ስለ ቅዱስ ቁርባን
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!" (ማቴ 3: 1-2)
ተከታታይ ትምህርትና ለጥያቄዎት ምላሽ ለማግኘት ቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ
ስለ ቅዱስ ቁርባን
ምስጢረ ቅዱስ ቁርባን
“ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።” (ዮሐ 6፡51)
ስለ ቅዱስ ቁርባን ትምህርት
ቀደም ሲል ጀምሮ ዛሬም ቢሆን ተረፈ አይሁድ የሆኑ አንዳንድ የኑፋቄ እና የክህደት ሰዎች የጌታን ቃል ለማስተባበል የማይፈነቅሉት የሀሰት ድንጋይ፣ የማይቆፍሩት የክህደት ጉድጓድ የለም። በአንድ በኩል የክርስቶስ መድኅኒትነት እና አዳኝነት እናምናለን እያሉ በሌላ በኩል ነገረ ድኅነት የተፈፀመበት እሱ እራሱ የዘለአለም ህይወት እንድናገኝበት በልግስና የሰጠን ቅዱስ ስጋውን እና ክቡር ደሙን አምኖ በመቀበል ዘለአለማዊ ድኅነት ለማግኘት አለመቻላቸውን ስናይ የእነዚህ ሰዎች ክህደት ከፈሪሳውያን እና ከአይሁድ ክህደት የባሰ እንደሆነ መረዳት ይቻላል።
በእውነተኛ ሃይማኖት እና ክርስቲያናዊ ስነምግባር ፀንቶ ለሚኖር ክርስቲያን ይህ የክህደት እና የኑፋቄ አስተሳሰብ ሊያስደነቀው እና ሊያሰናክለው ፈፅሞ አይገባም። ምክንያቱም እውነተኛ አማኝ ባለበት ሁሉ መናፍቅ አለ። ንፁህ ስንዴ ባለበት እንክርዳድ አለ፣ ሰው ባለበት ቦታ ኩርንችት አለ፣ ብርሃን ባለበት ጨለማ አለ፣ ህይወት ባለበት ሞት አለ፣ ደግነት ባለበት ክፋት አለና ነው። እውነተኛ ክርስቲያን ግን ሁሉን ቻይ አልፋና ኦሜጋ የሆነው እምነቱን ለዘለአለም በማይለወጠው እና በማይሻረው አማናዊ ቃሉ “እውነት እውነት እላችኋለሁ የሰውን ልጅ ስጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ህይወት የላችሁም።” በማለት ዘለአለማዊ ድኅነን ለማግኘት የመንፈሣዊ አገልግሎታችን ሁሉ መደምደሚያ እና የጽድቃችን ሁሉ ማረጋገጫ ቅዱስ ቁርባን እንደሆነ አስረግጦ ነግሮናል። (ዮሐ6፥53)
የክርስቶስን ቅዱስ ስጋ እና ክቡር ደም መታሰቢያ ነው እንጂ አማናዊ አይደለም ብሎ የሚያስተምር እና የሚያምን ቢኖር የክርስቶስ ጠላት ነው። ክህደቱንም ከሰይጣን ክህደት የከፋ ያደርገዋል። ምክንያቱም ሰይጣን ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅ ነህ በማለት የባህሪይ አምለክ መሆኑን እንደመሰከረ በቅዱስ ወንጌል ተጽፏል። እውነተኛ ክርስቲያን ዘላለማዊ ህይወትን ለማግኘት እና የእግዚአብሔርን መ
ንግስት ለመውረስ ይችል ዘንድ ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌል “ስጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ህይወት አለው። እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ ስጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና።” (ዮሐ6፥54 እና55)
ለሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች በፃፈው መልዕክቱ ላይ “ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ የሰጠሁትን እኔ ከጌታ ተቀብዬዋለሁና ጌታ እየሱስ አልፎ በተሰጠባት በዛች ለሊት እንጀራን አንስቶ አመሰገነ፣ ቆርሶም…እንካችሁ ብሉ ይህ ስለእናንተ የሚሆን ስጋዬ ነው…እንዲሁም ከራት በኋላ ጽዋውን ደግሞ አንስቶ ይህ ደግሞ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው…ይህንን እንጀራ በበላችሁ ጊዜ ሁሉ ይህንም ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ትናገራላችሁና።” በማለት የክርስቶስን ስጋ እና ደም ስንቀበል ቸሩ መድኅንያለም ከቤተልሔም ጀምሮ እስከ ቀራንዮ አደባባይ ድረስ ስለእኛ ኅጢአት እዳ ሊከፍል (ካሳ ለመክፈል) የተቀበለውን መከራ፣ ህመሙን፣ ሞቱን፣ ትንሣኤውን፣ እርገቱን እና ዳግም ምፃቱን እያሰብን እንድንቀበል ሲያስረዳን ነው። (1ቆሮ11፥23-26)
በቤተክርስቲያን ውስጥ ቆመን ስናስቀድስ በምንቀበለው የቅዳሴ ስርዓት ውስጥ ተፅፎ እንደምናገኘው “አቤቱ ሞትህን እና ቅድስት ትንሣኤህን እንናገራለን” በማለት ተሰጥኦ የምንቀበለውም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረውን ቃል መሰረት በማድረግ ነው።
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምሮ መሠረት ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የሚፈልጉ ክርስቲያኖች ሊያደርጉት የሚገባ ጥንቃቄ የሚከተለው ነው፦
በመሰረቱ ማንኛውም ክርስቲያን የክርስቶስን ስጋ እና ደም መቀበል ክርስቲያናዊ ግዴታው ነው። ይሁን እንጂ ወደ ቅዱስ ስጋው እና ክቡር ደሙ ከመቅረቡ አስቀድሞ ሊያደርገው የሚገባው ቅድመ ዝግጅት፦
1/ የሚቀድሱ ቀሳውስት እና የሚቆርቡ ክርስቲያኖች በስርዓተ ጋብቻ ተወስነው የሚኖሩ ከሆኑ ከመቀደሳቸው እና ከመቁረባቸው በፊት 3 ቀን፣ ከቀደሱ እና ከቁርባኑ በኋላ ደግሞ 2 ቀን ከሩካቤ ስጋ ርቀው ንጽህናቸውን ሊጠብቁ ይገባቸዋል።
2/ ቅዱስ ስጋውን እና ክቡር ደሙን ለመቀበል ያሰበ ክርስቲያን ከሁሉ አስቀድሞ እራሱን ለካህን በማስመርመር የሚሰጠውን የንስሓ ቀኖና ፈፅሞ ከኅጢአት ንፁህ ሳይሆን በድፍረት ቢቀበለው እዳ በደል ስለሚሆንበት መጠንቀቅ ይገባዋል።
ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ “ስለዚህ ሳይገባው ይህንን እንጀራ የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ስጋ እና ደም እዳ አለበት። ሰው ግን ራሱን ይፈትን፣ እንዲሁም ከእንጀራው ይብላ ከጽዋውም ይጠጣ ሳይገባው የሚበላ እና የሚጠጣ የጌታን ስጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና ይጠጣልና” (1ኛ ቆሮ 11፤27-29)
3/ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የተዘጋጁ ካህናትም ሆኑ ምዕመናን 18 ሰዓታት ከሚበላ እና ከሚጠጣ ምግብ ተከልክለው በጾም ተወስነው መቆየት ይገባቸዋል
4/ ካህኑ በሚቀድስበት ቀን እንቅፋት ቢያገኘው ይህ ማለት ቢነስረው፣ ትውኪያ ቢመጣበት፣ የበላው ምግብ ብስና ቢሆንበት፣ የአካል መድማት ቢያጋጥመው፣ አካሉ ላይ ቁስል እና የመሳሰሉ ሁሉ ቢያጋጥመው በዚያን ዕለት መቀደስም ሆነ መቁረብ አይገባውም።
5/ ለመቁረብ የተዘጋጁ ምዕመናን የቅዳሴው ስርዓት ከመጀመሩ በፊት ወደ ቤተክርስቲያን ገብተው ቁመው ማስቀደስ አለባቸው። ቅዳሴ ሲጀመር ያልነበረ ካህንም ሆነ ምዕመን ስጋውን ደሙን ሊያቀብልም ሆነ ሊቀበል አልተፈቀደለትም። (ፍትሐ ነገስት አንቀፅ 12 ገጽ 137/97)
6/ ስለ ምስጢረ ቁርባን ተገቢውን ትምህርት አግኝቶ መድኃኒት እና ህይወት መሆኑን ያላመነ ሰው ቅዱስ ሰጋውን እና ከቡር ደሙን በድፍረት ሊቀበል አይገባም። አውቆ በድፍረት ሳያውቅ በስህተት እንዳይቆርብ መቆጣጠር እና በጥንቃቄ መከታተል እንደሚያስፈልግ በቀኖና ቤተክርስቲያን ተደንግጓል። (ፍትሐ ነገስት አንቀጽ 13 ገጽ 140/44)
7/ ንስሓ ተቀብሎ የቀኖና ጊዜውን ሳይፈጽም ለሞት የሚያሰጋ ደዌ ቢታመም ስጋውን እና ደሙን ከመቀበል አይከለከልም። ስጋውን እና ደሙን ከተቀበለ በኋላ ከበሽታው ከዳነ ከምእመናን ጋር በፀሎት ሊሳተፍ ይችላል። በቀኖና (በንስሓ) ወደ ተለዩ ሰወች እንዲመለስ አይገደድም። (ፍትሐ ነገስት 13 ገጽ 139/15)
8/ የሚጥል እና አረፋ የሚያስደፍቅ በሽታ ያለበት፣ ጋኔን (ሠይጣን) ያደረበት ሰው፣ ልዩ ልዩ የባዕድ አምልኮት የሚፈፅም ሰውማለትም የሚጠነቁል፣ የሚያስጠነቁል፣ በዛፍ በተራራ የሚያመልክ፣ ለዛር እና ለመናፍስት መስዋእት የሚያቀርብ እና የመሳሰለውን ሁሉ በሃይማኖት ስርአት የማይፈቀደውን ጥፋት የሚፈጽም ክርስቲያን ስጋውን እና ደሙን ከመቀበል ይከለከላል።
9/ ቀዱስ ቁርባን ከተቀበልን በኋላ መደረግ ሰለሚገበው ጥንቃቄ በሚመለከት ፦
– ቅዱስ ቁርባን በተቀበሉበት እለት ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ መሟገት እና በማናቸውም የጭቅጭቅ ቦታ መገኘት ክልክል ነው፣
– በቆረቡ እለት የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ ፣ ከሚስት ወይም ከባል ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ማድረግ፣ አብዝቶ መብላት እና መጠጣት፣ ፀጉርን መላጨት፣ ጥፍርን መቁረጥ፣ ከአካሉ ደም ማውጣት፣ በውሀ መታጠብ፣ ልብስን አውልቆ ራቁትን መሆን፣ የመሳሰሉትን ጥፋቶች መስራት ክልክል ነው።
የተወደዳችሁ እና የተከበራችሁ የ ዮሐንስ ንስሓ ድረገጽ ተከታታዮች ፤ የምስጢረ ቅዱስ ቁርባን ትምህርት እጅግ ሰፊ እና ጥልቅ ምስጢር ከመሆኑ የተነሳ አብዝቶ ለመጻፍም ሆነ እውነቱን ለመረዳት ሰፊ ጊዜ የሚያስፈልገው ቢሆንም አንኳን፤ በዚህኛው ክፍል የምስጢረ ቅዱስ ቁርባን ትምህርታችን በቂ ግንዛቤ እና ትምሀርት ልታገኙበት ትችላላችሁ ብለን ያሰብነውን አጭር የቁርባን ትምህርት በዚህ መልክ ሰለቀረበላችሀ ያለመሰልቸት አና ያለመታከት አንብባችሁ በመረዳት የነፍሳችን መድኃኒት ወደሆነው እና ዘለአለማዊ ህይወት ወደምናገኝበት ወደ ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ እንድትቀርቡ፤ ቅዱስ ቁርባን የተቀበላችሁም ሳትሰለቹ እንድትቀጥሉ በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላችኋለን።
ይህን ትምህርታችንን አስጀምሮ ያስፈጸመን አምላካችን ሁላችንንም ለቅዱስ ቁርባን ያብቃን
ምስጢረ ቅዱስ ቁርባን ክፍል አንድ ትምህርትን ለመመልከት ይህን ይጫኑ፦ https://yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን/
ስለ ምስጢረ ቅዱስ ቁርባን ጥያቄና መልስ ለመመልከት ይህን ይጫኑ፦ https://yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን/
ስለ ቅዱስ ቁርባን (ለአጠቃላይ ግንዛቤ)
👉🏾👉🏾👉🏾ምሥጠረ #ቅዱስ #ቁርባን
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገፅ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምትከታተሉ አባላቶቻችን ሁሉ፤ ስለ ምስጢረ ቅዱስ ቁርባን በሚመለከት የሚከተለውን አጭር ትምህርት ልከንላችኋልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።
ምሥጢረ ቁርባን ማለት ክርስቶስ ስለ እኛ ኀጢአት በመስቀል ላይ መሥዋዕት ሆኖ በሥጋው በሞቱ የዓለምን ኀጢአት ያስወገደበት የዘለዓለም ሕይወትን ያስገኘበት የመዳናችን መሠረት የጸጋችን ሁሉ ምንጭ የሆነውን የቅዱስ ሥጋውንና የክቡር ደሙን የማዳን ጸጋ የሚያመለክት ታላቅ የክርስትና ሃይማኖት ምሥጢር ነው። ክርስቶስ እንደ መሥዋዕትም እንደ ዐቢይ ሊቀ ካህናትም በመሆን ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ፈጽሟል (ዕብ7፥20-28)። እንደ ዐቢይ ሊቀ ካህናትነቱ በመስቀል ላይ የተቆረሰው ሥጋውን ያፈሰሰው ደሙን የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር በማቅረቡ ሰውን ከራሱና ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ፤ የጥልንም ግድግዳ አፈረሰ የተራራቀውን አቀራረበ።
ይህን ነገር የቁርባንን የምሥጢር ትርጉም ያስረዳናል። ቁርባን ማለት በአንድ በኩል ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መሥዋዕት በሌላ በኩል ደግሞ እኛ ወደ እግዚአብሕር የምንቀርብበትን የምንቀራረብበትንና የምንዋሐድበትን ሁኔታ ያሳየናል። ልንቀርብና የመለኮታዊውንም ጸጋ ተሳታፊ ልንሆን የምንችለው በምሥጢረ ቁርባን አማካኝነት ኀብስቱና ወይኑ ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደም ተለውጦ ስንቀበለው ነውና ምሥጢር መሆኑን ከዚህ ላይ እናስተውላለን።
“ቁርባን” የሚለው ቃል መሠረቱ ከዕብራይስጥ ቋንቋ የመጣ ሲሆን የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም “ስጦታ” ማለት ነው። ይህም ማለት እንደ ኦሪቱ ቁርባን ሰው ለእግዚአብሕር ያቀረበውን ስጦታ ብቻ የሚያመለክት ሳይሆን እግዚአብሔርም በተለየ ሁኔታ ለሰዎች ደህንነት በዓለም ሁሉ የሰጠውን በሥጋና በደም የመጣውን የልጁን ስጦታ ያስገነዝባል። ስለዚህም ለዓለም መድኃኒት ሆኖ የተሰጠው በጸሎተ ኀሙስ ማታ ወደ ጌታ ሥጋና ደም የተለወጠው ኀብስትና ወይን ዛሬም በጸሎተ ቅዳሴ የጌታን ሥጋና ደም ሆኖ የሚቀርበው ቅዱስ ቁርባን ይባላል። እርሱም ከእግዚአብሕር የተሰጠ የተቀደሰ ስጦታና መሥዋዕት ነው። እንግዲህ ለኃጢአታችን መሥዋዕት ሆኖ ከእግዚአብሕር የተሰጠንን እኛ ደግሞ ከምስጋና ጋር መልሰን ለእርሱ እናቀርባለን።
ስለዚህ ነው በጸሎተ ቅዳሴ ካህኑ “አምላኪየ እግዚአብሔር ሆይ ደስ የሚያሰኝህ መሥዋዕት የልጅህ ሥጋ እነሆ። በዚህም ኀጢአቴን ሁሉ አቃልልኝ ስለ እኔ አንድ ልጅህ ሙቷልና። ስለ እኔ በቀራንዮ የፈሰሰ ንጹሕ የሚሆን የመሲሕም ደም እነሆ ስለ እኔ ይጮሀል። ይህ የሚናገር ደም የእኔን የባርያህን ኀጢአት የሚያስተሠርይ ይሁን” በማለት የእግዚአብሔርን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀርባል /የሐዋርያት ቅዳሴ፥ ቁጥር 105-106/ ።
ቅዱስ ቁርባን በምሳሌና በትንቢት
በብሉይ ኪዳን ታሪክ ውስጥ ለሥጋውና ለደሙ ማለት ለምሥጢረ ቁርባን የተመሰሉ ምሳሌዎች አሉ። በጠቅላላ የኦሪት መሥዋዕት ሁሉ ለወንጌሉ መሥዋዕት ምሳሌነት ቢኖራቸውም ዋና ዋናዎቹን ብቻ እንጠቅሳለን።
መጀመሪያው የልዑል እግዚአብሕር ካህንና የሳሌም ንጉሥ ያቀረበው የኀብስትና የወይን መሥዋዕት ለክርስቶስ ዘላለማዊ ሊቀ ካህናትነትና ለሥጋው ወደሙ ዓይነተኛ ምሳሌ ሆኖ ይነገራል (ዘፍ14፥18፣ ዕብ5፥6 እና 10፥7-17)።
ሁለተኛው ከቀሳፊ የሞት መልእክት አድኖ ከግብፅ ባርነት ነፃ ያወጣቸው የፋሲካ በግ ደም መረጨትና ሥጋውም ተጠብሶ መበላቱ የእግዚአብሔር በግ ለተባለው ለክርስቶስ አዳኝነትና ለምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ ሆኗል (ዘፀ 12፥1-51፣ 1ኛ ቆሮ 5፥7)።
ሦስተኛው እስራኤላውያን በምድረ በዳ ይመገቡት የነበረው ከሰማይ የወረደው መና ዛሬ ምእመናን ለነፍሳቸው ምግብ የሚቀበሉት የሥጋውና የደሙ ምሳሌ ነው (ዘቀ16፥ 16-23፣ ዮሐ 6፥ 49-51)።
አራተኛው ጥበብ ያዘጋጀችው ማዕድ ያረደችው ፍሪዳ የጠመቀችው የወይን ጠጅ የላከቻቸው አገልጋዮቿ የተጠሩት ሰዎች ሁሉ ምሳሌነት እንዳላቸው ይነገራል። ጥበብ የክርስቶስ ማዕድ የሥጋው የደሙ አገልጋዮች የካህናት፣ ተጋባዞች የምእመናን ምሳሌ ናቸው ተብሎ ይተረጎማል (ምሳ 9፤1-5)። ይህን የመሳሰሉ ሌሎች ምሳሌዎችም አሉ (ዘሌዋ 2፤23፥13-14፣ ሲራክ 24፥19-21)
ትንቢትም ስለ እውነተኛው ቁርባን ተናግሯል። “ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአዝሓብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና በየሥፍራውም ለስሜ እጣን ያጥናሉ፤ ንጹሕም ቁርባን ያቀርባሉ” (ሚል1፥11)። ይህ ስለ ወንጌል መሥዋዕት የተነገረ እንጂ ስለ ኦሪት መሥዋዕት አይደለም። ምክንያቱም የኦሪት መሥዋዕት በኢየሩሳሌም ከተማ በቤተ መቅደስ ብቻ እንጂ በሌላ ቦታ እንዳይፈጸም በሕግ የተከለከለ ነው። እንግዲህ ነቢዩ ሚልክያስ “ንጹሕ ቁርባን” ያለው እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ለአሕዛብ ወንጌል በተሰበከበት ሥፍራ ቤተ ክርስቲያን በተቋቋመበት ቦታ ሁሉ የሥጋውና የደሙ ንጽሕ መሥዋዕት መቅረቡን የሚያመለክት ነው።
ሌላው ደግሞ የኢሳያስ ትንቢት ነው። “እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ ወደ ውሀ ኑ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም፤ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ… በረከትንም ብሉ…” (ኢሳ.55፥1-2)። ይህ የነቢዩ ቃል በመብልና በመጠጥ ስለሚመጣው ስለ ምሥጢረ ቁርባን በትንቢትና በምሳሌ እንደ ተነገረ ይታመናል።
የምሥጢረ ቁርባን አመሠራረት
ምስጢረ ቁርባንን ጌታችን ከሕማማቱና ከሞቱ በፊት በዋዜማው ኀሙስ ማታ መሥርቶታል። ይህም ሰዓት በአይሁድ የቀን አቆጣጠር ወደ ዓርብ ይታሰባል። በዚያም ወቅት የኦሪት የፋሲካ በግ የሚሠዋበት ጊዜ በመሆኑ ጌታችን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የኦሪትን መሥዋዕት አሳልፎ መሥዋዕተ ወንጌልን መሥርቷል። በዚያች ምሽት የኦሪቱ በግ መሥዋዕትነት አበቃ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እውነተኛው የእግዚአብሕር በግ ይሠዋል። እርሱም የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው። ስለዚህ በማዕዱ ዙሪያ ለተሰበሰቡት ሐዋርያቱ በብሉይ ኪዳን ምሳሌ የተመሰለለትን፤ ትንቢት የተነገረለትን አዲሱን ቃል ኪዳን ጌታ በራሱ ሥጋና ደም መሠረተ። የእውተነተኛው መሥዋዕት ምሳሌ የሆነው የኦሪቱን ማዕድ እየበሉ ሳለ “ኢየሱስ እንጀራን (ኀብስትን) አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፤ እንካችሁ፤ ብሉ፤ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፤ ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” በማለት ምሥጢረ ቁርባንን መሠረተ (ማቴ 26፥26-28)። ኪዳን ማለት ከእግዚአብሔር ጋር የምንገባውን ቃል ኪዳን የሚያመለክት ነው።
በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት ከቤተ እሥራኤል ጋር ቃል ኪዳን የገባው በእንስሳት ደም ነበር (ዘፀ 24፥1-11ጥ። ያን ጊዜ ቤተ እሥራኤል ቃል የገቡት ሕገ ኦሪትን ሊፈፅሙ አሠርቱ ትእዛዛትን ሊጠብቁ ሥርዓቱን ሊያከብሩ ነበር። እግዚአብሔር ደግሞ በበኩሉ አምላካቸውና ጠባቂያቸው ሊሆን ምድረ ርስትንም ሊያወርሳቸው ተስፋ ሰጣቸው፤ ቃል ገባላቸው። በወንጌል ግን እግዚአብሔር ቃል ኪዳን የገባው በልጁ ደም ነው።
(ይቀጥላል)👇👇👇
👉🏾👉🏾👉🏾ምሥጠረ #ቅዱስ #ቁርባን
(ቀጣይ ክፍል)👆
እግዚአብሔርም የፈጸመልን አዲሱ ኪዳን ከብሉይ ኪዳን እጅግ የላቀ ነው። ምክንያቱም በክርስቶስ የሐዲስ ኪዳን ደም ኀጢአታችን ተወግዶልናል። ከእግዚአብሔር ታርቀናል፤ የእግዚአብሔርን ልጅነት አግኝተናል፤ እግዚአብሕርም አባት ሆኖን የመንግሥቱ ወራሾች እንድንሆን አብቅቶናል። ስለዚህ ይህን ወሰን የሌለው እስከ ሞት ድረስ የወደደንን የክርስቶስን ፍቅር እያሰብን እግዚአብሔርን በልጁ ስም ዘወትር ለማመስገን ወንድሞቻችንንም ለማፍቀርና ችግረኞችንም ለመርዳት የወንጌልንም ትዝዛዝ ለመፈጸም እኛም በበኩላችን ቃል መግባት ይኖርብናል።
ቃል ኪዳን ከገባንበት ዋናው ነገር በቆረብንና ቅዳሴ ባስቀደስን ቁጥር የበደላችንንና የኀጢአታችንን ሥርየት ያገኘንበትን ከእግዚአብሔር የታረቅንበትን የክርስቶስን ሕማምና ሞት ማሰብና ማስታወስ ነው። ስለዚህ ነው ጌታችን ህብስቱን አንሥቶ ባርኮና ቆርሶ ለሐዋርያቱ ከሰጣቸው በኋላ “ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ የኸን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” ብሎ ያላቸው (ሉቃ 22፥19)። መታሰቢያዬ የተባለው ስለ ሕማምና ሞቱ መሆኑንና ይህንንም የሞቱን ዜና የመስቀሉን ነገር ጌታ እስኪመጣ ድረስ በምሥጢረ ቁርባን አማካኝነት እንደሚነገር ከሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንማራለን (1ኛ ቆሮ 11፥23-26)። ዛሬም በጸሎት ቅዳሴ “ንዜኑ ሞተከ እግዚኦ” የተባለውን እያዜምን እናስታውሰዋለን። በምንቆርብበት ጊዜ የምናየው የተፈጥሮ ኀብስትና ወይን ብቻ መስሎን እንዳንሳሳት፤ የማይታየው መለኮት የተዋሐደው የጌታ ሥጋና ደም መሆኑን አምነን መቀበል አለብን፤ አለበለዚያ በራሳችን ላይ ፍርድን እናመጣለን።
ሳይገባው ራሱን ሳይፈትንና ሳይመረምር የሚቆርብ “የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና። በማለት ይህው ሐዋርያ ያስጠነቅቀናል።
“ስለዚህ ሳይገባው ይህን እንጀራ ኀብስት የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት። ሰው ግን ራሱን ይፈትን እንዲሁም ከእንጀራው ከኀብስቱ ይብላ ከጽዋውም ይጠጣ ፤ ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና ፤ይጠጣልምና። ስለዚህ በእናንተ ዘንድ የደከሙና የታመሙ ብዙዎች አሉ አያሌዎችም አንቀላፍተዋል። ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር፤ ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ፥ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን” (1ኛ ቆረ 11፥27-32)
በምሥጢረ ቁርባን የሚገኝ ጸጋ
የሚታየው ኀብስትና ወይን በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ በክርስቶስ ቃል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በካህኑ ጸሎት ወደ ጌታ ሥጋና ደም መለወጣቸውን በሙሉ ልብ አምነውና በንስሐ ተዘጋጅተው ለሚቀበሉ ሁሉ በወንጌል የተጸፃፈውን የማይታየውን ጸጋ ለማግኘት ይችላሉ። የሚከተሉትን የእግዚአብሕር ጸጋ ማግኘት ለአማኞች ሁሉ ከፍተኛ ጥቅምና እድል ነው።
– የመጀመርያው ጸጋ ሰውና እግዚአብሔርን ያራራቀውን ኀጢአትን ማስወገድ ነው። ስለዚህ ነው የቁርባን ምሥጢር ሲመሠረት ጌታችን ይህ ደሜ ነው ለብዙዎች የኀጢአት ሥርየት የሚፈሰው በማለት የጸጋውን ስጦታ የጀመረው (ማቴ 26፥27-28)። የኀጢአት ሥርየት ከተገኘ ከእግዚአብሕር ጋር እርቅና ሰላም ይወርዳል። እርቅ ከተገኘ ደግሞ ሌሎቹ ስጦታዎች ደግሞ ይጨመራሉ። ኀጢአታቸው የተተወላቸው ብፁዓን ናቸውና (መዝ 31፥1)።
– ከዚህ ቀጥሎ በምሥጢረ ቁርባን የምናገኘው ጸጋ ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆነን በኀብረት መኖር ነው። ይህም ማለት እኛ በእርሱ እርሱ በእኛ ይኖራል ማለት ነው። “ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ” በማለት ጌታ አረጋግጦልናል (ዮሐ 6፥56)። ነገር ግን ከቁርባን እርቀን ሥጋውና ደሙን ሳንቀበል ብንቀር በራሳችን ሕይወት አይኖረንም። ምክንያቱም አንዲት የወይን ሐረግ ከወይኑ ግንድ ተለይታ ለመኖር አትችልምና።
“ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ እውነት እውነት እውነት እላችኋለሁ የወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስን ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም” (ዮሐ 6፥53)። እንግዲህ የመጨረሻውን ፀጋ የዘላለም ሕይወትን የምናገኘው ለትንሣኤውም የምንበቃው በሥጋና በደሙ ነው። “ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ (ዮሐ 6፥54)።
– ከላይ ከተጠቀሱት ፀጋዎች ሌላ ምሥጢረ ቁርባን በንስሓና በፀሎት ሆኖ በሚገባ ተዘጋጅቶ የሚቀበል ሁሉ ነፍሱን ከመራብና ከመጠማት ያድናታል። ምክንያቱም ሥጋውና ደሙ እውነተኛ መንፈሳዊ ምግብ ስለሆነ ነው። “ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፥ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምን ሁል ጊዜ ከቶ አይጠማም” (ዮሐ 6፥35)።
– ምሥጢረ ቁርባን የሚያስገኘው ጸጋ ሰውን ከእግዚአብሕር ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ሰውንና ሰውንም ያቀራርባል። ስለዚህ የክርስቶስን ሥጋና ደም የተቀበሉ ሁሉ እርስ በርሳቸው በፍቅር የተሳሠረ ኅብረትና አንድነት አላቸው፦ ምክንያቱም በቁርባኑ ሁላችንም የክርስቶስ አካልና አባል ሆነናልና። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ሁላችንም ከአንዱ ኀብስት እንካፈላለንና። በሥጋ የሆነውን እሥራኤል ተመልከቱ፤ መሥዋዕቱን የሚበሉ የመሠዊያው ማሕበርተኞች አይደሉምን?” (1ኛ ቆሮ 10፥16-18፣ ዘሌዋ 7፥6 እና 15)። እንግዲህ ይህ ጥቅስ የሚያስተምረን በሥጋውና በደሙ ሁላችን አንድ የእግዚአብሕር ቤተሰብ መሆናችንን ነው። በአፀደ ነፍስም በአፀደ ሥጋም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ እንደ አንዲት የተቀደሰች ማሕበር ይቆጠራሉ። ሁሉም የአንድ የክርስቶስ አካል ሆነዋልና።
ይቀጥላል
ምንጭ ፦ ትምህርተ ሃይማኖትና
ክርስቲያናዊ ህይወት
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉🏾👉🏾👉🏾#ቅዱስ #ቁርባን ምሥጢር ስለተባለበት ምክንያት እና ምሥጢረ ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል ስለየሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን በሙሉ፤ ቅዱስ ቁርባን ምሥጢር የተባለበትን ምክንያት እናለ ምሥጢረ ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል ስለየሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች በሚመለከት ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁን ትምህርት እንደሚከተለው ስለላክን አብንባችሁ ትማሩበት ዘንድ በአጽንኦት አደራ እንላለን።
👉የቅዱስ ቁርባን ምሥጢርነት
የቁርባን ምሥጢራዊነቱ በሚታየው ካህን እጅ በሚሰጠው በሚታየው ኅብስትና ወይም ከመታየት በላይ ከሆነው አምላክ የማይታየውን ሕይወት መንፈሳዊን የምናገኝበት መሆኑ ነው። አንድም በሚታይ አገልግሎት ማለትም በጸሎተ ቅዳሴ ኅብስቱና ወይኑ በየትኛው ሰዓት እና እንዴት ባለው መንገድ ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደምነት እንደሚለወጥ አይታወቅምና ምሥጢር ተብሏል። የበቁ አባቶች ግን አይተውታል። አንዳንዶቹ “ሀበነ…” ሲሉ መሥዋዕቱ በግ ሆኖላቸው ሌሎች ደግሞ ራሱ ክርስቶስ ተሰቅሎ አይተው ተገርመዋል። ይሁንና በእምነትና በመንፈሳዊ ብቃት ካልሆነ በቀር የማይታይ እንደመሆኑ መጠን ምሥጢር ነው።
ጌታችን የቁርባንን (የሥጋውንና ደሙን) አስፈላጊነት ሲናገር “እውነት እውነት እላችኋለሁ ፤ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም” ብሏል። (ዮሐ 6፥53) እንደሚታወቀው ሰው የተገኘው ሕይወት ከሌለው አፈር ነው። ሕያው የሆነውም ከእግዚአብሔር እስትንፋስ የተነሣ ነው። ሊቀ ነቢያት ሙሴ ስለዚህ ነገር ሲናገር “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ” ብሏል። (ዘፍ 2፥7) ይህን የሰው ነፍስ የማትሞት ሕያዊት መሆንዋን ያሳያል። ነገር ግን ጽድቅን ካልሠራች ይልቁንም በኅጢአት ካደፈች መኖሪያዋ ሲኦል አኗኗሯም በስቃይ የተመለ ይሆናል። ይህ ደግሞ ትልቁ ሞት ነው።
ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ “ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው። በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ” ብሏል። (ራእ 20፥14) እዚህ ላይ ሁለተኛ ሞት ያለው የእሳት ባሕር በተባለች ገሃነም መኖርን ነው። እንግዲህ በዚያ በእሳት ባሕር ላለመጣል ይልቁንም ፍጹም ክብር ባለበት በመንግሥተ ሰማያት ለመኖር በሕይወት መዝገብ መጻፍ ያስፈልጋል። ይህ በሕይወት መዝገብ የመጻፍ ጥበብ ደግሞ ሕያው መለኮት የተዋሐደውን የክርስቶስ ሥጋና ደም ተቀብሎ ክርስቶስን መዋሐድ ነው።
👉ለምሥጢረ ቁርባን የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች
1. እምነት
ምሥጢረ ቁርባን ከሚያስፈልጉት ቅድመ ሁኔታዎች አንዱ እምነት ነው። ይህውም ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥሉስ ቅዱስ አንዱ አካል መሆኑን ፣ ፍጹም ሰው ፍጹምም አምላክ መሆኑን ማመን እና ሥጋውና ደሙም ነፍስ የተለየው መለኮት የተዋሐደው ነው ብሎ ማመንን ይጠይቃል።
ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው፤ አንድ አካል አንድ ባሕርይ መሆኑን የማያምን ማለትም እንደ ንስጥሮስ ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ አሊያም እንደ ልዮን አንድ አካል ሁለት ባህርይ ወይም እንደ አውጣኪ ሥጋ የሌለው መለኮት ብቻ ወይም እንደ አርዮስ ፍጹም ፍጡር (ዕሩቅ ብእሲ) የሚል ግን ሥጋውንና ደሙን መቀበል አይችልም። ቢቀበልም ሕይወት አያገኝበትም።
ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ስንል ተዋሕዶን ማለትም ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ መገኘቱን እንናገራለን። በዚህ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ያለበት ጉዳይ ሁለቱ አንድ የሆነው አንዱ ተጥሎ ሌላኛው ተወስዶ ወይም አንዱ በአንዱ ተጣፍቶ ሳይሆን ሥጋ የመለኮትን ባሕርይ መለኮትም የሥጋን ባሕርይ ገንዘባቸው በማድረግ መሆኑን ነው። ስለሆነም የምንቀበለው ሥጋና ደምም የዕሩቅ ብእሲ ሥጋና ደም ሳይሆን ሕያው ዘለዓለማዊ መለኮት የተዋሐደው መሆኑን አምነን ልንቀበለው ይገባል። ይህን እውነት በእምነት ሳይቀበል ማለትም ክርስቶስ መለኮት ብቻ ነው፥ አሊያም ሥጋ ብቻ ነው በሚል እምነት መቁረብ አይቻልም። ምክንያቱም መለኮት የተለየውን በድን ቢቀበሉ ሕይወት አይሰጥምና። ሥጋን ያልተዋሐደ መለኮትም ቢሆን ረቂቅ እንደመሆኑ ምግብ ሊሆን አይቻልምና።
2. ንስሐ መግባት
የክርስቶስ ስጋና ደም ለመቀበል ከእምነት በተጨማሪ በሥጋም በነፍስም ንጹሕ ሆኖ መቅረብ ያስፈልጋል። ይህም ሲባል እድፈ ነፍስን በንስሐ፥ እድፈ ሥጋን በውሀና በሳሙና መታጠብ ማለት ነው። እድፈ ነፍስ የተባለው ኅጢአት ነው። ከእድፈ ነፍስ ንጹሕ መሆንም ስንል የቀሙትን መልሰው የበደሉትን ክሰው፤ ኅጢአትንና በደልን ሁሉ ለካህን ተናዝዘው ካህን የሰጠውን ቀኖና በተገቢ ሁኔታ ከፈጸሙ በኋላ በንስሐ ጥምቀት መታጠብ የሚገባ መሆኑን ለመናገር ነው። በደልን ሳይናዘዝ እና ንስሐ ሳይጨርሱ መቁረብ ግን በሕይወት ፈንታ የሞት ፍርድ የሚያመጣ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ሲያብራራው “ሳይገባው ይህን እንጀራ የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት። ሰው ግን ራሱን ይፈትን እንዲሁም ከእንጀራው ይብላ ከጽዋውም ይጠጣ፤ ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታ ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድን ይበላልና፥ ይጠጣልምና”። ብሏል (1ኛ ቆሮ 11፥27-29)
ይቆየን
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን ላይ ያገኛሉ
👉🏾👉🏾👉🏾 ስለ ምስጢረ #ቅዱስ #ቁርባን
👉ቅዱስ ቁርባን ምንድነው?
👉ቅዱስ ቁርባን አመጣጡና ስርዓቱስ እንዴት ነው?
👉ቅዱስ ቁርባን ምስጢር የተባለውስ ለምንድነው?
👉ቅዱስ ቁርባን የሚገባው ለማን ነው?
👉ቅዱስ ቁርባን ከመቀበላችን በፊት የምናደርገው ዝግጅት ምንድነው
👉ቅዱስ ቁርባን በመቀበላችን ወቅት የምናደርገው ዝግጅት ምንድነው
👉ቅዱስ ቁርባን ከተቀበልን በኋላ የምናደርገው ጥንቃቄ ምንድነው
ሚስጥረ ቁርባን በቤተክርስቲያናችን ቀኖና መሰረት ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስተያን አንዱና ዋነኛው ነው። ቁርባን ማለት ቃሉ የሱርስትና የግሪክ (የአረብ) ቃል ሲሆን ትርጉሙም በቁሙ ገፀ በረከት፣ የገንዘብ፣ የእውቀት፣ የጉልበትና የጊዜ ስጦታ ማለት ነው። በብሉይ ኪዳን ዘመን እስራኤላውያን ስለ ኅጢአታቸው ሆነ ስለ እግዚአብሕር ክብር ብለው የሚያቀርቡት የእንስሳት ደም ሌላ እጅ መንሻ ሁሉ መሥዋዕት፣ ቁርባን ይባል ነበር።
በሐዲስ ኪዳን ግን ቁርባን ወይም መሥዋዕት ማለት እግዚአብሔር ራሱን ከሰው ልጆች ጋር ለማስታረቅ መባ፣ አምሀ አድርጎ ያቀረበው አማናዊ (እውነተኛው) መሥዋዕት የእግዚአብሕር በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በመሆኑም በዘመነ ሐዲስ ቁርባን ማለት የአምላካችን የመድኅኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሥጋውና ደሙ ነው።
አማናዊውን የቅዱስ ቁርባን ሥርዓት የመሠረተው ራሱ አምላካችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ስርዓቱንም የጀመረበት እለቱ የስቅለት ዋዜማ በጸሎተ ሀሙስ ነው። መድኅኒታችን ይህን ታላቅ ሥርዓትና ምስጢር ሲመሠርት ከእርሱ ጋር ያሉት አስራ ሁለት ደቀ መዛሙርቱ ብቻ ናቸው እን እንደቀድሞው ይከተሉት ለነበሩት ሕዝብ ሁሉ አልገለጸውም። ዛሬም ቤተክርስቲያን በመጎናዘፍያ ሸፍናና አክብራ የምታቀርበው ለዚህ ነው። አንድም ጌታችን በመስቀል ላይ በተሰዋ ጊዜ ፀሀይ ጨልማ ጨረቃ ደም ለብሳ ከዋክብት እንደ ቃርያ ፍሬ እረግፈው ሸፍነውታል። መሥዋዕቱን እንኳን ተራ ተርታ ሰው የሰማይ መላዕክት አይነኩትም ይህ በስልጣነ ሐዋርያት ለተተኩ ለካህናት ብቻ የተሰጠ ነው።
ቅዱስ ቁርባን ምሥጢር መባሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ህብስቱን አንስቶ ባርኮና ቀድሶ ለደቀመዛሙርቱ “ይህ ሥጋዬ ነው” ብሎ ሰጣቸው። ስለዚህ ህብስቱ ተለውጦ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር ፣ ወይኑም ተለውጦ ደመ ወልደ እግዚአብሕር መሆኑ ታላቅ ምሥጢር ነውና ምሥጢር የሚለውን ስያሜ ያገኘው ለዚህ ነው። (ማቴ 26፥26) ፣ ማር 14፥22) ዛሬም ቀሳውስቱ ኅብስቱን የሚያዘጋጁት ከንጹህ ስንዴ ብቻ ነው፥ ወይኑን የሚያዘጋጁት ከንጹህ የወይን ፍሬ ወይንም ዘቢብ ብቻ ነው። ኅብስቱ ሥጋ አምላክ ወይኑም ደመ አምላክ ለመሆን የሚለወጠው ቄሱ “አእኮተ ባረከ ወቀደሰ” ብሎ በባረከው ጊዜ የካህኑ ሥልጣን ፣ ቃለ እግዚአብሕር ፣ ግብረ መንፈስ ቅዱስ ህብስቱን ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር (ሥጋ አምላክ) ወይኑንም ደመ ወልደ እግዚአብሔር (ደመ አምላክ) አድርጎ ይለውጠዋል። ይህም ለአማኞች ብቻ በእምነት ዓይን የሚታይ ለማያምን የተሰወረ ስለሆነ ቅዱስ ቁርበባንን ምሥጢር ያሰኘዋል። በተጨማሪ የሚታይ አገልግሎት የማይታይ ጸጋ ስለሚገኝበት ምስጢር ተሰኝቷል።
ቅዱስ ቁርባን ከመቀበላችን በፊት መገንዘብ ያለብን
– የመሥዋዕቱን መለወጥ ፣ ህብስቱ ተለውጦ ሥጋው ወይኑ ተለውጦ ደሙ መሆኑን ከልብ ያለ ጥርጥር ማመን ይገባል። “ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና እንካችሁ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ጽዋውንም አንስቶ አመስግኖ ሰጣቸው እንዲህም አለ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ…ደሜ ይህ ነው” (ማቴ26፥26)
– ቅዱስ ቁርባን ለኅጢአት እድፍ መንጺሒ ለኅጢአት ቁስል ፈውስ የተሰጠ መሆኑን ማመን ይገባል። “እንዲህም አለ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኅጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” (ማቴ 26፥27)
– የዘለዓለም ሕይወትን የሚያስገኝ መሆኑን አምኖ መቀበል ይገባል “ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው እኔም በመጨረሻ ቀን አስነሳዋለሁ” (ዮሐ 6፥53)
– በሚቀበሉት ቅዱስ ቁርባን ክርስቶስ ከእርሱ ጋር እነርሱ ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆነው እንደሚኖሩ ፥ ሥጋውም ከሥጋቸው ደሙ ከደማቸው ተዋህዶ አምላካቸው ከእነርሱ ጋር በጸጋ ተዋህዷቸው እንደሚኖር ማመን ይገባል። (ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ ከእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ” (ዮሐ 6፥56)
– ከቀደመ ኅጢአት መጸጸት ፣ መናዘዝ ፣ መመለስ እንዲሁም ከሚመጣው ኅጢአት መጠበቅ ይገባል። “ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግስት ወንጌል እየሰበከና ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ” (ማር 1፥14) አንድም የእግዚአብሔር መንግስት ማለት አንድም ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን ነው።
– ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የተወሰነ የዕድሜ ገደብ የለም። በ40 እና በ80 ቀን ተጠምቀን የእግዚአብሔርን ልጅነት አግኝተን ቅዱስ ቁርባን መቀበል ከጀመርንባት ዕለት ጀምሮ እስከ ህይወት ፍጻሜያችን ከቅዱስ ቁርባን መራቅ የለብንም። ወጣትነትን በራሱ እንደ ኅጢአተኝነት ወይም ለቅዱስ ቁርባን ብቃት የሌለው ሕይወት አድርጎ በማሰብ ፥ መቁረብ የሚገባን በህጻንነት እና በስተርጅና እድሜ ብቻ እንደሆነ ማሰብ ትልቅ ስህተት ነው። እንዲያውም ነብዩ ሰሎሞን “በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ” (መክ12፥1) ነው ያለን። ስለዚህ ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብና ላለመቅረብ የተመደበ እድሜ የለም ። ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቀን በልዩ የኅጢአት ጎራ ከተዘፈቅን ብቻ ነው። ያለዕምነት በድፍረት ያለ ንስሐ በኅጢአት መቀበል አይገባም። “አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በጾምም በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ” (ት.ኢዮ. 2፥12) “ኅጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም (ሐዋ 3፥20)
– ባልና ሚስት በመጀመሪያ ጊዜ አብረው በአንድነት መቁረብ ይገባቸዋል። ምናልባት ባልና ሚስት ከዚህ በፊት አብረው ያልቆረቡ ከሆነ ተነጣጥለው ወይም አንዱ ወገን ለብቻው መቁረብ አይፈቀድም። አንድ ጊዜ አብረው ከቆረቡ በኋላ ባሉት ጊዜያት ግን ተነጣጥለው መቁረብ ይችላሉ። ይህ የመነጣጠል ጉዳይ ሳይሆን በቀን ልዩነት የመቁረብ ጉዳይ ነው።
– በአጠቃላይ፥ መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተው ለሁሉ ነውና ፥ ያገባ ያላገባ፣ የዘር፣ የቀለም፣ የጾታ፣ የዕድሜ ልዩነት እንደመመዘኛ መውሰድ የተሳሳተ አመለካከት ነው። ማንም ሰው ከልጅነቱ አንስቶ እስኪያገባ ድረስ፣ ሲያገባም ( ከባል/ከሚስት ጋር በአንድነት)፣ ከትዳር በኋላም እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል ሊኖር ይገባዋል።
ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የሚደረግ ዝግጅት
1. በፍፁም እምነት መዘጋጀት። የምንቀበለው ጌታችን በዕለተ አርብ በቀራንዮ መስቀ ላይ ለድህነተ ዓለም የቆረሰውን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደሙን መሆኑን ማመን ይገባል። በተጨማሪም ለሰራሁትና ንስሐ ለገባሁበት ኅጢአት ስርየት አገኛለሁ፣ ከሚመጣ ኅጢአት የምጠበቅበት ሃይል አገኛለሁ፣ ክርስቶስ በእኔ እኔ በክርስቶስ እኖራለሁ፣ የዘለዓለምን ድህነት አገኛለሁ፣ ከደዌ ሥጋ ከደዌ ነፍስ እጠበቃለሁ፣ እያልን በፍጹም እምነት መዘጋጀትና የተቀበልነውን ከኅጢአት ርቆ በንጽህና ጠብቀን በእምነት መዘጋጀት ይኖርብናል።
(ይቀጥላል)👇
ስለ ምስጢረ ቅዱስ ቁርባን
(ቀጣይ ክፍል)
2. ቅዱስ ቁርባን የሚቀበሉት በጋብቻ ሥርአት የሚኖሩ ከሆነ ከመቁረባቸው በፊት 3 ቀን ከሩካቤ ሥጋ መከልከል ይገባቸዋል። ይህ ግንኙነት ኅጢአት ሆኖ ሳይሆን ግብረ ሥጋ ግንኙነት (የሥጋ ሥራ) ስለሆነ ለተቀበሉት ክብር ነው።
3. ማንኛውም ሰው ስለሚያውቀው ኅጢአት ተናዝዞ ስለማያውቀው ይቅር በለኝ እያለ ከኅጢአቱ ነጽቶ ልቡን ከቂም በቀል ሰውነቱን ከበደል ማራቅ ይገባዋል።
4. ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል 18 ሰዓት ከእህል ከውሃ ተከልክሎ በመጾም ፥ የበሉት ከሆድ እስኪጠፋ መቆየት ይገባል
5. ወንድ ዝንየት (ህልመ ሌሊት) ካገኘው በዚያ ቀን አይቆርብም ፥ እንዲሁም ነስር፣ ትውኪያ፣ ብስና ማንኛውም የአካል መድማት መቁሰል ወደ አፍ የሚገባ እንደ ትንኝ ዝምብ ይህን የመሰለ ቢያጋትምም በዚያን ዕለት መቁረብም ማቁረብም አይገባም
6. በመቁረብ ዋዜማ ገላን መታጠብ የሚለብሱትን ንጹህ አድርጎ ማዘጋጀት ይገባል
7. ቅዳሴ ከመገባቱ አስቀድሞ ከቤተክርስቲያን መገኘትና በሚገባ ሆኖ ቅዳሴውን ማስቀደስ ይገባል። ቅዳሴ ሲገባ ያልነበረ በመሃል የመጣ ሰው መቁረብ አይገባውም።
8. ሴት በወር አበባ ላይ እስከ 7 ቀን መቁረብ አይገባትም። ከዚያ ሰውነቷን ታጥባ ትቀበላለች፣ በወሊድ ጊዜ ደግሞ የመታረስ ጊዜዋ እስኪፈጸም ድረስ ማለትም ህጻኑ ክርስትና ቀን ድረስ አትቀበልም። “ሴት ከወለደች 80 ቀን ወንድ ከወለደች 40 ቀን ማለት ነው” (ዘሌ 12 ፥1-5)
ለመቁረብ በቤተክርስቲያን በተገኘን ወቅት ማድረግ የሚገቡን ነገሮች
ይቆየን
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን ላይ ያገኛሉ
👉🏾👉🏾👉🏾 #ቅዱስ #ቁርባን ለማን?
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን በሙሉ፤ በርዕሱ የተጠቀሰውን የትምህርት ክፍል ከ ” ለቅዱስ ቁርባን እንድበቃ ምን ላድርግ?” ከሚለው መጽሐፍ ወስጥ ያገኘነው ሲሆን ይህም ጠቃሚ ትምህርትና ምክር ስለሆነ እንደሚከተለው ልከንላችኋልና አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።
«ኢየሱስም መልሶ ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጸድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው» /ሉቃ. 5፥31/
ይህን ቃል መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ከኃጢያተኞች ጋር በማዕድ በመቀመጡ ፈሪሳውያን ለምን ከኃጢያተኞች ጋር ይበላል /በማዕድ ይቀመጣል/ ብለው በማንጐራጎራቸው የተነሳ ነው::
ለነዚያ ኃጢአተኞች የሚያስፈልጋቸው መድኃኒተ ሥጋ ወነፍስ እርሱ እንደሆነ መለሰላቸው እንጂ የመጣው ለጻድቃንና ለንጹሀን እንደሆነ አይደለም የተናገረው፡፡
ቅዱስ ቁርባን ለማን የሚለው ጥያቄ በእያንዳንዱ አማኝ ሕይወት የራሱ የሆነ አንድምታ /ትርጉም/ የሚሰጠው ሲሆን የአብዛኛው አመለካከት አማኙን ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቅና የወንጌሉ ቃል ተቃራኑ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ይሁንና በዚህ ትምህርት ቅዱስ ቁርባን የሚገባቸው እነማን እንደሆኑ በዝርዝር ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡
ቅዱስ ቁርባን የሚገባቸው፣
ሀ./ የመሥዋዕቱን መለወጥ ለሚያምኑ ሕብስቱ ተለውጦ ሥጋው ወይኑ ተለውጦ ደሙ መሆኑን ከልብ ያለ ጥርጥር አምነው ለሚኖሩ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የነገራቸውን ቃል በእምነት ተቀብለው ለሚከተሉ፡፡
. “ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡ ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም ፡ አለ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ..ደሜ ይህ ነው” ማቴ 26፥26
ለ./ ይህ ቅዱስ ቁርባን ለኃጢአት አድፍ መንጺሒ ለኃጢአት ቁስል ፈውስ የተሰጠ መሆኑን ላመነ ባጠቃላይ ኃጢአትን የሚያስተሰርይ መሆኑንና የዕለት የዕለት የኃጢአት በሽታ መድኃኒትነቱን ለተቀበሉ በተለይ የሚዘጋጀው ለፃድቃን ሳይሆን ለኃጥአን መሆኑን ከልብ ላመኑ ለተቀበሉ «በእውነት አምነው ከእርሱ ለሚቀበሉ ሕይወትና መድኃኒት የኃጢአት ማስተስረያም ሊሆን የሚሰጥ የጌታችንና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደም ይህ «እማሬ ነው» /ቅዳሴ ሐዋርያት/ «እንዲህም አለ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው» /ማቴ. 26፥ 27
ሐ./ የዘለዓለም ሕይወትን የሚያስገኝ መሆኑን አምነው የዘላለም ሕይወት ያሰጠኛል ብለው ለሚቀርቡ፤ «ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው እኔም በመጨረሻ ቀን አስነሳዋለሁ»፡ ዮሐ. 6፥53/
መ./ በሚቀበሉት ቅዱስ ቁርባን ክርስቶስ ከእርሱ ጋር እነርሱ ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆነው እንደሚኖሩ ሥጋው ከሥጋቸው ደሙ ከደማቸው ተዋህዶ አምላካቸው ከእነርሱ ጋር በጸጋ ተዋህዷቸው እንደሚኖር ለሚያምኑ፡፡
«ሥጋዬን የበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ» /ዮሐ. 6፥56/ በተጨማሪ በቀደመ ኃጢአታቸው ለተፀፀቱ ለተናዘዙ ለተመለሱ ከሚመጣው ኃጢአት ለሚጠበቁ ነው::
«ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግስት ወንጌል እየሰበከና ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ፡:» /ማር. 1+14/
ይህን ሁሉ እውነትና የወንጌሉን ቃል በተረትና በአጉል ባሕል እየሸፈኑ የራሳቸውን አስተሳሰብ ያስተጋቡ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ይህንን ጸጋ የተጋፉ ናቸው እንግዲህ ቅዱስ ቁርባን ለማን ለሚለው ከላይ የቀረበው ማብራሪያ የማያንስ ቢሆንም በምዕመናን ውስጥ ለሚነሱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ከዚህ በታች በርዕስ በርዕሰ ማብራሪያ እናቀርብበታለን፡::
ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የተወስነ እድሜ አለን?
ብዙ ጊዜ ህፃናት እስከ ሰባት ዓመት ሲያቆርቡ ኖረው ከዚህ እድሜ ሲገፋ ወንዱን «ለአቅመ አዳም» ደርሰሀል መቁረብ አይገባህም ሴቷን «ለአቅመ ሔዋን ደርሰሻል መቁረብ አይገባሽም የሚለውን አባባል በአንዳንዶች ዘንድ ከአባበል አልፎ እንደ ቀኖና /ህግ/ ተወስዷል፡-፡ ወጣቶች በእድሜያቸው /በወጣትነታቸው/ ምክንያት ብቻ ወደ ቁርባን መቅረብ እንደሌለባቸው ሲነገርባቸው እንሰማለን፡፡
ራሳቸው ወጣቶች በዚህ ሰው ሰራሽ ትምህርትና ተራ አባባል ታምነው «ለአቅመ አዳም» «ለአቅመ ሔዋን» ደርሻለሁ ወደ ቁርባን መቅረብ አይገባኝም ሲሉ ይደመጣሉ፡:
የሚገርመው ወጣትነትን በራሱ ብቻ እንደ ኃጢአተኝነት ወይም ለቅዱስ ቁርባን ብቃት የሌለው ሕይወት አድርጐ መውሰድ በራሱ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ እንዲህ አይነቱን አባባል የሚቀበሉና እንዲህ አይነት አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ወጣቶች ወደ ሥጋ ወደሙ መመለስ የሚገባቸው በስተርጅና /አይን ሲፋዝ ጉልበት ሲደነዝዝ/ እንደሆነ ይስማማሉ፡፡ ይህንም አስተሳሰብና አባባላቸው? ለማጠናከር የሚጠቀሙበት ቢሂል አለ እርሱም «ጣጣውን ሲጨርስ /ስትጨርስ/ የሚሉት ነው::
እዚህ ላይ ለአንባብያን ላስገነዝብ የምወደው እነዚህ ስዎች በራሱ ኃጢአት «ጣጣ» መሆኑን መመስከራቸውን ወይም መንፈስ ቅዱስ እንዳስመሰከራቸው ልብ እንድትሉት ነው፡: ታዲያ በዚህ ኣባባል ሰው ኃጢአትን ሲሠራ እንዲኖር ወይም ኃጢአት ለመሥራት ተስማሚው እድሜ ይህን ወጣትነት አድርጐ እንደ መመደብ የሚቆጠር አባባል ነው::
ለሁሉም መልሱን የሚሰጠው የወንጌሉ ቃልና የቤተ ክርስቲያኒቱ ህግና ሥርዓት ስለሆነ ከዚህ በታች በአጭሩ እንመልከት፡፡
ታላቁ ሰው ንጉሱና ነብዩ ሰሎሞን «በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ» /መክ. 12+1/ በማለት ሰው በጉብዝናው እድሜ ራሱን ለአምላኩ እንዲያቀርብ በቅዱስ ቃሉ ይጣራል ቤተ ክርስቲያኒቱም ብትሆን መሥዋዕቱ በሚለወጥበት በታለቁ ጸሎት /በጸሎተ ቅዳሴው/ ለተዘጋጀውና ለቀረበው የሕይወት ማዕድ ምዕምናኗን ስታዘጋጅ ካህኑ የሚለው «በወጣትነት እድሜ ያላችሁ አትቅረቡ» ሳይሆን «ንጹህ ያልሆነ ግን አይቅረብ» ነው እንግዲህ ባጠቃላይ ከነቢያት ወገን ወጣቶች አሉ እግዚአብሔር እነ ሶምሶንን እነ ጌድዩንን ለሚፈልገው አምላካዊ ዓላማው የጠራቸው በጉብዝና እድሚያቸው ነው፡ ጌታ የቁርባንን ሥርዓት ሲሠራ ከነበሩት ከአስራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ወጣቶች ነበሩበት በየትኛውም እድሜ ለሚገኙ ክርስቲየኖች ኃጢአት የሚሰሩበት እድሜ ስላልተመደበላቸው ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብና ላለመቅረብ የተመደበም እድሜ የለም ወደ ሕይወት እንጀራ ወደ ሥጋ ወደሙ ለመቅረብ መስፈርቱም እድሜ ሆነ መወሰድ የለበትም።
(ይቆየን)
ምንጭ “ለቅዱስ ቁርባን እንድበቃ ምን ላድርግ?”
ከ መ/ም የሺጥላ ሞገስ
2014
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንም ሼር ያድርጉ፡-https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾👉🏾👉🏾#ቅዱስ #ቁርባን – የምሥጢራት ሁሉ መክብባቸው
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ የምክር አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን ፤ ከዚህ ቀጥለን ከላይ በተጠቀሰው ረሰእስ መነሻነት ስለ ምስጢረ ቅዱስ ቁርባን ከትምህርተ ሃይማኖትና ክርስቲያናዊ ሕይወት መጽሐፍ ላይ ያለውን አጭር መልእክት ትማሩበት ዘንድ እንደሚከተለው ስለላክንላችሁ ሁላችሁም እንድታነቡት እንመክራለን።
የምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ሁሉ የበላያቸው ፤ መክብባቸውና መፈፀሚያቸው የሆነው ቅዱስ ቁርባን በጌታ ትእዛዝ ጸሎተ ኀሙስ ማታ መመስረቱ ተገልጧል (ሉቃስ 22፥14-20)። ምሥጢረ ቁርባን ከሁሉ በላይ የሆነበት ምክንያት ጌታ የሰውን ልጆች ለማዳን በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ ሥጋውን በመቁረስ ደሙን በማፍሰስ ካሣ የከፈለበትን የማዳን ሥራውን ያፈፀመበትን ሁኔታ የሚያረጋግጥና የሚመሰክር ከመሆኑ ጋር አማኞች ከሥጋውና ከደሙ ተካፋይ እንዲሆኑ በማብቃት የህይወትን ጸጋ እንዲቀበሉ ስለሚያደርግ ነው። ስለዚህም የሌሎቹ ምሥጢራት ሁሉ በቅዱስ ቁርባን አማካኝነት የምሥጢራቸውን ትርጓሜና ፍፃሜ ያገኛሉ።
ምሥጢረ ቁርባን የሚከናወንበት ጸሎተ ቅዳሴ እጅግ የከበረና ለክርስቲያኖች ሁሉ ጸጋና በረከትን የሚያሰጥ ነው። የዝግጅቱ ክፍል ሳይቆጠር ጸሎተ ቅዳሴ ሁለት ዐበይት ክፍሎች አሉት። የመጀመሪያው ቃለ እግዚአብሕር የሚሰማበትና ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥበት ጊዜ ነው። ሁለተኛው መሥዋዕተ ቁርባን የሚፈፀምበት ነው። ስለዚህ ጸሎተ ቅዳሴ ሥርዓተ አምልኮት ብቻ ሳይሆን ስብከተ ወንጌል የሚካሄድበት፤ ክርስቲያናዊ ፍቅርና ሰላም የሚመነጭበት መልካም ሥራ የሚወጠንበትና የሚፈፀምበት በመሆኑ ቤተ ክርስቲያን ከምታከናውናቸው መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎቶች ሁሉ ከፍተኛውን ቦታ ይዞ ይገኛል። በኦሪቱ ሥርዓት በቤተ መቅደስ ይፈጸም የነበረው የብሉይ ኪዳን መሥዋዕት በቅዱስ ቁርባን በመተካቱ ለሐዲስ ኪዳኑ የአምልኮት ሥርዓትና ምሥጢር ሁሉ መሠረት ከመሆኑም ጋር ጌታ ዳግመኛ እስከመጣ ድረስ የክርስቶስ የሞቱና የትንሣኤው ምስክር ሆኖ ይቆያል።
ጽዋውን አነሥቶና አመስግኖ ሲሰጣቸው “ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኅጢአት ይቅርታ የሚፈስ የሐዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” ያለውን ቃለ ወንጌል (ማቴ26፥26-28) አምነው ክርስቶስ በመካከላቸው ተገኝቶ ዛሬውኑ እንደፈፀመው አድርገው በመቀበላቸው በእውነት የመዳኑ ጸጋ ለእነርሱ ደርሷቸዋል። ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው የተባለውም በእነርሱ ላይ ይፈጸማል (ዮሐ 6፥ 53) ነገር ግን ሳያምኑ የሚቀበሉትና በመጠራጠር የሚተውት ሁለቱም ከመዳን ጸጋ ውጭ ናቸው። ምክንያቱም እነርሱ ገና በምሥጢረ ሥጋዌ አላመኑም ማለት ነው።
ጸጋ እግዚአብሕር ለሰዎች ልጆች የተሰጠው ቃለ እግዚአብሔር ወልድ በሚታይና በሚዳሰስ በሥጋ ሰውነት በመምጣቱ ነው። በሰውነቱ ሕማማትን በመቀበል እኛን በማፅደቅ በቅዱስ ደም ፋሳሽነት ከኅጢአታችን በማንፃትና ከእግአዚአብሔርም ጋር በማስታረቅ ጸጋ በፀጋ ላይ እንድንቀበል አብቅቶናል። እንግዲህ በሚታይና በሚዳሰስ ሰውነቱ የማይታየውን መለኮታዊ ጸጋውን እንዳጎናጸፈን እናስተውል። እንደዚሁም ዛሬ አካሉ በሆነችው ቤተክርስቲን አማካይነት በሚታዩና በሚዳሰሱ ምሥጢራቱ የማይታየውን ረቂቁን ጸጋ መንፈስ ቅዱስን እንቀበላለን።
እንግዲህ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ሥጋ ከመልበሱ የተነሣ ጸጋ እግዚአብሔር በሥጋና በደሙ እንደመጣልን እንረዳለን። “ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው … ሥጋዬ እውነተኛ መብል ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና” (ዮሐ6፥54-55) የተባለውን የጌታን ቃል እንዴት በተግባር እንደምናውለው እስኪ በጽሞና እናስብ! ታድያ ይህን የወንጌል ቃል ለመፈፀም ዛሬ አንድ ሰው የጌታን ሥጋና ደም ከየትና እንዴት ያገኛል? መልስ፦ በጸሎተ ኅሙስ ማታ ጌታ ምሥጢረ ቁርባንን በመሠረተ ጊዜ የትና እንዴት እንደሚገኝ ለሐዋርያት አስተምሯቸዋል (ሉቃ 22፥ 14-20)። ይህውም ዛሬ በቤተ ክርስቲያናችን የሚገኘው ለሐዋርያት የተሰጠው የቅዱስ ቁርባን ምሥጢር ስለሆነ ምእመናን ንስሐ እየገቡ የጌታን ሥጋ እየበሉ ደሙንም እየጠጡ እንደ ወንጌሉ ቃል የዘላለም ሕይወትን ጸጋ ያገኛሉ።
ይህ ምሥጢር የፀጋ ሁሉ ምንጭ ስለሆነ ሌሎቹ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን ሁሉ በሥጋው በደሙ ምሥጢር አማካኝነት ይፈፀማሉ። ስለዚህ እያንዳንዱ ምሥጢረ ቤተክርስቲያን ከጌታ ሥጋና ደም ጋር በመንፈስ ቅዱስ ኅይል የተያያዘና ከጌታ ሕማም ሞትና ትንሣኤ ጋር የተዛመደ ስለሆነ የራሱ የራሱ ዮሆነ ልዩ ጸጋን የመስጠት ችሎታ አለው
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉🏾👉🏾👉🏾 ስለ #ቃል ኪዳን #ግዝረት እና #ቅዱስ #ቁርባን
1. ቃል ኪዳን
እግዚአብሔር ዓለምንና ሕዝብን የሚያስተዳድረው በቃል ኪዳን ሥርዓት ነው። ቃል ኪዳንም የሚከተሉትን ሊያሟላ ይገባዋል፡ ቃል ኪዳን ሰጪ፤ ቃል ኪዳን ተቀባይ፣ የአቀባበል ሥርዓት፣ የቃል ኪዳኑ ምልክት ተስፋና የተስፋው ምልክቶች ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ አግዚአብሔር ከአዳም ጋር ቃል ኪዳን ሲገባ አዳም መልካምና ክፉ የሚያሳውቀውን ዛፍ ቢጠብቅ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚያገኝበት ተስፋ እንደሚያገኝ የተስፋው ምልክት ደግሞ ዕፀ ሕይወት ነበር፡ለኖኅም ልጆቹ በምድር ላይ ያለ ጥፋት እንዲኖሩ የቃል ኪዳኑ የተስፋ ምልክት ቀስተ ደመና ነበር፡፡ ‹‹ቀስቴም በደመና ትሆናለች በእኔና በምድር መካከል በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘለዓለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ›› ዘፍ 9፥13-18
2. ግዝረት
አብርሃምም ወደ ፊት ልጆቹ ለሚወርሷት ለምድረ ከነአን የተስፋ ምልክት ሁኖ የተሰጠው ግዝረት. ነበር:: ሕዝበ እስራኤሌልም ለአባታቸው ለአብርሃም የተሰጠውን ይህን አጽንተው በሙሴ አማካኝነት በሀገራቸው ተዘልለው ጠላት ሳይነሳባቸው ምርኮ አባር ቸነፈር ሳይመጣባቸው ለመኖርና የፋሲካን በዓል በየዓመቱ ለማክበር የተሰጣቸው የተስፋ ምልክት ሰንበትን ማክበር የሚል ነበር። እነዚህ ሁሉ በቃል ኪዳናቸው ጸንተው ቢገኙ የማያደርገውን የማይናገር የተናገረውን የማያስቀር ልዑለ ባሕርይ አግዚአብሔር ተስፋ ያደረገላቸውን ፈጽሞላቸዋል፡፡
3. ቅዱስ ቁርባን
በሐዲስ ኪዳን ግን የቃል ኪዳኑ የተስፋ ምልክት ሥጋው ደሙ ነው: የዚህም ቃል ኪዳን ሰጩ ክርስቶስ ሲሆን ተቀባይ ደግሞ በክርስቶስ ክርስቲያን በመሲሕ መሲሐውያን የተሰኙ ምእመናን ወምእመናት ናቸው። ቃል ኪዳኑን የመቀበላቸው ምልክት ደግሞ ጥምቀት ነው፡: ከተጠመቁ በኋላ ሥጋውን ደሙን ይቀበላሉና፡። በሥጋውና በደሙ እግዚአብሔር የሚፈጽምላቸው የተስፋ ግብ ደግሞ ሐይው ከመ መላእክትን፣ ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን ማውረስ ነው። ሙሴ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን የሚያሳስባቸው የተሠዋውን የመሥዋዕቱን ደም በሕዝቡ ላይ ከረጨ በኋላ ነበር። ‹ከረጫቸውም በኋላ አግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ያደረገው የቃል ኪዳኑ ደም እነሆ ይላቸዋል›› ዘጸ 24፥60 ለእኛም እግዚአብሔር የገባልን ቃል ኪዳን የጌታችን ሥጋና ደም ነው። እርሱን ተቀብለን የሚያወርሰንን መንግሥት እንወርሳለን፡፡ ኤር 31፥34
4/ ተጨማሪ ማብራሪያ
(ግርዛት አሁንም የግድ ነውን?)👇
የሕፃን ልጅ ሥርዓተ ግርዛት በብሉይ ኪዳን የታወቀ ነው፡፡ በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 17ለአብርሐም የደረሰው የመጀመሪያው ትዕዛዝ “የሥጋህን ሸለፈት ተቆረጥ፣ ካንተ የተወለዱ ወንድ ልጆች ሁሉ የሥጋቸውን ሸለፈት ይቆረጡ፣ ይሔ ላንተና ለልጆችህ ሥርዓት ነው ሕግ ነው፣ ከግብረ አሕዛብ የተለየህ ፣እኔን አምላክህን የምታመልክ ፣በዚህ ዓይነት ሥርዓት የምትኖር ስለሆንክ፣ በአሕዛብና በአንተ መካከል ያለው ልዩነት ይህ ይሁን፡” ይህ ማለት በሥርዓተ ኦሪቱ እንደ ጥምቀት የሚቆጠር ነው፡፡
ማንኛውም ሕፃን ልጅ በስምንተኛው ቀን ወደቤተ ግዝረት ሄዶ የሥጋውን ሸለፈት ይቆረጣል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ እግዚአብሔር ማሕበር ይሆናል፤ ቆላፋነት ይቀራል፡፡ የአሕዛብነት ምልክት ከአብርሐም ልጆች የተለዩ መሆናችው በዘር ማንዘራቸው፣ የትውልድ ሐረጋቸው ወደ ላይ ስንወጣ፣ አብርሐምን በዘር ይመስሉታል፣ በአምልኮተ እግዚአብሔር ወይም የእግዚአብሔር ሕዝብ በመሆን ግን ያልሆኑትና የሆኑት የሚለዩበት ግዝረት ነው፡፡
በብሉይ ኪዳን በሥርዓተ ኦሪቱ በብዙ ቦታዎች ስለ ግዝረት እናገኛለን ፡፡ ገና በሕገ ልቦና ነው አብርሐም ድምፅ ወደ እሱ መጥቶ እግዚአብሔርን ተመራምሮ ነው አብርሐም ያገኘው፡፡ በእግዚአብሔር ማመን እንዳለበት፣ አብርሐም ከአባቱ ጋር ሲኖር ጣዖት እየሠራ ነበር የሚኖረው፣ እነዚያ ጣዖታት ደግሞ ሰዎች በጭንቀት ጊዜ በአሕዛብነት ግብር ዝም ብለው የሚንበረከኩላቸው፣ የሚያምኑላቸው ነበሩ፡፡
ጣዖቱ ሲያዩት ቅርፅ አለው፣ ዓይን አለው፣ ጆሮ አለው፣ እግር አለው፣ ራስ አለው፣ ሁሉም ግን አይሠራም፡፡ የሚያስብብት አይምሮ የለውም፣ የሚያይበት ዓይን የለውም፣ በዚያም ላይ በጣዖቱ ላይ የሚያድረው ሰይጣን ነው እንጂ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አይደለም፡፡ በአይምሮ ላይ ሲወጣ፣ ሲወርድ የነበረውን ነገር አስተውሎ አባታችን አብርሐም ዓይን እያለው የማያይ፣ እግር እያለው የማይሄድ፣ እጅ እያለው የማይዳስስ በሰው እጅ የተሠራውን ጣዖት አላመልክም፡፡ እኔ ከዚህ ከግብረ አሕዛብ፣ ወይም ከአሕዛብ ሥራ ከዛሬ ጀምሮ ወጥቻለሁ፡፡
እውነተኛውን አምላክ እፈልጋለሁ፣ የምፈልግህ፣ የምጠራህ፣ የፈጠርከኝ፣ ሰማይና ምድርን የፈጠርክ፣ ፍጥረታትን ሁሉ በመለኮታዊ ጥበብህ ያዘጋጀህ፣ የሠራህ፣ የፈጠርክ እግዚአብሔር ሆይ አነጋግረኝ ብሎ፤ በሥነ ፍጥረት ተመራምሮ አብርሐም አምላኩን አግኝቷል፣ ከዚያ በኋላ አብርሐም ለእግዚአብሔር የተለየ ሰው ነው፣ ከካራን ውጣ ተብሏል፤ ከአሕዛብ ግብር ውጣ ማለት ነው፡፡
ካራን ለከነዓን ቅርብ ናት፣ ከካራን ውጣ፣ ከዘመዶችህ ተለይ ፣ ከአሕዛብ ግብር ተለይ፣ ከኃይማኖታቸው ሁሉ ማለት ነው ያ ነው ግዝረቱ የተለየበት፡፡ ያን ጊዜ ግዝረተ አልተፃፈም፣ የተፃፈ ሕግ የለም፣ አብርሐም ግን በሕገ ልቦና እግዚአብሔርን ሲያገንኝ ከዚያ በኋላ ማድረግ የሚገባውን ነገር ከአሕዛብ ተለይተህ የእግዚአብሔር ሰው ስለሆንክ ፣ የአግዚአብሔር ሕዝብ ተብለህ የምትጠራ ነህ፡፡ ዘሮችህ ሁሉ እንደ ሰማይ ከዋክብት፣ እንደ ምድር አሸዋ አበዛቸዋለሁ ብሏል፡፡ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ተብሏል፡፡
በሚወለደው በጌታቸን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ተብሎ ተስፋውን ሁሉ ነግሮታል፡፡ የመጨረሻ ዘመን እኛን ለማዳን ከሰማየ-ሰማያት ወርዶ፣ ከድንግል ምርያም ተወልዶ፣ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ፣ ስለሚወለደው አምላክ በቀራንዮ ስለሚፈፅምልን ነገረ ድኅነት ሁሉ ተስፋውን በሚስጥር ነግሮታል፡፡ አሕዛብ የተባረኩት፣ ወይም አሕዛብ ከሕዝብ ጋር አንድ የሆኑት፣ በክርስቶስ ነው ፡፡
በዚያን ዘመን የተገረዙ ሁሉ የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ ወንድ ልጆች ሁሉ የአብርሐም ዘሮች ከዚያ በኋላ ሲረገዙ ይህንን ለአብርሐም የተነገረውን ቃል፣ የመገረዙን ሥርዓት፣ የሕጉን መጽሐፍ ሙሴ ከእግዚአብሔር እጅ ሲቀበል፣ ሕግ አድርጎ በኦሪቱ ሥርዓት አስቀምጦታል ማለት ነው፡፡
በሐዲስ ኪዳን ያለው ግዝረት ግን ለሚፈልጉትም፣ ለማይፈልጉትም ትርጉም የለውም፡፡ ሰው ለሥጋው፣ ለባሕሉ፣ ለጤንነቱ ያስፈልገኛል ካለ ሊገረዝ ይችላል፣ ላይገረዝም ይችላል፡፡ ግርዛት ሕግ እንደሆነ፣ በሕገ ኦሪቱ እንደተፃፈ፣ የአብርሐም ልጆች ሁሉ እንደሚገረዙ እናውቃለን ሕግ ነው አለ፣ ያንን አለማድረግ ያስቀጣል፡፡ ከእግዚአብሔር ማሕበር ውስጥ ሊለየን ይችል ነበር፡፡
ዛሮ ግን መገረዘም፣ አለመገረዝም አይጠቅምም ሁለቱም፡፡ ብትገረዝም በኃይማኖትህ፣ በመንፈሳዊ ሕይወትህ የሚያመጣብህ ነገር የለም፡ ባትገረዝም የሚያጎድልብህ ነገር የለም፡፡ ስለዚህ የምንገረዘውም፣ የማንገረዘውም ከባሕል፣ ወይም ከጤና አኳያ ሊሆን ይችላል ፡፡ ከቅዱስ መጽሐፍ በላይ እና ሌላ የምንፈለስፈው ነገር የለም፡፡
ምክንያቱም በሐዲስ ኪዳን የቃል ኪዳኑ የተስፋ ምልክትና እግዚአብሔር የገባልን ቃል ኪዳን የጌታችን ሥጋና ደም ነው። እርሱን ተቀብለን የሚያወርሰንን መንግሥት እንወርሳለን፡፡ ኤር 31፥34
(ይቆየን)
👉🏾👉🏾👉🏾ምሥጠረ #ቅዱስ #ቁርባን
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገፅ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምትከታተሉ አባላቶቻችን ሁሉ፤ ስለ ምስጢረ ቅዱስ ቁርባን በሚመለከት የሚከተለውን አጭር ትምህርት ልከንላችኋልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።
ምሥጢረ ቁርባን ማለት ክርስቶስ ስለ እኛ ኀጢአት በመስቀል ላይ መሥዋዕት ሆኖ በሥጋው በሞቱ የዓለምን ኀጢአት ያስወገደበት የዘለዓለም ሕይወትን ያስገኘበት የመዳናችን መሠረት የጸጋችን ሁሉ ምንጭ የሆነውን የቅዱስ ሥጋውንና የክቡር ደሙን የማዳን ጸጋ የሚያመለክት ታላቅ የክርስትና ሃይማኖት ምሥጢር ነው። ክርስቶስ እንደ መሥዋዕትም እንደ ዐቢይ ሊቀ ካህናትም በመሆን ሁለቱንም በአንድ ጊዜ ፈጽሟል (ዕብ7፥20-28)። እንደ ዐቢይ ሊቀ ካህናትነቱ በመስቀል ላይ የተቆረሰው ሥጋውን ያፈሰሰው ደሙን የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር በማቅረቡ ሰውን ከራሱና ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ፤ የጥልንም ግድግዳ አፈረሰ የተራራቀውን አቀራረበ።
ይህን ነገር የቁርባንን የምሥጢር ትርጉም ያስረዳናል። ቁርባን ማለት በአንድ በኩል ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መሥዋዕት በሌላ በኩል ደግሞ እኛ ወደ እግዚአብሕር የምንቀርብበትን የምንቀራረብበትንና የምንዋሐድበትን ሁኔታ ያሳየናል። ልንቀርብና የመለኮታዊውንም ጸጋ ተሳታፊ ልንሆን የምንችለው በምሥጢረ ቁርባን አማካኝነት ኀብስቱና ወይኑ ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደም ተለውጦ ስንቀበለው ነውና ምሥጢር መሆኑን ከዚህ ላይ እናስተውላለን።
“ቁርባን” የሚለው ቃል መሠረቱ ከዕብራይስጥ ቋንቋ የመጣ ሲሆን የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም “ስጦታ” ማለት ነው። ይህም ማለት እንደ ኦሪቱ ቁርባን ሰው ለእግዚአብሕር ያቀረበውን ስጦታ ብቻ የሚያመለክት ሳይሆን እግዚአብሔርም በተለየ ሁኔታ ለሰዎች ደህንነት በዓለም ሁሉ የሰጠውን በሥጋና በደም የመጣውን የልጁን ስጦታ ያስገነዝባል። ስለዚህም ለዓለም መድኃኒት ሆኖ የተሰጠው በጸሎተ ኀሙስ ማታ ወደ ጌታ ሥጋና ደም የተለወጠው ኀብስትና ወይን ዛሬም በጸሎተ ቅዳሴ የጌታን ሥጋና ደም ሆኖ የሚቀርበው ቅዱስ ቁርባን ይባላል። እርሱም ከእግዚአብሕር የተሰጠ የተቀደሰ ስጦታና መሥዋዕት ነው። እንግዲህ ለኃጢአታችን መሥዋዕት ሆኖ ከእግዚአብሕር የተሰጠንን እኛ ደግሞ ከምስጋና ጋር መልሰን ለእርሱ እናቀርባለን።
ስለዚህ ነው በጸሎተ ቅዳሴ ካህኑ “አምላኪየ እግዚአብሔር ሆይ ደስ የሚያሰኝህ መሥዋዕት የልጅህ ሥጋ እነሆ። በዚህም ኀጢአቴን ሁሉ አቃልልኝ ስለ እኔ አንድ ልጅህ ሙቷልና። ስለ እኔ በቀራንዮ የፈሰሰ ንጹሕ የሚሆን የመሲሕም ደም እነሆ ስለ እኔ ይጮሀል። ይህ የሚናገር ደም የእኔን የባርያህን ኀጢአት የሚያስተሠርይ ይሁን” በማለት የእግዚአብሔርን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀርባል /የሐዋርያት ቅዳሴ፥ ቁጥር 105-106/ ።
ቅዱስ ቁርባን በምሳሌና በትንቢት
በብሉይ ኪዳን ታሪክ ውስጥ ለሥጋውና ለደሙ ማለት ለምሥጢረ ቁርባን የተመሰሉ ምሳሌዎች አሉ። በጠቅላላ የኦሪት መሥዋዕት ሁሉ ለወንጌሉ መሥዋዕት ምሳሌነት ቢኖራቸውም ዋና ዋናዎቹን ብቻ እንጠቅሳለን።
መጀመሪያው የልዑል እግዚአብሕር ካህንና የሳሌም ንጉሥ ያቀረበው የኀብስትና የወይን መሥዋዕት ለክርስቶስ ዘላለማዊ ሊቀ ካህናትነትና ለሥጋው ወደሙ ዓይነተኛ ምሳሌ ሆኖ ይነገራል (ዘፍ14፥18፣ ዕብ5፥6 እና 10፥7-17)።
ሁለተኛው ከቀሳፊ የሞት መልእክት አድኖ ከግብፅ ባርነት ነፃ ያወጣቸው የፋሲካ በግ ደም መረጨትና ሥጋውም ተጠብሶ መበላቱ የእግዚአብሔር በግ ለተባለው ለክርስቶስ አዳኝነትና ለምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ ሆኗል (ዘፀ 12፥1-51፣ 1ኛ ቆሮ 5፥7)።
ሦስተኛው እስራኤላውያን በምድረ በዳ ይመገቡት የነበረው ከሰማይ የወረደው መና ዛሬ ምእመናን ለነፍሳቸው ምግብ የሚቀበሉት የሥጋውና የደሙ ምሳሌ ነው (ዘቀ16፥ 16-23፣ ዮሐ 6፥ 49-51)።
አራተኛው ጥበብ ያዘጋጀችው ማዕድ ያረደችው ፍሪዳ የጠመቀችው የወይን ጠጅ የላከቻቸው አገልጋዮቿ የተጠሩት ሰዎች ሁሉ ምሳሌነት እንዳላቸው ይነገራል። ጥበብ የክርስቶስ ማዕድ የሥጋው የደሙ አገልጋዮች የካህናት፣ ተጋባዞች የምእመናን ምሳሌ ናቸው ተብሎ ይተረጎማል (ምሳ 9፤1-5)። ይህን የመሳሰሉ ሌሎች ምሳሌዎችም አሉ (ዘሌዋ 2፤23፥13-14፣ ሲራክ 24፥19-21)
ትንቢትም ስለ እውነተኛው ቁርባን ተናግሯል። “ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአዝሓብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና በየሥፍራውም ለስሜ እጣን ያጥናሉ፤ ንጹሕም ቁርባን ያቀርባሉ” (ሚል1፥11)። ይህ ስለ ወንጌል መሥዋዕት የተነገረ እንጂ ስለ ኦሪት መሥዋዕት አይደለም። ምክንያቱም የኦሪት መሥዋዕት በኢየሩሳሌም ከተማ በቤተ መቅደስ ብቻ እንጂ በሌላ ቦታ እንዳይፈጸም በሕግ የተከለከለ ነው። እንግዲህ ነቢዩ ሚልክያስ “ንጹሕ ቁርባን” ያለው እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ለአሕዛብ ወንጌል በተሰበከበት ሥፍራ ቤተ ክርስቲያን በተቋቋመበት ቦታ ሁሉ የሥጋውና የደሙ ንጽሕ መሥዋዕት መቅረቡን የሚያመለክት ነው።
ሌላው ደግሞ የኢሳያስ ትንቢት ነው። “እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ ወደ ውሀ ኑ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም፤ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ… በረከትንም ብሉ…” (ኢሳ.55፥1-2)። ይህ የነቢዩ ቃል በመብልና በመጠጥ ስለሚመጣው ስለ ምሥጢረ ቁርባን በትንቢትና በምሳሌ እንደ ተነገረ ይታመናል።
የምሥጢረ ቁርባን አመሠራረት
ምስጢረ ቁርባንን ጌታችን ከሕማማቱና ከሞቱ በፊት በዋዜማው ኀሙስ ማታ መሥርቶታል። ይህም ሰዓት በአይሁድ የቀን አቆጣጠር ወደ ዓርብ ይታሰባል። በዚያም ወቅት የኦሪት የፋሲካ በግ የሚሠዋበት ጊዜ በመሆኑ ጌታችን ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የኦሪትን መሥዋዕት አሳልፎ መሥዋዕተ ወንጌልን መሥርቷል። በዚያች ምሽት የኦሪቱ በግ መሥዋዕትነት አበቃ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እውነተኛው የእግዚአብሕር በግ ይሠዋል። እርሱም የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው። ስለዚህ በማዕዱ ዙሪያ ለተሰበሰቡት ሐዋርያቱ በብሉይ ኪዳን ምሳሌ የተመሰለለትን፤ ትንቢት የተነገረለትን አዲሱን ቃል ኪዳን ጌታ በራሱ ሥጋና ደም መሠረተ። የእውተነተኛው መሥዋዕት ምሳሌ የሆነው የኦሪቱን ማዕድ እየበሉ ሳለ “ኢየሱስ እንጀራን (ኀብስትን) አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና፤ እንካችሁ፤ ብሉ፤ ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም አለ፤ ሁላችሁም ከእርሱ ጠጡ፤ ስለ ብዙዎች ለኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” በማለት ምሥጢረ ቁርባንን መሠረተ (ማቴ 26፥26-28)። ኪዳን ማለት ከእግዚአብሔር ጋር የምንገባውን ቃል ኪዳን የሚያመለክት ነው።
በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር በሙሴ አማካኝነት ከቤተ እሥራኤል ጋር ቃል ኪዳን የገባው በእንስሳት ደም ነበር (ዘፀ 24፥1-11ጥ። ያን ጊዜ ቤተ እሥራኤል ቃል የገቡት ሕገ ኦሪትን ሊፈፅሙ አሠርቱ ትእዛዛትን ሊጠብቁ ሥርዓቱን ሊያከብሩ ነበር። እግዚአብሔር ደግሞ በበኩሉ አምላካቸውና ጠባቂያቸው ሊሆን ምድረ ርስትንም ሊያወርሳቸው ተስፋ ሰጣቸው፤ ቃል ገባላቸው። በወንጌል ግን እግዚአብሔር ቃል ኪዳን የገባው በልጁ ደም ነው።
(ይቀጥላል)👇👇👇
👉🏾👉🏾👉🏾ምሥጠረ #ቅዱስ #ቁርባን
(ቀጣይ ክፍል)👆
እግዚአብሔርም የፈጸመልን አዲሱ ኪዳን ከብሉይ ኪዳን እጅግ የላቀ ነው። ምክንያቱም በክርስቶስ የሐዲስ ኪዳን ደም ኀጢአታችን ተወግዶልናል። ከእግዚአብሔር ታርቀናል፤ የእግዚአብሔርን ልጅነት አግኝተናል፤ እግዚአብሕርም አባት ሆኖን የመንግሥቱ ወራሾች እንድንሆን አብቅቶናል። ስለዚህ ይህን ወሰን የሌለው እስከ ሞት ድረስ የወደደንን የክርስቶስን ፍቅር እያሰብን እግዚአብሔርን በልጁ ስም ዘወትር ለማመስገን ወንድሞቻችንንም ለማፍቀርና ችግረኞችንም ለመርዳት የወንጌልንም ትዝዛዝ ለመፈጸም እኛም በበኩላችን ቃል መግባት ይኖርብናል።
ቃል ኪዳን ከገባንበት ዋናው ነገር በቆረብንና ቅዳሴ ባስቀደስን ቁጥር የበደላችንንና የኀጢአታችንን ሥርየት ያገኘንበትን ከእግዚአብሔር የታረቅንበትን የክርስቶስን ሕማምና ሞት ማሰብና ማስታወስ ነው። ስለዚህ ነው ጌታችን ህብስቱን አንሥቶ ባርኮና ቆርሶ ለሐዋርያቱ ከሰጣቸው በኋላ “ስለ እናንተ የሚሰጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ የኸን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” ብሎ ያላቸው (ሉቃ 22፥19)። መታሰቢያዬ የተባለው ስለ ሕማምና ሞቱ መሆኑንና ይህንንም የሞቱን ዜና የመስቀሉን ነገር ጌታ እስኪመጣ ድረስ በምሥጢረ ቁርባን አማካኝነት እንደሚነገር ከሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንማራለን (1ኛ ቆሮ 11፥23-26)። ዛሬም በጸሎት ቅዳሴ “ንዜኑ ሞተከ እግዚኦ” የተባለውን እያዜምን እናስታውሰዋለን። በምንቆርብበት ጊዜ የምናየው የተፈጥሮ ኀብስትና ወይን ብቻ መስሎን እንዳንሳሳት፤ የማይታየው መለኮት የተዋሐደው የጌታ ሥጋና ደም መሆኑን አምነን መቀበል አለብን፤ አለበለዚያ በራሳችን ላይ ፍርድን እናመጣለን።
ሳይገባው ራሱን ሳይፈትንና ሳይመረምር የሚቆርብ “የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና። በማለት ይህው ሐዋርያ ያስጠነቅቀናል።
“ስለዚህ ሳይገባው ይህን እንጀራ ኀብስት የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት። ሰው ግን ራሱን ይፈትን እንዲሁም ከእንጀራው ከኀብስቱ ይብላ ከጽዋውም ይጠጣ ፤ ሳይገባው የሚበላና የሚጠጣ የጌታን ሥጋ ስለማይለይ ለራሱ ፍርድ ይበላልና ፤ይጠጣልምና። ስለዚህ በእናንተ ዘንድ የደከሙና የታመሙ ብዙዎች አሉ አያሌዎችም አንቀላፍተዋል። ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር፤ ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ ፥ ከዓለም ጋር እንዳንኮነን በጌታ እንገሠጻለን” (1ኛ ቆረ 11፥27-32)
በምሥጢረ ቁርባን የሚገኝ ጸጋ
የሚታየው ኀብስትና ወይን በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ በክርስቶስ ቃል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በካህኑ ጸሎት ወደ ጌታ ሥጋና ደም መለወጣቸውን በሙሉ ልብ አምነውና በንስሐ ተዘጋጅተው ለሚቀበሉ ሁሉ በወንጌል የተጸፃፈውን የማይታየውን ጸጋ ለማግኘት ይችላሉ። የሚከተሉትን የእግዚአብሕር ጸጋ ማግኘት ለአማኞች ሁሉ ከፍተኛ ጥቅምና እድል ነው።
– የመጀመርያው ጸጋ ሰውና እግዚአብሔርን ያራራቀውን ኀጢአትን ማስወገድ ነው። ስለዚህ ነው የቁርባን ምሥጢር ሲመሠረት ጌታችን ይህ ደሜ ነው ለብዙዎች የኀጢአት ሥርየት የሚፈሰው በማለት የጸጋውን ስጦታ የጀመረው (ማቴ 26፥27-28)። የኀጢአት ሥርየት ከተገኘ ከእግዚአብሕር ጋር እርቅና ሰላም ይወርዳል። እርቅ ከተገኘ ደግሞ ሌሎቹ ስጦታዎች ደግሞ ይጨመራሉ። ኀጢአታቸው የተተወላቸው ብፁዓን ናቸውና (መዝ 31፥1)።
– ከዚህ ቀጥሎ በምሥጢረ ቁርባን የምናገኘው ጸጋ ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆነን በኀብረት መኖር ነው። ይህም ማለት እኛ በእርሱ እርሱ በእኛ ይኖራል ማለት ነው። “ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ” በማለት ጌታ አረጋግጦልናል (ዮሐ 6፥56)። ነገር ግን ከቁርባን እርቀን ሥጋውና ደሙን ሳንቀበል ብንቀር በራሳችን ሕይወት አይኖረንም። ምክንያቱም አንዲት የወይን ሐረግ ከወይኑ ግንድ ተለይታ ለመኖር አትችልምና።
“ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ እውነት እውነት እውነት እላችኋለሁ የወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስን ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም” (ዮሐ 6፥53)። እንግዲህ የመጨረሻውን ፀጋ የዘላለም ሕይወትን የምናገኘው ለትንሣኤውም የምንበቃው በሥጋና በደሙ ነው። “ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ (ዮሐ 6፥54)።
– ከላይ ከተጠቀሱት ፀጋዎች ሌላ ምሥጢረ ቁርባን በንስሓና በፀሎት ሆኖ በሚገባ ተዘጋጅቶ የሚቀበል ሁሉ ነፍሱን ከመራብና ከመጠማት ያድናታል። ምክንያቱም ሥጋውና ደሙ እውነተኛ መንፈሳዊ ምግብ ስለሆነ ነው። “ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፥ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምን ሁል ጊዜ ከቶ አይጠማም” (ዮሐ 6፥35)።
– ምሥጢረ ቁርባን የሚያስገኘው ጸጋ ሰውን ከእግዚአብሕር ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ሰውንና ሰውንም ያቀራርባል። ስለዚህ የክርስቶስን ሥጋና ደም የተቀበሉ ሁሉ እርስ በርሳቸው በፍቅር የተሳሠረ ኅብረትና አንድነት አላቸው፦ ምክንያቱም በቁርባኑ ሁላችንም የክርስቶስ አካልና አባል ሆነናልና። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ሁላችንም ከአንዱ ኀብስት እንካፈላለንና። በሥጋ የሆነውን እሥራኤል ተመልከቱ፤ መሥዋዕቱን የሚበሉ የመሠዊያው ማሕበርተኞች አይደሉምን?” (1ኛ ቆሮ 10፥16-18፣ ዘሌዋ 7፥6 እና 15)። እንግዲህ ይህ ጥቅስ የሚያስተምረን በሥጋውና በደሙ ሁላችን አንድ የእግዚአብሕር ቤተሰብ መሆናችንን ነው። በአፀደ ነፍስም በአፀደ ሥጋም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ እንደ አንዲት የተቀደሰች ማሕበር ይቆጠራሉ። ሁሉም የአንድ የክርስቶስ አካል ሆነዋልና።
ይቀጥላል
ምንጭ ፦ ትምህርተ ሃይማኖትና
ክርስቲያናዊ ህይወት
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
በቅዱስ ቁርባን የሚገኝ ጸጋ ( ጥቅም)
👉🏾👉🏾👉🏾 ሥጋሁ ወደሙ (#ቅዱስ #ቁርባን)
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገፅ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምትከታተሉ አባላቶቻችን ሁሉ፤ ከላይ በርዕሱ በተጠቀሰው ቃል መነሻነት ‘ኅብረ ሥርዐተ ዘቤተክርስቲያን ኦርቶዶክሳዊት”‘ መጽሐፍ ውስጥ ያለውን ጠቃሚ ትምህርት ልከንላችኋልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።
የተሠዋው መሥዋዕት ክርስቶስ ምንም አንድ ጊዜ ራሱን ያቀረበ ቢሆንም ምእመናን የሚድኑት ክርስቶስ ራሱን ስለነርሱ አንድ ጊዜ እንደ ሠዋ በማመን ብቻ ሳይሆን የተሠዋውን መሥዋዕት በትአዛዙ መሠረት በመቀበልም ጭምር ነውና፤ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን የሚሠዋው በዕለተ አርብ ከተሰዋው ጋር ምንም ዓይነት ልዩነት የሌለው ፍፁም አንድ መሆኑን በማስተማር ቤተ ክርስቲያን የራሷን ድርሻ ትወጣለች፡ ምእመናንም ይህን ያለ ኑፋቄ በእምነት ተቀብለው አንደ ቃሉ ያድጉበታል፡። ስለሆነም ከሁሉ በፊት ሊቀርብ የሚገባው ጥያቄ፦ ጌታ ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ ለምን አለ? የሚል ሲሆን ይህም ከዚህ በታች ባሉት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው፦
1. የፍቅሩን ጽናት ለማስረዳት ነው
ይህም ማለት ስለ ወደዱት ሰው ሲሉ ራስን አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር የለምና ‹‹ስለ ወዳጆቹ ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው ያለ እንደ ሆነ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም›› ዮሐ 15 ፥13 እግዚአብሔርም ሰውን የወደደበት ፍቅር በቋንቋ ሊገለጥ የማይቻል ጥልቅና ምጡቅ በመሆኑ ምን ያህል እንደ ወደደን ሊያስረዳን ሲፈልግ ‹‹ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ›› አለን፡፡‹እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው አይደለም›› ብሏልና፡፡ ዮሐ 14፥27 የዚህ ዓለም ሰው ቢሰጥ ያንዱን ለአንዱ ያውም ኃላፊውን ነው፡፡እርሱ ግን የባሕርዩን ነውና ሰው ቢሰጥ የምናየውንና ምናልባትም በሂደት ልናገኘው የምንችለውን በዚህ ዓለም ያለውን ግዙፉን ነው፤ የርሱ ግን እንዲህ አይደለም፡፡‹ዐይን ያላየው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልቡና ያልታሰበ እግዚአብሔር ለሚወድዱት ያዘጋጀው ነው›› 1ኛ ቆሮ 2፥9 ተብሎ የተነገረለትን ረቂቁን ሰጥቶ ማለትም በሰው ልቡና ባልታሳበ በጥምቀት ወልዶ በሰው ልቡና ባልታሰበ በሥጋው በደሙ ያሳድገናልና፡፡ ኋላም ሐይው ከመ መላአክትን ያድለናልና፡፡
የዚህ ዓለም ሰው ቢሰጥ ላደነቀውና ላመሰገነው፣ በከንቱ ውዳሴ ለሚጠልፈው፣ ለቀጣፊ ላዝማሪ ለዘዋሬ ነው፡፡ አርሱ ግን ውዳሴ ከንቱ የማይሻ ‹‹ሁሉ ከርሱ በርሱና ለርሉ›» የሆነ አምላክ ነውና ላመነ በሕጉ በትአዛዙ ለኖረ ሁሉ ይሰጣል። ሮሜ 11፥36 አንዲሁም ሰው ቢሰጥ ማፍጆት፣ ማርጀት፣ መሰቀቅ፣ መመረር፣ መሰልቸት፣ መጸጸት አለበት አርሱ ግን ይህ ሁሉ የለበትምና ለሁሉም ያለ አድልዎ ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ አለ፡፡ በዚያውም ላይ ክርስቲያን ተስፋ የሚያደርገው የዚህ ዓለም ልጅ ከአባቱ ዘንድ ተስፋ እንደሚያደርገው አይደለም። አባትነቱ ከዚህ ዓለም አባትነት እንደ ሚለይ ልጅነታችንም ከዚህ ዓለም ልጅነት ይለያልና፡፡ የዚህ ዓለም አባት በግዙፍ ወልዶ ግዙፋን በሆኑ በወተት በፍትፍት አሳድጎ እያየው እየተመኘው ተስፋ ሲያደርገው -. ያደገውን ሀብቱን ንብረቱን ርስቱን ጉልቱን ያወርሰዋል፡፡ እርሱ ግን በረቂቅ በጥምቀት ወልዶ በረቂቅ በሥጋው በደሙ አሳድጎ ሳናይ በእምነት ተስፋ የምናደርገውን መንግሥተ ሰማያትን ያወርሰናልና፡፡
«የሚታየውን ተስፋ ማድረግ ተስፋ አይደለም የሚያየውንማ አንዴት ተስፋ ያደርጋል? እንዴትስ ይጠብቃል? የማይታየውን ተስፋ ብናደርግ ግን አርሱን ተስፋ አድርገን በአርሱ አንደ ጸናን መጠን ትእግስታችን ይታወቃል›› ሮሜ 10፥20-25 ሌላው ደግሞ ክርስቶስ ሥጋውን ደሙን የሰጠው በነጻ ነው፡ «ጥበብ (ክርስቶስ)..ፍሪዳዋን አረደች የወይን ጠጅዋንም በማድጋዋ ጨመረች ማዕድዋን አዘጋጆች አገልጋዮቿን ልካ በከፍተኛ ዐዋጅ ወደ ማዕድዋ ጠራች አንዲህም አለች አላዋቂ የሆነ ወደ አኔ ይምጣ አእምሮ የጎደላቸውንም አንዲህ አለች አንጀራዬን ብሉ የጠመቅሁላችሁን የወይን ጠጅም ጠጡ ስንፍናን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ›› ትላለች፡፡ ምሳ 9፥ 2-5
ይህም ንባብ ሲተረጐም፦፡‹‹ፍሪዳ የተባለ የወልድ ሥጋ ነው፡፡ ወይንም የቅዱስ (ክርስቶስ) ደመ ገቦ ነው፡፡ የወይን ጠጅ መጥመቂያ ማድጋም ወይነ መለኮት የተጨመረባት ልበ ምእመናን ናት፡፡ የተዘጋጀ ማዕድም ክቡር ሥጋው ክቡር ደሙ ነው፡፡ የተላኩ አገልጋዮች ሰባክያነ ወንጌል ሐዋርያት ናቸው፡፡የተጠሩትም በስሕተት መንገድ የነበሩ አህዛብ ናቸው፡፡
አእምሮ የጎደላቸው የተባሉም አህዛብ ናቸው፡፡ ወልድ ሰው ከመሆኑ አስቀድሞ ሃይማኖት አልነበራቸውምና፡፡ የበሉት ኅብስትና የጠጡት የወይን ጠጅ የክርስቶስ ሥጋና ደም ነው፡፡ የተውት ስንፍናም አምልኮ ጣዖት ነው፡፡ በሕይወት ኑሩ ማለትም በክርስቶስ ዳኑ ማለት ነው›። መጽ ፀሐ ገጽ 76 ዳግመኛም ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ ማለቱ ሰው በመብል በመጠጥ ምክንያት ይፋቀራል፡፡ አርሱም በፍጹም ፍቅሩ እንዳፈቀረን ለማጠየቅ ነው:፡:
እንዲሁም መብል መጠጥ ከሰውነት እንዲዋሓድ በሥጋው በደሙ ምክንያት አንደ እሳትና አንደ ብረት የጸጋ ተዋሕዶ ተዋሕዶን በጸጋ አድሮብን ይኖራልና፡፡ ስለሆነም እርሱ ስለ ፍቅሩ ጽናት ስለ ሀብቱ ብዛት እኛን አንዲሁ ወዶ ራሱን ከሰጠን እኛ አርሱን የመውደዳችን አንዱ መስፈርት ደግሞ ሕጉን ትእዛዙን መጠበቅ ነው፡፡፡ ‹‹ኑ ከወደዳችሁኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ››ዮሐ 14፥15 “እናንተስ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ካደረጋችሁ ወዳጆቼ ናችሁ›› ።፡ ዮሐ 15፥14 ሥጋው ደሙን ሳይቀበሉ መዳን የማይቻለውም ስለዚህ ነው። ምክንያቱም ባለቤቱ “እውነት እውነት የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ የዘለዓለም ሕይወት የላችሁም›› ብሏልና፡፡ ዮ 6፥53
ዳግመኛም ጌታ ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ ያለው ከርሱ ጋር ተዋሕደን እንድንኖር አርሱም እኛን ተዋሕዶን እንዲኖር ነው።ይህም ማለት ሥጋውን ደሙን ስንቀበል ብረት ከእሳት ሲገባ እሳቱን እንዲመስል እኛም እርሱን መስለን እንኖራለንና በመንፈሳዊ ሕይወታችን ጽናትን እናገኛለንና ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በአኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ›› ዮሐ 6፥፡56 ‹‹የሚወደኝ ቃሌን ይጠብቃል አባቴም ይወድደዋል ወደ እርሱም መጥተን በአርሱ ዘንድ ማደሪያ እናደርጋለን›› ዮሐ 14፥23 “ቃሉን መጠበቅም ማለት በገቢር መፈጸም ነው እንጅ መስማትና ማወቅ ብቻም አይደለምና፡፡ ‹የጌታውን ፈቃድ ዐውቆ እንደ ፈቃዱ የማይሠራና የማያዘጋጅ የዚያ አገልጋይ ቅጣቱ ብዙ ነው ያላወቀ ግን ባይሠራም ቅጣቱ ጥቂት ነው ብዙ ከሰጡት ብዙ ይፈልጉበታልና ጥቂት ከሰጡትም ጥቂት ይፈልጉበታልና›› ሉቃ 12፥47
‹ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ ቃሉን ሰምቶ የማያደርገው ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመሥታዋት እንደሚያይ ሰው ይመስላል ራሱንም ተረድቶ ይሔዳል ወዲያውም እንዴት እንደሆነ ይረሳል ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ የሚመለከትና የሚጸናበት ሥራንም የሚሠራ እንጂ የሰማውን የሚዘነጋ ያይደለ ይህ በሥራው ብፁዕ ነው››ያዕ 1፥22-24፣ 2፥14-26 ‹‹በአግዚአብሔር ፊት ሕግን የሚያደርጉ ይጸድቃሉ እንጂ ሕግን የሚሰሙ አይጸድቁምና›› እንደ ተባለ ሮሜ 2፥13
2. የቃል ኪዳን ምልክት ነው
( ክፍል 2 ይቀጥላል)👇
👉🏾👉🏾👉🏾 ሥጋሁ ወደሙ (#ቅዱስ #ቁርባን)
(ክፍል 2)👆👇
2. የቃል ኪዳን ምልክት ነው
እግዚአብሔር ዓለምንና ሕዝብን የሚያስተዳድረው በቃል ኪዳን ሥርዓት ነው። ቃል ኪዳንም የሚከተሉትን ሊያሟላ ይገባዋል፡ ቃል ኪዳን ሰጪ፤ ቃል ኪዳን ተቀባይ፣ የአቀባበል ሥርዓት፣ የቃል ኪዳኑ ምልክት ተስፋና የተስፋው ምልክቶች ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ አግዚአብሔር ከአዳም ጋር ቃል ኪዳን ሲገባ አዳም መልካምና ክፉ የሚያሳውቀውን ዛፍ ቢጠብቅ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚያገኝበት ተስፋ እንደሚያገኝ የተስፋው ምልክት ደግሞ ዕፀ ሕይወት ነበር፡ለኖኅም ልጆቹ በምድር ላይ ያለ ጥፋት እንዲኖሩ የቃል ኪዳኑ የተስፋ ምልክት ቀስተ ደመና ነበር፡፡ ‹‹ቀስቴም በደመና ትሆናለች በእኔና በምድር መካከል በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘለዓለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ›› ዘፍ 9፥13-18
አብርሃምም ወደ ፊት ልጆቹ ለሚወርሷት ለምድረ ከነአን የተስፋ ምልክት ሁኖ የተሰጠው ግዝረት. ነበር:: ሕዝበ እስራኤሌልም ለአባታቸው ለአብርሃም የተሰጠውን ይህን አጽንተው በሙሴ አማካኝነት በሀገራቸው ተዘልለው ጠላት ሳይነሳባቸው ምርኮ አባር ቸነፈር ሳይመጣባቸው ለመኖርና የፋሲካን በዓል በየዓመቱ ለማክበር የተሰጣቸው የተስፋ ምልክት ሰንበትን ማክበር የሚል ነበር። እነዚህ ሁሉ በቃል ኪዳናቸው ጸንተው ቢገኙ የማያደርገውን የማይናገር የተናገረውን የማያስቀር ልዑለ ባሕርይ አግዚአብሔር ተስፋ ያደረገላቸውን ፈጽሞላቸዋል፡፡
በዚህም አንጻር በሐዲስ ኪዳን የቃል ኪዳኑ የተስፋ ምልክት ሥጋው ደሙ ነው: የዚህም ቃል ኪዳን ሰጩ ክርስቶስ ሲሆን ተቀባይ ደግሞ በክርስቶስ ክርስቲያን በመሲሕ መሲሐውያን የተሰኙ ምእመናን ወምእመናት ናቸው። ቃል ኪዳኑን የመቀበላቸው ምልክት ደግሞ ጥምቀት ነው፡: ከተጠመቁ በኋላ ሥጋውን ደሙን ይቀበላሉና፡። በሥጋውና በደሙ እግዚአብሔር የሚፈጽምላቸው የተስፋ ግብ ደግሞ ሐይው ከመ መላእክትን፣ ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን ማውረስ ነው። ሙሴ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን የሚያሳስባቸው የተሠዋውን የመሥዋዕቱን ደም በሕዝቡ ላይ ከረጨ በኋላ ነበር። ‹ከረጫቸውም በኋላ አግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ያደረገው የቃል ኪዳኑ ደም እነሆ ይላቸዋል›› ዘጸ 24፥60 ለእኛም እግዚአብሔር የገባልን ቃል ኪዳን የጌታችን ሥጋና ደም ነው። እርሱን ተቀብለን የሚያወርሰንን መንግሥት እንወርሳለን፡፡ ኤር 31፥34
3. የነፍስ ምግብ ነው
ይህ ማለት ግን ሥጋው ደሙ ለነፍስ እንጅ ለሥጋ አይጠቅምም ማለት አይደለም፡፡ይህንስ እንዳንል ዘወትር ካህኑ ሲያቀብል ‹‹ሥጋሁ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ለቀድሶ ሥጋ ወነፍስ ወመንፈስ – ሥጋንና ነፍስን ደመ ነፍስንም ለማክበር የሚሆን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ይህ ነው›› እያለ ያቀብላቸዋልና፡፡ ምንም ዛሬ ማሰብን ለነፍስ በመስጠት ኃጢአት የነፍስ ብቻ ቢመስልም በነፍስ አሳቢነት ፈጻሚው ሥጋ በመሆኑ በኋላ ዋጋውንም ሆነ ፍዳውን የሚቀበሉት በአንድነት ነውና ሥጋው ደሙ የሚጠቅመው ለሥጋም ጭምር ነው።፡ ሊቃውንትም ‹‹እሳት ማኅየዊ ለርቱዓነ ልብ ለእለ ይገብሩ ፈቃዶ›› ያለውን ኃይለ ቃል ሲተርገሩሙ ‹«አንድነቱን ሦስትነቱን አውቀው ህማሙን ሞቱን አምነው ኃጢአታቸውን ለመምህረ ንስሐ ነግረው መምህረ ንስሐ ያዘዘውን ሠርተው በሚገባ ለሚቀበሉ ሰዎች የሚያድን አሳት ነው፡፡ እሳት በመጠን የሞቁት እንደ ሆነ የበሉት የጠጡትን ያስማማል ደዌ ይከፍላል ይህም ከኃጢአት ነጽቶ ቢቀበሉት ሕይወተ ሥጋ ሕይወተ ነፍስ ይሆናል ደዌ ነፍስ ያርቃል›› ብለዋል። ትር ቅዳ ማር
በመሆኑም ባለቤቱ ‹‹ዘበለዓ ሥጋየ ወሰትየ ደምየ ቦ ሕይወት ዘለዓለም ወአነ አነሥኦ በደኃሪት ዕለት – ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው እኔም በኋለኛዬቱ ቀን አነሣዋለሁ›› ዮሐ 6፥54 ብሏልና፡፡ የዘለዓለም ሕይወት የሚወረሰው ነፍስና ሥጋ ተዋሕደው ቢሆንም ዓለሙ ግን ዓለመ ነፍስ ነውና፡፡ የሚኖረውም ዛሬ ሰው በሥጋ መደብ እንዲኖር ያን ጊዜ ደግሞ በነፍስ መደብ ነውና፡: ጌታ ሥጋዬን ብሉ ደሜንም ጠጡ ያለው የነፍስ ምግብ በመሆኑ ነው ያልነው ስለዚህ ነው፡፡ ዛሬ የተቀበልነው የጌታ ሥጋና ደም በኋለኛው ዘመን በመንግሥተ ሰማያት ምግብ ሆኖን ይኖራልና ሥጋው ደሙ ምግበ ነፍስ ይባላል፡፡
(ይቆየን)
ምንጭ፦ ‘ኅብረ ሥርዐተ ዘቤተክርስቲያን ኦርቶዶክሳዊት’ ገጽ 61-66
አዘጋጅ – መምህር አብርሃም አረጋ
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾👉🏾👉🏾የንስሐ ጥሪ
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ #ንስሐ ድረገፅ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና የምትከታተሉ አባላቶቻችን ሁሉ፤ “የንስሐ ጥሪ” በሚል ርዕስ የሚከተለውን እጅግ ጠቃሚ የሆነ ትምህርት ልከንላችኋልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ በአጽንኦት አደራ እንላለን።
የሰው ልጆችን አብዝቶ የሚወደውና መጥፋታቸውን የማይሻው ፈጣሪ ከጥልቅ ፍቅሩ የተነሣ ልጆቹን ዘወትር በአንድም በሌላ መንገድ ወደንስሐ ይጠራቸዋል፤ የጥሪውንም ድምፅ የሚሰሙት ሁሉ ሊጠቀሙበት እንዲችሉ የፈጣሪ ፈቃዱ ነው። ይህንንም ቅዱስ ጴጥሮስ “ነገር ግን ሁሉ ወደንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወድዶ ስለእናንተ ይታገሣል” (2ኛ ጴጥ 3፥9) በማለት አረጋግጦታል።
ቅዱስ ጳውሎስም ሲያስተምር “እንግዲህ እግዚአብሔር ያለማወቅን ወራት (በኀጢአት የመኖርን ዘመን) አሳልፎ አሁን በየቦታቸው ንስሐ ይገቡ ዘንድ ሰውን ሁሉ ያዛል” ብሏል (የሐዋ 17፥30)
በሕዝቅኤልም እግዚአብሔር ሞት በሚስማማው ባሕርይ የተፈጠረውን የሰውን ሞት የማይወድ በንስሐ ወደ ሕይወት መመለሱን ግን የሚያስደስተው መሆኑን ተናግሯል “ንስሐ ግቡ፤ ኀጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኀጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ። የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ ጣሉ። አዲስ ልብና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ… ስለምን ትሞታላችሁ የሟቹን ሞት አልፈቅድምና ይላል ጌታ እግዚአብሔር ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።” (ሕዝ 18፥ 30-32)
እንዲሁም ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ … ኀጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ ተመለሱም” በማለት ያሰማን የእግዚአብሔርን የንስሐ ጥሪ ነው (የሐዋ 3፥ 19-20)
“ወደ እኔ ተመለሱ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሕር” (ሚል 3፤7)
እግዚአብሕር የሚያቀርብልንን የንስሐ ጥሪ አዳምጠን ወደ እርሱ ብንመለስ ኀጢአትን ትተን ንስሐ ብንገባ ከኀጢአታችን ሊያጥበንና ሊያነፃን ፈቃዱ መሆኑን በቃል ኪዳን አጽንቶልናል። ይህም፦
“ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ፤ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፤ ክፉ ማድረግን ተዉ፤ መልካም መሥራትን ተማሩ።… ኀጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጣለች እንደ ደምም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች” (ኢሳ 1፥16-18)
“ጥሩ ውሀንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ትጠራላችሁ፤ ከርኩሰታችሁም ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ። አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ፤ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ” ሕዝ 36፥25-26)
በዮሐንስ ወንጌል እንደተፃፈው የመድኃኒታችን ሰው መሆን ዋና ምክንያቱ የሰው ልጆችን ወደድኀነት መጥራት ስለሆነ “ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድ አልመጣሁምና” በማለት ጌታችን ድኅነትን ወደምታሰጥ፥ ሥርየተ ኀጢአትን ወደምታስገኝ ንስሐ ይጠራናል። (ዮሐ 12፥47) እንዲሁም ደግሞ በማርቆስ ወንጌል “ሕመምተኞች እንጂ ብርቱዎች ባለመድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤ ኀጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም።” በማለት ከኀጢአት ደዌ ወደምትፈውስ ንስሐ የሚጠራን መሆኑን ይነግረናል።
ስለዚህ ንስሐ ከሞት ወደ ህይወት የምንመጣበት ስለእኛ ድኅነት ወደ ተቀደሰው ሕይወት እንድንገባ የተሰጠን እንጂ በላያችን የተጫነ ሸክም አለመሆኑን በመረዳት ልንጠቀምበት ያስፈልጋል።
የእግዚአብሔርን የንስሐ ጥሪ ብንቀበልና ከኀጢአታችን ሥርየት አግኝተን በተቀደሰ ሕይወት በእግዚአብሔር መንግሥት ብንኖር መልካም ነው። የምንወደውን ለመምረጥም ሙሉ ነፃነት አለን። በነብዩ ኢሳያስ አንደበት “እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እምቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ሠይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሯልና።” በማለት ነግሮናል (ኢሳ 1፥19-20)
በአጠቃላይ የንስሐ ጥሪ በቅዱስ መፅሐፍ ውስጥ ዋነኛውን ሥፍራ ይዞ ይገኛል። የሐዲስ ኪዳን መግቢያ የንስሐ ጥሪ ነው። መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የስብከቱ መጀመሪያ ያደረገው “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ” የሚለውን የንስሐ ጥሪ ድምጽ ነው። (ዮሐ 3፥2)።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ስብከቱን የጀመረው በንስሐ ጥሪ ነው። “ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር” ተብሎ ተፅፏል (ማቴ 4፥17)
ቅዱሳን ሐዋርያትም ደግሞ የንስሐን ጥሪ እንደአስተላለፉ መጽሐፍ ይነግረናል። “ወጥተውም ንስሐ እንዲገቡ ሰበኩ” (ማር 6፥12)
የመጀመሪያው የንስሐ ሰባኪ ኖኅ ነው። በኋላ ግን ብዙ ነቢያት መስለውታል። በዚህም የንስሐ ጥሪ ለማንኛውም ክርስቲያን የሚቀርብና ሊቀርብም የሚገባ የተቀደሰ የእግዚአብሔር ጥሪ መሆኑን እናስተውላለን። የንስሐ ጥሪውን ተቀብለው ምሕረትና ይቅርታ ድኀነትነም ሽተው ወደ እርሱ የሚመለሱትን ሁሉ ይቀበላል። ለዚህ ብዙ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል፦ የተጠፋው ልጅ – ሉቃ 15፣ አምስት ባሎች የነበሯት ሣምራዊት ሴት – ዮሐ 4፣ በጌታ ቀኝ የተሰቀለው ወንበዴ – ሉቃ 23፥24፤ እና ሌሎችም።
ጌታችንም ወደ እርሱ የሚመጡትን ኀጢአተኞች የሚቀበላቸው መሆኑን በቃሉ ያረጋግጥልናል “ወደ እኔ የመጣውን ከእኔ ከቶ አላወጣውም” (ዮሐ 6፥37) ይህን ሰው ፍለጋ ግን ዘወትር በልቡና ደጃፍ ቆሞ በንስሐ ጥሪ ያንኳኳል፤ የሚከፍትለት ቢያገኝ። “እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።” (ራእ 3፥20)
የእግዚአብሕር ቸርነት ከሠራነው ኀጢአት ሁሉ በላይ ነው። የኀጢአታችንንና የበደላችንን ብዛት ከእግዚአብሔር ምሕረትና ቸርነት ጋር ስናነፃፅረው በውቅያኖስ ባሕር ላይ እንደወደቀች ቆሻሻ ነው። ስለዚህ የኀጢአታችንን ብዛትና ክብደት ኀጢአተኞችን ለማንጻት በድኅነት ዓለም ከፈሰሰው የክርስቶስ ደም በላይ አድርገን መመልከት የለብንም። ከእግዚአብሐር ፍቅርና ከቸርነቱም በላይ አድርገን ማሰብ የለብንምና ኀጢአታችን ብዙ ነው ብለን ተስፋ ሳንቆርጥ የቀረበልንን የንስሐ ጥሪ በማድመጥ የመዳን ቀን ዛሬ ነው ተብሏልና አሁኑኑ ወደ ፈጣሪአችን ቸሩ እግዚአብሔር በንስሐ ልንመለስ ይገባናል። በአጠቃላይ ፤ መቼ በሞት እንደምንጠራ ቀንና ሰዓቱን (ዘመንና ጊዜውን) ለይቶ ማወቅ ከእሱ ከባለቤቱ በስተቀር ፈጽሞ የሚያውቅ የለምና ኅጢአትን ለመናዘዝ ቅድሚያ መስጠትና በንስሐ ሕይወት ራስን አዘጋጅቶ መጠበቅና ንስሐ ለመግባት መዘጋጀት ከእውነተኛ ክርስቲያን የሚጠበቅ ታማኝነት ነው በማለት እንመክራለን።
ይቀጥላል
👇👇👇
👉🏾👉🏾👉🏾የንስሐ ጥሪ (ክፍል 2)
👉🏾በምሥጢረ #ቅዱስ #ቁርባን የሚገኝ ጸጋ
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገፅ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና የምትከታተሉ አባላቶቻችን ሁሉ፤ በምሥጢረ ቅዱስ ቁርባን ስለሚገኝ ጸጋ የሚከተለውን አጭር ትምህርት ልከንላችኋልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።
የሚታየው ኅብስትና ወይን በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ በክርስቶስ ቃል በመንፈስ ቅዱስ ኀይል በካህኑ ጸሎት ወደ ጌታ ሥጋና ደም መለወጣቸውን በሙሉ ልብ አምነውና በንስሐ ተዘጋጅተው ለሚቀበሉ ሁሉ በወንጌል የተጻፈውን የማይታየውን ጸጋ ለማግኘት ይችላሉ። የሚከተሉትን የእግዚአብሔር ጸጋ ማግኘት ለአማኞች ሁሉ ከፍተኛ ጥቅምና እድል ነው።
የመጀመሪያው ጸጋ ሰውና እግዚአብሔርን ያራራቀውን ኀጢአትን ማስወገድ ነው። ስለዚህ ነው የቁርባን ምሥጢር ሲመሠረት ጌታችን ይህ ደሜ ነው ለብዙዎች የኀጢአት ሥርየት የሚፈሰው በማለት የፀጋውን ስጦታ የጀመረው (ማቴ 26፥27-28)። የኀጢአት ሥርየት ከተገኘ ከእግዚአብሔር ጋር እርቅና ሰላም ይወርዳል። እርቅ ከተገኘ ደግሞ ሌሎቹ ስጦታዎች ደግሞ ይጨመራሉ። ኀጢአታቸው የተተወላቸው ብፁዓን ናቸውና (መዝ 31፥1)።
ከዚህ ቀሎ በምሥጢረ ቁርባን የምናገኘው ጸጋ ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆነን በኅብረት መኖር ነው። ይህም ማለት እኛ በእርሱ እርሱ በእኛ ይኖራል ማለት ነው። “ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል፥ እኔም በእርሱ እኖራለሁ” በማለት ጌታ አረጋግጦታልና (ዮሐ 6፥56)። ነገር ግን ከቁርባን እርቀን ሥጋውና ደሙን ሳንቀበል ብንቀር በራሳችን ሕይወት አይኖረንም። ምክንያቱም አንዲት የወይን ሐረግ ከወይኑ ግንድ ተለይታ ለመኖር አትችልምና።
“ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፥ እውነት እውነት እላችኋለሁ የወልደ እጓለ እመሕያው ክርስቶስን ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። (ዮሐ 6፥53)። እንግዲህ የመጨረሻውን ፀጋ የሐላለም ሕይወትን የምናገኘው ለትንሣኤውም የምንበቃው በሥጋና በደሙ ነው። “ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ።”
ከላይ ከተጠቀሱት ጸጋዎች ሌላ ምሥጢረ ቁርባንን በንጽህና ሆኖ በሚገባ ተዘጋጅቶ የሚቀበል ሁሉ ነፍሱን ከመራብና ከመጠማት ያድናታል። ምክንያቱም ሥጋውና ደሙ እውነተኛ መንፈሳዊ ምግብ ስለሆነ ነው። “ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ሁል ጊዜ ከቶ አይጠማም” (ዮሐ 6፥35)።
ምሥጢረ ቁርባን የሚያስገኘው ጸጋ ሰውን ከእግዚአብሔር ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ሰውንና ሰውንም ያቀራርባል። ስለዚህ የክርስቶስን ሥጋና ደም የተቀበሉ ሁሉ እርስ በእርሳቸው በፍቅር የተሳሠረ ኀብረትና አንድነት አላቸው። ምክንያቱም በቁርባኑ ሁላችንም የክርስቶስ አካልና አባል ሆነናልና። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው ሁላችንም ከአንዱ ኅብስትና ጽዋ ተሳትፎ ስላለን ነው። “የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? አንድ እንጀራ ኅብስት ስለሆነ፤ እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን፤ ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ ኅብስት እንካፈላለንና በሥጋ የሆነውን እሥራኤል ተመልከቱ፤ መስዋዕቱን የሚበሉ የመሠዊያው ማኅበርተኞች አይደሉምን?” (ቀኛ ቆሮ10፥16-18፣ ዘሌዋ 7፥6 እና 15)። እንግዲህ ይህ ጥቅስ የሚያስተምረን በሥጋውና በደሙ ሁላችን አንድ የእግዚአብሔር ቤተሰብ መሆናችንን ነው። በአፀደ ነፍስም በአፀደ ሥጋም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ እንደ አንዲት የተቀደሰች ማኀበር ይቆጠራሉ። ሁሉም የአንድ የክርስቶስ አካል ሆነዋልና።
ይቀጥላል
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉🏾👉🏾👉🏾 ስለ #ቅዱስ #ቁርባን
ዘወትር የመቁረባችን ጥቅሙ?
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን፤ በርዕሱ መነሻነት የተዘጋጀው ይህ ገጸ ንባብ ከ ‘ኀብረ ሥርዐት ዘቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክስ’ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ፥ ይህንን ጠቃሚ ትምህርት ለእናንተ እንዲደርሳችሁ አድርገናልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።
ይህም ሲገለጥ ሥጋውን ደሙን ዘወትር በመቀበላችን የምናገኘው ረብኅ ጥቅም ምንድን ነው? የሚል ነው፡፡ ዘወትር ሥጋውን ደሙን በመቀበላችን ጽንዓ ሃይማኖትን፣በመንፈሳዊ ሕይወት መበርታትን፤ ዘለዓለማዊ ድኅነትን፣ሥርየተ ኀጢአትን እግዚአብሔሑርን፤ ኃይል መንፈሳዊን ከምእመን ጋር አንድ መሆንን ፤በሥጋው በደሙ ጌታን መማጸንን ማለትመሰ ስለ ቆረስኸው ሥጋ ስለ አፈሰስኸው ደም ብለህ ይቅር በለን እያሉ መለመንን፡‹‹በስሜ አብን ብተትለምኑት ሁሉን ይሰጣችኋል›› ብሎናልና፡፡ በሥጋው በደሙም ‹‹አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ ደስ የሚያሰኝህ መሥዋዕት የልጅህ ሥጋ እነሆ በዚህም ኀጢአቴን ሁሉ አቃልልኝ ስለ እኔ አንድ ልጅህ ሙቷልና ስለ አኔ በቀራንዮ የፈሰሰ ንጹሕ የሚሆን የመሲሕ ደም እነሆ ስለ እኔ ይጮኻል ይህ የሚናገር ደም የኔን የባሪያህን ኀጢአት የሚያስተሠርይ ይሁን ስለ አነርሱም ልመናዬን ተቀበል›› እያልን እንማፀናለንና፡፡ ቅ ሐዋ ቀ ፻፳
ይህም ማለት ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ስናስብ ለመቀበል የሚያበቁንን ቅድመ ዘግጅቶች አናሟላቸው ዘንድ እንተጋለን፡፡ እነዚህን ዝግጅቶች ስናደርግም አስቀድመን ንፅሕናን ከዚያም ቅድስናን ገንዘብ እናደርጋለን፡፡ ንፅሕናና ቅድስና በሃይማኖት የመጽናት በመንፈሳዊ ሕይወት የመበርታት ምልክቶች ናቸውና፡፡‹‹ከነዚህም በኋላ ለምእመናን ምሳ ሙሽራው በሙሽሪት አዳራሽ ይታረዳል መታረዱን ከማየት የተነሣ ጉልበቷ ይንቀጠቀጣል አንደቷም ይናወጣል በመሠውያው ቀንድ ሲንጠፈጠፍ ደሙን ባየች ጊዜ ሥጋውን በፍርሃት ትበላለች ደሙንም በመንቀጥቀጥ ትጠጣለች ከዚያም የሃይማኖት ወላፈን በልቧ ውስጥ ይግላል የፍቅሩም ሞገድ
በሆዷ ውስጥ ይፈላል›› እንዳሉ አባ ጊዮርጊስ መጽ ምሥ 6፥15
ጌታም በእርሱ ሐረገ ወይንነት አዕፁቅ እኛ እናድግ ዘንድ ‹‹አነሃ ውአቱ ሐረገ ወይን ዘጽድቅ ወአቡየ ተካሊሁ ውእቱ ወወለኩሉ ዓጽቅ ዘኢይፈሪ በላዕሌየ ይገዝምም ወያአትትዎ፦ እውነተኛ የወይን ሐረግ እኔ ነኝ ተካዩም አባቴ ነው በእኔ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍም ሁሉ ያስወግደዋል የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እንዲያፈራ ያጠራዋል…በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ከአልኖረ ብቻውን ሊያፈራ እንደማይችል እናንተም እንዲሁ በአረኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም እኔ የወይን ግንድ ነኝ ቅርንጫፎቹም እናንተ ናችሁ በእኔ የሚኖር እኔም በአርሱ ብዙ ፍሬ የሚያፈራ እርሱ ነው ያለእኔ ምንም ማድረግ አትችሉምና በእኔ የማይኖር ቢኖር እንደ ደረቅ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጥሉታል ሰብስበውም በአሳት ያቃጥሉታል፡›› ብሏል፡፡ ዮሐ 15፥1-5
ስለዚህ ዘወትር ሥጋውን ደሙን ስንቀበል በጌታችን እንኖራለን እርሱም በእኛ ይኖራል፡ እንዲሁም ሞተ ወልደ እግዚአብሔርን እናስባለን፡፡ይህን ስናስብ ለአኛ ሲል የተቀበለውን መከራ መስቀል በቀኖት መቸንከክሩን፣የእሾህ አክሊል መድፋቱን፣ምራቀ ርኩሳን አይሁድን መቀበሉን ፣በጦር መወጋቱን፣ ግርፋቱን፣ አምላክ ሲሆን የአይሁድን ተሳልቆ በትዕግሥት መስማቱን…በአጠቃላይ ነገረ መስቀሉን እንድናስብ ያደርገናል፡ በዚህ ውስጥ እግዚአብሔር ሰውን የወደደበት ፍቅሩ ምን ያህል ነው? ተብሎ ሊመዘን የማይቻል በዕፁብ የሚታለፍ መሆኑን እንረዳለን።ይህም በአንድ መዓርግ ከፍ የማለት ምልክት ነው፡፡
(ይቀጥላል )
👇👇👇
👉🏾👉🏾👉🏾 ስለ #ቅዱስ #ቁርባን
(ቀጣይ ክፍል)👆👇
ዘወትር የመቁረባችን ጥቅሙ?
ዳግመኛም ዘወትር ሥጋውን ደሙን በመቀበላችን ከተናዛዚ የቀሩ ሥርየተ ኃጣውእን እናገኛለን። ይህም ማለት ሥጋውን ደሙን የምንቀበለው ንስሐ ገብተን ቢሆንም መንፈስ ቅዱስ የገለጠውን እንናዘዛለን ሰይጣን የሰወረው(ያዘነጋው) በሥጋው በደሙ ይሰረይልናልና፡፡ ይህም ማለት ሰይጣን የሰወረውን መንፈስ ቅዱስ መግለጥ ያማይቻለው ሆኖ ሳይሆን ለጊዜው የጊዜ ብዛት በሌላም ምክንያት ዘንግተነው ሳንናዘዝ የቀረውን አይር ግን ‹እመቦ ዘወድቀ በኃጢአት ኢይርሳእ እስመ ዘኢይትረሳእ” ::.. ይላልና እኛ ብንዘነጋው በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ በመሆኑ ኀጢአትን መዘንጋት አይገባም። ቤተ ከርስቲያን ምእመናን ልጆቿን ዘወትር ንስሓ ግቡ ሥጋውን ደሙን ተወበሉ የምትለውም እንዲህ ኃጢአታቸውን ረስተው ሳይናዘዙ ሥርየተ ኀጢአት ሳያገኙ ቀጠሮ በማይሰጠው መልእክተኛ (ሞት) እንዳይወሰዱ ነው፡፡ በኅጢአት ያለ ሰው ወደ ሥጋው ደሙ እንዳይቀርብም – አስቀድሞ ነብዩ ‹‹የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ጎጢአተኛን ያስወግዱታል” ብሏል፡፡ ኢሳ 26+10
በመሆኑም ዘወትር ሥጋውን ደሙን የሚቀበል ክርስቲስ የሚያገኛቸው ጥቅሞች እነዚህ ብቻ አይደሉም።ሥጋውን ደሙን ሲቀበል የድሉ ተካፋይም ይሆናልና፡፡ ይህም ማለት ጌታ ‹‹ወዝንቱ ውእቱ ዘነገርኩክሙ ከመ በገቤየ ሰላመ ትርከቡ ወበዓለምሰ ህማመ ትርከቡ ሀለወክሙ ወባህቱ ጽንዑ እስመ አነ ሞዕክዎ ለዓለም፦በእኔም ሰላምን እንድታገኙ ይህን ነገርእቸችሁ በዓለም ግን መከራን ትቀበላላችሁ ነገር ግን ጽኑ እኔ ዓለሙን ድል ነስቼዋለሁና››ብሎ ነግሮናልና፡፡ ዮሐ 16-33 እርሱ ‹‹ዐርባዕቱ ዕድዋኒሁ ለሰብእ፦የሰው ጠላቶቹ ዐራት ናቸው›› እንደተባለ ሞትን፣ኃጢአትን፣ፍዳን፣ሰይጣንን ድል ነስቶ እናንተም ድል ንሱ ብሎናልና፡፡ ‹‹ወለዘሞዐሰ እሁቦ ይንበር ምስሌየ ውስተ መንበርየ በከመ አነ ሞዕኩ ወነበርኩ ምስለ አቡየ ውስተ መንበሩኑ አኔ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደ ተቀመጥሁ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ›› ራዕ 3:21 እንዲህ አድርጎ ሜዳውም ፈረሱም እነሆ እንደማለት የመወዳደሪያውን የመቀዳደሚያውን መድረክ ክፍቶልናል፡፡
በዚህም ጌታ ሰይጣንን በሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ ድል ከነሣው በኋላ ቅዱሳንም ጌታቸውን መስለው ግንባር ግንባሩን እያሉ የሚመልሱት ሁነዋል።:፡ስለሆነም ዘወትር ብቁ ሆነን ሥጋውን ደሙን ብንቀበል እነዚህን ከላይ ያየናቸውን አራት ነገሮች የምናሸንፍበትን ኃይል እናገኛለን፤ይህንም በማድረጋችን ኅብረተ ቅዱሳንን እናገኛለን፤ዘወትር ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ባካሄዳችን፣ በአኗኗራችን፣በአለባበሳችን፣በአነጋገራችን፣እነዚህን በመሰለው ሁሉ ስለርሱ እንመሰክራለን እንሰብካለን::እንዲሁም የአኗኗር ልቅነትን፤ግድ የለሽነትንና ንዘህላልነትን አጥፍተን እነዚህን ነገሮች ወደ መንፈሳዊነት እንድንለውጣቸው ያደርገናልና፡፡ በአጠቃላይ ዘወትር ሥጋውን ደሙን መቀበላችን ሐዋርያው ለደቀ መዝሙሩ ‹‹ጎየያ ለፍትወተ ውርዙት ወዴግና ለጽድቅ ወለሃይማኖትኑ፦እንግዲህ ከጉልምስና ምኞት ራቅ እግዚአብሔርንም በንጹሕ ልብ ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ጽድቅን፤ ሃይማኖትንም ፣ፍቅርንም፣ ሰላምንም ተከተል›› ያለውን ተግባራዊ በማድረግ በጥንቃቄ እንድንኖር ያደርገናል ፪ኛ ጢሞ ፪፥፳፪
እናም በሥጋው በደሙ ለመወሰን የሚመኝና የሚያስብ ሰው ሁሉ ነቢዩ ‹‹በተመረጠችው ዕለት ሰምቼሃለሁ ድኅነት በሚደረግበትም ቀን ረድቼሃለሁ›› ኢሳ 49:10 ሐዋርያውም ‹እነሆ የተመረጠችው ቀን ዛሬ ናት›› እንዳለ ነገ ዛሬ ሳይል መቅረብ ይገባዋል፡፡ርቀው ተለይተው የሚያማክሩት አጥተው በዚህ ዓለም ሐሳብ ተውጠው የሚኖሩ ያሉ እንደ ሆነ ደግሞ ጥበብ ወልድ ‹‹አላዋቂ የሆነ ወደ እኔ ይምጣ.. ኑ እንጀራዬን ብሉ የጠመቅሁላችሁን የወይን ጠጅም ጠጡ ስንፍናን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ በሕይወትም ትኖሩ ዘንድ ዕውቀትን ፈልጉ በመረዳትም ዕውቀትን አቅኑ›› ምሳ 9:4 እያለች ትጣራለችና ድምፅዋን ሊሰሙ ይገባቸዋል፡፥ ያም ባይሆን ጭንቀታቸውን አሳባቸውን ሁሉ«‹ለቤተ ክርስቲያን ይንገሯት›› መፍትሔ አታጣምና። በሥጋው በደሙ ተወስነው የሚኖሩ ያሉ እንደሆነ ደግሞ ‹‹እስከ መጨረሻው የሚታገሥ ግን መጨረሻው የሚታገስ ግን እረሰሱ ይድናል” ማቴ 24:13 ይላልና፡፡ እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ መጽናት ያስፈልጋቸዋል፡፡
ምንጭ፦ ‘ኀብረ ሥርዐት ዘቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክስ’
በመምህር አብርሃም ነጋ (2014)
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾👉🏾👉🏾ስለ #ምሥጢረ #ቁርባን
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሕር ለሰው ልጅ የዘላለም ሕይወት ይሆን ዘንድ ያቀረበው የራሱ ሥጋና ደም ነው። ቄሱ ኅብስቱን በጸሕል ወይኑን በጽዋዕ አድርጎ ሥርዓተ ቅዳሴ ሲያደርስ ወደ እውነተኛ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም ይለወጣል።
ቁርባን ቢያንስ 18 ሰዓት ከምግብና መጠጥ ተከልክሎ ነው። ፖም ግድ ነውሥጋውና ደሙ (ቁርባን) ለክርስቲያኑ ሁሉ በንስሐ የተፈቀደ ነው።
በመቁረብ ምን እናገኛለን: – እግዚአብሕር አምላክ አዳምንና ሔዋንን ፈጥሮ ያለሕግ አልተዋቸውም። የሰጣቸውም ሕግ ክፉንና ደጉን ከምታሳውቀው ዛፍ ፍሬ እንዳይበሉ ነበር። ከምክረ ሰይጣን ተታለው በበሉ ጊዜ ግን ወደቁ። አምላክም የሰውን ልጅ አልተወውምና ሊያድነው ከእመቤታችን ተወለደ። በቀራንዮ በመስቀል ተሰቅሎም ደሙን አፍስሶ የሞተውን አዳምን ሕይወት ሰጠው። የወደቀችውን ሔዋን አዳናት ። ዘፍ 3፥1፣ ገላ 4፥4፣ ማቴ 27፥32-34
ስለዚህ ሕይወትን ያገኘው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነውና፤ ይህን በቀራንዮ የተሰቀለልንን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ ስንበላ ክቡር ደሙን ስንጠጣ የዘላለም ሕይወት ይኖረናል። ማለትም ጌታችን ከእኛ ጋራ እኛም ከጌታችን ጋራ ለዘለዓለም እንኖራለን።
“…ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ።” ዮሐ 6፥53-59
ከዚህ የወንጌል ቃል የአምላካችን ትዕዛዝ የተነሣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በተቀበልን (በቆረብን) ጊዜ ሦስቱ ዋና ዋና ጥቅሞች ፦ 1/ የኃጢአት መደምሰሻ፣ 2/የአጋንንት ድል መንሻ፣ 3/ የመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ናቸው።
ጌታችን በመስቀል ተሰቅሎ ሕይወቱን የሰጠው ለሁሉ ነውና፤ በንስሐ ሕይወት በምክረ ካህን ያለ ክርስቲያን ሁሉ የዘላለም ሕይወት ያገኝ ዘንድ ያለ ዕድሜ ገደብ ሥጋውና ደሙን ይቀበል ዘንድ ይገባዋል። ቁርባን የሚከለክለው ዝሙት ስርቆት መግደል ሐሜትና የመሳሰሉት ሲሆን ከእነዚህ ርቆ በንስሐ ታጥቦ ሥጋ ወደሙን ተቀብሎ ሊኖር ይገባዋል። የሰው ልጅ ከኃጢአት ነጽቶ መኖር አይችልምና እግዚአብሔር ይህንን ስለሚያውቅ ለሁላችን የንስሐ ሕይወትን አዘጋጅቶልናል።
ይቆየን
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
በቅዱስ ቁርባን ለመቀበል በማሰብ ላይ ላሉ
👉🏾👉🏾👉🏾 #ቅዱስ #ቁርባን ለማን?
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን በሙሉ፤ በርዕሱ የተጠቀሰውን የትምህርት ክፍል ከ ” ለቅዱስ ቁርባን እንድበቃ ምን ላድርግ?” ከሚለው መጽሐፍ ወስጥ ያገኘነው ሲሆን ይህም ጠቃሚ ትምህርትና ምክር ስለሆነ እንደሚከተለው ልከንላችኋልና አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።
«ኢየሱስም መልሶ ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች መድኃኒት አያስፈልጋቸውም ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጸድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው» /ሉቃ. 5፥31/
ይህን ቃል መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ከኃጢያተኞች ጋር በማዕድ በመቀመጡ ፈሪሳውያን ለምን ከኃጢያተኞች ጋር ይበላል /በማዕድ ይቀመጣል/ ብለው በማንጐራጎራቸው የተነሳ ነው::
ለነዚያ ኃጢአተኞች የሚያስፈልጋቸው መድኃኒተ ሥጋ ወነፍስ እርሱ እንደሆነ መለሰላቸው እንጂ የመጣው ለጻድቃንና ለንጹሀን እንደሆነ አይደለም የተናገረው፡፡
ቅዱስ ቁርባን ለማን የሚለው ጥያቄ በእያንዳንዱ አማኝ ሕይወት የራሱ የሆነ አንድምታ /ትርጉም/ የሚሰጠው ሲሆን የአብዛኛው አመለካከት አማኙን ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቅና የወንጌሉ ቃል ተቃራኑ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
ይሁንና በዚህ ትምህርት ቅዱስ ቁርባን የሚገባቸው እነማን እንደሆኑ በዝርዝር ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡
ቅዱስ ቁርባን የሚገባቸው፣
ሀ./ የመሥዋዕቱን መለወጥ ለሚያምኑ ሕብስቱ ተለውጦ ሥጋው ወይኑ ተለውጦ ደሙ መሆኑን ከልብ ያለ ጥርጥር አምነው ለሚኖሩ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የነገራቸውን ቃል በእምነት ተቀብለው ለሚከተሉ፡፡
. “ሲበሉም ኢየሱስ እንጀራን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠና እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡ ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው እንዲህም ፡ አለ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ..ደሜ ይህ ነው” ማቴ 26፥26
ለ./ ይህ ቅዱስ ቁርባን ለኃጢአት አድፍ መንጺሒ ለኃጢአት ቁስል ፈውስ የተሰጠ መሆኑን ላመነ ባጠቃላይ ኃጢአትን የሚያስተሰርይ መሆኑንና የዕለት የዕለት የኃጢአት በሽታ መድኃኒትነቱን ለተቀበሉ በተለይ የሚዘጋጀው ለፃድቃን ሳይሆን ለኃጥአን መሆኑን ከልብ ላመኑ ለተቀበሉ «በእውነት አምነው ከእርሱ ለሚቀበሉ ሕይወትና መድኃኒት የኃጢአት ማስተስረያም ሊሆን የሚሰጥ የጌታችንና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደም ይህ «እማሬ ነው» /ቅዳሴ ሐዋርያት/ «እንዲህም አለ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው» /ማቴ. 26፥ 27
ሐ./ የዘለዓለም ሕይወትን የሚያስገኝ መሆኑን አምነው የዘላለም ሕይወት ያሰጠኛል ብለው ለሚቀርቡ፤ «ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው እኔም በመጨረሻ ቀን አስነሳዋለሁ»፡ ዮሐ. 6፥53/
መ./ በሚቀበሉት ቅዱስ ቁርባን ክርስቶስ ከእርሱ ጋር እነርሱ ከክርስቶስ ጋር አንድ ሆነው እንደሚኖሩ ሥጋው ከሥጋቸው ደሙ ከደማቸው ተዋህዶ አምላካቸው ከእነርሱ ጋር በጸጋ ተዋህዷቸው እንደሚኖር ለሚያምኑ፡፡
«ሥጋዬን የበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ» /ዮሐ. 6፥56/ በተጨማሪ በቀደመ ኃጢአታቸው ለተፀፀቱ ለተናዘዙ ለተመለሱ ከሚመጣው ኃጢአት ለሚጠበቁ ነው::
«ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግስት ወንጌል እየሰበከና ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ፡:» /ማር. 1+14/
ይህን ሁሉ እውነትና የወንጌሉን ቃል በተረትና በአጉል ባሕል እየሸፈኑ የራሳቸውን አስተሳሰብ ያስተጋቡ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ይህንን ጸጋ የተጋፉ ናቸው እንግዲህ ቅዱስ ቁርባን ለማን ለሚለው ከላይ የቀረበው ማብራሪያ የማያንስ ቢሆንም በምዕመናን ውስጥ ለሚነሱ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ከዚህ በታች በርዕስ በርዕሰ ማብራሪያ እናቀርብበታለን፡::
ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የተወስነ እድሜ አለን?
ብዙ ጊዜ ህፃናት እስከ ሰባት ዓመት ሲያቆርቡ ኖረው ከዚህ እድሜ ሲገፋ ወንዱን «ለአቅመ አዳም» ደርሰሀል መቁረብ አይገባህም ሴቷን «ለአቅመ ሔዋን ደርሰሻል መቁረብ አይገባሽም የሚለውን አባባል በአንዳንዶች ዘንድ ከአባበል አልፎ እንደ ቀኖና /ህግ/ ተወስዷል፡-፡ ወጣቶች በእድሜያቸው /በወጣትነታቸው/ ምክንያት ብቻ ወደ ቁርባን መቅረብ እንደሌለባቸው ሲነገርባቸው እንሰማለን፡፡
ራሳቸው ወጣቶች በዚህ ሰው ሰራሽ ትምህርትና ተራ አባባል ታምነው «ለአቅመ አዳም» «ለአቅመ ሔዋን» ደርሻለሁ ወደ ቁርባን መቅረብ አይገባኝም ሲሉ ይደመጣሉ፡:
የሚገርመው ወጣትነትን በራሱ ብቻ እንደ ኃጢአተኝነት ወይም ለቅዱስ ቁርባን ብቃት የሌለው ሕይወት አድርጐ መውሰድ በራሱ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ እንዲህ አይነቱን አባባል የሚቀበሉና እንዲህ አይነት አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ወጣቶች ወደ ሥጋ ወደሙ መመለስ የሚገባቸው በስተርጅና /አይን ሲፋዝ ጉልበት ሲደነዝዝ/ እንደሆነ ይስማማሉ፡፡ ይህንም አስተሳሰብና አባባላቸው? ለማጠናከር የሚጠቀሙበት ቢሂል አለ እርሱም «ጣጣውን ሲጨርስ /ስትጨርስ/ የሚሉት ነው::
እዚህ ላይ ለአንባብያን ላስገነዝብ የምወደው እነዚህ ስዎች በራሱ ኃጢአት «ጣጣ» መሆኑን መመስከራቸውን ወይም መንፈስ ቅዱስ እንዳስመሰከራቸው ልብ እንድትሉት ነው፡: ታዲያ በዚህ ኣባባል ሰው ኃጢአትን ሲሠራ እንዲኖር ወይም ኃጢአት ለመሥራት ተስማሚው እድሜ ይህን ወጣትነት አድርጐ እንደ መመደብ የሚቆጠር አባባል ነው::
ለሁሉም መልሱን የሚሰጠው የወንጌሉ ቃልና የቤተ ክርስቲያኒቱ ህግና ሥርዓት ስለሆነ ከዚህ በታች በአጭሩ እንመልከት፡፡
ታላቁ ሰው ንጉሱና ነብዩ ሰሎሞን «በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ» /መክ. 12+1/ በማለት ሰው በጉብዝናው እድሜ ራሱን ለአምላኩ እንዲያቀርብ በቅዱስ ቃሉ ይጣራል ቤተ ክርስቲያኒቱም ብትሆን መሥዋዕቱ በሚለወጥበት በታለቁ ጸሎት /በጸሎተ ቅዳሴው/ ለተዘጋጀውና ለቀረበው የሕይወት ማዕድ ምዕምናኗን ስታዘጋጅ ካህኑ የሚለው «በወጣትነት እድሜ ያላችሁ አትቅረቡ» ሳይሆን «ንጹህ ያልሆነ ግን አይቅረብ» ነው እንግዲህ ባጠቃላይ ከነቢያት ወገን ወጣቶች አሉ እግዚአብሔር እነ ሶምሶንን እነ ጌድዩንን ለሚፈልገው አምላካዊ ዓላማው የጠራቸው በጉብዝና እድሚያቸው ነው፡ ጌታ የቁርባንን ሥርዓት ሲሠራ ከነበሩት ከአስራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ወጣቶች ነበሩበት በየትኛውም እድሜ ለሚገኙ ክርስቲየኖች ኃጢአት የሚሰሩበት እድሜ ስላልተመደበላቸው ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብና ላለመቅረብ የተመደበም እድሜ የለም ወደ ሕይወት እንጀራ ወደ ሥጋ ወደሙ ለመቅረብ መስፈርቱም እድሜ ሆነ መወሰድ የለበትም።
(ይቆየን)
ምንጭ “ለቅዱስ ቁርባን እንድበቃ ምን ላድርግ?”
ከ መ/ም የሺጥላ ሞገስ
2014
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንም ሼር ያድርጉ፡-https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾ስለ #ቅዱስ #ቁርባን እና #ዕድሜ
👉ጥያቄ፡- ለመቁረብ ዕድሜ ይወስነዋል ? ማብራሪያ ፈልጌ ነበር እባክዎ ?
መልስ፡ ጠያቂያችን የጠየቁን አጭር ጥያቄ ሲሆን፤ ይኽም ስለ ምስጢረ ቁርባን ነው ፡፡ ስለ ምስጢረ ቁርባን በጣም በብዙ ጥየቄዎች መነሻነት በዚሁ በዮሐንስ ድረገጻችን ብዙ ትምሕርት ሰጥተናል፡፡ ጠያቂያችን እሱንም በተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሆንዎት ሊያዩት እንደሚገባ እየመከርን አሁን ለጠየቁት ጥያቄ ግን በአጭሩ የሚከተለውን ምላሽ ልከንልዎታል፡፡
ለመቁረብ የዕድሜ ገደብ የለውም ፡፡ ምክንያቱም ወንድ ልጅ በአርባ ቀኑ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ፣ ሴት ልጅ በሠማኒያ ቀን የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ፣ ልጅነታቸውንም ያረጋገጡት በቅዱስ ቁርባን ስለሆነ፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ማንኛውም የእግዚአብሔር ልጅ በእሱ ፊት ሰው ሆኖ ለመኖር፣ ወይም ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ለመቀጠል የማይለየው፣ የማይተወው፣ የማያቋርጠው ነገር ቢኖር የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን፣ ክቡር ደሙን መቀበል ነው፡፡ የማይቋረጥ ሥርዓት ነው፡፡ እንግዲህ ስለ ዕድሜ ክልል ስናነሳ ከኃጢያት ጋር በተያያዘ የሰው ልጅ ወንዱም ለአቅመ አዳም፣ ሴቷም ለአቅመ ሔዋን ደርሳለች ብለን በልማድ እናቶቻችን፣ አባቶቻችን አንዳንድ ካሕናትም ቢሆን፤ ዕድሜሽ ገና ነው አትቆርቢም፣ ዕድሜህ ገና ነው አትቆርብም ማለት ምን ማለት ነው? ያኔ ለአካለ መጠን ደርሰሻል፣ ሴቷም የሴት ሥራ ትሠሪያለሽ፣ ወንዱም የወንድ ሥራ ትሠራለህ ፣ልትዘሙት ትችላለህ፣ ልትሰርቅ ችላለህ፣ ልትዋሽ ትችላለህ፣ ብቻ ከቅዱስ ቁርባን ሊያርቅህ የሚችለውን ኃጢያት ልትሠራ ትችላለህ ብለው በማሰብ ነው፡፡ ግን ስህተቱ ምን ላይ መሰላችሁ? ይኼን ኃጥያት እንዳይሠሩ መጠበቅ ነው የሚሻለው? ወይስ ቀድሞ ከቅዱስ ቁርባን ማራቅ ነው? ይኼ ሰው እኮ እስከሚሞት ድረስ እኮ አዋቂ ነው፣ ይቺ ሴት እስከምትሞት ድረስ አዋቂ ነች። የዕድሜ ደረጃዋ ይለያይ፤ የእድሜ ደረጃው ይለያይ እንጂ፣ በየዕድሜ ደረጃቸው ኃጢያት ከመሥራት አይቆጠቡም፡፡
ስለዚህ፤ ይልቅ ዋናው ነገር የኃጢያትን መሥመሩን መቁረጥ ነው፡፡ የኃጥያት ኃይል እንዳይተላለፍ ከሰው ሕይወት ላይ መስመሩን ማቋረጥ ነው፡፡ ልክ እንደ ኤሌክትሪክ መስመር ወይም እንደ ሰልክ መስመር ማለት ነው፣ ወይም እንደ ውኃ መስመር ማለት ነው፡፡ እሱን ማቋረጥ ነው፡፡ ያንን ያቋረጥነውን ነገር መልሰን እንዳንቀጥለው፣ እንዳንዘረጋው፤ በሚያስችል የመጨረሻ ውሳኔ መስመሩን ማቋረጥ ያለብን ኃጢያት የሚመጣበትን፣ በኃጢያት የምንወድቅበበትን፣ በኃጢያት የምንፈተንበትን፣ ኃጢያተኞች የምንሆንበትን፣ ከእግዚአብሔር ጋር በኃጢያት የምንጣላበትን እሱን መስመር ነው ማቋረጥ እንጂ ከቅዱስ ቁርባን ሰዎች እንዲርቁ፣ ቅዱስ ቁርባን መቀበልን እንዲያቋርጡ ማድረግ በደሉ ሁለተኛ ነው የሚሆነው፡፡ እምነታችንም ፍፁም የሚሆነውም እኮ በቅዱስ ቁርባን የምንቀደሰው ሕይወት እኮ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንኖርበት ምስጢር ነው፡፣ ዘለዓለማዊ ሕይወትን የምንወርስበት ነገር ነው፡፡ ሥጋዬን የበላ፣ ደሜን የጠጣ የዘላዓለም ሕይወት ያገኛል ነው የሚለው፡፡
ስለዚህ የዘለዓለም ሕይወት የምናገኝበትን ነገር እንድናቋርጥ በዕድሜ ክልል ከመወሰን ይልቅ አንድ ቀንም ጠቅሞን፣ አክብሮን የማያውቀውን ኃጢያት እንድናቋርጥ ነው ፡፡ እናም የለም እንዲህ ዓይነት ሥርዓት ወጣት ወንድ ሆነህ ኃጢያተኛ ሁን፣ ወጣት ሴት ሆነሽ ኃጢያተኛ ሁኚ የሚል ሕግ የለም፡፡ በዚህ ዘመን ኃጥያተኛ ሆናችሁ እንደፈለጋችሁ ሆናችሁ ስትመለሱ፣ ወይም ዕድሜህ ሲሸመግል፣ ዕድሜዋ ሲሸመግል፣ ጉልበቱ ሲደክም፣ ጉልበቷ ሲደክም ተብሎ የግድ የዕድሜ ክልል ስለገደባቸው ያንን ለመዱትን ኃጢያት ለመሥራት ከልባቸው በንስሐ ሕይወት ስለታውት ሳይሆን አቅማቸው ስለማይፈቅድ፣ ጉልበታቸው ስለማይችል ብቻ ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ይሆናሉ ብሎ በማሰብ ነው፡ ይኼ ደግሞ የክርስትና የመጨረሻ ድክመት ነው ፡፡ እግዚአብሔር ወጣቱን ይፈልጋል፣ እግዚአብሔር ህፃናቱን ይፈልጋል፡፡ ኃጥያታቸውን ብቻ ነው የማይፈልገው፡፡ ኃጢያትን ደግሞ ማቋረጥ ይቻላል፡፡ ሰው ኃጢያት የማይጠቅም ነገር መሆኑ በግልፅ እየታየው፤ ይኼ ሞት ነው እየተባለ፣ ይኼ ሲዖል ነው እየተባለ፣ ይኼ ጉድጓድ ነው እየተባለ፣ ይኼ ማዕበል ነው እየተባለ፣ይኼ ጥፋት ነው እየተባለ ዓይኑ እያየ የሚገባ ሰው የለም፡፡ ሞትንና ሕይወትን፣ ፅድቅንና ኩነኔን፣ ጨለማና ብርሐንን፣ በጎ ሥራን ክፉ ሥራን ለይቶ የማሳወቅ ጉዳይ ነው፡፡
ከዚህ አንፃር ጠያቂያችን ማወቅ ያለብዎት ለመቁረብ ዕድሜ አይወስንም፡፡ ከዚህ ቀደምም ደጋግመን ተነጋግረናል፡፡ ያው ሁሉም ሰው መቸስ ከራሱ ጊዜ አትርፎ ወደዚህ ፕሮግራም የሚመጣበት ጊዜውንም፣ ሁሉንም ነገር በደንብ መከታተል ስለማይቻል ይመስለናል እንጂ፤ ያልመከርንበት መስመር የለም፡፡ እንዲያውም የትምሕርታችን ማዕከል እኮ ዋናው ምስጢረ ቁርባን ነው፡፡ ከቅዱስ ቁርባን ከተለየን ከእግዚአብሔር ጋር እንደተለየን ማረጋገጫችን ይኼ ነው የመጨረሻው፡፡ በጣም የሚያሳዝን ነገር አለ፡፡ ሁሉም ሰው የሚደክምበት በእርግጥ ከነ ድፍረታችን፣ ከነ ኃጢያታችን እንድንቀርብ አይደለም፡፤ በዕድሜ ክልል ተፈቅዶ የሚሠራ ኃጢያት የለም፤ በዕድሜ ክልል እንዳንቆርብ የምንከለከልበት ምንም ዓይነት ሥርዓት የለም፡፡ ይኼንን በደንብ አድርጋችሁ አስተውሉ፡፡ በዕድሜ ክልል ተወስኖ እንድንሠራ የሚፈቀድልን ኃጢያት የለም፡፡ ሕፃንም ሳለን ፣ ወጣትም ሳለን፣ ጎልማሳም ሳለን፣ሽማግሌም ሳለን ኃጢያት እንዳንሠራ ሕገ እግዚአብሔር ይከለክለናል፡፡ በዚህ መካከል ደግሞ ተፈትነን የወደቅንበት ኃጢያት ካለ ሳናውል፣ ሳናሳድር፣ ለሥጋዊ ክብራችን ሳንጨነቅ፣ ሳንፈራም ሄደን ንስሐ መቀበል አለብን ይኼ ነው ሕጉ፡፡
የጥያቄውን መልስ በአጭሩ ስንደመድመው የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር በሌላ ክብር ወደ እርሱ እስከሚጠራን ድረስ ከቅዱስ ቁርባን፣ ከነፍስ ምግብ ርቀን ሕይወት ስለማይኖረን አንድ ቀን እንዳንለይ የእግዚአብሔር ሕግ ያዘናል፡፡
በመጨረሻም፥ ጠያቂያችንም ሆኑ የድረገፃችን አባላት አደራ የምንላችሁ ሌሎች ያቀረቡትን ጥያቄ መሰረት አድርገን በየቀኑ ጠዋት እና ማታ የምናስተላልፈውን ትምህርት እና ምክር በዚህ የዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የቴሌግራም ግሩፕ፥ ካሉበት ስፍራ ሆነው ቢከታተሉን መንፈሳዊ ህይወትዎን በልማድና በመጠራጠር ሳይሆን በእውቀትና በትክክለኛው መንገድ እንዲመሩ ያግዝዎታልና በአገልግሎቱ ዘወትር እንዲጠቀሙ እንመክራለን ፤ ለሌሎች ወገኖችም ሊንኩን ሼር እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።👇
በዚህ ሁሉ የመከረን፣ የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን አሜን፡፡
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፦ #ቅዱስ #ቁርባን ለመቀበል የጋብቻ (#ትዳር) ሁኔታ ይወስነዋል ወይ? ለምሳሌ ፈት ብንሆን፣ ጨርሶ ያላገባን ብንሆን፣ አግብተንስ አጋራችን ፈቃደኛ ባይሆንስ?
መልስ፦ የአዲስ ኪዳን ቁርባን የምንለው የክርስቶስ ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙ ነው ብለናል። ይሄን የመቀበል ስርዓት ደግሞ ወንድ ልጅ በ40 ቀኑ ክስትና ሲነሳ ሴት ልጅ በ 80 ቀንዋ ክርስትና ስትነሳ ጀምሮ የታደልነው ልዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የዘላለም ህይወት ምግብ ነው ብለናል። ከዚህ መለየት ማለት በቁማችን መሞት ማለት ነው። ስጋ፥ የስጋ ምግብን ካጣ በእርግጠኝነት የተወሰኑ ሰዓታትና እለታት እንኳን ለመቆየት ያውም ለብዙዎች የሚቻል አይደለም ከዚያ በኋላ በህይወት መቀጠል አንችልም። ይሄ አንዱ ስጋዊ ህልውናችንን የምናጣበት የተለመደ የስጋ ደካማ ባህሪ ነውና በምድር ላይ። ነፍስም እንዲሁ የክርስቶስ ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን ካጣች ሞተች ህይወት የላትም፤ ገድለናታል ማለት ነው። ስለዚህ ባይሆን ይሄንን የዘለዓለም ህይወት ለመመገብ የዘለዓለም ህይወት የሚሰጠውን ጽዋ ለመጠጣትም እኛ መዘጋጀት ያለብን በምን አይነት ስርዓት እንደሆነ በምን አይነት መንፈሳዊ ዝግጅት እንደሆነ በእሱ ላይ ያለን ነገር ክርስቲያናዊ ጸባይ እንዲሆን ታዘዝን እንጂ በብዙ ማስፈራራትና በሌላ ምክንያት በማብዛት እንድንርቅ ለማድረግ የሚሰጥ ትምህርት የለም።
ሐዋርያዊ ቅዱስ ጳውሎስ እንደነገረን ሳይገባን ይሄንን በእለተ አርብ ስለእኛ ስለወዳጆቹ ሌላ በምንም ሳይሆን ስጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ የሰጠን የዘለዓለም ህይወት ብንበላ ብንጠጣ እዳ እንዳይሆንብን ያለው፥ ሁል ጊዜ ለንስሐ ህይወት እየተዘጋጀ ህይወት እንዲኖረን እና በነፍስ ጉዳይ አማካሪ የሆኑንን እግዚአብሔር ስለእኛ አገልጋዮችና እና የመንጋውም እረኛ ሆኖ ያቆማቸውን የቤተክርስቲያን አባቶችን መምህራንን እያማከርን ስህተት እንዳይመጣብን ሁል ጊዜ ተዘጋጅተን እንድንቀበል ታዘዝን እንጂ ከዚህ ለአንድ ቀንም እንድንለይ የታዘዝንበት አጋጣሚ የለም።
ስለዚህ ከጋብቻ በፊት ለተባለው ከላይ እንደገለጽነው ከክርስትና ጊዜ ጀምሮ ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቀንን ነውር ወይም ኅጢአት ሳንሰራ እየተቀበልን እንቀጥላለን ማለት ነው። ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቀንን ኅጢአት ወይም ነውር የተባለውን ምን እንደሆነ ሁሉ ሰው ያውቃል፤ ህጻን እንኳን ያውቃል። የኅጢአት አይነትን ከጥቃቅኑ እስከ ከፍ ያለው የኅጢአት ደረጃ የማያውቅ ሰው የለም። ነፍሰገዳይነት፣ ዘማዊነት፣ ሴሰኝነት እነዚህን የሚመስሉ ኅጢአቶች ሁሉ ከቅዱስ ቁርባን ሊያርቁ ይችላሉ እንጂ እስከ እድሜ ልኩን እኮ አንድ ሰው ሳያገባ እራሱን አግልሎም ከዚህ አለም ግብር ቆራቢ ሆኖ መኖር ይችላል፤ ያለዚያም ደግሞ አካለ መጠን እስከሚደርስ ወንዱም ሴቱም፤ ከዚያ በኋላ ወንዱም ቢሆን በመንፈሳዊ ህይወቱ እሱን የምትመስል መርጦ ሴቷም በመንፈሳዊ ህይወቱ እሷን የሚመስል መርጣ ይጋቡና በቅዱስ ቁርባን ይቀጥላሉ። ይሄም እድል ሳይገጥማቸው በቅዱስ ቁርባን ያልተጋቡ ሰዎች ደግሞ ወደ ንስሐ ቀርበው እነሱም ደግሞ ያንን ከጊዜ በኋላ የተዉትን ያቋረጡትን የተቀደሰ አላማቸውን ደግሞ ያስቀጥላሉ። ቤተክርስቲያን ስርዓት ስለሰራችልን ለሁሉም ማስታረቂያ አላት ከፈጣሪዋ።
ስለዚህ ጠያቂያችን በዚህ መሰረት ይረዱት እያልን ነገር ግን ዝም ብለን ያው አንዳንድጊዜ ትዝ ሲለን ብቻ ነገሮችንም አካብደንም በራሳችን ላይ ደግሞ ፈተና አድርገን የምናቀርባቸው ጥያቄዎች በቃል ደረጃ መልስ ስላገኙ ብቻ ለእግዚአብሔር መንግስት አያበቁንምና እንዲያው በትክክለኛ ለመጠቀም የቀረበ ጥያቄ ከሆነ ይሄንን አጭር መልእክት ተቀብላችሁ በስራ ላይ ብታውሉት በጣም እጅግ መልካም ነው።
በአጠቃላይ ቅዱስ ቁርባን የጋብቻ ሁኔታ ብቻ አይወስነውም፤ እስከ ጋብቻ ድረስ በሚኖረንም ቆይታ ከቅዱስ ቁርባን እንድንርቅ ቅድስት ቤተክርስቲያን አታዝም፤ አንድም ቀን አታዝም። ይሄ አንዳንድ ሰዎች በልማድ ያመጡት ወይም መካሪዎች አስተማሪዎችም ቢሆን በእግዚአብሔር ስርአት ሳይሆን በሕዝብ ስርዓት ተውጠው ተስማምተን ዝም ብለን እኛም ቢሆን ከቅዱስ ቁርባን እርቆ የሚኖረውን ህዝብ አባት ሆነን የመቀጠላችን ነገር ክብር ሳይሆን ለእኛ ትልቅ ውርደት ነው። ለምን? የመጀመሪያው ዋናውና ተቀዳሚ ተግባር ክርስቲያን የሆነ ሁሉ የክርስቶስን ስጋ እና ደም ይቀበላልን? አሁን እንደ እኛ አማናዊ ቅዱስ ስጋው ክቡር ደሙ አድርገው የማያምኑና መታሰቢያ የሚያደርጉ ሌሎቹ በክርስትና ውስጥ ነን የሚሉ በዓለም ዙሪያ ያሉ ወደ ቸርች በመጡ ቁጥር ያንኑ መታሰቢያ አድርገው የሚያስቡትን ሳይቀበሉ አይሄዱም ፥ በተአምር። ምናልባት የእኛ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ቁርባንን እንደዚህ በመታሰቢያነት ሳይሆን እንዲያው በድፍረት ሳይሆን በትክክለኛው እንደእለተ አርብ ፈጣሪዬ በዚያ ሁሉ መከራ ብዛት ስለእኔ ብሎ ያፈሰሰው ደሙ የቆረሰው ስጋው ስለሆነ አማናዊ ቅዱስ ስጋው አማናዊ ክቡር ደሙ ነው ብለን በፈሪሀ እግዚአብሔር ነው የምንቀበለው። የክርስቲያን ስነምግባር ይሄ ነው። በክርስቲያናዊ ስነምግባር ሆነን በደላችንን በንስሐ ህይወት አስተካክለን የምንቀበለው ስለሆነ ከሌሎቹ አንጻር የማይታይ ቢሆንም ግን ከሱ እንድንለይ አልታዘዝንም። ከጋብቻም በፊት በጋብቻም ጊዜ ከቅዱስ ቁርባን የሚያስቀረን ነገር ቢኖር የራሳችን ተግባር ነው።
ስለዚህ ለጥያቄው መልሱ ትልቁ ነገር ከዚህ የምንለይበት ጊዜ ካለ የራሳችን ምክንያት ነው። አንዱ ወይ ትምህርት አንሶናል ወይ ከስጋወደሙ የሚያርቀን የራሳችን በደል ወይም የምናውቀው በደል አለብን ማለት ነው። እንደዚህ ካልሆነ በስተቀር ከቅዱስ ቁርባን የምንከለከልበት ጊዜ የለም በማለት ህይን አጭር መልእክት ልከንልዎታል።
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾👉🏾👉🏾ስለ #ምሥጢረ #ቁርባን
1 ብሂል
ምስጢረ ቁርባን ማለት ጌታችን ኢየሱስ የመሠረተው ያስተማረውና በመጨረሻም ማዕድ አቅርቦ እንኩ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው ፤ እንኩ ጠጡ ይህ ደሜ ነው ብሎ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠው በሥራም የገለጠው እስከዛሬም ያለአድልዎ ለሁሉ የሚሰጠው የክርስቶስን ሥጋና ደም የመቀበል ምስጢር ነው።
ካህኑ ኅብስቱን በጻሕል ወይኑን በጽዋዕ አድርጎ ሚያቀርበው በጸሎትና በእግዚአብሔር ቃል ተለውጦ ኅብስቱ ሥጋ መለከት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው ሕዝብ ለድኅነትና ለዘለዓለም ሕይወት የሚቀበለው ምስሢረ ቁርባን ይባላል።
ምስሢረ ቁርባን ስንበላውና ስንጠጣው በኅብስትና በወይን መልክ ነው፤ ግን በካህኑ ጸሎትና ቡራኬ ተለውጦ የክርስቶስ አካል ይሆናል፤ ማለት ደሙ ፍጹም የክርስቶስ ደም በዕለተ ዓርብ የፈሰሰውን፤ ሥጋውም በዕለተ ዓርብ የተቆረሰውን ይሆናል፤ ለዚህም ለውጥ እንዴት እንደሆነ ስለማይታወቅ ምሥጢር ተብሏል።
እንግዲህ ክርስቶስ ሊቀ ካህናት ሆኖ ለአባቱ ያቀረበው ያሳረገው መሥዋዕት ስለሆነ የክርስቶስ ተከታይ የሆነ ሁሉ ከዚህ ሥጋ መብላት ከዚህም ደም መጠጣት ግዴታ ነው፤ ያለዚያ ተዋሕዶት የሚኖር ሕይወት የለውም፤ ክርስቶስ ሲያስተምር አስቀድሞ “እኔ ነኝ የሕይወት እንጀራ ፤ ከሰማይ የወረደ፤ ማንም ከዚህ እንጀራ የሚበላ ለዘለዓለም ይኖራል እኔም የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው” ሲል አስተምሯል (ዮሐ 6፥54 56) ከዚህም በማያያዝ “እውነት እውነት እላችኋለሁ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ እናንተ ሕይወት የላችሁም ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ ለርእሱ የዘላለም ሕይወት አለው፤ እኔም በኋለኛው ቀን አስነሣዋለሁ” ሲል ገልጦ ተናግሯል (ዮሐ6፥57) በዚህ መልክ ክርስቶስ ሲያስተምረው የቆየውን የመጨረሻ ጊዜ በተግባር ገለጠው፤ ማለት የመጨረሻ እራት አድዬጎ ሥጋውንና ደሙን “ንሡ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው ጽዋውንም አንስቶ አመስግኖ እንዲህ ሲል ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው ከዚህ ጠጡ የህ ደሜ ነው፤ ለአዲስ ኪዳን ለብዙ ሰዎች የሚሰጥ ኀጢአትን ለማስተሰረያ” ሲል (ማቴ 26 25፥30)
መቁረብ የሚገባው ማነው
በክርስቶስ ያመነ ክርስቶስንም የተከተለ ሁሉ የዕድሜ የጾታ ገደብ ሳይኖርበት በክርስቶስ ቃል መሠረት ሁሉም ከሥጋው መብላት ከደሙ መጠጣት ይገባዋል። ምእመኑ ሁሉ ከክርስቶስ ጋር አንድነት ይኖረው ዘንድ እንዲሁም ሁሉም አንዱ ከሌላው ጋር አንድነት ይኖረው ዘንድ መቁረብ አለበት። ክርስቲያን የሆነ ሀሉ ከክርስቶስ ጋር የሚዋሐደው ሥጋውን በመብላት ደሙንም በመጠጣት ስለሆነ በግድ መቁረብ አለበት።
ሁል ጊዜ መቁረብ እንደሚገባ
ምሥጢረ ቁርባን የሚደጋገሙ ምሥጢራት ውስጥ ነው፤ ስለዚ ማንም ክርስቲያን በየዕለቱ በየሰምንቱ፤ በየወሩ፤ መቀበል አለበት። ቢያንስ እንኳን በዓመት 3 ገዜ መቁረብ አለበት።
ካህኑ በሚያቆርቡበት ጊዜ “ሥጋሁ ለአማኑኤል አምላክነ ዘበአማን ዘነሥአ እም እግዝእተ ኩልነ” እያለ ፍጹም የክርስቶስ ሥጋና ደም መሆኑን እየመሰከረ ነው። የሚቀበለውም ምእመን “አሜን” ልክ ነው አምናለሁ ብሎ ይቀበላል።
ማንኛውም ምእመን ሲቆርብ ከሥጋው መብላት ከደሙም መጠጣት ግድ አለበት እንጂ አንዱን ተቀብሎ 2ኛውን መተው ተገቢ አይደለም፤ ምክንያቱም ክርስቶስ ሲያስተምር ሥጋየን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው ብሎ ከ2ቱም መቀበል እንደሚገባ አስተምሯልና (ዮሐ 6፤56)
በቁርባን ጊዜ ለሥርዓቱ መልክ እንዲኖረው፤ ዝብርቅርቅም እንዳይል መጀመሪያ ጳጳሳት፤ ቀጥሎም ካህናት፤ ቀጥሎም ዲያቆናት፤ ቀጥሎም ሕዝባውያን እንዲቆርቡ ሕግ ነው። እንዲሁም ከሴቶችም በፊት ወንዶች እንዲቀበሉ ሕግ ያዛል። ይህም የሥነሥርዓት አጠባበቅ እንጂ ልዩነትን የሚያመለክት አይደለም።
እንዴት መቁረብ እንደሚገባ
ቅዱስ ቁርባንን የሚቀበሉ ሁሉ መጾም አለባቸው፤ ይህም ማለት በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የውሎ ቅዳሴ ስላለ ጾሞ መዋል ስላለበት ነው። የጧት ቅዳሴም ከሆነ በዋዜማው በጊዜ መብላት እንዳለበት የመለክታል። እንዲሁም አስቀድሞ ንስኀ ገብቶ ኀጢአቱን ተናዝዞ ንጹህ ሆኖ መቁረብ አለበት።
ይቆየን
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉🏾ስለ #ቅዱስ #ቁርባን፣ የ #ንስሐ ህይወትና ስለ #ዝሙት #ፈተና
👉ጥያቄ፡- ንስሐ ገብቼ መልሼ እሳሳታለሁ፡፡ የዝሙት መንፈስ በጣም ይፈታተነኛል፡፡ እኔ ግን ንስሐ ገብቼ፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል እፈልጋለሁ፡፡ ልብስም ገዝቼ ይኼው መቼ ይሆን ከአንተ ቤት የምኖረው እያልኩ እሳላለሁ፡፡ ንስሐ ገብቼ ብቆርብስ ? የድፍረት ኃጢያት ይሆናል ወይ? አንድ አባት ቢያንስ 30 ዓመት ይሙላሽ አሉኝ፡፡ እኔ ግን ከእግዚአብሔር መራቅ አልፈልግም፡፡ ግን መኖር እፈልጋለሁ እስኪ አስረዱኝ በማርያም?
መልስ፡- የጠየቁን ስለ ንስሐ ሕይወት ነው፡፡ በመቀጠልም በንስሐ ሕይወት ስለሚፈፀም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ በሚመለከት ነው፡፡ ጠያቂያችን ከንስሐ የተሸለ ምን የሚያስፈልግ ነገር አለ? ሁልጊዜም ደጋግመን እንደምንለው ኃጢያት ላለመሥራት መጋደሉ፣ መታገሉ መቸስ የማይገኝ ዕድል ነው፡፡ ለሁላችን የማይቻል ነገር ስለሆነ፤ ሁላችንም ፈተና የበዛብን ተክል ስለሆንን፣ የፈለገንን ያህል ብንምል፣ ብንገዘት፣ አጥብቀን ብንጠላው ብንታገለው ሁላችንም ተሰናክለን የምንወድቅበት የጋራ የሆነ ኃጢያት ስላለ በዚያ ተጠልፎ መውደቁ የማይቀር ነገርና መጥፎ ዕድል ሆኖብን እንጂ፤ በዋናነት ከኃጢያት ርቆ መኖር ቁጥር 1 የምንመርጠው የተቀደሰ ተግባር ነው፡፡ ይኼ ሳይቻል ቀርቶ ደግሞ በአንድም፣ በሌላ መንገድም ወይም ከባድ በሆነ ወይም ቀላል በሆነ ኃጢያት በወደቅን ጊዜ፤ ዓይነተኛው መፍትሔ ወደ ንስሐ መምጣት ነው፡፡
በቅዱሳት መጻህፍትም የንስሐ ትርጉም ወይም የንስሐ ታላቅነት ተነግሮናል፡ ንስሐ ማለት ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው፡፡ በሙሉ ልብ በፍፁም እምነት ሆነን ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው.፣ መጸጸት፣ የንስሐ ሕይወት የሚባለው ነገር ይኼ ነው፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ ጥርጊያውን አቅኑ›› እያለ በመጣ ጊዜ የአዋጁ አብሣሪ ሆኖ ሲመጣ ፤ የመጀመሪያው የስብከቱ አዋጅ ንስሐ ግቡ የማቴዎስ ወንጌል ቁጥር 1 እና 2 ላይ ንስሐ ግቡ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና፡፡ ሐዋርያትም ጌታ በተነሣ በ 50 ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸው 72 ቋንቋም ተገልጦላቸው፣ ገና በጠዋቱ በአይሁድ ዘንድ ቆመው እጅግ የብዙዎቹ ልቡና የተመሰጠበትን ትምሕርት ባስተማሩ ጊዜ ብዙዎቹ አምነው ወዲያውኑ፤ ምን እናደርግ ሲሏቸው? ንስሐ ግቡ፣ እና አምናችሁ ከመጣችሁ ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን ተጠመቁ፡፡ ይኼን ነው እንግዲህ ያስተማረ ማለት ነው፡፡
ስለዚህ የዮሐንስ ትምሕርት የመጀመሪያው ነገር የበር መክፈቻው ቁልፍ ንስሐ ግቡ ነው፡፡ ሁላችንም ከነኃጢያታችን እንዲሁ ተሸፋፍነን እንድንኖር እግዚአብሔር አይፈቅድም፡፡ እና ለንስሐ የእድሜ ገደብ የለውም፡፡ ቅዱስ ቁርባን የእድሜ ገደብ የለውም፡፡ ይኼን በሚመለከት በጣም ብዙ ጊዜ ተነጋግረናል፡፡ መቸስ በእያንዳንዱ ትምሕርት ሳንዘነጋ የምናስታውሰው ነገር ስለ ምስጢረ ቁርባን ነው፡፡ ማንኛውም አማኝ፣ ማንኛውም ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን መቀበል እንዳለበት፡፡ ደጋግመን እንደተነጋገርነው፤ ወንድ ልጅ በ40 ቀኑ፣ ሴት ልጅ በ 80 ቀኗ የእግዚአብሔር ልጅ ሆነው በስመ ክርስትና፣ በቅዱስ ቁርባን ታትመው ልጅነታቸውን ካረጋገጡ በኋላ ከቅዱስ ቁርባን አንድ ቀንም ቢሆን መለየት የለባቸውም ብለናል፡፡
ስለዚህ ጠያቂያችን፤ በተለያየ የሥጋ ድካም፣ በተለያየ የኃጢያት ምክንያት ከሥጋወደሙ መሸሽ ወይም ማቋረጥ አያስፈልግም፡፡ ከእነጭራሹ ደግሞ የምንሰማው ጉድ 30 ዓመት ይሙላችሁ፤ 40 ዓመት ይሙላችሁ፣ 25 ዓመት ይሙላችሁ አይባልም እኮ፡፡ ከምን ጋር በማያያዝ ነው የእድሜ ጣሪያ የምናስቀምጠው? ለደቂቃም፣ ለሴኪንድም ከእግዚአብሔርጋር መለየት የለበትም የሰው ልጅ እያልን ፣ ሁሉም መላ ሕይወታችን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ነው፡፡ ምናልባት ከእግዚአብሔር ክልል ውጪ፣ እርሱ ከሚገዛው፣ ከሚያስተዳድረው፣ ከፈጠረው ዓለም ውጪ ሆነ ሌላ ዓለም ኖሮ፣ ሌላ አስተዳዳሪ፣ ሌላ ገዢ ኖሮ ከእሱ ተለያይተን ከፈለግን ደግሞ ሌላ አብረን ለመኖር ውል የምንመሠርትበት ኑሮ አይደለም እኮ ይኼ፡፡ በየትኛውም ሰዓት ውስጥ፣ በኃጢያት ውስጥም እያለንም የእግዚአብሔርን ስም እንጠራለን፡፡ ከዚያ ከወደቅንበት የኃጢያት ጉድጓድ፣ የኃጢያት ማጥ ውስጥ ሊያወጣን የሚችለው፤ መፍትሔ እንዲሰጠን እግዚአብሔር ቁልፍ የሆነውም የችግራችን መፍትሔም ያለው ከእግዚአብሔር እጅ ነው፡፡ ስለዚህ ፈፅሞ እንዲህ ዓይነት ትምሕርት ልንሰማም አይገባንም፡፡ ቆይ ልጅ ናችሁ፣ እንዲህ፣ እንዲህ እያሉ የሚሉ ትምሕርት ያነሰው ሰው፣ ወይ ደግሞ ፈጽሞ መንፈሳዊ ምክርና ትምሕርት ተፈልጎ የታጣበት ሰው የሚናገረው የሚያስረዳው የሌለው መጽሐፍትን ጠቅሶ የማያስተምር፣ እንዲህ ዓይነት ካሕን በልብ ወለድ ስለሚናገር ምንቸገረው? እንዳንመነኩስም ገና ነሽ፣ እንዳንቆርብም ገና ነሽ፣ ባይሆን ካሕን ማስተማር ያለበት ሁል ጊዜ ለምዕመናን እግዚአብሔር ቢረዳቸው ከኃጢያት እንዲለዩ ብቻ ነው፡፡ ጊዜ ሳንሰጥ መናገር ያለብን ቅዱስ ቁርባን እንዲቀበሉ፣ እንደዚህ አድርጉ ኃጢያት ላይ ወድቄያለሁ አባቴ ብንባል፤ በል ቶሎ ንስሐ ግባና ወደ እግዚአብሔር ተመለስ፣ ቶሎ ቁረብ ነው ማለት ያለብን፡፡ ሁሌ የምናገረው ቋንቋ ይኼ ነው፡፡የእግዚአብሔር ቅድስና የእኛን የረከሰውን ሕይወት ከኃጢያት ያነፃል፤ የእኛ ኃጢያት ግን የእግዚአብሔርን ቅድስና አያረክስም፡፡
ስለዚህ ጠያቂያችን፤ ቅዱስ ቁርባኑም፣ ፀበሉም፣ መስቀሉም ፣ ቃለእግዚአብሔሩም፣ ቅዳሴውም ይኼ ሁሉ እኛን ከኃጢያት የሚያነፃ ነው እንጂ ጨርሶ የሚያረክስን ኃጢያታችንን የሚያባብስብን ነገር አይደለም ይኼ፡ አሁንም ጠያቂያችን እንዲህ ዓይነት ፍላጎት፣ ምኞት እያለዎት ገና ነዎት፣ የወጣትነት ዕድሜ ነው፣ ብዙ ነገር አካብደን ፣ ተስፋ ቆርጠን የምንርቅበት የሕይወት ደረጃ አይደለም ያለነው፡፡ እርስዎ ያሉት እንግዲህ 30 ዓመት ይሙላሽ የሚለው ገና የእዚህ ዕድሜ ባለቤት እንኳን እንዳልሆኑ ፣ የልጅነት የወጣትነት ዕድሜ ላይ የተፈተኑበት ነገር ምን እንደሆነ፣ በግል ሕይወትዎ ምክርም መክረን፣ እንደ ቤተክርስቲያን መምህር፤ እንደ ቤተክርስቲያን አባት የሚስተካከለው ነገር እንዲስተካክል ይደረጋል፡፡ እግዚአብሔርም ያግዘናል፣ ቸርነቱ ፣ ምሕረቱ ብዙ ስለሆነ፣ በተለመደው የውስጥ አድራሻችን ደውለው ያግኙንና ተጨማሪ ምክር እንሰጥዎታለን፡፡ በነገሩ ሁሉ የሚመክረን እግዚአብሔር የተመሰገነ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ቤት የሚለየን የሚያርቀን፡ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ምንድን ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፣ ለሮሜ ክርስቲያኖች በፃፈው መልእክቱ በሮሜ መልእክት ምዕራፍ 8 ያለው ማለት ነው፡፡ ከቁጥር 35 ጀምረን ስናነብ የምናገኘው ማለት ነው፡፡ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ ማነው? በጣም ከባድ የተባሉ ብዙ ጦርነት ነው? ረሐብ ነው? ሠይፍ ነው? ደዌ ነው? ምንድን ነው? ብሎ ዘርዝሯቸዋል፣ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ የለም ፡፡ ስለዚህ ብዙ የሥጋ ምክንያቶችን እየደረደርን ከቅዱስ ቁርባን ፍቅር የሚለየን ነገር አንዳችም የለም፡፡ይኼንን ነው ማየት ያለብን።
(ይቀጥላል)👇
(ቀጣይ ክፍል)👆👇
👉🏾ስለ #ቅዱስ #ቁርባን፣ የ #ንስሐ ህይወትና ስለ #ዝሙት #ፈተና
በአጠቃላይ ከእግዚአብሔር ቤት ልንርቅ አይገባንም፡፡ ልበ አምላክ ዳዊት ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ በጣም ደስ አለኝ ነው ያለው፡፡ ይኼ የእስራኤል ገዢ ታዋቂው፣ ዝነኛው ንጉሥ ዳዊት፤ እንደ ሥጋዊ ሐሳብ ከሆነ በታላቁ ቤተ መንግሥት ነገሦ የሚኖረው ዳዊት፣ በሥጋው ብዙ የሚያስደስቱ ነገሮች እፁብ፣ ድንቅ የሚባሉ ነገሮች እንዳሉ የሚታወቅ ነው፡፡ ነገር ግን ዳዊት ምንድን ነው ያለው? ከምንም በላይ ሰው ሁሉ በሕይወቱ ደስ ከሚሰኝበት፣ ከሚደሰትበት ነገር፤ ወደ እግዚአብሔር ቤት መሄድ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ቤት አለመራቅ፣ አለመለየት፡፤ ይኸው ነው ሌላ ፀጋ የለም፡፡ እዚያ ቅዱስ መስቀል አለ፣ እዚያ ቅዱስ ጸበል አለ፣ እዚያ ቅዱስ ቁርባን አለ፣ እዚያ የእግዚአብሔር ቃል አለ፣እዚያ ቅዳሴ አለ፣ እዚያ ዝማሬ አለ፣ እዚያ በመንፈስ የመረጋጋት፣ የመጽናናት፣ ፍቅር አለ፣ ሠላም አለ ፣ትዕግሥት አለ ከእግዚአብሔር ቤት ሊለየን የሚችል አንዳችም ነገር የለ፡፡
ስለዚህ እንዳሉትም ለቅዱስ ቁርባን የሚሆንዎት ዝግጅት አድርገው፣ ልብሱ ሳይቀር፣ ተዘጋጅቶ ብለዋል፣ ይኼንን ምኞትዎትን፣ የልብዎትን ሐሳብ እግዚአብሐየር ይሞላዋል በእርግጠኝነት እኛ ደግሞ ሳይውሉ፣ ሳይድሩ፣ ቀጠሮ ሳይበዛ፣ ቶሎ ወደዚያ እንዲቀርቡ ተጨማሪ ምክር ስለምንሰጥዎት ቅድም እንዳልኩት በውስጥ መስመራችን ያግኙን፡፡
የመከረን፣ የገሰፀን የሠራዊት አምላክ ሥሙ ይመስገን፣ ፀጋ በረከቱን በሁላችን ላይ ያሳድርብን፡፡ ወስብሓት ለእግዚአብሔር አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾ስለ #ቅዱስ #ቁርባን እና #ዕድሜ
👉ጥያቄ፡- ለመቁረብ ዕድሜ ይወስነዋል ? ማብራሪያ ፈልጌ ነበር እባክዎ ?
