታን ጭኑን ግን አልሰበሩትምና የፋሲካው የበአሉ ሳምንት በየቤታቸው የቦካውን እርሾ እስራኤላውያን እንዲያስወግዱ እንደታዘዙ ሁሉ ፍፃሜው ግን የቀደመውን ስርዓተ ኦሪት ትታችሁ በአዲስ ኪዳን ህግ ወይም (ህገ ወንጌልን) ተቀበሉ ለማለት ነው።

19/ የአይሁድ የፋሲካ በአል በተከታታይ ለ 7 ቀናት እንደሚያከብሩት ሁሉ ጌታ የተነሳበትን የትንሳኤውን በዓል ማክበራችንን ለማጠየቅ ነው።

20/ ፋሲካ እስራኤል ዘስጋ 430 ዘመን ያህል በባርነት እና በሰቆቃ ከኖሩባት ከግብፃውያን ነፃ ለመውጣት ምክንያት እንደሆናቸው ሁሉ እኛም እስራኤል ዘነፍስ የተባልን የአዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች ከጨለማ ወደ ብርሃን ፣ ከሞት ወደ ህይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከመቃብር ወደ ትንሳኤ የተሸጋገርንበት ቀን መሆኑን ለማጠየቅ ነው።

በመጨረሻም (21) እሁድ የፋሲካ በአል በአዲስ ኪዳን ፋሲካ በሆነው በክርስቶስ ትንሳኤ (የትንሳኤ በአል) ተተክቷል። 

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት የአይሁድ ፋሲካ ምሳሌነቱ አማናዊ ፋሲካ የአዲስ ኪዳን ፋሲካችን ለሆነው በጌታችን በመድኅኒታችን እየሱስ ክረስቶስ ትንሳኤ መሆኑን ያመለክታ።

ስለዚህ ጠያቂያችንም ሆኑ የዚህ የዮሐንስ ንስኅ ድረገፅ መንፈሳዊ ትምህርት  ተከታታይ አባላት ሁላችሁም ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷል ያለበትን ምክንያት በአዲስ ኪዳን የሚያስፈልገን የእንስሳ በግ ሳይሆን የዓለምን ኅጢአት የሚያስወግደው ንጹኅ ባህሪ የሆነው የእየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም እንደሆነ ለመግፅ ነው። ይህ አማናዊ የሆነው እየሱስ ክርስቶስ በደሙ ፈሳሽነት የሰጠን ቤዛነት ወይም የከፈለልን የደም ዋጋ እንደ ብሉይ ኪዳንና ፋሲካው በግ ጊዜያዊ ሳይሆን ዘለዓለማዊ ፣ ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ፣ ስጋዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ መሆኑን ያመለክታል። ስለዚህ ሁላችንም ራሳችንን በምግባርና በሃይማኖት አንፀን ለቅዱስ ቁርባን የሚያበቃንን ቅድመ ዝግጅት አድርገን ንስኀ ገብተን ለዘለዓለም የማያስርብና የማያስጠማ የክርስቶስ ቅዱስ ስጋ እና ክቡር ደም ለመቀበል ጊዜው እና ወቅቱ አሁን ነው። ለነፍስ ድህነት እና ለበጎ ስራ ቀጠሮ  አያስፈልግም፤ ሁላችንም ለስጋችን ዘወትር ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ የነፍስ ምግቧ ቅዱስ ቁርባን ስለሆነ ነፍሳችንን እንዳናስርባት መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ እየመከርን ፤ ስለ ምስጢረ ቅዱስ ቁርባን  ተጨማሪ ግንዛቤ ለማግኘት ካስፈለገ ከዚህ በፊት ያስተላለፍናቸውን ተከታታይ ትምህርቶች እና የጥያቄ መልሶች ከድረገጻችን ላይ እንዲመለከቱ ሊንኩን  ከዚህ በታች ልከናል።

እግዚአብሔር በቸርነቱና በምህረቱ ሁላችንንም ጎብኝቶን ለቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙን ለመቀበል ያብቃን፤ አሜን

ስለ ምስጢረ ቅዱስ ቁርባን  ትምህርትን ለመመልከት ይህን ይጫኑ፦ https://yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን/

ስለ ምስጢረ ቅዱስ ቁርባን ጥያቄና መልስ ለመመልከት ይህን ይጫኑ፦ https://yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን/

ገድለ ቅዱሳን

መልካሙን ገድል ተጋድያለኹ፥ሩጫውን ጨርሻለኹ፥ሃይማኖትን ጠብቄያለኹ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል” (2 ጢሞ 47:8)

እጅግ የምንወዳችሁና የምናከብራችሁ የዮሐንስ ንስኀ ድረገጽ መንፈሳዊ ፓሮግራም አባላት የሆናችሁ ወገኖቻችን ከዚህ ቀጥለን  “ቅዱሳን ገድላትን ለመቀበል መፅሀፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ?” በማለት የጠየቁንን መሠረት አድርገን በአጠቃላይ የቅዱሳንን ገድል የሚዳስስ አጭር ትምህርት ስላቀረብን እናንተም ትከታተሉት ዘንድ አስቀድመን በእግዚአብሔር ስም በአክብሮት እንጠይቃለን።

ጥያቄ፦ ቅዱሳን ገድላትን ለመቀበል መፅሀፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ ?

መልስ፦ (መፅሀፍ ቅዱሳዊ ማስረጃና ማብራሪያ)

ገድል፦ ማለት በቁም መጋደል (ትግልን ሰልፍ ውጊያ፣ ፈተና ስቃይ፣ መከራ፣ሕማም፣ ድካም ወዘተ ይባላል። ይህ ማለት ለፈጣሪያቸው እስከ ሞት በሚደርስ መጋደል የታመኑ ቅዱሳን ሰዎች የተዘጋጀላቸውን የድል  አክሊል እስከሚቀዳጁበት መጨረሻው ሰዓት ድረስ ብዙ ሰማዕታትና ተጋድሎ የተቀበሉበት መንገድ ሁሉ ገድል ይባላል።

ማስረጃ፦ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ በርናባስ በደርባን ከተማ ወንጌል ሲያስተምሩ የደረሰባቸውን መከራና ስቃይ ከምንም ሳይቆጥሩ ወደ እግዚአብሔር መንግስት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልጋል እያሉ የስጋውን ስቃይና መከራ ታግሰው ወደ ቀጣይ አገልግሎት እንዴት እንደለፉ በሐዋርያት ሥራ ላይ ተመዝግቦ እናገኘዋለን። (የሐዋ 14፥21 እና 22)

ቅዱሳት ሰማታትና ቅዱሳን ፃድቃን የዚህን ዓለም ሀብት ፣ ንብረት፣ ሥልጣን  ፣ ክብር ፣ ተድላ፣ ደስታ የመሳሰለውን ምድራዊውን ሕይወት ንቀው በዓለማውያን ዘንድ ሞኝነት የሆነው የእግዚአብሔርን መንግሥት መርጠው አብዝተው መገረፍ ፣ አብዝተው ወደ ወህኒቤት (እስር ቤት) በመጣል አብዝተው በሰይፍ መቆረጥ፣ አብዝተው በድንጋይ መወገር፣ አብዝተው በመጋዝ በመሰንጠቅ ፣ አብዝተው በመራብና በመጠማት፣ አብዝተው በአላውያን ነገሥታት ፊት ቀርበው የሃሰት ፍርድ በመቀበል፣ በዱር በገደል በመጣል፣ የላመ  የጣመ ሣይቀምሱ ጤዛ ልሰው፣ ቅጠል በጥሰው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ድምጸ አራዊቱንና ግርማ ሌሊቱን ጸብአ አጋንንቱን ታግሰው፣ ከባለቤቱ ዘንድ የተማሩት መከራ መስቀል በፀጋ የመቀበላቸው የተጋድሎ ጉዞ ሁሉ ገድለ ቅዱሳን (የቅዱሳን ገድል) ይባላል።

ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ለእብራውያን በላከው መልዕክቱ ላይ “እነሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ ፣ጽድቅን አደረጉ፣ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ የአንበሶችን አፍ ዘጉ ፣ የእስትን ኅይል አጠፉ፣ ከሰይፍ ስእለት አመለጡ ፣ ከድካማቸው በረቱ፣ በጦርነት ኅይለኞች ሆኑ የሚበልጠውን ትንሳኤ እስኪያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ ፣ ሌሎቹም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወህኒ ፈተና በድንጋይ ተወግረው ሞቱ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ በዋሻና በምድረ ጉድጓድ ተቅበዘበዙ” በማለት ስለተቀበሉት መከራና ተጋድሎ ወደፊትም ስለሚጠብቃቸው ሰማያዊ ክብር ተናግሯል።(ዕብ 11፥33 – 38)

ቅዱሳን የሚጋደሉት ከራሳቸው ፈቃደ ሥጋና በረቂቅ መንፈስ ከሚዋጋቸው ዲያብሎስ ጋርም ነው።

ሐዋርያው በሮሜ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች በፃፈው ክታቡ “እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞታላችሁ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትጋደሉ በሕይወት ትኖራላችሁ” በማለት ከራስ የሥጋ ምኞትና ፍላት ጋር የሚጋደሉትን የገድል ዓይነት ይነግረናል።

ቅዱሳን በዓለም መከራ እየተቀበሉ የሚጋደሉት ራሳቸውን ብቻ ለማዳን ሳይሆን በመከራ መቀበል የእግዚአብሔርን የምስራች ወንጌል ለዓለም ሁሉ ለማዳረስ ነው። (1ተስ 2፥2)

ቅዱሳን ከጌታችን ከእየሱስ ክርስቶስ እጅ በአደራ የተቀበሉት የወንጌል ቃል ለፍጥረት ሁሉ ለማድረስ  ሲሉ አርነት ሲኖራቸው እንደ ባርያ ፣ ከአይሁድ ዘንድ እንደ አይሁዳዊ፣ ከሕግ በላይ ሲሆኑ ከህግ በታች፣ በኅጢአት የሚኖሩትን ለማዳን ሲሉ ከሕግ በታች ሆነው በእምነት የደከሙትን ለማበርታት እንደደካሞች ሆነው፣ እውነተኛ ሲሆኑ እንደ አታላዮች ተቆጥረው፣ ሁሉ አዋቂ ጥበባኛ ሲሆኑ እንደ አላዋቂዎች ተቆጥረው፣ በሥጋ እየተገፉ ፣ እየተደበደቡ፣ እየተጋደሉና እየሞቱ ሣለ ምንም ያልደረሰባቸው በመሆን ፣ ሀዘንተኞች ሆነው ሳለ ደስተኛ መስለው ፣ ድሆች ሲሆኑ ሀብታሞች መስለው፣ተጋድሏቸውን ፈፅመዋል (1ኛ ቆሮ 9፥11-23፣ 2ኛቆሮ 6፥9 -10)