መልስ፡ ጠያቂያችን የጠየቁን አጭር ጥያቄ ሲሆን፤ ይኽም ስለ ምስጢረ ቁርባን ነው ፡፡ ስለ ምስጢረ ቁርባን በጣም በብዙ ጥየቄዎች መነሻነት በዚሁ በዮሐንስ ድረገጻችን ብዙ ትምሕርት ሰጥተናል፡፡ ጠያቂያችን እሱንም በተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሆንዎት ሊያዩት እንደሚገባ እየመከርን አሁን ለጠየቁት ጥያቄ ግን በአጭሩ የሚከተለውን ምላሽ ልከንልዎታል፡፡
ለመቁረብ የዕድሜ ገደብ የለውም ፡፡ ምክንያቱም ወንድ ልጅ በአርባ ቀኑ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ፣ ሴት ልጅ በሠማኒያ ቀን የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ፣ ልጅነታቸውንም ያረጋገጡት በቅዱስ ቁርባን ስለሆነ፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ማንኛውም የእግዚአብሔር ልጅ በእሱ ፊት ሰው ሆኖ ለመኖር፣ ወይም ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ለመቀጠል የማይለየው፣ የማይተወው፣ የማያቋርጠው ነገር ቢኖር የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን፣ ክቡር ደሙን መቀበል ነው፡፡ የማይቋረጥ ሥርዓት ነው፡፡ እንግዲህ ስለ ዕድሜ ክልል ስናነሳ ከኃጢያት ጋር በተያያዘ የሰው ልጅ ወንዱም ለአቅመ አዳም፣ ሴቷም ለአቅመ ሔዋን ደርሳለች ብለን በልማድ እናቶቻችን፣ አባቶቻችን አንዳንድ ካሕናትም ቢሆን፤ ዕድሜሽ ገና ነው አትቆርቢም፣ ዕድሜህ ገና ነው አትቆርብም ማለት ምን ማለት ነው? ያኔ ለአካለ መጠን ደርሰሻል፣ ሴቷም የሴት ሥራ ትሠሪያለሽ፣ ወንዱም የወንድ ሥራ ትሠራለህ ፣ልትዘሙት ትችላለህ፣ ልትሰርቅ ችላለህ፣ ልትዋሽ ትችላለህ፣ ብቻ ከቅዱስ ቁርባን ሊያርቅህ የሚችለውን ኃጢያት ልትሠራ ትችላለህ ብለው በማሰብ ነው፡፡ ግን ስህተቱ ምን ላይ መሰላችሁ? ይኼን ኃጥያት እንዳይሠሩ መጠበቅ ነው የሚሻለው? ወይስ ቀድሞ ከቅዱስ ቁርባን ማራቅ ነው? ይኼ ሰው እኮ እስከሚሞት ድረስ እኮ አዋቂ ነው፣ ይቺ ሴት እስከምትሞት ድረስ አዋቂ ነች። የዕድሜ ደረጃዋ ይለያይ፤ የእድሜ ደረጃው ይለያይ እንጂ፣ በየዕድሜ ደረጃቸው ኃጢያት ከመሥራት አይቆጠቡም፡፡
ስለዚህ፤ ይልቅ ዋናው ነገር የኃጢያትን መሥመሩን መቁረጥ ነው፡፡ የኃጥያት ኃይል እንዳይተላለፍ ከሰው ሕይወት ላይ መስመሩን ማቋረጥ ነው፡፡ ልክ እንደ ኤሌክትሪክ መስመር ወይም እንደ ሰልክ መስመር ማለት ነው፣ ወይም እንደ ውኃ መስመር ማለት ነው፡፡ እሱን ማቋረጥ ነው፡፡ ያንን ያቋረጥነውን ነገር መልሰን እንዳንቀጥለው፣ እንዳንዘረጋው፤ በሚያስችል የመጨረሻ ውሳኔ መስመሩን ማቋረጥ ያለብን ኃጢያት የሚመጣበትን፣ በኃጢያት የምንወድቅበበትን፣ በኃጢያት የምንፈተንበትን፣ ኃጢያተኞች የምንሆንበትን፣ ከእግዚአብሔር ጋር በኃጢያት የምንጣላበትን እሱን መስመር ነው ማቋረጥ እንጂ ከቅዱስ ቁርባን ሰዎች እንዲርቁ፣ ቅዱስ ቁርባን መቀበልን እንዲያቋርጡ ማድረግ በደሉ ሁለተኛ ነው የሚሆነው፡፡ እምነታችንም ፍፁም የሚሆነውም እኮ በቅዱስ ቁርባን የምንቀደሰው ሕይወት እኮ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንኖርበት ምስጢር ነው፡፣ ዘለዓለማዊ ሕይወትን የምንወርስበት ነገር ነው፡፡ ሥጋዬን የበላ፣ ደሜን የጠጣ የዘላዓለም ሕይወት ያገኛል ነው የሚለው፡፡
ስለዚህ የዘለዓለም ሕይወት የምናገኝበትን ነገር እንድናቋርጥ በዕድሜ ክልል ከመወሰን ይልቅ አንድ ቀንም ጠቅሞን፣ አክብሮን የማያውቀውን ኃጢያት እንድናቋርጥ ነው ፡፡ እናም የለም እንዲህ ዓይነት ሥርዓት ወጣት ወንድ ሆነህ ኃጢያተኛ ሁን፣ ወጣት ሴት ሆነሽ ኃጢያተኛ ሁኚ የሚል ሕግ የለም፡፡ በዚህ ዘመን ኃጥያተኛ ሆናችሁ እንደፈለጋችሁ ሆናችሁ ስትመለሱ፣ ወይም ዕድሜህ ሲሸመግል፣ ዕድሜዋ ሲሸመግል፣ ጉልበቱ ሲደክም፣ ጉልበቷ ሲደክም ተብሎ የግድ የዕድሜ ክልል ስለገደባቸው ያንን ለመዱትን ኃጢያት ለመሥራት ከልባቸው በንስሐ ሕይወት ስለታውት ሳይሆን አቅማቸው ስለማይፈቅድ፣ ጉልበታቸው ስለማይችል ብቻ ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ይሆናሉ ብሎ በማሰብ ነው፡ ይኼ ደግሞ የክርስትና የመጨረሻ ድክመት ነው ፡፡ እግዚአብሔር ወጣቱን ይፈልጋል፣ እግዚአብሔር ህፃናቱን ይፈልጋል፡፡ ኃጥያታቸውን ብቻ ነው የማይፈልገው፡፡ ኃጢያትን ደግሞ ማቋረጥ ይቻላል፡፡ ሰው ኃጢያት የማይጠቅም ነገር መሆኑ በግልፅ እየታየው፤ ይኼ ሞት ነው እየተባለ፣ ይኼ ሲዖል ነው እየተባለ፣ ይኼ ጉድጓድ ነው እየተባለ፣ ይኼ ማዕበል ነው እየተባለ፣ይኼ ጥፋት ነው እየተባለ ዓይኑ እያየ የሚገባ ሰው የለም፡፡ ሞትንና ሕይወትን፣ ፅድቅንና ኩነኔን፣ ጨለማና ብርሐንን፣ በጎ ሥራን ክፉ ሥራን ለይቶ የማሳወቅ ጉዳይ ነው፡፡
ከዚህ አንፃር ጠያቂያችን ማወቅ ያለብዎት ለመቁረብ ዕድሜ አይወስንም፡፡ ከዚህ ቀደምም ደጋግመን ተነጋግረናል፡፡ ያው ሁሉም ሰው መቸስ ከራሱ ጊዜ አትርፎ ወደዚህ ፕሮግራም የሚመጣበት ጊዜውንም፣ ሁሉንም ነገር በደንብ መከታተል ስለማይቻል ይመስለናል እንጂ፤ ያልመከርንበት መስመር የለም፡፡ እንዲያውም የትምሕርታችን ማዕከል እኮ ዋናው ምስጢረ ቁርባን ነው፡፡ ከቅዱስ ቁርባን ከተለየን ከእግዚአብሔር ጋር እንደተለየን ማረጋገጫችን ይኼ ነው የመጨረሻው፡፡ በጣም የሚያሳዝን ነገር አለ፡፡ ሁሉም ሰው የሚደክምበት በእርግጥ ከነ ድፍረታችን፣ ከነ ኃጢያታችን እንድንቀርብ አይደለም፡፤ በዕድሜ ክልል ተፈቅዶ የሚሠራ ኃጢያት የለም፤ በዕድሜ ክልል እንዳንቆርብ የምንከለከልበት ምንም ዓይነት ሥርዓት የለም፡፡ ይኼንን በደንብ አድርጋችሁ አስተውሉ፡፡ በዕድሜ ክልል ተወስኖ እንድንሠራ የሚፈቀድልን ኃጢያት የለም፡፡ ሕፃንም ሳለን ፣ ወጣትም ሳለን፣ ጎልማሳም ሳለን፣ሽማግሌም ሳለን ኃጢያት እንዳንሠራ ሕገ እግዚአብሔር ይከለክለናል፡፡ በዚህ መካከል ደግሞ ተፈትነን የወደቅንበት ኃጢያት ካለ ሳናውል፣ ሳናሳድር፣ ለሥጋዊ ክብራችን ሳንጨነቅ፣ ሳንፈራም ሄደን ንስሐ መቀበል አለብን ይኼ ነው ሕጉ፡፡
የጥያቄውን መልስ በአጭሩ ስንደመድመው የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር በሌላ ክብር ወደ እርሱ እስከሚጠራን ድረስ ከቅዱስ ቁርባን፣ ከነፍስ ምግብ ርቀን ሕይወት ስለማይኖረን አንድ ቀን እንዳንለይ የእግዚአብሔር ሕግ ያዘናል፡፡
በመጨረሻም፥ ጠያቂያችንም ሆኑ የድረገፃችን አባላት አደራ የምንላችሁ ሌሎች ያቀረቡትን ጥያቄ መሰረት አድርገን በየቀኑ ጠዋት እና ማታ የምናስተላልፈውን ትምህርት እና ምክር በዚህ የዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የቴሌግራም ግሩፕ፥ ካሉበት ስፍራ ሆነው ቢከታተሉን መንፈሳዊ ህይወትዎን በልማድና በመጠራጠር ሳይሆን በእውቀትና በትክክለኛው መንገድ እንዲመሩ ያግዝዎታልና በአገልግሎቱ ዘወትር እንዲጠቀሙ እንመክራለን ፤ ለሌሎች ወገኖችም ሊንኩን ሼር እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።👇
በዚህ ሁሉ የመከረን፣ የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን አሜን፡፡
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾ስለ #ቅዱስ #ቁርባን እና #ዕድሜ
👉ጥያቄ፡- ለመቁረብ ዕድሜ ይወስነዋል ? ማብራሪያ ፈልጌ ነበር እባክዎ ?
መልስ፡ ጠያቂያችን የጠየቁን አጭር ጥያቄ ሲሆን፤ ይኽም ስለ ምስጢረ ቁርባን ነው ፡፡ ስለ ምስጢረ ቁርባን በጣም በብዙ ጥየቄዎች መነሻነት በዚሁ በዮሐንስ ድረገጻችን ብዙ ትምሕርት ሰጥተናል፡፡ ጠያቂያችን እሱንም በተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሆንዎት ሊያዩት እንደሚገባ እየመከርን አሁን ለጠየቁት ጥያቄ ግን በአጭሩ የሚከተለውን ምላሽ ልከንልዎታል፡፡
ለመቁረብ የዕድሜ ገደብ የለውም ፡፡ ምክንያቱም ወንድ ልጅ በአርባ ቀኑ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ፣ ሴት ልጅ በሠማኒያ ቀን የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ፣ ልጅነታቸውንም ያረጋገጡት በቅዱስ ቁርባን ስለሆነ፣ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ማንኛውም የእግዚአብሔር ልጅ በእሱ ፊት ሰው ሆኖ ለመኖር፣ ወይም ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ለመቀጠል የማይለየው፣ የማይተወው፣ የማያቋርጠው ነገር ቢኖር የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን፣ ክቡር ደሙን መቀበል ነው፡፡ የማይቋረጥ ሥርዓት ነው፡፡ እንግዲህ ስለ ዕድሜ ክልል ስናነሳ ከኃጢያት ጋር በተያያዘ የሰው ልጅ ወንዱም ለአቅመ አዳም፣ ሴቷም ለአቅመ ሔዋን ደርሳለች ብለን በልማድ እናቶቻችን፣ አባቶቻችን አንዳንድ ካሕናትም ቢሆን፤ ዕድሜሽ ገና ነው አትቆርቢም፣ ዕድሜህ ገና ነው አትቆርብም ማለት ምን ማለት ነው? ያኔ ለአካለ መጠን ደርሰሻል፣ ሴቷም የሴት ሥራ ትሠሪያለሽ፣ ወንዱም የወንድ ሥራ ትሠራለህ ፣ልትዘሙት ትችላለህ፣ ልትሰርቅ ችላለህ፣ ልትዋሽ ትችላለህ፣ ብቻ ከቅዱስ ቁርባን ሊያርቅህ የሚችለውን ኃጢያት ልትሠራ ትችላለህ ብለው በማሰብ ነው፡፡ ግን ስህተቱ ምን ላይ መሰላችሁ? ይኼን ኃጥያት እንዳይሠሩ መጠበቅ ነው የሚሻለው? ወይስ ቀድሞ ከቅዱስ ቁርባን ማራቅ ነው? ይኼ ሰው እኮ እስከሚሞት ድረስ እኮ አዋቂ ነው፣ ይቺ ሴት እስከምትሞት ድረስ አዋቂ ነች። የዕድሜ ደረጃዋ ይለያይ፤ የእድሜ ደረጃው ይለያይ እንጂ፣ በየዕድሜ ደረጃቸው ኃጢያት ከመሥራት አይቆጠቡም፡፡
ስለዚህ፤ ይልቅ ዋናው ነገር የኃጢያትን መሥመሩን መቁረጥ ነው፡፡ የኃጥያት ኃይል እንዳይተላለፍ ከሰው ሕይወት ላይ መስመሩን ማቋረጥ ነው፡፡ ልክ እንደ ኤሌክትሪክ መስመር ወይም እንደ ሰልክ መስመር ማለት ነው፣ ወይም እንደ ውኃ መስመር ማለት ነው፡፡ እሱን ማቋረጥ ነው፡፡ ያንን ያቋረጥነውን ነገር መልሰን እንዳንቀጥለው፣ እንዳንዘረጋው፤ በሚያስችል የመጨረሻ ውሳኔ መስመሩን ማቋረጥ ያለብን ኃጢያት የሚመጣበትን፣ በኃጢያት የምንወድቅበበትን፣ በኃጢያት የምንፈተንበትን፣ ኃጢያተኞች የምንሆንበትን፣ ከእግዚአብሔር ጋር በኃጢያት የምንጣላበትን እሱን መስመር ነው ማቋረጥ እንጂ ከቅዱስ ቁርባን ሰዎች እንዲርቁ፣ ቅዱስ ቁርባን መቀበልን እንዲያቋርጡ ማድረግ በደሉ ሁለተኛ ነው የሚሆነው፡፡ እምነታችንም ፍፁም የሚሆነውም እኮ በቅዱስ ቁርባን የምንቀደሰው ሕይወት እኮ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንኖርበት ምስጢር ነው፡፣ ዘለዓለማዊ ሕይወትን የምንወርስበት ነገር ነው፡፡ ሥጋዬን የበላ፣ ደሜን የጠጣ የዘላዓለም ሕይወት ያገኛል ነው የሚለው፡፡
ስለዚህ የዘለዓለም ሕይወት የምናገኝበትን ነገር እንድናቋርጥ በዕድሜ ክልል ከመወሰን ይልቅ አንድ ቀንም ጠቅሞን፣ አክብሮን የማያውቀውን ኃጢያት እንድናቋርጥ ነው ፡፡ እናም የለም እንዲህ ዓይነት ሥርዓት ወጣት ወንድ ሆነህ ኃጢያተኛ ሁን፣ ወጣት ሴት ሆነሽ ኃጢያተኛ ሁኚ የሚል ሕግ የለም፡፡ በዚህ ዘመን ኃጥያተኛ ሆናችሁ እንደፈለጋችሁ ሆናችሁ ስትመለሱ፣ ወይም ዕድሜህ ሲሸመግል፣ ዕድሜዋ ሲሸመግል፣ ጉልበቱ ሲደክም፣ ጉልበቷ ሲደክም ተብሎ የግድ የዕድሜ ክልል ስለገደባቸው ያንን ለመዱትን ኃጢያት ለመሥራት ከልባቸው በንስሐ ሕይወት ስለታውት ሳይሆን አቅማቸው ስለማይፈቅድ፣ ጉልበታቸው ስለማይችል ብቻ ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ይሆናሉ ብሎ በማሰብ ነው፡ ይኼ ደግሞ የክርስትና የመጨረሻ ድክመት ነው ፡፡ እግዚአብሔር ወጣቱን ይፈልጋል፣ እግዚአብሔር ህፃናቱን ይፈልጋል፡፡ ኃጥያታቸውን ብቻ ነው የማይፈልገው፡፡ ኃጢያትን ደግሞ ማቋረጥ ይቻላል፡፡ ሰው ኃጢያት የማይጠቅም ነገር መሆኑ በግልፅ እየታየው፤ ይኼ ሞት ነው እየተባለ፣ ይኼ ሲዖል ነው እየተባለ፣ ይኼ ጉድጓድ ነው እየተባለ፣ ይኼ ማዕበል ነው እየተባለ፣ይኼ ጥፋት ነው እየተባለ ዓይኑ እያየ የሚገባ ሰው የለም፡፡ ሞትንና ሕይወትን፣ ፅድቅንና ኩነኔን፣ ጨለማና ብርሐንን፣ በጎ ሥራን ክፉ ሥራን ለይቶ የማሳወቅ ጉዳይ ነው፡፡
ከዚህ አንፃር ጠያቂያችን ማወቅ ያለብዎት ለመቁረብ ዕድሜ አይወስንም፡፡ ከዚህ ቀደምም ደጋግመን ተነጋግረናል፡፡ ያው ሁሉም ሰው መቸስ ከራሱ ጊዜ አትርፎ ወደዚህ ፕሮግራም የሚመጣበት ጊዜውንም፣ ሁሉንም ነገር በደንብ መከታተል ስለማይቻል ይመስለናል እንጂ፤ ያልመከርንበት መስመር የለም፡፡ እንዲያውም የትምሕርታችን ማዕከል እኮ ዋናው ምስጢረ ቁርባን ነው፡፡ ከቅዱስ ቁርባን ከተለየን ከእግዚአብሔር ጋር እንደተለየን ማረጋገጫችን ይኼ ነው የመጨረሻው፡፡ በጣም የሚያሳዝን ነገር አለ፡፡ ሁሉም ሰው የሚደክምበት በእርግጥ ከነ ድፍረታችን፣ ከነ ኃጢያታችን እንድንቀርብ አይደለም፡፤ በዕድሜ ክልል ተፈቅዶ የሚሠራ ኃጢያት የለም፤ በዕድሜ ክልል እንዳንቆርብ የምንከለከልበት ምንም ዓይነት ሥርዓት የለም፡፡ ይኼንን በደንብ አድርጋችሁ አስተውሉ፡፡ በዕድሜ ክልል ተወስኖ እንድንሠራ የሚፈቀድልን ኃጢያት የለም፡፡ ሕፃንም ሳለን ፣ ወጣትም ሳለን፣ ጎልማሳም ሳለን፣ሽማግሌም ሳለን ኃጢያት እንዳንሠራ ሕገ እግዚአብሔር ይከለክለናል፡፡ በዚህ መካከል ደግሞ ተፈትነን የወደቅንበት ኃጢያት ካለ ሳናውል፣ ሳናሳድር፣ ለሥጋዊ ክብራችን ሳንጨነቅ፣ ሳንፈራም ሄደን ንስሐ መቀበል አለብን ይኼ ነው ሕጉ፡፡
የጥያቄውን መልስ በአጭሩ ስንደመድመው የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር በሌላ ክብር ወደ እርሱ እስከሚጠራን ድረስ ከቅዱስ ቁርባን፣ ከነፍስ ምግብ ርቀን ሕይወት ስለማይኖረን አንድ ቀን እንዳንለይ የእግዚአብሔር ሕግ ያዘናል፡፡
በመጨረሻም፥ ጠያቂያችንም ሆኑ የድረገፃችን አባላት አደራ የምንላችሁ ሌሎች ያቀረቡትን ጥያቄ መሰረት አድርገን በየቀኑ ጠዋት እና ማታ የምናስተላልፈውን ትምህርት እና ምክር በዚህ የዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የቴሌግራም ግሩፕ፥ ካሉበት ስፍራ ሆነው ቢከታተሉን መንፈሳዊ ህይወትዎን በልማድና በመጠራጠር ሳይሆን በእውቀትና በትክክለኛው መንገድ እንዲመሩ ያግዝዎታልና በአገልግሎቱ ዘወትር እንዲጠቀሙ እንመክራለን ፤ ለሌሎች ወገኖችም ሊንኩን ሼር እንዲያደርጉ እንጠይቃለን።👇
በዚህ ሁሉ የመከረን፣ የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን አሜን፡፡
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፦ #ቅዱስ #ቁርባን ለመቀበል የጋብቻ ሁኔታ ይወስነዋል? ለምሳሌ ፈት ብንሆን ጨርሶ ያላገባን ብንሆን አግብተንስ አጋራችን ፍቃደኛ ባይሆን ብትሆን?
መልስ፦ ጠያቂያችን፤ የአዲስ ኪዳን ቅዱስ ቁርባን የምንለው የክርስቶስ ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን ሲሆን ይሄን የምንቀበለው ደግሞ ወንድ ልጅ በ40 ቀን ሴት ልጅ በ80 ክርስትና ስንነሳ ሲሆን የታደልነውም ልዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የዘላለም ምግብ ነው። በመሆኑም ከዚህ መለየት ማለት በቁማችን መሞት ማለት ነው። ስጋ የስጋ ምግብን ካጣ በእርግጠኝነት የተወሰነ ሰአታትና እለታት ብንቆይ ያውም ለብዙዎች የሚቻል አይደለም እንጂ ቢሆን ግን ከዚያ በኋላ በህይወት መቀጠል አንችልም። ይሄ አንዱ ስጋዊ ህልውናችንን የምናጣበት የተለመደ የስጋ ደካማ ባህሪይ ነው። ነፍስም እንዲሁ የክርስቶስን ቅዱስ ስጋና ክቡር ደሙን ካጣች ሞተች ማለት ነው ወይም ገለናታል ማለት ነው። ስለዚህ ባይሆን እንኳን ይሄንን የዘላለም ህይወት በመመገብ የዘለአለም ህይወት የሚሰጠውን ጽዋ ለመጠጣትም እኛ መዘጋጀት ያለብን በምን አይነት ስርዐት እንደሆነ በምን አይነት መንፈሳዊ ዝግጅት እንደሆነ በሱ ላይ ያለን ነገር ክርስቲያናዊ ጸባይ እንዲሆን ታዘዝን ለማለት እንጂ በብዙ ማስፈራራት እና ምክንያት በማብዛት እንድንርቅ ለማድረግ የሚሰጥ ትምህርት ግን የለም።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደነገረን ሳይገባን ይህንን በእለተ አርብ ስለኛ ስለወዳጆቹ ሌላ በምንም ሳይሆን ስጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ የሰጠን ህይወት እዳ እንዳይሆንብን ያለው፤ ‘ሳይገባን’ ያለው ቃል ሁል ጊዜ በንስሐ የተዘጋጀ ህይወት እንዲኖረንና በነፍስ ጉዳይ አማካሪ የሆኑንን እግዚአብሔር ስለእኛ አገልጋዮችና የመንጋው እረኛ ያደረጋቸውን የቤተክርስቲያን አባቶችን መምህራንን እያማከርን ስህተት እንዳይመጣብን ሁልጊዜ ተዘጋጅተን እንድንቀለው ታዘዝን እንጂ ከዚህ ለአንድቀንም እንድንለይ የታዘዝንበት አጋጣሚ የለም። ስለዚህ ከጋብቻም በፊት ሰው ብቻውን ከኖረ ከላይ እንደገለጽነው ክርስትና ከመነሳታችን ጊዜ ጀምሮ ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቀንን ነውርና ኀጢአትን ሳንሰራ እየተቀበልን መቀጠል አለብን። ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቀንን ነውርና ጥፋት ሰው ሁሉ ያውቃል፤ የኀጢአት አይነቶችን ከጥቃቅን እስከ ከፍተኛ ደረጃ የማያውቅ ሰው የለም፤ እኛም በድረገፃችን ዋና ዋናዎቹን የኀጢአት አይነቶች በዝርዝር ለማስቀመጥ ሞክረናልና አሁን መዘርዘር አስፈላጊ ባይሆንም በዚያ እንድትመለከቱት ግን እንመክራለን። ለምሳሌ ነፍሰ ገዳይነት፣ ዘማዊነት ሴሰኝነት እነዚህን የመሳሰሉ ኀጢአቶች ከቅዱስ ቁርባን ሊያርቁ ይችላሉ። ሰው እኮ እድሜ ልኩን ሳያገባምኮ ከዚህ አለም ግብር እራሱነ አግልሎ ቆራቢ ሆኖ መኖር ይችላል፤ ወይም ደግሞ አካለ መጠን ከደረሱ በኋላ ወንድም ቢሆን ሴት ወደ ንስኀ ህይወት በመምጣት ወንድም እሱን የምትመስል መርጦ ሴትዋም እሷን የሚመስል መርጣ ይጋቡና በቅዱስ ቁርባን ይቀጥላሉ ማለት ነው። ይሄም እድል ሳይገጥማቸው በቅዱስ ቁርባን ሳይጋቡ የቀሩ ሰዎች ደግሞ እነሱም ወደ ንስሐ ቀርበው እንዲሁ ያንን ከጊዜ በኋላ ያጡትን ወይም ያቋረጡትን ቅዱስ ቁርባን ያስቀጥላሉ ማለት ነው። ቤተክርስቲያን ለሁሉም ማስታረቂያ አላት ከፈጣሪዋ።
ስለዚህ ጠያቂያችን ቅዱስ ቁርባንን ለመቀበል ከላይ እንደገለፅነው የጋብቻ ሁኔታ ብቻ አይወስነውም ፤ እስከ ጋብቻ ድረስ በሚኖረንም ቆይታ ከቅዱስ ቁርባን እንድንለይ ቤተክርስቲያን አንድም ቀን አታዝም። ምናልባት ሰዎች በልማድ ያመጡት መዘዝ ነው እንጂ መካሪዎች አስተማሪዎችም ቢሆን በእግዚአብሔር ስርአት ሳይሆን በሕዝብ ስርአት ተውጠንና ተስማምተን፥ ዝም ብለን እኛም ቢሆን ከቅዱስ ቁርባን እርቆ የሚኖረውን ህዝብ ተቀብለን አባት ሆነን የመቀጠላችን ነገር ክብር ሳይሆን ለእኛ ትልቅ ውርደት ነው። ምክንያቱም የመጀመሪያ ዋና አና ተቀዳሚ ተግባር ክርስቲያን የሆነ ሁሉ የክርስቶስን ስጋ እና ደም ይቀበላል። አሁን እንደ እኛ አማናዊ ቅዱስ ስጋው ክቡር ደሙ አድርገው የማያምኑና መታሰቢያ የሚያደርጉ ሌሎቹ በክርስትና ውስጥ ነን የሚሉ በአለም ዙሪያ ያሉ ወደ ቸርች በመጡ ቁጥር ያንኑ መታሰቢያ አድርገው የሚያስቡትን ሳይቀበሉ አይሄዱም በተአምር። ምናልባት የእኛ ቤተክርስቲያን እንደዚህ ቅዱስ ቁርባንን በመታሰቢያነት ሳይሆን እንዲያው በድፍረት ሳይሆን በትክክለኛው በእለተ አርብ ፈጣሪዬ በዚያ ሁሉ መከራ ብዛት ስለእኔ ብሎ የቆረሰው ቅዱስ ስጋው ክቡር ደሙ ስለሆነ አማናዊ ቅዱስ ስጋው አማናዊ ክቡር ደሙ ነው ብለን በፈሪሃ እግዚአብሔር ሆነን በክርስቲያናዊ ስነምግባር ሆነን በንስሐ ህይወት ኀጢአታችንን ታጥበን የምንቀበለው ስለሆነ በሌሎቹ አንፃር እማይታይ ቢሆንም ነገር ግን በዚህ አንጻር ለማስረዳት እንጂ ከእሱ እንድንለይ አልታዘዝንም።
ስለዚህ ጠያቂያችን ከጋብቻም በፊት በጋብቻም ጊዜ ከጋብቻም በኋላ እሚያስቀረንና የሚያርቀን የራሳችን ተግባር ነው። ለማጠቃለል፤ ለጥያቄው መልሱ ትልቁ ነገር ከዚህ የምንለይበት ነገር ካለ የራሳችን ድክመት አንዱ የትምህርትና የግንዛቤ እጥረት ነው ወይም እምናውቀው ኀጢአትና በደል አለ ማለት ነው እንጂ የምንከለከልበት ምክንያት የለም ማለት ነው።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ፦ ብዙዎቻችን በልጅነታችን ቆርበን እድገን ለአቅመ አዳም/ሔዋን ስንደርስ እናቆማሐን፡ንሰሀ እና #ቅዱስ #ቁርባን ደግሞ ወሳኝ ነገር ነው፡ ስጋዬን ያልበላ ደሜን ያልጠጣ የዘላለም ህይወት የለዉም ይላል፡ስለዚህ በልጅነታችን የተቀበልነው በቂ ነው ወይስ በንሰሀ ታጥበን መቁረብ ግድ ይለናል?
መልስ፦ ማንኛውም ክርስቲያን በ40 ቀን በ80 ቀን በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጅነት ከተቀበሉ ጀምሮ ከቅዱስ ቁርባን እንዲለዩ አይፈቀድላቸውም። ቅዱስ ቁርባን ለነፍሳችን ዘለአለማዊ ህይወት በስጋዊ ህይወታችን ደግሞ በበረከት እና በእግዚአብሔር አጋዥነት እንድንኖር ስለሚረዳን በእግዚአብሔር ፈቃድ በሞት እስከምንጠራበት ዘመን ድረስ ቅዱስ ቁርባን መቀበል ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው። በመንፈሳዊ ህይወታችን ውስጥ በሃይማኖትም በምግባርም ያበረከትናቸው የትሩፋት ስራዎች ሁሉ ማሳረጊያውና መደምደምያው ቅዱስ ቁርባን ነው። ስለዚህ ጠያቂያችን ምናልባት በስራ ብዛት የማንበብ እድል ካልገጠመዎ በስተቀር ስለቅዱስ ቁርባን እጅግ ሰፊ ትምህርት ማስተላለፋችንን እናስታውሳለንና እሱንም መልሰው መላልሰው ቢመለከቱት ለጥያቄዎ ይበልጥ መልስ ያገኛሉ። በዋናነት አሁንም መረዳት ያለብዎት የሰው ልጅ በራሱ ድካም የኀጢአት ሸክም ሲበዛበት ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ ድፍረት እና ብቃት ስለሚያጣ ማንም ሳያርቀው ራሱን ከቅዱስ ቁርባን እያራቀ ስለሚሄድ የነፍስ ረሃብና መታረዝን ያስከትላል እንጂ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን ማንኛውም ክርስቲያን ከህፃንነቱ ጀምሮ እስከ መጨረሻ የእድሜ ዘመኑ ከቅዱስ ስጋውና ከክቡር ደሙ እንዳይለይ ዘወትር ታስተምራለች ትመክራለች። እኛን ዘወትር ኀጢአት የሚያሰራን ጠላታችን ዲያብሎስ ስለሆነ የዘላለም ህይወት እንዳናገኝ ራሳችንን በኀጢአት ወጥመድ እየጠለፈ ወደ ዘለአለማዊ ሞት እንድንወድቅ ያስገድደናል ማለት ነው። ስለዚህ ጠያቂያችን ቅዱስ ቁርባንን መቀበል የማይቋረጥ ቀጣይነት ያለው መንፈሳዊ ስርአት እንደሆነ እንዲረዱት ይህን መልዕክት እንዲደርስዎ አድርገናል።
ስለ ቅዱስ ቁርባን ድረገጻችን ላይ ያንብቡ፦ https://yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን/
በቅዱስ ቁርባን ተወስነው ለሚኖሩ
👉🏾👉🏾👉🏾 ስለ ምስጢረ #ቅዱስ #ቁርባን
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን፤ በርዕሱ የተጠቀሰውን ጠቃሚ ትምህርትና ስለሆነ አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።
1. በሥጋ ወደሙ ተወስነው ለሚኖሩ
«እስከ መጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል» ማቴ 24
የክርስትና ሕይወት ግብ እስከ መጨረሻ ታምኖ መገኘት ነው: እስከ መጨረሻ ታምኖ ለመገኘት ደግሞ አይነት የማይገኝለት ጾናት ነው፡። ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ የነገራቸው ይህንኑ ነው: ክህነትን ለሚያህል ሥልጣን ወንጌልን ለሚያህል አገልግሎት ጠርቶ ወደ ዓለም ሲልካቸው የሚጠብቃቸው ለእግራቸው የአበባ ምንጣፍ ለአንገታቸው የአበባ ጉንጉን ሳይሆን ለሰውነታቸው እሳት ለአንገታቸው ስለት ነውና በሚገጥማቸው በማናቸውም መከራ የተሰጣቸውን እንዳይጥሉ እስከ መጨረሻው የሚታገስ እርሱ ይድናል ብሏቸዋል ።
አንተም ልብ ልትለው የሚገባህ ዓለሙን ያሸነፈው ጌታህ ካንተ ጋር መሆኑን ነው በብዙ ተጋድሎ በእግዚአብሔር ፍቅርና ችርነት በቅተህ በሥጋ ወደሙ መወሰንህን በየትኛውም ጊዜና ቦታ አትዘንጋው የራስህም አክሊል እንዳይወድቅ ተጠንቀቅ፡፡
ቀሪ እድሜህ በጽናት እንዲፈጸም በዚህች ምድር ላይ የቀረህና የሚያጓጓህ ነገር እንደሌለ እራስህን አሳምን እርሱ ካንተጋር ነውና ሁሉ ካንተ ስለመሆኑ አትጠራጠር፡ ሰርቶ ለማግኘት፣፤ ነግዶ ለማትረፍ፤አርሶና ዘረቶ ለማምረት፣ ተምሮ ለማወቅ፣ አጭቶ ለማግባት፣ አግብቶ ለማውለድ፣ ወልዶ ለማሳደግ፣ አሳድጐ ለመዳር፣ የማትከለከልና እንዲያውም እነፒህን ቀንበሮች ብቻህን እንዳትሸከም ኑሮህን ሁሉ በበረከት እንዲያልፍ አምላክህ ካንተ ጋር መሆኑን በማሰብ ትምክህትህ በእግዚአብሔር ላይ ሆኖ ህጉንና ሥርዓቱን ጠብቅ በዚህ ሁሉ አምላክህ ራስ እንጂ ጅራት አያደርግህም /ዘለ. 26፥3/ የሰማያት በረከትም ሁሉ በቤትህ በልጆችህና በንብረትህ ላይ ይሆናል።
የዲያቢሎስ ውጊያ በንቃት ትከታተለው ዘንድ የእግዚአብሔር ቃል የሚመክረውን ምክር ሁሉ ተጠቀምበት የሚገጥምህን ፈተና ቸል አትበል ሁል ጊዜ ከንስሀ አባትህ ጋር መነጋገንር አትተው የሚገጥምህን ሁሉ ለቤተክርስቲያን ንግራት /ማቴ. 18፥17/ ከዚህ ከበቃህበት ክብር በኋላ ከዚህ ክብር ሊያስወጣህ የሚችል ለሕይወትህ ተቃራኒ የሆኑ ልዩ ቦታና ልዩ ተግባር በፊትህ የተረገጠ እንዲሆን ሁል ጊዜ ጌታ እንዳለው ጸልይ «ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ» /ሉቃ. 22-40፥46/
2. በሥጋ ወደሙ ለመወሰን ለተነሳሱ
«የመዳን ቀን አሁን ነው» /2ቆሮ. 6፥2/
በሥጋ ወደሙ ለመወሰን የተነሳሳን መነሳሳታችን ወደ ዝግጅት እንዲደርስ ዝግጅታችን ፍሬ እንዲያፈራ የሐዋርያት ቃል ልብ ልንል ይገባል የመዳናችን ቀን ዛሬ መሆኑን።
ማንኛውም ክርስቲያን በውስጡ ያደረው ቅዱስ ቁርባንን የመቀበል ፍሳጐት የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ሊሆን ይገባል ለዚህም ደግሞ ለምን መቀበል ፈለግሁ ስለምቀበለው ምን ያህል ተረድ ቻለሁ ከተቀበልኩ በኋላ የሚጠብቀኝ ሕይወት ምን ይመስሳል የሚሉትንና መሰል ጥያቄዎችን የመመለስ ብቃት እንዲኖረው ወደ ቡቁ ዝግጅት ራሱን ማድረስ ይኖርበታል ይህ ደግሞ የጸና አቋም እንዲይዝ ያደርገዋል ።
ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ አለ «ጌታ ሆይ ወደ ማን እንሄዳለን» /ዮሐ. 6፥68/ ይህንን አቋሙን የገለጠው ከክርስቶስ የሚገኘውን ዘላአለማዊ ድህነት ላለማጣት ነው ቀጥሎም እንዲህ በማለት የተናገረው ቃል ያረጋጋጥልናል «አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ» /ዮሐ. 6፥68/ ብዙዎች ግን «ሥጋዬ አውነተኛ መብል ደሜ እውነተኛ መጠጥ ነው» የሚለውን የሕይወት ቃል ሸሹ ይህ ሰው ሥጋውን እንበላ ዘንድ ደሙን እንጠጣ ዘንድ እንዴት ሊሰጠ ን ይችላል የሰው ሥጋ ቢበሉት የሰው ደም ቢጠጡት ደዌ እንጂ እንዴት ሕይወተ ሥጋ ወነፍስ ይሆናል እያሉ በእነርሱም ላይ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ተጽፏል «ከዚህም የተነሣ ከተከተሉት ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም፡::> /ዮሐ. 6፥66/
እንደዚሁ አንተም ወደ ኋላ እንዳትመለስ ለሥጋ ወደሙ ያለህ መነሳሳት በምኞት ብቻ አይቀር መነሳሳትህ ከሥጋና ከደም ሃሳብ የተነሳ አይሁን ራስህን ለቃሉ ከማቅረብህ ከማስገዛትህ እና ከምክረ ካህን የተነሳ ይሁን፡፡
ወደ ቅዱስ ቁርባን ብትቀርብ እንዲህና እንዲያ ትሆናለህ እያለ ከጆሮህ ሥር ለሚያንሾካሹክ ሰይጣን እድል ፈንታ አትስጠው ሰዎችንም ተጠቅሞ የሚያደርገውን ጉትጐታ ቸል በለው ይልቁ ንም በጸና እምነት ለቅዱስ ቁርባን ዝግጅት ራስህን እኢእያነሳሳህ «አንተ ሰይጣን ከኋላዬ ዞር በል» በለው:፡:
3. ከስጋ ደሙ እርቀው ለሚኖሩ
«ለቤተክርስቲያን ንገራት» /ማቴ. 18፥17/
ማንኛውም ክርስቲያን ስለ ቅዱስ ቁርባን ቢረዳ ከቅዱስ ቁርባን አይሸሽም፡፡ አንድን ሰው ለምን ሥጋ ወደሙ አትቀበልም? ብንለው መልሱ ጠልቼው መሰለህ ይህ ይስተካከልልኝ እንዲህና እንዲያ ያለ ችግር ስላለብኝ እንጂ ይላችኋል የእግዚአብሔር ቃል ለዚህ መልስ አለው መልሱም ይህ ነው:: «ለቤተ ክርስቲያን ንገራት» /ማቴ. 18፥17/
በዚህች በያዝናት ዓለም ላይ ያለ ችግር ለማለፍ የሚያስቡ ሳዎች ሁሉ ልዩ በሆነ የዲያቢሎስ ፈተና ላይ ወድቀዋል ምክንያቱም ይህ አሳባቸው ከአሳብ በላይ አይዘልም እንዲያውም ክርስቲያኖች በዓለሙ ዘንድ እንደአምላክቸው ተጠልተው ተንቀውና ተሰድበው መኖራቸውን መዘንጋት የለባቸውም ቃሉ እንዲል «ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ስለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል» ዮሐ. 15፥18/
ስለዚህ ማናቸውንም ችግራችንን ወደ እግዚአብሒር ላለማቅረብ ምክንያት የምናደርግ ከሆነ ስህተታችን እጅግ ከሚባለው በላይ ነው: በአርግጥ ሕይወታችን የተዘበራረቀና ለእግዚአ ብሔር መቅረብ የማይገባው መስሎ ሊሰማን ለቤተክርስቲያን ልንነግራት በትምህርቷና በምክሯ ራሳችንን ከችግር ልናላቅቅ ይገባናል እንጂ በመሸሽ መኖራችን እግዚአብሔርን ከመፍራታችን የተነሳ የመነጨ አይደለም፡፡
ማንም ሰው ወደ እግዚአብሔር ሊቀርብና የዕለት ተዕለት ሕይወቱ እግዚአብሔርን በማምለክና በማስደሰት ላይ የተወሰነ አንዲሆን የሚያደርገው ቃሉ የገባውን ያህል ነው እንደዚሁ ቅዱስ ቁርባንን በመቀበል ለክብር የመዘጋጀቱ ሃሳብ በክርስቲያኑ ውስጥ ሊጸነስ የሚችለው የታመነውን ያህል ነው::
አምላክህ ታደርገው ዘንድ ያዘዘህንና ትልቁን የድህነትህን ጉዳይ እስከ መቼ እርቀህና ስለ እርሱ ሳታስብ ትኖራለህ፡ይልቁንስ የራቀህን ሁሉ መቋቋም ያልቻልከው ብቻህን ከመሆንህ የተነሳ እንደሆነ አውቀህ ወደ አምላክህ ቅረብ «ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ›አትችሉምና» /ዮሐ. 15፥5/ ይልቁንስ በጊዜያዊነት በእንግድነት የምትኖርበት የዚህች ዓለም ኑሮ ሳይፈጸም ሥጋህ ወደ አፈር ነፍስህም ወደ ሰጣት ወደ እግዚአብሔር ሳትመለስ የዚህ ኪዳን ባለቤት ሁን «የሰው ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሳዋለሁ፡፡» /ዮሐ. 6፥53/ /መክብብ 12፥7/
ምንጭ፦ “ለቅዱስ ቁርባን እንድበቃ ምን ላድርግ?”
ከ መ/ም የሺጥላ ሞገስ- 2014

👉ጥያቄ፡- ሥጋ ወደሙን (#ቅዱስ #ቁርባን) እየተቀበልኩ ነበር ያለሁት ጊቢ ጉባዔ ነበርኩ፤ አሁን ግን ተመርቄ ሥራ ፍለጋ ዘመድ ጋር ነኝ፡፡ ባለብኝ የሕይወት ጫና ምክንያት አሁን መቀበል አልቻልኩም አቋረጥኩት አሁን ምን ይመክሩኛል አባታችን?
መልስ፡- ጠያቂያችን ቅዱስ ቁርባኑን ለመቀበል የሚያደረጉትን ሁሉ ቅድመ ሁኔታዎች አሟልቶ ለመፈጸም ያላስቻለኝ ምክንያት አለ በማለት ከሆነ፤ እግዚአብሔር የማያውቅልን አንዳችም ችግር የለም፡፡ ግን ከተቀደሰው ሕይወታችን፣ ከተቀደሰው ቅዱስ ቁርባናችን የሚያርቀን ኃጢያት ከሠራን፣ ይሔ የሁላችንም አንገት ያስደፋል፡፡
የእኛ ከቅዱስ ቁርባን መለየት በኃጢያት ከሆነ የቁም ሞት ነው የሚሆነው፡፡ እንደገና ከቅድስና፣ ከክብር፣ ከልዕልና ወደ ውርደትና ወደ ጉስቁልና ተመልሰን፣ በዚህ ዓይነት ወድቀን ስንታይ እኛን ብቻ ሳይሆን የሚያሳፍረን፣የሚያሳዝነን፣ የሚያሳቅቀን እግዚአብሔር በእኛ ሊያዝንብን፣ ሊያፍርብን ይችላል፡፡
በዚህ በወጣትነት ዘመን ሥጋም ወደ አፈርነት ሳይመለስ፣ ነፍስም ደግሞ ወደ እግዚአብሔር ሳትጠራ፣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ ይላልና ጠቢቡ፤ ስለዚህ ገና በአርባ፣ በሰማኒያ ቀን የእግዚአብሔር ልጅ ሆነን የታተምንበትን የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውን፣ ክቡር ደሙን ባለማቋረጥ መቀጠል እንዴት ዓይነት ጸጋ፣ እንዴት ያለ ሐብት ነው፣ ይሔንን ሊያሳጣን የሚችል ሰይጣን ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምንም ዓይነት ሐሳብ ሊሆን አይችልም፡፡ የሌላ ምንም ዓይነት ለዚህ በጎ ነገር ጠላት አንድ ብቻ ነው፡፡ ዲያቢሎስ ነው፡፡
የነበረንን የቅድስና ሕይወት አስወጥቶ ነውረኞች፣ ኃጢያተኞች፣ በደለኞች አድርጎ ከዚሁ በልተነው፣ ከማያስርበን፣ ጠጥተነው ከማያስጠማን፣ የዘላለም ሕይወት ከምናገኝበት ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቀን የጠላታችን የሰይጣን እኩይ ተግባር ካልሆነ በስተቀር፣ሌላ ሊያርቅ የሚችል የለም፡፡ ይሔ በጊዜያዊነት አንድ ሰው በየቀኑ፣ በየወሩ፣ በየሁለት ወሩ፣ በየሦስት ወሩ፣ ቅዱስ ቁርባን የሚቀበል ከሆነ በዚያ መካከል ሁልጊዜ ንጽህ ጠብቆ ነው፡፡ ሰውነቱን ከኃጢያት አርቆ ነው የሚቀጥለውና፣ ምናልባት በሥራ ጫና፣ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት፣ በዚህ ከሆነ የተፈጠረው ክፍተት እኔ የምፈራው፣ የምሠጋው ሁልጊዜ ስለ ሕዝቤ፣ ስለ ወገኔ፣ ስለ እግዚአብሔር ሰዎች ሁሉ የሚያሳስበኝ፣ ሁላችንም በሕይወታችን ፈተና ስላለብን ከቅድስና ሕይወት በኋላ ሌላ የምንረክስበትን ሥራ እንዳንሠራ እንጂ፤ ይሔማ እግዚአብሔር የሚያውቅልን፣ የሚረዳልን፣ ስለሆነ ጠያቂያችን የሚስያጨንቅ ነገር የለም ፡፡
እርስዎ በየትኛው እንደተፈተኑ፣ አሁን ግን ቅዱስ ቁርባንን በተለመደው ሥርዓት መሠረት እንዳይቀበሉ የከለከልዎት ነገር ምን እንደሆነ በውስጥ መስመራችን አግኝተውን እንደሚያስረዱን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የእርስዎም የጥያቄዎ መልስ የሚሆን ነገር አሁን ባብራራሁት መሠረት ይሆናል፡፡ ምናልባት ከቅዱስ ቁርባን የራቁበት መንገድ ኃጢያት ከሆነ እኛም እናዝናለን፣ የእርስዎም ሕሊና እረፍት አያገኝም፡፡ የመጨረሻው የክብር ደረጃ ይሔ ነውና፣ የመመረጥ ደረጃ ነውና፣ የቅድስና ደረጃ ነውና፣ ከዚያ ክብር፣ከዚያ ልዕልና፣ ከዚያ ቅድስና ወርደን ዳግም የምንቆሽሽበት፣ በኃጢያት የምንወድቅበት ፈተና ከገጠመን ደግሞ ለእርስዎ ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ሊያሳዝን ስለሚችል እግዚአብሔር ይጠብቅዎታል፣ ከዚህ ፈተና ይታደግዎታል ብለን እናምናለን፡፡
እንዳልኩትም በውስጥ አድራሻችን ሲያገኙን ይነግሩናል፡፡ ምክሩ ለሁሉም ሰው ጠቃሚ ስለሆነ ትከታተሉት ዘንድ በእግዚአብሔር ሥም አደራ እላለሁ፡፡
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንም ሼር ያድርጉ፡-https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ #1፦ አባ በፊት #የቆረበ ሰው ከ #ቅዱስ #ቁርባን 3ወር ቢርቅ ማለት ቢተው ምን ማድረግ አለበት?
👉ጥያቄ #2፦ አንድ ሰው ብቻውን ቁርባን ተቀብሎ ወይም ተቀብላ በዝሙት ቢወድቅ ተመልሶ መቁረብ ይችላን/ች/ እስከ ስንት ጊዜ ነው?
መልስ፦ ስለ ቅዱስ ቁርባን የጠየቁን አባላቶቻችን ሆይ፤ በመሰረቱ ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በ40 ቀን እና በ80 ቀን የእግዚአብሔርን ልጅነት በጥምቀተ ክርስትና አግኝቶ በቅዱስ ቁርባን ከታተመበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መጨረሻ የዘመኑ ፍፃሜው ድረስ ከቅዱስ ሥጋውና ከክቡር ደሙ መለየት እንደሌለበት ክርስቲያናዊ ግዴታውም እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። ይህም በቅዱስ መፅሐፍ በግልፅ ታዟል። ምክንያቱም የጌታን ቅዱስ ሥጋ ካልበላን ክቡር ደሙን ካልጠጣን የዘለዓለም ህይወት የለንም። ሰው በሥጋው በህይወት ለመኖር ዘወትር ለስጋው ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ በነፍሱም የዘላለም ህይወት ለመውረስ የነፍሳችን ምግብ ቅዱስ ቁርባን ስለሆነ ነፍሳችን ደግሞ ቅዱስ ቁርበንን ካጣች እንደሞተች ወይም ህይወት እንደሌላት ማመን ያስፈልጋል።
ይሁን እንጂ ቅዱስ ቁርባን በሰው ህይወት ሲገለፅ በህፃንነት እድሜ ደረጃ ያሉ ክርስቲያኖች ሲቆርቡ ቆይተው አካለ መጠናቸው ወደ አዋቂነት ሲደርስ ይበልጥ ስለሚስጥረ ቁርባን ተምረውና አውቀው መቀጠል ሲገባቸው፤ ይባስ ብለው ቅዱስ ቁርባን እንደማይጠቅም በማሰብ ይሁን ባለማወቅ ባይገባንም ከቅዱስ ቁርባን የሚርቁ ብዙዎች ናቸው። ይሄም ነገር የቤተክርስቲያን አባቶች በእግዚአብሔር ቤት ዘንድ የሚያስጠይቃቸው የክህነት ሃላፊነት ነው። ምእመናንም ቢሆኑ የቅዱስ ቁርባንን ዘለዓለማዊ ህይወትነቱ እየተነገራቸው እያወቁና እየተረዱ ከቅዱስ ቁርባን የሚርቁ ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድ ይጠብቃቸዋል።
ስለዚህ ጠያቂያችን በዚህ የመነሻ ትምህርት ትክክለኛውን ሃሳብ በአጭሩ ከገለጽንልዎ እርስዎ ወደአቀረቡት ጥያቄ ስንመጣ፤ ምንም እንኳን የሰው ልጅ በልዩ ልዩ ኅጢአት የመወደቁ ሁኔታ የደካማ ሥጋ ባህሪ ቢሆንም በሰራነው ኅጢአት ተፀፅተን ወደ ንስኅ ህይወት ተመልሰን ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል የሚለክለን ህግ ግን የለም። ጠያቂያችን እንዳሉት ቅዱስ ቁርባን ሲቀበሉ ቆይተው በመሃከሉ በዝሙት ተሰናክለው ከቅዱስ ቁርባን ከራቁ ወይም ርቀው ከቆዩም አሁን ማድረግ ያለብዎት ፦
1ኛ የክርስቶስ ሥጋና ደሙ ከኅጢአት የሚያፀዳና የሚቀድሰንና የሚያነፃን እንጂ የሚያርቅ ስላልሆነ በኅጢአት መውደቆትን ቢያምኑም በንስኅ ተመልሰው ሥጋ ደሙን የመቀበሉን ስርዓት እንደገና መቀጠል አለብዎት።
በ2ኛ ደረጃ ሚስት ለማገባት እቅድ ካለዎት በሥጋ ህይወት ውስጥ ባይገደዱበትም እንደ መንፈሳዊነት ግን ወደ ትዳር ህይወት ሲገቡ በቅዱስ ቁርባን ቢሆን በሥጋም ሆነ በነፍስ በረከትንና ክብሮትን ያበዛዋል።
በ3ኛ ደረጃ ማግባት ካልፈለጉም ስለሰሩት ኅጢአት በንስኅ የኅጢአት ስርየት በማግኘት ብቻዎትን በቁርባን ተወስነው መኖር ይችላሉ።
ነገር ግን በተደጋጋሚ የሚፈተኑበት በደል ካለ ለጊዜው መቁረብዎን አቁመው ወደ ንስኀ አባትዎ ቀርበው የፈጸሙትን በደል ከተናዘዙ እና ንስኀዎትን ከጨረሱ በኋላ ለመቁረብ መቀጠል ይችላሉ። ምክንያቱም አንድ ሰው ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ እዳ በደል እንዳይሆንበት አስቀድሞ ከኀጢአት እና ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ ከሚከለከልባቸው ጥፋቶች መራቅ አለበት። ምክንያቱም ቅዱስ ቁርባን ከተቀበለ በክርስቲያናዊ ህይወት ውስጥ የመጨረሻው ክብርም ላይ የደረሰ ሰው ነውና፤ ይሄንን ታላቅ ክብር በማቃለል ተመልሶ የማይገባውን ነውር መፈፀም ማለት ግን ታጥቦ ጭቃ እንደማለት ይቆጠራልና ተመልሰን ንስኀ መግባት ብቻ ሳይሆን የንስኀውም ደረጃ እጥፍ ድርብ ሊሆን እንደሚችል ተገንዝበን ራሳችንን በመግዛት በምግባርና በሃይማኖት ጸንተን ለመኖር መታገል አለብን፤ በኀጢአት ከወደቅንም ቶሎ በንስኀ ልንነሳ ያስፈልጋል። በመሆኑም ለስንት ጊዜ ላሉት በመሰረቱ ጥፋቱን በመደጋገም ሁል ጊዜ በንስኀ እመለሳለሁ በሚል መንፈስ መሄድ እንደሌለብን የቤተክርስቲያን ቀኖና ይደነግጋል። ዋናው ቁም ነገር ግን ማንኛውም ክርስቲያን በምንም ይሁን በምን ከቅዱስ ቁርባን ላለመለየት በየጊዜው መንፈሳዊ አላማውን በማጽናት መታገል እንዳለበት እንመክራለን።
ለሁሉም ነገር ግን ስለ አንቀፀ ንስኅ ጠንቅቀው የሚያውቁ የቤተክርስቲያን አባቶች (ሊቃውንት) ሁልጊዜ በማነጋገርና በማማከር ትምህርት እያገኙ ማንኛውንም ነገር እንደ ስርዓቱና እንደ ህጉ ማስቀጠል የሚችሉበትን ፕሮግራም እንዲያደርጉ ይህን አጭር መልእክት ለእርስዎ እና ለዮሐንስ ንስኅ ድረገፅ መንፈሳዊ ፕሮግራም ተከታታይ አባሎቻችን ሁላችሁም አንብባችሁ ትረዱት ዘንድ መልዕክቱ እንዲደርሳችሁ አድርገናል።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ፦ አንድ ሰው ብቻውን #ቁርባን #ተቀብሎ ወይም ተቀብላ #በዝሙት #ቢወድቅ ተመልሶ መቁረብ ይችላን/ች/ እስከ ስንት ጊዜ ነው?
መልስ፦ ስለ ቅዱስ ቁርባን የጠየቁን አባላችን ሆይ፤ በመጀመሪያ ከዚህ ቀደምም ደጋግመን እንደገለፅነው ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በ40 ቀን እና በ80 ቀን የእግዚአብሔርን ልጅነት በጥምቀተ ክርስትና አግኝቶ በቅዱስ ቁርባን ከታተመበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መጨረሻ የዘመኑ ፍፃሜው ድረስ ከቅዱስ ሥጋውና ከክቡር ደሙ መለየት እንደሌለበት ክርስቲያናዊ ግዴታውም እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። ይህም በቅዱስ መፅሐፍ በግልፅ ታዟል። ምክንያቱም የጌታን ቅዱስ ሥጋ ካልበላን ክቡር ደሙን ካልጠጣን የዘለዓለም ህይወት የለንም። ሰው በሥጋው በህይወት ለመኖር ዘወትር ለስጋው ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ በነፍሱም የዘላለም ህይወት ለመውረስ የነፍሳችን ምግብ ቅዱስ ቁርባን ስለሆነ ነፍሳችን ደግሞ ቅዱስ ቁርበንን ካጣች እንደሞተች ወይም ህይወት እንደሌላት ማመን ያስፈልጋል።
ይሁን እንጂ ቅዱስ ቁርባን በሰው ህይወት ሲገለፅ በህፃንነት እድሜ ደረጃ ያሉ ክርስቲያኖች ሲቆርቡ ቆይተው አካለ መጠናቸው ወደ አዋቂነት ሲደርስ ይበልጥ ስለሚስጥረ ቁርባን ተምረውና አውቀው መቀጠል ሲገባቸው፤ ይባስ ብለው ቅዱስ ቁርባን እንደማይጠቅም በማሰብ ይሁን ባለማወቅ ባይገባንም ከቅዱስ ቁርባን የሚርቁ ብዙዎች ናቸው። ይሄም ነገር የቤተክርስቲያን አባቶች በእግዚአብሔር ቤት ዘንድ የሚያስጠይቃቸው የክህነት ሃላፊነት ነው። ምእመናንም ቢሆኑ የቅዱስ ቁርባንን ዘለዓለማዊ ህይወትነቱ እየተነገራቸው እያወቁና እየተረዱ ከቅዱስ ቁርባን የሚርቁ ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድ ይጠብቃቸዋል።
ስለዚህ ጠያቂያችን በዚህ የመነሻ ትምህርት ትክክለኛውን ሃሳብ በአጭሩ ከገለጽንልዎ እርስዎ ወደአቀረቡት ጥያቄ ስንመጣ፤ ምንም እንኳን የሰው ልጅ በልዩ ልዩ ኅጢአት የመወደቁ ሁኔታ የደካማ ሥጋ ባህሪ ቢሆንም በሰራነው ኅጢአት ተፀፅተን ወደ ንስኅ ህይወት ተመልሰን ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል የሚለክለን ህግ ግን የለም። ጠያቂያችን እንዳሉት ቅዱስ ቁርባን ሲቀበሉ ቆይተው በመሃከሉ በዝሙት ተሰናክለው ከቅዱስ ቁርባን ከራቁ ወይም ርቀው ከቆዩም አሁን ማድረግ ያለብዎት ፦
1ኛ የክርስቶስ ሥጋና ደሙ ከኅጢአት የሚያፀዳና የሚቀድሰንና የሚያነፃን እንጂ የሚያርቅ ስላልሆነ በኅጢአት መውደቆትን ቢያምኑም በንስኅ ተመልሰው ሥጋ ደሙን የመቀበሉን ስርዓት እንደገና መቀጠል አለብዎት።
በ2ኛ ደረጃ ሚስት ለማገባት እቅድ ካለዎት በሥጋ ህይወት ውስጥ ባይገደዱበትም እንደ መንፈሳዊነት ግን ወደ ትዳር ህይወት ሲገቡ በቅዱስ ቁርባን ቢሆን በሥጋም ሆነ በነፍስ በረከትንና ክብሮትን ያበዛዋል።
በ3ኛ ደረጃ ማግባት ካልፈለጉም ስለሰሩት ኅጢአት በንስኅ የኅጢአት ስርየት በማግኘት ብቻዎትን በቁርባን ተወስነው መኖር ይችላሉ።
ነገር ግን በተደጋጋሚ የሚፈተኑበት በደል ካለ ለጊዜው መቁረብዎን አቁመው ወደ ንስኀ አባትዎ ቀርበው የፈጸሙትን በደል ከተናዘዙ እና ንስኀዎትን ከጨረሱ በኋላ ለመቁረብ መቀጠል ይችላሉ። ምክንያቱም አንድ ሰው ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ እዳ በደል እንዳይሆንበት አስቀድሞ ከኀጢአት እና ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ ከሚከለከልባቸው ጥፋቶች መራቅ አለበት። ምክንያቱም ቅዱስ ቁርባን ከተቀበለ በክርስቲያናዊ ህይወት ውስጥ የመጨረሻው ክብርም ላይ የደረሰ ሰው ነውና፤ ይሄንን ታላቅ ክብር በማቃለል ተመልሶ የማይገባውን ነውር መፈፀም ማለት ግን ታጥቦ ጭቃ እንደማለት ይቆጠራልና ተመልሰን ንስኀ መግባት ብቻ ሳይሆን የንስኀውም ደረጃ እጥፍ ድርብ ሊሆን እንደሚችል ተገንዝበን ራሳችንን በመግዛት በምግባርና በሃይማኖት ጸንተን ለመኖር መታገል አለብን፤ በኀጢአት ከወደቅንም ቶሎ በንስኀ ልንነሳ ያስፈልጋል። ሆኖም ለሰሰንት ጊዜ ላሉት በመሰረቱ ጥፋቱን በመደጋገም ሁል ጊዜ በንስኀ እመለሳለሁ በሚል መንፈስ መሄድ እንደሌለብን የቤተክርስቲያን ቀኖና ይደነግጋል። ዋናው ቁም ነገር ግን ማንኛውም ክርስቲያን በምንም ይሁን በምን ከቅዱስ ቁርባን ላለመለየት በየጊዜው መንፈሳዊ አላማውን በማጽናት መታገል እንዳለበት እንመክራለን።

ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን በፈተና ብንወድቅ
👉🏾ስለ #ቅዱስ #ቁርባን፣ የ #ንስሐ ህይወትና ስለ #ዝሙት #ፈተና
👉ጥያቄ፡- ንስሐ ገብቼ መልሼ እሳሳታለሁ፡፡ የዝሙት መንፈስ በጣም ይፈታተነኛል፡፡ እኔ ግን ንስሐ ገብቼ፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል እፈልጋለሁ፡፡ ልብስም ገዝቼ ይኼው መቼ ይሆን ከአንተ ቤት የምኖረው እያልኩ እሳላለሁ፡፡ ንስሐ ገብቼ ብቆርብስ ? የድፍረት ኃጢያት ይሆናል ወይ? አንድ አባት ቢያንስ 30 ዓመት ይሙላሽ አሉኝ፡፡ እኔ ግን ከእግዚአብሔር መራቅ አልፈልግም፡፡ ግን መኖር እፈልጋለሁ እስኪ አስረዱኝ በማርያም?
መልስ፡- የጠየቁን ስለ ንስሐ ሕይወት ነው፡፡ በመቀጠልም በንስሐ ሕይወት ስለሚፈፀም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ በሚመለከት ነው፡፡ ጠያቂያችን ከንስሐ የተሸለ ምን የሚያስፈልግ ነገር አለ? ሁልጊዜም ደጋግመን እንደምንለው ኃጢያት ላለመሥራት መጋደሉ፣ መታገሉ መቸስ የማይገኝ ዕድል ነው፡፡ ለሁላችን የማይቻል ነገር ስለሆነ፤ ሁላችንም ፈተና የበዛብን ተክል ስለሆንን፣ የፈለገንን ያህል ብንምል፣ ብንገዘት፣ አጥብቀን ብንጠላው ብንታገለው ሁላችንም ተሰናክለን የምንወድቅበት የጋራ የሆነ ኃጢያት ስላለ በዚያ ተጠልፎ መውደቁ የማይቀር ነገርና መጥፎ ዕድል ሆኖብን እንጂ፤ በዋናነት ከኃጢያት ርቆ መኖር ቁጥር 1 የምንመርጠው የተቀደሰ ተግባር ነው፡፡ ይኼ ሳይቻል ቀርቶ ደግሞ በአንድም፣ በሌላ መንገድም ወይም ከባድ በሆነ ወይም ቀላል በሆነ ኃጢያት በወደቅን ጊዜ፤ ዓይነተኛው መፍትሔ ወደ ንስሐ መምጣት ነው፡፡
በቅዱሳት መጻህፍትም የንስሐ ትርጉም ወይም የንስሐ ታላቅነት ተነግሮናል፡ ንስሐ ማለት ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው፡፡ በሙሉ ልብ በፍፁም እምነት ሆነን ወደ እግዚአብሔር መመለስ ነው.፣ መጸጸት፣ የንስሐ ሕይወት የሚባለው ነገር ይኼ ነው፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ ጥርጊያውን አቅኑ›› እያለ በመጣ ጊዜ የአዋጁ አብሣሪ ሆኖ ሲመጣ ፤ የመጀመሪያው የስብከቱ አዋጅ ንስሐ ግቡ የማቴዎስ ወንጌል ቁጥር 1 እና 2 ላይ ንስሐ ግቡ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና፡፡ ሐዋርያትም ጌታ በተነሣ በ 50 ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስ ወርዶላቸው 72 ቋንቋም ተገልጦላቸው፣ ገና በጠዋቱ በአይሁድ ዘንድ ቆመው እጅግ የብዙዎቹ ልቡና የተመሰጠበትን ትምሕርት ባስተማሩ ጊዜ ብዙዎቹ አምነው ወዲያውኑ፤ ምን እናደርግ ሲሏቸው? ንስሐ ግቡ፣ እና አምናችሁ ከመጣችሁ ደግሞ የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆን ተጠመቁ፡፡ ይኼን ነው እንግዲህ ያስተማረ ማለት ነው፡፡
ስለዚህ የዮሐንስ ትምሕርት የመጀመሪያው ነገር የበር መክፈቻው ቁልፍ ንስሐ ግቡ ነው፡፡ ሁላችንም ከነኃጢያታችን እንዲሁ ተሸፋፍነን እንድንኖር እግዚአብሔር አይፈቅድም፡፡ እና ለንስሐ የእድሜ ገደብ የለውም፡፡ ቅዱስ ቁርባን የእድሜ ገደብ የለውም፡፡ ይኼን በሚመለከት በጣም ብዙ ጊዜ ተነጋግረናል፡፡ መቸስ በእያንዳንዱ ትምሕርት ሳንዘነጋ የምናስታውሰው ነገር ስለ ምስጢረ ቁርባን ነው፡፡ ማንኛውም አማኝ፣ ማንኛውም ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን መቀበል እንዳለበት፡፡ ደጋግመን እንደተነጋገርነው፤ ወንድ ልጅ በ40 ቀኑ፣ ሴት ልጅ በ 80 ቀኗ የእግዚአብሔር ልጅ ሆነው በስመ ክርስትና፣ በቅዱስ ቁርባን ታትመው ልጅነታቸውን ካረጋገጡ በኋላ ከቅዱስ ቁርባን አንድ ቀንም ቢሆን መለየት የለባቸውም ብለናል፡፡
ስለዚህ ጠያቂያችን፤ በተለያየ የሥጋ ድካም፣ በተለያየ የኃጢያት ምክንያት ከሥጋወደሙ መሸሽ ወይም ማቋረጥ አያስፈልግም፡፡ ከእነጭራሹ ደግሞ የምንሰማው ጉድ 30 ዓመት ይሙላችሁ፤ 40 ዓመት ይሙላችሁ፣ 25 ዓመት ይሙላችሁ አይባልም እኮ፡፡ ከምን ጋር በማያያዝ ነው የእድሜ ጣሪያ የምናስቀምጠው? ለደቂቃም፣ ለሴኪንድም ከእግዚአብሔርጋር መለየት የለበትም የሰው ልጅ እያልን ፣ ሁሉም መላ ሕይወታችን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ነው፡፡ ምናልባት ከእግዚአብሔር ክልል ውጪ፣ እርሱ ከሚገዛው፣ ከሚያስተዳድረው፣ ከፈጠረው ዓለም ውጪ ሆነ ሌላ ዓለም ኖሮ፣ ሌላ አስተዳዳሪ፣ ሌላ ገዢ ኖሮ ከእሱ ተለያይተን ከፈለግን ደግሞ ሌላ አብረን ለመኖር ውል የምንመሠርትበት ኑሮ አይደለም እኮ ይኼ፡፡ በየትኛውም ሰዓት ውስጥ፣ በኃጢያት ውስጥም እያለንም የእግዚአብሔርን ስም እንጠራለን፡፡ ከዚያ ከወደቅንበት የኃጢያት ጉድጓድ፣ የኃጢያት ማጥ ውስጥ ሊያወጣን የሚችለው፤ መፍትሔ እንዲሰጠን እግዚአብሔር ቁልፍ የሆነውም የችግራችን መፍትሔም ያለው ከእግዚአብሔር እጅ ነው፡፡ ስለዚህ ፈፅሞ እንዲህ ዓይነት ትምሕርት ልንሰማም አይገባንም፡፡ ቆይ ልጅ ናችሁ፣ እንዲህ፣ እንዲህ እያሉ የሚሉ ትምሕርት ያነሰው ሰው፣ ወይ ደግሞ ፈጽሞ መንፈሳዊ ምክርና ትምሕርት ተፈልጎ የታጣበት ሰው የሚናገረው የሚያስረዳው የሌለው መጽሐፍትን ጠቅሶ የማያስተምር፣ እንዲህ ዓይነት ካሕን በልብ ወለድ ስለሚናገር ምንቸገረው? እንዳንመነኩስም ገና ነሽ፣ እንዳንቆርብም ገና ነሽ፣ ባይሆን ካሕን ማስተማር ያለበት ሁል ጊዜ ለምዕመናን እግዚአብሔር ቢረዳቸው ከኃጢያት እንዲለዩ ብቻ ነው፡፡ ጊዜ ሳንሰጥ መናገር ያለብን ቅዱስ ቁርባን እንዲቀበሉ፣ እንደዚህ አድርጉ ኃጢያት ላይ ወድቄያለሁ አባቴ ብንባል፤ በል ቶሎ ንስሐ ግባና ወደ እግዚአብሔር ተመለስ፣ ቶሎ ቁረብ ነው ማለት ያለብን፡፡ ሁሌ የምናገረው ቋንቋ ይኼ ነው፡፡የእግዚአብሔር ቅድስና የእኛን የረከሰውን ሕይወት ከኃጢያት ያነፃል፤ የእኛ ኃጢያት ግን የእግዚአብሔርን ቅድስና አያረክስም፡፡
ስለዚህ ጠያቂያችን፤ ቅዱስ ቁርባኑም፣ ፀበሉም፣ መስቀሉም ፣ ቃለእግዚአብሔሩም፣ ቅዳሴውም ይኼ ሁሉ እኛን ከኃጢያት የሚያነፃ ነው እንጂ ጨርሶ የሚያረክስን ኃጢያታችንን የሚያባብስብን ነገር አይደለም ይኼ፡ አሁንም ጠያቂያችን እንዲህ ዓይነት ፍላጎት፣ ምኞት እያለዎት ገና ነዎት፣ የወጣትነት ዕድሜ ነው፣ ብዙ ነገር አካብደን ፣ ተስፋ ቆርጠን የምንርቅበት የሕይወት ደረጃ አይደለም ያለነው፡፡ እርስዎ ያሉት እንግዲህ 30 ዓመት ይሙላሽ የሚለው ገና የእዚህ ዕድሜ ባለቤት እንኳን እንዳልሆኑ ፣ የልጅነት የወጣትነት ዕድሜ ላይ የተፈተኑበት ነገር ምን እንደሆነ፣ በግል ሕይወትዎ ምክርም መክረን፣ እንደ ቤተክርስቲያን መምህር፤ እንደ ቤተክርስቲያን አባት የሚስተካከለው ነገር እንዲስተካክል ይደረጋል፡፡ እግዚአብሔርም ያግዘናል፣ ቸርነቱ ፣ ምሕረቱ ብዙ ስለሆነ፣ በተለመደው የውስጥ አድራሻችን ደውለው ያግኙንና ተጨማሪ ምክር እንሰጥዎታለን፡፡ በነገሩ ሁሉ የሚመክረን እግዚአብሔር የተመሰገነ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ቤት የሚለየን የሚያርቀን፡ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ምንድን ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ፣ ለሮሜ ክርስቲያኖች በፃፈው መልእክቱ በሮሜ መልእክት ምዕራፍ 8 ያለው ማለት ነው፡፡ ከቁጥር 35 ጀምረን ስናነብ የምናገኘው ማለት ነው፡፡ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ ማነው? በጣም ከባድ የተባሉ ብዙ ጦርነት ነው? ረሐብ ነው? ሠይፍ ነው? ደዌ ነው? ምንድን ነው? ብሎ ዘርዝሯቸዋል፣ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ የለም ፡፡ ስለዚህ ብዙ የሥጋ ምክንያቶችን እየደረደርን ከቅዱስ ቁርባን ፍቅር የሚለየን ነገር አንዳችም የለም፡፡ይኼንን ነው ማየት ያለብን።
(ይቀጥላል)👇
(ቀጣይ ክፍል)👆👇
👉🏾ስለ #ቅዱስ #ቁርባን፣ የ #ንስሐ ህይወትና ስለ #ዝሙት #ፈተና
በአጠቃላይ ከእግዚአብሔር ቤት ልንርቅ አይገባንም፡፡ ልበ አምላክ ዳዊት ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ በጣም ደስ አለኝ ነው ያለው፡፡ ይኼ የእስራኤል ገዢ ታዋቂው፣ ዝነኛው ንጉሥ ዳዊት፤ እንደ ሥጋዊ ሐሳብ ከሆነ በታላቁ ቤተ መንግሥት ነገሦ የሚኖረው ዳዊት፣ በሥጋው ብዙ የሚያስደስቱ ነገሮች እፁብ፣ ድንቅ የሚባሉ ነገሮች እንዳሉ የሚታወቅ ነው፡፡ ነገር ግን ዳዊት ምንድን ነው ያለው? ከምንም በላይ ሰው ሁሉ በሕይወቱ ደስ ከሚሰኝበት፣ ከሚደሰትበት ነገር፤ ወደ እግዚአብሔር ቤት መሄድ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ቤት አለመራቅ፣ አለመለየት፡፤ ይኸው ነው ሌላ ፀጋ የለም፡፡ እዚያ ቅዱስ መስቀል አለ፣ እዚያ ቅዱስ ጸበል አለ፣ እዚያ ቅዱስ ቁርባን አለ፣ እዚያ የእግዚአብሔር ቃል አለ፣እዚያ ቅዳሴ አለ፣ እዚያ ዝማሬ አለ፣ እዚያ በመንፈስ የመረጋጋት፣ የመጽናናት፣ ፍቅር አለ፣ ሠላም አለ ፣ትዕግሥት አለ ከእግዚአብሔር ቤት ሊለየን የሚችል አንዳችም ነገር የለ፡፡
ስለዚህ እንዳሉትም ለቅዱስ ቁርባን የሚሆንዎት ዝግጅት አድርገው፣ ልብሱ ሳይቀር፣ ተዘጋጅቶ ብለዋል፣ ይኼንን ምኞትዎትን፣ የልብዎትን ሐሳብ እግዚአብሐየር ይሞላዋል በእርግጠኝነት እኛ ደግሞ ሳይውሉ፣ ሳይድሩ፣ ቀጠሮ ሳይበዛ፣ ቶሎ ወደዚያ እንዲቀርቡ ተጨማሪ ምክር ስለምንሰጥዎት ቅድም እንዳልኩት በውስጥ መስመራችን ያግኙን፡፡
የመከረን፣ የገሰፀን የሠራዊት አምላክ ሥሙ ይመስገን፣ ፀጋ በረከቱን በሁላችን ላይ ያሳድርብን፡፡ ወስብሓት ለእግዚአብሔር አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፦ አንድ ሰው ብቻውን #ቁርባን #ተቀብሎ ወይም ተቀብላ #በዝሙት #ቢወድቅ ተመልሶ መቁረብ ይችላን/ች/ እስከ ስንት ጊዜ ነው?
መልስ፦ ስለ ቅዱስ ቁርባን የጠየቁን አባላችን ሆይ፤ በመጀመሪያ ከዚህ ቀደምም ደጋግመን እንደገለፅነው ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በ40 ቀን እና በ80 ቀን የእግዚአብሔርን ልጅነት በጥምቀተ ክርስትና አግኝቶ በቅዱስ ቁርባን ከታተመበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መጨረሻ የዘመኑ ፍፃሜው ድረስ ከቅዱስ ሥጋውና ከክቡር ደሙ መለየት እንደሌለበት ክርስቲያናዊ ግዴታውም እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል። ይህም በቅዱስ መፅሐፍ በግልፅ ታዟል። ምክንያቱም የጌታን ቅዱስ ሥጋ ካልበላን ክቡር ደሙን ካልጠጣን የዘለዓለም ህይወት የለንም። ሰው በሥጋው በህይወት ለመኖር ዘወትር ለስጋው ምግብ እንደሚያስፈልገው ሁሉ በነፍሱም የዘላለም ህይወት ለመውረስ የነፍሳችን ምግብ ቅዱስ ቁርባን ስለሆነ ነፍሳችን ደግሞ ቅዱስ ቁርበንን ካጣች እንደሞተች ወይም ህይወት እንደሌላት ማመን ያስፈልጋል።
ይሁን እንጂ ቅዱስ ቁርባን በሰው ህይወት ሲገለፅ በህፃንነት እድሜ ደረጃ ያሉ ክርስቲያኖች ሲቆርቡ ቆይተው አካለ መጠናቸው ወደ አዋቂነት ሲደርስ ይበልጥ ስለሚስጥረ ቁርባን ተምረውና አውቀው መቀጠል ሲገባቸው፤ ይባስ ብለው ቅዱስ ቁርባን እንደማይጠቅም በማሰብ ይሁን ባለማወቅ ባይገባንም ከቅዱስ ቁርባን የሚርቁ ብዙዎች ናቸው። ይሄም ነገር የቤተክርስቲያን አባቶች በእግዚአብሔር ቤት ዘንድ የሚያስጠይቃቸው የክህነት ሃላፊነት ነው። ምእመናንም ቢሆኑ የቅዱስ ቁርባንን ዘለዓለማዊ ህይወትነቱ እየተነገራቸው እያወቁና እየተረዱ ከቅዱስ ቁርባን የሚርቁ ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድ ይጠብቃቸዋል።
ስለዚህ ጠያቂያችን በዚህ የመነሻ ትምህርት ትክክለኛውን ሃሳብ በአጭሩ ከገለጽንልዎ እርስዎ ወደአቀረቡት ጥያቄ ስንመጣ፤ ምንም እንኳን የሰው ልጅ በልዩ ልዩ ኅጢአት የመወደቁ ሁኔታ የደካማ ሥጋ ባህሪ ቢሆንም በሰራነው ኅጢአት ተፀፅተን ወደ ንስኅ ህይወት ተመልሰን ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል የሚለክለን ህግ ግን የለም። ጠያቂያችን እንዳሉት ቅዱስ ቁርባን ሲቀበሉ ቆይተው በመሃከሉ በዝሙት ተሰናክለው ከቅዱስ ቁርባን ከራቁ ወይም ርቀው ከቆዩም አሁን ማድረግ ያለብዎት ፦
1ኛ የክርስቶስ ሥጋና ደሙ ከኅጢአት የሚያፀዳና የሚቀድሰንና የሚያነፃን እንጂ የሚያርቅ ስላልሆነ በኅጢአት መውደቆትን ቢያምኑም በንስኅ ተመልሰው ሥጋ ደሙን የመቀበሉን ስርዓት እንደገና መቀጠል አለብዎት።
በ2ኛ ደረጃ ሚስት ለማገባት እቅድ ካለዎት በሥጋ ህይወት ውስጥ ባይገደዱበትም እንደ መንፈሳዊነት ግን ወደ ትዳር ህይወት ሲገቡ በቅዱስ ቁርባን ቢሆን በሥጋም ሆነ በነፍስ በረከትንና ክብሮትን ያበዛዋል።
በ3ኛ ደረጃ ማግባት ካልፈለጉም ስለሰሩት ኅጢአት በንስኅ የኅጢአት ስርየት በማግኘት ብቻዎትን በቁርባን ተወስነው መኖር ይችላሉ።
ነገር ግን በተደጋጋሚ የሚፈተኑበት በደል ካለ ለጊዜው መቁረብዎን አቁመው ወደ ንስኀ አባትዎ ቀርበው የፈጸሙትን በደል ከተናዘዙ እና ንስኀዎትን ከጨረሱ በኋላ ለመቁረብ መቀጠል ይችላሉ። ምክንያቱም አንድ ሰው ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ እዳ በደል እንዳይሆንበት አስቀድሞ ከኀጢአት እና ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ ከሚከለከልባቸው ጥፋቶች መራቅ አለበት። ምክንያቱም ቅዱስ ቁርባን ከተቀበለ በክርስቲያናዊ ህይወት ውስጥ የመጨረሻው ክብርም ላይ የደረሰ ሰው ነውና፤ ይሄንን ታላቅ ክብር በማቃለል ተመልሶ የማይገባውን ነውር መፈፀም ማለት ግን ታጥቦ ጭቃ እንደማለት ይቆጠራልና ተመልሰን ንስኀ መግባት ብቻ ሳይሆን የንስኀውም ደረጃ እጥፍ ድርብ ሊሆን እንደሚችል ተገንዝበን ራሳችንን በመግዛት በምግባርና በሃይማኖት ጸንተን ለመኖር መታገል አለብን፤ በኀጢአት ከወደቅንም ቶሎ በንስኀ ልንነሳ ያስፈልጋል። ሆኖም ለሰሰንት ጊዜ ላሉት በመሰረቱ ጥፋቱን በመደጋገም ሁል ጊዜ በንስኀ እመለሳለሁ በሚል መንፈስ መሄድ እንደሌለብን የቤተክርስቲያን ቀኖና ይደነግጋል። ዋናው ቁም ነገር ግን ማንኛውም ክርስቲያን በምንም ይሁን በምን ከቅዱስ ቁርባን ላለመለየት በየጊዜው መንፈሳዊ አላማውን በማጽናት መታገል እንዳለበት እንመክራለን።
ለሁሉም ነገር ግን ስለ አንቀፀ ንስኅ ጠንቅቀው የሚያውቁ የቤተክርስቲያን አባቶች (ሊቃውንት) ሁልጊዜ በማነጋገርና በማማከር ትምህርት እያገኙ ማንኛውንም ነገር እንደ ስርዓቱና እንደ ህጉ ማስቀጠል የሚችሉበትን ፕሮግራም እንዲያደርጉ ይህን አጭር መልእክት ለእርስዎ እና ለዮሐንስ ንስኅ ድረገፅ መንፈሳዊ ፕሮግራም ተከታታይ አባሎቻችን ሁላችሁም አንብባችሁ ትረዱት ዘንድ መልዕክቱ እንዲደርሳችሁ አድርገናል።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ
በየስንት ጊዜ መቁረብ እንደሚገባ
👉🏾👉🏾👉🏾 ስለ #ቅዱስ #ቁርባን
ዘወትር የመቁረባችን ጥቅሙ?
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን፤ በርዕሱ መነሻነት የተዘጋጀው ይህ ገጸ ንባብ ከ ‘ኀብረ ሥርዐት ዘቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክስ’ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ፥ ይህንን ጠቃሚ ትምህርት ለእናንተ እንዲደርሳችሁ አድርገናልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።
ይህም ሲገለጥ ሥጋውን ደሙን ዘወትር በመቀበላችን የምናገኘው ረብኅ ጥቅም ምንድን ነው? የሚል ነው፡፡ ዘወትር ሥጋውን ደሙን በመቀበላችን ጽንዓ ሃይማኖትን፣በመንፈሳዊ ሕይወት መበርታትን፤ ዘለዓለማዊ ድኅነትን፣ሥርየተ ኀጢአትን እግዚአብሔሑርን፤ ኃይል መንፈሳዊን ከምእመን ጋር አንድ መሆንን ፤በሥጋው በደሙ ጌታን መማጸንን ማለትመሰ ስለ ቆረስኸው ሥጋ ስለ አፈሰስኸው ደም ብለህ ይቅር በለን እያሉ መለመንን፡‹‹በስሜ አብን ብተትለምኑት ሁሉን ይሰጣችኋል›› ብሎናልና፡፡ በሥጋው በደሙም ‹‹አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ ደስ የሚያሰኝህ መሥዋዕት የልጅህ ሥጋ እነሆ በዚህም ኀጢአቴን ሁሉ አቃልልኝ ስለ እኔ አንድ ልጅህ ሙቷልና ስለ አኔ በቀራንዮ የፈሰሰ ንጹሕ የሚሆን የመሲሕ ደም እነሆ ስለ እኔ ይጮኻል ይህ የሚናገር ደም የኔን የባሪያህን ኀጢአት የሚያስተሠርይ ይሁን ስለ አነርሱም ልመናዬን ተቀበል›› እያልን እንማፀናለንና፡፡ ቅ ሐዋ ቀ ፻፳
ይህም ማለት ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ስናስብ ለመቀበል የሚያበቁንን ቅድመ ዘግጅቶች አናሟላቸው ዘንድ እንተጋለን፡፡ እነዚህን ዝግጅቶች ስናደርግም አስቀድመን ንፅሕናን ከዚያም ቅድስናን ገንዘብ እናደርጋለን፡፡ ንፅሕናና ቅድስና በሃይማኖት የመጽናት በመንፈሳዊ ሕይወት የመበርታት ምልክቶች ናቸውና፡፡‹‹ከነዚህም በኋላ ለምእመናን ምሳ ሙሽራው በሙሽሪት አዳራሽ ይታረዳል መታረዱን ከማየት የተነሣ ጉልበቷ ይንቀጠቀጣል አንደቷም ይናወጣል በመሠውያው ቀንድ ሲንጠፈጠፍ ደሙን ባየች ጊዜ ሥጋውን በፍርሃት ትበላለች ደሙንም በመንቀጥቀጥ ትጠጣለች ከዚያም የሃይማኖት ወላፈን በልቧ ውስጥ ይግላል የፍቅሩም ሞገድ
በሆዷ ውስጥ ይፈላል›› እንዳሉ አባ ጊዮርጊስ መጽ ምሥ 6፥15
ጌታም በእርሱ ሐረገ ወይንነት አዕፁቅ እኛ እናድግ ዘንድ ‹‹አነሃ ውአቱ ሐረገ ወይን ዘጽድቅ ወአቡየ ተካሊሁ ውእቱ ወወለኩሉ ዓጽቅ ዘኢይፈሪ በላዕሌየ ይገዝምም ወያአትትዎ፦ እውነተኛ የወይን ሐረግ እኔ ነኝ ተካዩም አባቴ ነው በእኔ ያለውን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍም ሁሉ ያስወግደዋል የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እንዲያፈራ ያጠራዋል…በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ከአልኖረ ብቻውን ሊያፈራ እንደማይችል እናንተም እንዲሁ በአረኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም እኔ የወይን ግንድ ነኝ ቅርንጫፎቹም እናንተ ናችሁ በእኔ የሚኖር እኔም በአርሱ ብዙ ፍሬ የሚያፈራ እርሱ ነው ያለእኔ ምንም ማድረግ አትችሉምና በእኔ የማይኖር ቢኖር እንደ ደረቅ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጥሉታል ሰብስበውም በአሳት ያቃጥሉታል፡›› ብሏል፡፡ ዮሐ 15፥1-5
ስለዚህ ዘወትር ሥጋውን ደሙን ስንቀበል በጌታችን እንኖራለን እርሱም በእኛ ይኖራል፡ እንዲሁም ሞተ ወልደ እግዚአብሔርን እናስባለን፡፡ይህን ስናስብ ለአኛ ሲል የተቀበለውን መከራ መስቀል በቀኖት መቸንከክሩን፣የእሾህ አክሊል መድፋቱን፣ምራቀ ርኩሳን አይሁድን መቀበሉን ፣በጦር መወጋቱን፣ ግርፋቱን፣ አምላክ ሲሆን የአይሁድን ተሳልቆ በትዕግሥት መስማቱን…በአጠቃላይ ነገረ መስቀሉን እንድናስብ ያደርገናል፡ በዚህ ውስጥ እግዚአብሔር ሰውን የወደደበት ፍቅሩ ምን ያህል ነው? ተብሎ ሊመዘን የማይቻል በዕፁብ የሚታለፍ መሆኑን እንረዳለን።ይህም በአንድ መዓርግ ከፍ የማለት ምልክት ነው፡፡
(ይቀጥላል )
👇👇👇
👉🏾👉🏾👉🏾 ስለ #ቅዱስ #ቁርባን
(ቀጣይ ክፍል)👆👇
ዘወትር የመቁረባችን ጥቅሙ?