ቅዱሳን የአማላጅነት ስልጣን ከፈጣሪያቸው ዘንድ አንድ ጊዜ ስለተቀበሉት ለዘላለም በተሰጣቸው ቃልኪዳን በአጸደ ሥጋም ሆነ በአጸደ ነፍስ ሲያማልዱ እንደሚኖሩ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል። ምክንያቱም ከዚህ በላይ እንደተገለጸው እነዚህ  እግዚአብሔር አምላክ አስቀድሞ ከእናታቸው ማህጸን ጀምሮ ያወቃቸውና የመረጣቸው ሲሆኑ በአጸደ ሥጋ እያሉ የሚደርስባቸውን ተጋድሎ በጸጋ እየተቀበሉ ሞትም ቢሆን እንኳን ከአላማቸው ወደኋላ እንደማይሉ በፈጸሙት ገድላቸው ተመልክተናል።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ክርስቲያኖች በፃፈው መልዕክቱ ላይ “እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ ሃሳቡም ለተጠሩት ነገር ዅሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይኾን ዘንድ፥አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኗልና አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው።” በማለት የቅዱሳንን መመረጥ፣ ክብራቸውንና ፣ ጽድቃቸውን የገድላቸውን ጽናትም በሱ ኃይልና በሱ ውሳኔ እንደሆነ የአማላጅነታቸው ክብርም እስከመጨረሻው መሆኑን ነግሮናል ። (ሮሜ 8፥ 28-30)

ቅዱሳን በገድላቸው የደረሰባቸውን ነገረ መስቀል ሁሉ እንዲታገሱ እግዚአብሔር ጽናቱንና ኃይሉን  እንደሚሰጣቸው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲናገር “ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋራ መውጫውን ደግሞ ያደርግላችዃል።” (1ኛ ቆሮ 10፥13)

ቅዱሳን የሚጋደሉት ሰውነታቸውን የተወደደ ህያው መስዋዕት አድርገው እንደሆነ ሐዋርያው ሲገልጽ ፦ “እንግዲህ፥ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችኹን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሠኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችኹ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችዃለኹ” (ሮሜ 12፥1)

ቅዱሳን በዓለም ሲኖሩ የሚጠቅሙት ራሳቸውን ሳይሆን በኀጢአት እና በብዙ ስጋዊ ፈተና የወደቀውን የሰው ልጅ እንደሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ፊሊጵስዩስ ሰዎች በጻፈው ክታቡ ላይ “ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ሞትም ጥቅም ነውና። ነገር ግን፥በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢኾን፥ምን እንድመርጥ አላስታውቅም። በእነዚህም በኹለቱ እጨነቃለኹ ልኼድ ከክርስቶስም ጋራ ልኖር እናፍቃለኹ፥ከዅሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና። ነገር ግን፥በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው።” በማለት ቅዱሳን በሥጋ መኖራቸው በዓለም ለሚኖሩ መዳን ለሚገባቸው የሰው ልጆች ሲሆን እነሱ ግን ከስጋ መከራ የሚያርፉበትን ወደተዘጋጀላቸው ሰማያዊ የክብር ቦታ እንደሚሄዱ  ከክርስቶስም ጋራ ለመኖር እንደሚናፍቁ ይገልጻል ። (ፊሊጵ 1፥21-24)

ሰው ሁሉ የሚኖረው ለራሱ ነው ፤ ቅዱሳን የሚኖሩት ግን ለሰው ልጅ ነው። ስለ ጽድቅ የሚሰደዱና መከራን የሚቀበሉ መንግስተ ሰማያት የነሱ እንደሆነች በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈው ሁሉ ቅዱሳንም ገድላቸውን በትእግሰት የፈጸሙት በዓለም ሁሉ የደረሰባቸውን ሰማዕትነት በትእግስት የተቀበሉት ከሚያልፈው ወደ ማያልፈው ዓለም ፣ ከምድራዊ ክብር ሰማያዊ ክብር ፣ከምድራዊ ህይወት ሰማያዊ ህይወት እጅግ እንደሚበልጥ በተሰጣቸው ጸጋ በአይነ መንፈስ ያዩ ስለነበር ነው። (ማቴ 5፥10)

ቅዱሳን ዘወትር ፈቃደ ስጋታቸውን ለፈቃደ ነፍሳቸው እያስገዙ የሃይማኖት ገድል እየተጋደሉ እስከ መጨረሻው የጸኑበትን የሃይማኖት መንገድ እንከተለው ዘንድ አሰረ ፍኖት ሆኖናል።” እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ፤ የሚታገልም ዅሉ በነገር ዅሉ ሰውነቱን ይገዛል እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥እኛ ግን የማይጠፋውን ስለዚህ፥እኔ ያለዐሳብ እንደሚሮጥ ዅሉ፥እንዲሁ አልሮጥም ነፋስን እንደሚጐስም ዅሉ እንዲሁ አልጋደልም ነገር ግን፥ለሌላዎች ከሰበክኹ በዃላ ራሴ የተጣልኹ እንዳልኾን ሥጋዬን እየጐሰምኹ አስገዛዋለኹ።” (1ኛ ቆሮ 9፥25 -27)

እንግዲህ ጠያቂያችንም ሆኑ የዚህ ፕሮግራም ተከታታዮች ሁላችሁም ፤ የቅዱሳን ተጋድሎ እጅግ ሰፊና ጥልቅ ከመሆኑ የተነሳ ወደፊትም በስፋት የምናቀርብበት ትምህርት ቢኖረንም ለጊዜው ከጠያቂያችን ሃሳብ ተነስተን የቅዱሳንን ክብር መሰረቱና ምንጩ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንደሆነ ከነሱ ተጋድሎ ወይም መከራቸው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከእየሱስ ክርስቶስ የተሰጣቸው እንደሆነ ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ኃይለ ቃሎች መረዳት ያስፈልጋል። ጌታችን ከመድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ።”ሁሉን ነገር ከእኔ ተማሩ” ብሏል። (ማቴ 11፥29) ምክንያቱም እሱ ያላደረገውን ያልሰራውን አድርጉ ፈጽሙ በማለት የማይቻለውን ሸክም በሰው ጫንቃ ላይ የሚጭን አምላክ አይደለም። እንዲያውም የባረከው ስለሆነ በኛ ላይ የሚደርሰው ፈተናና ተጋድሎ ሸክሙ ቀሊል እንደሚሆን  “ሸክሜ ቀላል ቀንበሬ ቀሊል ነው” በማለት በወንጌል አስተምሮናል ። (ማቴ  11፥30)