ዳግመኛም ዘወትር ሥጋውን ደሙን በመቀበላችን ከተናዛዚ የቀሩ ሥርየተ ኃጣውእን እናገኛለን። ይህም ማለት ሥጋውን ደሙን የምንቀበለው ንስሐ ገብተን ቢሆንም መንፈስ ቅዱስ የገለጠውን እንናዘዛለን ሰይጣን የሰወረው(ያዘነጋው) በሥጋው በደሙ ይሰረይልናልና፡፡ ይህም ማለት ሰይጣን የሰወረውን መንፈስ ቅዱስ መግለጥ ያማይቻለው ሆኖ ሳይሆን ለጊዜው የጊዜ ብዛት በሌላም ምክንያት ዘንግተነው ሳንናዘዝ የቀረውን አይር ግን ‹እመቦ ዘወድቀ በኃጢአት ኢይርሳእ እስመ ዘኢይትረሳእ” ::.. ይላልና እኛ ብንዘነጋው በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ በመሆኑ ኀጢአትን መዘንጋት አይገባም። ቤተ ከርስቲያን ምእመናን ልጆቿን ዘወትር ንስሓ ግቡ ሥጋውን ደሙን ተወበሉ የምትለውም እንዲህ ኃጢአታቸውን ረስተው ሳይናዘዙ ሥርየተ ኀጢአት ሳያገኙ ቀጠሮ በማይሰጠው መልእክተኛ (ሞት) እንዳይወሰዱ ነው፡፡ በኅጢአት ያለ ሰው ወደ ሥጋው ደሙ እንዳይቀርብም – አስቀድሞ ነብዩ ‹‹የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ጎጢአተኛን ያስወግዱታል” ብሏል፡፡ ኢሳ 26+10
በመሆኑም ዘወትር ሥጋውን ደሙን የሚቀበል ክርስቲስ የሚያገኛቸው ጥቅሞች እነዚህ ብቻ አይደሉም።ሥጋውን ደሙን ሲቀበል የድሉ ተካፋይም ይሆናልና፡፡ ይህም ማለት ጌታ ‹‹ወዝንቱ ውእቱ ዘነገርኩክሙ ከመ በገቤየ ሰላመ ትርከቡ ወበዓለምሰ ህማመ ትርከቡ ሀለወክሙ ወባህቱ ጽንዑ እስመ አነ ሞዕክዎ ለዓለም፦በእኔም ሰላምን እንድታገኙ ይህን ነገርእቸችሁ በዓለም ግን መከራን ትቀበላላችሁ ነገር ግን ጽኑ እኔ ዓለሙን ድል ነስቼዋለሁና››ብሎ ነግሮናልና፡፡ ዮሐ 16-33 እርሱ ‹‹ዐርባዕቱ ዕድዋኒሁ ለሰብእ፦የሰው ጠላቶቹ ዐራት ናቸው›› እንደተባለ ሞትን፣ኃጢአትን፣ፍዳን፣ሰይጣንን ድል ነስቶ እናንተም ድል ንሱ ብሎናልና፡፡ ‹‹ወለዘሞዐሰ እሁቦ ይንበር ምስሌየ ውስተ መንበርየ በከመ አነ ሞዕኩ ወነበርኩ ምስለ አቡየ ውስተ መንበሩኑ አኔ ድል እንደ ነሣሁ ከአባቴም ጋር በዙፋኑ ላይ እንደ ተቀመጥሁ ድል ለነሣው ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ ይቀመጥ ዘንድ እሰጠዋለሁ›› ራዕ 3:21 እንዲህ አድርጎ ሜዳውም ፈረሱም እነሆ እንደማለት የመወዳደሪያውን የመቀዳደሚያውን መድረክ ክፍቶልናል፡፡
በዚህም ጌታ ሰይጣንን በሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ ድል ከነሣው በኋላ ቅዱሳንም ጌታቸውን መስለው ግንባር ግንባሩን እያሉ የሚመልሱት ሁነዋል።:፡ስለሆነም ዘወትር ብቁ ሆነን ሥጋውን ደሙን ብንቀበል እነዚህን ከላይ ያየናቸውን አራት ነገሮች የምናሸንፍበትን ኃይል እናገኛለን፤ይህንም በማድረጋችን ኅብረተ ቅዱሳንን እናገኛለን፤ዘወትር ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ባካሄዳችን፣ በአኗኗራችን፣በአለባበሳችን፣በአነጋገራችን፣እነዚህን በመሰለው ሁሉ ስለርሱ እንመሰክራለን እንሰብካለን::እንዲሁም የአኗኗር ልቅነትን፤ግድ የለሽነትንና ንዘህላልነትን አጥፍተን እነዚህን ነገሮች ወደ መንፈሳዊነት እንድንለውጣቸው ያደርገናልና፡፡ በአጠቃላይ ዘወትር ሥጋውን ደሙን መቀበላችን ሐዋርያው ለደቀ መዝሙሩ ‹‹ጎየያ ለፍትወተ ውርዙት ወዴግና ለጽድቅ ወለሃይማኖትኑ፦እንግዲህ ከጉልምስና ምኞት ራቅ እግዚአብሔርንም በንጹሕ ልብ ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ጽድቅን፤ ሃይማኖትንም ፣ፍቅርንም፣ ሰላምንም ተከተል›› ያለውን ተግባራዊ በማድረግ በጥንቃቄ እንድንኖር ያደርገናል ፪ኛ ጢሞ ፪፥፳፪
እናም በሥጋው በደሙ ለመወሰን የሚመኝና የሚያስብ ሰው ሁሉ ነቢዩ ‹‹በተመረጠችው ዕለት ሰምቼሃለሁ ድኅነት በሚደረግበትም ቀን ረድቼሃለሁ›› ኢሳ 49:10 ሐዋርያውም ‹እነሆ የተመረጠችው ቀን ዛሬ ናት›› እንዳለ ነገ ዛሬ ሳይል መቅረብ ይገባዋል፡፡ርቀው ተለይተው የሚያማክሩት አጥተው በዚህ ዓለም ሐሳብ ተውጠው የሚኖሩ ያሉ እንደ ሆነ ደግሞ ጥበብ ወልድ ‹‹አላዋቂ የሆነ ወደ እኔ ይምጣ.. ኑ እንጀራዬን ብሉ የጠመቅሁላችሁን የወይን ጠጅም ጠጡ ስንፍናን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ በሕይወትም ትኖሩ ዘንድ ዕውቀትን ፈልጉ በመረዳትም ዕውቀትን አቅኑ›› ምሳ 9:4 እያለች ትጣራለችና ድምፅዋን ሊሰሙ ይገባቸዋል፡፥ ያም ባይሆን ጭንቀታቸውን አሳባቸውን ሁሉ«‹ለቤተ ክርስቲያን ይንገሯት›› መፍትሔ አታጣምና። በሥጋው በደሙ ተወስነው የሚኖሩ ያሉ እንደሆነ ደግሞ ‹‹እስከ መጨረሻው የሚታገሥ ግን መጨረሻው የሚታገስ ግን እረሰሱ ይድናል” ማቴ 24:13 ይላልና፡፡ እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ መጽናት ያስፈልጋቸዋል፡፡
ምንጭ፦ ‘ኀብረ ሥርዐት ዘቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክስ’
በመምህር አብርሃም ነጋ (2014)
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾👉🏾👉🏾ስለ #ሥርዓተ #ቅዱስ #ቁርባን
👉ጥያቄ፡- አንድ ሰው ቢያንስ በየስንት ቀኑ መቁረብ ይኖርበታል ?
መልስ፡- ጠያቂያችን፤ ዋናው ነገር ከኃጢያት ርቆ፣ ከበደል ነፅቶ፣ በቅዱስ ቁርባን መወሰናችን ነው፥ ቅዱስ ቁርባን እንደምድራዊ መብልና መጠጥ በተለያየ አቀራረብ፣ በተለያየ ጣዕም፣ በተለያየ ዝግጅት አናገኝም፡፡ አንድ ነው፡፡ ሰው በገንዘቡ፣ በጉልበቱ በደከመበት ሴቶቻችን፣ እናቶቻችን፣ እህቶታችን ሙያቸውን ሁሉ ያስተባበሩበት የምድሩ ምግብና መጠጥ የአንዱ ሙያ ከአንዱ ስለሚለይ፣ የአንዱ ዝግጅት ከአንዱ ስለሚለይ በሙያም ደረጃ ይሁን፣ በአቅምም ደረጃ ይሁን፣ በአቅርቦትም ደረጃ ይሁን ፣መጠኑ፣ ዓይነቱ፣ ጣዕሙ ይለያያል፡፡ አንዳንዱ ዝግጅት እንደምናየው ከጣራ መለስ ወይም ከበር መለስ ሆኖ፣ ብዙ ተቆጥሮ የማያልቅ ዓይነት ሆኖ ቀርቦ የምንበላው አንድ ነው፡፡ በዓይነቱ በዝቶ እናየዋለን፣ ጣዕሙም አሉ የሚባሉ ባለሙያዎች ተፈራርቀውበት ለእያንዳንዳችን በምርጫችን አንስተን፣ ይኼ የሚጥም ነው፣ ይኼ የማይጥም ነው፣ የሚመች ይኼ ነው፣ የማይመች ይኼ ነው፣ ይኼ ለጤና ችግር ያስከትላል፣ ይኼ ለጤና ይስማማል እያልን ሁሉ ብዙ የምንተቸው ነገር የሚገርመው ነገር ከዚያው ከአንድ መዓድ ውስጥ፣ በአንድ ጠረጴዛ ከቀረበው ምግብ ውስጥ ለዝግጅቱ ወይም ደግሞ ለዚያ ዝግጅት የተጠራነው ሰዎች በሓሳብ ሳንስማማ የምንለያይበት ዝግጅት ይሆናል፡፡ እንግዲህ ምድራዊ መብል፣ ምድራዊ መጠጥን በደንብ አድርገን ደካማ የሆኑ፣ ውስን የሆኑ፣ አቅም የሚያንሳቸው የሰው ልጆች የተጠበቡበት የደከሙበት ነገር ስንጠቀመውም፣ ስንበላው ስንጠጣውም ብዙ ዓይነት ልዩነት ያለውና በሁላችንም አመለካከት የተለያየ አስተያየት የምንሰጥበት ኃላፊ ጠፊ ነው፡፡
ወደ ቅዱስ ቁርባን ስንመጣ ግን፤ በሰው እጅ ያልተሠራ፣ ያልተዘጋጀ ሰማያዊ መጠጥ፣ ሰማያዊ ምግብ ነው፡፡ያም ደግሞ የሁላችንም የዕለት እንጀራችን፣ የዕለት ምግባችን፣ የዕለት መጠጣችን ሆኖ የተሰጠን ከሰማይ የወረደው እየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ የራሱን ቅዱስ ሥጋውን ቆርሶ፣ ክቡር ደሙን አፍስሶ፣ እንካችሁ ብሉ ጠጡ የዘላለም ሕይወት ይኑራችሁ ብሎ የተሠጠን በቤተ መቅደሱ አባቶቻችን ካሕናት ልብሰ ተክህኖ ለብሰው፣ እየጸለዩ፣ እየቀደሱ በዚህ ዓይነት ተገዝተው ያከበሩት ያ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ለእኛ ለምዕመናን ሰማያዊ ምግብ፣ ሰማያዊ መጠጥ ሆኖ ሲሰጠን የመጀመሪያ ዕለት ወደ ቅዱስ ቁርባን ቀርበን የበላነው ቅዱስ ሥጋ፣ የጠጣነው ክቡር ደም እስከ መጨረሻው ጊዜ ያለምንም ለውጥ የዓይነት የቅርጽ ወ.ዘ.ተ. ሳይኖረው ያለ እሱ ነው፡፡ አንድ ጊዜ የተዘጋጀው በምድራውያን ሰዎች ሳይሆን በሠማያዊ አምላክ ያውም ደግሞ ይህንን ሰማያዊ ምግብ. ይህንን ሰማያዊ መጠጥ ለማዘጋጀት በሥነ ፍጥረት ከተገኘ ነገር ሳይሆን ከሰማያዊ አምላክ ከእየሱስ ክርስቶስ የራሱ ሥጋውን፣ ደሙን የሰጠን፡፡
ስለዚህ ይህንን ለዘላለም ሕይወት የሚሰጠውንና እንደ ምድራዊ ምግብ በልተን የማያስርበውን፣ እንደ ምድራዊ መጠጥ ጠጥተነው የማያስጠማውን የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን አንድ ጊዜ ከወሰድን በኋላ በተከታታይ የሚኖረው ሥርዓተ ቁርባን አንዳንዶቹ ልዩ ፀጋ አድርገውት ልዩ በረከት ያስገኝልናል በማለት ሳያቋርጡ ጨርሶ ከሥጋ ጠባይ ርቀው ንፅሐ ጠባያቸው ሳያድፍባቸው በኃጢያት ወደ ሥጋ ወደሙ ለመቅረብ የሚከለክልባቸው ነውር እንደሌለባቸው ያረጋገጡ ክርስቲያኖች ሁልጊዜ ሊቆርቡ ይችላሉ፡፡ ደግሞ የተለያየ ተግባረ ሥጋ መደበኛ ኃጥያት ባይሠሩም እንኳን ቤተሠብ በማስተዳደር፣ በሌላም በኩል ከጽድቅም አንፃር የሚቆጠርላቸው በማህበራዊ ጉዳይ የሚያገባቸው ጉዳይ ላይ ደግሞ ሥራ የሚበዛባቸው ሰዎች ቢያንስ በዓላትን ቆጥረው፤ የግድ ክርስቲያን የሆነ ሚስጥር ያላቸው የተለየ መቁረብ ያለበት በዓላቶች ብለን የምናምንባቸው እንደ ዕለተ ትንሣኤ፣ እንደ እርገት፣ እንደ ጥምቀት፣ እንደ ልደት የመሳሰሉት ቀናት ለአንድ ክርስቲያን የማይቀር ማለት ነው፡፡
ዋናው ጥንቃቄ ግን የጊዜ ክፍተት ነው፡፡ ለረዥም ጊዜ ሳንቆርብ እንኳን የወር፣ የሁለት ወር፣ የሦስት ወር ጊዜ ክፍተት ቢሆን ከቁርባን የሚያርቀንን ኃጢያት እንዳንሠራ ነው፡፡ የቁርባኑ ሕይወት በዘላቂነት ተጠብቆ ቅድስናችን በቆረብን ቀን ሳይሆን እስከ በማይባል ቀን እንዲቀጥል፡፡ ለዚህ ነው ቁርባን የመጨረሻ መደምደሚያ ነው የሚባለው ተመልሰን በኃጢያት እንዳንወድቅ ኃጢያተኞች ሆነን ቆይተን ወይም አንዳንዶቻችን ኃጢያት ሲበዛብን፣ ፍርሃት ሲነግስብን ቁርባኑን ልናቋርጠው እንችላለን፣ ወይም ደግሞ አንዳንዶቻችን በድፍረት እንገባለን፣ አንዳንዶቻችን ደግሞ ከሁሉም የተሻለውን አማራጭ ንስሐ ወስደን ወደ ንስሐ እንመለሳለን፡፡ የመጀመሪያው አማራጭ ግን ንጽህናና ቅድስና ነው፡፡ መቸስ ሠርታችሁ አትብሉ አላለንም፣ ገበሬውም አትረስ አላለም፣ ቅዱስ ቁርባን የተቀበለ ሰው አያርስም፣ አይቆፍርም፣ አያለማም አልተባለም፣ አይማርም፣ አያስተዳድርም አልተባለም፡፡
ስለዚህ ጠያቂያችን ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቀን ኃጥያት ለሥጋችን የማይጠቅሙ በማሕበራዊ ጉዳያችን የሚያገሉን አሳፈሪ የሆኑ ነገሮችን እነሱን መተው ነው፡፡ እንግዲህ ጥያቄው በአንድ መሥመር ብቻ የሚመለስ ወይም ‹‹አዎ›› ወይም ‹‹የለም›› የሚባል ነገር ሆኖ እያለ ግን፤ ከተጠየቀ አይቀር ሁለም ሰው ምክር እንዲያገኝ አድርጌ ነው ሰፋ የማደርገውና ይቅርታ ይደረግልኝ፡፡ በመሆኑም በየቀኑ የሚቆርቡ በገዳም ሕይወት ውስጥ ያሉ በዚህ በዓለም እየኖሩ ሩጫቸውን ጨርሰው ሌላ በሥጋ ሕይወቴ ውስጥ ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቀኝ ነገር የለም ብለው ጠዋት ማታ ሁልጊዜ ቤተክርስቲያን ኪዳን በማድረስ፣ ምክንያቱም ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ዝግጅት አለ፡፡ ከመቁረባችን በፊት ከአሥራ ስምንት ሰዓት በላይ መፆም አለብን፡፡ በሕገ ጋብቻ የሚኖሩ ባልና ሚስት ከመቁረባቸው በፊት ቢያንስ ሦስት ቀን ከግብረ ሥጋ ግንኙኘት መቆጠብ አለባቸው፡፡ ከቆረብንም በኋላም ሌላ ሌሎች ጥንቃቄዎች አሉ፡፡ስለ ቅዱስ ቁርባን ቀደም ብለን ትምህርት ሰጥተናል፡፡ እነዚህ ሁሉ ዝግጅት የሚጠይቅ ነገር ከቁርባን በኋላም መጠንቀቅ አለብን፡፡ በዚህ ሁሉ ችግር የለብኝም ያለ ሰው ሁልጊዜም መቁረብ ይችላል፡፡
(ይቀጥላል)👇
(ቀጣይ ክፍል)👆
👉🏾👉🏾👉🏾ስለ #ሥርዓተ #ቅዱስ #ቁርባን
ከላይ እንደገፅኩት እነዚህ በዓመት ያሉ በዓላት በእለተ ሰንበት አንዱ ነው፤ የእመቤታችን ፣ የቅዱስ ባለወልድ ይላሉ ፍቅር ካላቸው ፃዲቅ ጋር አያይዘው የሚቆርቡ፣ ዓመታዊ የንግሥ በዓሎችን በተለይም የጌታችንና የእመቤታችንን በዓላትን እያደረጉ እናቶቻችን የጽንሰቷ፣በጾመ ፍልሰታ እያደረጉ የግድ ከዚህ ውጪ ግን አንድኛውን ከቅዱስ ቁርባን ከራቅን የመተው ያህል ስለሚያስቆጥርብን በዚህ በሁለት ሐሳብ ነው አራርቆ፤ የግል ችግር ቢኖርብንም ጊዜ አርቀን የምንቆርብ ከሆነ አሁን እንደጠቀስኩት በዓመት ውስጥ እነዚህ ሁሉ በዓላት ይጠቀሳሉ፤ በእነሱ ውስጥ ከዚህ ግን ማለፍ የለበትም፡፡ ካሕናት ሁልጊዜ ይቀድሱ አይደለም? ይቆርቡ የለም? ቆርበው እኮ ነው የሚያቆርቡት፡፡ ቀን በቀን የሚቀድሱ፣ ለምሳሌ ተረኛ የሆነ ካሕን ወር ሙሉ ሊቀድስ ይችላል፡፡ ሳምንት ሙሉ ይቀድሳሉ፤ ሳምንት ሙሉ ይቆርባሉ፡፡ እንጂ በቀኖና አትቁረቡ ተብሎ አይከለከልም፡፡ ጨርሶ መተው ነው የሚከለከለው፡፡ በየቀኑ ለምን ቆረባችሁ ሳይሆን፤ ለመቁረብ የሚያስፈልገውን ቅድመ ዝግጅት ራስን ከቁርባን ከሚያስከለክል ነገር መቆጠብ ማራቅ መከልከል ነው የሚጠየቅ እንጂ በየቀኑ ለምን ቆረብክ አያስብልም፡፡ ሁላችሁም ይኼንን ጥያቄ በዚህ ዓይነት ማብራሪያና መልስ እንደተሰጠ እንድትከታተሉት፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ሁላችንንም ከነፍስም ከሥጋም ፈተና ይጠብቀን አሜን
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
ቅዱስ ቁርባንን ከመቀበላችን በፊት፣ በምንቀበልበት ወቅት እና ከተቀበልን በኋላ ማድረግ ስለሚገቡን ጥንቃቄዎች
👉ጥያቄ፦ ከመቁረባችን በፊትና በኋላ ልናደርጋቸው የሚገቡ ነገሮችን ኦርቶዶክሳዊ አስተምሮ በሆነ መልኩ ግለፁ? (ስለ #ቅዱስ #ቁርባን ቅድመ #ዝግጅት እና #ጥንቃቄ)
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ የምክር አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን በሙሉ፤ ከላይ አንድ አባላችን ያቀረቡትን ጥያቄ መሰረት በማድረግ፥ ከዚህ በፊት ስለ ቅዱስ ቁርባን መሠረታዊ የሆኑ ዋና ዋና ነጥቦች የዘረዘርንባቸው ትምህርቶች ስላሉ እነሱን በድጋሚ አቀናጅተን እንደሚከተለው ልከንላችኋልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ እንመክራለን።
በመሰረቱ ማንኛውም ክርስቲያን በ40 ቀን በ80 ቀን በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጅነት ከተቀበሉ ጀምሮ ከቅዱስ ቁርባን እንዲለዩ አይፈቀድላቸውም። ቅዱስ ቁርባን ለነፍሳችን ዘለአለማዊ ህይወት በስጋዊ ህይወታችን ደግሞ በበረከት እና በእግዚአብሔር አጋዥነት እንድንኖር ስለሚረዳን በእግዚአብሔር ፈቃድ በሞት እስከምንጠራበት ዘመን ድረስ ቅዱስ ቁርባን መቀበል ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው። በመንፈሳዊ ህይወታችን ውስጥ በሃይማኖትም በምግባርም ያበረከትናቸው የትሩፋት ስራዎች ሁሉ ማሳረጊያውና መደምደምያው ቅዱስ ቁርባን ነው።
ለቅዱስ ቁርባን የምንበቃባቸው ከአንድ ክርስቲያን የሚጠበቁ መልካም እሴቶች ፦
1/ የንሰሓ አባትቱን በማነጋገር ኀጢአት ካለ ንስሓ መግባት፣
2/ በስጋ ደሙ ከተወሰኑ በኋላ ወደ ኋላ መመለስ አይቻልምና ከቤተሰብዎም ይሁን ከማህበራዊ ኑሮ የሚያገናኙና የሚያጨቃጭቁ ቂም በቀል የሚያመጡ ሃሳቦች እንዳይኖሩ በተቻለ መጠን ሁሉንም ነገር ከመቁረብ በፊት ማስተካከል፣
3/ የተቀየምነው የተቀየመን፣ ያስቀየምነው ያስቀየመን፣ የተጣላነው የተጣላን ማንኛውም ሰው ካለ በንስሓ አባት ወይም በሽማግሌ አማካኝነት ይቅርታ ጠይቆ ቂም በቀልን መተዉ፣
4/ በግል ህይወታችን ሁል ግዜ በቋሚነት የምንጸልየው የጸሎት ፕሮግራም ለኖረን ያሰፈልጋል። ሰይጣን እንዳይዋጋንና በቅዱስ ቁርባን ያገኘነውን በረከት እንዳያሳጣን የምንቋቋምበት መንፈሳዊ ተጋድሎ በጸሎት ስለሆነ ነው፣
5/ ለመቁረብ ሁሉን ነገር አሳክተን ከወሰንን በኋላ ከምንቆርብ 3 ቀን በፊት ወንድ ይሁን ሴት ቤተሰብ ካለ ከግንኙነት (ፆታዊ ግንኙነት) መቆጠብ ያስፈልጋል።
6/ በሰጋ ወደሙ አንድ ሰው ተወሰነ ማለት እንደ ቤተክርስቲያን ስርአት ፈጽሞ ከአለማዊ ጠባይ ወጣ ማለት ስለሆነ በተቻለ መጠን አቀሙ የሚችለውን የበጎ ስራና የርህራሄ ስራ መስራት፣ ቅዱስ ቁርባን በበጎ ስራ መገለጽ ስላለበት ለድኆች ርህራሄ ማድረግ፣ ጠቃሚ የሆኑ መንፈሳዊ ስራ ላይ መሳተፍ፣
ስጋ ደሙን ከመቀበል በፊት አንድ ክርስቲያን ማድረግ ያለበት ጥንቃቄዎች ፦
1. የሚቆርበው ሰው በስርዓተ ተክሊል ጋብቻውን የሚፈፅም ከሆነ በድንግልና ህይወት ተወስኖ ለመኖሩ ራሱን ለካህን አስመርምሮ መቅረብ አለበት።
2. በስርዓተ ጋብቻ ተወስነው የሚኖሩ ባል እና ሚስት ቅዱስ ስጋውን እና ክቡር ደሙን ለመቀበል ከመቁረባቸዉ በፊት ወደ ንሰሐ አባታቸው ቀርበው ንስሐቸውን ተናዘው ከኀጥያታቸው ነፀተዉ መቁረብ አለባቸው።
3. ማንኛውም ክርስቲያን ለመቁረብ ባሰበ ግዜ ከመቁረቡ በፊት ሶስት ቀን፤ ከቁርባን በኋላ ሁለት ቀን ከሩካቤ (ከግብረ ስጋ ግንኙነት ) መከልከል ይገባቸዋል።
4. ስጋውን እና ደሙን ለመቀበል አስራስምንት ሰአት መፆም አለባቸው።
5. ለመቁረብ ያሰበ ምእመን ያልተጠበቀ እንቅፋት ቢያገኘው ማለትም ነስር፣ ትውኪያ፣ የአካል መድማት፣ መቁሰል ፣የተለያዩ ነፍሳት ወደ አፍ መግባት፣ የሴቶች ወርሀዊ ልማድ፣ አጋጣሚ የሆነ ቂም በቀል ( ከሰው ጋር መጣላት) የመሳሰለው ሁሉ ቢያጋጥመው በዚያን እለት መቁረብ የለበትም።
6. በቆረበበት እለት የቀደሰው ካህንም ይሁን ምእመን በተራ ቁጥር አምስት የተዘረዘሩት እንቅፋት ቢያጋጥሙት ንስሐ ሊቀበልባቸው ይገባል።
7. ቅዳሴ ሲጀመር ተገኝቶ ቁሞ ያላሰቀደሰ ሰው እንዲቆርብ አይፈቀድለትም። ስለዚህ ለመቅረብ ስንዘጋጅ ወደ እግዚአብሔር ቤት ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት መድረስ ይኖርብናል።
8. የሚቀበሉት ቅዱስ ቁርባን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አማናዊ ስጋው እና ደሙ መሆኑን አስቀድመው መማር እና ስለ ሚስጥረ ቁርባን ከመምህረ ንስሐቸው ሊማሩ ይገባል። ተምረው ሊቀበሉ ይገባል። ያላመኑትን እና ስለ ቅዱስ ቁርባን ያልተማሩ ሰዎች እንዳይቀበሉ ይከለከላል።
9. በጥመ ህይወት ቀኖና ላይ ያለ ክርሰቲያን ይህም ማለት ለንስሐ አባቱ ንስሐውን ተናዞ የንስሐ ጊዜውን ሳይጨርስ ለሞት የሚያበቃ ደዌ ቢታመም ስጋውን ደሙን ከመቀበል አይከለከልም። ከታመመበት ደዌ ከተፈወሰም ከምእመን ጋር በፀሎት ይሳተፋል፤ የጀመረውን የፀሎት ሱባዔውን ይጨርሳል።
አንድ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን በተቀበለበት እለት ማድረግ ያለበትጥንቃቄ፦
አንድ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን በተቀበለበት እለት በዋናነት ገላውን በውሀ መታጠብ የለበትም ፣ ልብሱን አውልቆ እርቃኑን መሆን የለበትም፣ ከሰውነቱ ደም ማውጣትን የለበትም ከሕግ ጋብቻ ጋር ቢሆንም የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ የለበትም ፣ በሰውነታችን ላይ ፈሳሽ ሊያስከትል የሚችል ከባድ ስራ መስራት የለበትም፣ እሩቅ መንገድ መሄድ የለበትም (እንደ ስራ ስለሚቆጠር) ፣ የሚያሰክር እና የበላነውን የጠጣነውን የሚያውክ መጠጥ መጠጣት የለበትም ፣ ጭቅጭቅ ያለበት አደባባይ ወይም የህዝብ ቦታ መሄድ የለበትም፣ ከሰው ጋር መጨቃጨቅ ሃይለ ቃል መነጋገር በአጠቃለይ ለፀብ የሚጋርድ ስራ እና እነዚህን የመሳሰሉ ሌሎችንም ከቁርባን በኋላ ማድረግ እንደሌለብን በቀኖና ቤተክርስቲያን ተደንግጎ ይገኛል።
ተያያዠና ተጨማሪ ማብራሪያዎች
1. ቅዱስ ቁርባን ከመቀበላችን በፊት ከማንኛውም የስጋ ኀጢአት መራቅ ፤ ማለትም ከዝሙት ድርጊት፣ ከነፍስ ገዳይነት፣ ከስርቆት፣ ከሀሜት፣ ከሱሰኝነት፣ ከአጭበርባሪነት፣ ከሀሰተኛነት፣ እና ከመሳሰሉት የሥጋ ስራዎች መራቅ :: እንዲሁም ቅዱስ ቁርባንን በድፍረት ተቀብለን እዳ እንዳይሆንብን ከመቀበላችን በፊት ወደ ንስኀ አባታችን ቀርበን እራሳችንን ማስመርመርና ተግሳፅ ተቀብለን የንስኀ ቀኖና መውስድአለብን። በተጨማሪም ቅዱስ ቁርባን ከመቀበላችን በፊት በተከታታይ የሚስጢረ ቁርባን ትምህርትን መማር ፤በአጠቃላይ የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ፣ወደ ቤተክርስቲያን መሄድን ማዘውተር፣ መፀለይ፣ መፆም፣ መስገድ ተገቢ ነው። በትዳት ብንኖር እንኳን ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ከ3 ቀን በፊት መቆጠብና ከ18 ሰአት በላይ መፆም፣ የሚያሰክሩ እና አይምሮ የሚያደንዙ መጠጦችን አለመጠጣት እነዚህን የሚመስሉ ተዛማጅ ድርጊቶችን አለመሰራት።
(ይቀጥላል)👇
(ቀጣይ ክፍል)👆
2. ወደ ቅዱስ ቁርባን እና ወደ እግዚአብሔር ቤት ስንቀርብ ራሱን የቻለ ለዚህ አገልግሎት ብቻ የሚውል ሙሉ ልብስ ቢኖረን ይመረጣል። ይህን በማድረጋችን በውስጣችን ፍጹም የሆነ ዝግጅትና ልባዊ ሃይማኖትና ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዳለ ያመለክታልና። ስለዚህ ያንን በቁርባን ጊዜ የለበሱትን ነጠላ ሌላ ጊዜም እያጠቡም መገልገል ይችላሉ። ነገር ግን የተለየ ልብስ ወይም ትርፍ ልብስ የሌላቸው በድህነት ያሉ ክርስቲያኖች ያንን ያላቸውን የድህነት ልብሳቸውን ባላቸው አቅም በንፁህ አጥበው መቁረብ እንዳለባቸው ደግሞ መዘንጋት የለበትም። ምክንያቱም ገና ሀብታሞች እንደሚለብሱት የተለየ ልብስ የለንም በሚል ምክንያት ከቅዱስ ቁርባን እርቀው መኖር ስለማይገባቸው ነው።
3. ቅዱስ ቁርባን በተቀበልንበት እለት በውሀ መታጠብ ወይም መንካት አይገባም ፤ ግን ምናልባት ከአቅም በላይ በሆነ አጋጣሚ ለምሳሌ ዝናብ ቢነካን ወይም ተሳስተን በእጃችን ውሀ ብንነካ ወይም እግራችንን ፈሳሽ ቢነካን ቁርባኑ ይከሽፋል ወይም እንደገና ቀኖና መቀበል ያስፈልገዋል ማለት አይደለም። ምክንያቱም ያ ስርዓት ሆን ብለን አስበን ጥፋት እንዳንሰራ እንጂ በሆነ አጋጣሚ ዘንግተነውም ይሁን ከአቅማችን በለይ በሆነ ጉዳይ ቢደረግ ሃይማኖትን እንዳጎደልን ወይም እግዚአብሔርን እንደካድን የሚያስቆጥርና መቅሰፍትን የሚያመጣ አይደለም። በአጠቃላይ አምልኮተ እግዚአብሔርን በስርዓት እንድናከናውን መመሪያ ሁሉ ነገር ለበጎ ለተግሳፅና ለምክር እንደተፃፈ ማመን አለብን።
4. ቅዱስ ቁርባን የተቀበለ ሰው ከቁርባን በኋላ ብቻውን አይሄድም የሚባለው የቆረበ ሰው ከምንም በላይ ህይወቱ የከበረና መንፈሳዊ ሙሽራ ስለሆነ የተለየ ክብርም ስለሚያስፈልገው ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን አማናዊ ክብር ለማመልከትና ነው። በሌላ በኩል በዚህ ህይወትና መድኅኒት በሆነው በቅዱስ ቁርባን የከበረውን ሰው ሰይጣን በክፉ መንፈስ በጠላትነት ስለሚቃወመው አንደ አንዳንድ ባለስልጣናት ወይም በሙሽርነት የከበረ ሰው ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ እንደሚያስፈልጉት ሁሉ ከዚህም በላይ የሰው ልጅ ፍጹም ሰማያዊ ክብር የሚያገኝበትን ቅዱስ ቁርባን በተቀበለ ጊዜ ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ ስለሚያስፈልገው ብቻ ነው። ከዚህም ጋር ለስጋ ደሙ ክብር ከመስጠት የተነሳ ነው እንጂ ስጋ ደሙን የተቀበለ ሰው ለሌላ አደጋ የተጋለጠ ይሆናል ብሎ ማሰብ የተሳሳተ ነው። እንዲያውም ከምንም በላይ ስጋውን ደሙን የተቀበለን ሰው የአጋንንት መንፈስም ሆኑ ሌላ ሃይል እንዳይቃወመው ታላቅ ግርማ ሞገስና ሃይልና ጉልበት ስለሚሆነው ብቻውን ስለሄደ ችግር ያጋጥመዋል ብሎ ማመን የተሳሳተ ሃሳብ ነው። በየገዳማትም ሆነ በየአብያተክርስቲያናት ቅዳሴ አስቀድሰው ቅዱስ ቁርባን የሚቀበሉና የሚያቀብሉ ብቻቸውን አገር አቋርጠው ሲሄዱ እነሱ ለሌላው ክብርና ሞገስ ይሆናሉ እንጂ በነሱ ላይ የሚደርስባቸው አንዳችም ክፉ ነገር የለም።
5. ‘ከቆረብን በኋላ የለበስነውን ልብስ መቼ ነው መቀየር ያለብን ወይስ ለብሰነው ነው ወይ የምናድረው?’ ብለው ለሚጠይቁ፤ በመሰረቱ የአንድ ቀን ቁጥር የሚጀምረው ከዋዜማው ወይም ከማታው 12 ሰአት ጀምሮ እስከ የቀኑ 12 ሰዓት በድምሩ 24 ሰዓት 1 ቀን ይባላል። በዚህም መሰረት ሲቆርቡ የለበሱትን ልብስ ማታ የተቀበሉበት ቀን ማታ ማለትም ከ 12 ሰአት በኋላ ወይም የእለቱ ሰአት ሲጠናቅ መቀየር ይችላሉ።
6. የማቁረሪያ ምግብ እስከሚቀምስ ድረስ ከሰው ጋር መነጋገር የማይችልበት ምክንያት መለኮታዊ እሳት የተዋሀደውን ቅዱስ ሥጋና ክብር ደሙን በተቀበለ ጊዜ ለነፍስ መድኅኒት ለስጋም በረከትን የሚያመጣውን የከርስቶስን ስጋውንና ደሙን ተቀብሎ ሌላ የሰውኛ ንግግርን መነጋገር ሃሳብን ማውጣትና ማውረድ ፈፅሞ ስለማይፈቀድ ነው። ከቅዱስ ቁርባን በላይ የሚከብር ነገር ባለመኖሩ በብዙ ፈተና የረከሰውን ህይወታችንን የቀደሰውንና የተዋረደውን ማንነታችንን ያከበረውን ቅዱስ ቁርባን ማቃለል ለኛም ከቅዱስ ስጋውና ከክቡር ደሙ ያገኘነውን ክብር ስለሚያሳንስብን ባጠቃላይ አፋችንን የመሸፈናችን ነገር ክፉ ከመናገር፣ ክፉ ከማሰብ፣ ክፉውን ድርጊት ከመፈፀም የራቅን ለመሆናችን የሚያመለክት ስርዓት ነው። ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ እህል ውሀ ቀምሰንም ቢሆን ከአንደበታችን የሚወጣው ነገር የተቀደሰና በጎ ነገር ሊሆን ይገባዋል ወይም ክፉ ሃሳብና ክፉ ድርጊት ከኛ እንዳይወጣ ያስፈልጋል ለማለት ነው።
በአጠቃላይ ዋናው ምክንያት የእግዚአብሔርን ቅድስና ወይም ቅዱስ ቁርባን ለማርከስ የሚችል ሌላ ነገር ኖሮ ሳይሆን፤ እኛ ግን ከክርስቶስ ስጋና ደም ጋር ስለተዋሀድን በኛ አላማ በቅናት ያበደው ሰይጣን ሊፈትነንና በሚያጠምደው መሰናክል ሊጥለን ስለሚችል ከሁሉ ነገር ተቆጥበንና ተሰብስበን ለዘላለማዊ ድህነት የወሰድነውን የክርስቶስን ቅዱስ ስጋና ክቡር ደም በልዩ ስርአት አክብረን የተወሰነውን ጊዜ ማሳለፍ ስላለብን ነው። ሰይጣን ብዙ ጊዜ እኛን የሚጥልበት መሰናክል ረቂቅ ስለሆነ ክርስቲያናዊ ንቃት ኑሮን መጠንቀቅ ስለሚያስፈልግ ነው።
ለቅዱስ ቁርባን ከበቁ በኋላ ተመልሰው በኀጢአት ከተሰናከሉ ማድረግ የሚገባዎት ነገር
ንስኀ ገብተው ለቅዱስ ቁርባን ከበቁ በኋላ ተመልሰው በኀጢአት ከተሰናከሉ ወይም ሲቆርቡ ኑረው በመካከል ወደ ቅዱስ ቁርባን የማያቀርብ ነውር ካጋጠመዎት ለጊዜው መቁረብዎን አቁመው ወደ ንስኀ አባትዎ ቀርበው የፈጸሙትን በደል ከተናዘዙ እና ንስኀዎትን ከጨረሱ በኋላ ለመቁረብ መቀጠል ይችላሉ። ምክንያቱም አንድ ሰው ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ እዳ በደል እንዳይሆንበት አስቀድሞ ከኀጢአት እና ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ ከሚከለከልባቸው ጥፋቶች መራቅ አለበት። ምክንያቱም ቅዱስ ቁርባን ከተቀበለ በክርስቲያናዊ ህይወት ውስጥ የመጨረሻው ክብርም ላይ የደረሰ ሰው ነውና፤ ይሄንን ታላቅ ክብር በማቃለል ተመልሶ የማይገባውን ነውር መፈፀም ማለት ግን ታጥቦ ጭቃ እንደማለት ይቆጠራልና ተመልሰን ንስኀ መግባት ብቻ ሳይሆን የንስኀውም ደረጃ እጥፍ ድርብ ሊሆን እንደሚችል ተገንዝበን ራሳችንን በመግዛት በምግባርና በሃይማኖት ጸንተን ለመኖር መታገል አለብን፤ በኀጢአት ከወደቅንም ቶሎ በንስኀ ልንነሳ ያስፈልጋል። ሆኖም ጥፋቱን በመደጋገም ሁል ጊዜ በንስኀ እመለሳለሁ በሚል መንፈስ መሄድ እንደሌለብን የቤተክርስቲያን ቀኖና ይደነግጋል። ዋናው ቁም ነገር ግን ማንኛውም ክርስቲያን በምንም ይሁን በምን ከቅዱስ ቁርባን ላለመለየት በየጊዜው መንፈሳዊ አላማውን በማጽናት መታገል እንዳለበት እንመክራለን።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ስለ-ቅዱስ-ቁርባን ላይ ያገኛሉ
👉🏾👉🏾👉🏾 ስለ #ምስጢረ #ቅዱስ #ቁርባን
👉የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ወዳጆች በዮሐንስ ንስሐ ድህረገጽ የሚተላለፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት በያላችሁበት የምትከታተሉ በእግዚአብሔር ሰላምታ ሰላም እንላችኋለን፣ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን እያልን ዛሬ በርእሱ እንደተጠቀሰው “ምስጢረ ቁርባን” በሚል ርዕሰ ነው የምንናገረው አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን፣
✍ ዛሬ የምንማረዉ ስለ “ምስጢረቁርባን” ነዉ፣ ምስጢረ ቁርባን ከአምስቱ አእማደ ምስጢራት እንዱና ዋናዉ ነዉ፣
አምስቱ አእማደ ምስጢራት ማለት:-
1ኛ ምስጢረ ሥላሴ፣
2ኛ ምስጢረ ሥጋዌ፣
3ኛ ምስጢረ ጥምቀት፣
4ኛ ምስጢረ ቁርባን፣
5ኛ ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን ናቸዉ።
ዛሬ የምናየዉ ከዘረዘርናቸዉ መካከል ተራ ቁጥር 4ኛ ላይ የምናገኘውን ስለ ምስጢረ ቁርባን በተመለከተ ይሆናል፤
የበለጠ ግልጽ እንዲሆን በሦስት ከፍለን ማየት ይኖርብናል፦
1ኛ ቅድመ ቁርባን/ከቁርባን በፊት/
2ኛ ጊዜ ቁርባን/በቁርባን ጊዜ/
3ኛ ድህረ ቁርባን/ከቁርባን በኋላ/
* ቅድመ ቁርባን ( ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል በፊት) መሆን ያለበት፦
1ኛ ስለ ምስጢረ ቁርባን መማር፣ የቀደሙት ሰዎች ሲቆርቡ ተጠይቀዉ ነበር የሚቆርቡት የተማሩ ስለነበሩ ይመልሳሉ፣ “ከመጠምጠም መማር ይቅደም” አባቶች ይላሉ፣ ቅድሚያ መማር ክርስቲያናዊ ግዴታ ነዉ ፣እሳት ማህያዊ ለርቱዓነልብ ለእለይገብሩ ፈቃዶ እሳትም ብየ ብላቹህ አንድነቱን ሶስትነቱን አዉቀዉ ህማሙን ሞቱን አምነዉ፣ ኃጢአታቸዉን ለንስሐ አባታቸው ነግረዉ፣ ንስሐ አባታቸዉ ያዘዛቸውን በሚገባ ለሚቀበሉ ሰዎች የሚያድን እሳት ነዉ፣ እሳትን በመጠኑ የሞቁት እንደሆነ የበሉት የጠጡትን ያስማማል ሥጋ ወደሙም ከኃጢአት ነጽተዉ ቢቀበሉት ሕይወተ ሥጋ፣ ሕይወተ ነፍስ ይሆናል ደዌ ነፍስ ያርቃልና።
2ኛ ማመን ነዉ፦ ህብስቱ ተለዉጦ ሥጋ ወልደ እግዚአብሔር፣ ወይኑ ተለዉጦ ደመ ወልደእግዚአብሔር እንደሚሆን ማመን ክርስቲያናዊ አስተምህሮ ነዉ፤ ኦ ማርያም በእንተ ዝናፈቅረኪ ወነዓብየኪ “ስለዚህ ማርያም ሆይ እናከብርሻን እናገንሻለን፣ አሁን እኛ እመቤታችን የምናገናት፣ የምናከብራት ሆነን አይደለም፣ ክብርሽን ገናንነትሽን እንናገራለን ሲል ነው እንጂ፣ እስመወለድኪ ለነ መብልዐጽድቅ ዘበአማን ወስቴሕይወት ዘበአማን እውነተኛውን ምግብ እና መጠጥ አስገኝተሽልናልና እውነተኛ አለ ከኦሪቱ ሲለይ ያ ሥጋዊ ነዉ፣ ይህ መንፈሳዊ ነውና፣ ያ አፋዊ ነዉ ይህ ውሳጣዊ ነውና፣ ያ ምድራዊ ነው ይህ ሰማያዊ ነዉና፣ ሲቀጥል እውነተኛ አለ ከዚህ ዓለም መብል መጠጥ ሲለይ ነዉ።
የዚህ ዓለም ምግብ ኃሠር ይሆናል፣ ይለወጣል በሱ ግን ይህ ሁሉ የለበትምና የዚህ ዓለም ምግብ ሞትን ያስከትላል፣ ሥጋ ወደሙ ግን ሕይወትን ይሆናልና፣ የዚህ ዓለም ምግብ ጧት በልቶ ለማታ፣ ማታ በልቶ ለጧት ያስፈልጋል፣ ሥጋ ወደሙ ግን ንስሐ ገብተዉ ከኃጢአት ርቀዉ በሚገባ ቢቀበሉት በኃጢአት ካላሳደፉት ህማሙን ሞቱን ለማሰብ ነው እንጂ፣ አንድ ጊዜ ከተቀበሉት ለሌላ ጊዜ አያስፈልግምና ሊቁ አባ ህርያቆስ እንዲህ ይላል እሳት በላኢ ለአማጽያን ለእለይክዱ ስሞ “ስመ አምላክነቱን ለሚከዱ ሰዎች የሚያቃጥል እሳት ነው” ስመ አምላክነቱን ከካዱ የማን ሥጋ የማን ደም ብለዉ ይቀበሉታል ቢሉ? ስመ ቁርባንነቱን ለሚክዱ ሰዎች ስመ ቁርባንነቱንስ ከካዱ ምን ይረባናል ምን ይጠቅመናል ብለዉ ይቀበሉታል ቢሉ?ብግብሩ መካድ አለና፤ ከኃጢአት ሳይነጹ ንስሐ ሳይገቡ ቢቀበሉት በፍዳ ላይ ፍዳ የሚያመጣ ስለሆነ፣ እሳት ነበልባሉ ከወረደው ፍህሙ ከመረተዉ ቀርበው ያለመጠን ቢሞቁት ያቃጥላል፣ ሥጋ ወደሙንም በማይገባ ቢቀበለት ፍዳ ያመጣልና 1ኛቆሮንቶስ ምዕራፍ 11 ቁጥር 28።
3ኛ ንስሐ መግባት እና ቀኖናን መፈጸም፦
4ኛ 18 ሰዓት መጾም፣ 18 ሰዓት የሆነበት ምክንያት ክርስቶስ የተያዘዉ ሐሙስ ማታ ምሸት3 ሰዓት ነዉ፣ የተያዘዉ ዓርብ ዘጠኘ ሰዓት ነዉ ያረፈዉ (ቅድስት ነፍሱ ከቅዱስ ሥጋው የተለየችው) ከዚያ ጀምሮ ስንቆጥር 18 ሰዓትት ይሆናል የክርስቶስን መከራ መሰረት ያደረገ ነው፣ ህጻናትን እና ህሙማን አይመለከትም። ከሰባት ዓመት በኋላ ንስሐ አባት መያዝ የግድ ነዉ፣ ህጻናት እሁድ እና ቅዳሜ ቢቆርቡ ይመረጣል።
5ኛ በጋብቻ ያሉ ሰዎች ከሩካቤ ሥጋ ለ3 ቀናት መከልከል፣ 1ኛ ሳሙኤል ምዕራፍ 21 ቁጥር 5 ሐዋርያት እና ሶስት መቶ አስራ ስምንቱ ሊቃዉንት በስርዓት አስቀምጠዋል ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን ምዕራፍ 13 ቁጥር 4
ጋብቻ ክቡር ነው፣ መኝታዉም ንጹህ ነዉ ብሏል፣ ይህን እናምናለን፣ ግን በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት የበረታ ሰውነት ይዘን እንቀርብ አለን እንጂ በሩካቤ ሥጋ የፈዘዘ እና የደነዘዘ ሰዉነት ይዘን መቁረብ፣ (መቅረብ ተገቢ አይደለም፣ምክንያቱም አቁራቢው /ካህኑ/ክርስቶስን መስሎ ቆራቢዎቹ እኛ ሐዋርያትን መስለን ስለምቀርብ ማለት ነዉ።
6ኛ ንጹህ ልብስ መልበስ፦ ዘፍጥረት ምዕራፍ 5 ቁጥር 2
7ኛ ጊዜ ቁርባን ከቅዳሴ በፊት ቀድሞ መገኘት፦ ይህ ማለት ከቅዳሴ በፊት ኪዳን ማስደረስ እና ቅዳሴ ሳይገቡ መገኘት ማለት ነዉ።
ቅዱስ ጳውሎስ 1ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 14 ቁጥር 40 ሁሉ በአግባብ እና በስርዓት ይሁን እንዳለ፦
1ኛ የ40 80 ቀን ህጻናት፣
2ኛ የ6 ዓመት የ7 ዓመት ህጻናት፣
3ኛ በድግልና የመነኮሱ መነኮሳት፣
4ኛ የ20 የ22 ዓመት ወጣቶች፣
5ኛ በንስሐ የመነኮሱ አባቶች፣
6ኛ ሕጋዉያን፣
7ኛ ተነሳህያን እንደየ ማእረጋቸዉ ይቀበላሉ፣ ሴቶችም እንዲሁ ይቀበላሉ ማለት ነዉ።
ድህረቁርባን
1ኛ መታጠብ ክልክል ነዉ፣
2ኛ ልብስ መቀየር ክልክል ነዉ፣
3ኛ መስገድ ተገቢ አይደለም፣ በመንግሥተ ሰማያት ድካም አለ ስለሚያሰኝ ነዉ፣
4ኛ ምራቅ መትፋት አግባብ አይደለም፣
5ኛ ጥፍር መቁረጥ የተከለከለ ነዉ፣
6ኛ ከመጠን በላይ መብላት ስርዓት አይፈቅድም፣ ወ.ዘ.ተ.
በኃጢአት ገደል የወደቅን በንስሐ ምርኩዝ ተነስተን ቅዱስ ሥጋዉን ክቡር ደሙን ተቀብለን የመንግሥቱ ወራሾች እንድንሆን አምላከ ቅዱሳን ቸሩ መድኃኔዓለም ይርዳን፣
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን
መምህር ስሙር ጌትነት
©ዮሐንስ ንስሐ
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር አድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾ለ #ቅዱስ #ቁርባን ስለሚደረግ #ጥንቃቄ
👉ጥያቄ፡- ሰላም ለእናንተ ይሁን አባቶች አንድ ሰው ከቆረበ በኋላ መሳሳም፣ ውኃ መንካት፣ ሳያቆሩ መናገር አይችልም ለምንድን ነው? ምሳሌነቱስ ምንድን ነው? በእግዚአብሔር ስም አስረዱኝ፣ ቢቻል መልስ በፍጥነት፤
✍መልስ፡- ቤተክርስቲያን ለሁሉ ነገር መልስ አላት እንደምንለው ሁሉ፤ በፍጥነት ለመመለስ ግን በመምህራን በመፃህፍት፣ የሚመለሱ መልሶች አሉ፣ ጊዜውን ጠብቆ የሚመለስ መልስ አለ፣ እንዲሁም ደግሞ በማንበብ የሚመለስ መልስ አለ፣ በእድሜ የሚመለስ ጥያቄ መልስ አለ፣ እንዲሁም ደግሞ ሞት የሚመልሰው መልስ አለ፣ ስለዚህ ለሁሉም ጥያቄ በጊዜው እለቱኑ መልስ ማግኘት አይቻልም፡፡
በእርግጥ እንዳልነውም መልስ የሌለው ጥያቄ የለም፣ ነገር ግን የመልሱ ዓይነት ግን ይለያያል፣ ለምሳሌ አንድ ሰው መንግሥተ ሰማያት እንዴት ነች? ብሎ ቢጠይቅ እንዲህ ናት ብለን ብንመለስ ላይረዳው ይችላል፣ በጊዜው መልሶች የማይገኝላቸው እንዲህ ዓይነት ጥያቄዎች አሉ ማለት ነው፡፡
ቤተሰባችን የጠየቁት ጥያቄ መሠረታዊና መጠየቅ ያለበት ነው፣ በመጀመሪያ መቁረብ ማለት ምንድን ነው? የሚለውን በተወሰነ መልኩ እንመልከት፣ ቸሩ መድኃኔዓለም በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ቁጥር 54 ጀምሮ እንደተናገረው “ሥጋየን የበላ፣ ደሜን የጠጣ የዘለዓለም ህይወት አለው፣ ከእኔ ጋር ይኖራል፣ እኔም ከእርሱ ጋር እኖራለሁ” ብሏል፡፡
የቆረበ ሰው ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የተቀበለው የቸሩ መድኃኔዓለም ነው፣ ይህ ማለት ደግሞ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የተቀበለ ሰው ከመድኃኔዓለም ጋር እየኖረ ነው፣ እርሱ እንደነገረን “ከእኔ ጋር ይኖራል” ነው ያለን፣ በኃጢአት ቢወድቁ በንስሐ ተነስተው ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መቀበል በጣም መታደል ነው፣ ከዚህ የበለጠ ክርስትና የለም፡፡
ስለዚህ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የተቀበለ ክርስቲያን መሳሳም ለምን አስፈለገው? መሳሳሙ የግድ ነው ወይ? ፍቅር ክርስቶስ ነው፣ ከክርስቶስ ፍቅር ጋር የተዋሐደ አካል ከዓለማዊ ፍቅር ጋር ምን አስፈለገ? እኛ በዚህ ዓለም የምንጾመው፣ የምንጸልየው፣ የምንሰግደው፣ የምንመፀውተው የክርስቶስን ፍቅር ለማግኘት ነው፣ ሰዎችን ብንወድም ፍቅረ ክርስቶስን ለማግኘት ነው፡፡
ስለዚህ ስንቆርብ ከክርስቶስ ጋር አንድ ነው የሆንነው፣ የተዋሐድነው፣ በዚህ ላይ ቅዱስ ሥጋውን፣ ክቡር ደሙን በተቀበልንበት እለት ማሰብ ያለብን የማይሞተው አምላክ ለእኛ ብሎ የሞተውን፣ ለእኛ ብሎ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ግርፋት ተገርፎ፣ በቀራንዮ አደባባይ ላይ ውሎ፣ ቅዱስ ሥጋውን ቆርሶ፣ ክቡር ደሙን አፍስሶ ዘላዓለም ህይወት የሰጠንን አምላክ መከራውን ማሰብ ነው ያለብን፡፡
ቅዱስ ሥጋውን፣ ከቡር ደሙን በተቀበልንበት እለት ምድራዊ ነገርን፣ ጨዋታ አሉባልታ የምናስብበት ሰዓት አይደለም፣ መከራውን ነው ማሰብ ያለብን፣ እኛን ለማዳን ብሎ ለእኛ ብሎ ሰው ሆኖ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ሰጥቶን እያለ፣ ፍቅር ክርስቶስን ስመን እያለ፣ ከእሱ ጋር ተዋህደን እያለ ሌላ ፍቅር ፍለጋ መሄድ አይኖርብንም፡፡
የክርስቶስ የቆሰለው ጀርባው፣ የተገረፈው፣ የተቸነከሩት እጆቹ፣ እግሮቹ፣ ያንን እያየን ማልቀስ፣ ማዘን ነው ያለብን እንጂ መሳቅ መደሰት አይኖርብንም፣ በእሱ መከራ ብንድንም እንኳን የማይሞተው አምላክ ሞቶ እኛን ሰው ስላደረገልን እያዘንን፣ ማሳለፍ ይኖርብናል ማለት ነው፡፡
ውኃ መንካት፣ ወይም መነጋገር ላሉት ጥያቄዎ ደግሞ፡- ውኃ ንፁህ ነገር ነው፣ ቢታጠቡት ያፀዳል፣ ቢጠጡት ያረካል እና እኔ ንፁህ ነኝ፣ ንፁሐ ባህርይ ነኝ ሲል ውኃን ፈጠረ፣ ስለዚህ ከንፁሁ ከቅዱሱ ጋር ሆነን ውኃ አያስፈልገንም ማለት ነው፣ ውኃ ልንካ ካልን ሌላ የሚያነፃን፣ የሚቀድሰን፣ የሚያከብረን ያስፈልገናል ማለት ነው የሚሆነው፡፡
ስለዚህ እኛ ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን ያለነው ከንፀሁ፣ ከክቡሩ፣ ከቅዱሱ ጋር ስላለን እሱም እግዚአብሔር ስለሆነ ውኃ አያስፈልገንም ማለት ነው፣ ውኃን የፈጠረ ፈጣሪ ነው፣ መተርጉማን አባቶቻችን ቅዱስ የሚለውን ቃል ሲረጉሙ ” ቅዱስ ማለት ንፁህ፣ ክቡር፣ ልዩ ” ማለት ነው ይላሉ፡፡
ሰውን ክቡር ቢሉት የራሱ አይደለም ከእግዚብሔር ባገኘው ገንዘብ ነው፣ እግዚአብሔር ግን ክቡር የማይሉት የከበረ፣ የማይሰጡት ባለፀጋ፣ የማይሾሙት ንጉሥ ነው፣ ጌታ የማይሉት ጌታ ነው ይሉና፤ አባቶቻችን ንፁህ የሚለውን ሲተረጉሙት ሰውን ንፁህ ቢሉት እንደ ነጭ ልብስ ነው፣ ነጭ ልብስ ቀይ፣ ጥቁር ቀለም ቢቀቡት ሌላውንም ነገር ሁሉንም ይቀበላል፣ ሰውም ኃጢአቱም ፅድቁም ይስማማዋል፣ እግዚአብሔር ግን ፅድቅ እንጂ ኃጢአት አይስማማውም፣ ይላሉ፡፡
ስለዚህ ከእግዚአብሔር ንፁሐ ባህርይ ነው፣ ከንፁሁ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ ሆነን፣ ተዋህደን እያለን ሌላ ውኃ ለምን ያስፈልገናል? ንፁሐ ባህርይ የሆነውን እግዚአብሔርን መዋሃዳችን ለማጠየቅ፣ ከእሱ ጋር አንድ መሆናችንን ለማስረዳት ውኃ የማያስፈልገን የሆነው ለዚህ ነው ማለት ነው፡፡
እንዲሁ ምግብ ሳይቀምሱ መቆየት፣ ሳይነጋገሩ መቆየት፣ ምስጢሩ ኋላ ሞተን ተነስተን በምንኖርበትን ዓለም፣ በመንግሥተ ሰማያት መብላት፣ መጠጣት እንደሌለ ለማስረዳት ነው፣ በዚያ ዓለም መኖር የሚቻለው፣ ዛሬ በንስሐ ለዚህ ተዘጋጅቶ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብሎ ለዚህ በቅቶ ነው፡፡
ስለዚህ ያንን ኑሮ መኖር እንዳለብን ለማስረዳት፣ እንደምንኖር ለማሳየት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለን ለተወሰነ ጊዜ ምግብ መመገብ አያስፈልገንም ማለት ነው፣ ይሄ ማለት ምግብ ሳንመገብ ምንም አናወራም፣ ቀምሰን ነው የምንነጋገረው እስከዚያው ዝም ብለን መቆየታችን ኋላ ሞተን ተነስተን የምንኖረው ኑሮ ያለ ምግብ መሆኑን ያሳያል፡፡
ምግብ መቅመሳችን ደግሞ ይህቺን ዓለም ገና ትተናት ስላልተሰናበትን የመጨረሻ እስከምንሄድ ድረስ ምግብ ስለሚያስፈልገንና መመገብ እንዳለብን ለማስረዳት ነው፣ ይህቺ ዓለምን እስክታልፍ ድረስ ምፅዓት እስኪሆን ድረስ እየቀመስን እንቆያለን፣ የሚሞተው እየሞተ፣ ያለው ቀጣዩ ትውልድ ደግሞ እየበላ ይቆያል ማለት ነው፡፡
ሌላው አለመብላታችን ደግሞ በዚያኛው ዓለም ሙሉ በሙሉ የዓለም ፍፃሜ ሲሆን መብላት መጠጣት የሌለ መሆኑን ለማስረዳት ነው፣ ክርስቶስን እየተዋሃድን ነው፣ የነበርንበት ዓለም ሌላ ስለነበር፣ በዚያኛው ዓለም ግን መብላት የማያስፈልግ መሆኑን ለማሳየት ሳንመገብ እንቆያለን ማለት ነው፣ ውኃም ቢሆን ክርስቶስን ይዞ መጠማት የለም፣ መብልም ቢሆን ክርስቶስን ይዞ መራብ የለም።
ስለዚህ ቤተሰባችን በዚህ ልክ እንዲረዱት እንላለን፣ በጥቅሉ ግን መብልም መጠጥም ክርስቶስ መሆኑን ማወቅ አለብን፣ እና ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ስንቀበል ያለ ክርስቶስ የሚያሳየው ትልቁ ምስጢር መጨረሻው፣ ምስጢር የሚሆነው ግን ሁሉ በክርስቶስ መሆኑን ያጠይቃል፣ ይሄ ማለት ከክርሰቶስ ጋር ያለ ሰው ሁሉ በእጁ፣ ሁሉ በደጁ ነው ማለት ነው፡፡
ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር እግዚአብሔር ያብቃን፣ በኃጢአት የወደቅን በንስሐ ተነስተን፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ያልተቀበልን እንድንቀበል እግዚአብሔር ይርዳን፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የተቀበልን ደግሞ በቤቱ እስከ ፍፃሜ ድረስ ፀንተን መንግሥቱን እንድንወርስ ቸሩ መድኃኔዓለም ይርዳን፣ ይቆየን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር አድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፡- ሰላም አባታችን ለእርስዎ ለመምሕራችን መልካም ልቦና፤ ለእኛም አስተዋይ ልቦና ያድለን፣ እኔ ንስሐ ገብቻለሁ ለመቁረብ ፈልጌ ተዘጋጅቼያለሁ፣ #ለመቁረብ (ቅዱስ #ቁርባን) ምን ማድረግ ነው ያለብኝ? እባክዎትን አባቴ ይንገሩኝ? #ዝግጅት
✍መልስ፡- እግዚአብሔር ይመሰገን ንስሐ ገብተዋል፣ ለመቁረብ ተዘጋጅተዋል፣ አሁን የሚያደርጉት የመጀመሪያ የመቁረቢያ ጊዜ መቼ እንደሚሆን ቢችሉ፣ ነገር ቢመቻችልዎት፣ የማይከበድዎት ከሆነ አባትዎትን ያግኙ፣ ያነጋገሩ፡፡
መቼ መቁረብ ይሻላል? ቀዳሜ ልቁረብ? እሁድ ልቁረብ? የማርያም እለት ልቁረብ? የገብርኤል ቀን፣ የሚካኤል ቀን ልቁረብ? ብሎ መነጋገሩ የበለጠ ፍቅር ያበዛል፣ የበለጠም ውስጥዎትን ደስታ ያበዛልዎታል፡፡
አለበለዚያ ቀኖና ገብተው፣ ቀኖናዎትን በሰላም ካስፈጸሙ ለቅዱስ ቁርባን ከተዘጋጁ፣ መብትም፣ ነጻነትም፣ የእግዚአብሔር ፈቃድም ስለሆነ፣ ሌላ ምክንያት የሌለበትን ጊዜ ወይም ቀን መርጠው ሔደው መቁረብ ይቻላሉ፡፡
ያንን ስንል ረዥም ጊዜ አያስፈልግም፣ ረዥም ቀጠሮ አያስፈልግም፣ ሁልጊዜ እንደምንለው የመዳን ቀን ዛሬ ነው፣ ያውም አሁን ነው ተብሏል፡፡ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል እኛ በልጅነት መንፈስ ነፃነቱ አለን፣ በአምላካችን፣ በፈጣሪያችን፣ በአባታችን በእግዚአብሔር ቤት እኛ በልጅነት መንፈስ የምንመላለስ ነን፡፡ እንደ ባሪያ ሆነን አይደለም፣ እንደ እንግዳ ሆነን አይደለም፣ የመንግሥቱ፣ የሐብቱ ወራሾ ሆነን ነው የምንመላሰው፣ ስለዚህ ችግሩ ከእኛ ካልሆነ በስተቀር የተነፈገን መብት የለም፡፡
ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያ ሔደን በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ቆመን፣ አስቀድሰን፣ ሰውነታችን ሁሉ ከእርኩሰት አንፅተን፣ ቀድሰን፣ በውስጣችን ፈረሐ እግዚአብሔር ኖሮን መቁረብ ብቻ ነው፡፡
ከቁርባን በፊት መደረግ ስለሚገባው ነገር ያው ንስሐ የገባ ምዕመን ትክክለኛውን መንገድ ተከትሎ ሄዷል፣ የቀረው ቅዱስ ቁርባን መቀበል ብቻ ነው ማለት ነው፡፡
ንስሐ የሰጡን አባት ደግሞ ሁሉን ነገር፣ ለቅዱስ ቁርባን የሚኖረን ክብር አስቀድመን ሊሆን የሚገባንን፣ በቆረብን ጊዜም መሆን የሚገባንን፣ ከቆረብን በኋላ የምናደርገው ጥንቃቄ ሁሉ ፣ ብዙ ጥንቃቄዎች አሉ፣ ግን ደግሞ የማይከብዱ ናቸው፡፡ የታወቁትን ሁሉም ሰው የጋራ ኃጢያት ያደረጋቸው፣ ከከዝሙት፣ ከነፍሰ ገዳይነት፣ ከስርቆት፣ ከሌላ ከታወቁ ሰውን ቅድስናውን ሊያረክስ ከሚችልበት ኃጢያት ብቻ መጠበቅ ሳይሆን፣ በቆራቢነት ጉዟአችንም መጠንቀቅ የሚገባን ነገር አለ፡፡
ከቆረቡ በኋላ ጭቅጭቅ ውስጥ፣ ፍቅር ነዋይ ውስጥ፣ ከመግባት፣ ጾም ከመሻር ፣ እነዚህን ከሚመስሉ ከባድና ጥቃቅን የሆኑ የስነምግባር ግድፈቶች መጠበቅ ስላለባቸው በቀጣይነት ልንወያይ እንችላለን፡፡
በእርግጥም እግዚአብሔር ይመስገን፣ አሁን የሰይጣንን እግሩን ስብረውታል፣ ታግለው አሸንፈውታል፣ የድሉን እክሊል ሊቀዳጁ አንድ ቀን ቀርቶዎታል ማለት ነው፣ ይቁረቡና ያንን ለሁላችንም የሚያስደስተውን የምስራቹን ቃል ያበስሩናል ማለት ነው፡፡
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን
ለተጨማሪ ግንዛቤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ያስተላለፍናቸውን መልእክቶች እንዲመለከቱ ሊንኮቹን እንደሚከተለው አያይዘናል👇👇👇
.
https://t.me/c/1172495782/32899
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾👉🏾👉🏾 #ቅዱሰ #ቁርባን ለመቀቀል የሚደረግ ቅድመ #ዝግጅት
የክርስቶስን ክቡር ሥጋና ክቡር ደም ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት ያስፈልጋል፡፡ ከእነዚህም :
ኢአማኒ ከሆነ አስቀድም ሳያምን ሳይጠመቅ ሥጋውን ደሙን ይቀበል ዘንድ አይፈቀድለትም: ምክንያቱም ኢአማኒ ከሆነ አስቀድሞ ማመን ከዚያም መጠመቅና በቅብዓተ ሜሮን መክበር ያስፈልገዋልና፡፡ ምስጢራትም የራሳቸው የሆነ ቅደም ተከተል አላቸውና፡፡ አንዱን ካንዱ ማስቀደም ማስተላለፍ አይቻልም፡በመሆኑም ክርስቲያን ሁሉ በተወለደ በዓርባና በሰማኒያ ዕለት ተጠምቆ ሥጋውን ደሙን የሚቀበል መሆኑ ቢታወቅም ‹ሰው ሁኖ የማይበድል እንጨት ሁኖ የማይጤስ›› የለም እንደሚባለው ነቢዩ ዕዝራም ‹‹አሁንም ከተወለደው ወገን የማይበድል እንደሌለ እውነት እናገራለሁ›› እንዳለ ዕዝ ሱቱ :6:35
አፈ ወርቅም ስለሰው ጠባይዕ ሲናገር ‹ከዲያብሎስ በቀር ጥቂት በጎነት የሌለው ክፉ (ሰው) – አይገኝም፡፡ ዳግመኛም ከእመቤታችን በቀር ጥቂት ክፋት የሌለበት ፍጹም ደግ ሰው አይገኝም፡፡
‹ስለ እኛ ሰው ከሆነው ከአንዱ ከእግዚአብሔር ቃል በቀር አንድ ሰዓት ስንኳ ያለ ኅጢአት የሚኖር ሰው የለምና›› ዲድ አን 6:19
መዝሙረኛው ንጉሥ ‹‹ ከራሴ ጀምሮ ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው አልሁ›› መዝ 115:2
ነገር ግን ምንም ቢሆን ሥጋውን ደሙን ለመቀበል የማይዘጋጀውን ሰው ‹በሃይማኖት(አምኖ) ለጥምቀት ያልበቃ ሰው አማኒ እንደማይባለው ሥጋውን ደሙን ለመቀበል በንጽሕና ያልተዘጋጀ ሰው አማኒ አይባልም፡፡ ወይም የጌታ ሥጋ የጌታ ደም እንደሆነ አያምንም››፡፡ ሙቀት የውሃን እርጥበት ካወቅንበት ጊዜ ጀምሮ ፍልስጣ የሚባል ክፉ ተመያኒ ግብዝ ሰይጣን አለ፡፡ ዕለት ዕለት የምንሠራውን ይመዘግባል ‹‹፦በሞትን ጊዜ ያሳየናል፡›› በምንሞትበት ጊዜ ያን እያሳየ ይካሰሰናልና፡፡
በጎልዮ፣በገቢር፣በነቢብ የተሠራው ኃጢአት ሁሉ ያስፈርዳል፡፡ ከዚህ ፍርድ ለመዳን ብቸኛው መንገድ በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን እየኖሩ በንስሓ እየታደሱ ሥጋውን ደሙን መቀበል ነው::‹በልቡ ሽንገላ ሳለ ጐርባን ለመቀበል የሚተጋ ሁሉ የይሁዳ ባልንጀራ ነው ንጉሥን ወዳልተጠረገ ቤት ያስገቡታልን? እሾህና አሜከላንስ ይጎዘጐዙለታልን? ንጹሕ ክርስቶስ የሥጋውም መንጻት ድንቅ ነውና በቀልን ወደ ተመላ የሥጋ አዳራሸ ይገባ ዘንድ ለእርሱ የተገባ አይደሰም…›› እንዳሉ አባ ጊዮርጊስ መጽ ምሥጢር 24:20-23
ሥጋውን ደሙን ለመቀበልም ኃጢአትን ለመምህረ ንስሓ መንገር፣መምህረ ንስሓ ያዘዘውን ቀኖና ሳያጐድሉ ምግባር ትሩፋት ጨምሮ መፈጸም ንጽሕናን ገንዘብ ማድረግ ከዚያም ሥጋውን ደሙን መቀበል ነው፡አባ ሕርያቆስ ‹‹አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ያነጽሑ፣ያጸርዩ፣ይቄድሱ ያለውን ሊቃውንት ሲተረጐሙ ‹‹ያነጽሑ›› ልብሱ ከሳሙና ሲገናኝ ‹‹ያጸርዩ›› ሲለቀለቅ ‹‹ይቄድሱ›› ደርቆ ሲለበስ ነው›› ካሉ በኋላ ‹‹ልብሱን ከሳሙና እንደማገናኘት ሰው ንስሓውን ለመምህረ ንስሓው ይናገራል፡ እንደ መለቅለቅ ቀኖናውን ተቀብሎ ንስሓውን ያደርሳል፡፡ይፈጽማል) ደርቆ እንደ መልበስ ንስሓውን አድርሶ ቀኖናውን ፈጽሞ ሲወጣ ሥጋውን ደሙን ይቀበላልና፡፡ ሥጋውን ደሙንም መቀበል በንጽሐ ሥጋ(ከርስሐት) በንጽሐ ነፍስ በሥጋዊ ሐሳብ ከመውጣት ከመውረድ) በንጽሐ ልቡና (ከቂም ከበቀል ንጹሕ) ሆኖ ነውና›› ብለዋል። ትር ቅዳ ማር ማር ይሳ አን 24 ይህም ማለት ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ከኃጢአት መንፃት ብቻ በቂ አይደለም፡፡ ምግባር ትሩፋት መሥራትም ይገባልና ምክንያቱም ከኃጢአት የተለየ ንጽሕ ሲባል ምግባር ትሩፋት የጨመረ ደግሞ ቅዱስ ይባላልና፡፡
ይህንም አስመልክቶ አፈ ወርቅ ‹‹ቅድሳት ለቅዱሳን›› ባለ ጊዜ ቅዱስ ያልሆነ ሰው ቢኖር አይቅሩረብ ከማለቱ ዘንድ ያስረዳልና፡፡ ከኃጢአት ንጹሕ ያልሆነ ሰው ቢኖር አይቁረብ አላለምና ‹.ቅዱስ ያልሆነ ሰው አይቀረብ አለ እንጂ›› ቅዱስ የሚባል መንፈስ ቅዱስ ቢያድርበት ቀጥሎ ቀጥሎ በጎ ምግባር ትሩፋት ቢሠራ ነው ኣንጂ ያለዚህ ከልብሰ ኃጢአት ስለ ተለየ ብቻ ቅዱስ አይባልምና፡፡እኔ አንደ ረግረማ ይዞ ከሚያስቀር ከኃጢአት ብቻ ንጹሓን ልትሆኑ አልወድም፡፡፡
በምግባር የተገለጻችሁ በክብር ያማራችሁ ትሆኑዘንድ እወዳለሁ አንጂ የባቢሎን ንጉሥ ከማረካቸው ሰዎች ወገን መልካችው የሚያምር ደም ግባታቸው ደስ የሚያለኝ ጐልማሶችን ከመረጠ ሰማያዊ ንጉሥ ወዳዘጋጆው ማዕድ የምንቀርብ አኛማ መልክዐ ነፍሳችንን የሚያምር ንጽሕናችንን ደስ የሚያሰኝ አንደምን አናደርግ? ንጽሓ ሥጋን ጌጥ አድርገን ምግባረ ወንጌልን ሠርተን ንጽሐ ነፍስን ይዘን ንጽሐ ልቡናን አግኝተን ዕውቀትን ገንዘብ አድርገን(አንቅረብ)፡፡ አንዲህ ያለው ሰው ሥጋውን ደሙን ይቀበል፡፡ ያደፈ ልብስ ለብሶ ወደ ንጉስ ማዕድ ይቀርብ ዘንድ የሚወድ(ካለ)3 ወዳጄ ሆይ የሚመጣበት መከራ ምን ያህል አንደሆነ ዕወቅ አስተውል፡፡
ስለዚህ ቂምና በቀል፣ቅናትና ጠብ እንዲሁም የዝሙት ሐሳብ በልቡናው ያለበት -ሁሉ ወደዚህ ቅዱስ ማዕድ ሊቀርብ አይገባውም፡፡‹‹መለኮት የተዋሐደው – ኅብስት እነሆ ተፈተተ ሕይወትን የሚያድል ጽዋ እነሆ ተዘጋጀ በቅቻለሁ ብሎ የሚቀበል ሰው ይምጣ ከመቀበል አስቀድሞ ከኃጢአት ነጽታችሁም እንደሆነ አልነጻችሁም እኔደሆነ ስውታችሁን መርምሩ መርምራችሁ ሰውነታችሁን በኃጢአት የተሰነካከለ ሰው ቢኖር ይከልከል በኀጢአት የተሰነካከለ ሰው ቢኖር አይርሳ በጌታ ዘንድ የማይረሳ ነውና›› ትር ቅዳ ማር
ሐኪም ወይም ባለመድኃኒት በሽተኛው በታመመ ጊዜ አስቀድሞ ይጠቀማቸው የነበሩ ነገሮችን ይተው ዘንድ እንዲያዝዘው ሐኪሙ ያለውን ባለመስማት ይተዋቸው ዘንድ ያዘዘውን ነገሮች ባይተው ግን በሽታው እጥፍ እንዲሆንበት
እንዲሁ አንድ ምእመንም ሥጋውን ደሙን በሚቀበልበት ጊዜ አስቀድሞ ያደርጋቸው ይፈጽማቸው የነበሩ ሥጋዊ ተግባራትና ፍላጎቶቹን – በመላ እንዲገቱ ያደርጋቸዋል::መድኃኒቱን ከመውሰድ በፊት ለመታመም መንሥኤ ከሆኑ ነገሮች መራቅ አንዱ የመዳን ምልክት ነውና፡፡ ከዚያም መድኃኒቱን(ሥጋውን ደሙን) ይቀበላል። እንዲህ የሆነ አንደሆነ የወሰደው መድኃኒት(ሥጋው ደሙ) መድኃኒተ ሥጋ መድኃኒተ ነፍስ ይሆነዋል፡:
(ይቀጥላል)👇
(ቀጣይ ክፍል) 👆👇
ገበሬም ንጹሑን ዘር በመሬት ላይ ከመዝራቱ አስቀድሞ መሬቱን ያርሠዋል ያርመዋል ይኩተኩተዋል ያሰለሰልሰዋል፡፡ ከዚያም ዘሩን በንጹሑ መሬት ላይ ይዘራል።:ይህን ሳያደርግ ቢዘራው ግን መሬቱ ዘሩን ይውጠዋል፡ ቢበቅልም አረም ያስቀረዋል ዘሩም ያለ ፍሬ ይቀራል። እንደዚኸውም ሁሉ ምእመንም የጌታን ሥጋና ደም ከመቀበሉ በፊት ለራሱ ሰውነት የገበሬውን ያህል ሊጠነቀቅላትና ሊጠበብላት ይገባል፡: መቼም ወደ አንድ ሹም ቤት የጥሪ ደብዳቤ የደረሰው ሰው ብዙ ጥንቃቄዎችንና ቅድመ ዝግጅቶችን የሚያደርግ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡እንኪያስ ሰያሜ ነገሥት ሰያሜ ካህናት ንጉሠ ነገሥት ሊቀ ካህናት ክርስቶስ ወዳዘጋጀው ምግበ ነፍስ ለመሄድ መጥሪያ የደረሰው ሁሉ አብልጦ ሊዘጋጅ ይገባዋል፡፡
ቀድሞ ፡‹ለሦስተኛው ቀን ተዘጋጅተው ይጠብቁ…እንዲሁም ከርሱ ማንኛውንም ክፍል አንዳትነኩ ተጠንቀቁ ተራራውንም የነካ ፈፅሞ ይሞታል›› ዘጸ 19:11‹‹ኃጢአት ሳለባት ለእግዚአብሔር ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ የበላች ሰውነት ያች ሰውነት ከሕዝብዋ ተለይታ ትጥፋ›› ዘሌ 7:20 ኃላፊት፣ህፅፅት፣ድክምት በነበረች በኦሪት ሕግ ይህን ያህል ጥንቃቄ ይደረግ ከነበረ በወንጌልማ እንዴት ይልቅ ተብሎ አብልጦ መጠንቀቅ ይገባ ይሆን!? ይህንም አስመልክቶ ቅ.ጳውሎስ ‹አሁንም ሳይገባው ይህን ኅብስት የበላ ይህንም ጽዋ የጠጣ የጌታችን ሥጋውና ደሙ ስለሆነ ዕዳ አለበት አሁንም ሰው ራሱን መርምሮና አንጽቶ ከዚህ ኅብስት ይብላ ከዚህም ጽዋ ይጠጣ ሳይገባው የጌታችን ሥጋም እንደ ሆነ ሳያውቅ ሰውነቱንም ሳያነጻ የሚበላና የሚጠጣ ለራሱ ፍርዱንና መቅሠፍቱን ይበላል ይጠጣልም፡፡
ስለዚህ ከመካከላችሁ የደከሙና የታመሙ ብዙዎች ናቸው ብዙዎችም በድንገት አንቀላፍተዋል›› ይላል፡፡ ‹‹የአረማዊነትን የአይሁድን ተግባር የሚፈጽም ክርስቲያን ሁሉ ከተቀደሰው ምሥጢር ይቀበል ዘንድ ንስሓ ሳይገባ ቢመጣ ሐሰተኛ ነውና የሚሰጠው የለም(አይትር) መላአክትም በረቂቅ ይነጥቁታል ለእርሱም ባላመጠው ጊዜ ኅብስተ ስርናይ ይመስለዋል››
በእነዚህ ነገሮች ራሱን ያበቃና ያዘጋጀ ሰው ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት ጸዐዳ ልብስ ለብሶ አስቀድሞ ተገኝቶ ሥርዓተ ቅዳሴው እስኪፈጸም ድረስ ቆይቶ መዮፉረብ ይገባዋል፡፡ ‹‹ስለዚህም ከቅዱስ ምሥጢር የሚቀበል ሁሉ ሦስት ቀንከሩካቤ ሥጋ ዐሥራ ስምንት ሰዓት ከእህል ይጾም ዘንድ ይገባዋል ከመቀበሉም በፊት ነጭ ልብስ ይልበስ›› እንዲል፡፡ ነገር ግን ጸሎተ ቅዳሴውን አቋርጦ በመግባት ወይም ሲያልቅ በመምጣት ሊቁርብ አይገባውም::እንዲሁም በእለቱ ሥጋውን ደሙን የሚቀበል ሰው ከኃጢአት እንደተጠበቀ ሁሉ ከአፍአዊ ርስሐትም ከሰውነቱ የሚወጣ
ማንኛውም ፈሳሽ ነገር እንዳይኖር ራሱን መጠበቅ ይገባዋል፡:
ዳግመኛም የሚቄርብ ሰው በዕለቱ ሰውነቱን መታጠብ ጥፍሩን መቁረጥ ራሱን መላጨት አይገባውም፡፡‹‹የሰው ልጅ ሚሠራው ሌላም ኀጢአት ካለ ስለ አንዱ ፈንታ ሠላሳ ስልሳ መቶ ያፈራ ዘንድ ንስሓ ገብቶ ንጹሕ ሆኖ ከዚህ መንፈሳዊ ምግብ ይቀበል በሕልም ርኩሰት ካለበት፣ጋብቻም ቢሆን ከሚስቱ ጋር በአንደበትም ቢሆን መሰናክሎች ከተገኙ ይወገድ(አይቀበል) በትንሽ ስህተትም ቢሆን ኀጢአት ይሆናልና።
ከአፉ ደም ከወጣ፤ከጥርሶቹም የምግብ ቅሪት የተገኘ የሆመጠጠ የረከሰ ከተፋ ከአፉም ዝንብ ከገባ እና ይህን በመሳሰለው ሁሉ ለአንድ ቀን – ያክል አይቀበል››
እንዲህ አድርጐ አሥራ ስምንት ሰዓት ጹሞ ለአፋ ምረት ሲሰማው ይቁርባል፡፡
በአጠቃላይ ከዚህ የሚቀበል ሰው ሥጋው ደሙ ተለውጦ የጌታ ሥጋ የጌታ ደም እንደሆነ የሚያምን፣ ኅጢአት እንደሚያስተሠርይ፣ የዘለዓለም ሕይወትን እንደሚያድል፣ጌታም በዚህ በሥጋው በደሙ እንደሚዋሐደው አምኖ፣በኅጢአቱ ተጸጽቶ ኀጢአቱን ተናዝዞ፣ከሚመጣው ለመጠበቅ ወስኖ ይቀበላል።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን ላይ ያገኛሉ፦ Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ
👉ጥያቄ፡- አንድ ሰው ለ #ቅዱስ #ቁርባን የሚያደርገውን #ዝግጅት አድርጎ፣ ንስሐ ገብቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥጋ ወደሙ በሚቀበልበት ጊዜ መጎናፀፊያ ባይለብስ ክፋት አለው?
✍መልስ፡- ጠያቂያችን፤ ሰዎች ሲቆርቡ ሚለብሱት ንዋየ ቅዱሳን፣ልዩ ለዚሁ አገልግሎት አገልግሎት የተቀደሰ፣ የተለየ፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለማስቀደስ፣ ለመቁረብ፣ እያስቀደስን በቆምንበት ቦታ የሚለበስ ልብስ አለ፣ እሱን ነው ያሉት፣ በስርዓተ ተክሊል የሚጋቡ ሰዎች የሚለበሱት ልብስ አለ፣ የማእስባን ተክሊል የሚባል፣ ባልና ሚስት የሆኑ ሰዎች፣ ከጊዜ በኋላ ባልና ሚስት ሽማግሌዎች ሊሆኑ ይችላሉ፣ በመካከለኛ እድሜ ወይም በወጣትነት ሊሆን ይችላል፣ ከተክሊል ጋብቻ ውጪ የሆነ ጋብቻ ሲሆን ሲቆርቡ ልብስ በአንድ ላይ ይለብሳሉ፡፡
የአንድነት መገለጫ ነው፣ በተናጥል አይደለም ቅዱስ ቁርባኑ ፣ በአንድ ላይ ነው አንድ አካል ናቸውና፣ በቅዱስ ቁርባንም አንድነታቸው ይገለፅበታል ማለት ነው፡፡ ያኔ የሚለብሱት ልብስ አለና፤ እሱን እንለብሳለን፣ ሁሉም አገልግሎት የተሟላ በሆነበት ቦታ ላይ የንስሐ አባት አሉ፡፡
ወይም ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ምእመናንን ለቅዱስ ቁርባን ሲቀርቡ የሚያስተባብር፣ የሚመራ፣ የሚያስተካክል የቤተክርስቲያን ባለድርሻ አካል አለ፣ ካሕን ወይም ዲያቆን አለ፤ እሱ አዲስ ቆራቢዎችን የማን ልጅ እንደሆኑ፣ የንስሐ አባታቸው ማን እንደሆኑ ከታወቀ በኋላ የሚያስፈልገውን ነገር ሊያሟሉ ይችላሉ፡፡
አብዛኛዎቹ አድባራት፣ ገዳማት ለጉዳዩ ትኩረት ባለመስጠት መሰልቸት እንጂ፤ እንዳሉት ምእመናንን ለቅዱስ ቁርባን ማብቃት ለቤተ ክርስቲያን ትልቁ ድሏም ይሄ ነው፡፡ ለካሕናትም ቢሆን፣ በ አገልግሎታቸው ውጤታማ ሆነው ያተረፉበት ነገር ይሄ ነው እና እንድንለብስ ቢያደርጉ መልካም ነው፣ ይሔ ሳይሳካ ወይም ደግሞ ሳይሟላ ቢቀር ለዚሁ ብለን ባዘጋጀነው ንጹህ ልብሳችን መቁረብ እንችላለን፡፡
የውጪው ልብሳችን የሚገልጠው በውስጥም ያለው ሕይወታችን፣ ልባችን፣ ሁሉ ከኃጢያት የነፃ፣ የጸዳ መሆኑን ማረጋገጥ ነው፡፡ ስለዚህ ልብሱ በድፍረት እንዳይሆን የቆሸሸውን፣ ያደፈውን፤ ለሌላ ተግባር ያዋልነውን በሥጋዊ ተግባራችን ያጎደፍነውን ልብስ በድፍረት ለብሰን እንዳንሄድ እንጂ፤ ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀውን ልብስ ለብሰን ሄደን መቁረብ እንችላለን፡፡
ነገር ግን ብዙ አባቶች አስበውበት፣ በትጋት፣ ችላ ሳይሉ ልጆቻቸውን በቁርባን ጊዜ መልበስ የሚገባቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳውቃሉ፡፡ ይሄ እንግዲህ የአባቶቻችንን ትጋትና ጥንካሬ ያሳያል ማለት ነው፣ ካልሆነ ችግር የለውም፡፡ ሌላው ደግሞ ሁለተኛ አድርገው፣ ሁሉንም ወስደው ወደ ቅዱስ ሥጋውና ደሙ ቀርቦ ቢወሰድ ጉዳት አለው ወይ? የሚለው ከላይኛው የተለየ አይደለም ምንም ጉዳት የለውም፡፡
በዋናነት ወደ ቅዱስ ቁርባን ስንቀርብ እዳ በደል እንዳይሆንብን፣ በድፍረት እንዳናደርገው፣ ምን ያመጣል፣ ምን ያደርጋል በሚል የደነደነ ሐሰብ አሰናክሎን፣ አዘናግቶን፣ በድፍረት እንዳይሆን እንጂ፣ ሕይወታችን በንስሐ ካስተካከልን፣ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ምንም ሌላ የሚከለክለን ነገር የለም፡፡
ይህንን ሁሉም ሰው ሊረዳ ይገባል፣ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዋናነት ቅዱስ ቁርባን ወይም ደግሞ የእሱን ቅዱስ ሥጋውን፣ ክቡር ደሙን እንድንቀበል ራሱ ከሰማይ የወረደ ሕብስት እንደሆነ ፣የሕይወት እንጀራ እንደሆነ ነገረን፣ ይሔንን ብሉ፣ጠጡ አለን፣ ይሄ ለብዙዎቹ የኃጢያት ስርየት በመስቀል ላይ፣ በነገው እለት ብሎ ነው በጸሎተ ሐሙስ፣ ወይም ደግሞ በምሴተ ሐሙስ የሚፈሰው ደሜ፣ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፣ ይሔን ብሉ፣ ጠጡ ብሎናል፡፡ ደግሞም በሌላ መልኩ በድፍረት እንዳናደርገው የሠርግ ልብስ ያለበሰ፣ በንጉሡ የሠርግ ቤት ብዙዎች ራሳቸውን ጠብቀው፣ ለሠርጉ ቤት ታዳሚ የሆነ ሰው የሚለብሰውን ልብስ ለብሰው፣ ያንን የሠርጉን ዳስ ብዙ ሰዎች ሞልተውት፣ አንድ ሰው ግን ከሰው ሁሉ በተለየ፣ በድፍረትም፣ ለዚያ ቤት የማይገባ ልብስ ለብሶ በመጣ ጊዜ፤
ወዳጄ የሠርግ ልብስ አለበስክምና ውጣ ብሎ ጌታ ወይም ንጉሡ (የሠርጉ ባለቤት) ሲያስወጣው፣ የለኝም የምለብሰው፣ እንደሌሎቹ ታዳሚዎች የምቆጠርበት፣ የምለብሰው ልብስ የለኝም ባለው ጊዜ አሮጌ የሆነውን፣ ይሔን የቆሸሸውን አጥበህ ብትለብሰው መልካም ነበር ተብሏል፡፡
ስለዚህ እኛ ምክንያቶችን በማብዛት፣ ሰውነታችን፣ መንፈሳዊ ሕይወታችን በንስሐ ሕይወት ሳንታጠብ እንዳንቀርብ ብቻ ነው ቤተ ክርስቲያን የምትመክረን፤
ሁላችንም ይህን ነገር እናስተውል ዘንድ እግዚአብሔር ልቦናችንን ይክፈትልን፣ ሚስጥሩን፣ ጥበቡን በሁላችንም ላይ ያሳድርብን አሜን

👉ጥያቄ #1፦ አባ!! ሰው ከቆረበ ሰው የማይስመው የማይታጠበው ወዘተ ለምንድነው?
👉ጥያቄ#2 ፦ #ቅዱስ #ቁርባን ለመቀበል 18 ሰዓት መፆም አለበት ነገር ግን ጠዋት ሲነሱ አፍን መቦረሽ ጥርስ ደም እንዲደማ ሊደርግ ስለሚችል አይመከርም ፡፡በዉሃ አፍን መጉመጥመጥስ ይቻላል? ወይስ አይቻልም ?
መልስ፦ ጠያቂያችን አንድ ኦርቶዶክስ ክርስቲየን ቅዱስ_ቁርባን ከመቀበሉ በፊትና ከተቀበለ በኋላ ምን ማድረግ አለበት የተባለውን ሃሳብ መሠረት በማድረግ ከአባላት ጥያቄ ቀርቦልን አፈጻጸሙንና ምክንያቱንም ጨምረን በተለያየ ጊዜ ለቀረቡ የተለያዩ ጥያቄዎች አብራርተን ምላሽ ለመስጠት መሞከራችንን እናስታውሳለን። ስለሆነም ያስተላለፍነውን መልዕክት በአጭሩ አጠቃለን ከዚህ እንደሚከተለው ልከንልዎታልና ምክንያቱን ከዚህ አንጻር እንዲረዱት ይረዱት።
በቅድሚያ መታወቅ ያለበት አንድ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን በተቀበለበት እለት በዋናነት ገላውን በውሀ መታጠብ የለበትም ፣ ልብሱን አውልቆ እርቃኑን መሆን የለበትም፣ ከሰውነቱ ደም ማውጣትን የለበትም ከሕግ ጋብቻ ጋር ቢሆንም የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ የለበትም ፣ በሰውነታችን ላይ ፈሳሽ ሊያስከትል የሚችል ከባድ ስራ መስራት የለበትም፣ እሩቅ መንገድ መሄድ የለበትም (እንደ ስራ ስለሚቆጠር) ፣ የሚያሰክር እና የበላነውን የጠጣነውን የሚያውክ መጠጥ መጠጣት የለበትም ፣ ጭቅጭቅ ያለበት አደባባይ ወይም የህዝብ ቦታ መሄድ የለበትም፣ ከሰው ጋር መጨቃጨቅ ሃይለ ቃል መነጋገር በአጠቃለይ ለፀብ የሚጋርድ ስራ እና እነዚህን የመሳሰሉ ሌሎችንም ከቁርባን በኋላ ማድረግ እንደሌለብን በቀኖና ቤተክርስቲያን ተደንግጎ ይገኛል።
ይህ ማለት ግን ጠየያቂያችን እንዳሉት ከቅዳሴ በኋላ ተሳስተን በእጃችን ውሀ ብንነካ ወይም ዝናብ ቢነካን ወይ እግራችንን ፈሳሽ ቢነካን ቁርባኑ ይከሽፋል ወይ እንደገና ቀኖና መቀበል ያስፈልገዋል ማለት አይደለም። ይሁን እንጂ ያ ስርዓት ሆን ብለን አስበን ጥፋት እንዳንሰራ እንጂ በሆነ አጋጣሚ ዘንግተነውም ይሁን ከአቅማችን በለይ በሆነ ጉዳይ ቢደረግ ሃይማኖትን እንዳጎደልን ወይም እግዚአብሔርን እንደካድን የሚያስቆጥርና መቅሰፍትን የሚያመጣ አይደለም። ምክንቱም አምልኮተ እግዚአብሔርን በስርዓት እንድናከናውን መመሪያ ሁሉ ነገር ለበጎ ለተግሳፅና ለምክር እንደተፃፈ ማመን አለብን።
ከመቁረብ በፊት ውሀ መንካት አይገባም የሚለው ሃሳብ፤ ለምሳሌ ነገ ቅዳሜ ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን የምንቀበል ከሆነ አርብ ማታ ላይ በጊዜ ገላን መታጠብ ያስፈልጋል፥ ነገር ግን ጠዋት ልንሄድ ስንል አፍ መጉመጥመጥ አይቻልም፥ በአይናችን ውሃ እንዳይገባ ፊትንም መታጠብ አይገባም። ትንሽ ነካ ነካ አድርጎ አድርገን ከላይ ከላይ ብንታጠብ ግን ችግር የለም። አባቶች ሲያስተምሩን ሰውነታችን ክፍት ስለሆነ ውሃ በአይን ይገባል ይላሉ፦ ስለዚህ ጠዋት ላይ ፥አፋችነን ባንጉመጠሞጥ ፥ይምረረን ግዴለም ፥ ምሬቱ መከራውን እንድናስብ ሀሞቱን እንድናስብ ለ 18 ሰዓት መጾም ለማለት እንጂ፥ እንደነገን የምንቆርብ ከሆነ ዛሬ ማታ መታጠብን አይከለክልም፥ መመገብ ወይም ውሃ መጠጣት ግን አይቻልም። በአጠቃላይ ይህ ስርአት የውስጣችንን ቅድስናና ንፅህና ለማጠየቅ ሲሆን በአካለ ሥጋችን የምናደርገው ፅዳትም ለእግዚአብሔር መታዘዝን ለማመልከት ነው።
ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የተዘጋጁ ካህናትም ሆኑ ምዕመናን 18 ሰዓታት ከሚበላ እና ከሚጠጣ ምግብ ተከልክለው በጾም ተወስነው መቆየት ይገባቸዋል። ጠያቂያችን ፤ 18 ሰዓት አፋችን ምሬት እስኪሰማው ለማለት ነው፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ 3 ሰዓት በአይሁድ ተያዘ፥ እስከ 9 ሰዓት ነፍሱ ከስጋው እስክትለይ ድረስ 18 ሰዓት ይሞላል እና ያን በማሰብ አፋችን ምሬት እስኪሰማው ድረስ ብላ ቤተክርስቲያናችን ታስተምረናለችና ነው።
ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ ስንዘጋጅ ወደ እግዚአብሔር ቤት ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት መድረስ ይኖርብናል። ተሰጥኦውንም እየተቀበሉ ቆይተው ቀዳሲያን ቅዱስ ሰጋውን ክቡር ደሙን ሊያቀብሉን ከቤተመቅደስ ብቅ ሲሉ ሁሉም ምእመን ለቅዱስ ሰጋውን ለክቡር ደሙ ክብር በመሰጠት በፊቱ እርግት ብሎ ሰግደው ስጋውን እና ደሙን ይቀበላሉ ማለት ነው። ሌላው ሰውም ከሰገዱ በኋላ ፤ ቀዳሲያን አቀብለው ሲመለሱና ፊታቸውን ወደ ምስራቅ ሲያዞሩ ሌሎቹ ሰግደው ከነበሩበት ቦታቸው ላይ ብድግ ብለውም ቆመው የራሳቸውን ቦታ ይዘው ወደፊት ለዚህ እንዲያበቃቸው ፈጣሪያቸውን እየተማጸኑ ቀሪ የሚቀጥለውን የቅዳሴ ቀሪ ጸሎቱን ስርዓት በጽሞና ሆነው ያዳምጣሉ ማለት ነው።
የማቁረሪያ ምግብ እስከሚቀምስ ድረስ ከሰው ጋር መነጋገር የማይችልበት ምክንያት መለኮታዊ እሳት የተዋሀደውን ቅዱስ ሥጋና ክብር ደሙን በተቀበለ ጊዜ ለነፍስ መድኅኒት ለስጋም በረከትን የሚያመጣውን የከርስቶስን ስጋውንና ደሙን ተቀብሎ ሌላ የሰውኛ ንግግርን መነጋገር ሃሳብን ማውጣትና ማውረድ ፈፅሞ ስለማይፈቀድ ነው። ከቅዱስ ቁርባን በላይ የሚከብር ነገር ባለመኖሩ በብዙ ፈተና የረከሰውን ህይወታችንን የቀደሰውንና የተዋረደውን ማንነታችንን ያከበረውን ቅዱስ ቁርባን ማቃለል ለኛም ከቅዱስ ስጋውና ከክቡር ደሙ ያገኘነውን ክብር ስለሚያሳንስብን ባጠቃላይ አፋችንን የመሸፈናችን ነገር ክፉ ከመናገር፣ ክፉ ከማሰብ፣ ክፉውን ድርጊት ከመፈፀም የራቅን ለመሆናችን የሚያመለክት ስርዓት ነው። ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ እህል ውሀ ቀምሰንም ቢሆን ከአንደበታችን የሚወጣው ነገር የተቀደሰና በጎ ነገር ሊሆን ይገባዋል ወይም ክፉ ሃሳብና ክፉ ድርጊት ከኛ እንዳይወጣ ያስፈልጋል ለማለት ነው። በዋናነት እንደማስረጃ የምናደርገው ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ቤዛ ለመሆን በመስቀል ላይ ቅዱስ ስጋውን ቆርሶ ክቡር ደሙን አፍስሶ ለኛ ያለውን ፍቅር በመስቀል ካረጋገጠ በኋላ 3 መአልትና 3 ሌሊት በከርሰ መቃብር በቆየ ጊዜ ቅዱሳን ሐዋሪያትና ሌሎችም ተከታዮቹ በሀዘንና በለቅሶ የላመ የጣመ እህል ውሀ ሳይቀምሱ መቆየታቸውን የሚያመላክት ነው። ስለዚህ ዛሬ ለኛ ህይወት መድሃኒታችን የሚሆነው የሚሰጠን የተገኘው መራራ በሆነ የመስቀል መከራ ስለሆነ እኛም ዛሬ ከሚበላ ከሚጠጣ፣ ከነገር እና ከክፉ ድርጊት ራሳችንን ቆጥበን መቀበል እንደሚገባን የሚያመለክት ነው።
የተቀደሰ ሰላምታ አስፈላጊ በሆኑ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በአካልም ሆነ በስልክ እኛንም ሆነ ቁርባኑን አያረክሰውም፤ ብቻ በህሊናችን ራሳችንን ለእግዚአብሔር ማስገዛት ያስፈልጋል ለማለት ነው።
ከቆረብን በኋላ የለበስነውን ልብስመቼ ነው መቀየር ያለብን ወይስ ለብሰነው ነው ወይ የምናድረው ለተባለው፤ በመሰረቱ የአንድ ቀን ቁጥር የሚጀምረው ከዋዜማው ወይም ከማታው 12 ሰአት ጀምሮ እስከ የቀኑ 12 ሰዓት በድምሩ 24 ሰዓት 1 ቀን ይባላል። በዚህም መሰረት ሲቆርቡ የለበሱትን ልብስ ማታ የተቀበሉበት ቀን ማታ ማለትም ከ 12 ሰአት በኋላ ወይም የእለቱ ሰአት ሲጠናቅ መቀየር ይችላሉ።
ወደ ቅዱስ ቁርባን እና ወደ እግዚአብሔር ቤት ስንቀርብ ራሱን የቻለ ለዚህ አገልግሎት ብቻ የሚውል ሙሉ ልብስ ቢኖረን ይመረጣል። ምክንያቱም ይህን በማድረጋችን በውስጣችን ፍጹም የሆነ ልባዊ ሃይማኖትና ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዳለ ያመለክታልና። ስለዚህ ያንን በቁርባን ጊዜ የለበሱትን ነጠላ ሌላ ጊዜም እያጠቡም መገልገል ይችላሉ።
(ይቀጥላል)👇
👉🏾👉🏾👉🏾 #ቅዱስ #ቁርባን ከምንቀበል በፊትና በኋላ ማድረግ ስለሚገቡን ጥንቃቄዎች

በሌላም በኩል የተለየ ልብስ ወይም ትርፍ ልብስ የሌላቸው በድህነት ያሉ ክርስቲያኖች ያንን ያላቸውን የድህነት ልብሳቸውን ባላቸው አቅም በንፁህ አጥበው መቁረብ እንዳለባቸው ደግሞ መዘንጋት የለበትም። ምክንያቱም ገና ሀብታሞች እንደሚለብሱት የተለየ ልብስ የለንም በሚል ምክንያት ከቅዱስ ቁርባን እርቀው መኖር ስለማይገባቸው ነው።
ቅዱስ ቁርባን የተቀበለ ሰው ከቁርባን በኋላ ብቻውን አይሄድም የሚባለው የቆረበ ሰው ከምንም በላይ ህይወቱ የከበረና መንፈሳዊ ሙሽራ ስለሆነ የተለየ ክብርም ስለሚያስፈልገው ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን አማናዊ ክብር ለማመልከትና ነው። በሌላ በኩል በዚህ ህይወትና መድኅኒት በሆነው በቅዱስ ቁርባን የከበረውን ሰው ሰይጣን በክፉ መንፈስ በጠላትነት ስለሚቃወመው አንደ አንዳንድ ባለስልጣናት ወይም በሙሽርነት የከበረ ሰው ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ እንደሚያስፈልጉት ሁሉ ከዚህም በላይ የሰው ልጅ ፍጹም ሰማያዊ ክብር የሚያገኝበትን ቅዱስ ቁርባን በተቀበለ ጊዜ ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ ስለሚያስፈልገው ብቻ ነው።
ስለዚህ መረዳት ያለብን ከላይ የገለፅናቸው የገለፅናቸው ምክንያቶች ለስጋ ደሙ ክብር ከመስጠት የተነሳ ነው እንጂ ስጋ ደሙን የተቀበለ ሰው ለሌላ አደጋ የተጋለጠ ይሆናል ብሎ ማሰብ የተሳሳተ ነው። እንዲያውም ከምንም በላይ ስጋውን ደሙን የተቀበለን ሰው የአጋንንት መንፈስም ሆኑ ሌላ ሃይል እንዳይቃወመው ታላቅ ግርማ ሞገስና ሃይልና ጉልበት ስለሚሆነው ብቻውን ስለሄደ ችግር ያጋጥመዋል ብሎ ማመን የተሳሳተ ሃሳብ ነው። በየገዳማትም ሆነ በየአብያተ ክርስቲያናት ቅዳሴ አስቀድሰው ቅዱስ ቁርባን የሚቀበሉና የሚያቀብሉ ብቻቸውን አገር አቋርጠው ሲሄዱ እነሱ ለሌላው ክብርና ሞገስ ይሆናሉ እንጂ በነሱ ላይ የሚደርስባቸው አንዳችም ክፉ ነገር የለም።
በአጠቃላይ ዋናው ምክንያት የእግዚአብሔርን ቅድስና ወይም ቅዱስ ቁርባን ለማርከስ የሚችል ሌላ ነገር ኖሮ ሳይሆን፤ እኛ ግን ከክርስቶስ ስጋና ደም ጋር ስለተዋሀድን በኛ አላማ በቅናት ያበደው ሰይጣን ሊፈትነንና በሚያጠምደው መሰናክል ሊጥለን ስለሚችል ከሁሉ ነገር ተቆጥበንና ተሰብስበን ለዘላለማዊ ድህነት የወሰድነውን የክርስቶስን ቅዱስ ስጋና ክቡር ደም በልዩ ስርአት አክብረን የተወሰነውን ጊዜ ማሳለፍ ስላለብን ነው። ሰይጣን ብዙ ጊዜ እኛን የሚጥልበት መሰናክል ረቂቅ ስለሆነ ክርስቲያናዊ ንቃት ኑሮን መጠንቀቅ ስለሚያስፈልግ ነው። ስለዚህ ጠያቂያችን ጥያቄዎት ለሁሉም አስተማሪ ይሆን በንድ ሰፋ አድርገንሆነ ለሁሉም ክርስቲያን ግልጽ በሆነ መልኩ የቀረበውን የህንን ትምህርት ልከንልዎታል።
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾 ስለ #ቅዱስ #ቁርባን #አቀባበል
👉ጥያቄ፡- በቅድሚያ ስለምታደርጉት ነገር ሁሉ በርቱ ጠንክሩ፣ ጥያቄዬ አንድ ሰው ሊቆርብ ሲሄድ በመጀመሪያ ቅዱስ ሥጋውን ከተቀበለ በኋላ፣ እሱን በዝግታ ከበላ፣ ከዋጠ በኋላ ነው ወደ አማናዊው ደሙ መሄድ ያለበት?
✍መልስ፡- ቅዱስ ቁርባን፣ ምስጢረ ቁርባን ትልቁ የቤተክርስቲያን ምስጢር ነው፣ በሰባቱ ምስጢራተ ቤተክርስቲያንም ውስጥ፣ በአምስቱ አዕማደ ምስጢራት ውስጥ ካሉት ምስጢራት አንዱና ዋናው ነው ማለት ነው፣ ስለዚህ እንዲህ ዓይነቶቹን ነገሮች ደግሞ በውስጥ መስመርም ቢሆን ቢጠይቁን መልካም ነበር፡፡
ከዚህ በፊትም ተጠይቆ ተነጋግረንበታል፣ አቀባበል ነው፣ አንድ ሰው ለቅዱስ ቁርባን ተዘጋጅቶ፣ አባቶች ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በፍፁም ልባዊ እምነታቸው ምስክርነት ሰጥቶ፣ በቃለ እግዚአብሔር በልዩ ልዩ ምስጢራት አክብረውት መጨረሻ ላይ እነሱ ተቀብለውት እነሱ ህይወትነቱን፣ አዳኝነቱን ስለሚያምኑ በመጀመሪያ እነሱ ይቀበሉታል፡፡
ከዚያ በኋላ ደግሞ ለዚሁ የተዘጋጁ ምእመናንን፣ እግዚአብሔር የፈቀደላቸውን፣ በንስሐ ህይወት የታጠቡትን፣ ለቅዱስ ሥጋው በቅታችኋል ብለው አባቶቻቸው የመከሯቸውን፣ የገሰጿቸውን፣ የናዘዟቸውን ምእመናን ያቆርባሉ፤ በመጀመሪያ ስንቆርብ ካሕኑ ሠራይው ካሕን፣ ቄሱ ቅዱስ ሥጋውን ያቀብለናል፡፡
ሦስቱ ነገሮች አይለዩም አንድ ናቸው፣ በእለተ ዓርብ ከእሱ የተገኙ፣ ህይወት የሚሰጡ፣ ይሄን ብሉ ጠጡ የተባልናቸው፣ ቅዱስ ሥጋው፣ ክቡር ደሙና ማየ ገቦው ከጎኑ የፈሰሰው ውኃ፣ ከእሱ አካል የወጣው ደም፣ ከእሱ አካል የተቆረሰው ሥጋው ብለን ህይወት የሚሰጠን ስለሆነ በፍፁም እምነት ነው የምንቀበለው፡፡
ስለዚህ ካሕኑ ቅዱስ ሥጋውን ለእኛ ሲያቀብለን ወዲውኑ ደግሞ በጽዋ ክቡር ደሙን ደግሞ ዲያቆኑ አብሮ ነው የሚያቀብለን በትዕግሥት በእርጋታ ሆነን ነው፣ ከዚህ ቀደምም ጊዜው ቆየት ቢልም ስለ አቀባበሉ ስርዓትና እኛም ደግሞ በእምነት ይሄን ነገር እንዴት እንደምናየው ተነጋግረናል፡፡
ፍፁም ከሕብስትነት ወደ ፍፁም ሥጋ ወልደ አምላክነት፣ ከወይንነት ወደ ፍፁም ደመ ወልደ እግዚአብሔርነት ተለውጦ በእምነት የምንቀበለው ነው፣ ስለዚህ በሥጋዊ ረሐብ እንደምንፈልገው ምግበ ሥጋ፣ መጠጥ ሥጋ አንመልከተው፣ የምንበላውን፣ የምንጠጣውን የሥጋ ምግብና የሥጋ መጠጥ እንዴት እንደምንመገበው እናውቃለን፣ ይሄ ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡
ጠያቂያችን ሥጋውን ተቀብለን እንደገና በመካከሉ ደሙን ለመቀበል ጊዜ ወስደን እንዲህ የምንቀበለው አይደለም፣ ያለው የጊዜ ክፍተት ብዙ ቆራቢዎች ስላሉ ሥጋውን እንቀበላለን፣ ወዲያውኑ ወደ ዲያቆኑ ሄደን ደሙን ለመቀበል የምንሄድባት ጊዜ ናት ያቺ ትንሽ ክፍተት የምትኖረው፣ ይሄንን የሚያመላልስ ምላስ፣ ይሄን የሚነክስ ጥርስስ ምንድን ነው? ተብሏል እኮ፡፡
ቅዱሳን ስለእሱ አካል፣ ወይም ስለእሱ ቅዱስ ሥጋው፣ ወይም ስለእሱ ክቡር ደሙ ሲናገሩ ማለት ነው፣ ይሄን የሚሸከም ምን አፍ ነው፣ ይሄን የሚያመላልስ፣ ወይም የሚያላምጥ ምን ዓይነት ምላስ ነው? እፁብ ድንቅ የሚባለውን፣ እንደ ሌላው ምግበ ሥጋ በልተነው የማይፈልጥ የማይቆርጥ፣ ጠጥተነው ራስ ምታት ወይም የስካር መንፈስ የማያመጣ ነው ቅዱስ ቁርባን፡፡
በምግበ ሥጋ የሚያመጡትን ሁሉ የሥጋ ድካም የማያመጣ ዘለዓለማዊ ህይወት የሚሰጥ፣ የሚያበረታ፣ በምድርም ሳለን ሥጋችን ሁሉ ከኃጢአት ተለይቶ፣ ከኃጢአት ርቆ የተቀደሰ የተባረከ፣ የሚሠራው፣ የሚያደርገው ሁሉ ብሩክ የሆነለት፣ በነፍስ ደግሞ ዘለዓለማዊ ሕይወትን የምንወርስበትን ይሄ ስለሆነ ጠያቂያችን እንዲህ አድርገን ነው መመልከት ያለብን፡፡
ሁሉን ነገር በጥርጣሬ ውስጥ እያየን ከትንሽ ጥርጣሬ ተነስተን ወደ ከፋ፣ ወደ ክህደት ወደሚያደርሰን ጥርጣሬ ከመግባት እንዳሉትም መነጋገር፣ መጠየቅ ክፉ አይደለም፣ ግን እንዲህ ያሉት ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ላይ ደግሞ፣ ያው እኛ ደግሞ እናንተን ለማገልገልና ለማስተማር፣ ታዛዦች ስለሆንን በውስጥ አድራሻ ስጡን ተብሎ ቢጠየቅ መልካም ነው፡፡
ስለዚህ ይሄንን እንኳን የብዙ ሰው ጊዜ ጨርሰን፣ ሌሎቹ ደግሞ የገባቸውም ያልገባቸውም ሊኖሩ ስለሚችሉ፣ በዚህ ምስጢር ውስጥ ያለውን ያልተረዳዎትን መምህሩ እንዲያስረዱኝ ተብሎ አድራሻ ጠይቆ መነጋገሩ ይሻላል፣ አሁን ስለ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ብለን ስለምንናገረው ምስጢር እንኳን ከስም ያለፈ ምንም ግንዛቤ የሌላቸው ብዙዎች ስላሉ ማለት ነው፡፡
እኚህ ጠያቂያችን ደግሞ እግዚአብሔር ፈቅዶላቸው ለቅዱስ ቁርባን፣ለምስጢረ ቁርባን የቀረቡ ስለሆኑ ነው ይህን ያደረጉት፣ ምናልባት ድፍረት እንዳይሆንባቸው፣ ጥፋት እንዳሆንባቸው ብለው አስበው ነው፣ እግዚአብሔር ይመስገን እንዲህ ለምስጢሩ የቀኑ፣ የቀረቡ ሰዎች እግዚአብሔር ስላሉት ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ቅዱስ ሥጋውን ተቀብለው ወዲያውኑ ወደ ክቡር ደሙ ሄደው በጽዋው የከበረውን ክቡር ደም ዲያቆኑ ያቀብላል ማለት ነው፣ ከዚያ ቀጥለን በዚያችው ትንሽ በሆነችው የጊዜ ክፍተት ማየ ገቦውን የያዘው ዲያቆን አለ እሱን የሚሰጥ፣ መጨረሻው እሱ ነው፣ በቀራኒዮ መስቀል ላይም በዚያው ዓይነት ቅደም ተከተል ነው ጌታ ለሰው ሁሉ
ህይወት እንዲሆን የሰጠው ማለት ነው፡፡
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፣ አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር አድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾 ለ #ቅዱስ #ቁርባን ስለሚደረግ #ጥንቃቄ
👉 ሰላም አባቶቼ ሁለት ጥያቄ ነበረኝ፡-
👉ጥያቄ 1ኛ፡- ወደ እግዚአብሔር ማእድ ልንቀርብ ስንል ካልሲ ማድረግ ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም?
👉ጥያቄ 2ኛ፡- ከቆረብን በኋላ ኬክ ነገር፣ ወይም ኩኪስ መብላት ቀኑን ሙሉ ማለት ነው ይፈቀዳል? ወይስ አይፈቀድም?
✍መልስ 1ኛ፡ – ካልሲ የልብስ አካል ሲሆን ሳናደርግም፣ አድርገንም መቁረብ እንችላለን፣ ሴቶቹ ቀሚስ ለብሰው፣ ነጠላ ለብሰው ወደ ቅዱስ ቁርባን እንደሚሄዱ ሁሉ ማለት ነው፣ የሚቀርቡ ቆራቢያን በመጀመሪያ በንስሐ የውስጣቸውን እድፍ አንፅተው፣ ቀድሰው ንፁህ ሆነው፣ ሲቀጥል ደግሞ ንፁሐ ባህርይ ሁሌም ከእኛ ከልጆቹ ንፁህ ነገር ይጠብቃል፡፡
ወደተዘጋጀው የሠርግ ቤት፣ ድግስ ቤት ሁላችንም በክብር የጠራን አምላክ ለዚህ ለሠርጉ፣ ለድግሱ፣ ለበዓሉ የማይመጥን ልብስ ለብሰን እንዳንሄድ፣ ብንሄድም ደግሞ ያንን በእግዚአብሔር ፈቃድ የተዘጋጀውን በዓሉን የሚያስከብር ጠባቂ አለና፤ ከበር እንዳይመልሰን ለቅዱስ ቁርባን የመጣን ሰዎች እንደሆንን ታውቀን ወደ ቅድስናው ቦታ በክብር ለመግባት እንችል ዘንድ ወደ ቅዱስ ቁርባን፣ ወደ ግሩም ማእድ ስንቀርብ፤ ለመቁረብ የቀረብን መሆናችን አለባበሳችን፣ አቀራረባችን ይነግራል፣ ይመሰክራልና በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው ወደ ቅዱስ ቁርባን መቅረብ ያለብን፡፡
ይሄም ማለት ቅዱስ ቁርባን የሚቀበል ሰው ውስጣዊ ህይወታችንን በንስሐ ህይወት፣ በምክረ ካሕን፣ በተግሳፀ ካሕን፣ ውስጣዊ ሥጋችን ደግሞ ለቁርባን የቀረብን ሰዎች ሆነን ከሌሎቹ ከማይቆርቡት የምንለይበት ምልክት የአለባበሳችን ስርዓት ነው፣ ይሄንን አድርጎ ወደ ቅዱስ ቁርባን መቅረብ በቤተክርስቲያን የተለመደ ስርዓት ስለሆነ ብናጣም እንኳን ያለንን ንፁህ አድርገን መጠቀም አለብን ማለት ነው፡፡
ካልሲው ንፁህ ከሆነ፣ የማይሸት ከሆነ፣ የተለያየ የሥጋ ደዌ ያለበት ሰው ካልሲ ባያደርግ በዚያችው ቅፅበት ሊያመው የሚችል ሰው ፈተና የሚመጣበት፣ ከእዚህ ጋር ተያይዞ ሊያመው የሚችል ሰው ከሆነ፣ እሱን እያደረጉ መቁረብ ይችላሉ፣ እንደ ሌላ ጫማ መጫማት ቆጥረነው ከሆነ ጫማ አድርጎ መግባትን የትዕቢትና የድፍረት ምልክት ስለሆነ ነው መታየት ያለበት፣ ካልሲ ከክር የተሠራ ነው፡፡
የእኛ ትህትና የሚገለፅበት፣ ራሳችን ዝቅ የምናደርግበት፣ ለክብራችን ቅድሚያ ሰጥተን የተገደድንበትን ወይም ደግሞ ያሰብነውን ነገር እንደማይጠቅም አስበን ጫማ ማውለቃችን የሚያሳየው ከላይ ለክብራችን መገለጫ ያደረግነውን ነገር ሁሉ ንጉሥም ቢሆን፣ ባለስልጣንም ቢሆን ዘውዱን ያውርድ ስለሚባል ነው፡፡
ወደ እግዚአብሔር ቤት ስንሄድ ከላያችን ላይ የጫንነውን ለሥጋዊ ክብር ብለን፣ ወደ ትዕቢት የሚወስደንን ነገር ሁሉ ትተን ባዷችንን መሆኑን የምንገልፅበት ያንን ነገር ሁሉ ማውጣት ያስፈልገናል፣ “ይህ ቦታ የተቀደሰ ስለሆነ የእግርህን ጫማ አውልቅ” ተብሎ ለአባታችን ለሊቀ ነቢያት ለሙሴ ተነግሮታል፣ ከዚህ አንፃር ነው፣ ካልሲ ማድረግ ግን ምንም ከሌላ ነገር ጋር የሚያያዝ አይደለም፡፡
✍መልስ 2ኛ፡- ከቆረብን በኋላ ኬክ መብላት ወይም ኩኪስ መብላት ብለዋል፣ በጤናችን ላይ ሁከት እንዳያመጣብን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፣ እንጂ ሌላ ጊዜ የምንበላውን፣ የተሠራበትን ካወቅን፣ ፆም ከሆነ የፆም፣ ፍስክ ከሆነ ደግሞ የፍስክ መብላት ይሄንንም እንደ አንድ ምግበ ሥጋ ነው የሚታየው፡፡
በእኛ በኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ዘንድ የማይከለለከል፣ የሚበላ ሆኖ ካገኘነው ዛሬ በመቁረባችን ጤናችን ታውኮ ወደ ሌላ ህመም እንዳያመራን መጠንቀቅ ነው ያለብን፣ አንዳንዶቻችን ምቾት የማይሰማን ሰዎች እንኖራለን፣ የሚያቅለሸልሸን ሰዎች እንኖራለንና ወደዚያ ነገር እንዳያመራን እንጂ መብላት ይቻላል፡፡
ነገር ግን አልኮልና ከባድ የሆነ ምግብ በብላት፣ ከባድ የሆነ መጠጥ መጠጣት አይፈቀድም፣ ይከለከላሉ፣ የተዋሐድነውን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ማቃለል ስለሚያደርግብን፣ እሱ የምግብ ሁሉ መደምደሚያ፣ መጨረሻ ነው፣ ህይወት የሚሰጥ ነው፣ የማያስርብ የማያስጠማ፣ ዘለዓለማዊ ምግብ፣ ዘለዓለማዊ መጠጥ ነው የተሰጠን፡፡
ስለዚህ ከዚህ በላይ ሌላ ተጨማሪ ለእኛ የሚያስፈልገን ነገር ባልኖረ፣ የምንበላውም ሰው በመሆናችን ለቁመተ ሥጋ እለታዊ ምግብ ስለሚያስፈልገን እንጂ ሌላ ምግብ አስፈልጎን አልነበረም፣ ሥጋችን ወይም አካላችን ደግሞ እንደ ሥጋ ኃይል የሚያገኘውና የሚንቀሳቀሰው፣ ለእሱ የሚስፈልገውን ምግበ ሥጋ ስንሰጠው ስለሆነ ነው፡፡
በተፈቀደልን ስርዓት መጥነን መብላት፣ መጠጣት ምንም ከቅዱስ ቁርባን ጋር አያጣላንም፣ ኬክ በመሆኑ፣ ኩኪስ በመሆኑ ብቻ ከሌላው ምግብ ለይተን ይከለከላል የምንልበት ምንም የተለየ አግባብ የለም፡፡
ሁሉም ሰው ለጥያቄው መነሻ ነገር ሊኖረው ይችላል፣ ብዙ ሰዎች ግን መጠንቀቅ ያለባቸው የግድም ቢሆን እየበሉት ግን ምቾት የማይሰማቸው ምግብ አለ፣ ጤናቸውን ሊያውክ የሚችል ምግብ አለ፣ በተለይ በቆረቡ ቀን እንደዚህ ዓይነት ምግቦች መመገብ በጣም ከባድ ነው፣ ቅዱስ ቁርባን ማቃለል ነው፣ እንደገና ደግሞ በቆረብንበት እለት ሌላ ፈተና ሊያመጣብን ይችላል፣ ጠያቂያችን ከዚህ አንፃር ይታይ ለማለት ነው፡፡
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፣ አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር አድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፦ #ቅዱስ #ቁርባን ስንቀበል መጀመርያ ስጋውን ተቀብሎ ከተዋጠ በኋላ ነው ደሙን የሚቀበሉ ወይስ በአፍቸው ይዘው ቆይተው ነው አብሮ የሚዋጠው?
መልስ፦ ጠያቂያች፤ ቅዱስ ስጋውና ክቡር ደሙን ስንቀበል ሁለቱንም በአንድነት ነው ማለትም ቅዱስ ስጋውን እንደተቀበልን ክቡር ደሙንም ወዲያው ስንቀምስ አብረን እንውጣለን ማለት ነው። እንደሌላው ምግብ ወደመንጋጋ የማይሄድ የማይላመጥ ጽኑ ነውና ዝም ብሎ የሚዋጥ ስለሆነ ቅዱስ ስጋውን እንደተቀበልን ክቡር ደሙን ሲያቀብሉን በህብር አንድ ላይ ወዲያው ሳናኝክ አብሮ ይዋጣል። ለተጨማሪ መረዳት ቅዱስ ስጋ ክቡር ደሙን በምንቀበልበት ጊዜ መረዳት እና መጠንቀቅ ስለሚገቡን ዝርዝር ጉዳዮች ወደፊት በስፋት ትምህርት ልንሰጥበት የምንችል ሲሆን እስከዚያው ግን ስለ ሚስጥረ ቅዱስ ቁርባን ስርዓት አፈፃፀም የሚገልጹ ቅዱሳን መጽሐፎችን በተለይም ቅዳሴ አትናቲዎስን መመልከት ይቻላል።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ
<<< ሰላም እንዴት ናችሁ? እህቶች፣ ወንድሞች፣ አባቶች ጥያቄ ነበረኝ ፣
👉ጥያቄ፦ 1ኛ/ የቆረበ ሰው ልብሱን አውልቆ ነው የሚተኛው? ወይስ ለብሶ?
👉2ኛ/ በሥርዓተ ቅዳሴ ላይ ካሕኑ ልዩ ሐሳብና ዝሙት ያለበት አይቁረብ ይላል፣ ልዩ ሐሳብ ምንድን ነው? አልገባኝም >>>
👉🏾 ለ #ቅዱስ #ቁርባን ስለሚደረግ #ጥንቃቄ
✍መልስ፡1ኛ- መልካም ጥያቄ ነው፣ በተለይ በቅዳሴ ላይ የሚነገረው ቃል የሚያስደነግጥና የሚያስፈራ ስለሆነ፣ ሁላችንም ጥያቄ የሚሆንብን ነው፣ ባለፈውም በዚሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረ-ገጽ ላይ ተጠይቆ መልእክቶችን አስተላልፈናል፤ ይሔ ብዙ ማብራሪያ አያስፈልገውም፣ በአጭሩ እናየዋለን ማለት ነው፡፡
ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የተቀበለ ሰው የቆረበበትን ልብስ ለብሶ ነው የሚተኛው፣ ምክንያቱም የጌታችን የመድኃኒታችን ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙን ተቀብዬ ከእርሱ ጋር ነው ያለሁት፣ ከብሬያለሁ ለማለት ሲባል አንራቆትም ማለት ነው፣ ራቁትነት እግዚአብሔርን ማጣት፣ ከእግዚአብሔር መራቅ፣ መጥፋት ሲሆን፣ ልብስ መልበስ ደግሞ ከክርስቶስ ጋር መኖር ነውና ቅዱስ ጳውሎስም እንደተናገረው “እናንተ በክርስቶስ ያመናችሁ ክርስቶስን ለብሳችሁታል፣ ብሎ እንደተናገረ” ስለ ቅዱስ ሥጋውና ስለ ክቡር ደሙ ክብር ስንል፣ በስርዓት እንደተናገረው፣ በስርዓት እንደተቀመጠ ልብሳችንን አናወልቅም ወይም አንቀይርም ማለት ነው፡፡
ምናልባት የለበስነው ልብስ ንፁህ ሆኖ ይቆሽሻል የሚል ሐሳብና ስሜት ከተሰማን፣ ከቤታቻችን የምንተኛበት ንፁህ የሆነ ልብስ አንጥፈን ከነ ልብሳችን እንተኛለን ማለት ነው፣ ለአንድ ቀን አዳር ስርዓቱ ሕጉ ይሕ ነው፣ የቆረበ ሰው፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የተቀበለ ሰው ልብሱን አይቀይርም ማለት ነው፣ ምናልባት ልብሱ ለመተኛት የማይመቸው ከሆነና ልብስ መቀየር ቢፈልግ እንኳን ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ንፁህ የሆነ ልብስ ሊቀይር ይችላል፡፡
✍መልስ፡ 2ኛ/ “ካሕኑ ልዩ ሐሳብ ያለበት” የሚለው እሱን ብቻ ሳይሆን ይዘረዝራሉ፣ ብዙ ነገር ይላሉ፣ የንስሐ አባት ያልያዙ፣ የንስሐ አባት ይዘው ሲቆርቡ፣ አይተው ቢቆርቡ፣ ልዩ ሐሳብ፣ ዝሙት፣ ያለበት ቢኖር፣ የተጣላችሁ ሳትታረቁ፣ የበደላችሁ ሳትክሱ፣ ወ. ዘ. ተ. ይላሉ፤ በጥቅሉ ግን እግዚአብሔርን የሚያሳጡ፣ መልካም ነገሮችን የሚያሳጡ ነገሮች ሁሉ ልዩ ሐሳብ ብሎ ገልፆታል፡፡
ልዩ ሐሳብ ማለት የተወሰኑትን ገልጠን በአንደበትም እንኳን መናገር እስከማይቻል ድረስ በውስጣችን የምናስበው መጥፎ ሐሳብ፣ መጥፎ ድርጊት ልዩ ሐሳብ ተብሎ ተጠርቷል፣ ስለዚህ የተወሰኑትን ካሕኑ ይጠቅሳሉ፣ ጠያቂያችንም ጠቅሰውታል ልዩ ሐሳብና ዝሙት ብቻ ግን አይደለም፣ ብዙ ነገሮችን ካሕኑ ይጠቅሳሉ ማለት ነው፡፡
ከላይ እንዳልነው የንስሐ አባት ያልያዛችሁ፣ የሰው ገንዘብ የወሰዳችሁ ሳትመልሱ፣ ያስቀየማችሁ ሳትምሩ፣ ይቅር በሉኝ ሳትሉ፣ ይቅርታ ሳታወርዱ፣ እያሉ እየጠቀሱ ይሔዱና ልዩ ሐሳብ ያለበት ቢኖር አይቅረብ ሥጋው እሳት፣ ደሙ ማዕበል ሆኖ እንዳያሰጥመው፣ ያስቀየምኳችሁ በእንተ እግዚአብሔር ይቅር በሉኝ ብለው ካሕኑ እጃቸውን ይታጠባሉ።
በጥቅሉ ስናየው ግን የእኛ ድርሻ የምንችለውን እናድርግ፣ በመጥፎ ድርጊት እንዳንወድቅ እግዚአብሔር የማይወደውን ሥራ እንዳንሠራ፣ ከእግዚአብሔር የሚለየንን ነገር እንዳናደርግ የምንችለውን እንጠንቀቅ በባለፈውም መልእክቶቻችን እንደተናገርነው ማን ቢሆን ከሐሳብ ንፁህ አይሆንም፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም በስተቀር ማለት ነው፣ ሆኖም ግን በሓሳባችን መጥፎ ድርጊቶች ቢነሳሱብን እነዚያን መጥፎ ድርጊቶች እንዳናደርጋቸውና፣ በልባችን ውስጥ እንዳይቀመጡ ለማድረግ እንታገል።
ከዚህ ውጪ ልዩ ውጪ ልዩ ሐሳብ
ከተባለ መጥፎ ሐሳብ ማለት ነው፣ ልዩ ከእግዚአብሔር የሚለይ፣ የሚያርቅ ኃጢአት ነው፣ መጥፎ ድርጊት የሆነ ሁሉ፣ እግዚአብሔር አታድርጉ ያለውን ሁሉ ማድረግ፣ መሥራት ሁሉ ኃጢአት ነውና፣ ይሔንን የመሳሰለውን የያዘ ቢኖር አይቅረብ ለማለት ነው፣ ግን የምንችለውን ንስሐ አንገባለን፣ እንፀፀታለን፣ እናለቅሳለን፣ ከዚህ ውጪ ግን በሐሳባችን ፍፁም ንፁህ አንሆንም፣ አንችልምም፡፡
ንፁህ መሆን የፍፁማን ነው፣ እኛ ወጣኒያን ነን፣ ክርስትና ወጣኒነት፣ ማእከላዊነት፣ ፍፁምነት ነውና፣ ክርስቶስም ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙንም የሚሰጠን እንደ ቸርነቱ መሆኑን አንዘንጋ፣ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ስንቀበል እኮ “አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነትህና እንደ እንጂ፣ እንደ በደላችን አይሁን እያልን ነው የምንቀርበው”
ስለዚህ በሕሊናችን ይሔንን መድገም ነው፣ እግዚአብሔር የሚሰጠን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን አሁንም የሰጠን እንደ እኛ መጥፎ ሐሳብ፣ እንደ እኛ መጥፎ ድርጊት ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቸርነት ነው።
ስለዚህ ልዩ ሐሳብ ማለት ከእግዚአብሔር የሚለይ ፣ እሱ አታድርጉ፣ አትሥሩ ያለን ድርጊት ነው፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የምንቀበለው እንደ እኛ ጥንቃቄ፣ እንደ እኛ ሥራ ብቻ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ቸርነት መሆኑ እንዳይዘነጋ፡፡
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፣ አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር አድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾 ለ #ቅዱስ #ቁርባን ስለሚደረግ ቅድመ #ዝግጅት
መልስ፦ ጠያቂያችን፤ ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ግነረኙነት ዝሙት ነው፤ እየዘሞቱ ደግሞ ቅዱስ ቁርባን መቀበል አይፈቀድም። ከዚህ በፊት ላጠፉት ጥፋት ንስሐ ገብተው፣ መቁረብ ይቻላል። ነገር ግን በመጀመሪያ ዝሙቱን ለማቆም መወሰን ይገባዎታል ፤ ካልሆነ ግን እርስዎ እንደገለጹት የዝሙቱን ሃሳብ ይዘውና እደሚፈተኑበትም ራስዎን መግዛት ሳይችሉ የጀመሩትን ኀጢአት እያስቀጠሉ ለመቁረብ፥ ይህ በቤተክርስቲያን ስርአት አይፈቀድም። ከአቅም በላይ ፈተና ገጥምን ብንወድቅ በንስሐ መነሳት ቢኖርም ነገር ግን ኀጢአትን ለመተው ቁርጠኝነቱ ሊኖረን ይገባል እንጂ የተቀደሰውን ህይወታችንን እና ማንነታችንን ገና ለገና ንስሐ አለ እያልን በየጊዜው በዝሙት የምንወድቅበት ወይም ኀጢአት ለመስራት አቅደን ታጥቦ ጭቃ የምንሆንበት ህይወት ሊሆን አይገባም።
የእድሜ ልዩነት ብለው የጠቀሱትም ላለመጋባት ምክንያት አይሆንም።ስለዚህ ሌላ ምክንያት ከሌለዎትና በምርጫዎን ካስተካከሉ ተማሪ ነኝ አልተዘጋጀሁም ያሉትም ቢህን ምክንያት ሊሆን ቢችልም በጋራ መስራትና ለወደፊት ወደ አንድ ሃሳብ ለመምጣት ወስኖ ከወዲሁ በምግባር መጽናት ነው።
ስለዚህ ወይ ከዝሙት ኀጢአት ለመራቅ ወስኖና ከልብ ተጸጽቶ ንስሐ ገብቶ መቁረብ ነው፤ ወይ ደግሞ መጋባትና በቅዱስ ቁርባን ተወስኖ መኖር ነው ፤አለበለዚያ ደግሞ ከዚህ የዝሙት ኀጢአት እርም ብለው መወሰን እስኪችሉ ለጊዜው በንስሐ ህይወት እየበረቱ ከአባቶች ምክርና ትምህርት አየተቀበሉ በመንፈሳዊ ህይወትዎን አጠንክረው ከንስሐ አባት ጋር እየተመካከሩ ራስዎን ለቅዱስ ቁርባን ማዘጋጀት ነው በማለት ይህን አጭር ምክር ልከንልዎታል።
ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጉዳይ ለሚፈተኑ ወገኖች ያስተላለፍነውን ምክር የሚከተሉትን ሊንኮች ተጭነው ማስተዋል አንብበው ይረዱት እንመክራለን ።
👇👇👇
https://t.me/c/1172495782/21969
https://t.me/c/1172495782/32899
https://t.me/c/1172495782/30895
👉ጥያቄ፡- ሰላም ለእርስዎ አባቴ አንድ ጥያቄ አለኝ #ቅዱስ #ቁርባን የሚቀበሉ ሲወጡ ለመቅመስ (#ማቁራሪያ #ምግብ) ዘቢብ ይዘው ቤተ መቅደስ መግባት ይችላሉ?
✍መልስ፡- እንዲህ ዓይነት ስርዓት በቤተክርስቲያናችን ዘንድ የለም፣ መድኃኔዓለም በቸርነቱ በሌላ በምንም ሳይሆን፣ በመስቀል ላይ ተሰቀሎ፣ ቅዱስ ሥጋውን ቆርሦ፣ ክቡር ደሙን አፍስሶ ከቀኝ ጎኑም ማየገቦውን ቀድቶ ይሔን ብሉ ፣ ይሔን ጠጡ ብሎናል፡፡ ይሔ ሕይወት ይሁናችሁ፣ መድኃኒት ይሁናችሁ ብሏል፤ ከዚያም በኋላ አባቶቻችን ሚስጥረ ቁርባንን እንዴት ማክበር እንዳለብን፣ እንዴት መጠንቀቅ እንዳለብን፣ ከመቁረብ በፊት ከመቁረብ በኋላ ስርዓት ሰርተዋል፡፡
ክርስቶስ በአጠቃላይ የሕይወት ምግብ ሰጥቶናል፣ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የቅዱስ ሥጋውንና የክቡር ደሙን የመቀበል ሚስጥር በጥንቃቄ እንዲሆን፣ እዳ በደል እንዳይሆንባችሁ ሳይገባችሁ እንዳትወስዱ ብሏል፡፡ በዚያ መሠረት አባቶቻችን ቅዱስ ቀርባን ለመቀበል መዘጋጀት እንዴት እንደምንችል አስቀድመው ሕግና ስርዓት ሰርተውልናል፤ እንዴት ብለን ብንቀበለው ነው እዳ የሚሆንብን? እዳ የማይሆንብንስ እንዴት ተዘጋጅተን ብንቀበለው ነው? የሚለውን ነገር ለይተው ለሕይወት ብለን የተቀበልነው የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋው፣ ክቡር ደሙ ለሞት እንዳይሆንብን፣ ለፍርድ እንዳይሆንብን፣ ለእዳ እንዳይሆንብን ከዚህ፣ ከዚህ ነገር ተጠንቀቁ ብለዋል፡፡
ስለ ቅዱስ ቁርባን መቀበልና፣ ከምን መጠበቅ እንዳለብን ከዚህ ቀደምም እኛም አስተምረናል.፣ መጻሕፍትም ያስተምራሉ፣ሊቃውንትም ያስተምራሉ፡፡
ከተቀበልን በኋላም ደግሞ ከምን፣ ከምን መጠበቅና ምን ማድረግ እንዳለብን፣ መመገብ ያለብን የምግብ ዓይነት፣ በምን መጠን ነው፣ እንዴት ነው፣ አንድ የቀደሰ ካሕን ወይም አንድ የቆረበ ምእመን ወዲያው ወጥቶ አፉን አፍኖ ነው የሚሔደው፡፡
ያ ማለት ከሁሉ የከበርኩበትን አንደበቴ አመፅ እንዳይናገር፣ ከአፌ ክፉ ነገር እንዳይወጣ በክርስቶስ ሥጋና ደም ታትሜያለሁ፣ ከብሬያለሁ፣ ተቀድሻለሁ፣ ከኃጢያት ነፅቻለሁ ፡፡ ስለዚህ ተራ የሥጋ ስሜት የሆነ ንግግር አልናገርም፣ አላሳዝንም፣ አላስቀይምም፣ ይሔ የተቀበልኩት ሥጋውና ደሙ እሳተ መለኮት ነው፣ ለአማፂያኑ የሚያቃጥል እሳት ነው፣ ላመኑበት ደግሞ የሕይወት እንጀራ ነው ብለው ይሔን ምስክርነት ሊሰጡ ይወጣሉ፡፡
ከዚያ በኋላ ከቤተክርስቲያን ራቅ እንዳልን መጀመሪየ አፋችሁን አድፉ ይባላል፣ ስለዚህ የምንጠጣው ነገር በመጠኑም፣ በስርዓተ ቤተክርስቲያን በታዘዝነው መሠረት ብናደርገው፣ ሥጋወ ደሙን ሊያረክሰው የሚችል፣ እኛም በሥጋ ወደሙ የከበረውን ሕወታችንን ሊያጎሰቁል የሚችል አይደለም፡፡
በዚህ ዓይነት ስርዓት ነው መቀጠል ያለብን እንጂ ዘቢብ በኪሳችን ቋጥረን፣ ደብቀን ገብተን ከዚያ ይሔንን መቅመስ የሚሉት ሌላ ዝም ብለው ባእድ የሆኑ ነገሮችና፣ በኑፋቄ፣ በጥርጣሬ ሐሳብ አንዳንድ ሰዎች የሚያደርጉት ስለሆነ በጥንቃቄ ያስፈልጋል፡፡
ለሁሉም ነገር እርስዎ ከዚህ በተጨማሪ ማለት የፈለጉት ነገር ካለ ደውለው ያግኙን
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04qየእድሜ ልዩነት ብለው የጠቀሱትም ላለመጋባት ምክንያት አይሆንም።ስለዚህ ሌላ ምክንያት ከሌለዎትና በምርጫዎን ካስተካከሉ ተማሪ ነኝ አልተዘጋጀሁም ያሉትም ቢህን ምክንያት ሊሆን ቢችልም በጋራ መስራትና ለወደፊት ወደ አንድ ሃሳብ ለመምጣት ወስኖ ከወዲሁ በምግባር መጽናት ነው።
ስለዚህ ወይ ከዝሙት ኀጢአት ለመራቅ ወስኖና ከልብ ተጸጽቶ ንስሐ ገብቶ መቁረብ ነው፤ ወይ ደግሞ መጋባትና በቅዱስ ቁርባን ተወስኖ መኖር ነው ፤አለበለዚያ ደግሞ ከዚህ የዝሙት ኀጢአት እርም ብለው መወሰን እስኪችሉ ለጊዜው በንስሐ ህይወት እየበረቱ ከአባቶች ምክርና ትምህርት አየተቀበሉ በመንፈሳዊ ህይወትዎን አጠንክረው ከንስሐ አባት ጋር እየተመካከሩ ራስዎን ለቅዱስ ቁርባን ማዘጋጀት ነው በማለት ይህን አጭር ምክር ልከንልዎታል።
ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጉዳይ ለሚፈተኑ ወገኖች ያስተላለፍነውን ምክር የሚከተሉትን ሊንኮች ተጭነው ማስተዋል አንብበው ይረዱት እንመክራለን ።
👇👇👇
https://t.me/c/1172495782/21969
https://t.me/c/1172495782/32899
https://t.me/c/1172495782/30895
👉🏾 ለ #ቅዱስ #ቁርባን ስለሚደረግ #ጥንቃቄ #ዝግጅት
👉ጥያቄ፦ ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች አንድ አስቸኳይ ጥያቄ አለኝ
1.የቆረበ ሰው ማማተብ ይችላል?
2.የትኛው ስግደት ነው የሚከለከለው ማለቴ የአምልኮት ስግደት እና ለቅዱሳን የሚሰገድ ስግደት ሊሰግድ ይችላልን?
3.ሌላው ደግሞ ዕህል እስኪበላ ድረስ ማውራት ካልቻለ ዕህሉን ከመብላቱ በፊት ፀልዮ መብላት አይችልምን?ማለቴ ሲፀለይ አፍ ይንቀሳቀሳልና መፀለዩ ችግር አለው?
4.ቅዳሴ አልቆ ይፍታ ሲባል መስገዱ ችግር አለውን?
5.በቅዳሴ ፀበል ብቻ ማውራት ይችላል?
6.ፀበል ፃዲቅ መቅመስ ይችላልን ማለቴ በእርሱ ማውራት ይችላልን?
መልስ፦ ጠያቂያችን፥ የቆረበ ሰው ማማተብ ይችላል ወይ ብለው ለጠየቁን፥ እንዴት አያማትብም? እንዴ ማማተብ እኮ ምንም ከቁርባን ጋር አይገናኝም ፤ ማማተብ ካለበት ያማትባል። ወገኖቼ፤ እባካችሁ ዝም ብለን በከንቱ ጥቃቅን ነገሮች ላይ በመጨናነቅ ጊዜ ከመፍጀት ብዙ ጊዜ የማይሰጡ ሃይማኖታዊ ጉዳዮችና ጥያቄዎች ላይ ብናተኩር መልካም ነው። የተለየ ምክንያት ወይ ክርክር ከገጠማችሁ ይሄን ይሄን ለማለት ፈልጌ ነው፤ ወይም ከዚህ ተነስቼ ነው የጠየቁት ቢሉን ያንን መሰረት አድርገን ልናብራራ እንችላለን። እንጂ ስለቆረብን አንጸልይም ወይ ስመ እግዚአብሔር አንጠራም እንደማለት እኮ ነው ይሄ። ስለዚህ ማማተብ በየትኛውም ጊዜ በየትኛውም ሰዓት ከምንም ጥፋት ጋር ወይም ከምንም መሳሳት ጋር፣ ከምንም የቤተክርስቲያን ስርዓት ከመሻር ጋር አይገናኝም።
ቆርበን የትኛው ስግደት ነው የማይፈቀደው ላሉት በንስሐ የተሰጠ ስግደት ቢኖር ወይም ራሳችን ወደን ፈቅደን በጾም ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ገብተን በጸሎት ጊዜ የምንሰግደው ስግደት ቢኖር ማለትም በግል ቀኖና ተሰጥቶን የምንሰግደው ቢኖር ይሄን ቆርቦ አይሰገድም። ሲጀመር የአምልኮት ስግደት ሰግደን ወደ ቤተክርስቲያን ገብተናል ቆርበን ወጥተናል ሌላ ቤተክርስቲያን በአጋጣሚ በሌላ ዝግጅት ብንሄድ ቤተክርስቲያን ስንገባ መቼስ ለፈጠረን አምላክ ስግደት ሳናቀርብ አንገባም።
እህል ከመብላቱ በፊት ፀልዮ መብላት ላሉት ችግር የለውም ጸሎትና ቅዱስ ቁርባን የተዋሀዱ ናቸው፣ ክብር የሚያበዛ ሃይለ አጋንንትን የሚቀጠቅጥ ነው። ተቀድሰን ባለንበት ሰዓት ሌላ ሃይለቃል ወይ ቅድስናችን የሚፈታተን ሃይለቃል ላለማውጣት እንጂ ምንም ሳንቀምስ አፍ በ ጸሎት ስለተንቀሳቀሰ እንደነውር ወይም ቅዱስ ቁርባንን እንደመድፈር አያስቆጥርም።
ቅደሴ አልቆ ይፍታህ ሲባል መስገድ ችግር አለው ወይ ላሉት፤ መስገድ ሳይሆን አሜን ብሎ ራስን ዝቅ ማድረግ ወይም በትህትና ለእግዚአብሕር ራሳችንን ስናስገዛ ማሳየታችን ከልብ እንደ አስተብርኮ ነውና አይሰገድም።
በቅደሴ ፀበል ብቻ ማውራት ላሉት ምናልባት ቅዳሴ ጸበል እኮ እንደቁርባን ነው፤ ሶስቱ ነገሮች አንድ ናቸው አንድ ሰው ቅዱስ ቁርባን ተቀብሏል የምንለው ሦስቱ ነገሮች አንድ ላይ ይተባበራሉ፤ በእለተ አርብ በመስቀሉ ላይ ለእኛ መድሃኒተ ስጋ መድሃኒተ ነፍስ እንዲሆኑን ይሄን የበላ እና የጠጣ የዘለዓለም ህይወት ያገኛል ብሎ የሰጠን ስጦታዎች ናቸው ደሙ ስጋውና ከጎኑ የወጣው ማየ ገቦ ነውና እሱ እንደ ቅዱስ ቁርባን ነው የሚቆጠረው ማለት ነው። እና በእግዚአብሔር ስም የከበረ ጸበልም የተለየ ሆኗልና እንደ ምግበ ስጋና መጠጥ አናየውም።
ጸበል ጻዲቅ መቅመስ ይቻላል ወይም በርሱ ማውራት ይቻላል ወይ ላሉት፤ አዎ ይቻላል።
ጠያቂያችን ለሁሉም ነገር በቅዱስ ቁርባን ሲኖሩ አንድም ስህተት ላለመፈፀም ተጨንቀው እንደሆነ እንረዳለንና ይህም በጣም ደስ ይላል፤ መጠየቅ ያደርጋል ሊቅ ነውና የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
ቅዱስ ቁርባን - ከንስሐ አባት ጋር በተያያዘ
👉ጥያቄ፡- አንድ ጥያቄ ነበረኝ፤ አሱም ከቤተሰብ ጋር አብረን #ንስሐ ተቀብለን ነበርና፤ቀኖና ከጨረስን በኋላ እኔና እህቴ #ቅዱስ #ቁርባን ለመቀበል አስበን ነበር፡፡ ነገር ግን የንስሐ አባታችን ይህ አይሆንም፤ እድላችሁን አልዘጋም፣ በኋላ የቆረበ ሰው ካልሆነ #ትዳር መያዝ አትችሉም ብለው ከለከሉን ምን ማድረግ አለብን?
መልስ፦ ጥያቄው በአጭሩ ቤተሰቡ አጠቃላይ የንስሐ ቀኖና እንደተቀበሉና፤ ከቀኖናቸው ፍፃሜ በኋላ የክርስቶስን ሥጋውንና ደሙን ለመቀበል ቢዘጋጁም ልጆች ናችሁና እናንተ መቀበል አትችሉም ፤፡ እድላችሁን በዚህ እድሜያችሁ አልዘጋም፣ ብለው የንስሐ አባታችን ከለከሉን የሚል ነው፡፡ ምንናልባት ጠያቂያችን ጥያቄውን ሲያብራሩ ያልተሟላ ሐሳብ ወይም የቀረ ሐሳብ ካላ እንደገና ማስተካከል ይችላሉ፡፡ነገር ግን እኛ በገባን፤ የቆረበ ካልሆነ ማግባት አይችሉምና እንዴት ይሆናል ? ለሚለው ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተንበታልና አንብበው ይረዱት።
ስለቅዱስ ቁርባን አስፈላጊነትም ሆነ እኛ በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በእርሱ ደግሞ “በወልድ ውሉድ” ተብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንባል ዘንድ የአባትነቱን ፀጋ የሰጠን እግዚአብሔር ገና በአርባ (40) ቀን እና በሠማኒያ (80) ቀን ክርስትና ተነስተን በቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ታትመን የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንንበት ጊዜ ጀምሮ፤ ማንም ኦሮቶዶክሳዊ የተዋሕዶ ልጅ ክርስቲያን ሁሉ ከቅዱስ ቁርባን መለየት የለበትም፡፡ ከቅዱስ ቁርባን የሚለየንና የሚያርቀን እራሳችን ወደን ፈቅደን የምንሠራው ኃጢያታችን፤ በደለኛነታችን፣ ወንጀለኛነታችን ካልሆነ በስተቀር ማንም አይከለክለንም፡፡ በሕፃንነት እድሜያችንም፣ አካለ መጠን በደረስንም ጊዜ፣ ከጋብቻ በፊትም፣ በጋብቻ ጊዜም፣ ከጋብቻ በኋላም ሰው ያለ ምገበ ሥጋ ሳይበላ፣ ሳይጠጣ፣ ሳይለብስ እንደማይኖር ሁሉ በሥጋው፣ በነፍሱም፣ ቅዱስ ቁርባን ሳይቀበል፣ የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን ሳይበላ፣ ክቡር ደሙን ሳይጠጣ መኖር ወይም መዳን፣ የዘላለም ሕይወት ማግኘት አይችልም፡፡ የሚያንሰውና ትንሹ ነገር ኃላፊውና ቀሪው የሥጋ ምግብ ነው፡፡ ለጊዜው ለቁመተ ሥጋ ሰው ሆነን በአጥንት፣ በጅማት፣ በሥጋ፣ በደም እንድንንቀሳቀስ አዳማዊ ተፈጥሮ ሆኖ እንዲህ የሚታይ፣ የሚዳሰስ፣ የሚራብ፣ የሚጠማ፣ የሚደክም፣ የሚበረታ፣ ሞት፣ ህልፈት ሁሉ በጊዜያዊነት የሚስማማው ይኼንን ሥጋ እግዚአብሔር እስከፈቀደ ጊዜ ወይም ደግሞ እስከተወሰነልን የእድሜ ገደብ ድረስ ለመቆየት ያህል ይኽንን የሥጋ ምግብ እንበላለን፣ እንጠጣለን፡፡ ከዚያ በላይ ግን፤ በልተነው የማያስርበን፣ ጠጥተነው የማያስጠማን፣ ጊዜያዊ ሳይሆን ዘለዓለማዊ፣ ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ፣ ኃላፊ ሳይሆን ለዘለዓለም የሚያኖር፣ የነፍስ ምግቧ የሆነውን ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል አንዳችም ጊዜ ልናቋርጥ የምንችልበት ጊዜ የለንም፡፡ ይኼን ነው ማወቅ ያለባችሁ፡፡
ወደ እያንዳንዳችን ዝርዝር ኃጥያት ከገባን፤ ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቀን ኃጥያት ምንድን ነው? አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት ብለን ኃጢያት የሆነው ነገር ሁሉ ማንም ሰው የክርስቶስን ሥጋ ሁልጊዜ መብላት፣ ደሙን መጠጣት እንዳለበት ከታዘዝነው ሐዋርያው እንደነገረን፤ እዳ እንዳይሆንባችሁ ያለን ነገር አለ፡፡ በድፍረት ሆናችሁ ማለት ነው፡፡ ምንም እዳ፣ ፍርድ እንደማያመጣ፣ እንደማያስፈርድብን፣ እንደማያስወቅሰን፣ ቅርበ ፈጣሪ እንደማያስቆመን ነገር አቃልለን፤ እንደ ሥጋ ምግብ እንዳናየው፤ ከእኛ የሚጠበቀው መጠንቀቅ አለብን፡፡ ሌላውን የሚበልጠውንና ብዙውን በእርሱ ቸርነት የሚያነፃን፣ የሚቀድስን ሥጋውና ደሙ ነው፡፡ ግን ወደዚህ ከሁሉ ወደ ከበረው በታቦተ ምስዋዑ ላይ በንፅሕና፣ በቅድስና ሆነው ካሕናት አክብረውት እንካችሁ ይኼ አማናዊ የክርስቶስ ሥጋው ነው፣ አማናዊ የክርስቶስ ደሙ ነው ከዚህ ብሉና ጠጡ፤ የዘላለም ሕይወት እንድታገኙ ብለው የሚሰጡን ቅዱስ ቁርባን ከዘላለማዊ ውድቀት፣ ወይም ሞት የሚያድነን ስለሆነ፣ እኛንም ደግሞ የበለጠ የሚቀድሰን ከኃጥያታችን “ወበደሙ ያንፅኃነ፣” በደሙ ፈሳሽነት ማለት ነው፡፡ ሰው በውኃ ታጥቦ እንደሚጠራ ከእድፈቱ፣ ከኃጥያት እድፈት የሚያነፃን የክርስቶስ ደም ነው ተብሏልና፤ ከኃጥያት ለመንፃት ነው፡፡ ያስፈለገንም ለዚህ ነው፡፡ ከነፍስ ረሐብ፣ ከነፍስ እድፍ ሁሉ ሊያነፃን ሊቀድሰን የሚችል የክርስቶስ ሥጋውና ደሙ ነው፡፡
እንግዲህ ወደፊት ስለ ጋብቻ፤ የቆረበ ታገባላችሁ፣ አታገቡም ለሚለው አዎ ክርስቲያን ሁልጊዜ ማሰብ ያለበት ቋሚ ምኞቱም ሆነ እድል ፈንታው እንዲሆንለት፤ እግዚአብሔርን የሚለምነውም ያንን ከአርባ ቀን፣ ከሠማኒያ ቀን ጀምሮ ያመጣነውን ቅዱስ ቁርባን አስከብሮ ለማስቀጠል አብሮ ከእኛ ጋር በቅዱስ ቁርባን የሚወሰን ባል፣ ሚስት ለማግኘት እንድንችል እሱን ማሰብ አለብን፡፡
ያን ጊዜ ከዚያ ስንደርስ ደግሞ፤ ሌላ በተቃራኒ ይኼን የማይፈልግ የትዳር ጓደኛ ቢመጣብን ምን እናድርግ? የሚለውን በምክረ ካሕን ችግሩ ይቃለላል፡፡ ከወዲሁ አጥር አጥሮ ከማስፈራራት፣ ነገ በቅዱስ ቁርባን ተወስናችሁ ከኖራችሁ፤ ወደ ትዳር ስትመጡ የቆረበ ሰው ካልሆነ፣ ሌላ ማግባት ስለማትችሉ የተባለው፡- ስለዚህሳ ይኼን ገና ወደፊት እግዚአብሔር በራሱ ፈቃድ ስለእኛ አስቦ ከወዲሁ እንዳንቸገር ነገሮችን አመቻችቶ እንደሚሰጠን ማመን ትተን፤ ገና የዛሬ 20 ዓመት፣ የዛሬ 18 ዓመት ለአካለ መጠን ስንደርስ በሚያጋጥመን ፈተና እንዳንቸገር፤ ዛሬ ጫካ ውስጥ ገብተን ወይም ከዘላለማዊ ሕይወት ተለይተን ከነኃጥያታችን መኖር አለብን ብለን ማሰብ አያስፈልግም፡፡
ስለዚህ ምናልባት ከአባት ጋር ስትነጋገሩ፣ ከካሕን ጋር ስትነጋገሩ ተወያይታችሁ የደረሳችሁበት ሐሳብ ምን እንደሆነ ደግሞ የበለጠ ለመረዳት በውስጥ መስመራችን አግኙንና አነጋግሩን፡፡ አስፈላጊ ከሆነና ምናልባት እኒህ አባት ለእናንተ አስበው ከሆነ፣ የተቸገሩበት ሌላ እኛ ያላየነው መንገድ ካለ በእርሱ ዙሪያ ተወያይተን፤ ከዚህ የሚበልጥ ነገር የለምና ለእናንተ በጎውን ነገር፣ ቀናውን ነገር ለመምከር እንድንችል አግኝታችሁን አማክሩን፣ ምክር እንሰጣችኋለን ማለት ነው፡፡ ለጊዜው ግን ቋሚው ትምህርት ይኼው ነው፡፡ በምንም ተአምር የሰው ልጅ በሆነው ሁሉ በአርባ ቀኑም፣ በክርስትና የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ በሠማንያ ቀኗም የክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ሆና ክርስትና ከተነሣች ጊዜ ጀምሮ እንዳለመታደል ሆኖ ሠይጣን ነጥቆን በመናፍቅነት፣ በክህደት ማዕበል ተወስደን፣ ተገፍተን፣ ሠይጣን ከእግዚአብሔር መንግሥት ለይቶን ካልሆነ በስተቀር፤ የተዋሕዶ ኦርቶዶክሣዊ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከቅዱስ ቁርባን መራቅ እንደሌለበት ቋሚ የቤተክርስቲያን ትምሕርት ነው፡ይኼንን እንድታውቁ ነው፡፡ ጠያቂያችንም ብቻ ሳይሆኑ ሁላችሁም የዚህ ፕሮግራም አባላት ይኼንን ትምሕርት ደጋግመን የምንሰጠው፣ አፅንአዖት የሰጠንበትም መታወቅ ያለበት፤ መመከርም ያለበት ጉዳይ ስለሆነ ቅድሚያ የምሰጠው ነው፡፡
የመከረን ያስተማረን የገሰፀን የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን ሁላችንንም በሕይወት ይጠብቀን፡፡አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፦ አባታችን ሰላም ዋሉ, #የንስሀ #አባት ነበረኝ ግን የውስጤን በደንብ ለመናገር አልቻልኩም እምነግራቸውን ሀጢያቶች በሙሉ ያቀሉታል በተማርኩት መሰረት ሀጢያቴን #በዝርዝር አርጌ ጽፌ ከላይ ከላይ እንድነግራቸው ያረጉኛል አሁን ደሞ እኔ ወደ ተውኩት ህጢያት እየተመለስኩ ነው ሂወቴ መስመር እየሳተ ነው…አሁን ላይ የውስጤን በደንብ እየነገርኩት ወደ #ቅዱስ #ቁርባን እሚያቀርበኝ ስለ ግንኙነቴ እማማክረው ሁለታችንም ወደ መንፈሳዊነት እሚመልሰን ረዳት ነው እምንፈልግው ምን ላድርግ?
መልስ ፦ ጠያቂያችን፤ የሚያስታውሱትንና የሰሩትን ኅጢአት አንዱንም ሳያስቀሩ ለንስኅ አባትዎ በዝርዝር ማስረዳት የግድ አስፈላጊ ነው። የእርስዎ ንስኅ አባት ሊናዝዙ ስልጣን ያላቸው የንስኅ አባትዎም በስነስርዓት አድምጠው የሰሩትን ኅጢአት በዝርዝር ካወቁ በኋላ ለእያንዳንዱ ጥፋት የቤተክርስቲያን ቀኖና በሚያዘው መሠረት ንስኅውን በፆም በፀሎት በስግደት ወይም በሌላ ቀኖና እንዲፈፅሙ ትዕዛዝ መስጠት ይጠበቅባቸዋል። ጠያቂያችን ግን እንዳሉት ገና ስለፈፁት ጥፋት ዘርዝረው ሳይጨርሱ ወይም ሃሳብዎን እስከመጨረሻው ባለማዳመጥ ቀላል አድርገው የሚተዉት ከሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ሊያስጠይቃቸው ስለሚችል ምንም እንኳን ጥፋቱ የካህኑ ቢሆንም እርስዎ የህሊና ነፃነት ያገኙ ዘንድ፦
1ኛ/ እንዳሉትም ለመንፈስ ልጆቻቸው ቅድሚያ ሰጥተው የሚያስተምሩና ዘወትር የሚፀልዩ ንስኅ አባት መርጠው በመያዝ ንስኅ መግባት፣ ወይም ደግሞ
2ኛ/ ወደ ገዳም አባቶች ሄዶ ንስኅ መቀበል፣
3ኛ/ እንደ ደግሞ አማራጭ ማድረግ ያለብዎት ወደ እግዚአብሔር ቤት ሄዶ በህሊና ፀፀት የሰሩትንና ተናግሬ ሳልጨርስ አቋረጡኝ ያሉትን ኅጢአት ሁሉ በመናዘዝ የሱባኤ ጊዜ ይዘው መፆም፣ መፀለይ፣ ልዩ ልዩ የቱሩፋት ስራ በመስራት የግልዎትን ቀኖና መፈፀም ይችላሉ።
የበለጠ ምክርና እገዛ እንድንሰጥዎ በውስጥ መስመር በተላከልዎ ቁጥር ደውለው ሊያገኙን ይችላሉ።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
ስለ ቅዱስ ቁርባን ሥርዓት በጋብቻ - (እጮኛሞች ማወቅ ያለባቸው)
👉🏾👉🏾👉🏾 #ጋብቻና #ቅዱስ #ቁርባን
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን በሙሉ፤ በርዕሱ የተጠቀሰውን የትምህርት ክፍል በገብረ እግዚአብሔር ኪደ ከተጻፈው ‘ትንሿ ቤተክርስቲያን’ መጽሐፍ ወስጥ የሚከተለውን ትምህርት ልከንላችኋልና ጠቃሚ ስለሆነ አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።
ጋብቻ በእውነት ታላቅ ምሥጢር ነው። በአንድ መልኩ ባል ካለመኖር ወደ መኖር ለመምጣት ምክንያት የሆኑትን የወለዱትን ያሳደጉትን አባትና እናቱን ይተዋል። አምጣ የወለደችውን እናቱን ለእርሱ ብለው ብዙ ውጣ ውረዶችን ያሳለፉ ወላጆቹን ይተዋል። ዕለት ዕለት ያዩት እርሱም ያያቸው የነበሩትን ወላጆቹን ይተዋል። ከዚያም ካለመኖር ወደ መኖር ለመምጣት ምክንያት ካልሆነችው አምጣ ካልወለደችው እርሱን ለማሳደግ ምንም አስተዋጽኦ ከሌላት ምናልባትም ለብዙ ዘመናት አይታው ከማታውቀው ሴት ጋር ይተባበራል። ከሌላ ከማንም በላይም አክብሮ ይቀበላታል። ሚስትም እንደዚያው! ዕጹብ ድንቅ የሚያሰኘው ደግሞ ይህ ሁሉ ሲሆን ወላጆች አያዝኑም። እንዲያውም ይደሰታሉ፤ ይደግሳሉም።
ይህንን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከጥምቀት ጋር ያመሳስለዋል። የሚጠመቅ ሰው አስቀድሞ ራሱን ከጣዖታት ካልለየ በቀር ነፍሱ ከሙሽራዋ ከክርስቶስ ጋር እንደማትዋሐድ ሁሉ ሰውም አባትና እናቱን ካልተወ በጋብቻ ከሚስቱ ጋር አይተባበርም። የሚጠመቅ ሰው ጣዖቱንና ያሳደጉትን ሁሉ ትቶና ደስ ብሎት ሁለንተናውን ለእግዚአብሔር ሰጥቶ ሲጠመቅ ምሥጢር እንደሚፈጸም ሁሉ ተጋቢዎችም በዚህ መንገድ ስለሚዋሐዱ ጋብቻ ታላቅ ሚስጢር ነው።
በሌላ መልኩ ደግሞ ይህ ሰርግ በክርስቶስና በቤተ ከርስቲያን መካከል ለተደረገው ሰርግ ምሳሌ ስለ ሆነ ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው ይህንንም ንዑድ ክቡር የሚሆን ጳውሎስ “ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፤ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተክርስቲያን እላለሁ” ሲል ገልጾታል (ኤፈ 5 ፥32) ቀዳማዊው አዳም ባንቀላፋ ጊዜ ሔዋን ከጎኑ እንደተገኘች ክብር ይግባውና ዳግማይ አዳም የተባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመልዕለተ መስቀል ላይ በተኛ (በሞተ) ጊዜም ከጎኑ ከፈሰሰው ውኃውና ደሙ ዳግሚት ሔዋን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተገኝታለችና። ቀዳማዊው አዳም ያን ጊዜ ሲተኛ በፈቃደ እግዚአብሔር እንጂ ከወደቀ በኋላ እንደሚተኛ እንዳልነበረ ሁሉ ጌታችን ክርስቶስም በመስቀል ላይ የተኛው ነውር በደል ኖሮበት ሳይሆን ንጹሐ ባህርይ ሆኖ ለካሣ ለቤዛነት ነው።
በሦስተኛ ደረጃ “ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው” የምንለው በመለኮትና በትስብእት መካከል ለተደረገ ተዋሕዶ ትእምርት ስለ ሆነ ነው። ይህንንም ሊቃውንቱ እመቤታችንን ሰርግ ቤት ካሏት በኋላ በእርስዋ፥
“እንደ መርዓዊና እንደ መርዓት ተዋሕዶ ትስብእትና መለኮት አንድ ሁነዋል። (በሰርግ) አዝማደ መርዓዊና አዝማደ መርዓት አንድ እንደሚሆኑባት ሰውና መላእክት ሰውና እግዚአብሔር ነፍስና ሥጋ ሕዝብና አህዛብ አንድ ሁነዋልና” ይላሉ
ይህ ሁሉ ሊሆን የሚችለው ግን በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ እስከተፈጸመና በሚታይ አገልግሎት የማይታይ ጸጋ ስንቀበል ከዚያም የዓቅማችንን ያህል በመንፈሳዊ ስርዓትና ምግባር ስንኖር ነው።
ሰርጋችንን እውነተኛና የክርስቲየን ጋብቻ የሚያደርገው ቅዱስ ቁርባን ነው። “በሥጋ ወደሙ አላገባም” የሚል ቢኖር እርሱ እንደ አረማውያን እንደ ሆነ ቅድስት ቤተክርስቲያን አጥብቃ ታስተምራለች። “አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም” እንደተባለ ባልና ሚስት ከሁለት አካል አንድ አካል የምንሆነው ከሁለት ፈቃድ ወደ አንድ ፈቃድ የምናደርገው በሥጋ ወደሙ ነው (ማቴ 19፥6)
ክብር ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋእለ ስብከቱ በአንድ መልኩ መንግሥተ ሰማያት “ለልጁ የሰርግ ድግስ ያደረገ ንጉሥን” እንደምትመስል ተናግሯል (ማቴ 22፥1) በሌላ መልኩ ደግሞ በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ተገኝቶ ውኃውን ወደ ወይን ለውጦ ለሙሽሮችና ለሰርገኞች መስጠቱን እውነተኛ ጋብቻና ቅዱስ ቁርባን የማይለያዩ መሆናቸውን በግልጽ የሚያስረዳን ነው (የሐ 2 1-11) በተአምር የተገኘው ወይን በጸሎተ ሐሙስ ማታ ጌታ የባረከው ጽዋ ያመለክታልና።
ቅዱስ ቁርባን በራሱ ሰርግ ነው፤ ሥጋችን ሥጋው አጥንታችን አጥንቱ የሚሆንበት ምሥጢር ነው። ስለዚህም በቅዳሴያችን፦
“በሰርጉ ጊዜ ሥጋውን የሚሠዋና ፈጽሞ ምግብ የሚሆን ሙሽራን ያየ ማን ነው? ወልደ እግዚአብሔር ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ከእርሱ በቀር እንደ እርሱ ያደረገው የሌለ እንግዳ ሥርዓትን በዚህ ዓለም ሠራ። በሰርጉ ጊዜ በሐዋርያት ፊት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ማዕድ አድርጎ ሠራ። ከእርሱ ይበሉ ዘንድ ያመነውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጉ ጊዜ መብል መጠጥ የሆነውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” እንላለን
ጨምረንም እንደዚሁ፦
“እውነተኛ አምላካችን ጌታችን ክርስቶስ ሆይ ፤ የገሊላ አውራጃ በምትሆን በቃና በጠሩህ ጊዜ ወደ ሰርግ የሔድህ ውኃውንም ባርከህ ጠጅ ያደረግህላቸው በፊትህ ተቀመጠ ይህን ወይን እንደ እርሱ አድርገው። አሁንም ባርከው ፤ አክብረው፤ አንጻውም ሁልጊዜ የሥጋችንና የነፍሳችን የልቦናችንም ሕይወት ይሆን ዘንድ” የምንለው ለዚህ ነው።
ሰርግም እንደዚሁ በሥጋ ወደሙ ፥ “ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፤ ሥጋም ሥጋዬ ናት” የሚለውን ቃለ እግዚአብሕር እውን የሚሆንበት (ዘፍ 2፥23) ከሥጋዊ አንድነት በላይ የመንፈስን አንድነትና ፍቅርን ገንዘብ ወደ ማድረግ የምናድግበት ነው።
በጋብቻችን ካህናት ከሌሉና ሁለታችንም አንድ የምንሆንበትን ሥጋ ወደሙ ካልተቀበልን ይህ ምሥጢር አይፈጸምልንም። ፍትሐ ነገሥቱ ይህንን እንዲህ ሲል አስቀምጦታል፥
“የጋብቻ አንድነት በካህናት መኖርና በሙሽሮቹ ላይ የሚጸለየው ጸሎት ካልሆነ በቀር አይሆንም። በተክሊል ጊዜ ሁለቱ አንድ የሚሆኑበትን ቅዱስ ቁርባንን ያቀብሏቸው ። ክብር ይግባውና ጌታችን እንደ ተናገረው አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ያለዚያ ግን ጋብቻ ተብሎ አይቆጠርላቸውም”
ይህ የሚሆንበት ዋና ምክንያትም በጋብቻ ሦስት አካላት ስላሉ ነው። ተጋቢዎቹና እግዚአብሔር! ከእነዚህ አንዳቸው ከሌሉ ጋብቻ ተብሎ አይቆጠርም።
(ይቀጥላል)👇
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ
👉🏾 ለ #ቅዱስ #ቁርባን ስለሚደረግ ቅድመ #ዝግጅት
መልስ፦ ጠያቂያችን፤ ከጋብቻ በፊት የሚደረግ ግነረኙነት ዝሙት ነው፤ እየዘሞቱ ደግሞ ቅዱስ ቁርባን መቀበል አይፈቀድም። ከዚህ በፊት ላጠፉት ጥፋት ንስሐ ገብተው፣ መቁረብ ይቻላል። ነገር ግን በመጀመሪያ ዝሙቱን ለማቆም መወሰን ይገባዎታል ፤ ካልሆነ ግን እርስዎ እንደገለጹት የዝሙቱን ሃሳብ ይዘውና እደሚፈተኑበትም ራስዎን መግዛት ሳይችሉ የጀመሩትን ኀጢአት እያስቀጠሉ ለመቁረብ፥ ይህ በቤተክርስቲያን ስርአት አይፈቀድም። ከአቅም በላይ ፈተና ገጥምን ብንወድቅ በንስሐ መነሳት ቢኖርም ነገር ግን ኀጢአትን ለመተው ቁርጠኝነቱ ሊኖረን ይገባል እንጂ የተቀደሰውን ህይወታችንን እና ማንነታችንን ገና ለገና ንስሐ አለ እያልን በየጊዜው በዝሙት የምንወድቅበት ወይም ኀጢአት ለመስራት አቅደን ታጥቦ ጭቃ የምንሆንበት ህይወት ሊሆን አይገባም።
የእድሜ ልዩነት ብለው የጠቀሱትም ላለመጋባት ምክንያት አይሆንም።ስለዚህ ሌላ ምክንያት ከሌለዎትና በምርጫዎን ካስተካከሉ ተማሪ ነኝ አልተዘጋጀሁም ያሉትም ቢህን ምክንያት ሊሆን ቢችልም በጋራ መስራትና ለወደፊት ወደ አንድ ሃሳብ ለመምጣት ወስኖ ከወዲሁ በምግባር መጽናት ነው።
ስለዚህ ወይ ከዝሙት ኀጢአት ለመራቅ ወስኖና ከልብ ተጸጽቶ ንስሐ ገብቶ መቁረብ ነው፤ ወይ ደግሞ መጋባትና በቅዱስ ቁርባን ተወስኖ መኖር ነው ፤አለበለዚያ ደግሞ ከዚህ የዝሙት ኀጢአት እርም ብለው መወሰን እስኪችሉ ለጊዜው በንስሐ ህይወት እየበረቱ ከአባቶች ምክርና ትምህርት አየተቀበሉ በመንፈሳዊ ህይወትዎን አጠንክረው ከንስሐ አባት ጋር እየተመካከሩ ራስዎን ለቅዱስ ቁርባን ማዘጋጀት ነው በማለት ይህን አጭር ምክር ልከንልዎታል።
ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ጉዳይ ለሚፈተኑ ወገኖች ያስተላለፍነውን ምክር የሚከተሉትን ሊንኮች ተጭነው ማስተዋል አንብበው ይረዱት እንመክራለን ።
👇👇👇
https://t.me/c/1172495782/21969
https://t.me/c/1172495782/32899
https://t.me/c/1172495782/30895
👉🏾ስለ ሁለት #ጥንዶች ስለ #ቅዱስ #ቁርባን ሁኔታና፣ ስለ ሥርዓተ ተክሊል ጋብቻ የቀረበ ጥያቄ
👉ጥያቄ፡- ለእራሴ ጥያቄ የሆነብኝ አንድ ወጣት ወንድ ወይም ሴት በክርስቲያናዊ ሕይወት እያለ፤ እያለች ንስሐ ገብቶ የመጨረሻው ማሳረጊያው ሥጋ ወደሙ ነው፡፡ ነገር ግን የንስሐ ገዜ ቁርባንና፣ ሌላው ቁርባን ይለያያል ወይ? እንደማይለያይ ባውቅም ምንያት አልባ ነኝ ብታስረዱኝ? ለማለት የፈለግሁት፣ አንድ ሰው ንስሐ ገብቶ
ሲቀጥል ሥጋወደሙ ቢወስድ ቀጣይ የሕይወት አጋሩ ጋር የሚደርገው ሰው ለልጁ ወይም ለልጇ ፈቃደኛ ባይሆን ያ ሥጋ ወደሙ የወሰደው ሰው ምን ማድረግ አለበት? ለምሳሌ እኔ ሥጋ ወደሙ ወስጄ በእሱ ተገድቤ እያለሁ የሕይወት አጋር የምላት ደግሞ ፈፅማ በዚህ የማትስማማ ቢሆን የእኔ ውሳኔ ምን ሊሆን ይችላል? ነገር ግን ነገ ከነገ ወዲያ ሥጋወደሙን አልቀበልም ብትል ይህን ሥጋወደሙን የወሰደው ሰው ፍላጎቱ በተክሊል ሲቀጥል በቅዱስ ቁርባን ቢሆን ከእርሱ ጋር ፈፅሞ በዚህ መስማማት ባይችል ምን ማድረግ አለበት? ሰፋ ያለ ማብራሪያ ከቻላችሁ በሪከርድም ወይም በፅሁፍ ብታደርጉልኝ ስል ውድ ልጃችሁ እጠይቃለሁ፡፡
መልስ፡- ለባልና ሚስትነት በቃል ኪዳን የተጫጩ ሁለት ጥንዶች አንደኛው ከመጀመሪያው ጀምሮ በቅዱስ ቁርባን ተወስኖ የመጣ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ለጋብቻ የተመረጠው ወይም የተመረጠችው በቅዱስ ቁርባን ወይም በሥርዓተ ተክሊል ለመጋባት ያልፈለገች ወይም ያልፈለገ ይሆናል፡፡ ይኼንን ችግር እንዴት መፍታት ይቻላል? እንግዲህ ያው የኑሮ ጉዳይ ነው፤ የሕይወት ጉዳይ ነው፣ የትዳር ጉዳይ ነው ፣ የፍቅር ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን የአብሮ፣ የጋራ ሕይወት ለማስቀጠል ከብዙ ጥናት በኋላ ተፈላልገው የተገናኙ ጥንዶች ሆነው እያሉ፤ ደግሞ የሚያሳዝነው በእነሱ መካከል ላይ ትልቅ ፈተና የሆነው አንደኛው ቅዱስ ቁርባንን ማስቀጠል የሚፈልግ፤ ሌላው ማስቀጠል የሚፈልግ ሌላው ደግሞ፤ ቅዱስ ቁርባኑም ቀደም ሲልም ያልመጣ ወይም በቅዱስ ቁርባን ያልተወሰነ ከመሆኑም በላይ ደግሞ አሁንም ጋብቻውን በቅዱስ ቁርባን አላደርግም የሚል ዓላማና፣ አቋም ያለው ወይም ያላት ነው ማለት ነው የጥያቄው ሐሳብ፡፡ ከዚያም ሥርዓተ ተክሊልም በድንግልና የኖሩ ሰዎች ናቸው እና ከዚህም ከሥርዓተ ተክሊሉ ጋ ተያይዞ አንደኛው በድንግልና ሕይወት የነበረ፣ ሌላኛው ደግሞ በድንግልና ሕይወት ያልነበረ፡፡ ስለዚህ ይኼንን ነገር እንዴት እናደርጋለን? ወይስ እንዴት ሊፈፀም ይችላል? ቤተክርስቲያን እንዴት ትላለች? የሚል ነው ሓሳቡ ማለት ነው፡፡
ሁላችንም ማሰብ ያለብን ከመጀመሪያው በጥምቀት የክርስትና ልጅነትን ካገኘንበት ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ሰው በቅዱስ ቁርባን ተወስኖ እንዲቀጥል ሥርዓቱና ቀኖናው ያዛል የሚለውን ዋና የቤተክርስቲያን አስተምህሮ በተደጋጋሚ ተነጋግረናል፡፡ እንደገና ደግሞ በቅዱስ ቁርባን ተወስኖ እንዲቀጥል ሥርዓቱና ቀኖናው ያዛል፡፡ የሚለውን ዋና የቤተክርስቲያን አስተምህሮ በተደጋጋሚ ተነጋግረናል፡፡ እንደገና ደግሞ በቅዱስ ቁርባን ተወስነው ንፅህናቸውን፣ ድንግልናቸውን ጠብቀው የመጡ ሴትም ይሁን ወንድ ሥርዓተ ጋብቻቸውን በተክሊል ለማድረግ የወደዱ፤ በተቻለ መጠን የሚያጯቸው የትዳር አጋሮች በዚህ ዓላማ ሊስማሙ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ሰውን መርጦ ሰውን ፈልጎ ማግኘት በተለይ በዚህ ዘመን ከባድ ነውና፤ ይህንን እንኳን እንደቀላል እንደዋዛ አይተን በሰው ላይ የማይቻለውን ሸክም ለማሸከም ወደን ሳይሆን ከኃይማኖትና፣ ከክርስትና፣ ከመንፈሣዊ ሕይወት የሚበልጥብን ነገር ባለመኖሩ፤ እኛ ራሣችን፣ ንፅሐ ጠባያችን ወይም ድንግልናችን ጠብቀን፣ በቅዱስ ቁርባን ተወስነን ከመጣን፤ እስካሁን ለትዳር የመረጥነው ሰው በብዙ ጥናት ውስጥ፣ ይቺ ለእኔ ትሆነኛለች፤ ይኼ ለእኔ ይሆነኛል ካልን ምርጫችንን ካስተካከልን፤ በሌላው ነገር የወደድናት፤ የወደድነው ሰው ለኑሮ ሊስማማን የሚችል በራሣችን ጥናት የጨረስነውን ከሆነ በዚህ በመንፈሣዊ ሕይወት እኛን እንዲመስል ደግሞ ድርሻውን ለቤተክርስቲያን አባቶቻችን እንሰጣለን፡፡ ምከሩልኝ፤ ዝከሩልኝ ብሎ የማሳመን ሥራ ነው፡፡
በእርግጥ በአንድ ጊዜ ሊሆን አይችልም፡፡ አንድን በጣም የደረቀን ጠማማ ነገር ለማቃናት ሌላ ጥበብ ሳንጠቀም ዝም ብለን በአንድ ጊዜ በጉልበት ልናርቀው ብንሞክር ይሰበራል፡፡ በብዙ ጥበቃ ለትዳር ፈልገን ያገኘነውን ሰውም በአንድ ጊዜ ብትፈልግ ይኼንን ተቀበል፣ ባትፈልግ ተወው ብንለው፤ ነገሮቻችን ሁሉ ይበለሻሻሉ፡፡ እንደገና ሌላ ደግሞ የሕይወት መዘዝን ወይም ደግሞ ፈተና ሊመጣብን ስለሚችል በሌላው ነገር ከተስማማን በዚህ በኩል ያለውን ክፍተት ደግሞ በጥበብ ለማሳመን ሙከራ ይደረጋል፡፡ ትምህርት፣ እግዚአሔርም በዚህ መካከል ስላለ ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው እኔ እንኳን ድንግልናዬን አጥቻለሁ ከተባለ ደግሞ በሱ ዙሪያ፤ ድንግልና ትልቅ ክብር ያለው ነገር ነውና ይኼ በቤተክርስቲያን የሚፈፀመው የተክሊል ጋብቻ ለድንግልና የሚሰጥ ዋጋ ነው ብለናል፡፡
ስለዚህ ድንግልና ያለው ሰው ለእርሱ የተለየ ፀሎት ደርሶለት ነው ሥርዓተ ተክሊሉ በእራሱ ላይ የምንደፋለት የድንግልና ክብር የሆነ አክሊል አለ፣ መጎናፀፊያው፣ካባው አለ፣ ቅዱስ ቅባቱ አለ፣ የቃልኪዳን ቀለበት አለ ትልቁ ነገር ሁሉ የሚለያቸው ሥርዓተ ተክሊሉን ስናደርስ የምናደርሳቸው ፀሎት ማለት ነው የጋብቻው ፀሎት ማለት ነው፤ ሥርዓተ ተክሊል የሚባለው፡፡ ፀሎቱ ራሱ ለተክሊል የሚሰጠውን ክብርና ዋጋ እሱ ራሱ ይናገራል፡፡
እንግዲህ ሁለተኛው ወገን ደግሞ በእግዚአብሔር ፊት የሚዋሽ ነገር የለም፡፡ እንደሰው ብናታለልለው፣ ብንቀጥፈው፣ ብንዋሸው ሊያምንልን የሚችል የሰው ልጅ ነው፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ እውቀቱ ውሱን ስለሆነ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን መዋሸት አንችልም፡፡ ልብን፤ ኩላሊትን የሚመረምረውን አምላክ አንዋሸውምና፤ በንስሐ አባታችን አማካኝነት እያንዳንዳችን ወደ ቅዱስ ቁርባን፣ ወደ ሥርዓተ ጋብቻ ስንመጣ እኔ እንኳን ድንግልና የለኝም፣ በዚህ ምክንያት ድንግልናዬን አጥቻለሁ፣ የድንግልናዬ ክብር አጥቻለሁ ብሎ ከተናገረ፣ በቅዱስ ቁርባን ‹‹ አስባን ፀሎት›› የሚባል አለ፡፡ ከዚህ በፊት ይህንን የጋብቻ ሥርዓት አስመልቶ በሰጠነው ትምህርትም በጣም ደጋግመን ገልፀነዋል፡፡ ዞሮ፤ ዞሮ ትምህርት እስከሆነ ድረስ አንሰለችም፡፡ እናተም መሰልቸት የለባችሁም፣ እና ለሴቶች ለወንዱ ክብረ ድንግልናውን ላልጠበቀ ሰው የአስባን ፀሎት ተደርሶ፤ ለእሱ የተዘጋጀ ራሱን የቻለ ለእሱም የተዘጋጀ መፅሐፍት እንዲህ አድርገን እናደርጋለን፡፡
(ይቀጥላል) 👇
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
ስለ ቅዱስ ቁርባን ሥርዓት በትዳር - (ባል እና ሚስት ማወቅ ያለባቸው)
👉🏾 ለ #ቅዱስ #ቁርባን ስለሚደረግ #ጥንቃቄ
👉ጥያቄ:- ጤና ይስጥልኝ አባታችን እንዴት ነዎት? ስለ ምስጢረ ቁርባን ጥያቄዎች ነበሩኝ:- ገላ መታጠብ ያለብን ከመቀበላችን ስንት ሰዓት በፊት ነው? ፊትንና እጅንስ ወዲያው ታጥቦ፣ አፍንስ ተጎማምጦ መግባት ይቻላል? ሰሞኑን ሲለበስ የቆየ ልብስን ለብሶ ገላን ሳይታጠቡ መቀበል ይቻላል? ባልና ሚስት ቅድመና ድህረ ተራክቦ ለስንት ሰዓት መታቀብ አለባቸው? ማለት የተለያዩ አባቶችን ስጠይቅ የተለያየ መልስ ሆኖብኝ ነው፣ የሆነ ያነበብኩት መጽሐፍ ላይ ያገኘሁት ከመቀበል በፊት 3 ቀን ከተቀበሉ በኋላ 2 ቀን ይላል፣ 2 ቀን ማለት 24 ሰዓት፤ 3 ቀን ማለትስ 36 ሰዓት ማለት ነው?