ስለዚህ የቅዱሳን ተጋድሎ በሱ በባለቤቱ የተባረከ የቃልኪዳን ዋጋ የሚያሰጥ፣ በረከትን የሚያበዛ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል።

እንግዲህ አኛ ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች የቃልኪዳን ልጆች እንደመሆናችን መጠን የነሱን ገድላቸውንና ቃልኪዳናቸውን አያሰብን በአማላጅነታቸው ስንማጸን፤ ስለኛም በዓለም ሳለን  ከብዙ መከራና ፈተና እንድንሰወር በተሰጣቸው ቃልኪዳን ይጠብቁናል፤ በወዲያኛውም ዓለም እግዚአብሔር አምላክ ለወዳጆቹ ያዘጋጀውን ሰማያዊ ርስት እንድንወርስ ያደርጉናል። 

ስለዚህ የቅዱሳን የገድል ቃልኪዳን መታሰቢያቸው ለበረከት መሆኑን አውቀን ሁላችንም የነሱን መንገድ እንድንከተል እግዚአብሔር ይረዳን ዘንድ ሁላችንም በሃይማኖትና በምግባር ጸንተን በየጸጋችን መጠን መኖር ያስፈልጋል።

የቅዱሳን የገድላቸውና የቱሩፋታቸው በረከት በኛ ላይ አድሮ ይኑር።

https://yohannesneseha.org/ስለ-ተዋሕዶ-ሃይማኖት

ምዕመናን ቅዳሴ ለማስቀደስ ማወቅ ስለሚገባቸው ሥርዓተ ቤተክርስቲያን የሚከተለውን የማብራሪያ መልእክት እንድትመለከቱ በአጽንኦት እንመክራለን። በድምፅ ወይም በምስል ተቀርፆ የተዘጋጀውን ስርዓተ ቅዳሴ በመኖሪያ ቤት ውስጥ ወይም በስራ ቦታ ሆኖ ማዳመጥ በቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ቆሞ እንደማስቀደስ ሊቆጠር ይችላል ወይ? በማለት ጥያቄ ለሚያቀርቡ ምእመናን ከዚህ እንደሚከተለው አጭር ማብራሪያ እንሰጣለን።

ቅዳሴ ስንቀድስና ስናስቀድስ የእግዚአብሄርን ሀልወት አምነን ተቀብለን ስርዓተ አምልኮት የምንፈጽምበት በባህሪው ንፁህ እና ቅዱስ ለሆነው አምላካችን ምስጋና እና የልመና ፀሎት የምናቀርብበት ስርዓት ሲሆን ይህንንም ከራሱ ከባለቤቱ የተቀበልነውን እና የተማርነውን ህገ እግዚአብሔር ነው። በቤተክርስቲያን ውስጥ በመዓልት እና በሌሊት በስርዓተ ማህሌት፣ ሰዐታት በመቆም፣ ስብሐተ ፍቁር እና ፀሎተ ኪዳን በማድረስ ለምናቀርበው አገልግሎት ሁሉ ማሠሪያው እና መደምደሚያው በቅዳሴ ፀሎት የምንሠዋው የክርስቶስ ቅዱስ ስጋው ክቡር ደሙ ነው። መንፈሳዊ አገልግሎታችን ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ቅቡል እንደሆነ የምናረጋግጥበት ምስጥር በቅዳሴ ሲከናወን ነው።

የቅዳሴ አገልግሎት ጥቅሙ ለእኛ በስሙ አምነን የኀጥያት ስርየት ማግኘት ለሚገባን የእግዚአብሄር ልጆች ሁሉ ነው እንጂ ምስጋና የባህሪው የሆነው ርኩሠት የሌለበት ሕያው አምላክ በባሕሪው ቅዱስ ነው። እልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክቱም በዓለመ መላእክት ሆነው ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ዘወትር ያለማረፍ ያመሠግኑታል። ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር ያከበራቸው ብዙ አበው ቅዱሳንም በፍፁም ተአምኖ ሲያመሰግኑ ኖረዋል። ዛሬም ቢሆን በገዳማት እና በልዩ ልዩ ቅዱስ ስፍራ ሆነው በእምነታቸው ፀንተው ስለቸርነቱ፣ ስለጠብቆቱ እና መግቦቱ እያሠቡ የሚያመሠግኑት ብዙ ናቸው።

ከላይ በመግቢያው ላይ ለመግለጽ እንደተሞከረው ሚስጥረ ቁርባንን የምናሣርግበት ዋናው ምስጢራዊ መሠረቱን ስንመለከት ጌታችን በእለተ ዐርብ መልዕልተ መስቀል ላይ ሆኖ ስለ ብዙዎቹ የኀሀጢአት ስርየት ይሆን ዘንድ የቆረሠውን ስጋውን እና ያፈሠሠውን ደሙን ዘወትር በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተመቅደሱ በታቦቱ ላይ መሥዋዕት አድርገን ስናቀርብ የምንጸልየው የምስጋና ፀሎት ነው። ቅዳሴ ለመቀደስና መሥዋዕት ለማሣረግ የተፈቀደላቸው ስልጣነ ክህነት ያላቸው ማለትም ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ኤጲስ ቆጶሳት ፣ ቀሳውስት እና ዲያቆናት ናቸው። ስለ ስርዓተ ቅዳሴ እና ስለ ሚስጥረ ቁርባን አፈፃፀም በሚመለከት በቤተ ክርስቲያን ቀኖና ተደንግጎ ይገኛል። የቀዳስያኑን ቁጥር በሚመለከት 5፣ 7፣ 12፣ 21 ሊሆን ይችላል። የቀዳሲያኑን ቁጥር ለማሟላት በማይቻልበት ቦታ ላይ ቁጥራቸው ከ 5 በታች ሁነው ሊቀድሱ ይችላሉ። ከሚቀድሱት ማለትም በቀዳሽነት ልብሠ ተክኖ ለብሠው ከሚያገለግሉት ካህናት ውጪ ያሉት ካህናቱም ሆኑ ምእመናኑ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እና በውጪም ቆመው ሊያስቀድሱ ይገባቸዋል። በመጨረሻም በንስሐ ሕይወት ተዘጋጅተው የቀረቡት ምዕመናን ይቆርባሉ ሌሎችም ለቅዱስ ስጋው እና ለክቡር ደሙ እንዲያበቃቸው ፈጣሪያቸውን ለምነው፣ መስቀል ተሣልመው፣ ፀበል ጠጥተው ወደ ቤታችሁ በሠላም ግቡ ሲባል ተሠናብተው ይሄዳሉ።

ነገር ግን በምስል እና በድምጽ የተቀረጸውን ስርዓተ ቅዳሴ እያዳመጡ በእለተ ሰንበትም ሆነ በሌሎች በዓላት ከቤቱ ተኝቶ እና በስራ ወይም በአልባሌ ቦታ ተቀምጦ ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ሠንፎ እንደማስቀደስ ይቆጠርልኛል ብሎ ማሠብ ፈጽሞ ተገቢ አይደለም። ምክንያቱም ከክፉ ነገር ርቀን፣ ንጽህናችንን ጠብቀን እየጾምን እየፀለይን የቅዳሴውን ተሠጥኦ እየተቀበልን በፍፁም ክርስቲያናዊ ህይወት ፀንተን በአፀደ ቤተክርስቲያን ውስጥ በፀጥታ ቁመን ስጋችንንም ሆነ ነፍሳችንን ለእግዚአብሔር በማስገዛት የምናቀርበው አገልግሎት ነው። ወደ ቤተክርስትያን መሄድ የማያስችል ካቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥም ግን አለማዊሙዚቃ ከማናዳምጥና ፊልም ከምናይ ይልቅ ባለንበት ቦታ ሆነን በድምፅም ይሁን በምስል ተቀርጾ የተዘጋጀውን ስርአተ ቅዳሴ፣ መንፈሳዊ መዝሙር፣ ትምህርተ ወንጌል ወዘተ… ብንከታተል ከስጋዊ ፈተና ሊያርቀን ይችላል። ስለሆነም በድምፅ የተቀረጹትን ስርአተ ቅዳሴ በማዳመጥ በዚህ አግባብ እንድትጠቀሙበት በቅርቡ የምንልክላችሁ ይሆናል። ይሁን እንጂ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአካለ ስጋ ቆመን የምናስቀድሰውን የቅዳሴ አገልግሎት ፈፅሞ እንደማይተካ እና እንደማይወክል ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል። ባጭሩ ለግዜው ይህን ያህል ካልን ስለስርአተ ቅዳሴ አፈፃፀምና አገልግሎት በቀጣይነት በምናዘጋጀው ፅሁፋችን በስፋት ማብራሪያ የምንሰጥበት መሆኑን ከወዲሁ አበክረን እንገልጻለን። በየዓለንበት መኖሪያችንና የሥራ ቦታችን አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር ይጠብቀን።

መልስ፦ ጠያቂያችን ከዚህ በፊት ስለ እመቤታችን ዘለዓለማዊ ድንግልና ፣ ቅድስና፣ እና ንፅህና ቋሚ ትምህርት እንዲደርሳችሁ አድርገናል። በዚያ ትምህርታችን ውስጥ ስለ ድንግል ማርያም በመፅሀፍ ቅዱስና በሌሎቹም ቅዱሳት መፃህፍት ተፅፎ ያለውን ማስረጃ በመጥቀስ፦ ድንግል፣ ቅድስት፣ ልእልት፣ክብርት፣ እመ አምላክ፣ ማህደረ መለኮት፣ ወላዲተ አምላክ፣ የተባለችበትን መስጢር ሁሉ በመጠኑ ለማብራራት ሞክረናል።አሁንም ጠያቂያችን መገንዘብ ያለብዎት እመቤታችን ወላዲተ አምላክ ንፁሐ ባህሪ የሆነው ቅዱስ አምላክ እናቱ እንድትሆን የመረጠችው እስዋ ሳትሆን እሱ ባለቤቱ እራሱ ፈቅዶ እራሱ ወስኖ በመለኮታዊ ረቂቅ ጥበቡ የአዳም ኀጢአት በዘር እንዳያልፍባት ንፅሒት እና ቅድስት አድርጎ ዘለዓለማዊ ማህተመ ድንግልናዋን አፅንቶ እናቱ ሊያደርጋት ጥንቱኑ አዘጋጅቷታል። 
 