✍መልስ፦ ስለ ቅዱስ ቁርባን በተመለከተ በዚህ ዙሪያ በድምፅም፣ በጽሑፍም ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል በፊት፣ በመቀበል ጊዜና፣ ከተቀበልን በኋላ መደረግ ስላለባቸው ዝግጅቶች በሚል በተደጋጋሚ ጊዜ ሰፋ ባለ መልኩ አስተላልፈናል፣ ገላችንን መታጠብ ስንል መላ አካላችን ማለት ከሆነ ቅዱስ ቁርባን ከመቀበላችን በፊት የሚደረግ ዝግጅት ሲሆን፣ ከሆነ ከአሥራ ስምንት ሰዓት (18) ሰዓት በፊት ነው፣ ይኼ ሊሰመርበት የሚገባ ነው፣ አፋችንን ግን ወዲያውኑ መጉመጥመጥም አይቻልም ምክንያቱም ስንጉመጠሞጥ ሆዳችን ውስጥ ውኃ ሊገባ ይችላል፣ ፊታችንን ሆነ መላ ሰውነታችን ከአስራ ስምንት ሰዓት በፊት ስለታጠብን ለጊዜው ወይም ለእለቱ እጅና እግርን ልንታጠብና ልናስቀድስ እንችላለን፣ ምክንያቱም ቀዳሹም፣ አባቶቻችን ካህናት፣ ዲያቆናት እጃቸውንና እግሮቻቸውን ታጥበው ነው በጊዜው የሚቀድሱት ማለት ነው፡፡
ሌላኛው ሰሞኑን የለበሱት ልብስን በተመለከተ ለጠየቁት ይኼ ምን ማለት ነው? ሰሞኑን የለበስነውን ልብስ የማናጥበው ማጠቢያ ውኃ አጥተን ነው? ማጠቡ ከብዶን ነው? ምናልባት ትናንትና የለበስነው ልብስ ያልቆሸሸ እንደሆነ ችግር የለውም፣ ለብሰነው እንገባለን፣ ነገር ግን ብዙ ጊዜ በተደጋጋሚ የተለበሰ ልብስ ከሆነ አይቻልም፣ አይሆንም፡፡
ልብሳችንን ማጠብ ግዴታ ነው፣ “ውስጥህም ውጪህም ይንፃ” ተሎ ተነግሯል፣ ይህ ማለት ውስጣችንን በንስሐ እናጥባለን፣ እናነፃለን፣ ውጪያችንን ወይም ገላችንን፣ ልብሳችንን ደግሞ በውኃና በሳሙና አጥበንና ታጥበን ሊሆን ይገባል ምክንያቱም ንጹሐ ባህርይ ኢየሱስ ክርስቶስን ልንቀበል ስለሆነ በምንችልው ሁሉ ነፅተን መቀበል ስላለብን ነው፡፡
ሌላው ባልና ሚስት የሚለው እርስዎም ዘርዝረውታል፣ ብዙ ሰዎች የተለያየ ሐሳብ ቢሰጥዎትም መጽሐፉ ላይ ያለው ወይም የተቀመጠው ግን ይኼ ነው፣ ከመቁረብ በፊት ሦስት (3) ቀን፣ ከቆረቡ በኋላ ደግሞ ሁለት (2) ቀን መሆን አለበት፣ ይህ ወደ ሰዓት ሁለት ቀን ማለት ሃያ አራት (24) ሰዓት አይደለም፣ ወደ ሰዓት ሲቀየር ሃይ አራት(24) ሰዓት ማለት ራሱ አንድ ቀን ነው፣ ቀን የሚባለው ለሊቱም መዓልቱም ነው፣ መዓልትና ለሊት አንድ ቀን ይባላል ፣ይህ ማለት መዓልቱ አሥራ ሁለት (12) ሰዓት፣ ለሊቱ አሥራ ሁለት (12) ሰዓት ሲደመር አንድ ቀን ይባላል፡፡
ስለዚህ ሁለት ቀን ማለት ሃያ አራት ሰዓትና፣ ሃያ አራት ሰዓት ሲደመር አርባ ስምንት (24 + 24 = 48 ) ሰዓት ይሆናል ማለት ነው፣ ሦስት ቀን ለማግኘት ሦስት ጊዜ ሃያ አራትን መደመር ነው 24 + 24+ 24 = 72 ወደ ሰዓት ስንቀይረው ሰባ ሁለት ሰዓት (72) ይሆናል ማለት ነው፣ ይኼ ማለት ከመቀበላችን በፊት ሦስት ቀን (72 ሰዓት) እንጠበቃለን ፣ ከተቀበልን በኋላ ሁለት ቀን (48 ሰዓት) የሚለውን እናገኛለን ማለት ነው፡፡
ከዚህ በፊትም በዚሁ በዮሐንስ ንስሐ ድህረገጽ ላይ በምስጢረ ቁርባን ዙሪያ የተላለፈ ትምህርትም ስላለ እሱንም ማየት ይጠበቅብናል ማለት ነው፣ እንደ ሁልጊዜውም ይህንን ትምህርት ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ አስተላለፉ ወይም ሼር አድርጉ፡፡
የመከረን የገሰፀን የአባቶቻችን አምላክ ልዑለ ባሕርይ እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን፣ አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን።
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር አድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፡- በ #ዐብይ #ጾም ጊዜ ከግብረ ሥጋ ግንኙነት ያልራቀ ባለትዳር #ቅዱስ #ቁርባን መቀበል ይችላል?
✍መልስ፡- ጠያቂያችን ፤ ጾም ቀኖናዊ ነው፣ አዋጅ ነው፣ በጾም ጊዜ ስለ ጾም ጥቅም የሚያውቁ፣ የቀኖናውን ጾም የሚጾሙ ክርስቲያኖች ከምን፣ ከምን መራቅ እንዳለባቸው፣ ወደ ጾሙ ከመግባታችው አስቀድመው፣ ለጾም ተዘጋጅቶ መጠበቅ ስላለበት፣ በዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚጾሙትን ጾም፤ የተከለከለውን አድርገው፣ በዚያ ላይ ደግሞ፣ በጾም ጊዜ ፈቃደ ሥጋ አሸንፎ የተከለከለውን ነገር በመፈፀም ጥፋት ከመሠራቱም በላይ እንደገና ደግሞ በዚሁ ቅዱስ ሥጋውን ፣ክቡር ደሙን እንቀበል ማለቱ አግባብነት የለውም፡፡
ሁላችንም በጾም ጊዜ ተጠንቅቆ ከእንዲህ ዓይነት ግድፈት፣ ከእንዲህ ዓይነት መፈተን ነፃ የሚሆን አለ ወይ? ብሎ ደፍሮ ለመናገር ከባድ ያደርገዋል፡፡ ሁሉም ሰው፣ ሰው ነው ሥጋ ለብሷል፣ ሌላው ሰው የሚፈተንበት፣ ሌላው ሰው የሚሳሳትበት፣ ሌላው ሰው የሚፈተንበትን ነገር ማነንም ሰው ይፈተንበታል፡፡
ነገር ግን ይሔንን ስንል በአዋጅ ጾም ጊዜ ባልና ሚስት ቢራራቁ መልካም ነው፣ ሕጋውያን ናቸው፤ የጾም ጊዜ የቅድስና ጊዜ ነው፣ እንደተባለውም ቅዱስ ቁርባን መቀበያው ጊዜ፣ በቀኖናውጊዜ፣ በሱባኤው ጊዜ፣ በጣም ደስ አይልም? ሰውነታችን ከብዙ ነገር ተጠብቋልና የሚሰማን ነገር ሁሉ ደስታ ነው፤ ቅድስና ነው፤ በዚህ ጊዜ መቁረባችን በጣም፣ በእጅጉ ያስፈልገን ነበር፡፡
ደግሞ እንግዲህ ይህንን አልቻል ብሎ፤ በዚያ በጾሙ ጊዜ አንድ ቀን ቢሆን ብንሳሳት፤ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል አያስችለንም በእውነቱ፡፡ ለምንድን ከእግዚአብሔር ጋር እንጣላለን? ስለዚህ ይሔንን ለአባቶቻችን በማማከር፣ ሁለተኛ እንዳይደግም የአንድ ቀን ስህተት ከሆነ፣ ወይም ሌላ ስሜታዊ ሊያደርገን የሚችልተጨማሪ ጥፋት አጥፍተን ሊሆን ይችላል፣ መጠጥ ወይም ሌላ ነገር ከሆነ እሱም ራሱን የቻለ ኃጢያቱን ከፍተኛ ያደርገዋል፡፡
በዚህ ስሜት ተገፋፍቼ ማለት ደግሞ ከባድ ነው፣ ሥጋዊ ፍትወት አሸነፈኝ ማለትና፣ በወቅቱ በዚህ በዚህ ስሜት ተገፋፍቼ ነው፣አንድ ሰው የሆነ ነገር አይቼ ነው፣ ወይም ጠጥቼ ነው፣ ለስሜት የመሚገፋ ነገር ሁሉ ምክንያቱ ይሄ ነው ከተባለ፣ ኃጢያቱን ምን ያደርገዋል ማለት ነው? ሌላ ደባልና፣ ተጨማሪ ነገር ያደርገዋል ማለት ነው፣ ስለዚህ ወደ አባት ቀርበው ያማክሩ፡፡
በተለይ በዚህ በዐቢይ ጾም ብዙ ጥቅም የምናገኝበት፣ ከእኛ ሕይወት አልፎ ለአገር፣ ለወገን፣ ለሕዝብ የሚጠቅም የሱባኤ ጊዜ፣ ከእኛም የሚጠበቅ ብዙ ነገር ባለበት ሰዓት፣ እንደዚህ ዓይነት መሰናክል ገጥሞን የአንድ ቀን እንቅፋት፣ የቅፅፈታዊ ሰዓት፣ ፈተና ከሆነ ደግሞ ወደ አባት ቀርቦ ማመከር ነው፡፡
አባቶች በብዙ ነገር ስልጣን አላቸው፣ የተዘጋውን በር ሁሉ ይከፍታሉ፣ አንድ የንስሓ አባት በትክክለኛ መንገድ ይሁን፣ ወይም ደግሞ ሳያስተውሉ በስህተት ይሁን፣ የሚወሰደዱትን ኃላፊነት ሁላችንም ሊያገባን አይችልም፡፡ስለዚህ ወደ አባት ቀርቦ መነጋገር አለዚያም ደግሞ ጠያቂያችን እኛንም ቢሆን በተለመደው የውስጥ አድራሻችን ሊያነጋግሩን ይችላሉ፣ እውነታው ግን ይሄን ይመስላል፡፡
ብዙ ጊዜ እኛ የምናደላው የምናሰምርበትም ዋናው መንገዳችን፣ እውነቱንና እውነቱን መነጋገራችን ነው፤ ሰውን ሁሉ ከስህተት እንድንጠብቅ፣ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ብዙ ኃጢያተኞች፣ ብዙ በደለኞች፣ ብዙ ደፋሮች የመኖራቸውን ያህል፤ በድፍረትም ያደረጉትን ሁሉ፤ በእግዚአብሔር ፊት ሳይቀር የሚያደርጉትን ነውር አብዝተን ስላወቅን፣ ስለዚህ ይሄን ያህል በቁጥር የበዙ ኃጢያተኞች ባሉበት አገር የአንተ ኃጢያት ከእነሱ የተሻለ ነው ብለን፤ ያልተፈቀደውን ነገር ሰው እንዲያደርግ አንመክርም፡፡
ለበረከት፣ ለፅድቅ፣ መልካሙን ነገር ለመምረጥ ብሎ ቀርቦ የሚያማክረን ወገናችንን፤ ምንመ ማለት አይደለም ብለን ጥፋት አናበረታታም፡፡ በአንጻሩም ደግሞ ነገሮችን በጣም አክብደንና፣ ሥጋት፣ ፍርሐት እየጨመርን ደግሞ ከእግዚአብሔር ፊት ሰው እንዲርቅም ደግሞ አንገፋፋም፡፡ ስለዚህ ነገሮችን ሁሉ በማቃናትና፣ በማስማማት፣ በማስታረቅ ከሁሉ ወደሚበልጥብን፣ ከሁሉ ወደሚቀድምብን ወደ አግዚአብሔር እና ወደ ቸርነቱ፣ ወደ ምሕረቱ እንድንቀርብ ሁሉ ዘወትር ምክራችን፣ ትምሕርታችን ነው፡፡
በነገር ሁሉ የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፦ ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ
1ኛ/ #ባለትዳሮች ይህ ማለትም ባልና ሚስት #ቅዱስ #ቁርባን በሚቀበሉበት ጊዜ ከመቀበላቸው በፊት ለሶስት ቀንና ከተቀበሉ በኃላ ደግሞ ለሁለት ቀን ከሩካቤ ስጋ መከልከል አለባቸው ይባላል።ሶስትና ሁለት ቀኖች የሆነበት ምከንያት ግልፅ ቢደረግልኝ?
2ኛ/ #አባቶች #የሚይዙት #ጭራ ከፈረሰ ፀጉር የተሰራ በቤተክርስቲያን አስተምህሮ እንዴ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ትርጉም ካለው ቢብራራልን?
ቀለሙስ ጥቁርና ነጨሸ ትርጉም ካለው ወይስ ጥቁሩም ነጨም ትርጉሙም አንድ ነዉ?
መልስ 1፦ (ከባለፈው የቀጠለ ምላሽ)፥ ጠያቂያችን የ ሁለት ቀን የምንቆይበት ምክንያት ወዲያውኑ ወደእንደዚህ አይነት ህይወት አንገባም የበለጠ ደስታ የበለጠ ህይወት በውስጣችን ስላለ ያንን ለማክበር ነው። ዘካርያስ እንኳን ደስ አለህ ጸሎትህ ተሰምቶልሀል ኤልሳቤጥም ትጸንሳለች ሲባል ወዲያውኑ ሄዶ አይደለም ከሚስቱ ከኤልሳቤጥ ጋራ ሩካቤ ስጋ ያደረገው ፤ ጊዜውን ከጨረሰ በኋላ እንደውም ትርጓሜው ይህም በጥቅሉ 5 ቀን የሚል የተለየ ምስጢር እንደሌለው ተገንዝበው በዋናነት ስለ ሰጋችን ንጽህና እና ስለ ቅዱስ ስጋውና ለክቡር ደሙ የምንሰጠው ክቡር መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባል። እግዚአብሔር ንጽሐ ባህሪይ ነው ነፍሳችን ብቻ ሳይሆን ስጋችንም ንጹህ ሊሆን ስለሚገባ ከዚህ አንፃር ነው ሥጋወ ደሙን ከመቀበላችን ለ3 ቀን ከተቀበልን በኋላ ለ2 ቀን የምንታቀበው።
መልስ 2 ፥ ጠያቂያችን ለዚህ የምንሰጥዎት አጭር ምላሽ አባቶች የሚይዙት ጭራም ሆነ የጭራው ቀለም ነጭና ጥቁር የመሆን ሁኔታ በአጠቃላይ ምንም የተለየ ትርጉም የለውም። በአብነት ትምህርት ቤት የአብነት መምህራን ጉባኤ አስፍተው ደቀመዛሙርት አብዝተው በሚያገለግሉበት ሰአት እንደ ዝንብ ያሉ ተዋህሲያን በላያቸው ላይ እንዳያርፉ መከላከያ ከመሆን ያለፈ ጌጥም አይደለም፣ ሃይማኖትምጋ የተያያዘ አይደለም። አንዳንድ አባቶች ከዚያ ይዘውት የመጡት ልምድ ስለሆነ እንዲሁ ይይዙት ይሆናል። ከዚህ ውጪ ግን አጠጋግተን ትርጉም እንስጠው ካልን ልንሰጠው የምንችል ካልሆነ በስተቀር ሃይማኖታዊ አስተምሮ ጋር የተያያዘ ትርጉም እንደሌለው ይረዱት ዘንድ ይህን አጭር መልእክት ልከንልዎታል።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉ጥያቄ፦ #ቅዱስ #ቁርባን ተቀብለው በ #ትዳር የተጣመሩና ወደ አራት ልጆች ያፈሩ ጥንዶች ከዚህ በፊት አብረው ስጋወደሙን ይቀበሉ ነበር አሁን ግን ካለየስራ ውጥረት የተነሳ ተነጣጥለው ስጋወ ደሙን ቢቀበሉ ችግር አለው ወይ ?
መልስ፦ ከላይ አንድ አባላችን ያቀረቡትን የጥያቄ ሃሳብ መሰረት በማድረግ ለሌሎች አባላትም ግንዛቤ እንዲሆን በማሰብ ምላሹን ሰፋ በማድረግ እንደሚከተለው የላክን ስለሆነ ሁላችሁም አንብባችሁ ትረዱት ዘንድ አደራ እንላለን ፦
ጠያቂያችን ፤ መጀመሪያ ከባለቤትዎ ጋር አብራችሁ ቆርባችሁ ከመጀመሪያው ቁርባን በኋላ ያለውን የቁርባን ጊዜ ግን ከባለቤትዎ ጋር ለመቁረብ አስበው ነገር ግን እንዳሉትም ለመቁረብ እንዳልቻሉ ለዚህም ምክንያቱ የስራ ብዛት እንጂ ከሌላ ጉዳይ ካልሆነ ማለትም ለእርስዎ እንደምክንያት የሆነብዎት የባለቤትዎ የስራ ብዛት ወይም የጊዜ ችግር ከሆነ ሁላችሁም በተመቻችሁና በተዘጋጃችሁ ጊዜ ሄዳችሁ መቁረብ ትችላላችሁ ። ምክንያቱም አንድ ሰው ከሚስቱ ጋር ወይም ከባሉ ጋር ከቆረበ በኋላ ከዚያ በየቀኑ ለቁርባን ከሚስት ጋር ወይም ከባል ጋር ሳይለያዩ የግድ መሄድ እንዳለባቸው አይጠየቅም። ነገሮች ከተመቻቹላቸው ግን ሁላቸውም በጋራ አቅደው ጊዜያቸውን በማመቻቸት አብረው መሄድ ይችላሉ። ካልተመቻቸው ግን በግላቸውም ቢሆን መቁረብ ይቻላል። እንግዲህ በቅዱስ ቁርባን ሁላቸውም ለመወሰናቸውና ከዚህ ሌላ የተለየ ህይወት እንደሌላቸው ቅዱስ ቁርባንን ሊያረክስ የሚችል የቆራቢዎቹን ከብር ሊያረክስ የሚችል በቤተክርስቲያን እና በአባታቸው ፊት በእግዚአብሔር ጉባኤ አረጋግጠዋል ፤ ከዚህ በኋላ ሁሉም የነፍስ ምግባቸውን ቅዱስ ቁርባን ስለሆነ ምስጢራትን ለመፈፀም በየጊዜው ሲመቻቸው እየሄዱ መቀበል ይችላሉ። ምክንያቱም ሁሉም በዚህ ምስጢረ ቁርባን አምነው አላማውን አንዴ በቋሚነት እያስኬዱ ስለሆነ ማለት ነው።
ነገር ግን የመጀመሪያ ስርአተ ቁርባንን ለመፈፀም ወይም ለመጀመሪያ ቅዱስ ቁርባንን በጋራ ለመቀበል አስባችሁ ከሆነ ባል ወይም ሚስት ያልተመቻቸው፤ ይሄ ግን በግል ለብቻ በመሆን መቀበል አይሆንም። ለምሳሌ በስራ ምክንያትም ይሁን ወይም ባለመፈለግም ይሁን ከባል እና ከሚስት አንዳቸው ለመቁረብ ፈልገው አምነው ሌላው ደግሞ ላለመቁረብ ምክንያት የሚሰጡ ከሆነ አንዱ ወገን ለብቻ አይቆርብም። ይሄን ምን ማድረግ እንዳለባቸው አንዱ ቅዱስ ቁርባንን እየፈለገ ሌላው ደግሞ አልቀበልም እያለ በማጓተት የስጋዊ ህይወትን በማስቀደም በነፍስ ዘላለማዊ ህይወት የምናገኝበትን የክርስቶስ ስጋውንና ደሙን ለመቀበል አንደኛው እየፈለገ አንደኛው የሚከላከል ከሆነ የቤተክርስቲያን አባቶች ይሄንን በቀኖና ሊፈቱት ይችላሉ። እንጂ ዝም ብሎ በፍርደገምድልነት ሁለታችሁም ካልቆረባችሁ መቁረብ አትችሉም በሚል ቃል ወይም ደግሞ በድፍረት ብቻሽን ወይም ብቻህን መቀበል ይቻላል በሚል አነጋገር የሚመለስ መልስ የለም። በቤተክርስቲያን ጉባኤ በቤተክርስቲያን ሊቃውንት ወይም አባቶች፣ በማህበረ ካህናት ቢያንስ ከሁለት በላይ የሆኑ አባቶች መክረው ዘክረው እስከመጨረሻ ድረስ እንዲሄዱ ከተደረገ ከዚያ ስርአተ ቤተክርስቲያንም የሚያዘው ነገር አለ።
ስለዚህ በአንደኛው መከላከል ያውም ደግሞ በመንፈሳዊ ህይወት አንዱ አምኖ ሌላው አላምንም በሚል በነፍስ ራሱንም ጎድቶ ሌላውንም እንዲጎዳ ይሄኛው ደግሞ ባልተባበረበት ኀጢአት የጽድቅ ስራ እንስራ እንጽደቅ እያለ፤ አንደኛው ደግሞ ለሃላፊው ለጠፊው ለማይጠቅመው ነገር ለማይከርምበት ለረጅም ጊዜ ለማይቆይበት ህይወት እየተስገበገበ የራሱን ድብቅ ኀጢአት እያስኬደ አልቆርብም ወደዚህ አልቀርብም ማን ይነካኛል ማን ያስገድደኛል ብሎ እንደመብት በመቁጠር በማከላከል ሌላውን ይዞ ሊጠፋ የሚችል ዕድል አይኖርም፥ ጊዜም አይሰጥም። እንዲያውም ይሄ ትዳርንም ኑሮንም ህይወትንም ሊበጠብጥ የሚችል ነገር አይደለም። ምናልባት ሚስት ከሆነች ወደቅዱስ ቁርባን ያደላችው ወይም ባል ከሆነ አረ እባካችሁ ሁላችንም እንድንድን አባቶቼ ባለቤቴን ምከሩልኝ ይባላል። መቼስ አንድ ሰው በሆነ ምክንያት በሆነ ብስጭት ራሱን አሳልፎ ለሚጠፋበት ጉዳይ ላውል ቢል በአካባቢው ያሉ ዘመድ አዝማድ ሽማግሌም አባቶችም ይሄን ሰው ገላግላችሁ ወይም ሸምግላችሁ ወይም መክራችሁ አድኑልኝ እንደሚባለው ሁሉ አልቆርብም የሚልም ሰው ምክር ያስፈልገዋል፤ ስለሱ መፀለይ ያስፈልጋል፣ ትምህርት ያስፈልጋል፣ በየቀኑ ሳይሰለቹ ሳይሳቀቁ ይሄ ሰው ወደዚህ የተቀደሰ አላማ እንዲመጣ የሚያስፈልገውን በቂ ምክርና ትምህርት መስጠት ይገባል። ያኔ የሚያጨንቀውና የሚያከላክለው መንፈስ ከሱ ለቆ ሲሄድ እሱም ከእንቅልፉ እንደባነነ ሰው ወደልቡ ይመለሳል ማለት ነው።
ስለዚህ፦ ገና አዲስ ልትቆርቡ ከሆነ ወደ ቤተክርስቲያን አባቶች ቀርበው መነጋገር ነው፤ አይ መጀመሪያ ላንለያይ ቆርበን ከዚያ በኋላ የባለቤቴ የጊዜ ማጣት ነው ለማለት ከሆነ ይሄ ምንም ማለት አይደለም ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቅና እኛን ኀጢአተኛ የሚያደርገን ስራ እንዳንሰራ መጠንቀቅ እንጂ በግልዎት ቢቆርቡም ይችላሉና ከዚህ አንጻር ይረዱት።
በተጨማሪም ንስሐን በሚመለከት፦ባልና ሚስት አንድ አካል አንድ አምሳል ናቸው ፤ ምናልባት አንድ ላይ እየኖሩ ከሁለት አንዳቸው በኀጢአት ቢወድቁ ንስሓ በሁለት አይነት መንገድ ሊገቡ ይቸላሉ። አንደኛው አብረው የንስሐ ህይወት የሚቀበሉበት አካሄድ ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ በየግላቸው በሚስጢር ወደ ንስሐ አባታቸው ቀርበው ንስሐ የሚገቡበት መንገድ ነው። ምክንያቱም ይሄን በደሌን ብንገልፀው ወይም ደግሞ ለባለቤቴ ባሳውቃት (ለባለቤቴ ባሳውቀው) ወይም ብታውቅብኝ/ቢያውቅብኝ ኑሯችን ህይወታችን ትዳራችን ይበላሻል ፣ ቤተሰብ ብትንትኑ ይወጣል ብሎ ከማሰብ ፤ ከዚያም በላይ የሆነ አደጋ ሊመጣ ይችላል ብሎ ከማሰብ አንፃር በግል ንስሐ መግባት ይቻላል።
ስለዚህ ሁላችሁም ስርአቱን በዚህ እንድትገነዘቡትና እንዲሁም ባልና ሚስት ለመቁረብ የሚችሉት የራሳቸውን ቅድመ ዝግጅት አድርገው ማለትም መንፈሳዊ ጥንቃቄን አስቀድመው በማድረግ ሲሆን ፥ ይህ ማለት ወደንስሐ አባታቸው በማማከር ከምን ከምን መቆጠብ እንዳለባቸው ለንስሐ የሚያበቃቸው የሰሩት ጥፋት ካለም የንስሐ ቀኖና ተቀብለው፣ ያለዚያም ደግሞ በሱባኤ ንስሐ የሚገቡበት ጥፋት ከሌላቸውም ስለ ቅዱስ ቁርባን ወይም ስለሚስጥረ ቁርባን ከአባታቸው ወይም ከንስሐ አባታቸው ሰፋ ያለ ትምህርትና ምክርን መቀበል አለባቸው። ቅዱስ ቁርባን ከመቀበላቸው በፊት፣ በሚቀበሉበትም ጊዜ እና ከተቀበሉ በኋላም ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባቸውን ዝግጅት መገንዘብ ስለሚገባ ይህንንም ከንስሐ አባት መረዳት ወይም በዚሁ ድረገጽ ያስተላለፍነው ትምህርት ስላለ ወደኋላ መለስ በማለት ለተጨማሪ ግንዛቤ እንድትመለከቱት እንመክራለን።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ
👉🏾👉🏾👉🏾 ባልና ሚስት ተነጣጥለው ቢቆርቡስ?
ያላገባ ወጣት መቁረብ ይችላል ወይ?
#ቅዱስ #ቁርባን #ዕድሜ #ትዳር
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን በሙሉ፤ በርዕሱ የተጠቀሰውን የትምህርት ክፍል ከ “ ለቅዱስ ቁርባን እንድበቃ ምን ላድርግ?” ከሚለው መጽሐፍ ወስጥ ያገኘነው ሲሆን ይህም ጠቃሚ ትምህርትና ምክር ስለሆነ እንደሚከተለው ልከንላችኋልና አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።
1. ባልና ሚስት ተነጣጥለው ቢቆርቡስ?
«ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ወደዚህ ነይ» /ዮሐ. 4-1//
ይህንን የጌታችንን ቃል አስተውላችሁት ታውቃላችሁ? ወሃ ለመቅዳት የመጣችው ሳምራዊቷ ሴት «ጌታ ሆይ እንዳልጠማ ውኃም ልቀዳ ወደዚህ እንዳልመጣ ይህን ውሃ ስጠኝ» ባለችው ጊዜ «ሂጂና ባልሽን ጠርተሽ ነይ» ብሎ መለሰላት። በዚሀ ቃል መሠረትነት ነው ቤተ ክርስቲያን ባልና ሚስት ተነጣጥለው መቁረብ የለባቸውም የምትለው:::
ለዚህ ጥያቄ በቂ መልስ ለማግኘት ለአንባብያን ተጨባጭ ማስረጃ ለማቅረብ በጋብቻ ዙሪያ የእግዚአብሔር ቃል ምን እንደሚል መመልከት አስፈላጊ ሆኖ አግንቼዋለሁ፡፡
<«..ፈጣሪ በመጆመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው አለም ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው» /ማቴ. 19፥4-6/
በዚህ አምላካዊ ቃል መሰረት ባልና ሚስት አንድ ሥጋ ናቸው: ጋብቻ ከልዑል እግዚአብሔር ዘንድ ለሰው ልጆች ከተሰጡ ታላላቅ ስጦታዎችና በረከቶች አንዱና የመጆመሪያው ነው::
ገና መጀመሪያ አግዚአብሔር አምላክ ከምድር አፈር አዳምን አበጅቶ በአፍንጫው የሕይወትን እስትንፋስ እፍ ብሎ ህያው ካደረገው በኋላ ስለ አዳም አስቦ ያለው እንዲህ ነበር ፦
«አዳም /ሰው/ ብቻውን ይኖር ዘንድ መልካም አይደለም የምትረዳውን እንፍጠርለት> /ዘፍ. 2፥18/ በዚህ መሰረት ከአዳም አጥንት ነስቶ ሔዋንን ፈጠረለት አዳምም ከአካሉ የተፈጠረችውን ሴት ተመልክቶ እንዲህ አለ፣
«ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል> /ዘፍ. 2፥23-25/
ደግሞም ጋብቻ በረከት ሆኖ ለሰው ልጆች እንደተሰጠ እንዲህ ተፅፏል «እግዚአብሔር እምላክ ሰውን በመልኩ ፈጠረ ወንድና ሴት አድርጐ ፈጠራቸው:: ከዚያም እንዲህ ብሎ ባረካቸው «<ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት ግዙአትም የባሕርን ዓሶችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዟቸው /ዘፍ. 1፥+26-31/
መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክረስቶስ ከድንግል ማርያም ተወልዶ በዚህች ዓለም ወንጌለ መንግስቱን በሚሰብክበት ጊዜ ጋብቻ እጅግ የተቀደሰ ባልና ሟስትም አንድ ሥጋ መሆናቸውን አስተምራል እንዲህ ብሎ፣
«እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው /ማቴ. 19 ፥6/
አምላካዊ ቃሉ እንዲህ እያለ አንድ ሥጋ በሆኑ ባልና ሚስት መካከል ተነጣጠሎ መቁረብ ለምን ታስቦ? ለመቁረብ እንቢ በሚለው ሰው ውስጥ ያለው ምክንያት ምንድን ነውን? የሚሉትንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች እንድናነሳ ያደርገናል በቅድሚያ አልቆርብም ባዩ ሰው በኃጢአት የመኖር አቅድ እንዳለውና የሚያስጠይቀውም መሆኑ ግልጽ ሲሆን በቃሉ መሠረት ግን ተነጣጥሎ መቁረብ ተገቢ አይደለም የቤተ ክርስቲያን ህግና ሥርዓትም አይፈቅደውም። ምክንያቱም አንዱ ሲቆርብ ሌላው ሲቀር አንድ ሥጋ ተለያየ ማለት ነው:: ሌላው በቅዱስ ቁርባን የአንዱ ሕይወት የተቀደሰ ፥ ከቅዱስ ቁርባን የራቀው የአንዱ ሕይወት ያልተቀደሰ በመሆኑ በግንኙነት ጊዜ የተቀደሰው ህይወት ይረክሳል። ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ ነገር እንዲህ አለ “ስጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች አንደሆነ አታውቁምን ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ ተብሎአልና» /1ቆሮ:. 6፥15-16/
ይሁንና ሁለቱም በመስማማት በመምህረ ንስሐቸው ምክር በመመራት አንዴ ከቆረቡ በኋላ /ቆራቢ ከሆኑ በኋላ/ ግን በተለያየ ምክንያት ለምሳሌ በሥራ ጉዳይ በመራራቅ፣ ሴቷ/ሚስቲቱ/ ስርዓተ አንስት ላይ በመሆን (በወር አበባ ጊዜ) ወልዳ በምትታረስበት ጊዜ ወንዱ (አንዱ) መቁረብ ቢፈልግ ቢቆርብ እንደመለያየት የሚቆጠር ኣይደለም ምክንያቱም ሁለቱም ቆራቢዎች ናቸው ይህ የመነጣጠል ጉዳይ ሳይሆን በቀን ልዩነት የመቀበል ሁኔታ ነው። ነገር ግን በተቀበሉ ቀን አብሮ መተኛት የተከለከለ ሲሆን ከዚያም በኋላ በልዩ ምክንያት ሳይቀበል የቀረው ሁኔታዎች ሲስተካከሉ ተዘጋጅቶ በመቀበል ሊቀጥሉ ይችላሉ። በተረፈ እንዲህ አይነት ምክንያቶች ካላጋጠሙ በስተቀር የመጀመሪያ ቀን በአንድነት በአንድ ቀን እንደተቀበሉ ሁል ጊዜ በአንድ ቀን መቀበላቸወሰ ለፈተና ከመጋለጥ ይጠብቃቸዋል። (1ቆሮ 7፥5)
2. ያላገባ ወጣት መቁረብ ይችላል?
ለዚህ ርዕስ በቂ ማብራሪያ ለአንባብያን ከማቅረቤ በፊት አንድ ነጥብ አስቀድሜ ልገልጽ እወዳለሁ፡፡
ይኹውም ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል በራሱ ያገባ ወይም ያላገባ ብሎ እንደ መስፈርት መውሰድ ትልቅ ስህተት መሆኑን፡:: መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተ ለሁሉ ነው ስለዚህ አምነው በተጠመቁና ለቅዱስ ቁርባን በተዘጋጁ መካከል «የማግባትና ያለማግባት»፣ «የዘርና የቀለም»፣ «የጾታና የዕድሜ»፣ ልዩነትን እንደመመዘኛ የሚወስድ ካለ ትልቅ ስህተት ውስጥ ገብቷል
«በአይሁዳዊና በግሪካዊ ሰው መካከል ልዩነት የለምና አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና» /ሮሜ. 10፥12/ በማለት ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን ክርስቲያኖች የጻፈላቸው ይህን ያረጋግጥልናል፡፡
በተረፈ የዚህ ርዕሳችን መሠረታዊ ነጥብ ግን ይህ ነው ማንኛይቱም ኦርቶዶክሳዊት ሴት ከልጅነቷ አንስቶ እስክታገባ ድረስ ካገባችም በኋላ ከሕግ ባሏ ጋር በአንድነት እስከ እለተ ሞቷ ድረስ ስትቀበል መኖር ይገባታል እንደዚሁ ወንዱ ከልጅነት እንስቶ የህግ ሚስቱን እስካገባበት ቀን ድረስ ካገባም በኋላ ከህግ ሚስቱ ጋር እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል ሲኖር ይገባዋል::
(ይቆየን)
ምንጭ “ለቅዱስ ቁርባን እንድበቃ ምን ላድርግ?”
ከ መ/ም የሺጥላ ሞገስ
2014
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንም ሼር ያድርጉ፡-https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾👉🏾👉🏾 #ቅዱስ #ቁርባን ከምንቀበል በፊትና በኋላ ማድረግ ስለሚገቡን ጥንቃቄዎች
👉ጥያቄ፦ ቆርበን ውሃ መንካት አይቻልም የተባለው ምክንያቱ ምንድን ነው? እና የቆረበ ሰው አይሳምም የሚባል ነገር አለ እና እነዚህን ቢያስተምሩን።
መልስ፦ ጠያቂያችን አንድ ኦርቶዶክስ ክርስቲየን ቅዱስ_ቁርባን ከመቀበሉ በፊትና ከተቀበለ በኋላ ምን ማድረግ አለበት የተባለውን ሃሳብ መሠረት በማድረግ ከአባላት ጥያቄ ቀርቦልን አፈጻጸሙንና ምክንያቱንም ጨምረን በተለያየ ጊዜ ለቀረቡ የተለያዩ ጥያቄዎች አብራርተን ምላሽ ለመስጠት መሞከራችንን እናስታውሳለን። ስለሆነም ያስተላለፍነውን መልዕክት በአጭሩ አጠቃለን ከዚህ እንደሚከተለው ልከንልዎታልና ምክንያቱን ከዚህ አንጻር እንዲረዱት ይረዱት።
በቅድሚያ መታወቅ ያለበት አንድ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን በተቀበለበት እለት በዋናነት ገላውን በውሀ መታጠብ የለበትም ፣ ልብሱን አውልቆ እርቃኑን መሆን የለበትም፣ ከሰውነቱ ደም ማውጣትን የለበትም ከሕግ ጋብቻ ጋር ቢሆንም የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ የለበትም ፣ በሰውነታችን ላይ ፈሳሽ ሊያስከትል የሚችል ከባድ ስራ መስራት የለበትም፣ እሩቅ መንገድ መሄድ የለበትም (እንደ ስራ ስለሚቆጠር) ፣ የሚያሰክር እና የበላነውን የጠጣነውን የሚያውክ መጠጥ መጠጣት የለበትም ፣ ጭቅጭቅ ያለበት አደባባይ ወይም የህዝብ ቦታ መሄድ የለበትም፣ ከሰው ጋር መጨቃጨቅ ሃይለ ቃል መነጋገር በአጠቃለይ ለፀብ የሚጋርድ ስራ እና እነዚህን የመሳሰሉ ሌሎችንም ከቁርባን በኋላ ማድረግ እንደሌለብን በቀኖና ቤተክርስቲያን ተደንግጎ ይገኛል።
ይህ ማለት ግን ጠየያቂያችን እንዳሉት ከቅዳሴ በኋላ ተሳስተን በእጃችን ውሀ ብንነካ ወይም ዝናብ ቢነካን ወይ እግራችንን ፈሳሽ ቢነካን ቁርባኑ ይከሽፋል ወይ እንደገና ቀኖና መቀበል ያስፈልገዋል ማለት አይደለም። ይሁን እንጂ ያ ስርዓት ሆን ብለን አስበን ጥፋት እንዳንሰራ እንጂ በሆነ አጋጣሚ ዘንግተነውም ይሁን ከአቅማችን በለይ በሆነ ጉዳይ ቢደረግ ሃይማኖትን እንዳጎደልን ወይም እግዚአብሔርን እንደካድን የሚያስቆጥርና መቅሰፍትን የሚያመጣ አይደለም። ምክንቱም አምልኮተ እግዚአብሔርን በስርዓት እንድናከናውን መመሪያ ሁሉ ነገር ለበጎ ለተግሳፅና ለምክር እንደተፃፈ ማመን አለብን።
ከመቁረብ በፊት ውሀ መንካት አይገባም የሚለው ሃሳብ፤ ለምሳሌ ነገ ቅዳሜ ቅዱስ ሥጋውን እና ክቡር ደሙን የምንቀበል ከሆነ አርብ ማታ ላይ በጊዜ ገላን መታጠብ ያስፈልጋል፥ ነገር ግን ጠዋት ልንሄድ ስንል አፍ መጉመጥመጥ አይቻልም፥ በአይናችን ውሃ እንዳይገባ ፊትንም መታጠብ አይገባም። ትንሽ ነካ ነካ አድርጎ አድርገን ከላይ ከላይ ብንታጠብ ግን ችግር የለም። አባቶች ሲያስተምሩን ሰውነታችን ክፍት ስለሆነ ውሃ በአይን ይገባል ይላሉ፦ ስለዚህ ጠዋት ላይ ፥አፋችነን ባንጉመጠሞጥ ፥ይምረረን ግዴለም ፥ ምሬቱ መከራውን እንድናስብ ሀሞቱን እንድናስብ ለ 18 ሰዓት መጾም ለማለት እንጂ፥ እንደነገን የምንቆርብ ከሆነ ዛሬ ማታ መታጠብን አይከለክልም፥ መመገብ ወይም ውሃ መጠጣት ግን አይቻልም። በአጠቃላይ ይህ ስርአት የውስጣችንን ቅድስናና ንፅህና ለማጠየቅ ሲሆን በአካለ ሥጋችን የምናደርገው ፅዳትም ለእግዚአብሔር መታዘዝን ለማመልከት ነው።
ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የተዘጋጁ ካህናትም ሆኑ ምዕመናን 18 ሰዓታት ከሚበላ እና ከሚጠጣ ምግብ ተከልክለው በጾም ተወስነው መቆየት ይገባቸዋል። ጠያቂያችን ፤ 18 ሰዓት አፋችን ምሬት እስኪሰማው ለማለት ነው፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ 3 ሰዓት በአይሁድ ተያዘ፥ እስከ 9 ሰዓት ነፍሱ ከስጋው እስክትለይ ድረስ 18 ሰዓት ይሞላል እና ያን በማሰብ አፋችን ምሬት እስኪሰማው ድረስ ብላ ቤተክርስቲያናችን ታስተምረናለችና ነው።
ወደ ቅዱስ ቁርባን ለመቅረብ ስንዘጋጅ ወደ እግዚአብሔር ቤት ቅዳሴ ከመጀመሩ በፊት መድረስ ይኖርብናል። ተሰጥኦውንም እየተቀበሉ ቆይተው ቀዳሲያን ቅዱስ ሰጋውን ክቡር ደሙን ሊያቀብሉን ከቤተመቅደስ ብቅ ሲሉ ሁሉም ምእመን ለቅዱስ ሰጋውን ለክቡር ደሙ ክብር በመሰጠት በፊቱ እርግት ብሎ ሰግደው ስጋውን እና ደሙን ይቀበላሉ ማለት ነው። ሌላው ሰውም ከሰገዱ በኋላ ፤ ቀዳሲያን አቀብለው ሲመለሱና ፊታቸውን ወደ ምስራቅ ሲያዞሩ ሌሎቹ ሰግደው ከነበሩበት ቦታቸው ላይ ብድግ ብለውም ቆመው የራሳቸውን ቦታ ይዘው ወደፊት ለዚህ እንዲያበቃቸው ፈጣሪያቸውን እየተማጸኑ ቀሪ የሚቀጥለውን የቅዳሴ ቀሪ ጸሎቱን ስርዓት በጽሞና ሆነው ያዳምጣሉ ማለት ነው።
የማቁረሪያ ምግብ እስከሚቀምስ ድረስ ከሰው ጋር መነጋገር የማይችልበት ምክንያት መለኮታዊ እሳት የተዋሀደውን ቅዱስ ሥጋና ክብር ደሙን በተቀበለ ጊዜ ለነፍስ መድኅኒት ለስጋም በረከትን የሚያመጣውን የከርስቶስን ስጋውንና ደሙን ተቀብሎ ሌላ የሰውኛ ንግግርን መነጋገር ሃሳብን ማውጣትና ማውረድ ፈፅሞ ስለማይፈቀድ ነው። ከቅዱስ ቁርባን በላይ የሚከብር ነገር ባለመኖሩ በብዙ ፈተና የረከሰውን ህይወታችንን የቀደሰውንና የተዋረደውን ማንነታችንን ያከበረውን ቅዱስ ቁርባን ማቃለል ለኛም ከቅዱስ ስጋውና ከክቡር ደሙ ያገኘነውን ክብር ስለሚያሳንስብን ባጠቃላይ አፋችንን የመሸፈናችን ነገር ክፉ ከመናገር፣ ክፉ ከማሰብ፣ ክፉውን ድርጊት ከመፈፀም የራቅን ለመሆናችን የሚያመለክት ስርዓት ነው። ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ እህል ውሀ ቀምሰንም ቢሆን ከአንደበታችን የሚወጣው ነገር የተቀደሰና በጎ ነገር ሊሆን ይገባዋል ወይም ክፉ ሃሳብና ክፉ ድርጊት ከኛ እንዳይወጣ ያስፈልጋል ለማለት ነው። በዋናነት እንደማስረጃ የምናደርገው ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ቤዛ ለመሆን በመስቀል ላይ ቅዱስ ስጋውን ቆርሶ ክቡር ደሙን አፍስሶ ለኛ ያለውን ፍቅር በመስቀል ካረጋገጠ በኋላ 3 መአልትና 3 ሌሊት በከርሰ መቃብር በቆየ ጊዜ ቅዱሳን ሐዋሪያትና ሌሎችም ተከታዮቹ በሀዘንና በለቅሶ የላመ የጣመ እህል ውሀ ሳይቀምሱ መቆየታቸውን የሚያመላክት ነው። ስለዚህ ዛሬ ለኛ ህይወት መድሃኒታችን የሚሆነው የሚሰጠን የተገኘው መራራ በሆነ የመስቀል መከራ ስለሆነ እኛም ዛሬ ከሚበላ ከሚጠጣ፣ ከነገር እና ከክፉ ድርጊት ራሳችንን ቆጥበን መቀበል እንደሚገባን የሚያመለክት ነው።
የተቀደሰ ሰላምታ አስፈላጊ በሆኑ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በአካልም ሆነ በስልክ እኛንም ሆነ ቁርባኑን አያረክሰውም፤ ብቻ በህሊናችን ራሳችንን ለእግዚአብሔር ማስገዛት ያስፈልጋል ለማለት ነው።
ከቆረብን በኋላ የለበስነውን ልብስመቼ ነው መቀየር ያለብን ወይስ ለብሰነው ነው ወይ የምናድረው ለተባለው፤ በመሰረቱ የአንድ ቀን ቁጥር የሚጀምረው ከዋዜማው ወይም ከማታው 12 ሰአት ጀምሮ እስከ የቀኑ 12 ሰዓት በድምሩ 24 ሰዓት 1 ቀን ይባላል። በዚህም መሰረት ሲቆርቡ የለበሱትን ልብስ ማታ የተቀበሉበት ቀን ማታ ማለትም ከ 12 ሰአት በኋላ ወይም የእለቱ ሰአት ሲጠናቅ መቀየር ይችላሉ።
ወደ ቅዱስ ቁርባን እና ወደ እግዚአብሔር ቤት ስንቀርብ ራሱን የቻለ ለዚህ አገልግሎት ብቻ የሚውል ሙሉ ልብስ ቢኖረን ይመረጣል። ምክንያቱም ይህን በማድረጋችን በውስጣችን ፍጹም የሆነ ልባዊ ሃይማኖትና ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዳለ ያመለክታልና። ስለዚህ ያንን በቁርባን ጊዜ የለበሱትን ነጠላ ሌላ ጊዜም እያጠቡም መገልገል ይችላሉ።
ወደ ቅዱስ ቁርባን እና ወደ እግዚአብሔር ቤት ስንቀርብ ራሱን የቻለ ለዚህ አገልግሎት ብቻ የሚውል ሙሉ ልብስ ቢኖረን ይመረጣል። ምክንያቱም ይህን በማድረጋችን በውስጣችን ፍጹም የሆነ ልባዊ ሃይማኖትና ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዳለ ያመለክታልና። ስለዚህ ያንን በቁርባን ጊዜ የለበሱትን ነጠላ ሌላ ጊዜም እያጠቡም መገልገል ይችላሉ።
በሌላም በኩል የተለየ ልብስ ወይም ትርፍ ልብስ የሌላቸው በድህነት ያሉ ክርስቲያኖች ያንን ያላቸውን የድህነት ልብሳቸውን ባላቸው አቅም በንፁህ አጥበው መቁረብ እንዳለባቸው ደግሞ መዘንጋት የለበትም። ምክንያቱም ገና ሀብታሞች እንደሚለብሱት የተለየ ልብስ የለንም በሚል ምክንያት ከቅዱስ ቁርባን እርቀው መኖር ስለማይገባቸው ነው።
ቅዱስ ቁርባን የተቀበለ ሰው ከቁርባን በኋላ ብቻውን አይሄድም የሚባለው የቆረበ ሰው ከምንም በላይ ህይወቱ የከበረና መንፈሳዊ ሙሽራ ስለሆነ የተለየ ክብርም ስለሚያስፈልገው ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን አማናዊ ክብር ለማመልከትና ነው። በሌላ በኩል በዚህ ህይወትና መድኅኒት በሆነው በቅዱስ ቁርባን የከበረውን ሰው ሰይጣን በክፉ መንፈስ በጠላትነት ስለሚቃወመው አንደ አንዳንድ ባለስልጣናት ወይም በሙሽርነት የከበረ ሰው ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ እንደሚያስፈልጉት ሁሉ ከዚህም በላይ የሰው ልጅ ፍጹም ሰማያዊ ክብር የሚያገኝበትን ቅዱስ ቁርባን በተቀበለ ጊዜ ልዩ እንክብካቤና ጥበቃ ስለሚያስፈልገው ብቻ ነው።
ስለዚህ መረዳት ያለብን ከላይ የገለፅናቸው የገለፅናቸው ምክንያቶች ለስጋ ደሙ ክብር ከመስጠት የተነሳ ነው እንጂ ስጋ ደሙን የተቀበለ ሰው ለሌላ አደጋ የተጋለጠ ይሆናል ብሎ ማሰብ የተሳሳተ ነው። እንዲያውም ከምንም በላይ ስጋውን ደሙን የተቀበለን ሰው የአጋንንት መንፈስም ሆኑ ሌላ ሃይል እንዳይቃወመው ታላቅ ግርማ ሞገስና ሃይልና ጉልበት ስለሚሆነው ብቻውን ስለሄደ ችግር ያጋጥመዋል ብሎ ማመን የተሳሳተ ሃሳብ ነው። በየገዳማትም ሆነ በየአብያተ ክርስቲያናት ቅዳሴ አስቀድሰው ቅዱስ ቁርባን የሚቀበሉና የሚያቀብሉ ብቻቸውን አገር አቋርጠው ሲሄዱ እነሱ ለሌላው ክብርና ሞገስ ይሆናሉ እንጂ በነሱ ላይ የሚደርስባቸው አንዳችም ክፉ ነገር የለም።
በአጠቃላይ ዋናው ምክንያት የእግዚአብሔርን ቅድስና ወይም ቅዱስ ቁርባን ለማርከስ የሚችል ሌላ ነገር ኖሮ ሳይሆን፤ እኛ ግን ከክርስቶስ ስጋና ደም ጋር ስለተዋሀድን በኛ አላማ በቅናት ያበደው ሰይጣን ሊፈትነንና በሚያጠምደው መሰናክል ሊጥለን ስለሚችል ከሁሉ ነገር ተቆጥበንና ተሰብስበን ለዘላለማዊ ድህነት የወሰድነውን የክርስቶስን ቅዱስ ስጋና ክቡር ደም በልዩ ስርአት አክብረን የተወሰነውን ጊዜ ማሳለፍ ስላለብን ነው። ሰይጣን ብዙ ጊዜ እኛን የሚጥልበት መሰናክል ረቂቅ ስለሆነ ክርስቲያናዊ ንቃት ኑሮን መጠንቀቅ ስለሚያስፈልግ ነው። ስለዚህ ጠያቂያችን ጥያቄዎት ለሁሉም አስተማሪ ይሆን በንድ ሰፋ አድርገንሆነ ለሁሉም ክርስቲያን ግልጽ በሆነ መልኩ የቀረበውን የህንን ትምህርት ልከንልዎታል።
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
በቅዱስ ቁርባን ሥርዓት ተጋብተው ለፍቺ የሚያበቃ ምክንያት ቢያጋጥም ምን ማድረግ እንደሚገባ
👉ጥያቄ፡ – በ #ቅዱስ #ቁርባን #ትዳር መስርተው በዝሙት ምክንያት ቢፋቱ፣ ንስሐ ገብቶ መታረቅ ይቻላል ወይ?
መልስ፡- ባልና ሚስት አንድ የሆኑበት ሚስጥር ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡ በቤተክርስቲያን የሚፈፀመው ጋብቻ በቅዱስ ቁርባን ነው፡፡ በተክሊልም ይሁን፣ ከተክሊል ውጪም ይሁን፣ በቤተክርስቲያን የተፈፀመ ጋብቻ ከሆነ፣ ትክክለኛ የቤተክርስቲያን ጋብቻ ነው የሚባለው፣ በቅዱስ ቁርባን ሲጋቡ ነው አንድ የሚያደርጋቸው፣ አንድነታቸውን የሚያረጋግጠው የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋው፣ ክቡር ደሙ ነው በዚህ ይታተማሉ ማለት ነው፡፡ አንድ ይሆናሉ፡፡ እነዚህ በቅዱስ ቁርባን አንድ የሆኑ ባልና ሚስቶች፤ በሆነ ነገር ተፈትነው ደግሞ እስከ ፍቺ የሚደርሱበትን መዘዝ ሠይጣን ይፈጥራል፡፡ አሁን ጠያቂያችን በዝሙት ነው አሉ፡፡ ይኼ እንኳን በባልና ሚስት ይቅርና፣ ቻውን የሚኖር ወንድ ሆነ ብቻዋን የምትኖር ሴት ከከባድ ኃጥያት መካከል የሚቆጠር መጥፎ መዘዝ ነው፡ጦሱ ራሱ አይለቅም፡፡ በደማችን ውስጥ አንድ ጊዜ ከገባ፤ መቸም ሠይጣን ይዞት የመጣ ስለሆነ ከእኛ ለመለየት ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ የዝሙት መንፈስ በጣም ከባድ ነው፡፡ ብዙ ረዥም መንገድ ሊያስኬደን ይችላል፡፡ መጥፎ ልማድ ሆኖ ከእኛ ጋር ተዋሕዶ፤ ጌታ ብሏል እኮ፤ ይህ የሥጋ ዘመድ እርኩስ መንፈስ ከባድ የሥጋ ዘመድ ስለሆነ ያለ ጾምና ያለ ፀሎት አይወጣም ብሏል፡፡ ይህን ያህል ውጊያ ያስፈልገዋል ማለት ነው፡፡ ከእንዲህ ዓይነት የኃጢያት ፆር ፈፅሞ ለመለየት ከባድ የመንፈስ ውጊያ ያስፈልገዋል፡፡ ቁጭ በለን በአጭር ቀን ውስጥ አስበን፣ በአጭር ቀን ውስጥ በምንቆያት የንስሐ ሕይወት አንድን ለዘመናት ከእኛ ተዋህዶ፣ በረቂቅ መንፈስ ሠይጣን አዋህዶን የነበረውን ኃጢያት እንገላገላለን ብሎ ማሰብ ራስን እንደማታለል ይቆጠራል፡፡ የእግዚአብሔርን ፀጋም በዋዛ ፈዛዛም መቀማት፤ በጣም ትንሽ ያልናት እንኳን የሥጋ ደዌ ወይም ደግሞ የታመምነው በሽታ ቢኖር በቀላል ህክምና ልንድን አንችልም፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ድነን አናይም፡፡ እሱ እንኳን ማለት ነው፡፡ በየጊዜው የሚገጥመን የሥጋ ደዌ አለ፤ የጤና መታወክ ማለት፣ ወረርሽኝ ብንል ስሙን፣ ቫይረስ ይሆናል፣ ባክቴሪያ ይሆናል፣ ሌላም ተዋሕስያን ለክፈውን ይሆናል፡፡ ብቻ እንደው ከትንሷ ነገር ጀምሮ፤ እጃችን ጥፍር ላይ ወይም ጣታችን ላይ፤ ወይም እግራችን ጣት ላይ ወይም በአንዱ የሰውነት ክፍለችን ላይ በትንሽ የምትከሰት ደዌ፤ የምታመጣብን መዘዝ አያምጣብን እንጂ፤ በከፍተኛ ደረጃ አስደንጋጭ ነገር ልንሰማ እንችላለን፡፡ አንዳንድ ጊዜ የማይድን በሽታ ተብሎ የሚነገረው ሁሉ ሊሆን ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ይጠብቀን፡፡
ስለዚህ የሥጋው ነገር፣ የነፍስ ነገር እንዲህ ከሆነ፣ እኛን ከእግዚአብሔር የሚለየን የኃጢያት ደዌ ወደ እኛ ገብቶ እንዲህ በቀላል ከእኛ የሚለይ፣ የሚላቀቅ አድርገን በብልጠት በአንድ ሳምንት ውስጥ ወደ ንስሐ አባት ቀረብ ብለን እንዲሁ ሰባት ቀንም ይሁን፣ አሥራ አራት ቀንም ይሁን ጹም፣ ጸልይ ተብሎ የሚባለው ነገር፤ ፈፅሞ ከዚያ ለረጅም ጊዜ ተጣብቆን ከቆየው ኃጥያት እንለያለን ብሎ ማሰብ አይደለም በየጥቂቱ በመንፈስ ማደግ፤ በየጥቂቱ አየታገሉንም ቢሆን በውስጣችን መንፈሳዊ ሕክምናችን እስከሚያልቅ ፣ ለዚህ ኃጢያታችን የምንወስደው መንፈሳዊ መድኃኒት በደንብ ወስደነው በፅናት እስከምንጨርስ ድረስ በትዕግሥት ነመቀጠል ነው ያለብን እንጂ ፣ የኃጢያት ደዌ በቀላሉ የሚላቀቅ አይደለም፡፡ የንስሐ ሕይወቱ ራሳችን ለእግዚአብሔር ማስገዛታችንና የሠራነውን ኃጢያት አምነን ተፀፅተን፣ ይቅር በለን ብለን መቅረባችን፣ ከዚያም በኋላ ግን ይኼ ለረጅም ጊዜ ሲዋጋን የነበረው የዝሙት መንፈስ፣ የስርቆት መንፈስ፣ የሐሰት መንፈስ፣ የሌላም መንፈስ አንደኛውን ከውስጣችን ጨርሶ እስከሚወጣ በዚህ ዓይነት መንፈስ የገባብን ጠላታችን ዲያቢሎስ ወይም እርኩስ መንፈስ ድንኳኑን ነቅሎ ከእኛ ተስፋ ቆርጦ ዳግም ላይመ፤ልስ እስከሚሔድ ድረስ ቀስ ብለን በትዕግስትና ፣በፅናት ሆነን እየወደቅንና፣ እየተነሳን በእግዚአብሔር ፊት ዘወትር በግል ጸሎታችን አብዝተን፣ እኛና እግዚአብሔር በምንገናኝበት መሥመር ከልብ ተፀፅተን እያለቀስንም ቢሆን እንነግረዋለን፡፡ በዚህ ዓይነት ነው ኃጢያት የሚለቀው፡፡ እንጂ ብዙ ሰዎች ናቸው እኮ፣ በብዙ ነገር ፀጋችው የበዛላቸው ሰዎች እንኳን ሳይቀር፣ በአንድ በሆነ አጋጣሚ እርኩስ መንፈስ ያመጣባቸው ፆር ወይም ደግሞ የኃጢያት ዓይነት ቶሎ አይለቅ፡፡› በብዙ ነገር በጸሎትም በፆምም እየኖሩ፣ እንዲህ ዓይነት የምፈተንበት ነገር አለኝ ይላሉ አባቶች፡፡ ሠይጣን በእንዲህ ዓይነትም ይፈትነኛል፣ ጌታየ ሆይ አሳልፈህ እንዳትሰጠኝ እያሉ በብዙ በመቶ እጥፍ ሊሆን ይችላል፣ ከእኛ ፀጋ የበዛላቸውን ሰዎች ሳይቀር፣ በለየለት ኃጢያትም ባይሆን በአንዳንድ ጥቃቅን እንቅፋት ይፈተናሉ እነሱም ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ይህንን ፈተናቸውን እንዴት እንደሚያርቁት ያውቃሉ ጥበቡ ገብቷቸዋል፡፡ እኛ ግን ለመዳን ስንፈልግም፤ ከገበያ እንደሚገዛ ዕቃ፤ በአንድ ቀን ብቻ ተሳክቶልን፤ ድነናል ማለትን ነው የምንመኘው፡፡ እንደገናም ደግሞ ስንወድቅም በኃጢያት፤ በትንሽ ተስፋ ቆርጠን ፣እጅ ሰጥተን ከነጉዳችን አብረን መኖርን እንመርጣለን፡፡ እንደዚህ አይደለም፣ መንፈሳዊነት እንደዚህ አይደለም፣ መጀመሪያ ጥበቡ ነው እኛ ማወቅ ያለብን ፡፡ መንፈሳዊነት የሚለው ነገር ፣ ክርስትና፣ ኃይማኖት የሚባለውን ነገር እንዴት ሆነን የምንኖረው ሕይወት ነው? ጥበብ ነው፣ እንዴት ነው አካሄዱ? ይኼ ከሆነ ነው እንግዲህ እንዲያው አያምጣብን እንጂ፣ በአቅማችን ልንሸከመው የማንችለው የኃጢያት ፈተና እንኳን ቢመጣብን፣ በእግዚአብሔር እርዳታ እንደምንቋቋመው ተስፋ አድርገን እጅ አንሰጥም ለሰይጣን፡፡ እንደምንድን እናውቃለን፡፡ ከባድ ሸክምም ቢባል፣ ከዚህ አንፃር ነው እንጂ ሁሉም ሰው የሚፈተነው ፈተና ነው፡፡
ስለዚህ ምንድን ነው ጠያቂያችን፤ በዝሙት ላለመውደቅ መታገል እንጂ፤ ከወደቁ በኋላ ሌላ ሕይወት ተመልሶ እንደገና አብሮ መኖርም፣ ቁርባንም ማስቀጠል ይቻላል፡፡ ታዲያ ድካማችን ይኼ አይደል? እግዚአብሔር ቁርባን ከማፍረስ ይጠብቀን፣ ትዳር ከመፍታት ይጠብቀን እንጂ፤ ይኼን ያህል ሰይጣን ፈትኖን፣ እጁ ውስጥ አስገብቶን፣ ያ ክፉ እኩይ ኣላማው ተሳክቶለት እኛን ትዳርችን ከበተነው፤ ቁርባናችንን ካስፈረሰን፤ መቸስ ሌላው የመጨረሻው እድላችን የመጨረሻው፣ አማራጫችን በንስሐ ሕይወት መመለስ ነው፡፡ ተመልሰን ደግሞ ሌላ ሚስት፣ ሌላ ባል አግብቶ እንደገና ሌላ ቆራቢ፣ እንደገና ሌላ ሁለተኛ የትዳር ሕይወት፣ ትዳሩን አፍርሶ ሌላ ሚስት አገባ፣ ትዳሯን አፍርሳ ሌላ ባል አገባች፣ ቁርባኑን አፍርሶ ከሌላ ሚስት ጋር ቆረበ፣ ቁርባኗን አፍርሳ ሌላ ባል ጋር ቆረበች ከመባል፤ በዚህ ዓይነት ቆራቢ ነበሩ፣ በጣም ጥሩ ሕይወት ነበራቸው፣ የሚያስቀና ሕይወት ነበራቸው፣ በመካከል በማይሆን ነገር ተፈትነው ነበር፣ ወይም በአንዳቸው ወይም በሁለታቸው የመጣ፣ ወይም በዝሙት ወይም በሌላ ምድራዊ ፈተና ተለያይተው ነበር እግዚአብሔር ይመስገን ተመልሰው አንድ ሆኑ፡፡ ይኸኛው ቀለል ያለ ነው፡፡ ወንዱም ሴቱም ሌላ ትዳር መስርቶ ለቁርባን ሕይወት ቢበቃ፡፡ ጠያቂያችን እንዳሉት በንስሐ ሕይወት ተመልሶ፣ ዳግም አብሮ መኖርም ሆነ መቁረብ ይቻላል፡፡ የመጨረሻው አማራጭ መሆኑን ግን ማስብ ይቻላል፡፡ ለማንም ሰው የምንመክረው፣ የምናበረታታው ምክራችን አይደለም፡፡ ቁርባንን ላለመተውነው፡፡ እንግዲህ ተፋትቶ በዝሙትም ሐሳብ፣ ሌላም ኃጢያት ይወደቃል፤ ይኼንን ሁልጊዜ የምንናገረው የሥጋ ባሕርይ ስለሆነ ነው፡፡ ሌላ እኮ ለዚህ ለእኛ በኃጢያት ችን መሠረት ኃጢያት የሠራ ሰው በእንዲህ ዓይለመውደቃችን ነገር መንፈሳዊ ሐኪሞቻችን፣ ዶክተሮቻችን የቤተክርስቲያን አባቶች ናቸው፡፡ የቤተክርስቲያን አባቶች ደግሞ የሚመሩበት፣ ይህን እውነት የሚናገሩበት ቋንቋ በልብ ወለድ ሳይሆን የእግዚአብሔር ሕግ የሚለውን ነገር ነው የሚናገሩት፡፡ ለዚህም ደግሞላችሁ በቀኖናነት የንስሐ ሕይወት ወደ እግዚአብሔር ይቅረብ ስለሚል ነው፡፡ ሰለዚህ እነዚህ ሰዎች እንደ ሰው ተፈትነው ነው እንጂ ሴትም ትሁን፣ ወንድም ይሁን በዝሙት ቢፈተኑ ጎበዝ ለሆነ፣ ትዕግሥቱ ላለው ሰው፣ ሁሉም እንደሚያልፍ ለሚያምን ሰው ፣ ሁሉንም ፈተና በእግዚአብሔር ማለፍ እንደሚቻል የሚያምን ሰው ከሆነ፤ እዚያው ላይ ሳይፋቱ ተራርመው ንስሐ ግባ፣ ወይም ንስሐ ግቢ እንዲያውም ሠፈራችን፣ መንደራችን፣ ቤተሰባችን ይኼንን ነውራችንን ቢሰማ ስንነቀፍ እንዳንኖር ፤በሚስጥር እንያዘውና ሳንፋታ እዚሁ ለተወሰነ ጊዜ ወደ ንስሐ ሕይወት ተመልሰን፣ ቀኖናችንን እስከምንጨርስ ድረስ፣ እግዚአብሔርን በድለናልና፤ ቅዱስ ሥጋውን፣ ክቡር ደሙን ደፍረናልና፣ ከቁርባን ቆም ብለን፤ በቀኖና ይኼንን የሠራነውን በደላችንን የኃጢያት ሥርየት እናግኝ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተብሎ፣ አገርና መንደሩ ሳይሰማው፣ ሽማግሌ ሳይሰበሰብ፣ እራሳችን ወደዚሁ ከንስሐ አባታችን ጋር ተነጋግረን መፍትሔ መፈለግ የተሻለ ነገር ነው፡፡ እንግዲህ ይኼ ጥንቃቄ ስለማይደረግበት ብዙ ሰዎች የሚያደርጉት ነው፡፡ ጠያቂያችን እንዳሉት አንድ ነገር ከሴቷ፣ ወይም ከወንዱ ከተሰማ አካኪ ዘራፍ ነው፣ ተደፍረናል፣ ሞተናል፣ ተዋርደናል፣ እንዲህ በሚል አተሳሰብ ባሕላዊ አስተሳሰብ፣ ወዲያውኑ ብትንትኑ ይወጣል፡፡ ቤተሰብ ብቻ አይደለም መንደሩ፣ ሰፈሩ ፣አገሩ ሁሉ ያውቀዋል ጉዱን፡፡ ነገሩ ሁሉ ከዚያ በኋላ ከእኛ እጅ ወጥቶ እየከበደ፣ እየከበደ፣ የማይሆን መዘዝ ውስጥ እንደርሳለን፣ ኃፍረትም ይይዘናል፣ ከዚያም በኋላ፣ ከጊዜ በኋላ እንደገና መከራው ፈትኖን፣ ሽማግሌም የመከረንን፣ የኃይማኖት አባት የመከረንን፣ቤተሰብ የመከረንን ነገር ሁሉ አንቀበልም ብለን ለዚሁ ፈተና ከደረስን በኋላ፣ እንደገና መከራው ፈትኖን ተመልሰንም ደግሞ ወደ ንስሐ ሕይወት መጥተን፣ ወደ አንድነትም መጥተን ከዚያ የቀደመውን ሕይወታችን ማስቀጠል፣ ከቻልን ይሔም አንድ ነገር ነው፡፡ እዚህ ደረጃ ባይደረስ ግን ምንአለ? ከምንም በላይ የእኛን ነውር የሚከድን፣ በደላችንን ኃጥያታችንን ይቅር የሚል ተመልሶ ወደ ቀደመው ክብራችን እንድንመለስ፣ ሁሉ የሚፈቅድ እግዚአብሔር የብዙ ነገራችን ሁሉ ከዳኝ እሱ ስለሆነ እሱ እንኳን በእኛ መዳን፣ በእኛ መመለስ፣ ሽማግሌ ሳያስፈልገው፣ ሳንለማመጠው፣ደጅ ሳይስጠናን፣ ይቅር ሊለን የታመነ አምላክ ሆኖ፣ እኛ ደግሞ የበዳይ አፍጣጮች ፣የኃጢያተኛ ፃድቅ ሆነን መታየት አያስፈልግም ነበር፡፡
እውነት ለመናገር ማንኛውም ሰው፣ ክርስቲያን የሆነ ሰው ሁሉ በቀላሉ ስለገጠመን ፈተና በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ በደንብ አድርገው ከሚመክሩን አባቶች ጋር ከተነጋገርን፣ እውነቱን ከተረዳን ይኸው በቂያችን ነው፡፡ አይ ይኼ ከሆነስ፤ እግዚአብሔር የፈቀደውን መንገድ እሱ የወደደውን መንገድ በዚሁ እቀጥላለሁ ማለት በእጅጉ ያስፈልግ ነበር ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት እንግዲህ ወደ ንስሐ ሕይወትም ተመልሶ ዳግም በቅዱስ ቁርባን መኖር መታደል ነውና እግዚአብሔር መጀመሪያ በኃጢያት ከመፈተን ይጠብቀን፡፡ ብንፈተንም ደግሞ ጠፍተን እንዳንቀር፣ ወደ ንስሐ ሕይወት እንድንመለስ እርሱ ይርዳን፣ ፀጋ በረከቱን በሁላችንም ላይ ያብዛብን፡፡ ተጨማሪ ምክር የምትፈልጉ ካላችሁ በውስጥ መሥመር ደውሉልን፡ አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ ፦ በ #ቅዱስ #ጋብቻ ተጋብተው የኖሩ ሰዎች በአንዱ አካል በትዳሩ መቀጠል አለመፈለግ ምክንያት ቢለያዩ ከ #ቅዱስ #ቁርባን መቀበል ሳታቋርጥ እየኖረች እንዴት በቅዱስ ቁርባን ካልተወሰነ ሰው ጋር መጋባት ትችላለች? እንዲ ብለው የሚመክሩ አባቶች በርከት ብለዋል በዚህ ምክንያት ብዙ ሰው እየተሳሳተ ነው። አባቶች ብለዋል እየተባለ ከወንድ ከሴትስ ፍቅር ዘላለማዊው ህይወትስ ይወዳደራል እንዲ ያለ ትምህርት ከቅዱስ መፅሐፍ አንጻርስ ምላሻችሁንና ምክራችሁን በጉጉት እጠብቃለሁ።
መልስ፦ ጠያቂያችን፤ በክርስቲያናዊ ስነምግባር ለመኖር ለመረዳት መጠየቅዎ እጅግ የሚያስደንቅዎ እና የሚያስመሰግንዎ ስለሆነ በአጭሩም ቢሆን ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምሮ አንጻር የሚከተለውን ማብራሪያ የሰጠንበት ስለሆነ ትክክለኛውን ስርዓት በዚህ አንብበው እንዲረዱት በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላለን።
በመሰረቱ ባል እና ሚስት የስጋ አስተሳሰብ በሆነ ፈተና ለሚያጋጥማቸው ችግሮች እንዲፋቱ አይፈቀድላቸውም። ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከተፋቱ እንኳን፦
1. በየግላቸው ስጋው ደሙን ለመቀበል የሚችሉት በቀጣይ ህይወታቸው ሴቷም እንደስዋ በቁርባን ተወስኖ የሚኖረውን ለማግባት፣ ወንዱም እንደሱ በቁርባን ተወስና የምትኖረውን ለማግባት ከሆነ እየቆረቡ ለመኖር ይችላሉ።
2. ወንዱም ሆነ ሴቷ አብረው የነበሩበት የጋብቻ ቆይታቸውንና የተፋቱበትን ዋና ምክንያት ተናዘው እንደነሱ በሃይማኖትና በምግባር የሚወሰነውን ባል ወይም ሚስት በማግባት እየቆረቡ መንፈሳዊ ህይወታቸውን ማስቀጠል።
3. ሁለተኛ ላለማግባት የወሰኑ ከሆነ ንፅህናቸውን እና ቅድስናቸውን ጠብቀው በየግዜው የነፍስ አባታቸውን እያማከሩ በስርዓተ ቁርባን ህይወታቸውን ማስቀጠል ይችላሉ።
4. ሌላው ቀጣይ ህይወታቸውን ስርዓተ ምንኩስና በመወሰን መንፈሳዊ ልባዊ ውሳኔ ካላቸውም በስርዓተ ቁርባኑ ተወስነው ከቆዩ በኋላ በቤተክርስቲያን ቀኖና መሰረት የንስሓ አባታቸውን አማክረው ለምንኩስና የሚያበቃቸውን መስፈርት ሲያሟሉ እንዲመነኩሱ ይደረጋል ማለት ነው።
5. ዲያቆን ወይም ቄስ ሚስቱ ብትሞትበት ወይም ከሱ አቅም በላይ በሆነ ፈተና ቢፋታ፤ ያለ ሚስት የሚቀድሰውም ሆነ አባት የሚሆነው እስከ 6 ወር እንደሆነ በፍትሐ ነገስት ተወስኗል። ከዚያ በኋላ ግን ወይ መንኩሶ በክህነቱ ይቀጥላል፤ ወይም ፈተናውን የማይችለው ከሆነ ለቤተክርስቲያን አባቶች በግልፅ ተናግሮ በቅዱስ ቁርባን ተወስና የምትኖረውን ያገባል። ከዚህ በኋላ ግን መቀደስም ሆነ አባት መሆን አይችልም። የውጭ አገልግሎቱን እያከናወነ እየፀለየ ለመንግስተ ሰማያት የሚያበቃውን የቱሩፋት ስራ እነሰራ መኖር ይችላል።
በአጠቃላይ ጠያቂያችን፤ ሃሳቡን በዚህ ተገንዝበው በመረጡት ክርስቲያናዊ ህይወት አብራዎት የምትቀጥለውን/የሚቀጥለውን መርጠው ማግባት ካሰቡ በቅዱስ ቁርባን ተወስነው መኖር ይገባል።
ተጨማሪ
በስርዓተ ቁርባን ተወስነው የሚኖሩ ባል እና ሚስት እግዚአብሔር ሳይፈቅድላቸው በሞት ወይም ደግሞ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ቢለያዩ፤ ቢቻል የመጀመርያው አማራጭ፦ ስጋቸውን ከኀጥያት ወይም ከዝሙት ጠንቅ የሚያሸንፉ ከሆነ በመጀመርያው አላማቸው ጸንተው ለመቀጠል እንደሚችሉ የቤተክርስቲያን ቀኖና ያዛል። የውስጥ ኑሯቸውን ግን በሞግዚት ወይም ሰራተኛ በመቅጠር ሊሸፈን ይችላል። ሁለተኛው አማራጭ፦ ስጋውን መግዛትና ማሸነፍ የማይችል ሰው በዝሙት ጠንቅ ተፈትኖ ከፈጣሪው ጋር ከሚጣላ በሃይማኖትና በስነ ምግባር የምትመስለውን/የሚመስላትን በነበረበት/በነበረችበት አላማ ማለትም በቅዱስ ቁርባን ተወስኖ/ተወስና አግብቶ/አግብታ መኖር ይችላል/ትችላለች። ማስረጃ፦ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ አገር ለሚኖሩ ክርስቲያኖች “ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ፦ እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው። ነገር ግን፤ በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና፥ ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ” (1ኛ ቆሮ 7፥8-9) በማለት በዝሙት መንፈስ እየተቃጠሉ ነፍሳቸውን ከሚወጉና ከፈጣሪያቸው ጋር የሚያጣላቸውን ስራ ከሚሰሩ ስርዓተ ቤተክርስቲያንን በጠበቀ መልኩ በኑሮ ወይም ደግሞ በአላማ የምትመስለውን/የሚመስላትን አግብቶ/አግብታ እንዲኖሩ እንደመከራቸው እንመለከታለን።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ
ከቅዱስ ቁርባን መሸሽ እንደማይገባ
👉ጥያቄ፦ 1 ኛ በቅዳሴ ሰዓት በልቡ የአመንዝራ ሀሳብ ያለበት ከዚህ #ቅዱስ #ቁርባን በድፋረት ቢቀበል ገሀነመ እሳት እና ስጋ ወደሙም እሳት እደሚሆንበትና እኛም ባለን ስልጣንአወግዝን ይላሉ ቄሱ ይህ አባባል እዴት ስጋናወደሙን መቀበል ያስችላል ወይስ ሀሳቡ ምን ሊባል ተፈልጎ ነው 2ኛ የማልፈልገው በሀልዮ የታሰበው ሀፅያት ንሰሀ ይገባበታል ወይ አመሰግናለው
መልስ፦ ጠያቂያችን ሃሳብ እና ዝሙት የሚለው ቃል በቤተክርስቲያን አተረጉጐም ብዙ ትርጉም አለው ። ይህ ማለት አንድ ክርስቲያን የዝሙት ስራ ሊሰራ ፣ሰው ሊገድል ፣ ገንዘብ ሊሰርቅ፣ አምልኮ ባዕድ ሊፈፀም ወይም ለጣኦት ሊያመልክ ፣ ሊያስጠነቁል፣ ሊጠነቁል ፣ሊያሟርት የቀን ቀጠሮ ይዞ እግዚአብሔርን ለማታለልና ለመደለል ወይም እግዚአብሔርን እንደ አላዋቂ ለመቁጠርና ለመፈታተን ወደ ቅዱስ ቁርባን መቅረብ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ፣ ማስቀደስ፣ መጸለይ ከንቱ ነው ማለት ነው። ሃሳብ ማለት ፍጹም መላ ሕይወታችንን ለኀጢአት ተገዢ ለማድረግ መወሰን ማለት ነው። ነገር ግን አንዳንድ ግዜ በሃሳብ እየተዋጋን ታግለን እያሸነፍነው በአላማችን የምንኖራቸውን እንደማይመለከት መገንዘብ ያስፈልጋል። ምክንያቱም የሰው ልጅ የሚያስተውል እና ሁሉን ለይቶ የማወቅ ጥበብ የተሰጠው የሚያስብ ስለሆነ በአይናችን ያየነው ነገር ወዲያውኑ በሃሳብ ሊፈትነን ይችላል ፤ነገር ግን ከዋናው አላማችን እስካልወጣን ድረስ ውስጣችንም ስለሚፀፀትበት እና የህሊና ንስሐም ስለምንገባበት ኀጢአተኞች ሊያስብለን እንደማይችል መረዳት ያስፈልጋል፡፡
ሰው በውስጣዊ ህሊናው አውጥቶና አውርዶ ገና በስራ ላይ ያልዋለው በሃሳቡ ብቻ ያቀደው የክፋት ምኞት ሁሉ ያሃልዮ (የሃሳብ) ኀጥያት ይባላል። በልቡ የታሰበው ኀጥያት በአፍ ሲነገር የነቢብ (የመናገር) ኀጥያት ይባላል። በአፍ የተነገረው ኀጥያት በስራ ላይ ከዋለ የገቢር (የተግባር) ኀጥያት ይባላል።
ስለሆነም በልብ ታስቦ ሳይናገርና ስራ ላይ ሳይውል ከቀረ የታሰበውን ኀጥያት የሚያውቀው ልብና ኩላሊትን የሚመረምር እግዚአብሔር በመሆኑ በልብ ታስቦ ስራ ላይ ስላልዋለው ኀጥያት እና አንዳንዴም ጥፋት ሳይመስለን ባለማወቅ የምንፈፅማቸው ጥቃቅን ጥፋቶች በየጊዜው ወደ ካህኑ ቀርበን እና ከልባችን አምነን መስቀሉን ተሳልመን ካህኑ እግዚአብሔር ይፍታህ ቢሉን ከጢያት የተፈታችሁ ሁኑ ሲሉን በውስጣችን የሚዋጋን ክፉ መንፈስ እንደ አሮጌ ልብስ ተገፎ እንዲወልቅ በካህኑ ላይ ያደረው ሃብተ ክህነት ያደርግልናል። ሆኖም በመናገርም ሆነ በመስራት የፈፀምነውን ከባድ በደል ግን እንደማያስፍቅልን መረዳት ያስፈልጋል።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ ላይ ያገኛሉ
👉🏾👉🏾👉🏾 ለምን ርቀህ ቆምክ?
ስለ #ንስሐ እና ስለ #ቅዱስ #ቁርባን
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገፅ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምትከታተሉ አባላቶቻችን ሁሉ፤ ከላይ በርዕሱ አንደተጠቀሰው ‘ለምን ርቀህ ቆምክ?”‘ ከሚለው መጽሐፍ ውስጥ ስለ ንስሐ እና ስለ ቅዱስ ቁርባን የሚመለከተውን ጠቃሚ ትምህርት ልከንላችኋልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።
1. ንስሐ
ንስሐ ማለት መጸጸት፤ መቆርቆር፣ ኃጢአትን ስለሠሩ ማዘን፤ ማልቀስ፣ መቆጨት ነው፡። የበጎ ሥራ ጠላት ዲያብሎስ የሰው ልጅ መንግሥተ ሰማያትን እንዳይወርስ ክፉ መርዙን እየረጨ ከንስሐ መንገድ ያርቀናል፡፡ ኃጢአትን በኃጢአት ላይ ደርቦ ደራርቦ ያሠራህና ራስህን እንደ ሰው መቁጠር እስኪያቅትህ ድረስ ያስጨንቅሃል። ንስሐ ለመግባት ስትፈልግ “ይህን ያህል ኃጢአት በሙሉ እንዴት ነው ለንስሐ አባትህ የምትነግራቸው? የሚያሳፍር ኃጢአትም ሰርተሃል። ስለዚህ አሁን ተወውና ስታረጅ አንድ ጊዜ ትገላገላለህ።” ይልሃል፡፡ የዕድሜ ዘመንህንም ረዘም አድርጎ ያሳይሃል፡፡ አንተም ትታለላለህ «ኃጢአተረን በሙሉ አንድ ጊዜ ልገላገለው» እያልህ ኃጢአትን ማጠራቀም ትጀምራለህ፡፡
እግዚአብሔር በሞት የሚጠራህ መቼ እንደኾነ ግን ታውቃለህ? በፍጽም አታውቅም፡ ጠላት ግን ሺህ ዘመን የምትኖር አስመስሎ ያሳይሃል፡፡ ጠላት አሁንም ይቀርብና «የሰራኸው ኃጢአት በጣም ከባድ ነው። ለንስሐ አባትህ ከነገርካቸወሰ በኋላ ለሌላ ሰው ቢነግሩብህሳ» ይልሃል፡ አንተ ግን አትስማው ለቅዱስ ጴጥሮስ የተሰጠው የማሰርና የመፍታት ሥልጣን ለንስሐ አባቴም ተሰጥቷቸዋል በለው። /ማቴ 17:19/ ዲያብሎስ ግን አሁንም ሌላ ወሬ ይጀምራል።፡ «ንስሐ አባት ምናምን እያልክ ለምን ጊዜ ትፈጃለህ ዝም ብለህ ወደ አምላክህ ቀርበህ ይቅር በለኝ ብትለው ይቅር ይልህ የለምን?» ይልሃል፡፡ አንተ ግን ምክሩን አትቀበል በኃጢአት ማሰሪያ እንደታሰርኽ ወደ ክርስቶስ ብትቀርብ «ራስህን ለካህን አሳይ» ይልሃል እንጂ አይቀበልህም፡፡ «ክርስቶስ ወደ አንዲት መንደር ሲገባ በሩቁ የቆሙ አስር ለምጻሞች ተገናኙት እነሱም እየጮሁ ኢየሱስ ሆይ ማረን አሉ።አይቶም ሂዱ ራሳችሁን ለካህን አሳዩ አላቸው።” ይላል። /ሉቃ 17፥12-14/ ላይ።
ስለዚህ የንስሐ አባት የግድ አስፈላጊ እንደኾነ ልትረዳ ያስፈልጋል። ንስሐ ሳትገባ መንግሥተ ሰማያት መግባት አትችልም፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ «መንግስቸ ሰማያት ቀረሸባለችና ንስሐ ግቡ » አያለ ይሰብክ የነበረው ለዚህ ነው፡ /ማቴ3 ፥1-2/ በንስሐ መመለስ ኃጢአትን ኹሉ እንዳይታስብ (እንዲሠረይ) ግዱፍ እንዲኾን ያደርጋል። ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ይላል «ሕመምተኞን እንጂ ባለጤናዎች ባለመድኃኒት አያስፈልጋቸውም ነገር ግን ሄዳችሁ ምህረትን እወዳለሁ መስዋእትንም አይደለም ያለው ምን እንደሆነ ተማሩ። ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጀመ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና»። (ማቴ 9፥12-13) ይላል፡፡ ስለዚህ ንስሐ መግባት ተገቢ ነው ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወደ ምድር የወረደ ኃጥአንን በንስሐ ለመጥራት እንጂ ለጻድቃን አይደለምና፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የለበሰ ለአብርሃም፤ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ አይደለም ኃጢአትን ላደረጉ ኃጥአን ነው እንጂ፡፡ ንስሐ ኃጢአተኛን ንጹሕና ጻድቅ የሚያደርግ ልዩ ምስጢር ነው: «በደላቸውን እምራቸዋለሁና ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና» ተብሎ አንደተጻፈ /ኤር 31፥34/ ላይ፡፡
ጠላት ያንተን ይቅር መባል አይወድምና ከዚህ ምስጢር እንድትርቅለት በርካታ መሰናክሎችን ያስቀምጥብሃሃል። ኃጢአት ስትሠራ እንደ ማር ይጣፍጥሃል። በኃጢአት ላይ ኃጢአት በበደል ላይ በደል ትደራርባለህ፡፡ የኃጢአት ካባ ሙቀት ይኾንሃል፤ የጽድቅ ሥራ ይቀዘቅዝሃል፡፡ ከዚህም የተነሣ ኃጢአት ባሪያው ያደርግሃል አንተም አገልጋዩ ትኾንለታለህ።፡ የታሰርክበትን ሰንሰለት ለመፍታት ስታስብ እንቅልፍህ ይመጣል፡። ዕድሜህ አንደ ዋዛ በከንቱ ትሮጣለች።: አንደ ኖኅ ዘመን ሰዎች የአግዚአብሔር ቁጣ ሳታስበው መጥቶ ንፍር ውኃ ቢዘንብብህ የት ትገባለህ? /ዘፍ6 እና ዘፍ 7 ሙሉውን ተመልከት/ የሞትህ ቀን መቼ አንደኾነ አታውቅምና ንስሐ ገብተህ ተዘጋጅተህ መኖር ተገቢ ነው፡፡ ሙሸራው ሲመጣ ዘይት ፍለጋ ልትሄድ አይገባም ዘይትህን ከመብራት ጋር ይዘህ መጠበቅ ነው አእንጂ፡፡ /ማቴ 25፥1–ፍጻ ተመልክት/
የጠላትን መሰክር አትቀበል ምክንያቱም እርሱ ጥሩ ምክር አይመክርህምና።
እናታችን ሔዋን የጠላትን ምክር በመቀበሏ ስትጎዳ እንጂ ስትጠቀም አላየናትም።፡ ስለዚህ ለጠላት ጆሮ ሰጥተህ አትስማው: ንስሐ አትግባ እያለ የሚያስጨንቅህ ወደ ዘላለም ቅጣት ሊጥልህ እንጂ የዘላለም ሕይወትን እንድታገኝ አይደለም። የቀደመው እባብ ጠላት ዲያብሎስ አሁንም ንስሐ አይጠቅምም እያለ የሚጨቀጭቅህ ከኾነ የጥጦስን (የፈያታዊ ዘየማንን) ታሪክ ዘርዝረህ ንገረው፡፡ ጥጦስ ቀማኛ፣ ሽፍታ እና ወንበዴ ነበር፡። በዕለተ ዓርብ በኢየሱስ ክርስቶስ ቀኝ በኩል ተሰቀለ፡፡ ሰባቱን ተአምራት በዓይኑ ተመሰከተ። በመስቀል ላይ ያለበደሉ የተሰቀለው ክርስቶስ አምላክ እንደኾነም አመነና «ጌታ ሆይ በመንግስትህ በመጣህ ገመዜ አስበኝ» የሚል ታላቅ ልመናን ለመነ፡። ኢየሱስ ክርስቶስም በንስሐ ተቀበለውና «እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኾናለህ።» አለው፡፡ ይህ ወንበዴም አዳምን ቀድሞ በክርስቶስ ደመ ማኅተም ፶፭፻ ዘመናት ያህል ተዘግታ የነበረችን ገነት ከፍቶ ገባ። /ሉቃ 23፥39-43) ፤ ሕማማተ መስቀልን ተመልከት/ ስለዚህ ንስሐ ቆሻሻን ኹሉ እንዲህ የሚያጠራ ሳሙና ነውና አታጠብበታለሁ እንጂ አልርቀውም አልሸሸውም በለው፡፡ የኅሊናን ሸክም የሚያራግፍ ኃጢአትን ኹሉ የሚደመስስ ልዩ መድኃኒት ነውና በየሰዓቱ ውሰደው ንስሐን፡፡
2. ሥጋ ወደሙ
ዲያብሎስ እጅግ በጣም አብዝቶ ማራቅ የሚፈልገው ከምስጢራት ኹሉ የበላይ ከኾነው “ምስጢረ ቁርባን” ። ነው ምስጢራት ኹሉ የሚደመደሙት በሥጋ ወደሙ ነው። ምስጢረ ጥምቀት፤ ምስጢረ ንስሐ፤ ምስጢረ ክኅነት፤ ምስጢረ ተክሊል የሚፈጸሙት በቁቀርባን ነው። ይህንን የሚያውቅ የውሸት አባት ዲያብሎስ የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር ከሥጋ ወደሙ ያርቅሃል። አንተ ግን «የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ከቶ አይጠማም» ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን አምናለኹና ከአመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የነሳውን ሥጋና ደም እመገባለሁ በለው፡፡ (ዮሐ 6፥35 ) የዘላለም ሕይወትን መውረስ አንደምትፈልግም አሳወቀው፡፡ «ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል» /ዮሐ 6፥41/ ያለውን የወንጌልም ቃል አሳየው፡)፡ ስለዚህ ሰዘላለም በመንግሥተ ሰማያት ለመኖር ከሰማይ የወረደውን እንጀራ እበላለሁ ብለህ ጠላትን አሳፍረው፡፡
ጠላት ግን በድፍረት እንድትቀርብ ሊፈትንህ ይችላል፡ የምትቀበለውን ሥጋና ደም የዕሩቅ ብአሲ ሥጋና ደም ነው ብሎ ሊያታልልህ ይሞክራል፡፡ አንተ ግን አትስማው የምበላው ሥጋ በዕለተ ዓርብ የተቆረሰው ነው፤ የምጠጣው ደምም በመስቀሉ የፈሰሰውን ደም ነው በለው። ሥጋና ደሙም መለኮት የተዋሐደው ነፍስ የተለየው እንጂ ጠላት እንደሚለው መለኮት የተለየው አይደለም፡፡
ጠላት ግን ውጊያውን አሁንም አያቆምም «ንስሐ ሳትገባ ሳትዘጋጅ ተቀበል» ይልሃል፡፡ እርሱን ከሰማኸው የይሁዳ እጣ ፈንታ አንተ ላይም ይደርሳል።፡ ሳይዘጋጁ ከኃጢአት ሳይነጹ ቢቀበሉት ግሩም ፍዳን የሚያመጣ የሚባላ እሳት ነው፡። ይሁዳ በጸሎተ ሐሙስ ከሌሎች ሐዋርያት ጋር ከቁርባኑ ሥርዓት ተካፋይ ነበረ፡።፡ ነገር ግን በልቡ የነበረው ጌታን በ30 ብር የመሸጥ ኃጢአት እንደወጣ እንዲቀር አድርጎታል፡፡ /ማቴ 26፥14-29 ፤ ማቴ 27፥3-9 ተመልክት/ ሥጋና ደሙ ግሩም ፍዳ የሚያመጣ ነው የሚባለው ስለዚህ ነው፡ ስለዚህ በንጽሕና በትሕትና ንስሐ ገብቶ ሊቀበሉት ይገባል። በዚህ መልኩ ለሚቀበለው የዘላለም ሕይወትን የሚያወርስ ጥበብን የሚገልጽ ምስጢርን ኹሉ የሚያድል ነው። ለዚህም ነው ካህኑ በቅዳሴ ሰዓት “ንጹህ የሆነ ከቁርባኑ ይቀበል ንጹሕ ያያልሆነ ግን አይቀበል ለሰይጣንና ለመልእክተኞቹ በተዘጋጀው በመለኮት እሳት እንዳይቃጠል በልቡናው ቂምን የያዘ ልዩ አሳብም ያለበት ቢኖር አይቅረብ እጁን ከአፍአዊ ደም ንጹሕ እንዳደረግሁ እንዲሁም ከሁላችሁ ደም ንጹሕ ነኝ። ደፍራችሁ ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደም ብትቀርቡ ከእርሱ ለመቀበላችሁ መተላለፍ የለብኝም በደላችሁ በራሳችሁ ይመለሳል እንጂ። በንጽሕና ሆናችሁ ባትቀርቡ እኔ ከበደላችሁ ንጹሕ ነኝ» ብሎ እጁን የሚታጠበው፡። ዲያቆኑም ተቀብሎ «ይህን የቄሱን ቃል ያቃለለ ወይም የሳቀና የተነጋገረ ወይም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በክፋት የቆመ ቢኖር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳሳዘነው በእርሱም እንደተነሣሣ ይወቅ ይረዳ ስለበረከት ፋንታ መርገምን ስለ ሓጢአት ሥርየት ፋንታ ገሃነመ እሳትን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል» ይላል። ይህ አዋጅ የሚታወጀው ከክርስቶስ ሥጋና ደም ርቀን እንድንቆም ወይም የበይ ተመልካቾች አንድንኾን በኋላ ነው፤
፨ ባለትዳር የኾኑ ከኾነ ከቁርባን በፊት 3 ቀናትን ከቁርባን በኋላ 2 ቀናትን ከሩካቤ ሥጋ መከልከል አለባቸው፤
፨ ቢያንስ 18 ሰዓታትን ከመቀበላቸው በፊት መጾም፣
፨ ወንድ ዝንየት (ሕልመ ሌሊት) ሴት የወር አበባ ባገኛቸው ጊዜ ስለሥጋና ደሙ ክብር ከምስጢሩ አይካፈሉም፣፤
፨ ማንኛውም ፈሳሽ የሚወጣባቸው ደም የሚፈሳቸው ሰዎች አይሳተፉም፣
፨ ቅዳሴው ከተጀመረ በኋላ የደረሰ ሰው ከቁርባኑ አይሳተፍም
፨ ከቁተርባን በኋላ ጥፍር መቁረጥ፣ ጸጉርን መላጨት፣ ረዥም መንገድ መጓዝ፤ ፍርድ ቤት መከራከር፣ ከልብስ መራቆት፣ በውኃ መታጠብ አይፈቀድም፣፤
፨ ለቁርባን የለበሱትን ልብስ ለአንድ ቀን ያህል አለማውለቅ፣
፨ ከቁርባን በኋላ መስገድ እና ላብ የሚስወጣ ሥራን መሥራት አስይፈቀድም፤
ከቁርባን በፊትም ኾነ በኋላ ቀለል ያሉ ምግቦችን መመገብ፣
፨ በቁርባን ጊዜ ንጹሕ ኾኖ መገኘት ንጹሕ ልብስ መልበስ ቢቻል ሙሉ ነጭ ልብስ መልበስ፣
ስለዚህ ይህን እና የመሠለውን ጥንቃቄ በማድረግ መቀረብ እንጂ የጠላት ከይሲን ምክር ሰምተህ ከዚህ ተግባር እንዳትርቅ እመክርሃለሁ፡፡
ይቆየን
ምንጭ፦ “ለምን ርቀህ ቆምህ?” መጽሐፍ
በ ዲያቆን መልካሙ በየነ
2014
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን ላይ ያገኛሉ፦ Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ
👉🏾👉🏾👉🏾 ዘወትር #ኃጢአተኛ ነኝ በሚል አጉል #ትህትና ከ #ቅዱስ #ቁርባን መሸሽ ይገባልን?