በመሰረቱ ጠያቂያችን ፤ በመፅሐፍ ቅዱስ ብቻ የተገኘውን ቃል ካልሆነ በማለት በክህደት እና በኑፋቄ እንደወደቁ ሰዎች ጥያቄ ማቅረቡ ለውድቀት እንጂ ለትንሳኤ አይሆንም። ምክንያቱም መፅሐፍ ቅዱስ ከዚህ በፊትም እንደተናገርነው የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ አምነን ካልተቀበልነው በስተቀር እኛ በዘመኑ ኑረን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚመራቸው ቅዱሳን አበውና ነብያት ቅዱሳን ሐዋሪያት ብሉይ ኪዳንን እና አዲስ ኪዳንን ሲፅፉ በወቅቱ ተገኝተን በአይናችን አላየንም በእጃችን አልዳሰስንም ብለን አንቀበልም ወይም አናምንም ማለት አንችልም። ሁል ጊዜ ሰይጣን ለሰው ልጅ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ምክንያት በማብዛት የጥርጣሬ መንፈስ እና የኑፋቄ ድንጋይ በመፈንቀል የሰው ልጅ በክህደትና በኑፋቄ ማዕበል እንዲናጥ በልቦናው ውስጥ የጥርጣሬ እንክርዳድን በመዝራት ማሰናከል ቋሚ ተግባሩ ስለሆነ እውነተኛ አማኝ ደግሞ በእያንዳንዷ ነገር ጥቃቅን ምክንያት ሳይፈልግ ለክህደተ የሚሆን ጥያቄም ሳያነሳ ሁሉን ነገር በእምነት ያያል። 
 
በእርግጥ የሄንን ስንል ለጠቅላላ ግንዛቤ እንጂ በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ እመቤታችን ያልተነገረና ያልተፃፈ ነገር አለ ብለን አይደለም። ስለ እመቤታችን በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተፃፈውን ለመናፍቃን ስንነግራቸው ‘ይሄማ ስለ ድንግል ማርያም አይደለም’ በማለት እውነቱን መቀበል አይፈልጉም። ‘ታድያ ስለምንድነው?’ ተብለው ሲጠየቁ ደግሞ መልስ የላቸውም። መፅሐፍ ቅዱስ አቅጣጫ ይሰጠናል እንጂ በሃይማኖት ስርዓት በትውፊት እና በሌሎቹ ቅዱሳት መፃህፍት ካልሆነ በስተቀር መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ሁሉንም ነገር በፈለግነው መንገድ ተዘርዝሮ፣ ተሰፍሮና ተቆጥሮ ልናገኘው ግን አንችልም። ለዚህም ነው ወንጌላዊ ዮሐንስ “ኢየሱስም ያደረገው ብዙ  ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል”(ዮሐ21፥25) እንዳለው። ስለሆነም፥ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ምስጢሩንና ጥበቡን የገለፀላቸው ቅዱሳን መፅሐፍ ቅዱስን መሰረት አድርገው ለእኛ ያቆዩልን የትምህርት እና የስርዓተ መፃህፍት አብዝተው እና አብራርተው ሁሉንም ያስረዱናል። 
 
ስለዚህ ጠያቂያችን ስለ እመቤታችን ስለድንግል ማርያም የአዳም ኅጢአት በዘር አላለፈባትም የሚለው ኅይለቃል ቤተከርስቲያን የምታስተምረው፦
 
1ኛ/  ነብየ እግዚአብሔር ኢሳያስ  “ የሰራዊት እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር”  በማለት ከሰው ልጅ መካከል የአምላክ እናት እንድትሆን በሰው ልጅ ላይ በዘር የሚተላለፈው የኅጢአት ዘር እንዳያገኛት ንፁህ ዘር አድርጎ የፈጠራት እና እሱን በመውለድዋ የድህነታችን ምክንያት ስለሆነች እንደ ሰዶም እና እንደ ገሞራ ሰዎች ጠፍተን እንዳንቀር እግዚአብሔር ከእሷ በተዋሀደው ስጋ ማዳኑን ያመለክታል። (ኢሳ 1፥9፣ ሮሜ 9፥29) 
 
2ኛ/ በሌላ መልኩ አሁንም ነብየ ኢሳያስ “ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” የሚለው ኃይለ ቃል የእመቤታንን ድንግልና ከሌሎቹ አንስተ አለም የድንግልና ህይወት የተለየ ድንግልና መሆኑን ስንመለከት እውነትም እመቤታችን በስጋዊ ልደትዋ የሰው ዘር ብትሆንም እንኳን በንፅሕና እና በቅድስና ግን ከሴቶች ሁሉ ልዩ ሆና የተፈጠረች በውርስ የመጣባቸው ጥንተ ተአብሶ እሷን ያላገኛት መሆኑን ያመለክታል (ኢሳ7፥14) 
 
3ኛ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ጌታን እንደምትፀንስ የምስራቹን ቃል ይነግራት ዘንድ ወደ እሷ በተላከ ጊዜ ያቀረበላትን ሰላምታ ወይም ክብር ስንመለከት፥ አለም ከተፈጠረ ጀምሮ እንዲህ አይነት የክብር ሰላምታ እንኳን ከሰው ዘር ለተገኘ ቀርቶ ለሰማይ መላእክትም አልተሰጠም። ምክንያቱም ቅዱስ ገብርኤል ወደ ካህኑ ዘካርያስ እና ወደ ቅድስት ኤልሳቤጥ አስቀድሞ በመሄድ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን እንደሚወልዱ ከነገራቸው በኋላ በመቀጠልም ጉዞውን ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ በማቅናት ድንግል ማርያምን በቤተ መቅደስ ባገኛት ጊዜ ወደ እርሷ ገብቶ ያቀረበላት ሰላምታ ‘ደስ ይበልሽ፥ ፀጋን የሞላብሽ ሆይ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው ፥ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ’ የሚሉት ቃላቶች እጅግ ልዩ ያደርጓታል። ምክንያቱም፦ 
 
– ‘ደስ ይበልሽ’ ሲላት የሷ ደስታ እንደ ሌሎቹ ሴቶች ንጉስ ለመውለድ፣ ወይም ነብይ ለመውለድ፣ ወይም ደግሞ ሰማእት ለመውለድ፣ ወይም ፃድቅ ለመውለድ፣ ወይም ፈላስፋ ለመውለድ፣ ወይም ተመራማሪ ለመውለድ ሳይሆን፥ አምላክን ለመውለድ ወይም የአምላክ እናት ለመሆን ስለሆነ ከፍጥረት ሁሉ የሚለያት አንዱ ይህ ነው። 
 
– ‘ፀጋን የተሞላብሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው’ የሚለውም የሌሎች ቅዱሳን ፀጋ የአንዱ ከአንዱ እንደሚበልጥም ሆነ ወይም ፃድቅን፣ ወይም ነብይን፣ ወይም ሰማዕትን፣ ወይም ካህንን፣ ወይም ንጉስን፣ ለመውለድ ይሄንን የመሰለውን ታላላቅ አስደናቂ ነገር ለማድረግ ብቻ በክርስትና ህይወትም ከእግዚአብሔር በሚሰጣቸው ሀብት መንፈስ ቅዱስ ፀጋቸው ብዙ ስለሆነ ደስ ሊላቸው ይችላል። ለእሷ የተሰጠው ፀጋ ግን ፈጣሪዋን ለመውለድ እሷም የፈጣሪ እናት ለመሆን የተሰጣት ፀጋ ልዩ ስለሚያደርጋት እንደተባለውም የአዳም ኅጢአት በዘር እንዳያልፍባት ምልኢተ ፀጋ ፣ምልኢተ ክብር ወይም ልዩ ፍጥረት አድርጎ እንደፈጠራት እንመለከታለን። 
 
– ‘እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና’ የሚለውም ቃል እግዚአብሔር ከሁሉም ፍጥረታት ጋር እንዳለ ብናምንም ከእሷ ጋር የሆነበት ምስጢር ግን ከአንስተአለም ለእናትነት መርጦ 9 ወር ከ5 ቀን መሀፀንዋን አለም አርጎ እንደአደረና ከስጋዋ ስጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ ስጋዋን ተዋህዶ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ ፍፁም አምላክ፥ ፍፁም ሰው መሆኑ የተገለፀበት ምስጢራችን እና መንፈሳዊ አይናችን ስለሆነች ፤ እግዚአብሔር ከእሷ ጋር የመሆኑን ምስጢር በእውነትም የተለየ መሆኑን ስናስብ፥ ታዲያ እናቱን ከአዳም ኀጢአት ለይቶ ፈጠራት ወይም የአዳም ኀጢአትን እንዳያልፍባት ከለከለ ብንል ምንድነው ሊበዛ የሚችለው? አንድ ትልቅ ባለስልጣን ወይም ጳጳስ ወይም እንግዳ ተጠርቶ፥ በእንግድነት በክብር ለመቀበል በተዘጋጀን ጊዜ እንኳን፥ እንግዳው የሚያርፍበትን አልጋ፣ የሚቀመጥበትን ወንበር ፣ የሚጠቀምበትን እቃ፣ የሚመገበውን ምግብ ፣ ብቻ በአጠቃላይ ለእንግዳው ክብር ይመጥናል ብለን የምናስበውን ሁሉ ምን ያህል ወጥተን ወርደን እንደምናሳምረው ሁሉ የሰማይና የምድር ፈጣሪ ዘለአለማዊ ንጉስ እግዚአብሔር ወልድ፥ እናቱ ያደረጋትን ድንግል ማርያምን ከውርስ ኀጢአት ቢከለክላት የሚያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለም። 
 
-‘ከሴቶች ሁሉ’ የሚለው ቃል የእሷ ድንግልና ለሴቶች ከተሰጣቸው የድንግልና አይነት የተለየ፥ በሃልዮ ድንግል፣ በነቢብ ድንግል፣ በገቢር ድንግል፣ ከወለደችውም በፊት ድንግል፣ በወለደችውም ጊዜ ድንግል፣ ከወለደችውም በኋላ ድንግል መሆኗን ስንመለከት ንፁሐ ስጋ፣ ንፁሐ ነፍስ፣ንፁሐ ልቡናን አስተባብራ የያዘች እውነተኛ ድንግል እና ቅድስት ስለሆነች ከሴቶች ሁሉ በዚህ  እና በሌሎችም ምስጢራት ትበልጣለች ማለት ነው። 
 
 4ኛ/  “ነብየ እግዚአብሔር ህዝቅኤልም ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ፤ ተዘግቶም ነበር፥እግዚአብሔርም ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል።” የሚለው ኃይለቃል፥ በምስራቅ በኩል ያለችው እመቤታችን ድንግል ማርያም መሆኗን በመሀፀንዋ ያደረውም የለዘርአብዕሲ የኃያላን ጌታ የጌቶች ጌታ የነገስታት ንጉስ ስለ እግዚአብሔር  ወልድ ስለሆነ እሱም ደግሞ በእራሱ ፈቃድ እና በመለኮታዊ ጥበቡ በሰዎች የተዋልዶ ልምድ ሳይሆን ያለዘርዓብእሲ ከመንፈስ ቅዱስ ስለሆነ እርሱ ያደረበት መሀፀን የድንግልናዋን እና የቅድስናዋን ክብር እጥፍ ድርብ ያደርገዋል ፤ ማህተመ ድንግልናዋም ለዘለዓለም ፀንቶ ይኖራል።(ሕዝ 44፥1-2) 
 
ይህ የነብዩ ቃል ለሌላ አይነት እምነት ትርጉም ሊሰጥ አይችልም ምክንያቱም ዘለአለም ተዘግቶ የሚኖር ቤተመቅደስ ከቶ በእስራኤል አገር ይቅርና በሌላም አለም የለም። ስለዚህ ይህ ምስጢራዊ ቃል ለድንግል ማርያም የተሰጠ ቃል ነው። 
 