በአጉል ትህትና የተገባሁ አይደለሁም እያሉ ሥጋውን ደሙን ሁልጊዜም ሳይቀበሉ መኖር ከኃጢአተኛነት አያወጣምና የኃጢአተኛነት ስሜት የሚሰማው ሰው ንስሓ ገብቶ በምክረ ካህን እየተመራ ለዚህ ክብር አብቃኝ ብሎ በመንፈሳዊ ህይወቱ ጸንቶ በአላማ መትጋት ይገባዋል። ለሁሉ ነገር መደምደሚያ የሆነው የክርስትናችን ዋና ማኅተም የሆነውን ቅዱስ ቁርባን መቀበል ነው። ስለዚህ ይኸን ሳያደርግ ዘወትር ኃጢአተኛ ስለ ሆንኩ ሥጋውን ደሙን ለመቀበል አልበቃሁም እያሉ ዘወትር መሸሸ በክርስቶስ የፍርድ ዙፋን ፊት በምንቆምበት ጊዜ መልስ ያሳጣል፡፡ “በራድ ወይም ትኵስ እንዳይደለኽ ሥራኽን ዐውቃለኹ።በራድ ወይም ትኵስ ብትኾንስ መልካም በኾነ ነበር።” ራእ 3፥15
አፈ ወርቅ ዮሐንስም ስለ እንደዚህ ዓይነት ሰው ሲናገር “ኀጥእ ነኝ እያለ ከንስሓ ወገን ምንም የማያስብ ኃጢአቱን የማያስብ በነቢብ በገቢር ይህን ሠራሁ ብሎ የማያስብ ሁልጊዜ ከንፈር በመምጠጥ ይኖራል”፡፡ በኀልዮ ብቻ መዳን አይቻለውምና፡፡ ከኃጢአት ይድን ዘንድ የሚወድ ሰው ግን እሊህን አንድ አድርጎ ይሥራ፡፡ ከኃጢአቱ አንዲቱን ሊናገር ቢወድ ፈጽሞ መናገሩ ጭንቅ ይሆንበታል፡፡ ይህን ልማድ እንተው›› ብሏል፡፡ ተግ 8 ገጽ 107
አውነት ነው፡፡ ከቅዱሳን መካከል አንዱ አርባ ዘመን ዘግቶ ናሮ በመልአኩ ትአዛዝ መሥዋዕት ከሚሠዋበት ቦታ ሂዶ ቆሞ ሲያስቀድስ ዲያቆኑ ‹‹ነጽር፦፥የበቃውንና ያልበቃውን ለይ›› ሲል ካህኑ ‹‹ቅድሳት ለቅዱሳን+፦ሥጋው ደሙ የተሰጠ ለበቁት ነው በቅቻለሁ የሚል ይምጣ ይቀበል እንጂ እኔ የበቃውንና ያልበቃውን በምን አውቀዋለሁ?›› ሲል እየሰማ በቅቻለሁማ ብየ ብቀበል ዕዳ በደል፣ድፍረት ይሆንብኝ የለምን? ብሎ እንይ ገና አርባ ዘመን ጨምሮ ሰማንያ ዘመን ከኖረ በኋላ ዳግመኛ መልአኩ ሥጋውን ደሙን ካልተቀበልህ አይረባህም ኦይጠቅምህም ብዬህ አልነበረምን? ብሎት እቀበላለሁ ብሎ ሂዶ ቆሞ ሲያስቀድስ ዲያቆኑና ካህኑ ቀድሞ የሰማውን ሲሉ ሰምቶ አሁንም ዕዳ ይሆንብኛል ብሎ ወጥቼ እሄዳለሁ ሲል መልአኩ ‹‹አሁንስ በቅተሃል ተቀበል ብሎ አጽናንቶት›› የተቀበለ ባሕታዊ አለ፡፡ ይህ ግን መመለሱ ካህኑ ሥጋው ደሙ የሚሰጥ በቅቻለሁ ነቅቻለሁ ከኃጢአት ተለይቻለሁ ለሚል ነው በቅቻለሁ የሚል ይምጣ ይቀበል ሲል እንዲህ ብየማ ብቀበል ዕዳ በደል ትዕቢት ይሆንብኝ የለምን? እያለ ነው አንጅ ኃጢአቱን ባለመናዘዙ አይደለም፡፡ ሰማንያ ዘመን ከዘጋ በኋላ ስንኳ መልአክ መጥቶ ሥጋውን ደሙን ካልተቀበልህ አይረባህም አይጠቅምህምና ተቀበል ብሎት መሥዋዕት ከሚሠዋበት ቤተ ክርስቲያን ካለበት ሂዶ ተቀብሏል፡፡
እናም የተገባሁ አይደለሁም እያሉ ከዚህ ቅዱስ ማዕድ መሸሽ ለሰይጣን በር መክፈት ከመሆኑም በላይ ወደ ቀቢጸ ተስፋ የሚያደርስ ቁልቁለት ያለበት ነው፡፡‹‹ወኢተሀብዎ ፍኖተ ለሰይጣን፦ ለሰይጣን መንገድ አትስጡት›› ኤፌ 4፥27 ‹‹እንግዲህ እግዚአብሔርን እሺ በሉት ሰይጣንን ግን እንቢ በሉት ከእናንተም ይሸሻል እግዚአብሔርን ቅረቡት ይቀርባችሁማል እናንተ ኃጥአን አጆቻችሁን አንጹ ሁለት ዐሳብም ያላችሁ እናንተ ልባችሁን አጥሩ›› እንዳለ፡፡ ያዕ 4፥8
እግዚአብሔር ለሚፈልጉት የማይታጣ ለማይፈልጉትም የማይገኝ አምላክ ነውና፡፡ በፍቅር በትህትና እርሱ የሚወደውን ሁሉ በመሥራት ወደርሱ ብንቀርብ እናገኘዋለን፡፡ ብንርቅም እናጣዋለን፡፡ ፀሐይ በዓለሙ ወጥታ ሳለ ሰው ከቤቱ ተቀምጦ ምነው ዛሬ ፀሐይ አትወጣም እንዴ? እያለ ሊጠይቅ ይገባዋልን? ከቤቱ ቢወጣ ፀሐይን ለዓለሙ ሁሉ ስታበራ ባገኛት ነበር፥ እንደዚኸውም ሁሉ. እግዚአብሔርና የእግዚአብሔር የሆነውን ሥጋውን ደሙንም ለማግኘት ከቤቱ ኃጢአት መውጣት ያስፈልጋልና፡፡ ዘሌ 26 ፥40-41 ሥጋውን ደሙን አለመቀበል ሁልጊዜ ከሥጋው ደሙ መራቅም እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያደረገውን ታላቅ የሆነውን ርኅራኄውን፣ የቸርነቱን ፍቅሩንና መድኃኒትነቱን አለመገንዘብ ነው፡፡
ስለዚህ ሥጋውን ዴሙን አለመቀበል ወይም አልበቃሁም በሚል ፈሊጥ መሸሸ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጣቸውን የአነዚህን ነገሮች ጥቅም አለመረዳት ነው።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ትምህርት ድረገጻችን ላይ ያግኙ፦ https://yohannesneseha.org/ነው
👉ጥያቄ፡- ሰላም አባቴ ስለምትሰጡት ትምሕርት ከልብ እያመሰገንኩ፤ ከዚህ በፊት በዐቢይ ጾም ንስሐ መግባት የሚል ጥያቄ ጠይቄ ነበር፣ እሱም ተመልሶልኛል፡፡ እግዚአብሔርን እኔ ደካማው፣ የማልረባው፣ ደካማው፣ ከንቱ ትቢያው አሳዘንኩት፣ እርስዎም ከሚገባው በላይ መክረውኝ፣ ገስፀውኝ፣ በመልካም ጎዳና ቢያራምዱኝም፤ አሁንም ጌታዬን መበደሌን አላቆምኩም ፤ አንድ አባት ጋር ሄጄ ያለውን ችግሬን ነገርኳቸው፡፡ ከዚያም በፊት ይመክሩኝ ነበርና አባ የሚገርምዎት ያን #ኃጢያት ከሠራሁ በኋላ እንደ እብድ ያደርገኛል፡፤ ደግሞም ሥራው፣ ሥራው ይለኛል፤በጭንቀት ውስጥ እንዳለሁ ነገርኳቸው፣ ንስሐ ሊሰጡኝ ቀጥረውኛል፡፡ እኔ ደካማ ነኝ መድኃኔ ዓለም ቢፈቅድ በአንደኛው ሳምንት #ቁርባን ለመቀበል አስብያለሁ፤ ያንን ካደረግሁ ሕይወቴ እንደሚቀየር አምናለሁ፣ ምክንያቱም አምላክ ቅርቤ ይሆናል እና አባቴ እርዱኝ፡፡
✍መልስ፡- ጠያቂያችን ፥ እጅግ አስተማሪ ነው፤ ከልብ በፍፁም እምነት ሆነው የሚፀፀቱ ሰዎች ሐሳብ ነው፡፡ ጥሩ ነገር አስበዋል፤ አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔርም እንደሚረዳዎት እንምናለን፤ የእግዚአብሔር እርዳታ የሚገለጸው በዚህ ሁሉ ነገር ነው፡፡
ሁል ጊዜ በየ ውድቀታችን፣ በየመሰናክላችን፣ በየፈተናችን እሱ ሊረዳን የታመነ አምላክ ነው፡፡ከወደቅንበትና ከገባንበት የኃጢያት መቃብር ውስጥ እጃችንን ጎትቶ ሊያወጣን እንደሚችል የታመነ አምላከ ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ አሁን በዚህ በታላቁ ጾማችን፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እየደጋገመ ከሚፈትንዎት ከዚህ እርኩስ መንፈስ ከሚያመጣው ፈተና ነፃ ለመውጣት በምክረ ካሕን፣ ይሔን በሚመስል ምክርና በቅርብ ካሉት የንስሐ አባትዎትም ምክር ምን ማድረግ እንዳለብዎት፣ እንዴት መጸለይ፣ እንዴት መስገድ፣ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚፈትንዎት መንፈስ ከውስጥዎ ተማርሮ እንዲወጣ ማድረግ ያለብዎትን ይረዳሉ ማለት ነው፡፡
በተጨማሪም እንዴት ማገልገልም እንዳለብዎት፣ የግል ሕይወትዎትን ፣ የሥራ ተግባርዎትን፣ ቋሚና መደበኛ የሆነውን ሥራዎትን ሳይጎዳ፤ ተማርሮ ከእርስዎ ጨርሶ ላይመለስ እንዲለይዎት ይሔንን በየጊዜው በኃጢያት የሚፈትንዎትን መንፈስ እንዲያስመርሩት፣ ባለችዎት ትርፍ ጊዜ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንዴት ማገልገል እንዳለብዎ ታሳቢ አድርገው ለተወሰነ ጊዜ መደበኛ ጸሎት አድረጉ፡
ሰው እኮ ገዳም ሄዶ ሱባኤ ይገባል፤ ያኔ እኛ ወደ እግዚአብሔር ስንቀርብ፣ እግዚአብሔር ወደ እኛ ሲቀርብ፣ ወይም ደግሞ እኛን ቀርቦ የነበረው እግዚአብሔር በቅዱስ መንፈሱ ሲጎበኘን የእግዚአብሔር የምሕረት እጁ ፣ የማዳን እጁ፣ በእኛ ላይ ሲሆን፣ ያኔ ያ እርኩስ መንፈስ ኃይሉ ሁሉ ተሸሮ ከእኛ ይለያል ማለት ነው፡፡
ስለዚህ በርቱና በዚህ የጾም ጊዜ ያሰቡትን፣ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል የሚያስችለውን ዝግጅት ያድርጉ፣ ተጨማሪ ምክር እንድንሰጥዎትና ፈተናዎትም በምን በምን የሚገለፅ እንደሆነ፣ ይሕንን የፈተና ጊዜ ደግሞ እርስዎ በአንፃሩ እንዴት ማሳለፍ እንዳለብዎት፣ በምን መቀየር እንዳለብዎት፣ እንዴት መጋደል እንዳለብዎት፣ እንዴት መትጋት እንዳለብዎት፣ እንዴት ከእግዚአብሔር ጋር መሆን እንዳለብዎት ተጨማሪ ምክር እንሰጥዎታለን፡፡ ለሁሉም ነገር የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ሆኖ ወደዚህ መጥተዋል፣ አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር ይርዳዎት፣ ወላዲተ አምላክ እመ ብርሐን፣ የጭንቅ አማላጇ እስዋም ከእርስዎ ጋር ትሆናለችና፤ ልጅዋን የምትረዳ እናት ናትና ይበርቱ ፣ ይትጉ ሁላችንም ይሔን ምክር እንደሚጠቅመን አስበን ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ፣ እኛም በትምሕርቱ የሚጠቅም ነገር እናገኝ ዘንድ እንድንከታተለው፣ ለሁሉም እንድታዳርሱ፣ ሼር እንድታደርጉ በእግዚአብሔር ስም አደራ እንላችኋለን፡፡
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
ቅዱስ ቁርባን እና ንስሐ
👉🏾👉🏾👉🏾 ለምን ርቀህ ቆምክ?
ስለ #ንስሐ እና ስለ #ቅዱስ #ቁርባን
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገፅ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የምትከታተሉ አባላቶቻችን ሁሉ፤ ከላይ በርዕሱ አንደተጠቀሰው ‘ለምን ርቀህ ቆምክ?”‘ ከሚለው መጽሐፍ ውስጥ ስለ ንስሐ እና ስለ ቅዱስ ቁርባን የሚመለከተውን ጠቃሚ ትምህርት ልከንላችኋልና ሁላችሁም አንብባችሁ ትማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።
1. ንስሐ
ንስሐ ማለት መጸጸት፤ መቆርቆር፣ ኃጢአትን ስለሠሩ ማዘን፤ ማልቀስ፣ መቆጨት ነው፡። የበጎ ሥራ ጠላት ዲያብሎስ የሰው ልጅ መንግሥተ ሰማያትን እንዳይወርስ ክፉ መርዙን እየረጨ ከንስሐ መንገድ ያርቀናል፡፡ ኃጢአትን በኃጢአት ላይ ደርቦ ደራርቦ ያሠራህና ራስህን እንደ ሰው መቁጠር እስኪያቅትህ ድረስ ያስጨንቅሃል። ንስሐ ለመግባት ስትፈልግ “ይህን ያህል ኃጢአት በሙሉ እንዴት ነው ለንስሐ አባትህ የምትነግራቸው? የሚያሳፍር ኃጢአትም ሰርተሃል። ስለዚህ አሁን ተወውና ስታረጅ አንድ ጊዜ ትገላገላለህ።” ይልሃል፡፡ የዕድሜ ዘመንህንም ረዘም አድርጎ ያሳይሃል፡፡ አንተም ትታለላለህ «ኃጢአተረን በሙሉ አንድ ጊዜ ልገላገለው» እያልህ ኃጢአትን ማጠራቀም ትጀምራለህ፡፡
እግዚአብሔር በሞት የሚጠራህ መቼ እንደኾነ ግን ታውቃለህ? በፍጽም አታውቅም፡ ጠላት ግን ሺህ ዘመን የምትኖር አስመስሎ ያሳይሃል፡፡ ጠላት አሁንም ይቀርብና «የሰራኸው ኃጢአት በጣም ከባድ ነው። ለንስሐ አባትህ ከነገርካቸወሰ በኋላ ለሌላ ሰው ቢነግሩብህሳ» ይልሃል፡ አንተ ግን አትስማው ለቅዱስ ጴጥሮስ የተሰጠው የማሰርና የመፍታት ሥልጣን ለንስሐ አባቴም ተሰጥቷቸዋል በለው። /ማቴ 17:19/ ዲያብሎስ ግን አሁንም ሌላ ወሬ ይጀምራል።፡ «ንስሐ አባት ምናምን እያልክ ለምን ጊዜ ትፈጃለህ ዝም ብለህ ወደ አምላክህ ቀርበህ ይቅር በለኝ ብትለው ይቅር ይልህ የለምን?» ይልሃል፡፡ አንተ ግን ምክሩን አትቀበል በኃጢአት ማሰሪያ እንደታሰርኽ ወደ ክርስቶስ ብትቀርብ «ራስህን ለካህን አሳይ» ይልሃል እንጂ አይቀበልህም፡፡ «ክርስቶስ ወደ አንዲት መንደር ሲገባ በሩቁ የቆሙ አስር ለምጻሞች ተገናኙት እነሱም እየጮሁ ኢየሱስ ሆይ ማረን አሉ።አይቶም ሂዱ ራሳችሁን ለካህን አሳዩ አላቸው።” ይላል። /ሉቃ 17፥12-14/ ላይ።
ስለዚህ የንስሐ አባት የግድ አስፈላጊ እንደኾነ ልትረዳ ያስፈልጋል። ንስሐ ሳትገባ መንግሥተ ሰማያት መግባት አትችልም፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ «መንግስቸ ሰማያት ቀረሸባለችና ንስሐ ግቡ » አያለ ይሰብክ የነበረው ለዚህ ነው፡ /ማቴ3 ፥1-2/ በንስሐ መመለስ ኃጢአትን ኹሉ እንዳይታስብ (እንዲሠረይ) ግዱፍ እንዲኾን ያደርጋል። ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ይላል «ሕመምተኞን እንጂ ባለጤናዎች ባለመድኃኒት አያስፈልጋቸውም ነገር ግን ሄዳችሁ ምህረትን እወዳለሁ መስዋእትንም አይደለም ያለው ምን እንደሆነ ተማሩ። ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጀመ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና»። (ማቴ 9፥12-13) ይላል፡፡ ስለዚህ ንስሐ መግባት ተገቢ ነው ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወደ ምድር የወረደ ኃጥአንን በንስሐ ለመጥራት እንጂ ለጻድቃን አይደለምና፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የለበሰ ለአብርሃም፤ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ አይደለም ኃጢአትን ላደረጉ ኃጥአን ነው እንጂ፡፡ ንስሐ ኃጢአተኛን ንጹሕና ጻድቅ የሚያደርግ ልዩ ምስጢር ነው: «በደላቸውን እምራቸዋለሁና ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና» ተብሎ አንደተጻፈ /ኤር 31፥34/ ላይ፡፡
ጠላት ያንተን ይቅር መባል አይወድምና ከዚህ ምስጢር እንድትርቅለት በርካታ መሰናክሎችን ያስቀምጥብሃሃል። ኃጢአት ስትሠራ እንደ ማር ይጣፍጥሃል። በኃጢአት ላይ ኃጢአት በበደል ላይ በደል ትደራርባለህ፡፡ የኃጢአት ካባ ሙቀት ይኾንሃል፤ የጽድቅ ሥራ ይቀዘቅዝሃል፡፡ ከዚህም የተነሣ ኃጢአት ባሪያው ያደርግሃል አንተም አገልጋዩ ትኾንለታለህ።፡ የታሰርክበትን ሰንሰለት ለመፍታት ስታስብ እንቅልፍህ ይመጣል፡። ዕድሜህ አንደ ዋዛ በከንቱ ትሮጣለች።: አንደ ኖኅ ዘመን ሰዎች የአግዚአብሔር ቁጣ ሳታስበው መጥቶ ንፍር ውኃ ቢዘንብብህ የት ትገባለህ? /ዘፍ6 እና ዘፍ 7 ሙሉውን ተመልከት/ የሞትህ ቀን መቼ አንደኾነ አታውቅምና ንስሐ ገብተህ ተዘጋጅተህ መኖር ተገቢ ነው፡፡ ሙሸራው ሲመጣ ዘይት ፍለጋ ልትሄድ አይገባም ዘይትህን ከመብራት ጋር ይዘህ መጠበቅ ነው አእንጂ፡፡ /ማቴ 25፥1–ፍጻ ተመልክት/
የጠላትን መሰክር አትቀበል ምክንያቱም እርሱ ጥሩ ምክር አይመክርህምና።
እናታችን ሔዋን የጠላትን ምክር በመቀበሏ ስትጎዳ እንጂ ስትጠቀም አላየናትም።፡ ስለዚህ ለጠላት ጆሮ ሰጥተህ አትስማው: ንስሐ አትግባ እያለ የሚያስጨንቅህ ወደ ዘላለም ቅጣት ሊጥልህ እንጂ የዘላለም ሕይወትን እንድታገኝ አይደለም። የቀደመው እባብ ጠላት ዲያብሎስ አሁንም ንስሐ አይጠቅምም እያለ የሚጨቀጭቅህ ከኾነ የጥጦስን (የፈያታዊ ዘየማንን) ታሪክ ዘርዝረህ ንገረው፡፡ ጥጦስ ቀማኛ፣ ሽፍታ እና ወንበዴ ነበር፡። በዕለተ ዓርብ በኢየሱስ ክርስቶስ ቀኝ በኩል ተሰቀለ፡፡ ሰባቱን ተአምራት በዓይኑ ተመሰከተ። በመስቀል ላይ ያለበደሉ የተሰቀለው ክርስቶስ አምላክ እንደኾነም አመነና «ጌታ ሆይ በመንግስትህ በመጣህ ገመዜ አስበኝ» የሚል ታላቅ ልመናን ለመነ፡። ኢየሱስ ክርስቶስም በንስሐ ተቀበለውና «እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኾናለህ።» አለው፡፡ ይህ ወንበዴም አዳምን ቀድሞ በክርስቶስ ደመ ማኅተም ፶፭፻ ዘመናት ያህል ተዘግታ የነበረችን ገነት ከፍቶ ገባ። /ሉቃ 23፥39-43) ፤ ሕማማተ መስቀልን ተመልከት/ ስለዚህ ንስሐ ቆሻሻን ኹሉ እንዲህ የሚያጠራ ሳሙና ነውና አታጠብበታለሁ እንጂ አልርቀውም አልሸሸውም በለው፡፡ የኅሊናን ሸክም የሚያራግፍ ኃጢአትን ኹሉ የሚደመስስ ልዩ መድኃኒት ነውና በየሰዓቱ ውሰደው ንስሐን፡፡
2. ሥጋ ወደሙ
ዲያብሎስ እጅግ በጣም አብዝቶ ማራቅ የሚፈልገው ከምስጢራት ኹሉ የበላይ ከኾነው “ምስጢረ ቁርባን” ። ነው ምስጢራት ኹሉ የሚደመደሙት በሥጋ ወደሙ ነው። ምስጢረ ጥምቀት፤ ምስጢረ ንስሐ፤ ምስጢረ ክኅነት፤ ምስጢረ ተክሊል የሚፈጸሙት በቁቀርባን ነው። ይህንን የሚያውቅ የውሸት አባት ዲያብሎስ የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር ከሥጋ ወደሙ ያርቅሃል። አንተ ግን «የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም በእኔ የሚያምንም ከቶ አይጠማም» ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን አምናለኹና ከአመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የነሳውን ሥጋና ደም እመገባለሁ በለው፡፡ (ዮሐ 6፥35 ) የዘላለም ሕይወትን መውረስ አንደምትፈልግም አሳወቀው፡፡ «ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል» /ዮሐ 6፥41/ ያለውን የወንጌልም ቃል አሳየው፡)፡ ስለዚህ ሰዘላለም በመንግሥተ ሰማያት ለመኖር ከሰማይ የወረደውን እንጀራ እበላለሁ ብለህ ጠላትን አሳፍረው፡፡
ጠላት ግን በድፍረት እንድትቀርብ ሊፈትንህ ይችላል፡ የምትቀበለውን ሥጋና ደም የዕሩቅ ብአሲ ሥጋና ደም ነው ብሎ ሊያታልልህ ይሞክራል፡፡ አንተ ግን አትስማው የምበላው ሥጋ በዕለተ ዓርብ የተቆረሰው ነው፤ የምጠጣው ደምም በመስቀሉ የፈሰሰውን ደም ነው በለው። ሥጋና ደሙም መለኮት የተዋሐደው ነፍስ የተለየው እንጂ ጠላት እንደሚለው መለኮት የተለየው አይደለም፡፡
ጠላት ግን ውጊያውን አሁንም አያቆምም «ንስሐ ሳትገባ ሳትዘጋጅ ተቀበል» ይልሃል፡፡ እርሱን ከሰማኸው የይሁዳ እጣ ፈንታ አንተ ላይም ይደርሳል።፡ ሳይዘጋጁ ከኃጢአት ሳይነጹ ቢቀበሉት ግሩም ፍዳን የሚያመጣ የሚባላ እሳት ነው፡። ይሁዳ በጸሎተ ሐሙስ ከሌሎች ሐዋርያት ጋር ከቁርባኑ ሥርዓት ተካፋይ ነበረ፡።፡ ነገር ግን በልቡ የነበረው ጌታን በ30 ብር የመሸጥ ኃጢአት እንደወጣ እንዲቀር አድርጎታል፡፡ /ማቴ 26፥14-29 ፤ ማቴ 27፥3-9 ተመልክት/ ሥጋና ደሙ ግሩም ፍዳ የሚያመጣ ነው የሚባለው ስለዚህ ነው፡ ስለዚህ በንጽሕና በትሕትና ንስሐ ገብቶ ሊቀበሉት ይገባል። በዚህ መልኩ ለሚቀበለው የዘላለም ሕይወትን የሚያወርስ ጥበብን የሚገልጽ ምስጢርን ኹሉ የሚያድል ነው። ለዚህም ነው ካህኑ በቅዳሴ ሰዓት “ንጹህ የሆነ ከቁርባኑ ይቀበል ንጹሕ ያያልሆነ ግን አይቀበል ለሰይጣንና ለመልእክተኞቹ በተዘጋጀው በመለኮት እሳት እንዳይቃጠል በልቡናው ቂምን የያዘ ልዩ አሳብም ያለበት ቢኖር አይቅረብ እጁን ከአፍአዊ ደም ንጹሕ እንዳደረግሁ እንዲሁም ከሁላችሁ ደም ንጹሕ ነኝ። ደፍራችሁ ወደ ክርስቶስ ሥጋና ደም ብትቀርቡ ከእርሱ ለመቀበላችሁ መተላለፍ የለብኝም በደላችሁ በራሳችሁ ይመለሳል እንጂ። በንጽሕና ሆናችሁ ባትቀርቡ እኔ ከበደላችሁ ንጹሕ ነኝ» ብሎ እጁን የሚታጠበው፡። ዲያቆኑም ተቀብሎ «ይህን የቄሱን ቃል ያቃለለ ወይም የሳቀና የተነጋገረ ወይም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በክፋት የቆመ ቢኖር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳሳዘነው በእርሱም እንደተነሣሣ ይወቅ ይረዳ ስለበረከት ፋንታ መርገምን ስለ ሓጢአት ሥርየት ፋንታ ገሃነመ እሳትን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል» ይላል። ይህ አዋጅ የሚታወጀው ከክርስቶስ ሥጋና ደም ርቀን እንድንቆም ወይም የበይ ተመልካቾች አንድንኾን በኋላ ነው፤
፨ ባለትዳር የኾኑ ከኾነ ከቁርባን በፊት 3 ቀናትን ከቁርባን በኋላ 2 ቀናትን ከሩካቤ ሥጋ መከልከል አለባቸው፤
፨ ቢያንስ 18 ሰዓታትን ከመቀበላቸው በፊት መጾም፣
፨ ወንድ ዝንየት (ሕልመ ሌሊት) ሴት የወር አበባ ባገኛቸው ጊዜ ስለሥጋና ደሙ ክብር ከምስጢሩ አይካፈሉም፣፤
፨ ማንኛውም ፈሳሽ የሚወጣባቸው ደም የሚፈሳቸው ሰዎች አይሳተፉም፣
፨ ቅዳሴው ከተጀመረ በኋላ የደረሰ ሰው ከቁርባኑ አይሳተፍም
፨ ከቁተርባን በኋላ ጥፍር መቁረጥ፣ ጸጉርን መላጨት፣ ረዥም መንገድ መጓዝ፤ ፍርድ ቤት መከራከር፣ ከልብስ መራቆት፣ በውኃ መታጠብ አይፈቀድም፣፤
፨ ለቁርባን የለበሱትን ልብስ ለአንድ ቀን ያህል አለማውለቅ፣
፨ ከቁርባን በኋላ መስገድ እና ላብ የሚስወጣ ሥራን መሥራት አስይፈቀድም፤
ከቁርባን በፊትም ኾነ በኋላ ቀለል ያሉ ምግቦችን መመገብ፣
፨ በቁርባን ጊዜ ንጹሕ ኾኖ መገኘት ንጹሕ ልብስ መልበስ ቢቻል ሙሉ ነጭ ልብስ መልበስ፣
ስለዚህ ይህን እና የመሠለውን ጥንቃቄ በማድረግ መቀረብ እንጂ የጠላት ከይሲን ምክር ሰምተህ ከዚህ ተግባር እንዳትርቅ እመክርሃለሁ፡፡
ይቆየን
ምንጭ፦ “ለምን ርቀህ ቆምህ?” መጽሐፍ
በ ዲያቆን መልካሙ በየነ
2014
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን ላይ ያገኛሉ፦ Yohannesneseha.org/ጥያቄና-መልስ
👉ጥያቄ፦ #ንሰሐ ቶሎ ቶሎ እየገባን ከኖርን #ቅዱስ #ቁርባን እንደተቀበልን ይቆጠራል ወይ?
✍መልስ፦ ጠያቂያችን ፤ የሰው ልጅ ለመዳን የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ነገሮች ማመን፣ መጠመቅ እና ሥጋውንና ደሙን መቀበል፣ ለሕግጋተ እግዚአብሔር ተገዢ መሆን ናቸው። ያለ እነዚህ ነገሮች ድኅነት አለመኖሩን ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነግሮናል። ለመዳን እስከመጨረሻ ሕቅታ በሃይማኖት መጽናት የግድ ነው። መዳን የአንድ ጀምበር ተግባር አይደለምና። እስከመጨረሻ መጽናትም ስንል በስመ ክርስትና ብቻ አይደለም በመንፈሳወዊ ሕይወታችን በየጥቂቱ እያደግን ፈቃደ ሥጋን እየተዋጋን በመንፈሳዊ አገልግሎት እየተጋን ብንወድቅ እንኳ በንስሓ ታጥበን በሥጋውና ደሙ ልጅነታችንን እያደስን እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ መጽናት ይገባናል።
“ያላመነ ይፈረድበታል” (ማር 16፥16) ፣ “ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም” (ዮሐ 3፥5) “የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም” (ዮሐ 6፥56) ወዘተ የሚሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሎች ያለእነዚህ የድኅነት መንገዶች መንግሥተ ሰማያትን መውረስ አለመቻሉን የሚያስገነዝቡን ናቸው። በመሆኑም ሁሉም በየደረጃቸው ለክርስትና ህይወታችን እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚ እንደሆኑ በቅዱስ መፅሐፍ ተነግሮናል።
የንስኀ ዋናው ጥቅም እውነተኛ ክርስቲያን የሰራውን ከባድ ኀጢአት ይሰረይለት ዘንድ የሚቀበለው የቀኖና ስርዓት ነው። በብሉይ ኪዳንም ሆነ በአዲስ ኪዳን ያመኑ ሰዎች ወደ ፈጣሪያቸዉ ቀርበው ምን እናድርግ ብለው ሲጠይቁ የመጀመሪያው ትዕዛዝ ንስኀ ግቡና በፍጹም ልብና በፍጹም እምነት ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ የሚል ነው። ስለዚህ የኀጢአት ነውር እስካለብን ድረስ ለእውነተኛ ክርስቲያን ንስኀ አስፈላጊ ነው። ንስሐ እንደ አስፈላጊነቱ ማለትም በኅጢአት በወደቅን ቁጥር የሚደገም ምስጢር ነው ሲባል ከአቅም በላይ ፈተና ገጥሞን ብንወድቅ በንስሐ መነሳት እንችላለን ነገር ግን ኅጢአትን ለመተው ቁርጠኝነቱ ሊኖረን ይገባል ለማለት እንጂ የተቀደሰውን ህይወታችንን እና ማንነታችንን ገና ለገና ንስሐ አለ እያልን በየጊዜው በኅጢአት የምንወድቅበት ወይም ኅጢአት ለመስራት አቅደን ታጥቦ ጭቃ የምንሆንበት ህይወት ሊሆን አይገባም። በአንጻሩ ኀጢአት የማይሰራ ሰው እራሱን በቅድስና ጠብቆ ለሚኖር ሰው ንስኀ ሊያስፈልገው አይችልም። ንስሐ እና ቅዱስ ቁርባንን በማነፃፀር ንስኀ ቶሎ ቶሎ ከገባን እንደ ቅዱስ ቁርባን ይቆጠርልናል የሚለው አባባል ግን ትክክል አይደለም፤ አንችልምም።
በመሰረቱ ማንኛውም ክርስቲያን በ40 ቀን በ80 ቀን በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጅነት ከተቀበሉ ጀምሮ ከቅዱስ ቁርባን እንዲለዩ አይፈቀድላቸውም። ምክንያቱም ቅዱስ ቁርባን ዘለዓለማዊ ህይወት የምናገኝበት ፣መንፈሳዊ ህይወታችንን የምናስተካክልበት፣ ተመልሰን ወደ ኋላ ምንም አይነት የኀጢአት ነውር ላለመስራት ቃል የምንገባበት፣ ከብዙ የሥጋ ተግባር የምንርቅበትና ነፍሳችንን ደግሞ ለዘላለማዊ ህይወት የምናበቃበት የምስጢራት መደምደሚያና ትልቁ አላማችን ነው። በመሆኑም ቅዱስ ቍርባን የእግዚአብሔር ልጅነት ኑሮት በሃይማኖትና በምግባር ለሚኖር ከቤተክርስቲያን አባቶች ጀምሮ እስከ ምዕመናን ድረስ ቅዱስ ቁርባንን መቀበል የመንፈሳዊ ህይወታችን ማሰሪያ ማህተም ነው።
በአጠቃላይ ንስሐ ገብተን ሥጋውን በልተን ደሙን ጠጥተን የስሙ ቀዳሽ የመንግስቱ ወራሽ ለመሆን ነው ዋናው ተስፋችን። በመሆኑም ጠያቂዎችን በዚህ መሰረት ሃሳቡን ተረድተው ከንሰኀ ህይወትና ከቅዱስ ቁርባን ጋር ሊኖሮት የሚገባውን ህብረት በዚህ በላክንልዎት መንፈሳዊ ምክር ያስተካክሉ እንዲሁም በቤተክርስቲያናችን ቀኖና ስለ ንስኀ ህይወትና ስለ ቅዱስ ቁርባን አፈፃፀም ምን ማድረግ እንዳለብን የተደነገገው ትምህርቱ በድረገጻችን በስፋት ስለሚገኝ እሱንም ተመልክተው ይማሩበት ዘንድ አደራ እንላለን።
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾 ለ #ቅዱስ #ቁርባን ስለሚደረግ #ጥንቃቄ
👉ጥያቄ፡- እሁድ፣ እሁድ ቁርባን እቀበላለሁ፣ ዛሬ ግን ከእህቴ ጋር ተጨቃጭቀን ስናደድ ኃይለ ቃል ተናገርኳት፣ ሰደብኳት እና ካለፈ በኋላ ግን ቆጨኝ፤ የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን፣ ክቡር ደሙን የምቀበልበት አፌ ክፉ ተናገርኩኝ፣ ንስሐ ሳልገባ ቅዱስ ቁርባን መቀበል አለብኝ?
መልስ፡- ጠያቂያችን ከጥቄያቸው እንደምንረዳው ጠንቃቃ የቤተክርስቲያን ልጅ ናቸው፡፡ በየሳምንቱ እሁድ እሁድ የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን፣ ክቡር ደሙን በምቀበልበት አንደበቴ ይሔንን መናገሬ፣ ከተቀደሰው ነገር ሊያገልልኝ ወይም ሊያርቀኝ ይችላል ያሉት፣ እንደዚህ ያለ አስተዋይ ልቦና ስለ ጥቃቅን ጥፋታችን ቶሎ መለስ ብለን አስበን፣ ያደረግነውን፣ የሠራነውን፣ የተናገርነውን ሁሉ ገምግመን፣ ከትንሽ ወደ ትልቅ፣ ከትልቅ ደግሞ ወደ ባሰ ጥፋት እንዳንሄድ ማለት ነው፡፡
ዛሬ ትንንሽ የሆኑ ጥፋቶቻን ነገ በጣም ተራራ ያክላሉ፡፡ አሁን ከቤተሰብ ጋር መሳደብ፣ መጨቃጨቅ፣ የማይገባ ነገር ሁሉ መነጋገር የተለመደ ነው፡፡ ፈቃድ ያለው ሕጋዊ ሥራ አድርገን ሁሉ እናስበዋለን፣ እህትን መስደብ፣ ወንድምን መስደብ፣ አልፎ ተርፎ እናትን፣ አባትን መገላመጥ፣ አበዛኸው፣ አበዛሽው በሚል ንግግር የተለመደ ሆኗል፡፡
ካህናት፣ እኛ አስተማሪዎች ነን የምንል ሰዎች ራሳችን በቤተሰባችን በአኗኗራችን ሁሉ ይሔን ነገር እንደ ጥፋት ቆጥረን፣ ነውር እኮ ነው፣ ይሔ እኮ የትልቁ ኃጢያት የመጀመሪያው ዋዜማው ነው፣ ብለን መክረን አናውቅም፡፡ “በእንቁላሉ በቀጣሽኝ” ይላሉ አባቶቻችን፣ እናቶቻችን በሕጻንነቱ ሐይ ሳይባል ያደገ፣ ባለጌ አፍ መጨረሻ የሚቀፈውን፣ የሚያሳቅቀውን፣ የሚያሳፍረውን፣ ከዚያም ቀጥሎ ጥፋት የሚያመጣውን፣ ጠብ የሚያመጣውን፣ ስድብ፣ ወይም ደግሞ ባለጌነት የሚፈጽመውን ሰው በሕፃንነቱ ካልቀጣነው፣የአካል ሕጻንነት አይደለም፡፡
በአፋችን የሚወጣው ነገር ሁሉ ስንጀምረው፣ ሳንለማመደው እርም ማለት ነው፡፡ ትልቅ ኃጢያተኛ መሆን ይቻላልና ፣ ምላስ እኮ ነው ዓለምን የሚያተራምስ፣ ነው፡፡ “ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ምላስ ሰደድ እሳት ነች ይላል”፡፡ በየሰፈሩ፣በየአካባቢው ለከባድ ፀብ፣ ዋጋ ለሚያከፍል ፀብ ሁሉ የሚያበቃን ምላሳችን ነው፡፡ እንዳሉትም መናገር ነው ምላስ የምንለው፣ ከአንደበት ከወጣ በኋላ ትንታግ ነው፣ ቦምብ ነው፡፡
መልካም ነገርም፣ ከአፋችን ሲወጣ፣ ለፅድቅ ያበቃል ፣ ክፉ ነገርም እንደዚሁ፡፡ ስለዚህ እንዳሉት በጣም መታረም ያለበት፣አርም ብለን ከዚህ መራቅ ያለብን ነው፣ ማንንም ሰው ቢሆን ዝቅ አድርጎ ያልተገባ ነገር መናገርን ብንተወው፣ ብንታገሰው፣ የምንከበረው እኮ እኛ ነን፣ የሕሊና እርካታ የሚበዛልን ለእኛ ነው፡፡ ምን ያደርግልናል? እንኳን እህት፣ ወንድም ይቅርና ሌላውንም ጠላት የምንለው ሰው ቢሆን ብንተወውስ፣ ብናልፈውስ፣ በትዕግሥታችሁ ፀጥ፣ ረጭ ብላችሁ፣ በአርምሞ፣ በማስተዋል፣ በምታልፉት ፣ በምትቀበሉት ነገር፣ በሰማይ የነፍሳችሁን ዋጋ ታገኛላችሁ፡፡
ለነፍሳችሁ የሚጠቅመውን ነገር ሁሉ ትረከባላችሁ፣ በመሳደብ ፣ በጠብ ፣በክርክር፣ በጭቅጭቅ፣ በስድብ ወደ መንግሥተ ሰማያት የገባ ሰው የለም፡፡ የሆኖ ሆኖ ግን ጠያቂያችን የእርስዎ ጥያቄና፣ የእርስዎ ገጠመኝ ያሉትን ሐሳብ፣ ከእህትዎ ጋር የተጋጩትን ግጭት ግን ለንስሐ ሕይወት የሚያበቃ አይደለም፡፡ ይሔ ምክሩ በቂ ነው፡፡ ከቻሉ ታላቅ ትሁን፣ ታናሽ፣ እርስዎም በምን የእድሜ ደረጃ እንዳሉ አልገለፁልንም፡፡ ስለዚህ እህቴ እንዲህ በማለቴ ይቅርታ፣ እንዲህ ብዬ ለመናገር ስሜት ውስጥ እንድገባ የሚያደርግ ነገር አንጠቀም፣ አንቺም አትጠቀሚ፣ እኔም አልጠቀምም፣ መጀመሪያ ለዚህ ስድብ ያበቃን መነሻ ሐሳብ አለና፣ አሱን ወደፊት እናርመው ብሎ መነጋገር፡፡ ይሔ በቂ ነው ለንስሐ ሕይወት፣ እንጂ መደበኛ ኃጢያት አድርገን ወደ ንስሐ አባት የምንሔድበት አይደለም ፡፡ ምክንያቱም ጥግ ድረስ የደረሰ ብዙ የሰዎች ክፋት አለና!!
ያንን እግዚአብሔር ቢፈቅድልን እሱን፣ እሱን ብናስተካክል፣ እርስዎም እንዳሉት፣ ዛሬ እህቴን፣ ወንድሜን፣ ባለቤቴን፣ እናት አባቴን፣ ማንጓገጠጥ መስደብ፣ ማዋረድ የእኔ መብት ነው ብለን የጀመርነው ይሔ የስድብ መንፈስ አድጎ፣ አድጎ እኛንም፣ ሌሎቹን ሰዎችም፣ ወገኖቻችን ሁሉ የሚጨምር፣ የሚያስጠይቅ፣ ዋጋ የሚያስከፍል ኃጢያት እንሠራበታለን፡፡ ወይም ደግሞ የመጨረሻ በሕግም የሚያስጠይቅ ጥፋት ሆኖ፣ በሕይወትም አድጎ እንዳይጎዳን ከአሁኑ እንዳሉትም እንደዚህ መቆርቆር ነው፣ ሌሎቹ ይሕንን እንደ ጥፋት ስለማይቆጥሩት ነው፣ ለሌሎቹ ይጠቅማል፡፡ እርስዎ ግን እግዚአብሔር ስላልተለየዎት እናመሰግናለን፡፡
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን
ለተጨማሪ ግንዛቤ ስለ #ስድብ መንፈስ ያስተላለፍናቸውን መልእክቶች እንዲመለከቱ ሊንኮቹን እንደሚከተለው አያይዘናል👇👇👇
https://t.me/c/1172495782/31255
https://t.me/c/1172495782/30473
https://t.me/c/1172495782/29211
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ ፦ እኔና ባለቤቴ #ቅዱስ #ቁርባን ተቀብለናል፤ አሁን መጠየቅ የፈለኩት ጥያቄ ለመቁረብ ተዘጋጅተን ለንስሐ አባታችን የሚያደርሱልን ጸሎት ወይም የሚያዙን ነገር አለወይ ብለን ያደረግነውን ነገር ነግረን #ንስሐ እንዲሰጡን ስንጠይቃቸው፤ ካላቸው እምነትና ፍቅር የተነሳ ለመቁረብ መቅረባችንም ደስ እያላቸው ችግር እንደሌለው ስለሚነግሩን እንቀበላለን፤ እኔ ግን ስለምፈራ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማኛልና ምን ማድረግ አለብን?
መልስ፦ ጠያቂያችን እግዚአብሔር ስለፈቀደላቸው ሁለቱም በህገ ጋብቻ ተወስነው እየኖሩ የክርስቶስን ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለዋል በየጊዜው ደግሞ ወደ ቅዱስ ስጋው ሲቀርቡ የራሳቸውን ንጽሐ ጠባይ እንዳያድፍባቸውና ከእሱ ከክርስቶስ ቅዱስ ስጋና ክቡር ደም የከበረ ሌላ ምንም ነገር የለም ልናከብረውም ልንፈራውም የምንችለው የእሱ ክቡር ደሙ ቅዱስ ስጋው ስለሆነ እኚህ በየጊዜው ወደ ቅዱስ ቁርባን ሲቀርቡ ለነፍሳቸው እረኛ ሆነው፥ አባት እና አስተማሪ ሆነው የተሾሙትን የንስሐ አባታቸውን እንደሚያናግሩና በዚህም ነገር ደስ እያላቸው ያለምንም መፍራት እንዲቀበሉ ሁሉ እንደሚያደርጓቸው ፤ እና ምናልባት ሳናውቅም አውቀንም እግዚአብሔርን ያስቀየምነው ያሳዘንነው ወይም ደግሞ ለቅዱስ ቁርባን በየጊዜው ስንዘጋጅ ማድረግ ያለብን የንስሐ ህይወት ካለ የሚል ነው ጥያቄያቸው።
ጠያቂያችን ይሄን ያህል ትኩረት ሰጥቶና ይሄን ያህል ሰውነታችን ከኀጢአት ለመጠበቅ ማሰቡ ክርስቲያናዊ ጠባይ ነው። እንዲህ አይነት ምእመናን በእግዚአብሔር ዘንድ ህይወታቸው ሁሉ የተወደደ እና በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚመራ እንደሆነ ሁላችንም ልናውቀው ይገባል። በመሰረቱ ከቅዱስ ቁርባን የበለጠ የምናከብረው የምንፈራውም ነገር መኖር የለበትም። የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው። እርሱ የሰጠን የራሱን ስጋ የራሱን ደም እንኩ ብሉ ጠጡ ብሎ ሲሰጠን፥ እንደው የሚበላ የሚጠጣ ነገር ያፋቅራል፣ አብሮ ያኖራል፣ ያቀራርባል ሁሉም በህብረት በሰላም በፍቅር እንዲኖሩ ያዋህዳል እና በዚህ በሚበላና በሚጠጣ ነገር ስለተጠራ ብቻ እሱን ከቶ እንደቀላል ነገር ልንደፍረው ልንቆጥረው የማንችል ለአመፀኞች የሚባላ እሳት ለሚገባቸውና በንስሐ ህይወት ተዘጋጅተው ለቀረቡት ደግሞ ዘለዓለማዊ ህይወትን የሚያድል ስለሆነ፤ እንደው በተለመደ ቋንቋ ክርስቶስን ቅዱስ ስጋውን ብሉ ክቡር ደሙን ጠጡ ሲባል እንደ ምግበ ስጋና መጠጥ አድርገን ልንቆጥረው ከቶ የማንችል ነው።
ያም እንኳን ለስጋችን የሚያስፈልገንን ምግበ ስጋ እና መጠጥም እንኳን ደረጃውን የጠበቀ የራሱ የሆነ ክብር አለው። ስርዓት ባለው መልኩ ተዘጋጅተን ክብር ሰጥተን ነው የምንበላው የምንጠጣው። በልተነው ጠጥተነው ነገ የሚያስፈልገንን የቤታችንን ምግብ እንኳን ማለት ነው። በጨዋ ቤት በአዋቂዎች ቤት እንደ አጠቃላይም ቢሆን በኢትዮጵያዊነት እንደየ ባህላችን ስርዓት ወደ ስጋዊ ማዕድ ስንቀርብ ለራሱ የሆነ የምንሰጠው ክብር አለ። ከዚህ የተነሳ ይሄንንም እንኳን እኛው ራሳችን ያዘጋጀነውን ምግበ ስጋ ነገም ጠዋትም ማታም በልተነው የሚያስፈልገንን አዘጋጅተን አቅርበን የምንበላው ሙሉ ስልጣንና መብት ያለን የሆነውን ምግብ እንደዚህ የምናደርግ ከሆነ የነፍስ ምግብ የሆነውን በልተነው የማያስርብ ጠጥተነው የማያስጠማ ዘለዓለማዊ ህይወት የሚያሰጥ በዚህ ምድር ላይ ሳለን መንፈሳዊ እርካታ ያለው ጸጋ በረከት የሚያድል ህይወታችንን የሚያስባርክ በወዲያኛው ዓለም ደግሞ ዘለዓለማዊ ህይወት የምናገኝበት የክርስቶስ ሥጋና ደም ከሆነ፤ እንዲህ ተጨንቆ ተዘጋጅቶ ጌታ ሆይ ለእዳ ለበደል አታድርግብኝ ብሎ በልዩ ዝግጅት ቅዱስ ቁርባን መቀበል አስፈላጊ ስለሆነ ጠያቂያችን ሁሌ ራሳችሁን መጠየቅ ወደ ራሳችሁ ህይወት ተመልክታችሁ እኛ ማን ነን ማለት ኀጢአትን መናዘዝና አባትን ማነጋገር ተገቢ ነውና ይህን አድርገው፥ ነገር ግን ለሁሉ ነገር መንፈሳዊ ኃላፊነት ያለባቸው አባት ደግሞ ደስ ብሏቸው እናንተን አመካክረው ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው የአባትነት ፀጋ ኃላፊነት ወስደው ቁረቡ ካሏችሁ መጨናነቅ አያስፈልግም። ሁሌ ደጋግመን እንዳልነው ከቅዱስ ቁርባን የሚያስርቅ አንዳችም ነገር የለም፤ ይሀው ደካማ ስጋችን በሚበድለው በደልና በሚፈፅመው የኃጢአት ነውር ስለሚሆን፤ ይሄንንም በየጊዜው አሁን እንደተባለው የዋለው አይደርብን ያደረው አይዋልብን እየወደቅን እየተነሳንም ቢሆን ኀጢአትን ላለመስራት መቼስ መታገል የተሻለ ማንነት የመንገልጽበት የራሳችን መንፈሳዊ ተጋድሎ ነውና፤ የደከምንበት ኀጢአት ካለ እሱን እያስወገድን መሄድ እንጂ በዚህ በማመካኘትና በዚህ ሽፋን ወደ በራሳችን ፈቃድ ዘላለማዊ ህይወት ከምናገኝበት ከቅዱስ ቁርባን መራቅ የለብንም በማለት ይህን አጭር መልዕክት እንዲደርስዎ አድርገናል።
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንም ሼር ያድርጉ፡- https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾ስለ #ቅዱስ #ቁርባን #ንስሐ እና የ #ሀጢያት #ስርየት
👉ጥያቄ፡- ንስሐ የገባ ሰው ቅዱስ ሥጋውን፣ ክቡር ደሙን ባይቀበል ኃጢያትቱ ይሠረያል? ወይስ አይሠረይም?
መልስ፡- ጠያቂያችን ፤ አንድ ሰው በትክክለኛ ንስሐ ገብቶ፣ ቀኖና ተቀብሎ ከኃጢያት ርቋል፣ ፈቃደ ሥጋውን ለፈቃደ ነፍሱ አስገዝቷል ፣ በፍፁም ክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወት ራሱን ለእግዚአብሔር አስገዝቷል፣ አካሄዱም ከእግዚአብሔር ጋር ነው፣ እሱማ ፍፁም መንፈሳዊ ሆኗል፣ እሱማ ታላቅ ሰው ሆኗል ብለን በክርስትና ሕይወት ውስጥ የምናቀው መንፈሳዊ ሰው በትክክለኛ አነጋገር ይህ የእግዚአብሔር ሰው የተባለው ምዕመን ወይም የተባለው ክርስቲያን የንስሐ ሕይወቱን ፣ የንስሐ ቀኖናውን በቅዱስ ቁርባን ከደመደመው ነው፡፡ የመጨረሻው ማሠሪያ ቅዱስ ቁርባን ነው፡፡
በቀኖናው ትዕዛዝ መሠረት እስከ አሁን ድረስ ከመንፈሳዊ ሕይወት ወጥቶ በአርባ ቀንና፣ በሠማኒያ ቀን የተገኘውን ልጅነት በኃጢያት እያረከሱ ከቅዱስ ቁርባንም ተለይቶ ፣ በአጠቃላይ ከመንፈሳዊ እና ከኃይማኖታዊ ትዕዛዝም ወጥቶ፣ እንዲያው በዘፈቀደ ኃይማኖት የሌላቸው የፈለጉትን፣ ያዩትን ሁሉ በማድረግ ከሚኖሩት ማኅበር ውስጥ ተደምሮ የቆየ ሰው እንኳንስ በነፍስ ጉዳይ ይቅርና፣ በሥጋዊ ሕይወቱ እንኳን አስፀያፊ በሆነ ምግባር የኖረ ሰው፣ የመጀመሪያው ነገር ተመልሷል የምንለው፣ ተጸጽቷል የምንለው፣ ወደ እግዚአብሔር ቀርቧል የምንለው ስለሠራው ኃጢያት ከልቡ በመፀፀት በፍፁም እምነት ወደ ካሕኑ ሄዶ አንድም ሳይቀር የሠራውን ጥፋት ሁሉ፣ የሠራውን ኃጢያት ሁሉ ተናዝዞ፣ በበደሉ ልክ ለኃጢያቱ የበደል ካሣ እንዲሆነው ካሕኑ ይህንን አድርግ ብለው የንስሐ ቀኖና ይሰጡታል፡፡ ቀኖናው በፆም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በሌላም መታዘዝ ነው፡፡ ሁሉንም እንደ ትዕዛዙ ይፈፅማል፡፡ ያውም ከልቡ እየተፀፀተ፣ እያለቀሰ፣ እያነባ፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እየጠየቀ፣ ጌታ ሆይ ይቅር ይበለኝ እያለ፡፡ በእሱ አቅም በሚያደርገው፣ በሚታዘዘው የንስሐ ቀኖና እግዚአብሔር ደግሞ ያንን ያክል ዘመን የፈፀመውን በደሉን ኃጢያቱን በቸርነቱና፣ በምሕረቱ ልጄ ሆይ ከልብ ተመልስህ፣ ከተፀፀተክ፣ ካለቀስክ ይቅር ብዬሃለሁ ከበደልህ፣ ከኃጢያትህ ሁሉ አንፅቼኃለሁ፣ ኃጥያትክን አስተሠርየዋለሁ፣ ደምስሼዋለሁ፣ ሁለተኛ ግን እንዳትበድል፣ በፍፁም ልብህ ወደእኔ በመመለስህ ደስ ብሎኛል ይላል እግዚአብሔር፡፡
በወንጌል እንደተነገረን ያ ከአባቱ ቤት በጥጋብ ምክንያት በደል ፈፅሞ የጠፋው ልጅ፣ ያ የነበረው ፀጋው ተገፎ፣ ባዶውን ሆኖ፣ እርቃኑን ሆኖ፣ የሚበላው የሚጠጣው አጥቶ፣ ከችግሩ ጽናት የተነሣ አሠርና ገሠሥ፣ ገለባና ሣር ከሚበሉ የዱር አራዊት ጋር ሁሉ ሳይቀር የተጋፋው የጥፋት ልጅ በመጨረሻው ሰዓት ተፀፅቶ ወደ አባቱ ቤት ተመልሶ ይቅርታ በጠየቀ ጊዜ አባትየው የጠፋው ልጄ ተገኝቷል ብሎ በእሱ መገኘት ምን ያህል ደስታ እንደሆነ፣ ምንዓይነት ዝግጅት እንደተደረገ፣ ዘመዶቹ፣ ጎረቤቶቹ ሁሉ በዚህ ልጅ መገኘት ደስ እንዲላቸው ወደ እዚያው እንደታደሙ ይነግረናል ወንጌሉ፡፡ ያ ምን ማለት ነው የጠፋው የሰው ልጅ ነው፣ ወይም አዳም ነው፣ ወይም እኛ ነን፡ የእኛ ደግሞ አባታችን እግዚአብሔር ነው፡፡
ስለዚህ ወደ ንስሐ ሕይወት ስንመለስ እንዴት አድርጎ ደስ ብሎት እግዚአብሔር እንደሚቀበለን ያሳያል ቃሉ፡፡ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር ይቅር የማይለው ኃጢያት የለም ማለት ነው፡፡ እና ጠያቂያችን የመጀመሪያው አንድ ሰው ኃጢያተኛ በደለኛ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር ተመልሷል ማለት የሚሰጠውን ቀኖና በሥርዓት መፈፀም ሲችል ከልብ በዓይኑ ባያየውም፣ በእጁ ባይዳስሰውም የኃጢያት ሥርየት አግኝቷል፡፡ ግን ይህንን በቀኖና ያስፋቀውን ኃጢያቱን ወደ ፊት ዳግመኛ ላያደርገው፣ ላይመለስ ወደእዚያ ወደ ጥፋት የመጨረሻው የቃል ኪዳኑ ስምምነት ውሉ የሚታሰርበት በቅዱስ ቁርባን ነው፡፡ እነዚህ ሁለቱ አብረው የሚሄዱ ነገሮች ናቸው እንጂ ከዚያ በኋላ አንድ ሰው በጎነትም ኖሮት፣ የንስሐ ሕይወትም ኖሮት፣ ሥጋወደሙ ሳይቀበል መቅረት ይኼ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አይደለም በፍፁም፡፡ ይኼማ ጥፋታችን ነው፡፡ እግዚአብሔርማ በቸርነቱ ቤተ ክርስቲያን ሳታስተምር፣ የንስሐ አባቶች ወይም ደግሞ የቤተክርስቲያን መምሕራን ሳያስተምሩት፣ ለሕዝቡ ሳይነግሩት፣ ስለቅዱስ ቁርባን የጠለቀ እውቀት ሳይኖረው፣ በልማድ ቤተክርስቲያን እየተመላለሰ እኛ የምናውቀው ብዙ በጎ ሥራም እያለው አንድ ሰው በሞት ቢለይ የማጽደቅ፣ የመኮነን የእግዚአብሔር ባሕርይ ስለሆነ በዚህ ጣልቃ አንገባም፡፡ እንደ ሕጉና እንደ ትዕዛዙ ግን ንስሐ መቀበል ራሱን የቻለ ሕገ እግዚአብሔር ነው፣ ትዕዛዝ ነው፣ ቅዱስ ቁርባንም ከሁሉ የሚበልጥ ትዕዛዝ ነው ማንኛውም ክርስቲያን ሥጋዬን ብሉ፣ ደሜን ጠጡ ይኼ የጌታ ቃል ነው፡፡ ስለዚህ በአስተያየት አንድ ሰው ንስሐ ከገባ ቅዱስ ቁርባን ባይቀበል ኃጢያቱ ተሠረየ ማለት ይቻላል ወይ? ብለን በአስተያየት ውስጥ ገብተን የምንተቸው ነገር አይደለም፡፡ ለአንድ ክርስቲያን ቋሚ ህግ ነው ይኼን ሁልጊዜ ለሁላችንም ዘንድ ትዕዛዘ እግዚአብሔር አድርገን፣ ሕገ እግዚአብሔር አድርገን፣ መንፈሳዊ መብትም ግዴታም አድርገን ማየት አለብን፡፡ የመጀመሪያው ነገር ኃጢያት እንዳንሠራ ፈፅሞ መጠንቀቅ፣ ከሠራን ደግሞ የንስሐ ቀኖና ተቀብለን ለእያንዳንዱ በደላችን ከልብ ተፀፅተን እግዚአብሔር ይቅር እንዲለን ቀኖናችንን መፈጸም፣ ሁለተኛው ትዕዛዝ ነው፡፡ በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ለሁሉ ነገር መደምደሚያ የሆነውን ገና በአርባ፣ በሰማኒያ ቀን የተሰጠንን በጎ ዕድል ወይም የክርስትናችን ዋና ማኅተም የሆነውን ቅዱስ ቁርባን መቀበል፡፡ እነዚህ ተለያይተው የሚፈፀሙ ሚስጢራት አይደሉምና ይኼን ማየት አለብን፡፡ ከዚያ ውጪ ከሕጉ፣ ከትዕዛዙ ፈቀቅ ብሎ፣ ንስሐ ገብቷል፣ ነገር ግን ሥጋ ወደሙን አልተቀበለም፣ ስለዚህ ንስሐ ስለገባ ሥጋወደሙ ባይቀበልም ኃጢያቱ ይሠረያል፣ አይሠረይም ይኼ የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፡፡ ሕጉ ግን ያለን ንስሐም እንድንገባ፣ ቅዱስ ቁርባንም እንድንቀበል ነውና ይኼንን ሕግ ነው በሥርዓት የምናየው፡፡
የመከረን፣ የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፡- አንድ ጥያቄ ነበረኝ፤ አሱም ከቤተሰብ ጋር አብረን #ንስሐ ተቀብለን ነበርና፤ቀኖና ከጨረስን በኋላ እኔና እህቴ #ቅዱስ #ቁርባን ለመቀበል አስበን ነበር፡፡ ነገር ግን የንስሐ አባታችን ይህ አይሆንም፤ እድላችሁን አልዘጋም፣ በኋላ የቆረበ ሰው ካልሆነ #ትዳር መያዝ አትችሉም ብለው ከለከሉን ምን ማድረግ አለብን?
መልስ፦ ጥያቄው በአጭሩ ቤተሰቡ አጠቃላይ የንስሐ ቀኖና እንደተቀበሉና፤ ከቀኖናቸው ፍፃሜ በኋላ የክርስቶስን ሥጋውንና ደሙን ለመቀበል ቢዘጋጁም ልጆች ናችሁና እናንተ መቀበል አትችሉም ፤፡ እድላችሁን በዚህ እድሜያችሁ አልዘጋም፣ ብለው የንስሐ አባታችን ከለከሉን የሚል ነው፡፡ ምንናልባት ጠያቂያችን ጥያቄውን ሲያብራሩ ያልተሟላ ሐሳብ ወይም የቀረ ሐሳብ ካላ እንደገና ማስተካከል ይችላሉ፡፡ነገር ግን እኛ በገባን፤ የቆረበ ካልሆነ ማግባት አይችሉምና እንዴት ይሆናል ? ለሚለው ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተንበታልና አንብበው ይረዱት።
ስለቅዱስ ቁርባን አስፈላጊነትም ሆነ እኛ በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በእርሱ ደግሞ “በወልድ ውሉድ” ተብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንባል ዘንድ የአባትነቱን ፀጋ የሰጠን እግዚአብሔር ገና በአርባ (40) ቀን እና በሠማኒያ (80) ቀን ክርስትና ተነስተን በቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ታትመን የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንንበት ጊዜ ጀምሮ፤ ማንም ኦሮቶዶክሳዊ የተዋሕዶ ልጅ ክርስቲያን ሁሉ ከቅዱስ ቁርባን መለየት የለበትም፡፡ ከቅዱስ ቁርባን የሚለየንና የሚያርቀን እራሳችን ወደን ፈቅደን የምንሠራው ኃጢያታችን፤ በደለኛነታችን፣ ወንጀለኛነታችን ካልሆነ በስተቀር ማንም አይከለክለንም፡፡ በሕፃንነት እድሜያችንም፣ አካለ መጠን በደረስንም ጊዜ፣ ከጋብቻ በፊትም፣ በጋብቻ ጊዜም፣ ከጋብቻ በኋላም ሰው ያለ ምገበ ሥጋ ሳይበላ፣ ሳይጠጣ፣ ሳይለብስ እንደማይኖር ሁሉ በሥጋው፣ በነፍሱም፣ ቅዱስ ቁርባን ሳይቀበል፣ የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን ሳይበላ፣ ክቡር ደሙን ሳይጠጣ መኖር ወይም መዳን፣ የዘላለም ሕይወት ማግኘት አይችልም፡፡ የሚያንሰውና ትንሹ ነገር ኃላፊውና ቀሪው የሥጋ ምግብ ነው፡፡ ለጊዜው ለቁመተ ሥጋ ሰው ሆነን በአጥንት፣ በጅማት፣ በሥጋ፣ በደም እንድንንቀሳቀስ አዳማዊ ተፈጥሮ ሆኖ እንዲህ የሚታይ፣ የሚዳሰስ፣ የሚራብ፣ የሚጠማ፣ የሚደክም፣ የሚበረታ፣ ሞት፣ ህልፈት ሁሉ በጊዜያዊነት የሚስማማው ይኼንን ሥጋ እግዚአብሔር እስከፈቀደ ጊዜ ወይም ደግሞ እስከተወሰነልን የእድሜ ገደብ ድረስ ለመቆየት ያህል ይኽንን የሥጋ ምግብ እንበላለን፣ እንጠጣለን፡፡ ከዚያ በላይ ግን፤ በልተነው የማያስርበን፣ ጠጥተነው የማያስጠማን፣ ጊዜያዊ ሳይሆን ዘለዓለማዊ፣ ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ፣ ኃላፊ ሳይሆን ለዘለዓለም የሚያኖር፣ የነፍስ ምግቧ የሆነውን ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል አንዳችም ጊዜ ልናቋርጥ የምንችልበት ጊዜ የለንም፡፡ ይኼን ነው ማወቅ ያለባችሁ፡፡
ወደ እያንዳንዳችን ዝርዝር ኃጥያት ከገባን፤ ከቅዱስ ቁርባን የሚያርቀን ኃጥያት ምንድን ነው? አንድ፣ ሁለት፣ ሦስት ብለን ኃጢያት የሆነው ነገር ሁሉ ማንም ሰው የክርስቶስን ሥጋ ሁልጊዜ መብላት፣ ደሙን መጠጣት እንዳለበት ከታዘዝነው ሐዋርያው እንደነገረን፤ እዳ እንዳይሆንባችሁ ያለን ነገር አለ፡፡ በድፍረት ሆናችሁ ማለት ነው፡፡ ምንም እዳ፣ ፍርድ እንደማያመጣ፣ እንደማያስፈርድብን፣ እንደማያስወቅሰን፣ ቅርበ ፈጣሪ እንደማያስቆመን ነገር አቃልለን፤ እንደ ሥጋ ምግብ እንዳናየው፤ ከእኛ የሚጠበቀው መጠንቀቅ አለብን፡፡ ሌላውን የሚበልጠውንና ብዙውን በእርሱ ቸርነት የሚያነፃን፣ የሚቀድስን ሥጋውና ደሙ ነው፡፡ ግን ወደዚህ ከሁሉ ወደ ከበረው በታቦተ ምስዋዑ ላይ በንፅሕና፣ በቅድስና ሆነው ካሕናት አክብረውት እንካችሁ ይኼ አማናዊ የክርስቶስ ሥጋው ነው፣ አማናዊ የክርስቶስ ደሙ ነው ከዚህ ብሉና ጠጡ፤ የዘላለም ሕይወት እንድታገኙ ብለው የሚሰጡን ቅዱስ ቁርባን ከዘላለማዊ ውድቀት፣ ወይም ሞት የሚያድነን ስለሆነ፣ እኛንም ደግሞ የበለጠ የሚቀድሰን ከኃጥያታችን “ወበደሙ ያንፅኃነ፣” በደሙ ፈሳሽነት ማለት ነው፡፡ ሰው በውኃ ታጥቦ እንደሚጠራ ከእድፈቱ፣ ከኃጥያት እድፈት የሚያነፃን የክርስቶስ ደም ነው ተብሏልና፤ ከኃጥያት ለመንፃት ነው፡፡ ያስፈለገንም ለዚህ ነው፡፡ ከነፍስ ረሐብ፣ ከነፍስ እድፍ ሁሉ ሊያነፃን ሊቀድሰን የሚችል የክርስቶስ ሥጋውና ደሙ ነው፡፡
እንግዲህ ወደፊት ስለ ጋብቻ፤ የቆረበ ታገባላችሁ፣ አታገቡም ለሚለው አዎ ክርስቲያን ሁልጊዜ ማሰብ ያለበት ቋሚ ምኞቱም ሆነ እድል ፈንታው እንዲሆንለት፤ እግዚአብሔርን የሚለምነውም ያንን ከአርባ ቀን፣ ከሠማኒያ ቀን ጀምሮ ያመጣነውን ቅዱስ ቁርባን አስከብሮ ለማስቀጠል አብሮ ከእኛ ጋር በቅዱስ ቁርባን የሚወሰን ባል፣ ሚስት ለማግኘት እንድንችል እሱን ማሰብ አለብን፡፡
ያን ጊዜ ከዚያ ስንደርስ ደግሞ፤ ሌላ በተቃራኒ ይኼን የማይፈልግ የትዳር ጓደኛ ቢመጣብን ምን እናድርግ? የሚለውን በምክረ ካሕን ችግሩ ይቃለላል፡፡ ከወዲሁ አጥር አጥሮ ከማስፈራራት፣ ነገ በቅዱስ ቁርባን ተወስናችሁ ከኖራችሁ፤ ወደ ትዳር ስትመጡ የቆረበ ሰው ካልሆነ፣ ሌላ ማግባት ስለማትችሉ የተባለው፡- ስለዚህሳ ይኼን ገና ወደፊት እግዚአብሔር በራሱ ፈቃድ ስለእኛ አስቦ ከወዲሁ እንዳንቸገር ነገሮችን አመቻችቶ እንደሚሰጠን ማመን ትተን፤ ገና የዛሬ 20 ዓመት፣ የዛሬ 18 ዓመት ለአካለ መጠን ስንደርስ በሚያጋጥመን ፈተና እንዳንቸገር፤ ዛሬ ጫካ ውስጥ ገብተን ወይም ከዘላለማዊ ሕይወት ተለይተን ከነኃጥያታችን መኖር አለብን ብለን ማሰብ አያስፈልግም፡፡
ስለዚህ ምናልባት ከአባት ጋር ስትነጋገሩ፣ ከካሕን ጋር ስትነጋገሩ ተወያይታችሁ የደረሳችሁበት ሐሳብ ምን እንደሆነ ደግሞ የበለጠ ለመረዳት በውስጥ መስመራችን አግኙንና አነጋግሩን፡፡ አስፈላጊ ከሆነና ምናልባት እኒህ አባት ለእናንተ አስበው ከሆነ፣ የተቸገሩበት ሌላ እኛ ያላየነው መንገድ ካለ በእርሱ ዙሪያ ተወያይተን፤ ከዚህ የሚበልጥ ነገር የለምና ለእናንተ በጎውን ነገር፣ ቀናውን ነገር ለመምከር እንድንችል አግኝታችሁን አማክሩን፣ ምክር እንሰጣችኋለን ማለት ነው፡፡ ለጊዜው ግን ቋሚው ትምህርት ይኼው ነው፡፡ በምንም ተአምር የሰው ልጅ በሆነው ሁሉ በአርባ ቀኑም፣ በክርስትና የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ በሠማንያ ቀኗም የክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ሆና ክርስትና ከተነሣች ጊዜ ጀምሮ እንዳለመታደል ሆኖ ሠይጣን ነጥቆን በመናፍቅነት፣ በክህደት ማዕበል ተወስደን፣ ተገፍተን፣ ሠይጣን ከእግዚአብሔር መንግሥት ለይቶን ካልሆነ በስተቀር፤ የተዋሕዶ ኦርቶዶክሣዊ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከቅዱስ ቁርባን መራቅ እንደሌለበት ቋሚ የቤተክርስቲያን ትምሕርት ነው፡ይኼንን እንድታውቁ ነው፡፡ ጠያቂያችንም ብቻ ሳይሆኑ ሁላችሁም የዚህ ፕሮግራም አባላት ይኼንን ትምሕርት ደጋግመን የምንሰጠው፣ አፅንአዖት የሰጠንበትም መታወቅ ያለበት፤ መመከርም ያለበት ጉዳይ ስለሆነ ቅድሚያ የምሰጠው ነው፡፡
የመከረን ያስተማረን የገሰፀን የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን ሁላችንንም በሕይወት ይጠብቀን፡፡አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገኖትም ሼር ያድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
ቅዱስ ቁርባን እና ጸሎት
👉🏾 ስለ #ስርዓተ #ፀሎት እና ለ #ቅዱስ #ቁርባን ስለሚደረግ ጥንቃቄ የተሰጠ ማብራሪያ
👉 ጥያቄ:- ሰላም እንዴት ናችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በቀናነት ለምትሰጡን መንፈሳዊ ትምህርትና መልስ እግዚአብሔር በእድሜ በጸጋ ይጠብቅልን፣ ጥያቄ ነበረኝ፦
👉ጥያቄ1ኛ፦ አንድ ሰው በዝሙት እና በተለያዩ ኃጢአቶች ከወደቀ በስንተኛው ቀን ነው የጸሎት መጽሐፍ አንስቶ መጸለይ የሚችለው?
👉ጥያቄ 2ኛ፦ለቁርባን ለመዘጋጀት ምንምን ነገሮችን መጠንቀቅ አለበት? (በቅዳሴ ላይ ዝሙት ያለበት ሰው ቢኖር አይቅረብ) ይላል፣ ማብራሪያዎችን ብትሰጡኝ? አባቶች በጣም እየፈራሁ ነው ወደ “ሥጋ ወደሙ” ለመቅረብ
👉 ጥያቄ 3ኛ:- ከቁርባን በኋላ የተከለከሉ ነገሮች ምሳሌ ውኃ አይነካም …ለስንት ቀን? በቁርባን ጋብቻ በቅርብ ስለምፈፅም ነው ከይቅርታ ጋር አመሰግናለሁ።
✍መልስ 1ኛ፡- የሰው ልጅ መንፈሳዊ ምግቡ ጸሎት ነው፣ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኝበት ቀጥተኛ መስመር፣ ወይም መንገድ ጸሎት ነው፣ እምነት ላለው ሰው፣ የጸሎትን ጥቅም ለሚያየውና ለገባው ሰው፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኝበት ቀጥታ መስመር ጸሎት ነው፣ መንፈሳዊ ምግባችን ጤንነታችን፣ ኃይላችን ሁሉ ጸሎት ነው፡፡
መጽሐፍት የሚመክሩን በመከራም ጊዜ፣ በመራብም ጊዜ፣ በመጠማትም ጊዜ፣ ረቂቅ ጠላት በበዛብንም ጊዜ የእናንተ ትልቁ መንፈሳዊ መሳሪያችሁ፣ ሰይፋችሁ የእግዚአብሔር ቃል ነው፣ እሱም ጸሎት ነው ብለው ያስተምሩናል፣ ኃይለ አጋንንትን፣ ረቂቁን የሰይጣን ሥራ ቆራርጠን የምንጥለው በጸሎት ነው፣ እኛ በጸሎት ኃይል መጠቀም ስንጀምር በሰይፍ ተመስሎ የማይታየው ኃይል ሁሉን ድል የሚነሳ ሰይፍ በእጃችን ይዘናል ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ጸሎት በእግዚአብሔር ፊት መቆም ከሆነ፣ መንፈሳዊ ምግብ ከሆነ፣ ሰዎች ሁሉ በጸሎታቸው ጨለማውን ወደ ብርሃን፣ ሞትን ወደ ሕይወት፣ መራራውን ወደ ጣፋጭነት፣ ክፉውን ወደ በጎነት የሚቀይሩበት፣ በጸሎት ከአንበሳ መንጋጋ ወይም ከእሳት ላንቃ የዳኑ ሰዎችን አይተናል፣ እነ ሠለስቱ ደቂቅን፣ እነ ሕፃኑ ቂርቆስን ብናይ በጸሎት ነው፣ የእነ ቅድስት ኢየሉጣን ታሪክ ብናይ የእሳቱን ኃይል ያጠፋው እምነት ነው፡፡
በእምነት ሆኖ መኖር ማለት ደግሞ እግዚአብሔርን ስም መጥራት ነው፣ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ደግሞ ጸሎት ነው፣ ጸሎት ነው፣ ስለዚህ እንዲህ ዓይነት ጥንቃቄ የሚያስፈልገውን ጸሎት ጠያቂያችን እንዳሉት በስንተኛው ቀን ነው? ብለው የጠየቁት መሆን ያለበት ለመሆኑ ዝሙተኛ ሆነን የምንጸልየው ጸሎት የት ሊደርስ ነው? እውነቱን ስንነጋገር እንዲያውም ድፍረት ነው የሚሆንብን፡፡
በልማድ ሕሊናችን የሚያውቅብን፣ ሕሊናችን የሚገምትብን፣ ከእኛ ቀድመው፣ ዝሙተኛ የሆኑ፣ ዘወትር በዝሙት የሚመላለሉ፣ ሰው እንዳይፈርድባቸው ክርስቲያን ሥራ እንሠራለን የሚሉ ምናልባት እግዚአብሔር ነገ ከነገ ወዲያ ከዚያ ዝሙት ሐሳብ አንድ ቀን አውጥቷቸው ጸሎታቸው ተሰሚ አንዲሆን ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡
አንዳንድ ጊዜ በጎዎች መስለን የበጎ ሰዎችን ሥራ እየሠራን፣ ደግሞ በሌላ በኩል እግዚአብሔር የማያየን ይመስል፣ እግዚአብሔርን በዚህ ነገር የሸነገልነው ይመስል፣ ያታለልነው በሚመስል ሁኔታ ደግሞ እንዲህ ዓይነት አስነዋሪ ኃጢአት እየሠራን በድፍረት ወደ እግዚአብሔር ቤት ስንመጣ ለእኛ ክፉ ብቻ ሳይሆን የሚደርገን፣ እግዚአብሔርን ሳይቀር የደፈርን የተፈታተንን፣ የተገዳደርን ኃጢአተኛ ሰዎች ያደርገናል፡፡
በሌላ መልኩ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሄዶ ስለሠራው ኃጢአት ዘወትር እየተማፀነ፣ እያለቀሰ፣ አንቃይዶ እያደረገ፣ እየወደቀ እየተነሳ የሚጮህ ከሆነ እግዚአብሔር ደግሞ ከዚያ ከገባበት የኃጢአት ጉድጓድ፣ የኃጢአት ደዌ፣ ከዚያ ከገባበት የኃጢአት ደዌ ይወጣ ዘንድ፣ ከዚህ ነገር በቸርነቱ ሊያስበው ይችላል፣ አባቶቻችን በቅዱሳት መጻሕፍት ” ቂም ይዞ ጸሎት፣ ሳል ይዞ ስርቆት” ይላሉ፡፡
ስለዚህ ጠያቂያችን መሠረታዊው ነገር በስንት ቀን የጸሎት መጽሐፍ መንካት ይቻላል የሚለው ሳይሆን፣ ሲጀመር ምናልባት ሰውነታችን እድፍም ሆነ ቆሻሻ ስንታጠበው ሊለቅ ይችላል፣ በቀን ብዛት የቆሸሸን ልብሳችንን ወይም በዝሙት የተዳራንበትን ሰውነታችን የቆሸሸውን የጎደፈውን ነገር አሁንም ብንታጠብ ሊፀዳ ይችላል፣ ውስጣችን ቅድስናችንን፣ ነፍሳችን ያቆሸሸውን ኃጢአት ግን በንስሐ ካልታጠብነው መቸም ጊዜ ቢሆን እርኩስ ነን፣ በዚህ ኃጢአት ረክሰንበታል፡፡
ከዚያ ዝሙት ሐሳብ ወጥተን ያንንም የሠራነውን በንስሐ ታጥበን ካልጠራን እኮ እንደቆሸሽን ነው ያለነው፣ ስለዚህ ቀን ቀጠሮ የለውም፣ ወደ ንስሐ ሕይወት በድፍረት ስንመለስ ብቻ ነው፣ በድፍረት ስናደርገው የነበረውን ነገር ሳንደባበቅ፣ ከምእመናን ውጪ በመንፈሳዊ አገልግሎት ያሉ አንዳንዶቹን ሰይጣን በኃጢአት ፈትኖ ይጥላቸዋል፣እንወድቃለን ማለት ነው፡፡
ያንን ለረጅም ጊዜ የደከምንበትን የመጣንበትን መንገድ በእንዲህ ዓይነት አንድ ቀን በመጣ ፈተና፣ አንድ ቀን በመጣ ኃጢአት ከዚያ ቅድስና ቦታ፣ ከዚያ የተቀደሰ አገልግሎት መለየት ስለማንችል ምናልባት በድፍረት ልንቀርብ እንችላለን፣ ይሄ ሰው ስላደረገው በግለሰብ ኃጢአት፣ በግለሰብ ድፍረት ደግሞ ለሌሎቹ ድፍረትንና ኃጢአተኛ ሆኖ መኖርን አናለማምድም፣ እውነተኛው ነገር ይሄ ነው፣ ማንም ሰው ቢሆን የእግዚአብሔር ፊት ያለው እውነት ይሄ ነው፡፡
ሁላችንም እንደበደልን፣ ኃጢአት እንደሠራን፣ እንደዘሞትን፣ እንደዋሸን፣ እንደሰረቅን፣ ይሄን የሚመስለውን ኃጢአት ሁሉ እንደሠራን ካወቅን ቀናት አስቆጥረን፣ ነገሩን አረሳስተን ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚረሳ፣ የሚዘነጋ ነገር የለንም፣ ማንም ሳያሳስብ፣ ሳያስረዳ በሥላሴ መዝገብ ዘንድ ክፋታችን እንደ ክፋት፣ ጽድቃችን እንደ ጽድቅ ተመዝግቧል ስለዚህ በቀን ብዛት የሚረሳልን ኃጢአት የለም፣ የምናስፍቀው በንስሐ ሕይወት ብቻ ነው፡፡
ጠያቂያችን ይሄንን መረዳት አለብዎት፣ በሕግ የሚደረግ ምናልባት ከሕግ ሚስት ጋር የሚደረግ ሩካቤ ሥጋ ከሆነ እንደተባለው ወደ እግዚአብሔር ቤት ሄዶ ለመጸለይ ከሆነ በስርዓት የሚሆን፣ በቤቱ የጸሎት ቦታ ለይቶ፣ ታጥቦ የእግዚአብሔርን ስሙን መጥራት፣ ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት መገናኘት የግድ ነው፣ በባልና በሚስት የሚከለከል ጸሎት የለም፣ ዋናው መታጠብ ነው፣ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ለመሄድ ደግሞ ቢያንስ ሁለት ቀን በኋላ መሆን አለበት ማለት ነው፡፡
✍መልስ 2ኛ፡- ለቁርባን የሚዘጋጅ ሰው ከምን መጠበቅ እንዳለበትና፣ ምን ማሟላት እንዳለበት ከዚህ በፊት በቀኖና ቤተክርስቲያን የተነገረውን በተደጋጋሚ ተነጋግረናል፣ በመጀመሪያ ጊዜ ቅዱስ ቁርባን የሚቀበል አንድ ሰው የመጀመሪያው ነገር ወይም ብቻውን ሆኖ የሚኖር ከሆነ፣ ከዝሙት ሐሳብም፣ እሱን ከሚያስነቅፉ ነውሮች ሁሉ የራቀ፣ የቤተክርስቲያን አገልግሎት በማንኛውም የአገልግሎት ዘርፍ ለመመረጥ እንኳን በሥጋ ወደሙ የተወሰነ ነው፡፡
አንድ ሰው በሥጋ ወደሙ ከተወሰነ፣ ቅዱስ ቁርባን ከተቀበለ፣ ከብዙ የኃጢአት ሥራዎች ወይም የሐሰት ነገሮች ነውር ከሆነው ነገር ሁሉ መጠበቅ አለበት፣ ከባል ውጪ፣ ከሚስት ውጪ ያለው ዝሙት ክርስቲያን ሆነም በእግዚአብሔር ፊት ለመመላለስ የማያስችል ነው በዚህ የዝሙት ሐሳብ መኖር ዋናው ነው ማለት ነው፣ ስርቆትም፣ ቢሆን፣ ሐሜትም ቢሆን ጭቅጭቅም ቢሆን፣ ጥላቻም ቢሆን ነውሮች ሁሉ ቢሆኑ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ራሱን ለካህን አስመርምሮ፣ የንስሐ ቀኖና ተቀብሎ በማወቅም፣ ባለማወቅም
የሠራውን ኃጢአት ሁሉ በንስሐ
ራሱን አጥቦ፣ አጥርቶና ቀድሶ ነው መቅረብ ያለበት፣ ከዚያ በኋላ የንስሐ አባቱ አሁን ይገባሃል፣ ተዘጋጅተሃል ለቁርባን የሚያበቃ ሕይወት አለህ አሁን ቁረብ ይሉታል፣ ትልቁን ኃላፊነት የንስሐ አባት ናቸው የሚወስዱት ማለት ነው፡፡
እንደተባለው “በመጽሐፈ ቅዳሴ ዝሙት ያለበት ሰው ቢኖር በድፍረት እንዳይቀርብ ይናገራል” እውነትም ነው፣ የዝሙት ሐሳብ የሚለው ነገር ለብዙዎቻችን ከባድ ነው፣ ለመዘሞት እንድናስብ ያየነው ነገር ሳይኖርም ሰይጣን ዝም ብሎ መንፈስን በአውሎ ንፋስም ሊያመጣው ይችላል፣ እሱን ራሱን ሐሳቡ፣ የሐሳቡ ሞገድ ወደ አይምሯችን መምጣቱ የሆነ ትዝታ መፍጠሩ፣ ብዥታ መፍጠሩ አይደለም፣ እሱኑ መከላከል ነው ማለት ነው፣ ወዲያውኑ ክፉ መንፈስ ለምን ሊፈትነኝ ፈለገ? ለምን እንዲህ ዓይነት ነገር ያመጣብኛል? ብሎ በአይምሮ ማሰብ ይጠበቅብናል፡፡
ብዙ ጊዜ ሰዎች ግለወሲብ የሚሉት ሁሉ ይሄ ነው፣ ሰይጣን በአይምሯቸው ላይ አምጥቶ ይሄን ነገር ይጭንባቸዋል፣ ወዲያውኑ ቶሎ ብለው አይምሯቸውን መግዛትና ማሸነፍ አቅቷቸው ወደ ድርጊቱ ይገባሉ፣ ምንም ሳይሆን ራሳቸውን በፍትወተ ሥጋ እያቃጠሉ ማለት ነው፣ ስለዚህ ይሄንን መደበኛ የሆነውን ኃጢአት ፈፅሞ መከልከል ነው መቁረብ፡፡
ሌላው በሕጋዊ ትዳር አብረው የሚኖሩ ባለ ትዳር ከሆነ ደግሞ ቢያንስ ለሦስት ቀን መከልከል ስርዓቱ ነው፣ አብረው በአንድ አልጋ ላይ ከመተኛት ይለዩ ይለናል፣ ከዚያ በእለቱ ማለትም በሚቆርቡበት እለት ደግሞ አለመታጠብ፣ ወደ ውስጣችን፣ ማንኛውም የአካላችን ክፍል ወደ ውስጥ ውኃ እንዳይገባ፣ ደም እንዳይፈሰን፣ ነፍሳት እንዳይገቡብን፣ ልብሳችን ንፁህ እንዲሆን፣ በተጨማሪ ደግሞ ለመቁረብ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ለመሄድ አስቀድመን ከኪዳን በፊት መገኘት አለብን፣ እነዚህን ሁሉ አካትተን ማለት ነው።
ከዚህ በፊት በስፋት ያስተላለፍናቸውና በጣም ጠቃሚ የሆኑ ትምህርቶች ስላሉ ጠያቂያችን ይጠቅምዎታልና እነሱን ተከታትለው ለመረዳት ይሞክሩ፡ በቆረብን ጊዜ የአልኮል መጠጥ መጠጣት፣ መጨቃጨቅ፣ መነታረክ፣ ረጅም የሆነ መንገድ መሄድ፣ መታጠብ፣ ከልብስ ተራቁቶ እርቃን መሆን፣ በቅዱስ ቁርባን ከታተምን፣ ከከበርን በኋላ ለእኛ የማይመጥኑን ነገሮችን ሁሉ አለማድረግን ሁሉ ያካትታል፣ ቅድመ ቁርባን፣ ከቁርባን በፊትም፣ በቆረበ ጊዜም ማለት ነው፣ አንድ ቆራቢ ሰው ከቁርባን በፊት ለአስራ ስምንት ሰዓት መጾም ያስፈልጋል፡፡
ከቆረበ በኋላም ለሁለት ቀን ከሚስቱ ወይም ከባሏ ጋር መገናኘት አይፈቀድም፣ ለመቁረብ ስንዘጋጅ ትልቁ ነገር ግን በንስሐ መታጠብ ነው፣ ይኸውም ከላይ እንዳልነው ለአባታችን ዘርዝረን ነግረን አሁን መቁረብ ትችላለህ ብለው እንዲፈቅዱሉንና ኃላፊነት እንዲወስዱ ያስፈልጋል፣ ጠያቂያችን ዝሙት እየተሠራም ይቆረባል ብለው እንዳይሳሳቱ፣ ብዙ ቀን ስለቆዩ፣ ቀኑ ስለረዘመ በድፍረት እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፣ ያሰቡት በጎ ነገር ስለሆነ፣ ለሌሎቹም አስተማሪ ስለሆነ ባለን አድራሻ ያግኙን፡፡
✍መልስ 3ኛ፡- የዚህ ጥያቄዎ መልስ የሚሆነውን በሁለተኛው የጥያቄ መልስ አካተነዋል ከመቁረባችን በኋላ መጠንቀቅ ያሉብን ነገሮች ምግብ አለማብዛት፣ ከአንደበታችን ከፉ እንዳይወጣ፣ መጠንቀቅ፣ እንደዚሁም የቆረቡ እለት እስከ ማታ ድረስ ባለው ጊዜ በውኃ አለመታጠብ፣ አልኮል አለመጠጣት፣ ልብስን መራቆት፣ አድካሚ የሆነ ጤናን ሊያውክ የሚችል ጉዞ አለማድረግ ይጠበቅብናል፣ ለቅዱስ ቁርባን ክብር ለመስጠት ነው እንጂ ይሄን ነገር ከባድ አድርገን ማየት የለብንም፣ የቆረበ ሰው በዚያን እለት ሙሽራ ነው፣ ንጉሥ ነው ተከብሮ በቤቱ ነው መዋል፣ ማደር ያለበት ማለት ነው፡፡
ጠያቂያችን በቅርቡ ላገባ ነው ብለውናል፣ የተመኙትን እግዚአብሔር ያስፈፅምዎት፣ ወላዲተ አምላክ ትርዳዎት፣ ስልክ ደውለው ያግኙን፣ ተጨማሪ ምክር እንሰጥዎታለን፣ ከዚህ በፊት ስለ ቅዱስ ቁርባን አዲስ ለሚቆርቡም፣ እየቆረቡ ላሉትም፣ በተክሊል ለሚጋቡም፣ በመአስባን ተክሊል ለሚጋቡም፣ በቁርባን ለሚያገቡም የሰጠነውን መልስ፣ ሊንኩን ተጭነው ይከታተሉት፡፡
ለሁሉም ነገር እግዚአብሔር በቸርነቱና በምሕረቱ ብዛት በቤተሰቦቻችን ላይ አድሮ ጥያቄ እያስነሳ እንዲህ የሚመክረን፣ የሚገስፀን እሱ ስለሆነ ምስጋና ለእሱ ይሁን አሜን፡፡
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር አድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
ቅዱስ ቁርባን እና ፀበል
👉🏾 ለ #ቅዱስ #ቁርባን ስለሚደረግ #ጥንቃቄ
👉ጥያቄ፡-ሰላም አባታችን፣ አሁን ያለፈው እሁድ በ29 ቅዱስ ቁርባን ተቀበልኩ፣ ከዚያ ማክሰኞ ጳጉሜን 1 የጳጉሜን ጸበል ልጀምር ብዬ የንስሐ አባቴን ጠየቅኳቸው፣ ሦስት ቀን ሳይሞላ መጠመቅ አይቻልም፣ ረቡዕ ግን ትችላለህ አሉኝ፣ ለምን እንደሆነ ፈርቼ አልጠየቅኳቸውም፣ ሥጋወደሙን ከተቀበልን በኋላ ሦስት ቀን ሳይሞላን መጠመቅ አይቻልም አባ?
✍መልስ፡- ጳጉሜን በተከታታይ መጠመቅ በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ዘንድ የበረከት ሳምንት ስለሆነ፣ ክርስቲያኖች ሁሉ ከእግዚአብሔር በረከት ለማግኘት፣ በጾምና በጸሎት፣ እንዲሁም ጠዋት፣ ጠዋት ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ በመጠመቅ የሚያሳልፉት ጊዜ ነው፡፡
በእርግጥ አባቶቻችን ይህንን የሚሉት አብዝተው ልጆቻቸውን ጠንቃቃ ለማድረግ፣ በውስጣቸው ፈረሀ እግዚአብሔር እንዲኖራቸው ለማድረግ አስበው ሊሆን ይችላል፣ ግን ከመቁረብ በፊት የምንጠነቀቃቸው ለሦስት ቀናት የምንታቀባቸው ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ ለይተን ከዚህ በፊት ተነጋግረናል፡፡
ከቆረብን በኋላም የምንጠነቀቅባቸው ከምን ከምን ጥፋት እንደሆነ፣ ያውም ደግሞ ወደ ኃጢአት የሚወስዱን፣ ማድረግ የሌለብን ነገሮች ምን ምን እንደሆኑ ይሄንንም ደጋግመን በዚሁ በዮሐንስ ንስሐ ድህረ ገጽ ተምረናል ያገኙታል፣ ወደዚያ ዝርዝር ሳንገባ አባታችን እንደ ክፉ ነገር፣ ወይም እንደ ስህተት ባንቆጥርባቸውም ግን ጥምቀት መጠመቅ አይከለክልም፡፡
ሌላው አንዱ የቤተክርስቲያን ትልቁ ፀጋዋ ጥምቀት ነው፣ ጥምቀት ከቅዱስ ቁርባን ጋር ሊያጣላ የሚችል፣ ከቅዱስ ቁርባን ጋር ሊያቃርን የሚችል፣ ከቅዱስ ቁርባን ያገኘነውን ትልቅ ክብር ሊያዋርድ ወይም ደግሞ እሱን ሊያሳጣ የሚችል አይደለም፣ ስለዚህ በቆረብንበት ዕለት የምንጠነቀቃቸው ብዙ ጥንቃቄዎች አሉ፡፡
ከእነሱም አንደኛው እንደተባለው በውኃ መታጠብም ሆነ መጠመቅ አንችልም፣ የቀደሱት ካሕናትም ሆኑ የቆረቡት ክርስቲኖች በዚያን ጊዜ በእለቱ የማያደርጓቸው ነገሮች አሉ፣ ከሰውነታችን ደም እንዳይወጣ፣ በውኃ መተጣጠብ፣ አብዝቶ መብላት፣ አብዝቶ መጠጣት በተለይም የአልኮል መጠጦችን መጠጣት፣ ኃይለ ቃልን መነጋገር፣ መጨቃጨቅ፣ መነታረክ በዚያን ጊዜ የማይደረጉ ናቸው፡፡
ይህም ለቅዱስ ቁርባን ለየት ያለ ክብር ስለምንሰጠው፣ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሚገኘውን ሰማያዊ ዋጋ፣ ዘለዓለማዊ ህይወት የምናገኝበት ስለሆነ ይሄንን የሚበልጥብንን በረከት ለማግኘት በዚያን ጊዜ መታገስ ስላለብን ነው ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ጠያቂያችን በቆረብንበት ዕለት ወይም የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን በተቀበልንበት በዚያን ዕለት ጸበል መጠመቅ አይቻልም፣ ከዚያ በኋላ ግን ጸበል አንዱ ቅዱስ ነገር ስለሆነ፣ አስፈላጊያችንም ስለሆነ ከቅዱስ ቁርባን ጋር የሚቃረን አይደለም፣ እንኳን በሦስተኛው ቀን ይቅርና ማለት ነው፡፡
ከዚህ አንፃር የንስሐ አባትዎ የሰጡዎት ምክር ለጥንቃቄ ስለሆነ፣ እንደ ትልቅ ስህተት ወይም ጥፋት አንቆጥረውም፣ እርስዎም እንዳሉትም የአባት ቃል ጠብቆ በማክበር ብዙ ነገር ማለት አልፈለጉም፣ ለምን እንደሆነ ግን አልገባዎትም፣ ወደ እኛ ይሄን ሐሳብዎን አምጥተው መጠየቅዎ መልካም ነው፣ ስለዚህ በብዙ ሐሳቦች መካከል አንዳንድ ጊዜ እኛም በቅንነት ለበለጠ ጥንቃቄ፣ ለመንፈሳዊ ፅናት ብለን የሚሰጡትን ምክሮች እንደ ስህተትም፣ እንደ አላዋቂነትም ቆጥረን ትርጉም አንሰጥም፡፡
የአባቶቻችን፣ የሊቃውንት ኃላፊነታቸውና አስተምህሯቸው በብዙ ነገር የተመሠረተ፣ ከግል የኑሮ ህይወታቸው በተጨማሪ ጧት ማታ የሰውን ስነ አይምሮ ሊያንፅ የሚችል፣ ምክር፣ ትምህርት፣ ተግሣፅ ለመስጠት ደፋ ቀና የሚሉ አባቶቻችን አንዳንድ ጊዜ በቅንነትና ለበለጠ መንፈሳዊ ጥንካሬ እንዲሆነን የሚናገሩትን ነገር ሁሉ፣ ከብዙ መካከል አንዷን በመምዘዝ እንደ ጥፋት፣ እንደ ነውር፣ እንደ ስህተት፣ እንደ አላዋቂነት መቁጠር የለብንም፡፡
ይሄ ለሁሉም ሰው የምንከርው ምክር መሆን አለበትና ነው፣ የሆነ ሆኖ ግን እርስዎ በዚህና ይሄን በሚመስለው ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ሆኖ እንድንመከርበት፣ እንድንገሰፅበት፣ ብዙ ነገር እንድንማርበት፣ እንድናውቅበት የእግዚአብሔር ፈቃድ ስለሆነልን ክብርና ምስጋና ለእሱ ይሁን አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፣ ይቆየን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር አድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
ቅዱስ ቁርባን ሥርዓት እና ክህነት
👉ጥያቄ፦ አንድ #ዲያቆን ድቁናውን ቢያጣ #ቁርባን ሲወስድ ልክ እንደ ምእመናኑ ነው?
✍ መልስ፦ መጀመሪያ ጥያቄው ወይም አማርኛችን መስተካከል ይኖርበታል፣ መሆን ያለበት ቁርባን ሲወስድ ሳይሆን፣ “ቅዱስ ሥጋ፣ ክቡር ደሙን“ስንቀበል ወይም ስንቆርብ ነው መባል ያለበት እንጂ፣ ሲወስድ የሚባለው መድኃኒት፣ ኪኒን ነው፣ በነገራችን ላይ የካሕኑንና የምእመኑን ያላቸውን ልዩነት ብናይ ካሕኑ በመቀደስና፣ በማቁረብ ነው፣ ክብሩ ለሁሉም ነው፣ ሁሉም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፣ ምእመን ማለት ታማኝ ማለት ነው።
በቤተክርስቲያናችንም ሆነ በትልልቅ ገዳማት በጣም ትልልቅ አባቶች ገብተው መቀደስ የሚችሉ፣ ገብተው ማቁረብ የሚችሉ፣ መቅደስ ውስጥ ገብተው መቁረብ የሚችሉ ሆነው እያለ ልክ እንደ ምእመናን ሆነው ቅዱስ ሥጋውን፣ ክቡር ደሙን ሲቀበሉ እናያለን፣ ክርስትና ማለት ራስን ዝቅ ማድረግ ነው።
በእርግጥ ዲያቆን የነበረ፣ መሪጌታ የነበረ፣ መምህር የነበረ ከምእመኑ የተሻለ እውቀት አለው፣ ግን ክብራችንን ማንም አያስቀርብንም፣ አንዳንዶች አባቶቻችን ካሕናትም ሆነው ማንም ክሕነታቸውን የማያውቅባቸው እንደ ምእመን ሆነው የሚቆርቡ አሉ፣ ይሔ ሁሉ ትዕግሥት ከእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋን ያስገኛል።
ካሕን ነኝ ሳይል እየኖረ እያለ ችግር ሲፈጠር፣ የሚቀድስ ካሕን ሳይኖር ሲቀር ካሕን መሆኑን ማሳወቅ ይችላል፣ እንዲሁም ገብቶ ሊቀድስ ይችላል፣ ግን የሚያገለግል እስካልጠፋ ድረስ እንደ ምእመናን መስሎ ይኖራል፣ ይሔ ራሱ ተጋድሎ ነው፣ እዩልኝ፣ ስሙልኝ ከማለት መቆጠብ፣ መታገስ ማለት ነው፣ ነገር ግን ካሕን ጠፍቶ የሚያገለግል ከጠፋ ግን ቄስ ሆኖ፣ ዲያቆን ሆኖ ክርስትና ሊታጎል ሲል ዝም ቢል ተገቢ አይደለም።
ጠያቂያችን እንኳንስ ድቁናውን ያጣ ቤተ መቅደስ የማይገባው ይቅርና ካሕንም፣ ዲያቆንም ሆነው እንደ ምእመን ይቀበላሉ ማለት ነው፣ እንደ ምእመን ሆነን ብንቀበል ደግሞ ያለው ክብራችን፣ የድቁናችን ዋጋ፣ የክህነታችን ዋጋ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ አይቀርብንምና እንደዛ ሆነን ብንቀበለው ችግር የለውም ለማለት ነው፣ ግን ሁሉም አይደለም፣ ክርስትናቸው በደንብ የተረዳቸው ናቸው፣ ተጋድሏቸው እዚህ ድረስ ነው።
ያፈረሰ ካሕንም ሆነ ዲያቆን ሲጀመርም ቤተ መቅደስ መግባት ስለማይቻል ውጪ ሆኖ ነው የሚቀበለው፣ ይሔ የታወቀ ነው፣ ካሕናትም ብንሆን ውጪ ሆነን ብንቆርብ፣ እንደ ምእመን ሆነን ብንቀበል ምንም የሚቀርብን ነገር የለም፣ እኛ ካሕናት እየቆረብን ለምእመናን ቁረቡ በማለት አርአያ፣ ምሳሌ መሆን ነው፣ ደስተኛ ያደርገናል፣ በእግዚአብሔር ቤት ዋጋ ያሰጠናል፣ ምንም የሚያጎድልብን ነገር አይኖርም።
ካሕኑ ለምእመን በተግባር ማስተማር ማሳየት አለበት፣ ከቅዱስ ቁርባኑ፣ ከክቡር ደሙ ፊት ሰግዶ፣ ተቀብሎ ከዚያ እነሱ እንዲቀበሉ ቢያደርግ፣ እሱ እያደረገ በተግባር ማሳየት ያ ነው ምሳሌና አርአያ መሆን ማለት ነው፣ ቤተ መቅደስ ከገባ ማለት እኮ ገብቶ ይቀድሳል ማለት ነው፣ በእውቀቱ፣ በተለያየ ዘርፍ ችሎታው ግን ከምእመናን በላይ ነው፣ ምእመናን አይደርሱበትም፣ ባገለገለው ዘርፍም ከእግዚአብሔር ዋጋ ያገኛል ማለት ነው።
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፣ አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር አድርጉ፦
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
ስለ ቅዱስ ቁርባን ሥርዓት - (ሴትች ማወቅ ያለባቸው)
👉🏾 ለ #ቅዱስ #ቁርባን ስለሚደረግ #ጥንቃቄ እና ስለ #ሴት #ልጅ #የወር #አበባ
👉 ጥያቄ:- ሰላም አባቴ እንደምን አሉ ይህ ጥያቄ በውስጥ መስመር የተጠየኩት ነው እና እኔ የተሳሳተ መረጃ እንዳልሰጣት ምክርዎት ይስፈልጋታል፣ ስለዚህ መልሱን በጽሑፍ አድርጉልኝ፣
አንድ ሴት ወደ ቤተመቅደስ ለመቁረብ ስትገባ የወር አበባ የላትም ነበር፣ ነገር ግን ሳታስበው በድንገት ቅዳሴ መሐል ላይ መጣ፣ ትታ መውጣት ነው ያለባት? ወይስ ውስጥ ሆና ስለመጣ ቆርባ መውጣት ነዉ ያለባት? ከቻላችሁ መልሳችሁ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ቢኖረው ማስረጃ ጥሩ ነው፣ እሷ አታውቅም እና አውቆ ሳይጣን ሊያስወጣኝ ነው በደህና ገብቼ እንዴ ይሆናል? በማለት ቆርባ ወጣች ምን ይሻላል?
✍መልስ፡- የሴቶች ወርኃዊ ልማድ በቁርባንም ጊዜ ሆነ ቤተክርስቲያን በገባንበት ጊዜ በአጋጣሚ ይመጣል፣ ጊዜው ተለይቶ ይታወቃል ወይም ደግሞ አይታወቅም፣ እንዲህ ዓይነት ክስተት ያጋጥማል፣ በጣም አክብደን የስህተት ሁሉ የመጨረሻ አድርገን ከኃጢአተኞች እንደሚያስቆጥረን አስበን ማመን የለብንም፡፡
እግዚአብሔርን አንዳችም ነገር ሊያረክሰው፣ ቅድስናውንም ሊያረክስ የሚችል፣ ቅዱስ ሥፍራውንም ሊያጎሰቁል የሚችል ምንም ነገር የለም፣ እስከ ጥግ ድረስ ኃጢአተኞች ብንሆንም እንኳን የእኛን ፍርድ ያፀናል፣ በበደል ላይ በደል ይጨምርብናል፣ በሸክም ላይ ሸክም ያከብድብናል እንጂ የእግዚአብሔርን ቅድስና ወይም ደግሞ እግዚአብሔርን ቅዱስ ከመሆን የሚያወጣ ኃጢአት የለም፡፡
ሰዎች ብዙ ጊዜ ጥፋታቸውንና ኃጢአታቸውን ከእነሱም አሳልፈው፣ እግዚአብሔርን ሁሉ ኃጢአተኛ እንደምናደርገው ወይም ደግሞ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ቦታ ሁሉ በእኛ ጥፋት፣ በእኛ ኃጢአት፣ በእኛ ርኵሰት እንደምናረክሰው አድርገን እናስባለን፣ ድፍረቱ የድፍረት ጥግ ሆኖ፣ ፍርዱም ሁሉ የድፍረት ፍጻሜ እንዳይሆንብን፣ ትዕቢተኞች ሆነን፣ ደፋሮች ሆነን የእግዚአብሔርን ቤት ደፍረን እንዳንገባ አስፈላጊም ስለሆነ እግዚአብሔር ደግሞ በዚህ ጉዳይ ላይ እንዴት እንደሚቀጣንም ታይቶ ይታወቃል፡፡
የእግዚአብሔር ቅድስናው ቦታ ከሌላው ቦታ በምን ለሊይ ይችላል፣ ይኼንን ባደርግስ ምን ያመጣል? ወይም በእኔ ላይ የሚከሰት ምን ነገር አለ? ብለን በትዕቢት ብንገባ ያን ጊዜ እግዚአብሔር እኛ የምናውቃቸውን የምድር ወታደሮች አይጠራም፣ እኛ በምናውቀው ዱላ ወይም መሳሪያ አይደለም የሚደበድበን፣ በሥጋ እንኳን ቸርነቱ በዝቶልን በእንዲህ ዓይነት ድፍረት ያለነውን እለቱኑ መጥቶ ቆርጦ ባይጥለንም፣ በፅኑ ደዌ ባይጥለንም አላወቅነውም እንጂ በመንፈስ ግን ከዚያን ሰዓት ጀምሮ ተመትተናል፡፡
የሐዲስ ኪዳን ኩነኔ በመንፈስ ነው፣ እንደ ብሉይ ኪዳን ቤታችን ላይ፣ ልብሳችን ላይ፣ ግንባራችን ላይ፣ ሰውነታችን ላይ የሚወጣ የኃጢአት ለምፅ የለም፣ በመንፈስ ግን ከአሁን ጀምሮ በኃጢአተኛው ላይ ተፈርዶበታል፣ ይኼ ፍርድ ደግሞ ጽኑ ነው፣ እግዚአብሔር ደግሞ ከዚህ ይሰውረን፣ ስለዚህ ማሰብ ያለብን ይሄንን ነው፡፡
ሴትየዋ በሆነ አጋጣሚ ሳታስበው የእግዚአብሔርን ቤት ለመድፈር፣ ወይም ደግሞ የቅድስናውን ቦታ ለማርከስ ወይም ደግሞ እግዚአብሔርን ለመገዳደር ብላ አይደለም፣ እሷማ በጎ ነገር አስባለች፣ መልካም ነገር አስባለች፣ ማንም ያልመረጠውን በጎ ዕድል መርጣለች፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለመቀበል ነው በዚህ ዓይነት መልካም ዝግጅት ሆኖ ወይም ቤተክርስቲያን ከገባች በኋላ ወይም ጊዜውን ጠብቆ፣ ሰዓቱን ለይታ ስላላወቀች ወሩ ገብቶ የመጣ ጉዳይ፣ ወይም ደግሞ በጤንነት መታወክ ሳይጠበቅ የመጣ ጉዳይ ሊሆን ይችላል፡፡
ስለዚህ ጠያቂያችንም ሆናችሁ ሁላችሁም መወዛገብ ሳይሆን፣ መነታረክ ሳይሆን እንዲሁ ዝም ብላችሁ የትኛው መጽሐፍ ውስጥ ይገኛል ብላችሁ እውነቱን ከመረዳት ይልቅ የጴንጤ ጥያቄ አድርጋችሁ የጴንጤ ሐሳብ አድርጋችሁ ማየት የለባችሁም፣ እነሱ ሁል ጊዜ ጽድቃቸውም፣ ኃይማኖታቸውም፣ ክርስትናቸውም ምላሳቸው ላይ ስለሆነ፣ እሱንም ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል ላያምኑበትም፣ ምስጢሩን ትርጉሙን ላይረዱትም እንዲሁ በአፋቸው ላይ ሲደናግሩ እናያለን፣ እኛም ሌላ ነገር የለንም፣ የእኛ አቅም የእኛ የሕሊና ጓዳ ምንም የቋጠረው ነገር ስለሌለው፣ እንዲሁ የሁላችን የመግባቢያ ቋንቋ ያደረግነው ብናምንበትም ባናምንበትም በውስጡ ያለውን ምስጢር ብንረዳውም፣ ባንረዳውም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለ ወይ? እንላለን፡፡
የእኛ ስንፍና መብዛት ካልሆነ በስተቀር መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረጉ እልፍ አእላፋት መጽሐፍት አሉን፣ ወርቃማ መጻሕፍት አሉን፣ አንዳቸውም የሰው ልብ ወለድ ያልሆኑ የእኛ ስንፍና ካልሆነ በስተቀር፣ አንዳቸውም ስህተት የሌላቸው፣ ማለት ነው፣ እንደዚሁ ጴንጤ በሚጠቅስልን በመጽሐፍ ቅዱስ ከሆነማ ለሴቶች ምን መልካም ነገር ይሰጣቸዋል? በኦሪቱ ሥርዓት እኮ የመርገም ደም ነው በእርግማን የመጣ ነው የሚለው፡፡
እግዚአብሔር ይመስገን በመስቀሉ ላይ የፈጸመልን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህ ጀምሮ ያ በደላችሁ እንደ ኃጢአት የተቆጠረባችሁ፣ የእርግማን ምልክት የሆነባችሁ ነገር ቀርቶላችኋል፣ በአዋጅ በእኛ ላይ የተጣለውን የእርግማን ቃል በመስቀሉ ሻረልን ነው ያለው፣ ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ መልእክቱ ምዕራፍ 3 “በሕግ የነበረውን የእርግማን አዋጅ፣ በሕግ በሆነው ነገረ ድኅነቱ በመስቀሉ ሻረው” ይላል፡፡
በብሉይ ኪዳን አንዱ የእርግማን ምልክት ወርኃዊ ልማዳቸው ሲታይ እንዲያውም እግዚአብሔር የረገማችሁ፣ ይኼ የእርግማናችሁ ምልክት ነው ተብሎ ነበር የሚሰደቡበት፣ የሚንቋሸሹበት፣ ከቤተ እግዚአብሔርም፣ ከእግዚአብሔር ጉባኤም የሚገለሉበት ሥርዓት ነበር፣ በእርግጥም ከዚያ የተወሰደው መልካም ነገር አንዲት ሴት ስትወልድም፣ የወር አበባም ሲመጣባት እስከምትነጻ ድረስ ከቤተክርስቲያን፣ ከቤተ እግዚአብሔር ምን ያህል መራቅ እንዳለባት ጊዜዋን ትጠብቃለች፣ ከዚያ ፈሳሽ እስትነፃ ድረስ በኦሪት ዘሌዋውያን ምዕራፍ 12 ያለውን ማለት ነው፣ ሌላው ቀኖናችን ሴቶች የወር አበባቸው ሲመጣ፣ ወንድ ልጅ ሲወልዱ፣ ሴት ልጅ ሲወልዱ እስከ ስንት ቀን መታገስ እንዳለባቸው ተነግሯል፣
ጠያቂያችን ያሉት አሁን ዋናው ነገር በአጋጣሚ መጣ ነው፣ ስለዚህ የምናየው ሁለት ነገር ነው መቁረብ አለባት? ወይስ የለባትም? ቅዳሴውን አቋርጣ መውጣት አለባት? ወይስ የለባትም? አስቀድሳ መውጣት ነው ያለባት? የሚለውን ማለት ያለብን፣ ስለዚህ ይቺ ሴት ቀድሞ ከመጣባት ቅዱስ ቁርባን አትቀበልም፣ ለምሳሌ እሷ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብላ ወዲያውኑ ሊመጣ ቢችል ከላይ እንዳልነው የእግዚአብሔርን ቅድስና ሊያረክስ የሚችል ነገር የለውም።
እሷ ድፍረት እንዳይሆንባት ምን ያመጣል፣ ምን ይከሰታል ብላ በድፍረት እንዳታደርገው እንጂ፤ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብላ በእሷ ሕይወት ላይ ትልቅ ሕይወት ላይ የሚሰጠውን የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብላ ከዚያ በኋላ ቢመጣ በዚህ እሷም አትጠየቅበትም፣ የቅዱስ ሥጋውንና የክቡር ደሙን ክብርም አይቀንስም፡፡
ክርስቲያን ግን አስቀድሞ ጠንቃቃ ነው፣ ወርኃዊ ልማድ ሊመጣ ጊዜው ከደረሰ የቅዱስ ቁርባኑን መቀበል ቀን ወይም እናሳልፈዋለን፣ ወይም ደግሞ ቀድመን እናደርገዋለን፣ ትልቁ ንዝህላልነታችን ሁልጊዜ ለመንፈሳዊ ነገር አስበን አለማድረጋችን እንደ ድፍረት የሚቆጠርብን ይኼ ነው፣ እውነት ለመናገር ይኼንን በደንብ አድርገው ይለዩታል፣ በጤንነት ችግር ካልሆነ በስተቀር ሴቶች ልማዳቸው ቢፈጥን መቼ፣ ቢዘገይ መቼ እንደሆነ በደንብ ጠንቅቀው ያውቁታል ማለት ነው፡፡
ይኼ እየታወቀ ለምን ቤተክርስቲያን ትሄዳለች ለሚባለው ግን ቤተክርስቲያን መግባት አትከለከልም፣ አንድትቆርብ ግን አትዘጋጅም፣ እንዲያው በአጋጣሚ ዝም ብሎ በክስተት ይመጣል፣ አንዳንድ ጊዜም ጸበል እየተጠመቁም ይመጣል፣ እየተጠመቀች ሊመጣ ቢችል፣ እንኳን እንዲሁም ወዲያውኑ ተጠምቃም ቢመጣ ምንም አይደለም፣ በዚህ የጥምቀቱን ሥራ በእሷ ላይ አያስቆምም፣ አያሰናክለውም፣ እኛ እያወቅን ነው ከእኛ የሚጠበቀውን ነገር ነው፡፡
ከዚህ አንፃር ግን ሳትቆርብ በፊት በዚያው ቅፅበት ይኼ ነገር ቢከሰት ሳትቆርብ ነው የምትወጣው፣ እንዲያውም በጣም አውኳት በጤና መታወክ ፈሳሽ ሊበዛባት ቢችል፣ በዚያ አካባቢ ለሌላውም ለራስዋም ፈተና እንዳትሆን፣ ፈሳሽም ደግሞ የቆመችበት ከዚያ የቅዱስ ቦታ ላይ ምልክቱ እንዳይታይም ቶሎ ፈጥና ብትወጣ ቅዳሴውን አቋርጣ ብትወጣ ከጤና መታወክ ጋር የሚያያዝ ነው፡፡
ብዙ ጊዜ አያምጣው እንጂ የሚቀድሰው ቄሱ፣ ካህኑ ቢታመም ይወጣል፣ በሌሎቹ በተሰየሙት ቅዳሴው ፍጻሜ ላይ ይደርሳል፣ ሥርዓቱን የሚያግዝ ሌላ አጠገቡ አለ፣ እንኳስ የሚያስቀድሱና የሚቆርቡት ቀርቶ የሚቀድሰው ካህን አያምጣው እንጂ፣ እግዚአብሔር ለዚህ አያጋልጠን እንጂ ካሕኑም ሊያቋርጥ የሚገደደው በጤና መታወክ ምክንያት ነው ማለት ነው፡፡
ስለዚህ እንደ ምድራውያን ክብራቸውን፣ ሥልጣናቸውን፣ እንደሚወዱ በሰው ላይ ቁጣቸውን ፍርዳቸውን ሁሉ እንደሚጠቀሙ ምድራውያን ባለ ሥልጣናት ፈጣሪን አንየው፣ ከእኛ በላይ ዛሬ ምን እንደምንሆን አልነገረንም እንጂ የሚያውቀው እሱ ነው፣ ሴቷም ሆነች ወንዱ ቤተ እግዚአብሔር ሄደው በመዋላቸውም፣ በማደራቸውም የሚገጥማቸውን ነገር ከእኛ በላይ ቀድሞ የሚያውቀው እግዚአብሔር ነው፣ በዚህ መሠረት ነው አንዳንድ የሐሳቦች መጋጨት፣ መጣረስ አንዳንድ ጊዜ እናያለን፡፡
ጠያቂያችን በውስጥ መስመር ይድረሰኝ ላሉት እኛ በተፈለገው ነገር ለቤተሰቦቻችን እንዲደርስ እናደርጋለን፣ አሁንም እርስዎ እውነቱን ንገሩኝ ብለዋል፣ ምናልባት ከቀኖና፣ ከንስሐ አንፃር የግል ሕይወት ስለሆነ ምን ማድረግ እንዳለብዎት የሚያስፈልግ ነገር ካለ ባለን አድራሻ ደውለው ያግኙን፡፡
ቤተሰቦቻችን ብታደርጉትም ባታደርጉትም ይኼንን ማለት የእኛ የኃላፊነት ድርሻ ስለሆነ የማይተው ስለሆነ፣ ሁልጊዜ ቤተሰቦቻችንም ሆኑ ምዕመናን መልመድ ያለባቸው ነገር ይሄ ነው፣ ማለትም አባቶችን የማማከር ማለት ነው፣ አንዳንድ ጊዜ ሲጨንቀን፣ ነገር ሁሉ ሲጠብብን፣ ጎራ ብለን በዚህ ጭንቀታችንን አራግፈን የሆነ ነገር ሰምተን መሄድ እናንተን ለሕይወት እንዳተረፍናችሁ ሳይሆን፣ እንደከሰርን ስለምንቆጥር ነው ባለን አድራሻ አግኙን የምንለው፡፡
ስንቶቻችሁ ወደ ንስሐ ሕይወት፣ ስንቶቻችሁ ወደ ቅዱስ ቁርባን፣ ስንቶቻችሁ ወጣቶች ወደ ጥሩ ሥነ ምግባርና፣ ወደ ቅዱስ ጋብቻ እንደቀረባችሁም እንድናይም፣ በዚህ እግዚአብሔር እንደሚደሰት እኛንም ደስ እንዲለን ነውና፣ ይኼንን መልእክት ለሁሉም ሰው አዳርሱ ወይም ሼር አድርጉ፡፡
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፣ አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር አድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፦ #ነፍሰጡር ሴት #ቅዱስ #ቁርባን መቀበል ትችላለች ? እናም #ፀበል መጠጣት እና መጠመቅስ ትችላለች ? ክቡር አባቶቻችን ይኽንን ቢያብራሩልን?
መልስ፦ ጠያቂያችን እርግዝና እራሱን የቻለ ልዩ እንክብካቤ እና ክብር የሚያስፈልገው የህይወት መሰረት ነው። ያረገዘች ሴት በተፈጥሮ ፀጋ ያገኘችው የእግዚአብሔር ስጦታ ቢሆንም እግዚአብሔር በአርአያውና በምሳሌው የፈጠረውን ስነፍጥረት በመሀፀንዋ 9 ወር ከ 5 ቀን ሃላፊነት ወስዳ መሀፀንዋን እንደ አለም አድርጋ በእግዚአብሔር ልዩ ጥበብ ፅንሱ ከእርሰዋ የህይወት እስትንፋስ እያገኘን የመቆየቱ ሂደት ከንስሓ ህይወት የበለጠ ፈጣሪዋን እንድታውቅ የሚያደርጋት ህይወት ስለሆነ ጠያቂያችን እንዳሉት ያረገዘች ሴት ንስሓ በመግባት መጾምና መስገድም ሆነ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል እንደሚያስቸግራት በማሰብ ባትገደድም ፥ ነገር ግን አትከለከልም። ከአቅምና አንጻር ስለሚከብዳት እና ምናልባት ፈሳሽ ሊኖር የሚችልበት አጋጣሚ ስለሚኖር፤ በግላቸውና በአቅማቸው መጠን አይተው ሊፈጽሙት የሚችሉት ቢሆንም አሰንደአጠቃላይ ግን በመጠኑ እንዲሆን እንመክራለን። ለምሳሌ ፀበል በራሱ ሃይልና ጉልበት ስላለው በብዛት መጠጣት የለባትም፤ ረጅም ሰአት መጾም መቆምና መስገድም እንደዚሁ።
ስለዚህ ጠያቂያችን፤ ስናጠቃልለው፦ አንዲት ሴት ፅንስ በማህፀንዋ ካደረበት እለት ጀምሮ 9 ወር ከ5 ቀን የእርግዝና ጊዜ የምታሳልፍበት ወቅት ነውና በዚህ የእርግዝና ወቅት ከእርግዝና በፊት የምትሰጠውን መንፈሳዊ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ማከናወን አቅምዋ ስለማይፈቅድና ስለሚደክማት ፣ የተሸከመችውም ሃላፊነት ከባድ ስለሆነ ማንኛውንም መንፈሳዊ ግዴታዋን ከሌላ ጊዜ እየቀነሰች እንደምታሳልፍ ስርአተ ቤተክርስቲያን ይፈቅድላታል። በመሆኑም ስለ ጾም፣ ስለ ስግደት ፣ ስለ ፀሎት እና ቆሞ ስለ ማስቀደስ ፣ ስለ መቁረብ የምታደርገውን መንፈሳዊ ስርአት ታደርግ በነበረው መጠን ብትቀጥል በአካልዋ ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግር ስለሚኖሩ ከዚህ አንፃር በቅርብ በመንፈሳዊ አባትነት የሚጠብቋትን የንስኀ አባት እያማከረች ከጊዜ ወደ ጊዜ አገልግሎቱ እየቀለላት እንዲሄድ ይደረጋል። ምንም እንኳን የተረጋጋ አካላዊ እንቅስቃሴዋ የበረታ ከሆነ እስከተወሰነ የፅንስ ጊዜዋ ፆምን ለተወሰነ ጊዜ እየጾመች ወደ ቤተክርስቲያን ሄዳ ቁማ መፀለይ፣ ቤተክርስቲያን መሳለም፣ ማስቀደስ ፣ መስቀል መሳለም፣ ፀበል መረጨት በአጠቃላይ እነዚህን መንፈሳዊ አገልግሎቶች እያገኘች መመለስ ትችላለች። የፅንሱ ጊዜ እየገፋ እየደከማት ሲመጣ ግን በቤትዋ ሆና ፆሙን እየቀነሰች መፆም ትችላለች፣ ያትችልበት ደረጃ ከደረሰችም ስለእርሷ መንፈሳዊ አባቷ በፆምም በፀሎትም ስለሚያስቧት እሷ ግን እንድትፆምና ሌሎቹን መንፈሳዊ አገልግሎቶች እንድትፈፅም እንደማትገደድ ቤተክርስተያን ስርዓት ያዛል። ምክንያቱም መንፈሳዊ ስርዓቱ የሚጠይቀውን ተያያዥ አገልግሎቶች ለምሳሌ ያረገዘች ሴት በእርግዝና ግዜ ንስሓ መውሰድና መቁረብ የማትችልበት (የሚከብዳት) ምክንያት መስገድን፣ ለረጅም ሰዓት መፆምን፣ ቁሞ መፀለይን የሚጠይቅ መንፈሳዊ አላማ ስለሆነ እነዚህን አይነት ንስሓ እንዲቀበሉ አይደረግም፤ የታመሙ ሰወችም እንዲሁ። ስለዚህ ጠያቂያችን ሃሳቡን ከዚህ አንፃር እንዲመለከቱት ይህን አጭር መልዕክት ልከንልዎታል።
ተጨማሪ መንፈሳዊ ምክርና ትምህርት ድረገጻችን https://yohannesneseha.org/ ላይ ያገኛሉ
ልዩ ልዩ (ስለ ቅዱስ ቁርባን)
👉🏾 ስለ #ተአምረ #ማርያም እና #ቅዱስ #ቁርባን የተሰጠ ማብራሪያ
👉ጥያቄ፦ በተአምረ ማርያም ላይ ተአምሯን የሰማ ሥጋወ ደሙን እንደተቀበለ ይሆንልኛል፣ ይደረግልኛል ቢል እንደተቀበለ ይሆንለታል ይላል? ይሄ ምሥጢሩ ምንድን ነው?
✍መልስ፡- እውነት ነው ሁልጊዜ በተአምረ ማርያም ሲነበብ የሚባል ቃል ነው፣ ተአምረ ማርያም ሲነበብ የሰማ ይህ ማለት ቅዱስ ቁርባኑን ክቡር ደሙን ቀበል፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ላለመቀበል የታወቀ ደዌ ህመም ምክንያት ካልከለከለው በስተቀር በዚህች ቀን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ይቀበል፣ ነገር ግን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መቀበል ካልተቻለው ግን ተአምሯን ሰምቶ ወደ ቤቱ ይሂድ፣ ሥጋወደሙን እንደመቀበል ይሆንልኛል፣ ይደረግልኛል በማለት ቢሰማ ይላል፡፡
ይህ ማለት ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለመቀበል ስርዓት አለ፣ እነዚያ ስርዓቶችን ያልጠበቀ ሰው ቢሆን ወይም ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መቀበል ካልቻለ፣ ዛሬ ሥጋወደሙን መቀበል አልችልምና ቤተክርስቲያን አልሄድም ማለት ሳይሆን ያለበት ሚስጢሩ ተአምሯን ይስማ ማለት ነው፣ ተአምሯን ሰምቶ የሚሄድ ከሆነ በረከትን ወደ ቤቱ ይዞ ይሄዳል፣ ዋጋ ያገኛል፣ ዋጋ ቢስ አይሆንም ማለት ነው ሚስጠሩ፡፡
የሰው ልጅ በመጀመሪያ ሲጠመቅ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ይቀበላል፣ ያኔ ልጅነትን ያገኛል፣ በኋላ ግን በየዓመቱ ጥምቀት እያልን እናከብራለን በዚያ ጥምቀት የምናገኘው የሥላሴን ልጅነት ሳይሆን የበረከት ጥምቀት ነው፣ አሁንም ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የምንቀበለው በረከት ለማግኘት ነው ማለት ነው፡፡
ሌላ ጊዜ ግን እየደጋገምን ቅዱስ ቁርባን እንቀበላለን፣ ስርዓቱን እየጠበቅን ማለትም ከቁርባን በፊት የሚደረጉ ጥንቃቄዎች ስላሉ ማለት ነው፣ ስለዚህ ተአምረ ማርያም ሲነበብ መስማት ያለብን የተባለው በማንቀበልበት ቀን ለምሳሌ ሴት የወር አበባ ሆና ሊሆን ይችላል፣ ወይም የተለያየ ነገር ሊገጥማት ይችላል፣ ወንድም ቢሆን እንደዚሁ ማለት ነው፣ በወንዱም የሚመጣ ነገር አለ ለምሳሌ ህልመ ለሊት ሊሆን ይችላል፣ የዘር መፍሰስ ሊሆን ይችላል፣ ባልና ሚስት አብረው አድረው ሊሆን ይችላል፣ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቁርባንንም መቀበል አይገባም ማለት ነው፡፡
ነገር ግን ማለት ያለበት ቤተክርስቲያን መሄድ የለብኝም ሳይሆን፣ ተአምሯን መስማት አለብኝ ማለት ነው፣ ምክንያቱም ይኼ ሰው ተአምሯንም ባይሰማ አስቀድሞ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ይቀበላልና ክብርን አግኝቷል፣ ስርዓቱን ጠብቆ ሁልጊዜም ይቀበላል፣ አሁን ግን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንዳይቀበል የከለከለው ባለው ቀን በዚያ ሰዓት፣ ወይም ቀን ቤቱ ተኝቶ መቅረት የለበትም፣ ቤተክርስቲያን ሄዶ ተአምሯን ይስማ፣ ተአምሯን በመስማቱ ዋጋ ያገኛል ማለት ነው፡፡
ይህ ማለት ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ አያስፈልገውም፣ ተአምረ ማርያምን እየሰማ ብቻ ይሂድ ማለት ግን አይደለም፣ ስለዚህ ይህ ሰው ተአምረ ማርምን ከመስማቱ በፊት፣ እንዲሁም በተመቸው ቀን ሁሉ ስርዓቱን እየጠበቀ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ይቀበላል ማለትም በረከትን ያገኛል ወይም ዋጋ አግኝቷል፡፡
ስለዚህ ተአምሯን እየሰማ ይሂድ ካልን በቅዳሴ ላይ እንዲህ የሚል አለ “በቅዳሴ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን የገባ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የማይቀበል ከሆነ ከቤተክርስቲያን ይውጣ፣ ይሰደድ ፣ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ አቃሏልና” ይላል፣ ስለዚህ ሕገ እግዚአብሔር አፍርሷልና፣ የአባቶቻችን የሐዋርያትን ተዕዛዝ ጥሷልና ተላልፏልና ይላል፡፡
በጥቅሉ ይሄ የተባለው ሐሳብ ለማለት የተፈለገው ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለመቀበል በተከሰቱ ጊዜ ተአምረ ማርያምን መስማት እንደሚገባ፣ ተአምረ ማርያምን መስማት እንደማይከለክል፣ ተአምረ ማርያምን በመስማት ዋጋ እንደሚገኝ፣ እመቤታችን እንደምትባርከው፣ የበለጠ ደግሞ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለመቀበል እንደሚበቃ መሆን ደግሞ ከእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ እንደሚሰጠን ማወቅ ይጠበቅብናል፡፡
የመከረን የገሰፀን የአባቶቻችን አምላክ ልዑለ ባሕርይ እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን፣ አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር አድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾 ለ #ቅዱስ #ቁርባን ስለሚደረግ #ጥንቃቄ እና ስለተለያዩ ጥያቄዎች የተሰጠ ማብራሪያ እና ምክር
👉 ሰላም ጤና ይስጥልኝ አባቶች እንዲሁም የዚህ መንፈሳዊ ግሩፕ ተከታታዮች በሙሉ በእግዚአብሔር ፍፁም ሰላምታ ሰላማችሁ ይብዛ እንደምን አላችሁ? በምትሰጡት ትምህርት እና ምክር እግዚአብሔር ፀጋውን ክብሩን ያብዛልዎት፣ ከዚህ በመቀጠል ጥያቄ ነበረኝ:-
👉ጥያቄ 1ኛ፦ በብስናት የቆረበ ኃጢያት ነው ይባላል ነገር ግን ሰው በጨጓራ ወይም በሌላ ምክንያት በባዶ ሆዱ ሳይበላ ይህ ይከሰታል፣ ይህ ሰው መከልከል አለበት ወይ?
✍መልስ 1ኛ፡- ብስና ወይም ብስናት ማለት እንዳሉትምብዙ ጊዜ በጨጓራ ህመም መነሻነት የሚመጣ ሽታ ያለው ሆኖ አንዳንድ ጊዜ የበላነው ነገር ቆይቶ ሌላ አላስፈላጊ ስሜት ይዞ የሚመጣ፣ ያንን ሰው ሲያስገሳው ለሌላው ሰው በድምፅ የሚሰማ፣ እንዲሁም ያ ሽታ ለሌላውም ሰው፣ ማለትም በአጠገቡ ላሉ ሰዎች ሊሸት የሚችልበት አጋጣሚ አለ፣ ይህ ብስና ወይም ብስናት ይባላል፡፡
ይኼንን የሚመስሉ ብዙ ዓይነት ወደ ቅዱስ ቁርባን ስንቀርብ የምንጠነቀቅባቸው ነገሮች አሉ፣ ጨርሶ ደግሞ አስቸጋሪ ካልሆነ፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን አሁንም ያ ነገር የሚቀጥል ዓይነት ልማድ ካለ ይኼኛው የሚያውከን፣ ጤና የሚነሳን ነገር ካለ እስከሚተወውና ጤናችን እስከሚረጋጋ ቀጠሮ እንይዝበታለን፡፡
ቅዱስ ቁርባን መቀበልና፣ የጤና መታወክን እኩል አናያቸውም፣ ምክንያቱም በጣም በፅኑ ደዌ ህመም ውስጥ ያለ ሰው እንኳን የዚህ የዕድሉ ተጠቃሚ ሳይሆን ወይም ደግሞ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚያገኝበትን የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን፣ ክቡር ደሙን ሳይቀበል በአጋጣሚ እንኳን በሞት እንዳይጠራ ተብሎ የታመመውን ሰው በአካል በራሱ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ስለማይችል በሰው እርዳታ ወስደው ያቆርቡታል፡፡
በእርግጥም እንደዋናው ቀኖናችንና ሥርዓታችን ሰው በሕይወቱ ራሱን በሚገዛበት፣ ራሱን በሚመራበት ጊዜ ቅዱስ ቁርባን መቀበል አቅቶት፣ ለመቀበል ሳያምን ቀርቶ፣ አሁን በጭንቅ ውስጥ ሲሆን ቤተሰብ በግድ አስገድዶ ወስዶ ማቁረብ በሌላ መልኩ ከእምነት ማነስም ወይም ከአስተማሪም፣ ከመካሪም ስንፍና ሊሆን ይችላል፣ ዞሮ ዞሮ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳያጣት ሰው ስለ ቤተሰቡ ማሰብም መርዳትም ያለበት ይሄ ስለሆነ ነው፡፡
ጠያቂያችን አሁን ብስናት ያሉት ነገር የታመመ ሰው እንኳን ሄዶ ይቆርባል፣ ምናልባት የምግቡ ስሜት ማለት አንድ ሰው በትንሹ አሥራ ስምንት ሰዓታት መጾም እንዳለብን ተደንግጓል፣ ቀኖና ሆኗል ከነጭራሹ ከዚህም በላይ ጾመን ደግሞ ብስናት ካለ፣ የጤናው አስቸጋሪነት እዚያም ቤተክርስቲያን ውስጥ እያለን እያስቀደስንም ለመቁረብ ቆርበንም እንዲህ ዓይነት ስሜት ካለው ከላይ እንዳልነው ለነገ ወይም ለነገ ወዲያ ቀጠሮ ይያዛል ማለት ነው፡፡
እርስዎ ባሉት ደረጃ አንደኛውን ኃጢአት ነው፣ በደል ነው፣ ንስሐ ያስገባል የሚባል ነገር ማስፈራሪዎችን ማብዛት ነው፣ ሁሉም ነገር በአፈፃፀሙ ነው፣ በድርጊቱ፣ በገጠመን ነገር ነው ኃጢአት ነው፣ ወይም ኃጢአት አይደደለም፣ ከፍተኛ ኃጢአት ነው፣ ወይም አነስተኛ ኃጢአት ነው ብለን ግምት መስጠት የምንችለው በድርጊቱ ክስተት መጠን ነው፣ ለእኛ ከምንም በላይ አስፈላጊያችን የሆነው ምክንያቶችን ሳንደረድር የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መቀበል ላይ ነው፣ በጥቃቅን ምክንያት እንዳንርቅ ግን አስቀድሞ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡
👉ጥያቄ 2ኛ፦ አንዳንድ የንሰሐ አባቶች እንድንቆርብ አይመክሩንም፣ አያነሳሱንም እና የግድ እነርሱ ቁረቡ እስከሚሉን መቆየት አለብን ወይስ እንደዚህ ከሆነ ዝም ብለን ንስሐ ገብተን ሳናማክር መቁረብ እንችላለን? ወይስ ሌላ የንሰሐ አባት መያዝ አለብን?
✍ መልስ 2ኛ፦ የሚገርመው ነገር ይኼ ነው፣ ካህኑ በዋናነት ከጌታ የተቀበላቸው አደራዎች አሉ፣ በምእመናን ላይ በእረኝነት ሲሾም የመግቦቱንና፣ የመጠበቁን፣ የማስተማሩን ሥራ፣ ቀድሶ የማቁረቡን ሥራ ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲሠራ ነው፣ ስለዚህ ካህን እንኳን የንስሐ ልጁን ይቅርና ማንኛውንም ምእመን ካህን በመሆኑ ይመለከተዋልና፣ ከሱ የሚጠበቀውም ትልቁ የኃላፊነት ደረጃ በጥበቃውም ሥራ፣ በመግቦቱም ሥራ አጥምቆ አቁርቦ፣ የእግዚአብሔር ልጅ በማድረግ ሥራ የመጀመሪያው ነገር ቁረቡ ማለት ነው፡፡
እንኳን ነፍስ ያወቀውን ተመክሮ፣ ተነግሮት፣ ተምሮ የሚሰማውን፣ የሚገባውን ሰው ይቅርና፣ ህፃናትን እንኳን በአርባና በሠማንያ ቀን አጥምቆ የእግዚአብሔር ልጅ እንዲያደረግ፣ ክፉውንና በጎውን ለይተው፣ ካህኑ ይኼንን አድርጉ ቢላቸው እንኳን ምን እንዳላቸው የማያውቁትን እነሱን እንኳን በቤተሰባቸው እቅፍ ውስጥ በአርባና በሠማንያ ቀን አጥምቆ እንዲያቆርባቸው የታዘዘው ካህን፣ ለምእመናን፣ ለንስሐ ልጆቹንና ቁረቡ ብሎ ካላስተማረ ምንስ አባት ነው? የምንስ ጥበቃ ነው? በዚህስ የምን ድርድር ያስፈልጋል? በዚህስ ቆሞ መጠበቅ ያስፈልጋል? ይኼንን ማድረግ የአባትነት ግዴታው ነው፡፡
እንዲያውም ምእመኑ አባቴ የእርስዎ ሥራ ምን ሊሆን ይችላል? እኔን ቁረብ ካላሉኝ፣ ወደቤተክርስቲያን ቅረብ ካላሉኝ፣ ጹም፣ ጸልይ፣ ስገድ ካላሉኝ፣ አንዳንድ የምችለውን መልካም ሥራ እንድሠራ ካላሉኝ የእርስዎ የአባትነት፣ የእኔ የልጅነት ደረጃ ምን ሊሆን ይችላል? ማለት ነው፣ ስለዚህ ምንም ድርድር የለውም መተውም ይሁን፣ ዝም ብለው መቁረብ ይችላሉ፣ ቢቻል እንዲያውም ላለማስቀየም ስንፍናቸውንና ስህተታቸው ተነግሯቸው አባትዎትን መቀየር ይችላሉ፡፡
ብዙዎቻችን በውል አደራውን ያለመቀበልና ያለመረዳት ነገር አለብን፣ በገጠር አካባቢ ስንኖር መቀደስና ሰዓታት መቆም፣ ኪዳን ማድረስ የቤተክርስቲያን ትልቁ የአገልግሎት ሥርዓት ነው፣ ከዚያ ያለፈ ልጁን እንዲያውም አልደረስክም፣ እንዲያውም ራስክን አላዘጋጀህም እየተባለ ማከላከል ይሄ ማለት ትክክል አይደለም፣ አንድን የቆሸሸ ልብስ ማጠብና ማፅዳት መፍትሔ ነው እንጂ ስለ ልብሱ መቆሸሽ ደጋግሞ መናገሩ መፍትሔ አይሆንም፣ አዲስ ልብስ ባይኖረን አጥበነው ወደ አደባባይ እንወጣለን እንጂ ልብሴ ቆሻሻ ነው እያሉ መራቅ አይደለም፡፡
ስለዚህ ገና ነህ (ሽ) አልደረስክም (ሽም) እየተባለ ጥርጣሬና ግምት አያስፈልግም፣ የወደቀውን ሰው ሁሉ በንስሐ አንስቶ እንዲቆርብ ማድረግ ነው የንስሐ አባት ድርሻው ማለት ሲሆን ይሄ ልክ የማይሆኑበት አካሄድ ስለሆነ ጠያቂያችን እርስዎ እንዳሉት ሌላ ንስሐ አባት ቀይሮ ይዞ፣ እግዚአብሔር ረድቷቸው መንፈሳዊ የአባትነት አደራቸውን የሚወጡ ካሉ መልካም ነው፣ እና እነዚህን አባቶች ቢይይዙ ጥሩ ነው፡፡
👉 ጥያቄ 3ኛ፦ ፀሐይን እንዳትንቀሳቀስ ያደረጋት ቅዱስ አባት ማን በሚባል ሰማይ እንደቆመች ስሙን ብትነግሩኝ?
✍መልስ 3ኛ፡- በዋናው “በቅዱስ መጽሐፍ ታሪክ ፀሐይን ያቆማት ኢያሱ ነው” ለአሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች ርስት ሳያካፍል ፀሐይ እንዳትገባበት ጊዜው አልበቃው ስላለ ያንን የጀመረውን ሥራ ቢያደር በማኅበሩ ዘንድ ሁከትና ብጥብጥ ሌላ ፈተና ያስነሳል ብሎ ስላሰበ፣ ይሄን ይህል በእግዚአብሔር ዘንድ ተሰሚነት ያለው፣ ፀሐይን ለማስቆም የሚያስችል ነቢይም ስለነበረ፣ “ፀሐይን በገባዖል ምድር አቁሟል” ርስተ እስራኤልን ከፍሎ፣ አድሎ እስከሚጨርስ ማለት ነው፣ በዜና ቅዱሳን ሌሌቹም ቅዱሳን የተለያየ ተአምራትን ሠርተዋል፣ ይኖራሉ፣ በአጭሩ ይህን እንረዳለን፡፡
👉ጥያቄ 4ኛ፦ እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ሲፈጥረው ሁሉንም አንድ ጊዜ ነው የፈጠረው አዳም ሲፈጠር እኛም አብረን ተፈጥረናል ነገር ግን ወደዚህ ዓለም እስከምንመጣ ድረስ እኛ
ነበርን? ሰው ሲጠይቅ ሰምቼ እኔም ጥያቄ ስለፈጠረብኝ ነው? ስላበዛሁ በጣም ይቅርታ፡፡
✍መልስ 4ኛ፡- ሰው እኮ የሥጋና የነፍስ ባህሪ ነው በአዳም የተፈጠረ እንጂ፣ አዳም ሰው ሆኖ በተፈጠረበት በዚያን ቀን ሁላችንም ያን ጊዜ በሥጋና በነፍስ ባህሪ ካልሆነ በስተቀር በአካል አልተፈጠርንም፣ አንድ አዳም ነው ብቻውን ነው በምድር ላይ ያለው፣ ሔዋን እንኳን ብቻዋን ከአዳም ጎኑ የተገኘችው ከአዳም በኋላ ነው፡፡
ጠያቂያችን ምናልባት ሊሉት የፈለጉት ነገር ያለ ይመስላል፣ መግለፅ ፈልገው ያልገለፁት ነገር ካለ እንጂ፤ ሰውን ሲፈጥረው ሁሉንም አንድ ጊዜ ነው የፈጠረው፣ ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ይላል፣ ይኼንን የሚለው ስለ ሰው ተፈጥሮ የሚናገረው፣ የሰው ፍጥረት የሚገለፅበት የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን ነገር ነው፣ ብዙ ተባዙ የሚለው ቃል እኮ አንድ ጊዜ የተፈጠርን አይደለንም፣ ለዚህም ነው እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ እያለፍን፣ እየተካን የምንሄደው፡፡
ይኼ ማለት ቀድሞ የተገኘው የሰው ዘር ትውልድ ተክቶ እንዲሄድ፣ ትውልድ በዚያ ላይ እንዳያቆም፣ የሰው ልጅ ከተሰጠን የተፈጥሮ ጸጋ አንዱ መተካከት ነው፣ ትውልድ ሲያልፍ ትውልድ ይተካል፣ እንዲህ እያልን የተፈጥሮ ጉዟችን፣ ወይም ደግሞ ሒደታችን ሳይቋረጥ እንሄዳለን፣ በአባባል በአጋጣሚ ውስጣዊ ምስጢሩን እርስዎ ባሉት ነገር ስንነጋገር ሰው ቀድሞ አንድ ጊዜ ተፈጥሯል ለሚለው ነገር ምናልባት ማብራራት ቢያስፈልግ፣ ወንዶቹም በፆታቸው ወንድ ሆነው የአዳምን የወንድነት ባህሪ ወይም አዳማዊ ተፈጥሮን ይዘው የሚቀጥሉ፣ ሴቶችም በፆታቸው የሔዋንን ተፈጥሮ ይዘው የሚቀጥሉ፣ እስከ መጨረሻው እስከ ዓለም ፍፃሜ የሚመጡ ወንዶችም፣ ሴቶችም ይኼንን ተፈጥሮ ይዘው ይቀጥላሉ ማለት ነው፡፡
በነፍስ ሦስት ግብራት ያሏቸው፣ በሥጋ ደግሞ አራት ባህርያተ ሥጋ ያሏቸው ፍጥረታት፣ ይሄ ነው መጀመሪያ የተፈጠረው አዳም ሲፈጠር በሥጋው አራት ባህሪ ነበረው፣ ዛሬም የሚፈጠሩ ወንዶች ሁሉ አራት ባህሪተ ሥጋ አለው፣ ለወንድም ለሴትም አንድ ነው፣ በፆታ ግን ወንድ ለመሆናችን፣ ሴት ለመሆናችን የምንለይበት፣ አካላዊ ቅርፅ አለን፣ ምልክት አለን እሱም ሳይቋረጥ ይኼ ነው ግብር የሚሆነው ይኼ ነው፣ ከተፈጠረው ነገር ነው ዘር እየወረስን፣ ልክ ከአባታችን ከእናታችን ዘር እየወረስን እንቀጥላለን፣ አዲስ ተፈጥሮ ይዞ የመጣ ሰው የለም፣ ይኼ ነው የሥጋ ተፈጥሮ፡፡
መጀመሪያ ተፈጥሯል የሚባለው ይኼ ነው እንጂ፤ የት ቆይተናል? የሚያስብል የለም፣ እኛ መቆየት ለምን አስፈለገን? በዚያን ጊዜማ ገና አልተወለድንም፣ እግዚአብሔርም አልፈጠረንም፣ ከእናት ከአባትም አልተወለድንም፣ እኛ የተወለድነው፣ እኛ በትክክል የተፈጠርነው ዛሬ ነው፣ ሁልጊዜ የመጀመሪያው ተፈጥሮ አዳም ነው፣ ይኼ ተፈጥሮ ደግሞ በሌላ ሰው ሠራሽ ነገር ስለማይተካ አንድ ጊዜ አንድ አዳም አንዲት ሔዋን ተፈጥረዋልና፣ እነሱን የሚመስል ወንድም፣ ሴትም ሌላ ጊዜ ለማስገኘት እግዚአብሔር ከፈጠረው ነገር ላይ ተነስቶ ሳይንስም፣ ሌላም ፍልስፍና፣ ሌላም ጥበብ ሊያስገኝ አይችልም፡፡
አሁንም በእናት ማሕፀን በሚገርም በሚደንቅ፣ ከአይምሮ በላይ በሆነ ጥበብ እግዚአብሔር ሰውን ውኃና ደም አድርጎ፣ በማሕፀን ቀስ አድርጎ የተፈጥሮ ሥርዓቱን ጠብቆ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በእናቱ ማሕፀን ቆይቶ እንዲወለድ ያደርጋል፣ እግዚአብሔር ነው ይሄን ያደረገው፣ በጣም የሚገርም ነው፣ ገና ከእናት ማሕፀን ጀምሮ እግዚአብሔር በጥበቡ የፈጠረው ፍጡር ወይም ሰው ሒደት በጣም የሚገርም ነው፣ በእናት ማሕጸን የነበረው የዕድሜ ደረጃም፣ የአካልም ከዚያ ከተወለደ በኋለ ወራት እያስቆጠረ፣ ዓመታት እያስቆጠረ ሲመጣ በዝግመት እንዴት ዓይነት የተፈጥሮ ሥርዓት ተጠብቆ፣ ከዚያ ለአካለ መጠን እንደሚደርስ ይኸው በምድር ላይ የምናውቀው ነገር ነው፣ የሚቆጠረውና የሚታወቅ የሰው ልጅ ነው፡፡
የመላእክትን ተፈጥሮ ባናስብ በየጊዜው እንደ ሰው ልጅ አይጋቡም፣ አይዋለዱም፣ እየተተካኩ አይሄዱም፣ አንዱ ሞቶ አንዱ አይተካም፣ “መላእክት ቁጥራቸውም አይታወቅም ብዙ ናቸው ብሎ መጽሐፍ ነግሮናል”፣ ይኼንን ነው የምናውቀው፣ አንድ ጊዜ ተገኝተዋል እንጂ፤ ትልቁ መልአክ፣ ትንሹ መልአክ አይባልም፣ በሥልጣንና በአገልግሎት ድርሻ ካልሆነ በስተቀር፣ የሰው ግን እንደዚህ አለው፣ በዚህ ነው የሰውን ተፈጥሮ የምናየው፡፡
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፣ አሜን።
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር አድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉🏾 ለ #ቅዱስ #ቁርባን ስለሚደረግ #ጥንቃቄ
👉ጥያቄ፦ ሰላም አባታችን ለምታደርጉልን ሁሉ እግዚአብሔር ይስጥልን በእውነት ፀጋውን ያብዛልዎት! በሰው መተት ድግምት ተደርጎ ሰው ላይ ክፋት ለማድረግ የሚያደርጉት ማለት በሚበላ ወይም በሚጠጣ ሰጥተው ሰውዬው ዘመኑን ሁሉ እየተሰቃየ ይኖራል፣ ሆዱ ውስጥ አድጎ እባብ፣እንሽላሊት፣ ወዘተ ሊሆን ይችላል፣ በዚህ የሚሰቃዩ ብዙ ወንድም እህቶች አሉ እና ጥያቄዬ እነዚህ ሰዎች ሆዳቸው ውስጥ ያለው ነገር ሳይወጣ ቅዱስ ቁርባን ልቀበል ቢሉ ይችላሉ?
እንደሚታወቀው ለማውጣት ከባድ ነው ሐኪምም የሚፈታው ነገር አይደለም፣ በእርግጥ እግዚአብሔር ፈቅዶ ሆኖ ብዙዎች በፀበል ይወጣላቸዋል፣ እግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ እስከሚወጣላቸው ድረስ ግን መቁረብ አይችሉም አባታችን? በመሰለኝ ስለማይሆን ነው ግን እኔ የሚቻል ነው የሚመስለኝ፣
✍መልስ፡- ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለመቀበል ስርዓት አለው፣ በዚሁ ዮሐንስ ንስሐ ድህረገጽ ላይ ስለ ቅዱስ ቁርባን አቀባበል፣ ቅድመ ቁርባን፣ ጊዜ ቁርባን፣ ድኅረ ቁርባን በማለት በተደጋጋሚ በጽሑፍም፣ በቃልም አስተላልፈናል፣ ከዚያ ላይ ማለትም ከመቁረብ በፊት፣ በመቁረብ ጊዜ፣ ከቆረቡ በኋላ ሊደርጓቸው ስለሚገቡ ስርዓቶች በሰፊው ተነጋግረናል፣ በዚሁ ድህረገፅ ገብቶ መለስ ብሎ ማየት ይቻላል ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ለመጀመሪያው ጥያቄ መልስ የሚሆነው እነዚህ ሰዎች ታመዋል፣ እርኩስ መንፈስ ከማደሩ የተነሣ ራሳቸውን ላይጠብቁ ይችላሉ፣ ከመቁረብ በፊት መደረግ ያለበት ስርዓት አለ ሐዋርያው ጳውሎስ “ሁሉ በአግባብና በስርዓት ይሁን” ብሎ እንደተናገረ የሚቆርብ ሰው ቅድመ ቁርባን፣ ወይም ከቁርባን በፊት ሊያደርጋቸው የሚገባቸው ስርዓት አለውና፣ እነሱን ስርዓት መጠበቅ ይችላል ወይ? ከዚያም ከቁርባን በኋላ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ስርዓቶች አሉ፣ በሱ መመራት ይቻላል ወይ? ይኼንን ስርዓት ጠብቀው ይሄዳሉ ወይ የሚለው ቢታሰብበት መልካም ነው፡፡
በጸበል አካባቢ እንደምናየው እነኚህ ሰዎች አሟቸዋል፣ የታመመ ሰው ደግሞ ራሱን የቻለ የሰው እርዳታ ያስፈልገዋል፣ ራሳቸው ቅዱስ ሥጋውን፣ ክቡር ደሙን ተቀብለው በስርዓት መቆም ይችላሉ ወይ? ይሄ ሁሉ ታሳቢ መሆን አለበት፣ በጸበል የማይለቀቅ ነገር የለም ደጅ መፅናት ይኖርብናል እንጂ በሽታ መልቀቁ አይቀርም፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን አይቀበሉም አንልም፣ ይቀበላሉ፣ ሲቀበሉ ግን የሚያስቀምጡት፣ ወይም የሚተገብሩት ስርዓት አለ ማለት ነው ትልቁ መሠረታዊ ጉዳይ የሚሆነው፡፡
እነዚህ ሰዎች ማለትም ንስሐ መግባት ቢችሉ፣ በተደጋጋሚ ቅዱስ ጸበል መጠመቅ ቢችሉ፣ ይኼን ሁሉ አድርገው መፍትሔ ካላገኙ ስርዓቱን እንጠብቃለን፣ እንችላለን፣ ራሳችንን የምናውቅ፣ የምንጠብቅ ሰዎች ነን ካሉ ከንስሐ አባቶቻቸው ጋር በመነጋገር ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መቀበል ይችላሉ ማለት ነው፣ ስርዓቱን የመጠበቅ አቅም ካላቸው፣ በመዳን ፋንታ መቅሰፍት እንዳሆን፣ ሰላም በማግኘት ፋንታ ሰላም ማጣት እንዳይሆን፣ እነኚህን ነገሮች በማድረግ፣ በማከናወን ሊቆርቡ ይችላሉ ማለት ነው፡፡
እንዲህ ዓይነት በሰው ላይ የሚጫወቱ ሰዉን እንዲሰቀይ መተት፣ ድግምት እያሉ የእርኩስ መንፈስ ማደሪያ የሆኑ ሰዎች ካሉ ምን ይባላል፣ እግዚአብሔር ይቅር ይበላቸው፣ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እግዚአብሔር ያሳየን “ለጠላቶቻችሁ ለሚያሳድዷችሁ፣ ለሚገፏችሁ ጸልዩላቸው” ብሎ ነውና፣ አግዚአብሔር ይቅር ይበላቸው፣ ሰው ለሰው መሰቃየት ምክንያት መሆኑ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡
እግዚአብሔር እኮ ሞቶ ነው ሰውን ሰው ያደረገው፣ እግዚአብሔር የሞተለትን ሰው ለምን ያንገላታዋለ፣ ለምን ያሰቀይመዋል፣ ሠርቶ፣ ወጥቶ ወርዶ፣ ላቡን አንጠፍጥፎ የሚኖረውን እንዲህ አድርጎ በድግምት ማሰቃየት እግዚአብሔር የማይወደው ተግባር ነው፣ የታመሙት፣ የተደረገባቸውን ሰዎች እግዚአብሔር በምህረቱ ይጎበኛቸዋል፡፡
ስለዚህ በእንዲህ ዓይነት የገጠማችሁ ቤተሰቦቻችን ካላችሁ ጸሎት መጸለይ፣ ጾም መጾም እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ ነው፣ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 17 ቁጥር 21 ” እንዲህ ዓይነቱ አብሮ አደግ እርኩስ መንፈስ ያለ ጾም፣ ያለ ጸሎት አይወጣም” ብሎ ተናግሯል፣ መንፈሳዊ ተግባራት የእርኩስ መንፈስ ጠላቶቹ ናቸው፣ ስለዚህ በእምነት መበርታት፣ ጸበል መጠጣት፣ ጸበል መጠመቁ፣ ጾም ጸሎት፣ ስግደት በጣም ወሳኝ የሆነ ነው፡፡
መንፈሳዊ ተግባራት የዲያቢሎስ ጠላት ናቸው፣ ሰዎች ብዙውን ጊዜ የሚቸገሩት ጸበልና ጸሎት ጀምረው እየተዉ፣ እያቋረጡ ነው፣ ጸበል ተጀምሮ አይተውም፣ ጸሎት ተጀምሮ አይቋረጥም፣ ደጅ ጥናት ያስፈልጋል፣ ትዕግስት ያስፈልጋል፣ ተጠምቄ ምንም ለውጥ አላመጣሁም አይባልም፣ ደጅ ጥናት ያስፈልጋል፣ ብዙዎች እናት አባቶችን፣ እህት ወንድሞችን ሁሉ በጸበል የዳኑትን ሰዎች ማየት ይቻላል፡፡
የተወደዳችሁ፣ የተከበራችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፣ በጾም፣ በጸሎት፣ በድፍረት፣ በጸበል፣ ወ.ዘ.ተ. በመሳሰሉት መንፈሳዊ ተግባራት እርኩስ መንፈስን እምቢ በሉት ተብሎ ስለተጻፈ፣ ተቃወሙት፣ ከዚያም በኋላ ከእናንተ ይወገዳል፣ ይርቃል ተብሏልና፣ እነዚህን እናድርግ፣ በመቀጠል የንስሐ አባቶቻችንን በማነጋገር ንስሐ እንግባ፣ ከዚያ ይኼንን ሁሉ ደክመን አድርገን መፍትሔ ካጣን፣ (በእርግጥ መፍትሔ አናጣም) የሚሆነው ነገር ግን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መቀበል ነው፡፡
ቅዱስ ሥጋን ክቡር ደሙን ለሚቀበሉ ሰዎች ማለትም በተለይ ለታመሙት ስርዓት መጠበቅ ይችላሉ ወይ? ምክንያቱም እርኩስ መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች ቤተክርስቲያን ይጮኻሉ፣ ይረብሻሉ፣ ሌላውን ሰው እረፍት ይነሳሉ፣ እንዲህ ሆነው ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መቀበል ካለው ስርዓት አንፃር ይከብዳልና፣ ይህን ማሟላት፣ ማከናወን ይችላሉ? የሚለውን ማየት ይጠበቅብናል፡፡
መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተው ለሰው ልጆች ነው፣ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ የሚያስፈልገው ለኃጢአተኞች ነው፣ “እኔ የመጣሁት ኃጥአንን ወደ ንስሐ ለመጥራት ነው፣ ለፃድቃን አይደለም” የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 9 ስለዚህ ኃጢአተኛ ማለት በሽተኛ፣ በኃጢአት የታመመ፣ ንስሐና ይቅርታ የሚስፈልገው ማለት ነው፡፡
ሆኖም ግን ይህ ሲሆን ነው ስርዓት እንጠብቃለን፣ “ሁሉ በአግባብና በስርዓት ይሁን” እንደተባለ ቤተሰቦቻችንም ወደ ቅዱስ ቁርባን የሚቀርቡበትን መንገድ ማመቻቸቱ የሌሎቻችን ድርሻ መሆን አለበት ማለት ነው፣ ጠያቂያችን በዚህ መካከል ውስጥ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ በውስጥ መስመር ሊያገኙን ይችላሉ ማለት ነው፡፡
የመከረን የገሰፀን መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በፈጠረው አንደበት ሁሉ ስሙ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን፣ አሜን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን።
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር አድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
👉ጥያቄ፡- ተወልጄ ያደግኩበት አባቢ የፍየል ደም ተሰርቶ ይበላል እና እኔም በልቻለሁ ነገር ግን ኦሪት ዘሌዋውያን ከምእራፍ 17 ጀምሮ ሳነበው የማንኛውንም የእንስሳት ደም አትብሉ ይላል፣ እና አባቴ እንደነገርኩዎት ይሔንን ደም በልቻለሁ፣ ቅዱስ ቁርባን ሰሞኑን መቀበል እፈልጋለሁ ነገር ግን ውስጤን ስለረበሸኝ ነውና እባክዎን አባቴ ምላሽ እንዲሰጡኝ እጠይቃለሁ፡-
👉🏾 ለ #ቅዱስ #ቁርባን ስለሚደረግ #ጥንቃቄ
✍መልስ፡- እንዳሉትም በአሪት ዘሌዋውያን ላይ ስለ እንስሳት በተለይ በኦሪቱ ስርዓት መስዋእት ሆነው ስለሚቀርቡ የእንስሳት ዓይነት በጣም እጅግ የተለየ የአቀራረብ ስርዓት፣ የተለየ ለመስዋእትነት የሚቀርቡ እንስሳትን የአመራረጥ ስርዓት፣ ከዚያም መስዋእቱ ሲቀርብም በማን አማካኝነት፣ እንዴት እና የት ቦታ፣ ከዚያ ደግሞ የእንስሳቱ መስዋእት ወይም ለመስዋእትነት ከታረዱ በኋላ የእግዚአብሔር ድርሻ፣ የሰው ድርሻ ተብሎ በውስጡ የረቀቀ ሚስጥር ያለበት፣ እግዚአብሔርና ሰው የሚገናኝበት፣ አማናዊው ለሆነው ለክርስቶስ ደምና ሥጋ ምሳሌ የሆነበት፣ ምንም ኃጢያት ያልሰራው ያልበደለው እንስሳው የሰውን እዳ በደል ኃጢያት ተሸክሞ ወደ በረሐ እንደሚጣል፣ ካሕኑ ስለራሱ ኃጢት፣ ስለ ሕዝቡ ኃጢያትና ስተቀደሰወው ስለ ንፁህ መእዋእት አቀራረብ ሁሉ ለእግዚአብሔር ስለሚሆነው እያቀረበ ስርዓቱን ያከናውን ነበር፣ ካሕኑም የመስዋእቱን ንፅህና ጥንቃቄ ያቀራረብ ስርዓት ሁሉ ያስጠብቅ ነበር፡፡
ይህ እንግዲህ ያኔ በስርዓተ ኦሪቱ በአባቶቻችን ዘንድ ጊዜያዊ የሆነ ለእግዚአብሔር ንፁህ መስዋእት ብለው የሚያቀርቡት የመስዋእት አቀራረብ ስርዓት ስለነበረ ለመስዋእትነት በሚመረጡ እንስሳት ላይና ከእነሱ ጋር በተያያዘው ነገር ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረጋል ሕዝቡ ሁሌ ይሔን እያወቀ ነው፡፡
ስለዚህ ጠያቂያችን በዋናት ከመጀመሪያው ጀምሮ እስከ መጨረሻው በስርዓተ ኦሪት ስለሚቀርበው የመስዋእት ዓይነት በጥንቃቄ፣ ቅደም ተከተሉን በደንብ ሲረዱት ይሔ ደም ያለመበላቱን ክልከላ ከመስዋእቱ ጋር የተያያዘ ሰው በተከለከለው ነገርና በማይገባው ነገር ላይ ተላልፎ እንዳይፈፅም ይሔን የማድረግ ነገር ከዚያው ከስርዓተ ኦሪቱ እና ከኦሪቱ መስዋእት ጋር በተያያዘ ነው፡፡
ለምሳሌ የዔሊ ልጆች ሁለቱ አንዱ ከእግዚአብሔር ጋር የተጣሉበት ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መስዋእት ሳያስቀድሙ የራሳቸው የሆነውን ድርሻ ብቻ ሳይሆን፤ የእግዚአብሔርን ድርሻ ያውም በድፍረት፣ በመሳሳት አይደለም፣ ከሌላ ችግር ጋር በተያያዘ ከአቅማቸው በላይ የገጠማቸው ነገርም ኖሮ አይደለም፣ ብቻ ሆን ብለው እያወቁ፣ ንቀትም ነው፣ ማቃለልም ነው መስዋእቱን ስለዚህ የማይገባቸውን ወስደው ለራሳቸው አደረጉ ወይም በሉ፡፡
አንደኛው ምክንያት ይሔ ነው በዚያን ጊዜ ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ንፁህ መስዋእት የሚባለው የንስሐ ነው፣ ዛሬ ግን ክብርና ምስጋና ለባለቤቱ ይሁን ለዚህኛው ለአማናዊው ለክርስቶስ ደምና ሥጋ ጥላ የነበረው ምሳሌ ይሔ ነበር፣ ወደዚህኛው እንድንደርስ ሞግዚት ሆኖ ያቀረበን መስዋእት፤ መሰዋት ለእግዚአብሔር አስፈላጊ መሆኑን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነታችንን ሁሉ እንዳናቋር፣ የጠበቀ የግንኙነት መስመር ያለን መሆኑን የሚያረጋግጥልን ይሔ ነበር፡፡
ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስም እየደጋገመ በእብራውያን መልእክቱ ላይ ስርዓተ ኦሪት የመስዋእት አቀራረብ ለሚያውቁት ለእብራውያን ነው የጻፈላቸው፣ ሰለዚህ የካሕናትን ጉዳይ አንስቷል፣ በዚያን ጊዜ የነበሩ የታወቁ በጣም ስመ ጥሩ የሆኑ ስለመስዋእተ አቀራረቡ፣ ስለመስዋእቱ፣ ስለ ስርዓተ ኦሪቱ፣ ስለ ሁሉም ነገር ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ ሊቀ ካሕናት ነበሩ፣ እነሱን ሞት ስለዚህ ከለከላቸው፣ ሞት የማይከለክለው ግን ለዘላለም ካሕን ሆኖ፣ ሊቀ ካሕናት ሆኖ፣ ክሕነት የባሕርይው ሆኖ፣ የማያልፍ የማይሻር፣ የማይቀር እንዲህ ዓይነት ክሕነት ያለው የመልከፀዴቅ ምሳሌ የሆነ ካሕን ለእኛ ያስፈልገን ነበር፣ እሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ሌሎቹን ሞት ከልክሏቸዋል፡፡
ያልገባቸው፣ ድንቁርና ጸጋቸው የሆነ፣ በተለይ በኃይማኖት አንድም ነገር መገንዘብ ያልቻሉ ሰዎች በቃ ሊቀ ካሕናት ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ ነው፣ ከአሁን በኋላ ካሕን አያስፈልገንም እያሉ ይዘላሉ፣ አባባሉ ግን ልክ እንደ ኦሪቱ እንደ ክሕነቱ ስርዓት ነው ሁሉንም ነገር ማለት ነው ፡፡
ስለዚህ ያ የነበረው የብሉይ ኪዳን የክሐነት አሿሿምም ሆነ በክሕነቱ አገልግሎት የነበሩ ሰዎችም ዓረፍተ ዘመን ይገታቸዋል፣ እንደገናም ደግሞ በክሐነታቸውም ሰው ናቸውና አንዳንድ ጊዜ ስህተት ሊሰሩ ይችላሉ፣ ያንን የነበረውን የክሕነት አገልግሎት እሱም ራሱ ለዚህ ለሐዲስ ኪዳኑ ክሕነትንሳሌና ጥላ ሆኖ የቆየ እንጂ ወይም ደግሞ የእዚህኛው ንባብ ነው ማስታወቂያ ነው፡፡
አስቀድመን የሆነ ነገር ልንፈጽም አንድ ነገር ገበያ ላይ ልናውል፣ በቤተክርስቲያን ጉባኤ ልናዘጋጅ አስቀድመን ማስታወቂያ እንሰራለን፣ ልክ እንደዚያው ስርዓተ ኦሪቱ ለሐዲስ ኪዳን ማስታወቂያ ነው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንትም እኮ የካሕናት አለቃ ነው፣ አሮንን የሾመ፣ ነቢያትን ሁሉ ሐብተ ትንቢት የሰተጠ በጸጋ እሱ እኮ ካሕን ነው፣ ክሕነት የባሕሪው ነው፣ እሱ ካሕን ተብሎ እኛን ካሕናት፣ እሱ ንጉሥ ሆኖ እኛን ነገሥታት፣ እሱ ሐዋርያ ተብሎ እኛን ሐዋርያት፣ እሱ ነቢይ ተብሎ እኛን ነቢያት፣ እሱ ክርስቶስ ተብሎ እኛን ክርስቲያን የሚያሰኝ ማለት ነው፡፡
መስዋእቱም ያም የኦሪቱ ስርዓት መስዋእትልክ እንደ ክሕነቱ ለዚህኛው ማስታወቂያ ነበር፣ ስለዚህ ያን ጊዜ መስዋእቱ ከእግዚአብሔር ጋር የምንገናኝበት፣ በፈረሐ በእግዚአብሔር ሆነን ማቅረብ ስላለብን እዚያ ላይ የደሙን፣ ለመስዋእቱን የሚቀርቡትን፣ የበጎቹን፣ የእንስሳቱን፣ የፍየሎቹን ደም መብላት ክልክል ነው ብሎ ያለው አንደኛው ምክንያት ትክክል ነው ጠያቂያችን፡፡
በሁለተኛው ደረጃ “እስመ ነፍስ ትሐድር በነፍስ” ይላል የእንስሳት እርድን በሚመለከት ስናየው በደም ላይ ነፍስ ትቆያለች፣ እሷም ቢሆን ዝርው ብላ ብትቀርም የሰው ዓይነት ነፍስ፣ ወይም ባሕሪ ዌም ተፈጥሯዊ ባሕሪ ባይኖራትም የእንስሳት ደም ላይ ነፍስ አለች፤ ስለዚህ በስርዓተ ኦሪቱ ክልክል ነበር፡፡
አሁን በዚህኛው ዘመን ከንፅህና፣ ከጤንነት፣ በልተነው ካለመስማማት፣ ለመብላት ለሕሊና የሚከብድ ካልሆነ በስተቀር ሥጋውን የበላነው ነገር፣ ይሔን ያህል ደሙን አብስለን ከሌላ ነገር ጋር ቀላቅለን ብንበላው ከቅዱስ ቁርባን መቀበል ጋር በፍፁም አይያያዝም፣ እኛ ኦርቶዶክሳያን የተዋሕዶ ልጀች የምንባለው ወይም ተዋሕዶን የተቀበሉ፣ በተዋሕዶ የሚያምኑ የሚባሉ አምስቱ ኦሪንታል ቸርች ይባላሉ፡፡
እነዚህ አምስቱ ኦሪየንታል ቸርች የሚባሉት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በሚለው እምነት የፀኑ ናቸው እነሱም፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ የግብፅ (የእስክንድርያ) ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ፣ የአርመን ኦርቶዶክስ ተወሕዶ፣ የሕንድ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶና፣ የሶሪያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናቸው፡፡
ከእነዚህ መካከልም የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የምትለይበት ሁል ጊዜ በአምልኮተ እግዚአብሔር የኖረች ቤተክርስቲያን ስለሆነች፣ የኖረ ሕዝብ ስለሆነ፣ በብሉይ ኪዳንም እንደ ዕብራውያን ስርዓተ ኦሪቱን ለአባቶቻችን ለነ አብርሐም፣ ለነ ይስሐቅ፣ ለነ ያዕቆብ የተሰጠውን ቃል ኪዳን ለኖኅ የተሰጠው ቃል ኪዳን አስቀድመን ከዓለም በፊት ቀድመን የተቀበልን በዚያ በኦሪቱ ስርዓት አምልኮተ እግዚአብሔር የፈጸምን ስለሆንን ማለት ነው፡፡
ዕብራውያን እኛኝ አይደርሱበንም፣ እነሱ ደግሞ ክርስቶስን መቀበል ተሳናቸው፣ እኛ ሁለቱም ነገር ተሳክቶልናል፤ከዚያ ያመጣነው ነው በሙሉ አብዛኛውም ያለው ከስርዓተ ኦሪት ነው፣ ስርዓተ ኦሪቱም ለዚህኛው መሠረት ስለሆነ በስርዓተ ኦሪቱም ይሔን ስናደርግ ነው ብለን ያልተሻረውን፣ ሕግም እንዳልተሻረ አፅንተን እንሔዳለን፡፡
ኦሪየንታል ቸርች የተባሉት ከእኛ ጋር ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ነው የምንላቸው፣ ብዙ በስርዓትም፣ በአምልኮት ስርዓት አፈፃፀም እኛ ጋር አይደርሱም፣ ለዚህም ነው ሰይጣንም ሸክም አበዛብን፣ እኛም ሸክሙ በዛብን እየዛልን አባቶቻችን በጥንቃቄ ያኖሩትን እምነት የምንዝረከረከው እና ከዚህ አንፃር የመጣ፣ እሱንም የተቀበልን እድለኞችም ስለሆንን ከዚህ ከዚህ አንፃር ነው ይሔን የደም ነገር የምናነሳው፡፡
ይደረግ ነበር እያሉ ነው ሌሎቹ ከክርስቶስ መምጣት በፊት አሕዛብ ነበሩ፣ በአምልኮ ውስጥ ባእድ ነበሩ፣ ስለዚህ ስርዓተ ኦሪቱን ለማጣቀሻ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ፣ እንዲህ ያደርጉ ነበር ብለው የራሳቸው ስርዓት አያደርጉትም፣ እኛ ግን በስርዓተ ኦሪትም ስናነብ አሁንም ቢሆን በኦሪት የተፃፈውን ብሉይ ኪዳን ስናነብ ራሳችን ስናደርገው የነበረ፣ ምክንያቱም መስዋእት ታላቋ አክሱም ላይ፣ ታላቋ መርጦ ለማርያም ተድባበ ማርያም ላይ፣ መስዋእተ ኦሪትን ጣና ቂርቆስ እነዚህን የመሰሉ፣ ይከናወኑ የነበረ የስርዓቱ ምልክት ዛሬም አሁንም አለ።
ይሔንን ሁሉ ማለት ያስፈለገን ” ነገሩን ከሥሩ ውኃን ከጥሩ” እንደሚባለው መረዳት ስላለብን ነውና ጠያቂያችን ቅዱስ ቁርባን ከመቀበል የሚያግድዎት ነገር የለም እግዚአብሔር ይመስገን እንኳን ተቀበሉ፣ ወደፊት ግን ባደረግ ለሕሊና የሚከብብድ ነገር ከሆነ፤ ይሔን ደም መብላት ማለት ባሕል ነው፣ በዚያ አካባቢ የተወለደ ሰው ያንን ልማድ ያደርጋል፣ በአንዳንድ አካባቢ ደግሞ በጣም ነውር ነው፣ እንዴት ይደረጋል ብለው የሚታዘቡ አሉ፡፡
እንግዲህ እንደየ አካባቢው ስርዓት ነው፣ አንዱ በአካባቢው የሚያደርገውን፣ በአንዱ አካባቢ ደግሞ እንዴት ይደረጋል? ብሎ የማያውቀውንና ተደርጎ የማያውቀውን በእሱ ዘንድ የማይታወቀውን መተቸት ያለ ነው ከዚህ አንፃር ነው እንጂ ከቅዱስ ቁርባን መቀበል እንዳልቀበል ያስከለክለኝ ይሆን ከሚል ነገር ጋር የሚያያዝ አይደለም፡፡
የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን አሜን
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
https://t.me/+ReLdpifiso4Sz04q
የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በዮሐንስ ንስሐ ድረገጽ የምናስተላልፈውን ኦርቶዶክሳዊ ትምህርትና መንፈሳዊ አገልግሎት የምትከታተሉ አባላቶቻችን፤ እንደሚታወቀው የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ የዛሬዋን ቀን የምናከብረው መድኃኒት ክርስቶስ ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ የገለጠባት በእንስሳት ደም ይቀርብ የነበረው መሥዋዕተ ኦሪትም አብቅቶ አማናዊው የሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት ለድኅነተ ዓለም የተበሠረባትና የተጀመረባት ዕለት በመሆንዋ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ እየተባለች ትጠራለች፡፡ መድኃኒት ክርስቶስ ‹‹ይህ ጽዋዕ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱም ጠጡ›› ፡(ሉቃ.፳፪፥፳)
የመንፈሳዊ ህይወታችን ሁሉ መደምደሚያ ምስጢረ ቁርባን ስለሆነ ይህን ክብር እንዳይቀርብን ከማድረግ አንፃር ትምህርቱን ዕለት ዕለት በስፋት መስጠት አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ስጋዬን ያልበላ ደሜን ያልጠጣ የዘለዓለም ህይወት የለውም ስለሚል ቃሉ ምንም ድርድር የለውምና ምእመናን የዘላለም ህይወት ሳያገኙ እንዳይቀሩ ሁሌም ቤተክርስቲየን ይህን በማስተማር ትደክማለች ትጥራለች።
በመሆኑም፤እኛም የዛሬውን ቀን ምክንያት በማድረግ ከዚህ ቀደም ስለ #ቅዱስ #ቁርባን በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ርዕስ ላይ ተመስርተን በጽሑፍ ካስተላለፍናቸው ትምህርቶች ውስጥ የተወሰኑትን ሊንኮች በአንድነት አድርገን እንደሚከተለው ልከናልና ጠቃሚ ግንዛቤ ስለምታገኙበት ሁላችሁም በማስተዋል አንብባችሁ ተረድታችሁ ለነፍሳችሁ መልካም ፍሬ ታፈሩበት ዘንድ በአጽንኦት እንመክራለን።
https://t.me/c/1172495782/36734
https://t.me/c/1172495782/37219
https://t.me/c/1172495782/37403
https://t.me/c/1172495782/36097
https://t.me/c/1172495782/36633
https://t.me/c/1172495782/36393
https://t.me/c/1172495782/36679
https://t.me/c/1172495782/35073
https://t.me/c/1172495782/35377
https://t.me/c/1172495782/34795
https://t.me/c/1172495782/35016
https://t.me/c/1172495782/33158
https://t.me/c/1172495782/32899
https://t.me/c/1172495782/32739
https://t.me/c/1172495782/32714
https://t.me/c/1172495782/32491
https://t.me/c/1172495782/31949
https://t.me/c/1172495782/32169
https://t.me/c/1172495782/29190
https://t.me/c/1172495782/31745
https://t.me/c/1172495782/31296
https://t.me/c/1172495782/31122
https://t.me/c/1172495782/31050
https://t.me/c/1172495782/30965
https://t.me/c/1172495782/30953
https://t.me/c/1172495782/30339
https://t.me/c/1172495782/30850
https://t.me/c/1172495782/29799
https://t.me/c/1172495782/29697
https://t.me/c/1172495782/29505
https://t.me/c/1172495782/28371
https://t.me/c/1172495782/27681
https://t.me/c/1172495782/29190
https://t.me/c/1172495782/25422
https://t.me/c/1172495782/27825
https://t.me/c/1172495782/22245
ቴሌግራም ግሩፓችንን በየቀኑ ይከታተሉ፣ ለወገንዎትም ሼር ያድርጉ፡-
ተከታታይ ትምህርትና ለጥያቄዎት ምላሽ ለማግኘት ቴሌግራም ግሩፓችንን ይቀላቀሉ