5ኛ/ በእድሜ ደረጃ አያትዋ የምትሆነው እናታችን ቅድስት ኤልሳቤጥ ድንግል ማርያም ለሰላምታ ወደእሷ እንደመጣች ባየች ጊዜ በእብራዊያን ባልተለመደ አነጋገር የእግዚአብሔር መንፈስ ገልፆላት እንዲህ ከፍጥረት ሁሉ ልዩ መሆኗን እና የአምላክ ማደርያ መሆኗን ስትናገር “የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።  ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።” (ሉቃ 1፥43-45) በማለት እንዲህ እናታችን ኤልሳቤጥም የድንግል ማርያም ክብር ከሷ እንደሚበልጥ ወይም በራስዋ የፈቃድ አክብሮት ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ እንዳናራትና የመሀፀንዋ ፅንስ ሳይቀር በደስታ መዝለሉን ስትናገር ስንሰማ ታዲያ እግዚአብሔር አምላክ በማይቸግረው ነገርና ሁሉ በእጁ በሆነ ነገር እግዚአብሔር አምላክ እናቱ ትሆን ዘንድ የመረጣትን ድንግል ማርያምን አንፅቶ ፈጠራት ማለት የሚከብድ አይሆንም። 
 
በተጨማሪም ሊቃውንትም ፦ 
 
–      ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በድጓ ድርሰቱ፣
–      የሶርያው ሊቀጳጳስ ቅዱሰ ኤፍሬም በውዳሴው፣
–      የብህንሳው አባህርያቆስ በቅዳሴው፣
–      ሰለስቱ ምዕት በቀኖና እና ስርዓታቸው 
 
ባዘጋጁት የትምህርት እና መፅሐፍ እመቤታችን ቅድስት ማርያም በስጋዋም በነፍስዋም ንፅሒት እና ቅድስት ሆና የተፈጠረች መሆንዋን እንደ ሌሎቹ የአዳም ልጆች የኅጢአት ዘር እንዳላለፈባት በስፋት አስተምረዋል።
 
ጠቢቡ ሰለሞንም በመኃሊዬ በመኃሊይ መፅሐፉ “በእሾህ መካከል ያለሽ የሱፍ አበባ (የፅጌረዳ አበባ)” በማለት በዙሪያዋ ያለው የዳም ኅጢአት ሲሆን እሷን ግን በሰው መካከል ልዩ ሆና የተፈጠረች መሆንዋን በሚያስደንቅ አነጋገር ገልፇታል። (መኃመኃ 2፥2) 
 
ስለዚህ እንግዲህ ስለ እመቤታችን ስንናገር በእኛ በኅጢአተኞቹ የአቅም ደረጃ የማይሆን እና የምንናገረውም ለእሷ ክብር የማይመጥን ቢሆንም ያወቅነውን እና የተረዳነውን በስምዋ ለሚያምኑና ለሚማፀኑ፥ እንዲሁም መዳን ለሚገባቸው እውነቱን ማሳወቅ ስላለብን ነው። በቀጣይነትም ስለ እመቤታችን ድንግል ማርያም ቀደም ሲል ጀምረን ካቆምንበት የሚቀጥል ትምህርት ስለሚኖረን ለጊዜው ግን ጠያቂያችንም ሆኑ የዮሐንስ ንስኅ ድረገፅ መንፈሳዊ ትምህርት ተከታታይ ወገኖቻችን ሁላችሁም ይሄንን ስለ ድንግል ማርያም ያቀረብነውን አጭር ትምህርታዊ ማብራሪያ ሁላችሁም በማስተዋል አንብባችሁ ትረዱት ዘንድ እንዲደርሳችሁ አድርገናል። 
 
የእመቤታችን ድንግል ማርያም አማላጅነት እና የእናትነትዋ ፍቅር በሁላችን ላይ ይደር! 
 
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ
 
የቄደር ጥምቀት በንስኀ ቀኖና ውስጥ የሚካተት ስርዓት ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው የቄደር ጥምቀት የሚታዘዝለት ሃይማኖቱ ወይም ኦርቶዶክሳዊ የክርስትና ስርዓት የማይፈቅድለትን የተከለከለውንና ነውር የሆነውን ተግባር የፈፀመ ክርስቲያን የሚፈፅመው የንስሀ ቀኖና እንደሆነ ማወቅ ይገባል። የቄደር ጥምቀት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች የምግባር ችግር ያለባቸው እንደሆኑ ከዚህ በፊት ቄደር ለመጠመቅ የሚያስፈልገንን ዋና ምክንያታዊ ነገር በፈፀምነው የኀጢአት ጥፋት ነው። ከዚህ በፊትም ለቄደር ጥምቀት የሚያበቁ የጥፋት ወይም የኀጢአት አይነቶችን በዝርዝር እና በስፋት ገልፀናቸዋል።  ስለዚህ ማንኛውም ኦርቶደክሳዊ ክርስቲያን የፈፀመውን ኢክርስቲያናዊ ተግባር ወይም ኀጢአት በራሱ አምኖ እና ተፀፅቶ ለመንፈሳዊ አባቱ  ሲናዘዝ እንደ ቤተክርስቲያናችን ቀኖና የቄደር ጥምቀት የሚያስፈልገው ጥፋት ሆኖ ከተገኘ የቄደር ጥምቀት እንዲደረግ ይደረጋል። በአንፃሩ የቄደር ጥምቀት የሚያስፈልገው አይነት ከሆነ ደግሞ አንቀፀ ንስኀው የቤተክርስቲያን ቀኖና በሚያዘው ሌላ የንስኀ ቀኖና ይሰጣል ማለት ነው። ስለዚህ ጠያቂያችን የቄደር ጥምቀት አንዱ የንስኀ ክፍል መሆኑን እንዲረዱት ይህን አጭር መልዕክት ልከንልዎታል።